Seid Social @seidsocial Channel on Telegram

Seid Social

@seidsocial


አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

Seid Social (Amharic)

ይኸው 'Seid Social' የሚሆነው አቀፋዊ መረጃዶችና ምልከቶች እና ታሪካዊ ክስተቶች ይሉት። በዚህ ቦታ ስለ ተጠቃሚነትና እናቴናለም ታሪካዊ ትክክለኛ መረጃዶች እና አቀፋዊ የተመረጠ መረጃዎችን እንዲያከናውነኝ መረጃዎችን እና መልሶልን የሚለውን ውስጥ ያስተምሩ። 'Seid Social' ከምልከቶች እና ምንም እድል አያገኙም እንዲሁም በአጭሩም ቡድኖቻቸውን ስኬት እየተወለደ እከባበረብኛለን። አገልግሎት በአለም መኪና በአለም ዋና እገልጻለሁ። የማይጠቅሙበትን መልክት ነግሥተኛለሁ።

Seid Social

21 Nov, 16:44


አሜሪካ እጅግ የተራቀቀ የጦር ቴክኖሎጂ ፈጠርኩ ብላ ወራቶች ሳይቆዩ ከቻይና እጅ ይገባል። ያውም ከአሜሪካም በተሻለ መልኩ!
አሜሪካ በዚህ ድርጊት በጣም ግራ ገብቷታል!

አሜሪካ በጦር ጄቶች የሚስተካከላት ሀገር ያለመኖሩ ይታወቃል። ይሁንና የቴክኖሎጂ ምስጢሮቿ ሁሉ በቻይና እየተሞነቼፉ የተቸገረቺው አሜሪካ " ይሄ ነገር ቻይና የምትወስደው የጦር ቴክኖሎጃዎችነሰ ከምሸጥላቸው ሀገሮች እየሞነቸፈች ይሆናል" በሚል ለማንም የማትሸጠውን እንኳን ሌላው ቀርቶ ለእስራኤል እና እንግሊዝ እንኳ የማታቀርበውን F-22 የተሰኘውን አምስተኛ ትውልድ የጦር ጄት አመረተች።

የሚገርመው ግን ቻይና የዚህን ጦር ጄት ረቂቅ ለማግኘት የአሜሪካን የመረጃ ደህንነት ሰብራ ለመግባት አመትም አልፈጀባትም። እንዳለ ዳታዎችን ወስዳ በቴራባይት የሚቆጠሩ ወታደራዊ ምስጢሮችን የጦር ቴክኖሎጃዎችን ወስዳ ለራሷ J-20 mighty dragon የተሰኘውን እጅግ የዘመነ የተራቀቀና ከየትኛውም ራዳር እይታ ውጭ የሆነ የጦር ጄት ሰራች። Mighty dragon እስካሁን በርካታ የቻይና ባላንጣ ሀገራትን አየር ክልል ጥሶ ገብቶ ቃኝቶ ተመልሷል ግና አንድም ጊዜ ታይቶ አይታወቅም።

በቅርቡ F-35 የተሰኘውን አምስተኛ ትውልድ የጦር አይሮፕላን የሰራቺው አሜሪካ ማንም የማይተስካከለውን የጦር ጄት ሰራሁ ብላ ነበር። ግና ቻይና ሰሞኑን ይፋ ያደረገቺው J-35 የጦር ጄት በየትኛውም መመዘኛ ከአሜሪካዎቹ የጦር ጄቶች ልቆ ቻይናን ሲያኮራ ጠላቶቿን ድንጋጤ ውስጥ ከቷል። ቻይና ዋነኛዋ የአሜሪካ ባላንጣ መሆኗን አረጋግጣለች።

በጣም የሚገርመው የአሜሪካ ጦር ከቻይና የተደበቀ መሳሪያም ሆነ ወታደራዊ ምስጢር የለውም። በእያንዳንዱ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ውስጥ የቻይና ሳይበር ሰራጊዎች ሰብረው የፈለጉትን መረጃ ሞንችፈው ይወስዳሉ።

ቻይና እየሄደችበት ያለው የቴክኖሎጂ ፍጥነትና የማምረት ተአምራዊ አቅም በጣም የሚደንቅ ነው።
በሁሉም መስክ እንደ ቻይና መሆን አሜሪካን የማስቆሚያ ትክክለኛው መንገድ ነው።

J-35 በጣም የሚደንቅ የጦር ጄት ሆኖ የቻይና ዘብ ሆኖ ቆሟል!በተፈለገም ጊዜ እስከ አሜሪካ ግዛቶች ድረስ መሸከም የሚችለውን 30 ቶን አውዳሚ መሳሪያ ለማራገፍ ሰአታት አይፈጁበትም።

ከሁሉ በላይ ግን H-20 የተሰኘው ቦምብ ጣይ አይሮፕላኗ ግርምትን የሚያጭር ነው።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

Seid Social

21 Nov, 12:38


ሂሳቡ የሚወራረደው በንፁሀን ደም ላይ ነው!
እንጅ ፅንፈኞቱ እርስበርሳቸው ይከባበራሉ ብቻ ሳይሆኖ ይተባበራሉ!

