Ramadan ረመዳን @remadan1444 Channel on Telegram

Ramadan ረመዳን

@remadan1444


ኢማናችን ጠብቀን ከመጥፎ ነገር በመራቅ መልካም ስራ ሰርተን ከሲኦል ድነን ጀነትን ኢንዲወርሱ ማገዝ ነው

Ramadan ረመዳን (Amharic)

ረመዳን በውስጣም ፈጣሪ ገጽ ነው እና በውስጣም አገልግሎቱ ውስጥ ተቋማትንና ፍላጎትን ለመቀበል የሲኦል ድነን ጀነትን ኢንዲወርሶችን ለመጠቀም የሚጠቀሙ ሴቶች እና የወጣላቸውን አሰፋላቸው በነገራችን መስራት እንደሚችሉ፣ ከፍተኛ እና ትንሽ ኢኮኖሚኛ ምክንያት ሲሆን ዘንድ ተግባር ንጹህ ይደረጋል። ረመዳን መሆኑ በውጭ ታሪካዊ እና ታሪኩን ለማስተናገድ መስራት አለበት። አቅርቦን ገንዘብ በሚጠብቁት አስፈላጊ መጠባበቂያችን እና ከአንድ ነገር በላይ በማያካት፣ ረመዳን ከሚስማማው ልዩ ሊቀመን የተማረ ሆኖ ለመገናኘት መስራት አለብን።

Ramadan ረመዳን

12 Feb, 18:21


አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) “አላህ እኔን የላከበት መመሪያና ዕውቀት ወደ መሬት በወረደ ዝናብ ሊመሰል ይችላል።
1⃣ከፊሉ የመሬት ክፍል ጥሩ ባህሪ አለው። ውሃን በጥሩ መልኩ በማስተናገድ ለግጦሽ የሚሆኑ ሳሮችንና ሌሎች በርካታ የዕፅዋት ዓይነቶችን ያበቅላል።
2⃣ሌላው የመሬት ዓይነት ዕፅዋት የማያበቅል መሬት ዓይነት ነው። ውሃን ቋጥሮ ይይዛል። አላህ በርሱ ሰዎችን ይጠቅማል። ሰዎች ይጠጡታል፤  ያጠጡበታል። ለእርሻ ግልጋሎትም ያውሉታል።
3⃣ዝናቡ ሌላ የመሬት ዓይነትን ያገኛል። ዝርግ የሆነን መሬት። ውሃን መቋጠር አይችልም። ዕፅዋትን አያበቅልም። (የመጀመሪያው የመሬት ዓይነት) የአላህን ዲን የተረዳ፥ አላህ እኔን የላከበት መመሪያና በዕውቀት ተጠቃሚ የሆነና ለራሱ አውቆ ሰዎችንም ያሳወቀ ሰው ምሳሌ ሲሆን፥ (የሁለተኛውና የሦስተኛው መሬቶች ዓይነት ምሳሌዎች ደግሞ) በአላህ ዲን ቅንጣት ተጠቃሚ ያልሆነና የተላኩበትን የአላህ መመሪያ ያልተቀበለው ወገን ምሳሌዎች ናቸው።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

«በምስክርነት ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ማነው» በላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «አላህ ነው፡፡ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው፡፡ ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስጠነቅቅበት ወደኔ ተወረደ፡፡ ከአላህ ጋር ሌሎች #አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላችሁን» በላቸው፡፡ «እኔ አልመሰክርም» በላቸው፡፡ «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔም #ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡  (  አንዓም 6:19)

Ramadan ረመዳን

11 Feb, 18:36


የረመዳን ወር መፆም አላህ ግዴታ አድርጎታል ከአምሰቱ አርካኑል ኢስላምም አንዱ ነዉ:: ፆም ማለት ከሚበላ
ከሚጠጣ፣ ከሚጨስ፣ ግንኝነት ከማድረግ እና ጾም ከሚያፈርሱ ነገሮች ከንጋት እስከ ፀሃይ መጥለቅ ድረስ
ለአላህ(ሱወ) ሲሉ መታቀብ ማለት ነው፡፡

እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት  በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ  ተጻፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡2፡183

ረመዷንን በተሳካ መልኩ ለማጠናቀቅን
ቀድመን ስለ ረመዷን ያለንን ግንዛቤ ማስፋት የግድ ነው። ረመዷናችንን ትርፋማ ሆነን እንድንጨርስ ከሚያደርጉ ነገራት መሀከል በዋነኝነት የሚጠቀሱ ነጥቦችን

1⃣ኒያ (በቁርጠኝነት  ማቀድ)፦ ኒያ
ማለት በውስጣችን አንድን ነገር ለመፈፀም የምናደርገው ቁርጠኛ
እሳቤ ወይም ውሳኔ ነው። ዲናችን ለዚህ ለኒያ እጅግ የላቀ ቦታን ሰጥቷል። ለዛም ነው የላቀው አላህ በላቀው መፅሀፉ ለአላህ ብሎ በአላህ መንገድ ላይ ተነስቶ ከቤቱ ወጥቶ ነገር ግን ግቡን ሳይመታ ሞት የቀደመውን ሰው አስመልክቶ{በርግጥም በአላህ ላይ የሱን ምንዳ መፃፍ ሆነ} ብሎ ገልፆታል። እንዲሁም የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) "ስራዎች በሙሉ በኒያ ናቸው" (ቡኻሪና ሙስሊም) ብለው አስምረውናል። ስለዚህም በረመዷን ያሰብነውን ያክል ስራ ለመስራት አቅም ብናጣ እንኳን በኒያችን እንድናገኘው ዘንዳ ኒያ ላይ ትልቅ ትኩረት ልናደርግ ይገባናል።

Ramadan ረመዳን

10 Feb, 18:13


ሙሳ (ዐሰ) ተውራትን ሙሉ በሙሉ ካነበበ በኋላ አላህን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡-
‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ በመጨረሻ የሚመጡ ሲሆኑ ግና ከሁሉም ህዝቦች #ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እባክህ የኔ ህዝቦች አድርጋቸው፡፡››
አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ #የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ህግጋቶቻቸውን በልቦቻቻው ሸምድደው ያነበንቡታል፡፡ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››
አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ #የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ ምርኮን ፈቅደህላቸዋል፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድርጋቸው፡፡››
አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ #የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ምጽዋትን ይለጋገሳሉ በሱም ትመነዳቸዋለህ፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድረጋቸው፡፡››
አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ #የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ጽድቅን ለመስራት አስበው ባይሳካለቸው አንድ ምንዳ ትመዘግብላቸዋለህ፡፡ ከተሳካላቸውም በ10 ታባዛላቸዋለህ፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድርጋቸው፡፡››
አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ #የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡- ‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ ለማመጽ ሲያስቡ ምንም አትመዘግብባቸውም፡፡ ግና ሲያምጹ አንዲትን ብቻ ትመዘግብባቸዋለህ፤ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››
አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ #የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ የቀደምትን እና የመጺኣንን ትውልዶች ዕውቀት በሙሉ አሸክመኃቸዋል፤ መሲሁ ደጃልንም ይገድሉታል፡፡ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››
አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ #የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም አለ፡-‹‹ በል እንግድያ እኔንም #የሙሐመድ ህዝብ አድርገኛ፡፡››

ሙሳም ንግግሩን ቀጠለ፡-‹‹ ቆይ ግን ጌታዬ ከኔ ህዝብ እሚልቅ ህዝብ አለን››

አላህም አለ፡-‹‹ሙሳ ሆይ #በሙሀመድ ህዝቦች እና በሌላው ህዝብ መካል ያለው ልዩነት በኔ እና በፍጥረቴ መከካል እንዳለው ልዩነት እንደሆነ አታውቅምን፡?>>
ሙሳም አለ፡-‹‹እንደው ይኸን የጉድ ህዝብ እንኳን አንዴ #አሳየኝ››
አላህም አለ፡-‹‹ልታያቸው አይቻልህም፤ ግና #ድምጻቸውን ላሰማህ፡፡››
ከፍጥረት አድማስ ወድያ ከሩሆች ስብስብ ከመናፍስት አለም ያሉ የሙሀመድ ህዝቦችን አላሀ ተጣራ፡፡
ህዝቦችም በአንድ ድምጽ፡-‹‹#ለበይከላሁማ ለበይክ›› ይሉ ጀመር።
አላህም አለ፡-‹‹በረከቴ በእናንተ ላይ ይስፈን ፤ እዝነቴ እናንተ ላይ ቁጣዬን ቀደመ ፤ ማርታዬ ስለናንተ ቅጣቴን ቀደመው፡፡
እናንተ ሳትጠይቁኝ አኔ እሰጣችኋለሁ ፤ ከእናንተ ውስጥ የኔን ጌትነት አምኖ በሙሀመድ መለዕክተኝነትም ያመነ መላ ሀጽያቶቹን እሽርለታለሁ፡፡››

Ramadan ረመዳን

10 Feb, 18:08


አላህ ለሰው ልጆች ቁርአን በማውረድ ነብይን በመላክ እስልምና ሀይማኖት ሰጠ በውስጡም በርካታ ስራዎች በማድረግ በቀላሉ ትልልቅ ምንዳ በማግኘት የመጭውን አለም ቤታችን እንድንገነባበት አመቻቸልን እኛ እንደሚገባው ባንጠቀመውም;  ከነዚህ ፀጋዎች እንዱና ዋነኛው የሆነው የረመዳን ወር በቅርቡ ይጀምራል

በዚህ በረመዷን በጣም በርካታ ወደ ጀሀነም እየተጓዙ የነበሩ ሰዎችን
አላህ ከእሳት ነፃ ይላቸዋል። ለሌሎችም በጣም ብዙ የሆኑ ሽልማቶችን
የያዘ ወር ነውና እያአንዳንዱ ሙስሊም ይህን የላቀ ወር በአግባቡ በመጠቀም  ወጀላችንን ለማስማርና  በርከት ያለ ስንቅ  ለእውነተኛ  ቤታችን ለመጫን በእውቀት
ልናገኘው ይገባል!! ስለዚህ ወሩ እስኪገባ ባሉት ጥቂት ቀናት ስለፃም የምንተዋወስ ይሆናል ኢንሻ አላህ

Ramadan ረመዳን

09 Feb, 18:40


የሞት መለይካ እዝራኤል እንዲህ አለ 

በምድር ላይ በምስራቅም ይሁን በምእራፍ አንድም ቤት ሳይቀር በቀን አምስት ጊዜ  ነዋሪዎቹን አጎበኛቸዋለሁ.  ነብዩ(ሰዐወ) ይህን እንደሰሙ እንዲህ አሉ እነዚህ  ወቅቶች አምስቱ የሰላት ወቅቶች ናቸው , ነዋሪዎቹም በነዚህ ወቅቶች ሰላታቸውን የሚጠብቁ ከሆነ የሞት መለይካም ሰዎቹ በሚሞቱበት ወቅት  ሸሀዳ ይልላቸዋል ሰይጣንም በዚህ ወቅት የሰውን እምነት ለመስረቅ ስለሚጥር  ከአጠገባቸውም ያባርርላቸዋል.

Ramadan ረመዳን

08 Feb, 18:21


በሰላት መሰላቸት

አንድ ሰው ሸሀዳ ሲይዝ ጀነት ውስጥ በጣም ሰፊ #ቦታ (ግዛት)  ይመራል  ይህ ቦታ  በርካታ  ነገሮች ሊኖረው ይገባል ይህ የሚሟላው በመልካም ስራ ልክ  ነው ስለዚህ  በርካታ መልካም ስራ ልንልክ ይጠበቃል አለበለዛ ምድረበዳ ይሆናል

ለዱንያ ስራ በየቀኑ ለብዙ ሰአት #እንለፋለን በቀን ቢያንስ ሶስት ጊዜ እንበላለን አይሰለቸንም ግን በሰላት እሰለቻለን, የምናገኘውን ምንዳ ብናቅ ኖሮ  እንኳን ፈርዱ ሱናው አይቀረንም ነበር ስለዚህ ምንዳውን እያሰብን እንበርታ

#ሰላት በትርፍ ጊዜ ወይም አንዳንድ ጊዜ የሚፈፀም ሳይሆን በወቅቱ በመደበኛነት መደረግ ያለበት ኢባዳ ነው ምክንያቱም  የቀልብ ምግብ ናት ኢማናችን እንዳይሞት ትከላከላለች.        

ነብዩ (ሰአወ  )     

     إِنَّ أَوَّلَ مَا يُحَاسَبُ بِهِ الْعَبْدُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ مِنْ عَمَلِهِ صَلاَتُهُ فَإِنْ صَلُحَتْ فَقَدْ أَفْلَحَ وَأَنْجَحَ وَإِنْ فَسَدَتْ فَقَدْ خَابَ وَخَسِرَ 

አንድ አማኝ  የፍርዱ  ቀን መጀመሪያ  የሚተሳሰበው  ሰላቱን ነው.  ሰላቱ ከተሟለች  ውጤታማ ይሆናል (ነጃ ይወጣል)  ከተበላሸች ግን ይከስራል. ቲርሚዚይ

Ramadan ረመዳን

07 Feb, 18:30


ሰውና  የተሰጠው ጊዜ

ሐሰነል  በስሪ   "የእያንዳንዱ #ዕለት ጎህ ከበስተምስራቅ ብቅ ባለ ቁጥር የአደም ልጅ ሆይ #እኔ አዲስ ፍጥረት ነኘ ስለስራህም መስካሪ ነኘ ሳላመልጥህ ተሰነቅብኘ #እኔ አንዴ ካመለጥኩህ እስከ ዕለት ትንሳኤ ድረስ አልመለስም ይላል" ብለዋል 

በሌላ ንግግራቸውም  

" የአደም ልጅ ሆይ አንተ #የቀናት ስብስብ እንጂ ሌላ አይደለህም  አንድ #መአልት በሄደ ቁጥር  ራስህ መጎደልህን ዕወቅ"  ብለዋል

ኢብን መስዑድ (ረዐ) " #እድሜዬ እየቀነሰ ስራይ ሳይጨመርበት ነግቶ እንደሚመሽ #ቀን የሚፀፅተኘ ነገር የለም"  በማለት #የጊዜን ዋጋ ገልፀውታል


ማንኛይቱም ነፍስ የሞት #ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ 63:11

በቀን የተሰጠን ጊዜ በዚህ መልኩ ብናውለው ይመከራል  8 ሰአቱን በተለምዶ የዱንያ ስራ ለሚባለው , 4 ሰአቱን ለቤተሰብ (ለልጆች ለትዳር አጋር  መመደብ.....), 4 ሰአት ለኢባዳ መመደብ, 8 ሰአት ለእንቅልፍ መመድብ

Ramadan ረመዳን

06 Feb, 18:05


መልካም ጎደኛ

ኢማሙ አል ሻፊዒ እንዲህ አሉ
የጀነት ሰዎች ጀነት በገቡ ጊዜ በዱንያ ላይ በመልካም ነገር ላይ የነበሩ #ጎደኞቻቸውን ጀነት ውስጥ ሲያጧቸው አሏህን እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ

" ጌታችን ሆይ ከኛ ጋር ሲሰግዱ እና ሲፆሙ የነበሩ #ጎደኞች ነበሩ ጀነት ላይ አጣናቸው " ብለው ይጠይቃሉ ፡ አሏህም እንዲህ ይላቸዋል ፡ ወደ እሳት ሂዱና ከቀልቡ የዘር ፍሬ የምታክል ኢማን ያለውን ሰው አውጡ ይላቸዋል ,

ሀሰን አል በስሪ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ

💟ሙእሚን የሆኑ #ጎደኞችን አብዙ የቂያም ቀን አሏህ በፈቃዱ መሸምገልን ይሰጣቸዋል              
                                                            ኢብኑ አል ጀውዚ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ ፡

💙በጀነት ውስጥ በመካከላችሁ ካጣችሁኝ , ስለኔ ጠይቁ ፡ ጌታችን ሆይ ያ ባሪያ በዱንያ ላይ ስላንተ ያስታውሰን ነበር የት አለ በሉ ከዛም አለቀሱ።

💙#ወዳጆቼ በጀነት ውስጥ ካጣችሁኝ ስለኔ ጠይቁ ምናልባትም በአሏህ መንገድ ላይ አንድ ጊዜም ቢሆን ስለሱ ታላቅነት ፣ ፈጣሪነት አስታውሻችሃለሁና።                                   ያጀመአ እኔንም ከዚህ ቻናል ከጠፋሁ  ወይም ጀነት ውስጥ ካጣችሁኘ አስታውሱኘ

Ramadan ረመዳን

05 Feb, 18:21


ሀዲሶች

🔻ምቀኝነትን ተጠንቀቁ🔥 እሳት እንጨትንእንደሚበላው ሁሉ ምቀኝነት ከይር መልከም ነገርን ይበላል🔥

🔻 ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? በማለት ነብዩ ሰ ዐ ወ ጠየቁ ሰሀቦችም አላህና መልእክተኛው ያውቃሉ አሉ (ወንድምህ በሚጠላው ነገር
ማንሳት ነው አሏቸው) የምናነሳበት ነገር ያለበትስ ቢሆን ሲሏቸው የምትለው ነገር ካለበት አማሀው ከሌለበተ ደግሞ ቡህታን ጫንክበት  ይባላል

🔻 አማኝ የሆነ ሰው ወንድሙን ከሶስት ቀን በላይ ማኩረፍ አይፈቀድም አማኝ ወንድሙን አመት ሙሉ ያኮረፈ ሰው ደሙን እንዳፈሰሰ ነው

🔻 ዝምድናን የሚቆርጥ ሰው ጀነት አይገባም

Ramadan ረመዳን

04 Feb, 17:43


የሙስሊሞች መሪ  የነበረው ዑመር  ኢብኑል ከጣብ(ረዐ) በሒምስ የሚኖሩ ድሆችን ለመደጎም ፈልጎ የድሆችን ስም ዝርዝር መዝግበው እንዲያመጡለት ባዘዘው መሰረት ተመዝግቦ ተሰጠው።

የስም ዝርዝሮችን ሲመለከት ከመሀል የሒምስን ግዛት የሚያስተዳድረው #መሪ ሰዒድ ኢብኑ ዓሚር ስም ተፅፎ አገኘ።

ዑመር ትክዝ አለ...፤ ወደ ሰዎቹም ዞር ብሎ፦ «የአንድ ትልቅ ግዛት #አስተዳዳሪ ሁኖ እንዴት ከድሆች ተርታ ተሰለፈ?»

«ሙሉ ደመወዙን ለድሆች ያከፋፍልና " ታድያ ምን ላድርግ አላህ ፊት ስለነሱ ስጠየቅ መልስ የለኝም" ይላል። » በማለት ሁኔታውን ለዑመር አስረዱት።

«እሱ ላይ የምታቀርቡት ስሞታ አለ?» በማለት ጠየቃቸው።

ሰዎቹም፦ «ሶስት ስሞታዎችን ብቻ እናቀርባለን።
1፦ረፋድ ላይ ነው ከቤቱ ሚወጣው
2፦በማታም ጭራሽ ይሰወርብናል
3፦በሳምንት አንድ ሙሉ ቀን ይሰወርብናል»

ዑመር የሒምሱን #አስታዳዳሪ ጠየቀው፦ «የቀረበብህ ስሞታ ትክክል ነው?»

አስተዳዳሪ፦ «ትክክል ነው ያ አሚረል ሙእሚኒን⁉️
1፦ረፋድ ላይ ነው ከቤቱ ሚወጣው' ላሉት እኔ ከቤት አርፍጄ የምወጣው ሚስቴ በሽተኛ ናት፤ አገልጋይ ስለሌለኝ ስራ ስሰራ ነው ማረፍደው።

2፦በማታም ጭራሽ ይሰወርብናል' ላሉትም እኔ ቀኑን ህዝብ ሳገለግል እውላለሁ፤ ማታውን ግን ጌታዬን አመልክበታለሁ።

3፦በሳምንት አንድ ሙሉ ቀን ይሰወርብናል' ላሉትም እኔ አንዲት ልብስ ብቻ ናት ያለችኝ፤ እሷን በሳምንት አንድ ቀን አጥባት'ና እስክትደርቅ ምለብሰው ስለሌለኝ ቤቴ ቁጭ እላለሁ።»

ዑመር ይህን ሲሰማ ፂሙ በእንባው መርጠብ ጀመረ.

ይህ #መሪ ከነብዩ (ሰዐወ) መድረሳ የወጣ ምሩቅ ነው።

Ramadan ረመዳን

03 Feb, 18:04


እንዲህ ነበር መተሳሰባችን

አቡ ጀህም ቢን ሁዘይፋ  የተባለ ሱሀባ (ረዐ)  እንዳስተላለፈው

በየምሩክ ጦርነት ወቅት የአጎቴን ልጅ ልፈልገው  ወጣሁ  እሱም በውጊያው የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ነበር  ትንሽ ውሀም ይዤለት ነበር በጦርነት ፊልሚ ማሀል ተመቶ ደክሞ አገኘሁት  ወደሱ ጠጋ ብይ ዉሀውን ልሰጠው ስል ከጎኑ  ሌላ የተጎዳ ባልደረባ በሀይለኛው ቆስሎ  ሲያቃስት ሰማሁ  የአጎቴም ልጅ  ፊቱን አዞረና  ውሀውን  መጀመሪያ   ለባልደረባው እንድወስድለት ነገረኘ  ወደ ባልደረባው ስሄድ ሂሻም ቢን አቢል የሚባል ሱሀባ ሆኖ አገኘሁት  እሱም ጋር ልክ እንደደረስኩ  ሌላ ሰው ብዙም ሳይርቅ  ተመቶ   በሀይለኛው እያጣጣረ  ድምፁ ተሰማኘ  ሂሻምም  ውሀውን ወደሱ እንድወስድለት አመላከተኘ ውሀውንም  ልሰጠው ወደሱ ጠጋ ስል  ነብሱ ወጣች ከዛም ዉሀውን ይዤ ወደ ሂሻም በፍጥነት ስመለስ  እሱንም ሞቶ አገኘሁዋት   ከዛም ወደ አጎቴ ልጅ  በምችለው  ልክ ፈጥኘ ስሄድ  እሱም እነሱን  ተከትሎ  ወደ አኼራ ሄዶል.

እኛ ግን እንትን ያልኳት እንትና ሊወስድብኘ
አንዱ የአንዱን ስራ ወይም ንግድ  ለማበላሸት  የምናደርገው ሴራ ምቀኘነት  አይገርምም  ከዚህ የከፋው ደሞ የሆነ  ቢድአ ካልተገበርን የሙስሊሙን ንብረት ለግል ጥቅማችን ካላዋል ብለን ኡማውን መስጊድ ውስጥ ሳይቀር የምንበጠብጥና ጥቃት የምናደርስ    ለንከለከል ይገባል


ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! 4:115

وَٱلْمُؤْمِنُونَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍۚ يَأْمُرُونَ بِٱلْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَيُطِيعُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ أُو۟لَٰٓئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ ٱللَّهُۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ 9:71

Ramadan ረመዳን

02 Feb, 16:21


አንድ አንድ ሰዎች አሉ። ኖሮ ለማለፍ ብቻ ያልመጡ።  የብዙሃንን ስቃይ ብቻቸውን የሚሸከሙ...በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሞትን የሚንቁ..በጠብመንጃ አፈሙዝ ፊት የሕዝባቸውን እውነት የሚናገሩ..በጋለ ብረት ተቀጥቅጦ የማይቀልጡ...ስለ አንዲት ነፍሳቸው ረስቶ ስለ ሕዝባቸው እጣፈንታ የሚጨነቁ...

ደግሞ ወንድ ልጅ እንዲያ ነው። ለቤተሰቡ ይቆማል። ለክብሩ ይዋደቃል። ለሀገሩ ይሞታል። ለአፈሩ አፈር ይለብሳል።

መቼስ የፍልሥጤማውያን መከራ ማብቂያ ያለው አይመስልም። አሁን ዓለም ላይ ብዙ ዓመታትን በእስር ቤት የቆየ የፖለቲካ እስረኛ ፍልስጤሞቹ << የኛ ማንዴላ >> የሚሉት ናኤል ባርጉቲ ነው። በእስራኤል እስርቤት ከተቆለፈበት 44 ዓመታት ተቆጥረዋል። አስበው 44 ዓመታት😐

ከሰሞኑ በስምምነቱ መሰረት በርካታ የፍልስጤም የፖለቲካ እስረኞች ከአስከፊው የእስራኤል እስር ቤቶች እየፈቱ ነው።  ባርጉቲ ባይፈታም በፍልስጤማውያን  የነፃነት ተጋድሎ ውስጥ በጉልህ የሚጠቀሱ በርካታ ታጋዮች ተፈተዋል። አንዱ Mohammed al-Tous ነው። የመገናኛ ብዙሃን ከስሙ ቀጥሎ ''Dean of Palestinian prisoners'' የሚል ገለፃ ይጨምሩበታል። በ29 ዓመቱ የወጣትነት ዕድሜው ታስሮ 40 ዓመታትን በእስር ቤት አሳልፎ...በእስር ቤቱ አርጅቶ በ69 ዓመቱ ባለፈው ቅዳሜ ተፈቷል። 40! ዓመታት...ስንት ነገር ተፈጥሯል..? ስንቱ መጥቶ ሄደዋል...? እሱ ሲታሰር ጨቅላ ህፃን የነበረው ልጁ የአርባ ዓመት ጎልማሳ ሆኖዋል።

አሳዛኙ ነገር ተፈቶም ነፃ አለመሆኑ ነው።እስትንፋሱ ከሆነው ሕዝቡ ጋር... በነፃነት በምወዳት ቀዬው...ዋጋ በከፈለላት ምድር እንዲኖር አልተፈቀደለትም። 
ጋዛን፣ ካኻን የኑስን፣ ጀኒንን፣ ራማላህን፣ ራፋን፣ ቤተልሔምን....እንዳያይ ተደርጎ ከእስራኤል ግብፅ ተወስዶ በዛው አልጀሪያ፣ ቱኒዚያ ወይንም ወደ ቱርክ ሂድ የሚል የማይመረጥ ምርጫ ሰጡት።

ብቻ ለመከራ ዘመን የሕዝብን መከራ ብቻቸውን ለመሸከም የተፈጠሩ ሰዎች አሉ። የሸክሙ ብዛት አያጎብጣቸውም። የጭካኔው አስከፊነት ተስፋ አያስቆርጣቸውም። የመከራው ርዝመት አያዝላቸውም። ይልቁንም ድቅድቅ ጭለማ ውስጥ የብርሃን ጭላንጭል ያያሉ። ፅናታቸው ከአለት ይጠነክራል። ፈገግታቻው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለመጭውም ትውልድ ስንቅ ይለግሳል።

የሚደንቅ የነፍስ ፅናት..! ©

Ramadan ረመዳን

01 Feb, 18:20


ሰው ቁርአን ሀፍዞ ሊወዳደር ይመጣል እኛ ከባለፈው ረመዳን ቡሀላ አንድ ጊዜ እንኳን ቀርተን ጨርሰናል ወይስ የአመቱን ጊዜ ብቻ ነው የጨረስነው

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ አለም አቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ በነገው እለት በአድስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል።

የቅድመ ዝግጅት ፕሮግራሙም የተጠናቀቀ መሆኑን አዘጋጅ ኮሚቴው አሳውቋል።

የውድድሩ ፕሮግራም  ላይ የፌደራል እና የክልል መጅሊስ አመራሮች፣ ታላላቅ አሊሞች፣ ዱዓቶች፣ ከውጪ የመጡ ዳኞች እና ተወዳዳሪዎች እንግዶች ይካፈላሉ።

በዚህ ታላቅ አለም አቀፍ የቁርአን ውድድር ከ60 በላይ ሀገራት ተወካዮች የሚሳተፉ ሲሆን ከውድድሩም ባሻገር ስለሀገራችን ለእስልምና እድገት እና አስተዋፅዖ የተበረከቱ አሻራዎችን ከመድናዋ ውጭ በመንቀሳቀስም እንደሚጎበኙም ይታወቃል።

ይህ ደግሞ እንደ ሀገር - እንደ ኡማ ለምናሳያቸው እንግዳ ተቀባይነት አምባሳደር ሆነው በየሀገራቸው ሲሄዱ አምባሳደር እንደሚሆኑ አልጠራጠርም።

የመግቢያውን ካርድ በቴሌብር  ማግኘት ይችላሉ።

ይህ ታሪካዊ ውድድር እንዳያመልጠን

ሸር እናድርገው

አድስ አበባ ስታድየም በአዛን እና በቁርዓን ድምፆች ይደምቃል።

Ramadan ረመዳን

31 Jan, 18:24


የሸዕባን #ጨረቃ ምሽቱን ብቅ ብላ ረመዷን  አንድ ወር  እንደቀረው  አሳስባለች

በግለሰብ ደረጃም ይሁን በድርጅት ለዝች #አለም አጭር ህይወት ውጤታማ ለመሆን ሰዎች ስትራቴጂ ነድፈው እቅድ አውጥተው ይተገብራሉ ውጤታቸውንም በየወሩ በየአመቱ እየገመገሙ እሄን ያክል አተረፍን ወይም  #ውጤት አመጣን እያሉ በየጊዜው ሪፓርት ያወጣሉ , #ድክመታቸውንም ለመቅረፍ ጠንክረው ይሰራሉ - ሲቀር ለሚቀረው

መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ  ለሌለው አገርም ስዎች ከዚህ በተሻለ መልኩ ስራችን #ልንተሳሰብ ይገባል

የሰው ልጅ ስራ #በሳምንት ሁለት ጊዜ ሰኞና ሀሙስ ረፓርት ይቀርባል እንዲሁም የአመት የስራችን #ሪፓርት  አላህ ዘንድ በዚህ  ባለንበት ሸአባን ወር በየአመቱ ይቀርባል.

