Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️ @palestine_quds Channel on Telegram

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

@palestine_quds


Ethio🦋 Palestine
በዚህ ቻናል ለፍልስጤም ለኢስላም ትልቅ መሰዋትነት የከፈሉ የታላላቅ ጀግኖች ታሪኮች ስለፍልስጤም አስገራሚ ክስተቶች ፍልስጤም የተላኩ ነብያቶች ታሪክ የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
ሼር አድርጉልን
ለአስተያየት
👇
@Palestinians_bot
🇵🇸ፍልስጢን አቅሳ🇪🇹
#አቅሷ_ትጣራለች

#FREE_PALESTINE

Ethiopian-Palestinian Friendship Channel (Amharic)

የኢትዮጵያ-ፍልስጢን መስከረም ቤትnnበዚህ ቻናል 'Ethiopian-Palestinian Friendship Channel' ይህ ታሪክ ለፍልስጢን ወንድም ለኢስላም ትልቅ መሰዋትነት የከፈሉ የታላላቅ ጀግኖች ታሪኮች ስለፍልስጢን አስገራሚ ክስተቶች ላይ ተሰምቷል። እናም ሼር @Palestinians_bot እንደጻፉ ከፍተኛ ቅንጅቶች አሉ።nnይህ ታሪኩ በዓለምን በትግል ምሽት ላይ በትክክለኛ መረጃው እንዲሁም የበመላ ምኞት እንዳለ አስተያየት እንዳለ፤ በዓለምና በፍልስጢን አቅማች ቻናል ነው።nnለምኞት፣ በዓለምና በፍልስጢን አቅሷች ከማቈለቍቃችሁ እየተሳካ እና እየበጠራ ለፍልስጢን እንደገና ቻናል፣ Ethiopian-Palestinian Friendship Channel ባለጠጎመሠረት አገልግሎት ማሰብከት እና ማንበብ ይችላሉ።nnለአቅሷ ትጣራለች! በአቅስማስ ፍልስጢን፣ እና ከዚህ በኋላ መረጃዎች እና አስራርና ትክክል አድራጊዎች ለአጋንንት እና ለቻናል አስራርና ትክክል እንቀርባለን።nn#አቅሷ_ትጣራለች #FREE_PALESTINE

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

29 Nov, 12:26


the International Day of Solidarity with the Palestinian People

በኢትዮጵያ የፍልስጤም  ኤምባሲ united nation ethiopa አረብ ሊግ በተዘጋጀ ክንፈረንሰሰ አለም አቀፍ የፍልስጤም ህዝቦች አንድነት ቀን ተከብሮ ዉሏል።

በዝግጅቱ ላይ ለኢትዮጵያ እውቅና የተሰጣቸው የዲፕሎማቲክ አካላት፣ የተመድ፣ የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተገኘቷል፣ የሲቪክ ማህበራት እና የፍልስጤም ወዳጆች ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ የፍልስጤም ግዛት አምባሳደር ንግግር አድርገዋል
-united national resdent coordinator
የስፔን አምባሳደር ንግግር አድርገዋል
የቱርክ የሞሮኮ አባሳደሮች ተገኝተዋል
በገዛ እየደረሰ ያለዉን እልቂት የሚዘግብ አጅጭር ፉልም ቀርቧል
በዝግጅቱ ላይ የፍልስጤም ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ እና  የፍልስጤም ብሄራዊ መዝሙር ከፍልስጥኤማውያንም ባንዲራ ተወለብልቧል

የፍልስጤም አባሳደር በአብሮነት ቀናታችን በመሳተፍ ድጋፋቸውን ላሳዩ ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል። ለኛ ፍልስጤማውያን በአለም ዙሪያ እየታየን ያለነው ድጋፍ ጉዳያችን ፍትሃዊ እና የተከበረ ለመሆኑ ማሳያ ነው። መብታችን እስኪከበር እና አገራችን ነፃ እስክትወጣ ድረስ አርፈን አንቀመጥም ብለዋል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

28 Nov, 18:11


ሰበር
ስምምነቱ ዉሃ ተቸለሰበት
የእስራኤል ጦር በሰጠው መግለጫ በደቡባዊ ድንበር አቅጣጫ ከሄዝቦላህጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።

በእስራኤል እና በሄዝቦላህ መካከል ለአስራ አራት ወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማርገብ ሁለቱ ኃይሎች በትናንትናው ዕለት የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገው ተግባራዊ እየሆነ እንደነበር ይታወቃል።ወራሪዋ አፃፋ መመለሷ ታዉቋል።

🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

28 Nov, 13:08


የሃማስ ከፍተኛ አመራር ሳሚ አቡ ዙህሪ “የሄዝቦላህ እና የእስራኤል ተኩስ አቁም ስምምነት በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት የሚያስቆም ስምምነት ላይ ለመድረስ መንገድ እንደሚጠርግ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል፡፡ 
አቡ ዙህሪ አክለውም ሃማስ ድርድሮችን ለማከናወን እና ሀሳቦችን ለመቀበል ችግር እንደሌለበት ገልጸው ነገር ግን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦርነቱ እንዲያበቃ ፍላጎት ያላቸው አይመስሉም ነው ያሉት፡፡
አርቲ እንዳስነበበው ቡድኑ ለግብፅ፣ ቱርክ እና ኳታር የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እና እስረኞችን ለመለዋወጥ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

🇪🇹የኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

28 Nov, 10:16


ነገ ........😊✌️ የምን ቀን ነዉ??

