Natinael Mekonnen @natinaelmekonnen21 Channel on Telegram

Natinael Mekonnen

@natinaelmekonnen21


ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21

Natinael Mekonnen (Amharic)

ናቲናኤል መኮንን በበደረገበት ቻናል ንግስግረድ ቴሌግራም ተጠፋ። በከፈቱት ችግር እና መከላከያውን በኮሌክሽን ዋጋ ለማወቅ ምንጮችን እና መንገዶችን ለቀላቀሉበት ለመቀረድ መረጃዎችን ከፈለጉ። ከእስከ ለማረጋገጥ @NatnaelMekonnen7 በመከታተል በአገሮች እና ቀይር መተየቢያዎች ላይ ለመዋጣት ሳትፈልጉም ለማስገንባት ዙር ሁሉ ላይ በኣኮንት አገናኝ መረጃዎችን እንዲደርሳቸው ሰላምተናል። ለማህበሩና ወደ ቴሌግራም ሽልማታ መሰረታዊ መዝገብ ለመሰብሰብ እና አናጋሪ ማወቅ ማቅረብ ይችላሉ። የሚሰብስበት የኮሌክሽን ቻናል @NatnaelMekonnen7 እና ሌሎች ከፈለጉት ችግሮችን መክፈት የሚለው ናታሰብ ነኝ።

Natinael Mekonnen

02 Dec, 15:19


አንድ ወስላታ በሚዲያ ቀርቦ እኔን “የቀድሞው ፕሬዚዳንት” እያለ ሲጠራኝ ነበር አሉ።እሱ ችግር የለውም።ፖሊስ ጋ ቀርቦ መልስ ይሰጥበታል።የእነዚህ ሰዎች ችግር ስራ አለመስራታቸው ብቻ አይደለም።ከበፊት ጀምሮ የወንጀልና የሌብነት ኔትወርካቸው እንደሚጋለጥና እንደሚጠይቁ ስለሚያውቁ የትግራይ ፖለቲካ እንዲስተካከል አለመፈለጋቸው ነው።በዘረፋ የተሰማሩባቸው የወርቅና የመዳብ ማዕድናቱ ከእጃቸው እንዲወጣ አይፈልጉም።የትግራይ ፖለቲካ ተበላሽቶ የቀረው በነዚህ ሰዎች ምክንያት ነው

ጌታቸው ረዳ

Natinael Mekonnen

02 Dec, 08:15


"ባለፉት የለውጥ አመታት በሶማሌ ክልል የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት የየበኩላችንን በመውሰድ እናስቀጥላለን"፦ በአውሮፓ የሚኖሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ

ባለፉት የለውጥ አመታት በሶማሌ ክልል የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት የበኩላችንን ወስደን ለማስቀጠል ቃል እንገባለን ሲሉ ኑሮዋቸውን በአውሮፓ በተለይ በስካንዴኔቭያን ሀገራት ያደረጉ የሶማሌ ክልል ተወላጆችና የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት ገለፁ።

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከአውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ የክልሉ ተወላጆች እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በስዊድን ስቶኾልም ከተማ ተወያዩ።

በውይይቱም ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው፣ በኢትዮጵያ በተለይ በሶማሌ ክልል የሰፈነው ለውጥ ያስገኛቸው ፍሬዎች እና ድሎል እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ገለፃ አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ በገለፃቸው፤ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መሪነት በፖለቲካው ዘርፍ በተደረገው ሪፎርም ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሆና ዜጎች በሀገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተረጋግጧል ብለው፣ ለዚህም ላለፉት ስድስት አመታት በሶማሌ ክልል የሰፈነው ሰላም፣ ልማትና የክልሉ ህዝብ በሀገር ጉዳይ ላይ ከተመልካችነት ወደ ውሳኔ ሰጪነት የመጣበት ሁኔታ ማሳያ ነው ብለዋል።

በተለይም ባለፉት ስድስት አመታት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ለውጥ አማካኝነት በሶማሌ ክልል የሀይማኖት ነፃነት፣ ሰበዓዊ መብት መጠበቅ፣ ፖለቲካ ምህዳር መስፋትና ማንም በፖለቲካ አመለካከቱ በሀሳቡ እንደማይታሰር እና የህዝቡን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ መልስ መስጠት መቻሉን ገልጸዋል።

አቶ ሙስጠፋ ባለፉት አመታት እንደ ጤና፣ መንገድ፣ ትምህርት፣ ከተማ ልማት፣ ግብርና፣ የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ ሃይልና የስራ እድል ፈጠራ፣ የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ያሉ አንኳር የልማት ሥራዎችን መሰራታቸውን አንስተዋል።

በሶማሌ ክልል የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት ከሰላሙ ባሻገር ለ50 አመታት ያልተሰሩ የልማት ሥራዎች ባለፉት ስድስት አመታት ብቻ መሰራታቸውን ጠቁመው፣ በተለይ በጤናው መስክ ከስድስት አመታት በፊት በክልሉ 9 ሆስፒታሎች ብቻ እንደነበሩና፣ ለውጡ ማግስት 9 አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንሆነና በአሁኑ ወቅትም 15 ሆስፒታሎች በግንባታ ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ የመንገድ አውታሮች ማስፋፋት መቻሉንና የፌደራሉ መንግሥት ከ2 ሺህኪ.ሜ በላይ የአስፓልት መንገድ በክልሉ መገንባቱንና ሌሎች በርካታ መነረገዶችም በግንባታ ላይ ናቸው ብለው፣ ከኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ጋር በተያያዘም ባለፉት ስድስት አመታት በክልሉ 80 የሚሆኑ ከተሞች ወረዳዎች እና በቀበሌ ደረጃ ያሉ የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በውይይት መድረኩ ላይ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም መንግሥት ለዲያስፖራው ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻነቱንና፣ በውጭ ሀገራት የቀሰሙትን እውቀትና ያፈሩትን ሀብት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ኢንቨስት በማድረግ እራሳቸውንም ሆነ ዜጎችን እንዲጠቅሙ ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ጥሪ አቅርበዋል።

በበኩላቸው በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በተወካዮቻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ በተደረገላቸው ገለፃ በኢትዮጵያ በተለይ በሶማሌ ክልል ያለውን ሁኔታ ጥሩ ግንዛቤ ማግኘት መቻላቸውን ገልፀው፣ የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት ለማስቀጠል የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ዲያስፖራው ሀገር ቤት ከተለያዩ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በሚሄዱበት ጊዜ መጉላላት እንዳለ ጠቁመው፣ ይህም እንዲስተካከል ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ዲያስፖራው ለክልሉ ልማትና ለዜጎች ኑሮ መሻሻል እያደረገ ያለውን የተያየ ድጋፍና እገዛ አመስግነው፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የተነሱት ጥያቄዎች እንደሚታረሙ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ በስካንዲናቪያን ሀገራት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታን ጨምሮ የሶማሌ ክልል አመራሮች እንዲሁም የስቶኾልም ከተማ ምክትል ከንቲባ ተገኝተዋል።

Natinael Mekonnen

01 Dec, 19:58


በቡሄ ግዜ የደነቆረው ስታሊን

ስታሊን ገብረስላሴ "ጃል ሰኚ የወቦን ትግል ከዳ" ብሎ በሀዘን ስሜት የፃፈውን አየሁትና አሳቀኝ። የኦሮሞ ልጆች "መገዳደል ይብቃ" ብለው እርቀሰላም ስለፈፀሙ የአንደኛው የህውሀት ክንፍ ደጋፊዎች ድንኳን ጥለው ለቅሶ ሲቀመጡ እንደማየት የሚገርም ነገር ነው 😁

የነ ስታሊን ካምፕ ህውሀት ፕሪቶሪያ ላይ እርቅ ስትፈራረም አጨብጭበው ሰላም ከሰፈነ በኋላ፥ አማራና ኦሮሚያ ክልል ግን በጦርነት ውስጥ እንዲከርሙ ሲቀሰቅሱ ይውላሉ። ምክኒያቱም ለትግራይ ማህበራዊ እረፍት የሰጠ የሰላም አየር በኦሮሚያና በአማራ ክልል ውስጥ እንዲነፍስ አይፈልጉም። በዚህ ሰአት እንደዚህ አይነት ተራ ብልጣብልጥነት የማይገባው ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን የተረዱት አይመስሉም።

"በቡሄ ግዜ የደነቆረ ሁልጊዜ ሆሆሆ ይላል" አሉ። ወንድሜ በድሮ በሬ ያረሰ የለም። እራስህ በጀመርከው ቁማር ጆከር ተጥሎብህ ከተሸነፍክ በኋላ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" እንዳለችው አህያ በሰገሌ ግዜ የቀረ ተንኮል አራምዳለሁ ካልክ የአዲሱ ትውልድ መሳለቂያ ትሆናለህ እንጂ የምታገኘው አንዳች የፖለቲካ ትርፍ የለም።

ቢያንስ ግዜውም ትውልዱም መለወጡትን አይተህ እውቀትህን ባታሳድግና ከትናንት ስህተትህ መማር ባትችል እንኳን የተሻለ ተንኮል ይዘህ ገበያ እንዳጣ ግሮሰሪ የቀዘቀዘ ዩቲዩብህን ብትሸቅል የሚል ወንድማዊ ምክር አለኝ። move on my brother.