አዎ ንፁሀን ወገኖቻችን ግን በየትኛውም አቅጣጫ የሂሳብ ማወራረጃ ሆነው ቀጥለዋል ለማን ሲባል የፅንፈኞቹ አላማ እንዲሳካ ህዝብ ለእልቂት እንዲንቀሳቀስ ሲባል!

ትላንት የኦሮሚያ ፅንፈኞች በወለጋ ላይ በነዚያ ምስኪን ወገኖቻችን ላይ ነው ታይቶ የማይታወቅ ግፍና ጭካና የፈፀሙት። ገና የተወለደ ጨቅላ ልጅ ሳይቀራቸው አር**ደው የሄዱት ! ይሄ ለኦሮሞ ብሔርተኞች አይታያቸውም! ኦነግ ደራ ገብቶ እኛን የመሰሉ ታላቅ አሊም ከየቤተሰቦቻቼው ከጨረሰ ገና ሳምንት አላለፈውም!

በተራቸው ደግሞ የአማራ ፅንፈኞች ሽፍታዎች ጨካኞች በስመአብ እያሉ ለወሬም ለማየትም የሚዘገንን ግፍ ፈፀሙ። እንኳንስ በብሔር የሚለያቸውን በሀይማኖት የተለዬዋቸውን የክልሉ ሙስሊሞች ላይ የፈፀሙትን ማመን ያስቸግራልና የአማራን ህዝብ ሌላ የእልቂት ማገዶ ለማድረግ በስመአብ ብለህ እንትን በለው ብለው ቪዲዮ ቀርፀው እንካችሁ አሉን። እኔ አላየሁትም በፍፁምም ላየው አልፈልግም ! እንድህ አይነቱን ጭካኔ እንደት ማየት ይቻለኛል!!

ሁለቱ ፅንፈኞች አይጣሉም። ቢጣሉና አላማቸው የህዝብ ቢሆን እርስበርሳቸው ተጋጥመው ይለይላቸው ነበር። ፋኖም ኦነግ ሸኔም ደራ ላይ አሉ። በአብዛኛው ቦታ ተጎራብተው ነው መንግስትን የሚዋጉት። ግና እርስበርስ አንድ ጊዜም ተዋግተው ቀርቶ አንድት ጥይት ተታኩሰው አያውቁም!

ግና የነርሱ ኪስ እንዲደለብ ሀገሪቷ እንድትታመስና የደም ቀጠና እንድትሆን የኦሮሞና የአማራ ህዝብን የሚያስተሳስሩ የዝምድና ገመዶች ተበጣጥሰው እርስበርሱ የሚተላለቅ ህዝብ እንዲሆን ይሻሉ። ይህንንም ከሁለቱም ወገን ንፁሀንን እየገደሉ ቪዲዮ እየቀረፁ ይለቁልናል።
የሚዲያው ፅንፈኞችም ይህንን እያራገቡ ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ ይዘምታሉ!

Seid Social

21 Nov, 11:40


የሩሲያ የሚሳኤል ዝናብ በዩክሬይን ላይ!

ዩክሬን ሩሲያ በህጉር አቋራጭ ባልስቲክ ሚሳኤል እየደበደበቸቺኝ ነው በማለት እየሰሞተች ትገኛለች።
የሩሲያ አስፈሪ ጥቃት በኬይቭ ላይ የሚጠበቅ ሲሆን አብዛኛው የምእራባውያን ሀገራት ኢምባሲዎቻቼውን በዩክሬይን ዘግተው ወጥተዋል

Seid Social

20 Nov, 18:23


ቲክቶክ የለየለት ሌላኛው አፋኝ ፕላትፎርም ሆኗል።
በአሜሪካ እንዲዘጋ ከቀረበበት ክስ አንዱ "ለፍልስጤማውያን ድምፅ ትሆናለህ" የሚል የነበረ ቢሆንም ቲክቶክ የአሜሪካ ገበያውን ላለማጣት ከነ ፌስቡክም እየባሰ ይገኛል።

እናም የትኛውንም እነ አሜሪካ የማይፈቅዷቸውን ኮንቴንቶች እያጠፋና አካውንቶችን እያገደ ይገኛል።

ብቻ ሀይልና አቅም ይኑርህ እንጅ ሁሉም ወዶ ሳይሆን ተገዶ አገልጋይህ ይሆናል!
የአሜሪካ አገልጋዮች የበዙትም ለዚያ ነው!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

Seid Social

20 Nov, 17:49


ይሄም ጀግና ሸሂድ ሆነ😢
ንግግሩን ሰምቼ ሳልጠግበው ወንድሞቹን ተከተለ!
ሸሂድ ሙሀመድ አፊፍ የሂዝቡላህ የሚዲያ ሀላፊ ነበር። ባለፈው ንግግሩን አጋርቻችሁ ነበር ። እንደት የሚያምር ተናጋሪ!