ባለፈው  ከረመዳን በኋላ እንፈፅማቸዋለን ብለን ያሰብናቸው መልካም ስራዎች ምን ያህሉ እንደተሳካልን እንመልከት እስቲ

🚫ከሃራም ነገር ለመቆጠብ አስበን ምን ያህል ተሳክቶልናል

🕌የፈርድ ስላት አፈፃፃማችን ምን ይመስላል

📗በተደጋጋሚ ቁርአን #ለማክተም አስበን ምን ያህል ተሳክቶልናል

#ቁርአንም ያልቀራን ለመማር አስበን ምን ያክል ፈፀምን

🌑 #ፈርድ ነገሮችን ሳንቸገር የምንከው  በሱና  ላይ ምን ያህል ተሳክቶልና

በአጠቃላይ ከባለፈው ረመዳን በኋላ ያለው  የአመት አፈፃፀማችን መገምገም ብልህነት  ነው.

Ramadan ረመዳን

30 Jan, 18:09


ጁምአ

ነብዩ  ﷺ  እንዲህ አሉ

ፀሀይ ከምትወጣበት ቀን ሁሉ ምርጡ  የጁምአ ቀን ነው. አደም የተፈጠረበት, ጀነትም የገባበት ከሷም የወጣበት ቀን ነው. #ሰአቷም(የፍርዱ ቀን) አትቆምም በጁምአ ቀን ቢሆን እንጂ.  ቲርሚዚይ 488 🤍

አብሁረይራ(ረዐ) እንዳስተላለፉት
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

አላህ  አደምን ከፈጠረው ቡሃላ  ጀርባውን በማበስ እስከቂያማ ድረስ የሚፈጠሩትን ዝርያዎችን ከጀርባው አወጣ በየአንዳዱም ስው አይን የሚያበራ ብርሃን አደረገበት.

ከዛም ለአደም አሳየው እሱም  እነዚህ እነማን ናቸው አለ ?
አላህም  እነዚህ ዝርያዎችህ ናቸው አለው
አደምም ሲመለከት ከአደኛው አይን  የሚወጣው ብርሃን አስደንቆት ጌታይ ሆይ ይህ  ማነው አለ?
አላህም አለው ይህ ከዝርዩችህ  ከኀለኞቹ ትውልዶች የሚመጣ ዳውድ የሚባለው  ነው
አሱም ጌታይ ሆይ  እድሜው ስንት አደረከው አለ?
ስልሳ አመት አለው
አሱም ከኔ እድሜ ላይ አርባ አመት ጨምርለት አለው

በአደም ምድራዊ ህይወቱ መጩረሻ ላይ የሞት መልአክ ሲመጣበት አደም አለ አርባ አመት ይቀረኘ የለ እንዴ አለው
እሱም ለዝርያህ ዳውድ ሰተህው የለ እንዴ አለው

አደምም አልሰጠሁም አለ  አደምም ካደ  ዝርያዎችም ይክዳሉ አደምም ረሳ ዝርያዎችም ይረሳሉ አደምም ይሳሳታል ዝርያዎቹም ይሳሳታሉ. (ሶሂህ ቲርሚዚ).

Ramadan ረመዳን

29 Jan, 18:01


በቁርአን ውስጥ
👌ተስፋ  8 ጊዜ ሲጠቀስ ስጋት 8 ጊዜ ተጠቅሷል
🖌መልካም ስራ 167 ጊዜ መጥፎ ስራ 167 ጊዜ ተጠቅስዋል
👉ጥቅም 50 ጊዜ  ጉዳት 50 ጊዜ ተጠቅሰዋል

በአለም ላይ ከ600 ገፅ በላይ  ሆኖ በሚሊዮኖች የሚተሃፈዝ (ቃል በቃል የሚሸመደድ) ብቸኛ መፀሃፍ ነው ይህም ተአምር ከአለማቱ  ጌታ ስለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ነው.

أَوَلَمْ يَكْفِهِمْ أَنَّآ أَنزَلْنَا عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَرَحْمَةً وَذِكْرَىٰ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

እኛ መጽሐፉን በእነሱ ላይ የሚነበብ ኾኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን (ከተአምራት) አይበቃቸውምን በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታና ግሳጼ አለበት.  29:51

በትምህርትም ሆነ በሌላ ምክንያት በርካታ መፀሀፍትን አንብበናል ታዳ ከፈጣሪ የተላከልልን አንድ መፀሀፍ ማንበብ እንዴት ያቅተናል ስለዚህ ሙስሊም ላልሆኑት ጭምር ለምን እንዲያነቡት አንጋብዝም

Ramadan ረመዳን

28 Jan, 18:24


"ህዝቦች እንዲያምኑበት  ተአምር  ያልተሰጠው ነብይ የለም. ለኔ የተሰጠኝ ተአምር የአላህ ወህይ ቁርአን ነው. ለዚህም ነው በቂያማ ቀን ብዙ ተከታይን ያለው ነብይ እሆናለሁ ብይ  እማስበው". (አህመድ)

📘የተለያየ ተአምራቶችን በወቅቱ ለነበሩ ህዝቦች ቢያሳዩም የተላኩበት ህዝብ በሳይንስና በስነፅሁፍ እውቀት ስለሚኖረን ለዚሁ የሚመጥን በርከት ያሉ ሳይንሳዊ ጥቅሶችን የያዘ በስነፅሁፉም የመጠቀ ተአምርነቱ የማያልቅ ለስውዘር በሙሉ ለምን እንደተፈጠሩ ፍፃሚያቸው ምን እንደሚሆን የሚገልፅላቸው መፀሃፍ(ቁርአን ) ከአለማቱ ጌታ ተሰቷቸዋል መፅሃፉን ያነበበ ሁሉ ይህን በቀላሉ መረዳት ይችላል.
🖌📝የቋንቋው ስነፅሁፉም የመጠቀ ሲሆን የቃለት አጠቃቀሙም የሚአጅብ ነው

የተወሰኑትን ብንመለከት

📜ህይወት የሚለው ቃል 145 ጊዜ ሲጠቀስ ሞት የሚለውም 145 ጊዜ ተጠቅሷል
📋ይች አለም 115 ጊዜ ሲጠቀስ ቀጣዩ አለምም 115 ጊዜ ተጠቅሷል
📖መለአክት የሚለው ቃል 88 ጊዜ ሲጠቀስ ሰይጣን የሚለውም 88 ጊዜ ተጠቅሷል.
🗳ሰው ለወንድ 24 ጊዜ ሲጠቀስ ሰው ለሴት የሚለውም 24 ጊዜ ተጠቅሷል

Ramadan ረመዳን

27 Jan, 18:39


ለብዙ ሺ አመታት ሳይንሲስቶች የፍጥረት አለም እንቆቅልሽ ሆኖባቸው ዩኒቨርሱ መጀመሪያም መጨረሻም የለዉም ነበነ ነበረ ለውጥም የለውም ብለው ይገምቱ ነበር በ20 ክፍለዘመን መጀመሪያ ላይ ግን ከብዙ ልፋት ብሃላ ፍጥረት አለሙ መጀመሪያ እንዳለውና አሁንም እየሰፋ መሆኑ መረዳት ችለዋል ቁርአንም ይህን እውነታ ቴሌስኮብ ባነበረበት ዘመን እንዲህ ተጠቅሶ ይገኛል

بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُۥ وَلَدٌ وَلَمْ تَكُن لَّهُۥ صَٰحِبَةٌ ۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَىْءٍ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ

(እርሱ) ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው፡፡ ለእርሱ ሚስት የሌለችው ሲኾን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ 6:101

وَٱلسَّمَآءَ بَنَيْنَٰهَا بِأَيْي۟دٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ

ሰማይንም በኀይል ገነባናት፡፡ እኛም በእርግጥ በማስፋፋቷ ላይ  ቻዮች  ነን. 51:47

Ramadan ረመዳን

26 Jan, 18:45


🪐ፕላኔቶች  በፀሀይ ዙሪያ  የሚያደርጉት መሸከርከር አመቶችን ይቀያይራል
🌍ምድር ፀሀይን  ለመዞር 365 ቀን ይፈጅባታል ይህም እንደ እንድ አመት ይቆጠራል,
🌔ሜሪኩሪ የምትባለው ፕላኔት ወደ  88 ቀን ይፈጅባታል ይህ ማለት  ምድር ላይ 30 አመት የሆነወ ሰው ሜርኩሪ ላይ ቢኖር ኖሮ እድሜው ከ120 አመት በላይ ነበር የሚሆነው
🌕ጁፒተር የሚባለው ፕላኔት አንድ ጊዜ ፀሀይን ለመዞር  12 አመት ይፈጅበታል, ምድር ላይ 60 አመት የሆነው ሰው እዚህ ፕላኔት ላይ ቢኖር  እድሜው ገና 5 አመቱ ነው

በአላህ ዘንድ ደሞ አንድ ቀን ማለት በምድር አቆጣጠር 1000 አመት ነው ይለናል  እንደ ፕላኔቶቹ በመሽከርከር ይሁን በሌላ ምክንያት አላህ ይወቀው



وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِٱلْعَذَابِ وَلَن يُخْلِفَ ٱللَّهُ
وَعْدَهُۥۚ وَإِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ

አላህም ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን በቅጣት ያቻኩሉሃል፡፡ ጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት (ቀን) እንደ ሺሕ ዓመት ነው፡፡ 22:47

ከትላት ጀምሮ በፀሀይ ዙሪያ ያሉ ፕላኔቶች በአንድ ረድፍ ተሰልፈው  ታይተዋል ይህ አሰላለፍ  ሰሞኑንም ይቀጥላል ተብሏል  -   የቂያማ መቃረቡን እያመላከቱ ይሆናል

Ramadan ረመዳን

25 Jan, 18:08


ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

በምድር ላይ ያልተፈተኑ ሰዎች ቆዳቸው ቢቆራረጥ  ይመኙ ነበር የተፈተኑ ሰዎችን #አጅር (ምንዳ) በሚመለከቱ ጊዜ.
ሶሂህ  ጃሚ 5484

Ramadan ረመዳን

24 Jan, 18:47


ይች ሀይወት #ፈተና ናት

አንዳንዴ ይህ የምንኖርበት አለም #ፈተና መሆኑን አንረሳለን. አሁን ያለንበትን ህይወት ስናስተነትነው  ትዳራችን $ፈተና ነው. በቤታችን ያለ የማይታዝ ልጅ #ፈተና ነው. የትዳር አጋር አለማግኘት #ፈተና ነው. ትግስቶን የሚፈታተን ሰው #ፈተና መሆነቸውን አስተውለናል?

አላህ ዱአችን ከተቀበለን እምነታችን ይጨምራል

ዱአችን ከዘገይ ትግታችን ይጨምራል

ዱአችን ካልተቀበለን ደሞ የተሻለ ነገር አስቦልን ይሆናል

አላህ ሰብርን ይስጠን ፈታኘ ግዚያቶችን እንድናልፍ.

አጠቃላይ የቀን ተቀን  እንቅስቃሴችን #ፈተና መሆኑንና ይህም ትግስተኛነታችን: ኢማናችን  እንደሚጨምር . በዚህ መልኩ ህይወትን ሲረዱ ነው ይችን #የፈተና አለም የሚያልፉት

Ramadan ረመዳን

23 Jan, 18:32


      ነብዩ  ﷺ     እንዲህ  ብለዋል
«በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።»

«ለይለቱል ጁምዓ ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ (በካዕባ) መካከል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።

መቅራትም ለማንችል ማዳመጥ ይቻላል  በምንችለው  ቋንቋ ትርጉም እየተረዱ ማንበብ ይቻላል

በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከተተረጎሙት ውስጥ በሴቶች የተተረጎመው ሰሂህ ኢንተርናሸናል ምርጡ ነው ይባላል

💦በዓለማችን ታዋቂውና የተሻለ የሚባለው የእንግሊዝኛ ቁርኣን ትርጉም Sahih International ሲሆን የተዘጋጀውም በ3 ሰለምቴ አሜሪካውያን ሴቶች ነው።

💧የመጀመሪያዋ ❝ኤምሊይ አሳሚ❞ ወይም አሚናህ ዑሙ-ሙሐመድ ትባላለች። የተወለደችው ካሊፎርንያ ሲሆን ቤተሰቦቿ እምነት የለሾች ናቸው። ኢስላም ሴቶችን እንደሚጨቁን ስትሰማ ለማጣራት ቁርኣንን ማንበብ ጀመረች። ከዚያ በወቅቱ በአሜሪካ በቂ የኢስላም መጽሐፍ ስላልነበሩ ወደ ሶርያ በመሄድ ከደማስቆ ዩኒቨርስቲ ዐረቢኛን አጥንታ ክሱ ቅጥፈት መሆኑን ስታረጋግጥ ኢስላምን ተቀበለች። ከዚያም በ1981 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

💧 ሁለተኛዋ ❝ሜሪ ኬኔዲ❞ የተወለደችው በኦርላንዶ ሲሆን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምሩቅ ናት። ቤተሰቦቿ ክርስቲያኖች ናቸው። በኋላም ወንድሟ ኢስላምን ሲቀበል በእሱ ምክንያት በ1985 ኢስላምን ተቀበለች። ከዚያም በ1987 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

💧ሶስተኛዋ ❝አመቱላህ ባንትሌይ❞ ስትሆን የካቶሊክ እምነት ተከታይ የነበረችና ከሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ የቢዝነስ ማኔጅመንት ምሩቅ ናት። የሰለመችው በ1986 በዓለምአቀፍ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር አማካኝነት በ20 ዓመቷ ነው። ከዚያም በ1987 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

💎 በ1990 አካባቢ በሳዑዲ ሳሉ በአጋጣሚ ተገናኝተው ተዋወቁ። በዚያው ሰሞን ሙስጠፋ የተባለ ሰው ቁርኣንን በቀላል እንግሊዝኛ ለመተርጎም ጀምሮት እንደሞተ ሲሰሙ ስራውን ለመጨረስ ተነሱ። በዚህም ከዚያ በፊት ፍፁም አስበውት የማያውቁትን የቁርኣን ትርጉም በ1994 ጀምረው በሶስት ዓመቱ በ1997 አጠናቀቁት።

💎 በኋላም መጽሐፉ በዓለም ላይ ቀላሉና የተሻለው የእንግሊዝኛ ትርጉም ለመሆን የበቃ ሲሆን ሶስቱም በህይወት በመኖራቸው የስራቸውን ፍሬ ለማየት ታድለዋል። ዑሙ-ሙሐመድ ኤምሊይም ከዚያ በኋላ ከ80 በላይ ኢስላማዊ መጽሐፍት አዘጋጅታለች። እነዚህ እህቶችም ኢስላም በቁርኣን ጭምር የሴቶችን እውቀት የሚተማመን መሆኑን ማሳያ መሆን ችለዋል። ©

አራህማን ሀቂቃ ባሮች አሉት

Ramadan ረመዳን

22 Jan, 18:22


ታለቅ  አስተዋዕኦ  ለእስልምና ያደረጉ ሴቶች

ለእስልምና  መጠናከር መስፋፋት ከባድ አስተዋፅኦ ካደረጉ ሴቶች መካከል  በቀዳሚነት  ሁለት ሴቶቾች ይጠቀሳሉ አንደኛዋ   ሀብታም (businesswoman)  ስትሆን ሌላኛዋ  ሙሁር(scholar) ነበረች

ነብዩ (ﷺ)በተልኳቸው  መጀመሪያ አመታት  በርካት ችግሮች  ከሙሸሪኮች ያጋጠማቸው ሲሆን አናሳ ተከታዮቻቸውም ላይ በርካታ መከራ ተቀብለዋል በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ  ገንዘቧን ጊዜዋን ጉልበቷን  ለነብዩ   (ﷺ)  ሰታ የነብይነት ተልኳቸውን እንዲወጡ  ትደግፋቸውና ታበረታተቸው ነበር  ደሀ ተከታዮቻቸውም መአቀብ ተጥሎባቸው  በእጅጉ በተቸገሩበት ወቅት  ገንዘቧን ያላት ተሰሚነት ተቅማ  ትረዳቸው ነበር  በነብዩ (ﷺ)   መልክትም ያመነች እስልምናን የተቀበለች የመጀመሪያው ሰው ነበረች  እስክትሞት ድረስ ነብዩ(ﷺ)  ተልኮቸውን አንዲወጡ እስልምናም ገና በእንጭጩ እንዳይቀጭ  የቻለችዉን ሁሉ አድርጋለች በዚህም መልካም ሰራዎ ምስጉን ቦታ በጀነት ውስጥ እንደተዘጋጀላት በጅብሪል ተነግሮላታል እሷም የነብዩ  (ﷺ) የመጀመሪያ ባለቤታቸው ከዲጃ ናት

#ሁለተኛዋ  ከ2000 በላይ የነብዩ (ﷺ) ሀዲሶችን ያስተላለፈች  ከትልልቆቹ ሀዲስ አስተላላፊዎች ውስጥ የምትመደብ,ነብዩ (ﷺ) ካለፉም ብሀላ  ከ40 አመት በላይ  ልጅነቷን ሁሉ መሰዋት በማድረግ  ሳታገባ ሳትወልድ እስልምናን ያስተማረች  ያስፋፋች  ታላቅ ሴት  ነበረች እሷም የነብዩ   (ﷺ) ባለቤት የነበረችው አይሻ ቢንት አብበከር ነበረች   ድንቅ መሰዋትነት

ገና በለጋነት እድሜዋ እንድታገባ የተፈለገውም በልጅ ጭቅላቷ የነብዩን (ﷺ) የለት ተለት እንቅስቃሴ በተለይ  በቤት ውስጥ የማያከናውኑትን በመያዝ እንድታስተላልፍ ስለተፈለገ ነው አንዳዶች ይህን ባለመረዳት ነብዩ  (ﷺ) ህፃን ልጅ አግብቶ እያሉ ሊሳለቁ ይሞከራሉ

ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ መጽዋቾች ወንዶችና መጽዋቾች ሴቶችም፣ ጿሚዎች ወንዶችና ጿሚዎች ሴቶችም፣ (ካልተፈቀደ ሥራ) ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ 33:35

Ramadan ረመዳን

18 Jan, 19:10


ይገርማል። የዚህ ሕዝብ ፅናት...የዚህ ሕዝብ ልባምነት..የዚህ ሕዝብ ቆራጥነት...ለክብር የመኖር ተምሳሌት...ለክብር የመሞት ምልክት...ድንቅ የሰው ልጅ ፍጥረት...

በቦንብ ዝናብ መሐል ቆሞ የሚራመድ..ወደባህር ነድቶ እንደ ጨው ሊያሟሙት ሲሞክሩ እንደ አለት የሚጠነክር..በቦንብ አረር፣ በረሃብ በእርዛት...በሰው ሰራሽ ውሃ ጥማት ሲቀጡት እጅ የማይሰጥ..በመከራ ብዛት የማይንበረከክ..በዘር ማጥፋት አዋጅ የማይጠፋ...ሁሉን የሚቋቋም ልባም!

ደግሞም የማይታጠፍ ቃል...በእምነት የታሰረ የተስፋ ቃንጃ...ትውልዶች የምቀባበሉት አደራ... የወል ብርታት ማሰሪያ ሀረግ..

[ አንድ ቀን ሀገር ይኖረናል ]





ሀ ገ ር  ወይንም  ሞ ት . . !

የሆነ ሆኖ... የመስዕዋትታቸውን ምክንያት ለምንረዳ...የመስዕዋትታቸው ልክነት ለሚገባን...ሕመማቸው ለሚያመን...የሚሞቱለትን ሃቅ ለምናውቅ...የህፃናቱ ዋይታ ለሚያስለቅሰን...
ትንሿ ፈገግታቸው ታስደስተናለች። በእንባ ምትክ ያገኙት ጭላንጭል ብርሃን እንዲበዛላቸው እንመኛለን።

ምንም ሆነ ምን የጋዛ ሕዝብ ከጋዝ አረር፣ ከቦንብ ንዳድ፣ ከታንክ ጋጋታ፣ ከሄሊኮፕተር ጩኸት... እፎይታን የሚያገኝበት ቀን በመምጣቱ አብዝቶ ደስ ይለናል

Ramadan ረመዳን

18 Jan, 19:05


እ-ስ-ማ-ኤ-ል ሃኒያ፣ ያ-ህ-ያ  ሲ-ን-ዋ-ር፣
ሳላህ አል አሩሪ፣ ሞሐመድ ዳኢፍ፣ ማርዋን ኢሳ...ባመኑበት መንገድ የሕይወት መስዕዋትነት ከፍለዋል። የእስራኤል መንግስት በምዕራባውያን የሃሳብ እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ ላለፉት 15 ወራት በጋዛ ከባድ ጦርነት ሲያካሂድ ቆይቷል። የጦርነቱ ዓላማ ሀ-ማ-ስን ሙሉበሙሉ ማውደም እና ታጋቾችን ማስለቀቅ ነበር። ግን ዓለም ላይ አለ የተባለ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ታጥቆ በሰማይ፣ በየብስ እና በባህር ወደ ጋዛ የዘመተው የእስራኤል ጦር ከ200 ምናምን ታጋች
አስር ታጋቾችን እንኳን በሀይል እርምጃ ማስለቀቅ አልቻለም። ሃማስንስ ሙሉበሙሉ ማውደም ችሏል...? ሲጀመር ሃ-መ-ስ የሚወድም ነገር ነው..?

በርካቶች እንደሚያስቡት ሃ-ማ-ስ ድርጅት አይደለም። የጥቂት ሰዎች ስብስብም አይደለም። በአስተዳደራዊ ክንፉ ድርጅት ሊመስል ይችል ይሆናል እንጂ አይደለም። ሃ-ማ-ስ ሀሳብ ነው። ሀሳቡ ፀረ ጭቆና፣ ለቅኝ ግዛት እምቢኝ ማለት ነው። በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ጨቋኝን መፋለም ነው። ለጨቋኞች አለመመቸቸት ነው። ከጠላቶቹ ጋር ምንም ያህል የአቅም ልዩነት ቢኖር አሜን ብሎ አለመንበርከ ነው።

ምንም ትግሉ የግሪክ Mythology ውስጥ እንደሚጠቀሰው Sisyphus ግዙፉን ክብ ድንጋይ የተራራው ጫፍ ላይ ለማውጣት የሚደረግ አይነት የማይቻለውን የመሞከር መከራና ተጋድሎ ቢሆንም ሃ-ማ-ስ-ነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው።

ደግሞም ድርጅት ይከስማል። በመከራ ግዝፈት፣ በመስዕዋት ብዛት፣ በጊዜ ርዝመት፣ በሰው ድክመት፣  በቅብብሎሽ ሂደት... ይዝላል ይወድቃል፣ ይሞታል።

የሕዝብ CAUSE ግን በመከራ አይወድቅም። በመስዕዋት ብዛት አያልቅም። ይልቁንም በመከራ ይጠነክራል። በጊዜ ሂደት ይዳብራል። ለትውልድ ይሻገራል። በመስዕዋት ይፀናል።  በጭቆናው አስከፊነት ይበረታል። ልክ እነሱ እንደሚኮሩበት የወይራ ዛፋቸው ችግሮችን ተቋቁሞ ፍሬ ያፈራል።

እናም ጭቆናው ካልቆመ...የብሶት ቋጠሮው ካልተፈታ  በመከራ ብዛት ሃ-ማ-ስ አይጠፋም። በሰው መሞት አይወድቅም። በመሪ መገደል አይከስምም። የሀሳቡ ነፍስ አታርፍም። መሪዎቹ እንጂ ትልሞቹ አይሞቱም።

- ( ©ጥላዬ ያሚ)

Ramadan ረመዳን

17 Jan, 18:40


የክርሰትናው አለም ከገነት ወተን ምድር ላይ የምንኖረው አዳም በሰራው አንድ ሀጢያት ነው ወደገነትም ለመመለስ ይህ ሀጢያት መሰረዝ አለበት ብለው ያምናሉ

ይህንን ምሀጢያት ለማሰረዝ አንድ ሜትር በማትሞላ የሰው ሆድ ውስጥ ፈጣሪ ኖሮ ተወለደ ብለው ያምናሉ ለዛውም በበረት ውስጥ ከዛም ተገረዘ እየሩሳሌም ውስጥም መኖር ጀመረ ከዛም ተጠመቀ ቀጥሎ አሰቃይተን ደብድበን ሰቅለን ገደልነው  ብለው ሲናገሩ ትንሽ አይከብዳቸው

እኛ የምናመልከው አላህ እኛን ለማዳን መወለድ መውለድ መሰቀል መገደል አያስፈልገውም  

ገነት ውስጥ የመኖር መብት ያላቸው ይመስል ለምን  ወጣን  ብለው  ይጠይቃሉ⁉️

አዳምም  ያንን  ወጀል  ባይሰራና  እኛም  እዛው የምንኖር ቢሆ ኖሮ ሰማዩን የብጥብጥ ቀጠና አድርገንው #መባረራችን አይቀርም ነበር

በርግጥ አላህ አደምና ዝርያዎቹን #ሊያስተምር የፈለገው  ትዛዜን #በመጣስህ ከጀነት ወተሀል,   ወደፊት መልክተኛችን  እልካለሁ  የሚነግሯችሁን ከተቀበላችሁና ከተገበራችሁ  ወደ  ገነት ትመለሳላችሁ  ግን  ዝርያዎች  ትዛዜን ካልተቀበላችሁና  ከጣሳችሁ  ከምድር #የከፋ ሲኦል ትገበላቹ  ተጠነቀቁ ለማለት ነው  ምድርማ ተመችቶን  ሰው ምድርን በሞት ሲለይ  እናዝ የለ እንዴ

👨‍👨‍👧‍👦አደምና ዝርያዎቹ ከዛ ብሃላ በሰሩት ስራ መሰረት ወደ ጀነትና ወይም ጀሃነም እንደሚገቡ ይገልጻል.

