️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹 @fana_televisions Channel on Telegram

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

@fana_televisions


This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions

#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን

ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT



https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹 (Amharic)

ይህ ከፋና ሚዲያ እና አባሊነት ኮርፓሬት ጠቅላላ ቴሌግራም አገልግሎት። ለተጨማሪ መረጃ እባኮታ ይሁኑ

በተጨማሪ መረጃ ለተከታተሉ በማልበት ይሁኑ
https://t.me/fana_televisions

#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን

ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT



ከዚህ በፊት ገጽ ያደርጋሉ፦ https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 15:19


የፋና ቀለማት የዚህ ሳምንት ጉዳዮች
#ፋናቀለማት
#ፋናላምሮት
#ፋና80

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 14:22


➔USDT
➔HMSTER
➔DOGS
➔NOTCOIN
➔X-empire
መሸጥም ሆነ መግዛት የምትፈልጉ በአሪፍ ዋጋ እንገበያያለን
በውስጥ አውሩኝ 👉 @ethio_Doge

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 14:09


ሳውዲ

በፈረንጆቹ 2024 ሳውድ አረቢያ ከ100 በላይ የውጪ ሀገር እና የሀገሯን ዜግች በስቅላት የቀጣች ሲሆን

ይህም ከባለፈው ዓመት ሲወዳደር
በ3 እጥፉ የበለጠ ነው ተብሏል::

ምክንያቱ ደሞ : -

* ሰው መግደል
* ሀሺሽ ወደ ሀገሯ ማስገባት
* ሴት , ህፃናትን መድፈር እና
* ሌሎችም ህገ ወጥ ከባድ ወንጀሎች የሰሩት ሲሆን

ከዚሁ ውስጥ :-

* 21 ፓኪስታኖች 🇵🇰
* 20 የመኖች 🇾🇪
* 14 ሱሪያውያን 🇸🇾
* 9 ግብፃውያን 🇪🇬
* 8 ጆርዳናውያን 🇯🇴
* 7 ኢትዮጵያውያን 🇪🇹
* 3 ሱዳናውያን 🇸🇩
* 3 ህንዳውያን 🇮🇳
* 3 አፍጋኒስታውያን 🇦🇫
* 1 ስሪላንካውያን 🇱🇰
* 1 ኤርትራውያን 🇪🇷
* 1 ፊሊፒንሳውያን 🇵🇭

ይገኙበታል::

🌴

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 12:55


በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች

ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ነው፡፡ ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በሶስተኛው ቀን ቆይታዋ የግል ተበዳይ ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ የወርቅ ጌጣጌጦችን ሰርቃ በመሰወሯ የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት ለሦስት ወራት ተከራይታ በነበረበት ቤት ተደብቃ በክትትል የፖሊስ አባላት ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት፣ የሴትና የወንድ ጫማዎች፣ 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ፣ የተለያዩ የወርቅና ልዩ ልዩ ጌጣጌጦች ጋር በቁጥጥር ስር ውለችል በተጨማሪም በሁለት የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያ ተገኝቶባታል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አበበ እንደገለፁት የግል ተበዳይ ተጠርጣሪዋን ለስራ ሲቀጥሯት ያቀረበችው የተያዥ ፎርም የራሷን ፎቶ በትክክል እንዳይለይ አድርጋ የለጠፈች ሲሆን የግል ተበዳይም ይህንን ሳያረጋግጡ በእምነት የቀጠሯት መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክረዋል።

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 12:55


በእንግድነት ለበርካታ ቀናት በመቆየቱ ወደ ቤቱ እንዲሄድ የተጠየቀው ግለሰብ በአባወራው ላይ የግድያ ሙከራ በመፈፀሙ በእስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የግድያ ሙከራ የፈጸመው ተከሳሽ ፈይሳ ቢፋ በእስራት መቀጣቱን ያሳያል።

