[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa] @ibnshifa Channel on Telegram

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

@ibnshifa


እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ!
በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ!
ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ!
ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa (Amharic)

ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa የሆነው በውጭ በተመቻች ነፃ የተጎበኝ በሙሉ አድራሻ ነው። ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድራሻዎችን ለከባድ ቀንና ሊከተል የተመቻቸው እና የማስረጃውን ተመኝ ማየት ለእናንተ ነው። ማስረጃንና ገንዘብን ለማስነሳት የሚገኝን በጣም ወደ በቃኝ እየተጎበኝ እና በሰዋም እንዳበላት። ሰላም።

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

10 Jan, 17:04


↪️ የጁመዓ ኹጥባ (ምክር)

↩️
خطبة الجمعة؛

➴➴➴➴➴
ርዕስ:-«በስሜት የተበከለ ልቦና» በሚል ወቅታዊ ርዕስ

عنوان
«القلب المريض بالهوى»

➴➴➴➴➴
🎙በኡስታዝ አቡ ዓብዱልዓዚዝ ዩሱፍ ብን አህመድ ሀፊዘሁሏህ

🗓ጥር ‐ 02 ‐ 05 - 2017 E.C

🕌ባህር ዳር ከተማ በሰለፍያ መስጅድ
🕌 بمدينة بحردار [إثيوبيا]؛ في مسجد السلفية

ዝርዝሩን ገብታችሁ አዳምጡ

ይ ደ መ ጥ

share/ሼር/አድርጉ ባረከሏሁ ፊኩም።

#size መጠን 8.36 MB

#length 32:17 min

🕌 በሰለፍያ መስጅድ

🌎ባህር ዳር፣ ኢትዮጲያ

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

10 Jan, 14:18


👉 የነሲሓዎች የአደባባይ ዝቅጠት ለአደባባይ ክስረት

ነሲሓዎች የነበሩበት መንገድ ለዱንያዊ ክብረት እንደማይሆን ሲያውቁ ሸይኻቸው ኢልያስ አሕመድ ህዝቡን አስተኝቶላቸው ከኢኽዋን ጋር ተቀላቅለው መስራት እንዳለባቸው ከወሰኑ በኋላ በ30 የእንቅልፍ ክኒን ወጣቱን አስተኛላቸው ። ቀጥለው የተኛው ህዝብ ሳይነቃ ቶሎ ወደ ሚፈልጉበት ለመድረስ ሩጫ ጀመሩ ። ሩጫቸው ታርጌት ያደረገው የእንጀራ አባቶቻቸው ኢኽዋኖችን ማስደሰት ላይ ነበር ። በዚህም ሸይኻቸው ዶ/ር ጀይላንን ከማወደስ ጀምሮ የተለያዩ ደረጃዎችን በፍጥነት እየተንደረደረ ነጎደ ።
አደባባይ እየወጣ ከነ ካሚል ሸምሱ ፣ አቡ በከር አሕመድ ፣ ያሲን ኑሩ ፣ ሙሓመድ ሓሚዲን ፣ ሓሚድ ሙሳና ሌሎችም ዋና ዋና መሪዮች ጋር በተለያዩ ፕሮግራሞች አብሮነታቸውን አሳየ ። እሱ መርጂዓቸው ስለሆነ እንጂ እነ አዩብ ደርባቸውም በፊናቸው በተለያዩ መድረኮች አብሮነታቸውን አረጋግጠዋል ። ይህ ሁሉ ሲሆን በ30 የእንቅፍ ክኒን እንዲተኙ የተደረጉ ሙሪዶች አልነቁም ነበር ። ይልቁንም እኛ ስለማናውቅ ነው እንጂ እነርሱ ያለ መስላሓ አይሰሩም የሚል የጋራ ድምፅ ያሰሙ ነበር ።
ኢልያስ አሕመድ 30 የእንቅልፍ ክኒን ሲሰጥ አብዛኛው ወጣት ኢኽዋኖችን ያለእውቀታችን በናንተ ላይ ተናግረን ነበር አሁን ተመልሰናል አውፍ በሉን ብሎ ነበር ። ያኔ የ30 ክኒኖቹ ሚስጢር የገባቸው ሰዎች ውስጣቸው እያረረ ኢኽዋኖች በድል አድራጊነት ስሜት ይጎርሩ ነበር ። መሻኢኾችና የተወሰኑ ወንድሞች ያደረጉት የነሲሓዎችን አካሄድ የማጋለጥ ትግል ብዙ ፍሬ ያፈራ የነበረ ቢሆንም የአሁኑ አይነት ድል ይገኛል ብሎ ያሰበ አልነበረም ።
በሚገርም መልኩ ብዙ ወንድምና እህቶች የነሲሓዎች ሸይኽ ሶሞኑን የሱፍያና ኢኽዋንያ ሚንሀጅ እስፕሪስ ጭማቂ ከሚያንቃርረው ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን ጋር የነበረውን ፕሮግራም ካዩ በኋላ አውፍ በሉን ነገሩ በዚህ መልኩ አልመሰለንም ነበር እያሉ ነው ።
ለእነዚህ ወንድምና እህቶች እንዲሁም ለሌሎችም የምንለው መጀመሪያ ምስጋና ሐቅን ላሳወቃችሁ አምላካችን አላህ ይገባው ። ቀጥሎ እኛን በግል በሰድብም ይሁን ስም በማጥፋት ላደረሳችሁት በደል በቅድሜያ እኔ በግሌ አውፍ ብያለሁ መሻኢኾችም ይሁን ሌሎች ወንድሞች ከዚህ የተለየ እይታ ይኖራቸዋል አልልም ። ምክንያቱም ሁላችንም ነብዩን ነውና የምንከተለው ። የአላህ መልእክተኛ አላህ መካን እንዲከፍቱ ድል ሲሰጣቸው እነዚያ መተተኛ ፣ ጠንቋይ ፣ ገጣሚ ፣ እብድ ሲሏቸው የነበሩ የመካ ሹማምንቶች ተሰብስበው ፍርዳቸውን ለመቀበል ሲጠብቋቸው ሂዱ እናንተ ነፃ ናችሁ ነበር ያሉዋቸው ። ነብዩላሂ ዩሱፍም ጉድጓድ ውስጥ የወረወሩዋቸውን ወንድሞቻቸው አላህ ድል ሰጥቶ የበላይ አድርጓቸው አንገታቸውን ደፍተው ይቅርታ ሲጠይቋቸው ሂዱ አላህ ምህረቱን ይስጣቸሁ ነበር ያሉዋቸው ። የሚፈለገው ሐቅን አውቆ ወደ አላህ መመለሱ ነውና የሰዎች ክብር የተነካው በአላህ መንገድ ላይ እስከሆነ ድረስ ከፍታ እንጂ ዝቅታ ስላልሆነ ቦታ አይሰጠውም ። ይልቁንም ይህን ወንጀል ከመስራታችሁ በፊት ከነበራችሁ ደረጃ ይጨምርላችኋል ። ምክንያቱም አላህ ዘንድ አንድ ሰው ወንጀል ሳይሰራ በፊት ከነበረው ደረጃ ወንጀል ሰርቶ ተውበት አድርጎ ሲመለስ ያለው ስለሚበልጥ ።
አሁንም ኢልያስም ሆነ ሌሎች በየቀኑ እየዘቀጡ ማየታችን ለኛ ህመም እንጂ ደስታን አይፈጥርም ። የወንድምና እህቶች መመለስ የሚፈጥረው ደስታ የነሲሓዎች ዝቅጠት ያደበዝዘዋል ። ሙሉ ደስታ የሚሰጠው ሙኻሊፎች ባጠቃላይ ተውበት አድርገው ወደ አላህ መመለሳቸው ነው ። አሁንም ለነሲሓዎች የምንለው በየቀኑ በአደባባይ የምታሳዩት ዝቅጠት ወደ አደባባይ ክስረት እየተቀየረባችሁ ነውና ቆም ብላችሁ አስቡና ተመለሱ ነው ።

https://t.me/bahruteka

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

09 Jan, 19:16


ይደመጥ
ከአል ባዒሱ'ል ሀሲስ ት/ት ክፍል 8 የተወሰደ

🎙ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

የበላይነትና ጥንካሬ ለሐቅ ባለ ቤቶች ነው

🔸አህባሹ አቡበከር ከወሃቢያ ጋር ትልቅ ልዩነት አለን ብሎ አቋሙን ሳያፍር በግልፅ እየተናገረ ወደ ሱንና እንጠጋለን ብለው የሚሞግቱ ሰዎች ግን አንድነት አንድነት እያሉ ከአሕባሽ ጋር ልዩነት የለንም ይላሉ

👉 በሰሞኑ ኢልያስ አህመድ ከኢኽዋኑ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲን ጋር "ወጣትነት እና የጊዜ አጠቃቀም" ብሎ ባደረገው ሙሃዶራ ላይ አንዳች ፋኢዳ ያለውን የተናገረበት ነገር አልሰማሁም!።

ወጣትነት እና የጊዜ አጠቃቀም ከተባለ ወጣቶች መመከር የነበረባቸው በምን ነበር?!

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

08 Jan, 03:43


ከስራዎች ሁሉ በላጩ አላህን በየትኛውም ቦታ ከልብ መፍራት ነው!!
———
ኢብን ረጀብ አል ሀንበሊ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
ከስራዎች ሁሉ በላጩ በድብቅም በግልፅም አላህን መፍራት ነው፣ አላህን በድብቅ መፍራት ከኢማን ጥንካሬ፣ ከነፍሲያና ከስሜት በመታገል የሚገኝ ነው፣ ስሜት በብቸኛነት ጊዜ ወደ ወንጀል ይጠራል፣ ለዚህም ነው ከከባባድ ነገሮች አንዱ አላህን በድብቅ መፍራት ነው ተብሏል።” [ፈትሁል ባሪይ 6/50]

🔸በዚህን ጊዜ አላህን በግልፅ ማመፅ በዝቷል!፣ ይህ የሆነውም አላህን በድብቅ መፍራት አላህ ያዘነላቸው ባሮቹ ሲቀሩ ብዙሃን ዘንድ መጥፋቱ ነው። አላህን በድብቅ መፍራት እየጠፋ ሲሄድ ወንጀል በግልፅ መሰራት ይጀምራል፣ ምክንያቱም አላህ ይጠብቀንና በድብቅ ወንጀል መስራት ከተጀመረ ቆይቷልና ነው።
✍🏻ኢብን ሽፋ
#Join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

07 Jan, 06:07


አይ ኢልያስ አህመድ!!!
➬➬➬➬➬➬

🏝 ከሰሞኑ ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን የነሲሃ ቲቪ እና የአፍሪካ ቲቪ ዱዓቶች ❴በሙመይዓዎች እና በኢኽዋኖች❵ መካከል ምንም ልዩነት የለም። ስለዚህ በአንድ ላይ መገኘት አለባቸው እያለ ተናገረ!

🎙 ➘➴➘➴➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9437

♻️ ንግግሩ መሬት ጠብ ማለት የለበትም ብሎ የሙመይዓዎቹ ተወካይ የሆነው ኢልያስ አህመድ ይሄው ቃሉን ሞላለት! አቤት መከባበር ¡ አቤት ውደታ¡ አቤት ቃል አጠባበቅ¡

👉 ሰዎቹ በደንብ ለይቶላቸዋል ገና ከዚህም የባሱ ጉዶችን እንፈፅማለን የሚሉ ይመስላል። ጉድኮ ነው! ኧረ ከጉድም በላይ!

🔎 አምና ከነካሚል ሸምሱ ከነአህመዲን ጀበል ከነሙሐመድ ሀይሚድን ጋር ሲገናኝ ኧረ ለግል ጉዳይ ነው። ኧረ ለለቅሶ ነው ኧረ.... እያላችሁ ኡዝር ስትደረድሩ የነበራችሁ ሙሪዶች ሆይ! አሁንስ ታለቅሱ ወይስ? መቼስ ለለቅሶ ሄዶ ነው አትሉም ኣ¡

➲ አንዳንድ ታማኝ ሙሪዶችማ «ለመስለሃ እንጂ...» አይይ ሚስኪን! እስከመቼ በዚህ መልኩ ራሳችሁን ትሸውዳላችሁ ኣ!? ዲንን እና ኢልያስን ለዩንጂ ሰዎች!

አጥፊዎች በጥፋት እክከዘወተሩ ድረስ እኛም በማጋለጥ እንዘወትራለን። ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር! አለቀ!

