ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service @courtsss Channel on Telegram

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

@courtsss


ጠቃሚ እና አዳዲስ ህጎችን እዚህ በነፃ ያግኙ

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service (Amharic)

ኢትዮ የህግ አገልግሎት የአማርኛ ቋንቋ እና እንግሊዝኛ አገልግሎትን የሚገኝ አመራሮች ለህጉዎ ከተሻገራ እንዲትምህር መቆረጥ ይደረጋል። የሚለውን መረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ያግኙ ፣ ህክምናኖችን በመጠቀም የተከበረ እና ተከታታይ በዓለም ለከፍተኛ እና ትንሹ እናምድ ስለሚፈልጉ አዳዲስ ህጉዎችን እዚህ በነፃ ያግኙ። የሚባለውን ወሬ የመረጣቸውን በአለም አቀፍ ደረጃ እና መድረስ ማለት ነው። የምርጫ ተከታታይ ምላሽ ለማድረስ እና የተመለከተ የምርጫ መረጃ ለመለዋወጥ እና አዳዲስ ህጉዎችን እዚህ በነፃ ይጠቀሙ።

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

21 Jan, 14:17


አዲሱ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1335/2017

Federal Civil Servants Proclamation Number 1335-2025

0943192020
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

20 Jan, 06:52


ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (One Man Company) በኢ.ፌ.ድ.ሪ የንግድ ህግ

መግቢያ
በአዋጅ ቁጥር 1243/2013 ሥራ ላይ የዋለው የኢፌድሪ ንግድ ሕግ ለውጥ ካመጣባቸው የህጉ ክፍል መካከል የንግድ ማህበርን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ህጉ በቀድሞ የንግድ ህግ ውስጥ ከተካተቱት ስድስት የንግድ ማህበራት አይነቶች መካከል ተራ የሽርክና ማህብር በመባል የሚታወቀው ከሕጉ እንዲወጣ ያደረገ ሲሆን በምትኩ ሁለት አዳዲስ የንግድ ማህበር ዓይነቶችን ማለትም ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር /Limited Liability Partnership/ እና ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት (One Man Company) አካቶ በጠቅላላ ሰባት የንግድ ማህበር አይነቶችን አካቷል፡፡ በዚህ ፅሁፍ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት (One Man Company) ባህርያትና ተያያዥ ጉዳዮችን በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (One Man Company) ምንነት
በንግድ ህጉ አንቀፅ 534 መሰረት ባለ አንድ አባል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማለት አንድ ሰው በግሉ በሚሰጠው መግለጫ መሠረት የተቋቋመ የንግድ ማህበር ሲሆን ማህበሩ ከአባሉ የተለየና የተነጠለ የራሱ የሕግ ሰውነት ያለው ነው፡፡