የወንጀሉን ዝርዝር አቃቤ ህግ እንዳስረዳው ተከሳሽ ፈይሳ ቢፋ ሰውን ለመግደል በማሰብ ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 7 ላይ በቀቤና ልዩ ወረዳ ልዩ ስሙ ጀረትማ ተብሎ በሚጠራው መንደር በግል ተበዳይ በአቶ ኢብራሂም ሀሰን መኖሪያ ቤት ውስጥ ተከሳሹ በእንግድነት ለማደር መግባቱን እና በርካያ ቀናትን በመቆየቱ ምክኒያት በቤቱ ባለቤት እንዲሄድ ቢጠየቅም አልሄድም በማለት ግጭቱ ተጀምሯል።

አልሄድም ከማለት ባለፈ እላፍ ንግግሮችን ተናግሮ አንደነበር የተበዳይ ባለቤት እንደተናገሩ የቀቤና ልዩ ወረዳ የወንጀል ጉዳዩች ከፍተኛ አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ በያን ሙሳ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በዕለቱ ተከሳሹ በቤቱ ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውለውን ቢላዋ በማንሳት የግል ተበዳዩን በስለት የቀኝ እጁ ሰዓት ማሰሪያው ላይ አንድ ጊዜ ሲቆርጠው በተጨማሪም የቀኝ እጁ አውራ ጣቱን፣ በቀኝ በኩል መንጋጋውን፣ የቀኝ ጆሮውንና ትከሻውን በቢላዋ በመውጋት ከፍተኛ ደም እንዲፈሰው በማድረግ የቀኝ እጁ ላይ የአጥንት ስብራት ያደረሰበት መሆኑን በክሱ ላይ ገልጿል።

አቃቤ ህግም በ1997 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣው የኤፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27/1 እና አንቀጽ 539 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ ተላልፏል በሚል በከባድ የግድያ ሙከራ ወንጀል ክስፍቅር አቅርቦበታል።የክስ ሂደቱን ሲከታተል የቆየው የቀቤና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ተከሳሽ ፈይሳ ቢፋ በቀለ አቃቤ ህግ የከሰሰውን የከባድ የግድያ ሙከራ ወንጀል ህግ ድንጋጌውን 113 / 2/ መሠረት በማሻሻል ወደ ወንጀል ህግ ቁ  540 ድንጋጌ ወደተራ የግድያ ሙከራ ወንጀል በመቀየር ጥፋተኛ ብሎታል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በማየት የቀረቡትን የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችን በመመዘን ሌላውን ያስተምራል ተከሳሹንም ያርማል በሚል ተከሳሽ ፈይሳ ቢፋን በ5 ዓመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የቀቤና ልዩ ወረዳ የወንጀል ጉዳዩች ከፍተኛ አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ በያን ሙሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 12:55


ህንድ እና ወርቅ

ህንዳዊያን የቤት እመቤቶች 11በመቶ የዓለም ወርቅ በእጃቸው ነው። ይህ ማለት አሜሪካ ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ጀርመን እና የአለም የገንዝብ ተቋም(IMF) ያላቸውን ወርቅ በጋራ ቢያደርጉ እንኳን የህንዳውያኑ የቤት እመቤቶች ይበልጣል።

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 12:49


ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ የተባለው ድርጅት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የጤና ስራ ለመደገፍ የሕክምና ቁሳቁስ በበቂ ሁኔታ እንደሚያስፈልግም የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ÷የሕክምና አገልግሎቱን በበቂ ሁኔታ ለመስጠትና ተደራሽ ለማድረግ የሕክምና…

https://www.fanabc.com/archives/271826

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 12:49


ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጋምቤላ ክልል የተገነባውን ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኩባንያው በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ በተከናወነው ትርጉም ባለው የኢንቨስትመንት ሥራም ለሁሉም አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሒደት ለብዙ ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገ-ወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ ለማዋል ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያሳይም ነው ያስረዱት፡፡

️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹

20 Nov, 12:49


አንድ ጉዳይ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን
#Fanapodcast
#Fanastream