تعلم ثم تكلم @bint_hashim_aselfiey Channel on Telegram

تعلم ثم تكلم

@bint_hashim_aselfiey


የሴቶች መስተካከል የማህበረሰቡ መስተካከል ስበብ ነው የወሬ ሳይሆን የተግባር ሰው እንሁን በስሜት ሳይሆን። በሽሪአ እውቀት እንመራ!!!የሴትልጅ ውበቷ ሀያእዋነወ

تعلم ثم تكلم (Amharic)

የሴቶች መስተካከል የማህበረሰቡ መስተካከል ስበብ ነው የወሬ ሳይሆን የተግባር ሰው እንሁን በስሜት ሳይሆን። በሽሪአ እውቀት እንመራ!!!የሴትልጅ ውበቷ ሀያእዋነወnn"تعلم ثم تكلم" አለምና አለም ሀይሎች ስበትን እንወቅ፡፡ በዓለም መረጃዎ ስለውጭ፣ ይከላከላል፣ እና የአዝናኝ ውበቷ ሀያእዋነወ፡፡ ወደእንቅስቃሴ ተያይዞ የተወሰነውን መፈናኛ መረጃ በመጠቀም ከሴት ጋር አገኘን፡፡nnየሴትልጁ ውበቷ ሀያእዋነወ ከሴት ኮሌክሽን ውስጥ ሲጫወት የሚገኝ እና መረብ የሚገኙት ነገራትን እንጠቀማለን፡፡ በላይ ነዋሪዎችን መበቃት እና የሴትን ሰው በሚያስለገቡ ወቅታዊ መመሪያ ምንድን ነው? ወደ ሀገርና አሰባ መንገዶች በመጠቀም ከባቸን እና ከአባላት የገንዘብ አካሄዷን እንዲጠቁ/ቀርብ ሰጡ፡፡

تعلم ثم تكلم

08 Jan, 05:25


😋
📣የዳዕዋህ ፕሮግራም

😓የፕሮግራሙ አቅራቢ፦
1️⃣ኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አልባጂ
ርዕስ፦ስለ ተቅዋህ
2️⃣ኡስታዝ አቡ ሒበቲላህ
ርዕስ፦ስለ ሞት
3️⃣ኡስታዝ ኑረዲን አል ዐረቢይ
ርዕስ፦ስለ ሶብር


✈️መድረክ መሪ፦ወንድም አቡ ሑዘይፋህ

0️⃣0️⃣0️⃣የሚተላለፍበት ቻናል፦
📥📥📥📥📥📥
t.me/tdarna_islam

😮ዛሬ እሮብ ከምሽቱ 3:30😓

تعلم ثم تكلم

07 Jan, 18:12


☞︎︎︎እኒህን የምድር ኮኮቦች ግቡና ተከታተሉ  ማሻአላህ!

🎙ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን
t.me/SheikhMuhammedZainAdam?livestream

🎙ሸይኽ አወል አህመድ
t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed/6161

🎙ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
    t.me/IbnuMunewor

🎙ኡስታዝ አቡ ሙስሊም
t.me/AbumuslimAlarsi

ተቀላቀሉ ትጠቀማላችሁ  ሸር በማድረግም ሌሎችን እናስታዉስ

تعلم ثم تكلم

07 Jan, 18:09


📚ዛሬ ሁላችንም ልንከታተለው የሚገባ አንድ ምርጥ ኪታብ በ ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ ይጀመራል!

▶️ትምህርት የሚሰጠው በዚህ ቻናል ሊንክ ነው👇
https://t.me/fewaidabdurazaq
https://t.me/fewaidabdurazaq

تعلم ثم تكلم

07 Jan, 17:50


የእህቶቼን ልጆች ቂርዓት እያቀራው! ልጅ ያላችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን አጠናክሩ የተሻለ ደስታ ለማግኘት አሏህ ይገዘን!

تعلم ثم تكلم

06 Jan, 19:28


ይች ደግም ገምና ናች 👇👇

«…አቅም ላላቸው ወንድሞች አላህ ያግራላቸዉ። አቅም ለሌላቸውም አቅሙን ይስጣቸውና 2, 3 ,4ም ያግቡ! ባሌና አባቴ ሲቀሩ! አላሁመ አሚን!»
ከአንድ እህት የተላከ መልዕክት ነው።
ኮፒ
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf

ነገሩ ወዲህ ነው

تعلم ثم تكلم

06 Jan, 14:44


https://t.me/SadatKemalAbuMeryem?livestream

تعلم ثم تكلم

05 Jan, 15:50


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته.

በሸይኽ አወል ቢን አሕመድ፦
በተከታታይ ሲሰጥ የነበረው የቁርአን ተፍሲር ትምህርት በትላንትናው እለት የተጠናቀቀ በመሆኑ፡ዛሬ"የአቂደቱል ዋሲጥያ" ትምህርት ይጀመራል።ስለሆነም፡በቦታው ተገኝቶ መከታተል የፈለገ፡#አምራች መስጅድ ፎቅ ላይ ስለሚሰጥ መሳተፍ ይችላል።#በአካል መገኘት ለማትችሉ ከስር ያለውን ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ ስርጭት መከታተል ትችላላችሁ።
t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed

በእራሳና ምክንያት መልእኩቱን ቶሎ ማድረስ ባለመቻሌ አፍወን።

تعلم ثم تكلم

05 Jan, 14:48


ትላልቅ ሰዎችን አክብሩ ዘመናቸው ባለሆነ ዘመን እየኖሩ ነውና

تعلم ثم تكلم

05 Jan, 05:43


👑          ⭐️             ⚡️
ٰ    • ○ ° 🌹🌹🌹• ○ °• ○ °• ○ °
 • ○    🌹🌹🌹🌹    • ○ °  👈አበባውን
• ○ °🌹🌹🌹🌹🌹           በመንካት• ○ °
  • 🌹🌹🌹🌹🌹🌹    ብቻ ምርጥ
○ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹    የሱና 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡  ° :.
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹         ያገኛሉ📡
 • 🌹🌹🌹🌹🌹      ° :.   * • ○       
• ○  🌿🌹🌹🌿      
  • ○ °   🌿🌿            👈
     •        🌿   • ○ °        🌿🌿
 • ○ °        🌿     • ○ ° 🌿🌿🌿
   • ○ °         🌿       🌿🌿🌿🌿
    • ○ °          🌿  🌿🌿🌿🌿🌿
        • ○ °       🌿   🌿🌿🌿🌿
      • ○ °         🌿  🌿🌿🌿
          • ○ °     🌿  🌿° :. * • ○
         °• ○ °      🌿° :.   * • ○
                    🌿° . °☆  . * ● ¸
.    ★  🌿° :.   * • ○ °
        ° .     🌿. * ● ¸
                  🌿       በቀላሉ ይቀላቀላሉ ።
☆  . * ● ¸ .
★ ° . *   ° . °☆  . * ● ¸
.    ★  ° :.   * • ○
🅰️🅰️🅰️⭐️🔗🔡🔡🔡
ለተጨማሪ ሀሳብ አስተያየት  ጥቆማ
@twhidfirst1 ⭐️🔗🔡🔡🔡

تعلم ثم تكلم

04 Jan, 17:51


ልንረሳቸው ብንፈልግም እንኳን  ውስጣችን የማይረሳቸው ብዙ ወንጀል ይዘን እየዞርን ነው  አላህ ይማረን

تعلم ثم تكلم

04 Jan, 17:50


በምድር ላይ አንድም ስኬታማ ሰው የለም ለወላጆቹ  መልካም የመዋል ታሪክ ያለው ቢሆን እንጂ

የወላጆቻችን ነገር አደራ ነፍሴንም ጭምር በጣም ችላ ያልናቸው ነገር ይመስላል በተለይ ወደ ከተማ ጥለናቸው የመጣነው ወላጆቻችን 
እስቲ ላስታውሳቹ ቢያንስ አሁን ይሄንን ፅሁፍ ያንበባቹ ወንድም እህቶቼ ደውላቹ ዘይሩ 👍

تعلم ثم تكلم

04 Jan, 09:43


https://vt.tiktok.com/ZS6ypnapx/

تعلم ثم تكلم

03 Jan, 09:21


ወደ አላህ እቃረብበታለሁ ብለህ የሰራሀቸው ማንኛውም አይነት ስራ
ነብዩ ሰለሏሁ ዐለይሒ ወሰለም ና ሶሀቦች ያልሰሩት /ማያውቁት ከሆነ ከንቱ ድካም እንጂ ሌላ የለውም በል እንደውም ወንጀል ታተርፋለህ

تعلم ثم تكلم

02 Jan, 17:30


ጥሩ ምክር ነው እስቲ እንመከር ወንድሞቼ
~~

ትዳርህን በሚዲያ አታስጣ!!
---------------------------

ደስተኛ ትዳር መመስረትህ እና በፍቅር በደስታ መኖርህ እንጅ ማግባትህን ለማሳወቅ ሚዲያውን ብታጨናንቀው ምን ፋይዳ አለው!?

በሚዲያ ያዙኝ ልቀቁኝ ያሉ (አላህ ካዘነላቸው ውጭ) አብዛኞቹ ባለ ትዳሮች ዛሬ ዘግናኝ ፀፀት ውስጥ ናቸው ።


ሸሪዓው በፈቀደልህ መልኩ ኒካህ ካሰርክ ጭብጨባና ሁካታ እውቅናና ፕሮግራም እያልክ ዋጋ አትክፈል!!ሹልክ አድርገህ አግባ  ወጩ አይቻልም የኔ ሚዜ የሷ ሚዜ አትበል!!

የሰው ልጆች አባት አደም አለይሒ ሰላም እና እናታችን ሀዋ ሲጣመሩ ከጀሊሉ ውጭ ማንም የለም።

➢ከሰማኸኝ ትዳርህን በሚዲያ አታስጣ!!
ሚዲያው ያየውን አሳዶ ማክሰም ልምድ አድርጓል።

የትዳር ጣዕም በዝምታ እና በቤት ውስጥ ሲሆን እንጅ በሚዲያ ከወጣ አፍራሹ ብዙ ነው ተጠንቀቅ!!
منقل

تعلم ثم تكلم

01 Jan, 20:07


Audio from አልሀምዱሊላሂ

تعلم ثم تكلم

01 Jan, 17:57


እሳት ኢብራሂምን አላቃጠለችም
ቢለዋ እስማኤልን አላረደችም
አሳም ዩኑስን አልበላችም
ባህርም ሙሳን አላሰመጠችም አለይሂሙ ሰላም
""قل لن يصيبنا إلا ما كتب الله لنا""
"" ብለህ በላቸው አላህ  ለኛ የፃፈው ነገር ቢሆንጅ አይነካንም""
በዚች የአላህ ንግግር ራስህን አፅና
አላህ ካልፈቀደ :-ማንም ምንም ሊጠቅምህ አይችልም
                        ማንም ምንም ሊጎዳህም አይችልም።



  

تعلم ثم تكلم

01 Jan, 06:14


🎁ታላቅ የሙሓደራ   ፕሮግራም📱


🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️
🔤🔤🔠🔤🔤🔤🔤🅰️🔤  ግሩፕ  ላይ  የዳዕዋ  ፕሮግራም  አዘጋጅተን  እየጠበቅናችሁ  እንገኛለን።

ተጋባዥ 🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠

⭐️ኡስታዝ ኸድር አህመድ
⭐️ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ አል-ባጂ
⭐️ኡስታዝ ዶ.ሰዒድ ሙሳ
⭐️ኡስታዝ አቡ ሱፊያን
⭐️ኡስታዝ አቡ ሙአዝ
⭐️ኡስታዝ አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
⭐️ሼህ አውል አል_ከሚሴ(አቡ አማር)

🔢መድረኩን የሚመሩልን ወንድሞች
አቡ ኹዘይፋ ሰኢድ
አቡ ሂበቲላህ ሁሴን
አቡ ፈዉዛን አብዱ ሽኩር

በእለቱም ታላቅ የምስራች ይኖረናል ሁላችሁም በጉጉት እንድትጠብቁን እናሳስባለን

❄️የፊታችን ጁማዓ✈️

ሰአት ⭐️ ከምሽቱ 3⃣:0⃣0⃣ጀምሮ

  ሙሓደራው  የሚካሄድበት  ግሩፕ
መርከዝ አቡ ፈውዛን🔤✈️🔤
    👇👇👇

t.me/merkez_abu_fewzan
t.me/merkez_abu_fewzan

تعلم ثم تكلم

01 Jan, 03:52


ጀነት አይገቡም

ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም!

ነብዩﷺ
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦

‹‹ከእሳት ሰዎች መካከል ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። እኔ ያላየኋቸው ወደፊት የሚመጡ!
አንደኛቸው ለብሰው ያለበሱ(የለበሰቱ ልብስ ሰውነታቸውን የማይሸፍን) አካሄዳቸው እና እንቅስቃሲያቸው ወደ ፀያፍ ተግባር ያዘነበሉ፤

ሌሎችንም የሚያሳስቱ ፀጉራቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የተከመረ ሴቶች
ናቸው።

እንደነዚህ አይነቶቹ ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም፡፡›› ሙስሊም ዘግበዉታል

አላህ ይጠብቀን መልካም ቀን

تعلم ثم تكلم

31 Dec, 15:10


~በቃ ምንም ብታፈቅሪው ምንም ያክል ብታምኚው..…ሰው ነው ብለሽ አስቢ… እንዳሰብሽው ባይሆን እና ስህተት ቢሰራ ህመምሽን ምትቋቋሚበት ትንሽ ጥንካሬ ለራስሽ አስቀምጪ። ለሱ ካለሽ ፍቅር እና እምነት ትንሽ ለራስሽም አስቀሪ።ሰው ነው ብለሽ አስቢ.... በፍቅርሽ እና በእምነትሽ ልክ ፍፁም አታድርጊው ጥንካሬ እንዲሆንሽ ለራስሽም የመፅናኛ ቃል አስቀምጪ ሰው ነው ብለሽ አስቢ .....

«ሰው ነው»
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan

تعلم ثم تكلم

31 Dec, 14:47


የሰው ልጅ ሚመዘነው ባለው ነገር ሳይሆን በሚሰጠው ነገር ነው

تعلم ثم تكلم

31 Dec, 03:31


ሻዒሩ እንዳለው ነው።

الموْتُ بابٌ وكلُّ الناسِ داخِلُهُ

يا ليْتَ شعرِيَ بعدَ البابِ ما الدَّارُ

الدَّارُ جنَّةُ خلدٍ إنْ عمِلتَ بِمَا

يُرْضِي الإلَهَ، وإنْ قصّرْتَ، فالنّارُ

هما محلان ماللناس غيرهما

فانظر لنفسك ماذا أنت تختار

تعلم ثم تكلم

30 Dec, 19:43


ለመርከዝ ኢብኑ ዐባስ አንደኛ አመት ተማሪዎች ከሚሰጠው ሳምንታዊ የምክር ፕሮግራም

በወንድም ጀላሉ ሁሰይን (አቡ ዚክራ)

በውስጡ:—
➡️ቁርአን በመሀፈዝ ሂደት ላይ አጋዥና
ወሳኝ የሚባሉ 9 ነጥቦች
➡️የሀፈዝነውን ቁርአን እየጠፋብን
ስንቸገር ማከሚያ የሆኑ 4 ወሳኝ
ነጥቦች ተዳሰውበታል

https://t.me/bin_Husseynfurii

تعلم ثم تكلم

05 Dec, 08:11


🎁 ihsan jobs
ኢህሳን
ይህ ቻናል ለሙስሊሙ ማህበረሰብ
ይጠቅም ዘንድ ታስቦ የተከፈተ የስራ ማስታወቂያ
የምንለቅበት አዲስ ቻናል ነው 💎

በቻናሉ ነፃ ማስታወቂያ እንለቃለን
ከናንተ የሚጠበቀው የትኛውም
ማስታወቂያ በውስጥ መሥመር
ለኛ ማሳወቅ ብቻ ነው ➡️

እኛም በነፃ ከሸሪዓ የማይጋጩ ስራዎች
አጣርተን በቻናሉ እንለቃለን
⭐️ @twhidfirst1
🌟 @Tolehaaaaaa
🌟 @AbuNuhibnufedlu

https://t.me/ihsan_jobs
https://t.me/ihsan_jobs

تعلم ثم تكلم

05 Dec, 05:31


ድክመትህን የሚነግርህ ሰው በፍፁም አትጥላ፣እንደውም አክብረው፣የተሻልክ ሰው እንድትሆን፣ የደከመውን ጎንህን፣ እንድታንፀው፣ ስለረዳህ፣ አመስግነው።

تعلم ثم تكلم

05 Dec, 05:24


ለምነድነው በየቀኑ ጀነት ውስጥ ዛፍ የማንተክለው

🎤አብደረዛቅ(🌷ابن مراد)

https://t.me/tulab_ibnumurad

تعلم ثم تكلم

04 Dec, 18:45


አዲስ አፕልኬሽን ተለቀቀ አውርደን እንጠቀም
ሼር በማድረግ እናሰራጨው
ኡሱሉ ሰላሳ ( ሰላሰቱል ኡሱል )
በኢብን ሙነወር በ11 ክፍሎች ተቀርቶ ያለቀ
ማውረጃ ሊንክ
📖📖📖
https://t.me/HUSSENISLAMICAPPS/19784

تعلم ثم تكلم

04 Dec, 09:41


ያኢላሂ ፍፃሜው ያማረ ደስታን ፤ ደርሶ የማይጨልም የማንጠፋበት አንተን ለመገዛት የሚያግዘን ከልባችን የሆነ ኢማን እና ፍቅር ስጠን 🤲

   

تعلم ثم تكلم

04 Dec, 03:54


በ ደግ  ውሎ  አምሽቶ፣
ደህና አድሮ እንደመንቃት፣
       ለሌላ ምእራፍ፣
    ታጭቶ ላዲስ ንጋት፣

ምን አለ የላቀ ለሰው ልጅ ስጦታ?
      ሞት በበዛው አለም
ቁሞ እንደመገኜት ከኗሪዎች ተርታ ።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
➛የጧት ዚክር

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

▪️የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

ውሎህን በዚክር ጀምር


〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
              
#ፈዘኪር   
                 
  

تعلم ثم تكلم

03 Dec, 15:28


ከሌሎች እንደምትሻል ካሰብክ
ሲሰድቡህ በመልካም መልስ
ድንበር ሲያልፉብህ ሚዛናዊ ሁን
መሻልህን በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባርም አሳያቸው!

تعلم ثم تكلم

03 Dec, 13:45


🍎የቁርኣን ግብዣ

      ሱረቱል አልኢምራን

   አንቀፅ 169–177

🇪🇹ቃሪዕ:–ኢብራሒም ኸይረዲን
📖ከቁርኣን ጋር እንኑር❗️

📱https://t.me/ibrahim_furii

تعلم ثم تكلم

03 Dec, 04:03


ቆንጆ ቲላዋ ግብዣ 🍃

تعلم ثم تكلم

03 Dec, 03:48


እቅዳችንን ብቻ ሳይሆን ያጋጠመንን ችግርም ቢሆን ለሰዎች ማውራት ትርፉ ፀፀት ነው።

በእርግጥ በጣም ውስን የሆኑ አላህ ያዘነላቸው ጥሩዎች አሉ ደስታችን የሚያስደስታቸው መልካም አስበው የሚያበረታቱን የአላህ ሰላም በነሱ ላይ ይስፈን

تعلم ثم تكلم

02 Dec, 22:07


ትክክለኛውም ሚዛን የዚያን ቀን ነው፡፡ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ ናቸው፡፡

تعلم ثم تكلم

02 Dec, 19:32


ለሴት ልጅ ሙያ እና አደብ ወሳኝ ነው። የአንዳንድ ባለሙያ ሴቶች ስራ በእግርም ቢሰራ ያስበላ ይመስላል። የአብዛኛው ረኸጦች ግን እጃቸውም ይዘጋል።

ሴቶች ሙያ ልመዱ።

تعلم ثم تكلم

30 Nov, 04:46


⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️📡

⭐️የመተዋወሻ እና ለህፃን አቲካ
⭐️የትብብር  ፕሮግራም

በትዳር እና ኢስላም ቻናል

ኑ! በልብ ህመም እየተሰቃየች የምትገኘው ህፃን አቲካን ሰበብ እንሁናት

በእለቱም ተጋባዥ ኡስታዞች እና ወንድሞች:
⭐️
➡️ኡስታዝ አቡ ሂበተላህ🎤
➡️ኡስታዝ ዓብዱረዛቅ ባጂ 🎤
➡️ኡስታዝ ኢብራሂም ኸይረዲን 🎤
➡️ኡስታዝ አቡ ዑበይዳህ🎤
➡️አቡ ሁዘይፋህ (ሰዒድ)🎤
➡️አቡ ማሂ (ሙሐመድ ኢድሪስ)🎤

የህፃን አቲካ ህመም ምንድነው?👇
t.me/tdarna_islam/4859?single
t.me/tdarna_islam/4863
⬆️
ቀን እና ሰዓት ነገ እሁድ 22/03/2017
ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ➡️

የሚተላለፍበት ቻናል
⭐️ t.me/tdarna_islam
      t.me/tdarna_islam ⭐️

تعلم ثم تكلم

29 Nov, 02:26


ነገ ካንተ የሚሸሸው ጠላትህ ሳይሆን የቅርብ ወዳጅህ ነው።
እናትህ ...እናትሽ
አባትህ ...አባትሽ
ወንድምህ ...ወንድምሽ
ሚስትህ ...ባልሽ
ጓደኛህ ...ጓደኛሽ
ነፍሲ ነፍሲ!
.
.
አንድ ሰው ግን ስለ አንተ ይጮኻል።
ስለ አንቺ አምላኩን ይማፀናል።
ኡመቲ ኡመቲ!

አላሁመሰሊ ወሰሊም ዓላ ሀቢቢ ቁሉቢና ሙሀመድ

تعلم ثم تكلم

28 Nov, 15:57


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ዛሬ የሠላሠቱል ኡሱል ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።

* ቦታ :- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
* ጊዜ :- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
*  የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:- https://t.me/IbnuMunewor/6487
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

تعلم ثم تكلم

28 Nov, 09:22


ሱብሀን አሏህ  !!!

ምንኛ  የሚያምር  ዲን  ነው ያለን ውዶቼ, አላህ እኛን መርጦ ሙስሊም ያደረገን ጌታ ምስጋና ይገባው !!!

ኢስላም  እንደ  ካፊሮች   ቫላንታይን ደይ እያለ ዝሙትን አያስፋፋም ፡፡

የቫላንታይን ደይ ጉዳቶችን በጥቂቱ እንመልከት 👇

➊  አስከፊ የሆነው ዚና ላይ መውደቅን ያስከስታል ፡፡

➋  ያለ  ኒካህ  ልጂ  መውለድና ሂወት መበላሸትን (ያልተፈለገ እርግዝና መከሰትን) ያመጣል ፡፡

➌   ተፋቃሪ ነን በሚሉት ሰዎች መካከል አለመጣጣምና አለመተማመን እንዲኖር ያደርጋል, እንድሁም ጌታቸው  ዘንድ  ውርደትን  ያከናንባቸዋል፡፡

➍  በዱንያም በአኬራም  ትንሺና የተዋረዱ  ይሆናሉ ፡፡

➎   የውስጥ  መረጋጋትና  ሰላምን ያጣሉ  ጭንቀትና  ትካዜ  ያካብባቸዋል፡፡

➏  ምርጥና  ደስ  ከሚሉ ጣፋጭ  የድን  ስርአቶች እንዲርቁ  ያደርጋቸዋል፡፡

➐ በሰዎቺ  መጠላት እንዲሁም በህብረተሰቡ ዘንድ እምነትን ያሳጣቸዋል፡፡

➑  ልቅና  ተቋጣጣሪ  የሌላት  ሴት  በመሆን  ክብሯን  ታዋርዳለች .........

