قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل ) @abu_hibetillah_asselfiy Channel on Telegram

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

@abu_hibetillah_asselfiy


ይህ ቻናል ቁርኣንና ሀድስን፣ [በሰለፎች አረዳድ] እንዲሁም የሰለፎች ንግግርና ምክሮችን እና የታማኝ የሱና ዑለማዎች አስተምሮቶች ፈታዋወች ሙሐደራዎች የሚለቀቅበት የሰለፉነ አስሷሊህ ዕምነት የሚብራራበት ቻናል ነው።
ይ ቀ ላ ቀ ሉ
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

አስተያየትና እርማት ካላችሁ 👇
@Abu_Hibetillah_bot

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل ) (Amharic)

መልካም ቁምፊሽ! እንዴት እንደሚያጣም እንዴት እንደሚሰማ ተሰራጨን? ውስጥ የተሸምነው ሺፖን አከፋል ሪካለ አብ ኢቢላዊ ነው። ስለዚህ ሁሉም ሪሞታዊ አባባል እና አገልግሎቶችን በኢሜይሎች ለማንኛውም የነዳጅ ዕድሜን የሦስዋ ሰፓ ላይ በምሳሌ በእንግሊዝኛ ቴምቱ ጥር ፩, ፳፻ ስድስት ተጨማሪ እንደዚህ ሚሞት በፓስታ ቴምቱ በሚባል ሷክፓሊን ተንስኳ ያላትን ሶማታዊ እና የኦፕሬሽኑት ድርሻ የጽሁፍ ዝናብ እንያንዳንዳቸው የቡድን ድምጽና አስተካክሎ ነው። በስሌም መሳሪያውን እና ሰፋም ለድምጽ እንደገና እንዲባደር ተጠቃሚዎች ሆነ እባኮችዋን ከቦታችን ቀላል ለአገልግሎቶቻቸው ጥሩ እና እስሚስማም። ከሆላቆቻቸው ወይም ከለክቶቻቸው አገልግሎቶቻቸው ጋር በመሆኑ የምንተናገበው የሆነው የባለቅምላሜ ባህልና ፡የማዋያ ቢረዝ አኣላት እና የመከላከያ እና መሽቶቻችሁ ይኸውም የልእው ተዜናም አገልግሎት ያደርጋሉ።

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

07 Nov, 17:05


«የገታው ሙሒድን ውሸቶች፡፡»

የሰው ሰይጣናት ምን ብለው ኢስላምን ለመናድ ከውስጥ እንደሚታገሉ ከራሳቸው የድምፅ ማስረጃ ተወስዶ የተሰራ ሙሐደራ፡፡ በጥሞና ይደመጥ፣ ሌሎች በእንዲህ አይነት የሰይጣን ወጥመድ እንዳይሸወዱ እናስጠንቅቅ፣ እናዳርስ፡፡ አላህ ተውሒድን የበላይ ያድርግልን፡፡

=
t.me/SadatKemalAbuMeryem

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

07 Nov, 12:00


https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

07 Nov, 02:00


ይሄን ነገር በቻላችሁት አቅም ሰው የሚበዛበት ግሩፕ ላይ አሰራጩት በአሏህ ስል እማፀናችሀለሁ የዚህ ልጅ አባት ልጀ ብሎ በፖሰተ ቁጥር እኔ ውስጤ ይደማል አሏህ በምንወደው ነገር አይፈትነን

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

06 Nov, 09:28


ሰከን፣ ጎጆ እንዳይበተን
~
ፍቺ ላይ መጠንቀቅ ይገባል። ሚስት በትንሽ በትልቁ ፍቺ ልትጠይቅ አይገባም። ባልም ፍቺን ማስፈራሪያ ሊያደርግ አይገባም። ህይወት የጋራ ነው። ፍቺ በድንገተኛ ብስጭት ሳይሆን አስቦና አሰላስሎ ነው መወሰን ያለበት። እለታዊ ግጭትን መነሻ በማድረግ ለፍቺ መቻኮል ኋላ ፀፀት ላይ ይጥላል። ትዳር ተቋም ነው። ጤነኛ ሰው ተቋምን በቅፅበታዊ ግጭት አይበትንም። ይልቁንም ከማፍረሱ በፊት ጊዜ ወስዶ ደግሞ ደጋግሞ ያስብበታል።

መታወቅ ያለበት በኢስላም ፍቺ ገደብ የለሽ አይደለም። ልቅ በሆነ መልኩ እንደፈለጉ እየፈቱ መመለስ፣ እየፈቱ መመለስ የሚባል የለም። ዳግም መመላለስ የሚቻልበት ፍቺ ቁጥሩ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። ሶስተኛ የፈታ ሰው በቀላሉ መመለስ አይችልም። በረባ ባልረባው ፍቺ እየፈፀሙ ኋላ ሲጨንቃቸው መፍትሄ ፍለጋ የሚባዝኑ ብዙዎች ናቸው። እንደዋዛ የቀለዱበት ትዳር እንደዋዛ አይጠገንም። ኋላ ለከባድ ፀፀት ከመጋለጥ በፊት በጊዜ መጠንቀቅ ነው የሚበጀው። በተለይ ደግሞ ልጅ ሲኖር ጉዳቱ ጥልቅ ስለሚሆን ይበልጥ መጠንቀቅ ይገባል።