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

27 Nov, 17:57


ነፃነት ሲባል ገና ብዙ ነፃነት የተነፈጉ አሉ በቻይና አይጉር ሀይቲ ከፈረንሳይ በዝባዥ መንግስት ማይናማር ሮሂንጋ ማንም የሰዉ ዘር በሀይማኖት በዘር መገፋትን እንቃወማለን ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

27 Nov, 17:54


ሰበር ዜና

የተባበሩት መንግስታት ዋና አቃቤ ህግ ካሪም ካን በምያንማር የሮሂንጋ ሙስሊሞች ላይ የሰብአዊ መብት ወንጀሎችን በመፈጸም በተጠረጠሩበት የወታደራዊ መሪ ላይ የእስር ማዘዣ ጠይቀዋል። ከጥልቅ እና ከገለልተኛ ምርመራ በኋላ በግልበጣ ስልታን የያዙት የጁንታው መሪ ሚን አንግ ህሌንግ በሰብአዊነት ላይ ለፈጸሙት ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው ብሎ ለመደምደም በቂ ምክንያቶች አሉ ሲሉ የአለማቀፉ የወንጀለኞች ፍ/ቤት ዋና አቃቤ ካሪም ካን ከሄድ በሰጡት መግለቻ ገልጸዋል።

የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ማይናማር በሮሂንጊያ ሙስሊም ወገኖቿ ላይ ፈጽማዋላች ያላቸውን ወንጀሎች በተመለከተ በየደረጃው ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል። ይህ እርምጃ እንደፈረንጆቹ በ2017 ና 2018 በሺዎች የሚቆጠሩ የሮሂንጋ ሙስሊሞች የተገደሉበት እና ከ 700,000 በላይ በአብዛናው ወደ ባንግላዴሽ የተፈናቀሉበትን የማይናማር ወታደራዊ ጥቃት በፈጸሙ አካላት ላይ የእስር ማዘዣ የሚያወጣ መሆኑ ነው የተሰማው።
🇪🇹የኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

27 Nov, 07:15


በእስራኤል እና ሄዝቦላ መካከል ለ 13 ወራት ሲካሄድ የቆየውን ጦርነት የሚያስቆም የተኩስ አቁም ስምምነት መፈጸሙን የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስታውቀዋል።
በዛሬው እለት በአካባቢው ሰአት አቆጣጠር (02:00 GMT)በመላው ሊባኖስ የተኩስ ድምጽ እንደሚቆም የተናገሩት ባይደን ስምምነቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ያለመ ነው ማለታቸው ተዘግቧል።
🇪🇹የኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

26 Nov, 08:40


የፍልስጤም ወዳጅ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን እንዲፈቱ የጠየቁ የተቃውሞ ሰልፈኞች የፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ እንደተጥለቀለቀ ቀጥሏል።

እሁድ በጀመረው ተቃውሞ ሰልፍ ፖሊስ በመቶ የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን ሲያስር ታይቷል። የካን ባለቤት ቡሽራ ቢቢ ሰልፉን ከሚመሩት መካከል ይገኙበታል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

26 Nov, 04:49


'በሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ለእኛ በጋዛ ለምንገኘው የተቃውሞ ኃይሎችም እንደ ድል እንቆጥረዋለን።

በሂዝቦላህ ያሉ ወንድሞቻችን ብዙ መስዋእትነት ከፍለዋል ማንም ከጎናችን በሌለበት ጊዜ ከህዝባችን ጎን ቆመዋል።

በዚያ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ አንድ እንደሆነ አጋር ኩራት ይሰማናል እና ደስተኛ ያደርገናል።የሐማስ ከፍተኛ ቃል አቀባይ ኦሳማ ሃምዳን:

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

25 Nov, 18:42


አጫጭር 🇪🇹የኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸

መረጃ 1

የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ በትላንትና ለሊት  250 ሮኬቶችን ወደ እስራኤል  በማስወንጨፉ እንደሻወር
ሮኬቶችን አዝንቦታል።
ከጥቂት ወራት ወዲህ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ከፍተኛ ነው በተባለው የሮኬት ጥቃት በርካታ ሰፉሪዎች  ሞተዋል፡፡

መረጃ 2
አይሲሲ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚኒን ኔታንያሁ፣በቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል
የኢራኑ ካሚኒ የእስራኤል መሪዎች የሞት ፍርድ እንዲጣልባቸው ጠይቀዋል። ካሚኒ አለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት(አይሲሲ) ባለፈው ሀሙስ እለት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚኒን ኔታንያሁ፣በቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት እና በሀማስ መሪ ኢብራሂም አል ማስሪ ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
"የእስር ማዘዣ አውጥተዋል። ያ በቂ አይደለም። በእነዚህ ወንጀለኞች ላይ የእስር ማዘዣ መውጣት አለበት" ሲሉ ካሚኒ የእስራኤል ወታደሮችን በማመላከት

መረጃ 3
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከሄዝቦላህ ጋር የተጀመረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳብ "በመርህ ደረጃ" መቀበላቸው ተሰማ፡፡

ምንም እንኳን ቴልአቪቭ እንዲስተካከሉ የምትፈልጋቸው የሰነዱ ሀሳቦች ካልተስተካከሉ ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ መቀበሏን ማረጋገጫ ባይሆንም ከበርካታ ወራት በኋላ ለስምምነት የቀረበው ሰነድ ይህኛው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

መመጃ 4

ጋዛዉያን ከባድ የዝናብ ዉችንፍር ጋር እየተጋፈጡ ይገኛሉ

ከባህር ዳርቻ አቅራቢያ የሚገኙ የድንኳን መጠለያዎች በከባድ ዝናብ የተነሳ ክፉኛ እየወደሙ ሲሆን እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት እና አሁን ካጋጠመው ከባድ ዝናብ የተነሳ የፍልስጥኤማውያንን ህይወት አስከፊ አድርጎታል።

ከባድ ዝናብ እና እየጨመረ የመጣው ማዕበል እንዲሁም የእስራኤልን የቦምብ ጥቃት ጨምሮ ከአካባቢው እንዲለቁ የሚጠይቀው ትእዛዝ አስደንጋጭ አደጋ ለሚጋለጡ ሰዎች እና ቤተሰቦች ነገሩን በጣም አስከፊ እያደረገው ይገኛል።

መረጃ  5
ሂዝቦላህ ቡድን ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆን የአሜሪካና የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦችም የተጠቃለሉበት የእስራኤልን የስለላ መረብ መበጣጠሱን ይፋ ያደረገበትን መረጃ ይፋ አድርጓል የሂዝቦላ መረጃ እንደሚያስረዳው ከሆነ ከሁለት መቶ በላይ ይሆናሉ የተባሉት የእስራኤል ሰላዮች የሃዝቦላህ  እንቅስቃሴ ላይ ጠንካራ የሆነ ስለላን ለእስራኤል ወታደራዊ ኃይል መረጃዎችን በማቀበል ስራ ላይ ተጠምደው ነበር ብሏል

የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዛሬ እንዳስነብበው ከሆነ ከአሜሪካና ከፈረንሳይ ዜግነት ካላቸው ተጠርጣል መካከል የሶሪያና የብራዚል ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች   ቁጥራቸውን ከሁለት መቶ በላይ ይሆናል ነው የተባለው የዝቦላህ  ቡድን የእስራኤልን የስለላሰለት መበጣጠስ የቻልኩበትን ወታደራዊ ዘመቻ በዛው በሊባኖስ በማከናውን ግለሰቦችን በማለት የገለጸ ሲሆን በቁጥጥር ስር ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች መካከል ከ 50 በላይ የሚሆኑት የሶሪያ ዜግነት ያላቸው ናቸው ሲል  ገልጿል አይአረብ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

23 Nov, 18:05


መግለጫ
የአል ቃሳም ብርጌድ ወታደራዊ ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳ

○ "እስራኤላውያንን ምርኮኞችን እንዲጠብቁ ከተመደቡት ኃይሎሳችን ጋር ያለን ግንኙነት ከተስተካከለ በኋላ በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት በተፈፀመበት አካባቢ የነበረች አንዲት ሴት ምርኮኛ መሞቷ ሪፖርት ተደርጎልናል። ከእሷ ጋር የነበረች የሌላ ሴት ምርኮኛ ህይወት አሁንም አደጋ ላይ ነው።"

○ " ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ መንግስቱ እና የእስራኤል ጦር መሪዎች ዜጎቻቸውን  ለመከራና ለሞት በሚዳርግ ቅድመ ሁኔታ ላይ የሙጥኝ በማለት ለእነዚህ እስረኞች ህይወት አደጋ ላይ መውደቅ ሙሉ ሀላፊነቱን ይወስዳሉ።"

○ “በጋዛ በደረሰው ውድመት እና በአንዳንድ ታጋቾችን በመጠበቅ ላይ የነበሩ ተዋጊዎች ሞት ምክንያት እስራኤል ከምርኮኞቹ መካከል ጥቂቶቹን በህይወት መመለስ ወይም አስክሬናቸውን ባለማግኘት እጣ ፋንታ ላይ ቆማለች።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

23 Nov, 18:03


ከ46 ቀን በኋላ ተወዳጁ አቡ ዑበይዳ መግለጫ ተሰጥቷል

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Nov, 13:45


ወራሪዋ ተስፋፊዋ እስራኤል በጋዛ ቤት ላሂያ ግዛት በሚገኝ ባለብዙ ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የፍልስጤም የሲቪል ኢመርጀንሲ አገልግሎት በህንጻው ውስጥ 70 ገደማ ሰዎች ይኖሩ እንደነበር ገልጿል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Nov, 10:00


በጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ መኖሪያ ቤት አጠገብ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተገለጸ።

የእስራዔል ፓሊስ ቅዳሜ ምሽት ከተሰነዘሩት ጥቃቶች ሁለቱን ማክሸፉን አስታውቋል።

በሰሜን እስራኤል በሚገኘው የኒታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ማን እንደፈጸሙ አልተገለጸም።

ጥቃቱ ሲፈጸም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነቤተሰቦቻቸው በመኖሪያ ቤታቸው እንዳልነበሩ ፖሊስ አብራርቷል።

የኒታንያሁን ቤት ኢላማ ያደረገ ጥቃት ሲፈፀም ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Nov, 06:18


እኔ እኮ የሳውዲ መንግስት ያናደደኝ እነ ሴሌንዲዮን ጄኔፈር ሎፔዝ ካሚላ ካቤሎ ዉድ በሆነ ክፍያ አስጠርቶ የፋሽን ትሪኢት ብሎ የነ አልይ አይነት ዙልፊቃር ሰይፍ አይነት አስታጥቆ ጄኔፈርን ማዘፈኑ ብቻ አይደለም የሳዉዲ ህዝብ ለጋዛዊያን ማሰባሰብ ሲጀምሩ አሸባሪን መደገፍ ነዉ ብሎ ያስቆመበትን ሳስበዉ ይጎዳኛል ኡለሙችን በምን ቢደልላቸዉ ነዉ ግን  እዉነት ኻሊድ አልራሺዲን እዉነትን ተናገሮ መተሳርን ሞትን ያልመረጠ አሊም ልለዉ አልችልም ። ለዚል ፋሽን ኢቨንት ወጪ ያወጣ መንግስት አንዴት ለጋዛዊን መርዳት አልተቻላቸዉም ......

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

12 Nov, 17:58


ተስፋፊዋ እና ወራሪዋ እስራኤል ዛሬ በፋይናንስ ሚኒስትር አማካኝነት ገራሚ የሆነ መግለጫ አዉጥታለች በቀጣይ 2025 ዌስት ባንክን እና እየሩሳሌም ወይም በነሱ አጠራር ሳማሪያን እና ጁዲያን መሬታችንን እንጠቃልላለን ብለዋል በእርግጥም መጥፊያቸዉ ተቃርቧል ።በዚህ መላዉ የፍልስጤም ደጋፊ በዚህ መግለጫ ብስጭትን ጭሯል የምናዬዉ ሆኗል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

12 Nov, 16:22


⚫️◼️◾️▪️

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

11 Nov, 13:44


ያሲን አረፋት(አቡ አማር)የፍልስጤም  ኩራት
ሙሉ ሥም ፦
መሐመድ ያሲር አብደል ራህማን ዓብደል ራኡፍ አልኩድዋ

ልክ በዛሬዋ ቀን November 11, 2004  ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

የተባረከዉ ምድር ምእራባውያን ፍልስጤምን ክደዉ ለአይሁዳውያን አስረክበዉ ጠቅልለዉ ፍልስጤምን ከአለምካርታ ፍቀዉ ሊያጠፉ ሩብ ጉዳይ ሲቀራቸዉ ጀግናዉ ያሲን አረፋት ከቸች ብለዉ ጠላትን አርበድብደዉ አንቀጥቅጠዉ ፍልስጤምን እንደ ሀገር አስቀጥለዋል ጠንካራ ድርጅት ፋታህ  ባይኖር ዌስትባንክ እና እየሩሳሌም,ቢታኒያ,ቤቴሌሄምን ፍልስጤማውያን ባላየን ነበር ። ያሲር አረፋት የሠላም የኖቤል ተሸላሚ ነበሩ። አረፋት ከሽሞን ፔሬዝ ጋር የ1994 የሠላም ኖቤል ሽልማትን ተጋርተዋል።ሁለቱም መሪዎች በኦስሎው ስምምነት መሠረት በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል ሠላም አውርደው ነበር የኖቤል ሽልማትን የወሰዱት።
ብዙም ሳይቆይ ሽሞን ፔሬዝ በአንድ አክራሪ አይሁድ የኮሌጅ ተማሪ ተገደሉ። ያስምምነት ዉሃ ተቸለሰ  ያሲር አረፋት በጠና ታመዉ ፈረንሳይ ውስጥ ሲታከሙ ቆይተው ልክ በዛሬዋ እለት ከ20 ዓመታት በፊት ህይወታቸው አለፈ።ዛሬም ድረስ በፍልስጤም ምድር አረፋት የጀግንነት ምልክት ናቸው።አንዳንድ ተንታኞች አሟሟታቸዉ አጠራጣሪ ስለነበር እስራኤል በመርዛ እንደገደለቻቸዉ ይታማናል ከአንድም ሁለት ጊዜ አስክሬናቸው እንደገና እንዲመረመር  ለማድረግ ሳይቻል ቀርቷል የሆነዉ ሆኖ ፋታህ ፋታህ ሲደክም ደሞ ሌሎች ጠንካራ ድርጅት ይመሰረታሉ እንደሀማስ አይነት በዚህ ሰዓት አንድ ተዋቂ ሚዲያ በዌስት ባንክ እና በእየሩሳሌም ያሉ ፍልስጤማውያን ማን ቢመራችሁ ትመርጣላችሁ ሲባሉ 85 ሀማስን ያሉ ሲሆን ቀሪ 15% የምእራባውያን ተላላኪ የሀማህሙድ አባስ ድርጅትን መርጠዋል ጊዜው የሀማስ ነዉ ፋታህ ተዳክሟል ።አረፋት የምንግዜም ጀግና ነዉ አራት ነጥብ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

11 Nov, 13:43


ይነበብ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

09 Nov, 20:37


update
ወቅታዊ መሪ ካሊድ ማሻልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ ዶሀን ለቀው እንዲወጡ ሊደረግ ይችላል፡፡
ከፍተኛ አመራሮቹ ሀገሪቷን ለቀው ለመውጣት እስከ መቼ ጊዜ እንደተሰጣቸው እና ቀጣይ የሚያርፉበት ሀገር የት ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም፡፡
ነገር ግን ቱርክ ፣ ኢራን፣ ሊባኖስ እና አልጄርያ ቀጣዮቹ የሀማስ መሪዎች መጠጊያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ኳታር የሃማስ የባንክ ሂሳቦችን እንድታግድ እና የባለስልጣናቱን ንብረት እንድትይዝ ጠይቋል።
ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ሀማስ በአንድ ከፍተኛ ባለስልጣኑ በኩል በሰጠው ምላሽ “አመራሮቹን ከኳታር ማስወጣትን በተመለከተ እየተናፈሰ የሚገኘው መረጃ መሰረተ ቢስ እና በቡድኑ ላይ ጫና የመፍጠር ስልት ነው” ብሏል። ከዚህ ቀደምም የሃማስ መሪዎች ከዶሃ ሊወጡ ነው የሚሉ በትክክለኛ መረጃ ያልተደገፉ ዘገባዎች ሲወጡ መቆየታቸውን በማስታወስ።
ባለፈው አንድ አንድ አመት በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ዋና ተዋናይ ሆና የቆየችው ኳታር ከዚህ ውሳኔ በኋላ በድርድሩ የሚኖራት ሚና ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

09 Nov, 20:00


የዚህ ፎቶ ምስል ሲገለጽ
የአለማችን ልእለ ሀያል ሀገር አሜሪካ አለምን ፔትሮ ዶላር አለምን ትዘዉራለች በዚህም ትልወቅ ባለ ግዙፍ  ኢኮኖሚ  ከተረጋጋችዉ ሳዉዲ አረቢያ  ጀርባ አሜሪካ ነዉ ያለችዉ ከጠንካራዋ  አሜሪካ ጀርባ ደግሞ ያለችዉ ሳዉዲ  አረቢያ ናት ለዚህ ነዉ ዶናልድ ትራምፕ ሳዉዲ ማለት ለአሜሪካ የምትታለብ  ላም ናት ሲሉ የገፃት ብዙ ጉድ የሚስብል ግንኝነት ሁለቱ ሀገራት አላቸዉ ዶናልድ ከዚህ ቀደም በነበረዉ ቃለምልልስ  እንዲህ ይላል ሳዉዲን በጣም እወዳታለሁሀገሪቱ ከገንዘብ ዉጭ ሌላ ነገር የላትም በዙሪያዋ የሚገጥማትን ጠላት አኛ እናጠፋለን ሳዉዲ ከኛ በገፍ መሳያ ትገዛለች 450 ቢሊየን ወጪ በማዉጣት የጦር መሳሪያ ገዝታለች ለዚህ ነዉ ሳዉዲን ማጣት የማንፈልገዉ ዶናልድ አንድ ጊዜ ለ ንጉስ ሰልማን ደወልኩለትና እንዲህ አልኩት ንጉስ ሆይ እኔ እወድካለሁ አልኩት ከዚያ አንተን ንግስናህን በመጠበቅ  አቅላችን አጣን  አነንተ ደሞ ብዙገንዘበ አለክ አልኩት አለ ትራምፕ …..ንጉስ ሰልማን ቀጠለና አሁን ለምን  ደወልክልኝ አለኝ ከዚህ በፊት የአሜሪካ መሪ ማንም እንደዚህ  ያለኝ የለም አለ  እንደዚህ ያላሉህ ደደቦች ስለሆኑ ነዉ አልኩት ይላል ትራምፕ ከዛም የሳዉዲ ንጉስ ትራም ለጉብኝት በመጣበት ጊዜ የሀገሪቱን ትልቅ ኒሻን ሸልመዉታል ባጠቃላይ ትራምፕ በመመረጡ ሳዉዲ ደስተኛ ከሆኑ ሀገራት መካከልናት  አሜሪካ  ሳዉዲ እና እስራኤል ግኑኝነታቸዉ እንዲጠናከር ትልቅ ድርሻ አላት  ግልፅ መናገር ችግር የሌለበት ትራንፕ ይናገራል ሳዉዲ እስራኤን ባታግዛት እስራኤል እዚህ ደረጃ አትደርስም ይላል የሚሰማዉን የመናገር ችግር የሌለበት ይህ እዉነታዉ ነዉ እስራኤል ችግር ዉስጥ እንዳትገባ ሳዉዲ ብዙ የኢራንን መረጃ አሳልፋ ትሰጣለች  ኳታር የአሜሪካ ወዳጅ ስለሆነች እስራኤል  ማንም የሀማስ መሪ በኳታር  እንዲገደል አትፈልግም  እን ይህ አብድ የሆነ ሰዉዬ  ዛሬ ለኳታር ቀጭን ትእዛዝ  ሰጥቷል  ሀማስ ከዚህ ቡኋላ በኳታር እንዳናይዉ ሲል አዟል የቀጣይ ሀማስ መዳረሻ የት ነዉ የሚለዉ ጉዳይ አጠያያቂ ሆኗል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

08 Nov, 18:41


My Palestine icon

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

08 Nov, 13:08


በኔዘርላንድ ወጣቶች በተፈፀመባቸው ጥቃት የተጎዱ እስራኤላውያንን ከሀገሪቱ ለማስወጣት የእስራኤል መንግስት አየር ሃይል አውሮፕላኖች በኔዘርላንድ ማረፍ አይችሉም በማለት የኔዘርላንድ የደህንነት ባለስልጣናት ከልክለዋል።

የኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ትክክለኛውን ምክንያት የኔዘርላንድ መንግሥት ከልክሎኛል ብለ ባይገልጽም “ወታደራዊ የነፍስ አድን ቡድን ወደ ኔዘርላንድ መላክ አስፈላጊ እንዳልሆነ ተወስኗል ብሏል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

08 Nov, 10:10


399 የጦርነት ቀናት በፍልስጤም

ለ399 ቀናት በዘለቀውና በቀጥታ በእስራኤል የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች ትዛዝ የሚፈጸመው ጥቃት ፍልስጤማውያን ሲቪሎችን ከመጨፈጨፉም በላይ ዜጎችን ለበረሃብ በመዳረግ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል፡፡
እስራኤል ሰሜን ጋዛን -በተለይ ከጃባሊያ ወደ ቤይት ሃኖን እና ወደ ቤይት ላሂያ የሚወስዱ ቦታዎችን ወደ እውነተኛ የግድያ ሜዳ በመቀየር ላይ ትገኛለች ። ባለፈው ወር በሰሜን ጋዛ እስከ 1300 የሚደርሱ ፍልስጤማውያን ሲገድሉ እስራኤል የፍልስጤምን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት "አጠቃላይ እቅድ" እየተባለ የሚጠራውን ተግባራዊ ስታደርግ ቆይታልች።
IOF በጥቅምት 29 በቤቴ ላሂያ ባለ 5 ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ ላይ ባደረሰው የአየር ድብደባ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በማነጣጠር 25 ህጻናትን ጨምሮ በ93 ፍልስጤማውያን ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
እስራኤል በUNRWA ትምህርት ቤቶች፤ መጠለያዎች ፣ሆስፒታሎች ፣የጤና አጠባበቅ ሰራተኞች እና በመሳሰሉ ተቁማት ላይ በምታደርሰው ጥፋት ፤ አዲስ የተወለዱ ሕፃናት እንኳን ሳይቀር የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡
እውነታውን የበለጠ ከባድ የሚያደርገው እነዚህ ስልታዊ እና ዕለታዊ የሆኑ በፍልስጤም አካባቢዎች የሚፈጸሙት ጥቃቶች በሰፋሪ አሸባሪዎች የተደገፉ መሆናቸውና ንብረቶች እንዲሁም እርሻዎችን ዒላማ በማድረግ ፍልስጤማውያን ነዋሪዎችን ከመኖሪያ መንደራቸው ለማጥፋት ያለመ ተግባር መሆኑ ነው።

ፍልስጤም ኢምባሲ በኢትዮጵያ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

08 Nov, 06:54


ኔታንያሁ በአምስተርዳም እስራኤላውያን ኢላማ ያደረገ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ሁለት የህይወት አድን አውሮፕላኖች እንዲላኩ ማዘዛቸውን ጽ/ቤታቸው በዛሬው እለት አስታውቋል።
ጽ/ቤቱ እንደገለጸው ከሆነ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከእግር ኳስ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ነው።
የእስራኤል የደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤንግቪር በኤክሰ (በቲዉተር"የእግርኳስ ጨዋታ ለማየት የሄዱ ደጋፊዎች የጸረ-ጽዮናዊ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል፤ አይሁድ እና እስራኤላውያን በመሆናቸው ብቻ ሊታሰብ በማይችል ጭካኔ ተጠቅተዋል" ብለዋል።
ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ ከጨዋታው በኋላ የፍልስጤም ደጋፊዎች ከተማዋ በጆሃን ክሩይፍ ስቴዲየም ሰልፍ እንዳያደርጉ ብትከለክልም በእዚያ ሰልፍ ለማድረግ ሲሞክሩ 57 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጿል።
ፖሊስ እስራኤላውያን ደጋፊዎች ከስታዲየም ጉዳት ሳይደርስባቸው መውጣታቸውን ቢገልጽም፣ ምሽት ላይ በከተማዋ ማዕከል ላይ በርካታ ግጭቶች መከሰታቸው ተዘግቧል

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

06 Nov, 16:02


የአሜሪካ ምርጫን አስመልክቶ የሐማስ ይፋዊ መግለጫ

"በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ላይ ያለን አቋም በፍልስጤም ህዝባችን ላይ በሚያሳየው አቋም እና ተግባራዊ ባህሪ እንዲሁም በፍልስጤማዊያን ፍትሀዊ ትግል ላይ በሚኖረው አስታዋጾ ዓላቸው ላይ የተመሰረተ ነው።

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በጋዛ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም የራሱ የአሜሪካ ህዝብ እያሰማ ያለውን ድምጽ ማዳመጥ ይጠበቅበታል፡፡

ከፍልስጤም ህዝብ ነፃነት እና የእራሳቸውን እድል በራሳቸው የመወሰን እንዲሁ እየሩሳሌምን ዋና ከተማዋ ያደረገች ነጻ እና ሉዓላዊት ሀገረ ፍልስጤምን ከመመስረት ያነሰ ማንኛውንም መንገድ አንቀበልም።'

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

06 Nov, 08:36


ወፈፌዉ ዶናልድ ትራምፕ ነጭ አክራሪ እና ጸረ-ሙስሊም ነዉ ግለሰብ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሲሆን ዓለም አቀፉን ህግ ጥሶ "እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት" በማለት ወስኖ እንደነበር ስንቶቻችን እናዉቃለን በዚህ ውሳኔ የተነቃቃው የእስራኤሉ ሊኩድ ፓርቲ ደግሞ December 29/2017 ባካሄደው ኮንግረስ "ምዕራባዊ ዳርቻ" (West Bank) ሙሉ በሙሉ ተጠቅልሎ ወደ እስራኤል ግዛት እንዲገባ ውሳኔ ማስተላለፋን አንረሳዉም ።ማንም ይምጣ ይሂድ ሁሉም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከእስራኤል ጎን ናቸዉ ዴሞክራቶችም ጋዛ ከእስራኤል ጋር ሲያስደበድቡ አንድ አመት ሞላቸው ይህ ሰዉ ምን አልባት የራሺያ ዮክሬን ጦርነት ሊያስቆመዉ ይችል ይሆናል የአሜሪካ በጀት ካዝናዉ ስለተሟጠጠ የጋዛ ጦርነት ያስቆመዉ ይሆን የሚለዉን አብረን የምናይ ይሆናል አቋሙ የማያስታዉቅ ሰዉ ስለሆነ የሚገመት ሰዉ አይደለም።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

05 Nov, 05:44


የየሕያ ኢብራሂም ሲንዋር መጽሐፍ ተጋበዙ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

04 Nov, 07:16


ጀግናው ያህያ ሲንዋር ታግሎ አታጋይ ባለ ራዕይ መሪ በጋዛ ምድር ምደረባንዳ አፅድቶ ጠንካራዉን ሀማስ ግንብቶ ጀግና ትዉልድ ትቶልን አለፈ ይህ የዘመናችን ጀግና የህይወት አፈፃፀም በሚፈለገው እና በሚጓጓለት ሸሂድነት ተሰዋ እደ እስራኤል ብሮድ ካስት ቻናል ሂብሩ 14 ዘገባ ያህያ አስ-ሲንዋር የአስከሬን ምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው ከመሞቱ በፊት ባሉት 72 ሰዓታት ምን አይነት ምግብ እንዳልቀመሰ ዘግቧል አስባችሁታል አራት ቀን ያለምግብ መቆየት 14 ሰዓት ፆመን ተርሀዊ ጨርሰን ለመስገድ የሚከብደን ሰዎች እኮ ነን! ሸሂድ ያህያ ሲንዋር ሲሞት ዋርዲያ ወጥቶ ለቅኘት ሲዋጋ ከሦስት ጠባቂዎች ጋር ተሰዋ እንጂ እነሱ እንዳሉት ከታጋቾች ጋር አልነበረም እሱ ሰማዓታት የሆነው በሚወዳቸዉ ዉሃ ሰማያዊ ሸሚዞች ሳይሆን የወታደራዊ መለዮ ዮኒፎርም ከነ ትጥቁ እየተዋጋ ነበር ።አላህ ይቀበልህ በጀነት ያሸሂድ

@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

03 Nov, 05:27


“የእስራኤል መሪዎች በር እና መስኮቶቻቸውን ይጠብቁ” አያቶላ አሊ ሀሚኒ

የኢራን ጠቅላይ መሪ እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን እና በአጋሮቿ ላይ ለሰነዘሩት ጥቃት "አስከፊ ምላሽ" እንደሚሰጡ ዛቱ።


ሀሚኒ “ጠላቶቻችን የጽዮናዊው አገዛዝም ይሁን አሜሪካ፣ በእርግጠኝነት በኢራን እና በኢራን ህዝብ ላይ ለፈጸሙት በደል አስከፊ ምላሽ ይጠብቃቸዋል” ሲሉ ተደምጠዋል
@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

02 Nov, 06:50


ሄዝቦላህ የእስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎችን እየደበደበ ይገኛል ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

02 Nov, 04:15


የእስራዔል ጦር የሰው ኃይል እጥረት ገጥሞታል ተባለ፡፡

ከሃማስና ከሂዝቦላህ ጋር ጦርነት ውስጥ የገባችው እስራዔል በአሁኑ ሰዓት ሁለት ብርጌድ ተጠባባቂ ወታደሮች ብቻ እንዳሏት ጦሩ አስታውቋል፡፡

እስራዔል በሊባኖስ ተጨማሪ የውጊያ ግንባር ለመክፈት አቅዳለች በተባለበት ወቅት ነው እስራኤል የወታደር እጥረት እንደገጠማት የተዘገበው፡፡

ከአንድ አመት በላይ የዘለቀው ጦርነት ያሰለቻቸው ወጣቶች ጦሩን የመቀላቀል ፍላጎታቸው ቀንሷል ተብሏል፡፡
France 22 እንደዘገበው

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

01 Nov, 17:40


ዘመቻ ኸይበር ብሎ ቆርጦ የተነሰዉ ሄዝቦላህ ወራሪዉን ቅንድብ ቅንድብ ቅንድቡን ሲለዉ በበቃኝ ተዘረረ እና ግዳጃችን ጨርሰናል አላሉም 😁😁የእስራኤል ወታደራዊ መሪዎች በጋዛ እና ሊባኖስ በወታደራዊ ዘመቻዎች አላማዎች በሙሉ አሳክተናል ፡፡
ሲኤንኤን እንደዘገበው መሪዎቹ በይፋ ባይሆንም ወታደራዊ ዘመቻዎቹ መጠናቀቃቸውን እና ጦሩ ከዚህ በኋላ በሁለቱ ስፍራ መቆየቱ እምብዛም ጥቅም እንደሌለው እየተናገሩ እንደሚገኝ ዘግቧል፡፡
በወታደራዊ ኃይል የምትችለውን ሁሉ እንዳሳካች የገለጹት አዛዦቹ ፖለቲከኞች ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜው አሁን መሆኑን አመላክተዋል፡፡

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

01 Nov, 14:23


አልቀሰም ብርጌድ የዛሬ ተጋድሏቸው

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

31 Oct, 14:58


ሄዞቦላህ አንጀት የሚያርስ ገድል እየፈጸመ ይገኛል

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

31 Oct, 13:24


UNRWA በተባበሩት መንግስታት ሲመሰረት እስራኤል የምትባል ሀገር አልተመሰረተችም ይህ የወራሪዋ ክልከላ ሀማስ ከነዚህ የእርዳታ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለዉ በሚል ቀሽም እሳቤ ነዉ ይህ በግልፅ የዘር ማፅዳት ወንጀል እንጂ ሌላ አይደለም

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

31 Oct, 13:20


በጋዛ ያለው የሰብአዊ ቀውስ ታይቶ ወደማይታወቅ ደረጃ እያሽቆለቆለ ባለበት የወራሪ ኃይሉ በUNRWA ላይ እገዳ አሳልፏል!!