➒  ልባቸው  ይደርቃል (ሀያዕ አይነ አፋርነት ከላያቸው ላይ ይገፈፋል)    .......................

የቫላንታይን ጉድ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም .........

ሴት ልጂ ክብሮን  መጠበቅ አለባት ፡ሴት ወንድ ሲፈለግ  የሚጥላት ሲፈለግ የሚያነሳት እቃ (ሸቀጥ) መሆን የለባትም፡፡


ሴት ልጂ ክብሯ ,ጥብቅ  ሆና  ቤተሰቦቿ ተማምነውባት መርቀዋት ,  ለዘመናት ሰትናፍቀው ለነበረው ባሏ ( ለዛ በጣም ለምትወደውና ስትጓጓለት  ለነበረው ህልሟና  ፍቅሯ ) እንድሁም  ትዳሯ  ሰጦታ  ስትሆን, እና  ንፅህናዋን ለባሏ ስታረጋግጥ ነው ፡፡ ይህ ሲሆን እንዴት ደስ  ይላል በረቢ !  

ይህ  ነው  ክብር ወላህ👆

ዲናችን ለዛም ነው  ዚናንና ወደሱ የሚያቃርቡ  መንገዶችን አትቅረቡ ያለን፡፡

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

تعلم ثم تكلم

27 Nov, 18:42


እውነት / ሀሰት 
((1)) ሸሪአዊ እውቀት መፈለግ መማር ግዲታ ነው ??

ጥያቄ ትክክለኛው መልስ ሰታገኙ የሚያመጣላችሁን add አድርጉለት 👇

تعلم ثم تكلم

27 Nov, 17:26


«ከሚስቶችዎ ሁሉ ማንን አብልጠው ይወዳሉ?» ዐኢሻ ረድየሏህ አንሀ  ነብዩ ﷺ ጠየቀቻቸው።

«አንችን ነዋ» አሏት

«እሺ እንዲህ ብለው አሁን ለሁሉም ሚስቶችዎ ይንገሩልኝ» አለች የበላይነቷን ልታረጋግጥ ጓግታለች።

ነብዩ ﷺ  ፈገግ እያሉ በእጃቸው ከያዙት ተምር አንዷን ሰጧት፦«በቃ ማታ ላይ ሁሉንም ሰብስቤያቸው በነሱ ፊት አረጋግጥልሻለሁ። ግን ተምር እንደሰጠሁሽ ለማናቸውም እንዳትናገሪ» አሏት።

ትተው ወጡ።

ወድያው ወደ ሁሉም ሚስቶታቸው ዘንድ ተራ በተራ ሄደው አንዳንድ ተምር በማከፋፈል፦«ተምር እንደሰጠሁሽ ለማንም እንዳትናገሪ» አሉ።

ቀኑ ጨለመ፤ ሁሉም ተሰብስቧል። ዐኢሻ  የበላይነቷ ሊረጋገጥላት በጉጉት ጠብቃለች።

«ከሚስቶችዎ ማናችንን ነው አብልጠው የሚወዱት?» ብላ ጠየቀች። መልሱ ከባድ ነው...ሁሉም ሚስቶች የነቢን ﷺ መልስ ለማዳመጥ ፈዘዙ።

ነብዩ ﷺ ፈገግ...ፈገግ አሉ።
«በጣም የምወዳት ቅድም ተምር የሰጠኋትን ነው» አሉ።
ተምሩን ቀን ላይ የተቀበሉት ሁሉም  ነብዩ ﷺ ሚስቶች ደስታቸው ልቦቻቸውን እስኪፈነቅል ድረስ ተደሰቱ። ግን ለማንም አትንገሪ ተብለዋል!

ፍትህ
ፍቅር
ብልሀት...ነበራቸው ነብዩ ﷺ

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ».

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

تعلم ثم تكلم

26 Nov, 04:48


ይህ ቻናል ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ባጠቃላይ
እጅግ ጠቃሚ ቻናል ነው
ወደ ቻናሉ ተቀላቀሉ ዛሬ ባይጠቅማችሁ
ነገ ይጠቅማችኋል
👇
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0

تعلم ثم تكلم

26 Nov, 02:42


ሁሌም አመስጋም እንሁን ይህ ፁፍ ብዙ መልክት አለው ስዞር ያገኘሁት ነው

تعلم ثم تكلم

26 Nov, 02:39


አላህ ለዋለልን ፀጋ አመስጋኞች እንሁን

አሁን ወደ ቤት እየሄድኩ ከሀይሌ ጋርመንት ወደ ሰፈራ የሚሄደውን ታክሲ ለመሳፈር ወደ ታክሲ ተራ ስሄድ በጣም ረጅም ሰልፍ አለ። እና እዚህ ከምሰለፍ ቅርብ ስለምወርድ ለምን ወክ አላደርግም ብዬ በእግሬ ጉዞ ጀምርኩኝ።

ወደ ቶታል አከባቢ ስደርስ ሰዎች ተሰብስበው ተመለከትኩኝ ጠጋ ብዬ ስመለከት አንድ ሰው መንገድ ላይ ወድቋል። በቦታው ያሉ ሰዎች ልያናግሩት ቢሞክሩም ምንም መልስ አይሰጥም፣ የሞተ ሰው ነው የሚመስለው። እዚያ የነበሩ ብዙ ሰዎች ቀስ በቀስ መበተን ጀመሩ። እዚያ የቀረነው ሶስት ሰዎች ትንፋሹን ለማየት ወደ አፉ ጠጋ ስንል ሎሊፖፕ (ባለ ዱላው ከረሜላ) አፉ ውስጥ አለ።

ከዚያ ከንፈሩን ስያንቀሰቅስ ተመለከትንና ጎንበስ ብለን ስንሰማው "ስኳር" "ስኳር" የሚል ድምፅ ሰማን። ከዚህ በፊት የዚህ ዓይነት ነገር አጋጥሞኝ ስለሚያውቅ ወደኋላ ሮጥ ብዬ ተመልሼ ካገኘሁት የጀቡና ቡና ሱቅ ትንሽ ስኳር ለምኜ ተመልሼ ወደ ሰውዬው በመሄድ ወደ አፉ ሳስጠጋለት ስኳሩን መላስ ጀመረ። ከጥቂት ሰከንዶች ብኋላ ሰውነቱ መንቀሳቀስ ጀመረ።

ከደቂቃ ብኋላ ድምፁም ትንሽ መሰማት ጀመረ። አጠገቡ ያለውን ፌስታል በእጁ እየጠቆመ ሚሪንዳ ስጡኝ አለ። ሚሪንዳውን ከፌስታል አውጥቼ ሰጠሁት። ትንሽ ቆይተን ሰውነቱ መፍታታት ሲጀምር አንሰተን በቂጡ አስቀመጥነው።

ከዚያ መውራት ጀመረ "በእጄ ከነበረኝ ብር ላይ እቺን ሚሪንዳና ሎሊፖፕ ገዝቼ እጄ ላይ የቀረኝ አስር ብር ብቻ ነው። በህይዎቴ ከሰው ገንዘብ ለምኜ አላውቅም እናም አስር ብሩ ለታክሲ ስለማይበቃኝ ከገላን ኮንዶሚኒየም በእግሬ ጉዞ ጀመርኩኝ። እየራበኝ ነበር ምግብ የምበላበት ብር ስለሌለኝ ዝም ብዬ ተጓዝኩኝ" አለን።

አስባችሁታል የስኳር በሽታ ያለበት ሰው ምግብ ሳይበላ እየራበው ከገላን እስከ ጋርመንት በእግሩ ሲጓዝ። ደግሞኮ ወደየት ነው መዳረሻህ ስለው ገና አብነት ነው የምሄደው አለኝ። ለታክሲ የሚሆን ብር እንኳን ልንሰጠው ስንል በግድ ነው የተቀበለን። የሰው እጅ ማየት የማይወድ ሰው እንደሆነ በደንብ ያስታውቃል።

ታድያ ስንቶቻችን ነን አላህ ሙሉ ጤና ሰጥቶን በትርፍ ነገሮች የምናማርር? ስንቶቻችን ነን አላህ የመድሃኒት መግዣ ብር ሳያሳጣን አሳመምከን ብለን የምናማረው? ስንቶቻችን ነን ከኛ በላይ ስላሉ ሰዎች እንጂ ከኛ በታች ስላሉት የምናስበው?

"إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ
አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና፡፡ ግና አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም"
ይላል አላህ በቁርዓኑ ላይ

ወላሂ ብዙዎቻችን አላህ የሰጠንን ፀጋ ብናውቀው ለሰከንድም ባላማረርን ነበር። አላህ ጤና የሰጠህ ወንድሜ ሆይ፣ አላህ ለህክምና የሚሆን ገንዘብ ያላሳጣሽ እህቴ ሆይ፣ አላህ የታክሲ ገንዘብ ያላሳጣን ሰዎች ሆይ እስኪ አልሀመዱሊላህ እንበል።

አልሀምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን።

تعلم ثم تكلم

25 Nov, 15:29


🔖ኢብኑል ጀውዚይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ :

«ልብ በንፅህናዋና በጥራቷ ላይ አትቆይም፣ ይልቁንስ ትዝጋለች። የዚህ ጊዜ ፅዳትና ህክምና ያስፈልጋታል ህክምናዋም የእውቀት ኪታቦችን መመልከት ነው።»

تعلم ثم تكلم

25 Nov, 09:11


ሱፊ፣ ኢኽዋኒ፣ ተክፊሪ፣… ከመሆን ጠብቆ ሰለፊ ላደረገህ ጌታ ተገቢውን ምስጋና አመስግነው።
① በችሮታው መስጂድ ውስጥ እራሱን እየነቀነቀ የሚጨፍር፣ ሙታን የሚማፀን፣ "ወሃ፞ቢዮ፞ችን አጥፉልን" እያለ ሙስሊሞችን ለማስጨፍጨፍ ካፊሮችን የሚወተውት ሱፊ ከመሆን ጠብቆሃል።
② በእዝነቱ ሙስሊሞችን የሚያርድ isis ከመሆን አትርፎሀል።
③ በጥበቡ በዲኑ የሚሸቅል 12 ፊት ያለው ኢኽዋኒ ከመሆን አድኖሀል። ታዲያ "አልሐምዱ ሊላ፞ህ" አትልም?
الحمد لله على نعمة السنة!