" ያ የህያ አንተ የህያ ሆይ ኪታብህን በሀይል ያዘው በያዝከው በትርም የጠላትህን ጦር ምታው ይበታተናልና!
እኛ ጋር የሚጋደደለው ሩሀችን የሩሀችን እንጥፍጣፊ ጭምር ነው።
ያ የህያ ሰላም ባንተ ላይ በወንድምህ በኢስማኢልም ላይ ይሁን !
ሰላም ባንተ ላይ ይሁን! ሙተህም እንደት ነው የምታምረው 😢
በህይወትም ሳለህ ሀይልህ  እንደት ያለ ትልቅ ነበር!!!
ጀግና ሆነህ ኖርክ የማይጠፋ ታሪክም ሆነህ አለፍክ!!!
የሀቅ ባለቤቶች ስለባጢል ዝም ባሉ ጊዜ የባጢል ባለቤቶች ሀቅ ላይ እንዳሉ አሰቡ......" የሚለውን ንግግሩን መቼም ላረሳው በውስጤ ይኖራል!

ሙሀመድ ተዋጊ ሳይሆን የሚዲያ ሰው ነበር። ግና አረመኔው የእስራኤል ወራሪ በአየር በፈፀመው ጥቃት ሸሂድ ሆኗል!

አላህ በጀነቱ ይቀበለው!

Seid Social

19 Nov, 17:20


ዘመነ ካሴን ከአፄ ቴዎድሮስ ጋር ብዙ ነገር ያመሳስለዋል።

1 ሁለቱም በጣም ትልቅና የተለጠጠ ህልም አላቸው ግና ህልማቸውን የሚያሳኩበት መነገድም ብልሀትም ብስለትም የላቸውም! ሁለቱም ትልቅ መሪነትን ያልማሉ ትልቅ መሪ እንደት እንደሚኮን ግን እውቀቱም ዝግጅቱም የላቸውም። ከሌሎች ስኬታማ መሪዎች እንዳይማሩ ኢጎ ጠፍሮ ይዟቸዋል።

2 ሁለቱም ለራሳቸው ያላቸው ግምት ከሆኑት በላይ እጅግ የተጋነነ ነው። ባልሆኑት ይፎክራሉ ! ራሳቸውን ሲያንቆለጳጵሱ አይሰቀጥጣቸውም። አፄ ቴዎድሮስ ራሱን " የኢየሩሳሌም እጮኛ " እያለ ነበር የሚደልለው። ይህን የሚለው እንኳን ኢየሩሳሌምን የኢትዮጵያን 1/10ኛ ግዛት እንኳ መቆጣጠር ባልቻለበት ሁኔታ ነው። ዘመነም እንደዚያ ነው ለራሱ ያለው ግምት በጣም በሚያሳፍር መልኩ የተጋነነ ነው። ራሱን " አርበኛ ዘሜ ፤ ዘሜ እንድህ ብሎ ፤ ዘሜኮ ንጉስ ነው" ሲል ያሳቅቃል። አንድት ከተማ ሳይቆጣጠር " አራት ኪሎን ከሰጡን እንደራደራለን" ሲል ደግሞ የአእምሮ ጤንነቱም ያጠራጥራል። አፄ ቴዎድሮስ ኢየሩሳሌምን መቆጣጠር እንደሚያልመው ሁሉ ዘመነም እንዲያ ነው- የምስራቅ አፍሪካው ሀያል መሪ መሆንን ይመኚል። እንደት የሚል ፍኖተ ካርታ ግን እንኳን እጁ ላይ ሀሳቡ ላይ እንኳ ውል አይልበትም።

3 ሁለቱም ሲበዛ የዋህነት ያጠቃቸዋል። የምትፈነዳ መሳሪያ አጠገባቸው ከተሰራች የጦር ሀያል የሆኑ ያክል ይሰማቸዋል። አፄ ቴዎድሮ የሀይማኖት ሰባኪ ሚሲዮናውያንን ገና ለገና ነጭ ናቸው ብሎ መድፍ ካልሰራችሁ እያለ ቢያስገድዳቸው አንድ መድፍ የሚመስል ነገር የግድ ሰሩለት። ያንን እንደ ትልቅ ነገር ያየው ቴዎድሮስ " ሴቫስቶፖል" ብሎ ሰየመው ግና መድፉ አንድ ጊዜ ፈንድቶ ፈረሰ። ዘመነም በየጫካው የማቀጣጠል ነገር ሁሉ እያስጮኸ " ሚሳኤል እየሰራን ነው" ይላል። ቀላል አያስቅም!

4 ሁለቱም በትንቢት ያምናሉ። " ቴዎድሮስ የሚባል ንጉስ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ኢየሩሳሌምን ከእስላሞች ነፃ ያወጣል" የሚል ትንቢት የሰማው ሽፍታው ካሳ ሀይሉ ራሱን ወደ ቴዎድሮስነት ለመቀየር ጊዜ አልፈጀበትም ነበር። ትንቢቱን ሊያስፈፅም መሆኑ ነበር። ግና ፖለቲካና ጦርነት በስትራቴጂ እንጅ በትንቢት አይመራምና ከመቅደላ ምሽጉ ሳይወጣ አቀለበ። ዘመኔም የካሳ ቢጤ ነው። እንደዚህ የሚገፋው ትንቢት ነው። ትነግሳለህ ብያለሁ ነው የርሱ ሙግት!

5 ሁለቱም ግትር ናቸው። Compromise የሚባል ነገር አያውቁም። ስልታዊ የሀሳብ ለውጥ የአካሔድ መስተካከል የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም። የያዙትን አይረሱም ብቻ ሳይሆን አይለቁም። ድርቅ እንዳሉ ይቀጥሉና መጨረሻቸው መሰበር ይሆናል። የማንንም ሀሳብ የመስማት ዝግጁነት ያላቸውም። ሁሉንም ነገር በሀይል መፈፀም እንደሚችሉ ብቻ ያምናሉ። ካለነርሱ ሀሳብ ሌላው ውድቅና ተራ ሀሳብ ነው። ይህ የሁለቱም ትልቁ ድክመታቸው ነው።

6 ሁለቱም የሚከተሉት የሀይል አሰላለፍ ጠላት አብዥና ከወቅቱ ጋር የማይሄድ መቶ አመታትን ወደሗላ ሂዶ የተቸነከረ ሀሳብ ነው። አፄ ቴዎድሮስ ከዘመኑ በጣም ወደሗላ ምናልባት በሺህ አመት የቀረ ሰው ነበር። ሂሳቡም ሀሳቡም ወደሗላ የተቸነከሩ በመሆናቸውና በወቅቱ የነበረውን የአለም ተጨባጭ ማወቅና መረዳት ባለመቻሉ ተበልቷል። በዚያ ላይ ከርሱ ውጭ ያለን ሁሉ የኔ ጠላት ነው ብሎ በማሰቡ ጠላቶቹ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንዲሆኑና ወዳጆቹ ደግሞ ጥቂት እንዲሆኑ ኧረ ምንም ወዳጅ እንዳይኖረው አድርጎታል።
ዘሜም ያው ነው😁 በጠላትነት የማይፈርጀው የለም። ጥቁር አማራ የሚባል አለ ፤ እዚያው ፋኖ ውስጥ ያለ ሌላ ሀይል አለ ፤ እስላም አለ ፤ ፔንጤ አለ ፤ ኦሮሞ አለ፤ ቅማንቱ አገው አለ ፤ ኧረ ምን የሌለ አለ ። እና በዚህ ሁሉ ጠላት አብዢ ፖለቲካ ውስጥ የት ሊደርስ ይችላል??? የትም!

ይልቅ የቴዎድሮስ አይነት ፍፃሜ እንዳይደርሰው ከታሪክ ቢማር ይሻለዋል!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

Seid Social

19 Nov, 15:23


የሀማስ አመራሮች ኳታርን ለቀው ወጥተዋል። መዳረሻቸውም የኤርዶጋኗ ቱርክ ሆኗል።

የሀማስ ተደራዳሪዎችና አመራሮች ኳታር ዶሀን ለቀው ቱርክ መግባታቸው ታውቋል። ኳታር በዛሬው እለት አመራሮቹ ሀገሯን ለቀው መውጣታቸውን አረጋግጣለች።

አሜሪካ ኳታርን የሀማስ አመራሮችን እንድታስወጣ መጠየቋን ተከትሎ ነው ኳታር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰቺው። ኳታር ሀማስና እስራኤልንም ማደራደር ማቋሟን ማስታወቋ ይታወቃል።

የኳታርን ሀላፊነት ቱርክ የምትረከብ ይሆናል። እንግድህ ቱርክ የሀማስ አመራሮችን በሀገሯ መቀበሏ ከአሜሪካ የሚያመጣባትን ጫናና ምን ያክልስ ትቋቋመዋለች የሚለውን የምናየው ይሆናል።

ቱርክ ከየትኛውም ሀገር በላይ አስተማማኝ መጠጊያቸው ልትሆን የምትችል ሀገር ናት።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

Seid Social

18 Nov, 19:51


ከሂዝቡላህ ሮኬት ለማምለጥ ሲሮጥ በመኪና ተጨፈለቀ!

የእስራኤላውያን ኖሮ በአሁኑ ሰአት ይሄን ይመስላል- ደወል በተደወለ ቁጥር ወደ ምሽግ ሩጫ!
እናም ዛሬ ሂዝቡላህ ርኬት ሲያስወነጭፍ ወደ መደበቂያ ሲሮጥ የነበረ እስራኤላውዊ በመኪና ተገጭቷል።

t.me/Seidsocial

Seid Social

18 Nov, 18:48


በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለእስራኤል ተሰልፈው ይዋጋሉ። ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የሄዱ ፈላሻዎች በብዛት በውትድርና ውስጥ ይገቡና ይጋደላሉ።
እስራኤልም እነዚህን ሰዎች የምትፈልጋቸው ለዚህ ብቻ ነው።