Natinael Mekonnen

01 Dec, 11:50


Good news : የኦሮሚያ ክልል መንግስት በኦሮሚያ ክልልና አካባቢው ይንቀሳቀስ ከነበረው ቡድን መሪ ጃል ሠኚ ነጋሳና እሱ ከሚመራው ሀይል ጋር የሰላም ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርሟል። ይህ ውሳኔ ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ዜና ነው። ሌሎቹም ሀይሎች የህዝባቸውን ድምፅ ሰምተው ባስቸኳይ ወደሰላም መድረክ ሊመጡ ይገባል።

በቦታው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተገኝተው የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ሃይሎችም ሆነ የሰላም ጥሪ ላቀረበው አካል ምስጋናቸውን አቅርበው ይህ አይነቱ ተግባር በሌሎቹም አካባቢዎችም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።

Natinael Mekonnen

19 Nov, 09:00


የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ
 
የአፍሪካ መዲና እና የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን በላቀ መስተንግዶ ለመቀበል ልዩ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች።
 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገራችንን በጎ ገፅታ አጉልቶ ለማሳየት መልካም አጋጣሚን በሚፈጥረው በዚህ መርሃግብር ላይ ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር  በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት ይፈልጋል።
 
በመሆኑም የእንግሊዘኛ፣ፈረንሳይኛና ዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የምትችሉ እና ዕድሚያችሁ ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳወቅን ለምዝገባ ስትመጡ የትምህርት ማስረጃችሁን እና ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንገልፃለን።
 
የአገራት መሪዎች፣የዓለምአቀፍና ቀጠናዊ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሚሳተፉበት የአህጉራችን ትልቁ ጉባዔ ላይ በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል በመሆን የዚህ ታሪክ አካል ሆናችሁ አገራችሁን ያለ ክፍያ በኩራት እንድታገለግሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪውን ያስተላልፋል።
 
ለተጨማሪ መረጃ፡-
 
+251911411045
+251912663737
 
ኑ! ሁሉም ዜጋ ለአገሩ ዲፕሎማት ነው!
 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Natinael Mekonnen

18 Nov, 18:08


ሉዓላዊ-የጎጃም ፋኖ የትግሉ ግምገማ ሰነድ ሲዳሰስ/በሕወሐት ውዝግብ ውስጥ የኤፈርት ሐብት ሚና/ማንነታችንን ለጨረታ አናቀርብም-ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ https://youtu.be/X50rDJNuLks

Natinael Mekonnen

18 Nov, 18:08


ክብር ኢትዮጵያን ለሚገነቡ እጆች።

የፌደራል ፖሊስ በክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል አመራር እየሰራ ያለው ነገር አስደናቂ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ የሐገሪቱ ፖሊስ የሚመራበትን doctrine ለመጀመሪያ ግዜ አዘጋጅተዋል። የፖሊስ ኮሌጅን ወደዩኒቨርስቲ አሳድገዋል። አጠቃላይ የኢትዮጵያ ፖሊስ ኢትዮጵያን እንዲመጥን አድርገው Reform ሰርተዋል። ለአባላቱ ከፍተኛ የሚባል ስልጠና በመስጠት ምናልባትም አንዳንድ ያደጉ ሐገራትን በሚስተካከል ደረጃ ተቋሙን በተማረ የሰው ሃይልም ሆነ በቴክኖሎጂ አዘምነዋል።

አሁን ደግሞ በአስራስምንት ወር የተሰራው የፎረንሲክ ምርመራና የምርምር ልህቀት መአከል ተአምር የሚባል ነው። ይህ ማእከል በአፍሪካ ትልቁ ከመሆኑ ባሻገር ለፍትህ ስርአቱ ምሉእ መሆን የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል አይደለምና ለዚህ ታላቅ ስራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይንና ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን እና ቡድናቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ይሆናል።

የሐገሪቱ ተቋማት ያለምንም ጣልቃ ገብነት ራሳቸውን በዚህ ደረጃ ሲያሳድጉና በዘመኑ ቴክኖሎጂ ሲያስታጥቁ እንደማየት የሚያኮራ ነገር የለም። ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ይገባታል።

ክብር ኢትዮጵያን ለሚገነቡ እጆች።

Natinael Mekonnen

15 Nov, 16:32


የሀዋሳ ከተማ 85% በካሜራ መሸፈኑን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ ገለፀ!!!

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ በሃዋሳ ከተማ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ እና የሰላም ማስከበር ሂደት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ኮማንደር መልካሙ በሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በተያዘው የፀጥታ ዘርፍ ሪፎርምን አቅጣጫ መሰረት እንደ መምሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የሆነው የሀዋሳ ከተማን በቴክኖሎጂ የበለፀገ ከተማ ለማድረግ ብሎም በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ ማስከበር ሂደት ያላት ከተማ ለማድረግ በተሰራው ስራ የከተማዋን 85% በካሜራ እንዲሸፈን ማድረግ ችለናል ሲሉ ኮማንደር መልካሙ ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በዚህ የሪፎርም እቅድ አንድ አካል የሆነውን በህብረተሰብ ተሳትፎ ግንባታዎች ሲሆኑ በዚህም እንደ መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ 3 ትላልቅ የፖሊስ ፅ/ቤት እና 40 የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች ግንባታዎች ተጠናቅቀው በከፊል ስራ እየሰሩ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በዚህም ሰዓት 40 ዘመናዊ የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች በሀዋሳ ከተማ ላይ ለ24 ሰዓት ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት በከተማችንን ላይ የሚገኙ የወንጀል ምርመራ እና የቃል አሰጣጥ ሂደት በቴክኖሎጂ የታገዘ እና በካሜራ የተደገፉ ሲሆን ይህም የሆነው የተመማሪውን ደህንነት እና መብት መረጋገጥ ለማረጋገጥ ከዛም በተጨማሪም የፋይል መረጃዎችን በማስቀመጥ ቀላል አሰራር እንዲዘረጋ ለማስቻል ሲሆን ይህ አግልግሎት በመላው ከተማችን ፖሊስ ጣቢያ የሚተገበር ነው።

በተጨማሪም 7614 ነፃ የፖሊስ መምሪያው የስልክ መስመር ሲሆን በማንኛውም ቀን እና ሰዓት በዚህ የነፃ መስመር በመደወል መረጃ ለመምሪያው የመረጃ ማዕከል ማድረስ ይችላል ተብላል። የስልክ መስመሩም በአንድ ላይ 5 ደዋዬችን በእኩል ሰዓት ማስተናገድ ስለሚችል ያለ ችግር ለማዕከሉ መረጃ ማድረስ ስለሚቻል ህብረተሰቡ ይህንን የነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቀም ኮማንደር መልካሙ የገለፁት።

(Hawassa Engeda) በሚል በከተማችንን አልጋ ቤቶች ጋር በጀመርነው አዲስ Software መሰረት ማንኛውም የአልጋ አግልግሎት የሚጠቀም አካል ሙሉ መረጃ በSoftware አማካኝነት ወደ ተቋማችንን ይመጣል በዚህም በአልጋ ቤቶች የሚፈፀሙ ወንጀሎች ለመቀነስ ያቀደ የቴክኖሎጂ ትግበራ በከተማች ላይ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ ተግባራዊ አድርገናል።

በአሁኑ ሰዓት በከተማችንን የሚገኙ ሁሉም የንግድ ተቋማት የድህንነት ካሜራ አግልግሎት እንዲጠቀሙ ባስቀመጥነው አስገዳጅ እቅድ መሰረት 583 ተቋምት የድህንነት ካሜራ በጊዜያዊነት የተከሉ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም ተቋማት የድህንነት ካሜራ አግልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ኮማንደሩ ገልፀዋል።

ኮማንደር መልካሙ አየለ አክለውም የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች በከተማችን ላይ በብዛት እየተሰሩ ሲሆን ፖሊስም ከማህበረሰቡ ጋር በህብረት በመስራት ሰላሙን ያረጋገጠ ከተማ የተገነባ ሲሆን በተጨማሪም 24 ሰዓት ያልተጎደለ የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች አግልግሎት የፖትሮል ቅኝት የአባላት ስምሪት በመንደሮች ላይ በማድረግ ሰላማዊ ከተማ ቀጠና መፍጠር መቻሉን ተገልፆል።

ማህበረሰቡ እና ወጣቱ ከፖሊስ ሃይሉ ጋር በቅንጅት በመስራቱ በተገኘው ድል መሰረት የከተማችንን ነዋሪዎች እና ወጣቶች ከልብ አመሰግናለሁ ሲል የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Natinael Mekonnen

09 Nov, 10:34


የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሽመልስ ቶማስ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የሃገራዊ የሰላም ኮንፍራስ ላይ የሙሉ ኮምሽነር ማዕረግ ሹመት ተሰጣቸው!!!

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ በርካታ ሪፎርሞችን ሰርቻለሁ ያለ ሲሆን ከተቋሙ ላይ ፍፁም ወገንተኝነት እና ብልሹ የሌቤነት አሰራርን ያለ ርራሄ በመታገል ፍትሃዊ ገለልተኛ መስመር ያለውን ጠንካራ ተቋም እንዲፈጠር አስችለናል ተብሏል።

በሲዳማ ክልል ብቻ ሳይሆን በአጎራባች ክልሎች ያለውን የሰላም ሁኔታ ለማስጠበቅ ቀን ሳይል ማታ ሳይል በብቃት ተልዕኮችን እየፈፀመ በብቃት እያከወነ ያለ ጠንካራ የፖሊስ ተቋም አቅም ያለው ሃይል ገንብተናል ብለዋል።

ከተቋሙ የሲዳማ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ የጀመርነው የግንባታ ሪፎርም እንደ ክልል አድጎ መሰረታዊ ቅርፅ ይዞ በመዋቅሩ ላይ አሻራ ጥሎ የሲዳማ ክልል ፖሊስ እስከ መጨረሻ ከክራይ ቤት ያዳነ ፕሮጀክት ይዘን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ የፖሊስ ተቋሙን ለመገንባት እና ለማዘመን በተያዘው እቅድ መሰረት ከህብረተሰብ ክፍሉ 1.1 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰበብ 42 የፖሊስ ፅ/ቤት 640 የመረጃ መቀበያ መሰረተ ግንባታዎችን በ90 ቀን ገንብተን ለማጠናቀቅ እየሰራን ሲሆን ያጠናቀቅነውም አለ።

በሲዳማ ፖሊስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፖሊስ ሃይሉ እና ለቤተሰባቸው ነፃ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት የፖሊስ ጤና ጣቢያ ከሟቋቋም ባለፈ ለፖሊስ ኮሚሽኑ ገራጅ እና ነዳጅ ማደያ ግንባታዎችን ከትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አስገብተን ሪፎርሙን እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል።

የዚህ የትራንስፎርሜሽ እቅድ አውራ አካል የሆኑት የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ በክልሉ የመጀመሪያው የሆነውን የሙሉ ኮምሽነር ማዕረግን አግኝተዋል።

በኮንፍራንሱ ላይ የሁሉም ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች, ኮሚሽነሮች, የመከላከያ ሰራዊቱ አመራሮች, የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አመራሮች, እና ሚኒስተሮች ተገኝተዋል።

Natinael Mekonnen

07 Nov, 17:08


የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር የመከላከያ ተቋማትን ጎበኙ።

የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዶ ኡሪ ባህ የኢፌዴሪ አየር ሀይልን እና የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንን ጎብኝተዋል። የሁለቱም ሀገራት መሪዎች በጉብኝቱ ሥለተደረገላቸው አቀባበል እና ገለፃ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን በዛሬው ጉብኝትም ይህንን ክብር የሚመጥን ተግባራት እያከናወነች መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል በጋራ በመስራታችንም ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

የኢፊዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ አየር ሃይልም ሆነ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለተቋሙ አባል ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊም ጭምር አኩሪ ተግባር የሚያከናውኑ የኩራት ምንጭ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ተቋማቱ ለጎረቤት ሀገራት በራቸውን ክፍት አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን ያስረዱት ሚኒስትሯ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ደስተኞች መሆናቸውን ጎብኝዎቹ እና ሌሎችም ጎረቤት ሀገራት እየነገሯቸው መሆናቸውን ገልፀዋል።  

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉአላዊነት በማስጠበቅ በከተማ ግብርና በምግብ ራስን ለመቻል እና በፀጥታው ዘርፍም ኢትዮጵያ የራሷን እና የጎረቤት ሀገራትን ሰላም ለማስፈን ጠንክራ አየሰራች መሆኗን ኢንጂነር አይሻ አስረድተዋል።

በጉብኝቱ የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እና የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

Natinael Mekonnen

07 Nov, 17:08


ኢትዮጵያ ሰሞኑን እንግዶቿን በዚህ መልኩ ተቀብላ አስተናግዳለች!

ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን

Natinael Mekonnen

05 Nov, 14:37


ዓመታዊው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሠራተኞች ቀን ተካሄደ

ኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ ሪፎርም ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እየተካሄደ ባላው የፌቤኮ የሰራተኞች ቀን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ፣ የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኮርፖሬሽኑ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ተላቆ ለሰባት ተካታታይ ዓመታት ስኬት እያስመዘገበ መቀጠሉን ገልጸው ፣ ከኮርፖሬሽኑ መንግስትና ሕዝብ ብዙ ይጠብቃሉና ሠራተኛው ላላቀ ስኬት እና ለውጥ እንዲተጋ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በተገኘው ስኬት እና ለውጥ መንግስት እና ሕዝብ ተስፋ እንዲሰንቁ ሆኗል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ለተገኘው ውጤት ለነበራቸው የላቀ አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ቀጣይ የኮርፖሬሽኑ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችል አስተማማኝ የለውጥ መሰረት የተገነባ በመሆኑ መጪው ጊዜ የኮርፖሬሽኑ የእድገትና የላቀ አገራዊ አበርክቶ የሚጎላበት ጊዜ ይሆናልም ሲሉ ነው ክቡር አቶ ረሻድ የተናገሩት ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር አቶ አባባው ዋለልኝ በዳረጉት ንግግር በኮርፖሬሽኑ አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ሠላም መስፈኑና በሰራተኛውና በአመራሩ መካከል የተግባርና የአመለካት አንድነት መኖሩ ለተቋሙ የስኬት ምንጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች በበኩላቸው ሠራተኛው ከነበረበት ተስፋ መቁረጥ ወጥቶ ተስፋ እንዲሰንቅና ኑሮው እንዲሻሻል መደረጉን አንስተው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና ማኔጅመንታቸው ሚለወጥ የማይመስለውን ድርጅት ለውጠው ሠራተኛው በተቋሙ እንዲኮራና ጥቅሙ እንዲከበር በማደረጋቸው በመድረኩ ልዩ ምስጋና አቅረበዋል፡፡

የተለወጠውንና ስኬታማውን ተቋም እያስመዘገበ ያለውን ቀጣይነት ያለው ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሠራተኛው በከፍተኛ ሞራልና የሥራ ዲስፕሊን ሥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ግዙፍ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል በራስ አቅም በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ሥራ ወደ ምርት የገባውን የኮርፖሬሽኑ ሌላ የስኬት ገጽ ማሳያ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸውም ተናግረዋል፡፡

የፌቤኮ ሠራተኞች ቀን በመደበኛነት በየዓመቱ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑን ስኬታማ አፈጻጸሞች መሰረት አድርጎ የሚካሄድ የኮርፖሬሽኑ ክብረ በዓል ነው፡፡

Natinael Mekonnen

03 Nov, 18:32


ይቅር እንላለን ግን አንረሳም።

ጥቅምት 24 በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ታትማ የምትቀመጥ አስቀያሚ ቀን ናት። ያ ለጠላት ብቻ ተዘጋጅቶ የተቀመጠ “የሰሜን እዝ ጦር” ድንበር ድንበር ሲመለከት ባልተዘጋጀበትና ባመነው ሀይል ከጀርባ የተወጋባት ጥቁር ቀን ናት። የሰሜን እዝ መከዳት ይዞት የመጣው እልቂትና ጥፋት ብዙ ነው። እንኳን ለተከዳው ለከዳውም ሀይል አልሆነም የጥቅምት 24 የጨለማ ተግባር።

አብሮ ለመኖር ስህተትን በይቅርታ መሻገር የውዴታ ግዴታ ነው። የተፈፀመውን ነገር ታሪክ ያውቀዋል። በሚዲያ ጋጋታ፥ በጩኸትና በግርግር መሸፈን አይቻልም። ይቅር እንላለን። ግን አንረሳውም። ኢትዮጵያን እስከመፍረስ ድረስ ወደቁልቁለት የሚልካት ተግባር የተፈፀመባትን ያቺን ቀን አንረሳም። ለአእላፋት ሰዎች መፈናቀል፥ ሞትና ውድመት ምክኒያት የሆነችን ጥቅምት 24 የምትባል የጥፋት ቀን አንረሳትም። እንማርባታለን። በቀጣይ ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይፈፀም ምስክር አድርገን እናቆማታለን። በዚያን ቀን በክህደት ያጣናቸውን ንፁሃን ጀግና የኢትዮጵያ ወታደሮችን እንዘክርበታለን። አዎ ጥቅምት 24ን አንረሳትም። ልንረሳትም አንችልም።

አመፅ፥ የጦር መሳሪያ አፈሙዝ አምልኮ፥ ትእቢትና ንቀት በቀላሉ የማይቆም ጥፋት እንደሚያመጡ ከዚያች ቀን በላይ ምስክር የለም። ዛሬም መሳሪያ የሚወዘውዙ ነገም ለጥፋት የተዘጋጁ ሰዎች ያቺን ቀንና ይዛ የመጣችውን ጣጣ ቆም ብለው እንዲያስታውሱ እንመክራለን።

ክብር ጥቅምት 24 ለሐገሩና ለመለዮው ሲል በክብር ለተሰዋው ጀግና የኢትዮጵያ ወታደርና በዚያ ዳፋ ላለቁ ንፁህ ኢትዮጵያውያን ይሁን።

Natinael Mekonnen

03 Nov, 11:31


ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የድሬዳዋ፣ የሀረረ፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገለጸ!

