Gamo Zone Government Communication @gamozonegovcommunication Channel on Telegram

Gamo Zone Government Communication

@gamozonegovcommunication


Gamo Zone Government Communication Affairs Department

የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

Gamo Zone Government Communication (Amharic)

ጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያnnየጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አንድ የትናንት መረጃን ነው። በዚህ መረጃና በተጨማሪ ሐዘን ለጋሞ ዞን ህዝብ አገልግሎትና መንግስት ነሐሴ ለጋሞ ዞን ህዝብ ሰላም እና የአካባቢ ፈቃድ አገልግሎት ያድምጡ የግእዝና የትራንስፓሉሲፕ የምክር አቅታች መረጃዊ ችሎትን በመቀጠል የተጠቁመውን ፕሮግራሞች ስኬሃው።nnጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የበለጠው ችሎት የህዝብን ፈቃድ እና የአካባቢ ብሄራዊ አፈቃቀሞችን መንገድ አለን። በዚህ መረጃው የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ እና ህዝብ በሚከተለው ወቅታዊ ተካሄደው በእኛ በተመረጠ ዕለታዊ ሳይነባብ እጣጭም እንዲሰጥሽና እንባርካትሽ ነው።nnይህ ግንብ ላይ በተለያዩ ችሎች ለሁሉም አገልግሎት ለንግግር ሕገ-መንግሥት፣ ለንግግር አካባቢ ልማት፣ ለንግግር መብት የትኩረት መሠረት፣ ለንግግር ህዝብ እና ለህጋዊ አፈቃቀር የፕሮፌሰንት፣ ሄሎዊት፣ ኤፌናት ማብራሪያ፣ ዲፓርትመንት፣ እና የአገልግሎት አስተዳደር እና ዝርዝሮች እና ማዳረስ አለው።

Gamo Zone Government Communication

18 Dec, 06:06


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኦዲተር መስራቤቶች ኦዲት ግኝት ተፈፃሚነት ክትትል ቡድን ለጋሞ ዞን ኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ ሀይል የኦዲት ግኝት እርምት እርምጃ አወሳሰድ ግምገማ ግብረ መልስ ሰጠ

አርባምንጭ ፣ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኦዲተር መስራቤቶች ኦዲት ግኝት ተፈፃሚነት ክትትል ቡድን ለጋሞ ዞን ኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ ሀይል የኦዲት ግኝት እርምት እርምጃ አወሳሰድ ግምገማ ግብረ መልስ ሰጥቷል።

የጋሞ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት አለሚቱ ዮሴፍ በምክር መድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት የዞኑ ኦዲት ግኝት አስመላሽ ኮሚተ በበጀት አመቱ የግብ ስምምነት በመፈፀም ወደ ስራ መግባቱን ገልፀው መስራያ ቤቶቹ ከኦዲት ግኝት አኳያ ምን ያህል አቅደው ተግባራዊ እንዳደረጉና ተፈፃሚነቱ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በየደረጃው ያለው የግብረሃይል አባል የራሱን ዕቅድ በማዘጋጀትና ዕቅዱን የጋራ በማድረግ የክትትል እና ድጋፍ አግባቡን በማጠናከር ፣ ውሳኔ በማሰጠት፣ ክስ በመመስረት መደበኛ ኦዲት ግኝት ታክስ፣ ከግብር ወለድ እና መቀጮ ፣ የአፈር ማዳበሪያ ፣ በኦሞ ኤጀንት እጅ በሚኖር፣በኦሞ ባንክ እና በማጤመ የተገኙ የኦዲት ግኝቶችን ግብረሃይሉ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኦዲተር ቢሮ ዳይሬክቶሬት አቶ እያሱ ኢርኮ በበኩላቸው ባለፈው በጀት አመት ክልል ኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ ሃይሉ ባደረገው ክhttps://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid0yCkCjXpdEJ4zyjnkA6Zzv3sxCSQEFJmwmRXRFxGEG93wnyh5tpJTNeHbWem9TBKzl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

18 Dec, 06:06


ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ከምን ጊዜውም በላይ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

አርባ ምንጭ ታህሳስ 8/2017 (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን) በጋሞ ዞን ሴቶች ህፃናት ጉዳይ መምሪያ እና በዩ ኤስ አይ ዲ ኢትዮጵያ ሄልዝ ሪሲሊየንስ አክቲቪቲ(USAID/Ethiopia HRA) አዘጋጅነት "የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል ሲከበር የቆየው የነጭ ሪቫን ቀን ተጠናቀቀ ።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተወካይና የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማዶ መንገሻ ለፆታ ጥቃት መፈፀም አስተዋጽኦ የሚበረክቱ የግንዛቤ ችግሮች፣ ከስነ ምግባር ወጣ ያሉ አለባበሶችና ጎጂ ትርክቶችን ለማስወገድ በቤተ እምነቶች፣ በትምህርት ቤቶች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች የግንዛቤ ስራዎች ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

የጋሞ ዞን ሴቶች ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሂሩት ማሞ በበኩላቸው ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የተነሱ ነጥቦችን መሰረት በማድረግ ተግባራዊ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ሁሉም የባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነትና በባለቤትነት ስሜት ከምን ጊዜውም በላይ ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበትም ኃላፊዋ አመላክተዋል ።

የጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጤናሁን ጨርቆስ በበኩላቸው በራስ ላይ እንዲደርስ የማንፈልገውን በሌላው ላይ ባለማድረግ እና ጥቃቶችን በመከላከል ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ከተወጣ በቀላሉ ወንጀልን መከላከል እንደሚቻል ተናግረዋል።

በፆታዊ ጥቃት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ለዋሉ አካላት የምንሰጠው ፍርድና የዋስትና https://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid0pL7Y4HyEw1nGiDFgoqJ7twciH99y2Ri9uvfYy31atnHoBbXxktph4v5djXe4MVql/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

17 Dec, 11:46


አግሮ እልፍ ጥምር ግብርና እርሻ ልማት ከ200 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የመድሃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ለጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ድጋፍ አደረገ

የአርባምንጭ ፣ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን) ፦በጋርዳ ማርታ ማሌ ውዴ ቀበሌ በአግሮ እልፍ ጥምር ግብርና እርሻ ልማት የተሰማሩት ዶ/ር እልፍአገድ ተካልኝ ግምታቸው 210 ሺህ 850 ብር የህክምና ቁሳቁስ እና የመድሃኒት ድጋፍ አድርገዋል።

በርክክቡ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሴይፉ ዋናቃ ለተደረገው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አመስግነው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ፣ የግል ባለሀብቶች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊን የህብረተሰቡን ጤና በሚጠብቁ እና አጋዥ ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል ።

በጋርዳ ማርታ ማሌ ኡዴ ቀበሌ በአግሮ እልፍ ጥምር ግብርና የተሰማሩት ዶ/ር እልፍ አገድ በበኩላቸው በውጭ ሀገር በህክምናው ዘርፍ ተሰማርተው ሲሰሩ እንደነበር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት መግባታቸውን ተናግረዋል።

እንደ ዶ/ር እልፍአገድ ገለፃ በሚሰሩበት አከባቢ ህብረተሰቡ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚሄድበትን ርቀት እና ችግሩን ለመቅረፍ ብሎም የህብረተሰቡን ጤና ለመታደግ የተደረገ ድጋፍ ነው ብለዋል።https://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid02ENsPKbbF7xPLSWbY7BFGmb8C37aFmCAPQcGHEn2oxHLD7vMQuiMGmgTEx6Ax8ZBfl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

17 Dec, 11:43


"የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል የነጭ ሪቫን ቀን በጋሞ ዞን እየተከበረ ይገኛል