የማህበሩ አመሰራረት
ከላይ እንደተመለከተው ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚመሰረተው አንድ ሰው በሚሰጠው መግለጫ መሠረት ሲሆን አባሉ የሚሰጠው መግለጫ ሰነዶችን ለማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት መደረግና መግልጫውም በንግድ መዝገብ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ የሚቀርበው መግለጫው
ማህበሩ አንድ አባል ብቻ ያለው መሆኑን
የአባሉን ስም፣ ዜግነትና አድራሻ
አባሉ የሞተ፣ የጠፋ ወይም በፍርድ የተከለከለ እንደሆነ ስለ ወራሾቹ ወይም ስለ አባሉ ሆኖ ሕጋዊ ተግባራትን እንዲፈፅም የታጨው የንብረት ጠባቂ ሰው ስም
ዕጩ ንብረት ጠባቂው ፍቃደኛ ሆኖ ኃላፊነቱን የተቀበለ መሆኑን
የማህበሩን ስም፣ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ቅርንጫፎች ካሉትም መሥሪያ ቤቶቹን
የማህበሩን የንግድ ዓላማ
የማህበሩ ዋና ገንዘብ መጠንና በሙሉ የተከፈለ መሆኑን የሚያሳይ መግለጫ
በዓይነት የተከፈለ መዋጮ ካለ ግምቱን
የሥራ አስኪያጁን ስምና ሥልጣን
ካለ ኦዲተሩን
ማህበሩ የሚቆይበትን ጊዜ
ማህበሩ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የሚያስታውቅበትን መንገድና ጊዜ እንዲሁም
ሌሎች በሕግ ወይም በአባሉ እንዲካተቱ የተወሰኑ ጉዳዮችን ማካተት አለበት፡፡
እንደሌሎች ማህበሮች ሁሉ ባለ አንድ አባል ኃለፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር የሚቋቋመው በመመስረቻ ጽሑፍ ሲሆን ማህበሩን ለመመስረት የሚቀርበው ዝቅተኛ ዋና ገንዘብ ከብር 15,000 (አሥራ አምስት ሺ) ማነስ የለበትም፡፡ በዚሁ መሰረት ቅድመ ሁኔታዎችን እስካሟላ ድረስ ግለሰብ ነጋዴ የንግድ ሥራውን ወደ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርነት መለወጥ የሚችል ሲሆን ሆኖም ግለሰብ ነጋዴው ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከመመሥረቱ በፊት ለገባበት ዕዳ ሁሉ ከማህበሩ ጋር በአንድነት እና በተናጠል ኃላፊ ይሆናል፡፡

ሌላው የምስረታው ቅድመ ሁኔታ የሆነው የእጩ ንብረት ጠባቂን የተመለከተ ሲሆን እጩ ንብረት ጠባቂው እጩነቱን የተቀበለ መሆኑ ሰነዶችን ለማረጋገጥ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መረጋገጥ እንዳለበት በንግድ ህጉ አንቀፅ 537 ተመልክቷል፡፡ በዚህም ዕጩ ንብረት ጠባቂው ዕጩነቱን የተቀበለ መሆኑን ሰነዶችን ለማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት ካላረጋገጠ በስተቀር ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሊመሠረት አይችልም፡፡ እንዲሁም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለተለያዩ ባለ አንድ አባል ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማህበራት የንብረት ጠባቂ ሆኖ መመረጥ አይችልም፡፡

የማህበሩ አመራር (Governance)
በንግድ ህጉ አንቀፅ 541 መሰረት ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲኖረው ሕጉ የሚያስገድድ ሲሆን አባሉ ራሱ ወይም ሌላ ሰው የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊሆን ይችላል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁም አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስኪያጅ ያለው ሥልጣን እና ተጠያቂነት ይኖረዋል፡፡
በተጨማሪም በህጉ አንቀፅ 542 መሰረት የማህበሩ አባል የአንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባላት ጠቅላላ ጉባዔ ያለውን ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ አባሉ በጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣኑ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ቃለ-ጉባዔ ውሳኔው በተሰጠ ከሦስት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በጽሑፍ ተዘጋጅቶ የማህበሩ ማህደር ውስጥ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ በማህበሩ ምሥረታ ጊዜ በተሰጠ መግለጫ ውስጥ የተካተቱትን ነገሮች የሚለውጥ ማንኛውም ውሳኔ ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በንግድ መዝገብ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ የአባሉ ውሳኔዎች የተጠቀሱትን ሁኔታዎች ያላሟሉ ቢሆኑ እንኳን በሕግ ፊት የፀኑ ሲሆኑ ጉድለቱ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አባሉና ማህበሩ በአንድነት እና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

የተጠያቂነት ሥርዓት
ከተጠያቂነት አንፃር አባሉ ወይም መስራቹ የራሱን መዋጮ ሙሉ በሙሉ እስከከፈለ ድረስ ከማህበሩ ላይ ለሚፈለግ ዕዳ በግሉ ተጠያቂ እንደማይሆን በህጉ አንቀፅ 534(3) ላይ ተደንግጓል፡፡ የማህበሩ ባህርይ ኃላፊነቱ የተወሰነ እንደመሆኑ ማለትም የሚመጣ ተጠያቂነት በማህበሩ ሀብት ላይ ብቻ የተገደበ በመሆኑ አባሉ ኃላፊነቱን ከተወጣ ማለትም መዋጮውን ሙሉ በሙሉ እና በወቅቱ እሰከከፈለ ድረስ ኃላፊነት የለበትም ማለት ነው፡፡