በሁርሶ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሚገኙ የድሬ ዳዋ፣ የሀረረ ፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በአካባቢዎቹ የሚገኑ ደንበኞች በኃይል ማከፋፊያ ጣቢያው ላይ የተፈጠረው ችግር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል፡፡

Natinael Mekonnen

03 Nov, 11:31


ዲሞክራቶች ትራምፕ ቆጣራው ሳይጠናቀቅ አሸንፌያለሁ ብለው ቢያውጁ የሚሰጡትን ምላሽ ማዘጋጀታቸውን ገለጹ

በ2020ው ምርጫ ትራምፕ ማሸነፋቸውን ያወጁት ምርጫ ከተጀመረ ከሰአታት በኋላ ነበር። ነገርግን በመጨረሻ በጆ ባይደን ተሸንፈዋል።
https://bit.ly/3YNj612

Natinael Mekonnen

03 Nov, 06:52


በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ‘ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ‘ ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል።

ትላንትና ለሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 ነበር የተመዘገበው ፤ የዛሬው 4.7 ነው የተመዘገበው።

Natinael Mekonnen

02 Nov, 11:18


የመምህራን ምገባ በሸገር ከተማ ተጀመረ !

በሸገር ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪና መምህራን የምግብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህ ፕሮግራም የተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥን ማስወገድ የተቻለ ሲሆን መምህራንም በማስተማር እና በመማር የበለጠ እንዲተጉ አድርጓል ተብላል።

በሸገር ከተማ በሚገኙ 256 ትምህርት ቤቶች የተማሪ እና የመምህራን ምግብ ፕሮግራም እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን ለ148,795 ተማሪዎች እና ለ3,707 መምህራን መስጠት ተችሏል።.

Natinael Mekonnen

02 Nov, 04:08


ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በአፋር ክልል ፣ ' አዋሽ ' አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

አንድ የአዋሽ ነዋሪ ፤ " የዛሬውስ በጣም ያስፈራ ነበር  " ሲል ሁኔታውን ገልጾታል።

ሌላ ነዋሪው ፥ " በጣም ነው ያስደነገጠን ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው አላህ ይጠብቀን " ብሏል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱንም ከነዋሪዎች የሚመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ  ከአዋሽ በምዕራብ በኩል 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር።

በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ጠቁሟል።

Natinael Mekonnen

01 Nov, 17:54


በተለምዶ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዉሏል‼️

በዛሬው ዕለት በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ከቀኑ 6 ሰዓት ከ35 ላይ በመኖሪያ ቤቶች ላይ አጋጥሞ የነበረዉ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

በአደጋዉ ቆሮቆር በቆርቆሮ ሆነዉ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችና ሁለት የውሀ ቦቴዎች ከ70 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርተው ነበር።

የእሳት አደጋዉ በአካባቢዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶችና ተቋማት እንደዚሁም በአቅራቢያዉ ባለ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንዳይዛመት ማድረግ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የአደጋዉ መንስኤና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን እየተጣራ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ጉዳት አለመድረሱን ኮሚሽኑ ጠቁሟል። አሁን ያለንበት የጥቅምት ወር ደረቅና ነፋሻማ አየር ያለዉ በመሆኑ ለእሳት አደጋ መከሰትና መባባስ አስተዋጾኦ ስለሚያደርግ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል።

Natinael Mekonnen

31 Oct, 17:20


አንዳንድ ኤምባሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍና በጥቁር ገበያ ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ጠ/ሚ አብይ አህመድ ገለጹ!

የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ መስራት ስራቸው የሆነ አንዳንድ ኤምባሲዎች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህን የገለጹት እየተካሄደ ባለው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበቅ ወቅት ነው።

“ነገር እንዳናበላሽ የታገስናቸው ስራቸው ግን ጥቁር ገበያ ማሯሯጥ የሆነ ኤምሲዎች አሉ” ያሉት አብይ አህመድ፤ “ጤናማ ዝምድና የማያደርግ ማንም ኤምባሲ እኛ አንፈልግም” ብለዋል።ስራቸው ይህ የሆነ ኤምባሲዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ እና የማይታረሙ ከሆነ እርምጃ እንደሚወሰድ በንግግራቸው አመላክተዋል።

በኩባንያ ስም፣ በፍራንኮ ቫሎታ ስም፣ በወርቅ ንግድ ስም የኢትዮጵያን ገበያ የሚያዛቡ ገለሰቦች መኖራቸውንም አክለው ተናግረዋል።የኢትዮጵያ የጥቁር ገበያ ዶላርና ወርቅ በባቡር እና በተሽከርካሪ ከአገር እንደሚወጣ የገለጹት ጠ/ሚንስትሩ ይህን ዘረፋ መከላከል ያስፈልጋል ሲሉ አክለዋል።አንዳንድ ሀገራት በዚህ መንገድ ኢትዮጵያን መዝረፍ መብት እንደሆነ እንደሚያስቡ ገልጸው ነገር ግን ኢትዮጵያ ከብሄራዊ ጥቅሟ አንጻር ጥያቄ ስታነሳ እንደ “ግስላ” ይሆናሉ ብለዋል።

Natinael Mekonnen

31 Oct, 17:20


አማራ ክልልን ወደ ቀደመ ሰላሙ ለመመለስ ተቋማት የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

በአማራ ክልል የተከሰተውን የሰላም መደፍረስ ወደነበረበት ለመመለስ የክልሉ ተቋማትና የሥራ ሃላፊዎች የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡

“ሠላም ለሁሉም፣ሁሉም ለሠላም” በሚል መሪ ሃሳብ ከክልሉ ተቋማት ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር የሠላም ኮንፈረንስ በባሕርዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል፡፡

በኮንፈረሱ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና ርዕዮት ዓለም ዘርፍ ሃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር)÷የሠላም ትርጉሙ የሚታወቀው ሠላም ሲደፈርስ መሆኑን በመጥቀስ ይህንንም በክልሉ ባለፈው አንድ ዓመት በተግባር አይተነዋል ብለዋል፡፡

ሠላም ለሰው ልጆች ፍላጎት መሻት ዋስትና በመሆኑ ከምንተነፍሰው አየር ባልተናነሰ ሁኔታ ከፍ ያለ ዋጋ አለው ነው ያሉት፡፡

ግጭት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና፣ በማህበራዊ መስኮች እጅግ አደገኛ ጥፋትን ያስከትላል፤ ግጭት ሰውና ሀብትን ከማውደሙ በተጨማሪ በትውልዶች መካከል ከፍተኛ ክፍተትን ይፈጥራል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ ካለው የግጭት አዙሪት ለመውጣት በክልሉ ዘርፈ ብዙ ስራ ሲከናወን መቆየቱን ገልጸው÷ በሁሉም ቦታዎች ውጤታማ ስራ መመዝገቡን አንስተዋል፡፡

የሰላም ኮንፈረንሱ በክልል ደረጃ መካሄዱ ዋና አላማ በባለፈው ዓመት የመጣንባቸውን ምዕራፎች በጥልቀት በመገምገም ሰላምን በክልሉ የማረጋገጥ ስራ በማጠናከር ሚናችንን እንደየሃላፊነታችን ለመወጣት ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ የባሕርዳሩን መድረክ ጨምሮ 41 የሰላም ኮንፈረስ መድረኮች እንደሚካሄዱ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Natinael Mekonnen

27 Oct, 17:22


የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ከክፍለጦሮች የተውጣጡ የመሀንዲስ ሙያተኞችን አሰልጥኖ አስመረቀ።

በምረቃው በክብር እንግድነት የተገኙት የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሀይል አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ ረጋሳ ተመራቂ ሙያተኞች እንደ ሠራዊት አስቸጋሪና  ውስብስብ ግዳጆች ሊያጋጥሟቸው እንደሚችሉ አውቀው በወሰዱት ስልጠና መሰረት መሥራት መምራትና ሀላፊነት መወሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሀይል የመሀንዲስ ሀላፊ ምክትል መቶ አለቃ ኦስማን ቃሲም በበኩላቸው ለሠልጣኞች  አጠቃላይ የመሃንዲሳዊ ሙያን መሠረት በማድረግ በገለፃና በተግባር ሥልጠና መሠጠቱን ገልፀው ሠልጣኞች ሙያዊ አቅማቸውን ለማሣደግ ሥልጠናውን በትኩረት መከታተላቸውን አሥረድተዋል።