ከዚያ ውጭ እነኝህን ፈላሻዎች እስራኤል እንደ ዜጎቿም አታያቸውም። ስልጣንም ለነርሱ የተገባ አይደለም። ኢኮኖሚውና ማህበራዊው ዘርፍ ውስጥ ለነርሱ የሚሆን ቦታ የለም። የሀገሪቱ የመጨረሻ ድሀዎች እነርሱ ናቸዎ። አንድም ፖለቲካዊ ውክልና የሌላቸው የተናቁና እስራኤላውያን በጣም የሚፀየፏቸው ናቸው።

እስራኤል እየተዋጋች ወታር ቢማረክባት ሁሉንም ነጭ እስራኤላውያን ስታስለቅቅ ለእነርሱ ግን አትደራደርም ሁላ።

እነኝህ ከኢትዮጵያ የፈለሱ አካላት እስራኤል ጋር ተወዳጅነት ለማግኘት ከማንም በላይ ቢዋጉና መስዋዕትነት ቢከፍሉም ግና ከነጭ እስራኤላውያን ወንድ ከባርነት የዘለለ ክብር የላቸውም። ሌሎቹ እስራኤላውያን እንዲኖሩ መስዋዕት መክፈል ያለባቸው ሰዎች ናቸው።

ዘረኝነቱ በጣም የሚገርም ነው። ከጦር ሜዳ አስክሬናቸው ሲመጣ እንኳ ተገቢው አቀባበር አይደረግላቸውም።

ግና እንኳንስ እስራኤላውዊ ነን ብለው የሄዱት እነርሱ ይቅሩና እዚህ ሀገራችን ያሉት መፍቀረ እስራኤላውያን እንኳ ይወዷታል ሳይሆን ያመልኳታል ቢባል ይቀላል።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

Seid Social

18 Nov, 18:11


መስጅዶችን ከእንደዚህ አይነት ኹራፋቶች ማራቅ ያስፈልጋል።

ኢስላም የዳንስ አምሮት መወጫ ድን አይደለም። እንደዚህ እየተጨማለቁና ከልክ ያለፈ ጋጠወጥነት እያሳዩ ሲተቹና ሲወገዙ " የዚክር ጠላቶች " እያሉ የሚጮሁ እንዳሉ ቢታወቅም ሰጋጁ ማህበረሰብ ከእንደዚህ አይነት ከኢስላማዊ አደብ የወጡ ተግባራትን ከመስጅዶቹ መከላከል አለበት። የሚጨፍሩበት ሂደው ይጨፍሩ መብታቸው ነው። ግና መስጅድ የገሪባ አይነት ስራ ማካሔጃ አይደለም!

ይሄን ጫት የሚባል ቆሻሻ ተክል ከህዝባችን ላይ አላህ ይንቀልልን!

Seid Social

18 Nov, 16:30


በአለማችን ላይ እንደ ቻይና የሚያምሩ የተራቀቁ በቴክኖሎጂ እጅግ የመጠቁ ከተሞች ያለው ሀገር የለም። የቻይና ከተሞች በምስል ሲታዩ እውነት እውነት አይመስሉም። አሜሪካም ጃፓንም እንደ ቻይና ያለ ውብና ረቂቅ ከተሞች የላቸውም።

ይሁን እንጅ ቻይና እነዚህን ከተሞቿን አማራቀቋ በፊት በመጀመሪያ የሰራቺው በድህነት ከአለም ቀዳሚ የሚያደርጋትን ህዝብ አድህነት አሮንቃ ማውጣት ነበር። ከ 30 አመት በፊት ቻይና 900 ሚሊዮን ድሆች የሚኖሩባት ሀገር ነበረች። በዚህም በድህነት የሚስተካከላት ቀርቶ የሚቀርባት ሀገር አልነበረም።
እናም ቻይና የተራበውን ህዝቧን መመገብ ፤ ስራ አጥ ህዝቧን የኢንዱስትሪ አብዮት በማፈንዳት ሀገሪቷን የምርት ውቅያኖስ ማድረግ ፤ ሰላምና ደህንነቷን ፍፁም በማረጋገጥ በሯን ለውጭ ኢንቨስተሮችና ለአለም ቴክኖሎጂ ክፍት ማድረግን የመውጫ መንገድ አድርጋ ሰርተው በማይጠግቡና ሙስናን አብዝተው በሚፀየፉ አመራሮቿ ሞተሯን ማንቀሳቀስ ጀመረች።

የቻይና የኢኮኖሚ አብዮት በተቀሰቀሰ በ 30 አመቱ 850 ሚሊዮን ህዝብን ከድህነት መንጭቆ በማውጣት ለማስረዳትም ለመንገርም የሚከብድ ተአምራዊ እድገት አስመዘገበ።
ልብ በሉ የዛሬ 40 አመት የቻይና ህዝብ 88% ቱ ድሀ የድሀ ድሀ ነበር። 12% ህዝቧ ብቻ ነበር በልቶ ለማደር የማይቸገረው። ዛሬ የቻይና ድሀዎች ቁጥር 0.5% አይሞላም። ይህም 11% ድሀ ህዝብ ካላት አሜሪካ ጋር ሲየፃፀር የቻይናን ከመገረም ውጭ ማስረዳት ይከብዳል። እነርሱም በጣም ገጠርና ጠረፍ አካባቢ የሚኖሩ ናቸው። እነርሱንም ቻይና ከድህነት ለማላቀቅ እረፍት የላትም።
እና ቻይና የጀመረቺው ድህነትን ከማጥፋት ምርትን ከማስፋፋት ምግብን ከማትረፍረፍ ቴክኖሎጂን አስገብቶ ሀገሪቱን የአለም ምርት ማእከል ከማድረግ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከማጥፋት ነበር። ከዚያ በሗላ ከተማውም ቢዋብ ቢገነባ ያምርበታል።