በነገራችን ላይ ሚስት የወር አበባ ላይ እያለች ፍቺ መፈፀም አይቻልም። እንደዚሁም ከወር አበባ ከጠራች በኋላ ግንኙነት ተፈፅሞ ከሆነም ፍቺ አይፈፀምም። ይህንን ሱና መጠበቅ በድንገተኛ ስሜት ፍቺ እንዳይፈፀም ይረዳል። አብዛኞቹ ትዳሮች የሚፈርሱት ጥንዶቹ የጦዘ ብስጭት ላይ በሚሆኑ ጊዜ ነው። ብስጭታቸው እስከሚበርድ ውሳኔያቸውን ቢያቆዩት ብዙ ኒካሕ ከመፍረስ ይድናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

05 Nov, 17:59


⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ባለቤቶች

የሱና ቻናል ተደራሽነት ይበልጥ ይሰፋ ዘንድ
የቻናል ሊንክ መላክ ትችላላችሁ  ⚡️

✍️መስፈርት 1/ :- የሱና ቻናል ሊሆን ስለማጣራ⚫️
✍️መስፈርት2/ ከ1k member በላይ 🔤 ከዛበታች
✍️መስፈርት 3/:-  ቻናሉን አይቼ አሳውቃቹኋለሁ

🚫ግሩፕ አልቀበልም

⭐️ @twhidfirst1
🌟 @twhidfirst1

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

05 Nov, 16:14


CMC አህባሾችና የተብሊጎች መርከዝ
ሙሓደራው በድምፅ ማስረጃ የተደገፈ ነው፡፡

1) የላኢላሃ ኢለላህን ትርጉም ማዛባት፣
2) ኢስላም ላይ መዋሸት፣
3) ውሸታም ሰዎችን ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣

4) በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሙስሊም እራሱን፣ ቤተሰቡን እና መላው ሙስሊም ማህበረሰብን ከ CMC መርከዝ ያርቅ፡፡

ማስረጃውን በጥሞና እናዳምጥ፣ ከዛም በነዚህ ሰዎች ለሚታለሉ ሰዎች እናሰራጨው፡፡

=
t.me/SadatKemalAbuMeryem

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

05 Nov, 13:59


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

04 Nov, 15:42


ጣዝ ማር ለመድሀኒት የምትፈልጉ ንፁህ የጥቅመት ጣዝማ ማር አስገብተናል።


ማዘዝ ለምትፈልጉ ይደውሉ
09 30 32 05 04 
09 30 32 05 04
አቡ ሒበቲላህ ብለው ይደውሉ ። ባሉበት እናደርሳለን

             ወይም

በቴሌግራም አድራሻየ ያናግሩኝ 👇👇👇
@Abu_Hibetilah_bot
@Abu_Hibetilah_bot
@Abu_Hibetilah_bot
@Abu_Hibetilah_bot

አድራሻየ  ደሴ አራዳ

አድስ ነገር ለማገኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

03 Nov, 06:18


أعمالك ثمارك، فلتكن ثمارك طيِّبةً، واجتنب الحرام؛ فإنَّ الحرام خبيثٌ، ولا يليق الخبيث بمَّن طيَّبه الله فجعله مسلمًا، اللَّهم طيِّبنا، وطيِّب لنا، وطيِّب بنا، وتوَّفنا طيِّبين، واحشرنا مع الطيِّبين.

#تغريد_العصيمي
=
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

02 Nov, 15:20


ልክህን እወቅ

🎙Abdu Razaq Baji

=

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

30 Oct, 21:29


ከቁርአን ጋር አንኑር

=
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

30 Oct, 08:29


𖣘ምክር

᯾የቀልቦቻችን ድርቀት

መርከዝ ኢማም አህመድ ላይ የተሰጠ ምክር

🎙ሙሐመድ ሲራጅ ሙ/ኑር


t.me/MedrestuImamuAhmed

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

29 Oct, 13:13


📢አድሱ የጥቅምት ማር ገብቷል

ንፁሄ እንጀራ ማር
ንፁህ ወለላ ማር
ንፁህ ጣዝማ ማር


ለመድሀኒት ለምግብነት የምትፈልጉ ንፁህ ማር አስገብተናል ሳያልቅ ቶሎ ይዘዙ

ማዘዝ ለምትፈልጉ ይደውሉ
09 30 32 05 04 
09 30 32 05 04
አቡ ሒበቲላህ ብለው ይደውሉ ። ባሉበት እናደርሳለን

             ወይም

በቴሌግራም አድራሻየ ያናግሩኝ 👇👇👇
@Abu_Hibetilah_bot
@Abu_Hibetilah_bot
@Abu_Hibetilah_bot
@Abu_Hibetilah_bot

አድራሻየ  ደሴ አራዳ

አድስ ነገር ለማገኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

29 Oct, 05:36


«ማንኛውም ሰው... መልካምን ነገር ጥቂትም ቢሆን ከመፈፀም፤ መጥፎን ነገርም ጥቂትም ቢሆን ከመራቅ ችላ ሊል አይገባውም።
ምክኒያቱም፤ አላህ በየትኛው መልካም ስራው
ምህረትን እንደሚለግሰው፤ በየትኛው ወንጀልም እንደሚቆጣበት አያውቅምና!»

ኢብኑ ሐጀር አል ዓስቀላኒይ (አልፈትህ 11/321)

=
t.me/https_Asselefya1

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

27 Oct, 09:00


استمع للقرآن بقلـبّك

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

27 Oct, 08:30


የመኗኗር ጥበብ
~


"ብልህና አስተዋይ ማለት ከቤተሰቡ፣ ከወዳጆቹ፣ ከጓደኞቹና ከጎረቤቶቹ ትንሽ ትልቁን አጥብቆ የማይዝ ነው።" .
ኢብኑል ጀውዚይ [ተህዝቡል ከማል፡ 19/370]

አንዳንዴ ስህተቶችን አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ ለማለት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

13,474

subscribers

1,580

photos

958

videos