Ethiopia Customs Commission @ethiopiacustomscommission Channel on Telegram

Ethiopia Customs Commission

@ethiopiacustomscommission


Ethiopia Customs Commission (English)

Welcome to the Ethiopia Customs Commission Telegram channel! This channel is dedicated to providing the latest updates, news, and information about customs regulations, procedures, and policies in Ethiopia. Whether you are a business owner, importer, exporter, or simply someone interested in the customs process in Ethiopia, this channel is a valuable resource for you. Stay informed about changes in customs laws, tariffs, and trade agreements that may impact your business or personal transactions. Our goal is to help you navigate the complex world of customs with ease and efficiency. Join our community today and be part of the conversation on all things related to customs in Ethiopia!

Ethiopia Customs Commission

22 Jan, 05:17


የብሄራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ
***************************************************
( ጉምሩክ ኮሚሽን፤ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም)

የብሄራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት አካሂዷል፡፡

ግብረ ሀይሉ በታክስ አስተዳደሩ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በሚያስችሉ የታክስ ፖሊሲ፣ የሀገር ውስጥ ታክስ አስተዳደር እና በጉምሩክ ቀረጥና ታክስ አስተዳደር ጉዳዮች ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት አፈፃፀሙን በየወሩ እየገመገመ ይገኛል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት የገቢ አሰባሰብ በእቅዱ መሰረት በተሳካ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን እና በቀሪ ስድስት ወራት በእቅድ የተያዘውን የገቢ እቅድ ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ግብረሀይሉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በተጨማሪም ለገቢ አሰባሰቡ አጋዥ የሆኑ የስጋት ስራ አመራር ስርዓትን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የውዝፍ እዳ ክትትል ማጠናከር፣ የጉምሩክ ዋጋን ወቅታዊ ማድረግ፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎችን ማጠናከር፣ አዳዲስ ታክስ ከፋዮች ወደ ታክስ ስርዓቱ እንዲገቡ ክትትል ማድረግ፣ የደረሰኝ እና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ቁጥጥር እና ክትትልን ማጠናከር ግብረሀይሉ በውይይቱ ያስቀመጣቸው የቀጣይ ወራት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡

የብሄራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት፣ ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከጉምሩክ ኮሚሽን በተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ግብረ ሀይል ነው፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

Ethiopia Customs Commission

20 Dec, 07:39


ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በሞጆ እና አዳማ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቶች የስራ ጉብኝት አደረጉ
***************************************************
( ጉምሩክ ኮሚሽን፤ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም)

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ የሞጆ እና አዳማ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቶች የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ኮሚሽነሩ በጉብኝታቸው በሁለቱ ቅ/ፅ/ቤቶች በገቢ አሰባሰብ፣ ህግ ተገዢነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች ላይ ምልከታ አድርገዋል፡፡

ቅ/ፅ/ቤቶቹ በኮሚሽኑ ገቢ አሰባሰብ እቅድ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑን እና በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደውን ገቢ ለማሳካት በተለይም በእቃ አወጣጥ እና እዳ አሰባሰብ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም ቅ/ፅ/ቤቶቹ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በላቀ ሁኔታ መፈፀም እንዲችሉ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም ቅ/ፅ/ቤቶቹ በገቢ አሰባሰብ፣ ህግ ተገዢነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ላሳዩት መሻሻል ኮሚሽነሩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission

Ethiopia Customs Commission

08 Dec, 13:04


ከ575 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
*********
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም )

የጉምሩክ ኮሚሽን ከህዳር 20 እስከ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 528 . 3 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 47 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 575.3 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የተለያዩ ማእድናት፣ ተሽከርካሪዎች እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሀዋሳ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 241 ሚሊዮን፣ 94 ሚሊዮን እና 86 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በደፈጣ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 17 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና አምስት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች እና አመራሮች፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

Ethiopia Customs Commission

07 Dec, 07:51


ቅ/ጽ/ቤቱ ከደንበኞች ጋር ታቀራርቦ በመስራቱ አገልግሎት አሰጣጡ ከፍተኛ መሻሻል እንዳሳየ ተገለጸ
***************************************
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም )
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከላኪዎች፣ ከአስመጭዎች እና በተለያየ ዘርፍ ከተሰማሩ አምራቾች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስራአስኪያጅ አቶ ተፈሪ መኮነን፣ የጉምሩክ ኮሚሽን በመንግስት የተሰጡትን ተግባር እና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቅ/ጽ/ቤቱም በ2017 የበጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት በገቢ አሰባሰብ፣ በህግ ተገዥነት ስራዎች እና በአገልግሎት አሰጣጥ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገቡን አስረድተዋል፡፡