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የሠራዊት አባላት በየትኛውም መልክዓ ምድር የሚሠጣቸውን ተልዕኮ በድል እየፈፀሙ ሲሆን በተለይም ደግሞ ፅንፈኛውን ቡድን እና ሽብርተኛውን ሸኔ በመደምሰስ የሀገራችንን የሠላም እና የልማት ጉዞ በማሳለጡ ረገድ ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ዘገባው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

Natinael Mekonnen

27 Oct, 17:22


ፅንፈኛው ለጥፋት ተልዕኮ ያዘጋጀው የጦር መሳሪያ በኮማንዶ ክፍለ ጦር ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ፅንፈኛው ቡድን በከተማው መሃል የሽብር ስራ ለመስራት ያዘጋጃቸውን በርካታ የጦር መሳሪያዎች ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ሠለሞን ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን ለእኩይ አላማው ለማዋል መሳሪያ በከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት ደብቆ መገኘቱን ገልፀው ይህ ቡድን የህዝብን ሠላም ላማወክ ያሠበው ሙከራ በሠራዊቱና በክልሉ የፀጥታ ሀይል ቅንጅት መክሸፉንም ነው የገለፁት።

ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተወሰደው እርምጃም ክላሽ ፤ ኋላ ቀር መሳሪያ፤ ሽጉጥ፤ የሞርተር ቅንቡላ ፤ የእጅ ቦንብ ፤ የክላሽ ጥይት ፤ የሽጉጥ ጥይት፤ የመትረይስ ጥይትና የወገብ ትጥቅ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ከፀጥታ አካላት ጋር በመስራት ፅንፈኛውን የመደምሰስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት አዛዡ ህዝቡ ያለ ስጋት እና ያለተኩስ ድምፅ በሰላም ወጥቶ የሚገባበትን ሁኔታ በመፍጠር ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

Natinael Mekonnen

27 Oct, 17:22


ታጣቂዎች በይቅርታ ወደ መንግስት እየገቡ ነው።

በሊቦ ከምከም ወረዳ አግድ ቅርኛ ቀበሌዎች አካባቢ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 15 አባላት በተደረገው የህዝብ ግንኙነት ስራ በ17/2/2017 ዓ/ም ወደ ወረዳው በይቅርታ መግባታቸውን የሊቦ ከምከም ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ ፶/ አለቃ ንጉሴ በየነ ተናግረዋል።

ኃላፊው በወረዳው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች በትጥቅ ትግል የሚፈታ ችግር እንደማይኖር በመረዳት ሌሎች ኃይሎችም ለህዝብ ሰላምና ልማት ሲሉ ወደመንግስት እንዲመጡና በምክክር ሀገር መገንባት እንደሚቻል በመግለፅ ጥሪ አቅርበዋል። አሁን ሰላም ይሻለናል ብለው የመጡ ታጣቂዎችም ከመንግስት ሙሉ ይቅርታና ከለላ አግኝተዋል ብለዋል። በቀጣይ የተሀድሶ ስልጠና ወስደው ወደማህበረሰቡ ከነትጥቃቸው ይቀላቀላሉ ሲሉ አስረድተዋል።

የታጣቂዎች መሪ አቶ አግማስ መኳንንት እንደተናገረው ትግሉ የእውነት ሀገር የሚለውጥ መስሎን ነበር።

አሁን ስህተታችንን በመገንዘብ ወደ ልማታችን ለመመለስና የበደልነውን ማህበረሰብ በልማት ለመካስ አስበን የመንግስትን ጥሪ ተቀብለን መተናል።

ሌሎችም እኛን በማየት ይቅርታውን እንዲቀበሉ ጥሪየን አስተላልፋለሁ ብሏል።

Natinael Mekonnen

24 Oct, 15:52


በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነታችን እያደገ ቀጥሏል። ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል።

My appreciation to President Vladimir Putin for our in-depth discussions during our bilateral meeting. Anchored in our historic ties, the bilateral relations between our two countries continues to grow. In addition, our common BRICS platform allows us to engage for broader economic cooperation.

Natinael Mekonnen

24 Oct, 09:59


የኢትዮጵያ የትምሕርት ሚኒስትር እና የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ከሉዓላዊ ሚዲያ ጋር- ሰሞኑን ይጠብቁን

Natinael Mekonnen

23 Oct, 19:02


ዛሬ ጠዋት ከኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጌያለሁ። በውይታችን ወቅት ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበት ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ገልጫለሁ።

Har'a ganama Pirezdaantii Iran Massuud Pezeshikyan waliin dhimmoota garlameefi nannawaa ilaallatan irratti marii'anneerra. Marii keenyaanis Itoophiyaan Giddugala Bahaatti haala muddiinsi jiru gadi bu'u danda'u irratti deeggarsa gochuuf qophee ta'uushee ibseera.

This morning I met with Iranian President Masoud Pezeshkian for a discussion on bilateral and regional issues. During our meetings I expressed that Ethiopia stands ready to support de-escalate tensions in the Middle East.

Natinael Mekonnen

23 Oct, 19:02


በብሪክስ ጉባኤ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር መልካም እድል አግኝተናል።

During the BRICS Summit I also had the opportunity to meet with South African President Cyril Ramaphosa. A good opportunity to reconnect and discuss bilateral and regional issues.

Natinael Mekonnen

22 Oct, 16:24


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በፒያሳ መልሶ ማልማት አካል የሆኑ ዘመናዊ የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤት በ6 ወራት ለመገንባት ከኦቪድ ግሩፕ ጋር ተስማማ

የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል በሆነው በ9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ግዙፍ የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤት በ6 ወራት በሆነ ጊዜ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል ።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሽን ዋና ሥራ አሰፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና የአቪድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ ስምምንቱን ፈርመዋል ።

በስምምነቱ የወርቅ ቤቶች የንግድ ሱቅ ሞል ( FHC Gold Plaza ) ፣ መዝቦልድ ሞል እና ጣይቱ የመኖሪያ አፓርትመንት በአልሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ ለ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ወደ አገልግሎት ለማስገባት የሚያስችል ነው፡ ፡

ግንባታውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁም ተገልጿል።

የአዲሲቷ ፒያሳ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ጉልህ አስተዋጽዖ ያላቸው የንግድ ሞሎችና ኘላዛዎች በአጭር ጊዜ ተገንብተው ለአገልግሎት እንደሚበቁ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በዚሁ ወቅት ተናግረዋል ።

በተጨማሪም ዘመናዊ የመኖሪያ ቤትም በዚሁ ስፍራ እንደሚገነባ ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልፀዋል።

ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር የዘረጋ በመሆኑ የሳይቶቹን ግንባታ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚያስችለውም ተናግረዋል።

በኮርፖሬሽኑ ታሪክም በብዛት እና በዘመናዊነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገነባ የመጀመሪያው የንግድ ሞሎችና ፕላዛ ግንብታ ፕሮጀክት እንደሆነም ክቡር ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል።

የአቪድ ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ከኮፖሬሽኑ ጋር በመሆን በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ገንብተው ማጠናቀቃቸውን አሰታወሰው ፣ ውለታ የገቡትን የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤቶችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ አቪድ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል።

ሳይቶችን በ6 ወራት ለማጠናቀቅ የሚያስችለው የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂም ለግንባታ ዝግጁ ማድረጋቸውንም አቶ ዮናስ ታደሰ አስተውቀዋል፡፡

ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ምቹ እንደሆነም ገልፀዋል።

ሞሎቹ እና የመኖሪያ ቤቶቹ የሚገነቡት በፒያሳ መልሶ ማልማት ለልማት ዝግጁ በሆኑት የኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች ላይ ነው፡ ፡

Natinael Mekonnen

22 Oct, 16:24


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር በካዛን ራሺያ ገብተዋል

Natinael Mekonnen

22 Oct, 16:24


በአዲስ አበባ ከተማ 14 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ ቀረበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 14 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ አቀረበ፡፡

የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

መግለጫውን የሰጡት በቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍና የሊዝ ክትትል ዳይሬክተር ጫሊ አብርሀም÷ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታው የቀረቡ መሬቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ አራተኛው ዙር ሲሆን÷ በዚህኛው ዙር ብቻ አጠቃላይ የቀረበው 143 ሺህ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ነው ተብሏል።

ይህም በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው መሆኑ ተመላክቷል።

Natinael Mekonnen

19 Oct, 15:28


የመቶ ተራራ ተስፈኞች

መቶ ተራራ በሌለበት ቦታ "ዘመቻ መቶ ተራራ" ብሎ የተነሳው ፅንፈኛ መቶ ቦታ ተበታትኗል። ብዙሃኑ ለመከላከያ በክብር እጅ እየሰጠ ነው። አንዳንዱ ከገበሬ ቀምቶ የታጠቀውን መሳሪያ ሸጦ በሊቢያ ተሰዷል። ገሚሱ በሩጫ ጎረቤት ሐገር ገብቷል። አሁን በየጉራንጉሩ እንደአሜባ የተበጣጠሰ ፅንፈኛና ጥቂት አመራሮቹ ብቻ ቀርተዋል። ባጭሩ የዘመቻ መቶ ተራራው ጉዳይ ዘማቹም ተራራውም የለም ነው ምላችሁ። ይልቅ ህዝቡ መከላከያን ሲያይ "እንኳን ከነዚህ መናጢዎች ገላገላችሁን" እያለ ነው።

