☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين) @almutehabin Channel on Telegram

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

@almutehabin


💥የዚህ ቻናል ስራዎች በአሏህ ፍቃድ፦

ኢስላማዊ ፅሁፎች፣📜
ጠቃሚ ምክሮች፤📜
በሸይኽ አህመድ አደም የሚቀርቡ ሙሀዶራዎች፤ ፈትዋዎችን መልቀቅ ።


ስህተት ስታገኙ

✍️ @Almutehabbot ያድርሱን።

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين) (Amharic)

የዚህ ቻናል ስራዎች በአሏህ ፍቃድ፦ ኢስላማዊ ፅሁፎች፣ 📜 ጠቃሚ ምክሮች፣ 📜 በሸይኽ አህመድ አደም የሚቀርቡ ሙሀዶራዎች፤ ፈትዋዎችን መልቀቅ ። ስህተት ስታገኙ 👇👇👇👇👇 @Almutehabbot ያድርሱን። nnአል-ሙተሀቢን(المتحابين) ከሚገኘው ጽሁፍ በሸይኽ አህመድ አደም ላይ በመወሰን መሳሪያዎችን ይከታተሉ። ይህ ቻናል የምርምር እና መጠቀም እንዲሆኑ ያልቻናል ሰዶምን፣ ፈትዎችን እና ሌላ መረጃዎችን ማግኘት ይችላል። ስለዚህ ስለእለት እና መልካም መሳሀፍን በሸይኽ አህመድ አደም ላይ መረጃ እንድንወደው እናሳል። ስለሆነ በየቻናል ተጨማሪ ያልቻናል ቻናል ይደርሳል።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

08 Jan, 07:11


📌ይህንን ኪታብ ከዐሱር በኋላ መቅራት የምትፈልጉ እህቶች አናግሩኝ።
አንዴ ነው የቀራነው ብዙ አልሄድንም

@Almutehabbot

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Jan, 20:07


☀️ጨዋነት ዝምታ ሳይሆን የሚናገሩትንና የሚናገሩበትን ቦታ ማወቅ ነው።ከንግግር የሚሻል ዝምታ እንዳለ ሁሉ ከዝምታ የሚሻልም ንግግር አለ።ሁሉም በቦታው ሲሆን ዝምታም ጌጥ፣ንግግርም ወርቅ ይሆናል።

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Jan, 19:27


📌ሳታደምጡ እንዳታልፉ ባረከሏሁ ፊኩም
#ሼርም_አድርጉት

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Jan, 19:11


📌አንድ ምርጥ ትንሽ የቆየ ሙሃዶሯህ ልጋብዛቹ
በተለይ ደግሞ ለኛ አስተማሪ ነን ባዮች።
እራሳችንን ለዘነጋን አሳዛኝ ፍጥረቶች

ትንሽ #ጠብቁኝ........

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Jan, 19:04


☀️"በሱና እንመራ"

🔸"የሱና ጎዳና"፥ እውቀት፣ፍትህና ቀናነት 
    የተሞላበት ነው!

👍የቢድዓ ጎዳና ደግሞ፥ አላዋቂነት፣ግፍ፣ ግምትና ስሜትን በመከተል የታጀበ ነው!

💡በግልም ይሁን በጋራ ጉዳዮች ላይ ሁላችንም
የነቢዩን صلى الله عليه وسلم
  እና የሶሓባዎቻቸውን رضي الله عنهم
ፈለግና ጎዳና ብንከተል ዲን ዱኒያችን ባማረና #ኡማውም ይሁን እራሳችን ላይ ችግሮች ባልበዙ ነበር

✍️ሱና ላይ የተመሰረተ አንድነት ኀይል ነው!
😀ቢድዓ ሽንፈት፣ ጥፋትና መለያየትን 
  ያስከትላል!

📥#በነቢዩሏህ ኑሕ ዘመን ምድር በጎርፍ በተጥለቀለቀች ጊዜ ወደ መርከቧ የሸሹ እና ከኑሕ ጋር የሆኑት እንጂ ማናቸውም  እንዳልዳኑት ሁሉ በዘመናችን ካሉ የዲን ፈተና ጎርፍ መዳን የሚችለውም ወደ ነቢያችን ሱና የሸሸ ሰው ብቻ ነውና ሱናን እንወቅ እንከተልም!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Jan, 17:54


☀️አሁን ላይ ማስረዳት ለደከመን ሰዎች...
  እሺ፣አዎ፣ደህና ነኝ፣ የምንወዳቸው #ቃላቶች ናቸው።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Jan, 10:42


☀️የኔ በህይወታችሁ መምጣት ከባዱን ጊዜያችሁን እንድታሳልፉ ሰበብ ከሆንኩባችሁ #ይቅርታ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Jan, 08:12


አልሙሂም

የሚፈጠረው፦ ሰላም 👈ብቻ ነው።

ለማረጋገጥ በትንሹ ለ 1 ሳምንት ወጥታቹ ተመለሱ !!!!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Jan, 07:14


📌ለ ሳምንታት፣ወራት፣አመታት ከሶሻል ሚድያ ብትርቁ/ብንርቅ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል????

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Jan, 21:23


☀️ስለ ማሊክ ቢን ነቢ የትዳር ምክንያት ሲነገር...
መፅሀፍት ቤት ይመላለሱ ነበር አሉ... ከዚያማ በየጊዜው ሊዋሳቸው የሚፈልጉትን መፅሀፍቶችን ሲጠይቁ ሁሌ የሆነች ሴት ቀድማ እንደተዋሰች ይነገራቸዋል ፤ ስለሷ ጠየቁና አገቧት።

አቅል እና ሩህ የተመሳሰለ ጌዜ ተመሳሳይ ነገር ላይ ትኩረት አደረጉ፤ ተመሳሳያዩንም አሏህ #አገናኘ....

እናንተም በምትፈልጉት ልክ ጥሩ ሁኑ ....ጥሩ ምሰሉ ተመሳሳዩን እና ከዚያም በላይ ታገኛላችሁ

وتأنَسُ النّفسُ في نفْسٍ تُوافِقُها
‏بالفكرِ والطّبعِ والغاياتِ .. والقيمِ

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Jan, 17:05


قال الإمام البخاري رحمه الله: إني لأرجو أن ألقى الله وليس أحدٌ يطالبني أني اغتبته.

-البداية والنهاية

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Jan, 12:53


☀️እንዴት ያዘቻችሁ ይቺ ብኩን አለም!!


እንዴት ያዘቻችሁ ይቺ ብኩን አለም!!
ፈተናዋ እንዴት ነው አይፈተን የለም።
ጣፈጠ መረረ እንዴት ያዘቻችሁ፣
ወይስ በኒዕማዋ አታለለቻችሁ።
በብልጭልጭ ቁሷ በእጇ አስገባቻቺሁ፣
እንዴት ያዘቻችሁ ይቺ ብኩን አለም!!
ኒካ አሰረቻችሁ አለች አልፋታም፣
እቀፉኝ ጨብጡኝ አለች አላስፈራም።
እናንተ ስትገፏት እንቢ አለች አለቅም ፣
እንዴት ያዘቻችሁ ይቺ ብኩን አለም!!
ገንዘብ እና ዝና አስረከበቻችሁ።
ምድር የናንተናት አብሽሩ አለቻችሁ፣
የስኬት ማማ ላይ ወረወረቻችሁ።
ጭንቀትን አራግፋ ደስታን ሰጠቻችሁ፣
በውሸት መሀላ ቃል ገባችላችሁ።
እኔን በፈጠረኝ በአሏህ እምላለሁ፣
ይህ ሁሉ ስጦታ ይህ ሁሉ ዝናችሁ።
ጀናዛ ከመሆን ላይከለክላችሁ፣
ከአኺራው ቅጣት ነጃ ላይላችሁ።
የዚች ዓለም ህይወት አታላይነቷ፣
ሞትን ችላ ብላ ስትኖር በስሜቷ።
የአሏህን ትዛዝ አልሰማም ማለቷ፣
ምን ይውጣት ይሆን ሲደርስ ሰዓቷ።
ይችን ምድር አትመኗት ፣
እጅግ በጣም አታላይናት።
ተሳስታ አሳሳች ናት፣
ፋፃሜዋ ዋጋም የላት።

እንዴት ያዘቻችሁ ይቺ ብኩን አለም!!

ጀርባዋን አዞረች አለች እልፈልግም፣
ሪዝቅን አራቀች ደስታንም አልሰጥም።
ሰራዊቷን ላከች ጦሯን ወረወረች፣
አንዱ ፈተና ሲያልቅ አንዱን እየላከች።
የማይለቅ በሽታ አስረከበቻችሁ፣
ሞትን በቀጠሮ ጠብቁ እለቻችሁ።
አስባችሁታል ሞትን በቀጠሮ፣
ዛሬ እሞት ነገ እሞት የስቀቀን ኑሮ።
አስባችሁታል ሞትን በማስረጃ፣
ለማይቀረው ህይወት ሊሆን መሰናጃ።
በትልቅ በሽታ አልጋ ላይ ያላችሁ፣
አንድ ጥያቄ አለኝ የምጠይቃችሁ።
እንዴት አያችሁት ሞትን በቀጠሮ፣
ምንስ ስንቅ ያዛችሁ ልአኺራው ኑሮ።
አብሽሩ አትዘኑ አሏህን ይዛችሁ፣
ጀነተል ፊርደውስን ጀሊል ያድላችሁ።
ለኔስ ለጃሂሏ ምን ምክር አላችሁ፣
#ዱዓም አድርጉልኝ አሏህም #ይስማችሁ።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Jan, 11:08


☀️ቃላትህን ለማያከብር #ዝምታህ ትልቅ መልስ ነው!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Jan, 03:51


☀️" በተናደድክ ጊዜ ወዲያው ወጥተህ አትፃፍ ፤ ቢያንስ አንድ ቀን አሳድረው!! "
____
#ከሸይኽ_ኢልያስ_ምርጥ_ምክሮች ውስጥ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

05 Jan, 20:08


☀️በሰው ስራ ትልቅ ሰው አይኮንም

▪️ከእገሌ ጋ ፎቶ ተነሳሁ፣እገሌ ፈረመልኝ፣ እገሌን ትመስላለህ ተባልኩ!
እሱ እኮ ዘመዴ ነው፣ የእገሌ አድናቂ ነኝ!
▪️በዚህ አንተ ምን ትጠቀማለህ?!
ጊዜህን በሚጠቅም ነገር ማሳለፍ ትትህ በነዚህና መሰል ነገሮች ራስህን አታታልል።
የምታደንቀው ሰው ጥሩ ስራ ሰርቶ ከሆነ ትልቅ የሆነው አንተም ሰርትህ ትልቅ ሰው ለመሆን ጣር።
لا تقل أصلي وفصلي أبدا-
إنما أصل الفتى ما قد حصل.
▪️እኔ የእገሌ ልጅ ነኝ፣ የእገሌ ወላጅ ነኝ፣ አባቴ፣ ወንድሜ፣ እንዲህ ነበር፣ እንዲህ ነገር አላቸው ወዘተ... አትበል።
ሰው በሰራው መልካም ስራ፣ ባለው ሙያና ችሎታው ነው የሚከበረውና ክብርን የሚያተርፈው።
▪️ሰውን ዱኒያም ይሁን ኣኺራህ ላይ የሚጠቅመውና እውነተኛ ክብርን የሚያከብረው ራሱ ደክሞ የሰራው ስራ ብቻ ነው።
▪️ዱኒያ ላይ ለፍተው የከበሩ ሰዎች አድናቂና ለስኬታቸው (አጨብጫቢ) ብቻ መሆን ዳገትን ወጥቶ ከፍታ ላይ መኖርን በመፍራት ሁሌም ገደልና ጉድጓድ ውስጥ መኖርን መምረጥ ነው።
▪️ኣኺራም ላይ ቢሆን "ከአሏህ የሚያርቅ ትልቅነትና የትልቅ ሰው ቤተሰብ አባል መሆን አይጠቅምም" ነው የተባለው።

🛫በዘመናችን ሰርቶ መክበር ያቃታቸው፣ ስንፍና የተቆጣጠራቸው፣ አካላቸው ትልቅ አዕምሯቸው ትንሽ የሆነ፣ ከመተኛትና ከመብላት ውጪ ምንም ሳይሰሩ ኸይርም ይሁን ሸር ሰርተው ዕውቅና ካተረፉ ሰዎች ጎን በመቆም ታዋቂነትና ትልቅነት ለማግኘት የሚጥሩ ሰዎች በዝተዋል።
ትልቅ ከሚሏቸው ሰዎች ጋ አብሮ ለመታየትና ፎቶ ለመነሳት ራሳቸውን ስተው ይሮጣሉ (ይቀብጣሉ)።

ወንድሜ እውነተኛ ትልቅነት የሚገኘው በስራ ነው።
ዋናው ነገር  የአኺራህ ትልቅነት ነው።
ይህ ደግሞ አሏህን በመፍራት፣ በመልካም ስነምግባርና በበጎ ስራ ነው የሚገኘው!!

➡️ጊዜን በማይጠቅም ነገር ማጥፋትና እንደ ሕጻን እቃቃ መጫወቱን ትተን ፡ ያዘዘንን በመታዘዝ፣ የከለከለንን በመከልከል፣ የነገረንን አምኖ በመቀበል፣ በውሳኔው በመደሰት ከአሏህ ጋር ያለንን ግንኙነት እናሳምር።

💡ለማይቀረው ጉዞም ስንቅ እናዘጋጅ።

😊የተፈጠርነው ለጫወታና ለመዝናናት እንዳልሆነም አውቀን ለሞት እንዘጋጅ።

🟠በሁለቱም ዓለም ትልቅነት፣ ደስታና ስኬት የሚገኘውም በዚህ ነው።


#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

05 Jan, 14:27


😋🥳😄🫣😬 መኮሳተር (ፊትን ማጨፍገግ)!
1️⃣#አህመድ_አደም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

01 Dec, 19:32


☀️ምርጥ አባት

አንድ ወጣት ወጣቷን ለትዳር ፈልጎ አባቷን ጠየቀ አባት ወጣቱን ተከታዩን ጥያቄ አቀረበለት ፤

የፈጅር ሶላት ስንት ሰዓት ላይ አዛን ይላል?