ቅ/ጽ/ቤቱ በርካታ ደንበኞች ያሉት መሆኑን ያስታወሱት ስራአስኪያጁ ዘመኑን የዋጀ እና የደንበኞችን ክብር የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎችም እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ተፈሪ አክለውም፣ ቅ/ጽ/ቤቱ ከደንበኞች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን በማድረግ ተቀራርቦ በመስራቱ አገልግሎት አሰጣጡ ከፍተኛ መሻሻል እንዳሳየ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት 36 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ ይዞ እየሰራ ሲሆን ባለፉት አራት ወራት 12 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ስራአስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡

”የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገር ብልጽግና የማይተካ ሚና አላቸው“ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ በቅ/ጽ/ቤቱ እና በደንበኞች በኩል የሚስተዋሉ ችግሮች እና ችግሮቹን ለመፍታት የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በመድረኩ የተገኙ ደንበኞች አገልግሎት አሰጣጡ መሻሻሉን ገልፀው በቀጣይም መሰል ውይይቶች እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

Ethiopia Customs Commission

12 Nov, 16:55


ከ294 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
***********
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም )

የጉምሩክ ኮሚሽን ከጥቅምት 22 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 279.7 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14. 8 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 294.5 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የምግብ ዘይት ፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና የወጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ጅግጅጋ፣ ድሬድዋ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 86 ሚሊዮን፣ 61 ሚሊዮን እና 52 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና 7 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች እና አመራሮች፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

Ethiopia Customs Commission

12 Nov, 16:52


አዲስ ለተቀጠሩ የኮሚሽኑ ባለሙያዎች በሰራተኞች አስተዳደር ደንብ እና በስነምግባር ኮድ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
****
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም )

አዲስ ለተቀጠሩ ባለሙያዎች በሰራተኞች አስተዳደር ደንብ እና በስነምግባር ኮድ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራር እና ስነምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም አበበ፣ ኮሚሽኑ በመንግስት የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ሁሉም አመራርና ባለሙያ የስነምግባር ህጎቹን መረዳት እና መከተል የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኮሚሽኑ አመራሮች እና ባለሙያዎች የተቀመጡ ህጎችና አሰራሮችን አክብረው እንደሚሰሩ የተናገሩት ዳይሬክተሯ በጥቂት አመራር እና ባለሙያዎች ላይ ግን የስነምግባር ዝንፈት እንደሚታይ አስረድተዋል፡፡

ብልሹ ተግባራትን ለመከላከል ተከታታይ የስነምግባር ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ የጠቆሙት ዳይሬክተሯ ህጎችና አሰራሮችን በሚጥሱት ላይም አስተማሪ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ስልጠናዉ በስነምግባር ትምህርት እና ኃብት ምዝገባ ቡድን አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ተወልደ ብርሀነ የተሰጠ ሲሆን ብልሹ ምግባርን ለመቀነስ እና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እንደሚረዳም ተመላክቷል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

Ethiopia Customs Commission

12 Nov, 16:51


በመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ( ጉሙሩክ ኮሚሽን)

በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉሙሩክ ኮሚሽን ስር ለተቋቋመው የገቢ አስተዳደር እና አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ዓይናለም ንጉሴ የኢትዮጵያ ተቋማት የግንባታ ሂደት ገና በጅምር ላይ ያለ መሆኑን አንስተው የመንግስት ዋነኛ ተቀዳሚ ተግባር ታክስ መጣል እና መሰብሰብ በመሆኑ በመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲ ማሻሻያ ዘርፍ ውስጥ የገቢው ዘርፍ ተጠቃሽ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የታክስ አስተዳደሩን አለም ከደረሰበት አቅጣጫ እንዲደርስ ለማድረግ በገቢው ዘርፍ በኩል የሰው ሀብት አስተዳደሩን የማደራጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጅታላይዝ የማድረግ፣ ወቅቱን የዋጀ የህግ አሰራር ስርዓትን መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስተሯ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም የታክስ አስተዳደሩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን የሚመጥን ለማድረግ ሪፎረሙ አስፈላጊ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የመንግስት ሰራተኞች የብቃት ስራ አመራር ፕሮጀክት ጽ/ቤት ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አጥሬ በበኩላቸው ስለፖሊሲ ምንነት፣ አስተዳደራዊ ሪፎረም አተገባበር እና ጠቀሜታን አስመልክተው አጭር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቆየታው የሰራተኞች የብቃት ግንባታና ማረጋገጫ ስርዓት ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች ጉዳዮችን ያካትታል ተብሏል፡፡