አርባ ምንጭ ታህሳስ 8/2017(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን) በጋሞ ዞን ሴቶች ህፃናት ጉዳይ መምሪያ እና በዩ ኤስ አይ ዲ ኢትዮጵያ ሄልዝ ሪሲሊየንስ አክቲቪቲ(USAID/Ethiopia HRA) አዘጋጅነት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ "የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል የነጭ ሪቫን ቀን የማጠቃለያ መድረክ እየተከበረ ይገኛል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተወካይና የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማዶ መንገሻ ሴት ልጅ እናት፣ እህት ፣ሚስት በመሆኗ ፆታዊ ጥቃቶችን ማድረስ አይገባም ብለዋል።

በዓሉን ስናከብር ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመከላከልና አጋርነትን በማሳየት የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ።

አክለውም የባለድርሻ አካላትም የአመለካከት ችግሮችን ለመቅረፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የጋሞ ዞን ሴቶች ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሂሩት ማሞ በበኩላቸው የነጭ ሪቫን ቀን በሁሉም መዋቅሮች በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱን ጠቁመዋል።

በሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃቶችን የሚፈፅሙ አካላትን በህግ አግባብ ተጠያቂ ለማድረግና አፋጣኝ የቅጣት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የበዓሉ ታዳሚ ወንዶች የነጭ ሪቫንን በደረታቸው ላይ በማድረግ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከልና አጋርነታቸውን ለማሳየhttps://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid0BDj1pwoMgH3xjjBUxqKoJKVEY9DFzGStrkCq7GdS6JuYCVwe7fYKYvXaN78p9dRBl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

17 Dec, 11:40


https://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid0ovzfobWMwRKmd1TsRYjvaSKAUAL7EJ5iFXEY5QwF37ww3pjmiyk5rW9BHn9WPMgjl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

28 Oct, 07:43


የህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ስራዎችን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ወንጀልንና ሀሰተኛ መረጃዎችን መከላከል እንደሚቻል ተገለጸ።

አርባ ምንጭ ፣ ጥቅምት 13/2017 0ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን )፦የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ በህዝብ ግንኙነት እና ገፅታ ግንባታ የሚዲያ ስራዎች ዙሪያ ለዘርፉ ማስተባበሪያ ኃላፊዎች ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቋል።

የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደበበ ኦንቶ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ እንደገለጹት ሰልጣኞች በወሰዱት ስልጠና የህዝብ ግንኙነት እና የማህበራዊ ሚድያ አዘጋገብ ስልጠናን መሰረት በማድረግ ህብረተሰቡንና መንግስትን በአግባቡ ማገልገል ይጠበቅባቿል ብለዋል።

ፖሊስ እየሰራ ያላቸውን ስራዎች ማስተዋወቅ፣ ህዝቡን ስለ ወንጀል አስከፊነት ለማስተማርና ለማንቃት፣ የምርመራ ዘገባዎችና ወቅታዊ ፖሊሳዊ መረጃዎችን ሙያዊ ስነ ምግባር በሚፈቅደው መሰረት በፍጥነት ለህብረተሰቡ በማድረስ ህዝብና መንግሥትን የማቀራረብ ስራ እንዲሰሩ አደራ ሲሉ አሳስበዋል።

የጋሞ ቴሌቪዥንን ጨምሮ የተለያዩ መንግስታዊ የሚዲያ አካላት በአቅራቢያችን መገኘታቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀም ይገባናል ያሉት ዋና አዛዡ በቅርቡም ሳምንታዊ የፖሊስ ፕሮግራም ለማስተላለፍ በሂደት ላይ እንደሚገኙ በመጠቆም በስልጠናው መሰረት ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

የጋሞ ዞን ፖሊስ ህዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ በበኩላቸው ስልጠናው በዞን ደረጃ ሲሰጥ የመጀመሪያው መሆኑን በመጥቀስ ወቅታዊ ፣ ሚዛናዊ፣ ትክክለኛ መረጃዎችን በፍጥነት ለህብረተሰቡ ማድረስ ይጠበቅቧችሃል ብለዋል

Gamo Zone Government Communication

28 Oct, 07:40


ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ፦

ሀ) ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ)፤ እና

ለ) ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ)፤ ቅጣት ይከፈላል፡፡

👉የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም፡፡
👉መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት በመጀመሪያ (ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የሚቀረውን ታክስ ሳይጨምር) ታክስ ከፋዩ በፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት የሚፈለግበትን ማንኛውንም ታክስ ክፍያ ማዋል፣ ቀሪው ታክስ ከፋዩ በሌላ በማንኛውም የታክስ ሕግ ለሚፈለግበት ታክስ ክፍያ ማዋል እንደተጠበቀ ሆኖ ተራፊ ገንዘብ ካለ ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል፡፡
👉 ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ የሚጣል ቅጣት በሚመለከተው ያልተከፈለ ታክስ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

ምንጭ፦የፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር

Gamo Zone Government Communication

28 Oct, 07:38


የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከዞኑ የፀጥታ ግብረ ኃይል ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ።

አርባምንጭ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/መኮሚዩኒኬሽን) ፦የጋሞ ዞን ፓሊስ መምሪያ አዛዥ ኢ/ር ደበበ ኦንቶ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ለዞኑ ዘላቂ ሰላም ፣ ደህንነት መከበር በሚደረገው ተልዕኮ የፀጥታ ችግሮች ሲከሰቱና ከመከሰታቸው በፊት ለህዝቡ ዘብ በመቆም የፀጥታ ግብረ ኃይሉ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውኑ በመቆየቱን ገልፀዋል ።

አያይዘውም ፖሊስ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ከማስጠበቅ ባሻገርም በአገልግሎት አሰጣጡ ለአከባቢው ሰላምና መረጋጋት የጉላ ሚና ስላለው የፀጥታ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት የአዝማሚያ ጥናቶችን በማካሄድ እና ቅንጂታዊ አሰራርን በማጠናከር የዞኑን አንፃራዊ ሰላም ለማስጠበቅ ያለመ መድረክ መሆኑንም ኢንስፔክተሩ አመላክተዋል።

ቀጣይ ሳምንት የሚከበረውን የጤና ጉባኤና የብሔር ቤሔረሰቦች በዓልን አስመልክቶ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን በመለየት፣ ማህበራዊን ሚዲያን ለእኩይ አላማ በመጠቀም የዞኑን ሰላም ለማናጋት የሚጥሩ አካላትን ፣ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን፣ ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር እና ከትራንስፖርት ጋር በተያያዘ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ ላይ ግብረ ኃይሉ በልዩ ትኩረት ሊተገብ ይገባል ብለዋል።

በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ የሚከበረውን የፌደራል ጤና ጉባኤ የሀገር ውስጥ እና ውጭ ሀገራት ዜጎች እንደሚሳተፉም ተመላክቷል።

የግብረ ኃይሉ አባላት በ

Gamo Zone Government Communication

28 Oct, 07:36


በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ የሚታደሙ እንግዶች በከተማዉ አይረሴ ጊዜን እንዲያሳልፉ እየተሰራ እንደሆነ ተገለፀ።

አርባ ምንጭ ፣ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን )፦ በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ የሚታደሙ እንግዶች በከተማው አይረሴ ጊዜን እንዲያሳልፉ እየሰሩ እንደሆነ በአርባምንጭ ከተማ በሆቴል ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ገለፁ።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በከተማው ዘመናዊና ጠንካራ የሆቴልና ቱሪዝም ሴክተር ለመገንባት እየተሰራ ይገኛል ብሏል።

በአርባምንጭ ከተማ በልማታዊ ባለሀብቶች የተገነቡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተበራከቱ መምጣትን ተከትሎ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ጎብኚዎች እየተጨመሩ መምጣታቸው ተጠቁሟል።

ይህንንም ተከትሎ ከተማው የተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ ጉባኤዎችንና ስልጠናዎችን እንዲያስተናግድ እድል ፈጥሮለታል ተብሏል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በአርባምንጭ ከተማ የሚዘጋጀው 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ለማድመቅ የቅድመ ዝግጅት ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ የሀይሌ ሪዞርት አርባምንጭ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት ታሪኩ እና የዳሮስ ሆቴል ባለቤት አቶ ብርሀኑ ዋሬ ይናገራሉ።

እንደእነሱ ገለፃ ከሆነ የአርባምንጭ ከተማ በበርካታ ባህላዊ፣ ሀይማኖታዊ፣ ተፈጥሮአዊና መልከዓ ምድራዊ ፀጋዎች የበለፀገ በመሆኑ 19ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶች በከተማው ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ የበኩላቸውን ይወጣሉ።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የከተሞች ቱሪዝም አገልግሎት ብቃት ማረጋገጥ ቡድን መ

Gamo Zone Government Communication

28 Oct, 07:34


የብሔር ብሔረሰቦች በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ምልከታ ተካሄደ

አርባ ምንጭ ፣ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን )፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት«ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት»በሚል መሪ ቃል በአርባምንጭ ከተማ የሚከበረው 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ለበዓሉ አከባበር እየተከናወነ ያለውን ዝግጅት ምልከታ ተካሂዷል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አፈ-ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ፀሐይ ወራሳ፤የብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ አዳማ ትጳዬ እንዲሁም የበዓሉ አከባበር ተልዕኮ የተሰጣቸው የኮሚቴ አባላት ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ተዟዙረው ተመልክተወል፡፡

ክብርት ወይዘሮ ፀሐይ ወራሳ እና የብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ አዳማ ትጳዬ ሁሉም ለበዓሉ አከባበር ስኬት አጽንኦት እንዲሰጥ ጠይቀው ቀሪ ሥራዎች በርብርብ እንደሚጠናቀቁ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

Gamo Zone Government Communication

28 Oct, 07:32


የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኳላላምፑር የልማት ስራዎች ጉብኝት - በምስል

Gamo Zone Government Communication

03 Oct, 08:43


በክልሉ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራ ህዝቡ የራሱ ፕሮጀክት እንደሆነ በማሰብ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል - ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ

ሀዋሳ፡ መስከረም 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራ ህዝቡ የራሱ ፕሮጀክት እንደሆነ በማሰብ ለስኬቱ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራን ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት በዲላ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት በክልሉ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የኮሪደር ልማት ስራ ትልቅ ድርሻ መኖሩን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ለዚህም ህዝብ የራሱ ፕሮጀክት እንደሆነ በማሰብ ለስኬቱ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያሳየው የበለፀጉ ከተሞች ለዜጎች ለመፍጠር በኮሪደር ልማት የተጀመረውን ስራ ህዝቡ ባለበት ሆነ እየተደረገ ላለው የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በዉይይቱ መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ይገኙበታል።

Gamo Zone Government Communication

03 Oct, 08:35


https://www.facebook.com/share/p/ZbyPoPytqb7hcUCM/?mibextid=qi2Omg

Gamo Zone Government Communication

27 Aug, 14:11


የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሠላምበር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ካስትሮ ካበሎ ሕጻን ላይ ግብረ ሥጋ ድፍረት አልፈጸመም በሚል በነጻ የለቀቀበትን ውሳኔ ሻረ

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የስር ሠላምበር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተከሳሽ ካስትሮ ካባሎ ከተከሰሰበት በህጻናት ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ-ሥጋ ድፍረት በደል ወንጀል የዐቃቤ ህግ ማስረጃ አላስረዳም በሚል በብይን በነፃ ያሰናበትበትን በመሻር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በወንጀል ይግባኝ ባይ ዐቃቤ ህግ እና በመልስ ሰጪ ካስተሮ ካባሎ መካከል ዛሬ ነሐሴ 21/2016 ዓ.ም በዋለው ልዩ ችሎት ግራ ቀኙን አከራክሯል፡፡

ችሎቱ በሥር ሠላምበር ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በከሳሽ በኩል የቀረበው የሰውና የሠነድ ማስረጃ እንደክሱ ይዘትና ጭብጥ በበቂ ሁኔታ አስረድቶ እያለ አላስረዳም በሚል ተከሳሽን በብይን በነፃ ያሰናበተው አግባብ አይደለም ሲል ውሳኔውን በመሻር ስነ-ሥርዓታዊ ሂደት እንዲቀጥል ውሳኔ ማስተላለፉን ከዐቃበ ሕግ የደረሰን ማስረጃ ያመለክታል፡፡

Gamo Zone Government Communication

31 Jul, 13:02


ኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን 51 ሺህ በላይ በዲጂታል ክህሎት ለማሰልጠን መዘጋጀቱን አስታወቀ

አርባምንጭ ፣ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦ በአገር አቀፍ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያን በዲጂታል ክህሎት የማሰልጠን ፕሮግራም ማዕቀፍ ውስጥ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከጋሞ ዞን 51 ሺህ 188 ወጣቶችን ይሰለጥናሉ።

በዙም ቴክኖሎጂ ውይይት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የጋሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማዶ መንገሻ የመረሃ ግብሩ ዓላማ ወጣቱ ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ መሳተፍ የሚያስችለው ክህሎት እንዲኖረው ማድረግ ነው።

በ3 ዓመታት በሀገር ደረጃ 5 ሚሊዮን ሰልጣኞችን በማሰልጠንና የምስክር ወረቀት እንዲወስዱ ለክልል ከተሰጠው 235 ሺህ 11 ውስጥ ለዞኑ 51ሺ188 (ኮዴሮች)በዲጂታል ክህሎት የሚሰለጥኑ መሆናቸውን አቶ ማዶ አመላክተዋል ።

የዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ቦዳ በበኩላቸው 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ዲጂታል ክህሎት ሠልጣኞች ፕሮግራም ምንነት እና ዓላማ የያዘ ሰነድ ለዙም ሚቲንግ ተሳታፊ s://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid02N58hemv4N5pAx9qiFKNsSe6hfNnVXFoJYSA9FSkdpyQUzXw6UJkUkTybr2h8meFil/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

31 Jul, 12:35


በጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተመንግስት እድሳት ተጀምሯል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተመንግስት እድሳት ተጀምሯል። በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይም ይገኛል። በአጭር ግዜ ውስጥ ፋሲልን ወደ ቀደመ ግርማ ሞገሱ እንመልሰዋለን።https://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid02agBiiCUK2jdt9jLtpXMpzNYr4PqkuZtGqQwvgB4StWNGSroyNtg4Pqe23RzuQwMhl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

31 Jul, 12:33


አልኮሆል ያለአግባብ መጠቀምና ሱሰኝነት ያለው ተፅዕኖ

አርባምንጭ ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦አልኮሆል ያለአግባብ መጠቀም እና ጥገኛ መሆን በህይወትዎ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል።

አልኮሆልን ያለአግባብ መጠቀም ማለት አልኮልን ከመጠን ያለፈ ወይም በብዛት መጠቀም ሲሆን፤ የአልኮሆል ጥገኛነት ለተወሰነ ጊዜ አልኮሆልን ያለማቋረጥ ሲጠቀሙ እና በዚህ ምክንያት ሰውነትዎ ሲለወጥ የሚፈጠር ነው፡፡

የአልኮሆል ጥገኛ ከሆኑ ካልጠጡ ሊታመሙ ወይም የተለየ ስሜት ሊሰማዎት ስለሚችል አልኮሆል መጠጣትን ማቆም ከባድ ይሆንብዎታል።

አዘውትረው አልኮሆል በብዛት የሚጠጡ ሰዎች የአልኮሆል አጠቃቀም መታወክ ተብሎ የሚጠራውን ሊያዳብሩ ይችላሉ።

አልኮሆል ያለግባብ መጠቀም እና ጥገኝነት:-

ከመጠን በላይ መጠጣት ወደ ሱስ ሊያመራ ይችላል፤ በመደበኛነት ለመስራት አልኮሆል እንደሚያስፈልጎ ሊሰማዎት ይችላል፤ ጠዋት ላይ ከስራዎ በፊት፣ በቀን ወይም ምሽት ከስራ ወደ ቤት እንደገቡ አልኮሆል እንዲጠጡ የሚያስገድድ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል።

የአልኮሆል አሉታዊ ተጽዕኖ:-

ደካማ የስራ አፈጻጸም፣ ሥራ ማጣት፣ የገንዘብ ችግሮች፣ የመኪና አደጋ ተጋላጭነት፣ ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ያለ ግንኙነት ላይ ችግሮች መከሰት፣ ስራ ባልደረቦች፣ ጓደኞች እና ቤተሰብ አመኔታ እና ክብር ማጣት ይጠቀሳል።

እንዲሁም ለረጅም ጊዜ መጠጣት ሰውነትዎን እና አዕምሮዎን በዘለቄታዊነት ይጎዳል፤ እንዲሁም የዕድሜ ልክ የጤና ችግሮችን ያስከትላል እነዚህም በጉበትዎ ወይም በቆሽትዎ ላይ የሚደርስ ጉዳት፣ የልብ ችግር፣https://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid02q6WwfTsWKwEaJwaNnvF7CTD8oqpZoapqi4aktRf9RKiFRfG6ZJhNqzt2VrvZqouvl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

31 Jul, 12:31


የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለጎፋ ዞን የ 5 ሚሊዬን ብር ድግፍ አደረገ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጃዋር የተመራ ልዑክ በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 5 ሚሊዬን ብር ድጋፍ አደረገ።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የፍቅር ተምሳሌት የሆነው የድሬ ህዝብ በሀዘናችን ሰዓት ከጎናችን ስለሆናችሁ ምስጋና ይገባችዋል ብለዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ክልሉ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት በመደገፍ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በአደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በድሬዳዋ ህዝብ ስም ገልፀው ለተጎዱ ወገኖችም መፅናናትን ተመኝተዋል።
ርዕሰመስተዳድርጽቤትhttps://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid02ocMGdZPKqtHSkLvMCKXz7joXCBmAowNxzkESz2spbzn3epLrwYbYgBhbxqgTRzBrl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

31 Jul, 12:30


የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለጎፋ ዞን የ 5 ሚሊዬን ብር ድግፍ አደረገ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጃዋር የተመራ ልዑክ በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 5 ሚሊዬን ብር ድጋፍ አደረገ።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የፍቅር ተምሳሌት የሆነው የድሬ ህዝብ በሀዘናችን ሰዓት ከጎናችን ስለሆናችሁ ምስጋና ይገባችዋል ብለዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ክልሉ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት በመደገፍ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በአደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በድሬዳዋ ህዝብ ስም ገልፀው ለተጎዱ ወገኖችም መፅናናትን ተመኝተዋል።
ርዕሰመስተዳድርጽቤትhttps://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid02ocMGdZPKqtHSkLvMCKXz7joXCBmAowNxzkESz2spbzn3epLrwYbYgBhbxqgTRzBrl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

31 Jul, 12:29


ሌሎችን ለማትረፍ ሲሉ መስዋዕትነት ከፍለው ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን መልካም ተግባር በመከተል ለሌች በጎ ማድረግ አለብን፦ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ

አርባምንጭ ፣ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን )፦በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች መታሰቢያ ሻማ የማብራት ስነ-ስርዓት በሳውላ ከተማ ተካሄደ።

የሻማ ማብራት ስነስርዓቱ የተከናወነዉ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የታወጀውን የ 3 ቀን ብሔራዊ ሀዘን መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

በስነ- ስርዓቱ መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የተፈጠረው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከዚህ በፊት ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ አደገኛና አሳዛኝ ክስተት መሆኑን ገልጸዋል።