ሆኖም በመርህ ደረጃ አባሉ መዋጮውን በወቅቱ ከከፈለ ለሚመጣው ተጠያቂነት በግሉ ኃላፊነት የለበትም ቢባልም ተጠያቂ የሚሆንባቸው ልዩ ሁኔታዎች ግን አሉ፡፡ ይህም በህጉ አንቀፅ 543 የተመለከተ ሲሆን አባሉ ወይም በማህበሩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቁጥጥር ያለው ሌላ ሰው
 ማህበሩን ወይም የማህበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች ጉዳት ላይ የሚጥል ህገ-ወጥ ድርጊት ሆን ብሎ ከፈፀመ
 የባለ አንድ አባል ማህበር ንብረትን ከራሱ ንብረት ጋር ከቀላቀለ
 የባለ አንድ አባል ማህበርን እና የራሱን ማንነት ካልነጣጠለ
 ስለ ማህበሩ የፋይናንስ አቋም የማህበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች ሊያሳስት የሚችል መረጃ ሆን ብሎ ካወጣ
 ያለ ተመጣጣኝ ክፍያ የማህበሩን ሀብት ለራሱ ወይም ለሶስተኛ ወገኞች የግል ጥቅም ካዋለ
 በሕግ ሊከፈል ከሚችለው በላይ የትርፍ ክፍያ ከፈፀመ ወይም
 ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ከፈፀመ
ከማህበሩ ጋር በአንድነት እና በተናጠል ተጠያቂ እንደሚሆን በግልፅ ደንግጓል፡፡
የማህበሩ መፍረስ እና የሚያስከትለው ውጤት
ማህበሩ በንግድ ሕጉ ጠቅላላ ክፍል በአንቀፅ 181 የተመለከቱ ለማህበራት መፍረሻ ምክንያቶች እንደአግባብነታቸው በሚያገጥሙበት ጊዜ ሊፈርስ ይችላል፡፡ ይኸውም
 ማህበሩ የተቋቋመበትን አላማ መፈፀም ሳይችል ሲቀር
 የማህበሩ የቆይታ ጊዜ ሲጠናቀቅ
 አባሉ ማህበሩ እንዲፈርስ ሲወስን
 ፍርድ ቤት ማህበሩ እንዲፈርስ ሲወስን
 የማህበሩ መክሰር በፍርድ ቤት ሲወሰን ናቸው፡፡

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

20 Jan, 06:52


ማህበሩ በሚፈርስበት ጊዜ አባሉ መደበኛ የሂሳብ ማጣራት ሂደትን በመከተል ሂሳብ እንዲጣራ ማድረግ ይችላል፡፡ በአንፃሩ አባሉ መደበኛ የሂሳብ ማጣራት ሂደት መከተል ካልፈለገ እና ያለበትን ዕዳ በሙሉ የከፈለ ከሆነ የማህበሩ ሀብት ሳይጣራ ባለበት ሁኔታ በጠቅላላው ለአባሉ እንደሚተላለፍ ከንግድ ህጉ አንቀፅ 544 መረዳት ይቻላል፡፡ ሆኖም በዚህ መልኩ ሂሳቡ ሳይጣራ ወደ አባሉ ከተላለፈ በኋላ ገንዘብ ጠያቂዎች የቀረቡ እንደሆነ አባሉ በግሉ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ አባሉን ተጠያቂ ለማድረግ የሚቀርብ ክስ ገንዘብ ጠያቂው የማህበሩን መፍረስ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በአምስት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ሲሆን የማህበሩ ሀብት ለአባሉ ከተላለፈ ከአሥር ዓመት በኋላ ግን ምንም ዓይነት ክስ ሊቀርብ አይችልም፡፡