Ethiopia Customs Commission

05 Nov, 17:06


”የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ የሚሰራቸው ስራዎች ለሌሎች የአፍሪካ የጉምሩክ ተቋማት ተምሳሌት የሚሆን ነው “ የናይጀሪያ ጉምሩክ አመራሮች እና ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተማሪዎች
****
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም )

የናይጀሪያ ጉምሩክ አመራሮች እና ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተማሪዎች “በጉምሩክ አስተዳደር ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በመፍጠር፤ በአፍሪካ የንግድ ስልጠትን ማረጋገጥ“ በሚል መሪ ቃል በጉምሩክ ኮሚሽን ሲያደርጉት የነበረውን ጉብኝት አጠናቀዋል፡፡

ሰልጣኞቹ በቆይታቸው በጉምሩክ ኮሚሽን ዋናው መስሪያ ቤት፣ በአዲስ አበባ ኤርፖርት፣ በሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ለአምስት ቀናት ሲያድርጉት የነበረውን ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በዋናው መስሪያ ቤት፣ በቅ/ጽ/ቤቶች እና በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን በጉብኝታቸው ወቅት ያገኙትን ተሞክሮ እና የቀሰሙትን ልምድ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና ዳይሬክተሮች በተገኙበት አቅርበዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና ስርዓትን ለማጠናከር እና ዘላቂ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የአፍሪካ የጉምሩክ ተቋማት መጠናከር እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ጉብኝቱም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማሻሻል እና በዘርፉ ያለውን ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ እንደሚረዳም አስረድተዋል፡፡

የናይጀሪያ ጉምሩክ አመራሮች እና ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተማሪዎች ልኡካን ቡድን መሪ አቡበከር ፈይሰል፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ የሚሰራቸው ስራዎች ለሌሎች የአፍሪካ የጉምሩክ ተቋማት ተምሳሌት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን ለተደረገላቸው አቀባበል እና እንክብካቤ የልኡካን ቡድኑ መሪ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

Ethiopia Customs Commission

30 Oct, 11:21


በኮሚሽኑ የሚያዙ ዕቅዶች ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ጋር የተቀናጁ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ፦ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

#####################
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም )

የጉምሩክ ኮሚሽን ዋናው መስሪያ ቤት ከፍተኛ አመራሮች ፣ አማካሪዎች ፣ ዳይሬክተሮች ፣ የቡድን አስተባባሪዎች እና በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎችበ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ ክንውን ላይ ውይይት አድርገዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፣ በ2017 በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በገቢ አሰባሰብ ፣ ኮንትሮባንድ እና ህገ ወጥ ንግድን በመከላከል እና በመቆጣጠር ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል::

በኮሚሽኑ የሚያዙ ዕቅዶችም ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ጋር የተቀናጁ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽነር ደበሌ አስረድተዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ አንዱ ምሰሶ ገቢን ማሳደግ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ ባለፉት ሶስት ወራትም 87 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 88 ነጥብ 2 ቢሊዮን ገቢ መሰብሰቡን አብራርተዋል።

ከኮንትሮባንድ መከላከል እና ከህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ስራዎችም 50 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ከህገወጦች ማዳን ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይ ወራትም የኮሚሽኑን ተልዕኮ ማሳካት የሚችል በዕውቀቱ የዳበረ ፣ በስነምግባሩ የተመሰገነ ፣ በአመራር ብቃቱ የተመሰከረለት አመራር እና ባለሙያ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ እና የስትራቴጂክ ፕላን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አብዲሳ ዱፌራ የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ ክንውን ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የኮሚሽኑ አመራሮች እና ባለሙያዎች በበኩላቸው በ2017 በጀት ዓመት በ ኮሚሽኑ የተያዘውን 390 ቢሊዮን ብር የገቢ እቅድ ለማሳካት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission