ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?
(አል ቂያማህ 36)
ቀደምት አረቦች ግመል ስታረጅ ስጋዋ ለምግብነት እንደማይሆን፣ ወተት ከመስጠትና ልጅ ከመውለድ ስትነጥፍ ወደ በረሀ ረዥም ጉዞ ይዘዋት ይሄዱና ከባድን ሸክም አሸክመው አውላላ በረሃ ላይ ጥለዋት ይመለሳሉ ይህች ግመል ሸክሟን ለማራገፍ እየታገለችና ወደ መጣችበት ለመመለስ እየሞከረች እስክትሞት ድረስ በረሃው ላይ እድሜዋ ያልቃል ...ይህቺን ግመል አረቦቹ "ስድ(ልቅ) የተተወች ግመል" ብለው ይጠሯት ነበር....አላህም አንቀፁ ላይ ይናገራል የሰው ልጅ ማንም ፈላጊ ሳይኖረው እንዲሁ አውላላ ሜዳ ላይ የተተወ አላማ ቢስ ፍጥረት ይመስለዋል እንዴ? ...ወዳጄ ትፈለጋለህ አላህ ይፈልግሃል ህይወትህ ዝም ብሎ አይደለም አላህ ለትልቅ ቁም ነገር ይፈልግሃል ...ሸክምህን ሊያራግፍ ....በውዴታው እየጠበቀህ ነው ...ዝም ብሎ ሊተው አልፈጠረህም ...
አብሽር የኔ መልካም! ❤
የተባረከ ጁምዓ ይሁንልን!
https://t.me/yenebi_umet