NEBE ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia @ethio_election_board_nebe Channel on Telegram

NEBE ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

@ethio_election_board_nebe


®This is Official page of NEBE(national election board of ethiopia).
©ይህ Channel የምያስተላልፈው/ስራው ከቢሮው የምወጠውን መራጃን ከዘርፉ ባለሙያ አማከይነት ለህዝብ ማድረስ ነው፡፡©

'አስተያየት' ወይም 'ሊታስተዋወቁ' የሚትፈልጉት ነገር ካላችሁ ከታች ባለው link ያናጋግሩን። If u have idea contact us
👉👉 @JackADMIN2015

NEBE ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia (Amharic)

ይህ የ NEBE (ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ) አስተካክል ሰራተኞችን መሃከል እና ምግብ ነገሮችን ያዳምጡን አባላትን ፣ ጠንካሬዎችን እና መንገዶችን ለማወጣት በአማከር የምስለን እና ልምፈገዶችን የሚገልጽን የቴሌግራም ቦርድ። ይህን ቦርዱን በቢሮ መንገድ በመኖር ወደ ህዝቡ ያገናኙታል። እሳትን እና በካሳያ መፃጠር ለመሳል በመተዳደር እኛን ወደን ይቀረብናል። ከዚህ በፊት እናወዳለን፡፡

NEBE ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

10 Jul, 15:32


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የወጣቶች የክርክር መድረክን አዘጋጀ

የኢትዯጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒቲ ሰስተነብል ዴቬሎፕመንት ኤይድ ከተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ጋር በመተባበር በ 3 የተለያዩ ከተሞች ማለትም ወላይታ ሶዶ፥ ሆሳዕና እና ወልቂጤ የክርክር መድረክ አካሂዷል። ይህ የክርክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፥ በሆሳዕና ከተማ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በወልቂጤ ከተማ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ ሲሆን የሕግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲዎቹ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል። ክርክሩም በዋናነት በምርጫ ፥ዲሞክራሲና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ሲሆን ተማሪዎች በንድፈ-ኃሳብ ደረጃ የተማሯቸውን ፅንሰ-ሀሳቦች ተግባራዊ እንዲያደርጉ እድል ያመቻቸ መድረክ መሆኑ ተጠቅሷል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የክርክር መድረክ ‘በኢትዮጵያ ፓርላሜንታዊ ወይስ ፕሬዜዳንታዊ የመንግስት ስርዓት የተሻለ ነው?’ በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ተማሪዎች ክርክር ያደረጉ ሲሆን በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዜዳንት በበኩላቸው ክርክር የሚደረግባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ወቅታዊና ወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች በመሆናቸው በሀገራችን በሚካሄዱ የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደቶች ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ ይኖራቸዋል ብለዋል...

👉 ተጨማሪ ይመልከቱ

NEBE ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

10 Jul, 15:32


ቦርዱ የ6ኛውን ሀገር አቀፍ ቀሪና የድጋሚ ምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤንሻንጉል-ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ያካሄደውን የ6ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ቀሪና የድጋሚ ምርጫ ውጤት ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል።

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በተጠቀሱት አራቱ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 29 ምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ በ1218 ምርጫ ጣቢያዎች መካሄዱ የታወቀ ሲሆን ውጤት ይፋ በማድረጊያ መርኃ-ግብሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች (ተወካዮች)፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቡአቸው ዕጩዎች፣ የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ የሚዲያ አካላት፣ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ አካላት እና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ታዳሚ ነበሩ ...

👉 ተጨማሪ ይመልከቱ