ማጠቃለያ
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (One Man Company) በንግድ ህጉ እውቅና የተሰጠው የንግድ ማህበር ሲሆን በዚህ መልኩ ንግድ ማከናወን የሚፈልጉ ዜጎች በህጉ የተመለከቱ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው ማህበሩን በመመስረት እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ንግድ የሚሰሩ ነጋዴዎች ወደ ማህበር በመለወጥ የንግድ ሥራቸውን ማከናወን እንደሚችሉ ከህጉ መረዳት ይቻላል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

የፍትህ ሚኒስቴርን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
Facebook
https://www.facebook.com/MOJEthiopia/
(x) Twitter
https://x.com/MOJEthiopia
YouTube channel
https://youtube.com/@fdreministryofjustice...3701...
Telegram
https://t.me/fdreattorneyGeneral_external

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

18 Jan, 05:46


አዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ሚያዝያ 03 ቀን 2015 ዓ.ም ካወጣው የከተማ ቦታ ኪራይና የቤት ግብር ስሌት ማሻሻያ የጥናት ሰነድ ጋር በተያያዘ እናት ፓርቲ የጥናት ሰነዱ ለተቋሙ በህግ ባልተሰጠ ስልጣን ላይ የመመሪያ አወጣጥ ስርአትን ባልተከተለ መልኩ የወጣ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት ሊከለስ ወይም ሊሻር ይገባዋል ሲል የመመሪያ ክለሳ አቤቱታውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ጉዳዮች ችሎት ያቀረበ ሲሆን፤
ፓርቲው ባቀረበው የክለሳ አቤቱታ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ከክስ ምክንያት እና ከይርጋ ጋር በተያያዘ ካቀረባቸው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች በተጨማሪ የጥናት ሰነዱ በአዋጅ ቁጥር 80/68 አንቀጽ 6/2 ፣ በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 52/6 እና በአዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 18(6) ድንጋጌዎች መሰረት በህግ ለከተማ አስተዳደሩ በተሰጠ የፋይናን ስልጣን (fiscal power) መነሻነት የተከወነ የታሪፍ ማሻሻያ እንጂ መመሪያ ስላለመሆኑ በመጥቀስ ክርክሩን አቅርቧል፡፡
ፍርድ ቤቱም የታሪፍ ማሻሻያ ጥናት ነው በሚል የቀረበው ሰነድ መመሪያ ነው ወይስ አይደለም? መመሪያ ነው ከተባለስ የመመሪያ አወጣጥ ስርአትን ጠብቆ ወጥቷል ወይስ አልወጣም እና በዚህ ረገድ ለፋይናንስ ቢሮው በህግ የተሰጠ ስልጣን አለ ወይስ የለም የሚሉ ጭብጦችን መስርቶ መዝገቡን በመመርመር የጥናት ሰነዱ መመሪያ ስለመሆኑና ይህ መመሪያም በህግ ከተሰጠ ስልጣንና ተግባር ውጪ በሆነ ጉዳይ ላይ የመመሪያ አወጣጥ ስርአትን ባልተከተለ መልኩ የወጣና በስራ ላይ የዋለ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ መመሪያው ሊሻር ይገባዋል ሲል ጥር 09 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

09 Jan, 13:12


https://www.facebook.com/profile.php?id=100065172933419&mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

06 Jan, 12:50


አንድ ሰው አስቦ ወደ ሌላ ሰው ሂሳብ ቁጥር ገንዘብ ካስተላለፈ በስህተት ወይም ተጭበርብሮ መሆኑን ካላስረዳ ገንዘቡ እንዲመለስ የመጠየቅ መብት የሌለው መሆኑን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
የሰበር መዝገብ ቁጥር 175660
ህዳር 25/2012 ዓ/ም።