👌 ➴➘➴
https://t.me/AbuImranAselefy/9437

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

06 Jan, 03:40


ጠንካራ መሆን የሚፈልግ በዒባዳ ይጠንክር
———
“የሰው ልጅ አላህን ማምለክ ባበዛ ቁጥር ውስጡም ውጩም ይጠነክራል፣ ልቡም ጠንካራ ይሆናል፣ በሐቅ ላይ ፅናቱም ጠንካራ ይሆናል፣ መሰረቱ ጠንካራ ይሆናል፣ አቅለ ጮሌ ይሆናል። ፊትና ቢከሰት አይጎዳውም፣ ክስተቶችም አይጫወቱበትም፣ የሰውም ሆነ የጂኒ ሸይጧን አይፈራም!። ከመወላወልና ከልብ ስብራት የራቀ ሆኖ እራሱን ልበ ሰፊና ደስተኛ እንዲሁም ነፍሱ የረጋች ሆና ያገኘል!፣ ምክንያቱም ልቡ ከአምላኩ ጋር ጠንካራ ግንኙነት አላት።” [ሸይኽ ረስላን ሀፊዘሁላህ]
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

06 Jan, 03:35


👌 ተአሱብ (ወገንተኝነት) የጥመት አባት እና እናት ነው። ለጎጥህ፣ ለሰፈርህ፣ ለቋንቋህ፣ ለኡስታዝህ፣ ለሸይኽህ፣ ስትወግን ታውረህ ገደል ትገባለህ።
መወገን ለሀቅ ብቻ ይሁን! ለቁርአን፣ ለሀዲስ፣ ለሰለፎች መንገድ፣ ለዲነል ኢስላም ይሁን

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

05 Jan, 08:39


👉 ልዩ የሙሃዶራ ዝግጅት
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

በአላህ ፈቃድ ነገ እሁድ ታህሳስ 27/2017 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሙሃዶራ ዝግጅት ተሰናድቷል

🕰 ሰዓት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

ተጋባዥ:-
ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን (ሀፊዘሁላህ)

ርእስ:- የመሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሪያዎችን የሚያስፈራራበት (የሚያስጠነቅቅበት) ክስተት ነው

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተ ቀኝ ባለው ቂያስ እንገኛለን።
ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

04 Jan, 05:47


በረጀብ ወር ውስጥ የተለየ የአምልኮ (ዒባዳ) አይነት ምን አለ??
—————
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
በረጀብ ወር ውስጥ የሚፆም ፆምና የሌሊት ሶላቶች እንዳሉ የሚጠቁሙ ሀዲሶች በሙሉ ውሸትና ቅጥፈቶች ናቸው።” [አልመናሩል ሙኒይፍ 96]

አል-ሃፊዝ ኢብኑ ረጀብ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
በረጀብ ወር የመፆምም ሆነ ሌሊቱን የመስገድን በላጭነት፣ እንዲሁም ከወሩ የተወሰኑ ቀኖችን መፆምም ሆነ የመፆም በላጭነትን የሚጠቁም አንድም ለማስረጃ የሚሆን ሶሂህ ሀዲስ አልመጣም።” [ለጣኢፉል መዓሪፍ 228]

አቢበክር ኢብኑ አቢ ሸይበህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
አቡ ሙዓዊየህ ከአዕመሽ ይዞ፣ አዕመሽ ከወበረ፣ ወበረ ከዐብዲረህማን፣ ዐብዲረህማን ከኸርሽ ኢብኒል ሁር ይዞ፣ እንዲህ ሲል ነግሮናል:- ሰዎች የረጀብ ወርን በመፆማቸው ምክንያት ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ፆማቸውን ትተው ምግብ እስኪበሉ ድረስ እጃቸውን ሲገርፋቸው አይቻለሁ። እንዲህም ይላቸው ነበር:- ረጀብ የቱ ረጀብ ነው? ረጀብማ በጃሂሊያ ዘመን ሰዎች ያከብሩት ነበር እስልምና ሲመጣ ተትቷል።” [አል-ሙሶኒፍ 9758]

አጃዒብ እኮ ነው! ሠለፎቻችን በዲን ላይ አዲስ ፈጠራን ያመጣን ሰው እንዲህ የገረፉበትም ሁኔታ ነበረ፣ ዛሬ ላይ ግን የሱንና ዑለማዎች በቢድዓ ባለ ቤቶች ላይ ጠንከር ያለ ንግግር ሲናገሩ ሙተሸዲድ፣ ተሳዳቢ፣ ተክፊር… ይባላሉ።

ታላቁ የኢስላም ሊቅ ሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረህመቱላሂ ዐለይሂ - ወቀደሰላሁ ሩሀሁ) እንዲህ አሉ:-
“የረጀብ ወርን በተለየ መልኩ መፆምን በተመለከተማ፣ ሀዲሶቹ በሙሉ ደካማ (ዶዒፍ) ናቸው፣ እንዲያውም ውድቅ የሆኑ (መውዱዕ) ናቸው። አንድም የእውቀት ባለቤቶች ሊደገፉበት የሚችሉበት ደረጃ ላይ አይደሉም። እንዳው ደካማ ቢሆኑም ፈዳኢል ስለሆነ ይሰራባቸዋል የሚባል ደረጃም ያላቸው አይደሉም። ሁሉም ውድቅ (መውዱዕ) የሆኑ በነቢዩ ـ ﷺ ـ ላይ የተዋሹ ናቸው።” [መጅሙዕ አልፈታዋ 25/290]

ታላቁ የኢስላም ሊቅ ዐብዲ'ልዐዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
የረጀብን ወር ‘ሶላተ-ረጘኢብ’ በማለት ወይም 27ኛውን ሌሊት በተለየ ዝግጅት የኢስራእ እና የሚዕራጅ ሌሊት ነው ብሎ ማክበር ሁሉም አዲስ ፈጠራ (ቢድዓ) ነው አይፈቀድም። በሸሪዓችን ምንም አይነት መሰረት የለውም።” [መውቂዑ ሸይኽ - ከዌብሳይታቸው የተወሰደ]

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“የረጀብ ወር ልክ እንደሌሎቹ ወራቶች ነው፣ ከሌሎች ወራቶች በአምልኮ (በዒባዳ) የሚለይ ነገር የለም። ምክንያቱም በሶላት፣ በፆም፣ በዑምራም ሆነ በእርድ በሌሎችም የአምልኮ ዘርፎች ከሌሎች ለየት የሚደረግበት ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተረጋገጠ ነገር የለም። በረጀብ ወር እነዚህ ተግባሮች ይፈፀሙ የነበረው በጃሂሊያ ዘመን ነበር እስልምና ውድቅ አድርጎታል።

አንድ ሰው በዚህ ወር አምልኮ (ዒባዳ) ከፈጠረ፣ በዚህ ወር የሚሰራ የተለየ አምልኮ (ዒባዳ) ነው ካለ፣ ይህ ሰው በዲን ላይ የሌለን አዲስ ነገር ፈጣሪ (ሙብዲዕ) ይሆናል። ምክንያቱም በዲኑ ያልነበረን አዲስ ነገር ፈጣሪ ነው፣ አምልኮ (ዒባዳ) ደግሞ የተገደበ ነው፣ በመሆኑም ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ከሌለው ምንም አይነት ነገር ፈጥሮ ማስቀደም አይቻልም። ምንም አይነት የረጀብ ወር እንደሚለይ የሚጠቁም ሊደገፉት የሚቻል ማስረጃ የመጣ ነገር የለም። የመጡ ሀዲሶች በጠቅላላ ከነቢዩ ـ ﷺ ـ ያልተረጋገጡ (ዶዒፍ) ናቸው። ሶሃቦች በጠቅላላ ከዚህ ተግባር (ረጀብን) በአምልኮ ለየት ከማድረግ በተለየ የረጀብ ወርን ለየት አድርጎ ከመፆም ይከለክሉ ያስጠነቅቁ ነበር። ነገር ግን አንድ ሰው በሌሎች ወራቶችም የሚያዘውትረው የሆነ የሌሊት ሶላትም ሆነ ፆም ከነበረው እንደሌሎች ወራቶች ረጀብ ወር ላይም መፆሙ ችግር የለውም።” [አል-ሙንተቋ ሚን ፈታዋ 1/222–223]

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ አል-መድኸሊይ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“እኛ ሙስሊሙን የምንመክረው እንዲህ ያለውን ውዳቂ ነገር እንዲተው ነው። የጮሀን ሁሉ መከተልንም እንዲተው ነው። ይልቅ በአላህ ገመድ ላይ እንዲጣበቅ ነው ምንመክረው፣ በአላህ ኪታብ (ቁርኣን) እና በነቢዩ ـ ﷺ ـ ሀዲስ ያልተደነገገን ነገር ሁሉ እንዲተው ነው።” [ከዌብሳይታቸው የተወሰደ]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

04 Jan, 05:43


🔥በአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው እሳተ ገሞራ
:
˙
🔘 አፋር ክልል የተለያዩ ቦታዎች ላይ  ሰሞኑን በተከታታይ የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ወደ ከባድና አስፈሪ እሳተ ጋሞራ እየተቀየረ ይገኛል።

🔵 የፈንታሌው የመሬት መንቀጥቀጥ ለኢትዮጵያ የማንቂያ ደወል መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ገለፁ። ሰሞኑን በሬክተር ስኬል እስከ 5 የሚደርስ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የተናገሩት ባለሙያዎቹ፤ ይህም በየቀኑ በተለያየ መጠን፣ በተደጋጋሚ እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።

🟢 የመሬት መንቀጥቀጡ ለመሬት፣ ለትምህርት ቤቶች፣ ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለአንዳንድ ሕንጻዎች እና የአስፋልት መንገዶች መሰንጠቅ ምክንያት መሆኑን አንስተው፤ ክስተቱ የማንቂያ ደወል ነው ብለዋል

🟣 ክስተቱ በፈንታሌ እሳተ ገሞራ አካባቢ ባሉ ነዋሪዎች ዘንድ ድንጋጤ መፍጠሩን ገልጸው፤ መጠኑ እየጨመረ ከሄደ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚፈጠረውን ስጋት ለመቀነስ ተገቢ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

⚫️ የፈንታሌ አካባቢ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ የሚያገናኘው መንገድና የባቡር መስመር የሚያልፉበት መሆኑን ጠቅሰው፤ ክስተቱን እንደማንቂያ ደወል በመውሰድ መንግሥት እንዲሁም የዘርፉ ምሁራንና ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ብለዋል።

🔴 የመሬት መንቀጥቀጥ እንዳይከሰት ማድረግ ባይቻልም አደጋው ቢፈጠር የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል ያሉት ባለሙያዎቹ፤ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለህዝብ ወቅታዊ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

♻️ EBC Facebook Page

© @Khedir_M_Abomsa
⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸
🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

04 Jan, 05:42


🚫 ማቆሚያ የሌለው የነሲሓ ሙሪዶች መከራ

የነሲሓ ከዐቅላቸው የተለያዩ ሙሪዶች ለሸይኻቸው ኢልያስ የሚደረድሩዋቸው ዑዝሮች መና የሚያስቀረው የኢልያስ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቅስማቸው ተሰብሮ አንገታቸውን እንዲሰብሩ ማድረጉን ቀጥሏል ። ነገር ግን ኢልያስ የገባበት እንገባለን የሚያቆመን የለም የሚሉት በውዴታው የታወሩና የሰከሩ ጭፍኖቹ ተከታዮች ስህተቱን የሚያዩበት አይናቸው እንዲታወር ዱዓእ አድርገው ተቀባይነት ያገኘ ይመስላል ።
የኢልያስ አሕመድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የማንነቱ ማሳያ ዛሬ ላይ ከሙሐመድ ዘይን ዘህረዲንና ከሀይደር ከድር ጋር የኢኽዋን ሱፍይና አሕባሽ ጥምር መጅሊስ በ27/4/2017 ቦሌ ወሎ ሰፈር አቡ ሁረይራ መስጂድ ባዘጋጀው የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ፖስተሩ ተለጥፎ እኔ ማለት ይሄ ነኝ እዩኝ እያለ ነው ።
ተቀጥፎት ነው እንዳትሉ ከተማው ላይ ዞር ዞር በሉ ለሱ ኩራት የመሰለው አሳፋሪው ከኢኽዋን አቀንቃኞች ጋር የተነሳው ፎቶ ፖስተር በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ እዩት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1qEAPEj2G4zg_4Qcomh8lShRul4N6XhK2/view?usp=drivesdk
ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን ማለት ማን ምን አይነት ሰው እንደሆነ በሚከተለው ሊንክ ገብታችሁ ተመልከቱ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1rRiinpobQ_AUp_CcJXCkzwZYiPvc-YB7/view?usp=drivesdk

መከረኛ ሙሪዶች ሆይ ይህ ነው ሸይኻችሁ ። ሱብሓነላህ !!! አሁንም ሲያነሱኝ ከአሮጊት ጋር አሁንም ሲያነሱኝ ከአሮጊት ጋር አለ ፎቶ ሲነሳ እድሉ ከአሮጊት ጋር የሆነው ሽማግሌ ። ምነው ሸይኻችሁ ከእነዚህ በኢኽዋንያ ፊክራ የጨረጨሱ አካላት ጋር አደረገው ጓደኝነቱ ? የናንተን ሙሪዶቹን መከራ ለማብዛትና ለኢኽዋኖች ታማኝነቱን ለማሳየት ነው ? ወይስ የናንተን መኖር ከነአካቴው ረስቶት ነው ? እናንተ ዐቅለቢስ መከረኛ ሙሪዶች አሁንስ ሸይኻችሁ ሰለፍይ ነው ? ወይስ ሰለፍይ ማለት ቢዳዓ ነው የደረሳችሁበት የመሟሟት ዝቅጠት ? ነው ወይስ ሁወ ሰማኩሙል ሙስሊሚን የሚለውን አንቀፅ ያለ አግባብ ተረድተው የሚያቅራሩት ቀረርቶ አደንቁሮዋችሁ ነው ? አው ካላችሁ የናንተና ቀብር ላይ ተደፍቶ እያለቀሰ እዱኝ ፣ አሽሩኝ ፣ አክብሩኝ ፣ ለምን ተውኝ እያለ የሙታን መንፈስን ከሚያመልከው ጋር አንድ ነው ? ካልሆነ ቀብር አምላኪዮችን ታከፍራላችሁ ማለት ነው ። ጣፋጩ መራራ ነው ከሁለት አንዱን ምረጡ ። እናንተና አቡ በከርን ፣ ዑመርን ፣ ዑስማንን ፣ ዓኢሻንና ሐፍሳን የሚያከፍሩ ሺዓዎች እስልምና አንድ ነው ? አሁንም አንዱን ምረጡ ።
ዲሞክራሱ ከተከበረ ዲኔ ተከበረልኝ ማለት ነው ። ዒሳም ፍቅርን ያስተማረ ጌታ ነው, ሁሉም ሰማያዊ እምነቶች ፍቅርን ነው ያስተማሩት, ኢትዮዽያ የሸሪዓ ሀገር መሆን አለባት ብሎ ማሰብ በራሱ ወንጀል ነው ብለን ነው የምናምነው, የፈለገ መውሊድ ያክብር የፈለገ ጫት ይቃም አንተ ምን አገባህ, የሚሉ ኢኽዋኖችና የናንተ እስልምና አንድ ነው ? ሸይኻችሁ አንድ ነን ብሎ አደባባይ ላይ አንድነቱን እያሳየ ነው ። እንደነዚህ አይነት ጥያቄዎች ሰምታችሁ መልሱን እንዳታስቡ ቃል ኪዳን ገብታችሁ ለሸይኻችሁ ቆርባችኋል?
አይ የነሲሓ ሙሪዶች ስታሳዝኑ ምነው መከራችሁ በዛ እስኪ የእንቅልፍ ክኒኑ ሀይል አልቆ ከሆነ ወደ አንደኛው ጎናችሁ ለመገልበጥ ሞክራችሁ እዩት !!! ነው ወይስ በድብቅ ካሜራ እይታ ውስጥ ናችሁ የሚል ፁሑፍ አለ ? ለማንኛውም አላህ ይድረስላችሁ ወደ ቅኑ መንገድ ይምራችሁ እንላለን ።

https://t.me/bahruteka

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

03 Jan, 03:15


  ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በሃሮ ከተማ

      ውድ የሱና ቤተሰቦቻችን የነብያት ውርስ የሆነው የተውሒድ ዳዕዋ በሰሜን ወሎ የነብያት አደራ ተረካቢ በሆኑ መሻኢኾች እያበበና አድማሱን እያሰፋ መሆኑ ይታወቃል ። አሁን ደግሞ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 27/04/2017 በሀሮ ከተማ የተውሒድን ችግኝ ለመትከል ቀጠሮ ተይዟል ። በዚህ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ከሰሜን ወሎ መሻኢኾች በተጨማሪ ሌሎች መሻኢኾችና ኡስታዞች ይካፈላሉ ።
     እነማን ካላችሁ የሚከተሉት ይገኙበታል ።

1 – ከስልጤ ዞን ሸይኽ ዐ/ሐሚድ አልለተሚ
2 – ከወልቂጤ   "  "  ሙባረክ ሑሰይን
3 – ከኮምቦልቻ  "  "  ሙሐመድ ጀማል
4 – ከሓራ          "  "    ሙሐመድ ሐያት
5 –  "  "            "   "    ሑሰይን ከረም
6 –  ከተንታ        "  "    ኢስማኢል ዘይኑ
7 –  ከወርቄ       "   "   ሑሰይን ዐባስ 
8 –  ከሃሮ          "    "    ሙሐመድ ስራጅ
9 —  ከሓራ        "   "      ሰዒድ ሙሐመድ
10 – ከኮምቦልቻ ኡስታዝ  ሙሐመድ ኑር
11 – ከአ/አ        "    "     ኡስታዝ ባሕሩ ተካ
12 – ከባሕር ዳር "   "    አቡ በከር
13 – ከመርሳ      "   "       ዐ/ራሕማን
14 –  ከኮምቦልቻ "   "      ኸድር ሐሰን
15 – ከመርሳ       "   "    ኑር አዲስ
16 –  ከሓራ         "   "    ሙሐመድ ሰልማን
17 – ከሸዋሮቢት  "   "    ሙሐመድ አሚን

      በዚህ ፕሮግራም ላይ የሃሮ አልፉርቃን መስጂድን ለማቋቋሚያ የሚሆን ተጨማሪ ፕሮግራም ይኖራል ። በመሆኑም የሱና ቤተሰቦች በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ  አሻራችሁን አኑሩ ይላል ጀማዓው ።

     ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል እንዳታስቡ ።

አላህ ካለ ፕሮግራሙ የሚጀመረው
          ከጠዋቱ  2 : 30 ይሆናል ።
     የእሁድ ፕሮግራማችን ከነቤተሰባችን ሃሮ ፉርቃን መስጂድ እናድርግ ።

   ለበለጠ መረጃ : –
     ስልክ ቁጥር     0920474161
                           0929732296
0935212614

https://t.me/hussenhas

https://t.me/heroselefi

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

02 Jan, 17:46


ስለ አክፍሮት ሀይሎች
ጠንካራ መልእክት!!


በስልጥኛ ቋንቋ (ይደመጥ)

🎙በሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ)

#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

01 Jan, 14:35


የሰዎችን ውዴታ መፈለግ የማይገኝ (የማይሳካ) ግብ ነው!!
—————
ሰዎችን እንዲወዱኝ ብለህ መልፋትህ የማይሳካ ግብ ነው። ዛሬ እንዲወዱህ ብታስደስታቸው ያመሰግኑህ ይሆናል፣ ነገ ስታስከፋቸው ግን ያወግዙሃል። ታዲያ እድሜህ ሁሉ በሰዎች ማመስገንና ማውገዝ መሃል ሆኖ ያልቃል።

ከሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ቀደሰላሁ ሩሀህ) ባልደረባ የሆኑት ኢማም ኢብን ሀብ-ባል አል-በዕሊይ (ረሂመሁላህ) ወደ አንድ ተማሪያቸው በፃፉት ፅሁፍ ላይ በወርቅ ውኃ የሚፃፍ ድንቅ ንግግር እንዲህ በማለት ይናገራሉ:-

= ከዚህ ቀደም ነግሬህ ነበር፣ ታላቃችን የሆነው ሸይኹል ኢስላም ተቂዩዲን አቡል ዐባስ አሕመድ ኢብኑ ተይሚየህ (አላህ ያግዘው፣ ወደርሱም መልካምን ያድርግ!) አንድ ጊዜ 703 አመተ ሂጅራ ላይ ድካ የደረሰ የሆነን ምክር መክሮኛል። ከእርሷም እንዲህ ማለቱን ሸምድጃለሁ:-
“በንግግርህም ሆነ በስራህ የሰዎችን ውዴታ አታስብ። የሰዎችን ውዴታ መፈለግ የማይገኝ (የማይደረስበት) ግብ ነው። ዛሬ ሰዎችን ብታስደስት ያመሰግኑሃል፣ በነጋታው ደግሞ ታስቆጣቸውና ይወቅሱሃል፣ እድሜህ እነሱ ሲያመሰግኑህና ሲቆጡብህ ያልቃል። ለየትኛውም (ለመውቀሳቸውም ሆነ ለማመስገናቸው) እውነታ የለውም። ይልቅ አላህን የምትታዘዝበት የሆነ ነገር ከቀረበልህ የሚያወግዙህ አንድ ሺህ ቢሆኑ እንኳን እሱን አስቀድም፣ ምክንያቱም የላቀው አላህ ሸራቸውን ይበቃሃል።

ይህም ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) በተረጋገጠው ነቢዩ ﷺ እንደሚከተለው በተናገሩት ሀዲስ በመተግበር ነው:-
ሰዎችን አስቆጥቶ አላህን ያስወደደ ሰው አላህ ከሰዎች ቁጣ ይጠብቀዋል።” [ትርሚዚይ 2414 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒይ ሶሂህ ብለውታል]

አላህን በማመፅ ላይ የሆነ ነገር ከቀረበልህ ከፊትህ የሚያወድሱህ ሺህ ሰዎች እንኳ ቢኖሩ ወየውልህ ተጠንቀቅ!! ተጠንቀቅ!!። የላቀው አምላካችን አላህ የሚያወድሱህ የነበሩ ሰዎችን መልሶ አንተው ላይ ይሾምብሃል። ነቢዩ ﷺ ይህን አስመልክተውም እንዲህ ብለዋል:- “አላህን በማስቆጣት ሰዎችን ያስደሰተ ሰው አወዳሾቹን ወቃሽ አድርጎ ይመልስበታል።” በሌላ ዘገባ እንዲህ ብለዋል:- “አላህ ጉዳዩን ወደ ሰዎች አስጠግቶ ይተወዋል፣ ሰዎች ደግሞ አላህ ዘንድ ካለው ነገር አንዳችም አያብቃቁትም።” [ትርሚዚይ፣ ኢብን ሂባንና እንዲሁም ኢብን አቢል ዒዝ በሸርህ ጦሃዊያ ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

ወላሂ በእድሜ ቆይታዬ ለዚህች ምክር ብዙ አስገራሚ ፍሬዎችን አግኝቻለሁ!! አላህ ልባችንን እርሱን በመታዘዝና እርሱንም በመውደድ ይሰብስብልን!! እርሱም ለጋሽና ቸር የሆነ ጌታ ነው።” [አን-ነሲሀት አል-ሙኽተሶህ 42-43]

አንተ ሐቅ ላይ መሆንህ እርግጠኛ ከሆንክ ለሰዎች ውዴታና ጥላቻ አትጨነቅ!! ሰዎችን ለሰዎች ጌታ ተዋቸውና በምትችለው መልካም ነገር ሁሉ ወደፊት ብቻ ተጓዝ!! አላህ በትክክለኛው መንገድ የእርሱን ፊት ፍለጋ ለመልፋት ይወፍቀን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

31 Dec, 17:22


ከጥመት ባለ ቤቶች ማስጠንቀቅ ከዲናችን መሰረታዊ ነጥቦች ነው
———
አንዳንድ አላዋቂ የሆኑ ሰዎች ከጥመት ባለ ቤቶች ማስጠንቀቅ እንደ ሀሜት ይቆጥሩታል። እኛም እንጠይቃቸዋለን:- አንድ ሰው ሆን ብሎ ያለ አግባብ መስጠት እየቻለ ዱኒያዊ ሀቃቹን (ገንዘብ) ነገር ቢበላችሁ አለያም አምናችሁት ቢከዳችሁና ቢያጭበረብራችሁ፣ አጭበርባሪና የሰው ገንዘብ እንደሚበላ አትናገሩም? ዝም ትላላችሁ? መልሳችሁም የታወቀ ነው!፣ በጭራሽ ዝም አትሉም!!
ታዲያ ሰዎችን ዲናቸውን ከሚያጭበረብር የዲን ሌባ ከሆነ ሰው ዝም አለማለት፣ ከጥፋቱና ከጥመቱ ማስጠንቀቅ የበለጠ የተገባ ነው!! ይህም ለእራሱ ምክር ከመሆን ባሻገር የብዙሃንን ዲንና አኼራ መጠበቅም ነው!!

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“ከጥመት፣ ከቢድዐህ እና ከስሜት ባለ ቤቶች ማስጠንቀቅ ከትክክለኛው እምነታችን መሰረት ነው። ይህም ጥርት ያለውን ሸሪዓችን ለመጠበቅ፣ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከተበላሹ እምነቶችና አጥፊ ከሆነው ስሜት ለመታደግ ነው።
- ከቢድዐህ ባለ ቤት ጋር መቀማመጥ ሁለት ጥፋቶችና አደጋዎች አሉበት:-
① ከቢድዐህ ባለ ቤት ጋር በመቀማመጥ የተወገዘን ነገር የመስማት አደጋ አለ
② ይህቺ ሁኔታ (ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር መቀማመጡ) አላዋቂ በሆኑ ሰዎች ላይ ብዥታ ለመጣል እንደ አንድ መንገድ ተደርጋ ትያዛለች።” [ደዓኢሙ ሚንሃጅ አን'ኑቡወህ 141]
✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa
#join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

31 Dec, 17:21


ከምን ጊዜውም በላይ የሰለፊዮችን አንድነት ማጠናከር ያስፈልጋል!
ክፍል 6

በክፍል አምስት ላይ የአል-ዋሊድ፣ ሸይኽ፣ዶኮተር፣ ፕሮፌሰር፣ አል-ዐላመህ፣ አል-ዋሊድ ረቢዕ ብን ሃዲ አላህ ፍፃሜያቸውን ያሳምርላቸውና...ከተለያዩ ከዓለማችን ክፍል፡ ከኢንግላንድ፣ከማልዲቭ፣ ከአሜሪካ፣ ከሲንጋፖር፣ ከሕንድ...በሀገረ መዲና ሸይኹ ጋር በተሰበሰቡበት ድንቅ የሆነን ምክር መለገሳቸውን በጥቂቱ ለማስታወስ ሞክሬ ነበር። ለማስታወስ ያክል ከሸይኹ ወርቃማ ምክሮች እንዲህ የሚል ይገኝበታል፦

❝...በመካከላችሁ (እናንተ ሰለፊዮች ሆይ!) አንድነትን በሁሉም ጉዳዮች ላይ ልታጠናክሩ ይገባል። እጅለእጅ ነው መጓዝ ያለባችሁ!፤በመልካምና በበጎ ተግባራት እንዲሁም አላህን በመፍራት ላይ ተጋገዙ። ከልዩነት፣ ከመከፋፈል... እንዲሁም ሰለፊዮችን ሊከፋፍል ከሚችሉ መንስኤዎችና አመክንዮዎች ራቁ፣ተጠንቀቁ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰለፊዮች ውስጥ የፊትና ማዕበል የሚፈጥሩ፤ይህ ደግሞ የሰለፎች ሚንሃጅ አይደለም። የሶሃቦችም፣ የታቢዒዮችም... ሚንሃጅ አይደለም። ሆን ብለው የሰለፊዮችን መበጣጠስና መከፋፈል የሚፈልጉ፤እንደነኝህ አይነት ሰዎች በእስልምና ውስጥ ክብር የላቸውም፤እንዲሁም በአላህ ዲን ላይ እምነት አይጣልባቸውም። ሰለፊይ ነን ብሎም ቢሞግቱም እነሱ ትክክለኛ "ሰለፍይ" አይደሉም። እንደነኝህ አይነት ሰዎች ትኩረት ተደርጎባቸው "ሰለፊዮችን ለምን ትከፋፍላለህ?" ተበለው ሊጠየቁ ይገባል። እንዲሁም ሰለፊዮችን ለመከፋፈል እነኝህን (ይዟቸው የመጣው የፊትና ወይም እዚህ ግባ የማይባሉ የልዩነት ምክንያቶች) ለምን አላማ ነው ይዘኸቸው የመኸው?! ተብሎ ሊጠየቅ ይገባል...❞ በሚል ድንቅ ምክር ቋጭተን ነበር። የሸይኹ ምክር አላበቃም እንዲህም በማለት ይቀጥላሉ፦

❝...ጥፋት ያጠፋ የሆነ አካል በጥበብ፣በትህትና፣ ለስለስ ባለ ሁኔታዎች ይመከራል። ሪፍቅ ነገራቶችን ያስውባል (ያሳምራል) ሪፍቅ ከሌለ ግን ነገራቶችን ያጎድፋል፤እንዲሁም ሀያእ (ዓይናፋርነትም) ነገራቶችን ያሳምራል።እራሳችሁን በጥበብ፣በሪፍቅ፣በትዕግሥት፣በይቅርታ (አይቶ እንዳላየ)፣...ልታስውቡ (ልታሳምሩ) ይገባል። ይህ በንዲህ እንዳለ፣በሀቅ ላይ ፅናትም ሊኖራችሁ ይገባል። ከፍ ያለው ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡ «ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡» (አሕዛብ:21) እንዲሁም አላህ መልእክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት አወድሷቸዋል፡ «አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡» (አል-ቀለም:4) የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እጅግ በጣም ባማረና በተሟላ (Perfect) በሆነ የስነምግባር ቁንጮ ላይ ነበሩ። ስነምግባራችሁን እንድታሳምሩ እመክራችኋለሁ።

እነኝህን (ከላይ የተጠቀሱትን) ከአይናችሁ ፊትለፊት አድርጓቸው (ተግብሯቸው) የአላህን ፍራቻ ተላበሱ፣ኢኽላስ ይኑራችሁ፣ ለአላህ ባሪያዎች መልካምን ዋሉ፣ቅን ሁኑላቸው፣እርስበርሳችሁ ወንድማማቾች ሁኑ፣ አንድነታችሁን ጠብቁ፣ ለልዩነት መንስኤ ከሆኑ ነገራቶች ሁሉ ራቁ፣ ትዕግሥትን አሳዩ፣ እርስበርስ በጥበብ፣ በሪፍቅ...ተመካከሩ ከፍ ያለው ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፦

«ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡» (ነሕል:125)

በጠላትነት፣በሀይለ-ቃል፣በስድብ...አትመካሩ። ምክንያቱም ይህ የሰለፎች መንገድ (ሚንሃጅ) አይደለምና። ለአላህ ብላችሁ አርበርስ ተፈቃቀሩ፣እርስበርስ ተዘያየሩ፣ ተጠያየቁ... ባረከላሁ ፊኩም!...እነኝህ ወሳኝና አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ናቸው፤በሰለፊዮች መካከል ሊተገበሩ፣ሊፈፀሙ የሚገገቡ ናቸው። አብዛኛው ሰው እነኝህን አስፈላጊና አንገብጋቢ ነጥቦች አሳሳቢ ሆነው ሳሉ ችላ በማለት ትቷቸዋል። እየተፈፀሙ አይደለም፣ እየተተገበሩም አይደለም። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

«ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ!፤ ጀነትን አትገቡም እስክታምኑ ድረስ፣ አታምኑም እርስበርስ እስክትዋደዱ ድረሥ...አልጦቅማችሁንምን እርስበርስ ምትዋደዱበትን?! በመካከላችሁ (እርስበርሳችሁ) ሰላምታን አሰራጩ።»
(ሙስሊም:54)

የሸይኹ ምክር እንደቀጠለ ነው...አላህ ፍፃሜያቸውን ያማረ ያድርገውና ከላይ የተጠቀሰውን የመልእክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐዲስ እንዲህ በማለት ያብራሩታል፦

«ኒያችሁን (Intention) በማስተካከል፣ ጀነተን ፍለጋ፣ ለአላህ ብላችሁ በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ። እንደ ለምድ አድርጋችሁ ሳይሆን ኒያችሁን በማስተካከል ነው መባል ያለበት፤ወደ አላህ እቃረበላሁ፣ ለጀነት ምክንያት ይሆነኛል ብሎ በማሰብ፣ የእንድነትን ዐሻራ (በሰለፊዮች መካከል) ታስቦ ነው ሰላምታው መሰራጨት ያለበት... በጌታዬ ይሁንብኝ! ትክክለኛ "ሰለፍይ" የሆነ ሰው ለሌላኛው የሰለፊዩ ጉዳይ: ያመዋል፣ ይሰማዋል፣ ያሳስቧል... ከአጠቡ የራቀ ቢሆን እንኳ!። እርቆ ያለው ሰለፍይ በሀገረ ጃፓን፣አሜሪካ...የሆነ ቢሆን እንኳ...»

እኛ ኢትዮጵያዊ የሆን ሰለፊዮች ሆይ! ከዚህ ስመጥር ከሆኑት ከሸይኽ፣ዶኮተር፣ ፕሮፌሰር፣አል-ዐላመህ፣ አል-ዋሊድ ረቢዕ ብን ሃዲ አል-መድኸሊይ አላህ ፍፃሜያቸውን ያሳምርላቸውና...ከዚህ ምክራቸው አንፃር የት ነው ያለነው?! እውን እርስበርስ እንዋደደላን? ወይስ....? መልሱን ከራሴ ጀምሮ ሁሉም ሕሊናውን ይጠይቅ! በነገራችን ላይ ባለፉት ጥቂት ጊዚያት ውስጥ ለሰለፊዮች ጉርጓድን ሲቆፍሩ የነበሩ ግለሰቦች አላህ መንጥሮ አውጥቷቸዋል። ይህም ሀገር ያወቀው፣ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ሀቅ ነው። ምን የህል የሞራል ውድቀት እንደደረሰባቸው እራሳቸው ያውቃሉ። ምክንያቱም ከመስመር ውጭ ስለ ተጓዙ። ከነሱ ትምህርት ልንወስድ ይገባል። ዛሬ ደግሞ አንተ ተሰማኒት አለኝ ብለህ፣የፈለከውን ያለማስራጃ ከፍ-ዝቅ የምታደርግ ከሆነ ሁሉም በቁጥጥሬ ውስጥ ነው ብለህ ሴራ፣ ተንኮል፣ እብሪት፣ማን አለብኝነት፣ እንዲሁም ለሰለፊዮች መከፋፈል መንስኤ ምትሆን ከሆነ...እወቅ! የትም አትደርስም። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ። የጥበበኛውና የአሸናፊው የጌታችንን እንዲህ የሚለው ቃል አበከረህ አስተንትን፦

«በምድር ላይ ኩራትንና በክፉ (ተንኮል) መዶለትንም (እንጂ አልጨመረላቸውም፡፡ ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም፡፡ የቀድሞዎቹን ደንብ እንጂ ይጠባበቃሉን? ለአላህ ደንብም መልለወጥን አታገኝም፡፡ ለአላህ ደንብም መዛወርን አታገኝም፡፡» (ፋጢር:43)
@semirEnglish
https://t.me/semirEnglish

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

31 Dec, 15:48


ሒጃብ የሚከለክል አዋጅ፣ ደንብ ወይም መመሪያ የለም
➩➩➩➩➩


🎙 አቶ ብርሃኑ እንዲህ አሉ፦ «በትምህርት ፖሊሲው ሒጃብ መልበስ የተከለከለ ነገር የለውም።»
ታዲያ በአክሱም ያሉት የትምህርት ቤት አስተዳደሮች በየትኛው ፖሊሲ እየተመሩ ነው? ተናበቡንጂ ጋሼ!

🎙 «በኒቃብና በጅልባብ መካከል ያለው ልዩነት...»
ተው በማይመለከትዎ አይግቡ በልኩ ሆኑ ኒቃብም እንደማንኛውም መብታችን የሚከበርልን የእምነታችን አካል ነው። security የሚሉትን ጉዳይ ሌላ መፍትሔ ፈልጉለት! ለመሆኑ ኒቃሲስቷ የምታመጣው አደጋ ካለ በሌሎቹ ምን ዋስትና አለ? ወይስ የሴኩሪቲው ጉዳይ ያለው በፊቷ ነው?

🎙 «በሒጃብ ደረጃ የተከለከለ የለም። ማንም ይሄንን የሚከለክለው አዋጅ የለም፤ ደንብ የለም፤ ይህንን የሚከለክል መመሪያ በትምህርት ሚኒስተር በኩል የወጣ የለም።»
እውነታው ይህ ከሆነ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ቀጥሎም አሁን በአክሱም እየተሰራ ያለው ምንን ተመርኩዞ ነው? ስንት አስተዳዳሪዎች ናችሁ? ሲከሰትስ በፍጥነት መልስ አትሰጡም?

🏝 ተናባችሁ የምትሰሩ ከሆነ ሞክሩ ካልሆነ ሙስሊሞችን እየነካካችሁ መውደቂያችሁን አታመቻቹ! የተደበላለቀ አካሄድ ይዞ ዜጎችን መረበሽ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመሆኑ ራሳችሁን መርምሩ!!!

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

30 Dec, 14:21


እንዴት - በአላህ ለመካድ እንኳን አደረሳችሁ - ይባላል?!
—————
አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ እያለ:-

قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ ۞ اللَّهُ الصَّمَدُ ۞ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ۞ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ

«በል፣ እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡» አል-ኢኽላስ 1-4

በዓለማቱ ጌታ በብቸኛው አምላክ አላህ ክዶ። "አልወለድኩም አልተወለድኩምም" እያለ፣ እርሱም በብቸኝነት እንዲመለክ ጥሪ የሚያደርጉ መልእክተኞችን ልኮ፣ ከመልእክተኞችም ውስጥ የላከውን መልእክተኛ ነቢዩ ዒሳን (ዐለይሂ ሰላም) "አምላክ ነው፣ ጌታ ነው፣ ለእኛ ብሎ ተሰቀለ…" ብለው የሚያመልኩ አካላትን አዕምሮ ያለው ስለ እስልምናው የሚያውቅ ሙስሊም እንዴት ለዚህ ክህደታቸው "እንኳን አደረሳችሁ" ይላል?!።

📩 የደረሰው ላልደረሰው ያድርስ!! ለየትኛውም የከሀዲዎች በዓላቶቻቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት በእስልምና ሀይማኖት የማይፈቀድ በጥብቅ የተከለከለ (ሀራም) የሆነ ከባድ ወንጀል ነው!!

ልብ በሉ! ለምሳሌ:- አንድ የሰውን ህይወት ያጠፋ ሰው "እንኳን ለዚህ አበቃህ (አደረሰህ)" ተብሎ የደስታ መግለጫ እማይደረግለት ከሆነ፣ ከዚህ የከፋውን ተግባር በመፈፀም በአለማቱ ጌታ በብቸኛው አምላክ አላህ ክዶ እንኳን በፈጣሪህ ክደህ ያሻህን ልታመልክ፣ ለጣዖት፣ ለፍጡራን ልታጎበደድና ልትሳል፣ ያሻህን እርም የተደረጉ ተግባራትን ሁሉ ልትሰራ፣ ልትሰክርና ልትጠጣ፣ ልታመነዝር፣ አደረሰህ ይባላልን?! በፍፁም!! እስልምና አጥብቆ ያወገዘው ተግባር ነው!!

በበዓላቸው ልጆች እንዳይቦዝኑብኝ ብሎ ማረድም ሆነ ሌሎችን ከነሱ የሚያመሳስል ነገር መስራት አይፈቀድም!! የሙስሊም ልጆችን የራሳችን የሙስሊም በዓል አለን ብሎ ማስተማር ነው!!

እነሱ ለበዓላቸው የሰሩትን ቅመሱ ብለው አምጥተው ቢሰጡ ተቀብሎ መብላትም አይፈቀደም!!

እነሱ ለራሳቸው ጊዜ ጥግ የደረሱ አክራሪዎች ሆነው የነሱን እምነትና ባህል የኛም እምነትና ባህል እንዲሆን ይተጋሉ!። እነሱ "የእኛ እምነትና በእምነታቸው የተመሰረተ ባህላቸውን ለምን የበላይ አልሆነ" ብለው ነው ሀገር የሚበጠብጡት። እኛን ደግሞ የራሳችን በሁሉ ነገር ላይ የእራሱ መለኮታዊ ህገ-ደንብ ያለው ድንቅ ሀይማኖት አለን ብለን ቆፍጠን ስንል "አክራሪ፣ ፀረ አንድነት፣ ፀረ ሰላም፣ ፀረ መቻቻል… ፀረ ፀረ ፀረ…" ይሉናል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖቱን እሴት አክብሮ ሊኖር ይገበዋል። ከከሀዲዎች ጋር የጋራ በዓልም ሆነ እምነት የለንም!!። ለኛ የራሳችን እምነትና በዓል አለን!!። የምናደምቀው የራሳችን እምነትና በዓል ነው። በነሱ በዓል ጊዜ ሙስሊሙ አብሮ ግርግር እንዲፈጥር የሚያደርገው ነገር የለም።

አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ ۝ لَا أَعْبُدُ مَا تَعْبُدُونَ ۝ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ ۝ وَلَا أَنَا عَابِدٌ مَّا عَبَدتُّمْ ۝ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ ۝ لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ

«በላቸው፣ እናንተ ከሓዲዎች ሆይ! "ያንን የምትግገዙትን አልግገዛም፡፡ እናንተም እኔ የምግገዛውን ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡ እኔም ያንን የተገዛችሁትን ተገዢ አይደለሁም፡፡ እናንተም እኔ የምግገዛውን (አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡ ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ!፡፡» አል-ካፊሩን 1-6

ይሄው ነው! እስልምናችን መጨመላለቅንና አጎብዳጅነትን አላስተማረንም!! ሀይማኖትህን ለማስከበር ቀድመህ አንተው መርሆዎቹን አክብር!!።

👉 በተለያዩ ቃላት ሊያጃጅልህ ሲሞክር መጃጃልህን ትተህ አትተሻሽ "አይ! እምነቴ አይፈቅድልኝም!።" በለው።

ይህን ጉዳይ የሚመለከቱ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎችን እንዲሁም የታላላቅ ሊቃውንቶችን ንግግር በርካታ ከመሆናቸውም ጋር ከጊዜ ጥበትና ፅሁፉ እንዳይረዝም፣ ብዙዎች ዘንድ በከፊሉም ቢሆን የሚታወቅ ከመሆኑም አኳያ አልጠቀስኩም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

29 Dec, 04:18


መንግስት ፅንፈኝነትን የሚያራምዱ ፅንፈኛ ክርስቲያኖችን ከመንግስት ተቋማት ሊያስወግድና እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል!!
—————
ለመንግስት ተቋማት እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ብዙ ጊዜ ከሙስሊሙ የተለመዱ አይደሉም። ሙስሊሙ ምንም ያህል ቢጨቆንና ቢሰቃይ በዝምታ አለያም ለጊዜው ብቻ ጮሆ ያቆማል። እነሱ የመንግስት ተቋማትን ተደግፈው አገሪቷን እንዳሻቸው ለማተራመስ እንቅፋት የሚሆንባቸው አንድ ሙስሊም ባለ ስልጣን ካለ ከማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አልፈው በኤሌክትሮኒክስና በህትመት ሚዲያዎች ይዘምቱበታል። ምን ይህ ብቻ፣ የማይፈልጉትን ሙስሊም ባለ ስልጣን ከነበረበት ስልጣን ዘወር እስኪደረግላቸው ድረስ ሁሉ የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን ቢሮዎች በር ከማንኳኳት አይወገዱም።

እነሱ ግን ሙስሊሙ ግብር የሚከፍልባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶችን እና ትምህርት ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ሙስሊሙን መጨቆኛና ማሰቃያ ልዩ መሳሪያ አድርገው ከያዟቸው ዘመናትን አስቆጥረዋል። መንግስት ት/ቤቶችንና ተቋማትን ሴኮላር ማድረግ እፈልጋለሁ ካለ በቅድሚያ እንዲህ ካሉ በተቋማት ስር ከተሰገሰጉ ፅንፈኞች ሴኮላር ያድርገው።

በተለያዩ ጊዜያት የሙስሊም ተማሪዎችን ሮሮ መስማት የተለመደ ቢሆንም የሰሞኑ ግን በአንፃሩ ለየት ያለ ነው።
ከዚህ ቀደም በነበሩ ጊዜያት ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን "ሙሉ ሃይማኖታችሁ የሚያዛችሁንና ግዴታ ያደረገባችሁን (ሙሉ ፊትን ጨምሮ) መሸፋፈኛ ሒጃብ አውልቃችሁ ተገላልጣችሁ ካልሄዳቹ አትማሩም" በሚል የተለያየ ስቃይ ሲደርስባቸውና የት/ት ፈተና በሚደርስባቸው ጊዜያት ጠብቀው ሲያስለቅሷቸው ቆይቷል። እንዲሁም ወንዶችን ግዴታ የሆነውን የጀመዓና ጁምዓ ሶላት አትሰግዱም እያሉ ሲያሰቃዩዋቸው ቆይተዋል።
አሁን ግን ጭራሽ የፀጉር መሸፈኛ ሻሻችሁን አውልቃችሁ እንደ እንስሳ እርቃናችሁን ሆናችሁ ካልሆነ አትማሩም እያሉ ነው። የከሀዲያን ምኞች ከዚህም ያለፈ እንደሆነ አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ በማለት ተናግሯል:-

وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ

«አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡» አል-በቀረህ 120
ይሄው ነው የእነሱ ምኞት።

በጭፍን ጥላቻ ተነሳስተው ፅንፈኛ ክርስቲያን ርእሰ መምህራን እና መምህሮች በእስልምና መተግበራቸው ግዴታ በሆኑ ተግባሮችና በሴት ልጅ ከሃይማኖቷም ባሻገር በተፈጥሮ ግዴታ የሆነባትን የመሸፋፈን መብቷን በመከልከል በ21ኛው ክ/ዘመን "ሰለጠን" የሚሉ ኋላ ቀር የሰው ሰይጣኖች አደገኛ ጭቆና ውስጥ ገብተዋል።

ይህ ፅንፍ የረገጠ ጭፍን ጥላቻቸው የወለደው የጭቆነ አይነት መሆኑ ነው። በቁጭት ነድደው ይከስሉ እንደሆን እንጂ ለአለማቱ ጌታ አላህ የላቀ ምስጋና ይገባውና ትላንት በተለያየ ጭቆና ከነ ፂማቸውና ኒቃባቸው ተምረው የጤና ባለ ሞያና መሀንዲስ ከሆኑ ብዙ ሙስሊም ወንድምና እህቶች የበለጠ ሙስሊሙ ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ የሚማርበት እድሉ ሰፍቷል። (ባይሆን ግን ከአሁን ቀደም በተለያዩ ጭቆናዎች ተምረው ጥሩ ደረጃ የደረሱ ሙስሊሞች በነሱ ላይ የደረሰው "በኛ ይብቃ" ብለው፣ ሸሪዓን በማይፃረሩ በተለያዩ ዘዴዎች በያሉበት ተቀናጅተውም ይሁን በግል ጭቆናው እንዲቀር ለማድረግ መታገል ይጠበቅባቸዋል።)

ገርሞ የሚገርመው! የከረረ ፅንፈኝነታቸውን እና የአፄ ሀይለ ስላሴን ሙስሊሙን ከትምህርት የማግለል እስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከራቸውን እያሳዩን መሆኑ ነው እንጂ የራሳቸውም እምነት መፅሃፋቸው ሴት ልጅ ፀጉሯን እንድትሸፈን ያዛል።

ሴቶች ኀፍረተ-ገላቸውን ተገላልጠው ወንዶችን ከመማር በሚረብሽ መልኩ ተራቁተው እየሄዱ "ነፃነትና መብት" የሚል ታፔላ ለጥፈውለት ሲያበቁ ሙስሊም ሴቶች ፀጉራቸውን እንኳን መሸፈኛ ሻሽ መከልከላቸው ጥላቻ ያወራቸው ባለ ዲግሪ ደደብና የሴቶችን ገላ የማየት ሴሰኝነት የተጠናወታቸው ርካሾች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። እንዲህ ያሉ ርካሽ ስነ-ምግባር ያላቸው መምህራን እና የት/ቤቶች ኀላፊ የሆኑ ሰዎች ለራሳቸው መልካም ስነ-ምግባር ሳይኖራቸው እንዴት የት/ቤት ኀላፊነት ይጣልባቸዋል?!

እደግመዋለሁ!፣ መንግስት እንዲህ ያሉ በሰዎች መብትና ነፃነት የግል ቂምበቀል የሚወጡ፣ መንግስትና ሕዝብን የሚያጋጩ ፅንፈኝነትን የሚያራምዱ ባለ ዲግሪ ደደብ ፅንፈኛ ክርስቲያኖችን ከተቋሙ ሊያስወግድና እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል!!

በተቻለ መጠን እንዲህ ያሉ ክስተቶችን ጊዜያዊ አጀንዳ ብቻ ከማድረግ ይልቅ በዘላቂነት መብት የሚከበርበትን መንገድ መፈለጉ ተገቢ ነው!።
✍🏻ኢብን ሽፋ: ጁማዱል አኺር 28/1446 ዓ. ሂ
» » » ታህሳስ 20/2017
#Join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

29 Dec, 03:29


ሌላም ማለታቸው አይቀርም
¯¯¯¯¯¯¯👌

የአክሱሞቹ ፀጉራችሁን አትሸፍኑ ይላሉ፤ በአንዳንድ ዩኒቨርስቲ ያሉ ቅሪቶቻቸው ደግሞ ፊታችሁን አትሸፍኑ ይላሉ። ቢሳካላቸው ከነዚህም የባሰ ማለታቸው አይቀርም።

ሰዎቹ ለኢስላም እና ለሙስሊሞች ያላቸው ጠላትነት ከአቅማቸው በላይ ነው። እሺ ፊታቸውን ከሸፈኑ የማንነታቸው ጉዳይ ያሳስበናል እያሉ ነበር። የፀጉራቸው መሸፈንስ? ምን ሊሉን ይሆን?

ቢያንስ አፄ ዮሃንስ የተባለው ጨካኝ ቦሩ ሜዳ ላይ በሰራው ሰይጣናዊ ተግባር በሙስሊሞች ላይ ምንም ተፅዕኖ ማድረግ እንዳልቻለ መገንዘብ ያቃታቸው ደካሞች ዛሬም በደልን በሙስሊሞች መጫን ይፈልጋሉ! አይ አለማወቅ በተካኩን ቁጥር ሀያል እንደምንሆን ቢያውቁ ኖሮ በእንክብካቤ በያዙን ነበር።

قُلْ مُوتُوا بِغَيْظِكُمْ
«በቁጭታችሁ ሙቱ፤» በላቸው


👌       ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/9548

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

29 Dec, 03:28


ፀጉራችሁን አትሸፍኑጉድኮ ነው!

በአክሱም እየተደረገ ያለው ግፍ በዚህ ዘመን መሆኑን ለማመን ይከብዳል። ተማሪዎች ፀጉራችሁን አትሸፍኑ በማለት ከሃይማኖታዊ ህይወታቸው ለመገንጠል እየተሰራ ነው። ሰዎቹ ግን ምን አይነት አስተሳሰብ ቢኖራቸው ነው?

በእርግጥም አላህ ነግሮናል፦
وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُم ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِن اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡

አል-በቀራህ - 120

👌 አዎ በሚችሉበት መንገድ ወደ ኩፍር መሳብ ይፈልጋሉ፤ የወዳሉም፤ ነገር ግን ለነሱ ፊት መስጠት አያስፈልግም።

👉 የነሱን ዝንባሌ መከተል ማለት ከሀያሉ አላህ መራቅ ነው። የአክሱም ሙስሊሞች ሆይ! ጠንከር በሉ

👌 የገረመኝ ❝በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም❞ ያሉት የትምህት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ሙሉ ስማቸው ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር  ነው
➶ እንዴ ከዚህ በላይ ሀይማኖትን ማንፀባረቅ አለ? መጀመሪያ ስሙን ይቀይር! ከፈለገ "ዝናቡ" ወይም "ዘላለም" ወይም “ዘነበ” ይበል። ካልሆነ አርፎ ይቀመጥ


🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
                 🏝 ⇣⇣⇣
https://t.me/AbuImranAselefy

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

27 Dec, 16:39


(☝️)
በዐቅሉ የተጫወተው የሙነውር ልጅ ሰለፊዮችን "ወፈፌ፣የእንጨት ሽበት፣ሸንበቆ... ብሎ የሚሳደብ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችን ፅሁፍ ደግሞ በቻናሉ ላይ ሼር ሲያደርግ ተመልከቱ....

የሙብተዲዕ ጤነኛ አላየንም ሲሉ ሰለፎች ለካስ በምክንያት ነው...

@semirEnglish

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

27 Dec, 15:51


↪️ የኢብኑ ሙነወር የድሮ የ2006ቱ አቋም እና የአሁኑ የ2017ቱ አቋም ሰማይና ምድር ሆነው አስታዘቡኝ

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

27 Dec, 03:43


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

25 Dec, 12:31


የሙነወር ልጅ ማምታቻ እስከ የት?!
—————
የሙነወር ልጅና የቡድኑ ዋና ዋና አባላት ከነበሩበት ጠንካራ የሱንና አቋምና በቢድዐህ ባለ ቤቶች የሰልላ ሰይፍ ሆነው ከማስጠንቀቅ ፈፅሞ ባልተጠበቀ መንገድ ቁልቁል ሲወርዱ (የተምይዕ ዋሻ ሲሆኑ) ከታላላቅ የሱንና መሻይኾችና ኡስታዞች ለሚደርስባቸው በማስረጃ የታገዘ ጠንካራ ምላሽ ተደናግረው ከትክክለኛ ማስረጃ የተራቆቱ በመሆናቸው መቋቋም ሲያቅታቸው ቲፎዞዎች እንዳይበተኑባቸው፣ የትቢትና በባጢል ላይ የጭፍን እልህ (ደራ) ባለ ቤት የሆነው የሙነወር ልጅ የሚደርስባቸውን ጠንካራ ምላሽ ይመክትልኛል ብሎ የያዘው መንገድ (ስልት) "በማስረጃ ማሳመን ካልቻልክ አደናግር" የሚለውን አባባል ነው።
ይህ የትም አያደርሳቹም!! ቲፎዞ እንዳይበተን ተጨንቆ ባለ በሌለ ሀይል ስራዬ ብሎ ለማደናገር መሯሯጡና አድፍጦ መጠበቁ የባጢልና የፖለቲካ ባለ ቤቶች መገለጫ ነው!!። ከእልህና ከትቢት ውጥረት ውጡና ትላንት የነበራችሁበት የሐቅ አቋም ላይ ሁኑ!! ለዱኒያቹም ለአኼራቹም የሚጠቅማቹ እሱ ነው።

🔸የሙነወር ልጅ ትላንት ከሶስት/ከአራት አመታት በፊት፣ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ (የነሲሃ) አመራሮች በድብቅ እየተሸማቀቁ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር በኢፍጣር ሰኣት የተነሱትን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለቆ "ነጭ ነጯን እንናገራለን" በማለት የጀመረውን ምላሽ የት አደረሰው? ወይስ የመርከዙ ሰዎች ከዛ በኋላ ደንግጠው ተውበት አድርገው ትተውት ወደ ሱናው ተመልሰው ነው?! በጭራሽ!!
የመርከዙ ሰዎችማ ከትላንቱ መደባበቅ ወጥተው ስለ ዲናቸው ጠንከር ያለ እውቀት ለሌላቸው ነጋዴዎች እንኳን ግልፅ በሚሆን መልኩ በአደባባይ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር መደባለቃቸውን አውጀዋል። በኮንፈረንሶቻቸውና በተለያዩ ዝግጅቶቻቸው ከአል ኢኽኑል ሙስሊሚን ጋር መደመራቸውን ከቱባ ቱባ መሪዎች ከነ ጀይላን፣ ኢብራሂም ቱፋና ሙሀመድ ሃሚዲን… መሰሎች ጋር ሆነው አንድ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ መድረኮች ሆነው ፎቶና ቪዲዮ በመልቀቅ ለህዝቡ በግልፅ አሳይተዋል። ከዚህም ባሻገር በየ ቦታው (በከተማ በገጠሩ) ከኢኽዋኖች ጋር ሆነው መጅሊስ ውስጥ ተሰግስገው የመንግስት የፀጥታ አካላትን በማሳሳት የሰለፊያ ደዕዋን ለማደናቀፍ እየታገሉ ነው። በነዚህ ሰዎች ላይ ብዕርህ ለምን ደለዶመ?!