የኛው ሀገር ብልፅግና የእድገት ሞደል ግን እጅጉን እንቆቅልሽና ግራ አጋቢ ነው። ከከበሩ በሗላ ከሚደረስበት የመዋብ ስራ የጀመረው ብልፅግና የሀገሪቱን የድህነት መጠን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮታል።መካከለኛ ገቢ ያላቸው ህዝቦቻችን ወደ ድህነት ወለል እንዲፈጠፈጡ ድሀዎቹ ደግሞ በፍፁም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ጎዳና ላይ እንዲወድቁ ያደረገው የብልፅግና ስርአት ድሀ ጠል ካፒታሊስታዊ ጨካኝ ስርአት እንጅ ድህነት የሚጠላ ድህነትን የሚታገል የህዝብ አለኝ አለመሆኑን ከጊዜ ወደጊዜ እያረጋገጠ ይገኛል።

በፓርክና መዝናኛዎች ቢሊዮነ ቢሊዮናትን እየከሰከሰ የሚገኘው ብልፅግና በሚከተለው የተበላሼ አስተዳደራዊ ስርአት ኢትዮጵያን የጦርነት ቀጠና አድርጓታል። የትምህርት ስርአቱን ገድሎታል። ተምረው የተመረቁትን ብቻ ሳይሆን ስራ ላይ ያሉትን ጭምር በማባረርና በመቀነስ ለህዝብ ፍፁም ግዴለሽነቱን ያሳየ ስርአት ሆኗል።
እድሜ ለብልፅግና በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ትምህርት ቆሟል። ብዙ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቼውን መመገብ አቅቷቸው ማስተማር አቁመዋል። እንኳንስ ተማሪ የዩኒቨርስቲ መምህራንም በልቶ ማደር ያልቻሉባት የዘር ሳይሆን የመደብ አፓርታይዳዊ ስርአት ባለቤት ሆነናል።

ኢንዱስትሪውን አውድሞ ፓርክና ሳር ተከተላ ፎንቴይን ገጠማ ላይ የተጠመደው ብልፅግና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ፓራላይዝድ አድርጎታል።
የታክስ መአት በመደራረብ ህዝባችን አንድ እጁን ለመንግስት ሁለት እጁን ለሌባ አመራርና ግብር ሰብሳቢዎች እየገበረ ጥቂቶች እየከበሩ አብዛኛው ህዝባችን ግን መቀመቅ እየወረደ ይገኛል።

ብልፅግና "ትለብሰው የላት ትከናነበው አማራት" አይነት ስርአት ነው። በድህነት ከሚማቅቀው ህዝብ እየቀማ ሰውሰራሽ ሀይቆችን ይገነባበታል፤ የድሀን ቤት ካለምትክ እያፈረሰ ባዶ ያደርገዋል። ብቻ ተዘርዝሮ አያልቅም።

እንድት ሀገር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ሳታልፍ የትም ፈቀቅ ልትል አትችልም። የኛው መንግስት ግን ሁሉንም አልፎ በሰርቪስ ሴክተሩ ላይ ተጠምዷል። ያውም በሌብነት የተትረከረከ ሴክተር!

ብቻ የብልፅግና ነገር ይገርማል!
ለህዝባችን አላህ ይድረስለት!

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial

Seid Social

18 Nov, 15:07


ህፃናትን ጨፍጭፎ እየተዝናና ነበር። እናም ስልኩን ይዞ የጭፍጨፋ ውጤቱን ሊያሰራጭ ሊሰማ ሲል ሙጃሂዶቹ በመነፅራቸው ውስጥ አስገብቸውት ኖሮ ጀርባውን በስናይፐር ነድለው አሰናብተውታል።
ዛሬ በርካታ የስናይፐር ኦፕሬሽኖችን ሲሰሩ የዋሉት ሙጃሃዶቹ የእስራኤል ወራሪዎችን መልቀም ተሳክቶላቸዋል

Seid Social

16 Nov, 19:01


እዚህች ምድር ላይ ስትኖር ወዳጅና ጠላትህን እንደመለየት ያለ አዋቂነት የለም።
ሙሀመድ ሙርሲ በህዝብ ወደ ስልጣይ ሲመጣ እንደ ጀኔራል አብዱልፈታህ አልሲሲ የሚያምነው የሚተማመንበት ሰው አልነበረም።