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

05 Jan, 06:49


ተከራካሪዎች ፈቃድ ሰጥተው በሸሪዓ ፍ/ቤት ተከራክረው በመካከላቸው የነበረው ጋብቻ ፍ/ቤቱ በሰጠው የፍቺ ውሳኔ ከፈረሰ፣ የፍቺ ውጤቱንም ሰምቶ ለመወሰን የሥረነገር የዳኝነት ሥልጣን ያለው ይኼው የሸሪዓ ፍ/ቤት ነው። ይህ በሆነም ጊዜ የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍቺ ውጤት የሆነውን የንብረት ክፍፍል ለማየት የዳኝነት ሥልጣን የላቸውም! የሰበር መዝገብ ቁጥር 175719

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

25 Dec, 16:48


የሰ/መ/ቁ 235844
🍁🍁🍁
ንብረቱ ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት መሆኑ ባልተካደበት ሁኔታ በይዞታ ማረጋገጫ ላይ የሌላኛው ተጋቢ ስም አብሮ መመዝገቡ ንብረቱን የጋራ የማያደርገው (አያደርገውም )ስለመሆኑ የተሰጠ የሰበር ትርጉም። የሰበር ውሳኔው የፍ/ህ/ቁ 1195 ማስተባበል የመቻልበት አግባብ የሚያሳይ ነው።

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

25 Dec, 15:18


በጽሁፍ መልስ ላይ መቃወሚያ በሚ
ል ርእስ ያልተጻፈ መቃወሚያ የሰ/መ/ቁ. 222041
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በጽሁፍ
መልስ ላይ መቃወሚያ በሚል ርእስ ባይፃፍም በፍ
ሬ ነገር መልስ ላይ ከተገለፀ ጉዳዩን የሚመለከተው
ፍርድቤት ይህ ክርክራቸው እንደ መጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ ተቆጥሮ በቅድሚያ አልባት ሊ ሰጠው
የሚገባ ነው፡፡ይህን ሳያደርግ የተሰጠ ውሳኔ መሰረ
ታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሊታረም የሚገ
ባው ነው።

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

25 Dec, 14:14


#የመንደር_ውል ረቂቅ ወይም የመንደር ውል በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ስለሚኖረው ውጤት የሰበር ውሳኔ

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

21 Dec, 12:26


የፌደሬሽን ምክር ቤት የሰጠው ውሳኔ።
================
ጋብቻ በህግ ከተደነገጉት የጋብቻ መፈፀሚያ ሥርዓት ውጭ ጋብቻ እንደሌለ ሁሉ በሁኔታ ፍችም እንደሌለ የፌደሬሽን ም/ቤት ወስኗል።
ሥለሆነም የዕርቅ ስምምነት ነጥቦች በባህል ወይም በሀይማኖት ወይም በማዘጋጃ ቤት ሹም ፊት ያልተፈፀመን ጋብቻ ነው ማለት አይቻልም።
በመሆኑም ባል እና ሚስት ከፍች ቡኃላ ይቅር ለቤቴ ተባብለው አብረው ቢኖሩ በሁኔታ ጋብቻ አለ ማለት አይቻልም።
ይቅር ለቤቴ ብለው መኖር ከጀመሩ ከሶስቱ የጋብቻ መመስረቻ መንገዶች በአንዱ እንደ አዲስ ጋብቻ መመስረት አለባቸው ተብሏል።
==================
https://www.facebook.com/profile.php?id=100065172933419&mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

12 Dec, 15:11


https://www.facebook.com/profile.php?id=100065172933419&mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

11 Dec, 11:37


https://www.facebook.com/profile.php?id=100065172933419&mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

10 Dec, 21:02


ማንኛውም ሰው ፌስታል (የፕላስቲክ የእቃ መያዣ ቀረጢት) ይዞ ከተገኘ ከ5,000 እስከ 10,000 የሚያስቀጣው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡


ረቂቅ አዋጁ የፕላስቲክ ምርት አምራቾች ላይ የሚከተሉትን ሀላፊነቶች ደንግጓል፡፡

በዚህም የ #ፕላስቲክ ምርቱ የአገልግሎት ዘመኑ ሲያበቃ እንዲሰበሰብ ለዳግም ጥቅም ወይንም መልሶ ሁደት ላይ ሊውል የሚችልበትን ሥርዓት መፍጠር የፕላስቲክ ምርቱ የአገልግሎቱ ዘመን እንዳበቃ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ በአምራቹ ላይ ጥሏል፡፡

የደረቅ ቆሻሻን ስለመሰብሰብ በተመለከተም ከሚመለከተው አካል በሚሰጥ ፈቃድ ለጥሬ ምርትነት ካልሆነ በስተቀር ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትም የሚከለክል ነው፡፡
ከመኖሪያ_ቤት ይዞታው ድንበር አንስቶ ቢያንስ እስከ 20 ሜትር ባለው ርቀት ውስጥ ደረቅ ቆሻሻን የማፅዳት ሀላፊነት አለበት፡፡

ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ወይንም የንግድ ተቋም ከይዞታው ድንበር አንስቶ ቢያንስ እስከ 50 ሜትር ባለው ርቀት ውስጥ ደረቅ ቆሻሻን የማጽዳት ሀላፊነት አለበት፡፡

ጠርሙስ፣ ጣሳ፣ የታሸገ ውሃ መያዣ ፕላስቲክን በተመለከተም ረቂቁ የምግብ፣ የመጠጥ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና የመዋቢያ ምርቶችን በጠርሙስ፣ በጣሳም ወይም በፕላስቲክ መያዣ የሚያመርቱ፣ የሚያስመጡ፣ የሚያከፋፍሉ ሰዎች ጠርሙስ ወይንም የቆርቆሮ ጣሳ የአገልግሎት ዘመኑ እንዳበቃ መልሶ የሚወገድበትን ዘዴ የመዘርጋት ግዴታ አለበት ይላል፡፡ 

ረቂቅ አዋጁ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የላስቲክ የእቃ መያዣዎችን ወደ ሀገር ማስገባት፣ ማምረት፣ መሸጥና ማከፋፈልን ይከለክላል፡፡

ይህን አድርጎ የተገኘም ከ50,000 ብር እስከ 200,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እና ከ5 ዓመት ያልበለጠ ፅኑ እስራት ይጠብቀዋል ተብሏል፡፡

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

08 Dec, 13:56


ክስ መስማት በኢትዮጵያ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሕጉና አተገባበሩ
በቴዎድሮስ ምህረት (ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት)
ለፍርድ ቤቶች የሚጠየቁ ዳኝነቶችን በገለልተኛ የዳኝነት ተቋም በስነስርአት እና ፍትሀዊነቱን በጠበቀ ሁኔታ በተፋጠነ ፍትህ አሰጣጥ በአነስተኛ ወጪ ፍትህ የመስጠት አላማዎች የስነስርአት ህጎች አላማዎች ናቸው፡፡

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

02 Dec, 14:59


ፍትህ በውድ ገንዘብ የሚገዛ የቅንጦት ዕቃ ሳይሆን የዜጎች መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት ነው!

''በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ከሣሽ ከመሆን ይልቅ ተከሣሽ መሆን በብዙ እጥፍ የተሻለ ነው!'' ፕሮፈሰር አላን ሴድለር

.........................................

የዳኝነት ክፍያ ጭማሪ የፍትህ ሥርዓቱ ወጪ ቆጣቢ፣ ተደራሽና ፍትሐዊ እንዳይሆን መሰናክል የሚፈጥር መሆን የለበትም ፤፤

በሀገራችን በፌደራል ፍርድ ቤቶች እንድተገበር በማለት በዚህ ሳምንት የፀደቀው የዳኝነት ክፍያ የሀገራችንን ዜጎች የኑሮ ደረጃ እና ፍትህ የማግኘት ህገ መንግታዊ መብት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ሳይሆን የዳኝነት አገልግሎቱን እንደ ንግድ ዘርፍ በመቁጠር የመንግስት ገቢ ለማሳደግ የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ ይሰማኛል፤፤