✳️ «አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ #ከበደለኞች ትኾናላችሁና» አልንም፡፡

📛ከርሷም ሰይጣን አሳሳታቸው በውስጡም ከነበሩበት (ድሎት) አወጣቸው፡፡ «ከፊላችሁም ለከፊሉ #ጠላት ሲኾን ውረዱ፤ ለናንተም በምድር ላይ እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ መርጊያና መጣቀሚያ አላችሁ» አልናቸው፡፡

✏️ አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ፡፡ በርሱ ላይም (ጌታው ጸጸትን በመቀበል) ተመለሰለት፤ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡

📘«ሁላችሁም ኾናችሁ ከርሷ ውረዱ፡፡ ከኔም የኾነ #መመሪያ ቢመጣላችሁ ወዲያውኑ መመሪያዬን የተከተለ ሰው በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም» አልናቸው፡፡

🔬እነዚያም (በመልክተኞቻችን) #የካዱ በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉ እነዚያ #የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ 2:35-39

ባልሰራንው ሀጢያት ከመጠየቅና ያላጠፈውን ሰው ከመስቀል ዝምብሎ ይቅር ብያችሁዋለ ማለት አይቻልም ነበር?

ሰ ው  የሚድነው  በአንድ ሰው መሰቀል ቢሆን ኖሮ በሚሊዮን የሚቆጠር ሙስሊም በፍቃደኘነት  ያለፍራቻ ለመሰቀል ፍቃደኛ ይሆኑ ነበር

የሰው ልጅ ተሳሳች ነው ጥፋቱን አውቆ እስከተመለሰ ድረስ  አላህ ሁሌም ይቅር ሊለው ይችላል ዋናው ነገር እኛ ተፀፅተን ወደ አላህ መመለሳችን ነው

Ramadan ረመዳን

17 Jan, 04:45


የጁምአ ቀን ነብዩን ﷺ  በብዛት የምናስታውስበት  ቀን ነው  
ወንጀልን ከሚያሥምሩ እና ሀሳብ እና ጭንቀት ከሚያስወግዱ ነገሮች መካከል በአላህ ነብይ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ ትልቁ ነው።

🪐ጁሙዐ ቀን ሲሆን ደግሞ ሰለዋት ማብዛት  ይወደዳል።

🌼የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) እርሳቸው ላይ ሰላት የሚያወርድን ሰው የሚከተለውን ብለዋል:–

🌾ለሚያሳስብህን ነገር አላህ ይበቃሀል ወንጀልህም ይማራል

Ramadan ረመዳን

15 Jan, 18:21


በአሜሪካው  ቃጠሎ በተአምር የተረፈው  በውስጡ መስጊድ የያዘው ራህመት ሆስፒታል

አከባቢው እሳት ተነስቶ በመንደሩ ያሉ ሰዎች እየሸሹ የሆስፒታሉም  ሰራተኞች እንዲወጡ ቢነገራቸውም  አንወጣም ብለው  በቁርጠኘነት  የሚችሉትን ሁሉ አደረጉ

የመስጊድም ኢማም  ማይክራፎኑን ይዘው ወደ ደጅ በመውጣት  አዛን ሲያደርጉ ከሰፈሩ ሲሸሹ የነበሩ ሰዎች ወደመስጊድ ለመጠለል መጡ ኢማሙም  ተረጋጉ አትረበሹ በማለት ወደሆስፒታሉ  ቤዝመን በወውሰድ  በርትታቹህ ፀለዩ አሉዋቸው  የመጡትም ሰዎች የተለያየ እምነት ያላቸው ነበሩ ኢአማኒያን ሁሉ ነበሩ

ከጊዜ ወደ ጊዜ እሳቱ እየበረታ  በአከባቢ    ያሉ ቤቶች በእሳት  ተያይዘው ሆስፒታሉም   በእሳት ባህር ተከቦ  እሳቱም  እየተጠጋ  ጭንቀቱም በርትቶ ሰውም  ዱአ ያደርጉ ነበር በዚህም  አላህ ንፋስ ልኮ እሳቱ ከሆስፒታሉ  ተቃራኒ አቅጣጫ እንዲነፍ በማድረግ  እሳቱ ወደ መስጊዱ እንዳይቀርብ ታደገው በዚህም በአከባቢው ሳይቃጠል  በብቸኘነት የቀረ ህንፃ ሆነ  ሚዲያዎችም ይህን ተአምር እየተቀባበሉ ዘገቡት   ለተጨማሪ መረጃ ከላይ ያለውን ቪዲዮ ይመልከቱ

Ramadan ረመዳን

15 Jan, 18:21


https://www.youtube.com/watch?v=SvoEICUWVIQ

Ramadan ረመዳን

14 Jan, 18:41


ነብዩ ﷺ   ከ10 ትልላቅ የቂያማ ቀን  ምልክቶች ውስጥ ሁለቱ

1⃣ ሶስት  የመሬት  መሸራተት,    በስተምስራቅ የ 1ከተማ መሬት መደርመስ ክስተት ማለትም ከተማዋ  የት እንደገባች እስከማይታወቅ ድረስ ትሰምጣለች

እንደዚሁ በስተ ምዕራብ አንድ ትልቅ ከተማ ተገለባብጣ ትጠፋለች።

ሶስተኛው  በመካከለኛው ምስራቅ ከተማ   የሚውጥ   የመሬት  መደርመስ     ይከሰታል  ሰዎች ምድር ምን ነካት⁉️ እያሉ ይነጋገራሉ !

2⃣ አለምን  የሚሸፍን ብርቱ የሆነ ጭስ ይነሳል በሰማይ ና በምድር ይሞላዋል ለአማኞች ወረርሽኝ ሲሆን ለከሃዲዎች ቅጣት የሆነ።

Ramadan ረመዳን

13 Jan, 18:13


https://www.youtube.com/watch?v=L3CxoUSn184

Ramadan ረመዳን

13 Jan, 18:11


የቂያማ ምልክቶች

ሁዘይፋ (ረዐ) በአንድ ወቅት  ተሰብስበን እያወራን ሳለ ነብዩ ሰዐወ ድንገት መተው ስለምንድ ነው የምትገጋገሩት አሉን እኛም  ስለ መጨረሻው ቀን ነው አልናቸው  እሳቸው  የአለም ፍፃሜ እነዚህ አስር ምልክቶች ከመታየታቸው በፊት አትከሰትም አሉ ከነዚህ ምልክቶች ውስጥ መጨረሻ ላይ የምትከሰተው ከየመን  የምትነሳ  እሳት ስትሆን በንፋስ እየታገዘች ሰዎችን  እየነዳች ወደ አንድ አከባቢ ትሰበስባቸዋለች. ሙስሊም 2901


ሳንታ አና የተሰኘና በሰአት 110 ኪሎሜትር የሚምበገዘግ ነፋስ ወደ ሎስአንጀለስ እየተጓዘ ነው። ነፋሱ እዚያ ከመድረሱ በፊት አሜሪካ እሳቱን መቆጣጠር ካልቻለች ሎስአንጀለስ እንዳለ ትወድማለች። አሜሪካ የሎስ አንጀለስ 10 ሚሊዮን ነዋሪዎች በጠቅላላ ከተማዋን ለቀው ለመውጣት እንዲዘጋጁ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

የሰደድ እሳቱ ውድመት ከ 300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲሻገር የሟቾች ቁጥርም 36 ደርሷል።
የካሊፎርኒያ ባለስልጣናት " በአሁኑ ሰአት ለማመን በሚያስቸግር ልብ ሰባሪ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን "ብለዋል።

በአሁኑ ሰአት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አሜሪካዊያን ሙሉ ንብረታቸው ወድሞ ለእርዳታ ጠባቂነት የተዳረጉ ሲሆን ግብረሰናይ ድርጄቶችና ምግብ ቤቶች ለተፈናቃዮች ነፃ ምግብ እያቀረቡ ይገኛሉ

Ramadan ረመዳን

12 Jan, 18:11


በ #አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ በመከልከላቸው የብሔራዊ ፈተና የኦንላይን ምዝገባ እንዳለፋቸው ገለጹ

በ #ትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና የኦንላይን ምዝገባ ለማከናወን "ሂጃብ እንዲያወልቁ" መጠየቃቸው ባለመቀበላቸው ትናንት ጥር 2 ቀን የምዝገባ ቀኑ እንዳለፋቸው ገለጹ።

ተማሪዎቹ “ሂጃባቸውን እስካላወለቁ ድረስ ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ትምህርት ቤቶቹ መከልከላቸውን” ገልጸው ይህም የሃይማኖታዊ እምነትን መጣስ ነው ብለዋል።

ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች አንድ ተማሪ፣ "ሃይማኖታችን ስለሚከለክል ለብሔራዊ ፈተና ለመመዝገብ ብለን ሂጃባችንን ማውለው አንችልም። ሃይማኖታዊ ግዴታችንን ከመተላለፍ ይልቅ ትምህርታችንን መተው እንመርጣለን” ስትል ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጻለች።

እዛ ሰፈር ያሉ ፅፈኞች በዚህ ዘመን እንኳን ለእስልምና ያላቸውን  ጭፍን ጥላቻ  ሊቀርፉ አልቻሉም ስለዚህ

እነዚህ እህቶቻችን በምንም መልኩ በእምነታቸው ምክንያት  ከፈተና መቅረት ሰለሌለባቸው የክልሉ  ት/ቢሮ ማሰስፈፀም ካልቻለ  ትምህርት ሚኒስተር  እነዚህ ተማሪዎችን ወደ አዲስ አበባም ቢሆን አምጥቶ ዩኒቨርስቲም ይሁን አዳሪ ት/ቤት አስገብቶ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ, የፈተናም ፎርም እንዲሞሉ ማድረግ አለበት

ለመሆኑ ይህ የሴቶች ሚኒስቴር የሚባለው ምን እየሰራ ነው
⁉️

Ramadan ረመዳን

12 Jan, 14:37


✴️እሳቱ የተነሳዉ በትንሽዬ 🐔 ወፍ 🦃 ምክኒየት ሲሆን የዚህች ወፍ እሳት ማስነሳት አለምን እያነጋገር ይገኛል

✴️በአለም ቁጥር አንድ የእሳት ማጥፊያ ያላት አሜሪካን ብቻ ናት ታዲያ እሳቱን እስካሁን ሊያጠፉት ቀርቶ እጅግ እየተባባሰ መጥቷል

✴️445 የእሳት አደጋ ሂልኮፍተሮች መኪናዎች ተሳትፈዋል ግን ወፍ ዬለም

✴️12 ሺህ ህንጻዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል

✴️ከአንድ ጫካ ወደ ሌላ ጫካ ከአንዱ ህንጻ ወደ ሌላኛዉ ህንጻ  በሰአታት ልዩነት እየተዛመተ ነዉ

✴️አሜሪካን አለኝ ያለችዉን የእሳት ማክሸፊያ ሁሉ ተጠቅማለች ግን አልቻለችም ከተማዉ ሌት ተቀን መንደድ ብቻ ሆኗዋል።


ወትሮስ አሜሪካ በየሄድችበት እሳት መጫርና በተጫረው ላይ ቤንዚን ጨምሮ ማቀጣጠል እንጂ እሳት ማጥፋት የት ታውቃለች!

ይሄው የሜክሲኮ እሳት አጥፊዎች ሊያግዟት ነው። ሆሊውድ ሳይቀር ይረምርምሽ! አላህ ንፁንን ብቻ ይጠብቃቸው። ለፈሳድ ባለቤቶች ልብ መግዢያም ስለሚሆናቸው ይቀጥል!

Ramadan ረመዳን

11 Jan, 18:03


ከጥቂት ሰአታት በፊት ይህ ቦታ  በሎሳንጀለስ የሚገኘ  የአለማችን ውዱ የሪል እስቴት ቦታ ነበር  አሁን ግን ወደ አመድነት ተቀይሯል

... ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ሀያሎች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡ 10:24



አሜሪካዊያን በግልፅ እየተናገሩ ይገኛል:-

"እስራኤል ለአመት ከመንፈቅ በአሜሪካ ታክስ ከፋዮች ፈንድ በተገዛ ሚሳይል ጋዛን ስታፈነዳ ነበር።የአምላክ ቅጣት በሚመስል መልኩ በሁለት ቀን ውስጥ በኛ ፋይናንስ ካጠቃናት ጋዛ የሚሰፋ የሀገራችን ክፍል በእሳት ወድሞብናል።እኛ ባወጣነው ታክስ በጋዛ ላይ የተፈፀመው ጭካኔ የተምላበት ጥቃት የጋዛ ነዋሪያንን ላልተቋረጠ ስጋት ዳርጓቸዋል።መሰረተ-ልማቷንም አውድሟል።ይህ ሁሉ ሲፈፀም አለም ዝም ብሎ ነው የተቀመጠው።በሁለት ቀናት መለኮታዊ ቅጣት በተፈጥሯዊ አደጋ መልኩ በአሜሪካ ጋዛን የሚበልጥ አካልን መቷል።ይህ ክስተት ስለ ፍትህ በእውነት ፤በዳዮችን መርዳትም ስለሚያስከትለው መዘዝ እንድንጠይቅ ያነሳሳናል።"

Ramadan ረመዳን

11 Jan, 16:31


በእሳት እና በረዶ የተፈተነችው ሀገር

ኃያል ነኘ የምትለው አሜሪካ ከሰሞኑ እሳት እና በረዶ ለጥፋት አብረውባታል ፡፡ 

ሀገሪቱ በአንድ በኩል ያገኘውን ሁሉ በሚበላ ከባድ ሰደድ እሳት፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጥንትን በሚሰረስር በረዶ ተፈትናለች፡፡

በሎስ አንጀለስ ከተማ የተነሳው ሰደድ እሳቱ እስካሁን የ10 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከ170 ሺህ የሚበልጡ ሰዎችም መኖሪያቸውን ለቀው ለመሸሽ በተጠንቀቅ እንዲያሳልፉ አድርጎ ነበር፡፡

በከባድ ሙቀት እና ኃይለኛ ንፋስ የታጀበው ሰደድ እሳቱ ከ10 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን፣ ህንጻዎችን እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን አውድሟል፡፡

ስመ ጥር የአሜሪካ የፊልም ባለሙያዎች መኖሪያ እና የግዙፉ የሆሊውድ የፊልም መንደር መገኛ የሆነችው ከተማዋ በእሳት እና ጭስ ጽልመት ለብሳ አሳልፋለች፡፡ 

በሌላ በኩል ከሰሞኑ 7 የሚደርሱ የሀገሪቱ ግዛቶች ከባድ በረዶ ወርዶባቸው ቅዝቃዜ ሲቆረጥማቸው ሰንብቷል፡፡

በበረዶ ውሽንፍሩ የ5 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሜሪላንድ፣ ቨርጂኒያ፣ ካንሳስ፣ ሚዙሪ፣ ኬንታኪ፣ አርካንሳስ እና ሌሎች ግዛቶችም የአደጋ ጊዜ አዋጅ አውጀው ነበር፡፡

የበረዶ ውሽንፍሩ በሀገሪቱ ከ2 ሺህ 300 በላይ በረራዎች እንዲሰረዙ፣ 9 ሺህ በረራዎችም እንዲዘገዩ እንዲሁም 190 ሺህ የሚደርሱ ቤቶች ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጩ እንዲሆኑም ምክንያት ነበር፡፡

ሀገሪቱን ያስጨነቀው የበረዶ ውሽንፍሩ እስከ 8 ኢንች ድረስ ወደ ላይ ሊወጣ እንደሚችል እና ደቡብ ምስራቅ ኦክላሆማን ይዞ እስከ ካሮላይና ግዛት ሊዘልቅ እንደሚልችልም የሀገሪቱን ብሔራዊ የአየር ትንበያን ጠቅሶ ዩኤስኤ ቱደይ ዘግቧል፡፡

በመሐመድ

أَفَأَمِنُوٓا۟ أَن تَأْتِيَهُمْ غَٰشِيَةٌ مِّنْ عَذَابِ ٱللَّهِ أَوْ تَأْتِيَهُمُ ٱلسَّاعَةُ بَغْتَةً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

ከአላህ ቅጣት ሸፋኝ አደጋ የምትመጣባቸው ወይም ሰዓቲቱ እነሱ የማያውቁ ሲኾኑ በድንገት የምትመጣባቸው መኾኑዋን አይፈሩምን
12:107

Ramadan ረመዳን

11 Jan, 14:16


በአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ በመከልከላቸው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ እንዳለፋቸው እየሰማን ነው። በጣም ይገርማል። የአክሱም ሙስሊሞች የማምለኪያ ስፍራ ተከልክሎ ...የመቃብር ቦታ ተነፍገው...አሁን ደግሞ በትምህርት ገበታ እንዳይገኙ እየተደረገ ነው። ይህ ደንበኛ የአፓርታይድ ምሳሌ ነው።

እንዲህ አይነት ሃይማኖታዊ አድሎና አክራሪነት ከምንጊዜውም በላይ ገዝፎ የነበረው በአጤ ዮሐንስ ዘመን ነው። በማግባባት ሳይሆን በሃይል የማጥመቅ ዘመቻቸው የበርካታ ንፁሃንን ደም አፍሷል። ይህ የሃይማኖት ፅንፈኝነታቸው በኃላ ላይ ሀገርንም ዋጋ አስከፍሎ የሳቸውንም ነፍስ ነጥቋል።

ኢጣሊያኖች ከባህር ወደ ደረቅ መሬት ወርዶ መስፋፋት ሲጀምሩ ዕቅዳቸው የቅኝ ግዛት እንደነበር ብዙ ምልክቶች ነበሩ። አጤ ዮሐንስ ግን የኢጣሊያን እንቅስቃሴ ከመግታት ይልቅ ወደ መተማ ለመዝመት ወሰኑ። ለምን ሲባሉ
<< ክርስቲያኑን ኢጣሊያን ከመውጋት እስላሙን ደርቡሽን መውጋት ይሻላል... >> ብሎ ትልቁን ጠላት ከደጅ ትቶ በሃይማኖት ጥላቻ የታወረ ውሳኔ ወሰኑ። መጨረሻቸውም እጅግ አብዝቶ በጠሉት ሙስሊሞች እጅ መውደቅ ሆነ።

አሳዛኙ ነገር አክሱም አሁንም ከአጤ ዮሐንስ ዘመን ባልተለየ ሁኔታ የሀይማኖት አድሎ የሚፈፀምባት መሆኗ ነው። ሰው ስደተኛ ሆኖ በሚኖርበት ሀገር እንኳ መሰረታዊ የእምነት መብቱ በሚከበርበት ዘመን በገዛ ወገኖቻቸው በአክሱም ሙስሊሞች ላይ እየተፈፀመ ያለው ነገር አስነዋሪ ነው። የከተማዋ ከንቲባ አጤ ዮሐንስ ፭ኛ ለመባል ፈልጎ እንዳይሆን...🤔
-  ጥላዬ ያሚ

Ramadan ረመዳን

10 Jan, 18:16


https://www.youtube.com/watch?v=_GVb7c8e0OA

Ramadan ረመዳን

10 Jan, 18:16


ይህ የሚታየው መብራት ሳይሆን  በእሳት እየተቃጠሉ ያሉ ህንፃወች ናቸው

  « وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ»

«አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡»  14: 42

Ramadan ረመዳን

10 Jan, 18:01


«እኔ አምላካችሁ #አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም #አያጋራ» በላቸው፡፡ 18:119

وَإِذْ قَالَ لُقْمَٰنُ لِٱبْنِهِۦ وَهُوَ يَعِظُهُۥ يَٰبُنَىَّ لَا تُشْرِكْ
بِٱللَّهِ ۖ إِنَّ ٱلشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን)
#አታጋራ፡፡ #ማጋራት ታላቅ በደል ነውና» ያለውን (አስታውስ)፡፡ 31:13

ልጆች ከአላህ የተሰጡ አማና ናቸው ወላጅ የዲን ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ አለባቸው ይህን የረፍት ግዜ ወደ መድረሳወች የሂፊዝ  ማአከላት በማስገባት በአግባቡ  እንዲጠቀሙበት ይከታተሏቸው.

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና #ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡ 66:6

Ramadan ረመዳን

09 Jan, 17:44


በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የተከሰተው ሰደድ አሳት ወደ ሆሊውድ ኮረብታዎች እየተስፋፋ ነው።

ከ100 ሺ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።

በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚገመት ገልጿል።

"ጄምስ ዉድ ይባላል።ታዋቂ አሜሪካዊ የፊልም አክተር ነው።
የዛሬ አመት በአሜሪካ ለተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚደግፍ ሰልፍ አስመልክቶ በትዊተሩ እንዲህ ፖስቶ ነበር።
"No ceasefire. No compromise. No forgiveness.

#KillThem*All "
"ተኩስ አቁም የለም! ስምምነት የለም።ይቅር ማለትም አይገባም።
ሁሉንም ግደ**ሏቸው።"

ዛሬ በሎሳንጀለስ የሚገኘው እጅግ ቅንጡ ቤቱ ተቃጥሏል።

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
በምሽቱ  የእሳት አደጋ ከወደሙ ቤቶች ውስጥ የጆ ባይደን ታላቅ ልጅ የሆነው ሃንተር ባይደን ቅንጡ መኖሪያ ይገኛል።

Ramadan ረመዳን

08 Jan, 18:46


لَّوْ أَرَادَ ٱللَّهُ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا لَّٱصْطَفَىٰ مِمَّا يَخْلُقُ مَا يَشَآءُۚ سُبْحَٰنَهُۥۖ هُوَ ٱللَّهُ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّارُ

አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው፡፡ 39:4

«ለአልረሕማን ልጅ (የለውም እንጅ) ቢኖረው እኔ (ለልጁ) የተገዢዎቹ መጀመሪያ ነኝ» በላቸው፡፡የሰማያትና የምድር ጌታ የዙፋኑ ጌታ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ፡፡ተዋቸውም፡፡ ያንን ይስፈራሩበት የነበሩትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ (በስሕተታቸው ውስጥ) ይዋኙ ይጫዎቱም፡፡

እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊግገዙት የሚገባው በምድርም ውስጥ ሊግገዙት የሚገባው አምላክ ነው፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ዐዋቂው ነው፡፡

ያም የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ንግሥና የእርሱ ብቻ የኾነው አምላክ ላቀ፡፡ የሰዓቲቱም (የመምጫዋ ዘመን) ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ 43 : 81 - 85

Ramadan ረመዳን

05 Jan, 18:08


በአለም ላይ በተለዩ እምነቶች የፈጣሪ ልጆች ተብለው የሚወሰዱ  ሰዎች ሲኖሩ ባለፈው ሳምንት በሌሎች አገሮች የተከበረለት እና እዚህም ሀገር በቀጣይ ሳምንት ልደቱ የሚከበርለት እየሱስ አንዱ ነው

በርግጥ እየሰሱስ ራሱ የፈጣሪ ልጅ ነኝ አላለም አንደውም በርካታ ቦታወች ላይ ባይብል ውስጥ #የሰው ልጅ ነኘ  ይላል

" ነገር ግን አሁን ከእግዙአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኩኋችሁን #ሰው
ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ.."  ዮሀንስ 8 ፡40

📓‹‹ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር #አልተላኩም ›› ማቴዎስ 15፡24

በርግጥ አላህ ልጅ አስፈልጎት ወለደ ካልን ልጁም ልጅ  ያስፈልገዋል ማለት ነው አንደዛ ከሆነ ደሞ ማቆሚያ የለውም ሊበዙ ነው
እየሱስም ብቸኛ ልጅ ይላሉ, እየሱስ ብቻውን ለምን ይሆናል ከወለደ አይቀር ወንድምና እህት አያስፈልገውም እንዴ⁉️

ከዚህም አልፈው ፈጣሪ ነው የተወለደው ብለው የሚያመልኩትም አሉ ለነዚህም ራሱ እየሱስ በባይብል ውስጥ እንዲ ይላል

"እኔን ከፍ ከፍ አታድርጉኘ ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም " ዩሀንስ 8:28  
በሌላም ቦታ
" የሰውም ስርአት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ #በከንቱ ያመልኩኛል" ይላል. ማቴዎስ 15:9

በቁርአን ውስጥም አላህም እንዲ አለ

📗«አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ. ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ. ከእርሱ (ከንግግራቸው) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ.
ለአልረሕማን #ልጅ አልለው ስለአሉ. ለአልረሕማን #ልጅን መያዝ አይገባውም. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡ መርየም 98 ፡ 88-93

Ramadan ረመዳን

04 Jan, 18:40


በ ኡመር (ረ.አ) ዘመን መዲና ስትንቀጠቀጥ ህዝቡን ከወንጀል ቶብቱ ብሎ ኡመር አስጠነቀቀ.. ከዛም አላቸው  " ምድር ደግማ ከተንቀጠቀጠች ከ እናንተ ጋር እዚህ አልኖርም"

وقال صلى الله عليه وسلم : « من قال أَسْتَغْفِرُ اللهَ الْعَظِيْمَ الَّذِيْ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّوْمُ وَأَتُوْبُ إِلَيْهِ , غفر الله له وإن كان فر من الزحف »

‘"አስተግፍሩላህ አልዐዚም አለዚላኢላህ ኢላ ሑወል ሐዩል ቀዩም ወአቱቡ ኢለይህ

<<ከርሱ ውጭ ሌላ አምላክ የሌለ ህያውና ራሱን ቻይ የሆነውን አላህን ምህረት እለምነዋለሁ፤ ወደር ሱም ተውበት አደርጋለሁ››  ያለ ወንጀሉን ይምርለታል  .....’ .’

Ramadan ረመዳን

03 Jan, 18:13


ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ አሉ፦

ሰአቷ አትቆም
📗እውቀት ሳይነሳ (ሳይወሰድ),
መሬት መንቀጥቀጥ ሳይበዛ
ግዜው ሳይሮጣ
አስጨናቂ ነገሮች ሳይከሰቱ
ግድያ ሳይበዛ
ገንዘብ ሳይበዛ.
ቡኻሪ 1036

ምፅዋት ሳታዘገዩ ስጡ በላን ትከላከላለችና. (ቲርሚዚ)

አላህም እነሱ  #ምህረትን (እስቲግፋር ማድረግ) የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም፡፡ 8:33

Ramadan ረመዳን

02 Jan, 17:48


1446 ግማሽ አመት እንዴት አለፈ

ረዳንም ሁለት ወር ያነሰ ቀርቶታል 1446 ተጋምሷል ከእድሜያችን  ቀንሰናል     ስራችንስ     ጨምሯል  ወይስ  ....

የ6 ወር በነዚህ ነገሮች  ይተሳሰቡ

👉 ሰላትን ወቅቱን ጠብቆ መስገድ 
በተለይ የሱብሂ ስላት 🌼

👉የጅመአ ሰላት ከ26 ምን ያህሉን ጠብቀናል

👉ቁርአን መቅራት ምን ያህል ፈፅመናል

👉ምን ያህል ከሀራም ተጠብቀናል
  
  👉 በተሰቦቼን ወደ ዲን እንዲቀርቡ ምን ጥረት እያደረኩነው ብለው ይጠይቁ⁉️

የቤተሰብ አባላትን በጥሩ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል
🧎🧍‍♂ልጆችን በተርቢያ ማሳደግ ማስቀራት መከታተል
🌓ወላጆችን ማስተማር እምነታቸው ከሽርክ ማፅዳት
🌒የቤተሰብ አባላት ለሱብሂ መቀስቀስ እነዚህ ጉዳዮች መተግበር በአላህ መንገድ መታገል ነው ብዙም ምንዳ ያገኙበታል ትኩረት እንስጠው

Ramadan ረመዳን

01 Jan, 18:37


ዛሬ ረጀብ አንድ  ብሏል

ረጀብና ሸአባን ከተቀደሱ ወሮች ውስጥ ይመደባሉ

ነቢዩ (ﷺ)
አላህ ሆይ የረጀብና የሸአባን ወር ባርክልን የረመዳን ወር አድርሰን ይሉ ነበር.

የረጀብ ወር ወንጀል የኢማን  ብርሀንን ያጠፋዋል። የኢማን ጥፍጥናህን ይቀንሰዋል። ገና ከወዲሁ ነፍስያህን ከወንጀል በማቀብ ለረመዳን እናዘጋጃት።

ረጀብ ነፍስ ይበልጥ ከማይበደልባቸው አላህ እርም ካደረጋቸው 4 የአመቱ የተከበሩ ወራት መካከል አንዱ ስለሆነ፤ በዚህ ወር  ወንጀል ላይ ልንጠነቀቅ ይገባል

ቀደምቶችም ረጀብ ዘር የሚዘራጀት ወቅት  ሸአባን  የዘረሀውን የምትከባከብ ወር ረመዳን ፍሬው የምትሰበስብበት
ወቅት ነው አሉ

Ramadan ረመዳን

31 Dec, 18:52


🎯 አመተ   ሂጅራ 1446 ተጋመሰ ስድስት ወር ሞልቷል   

ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
"ብልጥ ሰው ብሎ ማለት ራሱን  (ነብሱን) የሚገመግምና ከሞት ብኋላ ላለው ህይወቱ መልካም ስራ የሚስራ ሲሆን ሞኝ ብሎ ማለት ስሜቱን የሚከተልና አላህን በባዶ ተስፋ የሚያደርግ ነው" (ቲርሚዚ
)

ለቅርቢቷ አለም ስኬት የመስሪያ ቤቶች የ6 ወር አፈፃጸም ረፖርት እየቀረበ ይገኛል ለአኼራ  የምንሰራው ስራ በ6 ወር አንድ ግዜ እንኳን እንተሳሰብ እንጂ ⁉️

አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡   «በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና»... 23:99-100

Ramadan ረመዳን

31 Dec, 18:33


በአለም ላይ ተለያዩ አገሮች  የተለያየ የዘመን  መቁጠሪያ ሲኖሩ  ነገ 2025  አንድ  ብሎ የሚጀምረው  የምእራቡ  አለም  አቆጣጠር  አንዱ   ነው  ከሁሉም ረጅም አመት ያስቆጠረው የቻይናዊያን አቆጣጠር ሲሆን በዚሁ መሰረት አሁን ላይ  4722  አመት ላይ ይገኛል

🌙የሂጅራ አቆጣጠርን  1446
☀️የግሪጎሪያን አቆጣጠርን  2025
💥የቻይና  መቁጠሪያ 4722
🌝ኢትዮጵያ 2017
🎋ሰሜን የኮሪያ   114
🌹የህንድ(ጉጅራቲ) 1946
ማይናማር 1387
የታይ 2568
🌛የመሳሰሉት አቆጣጠሮች ይጠቀሳሉ

በተለያዪ ህብረተሰቦች ዘንድ አመት ሳይቆጠር በወቅቶች የሚጥሩ አሉ በጋ ክረምት አይነት

Ramadan ረመዳን

30 Dec, 18:32


በ #ጀርመን #በርሊን የሚገኘው ቤተክርስትያን ሙስሊሞች እንዲሰግዱበት ተደረገ

ጭፍን ጥላቻ ያሰከረን   የብቃታችን      መለኪያ    የሰዎችን  መብት በመጠጣት እንደ ጀብዱ  የምንቆጥር   ከዚህ ትምህርት ትቀስሙ ዘንድ ይፈለጋል

በጀርመን በሊን የሚገኙ ሙስሊሞች  የኮሮና ጊዜ  በአገሪቱ የወጣው ህግ ለመተግበር መቸገራቸውን የተመለከቱ የቤተክርስትያን አገልጋዮች ህጉን በመተግበር ተራርቀው እንዲሰግዱ ቤተክርስትያን ፈቅደውላቸው የጁምዓ ሰላታቸውን ሰግደዋል ።

#ዳሩሰላም በበርሊን የሚገኝ መስጊድ ነው ። መስጊዱ በአገሪቱ የወጣው ተራርቀው እንዲሰግዱ የሚያዝ ህግ ለመተግበር የሚያስቸግር ነው ። ምክንያቱም ተራርቀው ቢሰግዱ የመስጊዱ ስፋት አይፈቅድም ፤ አይበቃም ።
በዳሩ ሰላም መስጊድ አጠገብ ግን አንድ ቤተክርስትያን አለ። ይህን ቤተክርስትያን ሙስሊሞቹ እንዲሰግዱበት የቤተክርስትያኗ አገልጋዮች ሰጥተዋቸው የጁምዓ ሰላታቸውን ያለ ምንም ችግር ሰግደውበታል ።

ይህ እንግዳ ነገር ነው ። በተለይ በአገራችን አልተለመደም ። «ይህ የእኔ ከተማ ነው»፤ «እዚህ ከተማ መስጊድ አትሰሩም» ፤ «ብተሞቱም እዚህ ከተማ አትቀበሯትም» የሚል በመሆኑ ይህ የጀርመኑ ለእኛ መልካም አርአያ ነው የሚል እምነት አለኝ

እምነት ይኑረኘ በስርአት ልልበስ ስላሉ ከትምህርት ይታገዳሉ እንደ አክሱም አይነት ከተሞች

Ramadan ረመዳን

29 Dec, 18:34


ለምን  ትሰግዳላችሁ ሂጃብ ታደርጋላችሁ

ሴት ገላዋን መሸፈን ሂጃብ ማድረግ  ከመጥፎ ነገር መጠበቂያዋ በዋናነት ደሞ ለጌታዋን ትእዛዝ  ማደሯን,  የእምነቷ  ምልክቷ,  ጀነት መግቢያዋ ነው

ለአንድ ሙስሊም ወቅቱን ጠብቆ ስላት መስገዱ እምነቱን መጠበቂያ ለጌታው ታዛዠ መሆኑን ማሳያና የገነት ቁልፉ ናት

አንድ ሙስሊም ላልሆነ ሰው ሂጃብ መልበሰ ማለት አንድ ሜትር  የማይሞላ ጨርቅ ማድረግ , ሰላት መስገድ  ማለት ለአንድ አስር ደቂቃ ጎምበስ ቀና ማለት ነው ብሎ ቢረዳው ነው........ ግን ⁉️

ሂጃብ ማድረግ ሰላት መስገድ ሌሎችን የሚጎዳ ነገር የለውም  ግን አሳስቧቸው ለምን ሂጃብ  ታደርጋላችሁ ስላት ትሰግዳላችሁ  ይሉናል⁉️

ሂጃብ ማድረግ ሰላትን መስገድ አላህን መታዘዝ, እምነትን በመጨበቅ  ከሲኦል ድኖ ገነት መግቢያ  እንደሆነ  ሰይጣን በደብ  ይረዳል;  ስይጣን ደሞ ጉዳዮን የሚያስፈፅመው  በመጥፎ ሰዎች ስለሆነ  ምንም የማይጎዳቸውን ነገር  በማድረጋችን ስጋት ይገባቸዋል ሰይጣናቸውም  ሂጃብ የለበሰች, ሰላት የሚሰግድ ሰው  እንዲጠሉ ስለሚያደርጋቸው ነው  እንጂ አንድ
ሜትር የማይሞላ ጨርቅ ተደረገ አልተደረገ , ለአስር ደቂቃ ጎምበስ ቀና ስላለ ምኑም አስቸግሯቸው አይደለም

ሰሞኑንም በአክሱም ሂጃብ ካላወለቃችሁ አትማሩም የሚሉት ያው  በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሰይጣን ጉዳይ እያስፈፀሙ ነው እንጂ ለስሙ እነዚህ ሰዎች የኦርቶዶክስ እምነት  ተከታይ ነን ይላሉ እንደ ሚያምኑባት  ማሪያም ሂጃብ የሚለብሱትን  ማየት ግን ምቾት አይሰጣቸውም ለምን እላያቸው ላይ ባለው ሰይጣን ምክንያት

Ramadan ረመዳን

28 Dec, 18:44


ሂጃብ
ሴት ልጅ የተሟላ ሂጃብ በመልበስዋ ወንዶች እርሷን አይተው ከመፈተን ትጠበቃለች፤ መከላከያ ትሆናለችም።
ነገር ግን በተቃራኒው ማራኪ ገፅታዋ የሚታይ የምትገላለጥ ከሆነ ፈታኙ የጥፋት በር በትልቁ ይከፈታል

የሴት ልጅ አካል  ሳቢና ማራኪ ነው።
አይደለም የሚዳሰስና የሚታየው ቀርቶ አረማመዷ፣ አነጋገሯና አስተያየቷ እንዲሁም ከጅልባብ ስር የምትለብሳቸው ልብሶች እንኳን ልብን ይረብሻሉ ፤ በሽታውንም ይቀሰቅሳሉ።

በኢስላም ሴትን ልጅ ጥቡቅነቷን እና ሰላሟን ታስጠብቅ ዘንድ የተጠኑ ስርዓቶችን አስቀምጦላታል።

ሂጃብ ሴት ልጅ ሙሉ ውበቷን ባዕድ ከሆኑ ወንዶች እንድትሸፍን የታዘዘችበት ክብሯን ለመጠበቅ የተደነገገላት ድንቅ ድንጋጌ ነው ።

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ قُل لِّأَزْوَٰجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَآءِ ٱلْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَٰبِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًۭا

አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

وَقُل لِّلْمُؤْمِنَٰتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَٰرِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ
ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡
እምነት  ያስፈለገው    ከመጥፎ    ስራ ለመቆጠብና  መልካም ስራ  ሰርቶ   ጀነት   ለመግባት  ሲሆን የአንዳንዶች እምነት ግን ለሰይጣን መጠቀሚያነት ሲውል ይስተዋላል.

ለምን ሂጃብ ትለብሳላችሁ ሲጀመር የነሱ መልበስ ምን ችግር ስለፈጠረ አጀንዳ  የሚሆነው  ምናልባት ስታያቸው  ላይመቻቹህ  ይህ ግን  የሚያቃጥለው እላያችሁ  ላይ  ያለው ሴጣን ነው  ስለዚህ ባለማወቅ  የሰይጣን መጠቀሚያ  አትሁኑ  ,መልበሳቸው መብታቸው ሲሆን  ይንንም በማድረጋቸው የማንንም መብት አልነኩም  

በባይብል   ውስጥ ሴት ሱሪ መልበስ    እንደሌለባት,    ሂጃብ ማድረግ  እንዳለባቸው,    እንዲሁም  ኒቃብ(የፊት   መሸፈኛ) እንደሚያደርጉ   ስለሚጠቅስ  ለእምነታችሁ ትዛዝ     ለመተግበር    ብትጥሩ ኖሮ  ሙስሊም  ሴቶችን ማድነቅና    መደገፍ    ሲገባችሁ  መበደልና ከትምህርት ማገድ  የስይጣን ጉዳይ  አስፈፃሚ  መሆን    ነው
 
"ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት
ልብስ አይልበስ። ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።" [ኦሪት ዘዳግም 22፥5]
"ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።" [1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 6]

* "በአይነ ርግብ(የፊት) መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭሽን እንደተከፈለ ሮማን ናቸው።" [መሀልየ ዘሰለሞን 6፡7]

* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ አይኖችሽ እንደርግብ ናቸው።" [መሀልየ ዘሠለሞን 4፡1
]

Ramadan ረመዳን

27 Dec, 18:21


ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

ከዚክር ሁሉ በላጩ
ላኢላሀ ኢ ለላህ  የሚለው ሲሆን

ከዱአ ምርጡ
#አልሀምዱሊላህ ነው
ቲርሚዚ

Ramadan ረመዳን

26 Dec, 18:09


ጁምአ ቀን በጊዜ መስጂድ መሄድ የሚያስገኘው

💎እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡ 62:9

💎አቡ ሁረይራ( ረዲየሏሁ አንሁ) ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ(ﷺ) እንዲህ አሉ

1⃣የጁምዓ ቀን በጠዋቱ ታጥቦ በመጀመሪያ ሰአትዋ ወደ መስጂድ የሄደ ልክ ግመል ሰደቃ እንዳቀረበ ይፃፍለታል

2⃣በሁለተኛው ሰአት ላይ የሄደ ደሞ ልክ በሬ ሰደቃ እንዳቀረበ ይፃፍለታል

3⃣በሶስተኛው ሰአት ላይ የሄደ ልክ ቀንዳማ ሙኩት በግ እንዳቀረበ ይፃፍለታል

📘✏️ኢማሙ ሚበሩ ላይ ከዎጣ መላኢኮች መዝገባቸውን አጥፈው ኹጥባውን  ለማዳመጥ ይሰየማሉ ከዛ ብሀላ ከደረስክ  የጁምአ አቴንዳስ አምልጦሀል  ምን አናልባት ስምህን ከዝንጉዎች መዝገብ ፈልገው

💎 ሶላቷም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡  62:10 

Ramadan ረመዳን

25 Dec, 18:30


ነብዩ (ሰዐወ) ለመካ ሙሽሪኮች  ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም  ብላችሁ መስክሩ ነገ በፍድዱ ቀን ከሞት ብሀላ ተቀስቅሳችሁ ስለ ሰራችሁት ስራ  ከጌታችሁ ዘንድ ትጠየቃላችሁ  ሲሏቸው  የተፈረካከሰ አጥንት ይዘው ይመጡና አጥንቱን አየፈረፈሩ ሞተ እንደዚህ  ከፈራረስነና  አፈር ከሆንን ቡሀላ ትቀሰቀሳላችሁ ይለናል እንዴ እያሉ ይሳለቁ ነበር  አላህም ከሞታችሁ ብሀላ ለፍድ  ቀን ስትቀሰቀሱ አጥንታችሁን  ወደ ነበረበት   መመለስ  አይደለም የጣት አሻራችሁን ሳይቀር እንደነበረ እንመልሰዋለን  ይላቸዋል

(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡
(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?  አይደለም (አጥንቶቹን) #ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡ 75: 1-4

ምድር ላይ 10 ቢሊዮን ሰዎች ቢኖሩ የ10 ቢሊዮን ሰዎች የጣት አሻራቸው የተለያየ ነው , በጣት ጫፍ በምታክል ቦታ 10 ቢሊዮን አይነት ቅርፅ መፍጠር አይገርምም እጅግ  ድንቅ  ጥበብ ነው

Ramadan ረመዳን

24 Dec, 17:45


(1) ቀ (ቃፍ) በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ
(2) ይልቁንም ከነሱ ጎሳ የኾነ አስፈራሪ ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም «ይህ አስደናቂ ነገር ነው» አሉ፡፡
(3) «በሞትንና ዐፈር በኾን ጊዜ (እንመለሳለን?) ይህ ሩቅ የኾነ መመለስ ነው፤» (አሉ)፡፡
(4) ከእነርሱ (አካል) ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አልለ፡፡
(5) (አልተመለከቱም)፡፡ ይልቁንም በቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ አስተባበሉ፡፡ እነርሱም በመደናገር  ውሰጥ ናቸው፡፡
(6) ወደ ሰማይም ከበላያቸው ስትኾን ለእርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏት ኾና እንዴት እንደ ገነባናትና (በከዋክብት) እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን?
(7) ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት፡፡ በውስጧም ከሚያስደስት ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡
(8) (ይህንን ያደረግነው) ተመላሽ ለኾነ ባሪያ ሁሉ ለማሳየትና ለማስገንዘብ ነው፡፡
(9) ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን፡፡ በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን (አዝመራ) ፍሬ አበቀልን፡፡
(10) ዘምባባንም ረዣዢም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትኾን (አበቀልን)፡፡
(11) ለባሮቹ ሲሳይ ትኾን ዘንድ (አዘጋጀናት)፡፡ በእርሱም የሞተችን አገር ሕያው አደረግንበት፡፡ (ከመቃብር) መውጣትም እንደዚሁ ነው፡፡
(15) በፊተኛው መፍጠር ደከምን? በእውነቱ እነርሱ ከአዲስ መፍጠር በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡
Qaf 50:1-15 ....

Ramadan ረመዳን

23 Dec, 18:47


ኢ-አማኒያን ( Atheism)

በአውሮፓ አብዛኛው ሰው እምነት አልባ ሲሆን ለዚህም መነሻው  የነበራቸው እምነት ክርስትና  ከሰው ልጅ አስተሳሰብ ጋር የማይሄዱ  በመሆኑ  እንደ ፈጣሪ ተወለደ, ተሰቀለ, ሞተ ሌላው  ደሞ ባይብል እርስበርስ  መጋጨቱ እንዲሁም ከሳይንስ ጋር የሚቃረኑ ጥቅሶች መያዙ በዋናነት ሲጠቀሱ ሌላው ደሞ ከሀብት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሰልጥነናል የሚል ጥጋብ ነው ባላየነው አገር አናምንም የሚል ምክንያት

የፈጣሪን  ሲፈጥር ማየት አይደለም ማንም ሰው ሲወለድ እንኳን የት እንደተወለደ መቼ እንተወለደ በምን ሁኔታ እንደተወለደ ሰዎች ነግረውት እንጂ በወቅቱ ይህ መረዳት አይችልም እናቱን እንኳን ተነግሮት እንጂ  ስትወልደው አላየም

ስንና ስንት ነገር የማይታዮ  ግን መኖራቸው  የምናቅ ነገሮች በዙሪያችን አሉ ለምሳሌ  የሞባይል ኔት ወርክ  , የምንላላከው ሚሴጆች በአየር ላይ ተጉዘው ሞባይለችን ላይ ይገባሉ ግን አየር ላይ አይታዩም ,  የቴሌቪዠን ዲሽ ከሳተላይት  ምስሎችን ድምፃችን  ስቦ ያስተላልፋል ግን  በአየር ላይ  ሲስብ አናያቸውም


وَلَقَدْ خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِۦ نَفْسُهُۥۖ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ ٱلْوَرِيدِ

ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡ 
Qaf 50:16

Ramadan ረመዳን

08 Dec, 18:11


ነቢዩ (ﷺ) ስለ ትላልቅ ሃጢያት ተጠይቀዉ  እነሱም

  🛐 ለአላህ ተጋሪ ማድረግ
👉ወላጆችን አለመታዘዝ ሃቃቸውን አለመጠበቅ
ስዉን ያለአግባብ #መግደልና
በሃሰት መመስከር  ናቸዉ  አሉ ቡኻሪ 3/821

በሌላ ሀዲሳቸውም

የፍርዱ ቀን መጀመሪያ የሚዳኘው የሰውን ደም ማፍሰስ(#ግድያ) ወንጀል ነው  ብለዋል

አንድ ሰዉ በምስራቅ ያላግባብ #ቢገደልና በምእራብ የሚኖረዉ ሰዉ በዚህ ነገር ቢደሰት  የግድያዉ ተካፋይ ይሆናል. ኢማም አልመባቂር

Ramadan ረመዳን

07 Dec, 17:41


ከሞት በኃላ ያለ ፀፀት

የሰው ልጅ አላህ የሚለውን ባለመስማቱ ከሞት በኃላ በጅጉ ይፀፀታን;  ስራውንም ሲያ ምነው እነንትናን ጓደኛ አድርጌ  ባልሊያዝኩ; የስራ   መዝገቤብ ባልተሰጠኝ ይላል;  አፈር ሆኖ መቅረትንም ይመኛልሸ

«ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድም ባላጋራሁ» የሚል ኾነ፡፡ 18:42

ፊቶቻቸው በእሳት ውሰጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ፡፡ 33:66

«ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡ 25:28

እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡ 78:40

መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡ 69:25

በእሳትም ላይ በተቆሙ ጊዜ ምነው (ወደ ምድረ ዓለም) በተመለስን በጌታችንም አንቀጾች ባላስተባበልን ከምእምናንም በኾንን ዋ ምኞታችን! ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያሰደነግጥን ነገር ባየህ ነበር
)፡፡6:27

(የጀነት   ነዋሪዋች ይሏቸዋልም) «በሰቀር ሲኦል ውስጥ ምን አገባችሁ; (እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም
«ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡
«ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡
«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡ 74:42-46

ፀፀት የማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት አላህ ያዘዘንን መታዘዝ አላህን ያመፁ ሰዋች ስራቸውን በሚያዩበት  ጊዜ ሞት ቢኖር ኖሮ ከፀፀት ብዛት ይሞቱ ነበር

Ramadan ረመዳን

06 Dec, 18:07


(185) 💔ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡

(190) 🌓ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትና ቀንንም በመተካካት ለባለ አእምሮዎች በእርግጥ ምልክቶች አሉ፡፡

(191)🌍 (እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡

(192) 🔥«ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታገባውን ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሉዋቸውም፡፡»

(193) 💙«ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፡፡ አመንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤»

(194) 💙«ጌታችን ሆይ! በመልክተኞችህም ላይ ተስፋ ቃል ያደረግክልንን ስጠን፡፡ በትንሣኤ ቀንም አታዋርደን፡፡ አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና» (የሚሉ ናቸው)፡፡

(195) 💚ጌታቸውም «እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠሪን ሥራ አላጠፋም፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው፤ በማለት ለነርሱ ልመናቸውን ተቀበለ፡፡ እነዚያም የተሰደዱ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ በመንገዴም የተጠቁ የተጋደሉም የተገደሉም ክፉ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በእርግጥ አገባቸዋለሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ የኾነን ምንዳ (ይመነዳሉ)፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አልለ፡፡ »

(198) 💙ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ ለእነሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ከአላህ ዘንድ (የተሰጡ) መስተንግዶዎች አሏቸው፡፡ አላህም ዘንድ ያለው (ምንዳ) ለበጎ ሠሪዎች በላጭ ነው፡፡

(200)💙 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ታገሱ ተበራቱም፡፡  ተሰለፉም፡፡ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ 3:165 - 200

Ramadan ረመዳን

05 Dec, 18:24


🌾በዱኒ ውስጥ ሰዎች ገበያ ሄደው ሲመጡ ደክሟቸው አቧራ ለብሰው ጠወላልገው ተሽውደው መምጣት የተለመደ  ነው 
🌼በጀነት     ውስጥ ግን አርብ አርብ ሰዎች የሚወጡበት ገበያ አለ. ንፋስም ሸቶ በፊታቸውና በልብሳቸው ላይ በመነስነስ ክብራቸውንና ውበታቸውን ትጨምራለች. ወደቤታቸውም ሲመለሱ ውበታችሁ ጨምሯል ይባላሉ እነሱም ለቤተሰቦቻቸው የናንተም ጨምሯል ይሏቸዋል.

Ramadan ረመዳን

04 Dec, 17:41


🔥እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን #መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡

🔥 እናንተ የካዳችሁ ሆይ! ዛሬ አታመካኙ፡፡ #የምትመነዱት ያንን ትሠሩት የነበራችሁትን ብቻ ነው (ይባላሉ)፡፡

🔥 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ንጹሕ የኾነችን #ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፡፡ ጌታችሁ ከእናንተ ኀጢኣቶቻችሁን ሊሰርይላችሁ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ሊያስገባችሁ ያስባልና፡፡ አላህ ነቢዩን፣ እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት ቀን #ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲኾን «ጌታችን ሆይ! ብርሃናችንን ሙላልን፣ ለእኛ ምሕረትም አድርግልን፣ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና» ይላሉ፡፡ 66:6 8

Ramadan ረመዳን

03 Dec, 18:08


አንድ ቀን ጂብሪል(ዐ.ሰ) ያለወትሮው ረሱል  ﷺ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ መጣ።
ረሱል(ﷺ) በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ እኮ ተቀየሯል?" አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁበት ሰዐት አላህ(ሱ.ወ) የጀሀነም አቀጣጣዮችን እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት
ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም" ብሎ መለሰላቸው።
ረሱል (ﷺ)፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም🔥 ንገረኝ" አሉት።
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ
አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን /ጀሀነም ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም።
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.... የመርፌ ቀዳዳ ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር።
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ....ከጀሀነም ሰዎች ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር።
ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ....አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው መሬት ድረስ ይቀልጣል።
ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ👉በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ ነው። 7 በሮች አሏት።ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ መለሰላቸው።
ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ)፦"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?"
ብለው ሲጠይቁት
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር
ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት ያስኬዳል። እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል።የአላህ ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል። ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ ይታሰራል። እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል። ከዚያም
በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ ይመቷቸዋል። ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ መለሰላቸው.

Ramadan ረመዳን

02 Dec, 18:16


ሙዓዝ ኢብን ጀበል ለነብዩ  ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ

ጀነት አስገብቶ ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ አላቸው

እሳቸውም እንዲህ አሉ፦”
በእርግጥም ትልቅ ነገር ጠይቀሃል። ነገሩ ደግሞ አላህ ላቀለለለት ቀላል ነው

አላህን ምንም #ሳታጋራ ታመልከዋለህ።
ሶላትን ቀጥ አድርገህ ትሰግዳለህ።
ዘካን ታወጣለህ።
ረመዳንን ትጾማለህ።
የአላህን ቤት ትጎበኛለህ።  (ሃጅ)”  ከዚያም እንዲህ አሉ

“የመልካም በሮችን ላመላክትህ
ጾም ጋሻ ነው።

ሰደቃና በሌሊት የሚሰገድ ሶላት ደግሞ ልክ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው  ስህተትን ያጠፋሉ።”

ከዛም ይህንን አነበቡ “ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ፡፡

ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለገሳሉ፡፡ (16) ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ  የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡ (17)”
ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺴﺠﺪﺓ
ከዛም እንዲህ አሉ
“ስለ ነገሮች ሁሉ ራስ፣ ስለ ምሶሰው እና ስለ ሻኛው ጫፍ ምን እንደሆኑ አልነግርህምን
አዎን ንገሩኝ አለ።
ነብዩ   ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ

እንዲህ አሉ “ የነገራት ሁሉ ራስ እስልምና ነው።
ምሶሰውም ሶላት ነው።  የሻኛው ጫፍ ደግሞ ጅሃድ ነው።”

ከዚያም እንዲህ አሉ
“ይህንን ሁሉ  ጠቅልሎ የሚይዘውን አልነግርህምን

አዎን ንገሩኝ አለ።
ምላሳቸውን ያዙና “ይህንን ተጠንቀቅ” አሉ።

እኔም "በምንናገረው ነገር እንጠየቃለን እንዴ " አልኳቸው
እሳቸውም “እናትህ ትጣህና(እንዲከሰት ተፈልጎ አይደለም) ሰዎች በፊቶቻቸው እሳት ውስጥ  የሚወረወሩት በምላሳቸው ውጤት አይደለምን ? (ቲርሚዚይ )

Ramadan ረመዳን

01 Dec, 17:57


የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦

"ሙሳ አምላካቸውን፦ 'ከጀነት ሰዎች የመጨረሻ ዝቅተኛ የሆነው ሰው የሚያገኘው ደረጃ እንዴት ዓይነት ነው?' በማለት ጠየቁ። አላህም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ 'ይህ ሰው፥ ሰዎች ሁሉ ጀነት ገብተው ከጨረሱ በኋላ የሚመጣው ነው። 'ወደ ጀነት ግባ' ይባላል። 'ጌታዬ ሆይ! ሁሉም ሰዎች ማረፊያቸውን በያዙበት ሰዓት፣ የየድርሻቸውንም በወሰዱበት ሁኔታ እንዴት እገባለሁ?' ይላል። 'በምድረ ዓለም ውስጥ አንድ ንጉሥ የነበረውን ያህል ግዛት እንዲኖርህ ትፈልጋለህን?' ይባላል። 'ጌታዬ ሆይ! እፈልጋለሁ' ይላል። 'እርሱን እና እርሱን የሚያክል ሌላ ተሰጥቶሃል' ይባላል። በአምስተኛው 'አምላኬ ሆይ! ተስማምቻለሁ' ይላል። እስከሁን የተሰጠህን አሥር እጥፍ ታክሎልሃል። ነፍስህ የፈለገችው፣ ዓይኖችህን የሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ ይሰጡሃል' ይባላል። 'አምላኬ ሆይ! ተስማምቻለሁ' ይላል።

ሙሳም፦ 'ከፍተኛ ቦታ ያለው ሰው የሚያገኘው ደረጃስ?' በማለት ጠየቁ። አላህም ሲመለስ፦ 'የነርሱን ልዕልና በእጄ ሠራሁት፣ አሸግኩትም። (የሚጠብቃቸውን ድሎት) ዓይኖች አላዩትም፣ ጆሮዎችም አልሰሙትም፤ የሰዎች ልቦናዎችም አስበውት አያውቁም' ይላል።" (ሙስሊም)

ከናንተ አንዳችሁ ሲሞት ጠዋትና ማታ ማረፊያውን እንዲያይ ይደረጋል  የጀነት ሰው ከሆን ጀነት ውስጥ ቦታውን እንዲያይ ይደረጋል የጀሀነም ከሆነ የጀሀነም ቦታውን እንዲያይ ይደረጋል. ብሃሪ 3240

Ramadan ረመዳን

29 Nov, 18:26


እውነተኛዋ አገር

🗻ጀነት መልካምድሯ ገደል ጋራ የሌለበት ሜዳ የሆነች

🌈🌤አየር ንብረቷ የበረዶም ሆነ የሙቀት☔️ በረሃነት የሌለባት ፀሀይ ረፋድ ላይ ስትሆን ያለው አይነት አየር ሁሌ ያለበት

🚽🚿🛁ነዋሪዎቿ ንፍጥ የላቸው, ሽንት ቤት አይሄዱ የሚበሉት ነገር በላብ ይወጣል ላቡም እንደሽቶ ነው  ጠረኑ, ሴቶች ፔሬድ የላቸው

🙆🙆‍♀🙅‍♂ ሃሳብ, ጭንቀት, ወጥፎ ንግግር, መጣላት ; ጦርነት , ሀዘን, በሽታ,  እርጅና  የሌለበት አገር  ነው

  ? ?በሰዎች መካከል የሃሳብ ልዩትነት  የለም በውስጧ  ያሉ ሰዎች  ሁሉ እንደ አንድ ልብ የተስማሙ ናቸው     

አላህ እንዲህ ብሏል፦
"(ለነርሱስ) «ባሮቼ ሆይ! ዛሬ ቀን በእናንተ ላይ ፍርሃት የለባችሁም እናንተም የምታዝኑ አይደላችሁም»  (ይባላሉ)። እነዚያ በአንቀጾቻችን ያመኑና ፍጹም ታዛዦች የነበሩ (ባሮቼ ሆይ!)። «ገነትን ግቡ እናንተም ሚስቶቻችሁም ትደሰታላችሁ ትከበረላችሁ» (ይባላሉ)። ከወርቅ የኾኑ ሰፋፊ ዝርግ ሳሕኖችና ኩባያዎች በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ፡፡ በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት፣ ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አልለ፡፡ እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ። ይህችም ያቺ ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የተሰጣችኋት ገነት ናት።" (አዝ-ዙኽሩፍ፡ 68-72)

#ሐዲሥ  372 / 1881

አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ "ለደጋግ ባሮች ዓይኖች አይተውት፣ ጆሮዎች ሰምተውት የማያውቁት፣ በሰው ልጅ ልቦና ውስጥም ታስቦና ታልሞ የማያውቅን ጸጋና ድሎት አዘጋጅቼላቸዋለሁ፥ በማለት አላህ ተናግረዋል። ከፈለጋችሁ 'ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም ' የሚለውን የቁርአን አንቀጽ አንብቡ።" (አስ-ሰጀዳህ፡17) (ቡኻሪና ሙስሊም
)
 

 ⭐️በዱንያ ጉዳይ እንኳን ስኬታማ ለመሆን ከአዘናጊ ነገሮች በመራቅ ለዛ   ነገር ሙሉ ጊዜህ ማዋል ይጠይቃል.

🪐ታዲያ የህወትን ፈተና አልፎ ጀነት ለመግባት ከዘባራቂዎች ጋር ስዘባርቅ እየዋልን ጊዜያችን በማይጠቅመን ነገር አያሳለፍን ፀሀይ እስክትወጣ እየተኛን ይታሰባል እንዴ⁉️                         

Ramadan ረመዳን

28 Nov, 18:44


🏝🚅ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡   3:133

ገነት መቶ ደረጃዎች አሏት. በያንዳንዱ ተከታታይ ደረጃ መሃል ያለው እርቀት ልክ በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው እርቀት ነው... ቲርሚዚ 2531

«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)
የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡
ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡ 23:115-117

ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው!  38:27

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው
ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።

Ramadan ረመዳን

27 Nov, 18:50


የፍጥረት አለሙ ስፋት

ይህ ጉዳይ  ከግንዛቤ በላይ ነው ግን ትንሽ ለማስረዳት ልሞክር  እስቲ

በመኪና ስንጓዝ መቶ  ኪሎሜትር  በሰአት ከተጓዘ ስጋት አድሮብን ቀስበል  እንለዋለን
የመንገደኞች አውሮፕላኖች ከዚህ 10 እጥፍ ድረስ ፍጥነት(1000ኪሎሜትር በሰአት ይከንፋሉ) አላቸው ይህም ከባድ ፍጥነት ነው

በዚህ ፍጥነት የሚገጓ ፕሌን ወደ ፀሀይ ቢጓዝ ለመድረስ  ከ15 አመት በላይ  ይፈጅበታል

ይህ ፕሌን እኛ ካለንበት ጋላክሲ ጫፉ ላይ ለመድረስ  ከሁለት ቢሊየን አመት በላይ መጓዝ  አለበት    -  ይህ ፕሌን አደም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ጉዞ ላይ ቢሆን ኖሮ እስከ አሁን 1% እንኳን አልተጓዘም

ይህ ፕሌን በተለያዪ መሳሪያዎች እገዛ የሰው ልጅ  ማየት የቻለውን ፍጥረት አለም ጫፍ ለመድረስ የሚፈጅበትን ጊዜ  በቁጥር ለመግለፅ  ያን ያህል መጠን ያለው  ቁጥር ምን እንደሚባልም አላቀውም

ግን ከዚህ ፕሌን በአንድ ሚሊየን እጥፍ  ፍጥነት የሚጓዝ  በብርሀን ፍጥነት ማለት ነው 90 ቢሊዮን አመት ይፈጅበታል
   
ይህ ፍጥረት  አለም እጅግ ግዙፍ ከመሆኑ  የተነሳ  ለመግለፅ ራሱ ፈተና ነው

ለዚህም ነው ይህን ሁሉ የፈጠረው አላህ ከኔ ጋር ሌላን አካል ዝብን እንኳን መፍጠረ የማይችሉ እኩል አድርገህ  ብታመልክ አልምርም የሚለው

  
   (1 0) خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَاۖ وَأَلْقَىٰ فِى ٱلْأَرْضِ رَوَٰسِىَ أَن تَمِيدَ بِكُمْ وَبَثَّ فِيهَا مِن كُلِّ دَآبَّةٍۚ وَأَنزَلْنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَنۢبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ كَرِيمٍ
(11) هَٰذَا خَلْقُ ٱللَّهِ فَأَرُونِى مَاذَا خَلَقَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦۚ بَلِ ٱلظَّٰلِمُونَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
(12) وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا لُقْمَٰنَ ٱلْحِكْمَةَ أَنِ ٱشْكُرْ لِلَّهِۚ وَمَن يَشْكُرْ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِۦۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِىٌّ حَمِيدٌ

ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ፡፡ ከሰማይም ውሃን አወረድን፡፡ በእርሷም ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡

(11) ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡  31:10-11

Ramadan ረመዳን

25 Nov, 17:51


قال الرّسول -صلّى الله عليه وسلّم-: (لو كانتِ الدُّنيا تعدلُ عندَ اللهِ جناحَ بعوضةٍ ما سقى كافرًا منها شربةَ ماءٍ).[٣]
ረሱል ሰለላሁ አይሂ ወሰልለም እንዲህ ይላሉ  ዱንያ  አሏህ ዘንድ  የትንኝ  ክንፍ ያህል  ዋጋ ቢኖራት  ካፊሮችን  አንድ  ጉንጭ ውሃ እንኳን ባላጠጣቸው ነበር

የዝች አለም  ድርሻ ከቀጣዮ አለም አንፃርክ ልክ አንድ ሰው ጣቱን ባህር ውስጥ  ከቶ ሲያወጣው  ይዞት እንደወጣው ውሀ ነው.     


Al-Kahf 18:109

قُل لَّوْ كَانَ ٱلْبَحْرُ مِدَادًا لِّكَلِمَٰتِ رَبِّى لَنَفِدَ ٱلْبَحْرُ قَبْلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَٰتُ رَبِّى وَلَوْ جِئْنَا بِمِثْلِهِۦ مَدَدًا

«ባሕሩ ለጌታዬ ቃላት (መጻፊያ) ቀለም ቢሆን ኖሮ  የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባሕሩ ያልቅ ነበር እንደው  ሌላ ተጨማሪ ባህር ብናመጣ  እንኳን   » በላቸው፡፡   

Ramadan ረመዳን

24 Nov, 17:51


ሀሳቡ ሁሉ ዱኒያ ብቻ የሆነ

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿من كانت الدُّنيا همَّه، فرَّق اللهُ عليه أمرَه، وجعل فقرَه بين عينَيْه، ولم يأْتِه من الدُّنيا إلّا ما كُتِب له، ومن كانت الآخرةُ نيَّتَه، جمع اللهُ له أمرَه، وجعل غناه في قلبِه، وأتته الدُّنيا وهي راغمةٌ﴾

“ሀሳቡና ጭንቁ ዱኒያ የሆነ ሰው፣ አላህ ጉዳዩን ይበታትንበታል። ድህነቱን በአይኑ መሀል ያደርግበታል። ከዱኒያ የተወሰነለትን እንጂ አያገኝም። ሀሳቡና ጭንቀቱ አኼራ የሆነ፣ መብቃቃትን በልቡ ያደርግለታል። ጉዳዩን ይሰበስብለታል። ዱኒያ የግዷን ወደሱ ትመጣለታለች።”
ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 950

وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِى فَإِنَّ لَهُۥ مَعِيشَةً ضَنكًا وَنَحْشُرُهُۥ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَعْمَىٰ

«ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን፡፡  20:124

ነብዮ ﷺ ይህን ዱአ ያዘመትሩ ነበር

رَبَّنَآ ءَاتِنَا فِى ٱلدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِ ٱلْءَاخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ

ከእነርሱም ውስጥ፡- «ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱም አገር ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ሰዎች አልሉ፡፡   2:201

Ramadan ረመዳን

23 Nov, 18:36


ገንዘብ ይመጣል ይሄዳል፥ ውበትም  እየጠወለገ ይጠፋል፥ ጤናም በግዜ ብዛት ይሸረሸራል. ይችም አለም እስከነ ግርግሯ አላፊ ናት. ለአላህ ተብሎ የተሰራ መልካም ስራ ብቻ እስከወዳኛው ይዘልቃል.

ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
"ብልጥ ሰው ብሎ ማለት ራሱን  (ነብሱን) የሚገመግምና ከሞት ብኋላ ላለው ህይወቱ መልካም ስራ የሚስራ ሲሆን ሞኝ ብሎ ማለት ስሜቱን የሚከተልና አላህን በባዶ ተስፋ የሚያደርግ ነው" (ቲርሚዚ)

የደጋግ  ሰዎች ስለ ዱንያ

🌹ወህብ ኢብኑ ሙነበህ (ረሁ) እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ ለብልሆች መስሪያ አገር ናት፡፡ መሃይማን ደግሞ በሷ ላይ ተዘናግተዋል፡፡ ከሷ እስኪለቁ ድረስ ስለሷ ምንም አላወቁም፡፡ ወደኋላ ለመመለስ ፈልገው ቢጠይቁም መመለስ አልቻሉም፡፡›

🌹 አል-ሐሰን አል-በስሪ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-  
‹አራት ነገሮች የዕድለ ቢስነት ምልክቶች ናቸው፡፡ የቀልብ መድረቅ፣ የዐይን እንባ ማጣት፣ ረጅም ምኞት እና በዱንያ ላይ ለመቆየት መስገብገብ፡፡›

🌹ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- 
‹ለዱንያ ባለህ ሀሳብና ጭንቀት ልክ ለአኺራ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡ ለአኺራ ባለህ ጭንቀት ልክ ለዱንያ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡›

🌹ሰዕድ ኢብኑ መስዑድ  ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አንድ ሰው ዱንያው ስትጨምርና አኺራው ስትቀንስ እሱም ይህን ሁኔታውን ወዶ የሚኖር መሆኑን ካየህ የዚህ ዓይነቱ ሰው የተታለለና ሳያውቅም በራሱ የሚጫወት መሆኑን እወቅ፡፡›

🌹ከሢር ኢብኑ ዚያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- 
‹ዱንያችሁን በአኺራችሁ ሽጡ፡፡ ወላሂ ሁለቱንም ታተርፋላችሁ፡፡ አኺራችሁን በዱንያ አትሽጡ ወላሂ ሁለቱንም ትከስራላችሁ፡፡›

🌹ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡- 
‹ልጄ ሆይ! ወደዚህች ምድር ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ ለዱንያ ጀርባህን እየሰጠህ ነው፡፡ አኺራ ደግሞ እየመጣች ነው፡፡ አንተም ርቆ ከሄደው ይልቅ እየቀረበ ላለው ቅርብ መሆንህን አስተውል፡፡›

Ramadan ረመዳን

22 Nov, 18:43


ዱንያ ምናባቱ

የዝችም ምድር ህይወት ዛዛታና ጫዋታ ናት አለ ለዚህ ጥሩ ማሳያ  ብዙ ጥረው ግረው ረጅም አመት በትምህርት ለፍተን በተለይ እዚህ  ሀገር የሚከፈለው ለመኖር እንኳን  በቂ አይደለም  ግን ለሚቀልዱ ለሚጫወቱ ሰዎች ከፍተኛ ክፍያ ያገኛሉ እንደ ዘፋኘ ኳስ ተጫዋች  ብዙ ሚሊዮን ይከፈላቸዋል  ሰሞኑን እንኳን  ታይሰን
ቦክስ ግጥሚያ አካሂዶ 20 ሚሊዮን ዶላር  ተከፍሎታል ለዛውም ተሸንፎ,   ስንቱ በተለያየ  መስክ እድሜውን ሙሉ ለፍቶ ይህን ያህል ገንዘብ አላገኙም   …  ታዳ ዱንያ የቀልድ አገር አይደለችም ትላለህ

وَمَا هَٰذِهِ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَآ إِلَّا لَهْوٌ وَلَعِبٌۚ وَإِنَّ ٱلدَّارَ ٱلْءَاخِرَةَ لَهِىَ ٱلْحَيَوَانُۚ لَوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ

ይህችም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ሕይወት አገር ናት፡፡ የሚያውቁ ቢኾኑ ኖሮ፤ (ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር)፡፡  29:64

Ramadan ረመዳን

21 Nov, 18:21


እንዲሁ  ሞልቶ ለማይሞላ ዱንያ  እንደሮጥን  ቀኑ በሳምንት ሳምቱም በወር ወሩም  አመት ያስከተለ  አንድ ቀን እንኳን ሳንረጋጋ  የተሰጠን ጊዜም  ወደ ማለቂያው እየበረረ   ይገኛል, ረመዳንም ከመቶ ቀን ያነሰ ይቀረዋል
 
አንድም ቀን ቁርአን ቀርተን ላናቅ እንችላለን በሳምንት አንድ ግዜ  እንኳን  ጅምአ  ሱረቱል ካህፍ ብንቀራ

አንድም ቀን ሱብሂ  በጀመአ ላንሰግድ እንችላለን በሳምንት አንድ ግዜ  እንኳን  ጅምአ ሱብሂን በጀመአ  እንዴት ያቅተናል

አንድም ቀን ምድር ላይ በዋናነት የምንኖርለትን አላማ  ገምግመን ወይም ተሳስበን  ላናቅ እችላለን   በሳምንት    አንድ ግዜ  እንኳን  ጅምአ
ከአስር እስከ መግሪብ እናስተንትን ተፈኩር    እእቲካፍ  እናድርግ

Ramadan ረመዳን

20 Nov, 18:07


🪐ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡67:2
🪐«ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው፡፡62:8

Ramadan ረመዳን

19 Nov, 18:21


"ድንቅ ታማኝነት" በአንድ ወቅት ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረዲየላሁ አንሁ) ተቀምጦ እያለ ሁለት ወጣቶች አንድን የገጠር ሰው እየገፈታተሩ ይዘው መጥተው ዑመር (ረዲየላሁ አንሁ) ፊት ለፊት አቆሙት፡፡ ዑመርም “ምንድን ነው አላቸው?”

ወጣቶችም “የሙእሚኖች መሪ ሆይ! ይሄማ አባታችንን ገድሎ ነው፡፡ ”አሏቸው፡፡ ዑመርም (ረዲየላሁ አንሁ) ወደ ሰውየው ዘወር ብለው “አባታቸውን ገደልክባቸውን?” ሲሉ ጠየቁት ሰውየውም “አዎ ገደልኩት” ሲል
መለሰላቸው፡፡ “እንዴት ገደልከው?” ሲሉ ደግመው ጠየቁት “መሬቴ ላይ ከነግመሉ ገባ፡፡ እንዲከለከል ነገርኩት መከልከል አልቻለም፡፡ ዱላ ስወረውርበት ድንገት ጭንቅላቱ ላይ አረፋና ገደልኩት” አላቸው፡፡ ዑመር (ረዲየላሁ አንሁ) “ነፍስን ያጠፋ ነፍሡ ይጠፋል፤ ስለዚህም አባታቸውን እንደገደልክ ትገደላላህ” አሉት፡፡

ሰውዬውም እንዲህ አላቸው “ምድርን ያለምሰሶ ባቆመው አምላክ እለምንሃለሁ አንዲት ሌሊት እንድትተወኝ፤ ወደ ገጠር ሄጄ ለባለቤቴና ለልጆቼ እንደምገደል ነገሬያቸው ልመለስ ፡፡ በአላህ ስም
እምላለሁ ከአላህ ውጭ ረዳት የላቸውም ከዚያም እኔ” አላቸው ፡፡ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረዲየላሁ) “አንተ ገጠር ሂደህ እስክትመለስ ማነው ተያዥ(ዋስ)
የሚሆንህ?” አሉት፡፡ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች ሁሉ ፀጥ አሉ፡፡ ስለእርሱ
ምንም የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ስሙን አያውቁ፣ ቤቱን አያውቁ፣ ዘሩን
አያውቁ… እንዴት ተያዥ ይሁኑት! ተያዥነቱ የጥቂት ገንዘብ… የመሬት…
አሊያም ደግሞ የእንስሳ አይደለም፡፡ ተያዥነቱ (ዋስትናው) የነፍስ ጉዳይ
ነው፡፡ አንገትን በሠይፍ የመቀላት ተያዥነት (ዋስትና)! ፤ ሰዎቹ ዝም እንዳሉ ነው፡፡ ዑመር (ረዲየላሁ አንሁ) ልዩ ስሜት ውስጥ ተዘፍቀው ውሳኔ መስጠት አቅቷቸዋል፡፡ ሰውየው ላይ ፈጣን ውሳኔ ሠጥተው እንዲገደል ቢያደርጉ እዚያ
ልጆቹ በርሃብ ይሙቱ ማለት ነው፡፡ ያለተያዥ ለቅቀውት እንዳይሄድ የተገዳይ
ቤተሠቦችን የደም መብት ማጓደል ነው… ምን ያድርጉ .. ግራ በተጋባ መንፈስ ውስጥ ናቸው ዑመር (ረዲየላሁ) ፡፡ ጀምዓው አሁንም ፀጥ እንዳለ ነው፡፡
ዑመርም አቅርቅረዋል፡፡ ቀና ብለው ወደ ወጣቶቹ ተመለከቱና “ይቅርታ
ታደርጉለታላችሁ? አፉ ትሉታላችሁን?” አሏቸው፡፡ “በፍፁም!” አሉ ወጣቶቹ
“አባታችንን የገደለማ የግድ መገደል አለበት እንጂ ያ አሚረል ሙእሚኒን…
የምን ይቅርታ ነው …” ዑመር አሁንም ተስፋ አልቆረጡም “ይህን ሰው ማን
ነው ተያዥ የሚሆነው… ማነው የሚዋሠው?” አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ አቡ ዘር
አልጊፋሪ ብድግ ብለው “እኔ እዋሠዋለው! እኔ ተያዥ እሆነዋለሁ!” አሉ፡፡
ዑመር (ረዲየላሁ አንሁ) “ግድያ ነው፡፡” አሏቸው፡፡ “ግድያ ቢሆንም” አሉ አቡ ዘር፣
ዑመር “ታውቀዋለህ?” ሲሉ ጠየቋቸው ፡፡ “አላውቀውም” አሉ አቡ ዘር፡፡
“እንግዲያ እንዴት ዋስ (ተያዥ) ትሆነዋለህ?” አሉቸው ዑመር “በፊቱ ላይ
የሙእሚን ባህሪ ተመልክቻለሁ፣ አይዋሽም ቃሉንም ይሞላል ኢንሻአላህ
አሉ፡፡ ” ዑመር (ረዲየላሁ አንሁ) “ያ አባ ዘር ሆይ! ከሦስት ቀን ካለፈ ዑመር ይተወኛል ብለህ ታስባለህ?!” “አላህ ይብቃኝ (አላሁል ሙስተአን)” አሏቸው ዑመርን

ሰውየው እራሱን እንዲያዘጋጅና ቤተሰቦቹን እንዲሰናበት ከእርሱ በኋላ
ሁኔታቸውን እንዲያስተካክል ሦስት ቀን ተሠጥቶት ሄደ ፡፡ ተመልሶ ቅጣቱን
ሊቀበል ይመጣል፤ ምክንያቱም ግድያ ነውና፡፡ ከሦስት ቀን በኋላ ዑመር
ቀጠሮውን አልረሡትም፡፡ አሱር ላይ የከተማው ሰው እንዲሠባሰብ አዘዙ፡፡
ወጣቶቹም መጡ ሰውም ተሠባሰበ፡፡ አቡዘርም ዑመር ፊት ለፊት ተቀመጡ
ዑመር (ረዲየላሁ ) “ሠውየው የት አለ?” አሉ፡፡ “አላወቅኩም የሙእሚኖች መሪ
ሆይ!” አሉና አቡዘር ወደ ፀሃይዋ መመልከት ጀመሩ፡፡ ፀሃይዋም ከተለምደ
ውጭ እጅግ ፈጥና የምትሄድ ሆና ታየቻቸው፡፡ ልትጠልቅ ጥቂት ሲቀራት
ሠውየው ብቅ አለ ዑመር (ረ.አ ) በደስታ አላሁ አክበር አሉ፡፡ ሙስሊሞችም
አብረዋቸው አላሁ አክበር አሉ፡፡ ዑመር (ረዲየላሁ) “ወይ አንተ ሰው ስለአንተ
አናውቅ፣ አገርህን አናውቅ፣ እዛው በትቀር ምን ይውጠን ነበር? ቃልህን
አክብረህ ለመገደል መጣህ?” አሉት

“አንቱ የሙእሚኖች መሪ ሆይ! አንቱን
ብዬ ሳይሆን ሚስጥርና የተደበቀን ሁሉ የሚያውቀው ጌታ ከበላይ አለብኝ
ብዬ ነው፡፡… ተመልከት ያ አሚረል ሙእሚኒን ልጆቼን እንደ በራሪ ጫጩት
ውሃ የላቸው፣… ዛፍ የላቸው፣… እንዲሁ ጥያቸው ነው ለመገደል የመጣሁት… ከሰዎች ዘንድ ቃላቸውን መሙላት ተወግዷል እንዳይባል ሰግቼ
ነው፡፡” አለ፡፡ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.አ.) “ለምን ተያዥ (ዋስ) ሆንከው?”
ሲሉ አቡ ዘርን ጠየቁት፡፡ “ከሠዎች ዘንድ መልካም የሚሠራ ጠፋ እንዳይባል ሠጋሁ” አሉ አቡ ዘር፡፡ ዑመር (ረዲየላሁ) ቆሙና ወጣቶቹን “ምን ትላላችሁ?” አሏቸው፡፡ ወጣቶቹም እያለቀሱ “ይቅር ብለነዋል፡፡ ቃሉን ለማክበሩና ለእውነተኝነቱ” አሉ… እንዲህም አከሉ “ከሠዎች ዘንድ ይቅርታ ማድረግ አፉ መባባል ተወገደ እንዴ እንዳይባል ሠጋን” አሉ፡፡ ዑመር (ረዲየላሁ) “አላሁ አክበር!” አሉ፡፡ እንባቸው ፂማቸው ላይ ይንጠባጠብ ነበር…
ሱብሃነላህ !

Ramadan ረመዳን

18 Nov, 18:46


1.🔷ያ ፉርቃንን(ቁርኣን)  በባሪያው ላይ   ለዓለማት አስጠንቃቂ  ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡ 
2.🔹(እርሱ) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ የኾነ፣ ልጅንም ያልያዘ፣ በንግሥናውም  ተጋሪ የሌለው፣ ነገሩንም ሁሉ የፈጠረና በትክክልም ያዘጋጀው ነው፡፡
3.🔹(ከሓዲዎች) ከእርሱም ሌላ ምንንም የማይፈጥሩን፣ እነርሱም የሚፈጠሩን፣ ለነፍሶቻቸውም ጉዳትን ለመከላከል ጥቅምንም ለማምጣት የማይችሉን ሞትንና ሕይወትንም መቀስቀስንም የማይችሉን፣ አማልክት ያዙ፡፡
4.🔹እነዚያም የካዱት ይህ (ቁርኣን ሙሐመድ) የቀጠፈው በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም አሉ፡፡ በእርግጥም በደልንና እብለትን ሠሩ፡፡          
5.🔹አሉም «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት፡፡ አስጻፋት፡፡ እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች፡፡»    
6.🔹 «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡
25.🔹ሰማይም በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትም መወረድን የሚወርድበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
26.🔹እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልራሕማን ብቻ ነው፡፡ በከሓዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡                 
27.🔹 በዳይም «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
28.🔹 «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡
 29.📣 (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)፡፡ ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው፡፡(25:29)⁉️

Ramadan ረመዳን

17 Nov, 18:02


የነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ሚናና ተልዕኮ

ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ለመላው የሰው ዘር የተላኩ የመጨረሻው ነቢይ እንደመሆናቸው መጠን ተልዕኮዋቸው በሚከተሉት አበይት ነጥቦች ላይ ያተኩራል :;

🌴በማንኛውም መልኩ እና ትርጓሜው አምላክ ፍፁም አንድ ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ :: ማለትም የሰው ልጅ የጌታውን ፍፁም አንድነት እንዲገነዘብ እና መለኮታዊውን መመሪያም በሁሉም የሕይወት መሥኮች ተግባራዊ በማድረግ

ለፈጣሪው ተገዢነቱን ማረጋገጥ በአንፃሩም ከአንዱ አምላክ ውጭ ለማንም ለምንም ኀይል አለማጎብደድ አለመስገድ

🌴የሰው ልጆችን ሁሉ እኩል ወንድምማማቾች የመሆናቸውን ጉዳይ በተግባር መተርጎም ለወደፊቱም ይህንን ሐቅ በአስተማማኝ መሠረት ላይ ማስቀመጥ

🌴 በሁሉም መሥክ የተሟላውንና እንከን የለሹን መለኮታዊ የሕይወት ፈር : ኢስላምን : ለመላው የሰው ዘር ማስተዋወቅ : በተግባርም ሰርቶ ማሳየት ::

🌴የመጨረሻ መለኮታዊ መልዕክት የሆነውን ቁርኣንን ለሰው ልጆች ማስተላለፍ

🌴ይህ መልዕክት ; ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ያመጡት መልዕክት : ከተልዕኮው ስፋት እና ሁለንተናዊነት የተነሣ የዘርም ይሁን የቋንቋ ወይም የፓለቲካ ድንበሮች አይገድቡትም ::

ነቢዩ ሙሐመድም. (ﷺ) የተላኩት ለመላው የሰው ዘር እንጂ : እንደ ቀደምቱ ነቢያት ለአንድ አካባቢ ሕዝብ : ወይም ለአንድ ዘር ብቻ አይደለም :: ቁርአን የሚመሰክረውም ይህን ሐቅ ነው

" ... ለሰዎች ሁሉ መልዕክተኛ ኾነህ ላክንህ : መስካሪም በአላህ በቃ ::" (አል - ኒሳእ : 79)

"(ሙሐመድ ሆይ ) ! ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አላክንህም ::"
( አል - አንቢያ : 107)

" አንተ ነቢዩ ሆይ ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን ላክንህ :: ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ : አብሪ ብርሃንም ( አድርገን ላክንህ )" (አል - አሐዛብ : 45 - 46 )

የሰው ልጅም የነቢዩ ሙሐመድን (ﷺ) መልዕክት ከልብ ተቀብሎ እንዲተገብር ቁርኣን ይመክራል :; ይህው ነው የህይወት ትርጉምም, መንገድም

"እናንተ ሰዎች ሆይ ! መልዕክተኛው እውነትን ከጌታቹሁ አመጣላቹሁ : እመኑም : ለናንተ የተሻለ ( ይኾናል ) :
ብትክዱም ( አትጎዱትም ) : በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና : አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው
"( አል - ኒሣእ : 170 )

"ሙሐመድ : ... የአላህ መልዕክተኛ እና የነቢዮችም መደምደሚያ ነው ::
(አል - አህዛብ : 40)

" መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ ... "(አል - ኒሳእ : 80)

ሙሀመድ ሆይ :--

«እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ ካህፍ 18 :110

Ramadan ረመዳን

16 Nov, 18:22


☞እራስህን ፈትሽ/ሺ

📚ሱፍያን ኢብን ዑየይና ፦

"ቀኔ የሞኞች አይነት ከሆነ፣ ለሊቴ የጃሂሎችን ከመሰለ በተማርኩት ዒልም ምን ተጠቀምኩ!?"