    ~ t.me/IbnuMunewor/980

تعلم ثم تكلم

25 Nov, 03:24


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
በመኖርህ ውስጥ ስለኖሩልህ ሰዎች ውለታ ታስባለህ። በአንፃሩ ስለምትኖርላቸው ሰዎች እጣ ፈንታም ትጨነቃለህ። ህይወት ፍቅርን ታስተምርሀለች። በልምድ ጉዞህ ውስጥ ሰውን በማንነቱ መምረጥ ትችላለህ። ማንን መውደድ እንዳለብህም ትገነዘባለህ። በተለያዩ ክስተቶች መሀል የእውነት አንተን የሚወድህ ማን እንደሆነም ታውቃለህ ። ክስተቶች ሰዎችን ያበጥራሉ። ምርጫህን ለይ !!!
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄


የጧት ዚክር

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

▪️የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

ውሎህን በዚክር ጀምር


〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
              
#ፈዘኪር   
                 

   💐ሰባሃል ... ኸይር 🌸🌸

تعلم ثم تكلم

24 Nov, 09:29


🔖ሰዎችን መለመን ባበዛሽ ቁጥር ታንሻለሽ!
አላህን መለመን ባበዛሽ ቁጥር ግን ትከብሪያለሽ።

تعلم ثم تكلم

23 Nov, 20:32


☝️☝️ሳዑዲዎች !! እንግዳችሁን ተቀበሉት እንጂ !
   ከቻላችሁ በቀጥታ ደውላችሁ
እንደዛ ካልቻላችሁ በኔ በኩል አሳውቁኝ
@Fo1249  ስራ ካለ የሱ username  በውስጥ እሰጣችኋለሁ   ኑ ሀቂቃ ወንድማችን ገና የሳዑዲን ምድር የረገጠው በዚሁ አመት ነው  ተቸግራችሁም ቢሆን ፈልጉለት

تعلم ثم تكلم

23 Nov, 20:32


ስራ ፈልጉልኝ ቤተሰብ

በተለይ.. መካ ፣መዲና፣ጂዳ ያላችሁ

👉ከተገኘ ሪያድም ቢሆን እመጣለሁ።
http://t.me/nuredinal_arebi

تعلم ثم تكلم

23 Nov, 16:34


ሷሊህ የሆነች ሴት(ከስህተት) ጥብቅ አይደለችም:

ነገር ግን ስትገሰጥ ትገሰጣለች፣ ስትመከር ትቀበላለች ከስህተቷ ተመልሳ (ጌታዋን ) ምህረት ትጠይቃልች"

تعلم ثم تكلم

23 Nov, 05:14


አብሽሩ !

ህይወት ሁል ጊዜ ቀጥ አትልም
የሚሰብርህ ችግር ሊፈጠር ይችላል። መሰበርህ ግን መጨረሻህ ነው ማለት   አይደለም ። ማን ያውቃል ለየት ላለ ህይወት የመጀመሪያው ሰበብ ሊሆን ይችላል።  🍃

'' ከችግር ጋር በርግጥ ምቾት አለ''

    

تعلم ثم تكلم

22 Nov, 18:24


🔠🔠🔠🔠

  

    

      
   ረ 

ገባ ገባ በሉ


🖋ርዕስ    ኹሹዕ ፊ ሰላህ ⚫️

🎙አቅራቢ ፦ ከማል አህመድ

የሚተላለፍበት ሊንክ

⬇️
t.me/tdarna_islam?livestream
t.me/tdarna_islam?livestream

تعلم ثم تكلم

22 Nov, 15:27


የተወለደ ህፃን ልጅ ብር ወይም ወርቅ ስጦታ ቢሰጠዉ  የልጁ እናት መዉሰድ ትችላለችን??

መልስ

መዉሰድ አትችልም

ባሏ የልጁ አባት የተስማማ እንደሆነ ሲቀር

የልጁ አባት ወልይ አባቱ ነዉ

ፍርዱ የአባቱ ነዉ

የልጁ አባት ለልጁ እናት እንድትወስድ ከፈቀደ ችግር የለዉም
👇👇👇
https://t.me/HuzeyfaAhmed

تعلم ثم تكلم

22 Nov, 15:03


🍃 እናታችን አዒሻ የሳቀች እለት 🍃

እናታችን አዒሻ እንዲህ አሉ፦ ከእለታት አንድ ቀን የረሱልን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም መደሰት ባየሁ ግዜ እንዲህ አልኳቸው - "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! እስኪ ዱዓ አድርጉልኝ" ? - ከዚያም እንዲህ ብለው ዱዓ አደረጉልኝ ፡ "ጌታዬ አላህ ሆይ ! የአዒሻን ኃጢያት ማርላት ያሳለፈችውንም ወደፊት የሚመጣውንም እንዲሁም  በድብቅ የሰራችውንም በገሀድ በግልፅ የሰራችውንም ሁሉንም ማርላት" አሉ።

ከዚያም እናታችን አዒሻ ከደስታ ብዛት በጣም ሳቀች ፡ በጣም ከመሳቋ የተነሳ በጭንቅላቷ ከረሱል ታፋ ላይ እስክትወድቅም ድረስ ደረሰች ፡

ከዚያም የአላህ መልዕክተኛ - ምነው ዱዓዬ አስደሰተሽ ? አሏት ፡

ከዚያም እናታችን አዒሻ - እንዴታ አያስደስተኝ ዱዓችሁ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ አለች ፡

ከዚያም የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦ በአላህ ስም እምላለሁ ይህ ለአንቺ ያደረግኩልሽ ዱዓ በእያንዳንዱ ሶላቴ ላይ ለሁሉም ለዑመቶቼ (ለህዝቦቼ) የማደርግላቸው ዱዓዬ ነው ።

ምንጭ፦ ሲልሲለቱ ሶሒሀህ [(5/324)]

    ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
      
#ሱብሀንአላህ

تعلم ثم تكلم

22 Nov, 11:37


🛜ዛሬ እና ነገ የሚደረጉ የዳዕዋ ፕሮግራሞች

ዛሬ ምሽት በትዳር እና ኢስላም ቻናል

t.me/tdarna_islam/4730
t.me/tdarna_islam/4730

ዛሬ ምሽት በኢብኑ ተይሚያህ ቻናል
⚫️
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13943
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13943
⭐️
ነገ እለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
በደሴ ከተማ
🌟
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/19805
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/19805

🛜ከላይ ባለው ልንክ እየገባችሁ ሙሉ ተጋባዥ እንግዶች እና ርዕስ አንብቡ

تعلم ثم تكلم

22 Nov, 03:46


ሱረቱል  ካፍ   
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ #سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት
اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَوَاتِكَ وَبَرَكَاتِكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ إمَامِ الخَيْرِ وَقَائِدِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ»

تعلم ثم تكلم

21 Nov, 18:45


ጥያቄ ? እውነት/ሀሰት
በአላህና  በመልእክተኛው እንዲሁም በቁርአን መቀለድ ከእምነት ያስወጣል

⭕️ ትክክለኛው  መልስ ስትነኩ  ብቻ  የሚመጣውን
𝕒𝕕𝕕   በመጫን ጠቃሚ የሱና ቻናል ታገኛላችሁ 🛰
    👇👇👇

تعلم ثم تكلم

21 Nov, 15:57


"ያሸባብ ምርጥ አባት ለመሆን ተዘጋጅ"

ልጅክ ባንተ ላይ 3 ሀቅ እንዳለው ታቃለክ?

         1/ምርጥ እናት ልትመርጥለት
         2/ጥሩ ስም ልታወጣለት
         3/ ልጅክን ከቁርዓን ጀምረክ 
           በኢልም ልታነፀው ግደታህ ነው!

➥ አወ ነገ ያላስተማርከውን ካደገ በኋላ አንተ ዱርየ አንተ የማትረባ እያልክ ልትወቅሰው አይገባምና አስቀድመክ ሀቅህን ተወጣ!

አንችም ውዷ እናት ሆይ❗️

እናት=መድረሰቱል አውላድ እንደሆነች ታውቂያለሽን?

አወ እናት መድረሳ ነች❗️

ቡኻሪን እናቱ ናት ያሳደገችው

ኢማሙ አህመድን እናቱ ናት
ያሳደገችው ።

ኢማሙ ሻፊዒን እናቱ ናት ያሳደገችው

እናት ካማረች ልጆች ቤተሰብም ያምራል በአሏህ ፈቃድ!

ለዛም ነው  "ሴት በዲኗ"ና በስነ-ምግባሯ" ካማረች ሁሉም ነገር ያምርልሀል የሚባለው!

ሰለዚህ ለልጆችህ የምትሆንን ምርጥ እናት ምረጥላቸው ኑሯቹህም ያምራልና!

"ሴቶቹም ወንዶቹም ምርጫቹህን አሳምሩ"

    ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

تعلم ثم تكلم

21 Nov, 15:23


በጥቅም ላይ የተመሰረተ ነገር ሁሉ ዘላቂነት የለውም
ሰምታችሆል

تعلم ثم تكلم

21 Nov, 02:04


💯ጀግና ወንድ ማለት ጠዋት ተነስቶ ብረት የሚያነሳው ባለ ጡንቻ ሳይሆን
ብርድ ልብሱን ከላዩ ላይ አንስቶ ለሱብሂ ሰላት ወደ መስጂድ የሚሄደው ነው።

የፈጅር ሰላት

ተነስታችሁ ስገዱ አትተኙ  በእናንተ እና በአላህ መካከል ያለውን ገመድ አትቁረጡ

ሰላት ብርሃን ነው።

ፈጅር ሰላት
አይኖችን ከህልሞቿ ሳይሆን
ለህልሞቿ ነው የሚቀሰቅሳት


🤲አሏህ ሆይ! ከሰጋጆች አድርገን

ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል
አንድ ባሪያ ወደ ሶላት መቆምን ባሰበ ግዜ
ወንጀሉ ሁሉ ትመጣና ጫንቃው ላይ ትደረጋለች
ባጎነበሰ(ሩኩእ) እና ወይን በተደፋ(ሱጁድ) ግዜ ከአርሱ (ወንጀሉ)ትረግፋለች።

🎤አልባኒ ሶሂህ ብለውታል

ከሳሊሆች አንዱ ነውና ሁሌ ከአዛን በፊት ወደ መስጅድ ለምን ትሄዳለክ ተብሎ ተጠየቀና እንዲህ ብሎ መለሰ:-

«አዛን'ኮ ዝንጉዎችን ለማስታወስ ነው ከእነርሱ እንዳልሆን እፈልጋለሁ

ትተኛላችሁ ወይስ ትሰግዳላችሁ ኬትኛው ናቹ ከሰግምጆች ⁉️ወይስ ሸይጧን ካሸነፋቸው
እራሳችሁን ፈትሹ በጊዜ ተኙ ለሱብሂም ተነሱ

تعلم ثم تكلم

21 Nov, 01:31


✿ያንተ ያልሆነን ነገር ያንተ ለማረግ ብዙ አትድከም
ውሳኔው የአላህ ነውና
በሁሉም ነገር ላይ ታገስ አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና
ለሁሉም ነገር አትችኩል(ይ) ችኮላ የሸይጧን ነውና ።

تعلم ثم تكلم

20 Nov, 21:46


🌺ሰኞና ሀሙስን መፆም🌺


💎አቡ ሁረይራ [رضي الله عنه‌‎ ] እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ [صلى الله عليه وسلم] የሚከተለውን ብለዋል፡-

💎“የጀነት በሮች ሰኞና ሐሙስ ይከፈታሉ፡፡ ወንድሙ ጋር የተኳረፈ ሰው ብቻ ሲቀር ከአላህ ጋር ምንም ነገር ለማያጋራ እያንዳንዱ (የአላህ) ባሪያ ይቅርታ ይደረግለታል።

💎እነኝህ ሁለቱን እስኪታረቁ ድረስ
አቆዩአቸው፡

🌺እነኝህን ሁለቱን እስኪታረቁ ድረስ አቆዩአቸው፡፡

💎እነኝህን
ሁለቱን እስኪታረቁ ድረስ አቁዩአቸው፡፡” (በተደጋጋሚ) ሶስት ጊዜ ይባላል፡፡”
በሌላ ሀድስ👇👇

وعن أَبي هريرة رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم قَالَ: ((تُعْرَضُ الأَعْمَالُ يَومَ الاثْنَيْنِ وَالخَمِيسِ، فَأُحِبُّ أنْ يُعْرَضَ عَمَلِي وَأنَا صَائِمٌ)) رواه الترمذي،
🌺አቢ ሁረይራ ባወሩት ሀዲስ ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦

🌺«በሰኞ  እና በሀሙስ ቀናት  ስራዎች ወደ አላህ ይወጣሉ፣ እኔ ፆመኛ ሁኜ ስራዬ ወደ አላህ እንዲወጣ እወዳለሁ» ቲርሚዚይ ዘግበውታል።

🌺ኢንሻ አላህ ውዶች ነገን መፆም አንርሳ ካልቻልን ራሱ ሌሎችን እናስታውስ
🍒🍒🍒
«أدال على الخير كفاعله» أو كما قال رسول.
«🌺ወደ ኸይር አመላካች ልክ እንደሰሪው ነው» ረሱል እንዳሉት።