ወጣቱ ፦ መልስ አልሰጠም

አባት ፦ ልጄ ውድ ናት 'መህሯ' ደግሞ ከአንተ ዘንድ የለም ልጄን አልሰጥህም። ሲሉ መለሱለት።

አሏህ እንዲህ ብሏል፦

ٱلۡخَبِيثَٰتُ لِلۡخَبِيثِينَ وَٱلۡخَبِيثُونَ لِلۡخَبِيثَٰتِۖ وَٱلطَّيِّبَٰتُ لِلطَّيِّبِينَ وَٱلطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَٰتِۚ أُوْلَٰٓئِكَ مُبَرَّءُونَ مِمَّا يَقُولُونَۖ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ

"መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡ ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ ናቸው፡፡ እነዚያ (መጥፎዎቹ) ከሚሉት ነገር ንጹሕ የተደረጉ ናቸው፡፡ ለእነርሱ ምህረትና መልካም ሲሳይ አላቸው፡፡"
[An-Noor:26]

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

01 Dec, 18:53


☀️ሀራም የሆነ ፍቅር ልክ እንደ ጨዋማ ውሃ ነው.. ምንም ያህል ከርሱ ብትጠጣ ጥምህን አይቆርጥልህም፤እንዲያውም ጥማትህን ይጨምረዋል።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

01 Dec, 18:21


⭕️ሁለቱ ገጣሚ ሚስቶች

الزوجتان الشاعرتان

📚 يُحكى أنه كان لأعرابي زوجتان فولدت إحداهما ولداً والأخرى بنتاً،

☞ሰዎች ዘንድ የሚተረክ ታሪክ ነበረ እሱም ፦

⬇️⬇️
☀️አንድ አዕራቢይ ሁለት ሚስቶች ነበሩት። አንደኛዋ ወንድ ልጅ ስትወልድ ሌላኛው ሴት ልጅ ወለደችለት።

📍فكانت أم الولد تحمله وترقص به أمام ضرتها لتغيضها وتقول:

☀️ወንድ የወለደችው ሚስቱ ወንድ ልጇን ተሸክማ ጣውንቷ ፊት ለፊት ሆኖ ልጇን እያጫወተችና እየተወዛወዘች ትቦርቃለች። ሴት ወላዷን ለማናደድም እንዲህ እያለች ትገጥም ነበር⬇️

🎊 الحمد لله الحميد العالي
أكرمني ربي وأعلى حالي
    ولم ألد بنتاً كجلدٍبالي
لا تدفغ الضيم عن العيال.

☀️ከፍ ላለው አሏህ ምስጋና ይገባው 
ክብሬን ደረጃዬን እጅግ ከፍ አደረገው
ሴትን አልወለድኩ እንደ ብስብስ ቆዳ
ከቤተሰቦቿ በደል መከራን ማታፀዳ

فاغتاضت أم البنت وراحت تشكوا ضرتها إلى زوجها ،فقال لها كلمة بكلمة، قولي لها: مثل ماتقول،

☀️ሴት የወለደችው ሚስቱ ይህን የሰማች ጊዜ በጣም ተናደደች። ለባሏም ስሞታ ልታቀርብ ሄደች። ይህን ግዜ ባሏ "እሷ እንዳለችሽ አንቺም በያት!" አላት።

فنظمت أم البنت أبياتاً وأصبحت ترقص بإبنتها وتقول:

☀️የሴቷ እናትም እንዲህ የሚል ግጥም እየገጣጠመች ልጇን ይዛ መወዛወዝ ጀመረች።

🎉 وما علي أن تكون جارية
تغسل رأسي وتراعي حالية
     وترفع ماسقط من خمارية
حتى إذا ما أصبحت كالغانية
زوجتها مروان أو معاوية
     أصهار صدقٍ ومهورغالية.

☀️ሴት ብትሆን እኔ ምን ገዶኝ
ፀጉሬን ምታጥብ ምታሰናዳኝ
የወደቀ ሻርፔን አንስታ ምትሰጠኝ
ውበቷ ደምቆ እጅግ ስታማልል
መርዋን ወይም ሙዓውያ ያገቧታል
የእውነት አማቾች መህሯ ይወደዳል

🔊 فشاعت أبياتها في الناس،
🔄 ولما كبرت البنت قال الأمير مروان بن الحكم : أكرم بالبنت ولاتُخيب ظن الأم ،
فخطب البنت وقدم لها مئة ألف درهم مهرا.

☀️ይህ የሴቷ እናት ግጥም በሰዎች መሀል በጣም ተሰራጨ። ልጅቷ ያደገች ጊዜ አሚር የነበረው መርዋን ኢብኑል ሐከም "የእናቷን ምኞት ከንቱ አላደርግም!" ብሎ ልጅቷን አጭቶ አገባት። አንድ መቶ ሺህ ዲርሀም መህርም ሰጣት።

فلما علم _ معاوية ابن أبي سفيان- بالأمر قال: لولا أن مروان سبقنا إل
يها لضاعفنا لها المهر،ثم بعث للأم بمئتي ألف درهم هبة من عنده.

☀️ሙዓውያም ይህን ታሪክ ሲሰማ "መርዋን ባይቀድመኝ ኖሮ ከሰጣት መህር በላይ እጥፍ አርጌ አገባት ነበር!" አለ። ከዚያም ለእናትየው ሁለት መቶ ሺህ ዲርሀም ስጦታ ብሎ ላከላት።

#ምንጭ


📚 فوائد ..... من كتاب،
"# لطائفـ المعارف#"
لإبن رجب الحنبلي رحمه الله

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

01 Dec, 15:00


🌹ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ🌷

🍁የቀብር ዓለም መጠሪያው ____ይባላል

🍃ትክክል መሆናቹን የምታቁት ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🍃

add በማለት ውሰዱ

🌐መልካም እድል🌐🌐

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

01 Dec, 14:33


☀️ጥሩ ሚስት የታለ ብለህ አውርተሀል
ደህና ሚስት የታለ ስትል ተደምጠሀል

ጥሩ ባል  ለመሆን አንተስ አስበሀል?

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

01 Dec, 10:42


📌ዛሬም በምትወዱት ቋሪዕ የቁርኣን ቲላዋህ ጋብዙኝ


@Almutehabbot

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

01 Dec, 08:29


☀️ፍቅር #እና ዉዴታ

አንድ ቆንጅዬ  አበባ ሽታዋ የሚያዉድ ዉብ አበባ  ታያለህ ከዛም  ደስ ትልህና ትቆርጣታለህ። የግልህም ታደርጋታለህ
ይህ #ዉዴታ  ይባላል

በተመሳሳይ አንድ ቆንጅዬ  አበባ ሽታዋ የሚያዉድ ዉብ አበባ  ታያለህ ከዛም ዉሐን በማጠጣት ትንከባከባታለህ ሌሎች እንዳይቀጥፏትም ትከላከልላታለህ።

ይህ ደግሞ #ፍቅር ይባላል።

ስትወዳት ትቆርጣታለህ
ስታፈቅራት ግን ትንከባከባታለህ

ወዳጆቼ  በዉዴታ እና ፍቅር መካከል  ሰፊ ልዩነት  አለ  መጀመሪያ ፍቅር ምን እንደሆን እወቁ የወደዳችሁም  የተመቻችሁም ጊዜ አፈቀርን እያላቹህ እንደዉ ዝምብላቹህ  ሚዲያ ላይ #አትነፋረቁብን!  ሲቀጥል  ፍቅር እንዲህ  አታቅልሉት Or አታርክሱት!  ቀላል ነገርኮ አይደለም! ብዙ መስዋዕትነት ብዙ ዋጋ ብዙ ህመም  ብዙ ስቃይ አለዉ። ዛሬ ይዞ ነገ ሚለቅ ዛሬ ፈልጎ ነገ የሚጠላ አይደለም!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

01 Dec, 07:09


☀️ሰው እንደ ባህር ነው ዳርቻውን አይተህ ስለ ጥልቀቱ ለማውራት አትሞክር!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

30 Nov, 19:19


☀️#ወሬህን ትተህ መሳሪያህን ተጠቀም

💥"ዲኑን የበላይ ለማድረግ የሚጥርን ሁሉ
አሏህ ይርዳው

~ዲኑን ለማበላሸት ቆርጦ የተነሳ ሸረኛን ሴራ በሙሉ የራሱ አናት ላይ አላህ ይመልስበት  ("ኣሚን")

☀️ወሬ ማብዛትና በጭፍን መደገፍንም ይሁን መንቀፍን ትተን ገንቢ ሃሳቦችን    
  ለማመንጨት እንሞክር!

~በታላላቅ ጉዳዮች ዙሪያ አቅላቸው ያልበሰለና ዲንም ይሁን ዱኒያን ጠንቅቀው የማያውቁ  ተራ ሰዎች ዝም ብለው ከማውራት ይቆጠቡ
ወሬ ዲንን አይነስርም ሀገርም አይገነባም  ፣ይልቅ የሁሉንም ጊዜና ጉልበት ያባክናል!

☀️የዲኑ ጉዳይ ከልቡ የሚያሳስበው በሙሉ
ሌሊቱን ዜና በመለቃቀም ወይም በእንቅልፍ ማሳለፍን ትቶ ቢያንስ እንኳ ለአንድ ሰዓት በሙሉ ልብ- እየሰገደ ጌታውን ይማጸን! ቀኑንም አሏህ በሚወደው መልኩ ያሳልፍ ዱዓው መቅቡል እንዳይሆን የሚያደርጉ ነገሮችንም ይራቅ!

ዱዓ የሙእሚን መሳሪያ ነውና

💥ይህ ነው ለራሳችንም ይሁን ለዲኑ ሊጠቅም የሚችለው ከንቱ ወሬ የሚያበዛ ግን ቀልቡ ስለሚደርቅ ይህን ማድረግ አይችልም!

☀️ምላሳችንን እንቆጥብ
ከአሏህ መልካምን ነገር ተስፋ እንዳርግ!
~ዲኑን ለመርዳትም ዲኑን እንከተል!
~ስህተትን ስናወግዝም ሌላ
ስህተት ላይ አንውደቅ!

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

30 Nov, 18:00


ሁሉም ነገር ሁለተኛ እድል አለዉ
#እምነት  ሲቀር!

ታማኝነታቹህን  አትጡ! አንዴ ካጣቹህት ግን.....

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

30 Nov, 11:03


☀️ወደ ሰው ህይወት ለመግባትና የሌላውን ልብ ለማሸነፍ ተብሎ ዲነኛና ኢማነኛ የመምሰልና የማስመሰል ሁኔታም #ንፍቅና ነው❗️

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

30 Nov, 07:38


☀️ዛሬ ላይ ከሐራም ወከባ የሚያመልጡት ጥቂት ናቸው።እነርሱም ቢሆኑ ሐራም ነገር ሳይስባቸው፣ሳያምራቸው ቀርቶ አይደለም።የሐራም መጨረሻው እንደማያምር፣ቁጭቱ ከባድ እንደሆነ የፀፀት ግርፋቱ እንደማያስተኛ ስለ ተገነዘቡ ነው

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Nov, 19:43


🚫 በደረት(በሆድ) ተደፍቶ መተኛት

☀️የዒሽ አልጊፋሪ የሚባሉት ሶሓቢይ رضي الله عنه  እንዲህ ይላሉ፥ ( መስጂድ ውስጥ በሆዴ ተደፍቼ በተኛሁበት የሆነ ሰው በእግሩ እየነካካኝ "*ተነስ ይህ አሏህ የሚጠላው አስተኛኘት ነው*" አለኝ ቀና ብዬ ሳይ ረሱል   ﷺ ናቸው
رواه أبو داود وصححه الألباني
📂ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው በሆድ/በደረት ተደፍቶ መተኛት ለወንድም ይሁን ለሴት ክልክል (የተወገዘ ተግባር ) መሆኑን ነው

☀️ታሞ (ምክንያት ኖሮት) በሌላ ጎኑ መተኛት ያልቻለ ሰው ግን ለጊዜው በደረቱ( በሆዱ) ተደፍቶ ቢተኛ ችግር አይኖረውም፣ ይህ በእንዲህ እንዳለ በደረት ላይ መተኛት ለጤናም ጥሩ እንዳልሆነ የህክምና  ባለሙያዎች ተናግረዋል::

☀️ሴት ልጅ በጀርባዋ ተንጋላ መተኛት እንደ ማይፈቀድላት ወይም ተገቢ እንዳልሆነም ታላቁን ታቢዒይ፥
📂 ኢብኑ ሲሪን፣ ዑመር ኢብኑ ዐብዲል-ዐዚዝንና ኢማሙ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የዲን ሊቃውንት ገልጸዋል
በተለይ ደግሞ ሰው ያለበት አካባቢ ላይ ከሆነ:: ይህም ከላይ እንደተገለጸው  በቂ ምክንያት ካለና በሌላ ጎን መተኛት  የማይቻል ከሆነ ግን ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ይቻላል

☀️መላው የህይወታችን ዘርፍ ላይ ሊገጥሙን የሚችሉ ነገሮችን በሙሉ ግልጽ አድርጎ የሚያብራራ ሀይማኖት (ኢስላም) ተከታዮች ያደረግን ጌታ አሏህ የላቀ ምስጋናና ውዳሴ ይገባው
(الحمد لله )

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Nov, 17:10


☀️ሴትነት ክብሬ
      
አልሀምዱሊሏህ ብዬ ልጀምር
ሴት ላደረገኝ የዱንያ ቀንበር የአኺራ ሞፈር።
ሴትነት ስሜ ሴት መሆን ክብሬ፣
የጌታየን ቃል ከኖርኩ አክብሬ።
አንዳንድ ሰው ይገርመኛል፣
ከሴት ወቶ ሴትን ሲንቅ የአጅበኛል።
በሴት አድጎ ሲያሳንሳት ይደንቀኛል፣
አጃኢብ ነው በአንድ አድረው ዘሩንሰታው።
አይኑን በአይኑ አሳይታው፣
ደሞ ሴት ሲል ኧረ ጉድ ነው ።
እናት እህት ሚስት ልጁን፣
ደሞ ሴት ሲል ሲክድ ዘሩን።
ሴትብትልኝ ላንተ መስሎህ ያረክስከኝ፣
ጀዛከሏህ ስሜን ጠራህ አከበርከኝ።
ነብያችን  ያዘዙህን ሶኺኽ ብትል ፣
አደራህን ብትውጣ ሀዲስ ሱናን ብትከተል
ስሜትህን ባታባርር፣
ነበርኩ ላንተ የጀነት በር
&_
የአርሹ ጌታ ያከበረኝ
የጀነት ሰበብ ያደረገኝ
እስልምና ስም የሰጠኝ
  በትክክል እኔ ሴት ነኝ
&_

የእናትን ሀቅ ትንሽ እንኳን ብትታግል፣
ስሜን ብቻ በቁልምጫ ኡሚ ብትል
በርጅናዬ ምላርግልሽ እማ ብትል፣
የኔን ዱዓ ለማግኘት ብትልፋ በቀን ለይል።
እትመልስም ብድርህን ፣
አንዷን እንኳን እ ያልኳትን።
ብትንከባከበኝ ሀቄን ብትወጣ፣
አልሁሽ ብትለኝ ወዳንት ስምጣ።
በሌለህ አይደለም ያለህን ብሰጠኝ፣
በጣፋጭ ቃላት ብታበሽረኝ
ያንተው አካልህ ግራ ጎንህ ነኝ
የነቢ አደራ ጀነት መግቢያህ ነኝ
&__
እናትህ ስሆን ላንተ ፅድቅህ
እህት ስሆን መከበሪያህ
ሚስትህ ስሆን ግማሽ ጎንህ
ልጅህ ስሆን ያንተው ደምህ
ነበርኩ ላንተ ዱንያ አሄራህ
ባትንቀኝ ሴት ናት ብለህ
ቆይ እንዴ ልጠይቅህ
ማንን ልትንቅ ከማን ወተህ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Nov, 13:16


☀️እያመመኝ...