[አኽላቁል ዑለማ ሊል ኣጁሪይ (44)]

☞ሸይኽ ዐብዱረዘቅ አል በድር፦

☞ይህ ጣሊበል ዒልም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ታላቅ ምክር ነው። ሰለፎች የተማሩት እውቀት በተግባራቸው ላይ ይስተዋል ነበር። እውቀታቸው በዒባዳቸው፣ በማህበራዊ ህይወታቸውና በስነምግባራቸው ላይ ይንፀባረቃል።


☞ልኩን ያወቀ ሰው አላህ ይዘንለት!

»»»ታላቁ የሙስሊሞች ኸሊፋ የነበረው ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዐዚዝ ልጁ በአንድ ሺህ ዲርሀም የጣት ቀለበት እንደገዛ ሰማ። ወዲያውኑ ይህን ደብዳቤ ፃፈለት!

"በአንድ ሺህ ዲርሀም የጣት ቀለበት እንደገዛህ ሰምቻለሁ። ይህን ቀለበት ሽጠህ አንድ ሺህ የተራቡ ሰዎችን መግብበት። ለራስህ የነሀስ ቀለበት ግዛና በቀለበቱ ላይ "ልኩን ያወቀ ሰው አላህ ይዘንለት" ብለህ ፃፍበት!" አለው.

Ramadan ረመዳን

14 Nov, 17:54


   ድንቅ ታሪክ

በሙሳ ዐ.ሰ ዘመን ነው....አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው ለዘመናት በችግር እና በረሀብ የኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ።

      ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዘመናት በሰብር አሳልፈዋል...። እናም አንድ ቀን እቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ ሚስት ለባለቤትዋ፦"ሙሳ አላህን ማናገር የሚችል ነቢይ ነው አይደል?" ብላ ትጠይቀዋለች።

 እሱም፦"አዎን" ይላታል። "ታዲያ ለምን እሱጋ ሄደን ስለ ሁኔታችን አንነግረውም አላህንም ስለኛ ያናግረው ሀብታም እንዲያረገን ቀሪ ህይወታችንን በድሎት እንድንኖርም ይጠይቅልን።" አለችው።
ባልም በሚስቱ ሀሳብ ይስማማና ሌሊቱ እንደነጋ ጉዞ ወደ ሙሳ ዐ.ሰ ቤት ጀመሩ። ሙሳንም ዐ.ሰ አገኟቸው። ስለድህነታቸው ነግረዋቸውም በዚህ ጉዳይ እሳቸው አላህን እንዲለምኑላቸው ጠየቋቸው።

 ሙሳም ዐ.ሰ አላህን ለመኑላቸው። አላህም፦"ሙሳ ሆይ! እኔ እነዚህን ሰዎች በችሮታዬ ለአንድ አመት ያህል ሀብታም አደርጋቸዋለሁ አንድ አመት ካለፈም ወደነበሩበት ድህነት እመልሳቸዋለሁ።" ብሎ መለሰላቸው።

  እሳቸውም ጥንዶቹ ጋ በመሄድ አላህ ዱዓቸውን ሙስተጃብ እንዳደረገላቸው ሀብታምም እንደሚሆኑ ነግረዋቸው እናም ግን ለአንድ አመት ብቻ እንደሚቆይ አክለው ነገሯቸው። እነዚህ ምስኪኖችም የሰሙትን ማመን ተሳናቸው። በአጭር ግዜ ውስጥ ካለሰቡበት መንገድ ሀብታም መሆን ጀመሩ።ማንም ከሚኖረው የተሻለ ኖሮ መኖርም ጀመሩ።

እናም አንድ ቀን ይህች ብልህ ሚስት ለባሏ እንዲህ አለችው፦"ይህ ፀጋ ይህ ድሎት ለአንድ አመት ብቻ እንደሚዘገይ ታውቃለህ አይደል? ስለዚህ በዚህ ንብረታችን አንድ መልካም ስራ እንስራ" ባልይውም በሀሳቧ ይስማማል።

ከዚያም በከተማዋ ግንባር ቦታ ላይ አደባባይ መልክ አንድ ትልቅ ቤት ይገነቡና 7 በር አበጁለት። ለሰውም መተላለፊያ ሰሩ። ቤቱ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እዛ ቤት ውስጥ ምግብ እያዘጋጁ ለአላፊ አግዳሚ ጠዋት ማታ ምግብ ይቀልቡ ጀመር...። በዚህ ሁኔታ ሳሉ ወራት አስቆጠሩ።

ሙሳም በትኩረት ይከታተሏቸው ነበር። ማይደርስ ቀን የለምና ያ የተወሰነላቸው ቀን ቀጠሮውን ጠብቆ ከች አለ። እነሱ ግን የቀጠሮ ቀኑ ሁላ ትዝ አላላቸውም በስራቸው ተጠምደዋል። ያ ቀጠሮ ቀናቸው አለፈ እነሱ ግን ያው ናቸው ምንም አልቀነሱም ብቻ በስራቸው ተጠምደዋል....

ሙሳም ዐ.ሰ ባዩት ሁኔታ ተገርመው፦ "ያ ረብ ቃል የገበኽላቸው ለ አንድ አመት ሆኖ ሳለ እንዴት እስካሁን እልደኸዩም?" ብለው አላህን ጠየቁ። /እዚጋ እሳቸው ሰዎቹን ተመቃኝተው ሳይሆን የአላህን ሂክማ ለማወቅ ነው የጠየቁት/

ቸር የሆነው አላህም፦ "ሙሳ ሆይ! ለነዚህ ጥንዶች ከፀጋ በሮቼ አንዲትን በር ስከፍትላቸው...እነሱ ደሞ 7 በር ከፍተው ባሪያዎቼን መቀለብ ጀመሩ። ሙሳ ሆይ! እነሱ ይሄን ሲያረጉ አይቼ የከፈትኩላቸውን በር መዝጋት ከበደኝ"አለው።

Ramadan ረመዳን

13 Nov, 18:51


ሴት ልጅ

ﻭَﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﻭَﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨَﺎﺕُ ﺑَﻌْﻀُﻬُﻢْ ﺃَﻭْﻟِﻴَﺎﺀُ
ﺑَﻌْﺾٍ ۚ ﻳَﺄْﻣُﺮُﻭﻥَ ﺑِﺎﻟْﻤَﻌْﺮُﻭﻑِ ﻭَﻳَﻨْﻬَﻮْﻥَ ﻋَﻦِ
ﺍﻟْﻤُﻨْﻜَﺮِ
”ኣማኝ ወንዶችና ኣማኝ #ሴቶች ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው በመልካም ያዛሉ ከመጥፎ የከለክላሉ።” (ሱራ 9:71)

ነብዩ. (ﷺ)  ግን “ከአማኞች ኢማኑ(እምነቱ) የተሟላው ስነ ምግባሩ ያማረው ነው፡፡ ከናንተ በላጫቻችሁ #ለሴቶቻቸው በላጭ የሆኑት ናቸው” ብለው ነበር፡፡ [አስሶሒህ፡ 284]

ረሱል (ሰዐወ)  እንዲህ አሉ                    #ሴትን ልጅ #የሚያልቅ ሰው የለም እርሱ #የላቀና የተከበረ ሰው ቢሆን እንጂ

#ሴትን #የሚያዋርድ ሰው የለም እርሱ #የተዋረደ ሰው ቢሆን እንጂ ።

Ramadan ረመዳን

12 Nov, 18:15


*WISDOM FOR WOMEN👩🏻👩🏻‍🦱👵🏻*

1. A First Class degree won't make you a first class wife, rather, your submission and respect will.

2. The woman who respects her husband is the best wife anyone would ever have.

3. Your character and attitude will go a long way in determining whether your husband will wish he never regret getting married to you.

4. To be a great wife, you need more anger management skills than nagging skills.
,,,
5. Be a leader at work or anywhere else, but be a companion at home... it's wisdom.

6. Don't compete with your husband, complement him.

7. Your strength is in humility and submission, not in strife and contention.

8. Be tender, every man respect a tender woman but firm.

9. Never punish your husband by starving him of food or sex, he may be forced to get it outside.

10. There is nothing wrong in accepting that you are wrong when you are wrong.

11. Prepare to forgive your husband if he wrongs you. For a forgiving wife is better than a vengeful wife.

12. Make a decision to be a good wife, you will need it in the long run.

የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል

ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሰላቷን (በትክክል) ከሰገደች፣ የረመዷን ፃም ከፃመች፣ ብልቷን ከዝሙት ከጠበቀችና ባሏንም (በመልካም) ከታዘዘች ከጀነት በሮች በፈለግሽውን መርጠሽ ግቢ ትባላለች። (ኢብኑ ሂባን)

Ramadan ረመዳን

11 Nov, 18:44


“ሦስት ሰዎች ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ቤቶች መጡና ስለ አምልኮአቸው ሁኔታ ጠየቁ። በተነገራቸውም ጊዜ ሁኔታውን ለማሣነስ ሞከሩ። እንዲህም አሉ። ‘ታዲያ እኛ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንፃር የት ነን። በርግጥ እርሣቸው የቀደመውም ሆነ የቀረው ሀጢዓታቸው ሁሉ ተምሮላቸዋል።’ ካሉ በኋላ አንደኛቸው ‘እኔ እድሜዬን በሙሉ ለሊቱን እሰግዳለሁ።’ አለ። ሁለተኛው ሰው ‘እድሜ ልኬን እፆማለሁ። ፈፅሞ አላፈጥርም።’ አለ። ሦስተኛው ደግሞ ‘እኔ ከሴቶች እርቃለሁ። ፈፅሞ አላገባም።’ አለ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መጡ። ‘እናንተ ናችሁ ወይ እንዲህ እንዲያ ያላችሁት?’ በማለት ጠየቋቸው። በማስከተልም ‘ወላሂ እኔ ከናንተ ይበልጥ አላህን ፈሪ እና ጠንቃቃ ነኝ። ነገርግን እፆማለሁ አፈጥራለሁ፤ እሰግዳለሁ እተኛለሁ፤ ሴቶችንም አገባለሁ። ከኔ መንገድ ያፈነገጠ ከኔ አይደለም።’ አሏቸው።”   ቡኻሪና ሙስሊም

ሳውዲአረቢያ ለአዲስ ተጋቢዎች  ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ትሰጣለች , ትውልዱን ከዝሙት ለመጠበቅ እንደዚህ አይነት ነገሮች ማመቻቸት ያስፈልጋል

Ramadan ረመዳን

10 Nov, 18:15


አብደላህ ብኑ ኡመር(ረ ዐ) እንዲህ አሉ ፣  አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ ﷺ ወደ  እኛ ዞሩና እንዲህ አሉን " …

🔥— ብልግና በህዝቦች መሀል በአደባባይ አይስፋፋም አላህ በነሱ ላይ ወረርሽኝ በሽታ ያመጣባቸው ቢሆን እንጂ ፣ እንዲሁም ከነሱ በፊት በነበሩ ህዝቦች ያልነበሩ በሽታዎች የሚመጡ ቢሆን እንጂ

🔥— ሰዎች ሚዛንንና ስፍርን አያጎድሉም በድርቅ፣ በቸነፈር እና በባለስልጠን አምባገነንነት ቢፈተኑ እንጂ

🔥— ሰዎች ከሀብታቸው ዘካን አይከለክሉም ከሰማይ ዝናብን የተከለከሉ ቢሆን እንጂ ፣ እንስሳዎች ባይኖሩ ኖሮ አንድም አይዘንብላቸውም ነበር

🔥— የአላህንና የመለእክተኛውን ቃል አይጥሱም በውጭ ጠላት የተወረሩና ከይዞታቸውም የሚወስዱባቸው ቢሆን እንጂ

🔥— መሪዎቻቸው በአላህ ባወረደው ኪታብ ካልመሩና  አላህ ከወረደው መመሪያ የሚመቻቸውን ብቻ አይመርጡም አላህ ጦርነትን በመሀላቸው የሚያደርግባቸው ቢሆን እንጂ

Ramadan ረመዳን

08 Nov, 19:25


የሙሳ ጎረቤት በጀነት

ነብዩ ሙሳ  አላህን በጀነት ውስጥ ጎረቤቴን አሳየኘ ብለው ጠየቁ  አላህም አላቸው ባለህበት ቦታ ሆነህ   ወዳንተ መቶ በአጠገብህ የሚያልፈው ሰው ጎረቤትህ ነው አላቸው. ሙሴም ማን ወደሳቸው መቶ እንደሚያልፍ ጥቂት ከጠበቁ በኃላ የሆነ ወጣት መቶ በአጠገባቸው አለፈ ከዛም ሙሳ የት እንደሚኖር  ለማወቅ  ተከተሉት.

ከተከታተሉት ብኃላ ወደሆነ  አጠር  ያለ  የደሀ   ቤት ሲገባ ተመለከቱት  ከውጭም ሆነው ይከታተሉት ጀመር, ልጁም  በእድሜ የገፉ ሴት ተሸክሞ ወንበር ላይ አስቀመጣቸው  ከቦርሳውም የሆነ ነገር አውጥቶ ሰጣቸው ነብዩ ሙሳም በአትኩሮት  ይከታተሉት ጀመር.

በልታ ከጨረሰችም ብኃላ ውሃ ሰጣት ከዛም እጆን ወደ ላይ አንስታ ዱአ አደረገች ሙሳም ስለምን ዱአ እንዳደረገች አልተሰማቸውም ነበር
ግን እንቅስቃሴዋን ከውጭ ሆኖ ያይ ነበር. ከዛም ያ ወጣት ልጅ ዱአውን ከጨረሰች ብኃላ ተሸክሞ ቤቱ ውስጥ አስገባት.

ወጣቱም ሲወጣ ሙሳ ቁም አለው ይች ሴት
ማናት አለው  አልመለሰላትም  ለምን ትጠይቀኛለህ አለው  ሙሳም በአላህ ይሁንብህ ይች  ሴት  ማናት ንገረኘ አለው  ልጁም አለ እናቴ ናት. የሆነ ነገር  አውጥተህ ስትሰጣት አይቻለው ምንድነው የሰጠሃት አለው ልጁም ጉበት ነው የሰጠሁዋት ከማርጀቷ በፊት ጉበት ስለምትወድ  እያመጣሁ ሰጣታለሁ አለው. ውሃ  ከሰጣት ብኃላ  እጆን ወደላ ከድርጋ ዱአ ስታደርግ ነበር ስለምድነው ዱአ ያደረገችው ⁉️ ልጁም አለ ከልጅነቴ ጀምሮ ዱአ ታደርግልኛለች እንዲህም ብላ

አላህ ሆይ ልጄን የሙሳ ጎረቤት አድርገው ብላ አለ በጨረሻም እኔ ሙሳ የኢምራን ልጅ  ነኘ  አላህን ጎረቤቴን  በጀነት  አሳየኘ  ብየው  አንተን  አመላክቶኝ  ነው  የተከታተልኩህ , የናትህን ዱአ አላህ ተቀብሏታል አለው ልጅም አለቀስ ሙሳም ላይ ተጠመጠመ

ስለዚህ ወላጆቻችንን ከመርዳት አዘግይ በእዝነት ከተንከባከብናቸው ጀነት ሸልማታችን ነው

Ramadan ረመዳን

07 Nov, 18:32


           ሱረቱል  ጁምአ

(1) 💎 በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ ቅዱስ፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ለኾነው ያሞግሳል፡፡                                          (2)  💎እርሱ ያ በመሃይሞቹ ውስጥ አንቀጾቹን (ቁርኣንን) በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፣ (ከማጋራት) የሚያጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልክተኛ (ሙሐመድን) ከእነርሱው ውስጥ የላከ ነው፡፡ እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነበሩ፡፡
(3)💎 ከነሱም ሌሎች ገና ያልተጠጉዋቸው በኾኑት ላይ (የላከው ነው)፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
(4)💎 ይህ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡
(5) 💎የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት (ያልሠሩባት) ሰዎች ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ብጤ ነው፡፡ የእነዚያ በአላህ አንቀጾች ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ከፋ፡፡ አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡
(6) 💎«እናንተ አይሁዳውያን የኾናችሁ ሆይ! ከሰው ሁሉ በስተቀር እናንተ ብቻ ለአላህ ወዳጆች ነን ብትሉ እውነተኞች እንደኾናችሁ ሞትን ተመኙ» በላቸው፡፡
(7)💎 እጆቻቸውም ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት በፍጹም አይመኙትም፡፡ አላህም በዳዮቹን ዐዋቂ ነው፡፡
(8)💎 «ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው፡፡
(9) 💎እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡
(10)💎 ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡
(11) 💎 ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡ «አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነው» በላቸው፡፡

Ramadan ረመዳን

06 Nov, 18:58


❤️ ነብዩ ﷺ  “ከአማኞች ኢማኑ የተሟላው ስነ ምግባሩ ያማረው ነው፡፡ ከናንተ በላጫቻችሁ ለሴቶቻቸው በላጭ የሆኑት ናቸው” ብለው ነበር፡፡ [አሶሒሐህ፡ 284]
መልእክተኛው ﷺ “በሴቶች ጉዳይ አደራችሁን” ብለው ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
❤️ ነብይ ﷺ “ከምትበሉት አብሏቸው፡፡ ከምትለብሱትም አልብሷቸው፡፡ አትምቷቸውም፡፡ ...” ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1861]
ልክ አንተ በሚስትህ ላይ ሐቅ እንዳለህ ሁሉ ሚስትህም ባንተ ላይ ሐቅ አላት፡፡ 
- (وَلَهُنَّ مِثۡلُ ٱلَّذِی عَلَیۡهِنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ)
❤️ለእነሱም (ለሴቶቹ) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ሃላፊነት) አምሳያ (ሐቅ በባሎቻቸው ላይ) አላቸው፡፡” [አልበቀራህ፡ 228]
- (وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ)
(በመልካም ተኗኗረዋቸው፡፡) [አኒሳእ፡ 19]
❤️“አዋጅ! ለናንተ በሴቶቻችሁ ላይ ሐቅ አላችሁ፡፡ ለሴቶቻችሁም በናንተ ላይ ሐቅ አላቸው.”  [ሶሒሑልጃሚዕ፡ 7880]
❤️ “ለቤተሰብህም ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ እያንዳንዱን ባለ ሐቅ ሐቁን ስጥ!” [ቡኻሪ]
-❤️“ለሚስትህ ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]

❤️ ነብዩ ﷺ “ዱንያ መጣቀሚያ ናት ፤ ከመጣቀሚያዎቿ ሁሉ በላጩ ደግ (ሷሊሐህ) የሆነች ሴት ናት” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]

Ramadan ረመዳን

05 Nov, 18:20


ይቺ ምድር የሰው ልጅ ከመኖሩ በፊት የጂኒዎች መኖሪያ ነበረች አልታዘዝም ብለው ብዙዎቹ  ስላመፁ  ብዙዎቹ እንዲጠፉ  ተደረጉ  የተረፉትም  በምድር  ላይ ይገኛሉ ከነሱ ውስጥም አማኘ አለ ከሀዲም አንደዚሁ በአንድ ወቅት የተወሰኑ የዲኒ ስብስብ  ቁርአን አዳምጠው አስደናቂ መፀሀፍ እንደሆና  እንዲህ ብለው ተናግረዋል

(1) (ሙሐመድ ሆይ!) በል «እነሆ ከጂን የኾኑ ጭፈሮች (ቁርኣንን) አዳመጡ፡፡‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም› አሉ ማለት ወደእኔ ተወረደ፡፡
(2) ‹ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርአን ሰማን)፡፡ በእርሱም አመንን፡፡ በጌታችንም አንድንም አናጋራም፡፡›
(3) ‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም፡፡›
Al-Jinn 72:1-4


🔰ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለእነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል፡፡17:9

🔥እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅተንላቸዋል፤ 17:10

Ramadan ረመዳን

04 Nov, 18:37


ዝነኛዋ አነቃቂ ተናጋሪዋና ( motivational speaker) አስተማሪዋ  ሰባሪማላ  ከታሚል  ባሁን መጠሪያዋ ፋጡማ በመጀመሪያ የመካ ጉዞዋ  እንዲህ አለች

"በዚህ ሀገር ይህን ያህል ጥላቻ ለሙስሊሞች ለምን ብይ ራሴን ጠየኩ  እና  ገለልተኛ  ሆኜ ቁርአን ማንበብ ጀመርኩ  ከዛም እውነትን ተረዳሁ  አሁን ከራሴ በላይ እስልምናን እወዳለሁ"

ሙስሊሞችንም  ቁርአን በዙሪያቸው  ላሉት ሁሉ እንዲያነብት  ማስተዋወቅ አለባቸው አለች በተጨማሪም

" እናተ ሙስሊሞች በቤትችሁ የደበቃችሁት ድንቅ መፀሀፍ አላችሁ አለም ይሀን መፀሀፍ ሊያነብ ይገባል "  አለች

ሙስሊም ያልሆኑ ሰዋች ብዙ ጊዜ  በደፈናው ለእስልምናና  ለሙስሊሞች ጥላቻ አላቸው  ይህም እስልምናን ማንም ካወቀው  ሀቅ መሆኑን ስለሚረዳ  ይህን ለመከላከል ሰይጣን በሩቂ እንዲጠሉት ስለሚያደርጋቸው ነው, በሰይጣንና ተከታዮቹን  የስም   ማጥፋት   ሳይታለል   ሚዛናዊ   ሆኖ እስልምናን ለመረመረ በቀላሉ  እውነተኛው እምነት  መሆኑን ይረዳል.

Ramadan ረመዳን

03 Nov, 18:25


ዶ/ር  ቶምፕሶን በጀርመን ሆስፒታል ውስጥ የሚሰራ እንግሊዛዊ ሀኪም ሲሆን  እውነትን ከልቡ በመፈለግ ቁርአንን አጥንቶ  እስልምናን ተቀብሎ  ወደ መካ በመገጓዝ ኡምራ አድርጓል  አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው  በኢማኑም ላይ ያጠንክረው 

በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች በትምህርትም ይሁን በሌላ ምክንያት በርከት ያሉ መፀሀፍትን አንብበናል ቁርአንን የመጀመሪያው ሀምሳ ገፅ  ብቻ እንኳን በነፃ አይምሮ ያነበበ የፈጣሪ መፀሀፍ እንደሆነ ለመረዳት አይከብደውም
ስለዚህ ስንትና ስንት መፀሀፍ አንብበን እንዴት ከፈጣሪ የተላከልንን አንድ መፀሀፍ ሙስሊም ላልሆኑ ሰዎች  እንዲያነቡት  አንጋብዝም⁉️

እናንተ  ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ የሚመለስ ሰው አላህ (በእነርሱ ስፍራ) የሚወዳቸውንና የሚወዱትን፣ በምእመናን ላይ ትሑቶች፣ በከሓዲዎች ላይ ኀያላን የኾኑን በአላህ መንገድ የሚታገሉን የወቃሽን ወቀሳ የማይፈሩን ሕዝቦች በእርግጥ ያመጣል፡፡ ይኸ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፤ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡ 5:54

Ramadan ረመዳን

02 Nov, 18:37


እነዚህ ጋዛዊያን በዚህ ሁሉ  መከራ ቁርአን
እየቀሩ እኛ በሰላም ውስጥ ሆነን መቅራት ከብዶናል አይደል⁉️

ቁርአን ተምሮ አለመቅራት ከባድ ቅጣት ያስከትላል ቢያንስ አስር አንቀፅ በቀን አለመቅራት ከዝጉዎች መዝገብ ውስጥ እንድንሰፍር  ያደርጋል አስር አንቀፅ  ማለት አንድ ገፅ እንደማለት ነው አስር ደቂቃም አይወስድም ትልቅም አጅር እናገኝበታለን.