🔸 የሙነወር ልጅ ሆይ! እስቲ ልጠይቅህ ለማደናገር መፍጨርጨርህን ትተህ በግልፅ ተናገር፣ ዛሬ ላይም እነዚህ የመርከዙ አመራሮች አንተ ዘንድ ሰለፊይ ናቸው?!
የጀርህና ተዕዲልን ነጥብ ጉዳይ አቆየውና ይህን ጥያቄ መልስ፣ ምክንያቱም አንተ ስለ ጀርህና ተዕዲል ነጥብ የእውቀቱም ሽታ የለህም!! ለዚያም ነው "ውሃ ሲወስድ ውሃ ይጨበጣል" እንደሚባለው፣ ጭልጥ ወዳለው የተምይዕ ዋሻ ውስጥ ስትገባ በዚህ ርእስ ላይ ይረዳኛል ያልከውን አሰስ'ገሰሱን ኮተቱን ሁሉ ምኑንም ከምኑም ሳትለይ ከተለያዩ ዌብሳይቶች እየለቃቀምክ የነበረው። ይህ አላዋጣ ሲልህ ነው
ሰለፊዮችን አድፍጠህ ጠብቀህ የተቆራረጡ የሰለፊዮችን ቃላቶች እየመረጥክ በቃላት ስንጣ የተጠመድከው።
- ያ ሁሉ በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ የነበረህ ሀይል የት ገባ?! ተውበት አድርገው ሁላቸውም ሰለፊዮች ሆነው ነው ወይስ አንተ ወደ ባጢል ሰዎች ተውበት አድርገህ ነው በሱንና ሰዎች ላይ አንበሳ በቢድዐህ ሰዎች ላይ ሬሳ የሆንከው?!
ለቀድሞዎቹ ኢኽዋኖችና ለቅርብ ጊዜዎቹ የነሲሃ ቲቢ ባለቤት ኢኽዋኖች ሽንጥህን ገትረህ ትከላከላለህ፣ በቀድሞው አቋማቸው የፀኑ መፅሃፍህን መቅደም በማድረግ ሲያበረታቱህ የነበሩ ጠንካራ የሱንና መሻይኾችን ደግሞ የተለያየ ጥላሸት በመቀባትና ውሃ በማይቋጥሩ ነገሮች በመተቸት ሰዎች እንዲርቋቸው ለማድረግና ጭፍን ተከታይ ቲፎዞዎችህ እንዲቆዩልህ ትፍጨረጨራለህ!!። በዚህ ስልትህ ጭፍን ተከታዮችህን ከጥመት ቡድኖች ጋር እንዲግበሰበሱ አድርገሃል።
ይህ ነው አይን ያወጣ ያፈጠጠ ጥመትና የተምይዕ ዋሻ መሆን። ሑዘይፋ ኢብኑል የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ጥመት ብሎ ማለት፣ ትክክለኛው ጥመት የምታወግዘው የነበረውን ነገር እውቅና መስጠትህ ነው። የምታውቀው የነበረን ሀቅ ደግሞ ማውገዝህ ነው። ወዮልህ በዲን ላይ መቀያየርን ተጠንቀቅ!፣ የአላህ ዲን አንድ ነው።” [አል-ኢባነቱል ኩብራ 571]
አላህ ከጭፍን ተከታይነትና በባጢል እልህ ውስጥ ከመግባት ጠብቆ እሱን እስክንገናኘው ድረስ በሐቅ ላይ ያፅናን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

25 Dec, 04:22


ኢብኑ ሙነወር በራሱ ብዕር የሚከተሉትን መስክሯል፦
👉 ኢብኑ ሙነውር ድንበር አላፊ መሆኑን
👉 ኢብኑ ሙነውር አስቀያሚ ባህሪ እንዳለው
👉 ኢብኑ ሙነውር ነውረኛ ግለሰብ መሆኑን በአግባቡ ተናግሯል።

ምክንያቱም ሰሞኑን ሸይኽ አብዱልሐሚድ ባስተካከሉት ነጥብ «ብየም ከሆነ ተመልሻለሁ» ባሉበት ነጥብ መነሻ አድርጎ “ወፈፌ” እያለ የአደበ-ቢስ ወይም ስርዓት-አልባ ሰው ገለፃ አስቀምጧል። ስለዚህ ራሱ እንዳለው «ድንበር አላፊ መሆኑን፣ አስቀያሚ ባህሪ እንዳለው፣ ነውረኛ ግለሰብ እንደሆነ አረጋግጠናል።

بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ
በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡
[አል-ቂያማህ - 14]

የሚነሳ ማምታቻ፦
👉 ምናልባት ሸይኽ አብዱልሐሚድ የሰጡት ማስተካከያ ሳይደርሰው ቢሆንስ? የሚል ሀሳብ ከተነሳ የሚከተሉትን እላለሁ፦
❶ኛ በኔ ግምት ይደርሰዋል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም ከማንም በላይ ለሚዲያ Active ነውና። በተጨማሪም ይህንኑ ተግባር ከዚህ በፊት ፈፅሞ ሰዎችን እንዲጠሉ ለማድረግ ተጠቀመበት እንጂ ማስተካከያ አላደረገም። ስለዚህ የሸይኽ አብዱልሐሚድ ማብራሪያ ያልደረሳቸውን ሰዎች ሸይኹን እንዲጠሉ ማድረግ ዋና ፍላጎቱ ነው።

ኢብኑ ሙነወርና ግብረአበሮቹ ከዚህ በፊት ልክ የአሁኑን አምሳያ ማጭበርበሪያ ሲያሰራጩ አላህን ፍሩ በተመለሱበት አትውቀሱ ብለናቸው ነበር ግን ግፋቸውን አላስተካከሉም።
ተመልከቱ ➴➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/8723

ሌላኛውን እዩት ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/7993

👌 ስለዚህ ሰዎቹ እንደምንም ተፍጨርጭረው የመረጃ እጥረት ያለባቸውን ሰዎች ማታለል ዋና አላማቸው ነው።

❷ ሸይኹ ያስተካከሉበት ካልደረሳቸው ይሄው ልከንላቸዋልና ያስተካክላሉ። ካልሆነ ግን እንዳሉትም ነውረኞች ናቸው!

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

25 Dec, 04:17


አዲስ ደርስ ተጀምሯል

ኪታብ:- ኢጅማዑል ዑለማእ ዐለልሐጅሪ ወትተህዚር ሚን አህሊል አህዋእ

ቀን:- ከሰኞ እስከ ጁምዐህ
ሰኣት:- ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ

🎙ሸይኽ አህመድ አወል (ሀፊዘሁላህ)
የኪታቡን pdf ለማግኘት⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/9100

ገባ👇ገባ👇በሉ
https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=bc12aa84a6bc7f76d9

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

24 Dec, 14:18


የሙነወር ልጅ ማምታቻና የሸይኽ ዐብዱልሀሚድ (ሀፊዘሁላህ) መልስ

🔹የዲን አጭበርባሪው የሙነወር ልጅ፣ አንድ በክርክር መሃል ከሸይኽ ዐብዱልሀሚድ ተቆርጣ የወጣችን የቆየችና ከዚህ በፊት መልስ የሰጡባትን ድምፅ ለቆ ቲፎዞዎቹን ለማምታታት ሲሞክር "የሚጮሁትን የማይኖሩ…" በማለት እየቃዠ ለቋታል።

ከሸይኽ ዐብዱልሐሚድ (ሀፊዘሁላህ) ተቆርጦ ሲበተን ለቆየው ድምፅ ወንድማችን ኡስታዝ ባህሩ ተካ (ሀፊዘሁላህ) ጠይቋቸው ሸይኹ የሰጡትን መልስ ከራሳቸው አንድበት አድምጡት።
#join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

24 Dec, 11:41


ተስፋ አትቁረጥ!! ይልቅ ፈጣንና ብልህ ሁን!!
———
ኢማም ዐብዱል ዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
“ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም!!። የቢድዓ ሰዎች ርስበርሳቸው ይተባበራሉ ተስፋ አይቆርጡም፣ ይልቁንም በሁሉም መዳረሻዎች ወደ ጥመት ይጣራሉ፣ በማህበራዊ ሚዲዎች፣ በቲቪ፣ በጋዜጣ፣ በመፅሃፎች… ይጣራሉ። ይህ እንግዲህ ባጢል ነው። ወደ እሳት ነው የሚጣሩት። እነዚያ ወደ ጀነት የሚጣሩ ሰዎች ከነሱ የተሻለ የሚጓጉ ጀግናና ፈጣን ሊሆኑ ይገባል!!።” [አት-ተዕሊቅ ዐለ ነድወቲ ዘካት ከሚለው ካሴት]

ሸይኽ ብን ባዝ ይህን ያሉበት ወቅት ሶስት አስርተ አመታት ገደማ ነበር። ዛሬ ነገሩ ሸይኹ ከተናገሩትም በርትቷል። የቢድዓ ሰዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችንም ሆነ ሌሎችን የብዙሃን መገናኛዎችን በመጠቀም የሱንና ሰዎች እንዳይታዩና ሀቅን እንዳያሰራጩ ጥረታቸውን ተያይዘውታል። ነፍሲያ፣ ስሜትና ቡድንተኝነት የሚጋልባቸው ሰዎች ብሰዋል። በተቻላቸው ሁሉ ሱንናን ይዋጉበታል፣ እስልምና ስሙ እንጂ እንዳይቀር ይተጋሉ፣ (ምክንያቱም ቢድዐና ስሜታዊነት ሲስፋፋ እስልምና ስሙ እንጂ ተግባሩ እየቀረ ይሄዳል።) ባለ በሌለ ሀይላቸው ድፍን ጥቁር የሆነን ውሸት በሰለፊዮች ላይ በመዋሸትም ያጠለሹዋቸዋል!። የሚስኪኑን ለዲኑ የሚጨነቀውን ህዝብ ልብ አውቀው እውነት ሊመስለው በሚችለው ነገር ላይ በሱኒዮች ላይ ውሸት ቀጥፈው ያቀርቡለታል። ሀራሙን ከሀላል፣ ሀላሉን ከሀራም በማደባለቅ ያመሳስሉበታል። ሳያጣራም ይከተላቸዋል፣ እውቅናም ይሰጣቸዋል።

ከምንም በላይ እውቅናን ፍለጋና ሚዲያን ለማግኘት ይተጋሉ። ታዲያ እውቅናንና ሚዲያን ባገኙ ቁጥር ሱኒዮችን ለማጠልሸትና ሰዎች ዘንድ የሀቅ ሰዎች እንዳይታወቁ ሰዎች ወደ እነሱ ሄደው ሀቅን እንዳይማሩ ለመሸፈን፣ መንገድ ለመዝጋት ነው የሚጠቀሙት። ፈፅሞ እንግዳነትና ባይተዋርነት ተሰምቶህ ተስፋ ልትቆርጥ አይገባም!!። ይልቅ ሰበቡን ካደረስክ ዲኑን እንደሚረዳው በአላህ ላይ ፅኑ እምነት ኖሮህ ከምንጊዜውም በላይ ልትነቃና ለህዝባችን በተቻለህ ሁሉ እውነቱን ግልፅ ልታደርግለት፣ ግልፅና ተጨባጭ ማስረጃዎችን ልታስጨብጠው ይገባል። አላህን (ተባረከ ወተዓላ) በሐቅ ላይ ፅናት ልንጠይቀው፣ በሀሳብና በእውቀት በተቻለን ሁሉ ርስበርሳችን ልንደጋገፍና ልንተዛዘን ፍቅር ሊኖረን!! ልንበረታታ ይገባል!!።
✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

23 Dec, 03:28


🔹 ይህ☝️ ኪታብ እጅግ በጣም ወሳኝ ኪታብ ሲሆን! ሺርክና ቢድዓን አንኮታካች ተውሒድና ሱናን አንጋሽ የሆነ ሁሉም ሊያነበው የሚገባ መፅሃፍ ነው። ጠንካራ በሆነ የሱንና ሰው ተተርጉሞ ለአንባቢያን መቅረቡ እጅግ በጣም አንጀት የሚያርስ ደስታን የሚፈጥር ነው።
አላህ ለአዘጋጁ ለሸይኽ ሷሊህ ፈውዛንና ለተርጓሚው ለሸይኽ ዩሱፍ አህመድ በሱንና ላይ እስከ መጨረሻው ከመፅናት ጋር ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቆ የላቀ ምንዳ ይክፈላቸው!!
ኪታቡ ይነበብ!! መቅራት የቻላቹ ጥሩ!!፣ ያልቀራችሁት ግን አማርኛውን በደንብ አንብቡት!!
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

23 Dec, 03:10


ተለቀቀ‼️

📌📚📖አዲስ መፅሐፍ 📖📚📌

"አል ኢርሻድ - ወደ ትክክለኛ እምነት መምራትና በማጋራትና በጥመት ባለቤቶች ላይ ምላሽ መስጠት"


الإرشاد إلى صحيح الإعتقاد والرد على أهل الشرك والإلحاد

በሸይኽ ዶክተር/ሷሊሕ ብን አል'ፈውዛን ሐፊዞሁሏህ ተዘጋጅቶ

በአቡ ዓብዲልዓዚዝ/ዩሱፍ አሕመድ ሐፊዞሁሏህ ወደ አማርኛ የተመለሰ

በዚሁ ቻናል በPDF ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን የሚተላለፍ ይሆናል ተብሎ ቃል በተገባው መሰረት እነሆ የአላህ ፈቃድ ሆኖ ለአንባቢያን ቀርቧል‼️

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን‼️
አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን‼️
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

21 Dec, 06:44


የጥመት ቡድኖች በአላህ ዲን ያለ እውቀት ይከራከራሉ!!
———
የጥመት አንጃዎችና ቡድኖች በአላህ ዲን ላይ ባጢልን የበላይ ለማድረግ ሐቅን የበታች ለማድረግ ያለ እውቀት ይከራከራሉ። አምላካችን አላህ ይህን አስመልክቶ ሲናገር በተግባራቸውም አመፀኛና ሞገደኛ የሆነውን ሸይጧንን እንደሚከተሉ እንዲህ በማለት ተናግሯል:-

وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّبِعُ كُلَّ شَيْطَانٍ مَّرِيدٍ ۞ كُتِبَ عَلَيْهِ أَنَّهُ مَن تَوَلَّاهُ فَأَنَّهُ يُضِلُّهُ وَيَهْدِيهِ إِلَىٰ عَذَابِ السَّعِيرِ

«ከሰዎቹም ያለ እውቀት በአላህ ነገር የሚከራከር፤ ሞገደኛ ሰይጣንንም ሁሉ የሚከተል ሰው አለ፡፡ እነሆ! የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል፡፡ ወደ ነዳጅ እሳት ስቃይም ይመራዋል ማለት በርሱ ላይ ተጽፏል፡፡» አል-ሐጅ 3 - 4

ታላቁ ሊቅ ሸይኽ ዐብዱረህማን ናስር አስ-ሰዕዲይ (ረሂመሁላህ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል:-
“ከሰዎች የጥመትን መንገድ የተጓዙ ቡድንና አንጃዎች አሉ። ሐቅን በባጢል መከራከርን ተግባራቸው የደረጉ፣ ባጢልን የበላይ ለማድረግ (ለማረጋገጥ) ሐቅን ደግሞ ውድቅ ለማድረግ የሚከራከሩ አሉ። ሁኔታቸው ድካ በደረሰ አላዋቂነትና ከእውቀት ምንም የሌላቸው ናቸው። እነርሱ ዘንድ ያለው ግብ የጥመት መሪዎችን መከተል ነው። ከአላህና ከመልእክተኛው አፈንጋጭ ሞገደኛና አመፀኛ ከሆነው ሸይጧን ጋር ናቸው። አላህንና መልእክተኛውን ያመፀና ወደ ጀሀነም ከሚጣሩ የጥመት መሪዎች ሆኗል። ˝እነሆ! የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል…˝ማለት:-  ሸይጧን ከትክክለኛው መንገድ ያርቀዋል፣ በትክክልም የሸይጧን ምትክ ነው። ይህ በአላህ መንገድ ላይ ያለ እውቀት የሚከራከር አካል ሁለት ጥመቶችን ሰብስቧል። አንደኛው እራሱን ማጥሙ ሲሆን ሁለተኛው ሰዎችን ከሀቅ መንገድ ዘግቶባቸው ማጥመሙ ነው። እርሱም ለአመፀኛና ለሞገደኛው ሸይጧን ተከታይና በጭፍን ተጎታች ነው። ይህ ደግሞ አንዱ በአንዱ ላይ የተደራረበ ጨለማ ነው። በዚህ ላይ አጠቃላይ ከሀዲዎችና የቢድዐ ባለ ቤቶች ይካተታሉ። አብዘሃኞቹ ጭፍን ተከታዮቻቸው ያለ እውቀት ይከራከራሉ።” [ተፍሲሩ ከሪሚ ረህማን ሊሸይኽ ናስር አስ-ሰዕዲይ - ረሂመሁላህ]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

20 Dec, 06:03


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

19 Dec, 17:25


ይሄው ነው እውነታው። ⤵️⤵️
https://t.me/IbnShifa/4469
ዛሬስ እነ ኢልየስ አህመድ ተስተካክለው ነው? ወይስ እነ ኢብኑ ሙነወር ወርደው ነው ከነሱ ማስጠንቀቁን የተውት? አቅል ላለውና ከጭፍን ተከታይነት ለወጣ ሁሉም ነገር ግልፅ ነው። አልሀምዱ ሊላህ እነ ሸይኽ ሑሰይን ግን ባሉበት ነው ያሉት። አላህ ሳይቀያየሩ በሐቅ ላይ እንዳሉ አላህን እስኪገናኙት ያፅናቸው!! እኛንም ጭፍን ተከታዮች ሳንሆን፣ አላህን እስክንገናኘው ከሐቅና ከተከታዮቹ ጎን ፀንተን የምንቆምና ሐቁንም በማስረጃ ግልፅ ለማድረግ ይወፍቀን!!
#join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

19 Dec, 17:07


ኢብኑ ሙነወር የመከራችሁን ተቀበሉ!