{ሙስሊም፣ ማሊክና አቡ ዳዉድ ዘግበውታል}

      #መልካምለይል የመኝታ አዝካር እንዳረሱ

تعلم ثم تكلم

20 Nov, 18:14


🔠🔠🔠🔠⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️


  

    

      
   ረ 

ገባ ገባ በሉ


🖋ርዕስ    የቀልብ መድረቅ ⚫️

🎙አቅራቢ ፦ አቡ ዚክራ

የሚተላለፍበት ሊንክ

⬇️
t.me/tdarna_islam?livestream
t.me/tdarna_islam?livestream

تعلم ثم تكلم

20 Nov, 17:42


ክፍል 1

ጉዞ ወደ አላህ እና ወደ አኼራ

በኡስታዝ- አቡል አባስ
ይቀጥላል.....

https://t.me/wereda07wetat
https://t.me/wereda07wetat

تعلم ثم تكلم

20 Nov, 14:44


➡️አዲስ የሙሀደራ ፕሮግራም  🔈
በትዳር እና ኢስላም ቻናል 🟢

ተጋባዥ እንግዶቻችን ▼
⭐️ኡስታዝ ጅላሉ ሁሰይን አቡ ዚክራ
🛜ርዕስ➡️ የቀልብ መድረቅ🔻

🌟ኡስታዝ ኑረዲን አል አረቢ 🎤
                          ርዕስ🎤 ስኬታማ ትዳር
ኡስታዝ አቡ ሂበቱላህ 🎤

⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️📡
ይህ ፕሮግራም ለየት የሚያደርገው
🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤 መሆኑ ነው 

ሰአት እና ቀን
ቀን  ➡️ ዛሬ እሮብ
ሰአት➡️ ከ3:00 ጀምሮ

🔈የፕሮግራም መሪ አቡ ሱፊያን🟢
🕯 🔤🔤🅰️🔤🔤🅰️🔤⬇️

➡️ http://t.me/tdarna_islam
➡️ http://t.me/tdarna_islam

تعلم ثم تكلم

20 Nov, 09:16


የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲሱ  ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው 
በሀገር ውስጥም ይሁን ካሀገር ውጪ ያላችሁ
የሱና ወንድም እና እህቶቻችን 
ይህ ቻናል ይጠቅማችኋል ተቀላቀሉ
👇
join request የሚለውን በመጫን✅️
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0

تعلم ثم تكلم

20 Nov, 02:18


በጀነት ውስጥ ባሉ ፀጋወች አደም ነፍሱ ልተረጋጋ አልቻለችም .ሀዋን አሏህ ሚስት እና መረጋጊያ (سكن)አድርጎ እስከሰጠው ድረስ.
قال الله تعالى: هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا

ባለ ትዳሮች ተመዋደዱ ተመካከሩ ፍቅራችሁን ተገላለፁ، አንዳችሁ ለሌላችሁ ምን ያክል አስፈላጊ እንደሆነ ተነጋገሩ. የአንዱን ደካማ ግን ሌላችሁ ያጠንክር እንጂ በደካማ ጎኑ አታነውሩት እየወሰዳችሁ ለሰው አታውሩ.
እና በሆነ ባልሆነው አትፋቱ please !

تعلم ثم تكلم

19 Nov, 15:02


አላህዬ የፊርዓውን ፈተና ተቋቁማ በተውሂዷ ፀንታ ጀነትል የተሸለመችው የአሲያን ፅናት ለእኛም አጎናፅፈን ጀነትንም ሸልመን

تعلم ثم تكلم

19 Nov, 01:56


አምስት አይነት ሴቶችን ከማግባት ተጠንቀቅ

አንናናህ፣ወሓንናናህ፣ወሐዳቃህ፣ወበራቃህ፣ወሸዳቃህ

① አንናናህ የተባለችዋ:- ስሞታ የምታበዛ ማለት ነው። ምንም ነገር አትወድም ምንም ነገር አያስደስታትም
ከባሏ ጋር ደስተኛ ለመሆን አትችልም
(ሁሌ ስለሁሉ ነገር ስሞታ የምታቀርብ ነዝናዛ ናት)
ባሏ ከውጭ ከገባ ሳአት ጀምራ እስከሚተኛ ከቤትም መልሶ እስከሚወጣ ትነዛነዘዋለች
እንዲህ ያለቸዋ ሴት ሒይዎት ከርሷጋር አያምርም

② ወሐንናናህ የተባለችዋ:- ሁሌም (ባሏን) አንተላይ ማነው የጣለኝ በማለት በነፍሷ የምትመፃደቅ በት ናት። የኔ አምሳያ ላንተ በጤ አትገባም የኔ ቢጤዋ ለእገሌ ነበር የምትገባዋ ሁሌ ወደርሱ ዘወር ባለች ግዜ እድለ ቢስ ነኝ ትለዋለች እደለቢስማ ባልሆን (የአንተ ቢጤ ሳይሆን) እንዲህ እንዲህ ያለ ሰው ያገባኝ ነበር ትለዋለች።

③ ሓዳቃህ የተባለቺዋ:- በአይኗ ሁሉን ነገር የምትቃኝና ሁሉንም ለመያዝ(ለመግዛትን) የምትጓጓ ነች አሉ። ወደቤቷ የመጣች ግዜ ወደባሏ ፊቷ የተቀያየረ ሁና ትመጣለች ማሻአሏህ እገሊት ዘንድ እሄ እሄ እሄ ነገር አለ እኔ ግን ሚስኪን ነኝ(ምንም ነገር የለኝ) ወደ ገበያም ቦታ የሄደች ግዜ ሁሉን ነገር ልትገዛ ታስባለች(ያየችው የሚያምራት ነች)

④ በራቃ የተባለችዋ:- ከባሏና ከቤቷ በራሷ ቢዚ የሆነች ነች አሉ። ነፍሷ እንጅ ሌላ ምንም ነገር አያሳስባትም ነፍሷንና ፕሮተኮሏን በመጠበቅ ከባሏና ከቤቷ ቢዚ የሆነች ነች

⑤ ሸዳቃህ የተባለችዋ:- ወሪየዋ ብዙ ዝምታዋ ቀላል የሆነች ብዙ የምታወራ ማለት ነው።

👇👇👇
https://t.me/HuzeyfaAhmed

تعلم ثم تكلم

17 Nov, 02:23


የፈጅር ሶላትን ጠብቆ ለሚሰግድ ሰዉ 10 ትላልቅ ሽልማቶች እና ስጦታዎችን አላህ ይሰጠዋል።

1- ከሙ^ናፉቆች አለመሆኑ ይረጋገጥለታል።

📌ረሱል (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ለሙናፊቆች በጣም አስቸጋሪ የሆኑ ሶላቶች የኢሻዕ ሶላት እና የፈጅር ሶላት ናቸው።

2- የጀነት መግቢያ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ነዉ።
📌ረሱል (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ፈጅር እና አሱርን የሰገደ ሰው ጀነት ገብቱዋል”።

3- ከጀሀነም ማምለጫ ምክንያት ይሆነዋል።

📌ረሱል (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ፀሐይ ከመውጣቷ በፊትና ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት የሰገደ ሰው ጀሀነም አይገባም።

4 - የአላህ እንክብካቤ እና ጥበቃ ስር ይሆናል።
📌ረሱል (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “የፈጅርን ሰላት የሰገደ ሰው በአላህ ጥበቃ ስር ነው።

5- ሌሊቱን ሙሉ እንደሰገደ ሰዉ ምንዳ/አጅር ይፃፍለታል።
📌ረሱል(ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “በጀመዓ ሆኖ የኢሻእ ሶላትን የሰገደ ሰው ግማሽ ለሊት አጅር ይፃፍለታል፣ ኢሻእ እና ፈጅርንም በጀመዓ የሰገደ ሰው ደግሞ ሌሊቱን ሙሉ ቁሞ ሲሰግድ እንዳደር ይቆጠርለታል።

6- ከመላኢካዎች ጋር መገናኘትን ይገናኛል ስሙም ከመዝገቦቻቸው ላይ ይመዘገባል።

📌ረሱል(ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በናንተ ውስጥ መላኢካዎች በሌሊት እና በቀንም ይሰበሰባሉ በፈጅር እና በአሱር ላይ መስጂድ በጀመዓ ለሰገዱ ሰዎች ወደ አላህ ሪፖርት ያቀርባሉ.......> አልሀዲስ

7- በቂያማ  ቀን ሙሉ የሆነ ብርሃንና ኑር ያገኛል
📌ረሱል(ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹እነዚያ በጨለማ ውስጥ ወደ መስጂድ የሚሄዱትን
#ቂያማ ቀን በሙሉ ብርሃን አብስሯቸው።

8- ከዚህች አለም ሀብቶች እና ጌጣጌጦቿን የሚስተካከለውን ሽልማት ያገኛል ።

📌ረሱል (ዐለይሂ-ሰላም)ሲናገሩ፡- “ሁለቱ የፈጅር ቀብሊያ ሱና ረከዓዎች ከዱንያና በውስጧ ካሉት ሁሉ የተሻሉ/የበለጡ  ናቸው።

የሱና አጅሩ እንዲህ ከሆነ የፈርዱ ሰላት አጅር ምን እንደሆነ መገመት ይከብዳል።

9- ከትላልቅ የአላህ ወፍድ/እንግዶች ዉስጥ ይመደባል።

📌ረሱል (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በቤቱ ውስጥ ውዱእ ያደረገና ሁለት ረከዓን የሱብሂን ሱና ሰግዶ ከዚያም የፈጅርን ፈርድ ጠቀምጦ ጠብቆ የሰገደ ሰዉ ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እና በረህማን እንዳዎች ዉስጥ ይመዘገባል።

10-በርካታ ቸርነትንና በረከቶችን ምንዳንና መልካም ሥራንም ይጎናፀፋል።

📌ረሱል (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ሰዎች ኢሻዕ ሶላትና በፈጅር ሶላት ውስጥ ያለውን አጅር/በረከት/ስጦታ ቢያውቁ ኖሮ መሬት ላይ እየተንከባለሉም ቢሆን ይመጡ ነበር።

ሙእሚን ሰዉ የዱኒያንም ሆነ የአኺራዉን መልካም ነገሮች ሁሉ ለመስብሰብ ይጥራል።

አላህ ሙዕሚን ያድርገን ።

የፈጅርን ሶላት ሁሌ በወቅቱ እና በጀመዓ መስገዱንን ይወፈቀን ያግራልን።🤲

       
#ወደሶላት

      

تعلم ثم تكلم

08 Nov, 15:35


ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ደርሱ የሚተላለፈው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ነው:-

https://t.me/IbnuMunewor

تعلم ثم تكلم

08 Nov, 14:01


አላህ ሆይ እኔ ደካ ማባሪያህ ነኝና እኔ ለኔ አትተወኝ የአላህ በመልካም ዱአችሁ አስራውሱኝ ውድ ቤተሰቦቼ

تعلم ثم تكلم

08 Nov, 09:20


ከዝሙት ራሳችሁን ጠብቁ። ለዚህ ደግሞ ለቻለ ሰው ከትዳር የበለጠ ምርጫ የለም። ለትዳር ቅድመ ሁኔታ አትደርድሩ። መስፈርት የሚያበዛ መጨረሻው አያምርም። ከትዳር ሸሽታችሁ ዝሙት ላይ እንዳትወድቁ። ዝሙት በየትኛውም ዘመን ሰቅጣጭ ወንጀል ነው። በዚህ ዘመን ግን አደጋው ጨምሯል። በአንዱ ባለ ጌ ወንጀላችሁ በቪዲዮ ተሰራጭቶ ጭራሽ ከማትወጡበት ማጥ ውስጥ ይከታችኋል።