እሺ ሀኪም ጋር ሂጂ?!?

      አይ..

ታዲያ እዚሁ ልትሞቺ ነው??
      
       ሀኪም የሚያድነው አይደለም።

ታዲያ ማነው ሚያድነው???

        አሏህ።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Nov, 11:40


☀️#ብቸኝነት አይሰማቹ ሁሌም ከአሏህ ቀጥሎ በዝምታ ስለ እናንተ የሚጨነቅ አንድ ሰው አለ።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Nov, 07:40


☀️አሳውን ከውሀው አውጥቶ "ከመስመጥ አዳንኩት" ከሚል ሰው ጋ እንዴት መግባባት ይቻላል?

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

28 Nov, 19:02


☀️ብዙዎች ተዋውቀናል
በከፊሉም ቢሆን አሳልፈናል
ባንከስራችሁም ተምረንባችኋል እናመሰግናለን።

‏ نتمنى لكم كل الخير!

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

28 Nov, 15:43


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

የጀነት ገበያ የምትቆመው በየትኛው ቀን ነው

🌱ትክክል መሆናቹን የምታቁት ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

add በማለት ውሰዱ

🔘መልካም እድል🔘

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

28 Nov, 13:39


☀️ሰዎች አብዝተው ሲፈልጓችሁ ችላ አትበሏቸው...የሄዱ ቀን አይመለሱምና!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

22 Nov, 18:15


አልሙሂም በዱዐቹህ አትርሱኝ እሺ
ያ አሏህ....
እና ደግሞ አትጨቃጨቂ አትበሉኝ እሺ 👌
አሏህ ዐፍያ ያድርገን
#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

22 Nov, 17:14


📌የሰሞኑን ጉንፋን ስንቶቻቹን ዘይሯቿል?
እኔም አህለን ብዬዋለሁ
#አልሃምዱሊላህ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

22 Nov, 15:03


☀️ሱለይማን ኢብኑ አል-አዕመሽ ልጃቸውን "በል ሂድና ሰላሳ ሜትር ያህል ርዝመት ያለው ገመድ ገዝተህ ናልን።" አሉት።
"ስፋቱስ?" አላቸው።
"ስፋቱማ አንተን የምታናድደኝ ያህል ይሁን ። " አሉት።

አንዳንድ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ የዚህ ዓይነት ነው። የፈትዋ መስኮት ላይ የተቀመጡ ዑለሞች ትዕግስት ይገርመኛል ።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

22 Nov, 13:14


☀️ለፍቅር በሽታ ከኒካሕ ውጪ መድኃኒት የለውም።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 19:34


☀️የንቃት ደውል
 
    መቃብር እየተዘጋጀልን ነው ፤ እኛስ ተዘጋጅተናል ወይ ?
      መላኢኮች እየፃፉ ነዉ ፤ እኛስ መርጠን እየተናገርን ነው ወይ ?
    ጀነት ተኳኩላ እየጠበቀች ነው፤ እኛስ እየሠራንላት ነው ወይ?
      ጀሀነም ታዳኝ ፍለጋ አፏን ከፍታለች፤ እኛስ እየሸሸናት ነው ወይ?
      ቂያማ /የትንሣኤ ቀን/ እየተቃረበ ነው፤ እኛስ ተሰናድተናል ወይ?
   የጉዟችን ቀን ደርሷል፤  እኛስ ትክክለኛና በቂ ስንቅ ሰንቀናል ወይ ?

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 19:02


☀️አንዳንድ ሰዎች ስትርቃቸዉ  ስለ አንተ ችግር ምን እንዳጋጠመህ ከመጠየቅ እና የዉስጥህን ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ ...
ከተወኝ ጉዳዩ እሚሉት ነገር .....🙌

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 18:40


☀️አብዛኛው ሰው ቤት ሲገባ የመጀመሪያው ጥያቄ......

እናቴ የታለች ??.....

ፈልጊያት ሳይሆን
በቃ ሳያት ሰላም ስለሚሰማኝ ነው።

#ኢሚሚሚሚሚ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 15:33


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

አባታችን አደም 『عليه السلام』 የተፈጠሩት በየትኛው ቀን ነው

🌱ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  እሁድ 『الأحد 』

ለ}  ሐሙስ 『الخميس 』

ሐ}  ጁሙዓህ 『 الجمعة 』

መ}   ሰኞ  『الاثنين 』

⚠️መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላቹም ማለት ነው⚠️

🔘🩵መልካም እድል🩵🔘

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 13:59


'
☀️ዘግተን ስናለቅስ እንዉልና እንባችንን ጠርገን የሚያለቅሱትን ለማጽናናት እንወጣለን።
"በጎ ማስመሰል" ይሏል ይህ ነው።
እንዲያ ካልሆንን ታዲያ ምን ኸይር አለን።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 10:23


📌إنها الدنيا

ጭንቅ፣ጥብብ ሲለኝ ሐዘኔ ይበዛል።.......ብዙ ጥርቅም ያለበት በትንሹ ይከፋል እንደሚሉት ሲሆንብኝ...ኧረ ያ ረብ እዝነትህን እላለሁ........ደገሞም መለስ እልና
إنها الدنيا
ይቺህ እኔ ምጨነቅባት ዱንያ ናት። ጠፊ ዓለም እንጂ ሌላ አይደለችና ጌታዬ በምድር ላይ ሳለሁ የዱንያ ጀነትን አኑረኝ እላለሁ።
.
.
.https://t.me/My_thoughts_me

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 09:24


☀️ ወረቀት ላይ ላፒስ ደጋግመህ
ስትጠቀም ወረቀቱ ይቀደዳል‥
ልክ እንደዛው ልብን የሚሰነጣጥቀው
በተመሳሳይ ነገር በተደጋጋሚ ይቅር
ማለቱ ነው ።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 07:07


☀️በአሁን ጊዜ...
#ኢማን የሴት ስም
#ሷሊህ ደግሞ የወንድ ስም ብቻ ሆኖ ቀርቷል።
አሏህ ይዘንልን 🤲

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

21 Nov, 03:12


📌ትንሽ ብቻ ሰብር እናድርግ የሚመጣ ነገር ሁሉ ቅርብ ነው.....

☀️ ያ ብዙ ነገር እያማረህ ለአላህ ብለህ ስሜትህን ገተህ የተውክበት የወጣትነትህን ጊዜ ትእግስት አላህ አይረሳውም....

☀️ ነፍስያህን ስትታገል የቆየህበት ጊዜ ሁሉ ውጤትህ ያማረ ሆኖ ታገኘዋለህ ...

☀️ በአላህ ፈቃድም ያ ከእርሱ ጥላ ውጪ ምንም ጥላ በሌለበት ጭንቅ ጊዜም በጥላው ስር ከሚሆኑት ትሆናለህ ......!!
اللهم اجعلنا منهم

™️ @ALMUTEHABIN
™️ @ALMUTEHABIN

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

20 Nov, 17:38


📌 "አንዳንዴ...

☀️ እየወደድክ የምትርቀው ማውራት እየፈለክ በዝምታ የምታልፈው ከቃላት ይልቅ እንባ የሚገልፃቸው ነገሮች አሉ ...."

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

20 Nov, 17:10


☀️ከእርሱ ዉጪ የሚጠግናችሁ ሁነኛ ጠጋኝ የለምና ስለ ዉስጣችሁ ህመም ለአሏህ ንገሩት።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

20 Nov, 15:51


☀️በህይወታችን የማንቆጭበት ነገር #ቢኖር
ዝምታ ነው

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

20 Nov, 14:27


☀️ያረብ...
ምላሴ መናገር ያቃተውን ዱዐዬን ተቀበለኝ🤲

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

20 Nov, 13:28


☀️ዒልም ኖሮት!
አደቡ አኽላቁ (ስነ–ምግባሩ) የወረደ  የዘቀጠ
           መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ!
►ዒልምን ከመማሩ በፊት አደብን  አኽላቅን
          (ስነ - ምግባርን) ይማር ነበር!!

☀️ዐብደሏህ ኢብኑ ሙባረክ -ረሒመሁሏህ-
              እንዲህ ይላሉ: -
➧ስነ-ምግባርን ለሰላሳ ዓመታት ያህል ተማርኩኝ! ዒልምን ግን ለሀያ ዓመታት ተማርኩኝ!!!
[غاية النهاية في طبقات القراء(١/١٩٨)]
      ፞ ፞

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

19 Nov, 19:10


☀️በአከባቢህ ብዙ የሞት ዜናዎችን ትሰማለህ
ትልቅ ትንሽ ሳይል የሚወስደውን ሞት ተመልከት!
ዱንያ መሸጋገሪያ ድልድይ እንጂ ሌላ አይደለችም
እወቅ! ይህች ዱንያ አሏህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ያህል
አትመዝንም!በዱንያ ቆይታህም ....
የሰውን ደስታ አታበላሽ ልባቸውንም አትስበር ❗️
የተሰጠን እድሜ ትንሽ በጣም ትንሽ ነው
ወደ ቀብርም ስንገባም ዱዓ ሚያደርግልን እንሻለን
መልካም ያስቀደምን አንደሆን እናገኘዋለን ከዚያ
ውጪ ከሆነም እንደዚያው

አሏህ በኸይር የተሞላ እድሜን ይወፍቀን 🤲
#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

19 Nov, 18:44


☀️አንድ የታወቀ ሽፍታ
#የማሊክ_ኢብኑ_ዲናር ቤት በሌሊት ይገባና አንዳች የሚወሰድ ነገርን ፍለጋ ግራና ቀኝ ይዟዟራል ድንገት ማሊክ ቢን ዲናርን ሰላት እየሰገዱ ይመለከታቸዋል። ማሊክም ሰላታቸውን ጨርሰው ካሰላመቱ በኋላ ወደ ሌባው ዞር አሉና፦
"የዱንያን ቁሳቁስ ለመስረቅ መጥተሃል ግን ምንም አላገኘህም ና የአኺራን ሸቀጥ ሰርቀህ ብትሄድ ምን ይመስልሃል!? ይሉታል። ሌባውም በማሊክ ሀሳብ በጣም ተገርሞ ጥሪያቸውን በመቀበል ምክራቸውን ለመስማት ይቀመጣል። እሳቸውም  ረጋ ብለው ፊቱን በእምባ እስኪታጠብ ድረስ  ምክራቸውንም ለገሱት እንደጨረሱ አብረውት ወደ መስጂድ ሄዱ። በመስጅድ ውስጥ የተመለከታቸው ሰው  ሁሉ እነዚህን ሁለት የማይገጣጠሙ ሰዎች ምን አገናኛቸው በማለት እጅግ ተገረሙ።
እንዴት ብሎ ታላቅ የሆኑ አሊም ከለየለት ሌባ ጋር ሊገጣጠሙ ይችላል ! ሲሉ ማሊክን ጠየቋቸው።
ማሊክም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦
´´ሊሰርቀን መጣ ልቡን ሰረቅነው´´.

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

19 Nov, 18:02


☀️አንድ ትልቅ ዓሊም ጋር ሄዳ

ያሸይኽ ሂጃብ(ኒቋብ) መልበስ በሁሉም ሴትች ላይ ግዴታ ነው እንዴ? ብላ ጠየቀች

አይ የኔ ልጅ በሁሉም ሴት ላይ ግዴታ አልተደረገም አላህ ያለው ለምእመናን ሴቶች እዘዛቸው ነው አንቺ እኔ ሙእሚን ሴት ነኝ ብለሽ ካሰብሽ ትእዛዙ ይመለከትሻል አይ ካልሽም... ብለው መለሱላት

ለገባው👌

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

19 Nov, 17:32


              ☀️ለአንድ ፈቂህ

የጂሀድ ባብ(አህካም)  ከሌሎች አህካም መጨረሻ ለምን ተደረገ ተብለው ተጠየቁ⁉️

  .ጦሓራ ያላስተካከለ (ስለ ጦሓራ
      ያልተማረ )ሰው ስለ ጂሀድ እንዳያወራ
       ተብሎ ነው ብለው መለሱ።


     ለገባው ጉድ ያለው መልስ ነው የመለሱት

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

19 Nov, 13:30


☀️ከቀደምት ዓሊሞች መካከል አንዱ እንዲህ አሉ፦
<< ሰማንያ መስመር ተጠቅመው ሰደቡኝ። ነገር ግን "አንተ #ላጤ"!ከሚለው ስድብ ዉጪ የትኛውም  አላስከፋኝም..?

#ላጤዎች.....

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

19 Nov, 04:10


☀️ዝምታ ከወርቅ በላይ ነው!!

ዙበይድ አልያሚ የታላቁን ሰሃቢይ የዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድን የማስጠንቀቂያ ንግግር በመጥቀስና የራሰቸውን ጥንቃቄ በማውሳት ይመክሩናል።

አሏህ ይዘንላቸው ስራቸውንም ይውደድላቸው። እንዲህም ይላሉ ፦

{ የኢብኑ መስዑድ ንግግር ለሀያ አመታት ዝም አሰኘችኝ። እሷም "ንግግሮቹ ከተግባሩ የማይስማማ ሰው ራሱን ያስጠንቅቅ" የምትለዋ ናት። }
📚ዑዩኑል-አኽባር: 2/179】

እኛም የአንድ እለት ተግባርና ንግግራችንን እንኳ ብንመረምር ምን ያህሉ እንደሚለያይ እንረዳ ይሆናል።

ከዚያም እድሜ ልካችንን በዝምታ ማሳለፍን እንመርጥ ይሆናልና በራሳችን ላይ እንዝመት

▪️አ ን ዋ ሽ
▪️አ ን ቅ ጠ ፍ
▪️አ ና ስ መ ስ ል
▪️ቃ ላ ች ን ን እ ን ጠ ብ ቅ
▪️ቀ ጠ ሮ ዎ ች ን እ ና ክ ብ ር
▪️የ ማ ን ተ ገ ብ ረ ው ን አ ና ው ራ

እኛ የማንችለውን በሌሎች አንጫን
አሏህ ልቦናችንን ያፅዳልን፣ አንደበታችንንም ይጠብቅልን፣ ከተግባሮቻችንም ያስማልን።

#ደህና_ዋሉ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

18 Nov, 19:43


☀️ያኢላሂ...

በዚህች ስልካችን

የማትፈቅደውን አይተን
የማትወደውን ተናግረን
ያልፈቀድከውን ልከን
የማትወደውን አድርገን
የማትወደው ላይ ተተክለን


ስነቶቻችን ነን ኸልዋ አድርገን ከሰዎች ተደብቀን ሀያል የሆነውን ጌታችንን እይታ ረስተን ከሰዎች እይታ ተደብቀን ባልተፈቀደልን የተጠመድን ስንቶቻችን ይሆን.......?

በስልካችን ኸልዋ አድርገን ትንሽ እያልን ወንጀላችንን እያጠራቀምን ያለን...?

ሞ................ትን። ረስተን?!

ስንቶቻችን እናውቅ ኖሯል ?ወንጀልን ሸምተን ጀሀነምን እየገዛንባት መሆኑን ሞትን ረስተን!

ስንቶቻችን ነን ያ አሏህ በስልካችን የምናደርገው ሁሉ የማይመዘገብ መስሎን ስንቱን ያስመዘገብን ስንቶቻችን ይሆን ያአሏህ....?!

አንተው በራህመትህ እየን የኛስ ነገር ከባድ ነው...

ጌታችን ሆይ ከማትወደው ነገር ሁሉ አርቀን ጠብቀን ያአሏህ  ከወንጀል በአንተው እንጠበቃለን ዃቲማችንን መሄጃችንን ማረፊያችንን አሳምርልን አሚን!

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

18 Nov, 18:37


☀️እህቴ ሆይ!

በህይወትሽ ውስጥ ወሮ በላ ተኩላወች
የሰውና የጅን ሰይጣኖች ሊወተውቱሽ
ይመጣሉ‼️

በአካል ከመጡ በሂጃብሽ ተከናንበሽ አምልጫቸው!!

በሚድያ ከመጡ መጃጃልን ትተሽ በ block መልሻቸው!!

ሴት ልጅ በየ ሚድያው በቀላሉ ሰርች ተደርጋ የምትገኝ ርካሽ የሆነ ፖስት አይደለችምና‼️

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

18 Nov, 17:26


☀️አንዳንዴ ሰውን ከማስከፋት እራስን ከግንኙነቶች ማራቅ መልካም ነው ....🙌

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

18 Nov, 14:38


☀️ከአሏህ በታች...
ለኛ ብዙ ዉለታን የዋሉልን ምርጥ ሰዎች አሉ::👌
ምንም ባናደርግላቸዉም
#በዱዐ ግን የማንረሳቸዉ...

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

18 Nov, 13:18


☀️ውሃ እንኳን ዘግይቶ ሲመጣ ድርቀት የገደለውን አበባ አያድነውም ቆይተን ሁሉንም ይዘን ብንመጣ ራሱ በመዘግየታችን የምናጣቸው ነገሮች ይኖራሉ 
«ይዘገይ ይሁን ወይስ ልሂድ»?  በማለት የሚጠብቁ ልቦችም እዚህ መሀል ይፈተናሉ ...

አታርፍዱ ማርፈድ ከት/ት ቤት በላይ ህይወት ላይ ዋጋ ያስከፍላል ...

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

17 Nov, 19:30


☀️አል-በይሀቂ ሹዐቡል-ኢማን ላይ  እንደዘገቡት አቡ-ድደርዳእ የሚባሉት ታላቅ ሶሓቢይ رضي الله عنه
አንድ ሌሊት ላይ ለይል እየሰገዱ የሚከተለውን ዱዓእ ብቻ እየደጋገሙ ለሊቱ ነጋ፣ (አሏህ ሆይ፥ ውጫዊ ገጽታዬን/አፈጣጠሬን እንዳሳመርከው ሁሉ ስነ-ምግባሬንም አሳምርልኝ)
በማግስቱ ባለቤታቸው "የደርዳእ አባት ሆይ፥ ምነው ማታ ስለ መልካም ስነ-ምግባር ብቻ ዱዓእ እያደረግክ አደርክ?!" አለቻቸው። እሳቸውም "የደርዳእ እናት ሆይ፥ ሙስሊም ስነ-ምግባሩ እያማረ..እያማረ ሲሄድ መጨረሻ ላይ መልካም ስነ-ምግባሩ ጀነት እንዲገባ ያደርገዋል፣
ስነ-ምግባሩ እየተበላሸ... እየተበላሸ.. ሲሄድ ደግሞ መጨረሻ ላይ የጀሀነም እሳት ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል..."ብለው መለሱላት።

❗️አሏህ አኽላቋችንን ያሳምርልን፣
☀️እርሱና የአዕምሮ ባለቤቶች ከሚጠሉት ዓይነት አኽላቅ በሙሉ ያርቀን።
መልካም አኽላቅ ይህን የላቀ ደረጃ የሚያስገኘው ለብዙ መልካም ነገሮች ሰበብ ስለሚሆን ነው።
መልካም ስነ-ምግባራችን ብዙዎች ዲናችንን እንዲወዱ ያደርጋል፣ በህይወት እያለንም ይሁን ከሞትን በኋላ ያስታወሱን ሁሉ ዱዓእ ያደርጉልናል።
መጥፎ ስነ-ምግባር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ ብዙ ችግሮችን ያስከትላል።
ስለዚህ ሙስሊሞች ሆይ፥ ባላችሁበትና በሄዳችሁበት ሁሉ መልካም ስነ-ምግባርን ተላበሱ! ትሁት፣ቅን፣ ታጋሽና ቻይ፣ አዛኝ፣ለጋስና ታታሪ፣ ታላቅን አክባሪና ታናሽን መካሪ ወዘተ እንሁን።
ይሄኔ አሏህ ይወደናል፣ ትክክለኛ የነቢዩ ‌‎ﷺ ተከታይም እንሆናለን፣
ነገ በኣኺራም ከርሳቸው ቅርብና ጎረቤት የመሆንን እድል እናገኛለን!

🔅አሏህ ሆይ፥ ውጫዊ ገጽታዬን/አፈጣጠሬን እንዳሳመርከው ሁሉ ስነ-ምግባሬንም አሳምርልኝ

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

17 Nov, 15:31


💜ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ💜

የነቢዩ 『 ﷺ』 አጎት እና የጥቢ ወንድም ማነው

🌱ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

መልሱን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ〗ሐምዛ 『رضي الله عنه 』

ለ〗ዐባስ 『رضي الله عنه 』

ሐ〗ዑመር 『رضي الله عنه 』


🔘⭐️መልካም እድል⭐️🔘

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

17 Nov, 12:31


☀️ሲከፋኝ ስታዩ ምን ሆንሽ አትበሉኝ
መፍትሄ ላትሠጡ ጥያቄ አጠይቁኝ
ተዉት አታባብሉኝ እኔ ይብስብኛል
በሳቄ ሸፍኜዉ ብኖር ይሻለኛል
ሲሰባበር ልቤ ሲጎዳ ሥሜቴ
መፃፍ እና ማልቀስ ናቸዉ መዳኒቴ

እናም
አትሰቡ ለኔ አልቅሼ አልፈዋለሁ
መተንፈስ ሲያሻኝም ፃፍ አደርገዋለሁ
ግን ለጥያቄያችሁ  አመሠግናለሁ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

17 Nov, 11:39


☀️ፀባዬ ከሆነ አንተን የሚያስደብር
እኔ ዘንድ  ካለ  የሚያሥጠላህ ነገር
በጥሩ እንድለዉጥ እንዳ ሥተካክለዉ
አትሂድ ወደሌላ በል ንገረኝ  ለኔዉ

ስህተት ካለ ለእኔዉ ንገሩኝ  ማሥተካከከልም  መቀየርም  የምችለዉ ራሤዉ ነኝና

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

17 Nov, 07:46


☀️ምስጋና...
ወደ አሏህ እንድንመለስ ላደረጉን ስብራቶች

#አልሃምዱሊላህ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 19:30


                                       
      💥"የምርጦችምርጥ"  💥

☀️ነቢዩ ሙሐመድን አሏህ የነቢያት መደምደሚያ ለማድረግ አጫቸው በዚህም የትልቅ መልእክትና አደራ ተሸካሚ አደረጋቸው ።

☀️የሰውልጆች ከጨለማ ወደ ብርሃን ከመሀይምነት ወደ ዕውቀት እንዲወጡ ነቢዩ ሙሀመድን ሶለሏሁ ዐለይሂ
ወሰለም በስጦታነት አበረከተላቸው።

☀️የተላኩለት ዓለማም ይሳካ ዘንድም አሏህ ነቢዩን ረዳ!ሰዎችእንዲቀበሏቸውም ባማሩ ስነምግባሮች አስዋባቸው በአደብም አነጻቸው ምንምእንኳ ወላጅ አልባ ሆነው ቢያድጉም! የእናትን ፍቅር ቢያጡም! የአባትን ርህራሄና ክብካቤ ባያገኙም ሁሉ በእጁ የሆነው ጌታ በሁለት ወላጆቹ  መሀል ካደገ ጅል የተሻለን ጥበቃ አደረገላቸው!
ወላጆች ልጆቻቸውን አደብና ስርኣትንከሚያስተምሩት
በላቀ መልኩም አሏህ ቀረጻቸው!

☀️በዚህም በጊዜያቸው ከነበሩ የባለባት ልጆች ሁሉ ተሽለው ተገኙ ሁሉም ወደዳቸው፣ ሁሉም አቀረባቸው፣ ሁሉም አዘነላቸው፣አቀፋቸውም እንደ ትልቅ ሰውም አከበራቸው ፣አድገው ከትልልቅ ሰዎች ተርታ መሰለፍ ሲጀምሩም ለሀገራቸውና ህዝባቸው ትልቅን ነገር የሚያደርጉ ሰው እንደሚሆኑ በማመን ልዩ ትኩረት ሰጧቸው አብሯቸው ያደገውን መልካም ስነምግባር የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠሉን በማየታቸውም
"አሷዲቁል አሚን" ብለው ሰየሟቸው (ፍጹም እውነተኛውና ታማኙ ) ማለታቸው ነው ይህንን ስያሜና ከፍተኛ ማዕረግ ያሰጣቸው ሁሉም የሚወደውና የሚመኘውን ግን ጥቂቶች እንጂ የማይታደሉትን አላህ የሚወደውን ኢስላማዊ ባህሪይ በመላበሳቸው ነበር፥ ሲናገሩ አይዋሹም፣ ቃላቸውን አያፈርሱም፣እንግዳንያከብራሉ፣ዝምድናን ይቀጥላሉ፣ አቅመ ደካማን በሚችሉት ሁሉ ይረዳሉ፣የተጣላን ያስታርቃሉ፣ ታላቃቸውን ያከብራሉ፣ በዕድሜ ለሚያንሳቸው ይራራሉ፣ ውለታን ይመልሳሉ፣ ጉረቤትን ይንከባከባሉ፣ ከኩራት የፀዱ ናቸው፣ የግልም ይሁን ያከባቢ ንፅህናን መጠበቅ ይወዳሉ፣ ሽቶ ያዘወትራሉ፣ የጥርስ መፋቂያ አይለያቸውም፣ነጭ ልብስን እንደሚወዱትና እንደሚጠቀሙትሁሉ :-
ልባቸውም ነጭ ፣ንፁህ ነው ።
☀️የንፁህ ልብ ባለቤቶችንም ይወዳሉ፣
ከጌታቸው በቀር ማንንም አይፈሩም!ከመሆኑም ጋር ለወገናቸው ይተናነሳሉ፣ ማንንም አይበድሉም፣ የጌታቸው ድንበር ካልተጣሰ  በስተቀር ለራሳቸው ክብር ብለው አይቆጡም!በአላህ መንገድ እየተፋለሙ ካልሆነ በስተቀር በእጃቸው ማንንም መተው አያውቁም፣ ፍትህን ይጠብቃሉ በዚህም እንደ ሁኔታው እራሳቸውም ላይ ይፈርዳሉ!

☀️ሀቅን ከመናገር ማንንም ምንንም ፈርተው ወደ ኋላ አይሉም፣ ሰውን የሚያስቀይምና ትርፍ ንግግርን አይናገሩም፣ ንግግራቸውም አጠር ያለና ግልጽ ነው፣ ከሰዎች ጋር ሲገናኙ እንደ ደረጃቸውና እንደ ሁኔታቸው ሳይበዛ ቀልድን ይጠቀማሉ ሆኖም ግን ለቀልድ ብለው አይዋሹም! ሲስቁም የሳቃቸው ድምጽ አይሰማም፣ ለመላው ፍጡር ያዝናሉ፣ አንዲት እርግብ ካጠገባቸው ዝቅ ብላ ክንፏን እያርገበገበች ስትሽከረከር ማነው ልጇን የወሰደባት? ብለው ሲጠይቁ አብረዋቸው ከነበሩ ሶሃቦች መሀል አንዱ እኔ ነኝ ብሏቸው እንዲመልስላት አዘዋል።

☀️ህጻን ልጅ ሲስሙ ያየ አንድ ግለሰብም፥ እኔ 9 ልጆች አሉኝ ከነሱ መሀል እስከ ዛሬ የትኛውንም ስሜ አላውቅም ሲላቸው "እዝነት ከልብህ ወጥታ ከሄደች እኔ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?!" በማለት ተችተዋል፣ ለአረጋዊያንና ጠዋሪ ለሌላቸው ሴቶች በተለየ መልኩ ያዝናሉ፣ ከሁሉም በላይ የጌታቸውን መመሪያ ለሚያክብሩ የአሏህ ባሪያዎች ጌታቸው ባዘዛቸው መሰረት ልዩ እዝነትና ርህራሄ አላቸው፣

☀️ለሁሉም የሚገባውን ክብር ይሰጣሉ፣ የታመመን ይጠይቃሉ፣ የሞተን ይቀብራሉ፣ ሞተው የተቀበሩ ወንድምና እህታቸውን ቀብር በየጊዜው ሄደው እየዘየሩ ምህርት ይጠይቁላቸዋል፣ መስጂድ ታጸዳ የነበረች ሴት ሞታ እሳቸው ሳያውቁ ሶሃቦች ቀብረዋት በኋላ ሲሰሙ" ለምን ሳትነግሩኝ?! በማለት
"ቀብሯን አሳዩኝ" በማለት ሄደው ሰግደውባት ዱዓ አድርገዋል፣ ከሰዎች የተበረከተላቸውን ስጦታ ትንሽም ቢሆን ይቀበላሉ፣ ሲመልሱ ግን በተሻለ  መልኩ ይመልሳሉ፣ ምንም የሌለው ደሃ እንኳ ቢሆን ጥሪን አክብረው ይሄዳሉ፣
ሰውን ስያገኙ ቀድመው ሰላም ይላሉ፣ ሀብታሙንም ደሃውንም ይጨብጣሉ፣ ህጻናትን ያጫውታሉ።ታፋቸው ላይ በማስቀመጥም ያቅፋሉ፣ ከሶሃቦቻቸው ጋር በመሆንም እነሱ የሚሰሩትን ስራ አብረው ይሰራሉ፣ ምግብም አብረዋቸው ይበላሉ።
☀️ከእለታት አንድ ቀን አይቷቸው የማያውቅ ግለሰብ ወዳሉበት ደርሶ ከቅርበት ሲያያቸው ከነበራቸው ግርማ ሞገስ የተነሳሰውነቱ ሲንቀጠቀጥ አይተው " እራስህን አረጋጋ እኔ እኮ የአንዲት ስጋን አድርቃ እያቆየች ትበላ ከነበረች ሴት የተወለድኩ ሰው ነኝ"በማለት አረጋግተውታል፣ ከሶሃቦቻቸው ጋር ጉዞ ላይ ሳሉ በግ ማረድ ፈልገው ከነሱ መሀል አንዱ፥ እኔ አርዳለሁ ሲል ሌላኛው እኔ
እገፋለሁ እያለ ሌላኛው ደግሞ እኔ አበስላለሁ በሚልበት ሰኣት ታላቁ ሰው (ነቢዩ  ሙሐመድ ሶለሏሀ ዐለይሂወሰለም) እኔ ደግሞ እንጨት ለቅሜ አመጣለሁ
ብለው እራሳቸውን ዝቅ አድርገዋል!!

👉በዚህም አሏህ ዘንድ
ከፍ ብለዋል አማኞች ልብ ላይም
ውዴታቸውን ዘርተዋል !

☀️የሰው ልጆች ምርጥ እንደሆኑ፥ የሩቁም የቅርቡም፣ወዳጅ ዘመዱም መስክሯል!እነሆ እኚህ ናቸው ነቢያችን እንወዳቸዋለን! እናከብራቸዋለን!
👉የሙስሊሞች አርኣያና
ተምሳሌትም እሳቸው ናቸው  !

💥አሏህ ሆይ፥ በፈጠርካቸው
ነገሮች ልክ ነቢዩ ሙሀመድ
ላይ ሰላትና  ሰላምን አስፍን!

#ወሰላሙዐለይኩም
                                                                        

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 18:25


☀️ከሰዎች ጋር ያለን ስነ-ምግባር እንዲስተካከል ከሚያግዙ ትልልቅ ነገሮች መካከል አንዱ፤ እራስን ዝቅ ማድረግና ጥፋተኝነትን ማመን (ልሳሳት እችላለሁ ማለት) ነው።ይህን ያልታደለ ሰው ሁሌም እራሱን ንጹህ አድርጎ በማየቱ ሰዎችን እየበደለ ይኖራል።

☀️የሰዎችን ጉድለት እንደምናያው ሁሉ የራሳችንን ጉድለትም የምናይበትን የልብ ዓይን አሏህ #ይስጠን

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 17:03


🌷 የምስራች ለ 🔠🔤🔠🔤🔠

🔤🔠🔠🔠🔠🔤🔠 ባለቤቶች 🌹

⭐️ የሱና ቻናሎችን የማስፋፋት ፕሮጀክት ⭐️

ያለን ቦታ አነስተኛ ነው 20 ቻናሎችን ብቻ አየተጠባበቅን እንገኛለን

🆘ሳይቀደሙ ይቅደሙ🆘

🌸የሱና ቻናል ባለቤቶች  ቻናላቹን ማሳደግ  የምትፈልጉ በነፃ መመዝገብ ትችላላቹ🌸

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤

1k+ Subscribers    🔘
5k+ Subscribers   🔘
10k+ Subscribers  🔘
15k+ Subscribers  🔘
20k+ Subscribers  🔘

የሱና ቻናል ያላችሁ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ ተቀላቀሉን

ከ 1k በታች አንቀበልም

🩷ለመመዝገብ ➪ @IbnuRahmeto 🩷

🔠🔤🔠🔤   🔠🔤🔠🔤  

🤎መልካም እድል🤎

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 16:55


💜ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💜

نور التوحيد وظلمات الشرك
የተውሒድ ብርሃን እና የሺርክ ጨለማዎች በሚል ርዕስ

🩵በኡስታዝ ፉኣድ ከማል [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።


ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3️⃣🔤3️⃣0️⃣ ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡

https://t.me/abufurat

🔘በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ🔘

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 16:50


☀️ፈጥነሽ ሰውን አትመኚ..ጨው ራሱ መጀመሪያ ስታዪው ስኳር ይመስላል!

#ተግባባን?

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 13:41


❗️ስህተት ስታገኙ ለማሳወቅ እንዲሁም ምክር ለመስጠት
@Almutehabbot

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 13:13


☀️ዝምታዋን ፍራ
ስታጠፋ እያየች ዝም ካለችህ ሴት
ፍፁም አትየው እንደሞኝነት
ውስጧ እየሞተ ነው ላንተ ያላት ስሜት

ደጋግመህ ስትዋሽ በደል ስትሰራ ..
       ሴት ዝም ካለች
ንዝንዟን ሳይሆን ዝምታዋን ፍራ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 10:27


🚫ከሚሰግድ ሰው አጠገብ ሆነን አናውራ!🚫

☀️አሏህን ከማክበር አንዱ የዲን ህግጋትን ማክበር ነው በተለይም አሏህን ከሰው ልጆች ጋር የሚያገናኝ የሆነውን ሰላትን ማክበር ለአላህና ለዲኑ ያለንን ክብር ከሚያሳዩ ነገሮች መሃል አንዱ ነው


☀️ሶላት ከሚሰግድ ሰው አጠገብ ሆነን ድምጽን ጮኽ አድርጎ ማውራት የሰጋጁን ሃሳብ የሚሰርቅ ነገር ማድረግ ጌታውን ከሚያከብር ሰው የማይጠበቅ ተግባር ነው

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 07:43


☀️ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፦

ልቡ ውስጥ የደስታ ስሜት የማይሰማው
የኢማንን ጣእም ያላገኘ
ተውበትና ኢስቲغፋር ያብዛ

(አልፈታዋ ኩብራ 5/62)

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

16 Nov, 04:57


☀️ "አዒሻ ቢንት አቡበክር (አሏህ ከ እርሷ እና ከአባቷ ስራቸውን ይውደድ እና) እንዲህ ትላለች:- ረሱል ﷺ እና አቡበክር የተቀበሩበት ወደሆነው ቤቴ ፊቴን ተገልጬ እገባ ነበር።
በአላህ እምላለሁኝ ዑመር አብሯቸዉ ከተቀበሩበት ግዜ አንስቶ ከዑመር ሐያእ በማድረግ ፊቴን ተሸፍኜ ካልሆነ በስተቀር አልገባም ነበር ።
[ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል]
[አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]
===============

አጂብ! ይህ ከሆነ ታድያ በህይወት ያሉ
ወንዶችን ሐያእ ሳታደርግ ሂጃቧን አውልቃ
የምትሄድ ሴት ምን ይሏታል? አላህ በምህረቱ የ ሀያዕን ካባ ያልብሰን። ከነብሳችን እና ከሰይጣን ተንኮል ይጠብቀን!
©
™️ @ALMUTEHABIN

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 19:13


☀️አንዳንዴ ማስቀየም የማትፈልገውን ሰው ልታስቀይም/ልታስከፋ ትችላለህ... ብዙ ነገር አሳልፈህ ትንሽ ነገር ሁሉንም ሊያስጠፋው ይችላል በጊዜ ሂደትም ልትለያይ ልትረሳሳ ትችላለህ ነገር ግን አብረህ እያለህ ያሳለፍካቸው የደስታ፣ የሀዘን፣ የፍቅር ጊዜያቶች መቼም አይረሱም በሰማይ ላይ እንዳሉ ከዋክብቶች ያበራሉ!
{ምንም ያህል ብትኖር አንተ ሟች ነህ}
{የቱንም ያህል ብትዋደድ አንተ የምትለያይ ነህ}

-ህይወት እንዲህ ናት።

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 18:56


💜ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💜

نور التوحيد وظلمات الشرك
የተውሒድ ብርሃን እና የሺርክ ጨለማዎች በሚል ርዕስ

🩵በኡስታዝ ፉኣድ ከማል [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።


ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3️⃣🔤3️⃣0️⃣ ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡

https://t.me/abufurat

🔘በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ🔘

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 18:53


ቤታችን ይሄ ነው እሺ?

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 18:33


☀️ዝም ያልንበት ምክንያትኮ አያስጨንቃቸውም ሰምታችሁን ግን ታውቃላችሁ?ምን እንደሚሰማን ለመረዳት ሞክራችሁ ታውቃላችሁ....?ያው እኛም ለማስረዳት ብዙ ጊዜ እንሞክርና ከዚያም  በቀልዶቻችሁ እና በጨዋታቹ ታሰረሱናላቹ  እኛም ስቀን ብቻ እንመለሳለን

#ዝም!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 16:12


አሏህ ካለ በቅርቡ አንዲት የዚህ ቻናል ምርጥ እህታችንን ልንድራት ነው ማለትም ልትዘወጅ ነው።
እናም ዱዐ አድርጉላት አሏህ ትዳራቸውን እንዲያሳምርላቸው 
ኒካህም አስራለች ለዚህም፦
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير....

እናም እየተዘወጃቹ ማነው እይተዘወጅን

#ኡኽታ 📦 📦📦

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 16:03


☀️ኒካህ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿النكاحُ من سُنَّتِي، فمن لم يعمَلْ بسنَّتِي فليس منِّي﴾

“ኒካህ (ትዳር) የኔ ፈለግ ነው። የኔን ፈለግ ያልሰራ ከኔ መንገድ አይደለም።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ: 6807

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 14:42


☀️«መከራው ሲበረታ መፍትሔው መቅረቡን እወቂ !»

✹ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ ።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 11:04


🌷 የምስራች ለ 🔠🔤🔠🔤🔠

🔤🔠🔠🔠🔠🔤🔠 ባለቤቶች 🌹

⭐️ የሱና ቻናሎችን የማስፋፋት ፕሮጀክት ⭐️

ያለን ቦታ አነስተኛ ነው 20 ቻናሎችን ብቻ አየተጠባበቅን እንገኛለን

🆘ሳይቀደሙ ይቅደሙ🆘

🌸የሱና ቻናል ባለቤቶች  ቻናላቹን ማሳደግ  የምትፈልጉ በነፃ መመዝገብ ትችላላቹ🌸

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤

1k+ Subscribers    🔘
5k+ Subscribers   🔘
10k+ Subscribers  🔘
15k+ Subscribers  🔘
20k+ Subscribers  🔘

የሱና ቻናል ያላችሁ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ ተቀላቀሉን

ከ 1k በታች አንቀበልም

🩷ለመመዝገብ ➪ @IbnuRahmeto 🩷

🔠🔤🔠🔤   🔠🔤🔠🔤  

🤎መልካም እድል🤎

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

15 Nov, 04:11


☀️«እህቴ የሆሊውድ ወይም የቦሊውድ አርስቲስቶችን እርሺ "አምራህን " ግን አስታውሺ !!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

14 Nov, 18:26


⭐️ ከሁሉም በፊት መጀመሪያ
የሰለመችው ሴት ልጅ ነበረች‥

☀️አሏህ ወደ ረሱል ዳእዋ
እንዲያደርግና እንዲያስጠነቅቁ ወህይ
ሲያደርግላቸው ረሱል መጀመሪያ ጉዳዩን
ለኡሙል ቋሲም  ነበር ያቀረቡት‥
๏ እሷም በሙሉ እምነትና ፍላጎት ልቧን ለዲኑ
ዝቅ አድርጋ ያቀረቡላትን ተቀበለቻቸው ።
በዚህም የመጀመሪያ አማኟ ሴት ሆነች ። መጀመሪያ ሶላት የሰገድችውም ሴት ሆነች ።
๏ በሀብቷ ፣ በነፍሷና ባላት ነገር ሁሉ ከቁረይሾች የሚደርሱበትን ትከላከልለት ነበር ። ከጎኑ አንዴም ቢሆን ጠፍታ አታውቅም ነበር ። ስለዚህም ነው በረሱል  ልብ አሸንፋ ከሌሎች እንስቶች የበለጠችው ። ሁሉም ይቀኑባት ነበር ። በዛም አላበቃም ጀሊሉ አሏህ ከሰባት ሰማያት በላይ ሰላምታውን የላከላት ሴት ሆነች ። ጀነት ውስጥ ከዳይመንድ በተገነባ ቤተመንግስትም ተበሰረች ።
☀️ኸዲጃህ እስልምናን ከረዱት በላጯ ነበርች ፣ አሏህ በሷና በአምሳያዎቿ ነው ዲኑን የረዳው ። እስልምናን በመርዳቷ እና ቀዳሚ በመሆኗ በዱንያም በአኺራ ትልቅን ክብር አግኝታለች ።

๏ ውድ እህቴ አንቺም ይህን ክብር ታገኚ ብዬ በጣሙን ተመኘሁልሽ‥
☀️ ልክ እናታችን ኸዲጃህ ረዲየሏሁ ዓንሃ በመስለም ቀደሚ እንደሆነችው አንቺም ወደ ዲኑ በመመለስ ቀዳሚ ሁኚ ። የዛኔ እስልምና ልክ እንደ እንግዳ ነበር ፣ ዛሬም ያው እንግዳ እየሆነ ነው ፣ በሁሉም በኩል ጠላቶች ጣታቸውን እየቀሰሩበት እንደሆን እያየን እየሰማን ነው ። እናም ውድ እህቴ ዲናችንን ሌላ አካል መጥቶ አይረዳልንምና ልክ እንደ እናታችን ኸዲጃህ  ቀዳሚዋ ሆነሽ ለዲኑ ረዳት ሁኚ ፣ አሏህና መልዕክተኛው የሚያዙትንም ተግብረሽ ተምሳሌትሽን ኸዲጃህን  አድርጊ ፣ የመንገዱንም አስፈሪነት ቻይውና ታገሺውም ።
๏ የጀነት መንገድ ነፍስ በማትወደው ነገር ነው የተሸፈነችው ፣ የእሳት ደግሞ ነፍስ በምትፈልገው ነገር ነው የተሸፈነችውና ።

ምክሩ ከነፍሴም ጭምር ነው
#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

14 Nov, 17:51


☀️ጨለማ ውሰጥ እያለን መብራት ይዘውልን የመጡትን ሁሉ አንረሳም።
የምክር...የአብሽር መብራት!