ከ Facebook ባገኘሁት ትክክለኛ መረጃ መሰረት Dawit Ali Abuabdurahmann የተባለ ወንድም ኢብኑ ሙነወርን ኢልያስ አህመድ ስላቀረባቸው 30 ምክሮች ይጠይቀዋል። የጥያቄው አቀራረብም «ሰዎች ሰላሳ ምክሮችን ስህተት አለበት ይላሉ ግን ስህተቱ አልታየኝም እና እስኪ አብራርተህ ፃፍልን» ይለዋል
ኢብኑ ሙነወርም
❝ወንድም ሁሰይን ሙሐመድ የሰጠውን ምላሽ አንብበው❞ በማለት ወደ ሸይኽ ሁሰይን ሙሐመድ አስልጢ ረዶች ጥቆማ አደረገ

በጣም ጥሩ አዎ ሁላችሁም የሸይኽ ሁሰይንን ማብራሪያ አንብቡ በውስጣችሁ ያለው የኢልያስ ውደታ የጋረደው ሀቅን የመቀበል ፍላጎት ቦግ ይልላችኋል

አዎ ከሸይኽ ሁሰይን በኩል የተሰጡ ረዶችን አንብቡ አዳምጡ ወላሂ ከተመዩዕ ቫይረስ ለመዳን ሰበብ ሊሆናችሁ ይችላል

አዎ አዳምጡ አንብቡም። ሸይኽ ሁሰይን እያንዳንዱ ሙኻሊፍ ስለሚያመጣው ማምታቻ በቂ ምላሽ ሰጥተዋል።

በነገራችን ላይ በዛው የFacebook Comment ሳጥን ላይ የምናገኝበትን ሊንክ ስጠን እያሉ የጠየቁ ሰዎችን አይቻለሁ። ለነሱም ለሌሎችም ይጠቅም ዘንድ በሚከተለው መልኩ በየክልሉ አዘጋጀሁላችሁ።

በኢልያስ አሕመድ "30 ምክሮች ለወሰን አላፊዎች" በሚል ሙሐደራ ላይ በሸይኽ ዶክተር ሑሰይን ቢን ሙሐመድ አስሲልጢ ከዓመታት በፊት የተሰጠ ምላሽ

ክፍል ❶ ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/7455

ክፍል ❷ ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/7611

ክፍል ❸ ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/7708

ክፍል ❹ ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/7761

ክፍል ❺ ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/8095

ክፍል ❻ ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/8411

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

19 Dec, 15:00


🔹 ወንድሜ ኢብኑ ሽፋ ባነሳው ሐሳብ ላይ ትንሽ ለማከል የመርከዙ ሰዎች በኢብኑ መስዑድ ስም የሰበሰቡት ገንዘብ የመስራቾቹ የግል ሀብት እንጂ የሰለፍዩ ማህበረሰብ ንብረት አይደለም። ለዚህ ማረጋገጫው ለህብረተሰቡ ለመርከዙ ነው ተብለው የተገዙ ቦታዎችም እንዲሁም መኪኖችና የባንክ አካውንቶችንም ጨምሮ በመስራቾቹ ስም ነው የሚገኙት ። አል ዓፊያ አክሲዮን የያዘው ድርሻ የኢብኑ መስዑድ መርከዝ እንደሆነ ቅርበት ያላቸው ሁሉ ያውቃሉ። ዛሬ ግን ከእነዚህ መስራቾች የግል ሀብትነት ማውጣት የሚቻልበት የህግ አግባብ ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም መሪዎቹ በዚህ ጉዳይ የተካኑ ስለሆኑ። የዛሬ 10 አመት አካባቢ ሸይኽ ዐ/ ባሲጥ (ረሂመሁላህ) በነበሩ ጊዜ ዛሬ በጉያቸው ከከተቱዋቸው ዳዒዎቻቸው ውስጥ ሁለቱ ኢብኑ መስዑድ ላይ ባነሱት ቅሬታ ፉሪ ሐጂ ሪል እስቴት አካባቢ የተወሰኑ ወንድሞች በወንድም ዙበይር ቤት ተሰብስበው የእስትራክቸር ለውጥ መደረግ አለበት ብለው ኢልያስ አሕመድን መልእክት እንዲያደርስ ልከው ቀጠሮ ተይዞ ተገናኝተን ኢልያስ አወል ለተሰብሳቢው ኢብኑ መስዑድ ማለት እኮ ንብረት ነው ለማን እንድናስረክብ ነው የምትጠይቁት ነበር ያለው።
    ይህ ማለት የዛኔ ራሱ ኢብኑ መስዑድ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንጂ የሰለፍዩ ማህበረሰብ አልነበረም። ዛሬማ በዐቂዳ እንጂ በገንዘብ ከማይገናኙዋቸው ሌሎች ድርጅቶች ጋር ተደምረዋል። ሁሉም የሰበሰበውን ይወስዳል ባይሆን አንዱ ሌላውን እንዳያሸንፍና እንዳይበልጥ ፍልሜያ ነው ያለው።
    የመርከዙ ሰዎች በተጠና መልኩ ከኢትዮዽያ 20 ባለሀብቶች ተርታ ለመመዝገብ በሚያደርጉት ሩጫ የተለያዩ ገንዘብ መሰብሰቢያዎችን በመሀል ከተማ በክ/ሀገርና በውጭ ሀገር ይነድፋሉ። ከእነዚህ ውስጥ ነሲሓ ቲቢ ፣ ነሲሓ በጎ አድራጎት ፣ አልሂዳያ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል። የዛሬ አመት አካባቢ በጉመር ወረዳ አረቅጥ አካባቢ ባስገነቡት መርከዝ አማካይነት ገንዘብ ለማሰባሰብ ከላይ ወንድሜ ኢብኑ ሺፋ የጠራቸው አይነት የተለያዩ ባለብትና ነጋዴዎችን እንዲሁም ያብሬት ሸይኽና የቃጥባሬ ሸይኽን የሚያመልኩ ገበሬዎችና ሙሪዶች በተሰበሰቡበት አቶ አዩብ ደርባቸው ፣ ሰላሁዲን መለስና ዐ/ካፊ መሐመድ መድረክ መሪ የነበሩ ሲሆን አዩብ ደርባቸው በአብሬት ሸይኾች ስም መቶ ሺህ ብር በቃጥባሬ ሸይኾች ስም መቶ ሺህ ብር በማለት ቀብር አምላኪው ሱፍዩና አሕባሹም ጭምር እያስጮኸ ነበር ያስነየተው።
     እነዚህ አካላት አጋጣሚዎችን በመፍጠር ወላእና በራእን በማጥፋት ሁሉም የእነርሱን ኪስ እንዲያደልብ መስራታቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስልቱን እየቀያየረ የመጣ ጉዳይ ነውና የነሲሓ መዘጋት አጀንዳም የዚህ እስትራቴጂ አንዱ ክፍል ነው ለማለት እወዳለሁ።
https://t.me/bahruteka

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

18 Dec, 16:03


👇
ነሲሃ ቲቢ
——
ዛሬ አንድ ቦታ ቁጭ ብዬ ስልኬ ላይ አንድ ፅሁፍ እየፃፍኩ አንድ የምንተዋወቅ ነጋዴ ባለ ሀብት ሰላም ብሎኝ ከአጠገቤ ቁጭ አለ፣ አጋጣሚ ቤቱ ላይ አንድ የኢኽዋኔይና የሱፊይ የሆነ ቲቢ ተከፍቶ ተመለከተና ቆይ ነሲሃ ቲቢ ሲዘጋ እነዚህ ያልተዘጉት እስፖንሰር ስላላቸው ነው አይደል? አለኝ፣ እኔም ነሲሃ ቲቢስ ቢሆን ምስጢሩ ሌላ ነው እንጅ የምር በገንዘብ እጥረት ነው የተዘጋው ብለህ ታምናለህ? በቀላሉ አልኩትና (አንድ ሁሉም የሚያውቀውን ትልቅ የሆነ የገቢ ምንጫቸውን) ጠቅሼለት እሱ ብቻ አይሸፍነውም እንዴ አንተ ነጋዴ ባለ ሀብት ነህ፣ ነገሮችን ታውቃለህ ብዬው ለሶላት ኢቃም ብሎ ነበርና ብድግ አልኩ፣ ጭንቅላቱን ደጋግሞ እየነቀነቀ ለነገሩ እውነትህን ነው… ልክ ነህ… ልክ ነህ…አለኝ።

እየፃፍኩት የነበረውንም ፅሁፍ እንደሚከተለው ጋብዣችኋለሁ መልካም ንባብ!

✍🏻ኢብን ሽፋ

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

18 Dec, 16:03


ነሲሃ ቲቢ በገንዘብ እጥረት ተዘግቶ አይዘጋም! የሙስሊሙ ህብረተሰብ ኪስ ይበዘበዝበታል እንጂ!!
—————ክፍል አንድ
በ ኢብኑ መስዑድ መርከዝ ስር የሚተዳደረው የሙመይዓ - ኢኽዋኑ ነሲሃ ቲቢ ተዘጋ በሚል ሙሾ አውራጅና አስለቃሽ ጭፍን ተከታዮች በየ ማህበራዊ ሚዲያው በዝተው እየተመለከትኩ ነው። የኢኽዋንና የሙመይዓ የጥምር የጥመት ቡድኖች የሆነው ነሲሃ ቲቢ መስኮት አንዳንድ ምስጢሩ ያልገባቸው ሰዎች በገንዘብ እጥረት ተዘጋ ሲባሉ እውነት መስሏቸዋል። አብዘሃኞቹ ደግሞ አፈቀላጤ የሆኑ ጭፍን አራጋቢ ሙሪዶችን አዘጋጅተው እያስጮሁ ስለሆነ ተጨባጩ ቢነገራቸውም እውነት ብለው ለመቀበል ሊከብዳቸው ይችላል።

በቅድሚያ ነሲሃ ቲቢ እውነት በገንዘብ እጥረት ነው የተዘጋው ወይ? በሚለው ነጥብ ላይ የተወሰነ ልበል።
ነሲሃ ቲቢ በየትኛውም ስሌት በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ አይችልም!!።

ምክንያት አንድ:- በተለያየ መንገድ ገንዘብ ለመሰብሰብ እንቅልፍ የማይተኙ በመርከዟ አመራርነት ደረጃ የተቀመጡ ሰዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ከፍተኛ ባለ ሀብቶችን እና በየ ደረጃው የሚገኙ ነጋዴዎችንና በደሞዝ የሚተዳደሩ ደሞዝተኞችን ሳይቀር በተለያየ መንገድ በማጥመድ ለቲቢዋ ድጋፍ እንዲያደርጉ ከስራቸው አድርገዋል። ከነዚያ ባለ ሀብቶች ከፊላቸው በየ ወሩ መዋጮ በማድረግ ከፊላቸው ደግሞ በየ አመቱ ከፍተኛ የሆነ (ተራ ብር እንዳይመስላችሁ እያንዳንዱ ባለ ሀብት በሚሊየን ቤት) መዋጮ እንዲያደርግ አድርገዋል። ልብ በሉ! ገንዘቡ ሳይሰበሰብ እንዳይቀር ሰዎቹ ፖለቲካዊ ጫወታው ላይም የተዋጣልን አካሄድና የብር መሰብስብ ብቃት ያለን ብልጦች ነን ብለው ስለ ሚያስቡ ለባለ ሀብቶች ባለ ሀብት አስተባባሪዎችን ነው ያሰማሩት። ለሌሎች ደግሞ በየ ደረጃቸው በዘመድ፣ በአከባቢ ልጅነት፣ በየ ደርስ ቦታው… ወዘተ በየ ደረጃቸው ተመድቦላቸዋል። የተሰማሩ ባለ ሀብቶች ደግሞ በመሪያቸው ፍቅር ያበዱ የእነሱ ቀንደኛ ተላላኪና እራሳቸው ከፍተኛ የሆነን ገንዘብ ነይተው ሌሎችን በፉክክር የሚያስነይቱ ናቸው። ከባለ ሀብቶቹ ስለ ሚንሃጅ ብዙም ግንዛቤ የሌላቸው ኢኽዋኑም ሙመይዓውም… ሌላውም ለመልካም ነገር (ለዲን) ነው በሚል ስም እንዳሻው የሚያልባቸው አሉ፣ ከጅህልናቸውም ጋር በተለያየ ፊክራ የተዘፈቁ አሉ፣ ከነዚህም ውስጥ በኢኽዋን ፊክራ የተዘፈቁ ሆነው የመርከዙ ሰዎች ከእኛው ጀመዓ (ከኢኽዋኑ) ጋር አንድ ሆነዋል መደገፍ አለብን በሚል ስሜት የሚደግፉ አሉ፣ ቀደም ሲልም መርከዟን ባለ በሌለ ሀይላቸው ለዚህ ደረጃ እንድትበቃ ያደረጉ ለደዕወቱ ሰለፊያ ጉጉት የነበራቸው አሁን የመርከዙ አመራሮች ሲቀልጡ ይዘዋቸው የቀለጡና የሟሙ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ባለ ሀብቶች አሉ። አይደለም እንዲህ ተረባርበው ይቅርና ብቻቸውን የቲቢውን ወጪ መሸፈን የሚችሉ ጠንካራ አቅም ያላቸው ባለ ሀብቶች ባሉበት "በገንዘብ እጥረት ተዘጋ" ብለው አስለቃሾችን ቀጥረው ሙሪዶችን አደራጅተው ማስጮሃቸው አሁንም ምስጢራቸውን ያላወቀውን ሙስሊሙን ማህበረሰብ "ና! አይንህን ጨፍንና እናሙኝህ" እያሉት ነው። ልብ ያለው ልብ ይበል!!