ሁሌም እያዘንን መቆየት ስለሌብን ከሃዘን ወጥተን በቀጣይ ስራዎች ላይ ማተኮር እንዳለብን አሳስበዋል።

ህይወታቸውን ያጡ በርካታ ወገኖች ሌሎችን ለማትረፍ ባደረጉት መስዋዕትነት ህይወታቸውን ያጡበትን መልካም መንገድ በመከተል ለሌሎች በጎ ማድረግ አለብን ነው ያሉት።

በአደጋው በክረምት ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ የሄዱ 48 ተማሪዎችን ጨምሮ የቀበሌ አስተዳደር፣ የፓሊስ አባላትና ሌሎችም በአደጋው ህይወታቸው ያለፈ በመሆኑ ልብ የሚሰብር ሀዘን መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም የተፈጥሮ አደጋን ለመከላከል የአከባቢ ጥበቃ ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ተመሳሳይ ጉዳት እንዳይደርስ መጠንቀቅ እና የተጎዱትን በዘላቂነት በመደገፍ ስራ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋልhttps://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid02M34sg5AuvZevEyzuz5q6R2zCDLCftaNHy57YFHFHf1Ch4Kpej2Nh3b6Bru3h9qYNl/?app=fbl

Gamo Zone Government Communication

31 Jul, 12:18


ብሔራዊ የሐዘን ቀን ማጠናቀቂያ መረሀ ግብር በአርባምንጭ ከተማ ሻማ በማብራት ተካሄደ

አርባምንጭ ፣ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦በመረሀግብሩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር ተገኝተዋል።

በአርባምንጭ ከተማ በአብሌ ጨዶ አደባባይ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዚዲ ቀበሌ በድንገተኛ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች መታሰቢያ ጧፍ የማብራት ስነ-ሥርዓት ተካሄደ ።

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዚዲ ቀበሌ በተፈጥሮ የመሬት ናዳ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የሀዘን መግለጫ ጧፍ የማብራት መርሀግብር በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ከሰዓት 11 ሰዓት ጀምሮ ተካሂዷል ።

በመርሃ-ግብሩ የክልል ፣ የዞን እና የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ፣የመንግስት ሠራተኞች ፣ የከተማው ነዋሪዎች https://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid0RA2A9y54TzF2oc3FAm9HeGhhbU7WDJavANh9DwQfT1PGHKdjKVyVNkSQFgXHzgq1l/?app=fbl።

Gamo Zone Government Communication

31 Jul, 12:15


የክረምት ዝናብን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የመሬት መንሸራተት አደጋን ለመከላከል በቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ መጠቀም እንደሚገባ ተገለፀ

ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን የመሬት መንሸራተት አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክት አስተላልፏል።

በክልላችን ከሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች መካከል በዋነኝነት ድርቅና ጎርፍ ይጠቀሳሉ፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ከድርቅና ጎርፍ በተጨማሪ በበልግ እና በመኸር የዝናብ ወቅቶች ከዝናብ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰት የመሬት መንሸራተት በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ሲያስከትል ይታያል፡፡

ይህን ግንዛቤ በመጨበጥ አደጋውን በቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃና ዝግጁነት መከላከል አስፈላጊና ተገቢ በመሆኑ የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ይህን መረጃ ሰጥቷል።

ኮሚሽኑ በክልላችን በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰ የመሬት መንሸራተት መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስትቲዩት የ2016 ክረምት ዝናብ ትንበያ አውጥቷል።

በኢንስቲትዩቱ መረጃ መሠረት ወቅቱ በኤል ኒኖ (EL NINo) ሁኔታ ተፅዕኖ ስር መዋሉን ተከትሎ በርካታ አካባቢዎች በመጠንና በስርጭት መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን ።https://www.facebook.com/100069415860348/posts/pfbid02TJjiQxSRPpgRcaH96ugLJUH8Hfc73AQovMVjekkyHy19Mra84vo5fHFhrSLoQ7GPl/?app=fbl