ካልሆነማ ክደናቸዋል

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

08 Nov, 19:23


📌ጥቂት ኹፍና ካልሲ ላይ ማበስን የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች

☀️ኹፍ ላይ ማበስ በበርካታ ሰሒሕ ሐዲሦችና በሙሉ የሱና ዑለሞች ስምምነት የተረጋገጠ ሱና ነው።
ካልሲ ላይ ማበስ በተወሰነ መልኩ ኺላፍ ቢኖርበትም ትክክለኛው አቋም ይቻላል የሚለው ነው።

☀️ካልሲው ወፍራም ቢሆን ይመረጣል እጅግ በጣም ሳስቶ የቆዳ ከለርን አስካላሳየ ድረስ ስስም ቢሆን ችግር የለውም፣ቢያረጅና ትንንሽ ቀዳዳዎች ቢኖሩበትም ማበስ  ይቻላል።

☀️በላጩ ማበስ ነው ወይስ ማጠብ? በውዱእ ጊዜ እግር ሸርጡን ባሟላ መልኩ ተሸፍኖ ከተገኘ ማበሱ በላጭና ሱና ሲሆን፣ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ላይ ማጠቡ የግድ ይሆናል

☀️መስፈርቱ ከመሟላቱ ጋር ለማጠብና ላለማበስ ብሎ ማውለቅ ሱና አይደለም።

☀️ኹፍም ይሁን ካልሲ ላይ ለማበስ፥
1/ ሁለቱም ሐላልና ጦኀራ መሆን አለባቸው
2/ ከማጥለቃችን በፊትም ሙሉ ውዱእ ሊኖረንም ይገባል፣
አንድ እግርን አጥቦ ሌላኛውን ሳያጥቡ በፊት ባጠለቁት ኹፍና ካልሲ ላይ ማበስ አይቻልም።
3/ ቢያንስ በውዱእ ሰዓት ማጠቡ ግዴታ የሚሆነውን የእግር አካል ሙሉ በሙሉ የሚሽፍን ርዝመት ያለው ሊሆንም ይገባዋል።
4/ ማበስ ከሚፈቀድበት ጊዜም ሊያልፍ አይገባውም፥
~ሀገር ውስጥ ላለ ሰው ማበስ የሚቻለው ካጠለቁ በኋላ ውዱእ አፍርሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ካበሱበት ሰዓት ጀምሮ ለ24 ሰዓት ሲሆን 
  ~ለመንገደኛ(ሙሳፊር)  ደግሞ
ለ 72 ሰዓት (ለሶስት ቀን እስከ ሌሊቱ)  ነው
5/ ማበስ የሚቻለው በውዱእ ጊዜ ብቻ ነው የገላ ትጥበት ግዴታ የሆነበት ሰው አውልቆ እግሩንም ማጠብ ይጠበቅበታል።

☀️ሽንት ቤት መግባት ብቻ ማበስን አይከለክልም ኹፉ/ካልሲው እስካልተነጀሰ ድረስ!

☀️ለማበስ አስቀድሞ ካልሲውን/ኹፉን ሲያጠልቁ መነየት የግድ አይደለም።

☀️የሚታበሰው የእግራችን የላይኛው አካል ነው ውስጡ አይታበስም የሚታበሰውም እስከ ቁርጭምጭሚት ትይዩ ብቻ ነው ከዛ አይታለፍም።
☀️ሁለቱን በአንዴ ማበስም ቀኙን ከዛ ግራውን ማበስም ይቻላል።

☀️ረስቶም ይሁን አውቆ ጊዜው ካለቀ በኋላ አብሶ የሰገደ ሰው ውዱኡን አስተካክሎ መልሶ መስገድ ይጠበቅበታል።

☀️ውዱኡ ሳይፈርስበት የማበሻ ወቅቱ ያለቀበት ሰው ግን ውዱኡ እስካልተበላሸ ድረስ ዳግም ውዱእ ማድረግ ሳያስፈልገው መስገድ ይችላል።

☀️የማበሻ ጊዜ ማለቅ/አለማለቁ ላይ የተጠራጠረ ሰው አለማለቁን በእርግጠኝነት እስቃላወቀ ድረስ እየተጠራጠረ አብሶ መስገድ አይፈቀድለትም!  አውልቆ ማጠብ ይጠበቅበታል።

☀️ማበስ ለወንድም ለሴትም ይቻላል
~ሴቶች ግን ቁርጭምጭሚትንም ጭምር የማይሸፍኑ ካልሲዎች ላይና አጫጭር (በከፊል ግልጥ/ክፍት) የሆኑ የቤት ውስጥ ጫማ /የሙቀት ጫማዎች ላይ ማበስ አይቻልም!

☀️ካልሲ የደረበ ሰው፥ ማበስ ከመጀመሩ በፊት ከሆነ የደረበው በላይኛውም ይሁን በታችኛው ላይ ማበስ ይችላል
~የደረበው ማበስ ከጀመረ በኋላ ከሆነ ግን በታችኛው ላይ እንጂ ማበስ አይችልም
~የስረኛው ማበሻ ሰዓት ካበቃ እግሩን ማጠብ ግዴታ ይሆንበታል።

=ሀገር ውስጥ ሆኖ ማበስ ከጀመረ በኋላ የተሳፈረ ሰው ማበስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለመንገደኛ የተፈቀደው የጊዜ ገደብ እስኪያልቅ ድረስ ማበስ ይችላል።

☀️መንገደኛ ሆኖ ማበስ ከጀመረ በኋላ ወደ ሀገር/ማረፊያ የተመለሰ ሰው ደግሞ ማበስ ከጀመረበት ሰዓት ጀምሮ 24 ሰዓት እስኪሞላ ድረስ ማበስ ይችላል።

ወሏሁ አዕለም

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

08 Nov, 18:51


☀️#አንዳንድ ሰዎች
መጡም አይጠቅሙኝም ቀሩም አይጎዱኝም❗️

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

08 Nov, 18:36


☀️አንዳንድ ልቦች
በዝምታም ቢሆን ይግባባሉ።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

08 Nov, 17:12


🔘🔠🔤🔠🔤🔤🔠

🔠🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔠ባለቤቶች🔘

🌹የሱና ቻናሎችን የማስፋፋት ፕሮጀክት🌷

💚የሱና ቻናል ባለቤቶች፡ ቻናላችሁን ማሳደግ የምትፈልጉ በነፃ መመዝገብ ትችላላችሁ💚

Ʀᴏʏᴀʟ ᴡᴀᴠᴇ

⭐️1k+ subscribers 
⭐️5k+ subscribers 
⭐️10k+ subscribers 
⭐️15k+ subscribers 
⭐️20k+ subscribers 

🔈የሱና ቻናል ያላቹ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ!

ከ 1k በታች ያላችሁ በስምምነት

🔘ለመመዝገብ ➪ @ibnurahmeto🔘

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

08 Nov, 13:21


☀️ሰላም ለነዛ...
ችግራችን ለሚያሳስባቸው
ደስታችን ለሚያስደስታቸው
ወዳጅነታችንን ለሚረዱ
ለደስታችን ሰበብ ለሚሆኑ...🌹

#M

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

08 Nov, 03:19


☀️اللهم إني ظلمت نفسي ظلماً كثيراً ولا يغفر الذنوب إلا انت فاغفرلي مغفرة من عندك وارحمني إنك أنت الغفور الرحيم

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Nov, 18:38


☀️ሙስሊም ዘፋኞች ሆይ-

በኢስላም ዘፈን ሐራም/ክልክል ወይም የማይበረታታ ተግባር መሆኑን ልባችሁ ጠንቅቆ ያውቃል።
ይፈቀዳል ያሉ አዋቂዎች አሉ ብትሉ እንኳ ዛሬ የሚታያውን አይነት የብልግናና ስሜት ቀስቃሽ ቃላት የተሞሉበትን፣ ልብን በሚያስኮበልሉ የሙዚቃ መሳሪያዎች የታጀበን ዘፍን አይደለም!።
ይልቅ ጥሩ መልዕክት ያላቸውን ግጥሞች (በሙዚቃ መሳሪያ ሳይታጀብ) ድምጽ ጮክ አድርጎ ማዜምን ብቻ ነው ይፈቀዳል የተባለው።

☀️የዘመኑን ወደ ዝሙት ተጣሪ፣ የሐያእን አጥር ሰባሪ ዘፈኖችንም ጭምር መዝፈንና ማድመጥ ይቻላል ብላችሁ እንኳ ብታደርጉት ይህ ዘፈናችሁ ውስጥ የአላህን ስም ማንሳት እጅግ እጅግ በጣም ሲበዛ ትልቅ ወንጀልና የአሏህን ስም ማርከስና በርሱም ማሾፍ ነው የሚሆነው!።
ስለዚህም አላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ሱብሓነሏህ፣ ላ ኢላሀ-ኢለሏህ ወዘተ የሚሉ የተከበሩ የዚክር ቃላቶችን አክብሯቸው! ሸይጣን ከሚወደው ዘፈን አርቋቸው።
ጌታችሁን ፍሩ፤ ዛሬ አሏህና መልዕክተኛው በሚጠሉት ዘፈን የተፍታታ ምላስ ነገ ሞት ሲመጣ ሸሃዳ ለመያዝ በቀላሉ እንደማይታደል አትዘንጉ!
"ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል፤ በሞተበት ነገር ላይም ይቀሰቀሳል" ተብሏል።
ሶሓባዎች "ውሃ አትክልትን እንደሚያሳድገው ዘፈን ልብ ላይ ሙናፊቅነትን ያሳድጋል-ቀልብን ያደርቃል-" ማለታቸውንም አስታውሱ።
ማስታወስ አማኞችን ይጠቅማልና!

☀️ሙስሊም የጌታውን ቃል (ቁርኣነል-ከሪምን) ሲቀራና ሲያደምጥ ነው የሚያምርበት እንጂ የሸይጧንን መዝሙር ማድመጥና ማስደመጥ ፈጽሞ ከሙስሊም ጋር አይሄድም።

ችግሩ የዘፋኞች ብቻም አይደለም፤ አድማጭ ባይኖር ዘፋኝም አይኖርም ነበርና "ጆሮ፣ምላስና ልብ አሏህ ዘንድ እንደሚያስጠይቅ የሚያውቅ አማኝ በሙሉ ምላስና ጆሮን ከዘፈን ሊያርቅ ይገባዋል።

አሏህ ቀልባችንን ወደሱ ይመልስልን፤ ከቁጣውና ከቅጣቱ ሰበቦችም ያርቀን።

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Nov, 14:05


ማር እና መልካም ስነምግባር

☀️ከታላቁ ሶሓቢይ ዐብዱሏህ ኢብኑ ዑመር رضي الله عنهما
ጦበራኒይ እና አልባኒይ እንደዘገቡት ነቢዩ صلى الله عليه وسلم የተለያዩ የመልካም ስራ ዓይነቶችንና ትሩፋቶቻቸውን ከዘረዘሩ በኋላ የሚከተለውን ብለዋል፥
(وإِنَّ سُوءَ الخُلُقِ يُفْسِدُ العَمَلَ، كما يُفْسِدُ الخَلُّ العَسَلَ.)
"መጥፎ ስነ-ምግባር ስራን ያበላሻል፤ ልክ ኮምጣጤ ማር ላይ ሲጨመር ማር እንደሚበላሸው ሁሉ።"

☀️መልካም ስራ መስራት መቻሉ ብቻ ስኬት አይደለም።
የአንድ ሰው ስኬትና እድለኝነት የተሟላ የሚሆነው መልካም ስራን ዋጋ ከሚያሳጡ ነገሮች መጠንቀቅና መዳን ሲችል ነው።
☀️ለፍተንና ደክመን የምንሰራቸው መልካም ስራዎችን ከአሏህም ይሁን ከሰዎች ጋር ስነምግባራችን በመበላሸቱ ምክንያት ዋጋ ቢስ አንዳይሆንብን ልክ እንደ ስራዎቻችን ስነምግባራችንም ያማረ ይሁን።
☀️ከማንም በላይ ለቤተሰቦቻችን ስነምግባራችንን እጅጉን ያማረ ሊሆን ይገባል።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Nov, 03:47


☀️ ችግርና መከራ ምንም ቢበረቱ ተከትሏቸው መምጣቱ መቼም በማይቀረው ድልና ድሎት ይሸነፋሉ።

ይህም የአሏህ ቃል ነው።

የቃሉን ተፈጻሚነት በተስፋ መጠባበቅ ሙእሚንነት ነው

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

07 Nov, 03:02


☀️اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ يَا اللَّهُ بِأَنَّكَ الْوَاحِدُ الْأَحَدُ، الصَّمَدُ، الَّذِي لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ، وَلَمْ يَكُنْ لَهُ كُفُوًا أَحَدٌ، أَنْ تَغْفِرَ لِي ذُنُوبِي، إِنَّكَ أَنْتَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Nov, 19:04


☀️አንዲት አባቷ የመስጂድ ኢማም የሆነች ልጅ ነበረች። ልጁ በቁንጅናዋ ተማርኮ ዚና እንዲሰሩ ይጠይቃታል፤ ቆንጆይቱም "እሺ ነገር ግን ሁለት መስፈርቶች አሉኝ እነርሱን ካሟላህ " ትለዋለች። መስፈርቷንም በዚህ መልኩ ትነግረዋለች።
1ኛ) ትንሽ ጊዜ ስጠኝ።
2ኛ) እንደምታቀው አባቴ የመስጅድ ኢማም ነው እና ስጠኝ እስካልኩህ ጊዜ ድረስ መስጂድ እየሄድክ በጀምዐህ ሶላትህን ስገድ" ትለዋለች።
:
ልጁም እሺ ብሎ ተስማማ።
ቃሉንና መስፈርቱን ለመጠበቅ ሲል መስጂድ መሄድን አዘወተረ።

በመጨረሻም የሰጣት ጊዜም አለቀ።
"ያንን የሰጠሁህን መስፈርት ተገበርከው ቃልህንስ በትክክል እያከበርክ ነው"? የሚል ጥያቄ አነሳችለት።
እርሱም "አው! እየተገበርኩ ነው ነገር ግን ቃል ያስገባሁሽን ነገር አሏህ ይቅር ይበለኝ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል። መስጂድ በምመላለስበት ሰዓት ወደ አሏህ ተመልሻለሁ" አላት።

አርሷም "ማሻ አሏህ! እኔም እሺ ያልኩህ ዝሙት ለመስራት ሳይሆን "ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች" በሚለው በዚህ በአሏህ ቃል እርግጠኝነት ተሞልቼ ነው።

اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ ۖ إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ
ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አሏህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አሏህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡
📒ሱረቱል ዐንከቡት (45)

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Nov, 13:57


ይህ ነገር ምን እንደሆነ የሚነግረኝ
.........

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Nov, 06:41


☀️ጀግና ወንድ ማለት በስሜት የሚነዳ ለጊዜያዊ አካላዊ ጥቅሙ የሚያስብ አይደለም።

ወንድ ማለት ራሱን ከስሜት ነበልባል ጠብቆ ስለቀጣይ ሂይወቱ በብዙ አቅጣጫ በማጥናት እና አርቆ በማሰብ የምትጠቅመውን ሚስት መምረጥ የቻለ ነው።

ለዚህም ነብዩ صلى الله عليه وسلم ምርጥ ምሳሌ ናቸው። በአፍላ ወጣትነታቸው በስሜት ሳይሸወዱ በእድሜ የምትበልጣቸውን ሴት ነው ያገቡት። ብልህነቷን፣ ዝናዋን፣ ክብሯን እና እገዛዋን በማሰብ ነበር የመረጧት።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

06 Nov, 04:25


☀️በኢስላም የፍቺ ስልጣኑ ለወንድ የተሰጠ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። አሏህ ይህን ያደረገበት የራሱ ሒክማ አለው።

ነገር ግን ይህንን ስልጣኑን ያለ አግባብ የሚጠቀም ብዙ "ወንድ" ያጋጥማል። በትንሽ በትልቁ "እፈታሻለሁ!" እያለ የሚያስፈራራ ቂላቂል ገና ትዳር የጋራ ህይወት እንደሆነ ያልተረዳ፣ ለአቅመ ሀላፍትና ያልደረሰ የወንድ አልጫ ነው።

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

05 Nov, 17:53


☀️አንድ የቀዶ ጥገና ባለሙያ አንድ ድንገተኛ ታማሚ ስለመጣ  ከሆስፒታል አስቸኳይ ጥሪ ተደወለለትና መጣ።

ቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ከመግባቱ በፊት በር ላይ የታማሚው ልጅ አባት ጠበቀውና "ለምን ዘገየህ? ልጄ አደጋ ላይ ነው! ትንሽ እንኳ እዝነት የለህም?" አለና ጮኸበት።
ዶክተሩም ፈገግ አለና በተረጋጋ መንፈስ "ተረጋጋ! ሥራዬን ልሥራበት። ልጅህ በአሏህ ጥበቃ ስር መሆኑን እወቅ!" አለና መለሰለት።

እኚህ አባትም "እንዴት ልትረጋጋ ቻልክ? አሁን ይህ ያንተ ልጅ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ትረጋጋ ነበር? ሌሎችን መምከር ቀላል ነው!" አሉት ለዶክተሩ።

ዶክተሩም ዝም አላቸውና ወደ ቀዶ ጥገና ክፍሉ ገብቶ ለሁለት ሰዓታት የቆየ ቀዶ ጥገና ካካሄደ በኋላ ሲወጣ "አል-ሐምዱ ሊላህ! ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። ልጅህ በጣም ደህና ነው። አሁን ሌላ ቀጠሮ ስላለብኝ ይቅርታ አድርግልኝና ልሄድ ነው ብሎት ምንም ጥያቄ ለማዳመጥ ሳይሞክር ሄደ።

ነርሷ ከቀዶ ጥገና ክፍሉ ስትወጣ "ይሄ ጨካኝ ዶክተር ምን ሆኖ ነው?" ሲል ጠየቋት የታማሚው ልጅ አባት።

እርሷም "ልጁ በመኪና አደጋ ሙቶበታል። አስቸኳይ የስልክ ጥሪውን መልሶ የመጣው ልጅዎ ያለበትን ሁኔታ ስለተረዳ ነው። እናም አሁን የርስዎን ልጅ ካዳነ በኋላ የልጁን ቀብር ለመታደም በአስቸኳይ መሄዱ ነው።" ብላ መለሰችለት!

ጭብጥ‼️
------------
❗️ነገሮችን በአንድ አቅጣጫ ብቻ መመልከት እንደሌለብን፤ በሰዎች ላይ በችኮላ መፍረድ እንደሌለብን፣ ሁሌም እኔ ትክክል ነኝ ማለት እንደሌለብን ያስረዳል።

አስቡት ዶክተሩ ልጁ ሞቶበት የሰውን ልጅ ለማከም መምጣቱ፣ የታማሚው አባት ሲጮህበት ታግሶ ምንም ነገር ሳይናገር መሄዱ ታጋሽነቱን አሳይቶናል።
ትዕግስትን የሚያክል ነገር የለም ከታጋሾች ያድርገን‼️

#ወሰላሙዐለይኩም

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

05 Nov, 17:43


❗️ስህተት ስታገኙ ለማሳወቅ እንዲሁም ምክር ለመስጠት
@Almutehabbot

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

05 Nov, 17:14


☀️أحبب حبيبك هونا ما عسى أن يكون بغيضك يوماً ما، وابغض بغيضك هوناً ما عسى أن يكون حبيبك.

“ወዳጅህን በመጠኑ ውደድ፤ ምናልባትም ወደፊት ጠላትህ ሊሆን ይችላልና። ጠላትህንም በመጠኑ ጥላ፤ የሆነ ቀን ወዳጅህ ሊሆን ይችላልና”።

ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

05 Nov, 15:42


☀️ትዳር ስትፈልግ ሴት ያለችበት ሳይሆን ወንዶች ያሉበት ቤት ፈልግ።
በጠንካራ ወንድ ቤት ጠንካራ ሴት ትገኛለች‼️

አብዛኛውን ከማየት ነው እንጂ በጣም ብዙ «ወንድ ለምኔ?» የሚያስብሉ ጠንካራ #እህቶች ከደካማ ወንድ ቤት መኖራቸውም መረሳት የለበትም!

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

05 Nov, 13:27


☀️ማስታገሻ እየሰጡ ከሚያቆዩዋቹ ሰዎች ራቁ❗️

☀️አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

05 Nov, 04:28


☀️እርግጠኛ ሁን
ዛሬ የጎዳህ ነገ እሱንም የሚጎዳው ሰው አያጣም
ዛሬ ያስለቀሰህ ነገ ሚያስለቅሰው ሰው አያጣም ምድር ትዞራለች ካንተ የሚጠበቀው መታገስ ብቻ ነው።

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

04 Nov, 19:01


☀️ስለ አንድ ሰው ማወቅ አለብኝ በሚል ሰበብ ጥያቄ አታብዛ የማይመለከትህን ተው።አንተ ለጥያቄህ ምላሽ ታገኝ ይሆናል ግን ለዛ ሰው የረሳውን ሀዘን መቀስቀሻ አሊያም ያለፈው ህመም ማስታወሻ ይሆንበታል።
ሰዎችን ከርቀት አይተህ መገመት አቁም ትክክለኛ ማንነታቸውን ስታውቅ ይቆጭሀል።
በቃ ሰው ለምትጠይቀው ጥያቄ ምላሽ ካልሰጠህ አትፈላፈለው ሁሉም ነገር ለሁሉም ሰው አይነገርም።
ደግሞ ተጠንቀቅ ለጥያቄህ ምላሽ አጣሁ ብለህ ያልሆነ ንግግር አትናገር።የሁለት የሶስት ሰዎችን ባህሪ አወቅክ ማለት ሁሉም ሰዎች አንድ ናቸው ማለትን አያሲዝም።
ሁሉም ነገር የሚሆነው አሏህ ስለፈቀደ እንጂ አንተ ስለፈለግክ አይደለም ይህንን በደንብ ልታውቅ ይገባል።
ሰዎችን ሁሉ እንደ ራሰህ አትመዝናቸው!

#ወሰላሙዐለይኩም 🙌

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

04 Nov, 18:11


☀️ሁሉም ቦታ በህመም እሾህ መጠርቆስ ያደክማል።ያማል! በነፃነት የማንባትን አቅም ማጣት።የዚህ ሁሉ መፍትሄ በምንደረድራቸው ምክንያቶች ላይ ይወስናል።የምር ግን ስለ ልባችን ህመም የሚያቅልን የለም?ያውም ከኛው በላይ?ስለ እምባችን ዘለላ ብዛት ጨምሮ....

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

04 Nov, 17:51


እንሞታለን❗️

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

31 Oct, 19:54


👉 አሳታፊ ጥያቄ 🌹

ነብዩ ሙሀመድ ﷺ በስንት አመታቸው አኺራ ሄዱ⁉️

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

31 Oct, 02:42


☀️ትልቅ እድል ነው ያመጣሁላቹህ ቻናሉን ጆይን ብላቹህ ነፃ የ graphics design እድል ነው ተወዳደሩ መልካም እድል
👇👇👇👇👇
https://t.me/+a97xeix9v0E3MDc0

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 18:28


☀️ኒቋብ ሰውነቴን እንጂ አእምሮዬን አይሸፍነውም።
በኒቋባችን አንደራደርም።

#ክብር_ለሙተነቂቦች

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 17:52


#ሰህ?

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 17:04


☀️*أجمل ما يقال في الحب
ስለ ፍቅር ከተባለው ምርጥ ነገር
*ربي هناك فتاة سرقتني
ጌታዬ.. የሰረቀችኝ ልጅ አለች
*أنت من خلقتها و خلقتني
እኔንም እሷንም የፈጠርከን አንተው ነህ
*وأنت من أبدع بها وهي سحرتني
አንተው ነህ ያሳመርካት.. እናም አስደነቀችኝ
*لا تجعلها من نصيب غيري
የሌላ ሰው አታድርጋት
*اريدها في الدنيا
ዱንያ ላይ እፈልጋታለው
*واجعلها في الجنة حور عيني
ጀነትም ላይ የ አይኔ ማረፍያ አድርጋት

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 13:51


#አዎ
#የሴት ልብ እና #የውሻ አይን ተመሳሳይ ናቸው!
ነገሮችን በጥልቀት ያያሉ። የሆነ ነገር ሲከባቸው ይሰማሉ።ሴት ልጅ ልቧ ብዙ ነገርን ያነባል። የሴት ልጅ መንፈስ በጣም ብዙ ነገርን ማየት ይችላል።ሴት ልጅ ቀልቧ/መንፈሷ ሴት ልጅ ልቧ ረቂቅ ነገሮችን ያያል።ይሄንን በጣም ማስተዋል አለባቹ እንኳን ትልቅ ሴት ሆና ይቅርና ህፃን ልጅ እንኳ የ 7/6 አመት ልጅ አባቴ ይሄንን ነገር ተው! ስትልህ ልታስተውል ይገባል። እንደ ልጅ እንዳትንቃት ሴት ናት።
በሴት ቀልብ ላይ የሚከናወን ትልቅ ነገር አለ።የሴት ልጅ መንፈስ ብዙ ነገሮችን አርቆ መመልከት ይችላል።
የሆነ የሸከካትን ወይም ደስ ያላላትን ነገር ልትመረምረው ይገባል።ሴቶች ቀልባቸው ነገሮችን የማንበብ ከፍተኛ አቅም አለው።
ይሄንን እወቅ!!!

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 13:39


☀️የሴት ልብ እና የውሻ አይን ተመሳሳይ ናቸው።

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 12:11


❗️የምታስበውን ሁሉ post አታድርግ❗️

#A

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 10:33


ኸይር
ያው ኪታቡ አዲስ አይደለም። በዚያ ላይ ትንሽዬ ነች።
#ሸይዃችን #አህመድ_አደም ይህንን ኪታብ ካስቀሩ ቆይተዋል።
ኦድዮው ደግሞ በቅርቡ ከ
ክፍል/1  ጀምሮ መፖሰት ተጀምሯል። ሳይደራረብባቹ መቅራት ጀምሩ
#ኪታቡ ከሌላቹ ደግሞ የግድ መግዛት አለባቹ ያላቹ ደግሞ በተደጋጋሚ ቅሩት
ትንሽ ስለሆነ ችላ አንበለው። እንዲሁም መደጋገም አልፈልግም አንበል ቀደምቶች አንድን ኪታብ ከ 40 ጊዜ በላይ ይቀሩት ነበር።
አውቀዋለሁ ተብሎ የሚተው ኪታብ የለም ።
ዒልምን ማጥናቱ በራሱ ዒባዳህ ነው።
ዒባዳህ ሶላት፣ሀጅ ብቻ አይደለም።


አልሙሂም ይህንን ንኩና ተከታተሉ
👇    👇     👇     👇     👇    👇
https://t.me/ahmedadem/8954

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 09:12


❗️ኹዝ ዐቂደተክ👈ኪታብ ያላቹህ እጃቹን አውጡ❗️

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

29 Oct, 06:50


☀️ ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«ሐቅ እንደተነጠረ ንፁህ ወርቅ ነው፤ በተፈተነ ቁጥር ጥራቱ ይጨምራል። ባጢል ደግሞ እንደ አርቲፊሻል ወርቅ ነው፤ በተፈተነ ቁጥር ግድፈቱ ይጎላል።»

۞ الجواب الصحيح【1/88】۞
@ALMUTEHABIN

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

28 Oct, 17:55


❗️ደህና እደሩ❗️
ስህተት ስታገኙ
👉@Almutehabbot

#ወሰላሙዐለይኩም

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

28 Oct, 16:40


❗️አንድም ቀን ጥሩ ሰዉ እንድሆን ሳትመክሪኝ በየቦታዉ ከሰዎች ጋር ቁጭ ብለሽ መጥፎ ሰዉ ናት ብለሽ አትሚኝ!!❗️

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

28 Oct, 13:26


☀️ሸyኽ ሷሊህ አልፈውዛን "አሏህ ይጠብቃቸው" እንዲህ ብለዋል።

  ሸሪዐዊ እውቀት የሌለው የሆነ ሰው ምስኪን ማለት እሱ ነው። ሰዎች እንደፈለጉ ሊጫወቱበት የቀረበ ሰው ነው።

🗓 درس فتح المجيد ١٤ - ٥ - ١٤٣٧هـ

@almutehabin

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

28 Oct, 09:20


☀️አሏህን የህሊና እረፍት
ስጠኝ ብለህ ከለመንከው በኋላ
ሰዎች ካንተ ሲርቁ ካየህ አትደናገር ።

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

28 Oct, 07:06


☀️ፖለቲከኞች ልክ ጫካ ውስጥ
እንዳሉ ዚንጀሮዎች ናቸው‥
๏ ሲጣሉ ተክልን ያበላሻሉ
ሲስማሙ ደግሞ ምርቱን ይበላሉ ።

            

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

27 Oct, 19:01


☀️ነገር ሁሉ ይረሳል ……ዛሬ ትኩረት የሰጠነው... ትላንት ሀሳባችንን ጭንቀታችንን የተቆጣጠረው ነገር ሁሉ ነገ ይረሳል …… ትላንት ሳናያቸው መዋል የሚያቅቱን ... ሳናወራቸው... ሳናገኛቸው ካለነሱማ እንዴት እንኖራለን ያልንላቸው ሰዎች ሁሉ ዛሬን ስማቸሁን ሁሉ ሳንዘነጋው አልቀረንም ……

እናም ሲመስለኝ ችግሮቻችን ሁሉ እንደዛው ናቸው …… ይረሳሉ ይዘነጋሉ …… ትላንት ያዘኑልን ዛሬን የወደዱን በችግራችን ጊዜ ተገኝቶ አይዞን ያሉን እልፍ ሰዎች የኖሩ አሁን ግን ደብዛቸው የጠፉ እነሱነታቸው የደበዘዙ ሰዎች ይኖራሉ…… እናም ልክ እንደደበዘዙት እንደጠፉት ሁሉ የተረሳን ቢመስለንም  ዛሬም እላለሁ ሁሉም ቢረሳ በእርግጥ…

وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا
ጌታህም ረሺ አይደለም፡፡

በርግጥም አሏህ አለ እሱ አይረሳምና
.
.
#ወሰላሙዐለይኩም

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

27 Oct, 17:06


☀️በሕይወታችን ድንገት የሆነ ሰው
ይመጣና ሌሎች ጥለውን ስለሄዱ
  #እንድናመሰግን ያደርገናል።

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

27 Oct, 13:26


☀️ፈትዋ መጠየቅያ ቁጥሮች ሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ላላችሁ ወንድም እህቶች

Nb፡ የጠየቃችሁት ፈትዋ መልሱ በሌላ ጥያቄዎች መብዛት ሊዘገይ ስለሚችል ታግሳችሁ ጠብቁ

#በሸይኽ_አህመድ_አደም

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

27 Oct, 11:59


📌የፂም ማብቀያ መድሀኒት መጠቀም ይቻላልን?ያብራሩልኝ!



@almutehabin

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

27 Oct, 10:11


☀️አንዳንድ ሰው....
የሌሎች ጉድለቶችን ይወቅሳል
ነገር ግን የራሱ ጉድለቶች ላይ
አይነ ሰውር ነው!!

#ለምን?

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

27 Oct, 07:39


☀️አትርሱ  እንዲህ አይነት ሰው አለ
ለናንተ ፈገግታ ብሎ ቀን ማታ የሚለፋ ውስጡ በሀዘን በህመም በቁስል ተሞልቶ እናንተን ለማስደሰት ሳይደሰት እንደተደሰተ  የሚያስመስል።
☀️እናንተ ፊት ለናንተ ብሎ በጣም የሚዝናና የሚጫወት ከናንተ ሲርቅ(ብቻው ሲሆን) አይኑ እስኪጠፋ እንባውን የሚያፈስ
ሆድ ብሶት ለብቻው የሚያወራ በሃሳብ ሌላ ዐለም ውስጥ ለረዥም ሰዐታት የሚቆይ 
☀️እራሱን ትቶ ለሌላው ፈገግታ የሚታገል
ውስጡ እያረረ በጥርሱ የሚስቅ ......... አረ ብዙ

#A

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

27 Oct, 03:10


☀️ «ለማንኛውም ፀጋ ምቀኛ እንዳለው ሁሉ ለማንኛውም ሀቅ ደግሞ አስተባባይና ተእቢተኛ አለው።»

ኢብኑል_ቀዪም አለይሂ ረሒመሁሏህ

۞ مفتــاح دار الـســعادة[1/2]
@ALMUTEHABIN

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

26 Oct, 18:49


☀️እኔ ብሆን ኖሮስ የሚል
ህሊና ያድለን!

#ወሰላሙዐለይኩም

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

26 Oct, 18:04


☀️ ሸይኽ ሱለይማን አር’ሩሐይሊ እንዲህ ብለዋል :-
"ከኢማን ሙሉ መሆን ምልክቶች መካከል ፤ አንድ አማኝ (ግለሰብ) መልካም ነገርን ወደ ሌሎች ለማድረስ ጉጉት ያለው መሆኑ ነው።"
@ALMUTEHABIN

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

26 Oct, 16:57


☀️አንዳንዴ.......
የሆኑ ሰዎችን ለዘላለም አናያቸውም
እነርሱ ሙተው ሳይሆን እኛ ውስጥ
ያለው የእነሱ ማንነት #ስለሞተ

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

26 Oct, 14:58


☀️በቁጣ ሚወጣ ..ብዙ ጊዜ ይመለሳል
ፈገግ ብሎ የሚወጣ ..ተመልሶ አይመጣም።

#አይደል?

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

26 Oct, 13:19


❗️ኒቋቤንም እለብሳለሁ ትምህርቴንም እማራለሁ❗️

#ኒቋቤ🌹🌹🌹

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

26 Oct, 10:38


💥 ከተውሒድ ቅድሚያ የሚሰጠው አንድም አንገብጋቢ ጉዳይ የለም። ምክንያቱም የአንድ ሰው እስልምና መሰረቱ ተውሒድ ስለሆነ።

💥 ተውሒዱ የተስተካከለ መላ ስራው ይስተካከላል። መሰረቱ ከተበላሸ ግን ግንቡ ያምራል ተብሎ አይጠበቅም። የሰራውም ስራ ከሽርክ ከተነካካ ዋጋ የለውም።

«وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ »

«ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትሆናለህ ማለት ወደ አንተም ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደ ነበሩት በእርግጥ ተወርዷል»
[ ዙመር-65]

#ተውሒድ

@ALMUTEHABIN

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

26 Oct, 07:39


☀️ድምፃቸውን ከፍ አድርገው
   በአጠገባችን የሚያለቅሱ ሰዎችን ስናይ
ያሳዝኑናል....ልንረዳቸውም እንሞክራለን፡፡
ነገር ግን እነዛ በዝምታ ለሚያለቅሱ ሰዎች
      ማን አላቸው ???

#አሏህ_ብቻ

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

25 Oct, 19:20


☀️ስድብና መጥፎ ንግግር ያላዋቂ መሳሪያ ነው

ለጃሂል/አላዋቂ ለሆነ ሰው ትርፍ ንግግር መልስ መስጠት ጥንብን ደጋግሞ እንደመነካከት ነው።
ካላዋቂ ጋር መከራከርን መተው ልብና ሰውነትን ማሳረፍ ነው።
የማይጠቅም ወይም መሰረተ-ቢስና የሰውን ክብር የሚነካ ወሬ ለማውራት ምላስህ ከበላህ ነገ ቀብር ውስጥ ምላስህን ትል እንደሚበላው አስታውስ!፤ ይሄኔ ምላስህ አደብ ይይዛል!
"የወራዶች መሳሪያ መጥፎ ንግግር ነው سلاح اللئام قبيح الكلام"
ተብሏልና ሁሌም ንግግራችንን እንለካ።
ሐዲሡም (ሙስሊም ማለት ከእጁና ከምላሱ ጣጣ ሙስሊሞች የዳኑ ሰው ነው)።... (በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካምን ንግግር ይናገር፤ ካልሆነ ዝም ይበል) ይላል።


#ወሰላሙዐለይኩም

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

25 Oct, 19:05


☀️ምላስ አጥንት አይደለም ...ግን አጥንት ይሰብራል!

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

25 Oct, 17:44


☀️ከእግራቸው ይልቅ በምላሳቸው ከሚራገጡ ሰዎች አሏህ ይጠብቀን!

<<የወራዶች መሳሪያ መጥፎ ንግግር ነው>>

#ተጠንቀቅ 🫵

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

25 Oct, 16:07


☀️ አንድ ቀን ከእናንተ ጋር
የማልሆንበት ጊዜ ይመጣል
๏ የፃፍኩትን ለማንበብ ወደዚህ ቻናል ትገቡ(ትቀላቀሉ) ይሆናል
አጅር የሚያሰገኝልኝን ነገር ስታገኙ
ወይም ስታነቡ አሰራጩልኝ አደራ‥
✘ የሚያስወነጅለኝን ነገር ስታገኙ ወይም
ስታነቡ ደግሞ ተውት ።

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

25 Oct, 05:47


☀️رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ الأبْرَارِ رَبَّنَا وَآتِنَا مَا وَعَدتَّنَا عَلَى رُسُلِكَ وَلاَ تُخْزِنَا يَوْمَ الْقِيَامَةِ إِنَّكَ لاَ تُخْلِفُ الْمِيعَاد

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

24 Oct, 18:09


☀️اللهم اجرني من موت الغفلة ولا تأخذني من الدنيا الا وانت راض عني


#ወሰላሙዐለይኩም

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

24 Oct, 13:23


☀️ክብርህ አንተው ቁልፉን የያዝከው በር እንደማለት ነው:: ዝም ብለህ ለማንም ከፍተህ ክብርህን አታስነካው ❗️

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

24 Oct, 04:34


☀️ኢንተቢህ ፈንተቢህ ቁልቱ ቢህ..ኢን ኩንተ ሙንተቢህ

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

23 Oct, 19:38


☀️ነገሮችን ባላየ ማለፍን ልመጂ...... የማይጠቅሙሽን ነገሮች!
ህይወትሽ ላይ ምንም የማይጨምርና ...የማይቀንሱን ነገሮች በመዝለል ላይ በርቺ .....ትተሽ ያለፍሻቸውን ነገሮች ዞረሽ ባለማየት ላይ ጀግኚ ......ላልሆንሻቸው ስያሜዎችሽ መልስ በመስጠት ላይ አትገኚ .......በቀኖችሽ ውስጥ የሚጠቅምሽን ብቻ ዝገኚ!!!!!

#እህቴ ትኩረት አልባ ሁኚ ማለቴ አይደለም ነገር ግን መርጠሽ ትኩረት ስጪ የማይጠቅምሽን እያሰብሽ እንቅልፍ አጥተሽ አትደሪ ነቃ በይ። 

#ወሰላሙዐለይኩም

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

23 Oct, 18:39


☀️ በሂወታችን ውስጥ አንዳንድ ሰዎች አሉ እኛን በረጅም ገመድ አስረው የሆነ ሰዐት ይለቁናል ስናስፈልጋቸው ደግሞ ባሰሩን ገመድ መልሰው ይስቡናል ከዛም ትንሽ ቆይተው ይለቁናል እንዲው በመጎተት እና በመልቀቅ የሚኖሩ።

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

23 Oct, 15:45


☀️አንዳንዴ ከቀን ወደ ቀን ከሰው መራቅ ትመኚያለሽ ግን እኮ የሰው ጥላቻ ሳይሆን... አንዳንድ ሰዎች በሚያሳዩሽ ገፀ ባህሪያት ነው።

#A

  

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

23 Oct, 14:27


☀️ያልተዘጋጀ ቢሆንም እንኳ አንቺ እሱ ሚፈልጋት አይነት ሴት ከሆንሽ ላንቺ ሲል ይዘጋጃል። አንቺን አሏህ እንደሚለዉና እንደሚፈልገዉ የግሉ ያደርግሻል።

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

23 Oct, 10:48


#ተጠየቀ...
☀️እንዴት ናችሁ... ከእሷ ጋር?!
=ከእሷ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም...ግና አሏህዬን በየ ዊትሩ እና በየ ሱጁዱ ከእሱ እጠይቃታለሁ...ለዚያዉም በሀላሉ ነዋ !

ربي إني لما أنزلت إليّ من خيرٍ فقير

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

23 Oct, 07:26


☀️"ኢምራን ኢብኑ ሀطاን ከخዋሪጅ
የሆነችን ቆንጆ ሴት ያገባል: አህለ ሱና አደርጋታለዉ ብሎ,
ከخዋሪጆች አቀንቃኝ መሪም ሆነ"

🫱ሲየር አعላም አኑበላእ [ 214 ]

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

23 Oct, 05:11


☀️ኢብኑ ሀጀር አሏህይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

መንገድ ላይ የሚያልፉ ሴቶችን ለመመልከት ሱቅ በር (መንገድ ዳር) መቀመጥ (ከወንጀሉ ባሻገር) የአንድን ሰው ማንነት ከሚያጎድሉ ተግባሮች ውስጥ አንዱ ነው።

📚فتح الباري (٤٠/١١)

#ወንዶች??

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

22 Oct, 19:15


☀️ማንንም ሰው ከመጠን በላይ አትቅረበው።አለም ላይ ብቸኛው አማራጭህ እሱ ብቻ ይመስለዋል።

#ወሰላሙዐለይኩም

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

22 Oct, 18:19


☀️በከተማዋ ውስጥ ካለ መስጂድ መግቢያ በር ፊት ለፊት አንድ አህያ ሞቶ ተገኘ። ሽታውም ምዕመኑን አስቸገረ....የአካባቢው ማህበረሰብ ለሚመለከተው የከተማው መንግስት መስሪያ ቤት የአህያውን ሬሳ እንዲያነሳ በተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርጉም ምላሽ ማግኘት ግን አልቻሉም።

  ከዛም ይህን የተመለከቱ የመስጅዱ ኢማም ወደ አንድ ባለስልጣን ስልክ ደወሉ።  በሁለቱ መሀከል የተካሄደው የስልክ ንግግር ልውውጥ ይሄን ይመስላል።

የመስጅዱ ኢማም ፦ "ክቡርነትዎ፣ ከመስጂዳችን መግቢያ በር ፊት ለፊት አንድ የሞተ አህያ አለ። አካባቢው በመጥፎ ሽታ ታጥኗል። እናም..." ብለው ንግግራቸውን ለመቀጠል ሲምክሩ ባለስልጣኑ ንግግራቸውን አቋረጧቸው።

  ባለስልጣኑ ፦ "እና ምን ? መናገር የፈለጉት ፍሬ ሀሳብ ምንድነው? አሉ በቁጣ

  የመስጅዱ ኢማም ፦ " አይ የከተማዋ ከንቲባ የአህያዋን ሬሳ ከመስጅዱ አቅራቢያ የሚያነሳበት ሁኔታ ቢመቻችልን ብዬ ነው።"

  ባለስልጣኑ በንቀት እና በማሾፍ ታጅቦ ፦" ሼይህ ፣ ለመሆኑ ሙታንን አጥቦ መገነዝ የእናንተ ስራ መሰለኝ?"

  የመስጅዱ ኢማም እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ፦ " አይ...እሱስ ልክ ነዎት ። ግን ደግሞ አህያውን አጥበን እና ገንዘን ከመቅበራችን በፊት ለሟች ቤተሰብ መርዶውን ለመንገር ብዬ ነው የደወልኩልዎት...እና ሞት ለማንም አይቀርም አላህ ፅናቱን ይስጥዎት።" ብለውት አረፉ

#ፈገግታ_ሱና_ነው!

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

22 Oct, 17:50


እስኪ...እንዲየው...ይሄንን ሳሙና

አኡዙ ቢላህ ብለን ነዉ የምንጠቀመዉ...ወይስ...
ኢና ሊላህ...

💥አል-ሙተሀቢን(المتحابين)

22 Oct, 17:05


💧ፊትለፊትህ ከመጣ ዘንዶ ይልቅ ሳር ውስጥ የተደበቀን እባብ ፍራ..!

5,517

subscribers

373

photos

366

videos