የውጭ ሀገራት የገንዘብ ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰን መደረጉም ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አስገኝቷል ብለዋል፡፡
***************
አቶ አቤ ይህንን ያሉት “የውጭ ሀገራት ገንዘብ ዋጋ በገበያ እንዲወሰን መደረጉ ያለው ኢኮኖሚያዊ አንድምታ" በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ባለው ዓለምአቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ የተለያዩ ሪፎርሞች እያካሄደች መሆኑን የጠቆሙት አቶ አቤ ሳኖ የውጭ ሀገራት ገንዘብ የምንዛሬ ዋጋ በገበያ እንዲወሰን እና በሥርዓት እንዲመራ መደረጉ ትልቁና ወሳኝ ሪፎርም መሆኑን አንስተዋል።
የውጭ ሀገራት ገንዘብ እጥረትን ለመቅረፍ ተጨማሪ ገንዘብ ማተም የገበያውን እንቅስቃሴ የሚያዛባ እንደሆነ የገለፁት አቶ አቤ የገንዘብ አጠቃቀም በህግና በሥርዓት እንዲመራ መደረጉ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ዋጋ ተለዋዋጭ እንዳይሆን እና ገበያውን ለማረጋጋት አግዟል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የውጭ ገንዘብ ክምችትን በማጠናከር የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳይፈጠር በማድረግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ብለዋል።
ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨትመንትን በማሳደግና ተለዋዋጭ የገበያ ሁኔታን በማረጋጋት ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ተወዳዳሪነቷ እንዲጨምር፤ የሀገር ውስጥ ምርትና ምርታማነትም እንዲያድግ የሚያግዝ ሪፎርም እንደሆነም አቶ አቤ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ምንዛሬ ተመን በቀዳሚነት በማስጀመር የላቀ ድርሻ ተጫውቷል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በበኩላቸው ሪፎርሙ የሀገር ውስጥ ገንዘብ ክምችት እጥረት በመቅረፍ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በላቀ ደረጃ የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ፍቃዱ ፀጋ በበኩላቸው ረፎርሙ በተለዋዋጭ ገበያ ምክንያት የማይዋዥቅ የተረጋጋ ገበያ የሚፈጥር በመሆኑ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚችል አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ የፋይናንስ ሚኒስቴር፣ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማህበር፣ የተለያዩ ኤምባሲዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በፖናሊስትነትና ጥናታዊ ፅሑፍ አቅራቢነት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
#commercialbankofethiopia #cbe #floating #Ethiopia #ExchangeRate