የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የችግኝ ተከላ መረሀ-ግብር አካሄዱ
"የምትተክል ሀገር; የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ አምስት ሰሚት የችግኝ መትከያ ቦታ 6ኛ ዙር ችግኝ ተከላ መረሀ-ግብር አከናውነዋል።
በዕለቱ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በመልዕክታቸው የእንኳን ደህና መጣችው መልዕክት በማስተላለፍ የምንተክለው ችግኝ የትላንት፣ የዛሬንና የነገ ትውልድ የሚያስተሳስር፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ችግር ለመከላከል፣ የደን ሽፋንን ለማጠናከር፣ በመልካ ምድራችን ብዝሀ-ህይወትን ለመጠበቅ እንዲሁም የተሻለች ሀገር ለዜጎች ለመገንባት እና ለማስረከብ ጥረት እያደረገች ያለች ሀገር ኢትዮጵያን መሆኗንም ለማሳየት ነው ብለዋል። አያይዘውም በችግኝ ተከላውና እንክብካቤ ላይ ሁሉም የሀገራችን ዜጎች እንደተለመደው በያሉበት አካባቢ በንቃትና በባለቤትነት እንዲሳተፋ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ ማኖራችን ነገን ታሳቢ ያደረገ እና ፓርቲያችን ለነገው ትውልድ የሚያስተላልፈው የበለፀገች ኢትዮጵያን አንዱ ማሳያ ተግባር ነው ብለዋል። ይህንን የምናደርገውን ጥረት ለአለም እያሳየን ያለንበት ጊዜ ነውና በቀጣይ የችግኙንም የፅድቀት ሁኔታ በቅርብ እንድንከታተልም አሳስበዋል።