ይህ የተጋነነ የዳኝነት ክፍያ ፍርድ ቤቶች እንደ ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ለጥቅት ሀብታሞች ክፍት ለሰፊው ደሃ ዜጎች ዝግ የማድረግና በህግ ፊት ዕኩል የመታየትና የመዳኘት መብት አደጋ ላይ ይጥላል፤፤

ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ አንፃር ሲታይም እጅግ የተጋነነ ሆኖ አግኚችያለሁ ፤ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዚህ ደንብ ላይ ሚናውን የተወጣ አይመስለኝም ፤፤

ይህ ደንብ በጊዜ ሊታረም የሚገባ ነው፤፤ በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ comparative ጥናት በማድረግ ህጉ ከነባራዊ ሃቅ ጋር የተፋታ ስለመሆኑ ነጥብ በነጥብ እንሞግታለን ፤፤

እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠበቆች ማህበርም በሥራ አስፈፃሚ ደረጃ የውይይት አጀንዳ ሆኖ አቋም ይያዛል፤፤

ፍትህ የቅንጦት ዕቃ ሳይሆን የዜጎች መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት ነው! መንግስት ዜጎችን ሰብዓዊ መብት የማከበር፣የማስከበርና የማሟላት አለም አቀፋዊና ህገ መንግስታዊ ግዴታ አለበት!
ጠበቃ ተከተል ላቤና

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

19 Nov, 18:34


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን በስብሰባዉም የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።።

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

16 Nov, 15:21


#በአዲሱ_የተጨማሪ_እሴት_ታክስ_አዋጅ_የተደረጉ_ለውጦች
=====================
በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ. 1341/2016 የተካተቱ ወይም ከቀድሞው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 የተደረጉ ለውጦች
====================

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

13 Nov, 17:45


በደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በ2011 ዓ.ም ወጥቶ የነበረውን የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ ቁ.149/2011 ለማሻሻል ይህን አዲስ ማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

"የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ /ማሻሻያ/ ቁ. 188

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

07 Nov, 16:14


ህግ ማጥናት ይፈልጋሉ? ለ2024 የትምህርት ዘመን ምዝገባ አለ።
👇👇
https://tinyurl.com/26ro7eas

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

04 Nov, 14:36


ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ማስመለስ
“የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ,
ማንኛውም ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ ይወረሳል፡፡

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

17 Oct, 07:00


የቴሌ አክሲዮን ሽያጭ፦ ሰነድ
prospectus

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

16 Oct, 16:58


የቴሌ አክሲዮን ሽያጭ፦

📌 አጠቃላይ የሼር ድርሻ = 100 ቢሊዮን ብር

📌 በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው = 100 ሚሊዮን አክስዮን

📌 የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር

📌 ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  = 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

📌 ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር

📌 መግዛት የሚቻለው ከጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

📌 የሼር አባላቱ የሚታወቁት = ጥር 23/2017

📌 ሽያጩ በቴሌብር የሚደረግ ይሆናል።

📌 ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።

📌 አክሲዮን ገዢዎች ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍሉ ይሆናል።

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

20 Sep, 13:43


ቅፅ 26 የሰበር ውሳኔ ታትሞ ወጥቷል
አስገዳጅ የሆነው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች የያዘው ቅፅ 26
እዚህ ያገኙታል

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

30 Aug, 18:41


አዲሱ አዋጅ በውሃ ፣ በመብራት እና በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዲከፈልባቸው የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 1341/2016

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

15 Jul, 14:25


ያልታተሙ የፌደራል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

06 Jul, 06:28


Channel photo updated

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

23 Jun, 16:03


በገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ መሰረት-ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሆኑ እቃዎች፣:

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

17 Jun, 16:50


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የመኖሪያ  ቤት ኪራይ ቁጥጥር  እና አስዳደር መመሪያ