ሴቶች እየተሰማ ያለው ደስ የሚል ነገር አይደለም። አግቡ። እንዲሳካላችሁ ዱዓ አድርጉ። ስነ ምግባር ያለው ካገኛችሁ ሁለተኛም፣ ሶስተኛም፣ አራተኛም ቢሆን ሆናችሁ አግቡ። ሊተናነቃችሁ ይችላል። ይሄ ተፈጥሯዊ ስለሆነ ስሜቱ ለመረዳት የሚከብድ አይደለም። ይበልጥ መፍራትና መጥላት የሚገባው ግን ዝሙትን ነው።

ወንዶች አላህን ፍሩ። ከዝሙት ራቁ። ከቻላችሁ አግብታችሁ ተሰተሩ። ዝሙት ብድር ነው። ባላሰባችሁ አቅጣጫ እዳውን ትከፍላላችሁ። ደግሞም ለትዳር ዋጋ ስጡ። ለሴቶች ፈተና እየሆናችሁ ወደ ወንጀል አትግፉ

ኡስታዝ ኢብኑ መነወር

تعلم ثم تكلم

07 Nov, 09:58


ድርጅት አቋቁሙ
~
ለመስጂድ ማሰሪያ፣ የተቸገሩን ለመርዳት ከበጎ ፈቃደኞች ገንዘብ መሰብሰብና ማስተባበር በቁርኣንና በሐዲሥ መሰረት ያለው ትልቅ ኸይር ነው። ይሄ በተቋም ደረጃም ይፈፀም፣ በግለሰብ ደረጃም ይፈፀም የሚደነቅ እንጂ የሚወገዝ ተግባር አይደለም። እንዲያውም ቁርኣን ውስጥ ደካሞችን በማገዝ ላይ አላማነሳሳት ነው የከሃዲዎች ተግባር እንደሆነ ተወግዞ የምናገኘው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ أَرَءَیۡتَ ٱلَّذِی یُكَذِّبُ بِٱلدِّینِ (1) فَذَ ٰ⁠لِكَ ٱلَّذِی یَدُعُّ ٱلۡیَتِیمَ (2) وَلَا یَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِینِ (3) }
"ያንን በምርመራው የሚያስተባብለውን አየህን? (ዐወቅከውን?) ይህም ያ የቲምን በኀይል የሚገፈትረው፤ ድሃንም በማብላት ላይ የማያግባባው ሰው ነው።" [አልማዑን፡ 1-3]

ነብያችንም ﷺ በተደጋጋሚ ሰዎችን ለሶደቃ አነሳስተዋል። በዒድ ቀን ሴቶችን ለሶደቃ ቀስቅሰዋል። መስጂድ ላይ ከሙዶር ጎሳ ለሆኑ ችግረኞች እርዳታ ሰብስበዋል።

ስለዚህ በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን ልመና ላይ ተሰማርተዋል እያሉ ማንቋሸሽ በማንም ቢነሳ ተቀባይነት የሌለው ትችት ነው። "ረቢዕ እንዲህ ብለዋል"፣ "ሙቅቢል እንዲህ ብለዋል"፣ "ሙሐመድ ብኑ ሃዲ እንዲህ ብለዋል" እያዩ የተንጓለሉ ጥቅሶችን ማራገብ አጉል ጭፍን ተከታይነት ነው።
1ኛ፦ የነሱን ንግግር ባልተገባ መልኩ ከኸይር ስራ ማሰናከያ እያደረጉ መመንዘር አይገባም።
2ኛ፦ ከከልካዮቹ በዒልምም በብዛትም የሚልቁ ዓሊሞች ፈተዋዎች እጅግ ብዙ ናቸው።
3ኛ፦ ከምንም በላይ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃ ያለው ከሚፈቅዱት ጋር ነው። ለኸይር ስራ እርዳታ ማሰባሰብን የሚነቅፍ አንድም መረጃ የለም።
አለኝ የሚል ካለ በአደብ ማቅረብ ይችላል። ከነጥብ ከወጣ፣ ከአደብ ካፈነገጠ አስወግዳለሁ።

ተግባሩ ላይ የተሰማሩት እምነት የማይጣልባቸው መሆናቸው ከተረጋገጠ ያኔ ለይተን እንናገራለን። ሂደቱ ላይ ስህተት ከታየም እንዲሁ ነጥሎ ስህተቱን ብቻ ለማረም መሞከር ነው። እንጂ በደፈናው እያወገዙ ደካሞች የሚታገዙበትን ስራ ማሰናከል የተሳሳተ አካሄድ ነው።

የሚገርመው እንዲህ አይነቱን ተግባር ልመና እያሉ የሚያጣጥሉ አካላት ራሳቸው የተቸገረን ለመርዳት፣ መስጂድ ለመገንባት፣ የራሳቸውን ቡድናዊ ተግባር ለመፈፀም ሲሆን ልመና ላይ የሚሰማሩ መሆናቸው ነው። ለምን? የሚወገዘው ተግባሩ ሳይሆን አተገባበሩ ከሆነ በጅምላ እያወገዝክ የተዛባ መልእክት አታስተላልፍ። የሚወገዘው ተግባሩ ሳይሆን እንደ ፈፃሚዎቹ ማንነት ሑክሙ የሚለያይ ከሆነ ይሄ ዲን ሳይሆን ቡድንተኝነት ነው።

ለማንኛውም ፕሮጀክት መቅረፅ፣ ፈንድ ማሰባሰብ የምትችሉ አቅሙ ያላችሁ ወገኖች ድርጅት እየከፈታችሁ አካባቢያችሁን አግዙ። ወገናችሁን እርዱ። መስጂዶችን ስሩ። መሻይኾችን አቋቁሙ። የቲሞችን አልብሱ። ትምህርት ቤት፣ ሃኪም ቤት ስሩ። ውሃ አውጡ። በጦርነት ወይም በሌላ ምክንያት ህይወታቸው የተመሰቃቀለባቸውን ወገኖች በምትችሉት ከጎናቸው ቁሙ። እነዚን ስራዎች እየሰሩ ነው እምነት የሚያስቀይሩ ሚሺነሪዎች ወገኖቻችን ላይ እየዘመቱ ያሉት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

تعلم ثم تكلم

07 Nov, 02:19


ይሄን ነገር በቻላችሁት አቅም ሰው የሚበዛበት ግሩፕ ላይ አሰራጩት በአሏህ ስል እማፀናችሀለሁ የዚህ ልጅ አባት ልጀ ብሎ በፖሰተ ቁጥር እኔ ውስጤ ይደማል አሏህ በምንወደው ነገር አይፈትነን

تعلم ثم تكلم

06 Nov, 23:34


CMC አህባሾችና የተብሊጎች መርከዝ
ሙሓደራው በድምፅ ማስረጃ የተደገፈ ነው፡፡

1) የላኢላሃ ኢለላህን ትርጉም ማዛባት፣
2) ኢስላም ላይ መዋሸት፣
3) ውሸታም ሰዎችን ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣

4) በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሙስሊም እራሱን፣ ቤተሰቡን እና መላው ሙስሊም ማህበረሰብን ከ CMC መርከዝ ያርቅ፡፡

ማስረጃውን በጥሞና እናዳምጥ፣ ከዛም በነዚህ ሰዎች ለሚታለሉ ሰዎች እናሰራጨው፡፡

=
t.me/SadatKemalAbuMeryem

تعلم ثم تكلم

06 Nov, 14:45


ስደት ሰው ይገድላል

ስንቱ ቆንጅ ሁሉ ውበቱ ረገፈ፡
ስንቱ ጎበዝ ጀግና በእንጨት ተደገፈ፡
ስቃዩ ገደቡን እየተላለፈ፡

ስንቱ አንገቱን ደፋ ስንቱ አቀረቀረ፡
ትዳር እያማረው ስንቱ ቁሞ ቀረ፡
ችግር በችግር ላይ እየተዋቀረ፡

ሀገር ሆነው ሲያዩት ተስፋው ያማልላል፡
ሲገመት ሲታሰብ በጣሙን ደስ ይላል፡
ገብተው ሲቀምሱት ግን ስደት ሰው ይገድላል፡

#...አልተቋጨም....

....✍️ኑረዲን አል አረብ

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

تعلم ثم تكلم

06 Nov, 09:42


ሴትነት ብቻውን ራሱን የቻለ ውበት ነው! አሏህን መፍራትና ቁጥብነት ሀያዕ ሲጨመርበት ደግሞ ይበልጥ ይደምቃል

تعلم ثم تكلم

05 Nov, 17:59


⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ባለቤቶች

የሱና ቻናል ተደራሽነት ይበልጥ ይሰፋ ዘንድ
የቻናል ሊንክ መላክ ትችላላችሁ  ⚡️

✍️መስፈርት 1/ :- የሱና ቻናል ሊሆን ስለማጣራ⚫️
✍️መስፈርት2/ ከ1k member በላይ 🔤 ከዛበታች
✍️መስፈርት 3/:-  ቻናሉን አይቼ አሳውቃቹኋለሁ

🚫ግሩፕ አልቀበልም

⭐️ @twhidfirst1
🌟 @twhidfirst1

تعلم ثم تكلم

05 Nov, 13:50


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

تعلم ثم تكلم

05 Nov, 10:08


https://youtu.be/3EXk7WaLT4k?si=kcel66VEZlpPSR0z

تعلم ثم تكلم

05 Nov, 09:43


በሰማነው መጠቀምና መስራት

ሑዘይፋ መስጂድ የቀረበ ሙሓደራ

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

تعلم ثم تكلم

04 Nov, 17:22


የኔ እህት መህርሽን ቀለል አድርገሽ ከዚና መጠበቅ ባንቺ እጅ ነው።

ይሰማሻል አ"!??

    

تعلم ثم تكلم

04 Nov, 14:23


ገንዘብን የመስጠት ጥቅም

ገንዘብን በኢክላስ የሰጠ ሰው አሳማሚ ከሆነ  ቅጣት እንደሚጠብቀው እና ትልቅ ምንዳ እንደሚመነዳው እንዲሁም ፍርሀትና ሀዘንም እንደሌበት አሏህ ነግሮናል።

አሏህ እንዲህ ይላል

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰ تِجَارَةٍ تُنجِيكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ


«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የምታድናችሁ የኾነችን ንግድ ላመላክታችሁን?» (በላቸው)፡፡


تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُجَاهِدُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ


(እርሷም) በአሏህና በመልክተኛው ታምናላችሁ፣ #በአሏህ #መንገድም #በገንዘቦቻችሁ #በነፍሶቻችሁም #ትታገላላችሁ፣ #ይህ #የምታውቁ #ብትኾኑ #ለእናንተ #የተሻለ ነው፡፡


الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُم بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ سِرًّا وَعَلَانِيَةً فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

#እነዚያ #ገንዘቦቻቸውን #በሌሊትና #በቀን #በድብቅም #በግልጽም #የሚለግሱ #ለእነርሱ #በጌታቸው #ዘንድ #ምንዳቸው #አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ #ፍርሃት #የለባቸውም #እነርሱም #አያዝኑም፡፡

➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
ስለሆነም ገንዘባችንን በመስጠት ላይ እንበርታ !!!!

 ┈┈┈┈┈┈••✦🌹✦••┈┈┈┈┈

         

تعلم ثم تكلم

04 Nov, 09:52


«አሏህን ማውሳት»
-----------------

👉ከዚክር በጣም ተዘናግተናል
👉አሏህን ከማስታወስ ርቀናል
👉የሁሉም መፍትሔ አሏህን ማስታወስ ነውና ወደ አሏህ እንመለስ

🎙በወንድም አቡ-ሀሳን حفظه الله
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

تعلم ثم تكلم

04 Nov, 02:37


~ሁሌም ካንተ ጋር ነኝ፣ ፈፅሞ አልለይህም ለሚሏችሁ ...ሁሌም ከኛ ጋር የሚሆነው አላህ ብቻ ነው በሏቸው።

በዚህች አጭር የዱንያ ላይ ዕድሜያችን ከስንቱ ጋር ወዳጅነት ጀምረን፤ ስንትና ስንት ሰው ወደኋላ ጥለን እዚህ ደርሰናል።ሰው ይረሳል። ይረሳና ሁሉንም ነገር ይረሳል።

ቢሆንም በሂደትም ቢሆን መርሳት የማትፈልጉት ሰው በሕይወታችሁ ውስጥ ይኖራል።ሆነብላችሁ ሳይሆን እረስታችሁ እንዳታጡት አልፎ አልፎ «እባክህን አለህ ወይ» በሉት።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

تعلم ثم تكلم

03 Nov, 15:15


አስታውስ/ሺ !

