===========
የኢኖቬሽናን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከ እስራኤል አምባሳደር አቭርሃም ንጉሴ ጋር ተወያዩ
ውይይቱ በሁለተኛው የኢትዮ- እስራኤል የኢኖቬሽን ሳምንት ዝግጅት ወቅት በሁለቱ ሀገራት መግባባት ላይ በተደረሱባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር።
በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ የተደረሰባቸውን ስራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል ከሁለቱም ሃገራት በኩል ጥምር ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ስራ መግባት እንዳለበት አንስተዋል።
ሚኒስትሩ እያይዘውም በኢትዮጵያ ያለውን የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ከእስራኤል ልምድ በመውሰድ ለማጠናከር በፍጥነት ወደ ስራ መግባት እንዳለበት ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ክቡር አቭረሃም ንጉሴ የሁለቱ ሃገራት የኢኖቬሽን ሳምንት ጥሩ የልምድ ልውውጥ የተደረገበት ስኬታማ ዝግጅት መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም የዝግጅቱን እልም ከግብ ለማድረስ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ሃሳብ ገዥ መሆኑን በማረጋገጥ ባስቸኳይ ወደ ስራ እንዲገባ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚቋቋመው የጋራ ኮሚቴ ላይ ከመግስት ተቋማት፤ ከግል እና ከ ብዝሃ መንግስታት ተባባሪ ድርጂቶች በማካተት እንዲቋቋም አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን ይንኑ በቅርብ ጊዜ እውን እንደሚያደርጉ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