በሶደቃው በኢባዳው በመደሰት አልሲሲን አጋሬ ባደርገው የማልማትን ግብፅ መፍጠር እችላለሁ ብሎ ነበር ፊልድ ማርሻል ሁሰይን ተንታዊን ከጦር መሪነቱ አንስቶ የግብፅን ጦር አመራርነት ያስረከበው።

አልሲሲ ግን ላዩ ሌላ ውስጡ ሌላ የነበረ ሰው ነበርና የሙርሲን መልካም ልብ በመክዳት ለወጠው። እናም የህልም አጋሬ ያለው አልሲሲ የሙርሲ የህይወት ጠላት ሆኖ መፈንቅለ መንግስት አድርጎ ሙርሲን እስርቤት እንዲሞት አደረገው።

የነ ሳኡዲ አረቢያና ኢማራት ረብጣ ቢሊዮን ዶላሮች የአሜሪካና እስራኤል ስለላ መንገዱን የጠረጉለት አብዱልፈታህ አልሲሲ ከሙርሲ የተዘረጋለትን የፀጋ እጅ ቆርጦ ዛሬ ግብፅን በፈላጭ ቆራጭነት ይመሬት ይዟል።

ፖለቲካ ለእንደነ ሙሀመድ ሙርሲ አይነቶቹ ቅንና ሰዎችን በላይኛው ገፅታቸው አይተው ለሚወዲ ሰዎች የሚሆን አይደለም። ፖለቲካ ደግ እንኳ ሆነህ መሰሪነትን ይጠይቃል!
ዛሬ የግብፅ መሪ ሙርሲ ሆኖ በነበር ምናልባት የፍልስጤማውያን ሰቆቃ እንደዚህ ባልሆነ ነበር። ቢያንስ የግብፅ በር እንኳ ይትላቸው ነበር!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

Seid Social

16 Nov, 18:14


የሙዚቃ ድግሱን ይደግሱ ምናልባት ሀገራቸው ስለሆነ መብታቸው ይሆናል!
ግና እንደት የካእባን ምስል ከሙዚቃ ድግሱ ከራቁት ጭፈራው ጀርባ የማድረግ ድፍረት አገኙ?
እንደት በኢስላም ሸአኢሮች ላይ በዚህ ልክ የመሳለቅን ድፍረት አገኙ?
እጅግ ያሳዝናል!

ሁላችንም ወንጀለኞች ነን። እንድህ አይነት ፈሳድ በምድር ላይ ተስፋፍቶ ካእባ ያውም በሙስሊሞች ያውም ሳኡዲ ላይ መሳለቂያ ይሆናል ብሎ ከመካከላችን ያሰበ ነበር?? በጭራሽ!!
ብቻ አላህ ይሁነን።

ይደክማል ሀቂቃ! በስንቱ ተበሳጭተን እንዘልቀዋለን!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

Seid Social

16 Nov, 07:49


እንደው ሌላውን ተውት እኔ ለዚህ ኢዛቼው ለዚህ የሞራል ልእልናቸው ትልቅ ክብር አለኝ!
አለም የሚሰግድላት አሜሪካ ላይ ላላቸው የሞራል ልህቀት ትልቅ አክብሮት አለኝ!
እንኳን ሙስሊም ወንድሞቼ ሆነው ባይሆኑ እንኳ ለአምባገነኖችና ፈላጭ ቆራጮች ለማያጎበድድ ሁሉ አለማድነቅ አልችልም።
ጀግናን እንኳን ወዳጁ ጠላቱ ያከብረዋል !

Seid Social

15 Nov, 17:50


ቢዘገንንም የግድ ማየት ስላለባችሁና የሁለቱ ቅዱስ ከተሞች መገኛ የኢስላም መነሻ ምድር ምን ያክል ውድቀት እና እርክሰት እየተፈፀመበት እንዳለ ማወቅ ስላለባችሁ ለጠፍኩት።

ይህ የሰሞኑ የሳኡዲ ክራሞት ነው። ሳኡዲ የአሜሪካዋን ላስቬጋስ የሚያስንቅ እጅግ ከሞራል የወጣ የሙዚቃ ኮንሰርት በዚህ መልኩ እያዘጋጀች ትገኛለች። የሪያድ ኮንሰርት ሳኡዲ አረቢያ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮችን ከስክሳ እነ ጄኒፌር ሎፔዝን ከአሜሪካ አስመጥታ የአድሷን ጉዞ ያሳይልኛል ያለቺውን የሙዚቃ የፋሽን ትርኢት በዚህ መልኩ እያሳየች ትገኛለች።

የሀቅ ኡለሞችን በሙሉ ለቃቅማ አስራ የቀሩትን አንድም በማስፈራራት አንድም በስልጣንና ገንዘብ ደልላ ሀገሪቷን ወደለየለት የጅህልናው የቁረይሾች ዘመን መልሳታለች።

ይህንን እንኳ በቅዱሱ የመድናና መካ መገኛ ምድር እናያለን ብለን አስበንም አናውቅ ነበር😢

Seid Social

15 Nov, 16:14


#ከዳተኛዋ_ሞሮኮ !