ቀብርም ሆነ አላህ ፊት ስንቀርብ የምንጠየቀው ስለ ራሳችን ብቻና ብቻ ነው ። ይህን ዕድሜ ሰጥቼህ ነበር ምን አደረግክበት… ዓይን ፣ ጆሮ ፣ እጅ ፣ እግር ፣ አዕምሮ… ሌላም ሌላም ። በዱኒያ ሳለህ ትሰራው የነበረው ሁሉ ይህ ነበር ። ተብሎ የሚቀርብልኝ የግሌ መዝገብ ብቻ ነው ። የማንም አይመጣልንም የማንንም አናይም ። በቃ ይኸው ነው ። መዝገብህን የሚያኮራም የሚያሳፍርም የማድረግ ስልጣኑ ያንተው ነው ። ዋ! እገሌንኮ ወዳጅ አድርጌ ባልይዝ ኖሮ ፣ ዋ! ሰላቴን በአግባቡ ሰግጄ በነበርኮ የሚሉ ፀፀቶች የማይጠቅሙበት ሰዓት በእርግጥ ይመጣል ።  ከመምጣቱ በስተፊት ግን…

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡

የሚለውን የአሏህ መልዕክት መርሃባ ስንል ነው ። ከእሳቱ የምንድነውም የምናድነውም ከክልከላው ፍፁም በመራቅ ወደ አላህ በመሸሽ ነው ። ትዕዛዛቱን በመፈፀም ወደ አላህ በመቅረብ ነው ። መራቅ ካለብንም በሚያቃርበውም ላይ ስንተዋወስ አደራ ስንባባል ነው ። የሀቂቃ መዋደድም ፣ የሀቂቃ ወዳጅነትም ይኸው ነው ። የአላህ ሰላምና እዝነቱ ከዝህች አስቀያሚ  ዱኒያ አሻግረው ስለ ነገው ህይወታችን እንድንጨነቅ ፣ የተፈጠርንለትን ዓላማ እንዳንዘነጋ ፣ ከአላህ እዝነት ተስፋ እንዳንቆርጥ ፣ ድንበሩንም እንዳንጥስ ፣ የሸይጧንን መንገድም እንዳንከተል በሚያስታውሱንና በመልካሙ ዱዓቸው በማይረሱን ላይ ሁሉ ይሁን ።

تعلم ثم تكلم

02 Nov, 16:33


ሰርግ🌺

🥀ሰርግን በተመለከት አጠር ያለ ነሲሀ ለሴቶች
📚ከሪሳለቱል ሂጃብ ደርስ የተወሰደ

🎙ibnu murad
አስታየት ካላቹ 👉@ibnumurad_bot

تعلم ثم تكلم

01 Nov, 18:45


ሀቢብቲ ድክመትሽን የጥንካሬሽ ጉልበት አድርጊው! ውድቀትሽ ለስኬት መድረሻ የሚሆን ሙከራ የመማረያ ቁልፍ አድርጊው።

አንቺ ለውድቀት አልተፈጠርሽም
ምንም እንኳን ሂይወት ብትጠብሽ
ኡኽታዬ ጠንካራና ብርቱ ሁኚ ምክንያቱም ጥሎ የማይጥል የአለማቱ ጌታ አላህ አለልሽና።

    

تعلم ثم تكلم

01 Nov, 12:44


ኡሙ ፋሩቅ ትራስ ጨርቅ መጋረጃ መሸጪያሁሉም ቦታ እዳርሳለን ሊንኩ ከታች ያለውን በመጫን ጆይን በሉ ባረካሏሁ ፊኩም!! https://t.me/+daIuJzn6jKpmMjI0

تعلم ثم تكلم

01 Nov, 02:29


ሱረቱል  ካፍ   
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ #سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት
اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَوَاتِكَ وَبَرَكَاتِكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ إمَامِ الخَيْرِ وَقَائِدِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ»