Ramadan ረመዳን

31 Oct, 18:32


ፋጢማ ካውኩጂ

በ1999 በወቅቱ የቱርክ ፕሬዝደንት የነበሩት ሱለይማን ደምሪል የዘማናዊ ቱርክ አስተሳሰብ ማራመድ ጀምረው ሂጃብ በመንግስታዊ ተቋማት እንዲታገድ ትእዛዝ ይሰጣሉ

በወቅቱ የቱርክ መንግስት ከተለያዩ ሀገራት አቻቸው ጋር የተናጠል ውይይት እና ስብሰባ ሲኖራቸው በትርጉም ስራ ተሰማርተው  ከነበሩት ውስጥ አንዷ መርዋ ካውኩጂ ትገኝበታለች

መርዋ በእስልምና የታነፀች ሂጃቧን ጠብቃ የምትንቀሳቀስ ስትሆን በቱርክ መንግስት የፀደቀው በመንግስት ተቋማት የሂጃብ ክልከላ ስራዋ ላይ እክል ፈጠረባት

በፕሬዝዳንታዊ የትርጉም ስራ ለመቆየት የነበራት አማራጭ አንድ ብቻ ነው ሂጃቧን ማውለቅ

መርዋ ግን አላደረገችውም
ምንም እንኳ ቤተሰቦቿን የምታስተዳድርበት እና የምትወደው የስራ ዘርፍ ቢሆንም ሂጃቧን ከማውለቅ  ስራዋን በፈቃዷ ለቀቀች

ፕሬዝዳንት ኤርዶጓን ስልጣን ከተረከቡ በኃላ በመንግስት ተቋማት የተጣለውን የሂጃብ እገዳ እንዲነሳ ትእዛዝ ሰጡ

ፕሬዝዳንት ኤርዶጓን ሂጃብ ከማወለቅ ስራዋን መልቀቅ የመረጠችውን መርዋ ወደ ቤተመንግስት በክብር ጋብዘው አድናቆታቸውን የገለፁላት ሲሆን ወደ ስራዋ ለመመለስ የጡረታ እድሜ ላይ መሆኗን ነገርግን የጡረታ መብቷን እንደ ሚያስከብሩላት ይገልፁላታል

እናት መርዋ ከጡረታው ይልቅ ሴት  ልጇ ፋጢማ ካውኩጂ በትምህርቷ ጠንካራ ተማሪ መሆኗን እንዲሁም የእኔን አርአያ ተከትላ አስተርጓሚ መሆን ፍላጎት ስላላት የስራ ዕድል እንዲሰጣት ፕሬዝደንቱን ጠየቀች

ቃሌ ነው ትምህርቷን ስትጨርስ አሳውቂኝ ነበር ያሉት ኤርዶጓን

ዛሬ ላይ ፋጢማ ካውኩጂ የኤርዶጓን ዋና አስተርጓሚ በመሆን የምታገለግል  በተለያዩ ሀገራት ጉብኝት እና ስብሰባ ላይ የማትጠፋ ሆናለች
ኤርዶጓን በብራስልስ የኔቶ ስብሰባ  ከፕሬዝዳንት ጆው ባይደን ጋር በነበራቸው  ውይይት ላይ ፋጢማ ከጎናቸው

Ramadan ረመዳን

30 Oct, 18:35


ትምህርት ተቋማት,  ት/ሚ

በየአመቱ 95%   በላይ ተማሪ  በሚወድቅበት የትምህር ስርአት ላይ መስራት ሲገባቹህ በማይመለከታችሁ ጉዳይ  እየገባችሁ  ይህን መልበስ አትችሉም  እያላችሁ በየጊዜው አጀንዳ ባትፈጥሩ

በኢሀዴግ ጊዜ እንኳ የልተከለከ አሁን  እንዴት  ይከለከላል ምናልባት  የብልጥግናን  መንግስትን  ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር በማጣላት ነጥብ ለማስጣል  የሚሰሩ  ስለሚኖሩ  ነገሩን ለራሳችሁ ስትሉ ብታስተካክሉ

እነዚህ የትምህርት ተቋማት  ስለትምህር
ቢያስቡ ኖሮ  አንዲት ሴት  በዚህ ምክኒያት ሳትማር  ከምትቀር  የተወሰነ  ጉዳት እንኳን ሲኖረው  ለብሳ መማሩዋን አይከለክሉም ነበር

ለአይናችን አልተመቸንም  ከሆነ   እነዚህ ሲታዮ  ምናቸው ነው የሚያስጠላ  እንደው አላህ  እነዚን ሁላ ቢሰጠን እራሱ

Ramadan ረመዳን

29 Oct, 18:19


አንዳንድ ሰዎች  እንደዚሁ ይጠሉሀል ምክኒያቱም ያንተ  የእምነት ገፅታህ እምነትህ የነሱን ሰይጣናት ስለሚያቃጥላቸው ነው

Ramadan ረመዳን

29 Oct, 17:54


እምነት  ያስፈለገው    ከመጥፎ    ስራ ለመቆጠብና  መልካም ስራ  ሰርቶ   ጀነት   ለመግባት  ሲሆን የአንዳንዶች እምነት ግን ለሰይጣን መጠቀሚያነት ሲውል ይስተዋላል.

ለምን ኒቃብ ትለብሳላችሁ ሲጀመር የነሱ መልበስ ምን ችግር ስለፈጠረ አጀንዳ  የሚሆነው  ምናልባት ስታያቸው  ላይመቻቹህ  ይህ ግን  የሚያቃጥለው እላያችሁ  ላይ  ያለው ሴጣን ነው  ስለዚህ ባለማወቅ  የሰይጣን መጠቀሚያ  አትሁኑ  ,መልበሳቸው መብታቸው ሲሆን  ይንንም በማድረጋቸው የማንንም መብት አልነኩም  

በባይብል   ውስጥ ሴት ሱሪ መልበስ    እንደሌለባት,    ሂጃብ ማድረግ  እንዳለባቸው,    እንዲሁም  ኒቃብ(የፊት   መሸፈኛ) እንደሚያደርጉ   ስለሚጠቅስ  ለእምነታችሁ ትዛዝ     ለመተግበር    ብትጥሩ ኖሮ  ሙስሊም  ሴቶችን ማድነቅና    መደገፍ    ሲገባችሁ  መበደልና ከትምህርት ማገድ  የስይጣን ጉዳይ  አስፈፃሚ  መሆን    ነው
 
"ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት
ልብስ አይልበስ። ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።" [ኦሪት ዘዳግም 22፥5]

"ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።" [1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 6]

* "በአይነ ርግብ(የፊት) መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭሽን እንደተከፈለ ሮማን ናቸው።" [መሀልየ ዘሰለሞን 6፡7]

* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ አይኖችሽ እንደርግብ ናቸው።" [መሀልየ ዘሠለሞን 4፡1
]

ሙስሊሙ  ህብረተሰብ ግን ለሌሎች እምነት እንደዚህ እይነት እንቅፋት ሲፈጥር አይስተዋልም ሙስሊም በበዛበት  አከባቢ  እንኳን,  ሊመሰገን ይገባዋል👏👏👏👏

ይች ከላይ  የምትታየው እህታችን በእንግሊዝ  ከኦክፎርድ ዩኒቨርሲቲ ኒቃብን ለብሳ በከፍተኛ መአረግ ተመርቃ የተሸለመች ናት የሌላው ሀገር ምን ያህል የሰው እምነት እንደሚያከብሩ  መረዳት ብትችሉ.

Ramadan ረመዳን

28 Oct, 18:04


የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ያኢርሰ ለፒድ ወደ 12 ሺ ወታደር ሞቶብናል ወይም ቆስሏል ግን የእስራኤል ጦር ሪፓርት ቁጥሩን እየቀነሰ ነው የሚያወጣው አሉ

የፍልስጤም ተዋጊዎች የሚገሉት ወታደር ሲሆን እስራኤሎች ግን  መኖሪያ ቤቶች, ት/ቤቶች, ሆስፒታሎች ላይ አሜሪካ ሰራሽ ቦምቦችን በመጣል  ህፃናት ሴቶች ሀኪሞችን ጋዜጠኞችን ትገላለች

ነብዩ (ሰዐወ) እንዲህ ብለው ትዛዝ ይሰጡ
ነበር

"በአላህ መንገድ በአላህ ስም ዝመቱ፤ ሕፃን፣ ሴት፣ ሽማግሌና ከሰው ተለይቶ በገዳም ውስጥ የተቀመጠውን ሰው አትግደሉ፤ የተምር ተክልም ሆነ ማንኛውንም ዛፍ አትቁረጡ፤ ቤት አታፍርሱ።" አሏቸው። 

Ramadan ረመዳን

27 Oct, 17:54


ከአጠራጣሪ ነገሮች መራቅ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ الحَلالُ بَيِّنٌ، والحَرامُ بَيِّنٌ، وبيْنَهُما مُشَبَّهاتٌ لا يَعْلَمُها كَثِيرٌ مِنَ النّاسِ، فَمَنِ اتَّقى المُشَبَّهاتِ اسْتَبْرَأَ لِدِينِهِ وعِرْضِهِ، ومَن وقَعَ في الشُّبُهاتِ: كَراعٍ يَرْعى حَوْلَ الحِمى، يُوشِكُ أنْ يُواقِعَهُ، ألا وإنَّ لِكُلِّ مَلِكٍ حِمًى، ألا إنَّ حِمى اللَّهِ في أرْضِهِ مَحارِمُهُ، ألا وإنَّ في الجَسَدِ مُضْغَةً: إذا صَلَحَتْ صَلَحَ الجَسَدُ كُلُّهُ، وإذا فَسَدَتْ فَسَدَ الجَسَدُ كُلُّهُ، ألا وهي القَلْبُ.﴾

ሐላል (የተፈቀደ ነገር ) ግልፅ ነው፡፡ ሐራምም (የተከለከለ ነገር) ግልፅ ነው፡፡ በመካከላቸው አሻሚ ነገሮች አሉ፡፡ በእርግጥም ከሰዎች ብዙ አያውቋቸውም፡፡ ከአሻሚ ነገሮች የተጠበቀ ሃይማኖቱንም ክብሩንም ጠበቀ፡፡ በአሻሚ ነገሮች ላይ የወደቀ ሐራም ላይ ወደቀ፡፡ ልክ በጥብቅ ክልል ዙሪያ (እንስሳቶቹን) እንደሚጠብቅ እረኛ፡፡ ከሱ ውስጥ (ግጦሽ) ሊግጡበት ይቀርባሉ፡፡ ንቁ! ለእያንዳንዱ ንጉስ ጥብቅ ክልል አለው፡፡ ንቁ! የአላህ ክልሉ ክልከላዎቹ ናቸው፡፡ ንቁ! በአካል ውስጥ ቁራጭ ስጋ አለች፡፡ እሷ ስትሰምር አካል በሙሉ ይሰምራል፡፡ እሷ ስትበላሽ አካል በሙሉ ይበላሻል፡፡ ንቁ! እሷም ልብ ነች፡፡”

ቡኻሪና ሙስሊም

Ramadan ረመዳን

24 Oct, 18:13


ሲጃራ ማጫስ በራስ  እጅ ራስን መጉዳት  ነው ገበያ ቦታ ለሚፈጠር  እሳት አደጋም መሰኤ ይሆናል

ሲጃራ እያጨስክ ራስን ለጉዳት ከምትዳርግ ለዚህ ሱስ ብለህ የምታወጣው ገንዘብ ሰደቃ ብትሰጠው ምን ያህል ምንዳ እንደምታገኘ አስበው

በተለይ  ባለትዳር  ሆናችሁ  የምታጨሱ ምን ያህለ ባለቤትህን በመጥፎ ጠረንህ አዛ እንደምታደርጋት አስብ
           
    وَأَنفِقُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا تُلْقُوا۟ بِأَيْدِيكُمْ إِلَى ٱلتَّهْلُكَةِۛ وَأَحْسِنُوٓا۟ۛ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡ 2:195

Ramadan ረመዳን

23 Oct, 18:30


በላን ለመከላከል

ምርት ሰብስቦ ዘካ አለማውጣት, ከሀብት ላይ  ዘካ አለማውጣት ወይም  ሰደቃ አለመስጠት  በላን ወይም ውድመትን ያስከትላል

ከደሞዝ ላይም ቢሆን በተቀበልን ጊዜ ትንሽም ብትሆን  መስጠት  በተለይ ሀብት ያላችሁ,  በግብርናም የተሰማራችሁ   ምርት በሰበሰባቹ ጊዜ ስጡ  አለበለዚያ  በተለያየ  ነገር ውድመት ሊከሰት ይችላል  በተለይ በቀጣይ የምርት ወቅት  ዝናብ ልንከለከል ወይም  በጎርፍ የደረሰ ሰብላችን በተባይ, በወፎች, በአምበጣ  መንጋ...  ውድመት ይደርስበታል

ሰደቃ አደጋን በእጅጉ ይከላከላል መንገድ ስንሄድ መስጠት  ትንሽም ብትሆን  ለምሳሌ አንደ የተቸገረ ሰው ምሳ ነገር ብናበላ

Ramadan ረመዳን

22 Oct, 17:39


አልሀምዱሊላህ!
በውሳኔህ ተሳስተህ አታውቅም !
ብዙ ሰተኸኝ ነበር ጥቂት ወስደህብኛል ክብርና ልቅና ላንተ የተገባ ይሁን!

አሁንም ቢሆን የጉዳት መጠናችን በውል አልታወቀም ቢሆንም የብዙዎች ወንድሞቼ ንብረት በአጠቃላይ በሚባል መልኩ ወድሟል አላህ ለሁላችንም መፅናናትን ይስጠን የተሻለውን አላህ ይተካልን!!

ሲቀጥል ብዙዎቻችሁ CBE account እየተቀባበላችሁ ልታግዙኝ እየሞከራችሁ ነው!!! በጣም አመሰግናለው!! ግን እኔ ከብዙ አላህ ከሰጠኝ ፀጋ በጥቂቱ ስለሆነ የነካኝ ለኔ የምታረጉትን ገቢ ለወንድሞቼ እንድታረጉ በትህትና እጠይቃለው!!! እንዲሁም የኔን የለጠፋችሁትን እንድትሰርዙት በአክብሮት እጠይቃለው!!!!
Via: #ሐሩን_ሰዒድ

የኢማን ልክ👌🥰
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

አቡ ሙሳ  እንዲህ አለ

አንድ ቤት በመዲና ለሊቱን እሰከ ነዋሪዎቹ እንደተቃጠለ ለነብዩ  ﷺ ተነገራቸው . እሳቸውም እንዲህ አሉ እሳት ጠላታቹህ ነው  ስለዚህ ወደመኘታ ከመሄዳቹህ በፊት አጥፉት አሉ. (ብሀሪና ሙስሊም) 
وعن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه قال‏:‏ احترق بيت بالمدينة على أهله من الليل، فلما حدث رسول الله ﷺ بشأنهم قال‏:‏ ‏ "‏إن هذه النار عدو لكم، فإذا نمتم فأطفئوها‏"‏ ‏(‌‏(‏متفق عليه‏)‌‏)‌‏


መሰል የእሳት ጥንቃቄዎችን(safely  protocol) መከተል አለብን ለምሳሌ

ከቤት ስኖጣ  ቤት ውስጥ ሰው ከሌለ  ከቆጣሪ ማጥፋት

ከቢሮ ስኖጣ በተመሳሳይ የተጠቀምንባቸው  መሳሪያዎች በትክክል መዝጋት, ከማፋፈያውን ማጥፋት

ህንፃዎች የእሳት አደጋ መከላከል ታሳቢ ተደርገው መሰራት አለባቸው

Ramadan ረመዳን

21 Oct, 18:28


‼️ እስራኤል ሆይ! በሠፈረሽው ቁና መሰፈርሽ አይቀርም!
~
#የቢላል_ትዝብት
.
እስራኤል በፍልስጤም ህዝቦች ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት የጅምላ ጭፍጨፋ ዘምቻዋን ከጀመረች ጊዜ እንስቶ በርካት የፍልስጤም ህዝቦች ትግል መሪዎች ላይ ግድያ ፈጽማለች። ሆኖም በእነኝህ ሁሉ ግድያዎቿ ሌሎች አዳዲስና ቀድሞ ከነበሩትም በበለጠ አመራር የመስጠት ብቃት ያላቸው መሪዎች ወደፊት እንዲመጡ ከማድረግ በዘለለ የተጀመረውን ትግል ማስቆምም ሆነ ማዳከም አልቻለችም። በቅርቡ የተሰውት የሃማስ መሪዎች ከእነሱ ቀደም ብለው ከነበሩት መሪዎች ድርጅቱን ተረክበው ሲመሩ የነበሩ ታጋዮች ናቸው። ከእነሱ ቀደም ብለው በነበሩት መሪዎች አመራር ሰጪነት ከባድ ፍልሚያዎች ተደርገዋል። የቀድሞዎቹ መሪዎች ተሰውተው በአዳዲስ አመራሮች ሲተኩ አዳዲሶቹ ቀድመዋቸው ከነበሩት በበለጠ በመደራጀት ትግሉን በአንድ ደረጃ ከፍ አድርገው ጠላታቸው ላይ አሳማሚ በትር አሳርፈው ተሰውተዋል። ጥቅምት 7 2023 ፍልስጤማውያን ታጋዮች እስራኤል ላይ ያሳረፉት በትርም ሆነ ከዚያም በኋላ እስከ አሁን እያደረጉ ያለው ተጋድሎ ቀደም ብሎ ከነበሩት ፍልሚያዎች በሙሉ በእጅጉ የተለየና ጽዮናውያኑ የፍልጤም ህዝቦችን ለማንበርከክ ፈጽሞ እንደማይችሉ በግልጽ ያመላከተ ነው።
.
የመሪዎቹ መገደል ለአጭር ጊዜም ቢሆን ችግር መፍጠሩ የሚጠበቅ ቢሆንም በረጂም ጊዜ ግን የሚኖረው ተፅዕኖ ቀጣዮን የትግል ምእራፍ ይበልጡኑ ስኬታማ ማድረግ እንደሚሆን ምንም የሚያጠራጥር አይደልም። የፍልስጤምም ሆነ የሌባኖስ ታጋዬች የሚያደርጉት ተጋድሎ ፍትሃዊ የሆነ መነሻ ያለው በመሆኑ ተጋድሎው በመሪው መገደል የሚቆም ሳይሆን ያለ መሪም እንኳን የሚቀጥል ነው። ሂዝቡላህ ለሶስት አስርተ አመታት ሲመራው የነበረው መሪውና ምክትሉ ቢገደሉም ትግሉ ለደቂቃዎችም አልተገታም። እንዲያውም አልፎ እንደ ጭራቅ የሰው ደም የሚቀለበውን የጽዮናውያን መሪ ንብረት እስከማጥቃት የደረሰ ኦፕሬሽን ማሳካት ችለዋል።
.
እስራኤል እንደለመደችው ሰማይ ሰማዩን እየበረረች ቤት ከማፍረስና መሳርያ ያልታጠቁ ህጻናትና ሴቶችን ከመግደል በዘለለ ድንበር ሰብራ ለመግባት ያደረገቻቸው ሙከራዎች በሙሉ ከባድ ዋጋ እያስከፈሉዋት ከሽፈዋል። እስራኤል አሸናፊ መስላ ለመታየት የፈለገችውን ያህል ብትጋጋጥም ጭንብሏ ተጋልጦ እርቃኗን ቀርታለች። እስራኤል እንኳንስ ኢራንን የሚያክል ሃገር ይቅርና ሃማስና ሂዝቡላህን የመሳሰሉ በጣም ውሱን አቅም ያላቸውን ቡድኖች እንኳን ካለ አሜሪካና አውሮፓውያን እርዳታ ማሸነፍ እንደማትችል አሳይታናለች። የእስራኤል ቴክኖሎጂም ሆነ ገደብ የሌለው አረመኔያዊ ጭካኔዋ አስፈሪነቱ አክትሟል። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ በሰፈረችው ቁና መሰፈሯ እንደማይቀር እነሆ ገሃድ ሆኗል፤ ኢንሻ አላህ!
.........
የተፃፈ በ #RN05 ነው!

Ramadan ረመዳን

20 Oct, 18:59


አላህ(ሱወ) ሰማይና ምድርን ከመፍጠሩ ከሁለት ሺ አመት በፊት 📗መፀሀፍን ፃፈ, ከዛም ላይ ሁለት #አንቀፆችን አውርዶ ሱረቱል በቀራን አጠናቀቀበት, በአንድ ቤት ውስጥ ለሶስት ቀን እነዚህ አንቀፆች #ከተቀሩ ስይጣን ወደዛ ቤት በጭራሽ አይቀርብም.
ቲርሚዚ 2882

የመጨረሻዎቹ  የበቀራ  አንቀፆች

ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِۦ ۚ وَقَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ ٱلْمَصِيرُ

لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا ٱكْتَسَبَتْ ۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَآ إِن نَّسِينَآ أَوْ أَخْطَأْنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَآ إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِۦ ۖ وَٱعْفُ عَنَّا وَٱغْفِرْ لَنَا وَٱرْحَمْنَآ ۚ أَنتَ مَوْلَىٰنَا فَٱنصُرْنَا عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ

285. መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፡፡ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንድም መካከል አንለይም» (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ፡፡ «ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው» አሉም፡:

286. አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርስዋ የሠራችው አላት፡፡ በርስዋም ላይ ያፈራችው (ኀጢአት) አለባት፡፡ (በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፡፡ ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ላይ አትጫንብን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለኛም በርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፡፡ ከእኛም ይቅርታ አድርግ ለእኛም ምሕረት አድርግ፡፡ እዘንልንም፤ ዋቢያችን አንተ ነህና፡፡ በከሓዲዎች ሕዝቦች ላይም እርዳን፡፡ 2:285-286

Ramadan ረመዳን

19 Oct, 18:32


ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ "የህዝቦቼ እድሜ ከስልሳ(60) እስከ ሰባ(70) ነው ፤ ይሄን የሚያልፉት ጥቂቶች ናቸው"
(ቲርሚዚይ እና ኢብኑ ማጀህ )

ነብዩ  ﷺ ራሳቸው, አቡበከር
, ኡመር የሞቱት በስልሳ ምናምን አመታቸው ነው ,  በጋዛ ጦርነት ሸሂድ የሆኑት የሀማስና የሂዝቦላህ አመራሮችም እድሚያቸው ስልሳ ቤት ነበር  እና መሞቻ እድሚያቸው ነበር  ያህያ ሲንዋሪም በአንድ ወቅት  ከሶስት አመታት በፊት እንዲህ ብሎ ነበር

"ወራሪው የጠላት ኃይል ለኔ መስጠት የሚችለው ስጦታ ካለ፤ ትልቁ እኔን መግደሉ ነው።በነሱ እጅ መስዋት ሆኜ ወደ አሏህ መሄድን ነው የምፈልገው።አሁን አድሜዬ 59 ነው።በኮሮና ከመሞት ይልቅ በF-35 ወይም በሚሳይል ተመትቼ መሞትን ነው የምመርጠው።...ከጥቂት ጊዜ በኃላ ስድሳዎቹ እገባለሁ።ያ ማለት የማረፊያና ወደ መጨረሻው የእውነት ዓለም የመሄጂያ ጊዜዬ ደርሷል ማለት ነው።በተለመደ መልኩ ከመሞት ሸሂድ ሆኜ ጌታዬን መገናኘትን እመርጣለሁ።"

በሻይረስ, በባክቴሪያ, በፈንገስ, በካንሰር... ተሸንፈህ  ከመሞት , እድሜ  ልክህን  በሀቅ መንገድ ተሰልፈህ ሰይጣንና አገልጋዮቹን ስትታገል መሰዋት  ምርጥ ፍፃሜ ነው  -  ሞት ላይቀር

Ramadan ረመዳን

18 Oct, 18:43


እኚህ ሁለት ጆርዳናዊያን ወጣቶች በጎረቤታቸው ፍልስጤም የሚደርሰው ግፍ አንገሽግሿቸዋል።ለአመት የዘለቀውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደ አብዛኛው ዐረብና የሙስሊሙ ዓለም አይቶ ማለፉ ከእምነታቸው ጋር አብሮ ሊሄድ አልቻለም።በተቀረፀ ቪድዮ ለቤተሰብና ወዳጆቻቸው ይቅርታን በመጠየቅ በቅርብ ያገኙትን ትጥቅ ታጥቀው ወደ እስራኤል ድምበር በመግባት ከወራሪው ኃይል የሚችሉትን ጥለው ተሰውተዋል።
አሏህ ይቀበላቸው

Ramadan ረመዳን

18 Oct, 18:40


አብዛኛው የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች የወራሪዋን ሀገር ጄኖሳይድ ድርጊት ይደግፋሉ
በተቃራኒው ደግሞ በአውሮፓ ህዝቦች በዚህ አንድ አመት ውስጥ ብቻ ከ26,000 በላይ ለፍልስጤም ድጋፍ ሰልፎች እና ዝግጅቶች ተካሂደዋል ከነዚህም
ውስጥ  በስፔኔና ጀርመን ከ4000 በላይ ሰልፎች, በፈረንሳይና ጣሊያን ከ3000 በላይ በአሜሪኪም እንዲሁ
በመካከለኛ ምስራቅ ሰልፎች በተለይ በኢራን በየመን በኢራቅ ቢካሄድም  በሳውዲ በግብፅ በUAE በካሂዶ አያቅም ማለት ይቻላል በተለይ በሳውዲ  ታዳ አላህ ቀጣት ቢልክ የትኞቹን ሀገሮች የሚቀጣ ይመስላችሁዋል

እነዚህ መሳሪያ የሚያቀብሉ ሀገራት ላይ  ቅጣቱ የዘገየው  ሰላሚ ሰልፍ በሚወጡ ሰዎች ምክንያ ሳይሆን አይቀርም

በተለይ በአሜሪካ  ሰልፍ ባያደርጉ ጥሩ ነበር

Ramadan ረመዳን

17 Oct, 18:05


ጁምአ

ነብዩ  ﷺ  እንዲህ አሉ

ፀሀይ ከምትወጣበት ቀን ሁሉ ምርጡ  የጁምአ ቀን ነው. አደም የተፈጠረበት, ጀነትም የገባበት ከሷም የወጣበት ቀን ነው. #ሰአቷም(የፍርዱ ቀን) አትቆምም በጁምአ ቀን ቢሆን እንጂ.  ቲርሚዚይ 488 🤍


#ሰዓቷ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ በእርሷ ጥርጥር የለም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡  40:59

#ሰዓቷም በምትቆምበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ

ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው (ጣዖታት) አማላጆች አይኖሯቸውም፤ በሚያጋሯቸውም (ከአላህ  ውጪ በሚያመልኩት ነገር) ከሓዲዎች    ይኾናሉ

#ሰዓቷ በምትቆምበት ቀንም በዚያ ቀን ይለያያሉ፡፡

እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን ሥራዎች የሠሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ

እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡
እነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡
በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች ነው፡፡ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ይገቡባቸወል)፡፡ አላህ ከእነርሱ ወደደ፡፡ ከእርሱም ወደዱ፡፡ ይህ ጌታውን ለፈራ ሰው ነው፡፡   98:6-8

Ramadan ረመዳን

15 Oct, 18:19


እውነታው ይነገር!
-----
አፈንዲ ሙተቂ
------
የአውሮጳ ሀገራት እና አሜሪካ ለ1800 ዓመታት አይሁዶችን ሲወቁ፣ ሲያስፈራሩ፣ ሲዘልፉ፣ ሲጨቁኑ፣ ሲያሰቃዩ፣ ሲዘርፉ፣ ሲገድሉ፣ ሲጨፈጭፉ እና ሲገርፉ ነበር። አይሁዶች የጭካኔ እና የስግብግብነት ምልክት ተደርገው ሲጻፍባቸው ነበር።

=>  ዊሊያም ሼክስፒር በጻፈው "የቬኒሱ ነጋዴ" ውስጥ "ገንዘቤን በጊዜ ካልከፈልከኝ ከሰውነትህ አንድ ኪሎ ስጋ ቆርጬ እወስዳለሁ" ብሎ ገንዘብ የሚያበድረው ሻይሎክ የተባለ አራጣ አበዳሪ አይሁድ ሆኖ ነው የተቀረጸው።

=>  "ጄኔራል ድሬይፉ" የተባለው አይሁዳዊ የፈረንሳይ ጄኔራል ምንም ሳያጠፋ "የፈረንሳይን ወታደራዊ ደህንነት መረጃ ለጀርመን አሳልፈህ ሽጠሃል"በሚል ተወንጅሎ የደረሰበት መከራ ዓለምን አነጋግሮ ነበር።

=> የናዚ ፓርቲ በጀርመን ስልጣን ሲይዝ የአይሁዶችን ንብረት ከመቀማት ጀምሮ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን በእቶን እሳት አቃጥሏል።
------
የምዕራቡ ዓለም አይሁዶችን በሚያሰቃይበት እና በሚፈጅበት የመከራ ዘመን በሐዘኔታ አቅርቦ ያስጠለለው የሙስሊሙ ዓለም ነው። በተለይም የኦቶማን ቱርኮች ኢምፓየር በ15ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ መርከቦችን በማሰማራት የስፔን አይሁዶችን ከግድያ ለማትረፍ ጥሯል።