ምክንያት ሁለት:- ይህ መርከዝ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከላይ እንደጠቀስኩላችሁ ገንዘብ ለማግበስበስ ሌት ከቀን እንቅልፍ በሌላቸው አመራሮቹ አማካኝነት ከፍተኛ የሆነ የእራሱ የገቢ አቅም አለው። ይህ የገቢ አቅምም አዲስ አበባ ላይ ብዙዎች የሚያውቁት አል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር ነው። ማህበሩ በተለያዩ ቦታዎች ጠንከር ያለ ክፍያ እያስከፈ ከሌሎች የግል ትምህርት ቤቶች ጋር የሚወዳደር ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ት/ቤቶች አሉት። የእራሱን ቦታ ገዝቶ የገነባውን ሆስፒታል ጨምሮ ሌሎችም አቅሞች ያሉት አክሲዮን ነው። ብዙ ሰዎች ይህን አክሲዮን ከመርከዙ ለይተው ሲመለከቱት ይስተዋላል። አይፈረድባቸውም 1ኛ, እነዚህ በመሪነት ደረጃ ያሉ አካላት ወሳኝ በሆኑ ቦታዎች ካልሆነ በስተቀር ስሙን ከመርከዟ ጋር አያይዘው ማንሳት አይፈልጉም። 2ኛ, ብዙ ሰዎች አመሰራረቱንና አሁን ከሚያስተዳድሩት ሰዎች ጋር ምን ያህል ትስስር እንዳለው በቅርበት የሚያውቁት ነገር ስለ ሌለ እራሱን የቻለ የንግድ ተቋም አድርገው ይመለከቱታል።
መጋቢት 29/2010 ላይ 18 አካባቢ በሚገኘው በመርከዙ ዋና ህንፃ "ከመጅሊሱ ተቀላቅለን ልንሰራ ስላሰብን እንዲሁም ቲቪ ለመክፈት ፕሮሰስ ጨርሰን እቃዎቹን እያስገባን ስለሆነ ልናወያያችሁ አስበን ነው" የሰበሰብናችሁ በማለት ከተለያዩ ቦታዎች በኡስታዝነት ደረጃ ተቀምጠው በስራቸው የሚገኙ ሰዎችንና የሱሩሪያ ፊክራ የነበራቸውን ሰዎች በሰበሰቡበት ወቅት ከመርከዙ በዋና አመራርነት ከሚጠቀሱ ሰዎች አዩብ ደርባቸው የሚባለው አል-ዓፊያ አክሲዮንን አስመልክቶ የመርከዙ ዋና ሀብትና የገቢ ምንጭ መሆኑን ተናግሯል። ይህን መናገሩን ያስታውስ አያስታውስ አላውቅም እንጂ በወቅቱ ወንድሜ ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ከሀዋሳ መጥቶ ተሳትፎ ነበር። ይህን እውነታ በተጨማሪ አክሲዮኑ ሲመሰረት የነበሩ አንዳንድ በገንዘባቸውም ጭምር ያገዙ ባለ ሀብቶች አጫውተውኛል። ታዲያ ይህ ሁሉ አቅምና የገቢ ምንጭ እያለ ቲቢዋን ዘግቶ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ገንዘብ መበዝበዙ ለምን አስፈለገ? ህዝበ ሙስሊሙን መንሀጁንና ገንዘቡን አጭበርብረውት የት ሊያደርሳቸው ይሆን?!

በነገራችን ላይ በመጋቢት 29/2010 ስብሰባ ላይ የነበሩት አብዘሃኞቹ ተሰብሳቢዎች በቅርበት የማውቃቸው ሲያኮርፉና ሲያሻቸው ወደ ሱሩሪዮች ሲላቸው ወደ መርከዟ ልጥፍ የሚሉ የነበሩ የዛኔም ሚናቸውን ያልለዩ በሁለት ማሊያ እየተጫወቱ የነበሩ ሰዎች ነበር የሞሉት። እኔና ወንደሜን አቡ ሀመዊያን ጨምሮ አንድ ከሀረር የመጡ አሁን በትክክል ስማቸውን የማላስታውሳቸው ከመጅሊስ ስለ መስራት ሲነሳ በቁጣና በጩሀት አውግዘው ከተናገሩ በኋላ ጥለው የወጡ ሸይኽና ከባህር ዳር የመጡ በወቅቱ በእጅጉ አውግዘው በመናገር "ለምን እራሳችንን ችለን አንጓዝም?፣ ለሰለፊያ ደዕዋ እንዲህ ያለ መሰረት ካገኘን በኋላ (ህንፃውን ማለታቸው ነው) ለምን ትላንት ስናወግዛቸው ከነበሩት ከኢኽዋንና ከሱፊይ እንጨመራለን?!" በማለት ቁጣ አዘል ጥያቄ ያቀረቡ ሸይኽና በሰለፊያው ጀመዓ የሚታወቁ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነው የነበሩት። ከስብሰባው በኋላ በተለምዶ (አባ ዱላ) በሚባለው በመርከዙ መኪና ወደ አየርጤና ስንሄድ ከመርከዟ አመራሮች አንዱ የሆነውን ኤልያስ አወልን በጠንካራ አቋማቸው የማውቃቸውን ሰዎች ስም ጠቅሼ ለምን አልመጡም?፣ ለምን አልተሳተፉም ወይስ አልጠራችኋቸውም ነው አልኩት? ምንም እንኳን ጥያቄ ምቾት ባይሰጠውም ሳይመልስልኝ ማለፍ አልቻለምና "እነ ባህሩ ተካን ማለትህ ነው አለኝ?" አዎ፣ ሌሎችም ብዬ የአሁኖቹን የአዲሶቹን ሙመይዓዎችንም ስም ጠቃቀስኩለት። "እነሱ ቢመጡም አንግባባም፣ ይልቁንም ሌላውንም ያስበረግጉብናል" አለኝ። እኔም:- ታዲያ በዚህ መልኩ መጓዝ ይሻላል? አልኩት። "አዎ በተለያየ ጊዜ እንወያይ ብለን ስንገናኝ ትርፉ ጭቅጭቅ ነው፣ ዝም ብለን ስራ ብንሰራ ይሻላል" አለኝ። እኔም ትዝብቴን ይዤ በጭንቅላቴ የሚመላለሱ ጥያቄዎችን ከዚህ በላይ መቀጠል ስላልፈለግኩ ዝምታዬን መርጬ አየርጤና ስንደርስ አውርዱኝ ብዬ ወደ ፉሪ ጉዟቸውን ቀጠሉ።
የተያያዘ ቀጣይ⤵️ፅሁፍ⤵️
https://t.me/IbnShifa/4467

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

18 Dec, 16:03


ወደ ርእሴ ልመልሳችሁ…
ምክንያት ሶስት:- ሌላኛው የገንዘብ መበዝበዢያ መንገድ ብዙዎቻችን ከሁለት አመት በፊት በአደባባይ ሲሰበስቡ የተመለከትነው "ዳሩ ተውሒድ ፕሮጀክት" በሚል ስም ግዙፍ ህንፃ ገንብቶ ለማከራየት ሲሰበሰብ የነበረው ከፍተኛ ገንዘብ ነው። ይህ ህንፃ ተገንብቶ ከተከራየ ገቢው በቁጥር 1 ለነሲሃ ቲቢ… ወዘተ ወጪ መሸፈኛ ብለው ነው ሲያስተዋውቁት የነበረው። ገንዘቡ 100 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልጋቸው አስተዋውቀው ስለነበር ብዙ ሰዎች ለዲን ነው በሚል ስም መኪናቸውንና መሬታቸውን ሁሉ ሳይቀር አስረክበዋቸው ካሰቡት በላይ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሰበሰቡና የህንፃው ማሳረፊያ ቦታ እንደገዙ በተጨባጭ አውቃለሁ፣ ይህ ብዙዎች የሚያውቁትም የቅርብ ጊዜ እውነታ ነው። ታዲያ በየትኛው ስሌት ገንዘብ አጥቶ ተዘጋ?!

ምክንያት አራት:- ይሀው ልክ በዚህ መልኩ "ነሲሃ ቲቢ ተዘጋ፣ ሊዘጋ ነው…" እያሉ ስንት ጊዜ ነው ብር ያግበሰበሱት? ስንት ጊዜ ነው በዲን ስም ለዲኑ ሲባል በየዋህነት ምስጢሩን ባላወቀው ነገር ያለውን ጠራርጎ የሚሰጠው ህዝበ ሙስሊም ከፍተኛ ገንዘብ ያዋጣው? በቲቢዋ ስም ብቻ ህዝቡን ኪሱን የበዘበዙት ያ ሁሉ ገንዘብ የት ገብቶ ነው አሁንም ተዘጋ ብለው ህዝቡን ሊበዘብዙት የተነሱት?? ልብ ያለው ልብ ይበል!
ክፍል 2 ⤵️
https://t.me/IbnShifa/2628
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

17 Dec, 10:48


👉 አዲስ ኪታብ pdf       የገፅ   ብዛት   313

عنوان:- الواضح في تيسير منهج السلف الصالح
የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ ገር በሆነ መልኩ ግልፅ ማድረግ
للشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي حفظه الله

✍🏻አዘጋጅ:- ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ)

Pdf ን ለማግኘት👇👇
https://t.me/IbnShifa/4456

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት፣ የምታቀሩም አቅሩት)

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/HussinAssilty
https://t.me/HussinAssilty

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

17 Dec, 10:46


አዲስ ኪታብ Pdfን ለማግኘት👇👇
https://t.me/IbnShifa/4456

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

17 Dec, 10:46


አዲስ ኪታብ Pdfን ለማግኘት👇👇
https://t.me/IbnShifa/4456

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

16 Dec, 19:07


كلام الشيخ محمد أمان الجامي رحمه الله
عن الشيخ ناصرالدين الألبانى رحمه الله

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

16 Dec, 17:32


የማንበብ ልምዳችንን እናዳብር!!
———
ብዙዎቻችን አጫጭር የማህበራዊ ሚዲያ ፅሁፎችን ከማንበብ የዘለለ በትግስት የምንጠቀምበትን ረዘም ያለ ፅሁፍ የማንበብ ልምድ የለንም። ምንም እንኳ ሰው ከጉድለት ባይፀዳም በአባባል ደረጃ "ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል" ይባላል፣ ይህ የማንበብን ደረጃ ለመግለፅ የተፈለገበት አባባል ነው። የሱንና ፅሁፎችን በዐረቢኛም ሆነ በሌሎች በምንረዳቸው ቋንቋዎች ማንበብ መልመድ ትልቅ ተሰጦዖ ነው። ጊዜያችን በአጋጉል ነገርና በማይረባ ነገር ስልክ እየጎረጎሩ ማቃጠል አላህ ፊት ከተጠያቂነት አያድንምና በሚጠቅሙ ት/ት ነክ በሆኑ የሱንና ፅሁፎችና መፅሃፎችን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በትግስት አንብቦ ሀሳባቸውን ለመረዳት መሞከር ለላቀ አስተሳሰብና ሸሪዓዊ ነጥቦችን በማስረጃ ለማወቅ ይረዳል።
ታላቁ ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) اقرأ አንብብ ተብለዋል። ኢስላም የተስፋፋው በፅሁፍ ነው፣ ደጋግ ቀደምቶቻችን እነ ኢማሙ አሕመድ፣ ማሊክ፣ ሻፊዒይ፣ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ትርሚዚይ፣ እነ ኢብኑ ተይሚየህ… (ሁሉንም አላህ ይዘንላቸውና) የመሳሰሉት ሊቃውንቶች ዲኑን ያስተላለፉልን በፅሁፍ ነው። ማንበብ ካልቻልንና ለማንበብ ትግስት ከሌለን እንዴት ይህን ዲን በሚገባ ልንረዳ እንችላለን?!
በዚህን ጊዜ ሁሉም ነገር ተመቻችቷል፣ ዐረቢኛ የሚችል የተለያዩ የኢስላም ልሂቃን ሳይደክማቸው የተለያዩ ኪታቦችን ፅፈውልን ሄደዋል፣ ዐረቢኛ የማይችል በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሱንና መፅሃፎችን ማንበብ ይችላል። እነሱ ሲፅፉት ያልደከሙት እኛ ለማንበብ ደክመናል። በየ ደረጃው ለማንበብ ጥረት ማድረግ ግድ ይላል።
ስናነብ በማያሰላቸንና በሂደት ልምድ በምናደርገው መልኩ በትንሽ ትንሹ ሀሳቡን በደንብ እየተረዳን በማንበብ በሂደት ከፍ እያልን መሄድ እንችላለን።
🔸በዛው ልክ አጥፊ ከሆኑ ከጥመት ቡድኖችና ምንጫቸው ከማይታወቁ ልበ ወለድ የሆኑ የፈላሲፋ ፅሁፎችን ከማንበብ መጠንቀቅ ነው!! እንዲህ አይነት መፅሃፎችን ማንበብ የሚፈቀደው ለአንድ ነገር ብቻ ነው፣ እሱም ጠንካራ ሸሪዓዊ እውቀት ኖሮት ምላሽ (ረድ) መፃፍ ለሚፈልግ አካል ብቻ ነው።
"አንብብ" ተብለው የተላኩት የታላቁ ነቢይ ትውልድ (ኡማ) እንዴት አያነብም?!
የማንበብ ልምዳችንን እናዳብር!!
✍🏻ኢብን ሽፋ #join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

14,813

subscribers

914

photos

25

videos