تعلم ثم تكلم

31 Oct, 22:23


Dinar Graphic Design ነፃ የትምህርት ለማግኘት እየተወዳደርኩ ስለሆነ እባክዎ ይህን ሊንክ     👉👉

https://t.me/+zJluiEkeBYhmZDM0

በመክፈት ቻናሉን ይቀላቀሉት
አመሰግናለሁ

~~~~

تعلم ثم تكلم

31 Oct, 22:12


ወንድሜ አንድ ምክር ልምከርህ!

ከሰዎች ጋር የሚኖርህ ግንኙነት ቡዙ ነገር ያስተምርሀል። ለሰዎች ብለህ የምትከፍለውም ዋጋ ይኖራል።

  በተለይ ጊዜህን ለማን እና ለምን መስጠት እንዳለብህ አስተውል!

              

تعلم ثم تكلم

29 Oct, 12:49


የልቦቻችን ድርቀት

በሙሐመድ ሲራጅ መ/ ኑር

ሳይዝ ፦ 83 MB

Telegram - https://t.me/Muhammedsirage

YouTube - https://youtu.be/r-uhpdzZGWk?si=yM2wPs5fo8id-Tlq

تعلم ثم تكلم

28 Oct, 13:43


አንዳንድ እህቶች ሂጃብ/ሻሽ ነገር ካሰራችሁ/ከለበሳችሁ በኋላ፡ ጆሮአችሁ እንዲታይ ወደ ውጭ የምታደርጉት ለምንድነው?

ኔትዎርክ በደንብ እንዲስብ ነው? ወይስ ጆሮ አይቶ የሚማልል ይኖራል ብላችሁ ነው?

ሀቂቃ ያሳፍራል፡ ሴት ልጅ ክብሯ ሂጃቧ ነው ፡አሏህን እንፍራ።


      ሷህ ወለ ላ."""ያ በናት⁉️

      

تعلم ثم تكلم

28 Oct, 09:23


የምታነበው ቁርአን በዐይኖችህ እና በቀልብህ ላይ ተፅእኖ ማሳረፍ ካልቻለ
መልካም ስራ ላይ እንድትሳተፍ እና ከመጥፎው እንድትርቅ ካላደረገ መሰረታዊ የልብ በሽታ እንዳለብህ እወቅ።
:
ታዲያ ለበሽታው መድሀኒቱ ራሱ ቁርኣንኑን መደጋገም እንጂ ከእሱ መራቅ አይደለም።

"ወንጀል መስራት የሰውን ልጅ አንገቱን ሊያስደፋው እንጂ ደረቱን ሊያስነፋው አይገባም።"

ይሰማል
#አ⁉️  ጀብድ የሰራህ አትምሰል ያአኺ


          

تعلم ثم تكلم

27 Oct, 21:20


🫴 ነገ ሰኞ  ነው።

➷"ነብዩ ﷺ ስለ ሰኞ እና➷ ሀሙስ መፆም ተጠይቀው ‼️

➷ስራዎች ሰኞ እና 💎ሀሙስ (ወደ አላህ) ይወጣሉ  ስራዬ ➷ፆመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ” አሉ 💎
"ፆምና ቁርአን የቂያም ቀን
ለአላህ ባርያ ዋስ ይሆናሉ..."
ረሱል(ﷺ)
(ሰሂህ አልጃሚ:3882)

تعلم ثم تكلم

27 Oct, 19:21


ወሕብ ኢብኑ ሙነቢህ፡

"
#የላጤ_ምሳሌ: ልክ ነፋስ ወደዛ ወደዚህ እንደሚያወዛውዘው በምድረበዳ/በሜዳ ላይ እንዳልለ ዛፍ ነው" ብሏል🌴

ተወዛዋዦች አሏህ ይዘንላችሁ፡ እኛስ ቀጥ ብለናል።


           
          

تعلم ثم تكلم

27 Oct, 03:38


ኢማሙ አህመድን አሏህ ይዘንላቸውና፡

ለምን ሰዎችን አትወዳጅም? ሲባል
የመለየታቸውን ጭርታ ፈርቼ ነው አለ!
وبعضُ الحكماء سَمِعَ قائلا يقول:
الفِراقُ أخو الموتِ.
فقال: بل الموتُ أخو الفراقِ.

አንድ ጥበበኛ፡ መልለየት የሞት ወንድም ነው ሲባል ሲሰማ፡

አይ! ይልቁንስ ሞት የመልለየት ወንድም ነው አለ!

አሏህ በእዝነቱ እስከ ጀነተል ፊርደውስ ድረስ አብረን የምንዘልቀው ጥሩ ጓደኛ ይስጠን።

➡️የጧት ዚክር

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

▪️የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

ውሎህን በዚክር ጀምር


〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
               #ፈዘኪር   
                 

   ሰባሃል ... ኸይር


          

تعلم ثم تكلم

26 Oct, 09:33


ሐብታም ማለት ባለው የሚብቃቃ ነው።

ሥንት ሚሊዮን ያላቸው ድሆች አሉ መሰላችሁ።!

تعلم ثم تكلم

26 Oct, 02:10


ምናልባትም የፈጅርን ሶላት ሰግደህ፡ ዙሁር  ላይ ባንተ ላይ ሊሰገድብህ ይችል ይሆናል።

ስለሆነም ሁሌም በአሏህ ጥበቃ ላይ እንሁን!

የፈጅር ሶላት በጀመዓ በመስጂድ መስገድ በአሏህ ጥበቃ ስር ያደርጋል፡ ፊትን ልብን ቀብርን ያበራል።

ውሎአችንንም ስኬታማና ያማረ እንዲሆን ሰበብ ይሆንልናል።

ለይል|ዊትር|ፈጅር


➡️የጧት ዚክር

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

▪️የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

ውሎህን በዚክር ጀምር


〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
              
#ፈዘኪር   
                 

   ሰባሃል ... ኸይር


       

تعلم ثم تكلم

25 Oct, 15:24


መቼና የት እንደምትሞት አትጠይቅ!

ምክነያቱም ይህ ጉዳይ፡ ዱንያ አንተ ላይ የፈለገውን ያክል ብትረዝምም መሆኑ/መከሰተ አይቀሬ ነውና።

ነገር ግን ጥያቄው፡

በምን ሁኔታ ላይ ሁኜ ነው የምሞተው? የሚለው ነው።

ሸይኽ ሷሊህ ኢብኑ ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና።

አሏህ በእዝነቱ መልካም ፍፃሜን ይለግሰን።

تعلم ثم تكلم

25 Oct, 10:02


እህት ወንድሞቼ በዱአችሁ አስታውሱኝ

لا أحد يذكر شخصاً في دعائه إلا وقد صدق حبه

ውዴታው የእውነት ቢሆን እንጂ አንድም ሰው በዱአው ላይ አንድን ሰው አያስታውሰውም።

تعلم ثم تكلم

25 Oct, 04:21


ሱረቱል  ካፍ   
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ #سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት
اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَوَاتِكَ وَبَرَكَاتِكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ إمَامِ الخَيْرِ وَقَائِدِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ»

تعلم ثم تكلم

25 Oct, 02:07


ስንቶች አሉ የዛሬን መንጋት ለማየት ከጅለው ያልቻሉ። እኛ ግን አነጋን የዛሬዋን ፀሀይ አየን አልሃምዱሊላህ!!

ስንቶች አሉ ትላንት ሙሉ ጤነኛ የነበሩ ዛሬን ግን ያን ተነፍገው ያደሩ ። እኛ ግን በሙሉ ጤንነት አነጋን አልሃምዱሊላህ!!

የፈለግከውን በር አንኳኳ
- ወደ ፈለግክበት ሂድ
- ከሀዘንና ፈተናዎችም አምልጥ
#ግን ከአላህ በስተቀር ህመምህን አስረስቶህ ፣
ቁስልህን ፈውሶ እንዲሁም ሀዘንህን ወደ ደስታ
ሚቀይርልህ አታገኝም ።


የጧት ዚክር እንዳንረሳ!!
      〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
              
#ፈዘኪር   
                 

   ሰባሃል ... ኸይር

تعلم ثم تكلم

24 Oct, 19:04


ማነው ዐቅለኛ
ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና የተባሉ ሊቅ እንዲህ ይላሉ :-
" ዐቅለኛ ማለት ኸይርና ሸርን የሚያውቅ ሳይሆን
ዐቅለኛ ማለት ኸይርን አይቶ የሚከተል
ሸርን አይቶ የሚርቅ ማለት ነው "

تعلم ثم تكلم

24 Oct, 16:15


ፀጉራችሁን አታበላልጡ
               ▭▬▭

ከፊል የራስ አካልን ላጭቶ ከፊሉን መተው በእስልምና እጅግ በጣም የተወገዘ ነው።
ይህንንም የሚያመላክት በርካታ ሀዲሶች ከመኖራቸው ጋር በአላህ ፍቃድ ጥቂቱን ብቻ ለማውሳት እወዳለሁ

عن ابن عُمر رضي اللَّه عنهُما قَالَ: "نَهَى رسُولُ اللَّه ﷺ عنِ القَزعِ" متفق عَلَيْهِ.‎
አብደላህ ኢብን ኡመር ረዲየላሁ አንሁማ እንዲህ ይላል፦
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከቀዝዕ (የራስን ግማሹን ክፍል ላጭቶ ግማሹን ክፍል ከመተው) ከልክለዋል።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

وعَنْهُ ‎ قَالَ: رَأى رَسُولُ اللَّه ﷺ صبِيًّا قَدْ حُلِقَ بعْضُ شَعْر رأسِهِ وتُرِكَ بعْضُهُ، فَنَهَاهَمْ عَنْ ذَلِكَ وَقَال: ‎احْلِقُوهُ كُلَّهُ، أَوِ اتْرُكُوهُ كُلَّهُ‎ رواهُ أَبُو داود بإسنادٍ صحيحٍ عَلَى شَرْطِ البُخَارِي وَمُسْلِم.‎
ከአብደላህ ኢብኑ ኡመር ረዲየላሁ አንሁ ተይዞ እንዲህ ይላሉ፦
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የራሱን ክፍል ግማሹን ተቆርጦ ግማሹን የተወ የሆነን ህፃን ልጅ ተመለከቱ  ወዲያውም ከዚህ ነገር ከለከሉት። እንዲህም አሉ
ወይ ሁሉንም የራስ ክፍል ላጩት ወይም ሁሉንም ተዉት።
ኢማሙ አቡ ዳውድ በሶሒሃቸው  በቡኻሪና በሙስሊም መስፈርት ላይ ዘግበውታል

#ልብ እንበል
➲በዚህ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው ትንሽ ልጅ ነው፤ ምንም አያውቅም፤ ምን ችግር አለው ምናምን ብለው አላግራሩለትም። ይልቁንም ወይ ላጩት ወይ ተዉት ብለው ነው የመለሱለት።  እንደ ቀላል ነገርም አልተመለከቱትም መልዕክተኛው ﷺ ።

በአሁን ግዜ ያሉት ሰዎች ወጣትነት አታሏቸው አላህንﷻ ከማያውቁ መልዕክተኛውን ﷺ ከማያውቁ ፈረንጅ ኩፋሮች ይዘው አራዳነት መስሏቸው ሸይጧን ሲጫወትባቸውና ሲያሞኛቸው  ይስተዋላሉ።
   ለአቅመ አዳም ላልደረሱ አካሎች ላይ ፀጉርን ግማሹን ላጭቶ ግማሹን መተው ከተከለከለ በወጣቱ ላይ እማ ሊከለከል ይበልጥ ተገቢ ይሆናል።
وعَن عَلِيٍّ ‎ قَالَ: "نَهَى رسُولُ اللَّه ﷺ أنْ تَحْلِقَ المَرأةُ رَأسَهَا" رواهُ النّسائي
አሊይ ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ይላል፦
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሴት ልጅ እራሷን ከመላጨት ከልክለዋል።
رواهُ النّسائي
ፀጉራችሁን የምታበላልጡ ሰዎች ሆይ አላህን ፍሩ መልዕክተኛው ﷺ ከከለከሏችሁ ነገር አሁኑኑ በቁርጥ ተከልከሉ።
ۚ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
(ሱረቱ አል-ሐሽር - 7 )
۞ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَلَا تُبْطِلُوا أَعْمَالَكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡
(ሱረቱ ሙሐመድ - 33)
عَن أبي هُريرةَ عَبدِ الرَّحمنِ بنِ صَخْرٍ رَضِي اللهُ عَنْهُ قالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يقولُ:
مَا نَهَيْتُكُمْ عَنْهُ فَاجْتَنِبُوهُ، وَمَا أَمَرْتُكُمْ بِهِ فَأْتُوا مِنْهُ مَا اسْتَطَعْتُمْ،
رواه البخاريُّ ومسلمٌ.

ከዚህ አስቀያሚ ፋርነት ተግባር አላህ ይጠብቀን

አላህ ሆይ ወጣቱ ወደ ዲኑ የሚመለስበትን ግንዛቤ ስጣቸው

መልዕክቱን ለወንድሞች አስተላልፉልኝ
     ጀዛኩሙላሁ ኸይረን

              
          

تعلم ثم تكلم

24 Oct, 09:38


➡️ዱንያ ውስጥ ጓደኛ ስትይዝ

➠ስትርቀው የምትናፍቀው
➠ስትዘናጋ የሚያነቃህ
➠ዱዓእ ሲያደርግ የማይረሳህ
➠የህይወት መእበል መንገድ ሲያስትህ
የሚመራህን ጓደኛ ያዝ ።
ግን አሁን እድህ ያለ ጎደኛ አለ ወይ ነው ጥያቄው  በጣም አሳሳቢ ነው

تعلم ثم تكلم

24 Oct, 02:29


በዚህ ሌሊት ስንት ሰው ወደ አኼራ ተሻግሮ ይሆን ? ይህችን ንጋት ሳይታደል ከሞት የተገናኘ ስንት ይሆን ? እኔና አንተ ግን አንግተናል :: እኔና አንቺ ግን አንግተናል :: ለምን ? አላህ ስለፈቀደ ማለት ነው :: ምስጋና ይድረሰው :::

  ሁሉም ነገር ለእርሱ "ኩን ፈየኩን!" ነው :: ስለዚህ ባደለህ ንጋት ውስጥ መልካም ነገርን ይወፍቅህ ዘንድ ጠይቀው :: ትላንት ያገኘኸውን አይነት ብቻ ሳይሆን አገኘዋለሁ ብለህ የማታስበውን እንኳ ስጠኝ በለው :: በሩን ደጋግመህ አንኳኳ :: አዕምሮህ አንተ  አትችልም ብሎ የሚነግርህን ነገር በሙሉ ጠይቀው :: ምክንያቱም እርሱ የአለማት ጌታ ነው :: እሱ የተዓምራት ሁሉ ባለቤት ነው :: እሱ "ሁን!" ብሎ ነገሮችን ሁሉ እንዲሆኑ የሚያስችል ጌታ ነው ::

   አላህ በመልካም ነገሮች surprise ያድርጋችሁ !
   መልካም ውሎ !!


➡️የጧት ዚክር

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

▪️የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

ውሎህን በዚክር ጀምር


〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
              
#ፈዘኪር   
                 

   💐ሰባሃል ... ኸይር 🌸🌸


           

تعلم ثم تكلم

24 Oct, 00:33


ቲላዋ

تعلم ثم تكلم

23 Oct, 13:50


ታላቅ የደዕዋ ፕሮግራም ተጋብዛችኋል ቤተሰብ

መልዕክቱን በማሰራጨት የደዕዋው ተቋዳሽ እንሁን

ተጋባዥ ክቡር እንግዶቻችን

➊ዑስታዝ ኸድር አህመድ ከሚሴ ሀፊዞሁሏህ
➋ዑስታዝ አቡ ረይስ ሀፊዞሁሏህ
➌ዑስታዝ አቡ ሀሳን ሀፊዞሁሏህ
❹ዑስታዝ አቡ ሀፍሷ ሀፊዞሁሏህ

➨የሱና ፕሮግራም በሱና አናብስቶች በሱና ወጣቶች ቻናል....ሐያ...ሞቅ ደመቅ ሸብረቅ እናድርገው ቤተሰብ...


«ምክር ያስፈልጋል»

እንግዳ ሲመጣ ባንጥል እንኳን ሰንጋ፡
ሊንኩን ሸር አድርገን ብለን ጠጋ ጠጋ፡
ከተውሒድ ከሱና እንዳንዘናጋ፡
ከሀሳብ ከጭንቀት እንድንረጋጋ፡

ስሜት ተከትለን ጠመን እንዳንሰክር፡
በሀይማኖታችን እንድንጠነክር፡
በእውቀት ባለቤቶች ያስፈልጋል ምክር፡

የሰው ልጅ ሲገሰፅ ውስጡ ይረጋጋል፡
ከሌሎቹ ሸሽቶ ወደ አሏህ ይጠጋል፡
ይህን ለማድረግ ግን ምክር ያስፈልጋል።


ሐያ..ቤተሰብ ከወድሁ ቤታችንን እናሟሙቀው በርቱ እንበርታ..

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://彡t.me/nuredinal_arebi
http://彡t.me/nuredinal_arebi

تعلم ثم تكلم

23 Oct, 09:21


አላህዬ ውሎዋችሁን ፍክት ያለ የተዋበ የምትደሰቱበት ያድርግላችሁ

يَا حَيُّ يَا قَيُّومُ بِرَحْمَتِكَ أَسْتَغِيْثُ، أَصْلِحْ لي شَأْني كُلَّهُ، وَلَا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ

አንተ ህያዉ የሆንክ አምላክ ሆይ አንተ ራስክን የቻልክ አምላክ ሆይ በእዝነትክ እታገዛለሁ፡፡ ጉዳዩን ሁሉ የተስተካከለና መልካም አድረግልኝ፡፡ ለቅፅ በት እንኳ እኔን ለራሴዉ ብቻ አትተዎኝ፡፡

تعلم ثم تكلم

22 Oct, 15:13


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

تعلم ثم تكلم

22 Oct, 14:09


سُبْحَان الله ، والْحَمْدُ الله ، ولا إلَهَ إلا الله ، والله أكْبَر ، ولا حَوْلَ ولا قُوَّةَ إِلا بِالله : كررها وأنشرها ولك الأجر🌿🥀
🍃🌻

تعلم ثم تكلم

22 Oct, 09:11


ድኑ ላይ ጠንካራ የሆነ ሰው ዱኒያ ላይ ችግሮች ሁሉ ተሰብስበው እርሱ ላይ ቢሆኑ እንኳን ደሥተኛ ይሆናል

تعلم ثم تكلم

20 Oct, 09:31


ዱኒያ የጀመራት እንጂ የጨረሳት የለም

تعلم ثم تكلم

20 Oct, 07:50


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ውድ የተከበራቹህ ወንድምና እህቶች
ሃዋላ በታማኝነት መላክ የምትፈልጉ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

ቴሌግራም
@abureyyis

تعلم ثم تكلم

19 Oct, 16:41


ስትነቀቢ ግርማ ሞገስ አለሽ
አንቺ እኮ ውድ ሴት ነሽ፤
ስትራቆቺ ግን የረከስሽ ነሽ
ብዙ ዝንቦች ያርፉብሻል(ይከጅሉሻል)።

9,660

subscribers

588

photos

241

videos