ከአረብ ባ*ን**ዳ ሀገራት ውስጥ ሞሮኮ ቀዳሚዋ ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ሞሮኮ የምእራባውያን እና የእስራኤል ተላላኪ በመሆን ሙስሊሙ አለም ላይ ትልቅ ኪሳራ ካደረሱ አንገት ካስደፉ ሀገራት አንዷ ነች ።

እስራኤል የ 1967ቱን የ ስድስት ቀን ጦርነት ካለ ሞሮኮ የክህደት ስራ አታሸንፍም ነበር ። ይህ እስራኤል በፅኑ የምታምንበትና ለዚህም ሞሮኮን የምንጊዜም ወዳጅ ሀገር አድርጋ የያዘችበት እውነት ነው ።

እስራኤል ጦርነቱን በድንገተኛ ጥቃት ከፍታ ግብፅን ከማነኳኮቷ በፊት የአረብ ሀገራት መሪዎች በምስጢር ተሰብስበው እየመከሩ ነበር ። እስራኤል በጊዜው አረብ ሀገራቶች ጥምረት ከፈጠሩና አንድ ግንባር ከመሰረቱ ህልውናየ ያከትምለታል ብላ በከፍተኛ ሁኔታ የምትሰጋበት ወቅት ነበር ።

ታዲያ ከተሰብሳቢዎቹ አንዱ ባንዳው የሞሮኮ ንጉስ ሀሰን ዳግማዊ ነው ። እናም ይህ ንጉስ የአረብ መራዎችን የምስጢር ስብሰባ እየቀዳ ለእስራኤል አሳልፎ መስጠት ስራው ነበር ። እስራኤል ከንጉስ ሀሰን የሚደርሳት መረጃ ያስፈነድቃት ነበር ። የአረብ መሪዎች ይሰብሰቡ እንጅ አንድነት የሌላቸውና የተበጣጠሱ ነበሩ ። የግብፁ ፕሬዚዳንት ገማል አብዱልናስርና የዮርዳኖሱ ንጉስ ሀሴን እርስበርሳቸው የሚገለማመጡ የሚዋረፉ ሆነው ነበር እስራኤልን ለመታገል አብረው የሚሰበሰቡት ። የአረብ ሀገራት ጦርም ዝግጁነት የጎደለው የተዝረከረከና በሳል ወታደራዊ አመራር ያሌለው ነበር ። ይህን ሁሉ ጮማ ጮማ መረጃ የሞሮኮው ንጉስ ሀሰን ለእስራኤል እያሾለከ እየቀዳ ይልካል ። እስራኤል ስለቴ ሰመረ እያለች በመረጃው መሰረት የጦር እቅዷን ትነድፋለች ።

ሁሉንም መረጃ ካገኘች በሗላ ነው ግብፅ ላይ በ 1967 በከፈተቺው ድንገተኛ ጥቃት ስድስት ቀን ብቻ በፈጀ ጦርነት ያነኳኮተቻት ።

ሞሮኮ ከትላንት እስከዛሬ ከባንዳነት ተላቃ አታውቅም ። አሁንም ቢሆን የእስራኤል ቀኝ እጅ የስለላ ጆሮዋ ነች ።
እነኝህ እርኩስ ንጉሶቿ ከነብያችን ቤተሰብ እንወለዳለን የሚል ማጭበርበሪያ እየተጠቀሙ ንግስናቸው ከአላህ የተቀባ ለማስመሰል ቢደሰኩሩም ስራቸውና የግብር ዝምድናቸው ግን ከአብደሏህ ኢብኑ ሰሉል እንጅ ከሙሀመድ ኢብን አብደላህ ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ አይደሉም !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

Seid Social

15 Nov, 12:30


የሀይማኖት መሪ ነን ባዮች የሞራል ውድቀት እንደ ሀገር ለተከሰተው ኢሞራላዊነት የራሱ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

የሀይማኖት መሪ ነን እያሉ ብዙዎች ሌብነት ፤ ሴሰኝነት ፤ ሙስና ፤ ማጭበርበር ፤ መድፈር እንኳን ሌላው ቀርቶ ማሳገትና ማስገደል ደረጃ ላይ መድረሳቸው ከታች ያለውን ማህበረሰብ በሞራልና ስብእና እንዲበሰብስ የራሱን ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

በተለይ ፓስተርና ነብይ ነን እያሉ ያለ ሰዎች እየሄዱበት ያለው አስፈሪ ውድቀት የምእራብ አፍሪካ ሀገራት አስቀያሚ ክስተቶች ሀገራችን እንዲከሰት እያደረገ ይገኛል።
ይህ እንግድህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሸለሙትን አለምአቀፍ ሽልማት ለርሱ ያስረከቡትና " መልካም ወጣት" በሚል ብዙዎችን ከመልካም ወጣትነት ያራቀው የፓስተር ዮናታን አክሊሉ የአደባባይ ድርጊት ነው።
ጌታ አዞኛል እያሉ የስንቶቹን ጨዋ እንስቶች ህይወት እንዳመሰቃቀሉ ቀረብ ብሎ የሚያውቅ ያውቀዋል።

ድንቄም ነብይነት!