የዘመቻ መቶ ተራራ አቀንቃኞች አማርኛ ከማሳመር ውጪ ይሄ ነው የሚባል የውጊያ ሳይንስ አያውቁም። ጩኸታቸው ግን ጆሮ ያደነቁራል። ባቄላ የምታህል እንቁራሪት ሙሉ ሰፈሩን እንደምትረብሽ ሁሉ እነዚህም ቲክቶኩንና ፌስቡኩን በጩኸት ይረብሹታል።

ደግሞ የስማቸው ብዛት። አምስት ወይም አስር ሆነው "የሳተናው ተራራው ብርጌድ" ብለው ራሳቸውን ይሰይሙና "ብርጌድ ነን ብለናል ብርጌድ ነን" ይላሉ። ከዛ ከመሀላቸው ወፈር ያለውን አንዱን ወጠምሻ "ሻለቃ እገሌ ወይም ኮማንዶ እገሌ" ብለው ይሰይማሉ። ሰውየውኮ ሰርግ ላይ ከመተኮስ ውጪ ጦርነት ሚባል ተሳትፎ አያውቅም። /አንድ ቦታ እንደውም ሻለቃ ነኝ የሚል የብርጌዱ መሪ ሲማረክ የቀድሞ ስራው የቤት ሰራተኛ ደላላ ሆኖ ተገኝቷል 😄/ አብዛኞቹ የጨረቃ ብርጌድ የሚያቋቁሙት ሽፍቶች ቀን ሰብሰብ ብለው ሲቅሙ ይውሉና ወደማታ ወጣ ብለው ሶስት ጥይት ተኩሰው ይሮጣሉ። እንዲህ አይነቶቹ ናቸው በየሚዲያው የቦሊውድ ፊልምን በሚያስንቅ የውጊያ ገድል ሲያስተርኩ የሚውሉትና በትግል ስም የአረብ ሐገር እህቶቻችንን መቀነት የሚያራቁቱት።

ፅንፈኛው በውሸት ተፀንሶ፥ በውሸት ተረግዞ፥ በውሸት የተወለደ የተረት ተረት ነፃ አውጪ ነው። ድራማው አያልቅም። ተከታዮቻቸውም "እንዴት?" ብለው አይጠይቁም።
"ሸዋ ላይ ብቻ ሃያ ክፍለጦር አለን" ሲሉት ተከታዩ አንድ ክፍለ ጦር ቁጥሩ ስንት ነው? ይህን ሁሉ ጦር ምን ያበሉታል? ይህ ሁሉ ጦር ካለ እንዴት አንዲት ቀበሌ መያዝ ተሳናቸው? ብሎ አይጠይቅም። አንዱ ተነስቶ "ኮረኔል ነኝ፣ ሻለቃ ነኝ" ሲል ማእረጉን ኬት እንዳገኘው አይጠይቅም ፋኖን ሲቀላቀል አስር አለቃ ሆኖ በአመቱ ኮረኔል የሆነ የጃዊሳው መሪ ሁሉ አለ። በአንድ አመት ብቻ ከአስር አለቅነት ወደኮረኔልነት የሚያድግ ተአምረኛ ታጋይ ፅንፈኛው ሀይል ውስጥ ብቻ ነው ምታገኙት 😄

አሁን አሁንማ የአለም ሚዲያዎች ራሱ ፅንፈኛውን seriously እየወሰዱት አይደለም። ባለፈው እስክንድር ነጋ ከBBC ጋር ኢንተርቪው ሲያደርግ "ትንሽ ታገሱን አንድ እስክንሆን" ብሎ አስገርሟቸው ነበር። ቃለመጠይቅ ለመስጠት ቢቢሲን "አንድ እስክንሆን ጠብቁን" ያለ ነፃ አውጪ በ BBC ታሪክ አጋጥሞ አያውቅም። አንድ ሳይሆን አንድን ትልቅ ሰራዊት ለማሸነፍ ማሰብ ታይቶ የማይታወቅ እብደት ነው።

ሃሳዊው ነፃ አውጪ ከሌላው አለም ላይ ከታየ ታጣቂ የሚለየው በዚህ ብቻ አይደለም። የትግል ማኒፌስቶ ሳይፅፍ ትግል የጀመረ የመጀመሪያው ስብስብ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ዙፋን በሌለበት ለጫካ ንግስና እርስ በርስ መታኮሱ ደጋፊዎቹን ሳይቀር ግራ ያጋባ ብቻ ሳይሆን ውስጡ ምን ያህል በነዋይና በስልጣን ጥም የተቃጠሉ ዱርዬዎችን እንዳቀፈ ያሳያል።

ፅንፈኞቹ የአማራን ህዝብ ለማቆርቆዝ በጠላት ሃሳብ አመንጪነት የተደራጁ "እርግማኖች" እንደሆኑ ያደባባይ እውነት እየሆነ ነው። ነገረ ስራቸውም የአዋቂዎች እቃቃ ጫዎታ ከሆነ ቆይቷል። በአለም ላይ ፌሮ በይደው ታንክ ለመስራት የሞከሩ ነፃ አውጪዎች የኛው ጉዶች ብቻ ናቸው። የያዙት አንድ ቀበሌ ሳይኖር የዳቦ ቤት ቱታ አድርገው "በከፍተኛ ቴክኖሎጂ መሳሪያ እያመረትን ነው" ብለው መግለጫ የሰጡ የኛው ጉዶች ናቸው። ባህር በሌላት ሐገር "አብይን ስናሳድደው በባህር ሰርጓጅ መርከብ አመለጠን" ያለው የዚሁ የፅንፈኛው ቃል አቀባይ ነበር።

ነገር ግን ፅንፈኛው የመሀይም ጥርቅም ብቻ አይደለም። የወንጀለኛና የእብድ መከማቻም ጭምር እንጂ። ከእስር ቤት በተለያየ ወንጀል ተፈርዶባቸው ቆይተው ከእስር ያመለጡ ሴት ደፋሪዎችና ነፍሰገዳዮች ሁሉ የፋኖ አመራር ሆነው አይተናቸዋል። በአእምሮ መታወክ ጠበል ሲጠመቁ የነበሩ ሁሉ ቡድኑን ፋኖ ነኝ እያሉ መቀላቀላቸውን ሰምተናል። ለዚህ ነው ከዚህ የዱርዬ ስብስብ ህዝባችንን ነፃ የማውጣቱን ግዴታ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በሚገባ እየተወጣ ነው።

እስከቅርብ ግዜ ድረስ ሰፊ የይቅርታ እድል ተሰጥቶ ባለማወቅ ይህን የወንጀለኛ ስብስብ የተቀላቀሉትን ወጣቶች ነፍስ ለማዳን ተሞክሯል። ከዚህ በላይ ግን የትኛውም የአመፅ አንጃ ህዝባችንን ማህበራዊ እረፍት መንሳት ስለሌለበት መከላከያ ሰራዊታችን ክንዱን ጠንከር አድርጎ ማሳረፍ ጀምሯል። ገና በመጀመሪያው ምት የፅንፈኛው አመራሮች መንጋዎቻቸውን ጥለው ኮብልለዋል። አንዳንዶቹም ወደላይ ቤት ተሸኝተዋል። የነሱ አጋፋሪዎችም ዋይታ ላይ ናቸው። ፋኖ አራት ኪሎ ሲገባ የሚይዘውን ስልጣን ተመዳድቦ ጨርሶ ሱፍና ከረባት ተኩሶ ሲጠባበቅ የነበረው ተስፈኛም ሙሾ እያወረደ ነው። ማህበረሰባችንም የሰላም አየር መተንፈስን ጀምሯል።

ክብር ለታላቁ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት!

Natinael Mekonnen

19 Oct, 15:28


በሶማሌ ክልል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም በተንቀሳቀሱ 60 የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባላት ላይ እስከ ዕድሜ ልክ የፍርድ ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

በሀገራችን ሶማሌ ክልል አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 60 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለው በ10 የምርመራ መዝገብ ተከሰው እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በ60 የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ በቂ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃ በማቅረብ በሽብር ወንጀል ምርመራ አጣርቶ ለፍትህ ሚኒስቴር በመላክ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ተዘዋዋሪ ችሎት ሁለት የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በዕድሜ ልክ እስራት፣ 56 ተከሳሾች እንደወንጀል ተሳትፎአቸው ከ6 ዓመት እስከ 18 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአልሸባብ የሽብር ቡድን አባልነት የተከሰሱ ሁለት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲፈረድባቸው ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡፡

በዚያን ወቅት በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአልሸባብ የሽብር ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ቤዝ ለመመስረት፤ ከአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ወጣቶችን በመመልመል፤ በሶማሊያ ሀገር ወታደራዊ ስልጠና ወስደው የጦር መሣሪያ ሳይታጠቁ ሰላማዊ ሰው መስለው ወደ ሀገራችን እንዲገቡ በማድረግ፣ ለሽብር ቡድኑ በመሰለል፣ ፈንጂ በማፈንዳት ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም አካባቢዎችን የሚቆጣጠር ኃይል ለማዘጋጀት ሲንቀሳቀስ እንደነበር የምርመራ ቡድኑ ባካሄደው ማጣራት ደርሶበታል፡፡

የሽብር ቡድኑ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከሶማሊያ ሀገር በሰባት ተሸከርካሪና በአራት ሞተር ሳይክል በሌሊት ወደ ሀገራችን ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ሁሉል አካባቢ ሲደርስ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ከአራት ቀን እልህ አስጨራሽ ውጊያ በኋላ በርካታ የሽብር ቡድኑን አባላት በመደምሰስ ሁለት ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ 92 የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችን በመማረክ 406 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ67 ሳጥን መሰል ጥይቶች፣ 43 ላውንቸር እና 27 ብሬን ከአንድ ሳጥን መሰል ጥይት ጋር እንዲሁም በርካታ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን በኤግዚቢትነት መያዛቸውን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በስድስት የምርመራ መዝገብ 95 ተጠርጣሪዎች በሽብር ወንጀል ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ክርክር ላይ እንደሚገኝ ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Natinael Mekonnen

19 Oct, 15:28


ይኸው ነው
Kanumaa

Natinael Mekonnen

19 Oct, 15:28


" መዋጋት ርስት አይደለም። ለ42 ዓመታት በውግያ ቆይቻለሁ። እኔ እጣ ፈንታዬ መዋጋት ነው ብዬ አላምን ፤ አቋሜ ውግያ አያስፈልግም ይቁም የሚል ነበር ፤ አሁንም አቋሜ ያው ነው የተለወጠ የለም !! " - ጄነራል ሳሞራ የኑስ

ከሰሞኑን የቀድሞው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሳሞራ የኑስ አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር።

ከረጅም ጊዜ በኃላ ወደ ሚዲያ ቀርበው ቃላቸውን የሰጡት ብራኸ (ከፍታ) ለተሰኘ በዩትዩብ ላይ ለሚተላለፍ ፕሮግራም ነው።

ምን አሉ ?

የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከመተካታቸው በፊት በእሳቸው (ጄነራል ሳሞራ) እና በአገር ድህንነት ሃላፊ በነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ መካከል አለመጣጣም እንደነበር በዚህም ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር እያሉ እንዲያስሯቸው ሲጠይቋቸው " አላስርም ! " ማለታቸውን አንሰተዋል።

ጄነራል ሳሞራ የኑስ ፥

" ያኔ ዐብይን እሰረው ተብዬ አይሆንም ካልኩኝ ዛሬም ልክ ነኝ። ምክንያቱ እኔ የሰራዊት መሪ እንጂ የሲቪል ፓለቲከኛ አሳሪና መሃሪ አይደለሁም።

መከላከያ ሲቪል ፓለቲከኛ የማሰር ስልጣንና ልኡክ የለውም።

ዐብይ ያኔ የአንድ ታላቅ ክልልና ህዝብ አመራር ነበር። ታላቁ ህዝብ ማለት ኦሮሞ ነው። ያኔ የኦሮሞ ህዝብ መሪ የፓለቲካ ድርጅት የነበረው ኦህዴድ ነው። የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አብይ ነበር። በተጨማሪም የፓርላማ የህዝብ ተመራጭ አባል ነበር።

ዐብይ ያኔ መታሰር ከነበረበት ጥንካሬና ድክመቱ ወደ ሳራሞራ ሳይሆን ወደ ፓርለማ ነው የሚወሰደው።

ከፓርላማ ካለፈ ወደ ያኔው የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይቀርባል።

የኢህአዴግ ሊቀመንበሩና ጠ/ ሚንስትሩ የዐብይ ድክመት ልክ ነው ብሎ ካመነበት ከፓርላማ ሃላፊነቱ ማንሳት አለበት።

እንዲህ ሆኖ ራሱ ሃይለማርያም ደሳለኝ ዐብይን የማሰር ስልጣን ስለሌለው ወደ ኦህዴድ መላክ አለበት።

ኦህዴድ ካመነበት ደግሞ ይታሰር ብሎ ከወሰነ የሚመለከተው የህግ አካል እንጂ ሳሞራ ዐብይን የማሰር ስልጣን የለውም " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

- በትግራዩ ጦርነት በትግራይ ህዝብ ላይ እልቂት መፈጸሙን እንደሚያምኑ፤

- የትግራዩ ጦርነት መንስኤ የፓለቲካ ብልሽት ፤ የአመራሮች መበስበስና ከህዝብ አገልጋላይነት መውጣት ውጤት እነደሆነ፤ የአማራ ኤሊቶች የትግራዩ ጦርነት አንዲጋጋል ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ በርካታ እላፊ ነገሮች እንደተናገሩ፤

- የትግራዩ ጦርነት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የተወጣጡ ወታደሮች የተሳተፉበት ቢሆንም የሁሉም ክልሎች ህዝብ ደግፎታል ተሳትፎበታል ማለት እንዳልሆነ፤

- በትግራይ ጦርነት የሻዕብያ ሃይል አጋጣሚው በመጠቀም የትግራይን ህዝብ ያለ ስሙ ስም በመስጠት አንገቱ ለማስደፋትና ለማጥፋት እንደዘመተ፤

- ከጦርነቱ በፊት ከምርጫው ጋር ተያይዞ የነበሩት የእልህ አገላለጾችና አካሄድ እንዲቆሙ በሁለቱም በኩል ሲገስጹ እንደነበር፤

- ጦርነቱ እንዳነሳ ፤ ከዛም እንዲቆም ብዙ ጥረት እንዳደረጉ፤

- " ጄነራል ሳሞራ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ወግነው በድብቅ ጦርነት መርተዋል / ተሳትፈዋል " የሚለው ወሬ ጦርነቱ የከበዳቸው የትግራይ ፓለቲከኞች ለድክመታቸው መሸፈኛ የፈጠሩት እንደሆነ ፤ ጦርነቱ ሲጀመርም ሆነ ሲፋፋም ከቤተሰቦቻቸእ ጋር አዲስ አበባ እንደነበሩ፤

- መዋጋት ርስት እንዳልሆነ ፤ ለ42 ዓመታት በውግያ እንደቆዩ ፤ እኔ እጣ ፈንታቸው ውግያ ነው ብለው እንደማያምኑ ፤ አቋማቸው ውግያ አያስፈልግም የሚል እንደሆነ ፤ አሁንም ድረስ አቋማቸው ያው እንደሆነ፤

- ያልተዘጋጁበትን፣ ያላመኑበትን ወግያ እንደማይሳተፉ፣ እንደማይዋጉ፤

- እምነታቸው የትግራይ ህዝብ መዋጋት የለበትም የሚል እንደሆነ ፤ እንደ አመራር ህዝቡ ወደ ውግያ መግፋት የለበትም የሚል እንደሆነ ፤

- ውግያ ሲጀመር አከባቢ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ እና አቶ ግርማ ብሩን አግኝተው ውግያ እንዳይጀመር እንደጠየቁ ፤ እነሱም እንደ አመራር የሰጧቸው መልስ እንዳለ፤

- ጦርነቱ በተጀመረ ማግስት መንግስትንና ጀነራሎቹን ጦርነቱ እንዲቆም እንደጠየቁ ፤ እስከ መጨረሻ ድረስም ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ ጥረት እንዳደረጉ፤

- የትግራይ ህዝብ ሃያ ዓመት እየቆጠረ መዋጋት እንደሌለበት ፤ ጦርነትም እንደሰለቸው፤ የሰላም አርአያ መሆን እንደሚፈልግ ፤ ፓለቲከኞችም የህዝበ ሰላም መጠበቅ እንዳለባቸው፤

.... የሚሉና ሌሎችንም ጉዳዮች አንስተዋል።

የጄነራሉ አቋም የአሁን ወይስ የነበረ ?

የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ጄነራል ሳሞራ የኑስን ከ5 ዓመታት በፊት በ2012 ዓ.ም ህዳር እና ታህሳስ ወር ላይ እንዲሁም ጦርነቱ ተጀምሮ የፌደራል መንግስት መቐለ በተቆጣጠረበት ወቅት የካቲት 2013 ዓ.ም በአካልና በስልክ አግኝቶዋቸው ሃሳባቸውን ሰጥተው ነበር።

ጀነራል ሳሞራ ሀገራዊ ኒሻን ተሸልመው በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል አግኝቶ ባናገራቸው ወቅት ፥ በዚህም በዚያም በወጣቶች የሚታይ የነበረው የጦረኝነት ስሜት ፓለቲከኞቹ በማርገብ ሃላፊነታቸው እንዲወጡ ወታደራዊ ምክር ሰጥተው ነበር።

ጥር 2012 ዓ/ም ደጀና ላይ 45ኛው የህወሓት የምስረታ በዓል ለማክበር ለተሰባሰቡት ወጣቶች ባሰሙት ንግግር ፥ ወጣቶች ከዚህም ከዚያም ያሉ ፓለቲከኞች በሚለኩሱት ጦርነት ገብተው እንዳይቃጠሉ የሚያስገነዝብ አባታዊና ወታደራዊ ምክር አስተላልፈው ነበር።

ጦርነቱ ከተጀመረ እና ከተባባሰ በኃላ በሰጡትም አስተያየት ጦርነትን ከበፊቱ የባሰ እንደተጠየፉት ገልፀውለት ነበር።

ያንብቡ👇
https://teletype.in/@tikvahethiopia/lTm24ja5TwM

Natinael Mekonnen

18 Oct, 16:16


አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ በአማራና ትግራይ ክልሎች ያሉት ወቅታዊ ኹኔታዎች ሥራዬን ባግባቡ እንዳላከናውን እንቅፋት ኾነውብኛል ማለቱን ዶቸቨለ ዘግቧል።

ኮሚሽኑ፣ በአማራ ክልል አንጻራዊ ጸጥታ በሠፈነባቸው ወረዳዎች ተባባሪ አካላት የአጀንዳ መረጣ ተሳታፊዎችን ለመምረጥ ሙከራ ማድረጋቸውን መግለጡን ዘገባው አመልክቷል።

ኾኖም የኮሚሽኑ አሰልጣኞችና ተባባሪ አካላት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዳልቻሉ የጠቀሰው ኮሚሽኑ፣ አማራ ክልል በሂደቱ ሳይካተት አገራዊ የምክክር ጉባዔ ማካሄድ አስቸጋሪ መኾኑን ገልጧል ተብሏል።

Natinael Mekonnen

18 Oct, 16:16


“የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መስክ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች ለአህጉሪቱ የሚተርፉ ናቸው” - የአፍሪካ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች እና ወታደራዊ አታሼዎች

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና ወታደራዊ አታሼዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ እየሰራቸው ስላሉ ስራዎች ለሚኒስትሮቹ እና ወታደራዊ አታሼዎቹ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በገለፃቸው ኢንስቲትዩቱ በአፍሪካ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የልቀት ማዕከል ለመሆን የሰነቀውን ግብ ማሳካት የሚያስችሉት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሮች እና ወታደራዊ አታሼዎቹ ተቋሙ እየሰራቸው ባሉ ስራዎች መደነቃቸውን ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል፡፡

ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርህ በማሳካት ይህ ተቋም ረጅም ተጉዟል ያሉት ጎብኚዎቹ ይህንን ለውጥ በሁሉም የቀጠናው ሀገራት ማስፋትና ማሳደግ እደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ያላትን ተሞክሮ ለሌሎች ሃገራት በማካፈል የጀመረችዉን የመሪነት ሚና እንድታጠናክርም ጠይቀዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም ከእድሜው በላይ ብዙ እንደተጓዘ ገልፀዋል፡፡

አንድነቷ የተጠበቀ አፍሪካን ለመገንባት ቴክኖሎጂን መጠቀም የግድ ነው ያሉት ሚንስትሯ በፍጥነት እያደገ ያለውን ሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለመጠቀም በአህጉሪቷ ያለውን እምቅ አቅም ማውጣትና ተባብሮ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Natinael Mekonnen

18 Oct, 16:16


ቲክቶክማ አጨልሎናል

ከስር የምታይዋት አሜሪካዊት ቲክቶከር መንገድ ላይ እየተጓዘች አንድ ካፌ በር ላይ የተሰቀለ ባንዲራ ትመለከትና በብስጭት ትሞላለች። ተበሳጭታ ብታልፍ ጥሩ ነበር ስልኳን በማውጣት እንደጆን ዳንኤል የቲክቶክ ላይቭ በመግባት ራሷን እየቀረፀች ካፌው በር ላይ የተሰቀለውን ባንዲራ መበጣጠስ ጀመረች። በዚህም አልበቃትም እህታችን Free palestine እያለች መጮህ ጀመረች።

በሁኔታው ግራ የገባቸው የካፌዋ ሰራተኞች ወጥተው ሊያረጋጓት ሞከሩ። ነገር ግን ልጂቱ የሀበሻ ደም ሳይኖርባት አልቀረም መሰል "እንዴት የጄኖሳይደሯን የእስራኤልን ባንዲራ በራችሁ ላይ ታንጠለጥላላችሁ" እያለች ቀወጠችው።
የዚህ ግዜ ነው አለምን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት የሚያስቅ ቀልድ የተፈጠረው።

የካፌው ሰራተኛ የበጣጠሰችውን የሐገሩን ባንዲራ ከእጇ እየነጠቀ "ሴትዮ ስለምን እስራኤል ነው የምታወሪው ይሄ የሐገሬ የግሪክ ባንዲራ ነው" ብሎ መለሰላት። 😂

Natinael Mekonnen

18 Oct, 16:16


አሁን ያለው ትውልድ በትብብር መወሰን ያለበት አንድ ነገር ቢኖር ልጆቻችን ላይ አብዝተን በመስራት የድህነት መጠሪያችንን በልጆቻችን መበቀል እንዳለብን ነው።

ጠሚ ዶር አቢይ አህመድ

Natinael Mekonnen

18 Oct, 16:16


መልካም የስራ ዘመን ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል:-

1. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ - የቱርዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር

2. ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር

3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ- የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር

Natinael Mekonnen

17 Oct, 19:03


የባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ በሁለት ዓመት ቀድሞ እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 07 ቀን 2017 ዓ.ም

በግንባታ ላይ የሚገኘውን የባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ከተያዘለት ጊዜ በሁለት ዓመት ቀድሞ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አሥኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል ኢንጂነር በቀለ መለሰ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ጃንሜዳ አካባቢ በመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ በግንባታ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ጠቅላል መምሪያ በ8 ወራት ውስጥ ብቻ 37 ከመቶ መድረሱን የገለፁት የፕሮጀክት ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ኢንጂነር በቀለ መለሰ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተወሰዱ ተሞክሮዎች የአመራሩ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የፕሮጀክቱ ሰራተኞች ካላቸው ቁርጠኝነት አንጻር ሲገመገም ለግንባታው ከተያዘለት ጊዜ በሁለት ዓመት ቀድሞ ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡

ባህር ኃይል በተቋም ደረጃ በተከናወነው ሪፎርም ዳግም የተቋቋመ መሆኑን ያወሱት ኃላፊው የመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያም ትኩረት በመስጠት እያደረገ ባለው ድጋፍና ክትትል ግንባታው 24 ሰዓት እየተከናወነ ነው፡፡ የባህር ኃይል አመራሮችም በየጊዜው ሒደቱን በመከታተልና ሰራተኛውን በማበረታታት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የስራ ቢሮዎችን የህክምና አገልግሎት መስጫ ክሊኒኮችና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መገልገያዎችን ያሟላው ባለ አራት ወለል ህንፃ ከስሩ የተሸከርካሪዎች ማቆሚያንም ያካተተ ነው፡፡

የባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ግንባታ በጥራትና በፍጠነቱ ለሌሎች በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የገለፁት ደግሞ  የግንባታው ተቆጣጣሪ ኮሎኔል ኢንጂነር ተስፋዬ እሸቱ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ የግንባታ ግብዓት ጥራት በቤተሙከራዎች መመዘኛ መሰረት የሚረጋገጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከ250 በላይ ሲቪል ሰራተኞች በተለያየ የሙያ ዘርፍ በዚህ ፕሮጀክት ላይ የተሰማሩ ሲሆን በቂ ትራንሰፖርትና ሌሎች አቅርቦቶችን በማመቻቸት ረገድ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሎጀስቲክስ አስተባባሪ ሌተናል ኮሎኔል ወርቁ አበራ ገልፀዋል፡፡ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ቀድሞ በመለየትና በጊዜው በማቅረብ ረገድም በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በግንባታ ስራው ላይ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙት ወታደር ኢንጂነሮች በተቋሙ ባገኙት የትምህርት ዕድል ተጠቅመው በዚህ መሰል ፕሮጀክት ላይ በመሳተፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ጥር 2016 ዓ.ም የግንባታ ስራው የተጀመረው የባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ 2019 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ መርሃ ግብር የተያዘለት ቢሆንም አሁን ባለው ፍጥነት ግን ሰኔ 2017 ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Natinael Mekonnen

17 Oct, 19:03


የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ ያስፈልጋል - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን


የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ እንደሚያስፈልግ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተር ጄኔራሉ በአዲስ አበባ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ “በአፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች መካከል ያለውን ትብብር” የተመለከተ የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

ባቀረቡት ገለፃም "ዓለም በአሁኑ ወቅት አንዱ ሌላውን ጥሎ የሚያልፍበት የበይ እና ተበይ አውድ ውስጥ ይገኛል" ብለዋል፡፡

የዓለም ነባራዊ ሁኔታ የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ ቀርፆ ወደ ተግባር መግባትን የግድ እንደሚልም ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ዓለም አቀፋዊ አውድ ውስጥ አፍሪካ አንድነቷን ካላጠናከረች ልክ እንደ በፊቱ የሌሎች የመጫወቻ ሜዳ የመሆን ዕጣ እንደሚገጥማትም አንስተዋል፡፡