በዛሬው ዘመን ግን ታሪክ ተገለባብጦ በወንጀለኛነቱ የሚታወቀው የምዕራቡ ዓለም የአይሁድ ደጋፊ መስሎ ይታያል። አውሮጳዊያን በአይሁዶች ላይ ለሰሩት ግፍ ዕዳውን የሚከፍለው መከረኛው የፍልስጥኤም ሕዝብ ሆኗል።
------
ይስሐቅ ራቢን እና ያሲር አራፋት በ1993 በኦስሎ የሰላም ስምምነት ሲፈራረሙ ነፃ እና ሉዓላዊት ፍልስጥኤም በአስር ዓመት ውስጥ እንደምትመሠረት ተግባብተው ነበር። ይስሐቅ ራቢን ስምምነቱን ፈርሞ አንድ ዓመት ሳይሞላው " ሺን ቤት" የሚባለው የእስራኤል የሀገር ውስጥ ደህንነት ተቋም በሸረበው ሴራ ተገደለ። የሰላም ስምምነቱን ያፈራረመው የአሜሪካው ቢል ክሊንተን በጀመረው ጎዳና እንዳይቀጥል  የተለያዩ  መሰናክሎችን በማድረግ ስራውን  እንዳይሰራ ክፉኛ አወኩት። ክሊንተን በመጨረሻዋ ሰዓት አራፋትንና ኢሁድ ባራክን ለማገናኘት ያደረገውንም ጥረት አከሸፉበት። የኦስሎ የሰላም ስምምነትም ሳይተገበር ሰላሳ አለፈው። በመሃሉ እስራኤል የኒውክለር ቦምብ ታጣቂ ሆና ብቅ አለች።
-------
እውነተኛ የፍርድ ተቋም ቢኖር የምዕራቡ በፍልስጥኤማዊያን ላይ ለተሰራው የ75 ዓመት ግፍ ከእስራኤል በላይ ተጠያቂ ይሆን ነበር።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️😂❤️😂❤️

በኩባ ፕሬዝዳንት ሚጌል ዲያዝ ካኔል የተመራ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በጋዛ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ በሃቫና የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።

“ነፃ ፍልስጤም ለዘላለም ትኑር” የሚል ትልቅ ባነር የያዙ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ እና አጋሮቻቸው የፍልስጤም አጋርነት አርማ በመልበስ ድጋፋቸውን አሳይተዋል።

#PalestineShallBeFree  from land to sea

Ramadan ረመዳን

14 Oct, 18:06


እስራኤሎች ብዙዋቹ  ተጨፍጭፈው     የተወሰኑት  አምልጠው ከአውሮፓ  ተባረው  ወደ  ፍልስጤም ሲመጡ ይህን ይመስሉ ነበር

በጭፍጨፋውም ወቅት   እንዳይገደሉ በፈረንሳይ የሚገኘው ትልቁ መስጊድ መታወቂያ  ይሰጣቸው ነበር  ይህን ሁሉ ረስተው  ህነፃናት ሴቶችን  ይገይገድላሉ

ቀጀምትም ነቢያቶችን የሚገሉ  እንደነሳራዎች እምነትም እየሱስን የገደሉ ናቸው አሜሪካም የምትረዳቸው የሰይጣን አጀንዳ አስፈፃሚ ህዝቦች ስለሆኑ ነው


"በጋዛ የሚገኙ ህፃናት ፊታቸው በደም ተሸፍኖ እያየን  ይህ የሰላም ሽልማት ለእኛ መሰጠቱ አስገርሞኛል"

የጃፓን ፀር-ኒኩሊየር ቡድን ሀላፊ ቶሺዩኪ ሚማኪ

- ሀሩን ሚድያ ጥቅምት 4/2017

የጃፓኑ ፀረ-ኒውክሌር ዘመቻ አራማጅ ኒሆን ሂዳንኪዮ ቡድን ሀላፊ ቶሺዩኪ ሚማኪ የዚህ ዓመት የኖቤል ሠላም ተሸላሚው ስለሰላም ሽልማቱ ሲናገር ለጋዛ ሰላም አጥብቀው የሚታገሉ ሰዎች ይገባቸዋል ብዬ አስብ ነበር። እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማስቆም ከሚጥሩ ሰዎች ይልቅ ሽልማቱን ማግኘታቸው እንዳስገረማቸው ተናግሯል።

ከኖቤል ሰላም ሽልማት በኾላ በእንባ በታጀበ ድምፅ "ሁሌም እንደምናደርገው ኒኩሊየር መሣሪያዎች ከምድረ ገፅ እንዲጠፉ እንተጋለን። ለዘላቂ ሰላም እንሰራለን። ለምን ኒሆን ሂዳንክዮ?ይህ የኖቤል የሰላም ሽልማት ለኛ ሳይሆን በጋዛ ለሰላም ጠንክረው እየሰሩ ላሉ ሰዎች ይሰጣል የሚል ጽኑ እምነት ነበረኝ" ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም "አሁን በጋዛ ወላጆች በደም የጨቀዩ ልጆችን አቅፈው እያየን ነው...ይህ ልክ ከ80 አመት በፊት በጃፓን [ሄሮሽማ] ከነበረው ሁኔታ ጋር ይመስላል" ሲሉ ገልጸዋል።

© ሀሩን ሚድያ

Ramadan ረመዳን

13 Oct, 19:01


አላህ ነገሮች በተለያየ ህዝቦች ዘንድ ያዘዋውራታል 

በአንድ ወቅት ተበዳይ ነኘ ብሎ ሲታገል
የነበረው  ወያኔ ስልጣን ተጠሰውና እሱም በተራው  ምን  እንደሰራ  ታይቶ የተሰጠውን ጌዜ አጠናቆ ወደ ነበረበት አሰላለፍ ተመልሷል አሁን ደሞ ኳሷ  በብልፅገና  እጅ  ትገኛለች 

ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ 67:1-2

የስራኤልም ህዝብ  ግብፆች ለ 400 አመት  በላይ በብሩት  ጭቆና የሚወልዱትን  ወንድ   ልጆቻቸውን እያረዱ   ገዝተዋቸዋል

ከፈርዖንም ቤተሰቦች (ከጎሶቹና ከሰራዊቱ) ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሱዋችሁ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱ ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲኾኑ ባዳንናችሁ ጊዜ (የኾነውን አስታውሱ)፡፡ በዚሃችሁም ከጌታችሁ ታላቅ ፈተና አለበት፡፡ 2:49

በአውሮፓም በተለይ  በጀርመኑ ናዚ ተጨፍጭፈው ንብረታቸው ወድሞ ወደ ፍልጤም ተሰደው ማረፊያ ስጡን እናተም የመኖር ተስፋችን አታጨልሙት  ቤተሰቦችችን አልቀዋል ንብረቷቻችን ወድመዋል ብለው ለምነው እንዳልገቡ አሁን ይህው ብርቱ ግፍ ይሰራሉ

ወ ደ  እስራኤልም ልጆች በመጽሐፉ ውስጥ (እንዲህ በማለት) አወረድን፡፡ በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ታጠፋላችሁ፡፡ ትልቅንም ኩራት ትኮራላችሁ፡፡ 17:4

Ramadan ረመዳን

12 Oct, 18:30


አስ-ሱመይራዕ ቢንት ቀይስ ባሏ ፣ ወንድሟና አባቷ በኡሁድ ዘመቻ ተሰዉ ።  ሁሉም መሰዋታቸው በተነገራት ጊዜ " የአላህ መልዕክተኛስ እንዴት ሆኑ !??" ብላ ጠየቀች።
ከዛም የአላህ መልዕክተኛ ለአላህ ምስጋና ይገባው  እንደምትፈልጊው  ደህና ናቸው  ተባለች ። እሷም እስኪ ልያቸው ብላ አየቻቸው ። ስታያቸውም የእሳቸውን ውዴታ የሚገልፅ ታላቅ ንግግርን ተናገረች ፦

" ሁሉም መከራ ከእርሶ በኃላ ቀላል ነው "
ዲንን ለመጠበቅ ሰው እንዲህ ያለ መሰዋትነት ከፍለዋል ባሁኑ ወቅት የፍልስጤም እናቶች ከዝች ሱሀባ ይመደባሉ እኛ ግን የአንድ ለሊት እንቅልፋችን በመሰዋት አድርገን ዱአ ማድረግ ተሰኖናል

Ramadan ረመዳን

11 Oct, 18:02


በአሜሪካ እና በእስራኤል “ግትርነት” ምክንያት የጋዛ ጦርነት ቀጥሏል - ሩስያ

የጋዛ ጦርነት እስካሁን እንዲቀጥል የእስራኤል እና አሜሪካ “ግትርነት” ዋና ምክንያት እንደሆነ ሩስያ አስታውቃለች፡፡

ሁለቱ ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት “አስከፊውን የጥቃት አዙሪት እንዳያስቆም እንቅፋት ሆነዋል” ሲሉ በተመድ የሩስያ ተወካይ ተናግረዋል።

አንድ አመት በሞላው የጋዛው ጦርነት ዙርያ የጸጥታው ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ነው የሩስያ ተወካይ ቫስሊ ኔቤንዚያ ይህን ያሉት፡፡


ሚልተን የተሰኘው ደረጃ 3 አደገኛ አውሎ ነፋስ ትላንት ፍሎሪዳን ሲያቋርጥ ከፍተኛ ውድመትን አስከትሏል። ግዛቲቱ በአደገኛ አውሎ ነፋስ ስትመታ በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው

ባይደን:-"የሀሪኬን ሚልተን አውሎ ንፋስ እስካሁን የ50 ቢሊየን ዶላር ንብረት ውድመት አድርሶብናል።"
አሜሪካ ከኦክቶበር 7 አንስቶ ለእስራኤል ያደረገችው የመከላከያ ድጋፍ ከ12 ቢሊየን ዶላር ነው

Ramadan ረመዳን

10 Oct, 18:41


🚩የአሜሪካዋ ፍሎሪዳ "ሀሪኬን ሚልተን" በተባለ ከባድ አውሎ ነፋስ ተመታች😎
***

የአሜሪካዋ ፍሎሪዳ ግዛት ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ አስፈሪ በተባለለት ሀሪኬን ሚልተን በተባለ ከባድ  ማእበል መመታቷ ተነግሯል።

ሀሪኬን ሚልተን ማዕበል ነፋስና ነጎድጓዳማ ዝናብ ያዘለ በመሆኑ ጉዳቱን ከባድ እንዳደረገው ነው የተገለጸው።

በግዛቲቱ የሚገኙ 3 ሚሊዮን መኖርያ እና ንግድ ቤቶችም በዚሁ ምክንያት  የኤሌክትሪክ ሀይል ኢንዲቋረጥባቸው ሆኗል።

በተለይም በሃርዲ ካውንቲ ውስጥ ከ97 በመቶ በላይ ቤቶች ኤሌክትሪክ እንደሌላቸው ሪፖርት ተደርጓል።

የአሜሪካ ብሔራዊ አውሎ ነፋስ ማዕከል (ኤን.ኤች.ሲ) በሰጠው መግለጫ ሀሪኬን ሚልተን በፍሎሪዳ ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ በሰዓት በ90 ማይል (150 ኪ.ሜ.) የሚጓዝ መሆኑን አስታውቋል።

ይህም ጠንካራ ማእበል ነው ያለው ማእከሉ በከተሞች መሰረተ ልማትን እና ዛፎች እንዲወድቁ ምክንያት መሆኑን ነው የገለጸው።

የአሜሪካ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ማዕበሉ በቀጣይ ቀናትም ከባድ ዝናብ፣ ጎርፍ እና አውዳሚ ነፋስ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል።

እንደ ታምፓ ቤይ ታይምስ ዘገባ ከሆነ አሁን ላይ በማዕበሉ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት በፍሎሪዳ ግዛት የሚገኙ  ሁለገብ ስታዲየሞች ለብሔራዊ ጠባቂዎች እና ለኤሌክትሪክ ሰራተኞች እንደ ማረፊያ ቦታ እያገለገሉ ይገኛሉ።

በሀሪከን ሚልተን የተነሳ ብዙዎች ቤት ንብረታቸውን ሲያጡ ቁጥራቸው በውል ያልተለዩት ደግሞ ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ጠቅሶ ዶቼቬሌ ዘግቧል።

ምንጭ  #ዶቼቬሌ

ነገም ጁምአ ስለሆነ በዱአ እንበርታ

Ramadan ረመዳን

09 Oct, 18:44


እስራኤሎች

እስራኤሎች ሀይለኛ ናቸው  እሄን ሁሉ ግፍ ሲሰሩ ፈጣሪ ዝም የሚላቸው  የፈጣሪ  ህዝቦች ወዳጆቹ   ስለሆኑ  ነው  ብለው  የሚያስቡና   የሚናገሩ ሰዎች ይታያሉ

እውነት   እንደሚታሰበው  ሀይለኞች   ናቸው⁉️

ታሪክን ሰንመለከት  በጣም ደካማ ህዝቦች ሆነው እናገኛቸዋለን ለማሳያም  አንድ ሁለቱን ብንመለከት

ባለፉት ሁለት ሺ አመታት የተስፋይቱ ምድር ብለው የሚጠሯት  አሁን ከመሰረቱት መንግስት ውጪ  አንድም ጊዜ  የራሳቸው መንግስት መስርተው አስተዳድሪዋት አያቁም  ሌሌች ግን እየተፈራረቁ ገዝተዋታል   ሙስሊሞች በበላይነት ከ1000 አመት በላይ አስተዳድረዋታል,  አሁንም የመሰረቷት መንግስት አውሮፖዊያን ከሀገራቸው እንዲወጡላቸው  ስለፈለጎ ስላገዙዋቸው ነው

ከሰዎች ሁሉ ቀድመው ወደ ተለያዩ ሀገራት በተለይ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ስደት የጀመሩ ደካማ ህዝቦች ናቸው

የፈጣሪ ህዝቦች ስለሆኑ ይወዳቸዋል ⁉️

በሰው ልጆች ታሪክ እንደ እስራኤል እንደሚባል ህዝብ  መከራ የደረሰበት ህዝብ የለም

በአንድ ጊዜ ብቻ በጀርመኑ ሂትለር ከ6 ሚሊየን በላይ  አይሁዶች ተጨፍጭፈዋል በታሪክ ይህን ያህል ህዝብ በአንድ ጊዜ የተጨፈጨፈበት ህብረተሰብ የለም

በግብፅ በፊርአውን ስር  ለ400 አመታት በባርነት ቀበር ስር አሳልፈዋል

አሁንም የመሰረቷት ሀገር ከጅብቲ የቆዳ ስፋቷ የምታንስ  ትንሺ ሀገር ናት  ለሷም ይህው ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ጦርነት ላይ ናት የምትኖረውም በነአሜሪካ እርዳታ ነው  ታዳ የፈጣሪ ወዳጅ ከሆኑ ስንቶች ሰፋፊ ሀገር ይዘው እሷ ሚጢጢይ ሀገር ብቻ ደርሷት ጎረቤቷ ግብፅ እንኳን ከሷ ወደ 50 ጊዜ እጥፍ ስፋት ያላት ሀገር ናት

ፈጣሪ የወደደው መልካም ፅድቅ ስራዎችን, ሰዎችን መርዳት የሰዎችን መብት እንዲጠብቅ ያደርገዋል እንጂ ሌሎችን እየበደለ እየገደለ እያሰቃየ እያፈናቀለ  እንዲኖር አያደርገውም    

ግፍ እየሰራ የሚኖር ህዝብ በፈጣሪ ዘንድ የተጠላና የተረገመ ቢሆን እንጂ አይወደድም .....

Ramadan ረመዳን

08 Oct, 18:34


CBS journalist lights himself on fire over in Washington over US media coverage of Gaza war
October 6, 2024 by Presstv
US police move in to restrain a man as he apparently tries to set himself on fire during a pro-Palestinian rally near the White House in Washington, DC, on October 5, 2024. (Photo by AFP)
A journalist reportedly working with CBS News has lit himself on fire to protest the biased US media coverage of Israel's genocidal war in Gaza which has killed tens of thousands of people including women and children. 
The man was seen trying to light himself on fire during a pro-Palestinian rally near the White House in Washington, DC in Lafayette Park on Saturday. A large number of protesters attended the rally. 
Photos taken at the scene near the White House captured the harrowing moments the man's arm burst into flames.
Viewer discretion is advised!

A man identifying as a CBS journalist set himself on fire during a protest in Washington, DC, stating, “We spread the misinformation,” on the first anniversary of the Israeli-US genocide in Gaza. pic.twitter.com/sqIeMFABIH

— Palestine Highlights (@PalHighlight) October 6, 2024
Since the incident, the man has been reportedly identified as CBS photojournalist Samuel Mena Jr.
In the footage, he cries out that he is a journalist as the officers restrain him. “We spread the misinformation.”
Mena, who claims to be a "visual storyteller," was seen waving his burning arm through the air as he shrieked in pain.
In the disturbing photos and footage of the incident, Mena can be seen screaming after he set his left arm ablaze in the middle of the street as shocked DC Metropolitan police officers and bystanders rush over towards him.
Mena held his burning left arm high in the air to show the others as several people quickly doused him with water and beat out the flames with pieces of clothing.
People join rallies across world to condemn Israeli genocide
October 6, 2024 by Presstv
Mena, who used to work as a journalist in Phoenix, Arizona, was then taken to hospital with non-threatening burns to his arms.
He is a 2018 graduate of the Walter Cronkite School of Journalism and Mass Communication according to his LinkedIn and had worked at Arizona's Family for about two years. 
Local media reported Mena had been fired from his media employer after the act of self-immolation at the rally. 
Western media, particularly right-wing media, has been particularly hostile towards pro-Palestinian voices, resulting in the continued Israeli regime forces' genocidal war on the helpless Palestinians trapped in the besieged Gaza Strip for almost a year now.
Since Oct. 7, 2023, the Israeli war machine has killed about 42,000 Gazans, while extending the war to the West Bank, Lebanon and Syria, while threatening to attack other countries across West Asia. 

አሜሪካ በዚህ በኩል ህፃናትና  ሴቶች  እንዲጨፈጨፉበት ቦቦችን ትልካለ  በዛ በኩል ደሞ ሚዲያዎች የውሸት ዜና እንዲሰሩ ጫና ትፈጥሪለች ይህን በመቃወም ሳሙኤል የሚባል ለCBS  የሚሰራ ጋዜጠኛ ራሱን በሳት አያይዞል

አሜሪካ የያዝከው አጀንዳ በሰይጣን  ከፀደቀልህ ድጋፍ ታደርግልሀለች ለምሳሌ

እምነት ያላተውን ሰዎች ከተዋጋህ
ግብረሶዶም ከደገፍክ
ፆታ ቀይራለው ካልክ ....

Ramadan ረመዳን

07 Oct, 18:39


የጋዛ ጦርነት

የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ አንድ አመት ሞለው  ይህ በስልጣኔ ጫፍ ላይ ደርሻለሁ የሚለው  አለም  የንፁሀን ሰቆቃ  ማስቆም አልቻለም  እንደውም የዲሞክራሲ  የሰብአዊ መብት ጠበቃ
ነኘ  የምትለው አሜሪካ ወደ  ወደ አንድ
ሚሊዮን ኩንታል (ለያንዳንድ የጋዛ ነዋሪ ግማሽ ኩንታል) የጦር   መሳሪያዋችን (ቦንቦችን, ሚሳኢሎችን) ለወራሪዋ ሀገር  እያቀበለች  ንፅሀኖች እንዲጨፈጨፉ ከፍተኛ  አስተዋፆ  እያደረገች  ትገኛለች

የእራኤልም ስራ ከአሜሪካ በተሰጣት ተዋጊ ጀቶች ቦንቦቹን እየጫነች መኖሪያ ቤቶች , ት/ቤቶች , የጤና ተቋማት ላይ በመጣል  ንፁሀኖችን  መጨፍጨፍ ነው

ያ ረቢ ለነዚህ ሁለት አገሮች የፊርአውንና
የሰራዊቱን እጣ ፋንታ ስጣቸው

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ይህ ከቀሳሞች ብርጌድ ቃል አቀባይ ከአቡ ኡበይዳ የተሰጠ መግለጫ ነው

🔹የጡፋን አልአቅሳ ዘመቻ ከተጀመረ ከአንድ አመት በኋላ ከዛው ከፅኑዋ ሀገር ጠላትን ካንበረከከችው የጋዛ ምድር  ዛሬም እናናግራችኋለን

🔹ይህች ምድር የወይራ ፍሬን በየጊዜው እየሰጠች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዳሻገረች ጀግና ሙጃሂዶችንም ታፈራለች።

🔹 የዘመኑ ምርጥ ኮማንዶዎች ኦፕሬሽናቸው ከተጠናቀቀ እነሆ አንድ አመት አለፈ።

🔹ህዝባችን የጎረቤቶቻቸውን ክህደት፣ የአገዛዙን ፈሪነትና ተባባሪነት፣ የጠላትን ጭቆናን ግፍ ተቋቁሞ ዘልቋል።

🔹 በፍልስጤም ዙርያ ከህዝባችን ጎን የቆሙ፣ የሚደግፉ ጠላትን በቀጥታ የሚዋጉ ጦር ግንባሮች አሉ።

🔹የሉብናን የየመንና የኢራቅ ሙጃሂዶች በወራሪዋ ሰማይ ላይ እየዞሩ ጠላትን በመምታት ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል።

🔹 ይህ ጦርነት ከተጀመረ ከአንድ አመት በኋላ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መንግስት ወራሪዋን ለመዋጋት እውነተኛ ቃል ኪዳኑን አሳይቷል።

🔹በሺዎች የሚቆጠሩ የጠላት ወታደሮችን ገድለናል በርካቶችንም አቁስለናል። ለቁጥር የሚያዳግቱ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ከአገልግሎት ውጪ አድርገናል።

🔹 ከወራሪዋ ጋር ረጅምና እልህ አስጨራሽ ፍልሚያን መቀጠል ቀዳሚ ምርጫችን ሆኗል። ጦርነቱ የዚህን ምርጫ ስኬት በሚገባ  አረጋግጦልናል።

🔹ትዕቢተኛው የጠላት ጦር ከታሪክ አይማርም። ተጨባጩን አይረዳም። የሕዝባችንንና የኡማውን ባህልም አይገነዘብም።

🔹የሁለቱ ከፍተኛ መሪዎች የኢስማኢል ሃኒያ እና የሀሰን ነስረላህ ሞት ጠላት የጂሃዱን ምንነትና አካሄድ እንዳልተረዳው ግልጽ ማስረጃ ነው።

🔹መሪን መግደል ድል ቢሆን ይህ ስብስብ ድሮ ድሮ በተበተነ ነበር

🔹 ጠላት መሪን በመግደል የሚያገኘው ደስታ አጭር ነው። ግድያዎች ድል ቢሆኑ ኢዘዲን አል-ቀሳም ከተገደለ ወዲህ የጂሃዱ እንቅስቃሴ ባበቃ ነበር።

🔹የወራሪዋ ጦር በተለይም አሁን ያለው መንግስት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለውን ፍልስጤም ማየት አይፈልግም።

🔹ጠላት የሚገባው የሃይልና የጦር መሳሪያ ቋንቋ ብቻ ስለሆነ መጋፈጥ የምንችለው በጠመንጃ አፈሙዝ ብቻ ነው።

🔹 በዌስት ባንክ የሚገኙ ወንድሞቻችን ለጠላት ጭካኔ ምላሽ ለመስጠት ተቃውሟቸውን እንዲያጠናክሩ እንጠይቃለን።

🔹እኛን በመደገፍ ሌት ተቀን ለሚደክሙ የየመንና የሒዝቦላህ ጦረኞች ባላችሁበት ሰላምታችን ይድረሳችሁ።

🔹የወራሪዋ እስራኤል ዘመነ መንግስት በጋዛና በዌስት ባንክ ከሚገኙ መስጂዶችና አብያተ ክርስቲያናት ጫማ እድሜ ያነሰ ነው።

🔹ከዚህ በፊት በረፈህ በስድስቱ እስረኞች ላይ የደረሰው እጣ ፈንታ በሌሎች እስረኞችም ላይ ሊደገም ይችላል።

🔹እስረኞቹ ለአደጋ ከተጋለጡ ወይም ከቅርብ ርቀጥ ጦርነት ከተጀመረ ወደ ሌላ አስተማማኝ ቦታዎች እንደሚዘዋወሩ መመሪያ አለን።

🔹የወራሪዋ እስረኞች ላይ የሚደርሰው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው።

ኦክቶበር 7
via Mahi mahisho

Ramadan ረመዳን

06 Oct, 18:15


ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ አሉ፦

ሰአቷ አትቆም
📗እውቀት ሳይነሳ (ሳይወሰድ),
መሬት መንቀጥቀጥ ሳይበዛ
ግዜው ሳይሮጣ
አስጨናቂ ነገሮች ሳይከሰቱ
ግድያ ሳይበዛ
ገንዘብ ሳይበዛ.
ቡኻሪ 1036

ብዙ ቦታዎች ላይ ዛሬ የመሬት መንቀጥቀጥ ተስተውሏል

አላህም እነሱ #ምህረትን (እስቲግፋር ማድረግ) የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም፡፡ 8:33

Ramadan ረመዳን

05 Oct, 17:16


#ዱአ ኢባዳ ነው በአላህ ዘንድም ምርጥ ትልቅና ተወዳጅ  ተግባር ነው ነብዩ   (ሰአወ) በርግጥ #ዱአ ኢባዳ ነው ብለው የሚከተለውን አነበቡ  
وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِى سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ

ጌታችሁም አለ « #ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡ 40:60 ሱነን ኢብን ማጃሀ 3828

በሌላም ሀዲሳቸው  ዱአ የኢባዳ  ዋና ነገር ነው ብለው የሚከተለውን ቀሩ  40:60  ሱነን ተርሚዚይ  2969

ከአላህ ውጪ ያለን  አካል ማምለክ ሽርክ ነው , ዱአም መደረግ ያለበት ወደ አላህ ብቻ ነው  ስለዚህ ወደ የትኛውም  አካል  መለመን መጣራት አይፈቀድም.   

إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡1:5      

وَٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا۟ بِهِۦ شَيْـًٔاۖ وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَٰنًا وَبِذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱلْجَارِ ذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْجَارِ ٱلْجُنُبِ وَٱلصَّاحِبِ بِٱلْجَنۢبِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

አላህንም ተገዙ፡፡ በእርሱም ምንንም #አታጋሩ፡፡ በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው (ባሮች)፣ መልካምን (ሥሩ)፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡   4:36   

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِۦ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُۚ وَمَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَٰلًۢا بَعِيدًا

አላህ በርሱ #የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም #የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡ 4:116   

ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውሰጥ ያስገባል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፡፡ ሁሉም እተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ፡፡ ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ #የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡ 

#ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) #ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡  35:13-14   

እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ #የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡    46:5       

ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን
ለእነርሱም #መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን)

(ጣዖቶቹን) ወደ ቅን መንገድ #ብትጠሩዋቸውም አይከተሉዋችሁም፡፡ ብትጠሩዋቸው ወይም እናንተ ዝምተኞችም ብትኾኑ በእናንተ ላይ እኩል ነው፡፡
እነዚያ ከአላህ ሌላ #የምትገዛቸው ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች ናቸው፡፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ጥሩዋቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ፤ (መመለስ ግን አይችሉም)፡፡   7:191-194    
 
ከአላህ ውጪ ያለን አካል የሚጣራ  በተለይ  ከሙታን  መካከል  በጭራሽ  አይድንም  ከትልቁ ሽርክ ሰለሚመደብ ስራው ሁሉ ተበላሸ

Ramadan ረመዳን

04 Oct, 18:11


ይህ ፍልስጤማዊ ልጅ ተጎድቶ መግሪብ ሊያመልጠኘ ነው ልስገድ እያለ ይጨቃጨቃል ስቶቻችን ደሞ ምንም ችግር ሳይገጥመን ሰላታችንን ችላ የምንል አለን , ግማሹ በፈተና ምክኒያት አምነታችን ይገራገጫል የዚህ ፍልስጤሞች መከራ እምነታቸውን አጠንክሮታል

1,681

subscribers

848

photos

50

videos