የእስራኤል ኦፕሬሽን ፓርላማ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልስጤም ስደተኞች የእርዳታ ስራዎች ኤጀንሲ (UNRWA) በእስራኤል ግዛት እና በተያዘው የፍልስጤም ግዛቶች ውስጥ፣ የተጎዳውን የጋዛ ሰርጥ ጨምሮ እንዳይሰራ አግዷል።
(UNRWA) በአሁኑ ጊዜ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የሚሰራ ብቸኛው የሰብአዊ ርዳታ ኤጀንሲ ሲሆን ጥቃቱ ከጀመረ ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ በእስራኤል አረመኔያዊ ጥቃቶች ውስጥ ቆይቷል። በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩኤንአርዋኤ ሰራተኞች በእስራኤል ጦር ተገድለዋል፡፡ ይህም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች እጅግ አስከፊው ጦርነት ነው።
እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 31 ቀን 2024 ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ ከ43,163 በላይ የፍልስጤም ሲቪሎች በእስራኤል ወረራ ኃይሎች ሲገደሉ ከጥቅምት 7፣ 2023 ጀምሮ ቢያንስ 101,510 ቆስለዋል ።
በሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ የሚገኘው የቤቴ ላሂያ ማዘጋጃ ቤት በዘር ማጥፋት ጦርነት ምክንያት ከተማዋን የአደጋ ቀጠና የሚል ስያሜ ሰጥቶታል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

31 Oct, 07:24


ለታሪክ ተቀምጧል

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

24 Oct, 15:57


ጣልያናዊው ጓድ ፍራንኮ ፎንታና የፍልስጤማውያን ሰቆቃ ሲያንገሸግሸው ለነጻነታቸው ሊታገል በ1970ዎቹ ፍልስጤም ምድር የከተመ ሰው ነበር። በወቅቱ የነበሩ ሙጃ*ሒዶችን በተለይም በሮኬት ተኩስ ካገዙ ወታደራዊ ጠበብቶች መካከል ነበር። በመጨረሻም በጣልያን ያፈራውን ንብረት ሁሉ በመሸጥ ለትግሉ አበረከተ።

ይህ ቀና ሰው በስተመጨረሻም አላህም ﷻ ሒዳያውን ወፍቆታል። በ2005 እስከተገደ*ለበት ጊዜ ድረስ ለፍልስጤማውያን ህዝቦች ነጻነት ሲታገል እድሜውንም፣ ህይወቱንም፣ ንብረቱንም ሰውቷል። በመጨረሻ ጊዜዎቹ ከተናገረው ውስጥ፦

"ምናልባት እኔ የፍልስጤማውያንን ነጻነት ለመመልከት አልታደልኩ ይሆናል፣ ግን ያለምንም ጥርጥር ልጆቼና የልጅ ልጆቼ የፍልስጤማውያንን ነጻነት ያያሉ። ያኔም ለዚህች የተባረከች ምድር የከፈልኩትን መስዋዕትነት ይረዳሉ"

አላህ ﷻ ይዘንለት፣ ያለምንም ጥርጥር ቁድስ ከወራ*ሪዎቿ ነጻ ትሆናለች - ኢንሻአላህ..!

via yahya ibnu nuh

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

23 Oct, 19:32


https://youtu.be/9Dr0FgjvGtQ?si=Pa3qG5yAeSGNUW1h

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

23 Oct, 19:09


አየርላንድ ብሪቲሽ ጋዜጠኛ  Piers Morgan Uncensored show ዩቲዩብ ላይ በብዙ ሚሊየኖች የሚታይ ተወዳጅ ሾዉ ነዉ።  የፖርቹጋል ኮከብ ተጫዋች ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከማንቸስተር ለመውጣት ሲወስን የሄደው ፒርስ ጋር ነው በዛም እንደዛ ዮቲዮብ ተጨናንቋ አያቅም ።  ማንም ይሁን ማን ሀሳባቸዉን በሚዲያ ይገልፃል  እድል ይሰጣል ከዛ በተጨማሪ ጉዳዩ እስራኤል-ሃማስ ጦርነት   አንድ እንግዳ ይዞ፣ ሲያሻው በጦርነቱ ተቃርኖ የቆሙ ሰዎችን ጋብዞ ያከራክራል ። ሀሳብ አንሸራሽሯል። በስሜት የጋላ ሕይወት ያለው ሾው ማቅረብ ችለዋል።

በዚህ 12 ወር ዉስጥ ለ3 ጊዜ የተጋበዘዉ የግብፃዊ-አሜሪካዊ ኮሜዲያን Bassem Youssef ነው ። ሚስቱ የጋዛ ሰው መሆኗን የሚናገረው Bassem የምዕራባውያንን double standard ቁልጭ አድርጎ ከማሳየት አልፎ ፒርስ ሞርጋንንም በራሱ በፒርስ ጥያቄዎች ጦጣ አድርጎታል። ፒርስ የሁሉ ቀውስ መነሻ ሃማስ፣ ኦክቶበር 7 ምናምን ሲል፣ ሃማስ ዌስት ባንክ የለም..ታዲያ እዛ ያሉት ፍልስጤሞች በምን ዕዳቸው ነው የሚጨፈጨፉት ይለዋል። ሃማስ የጋዛን ሕዝብ እንደ ምሽግ እየተጠቀመበት ነው ሲለው ባሳም ሚስቴም እኮ ልጆቼን ይዛ እንደምሽግ ትጠቀምባቸዋለች እያለ ያላግጦበታል ። ባሳም የፒርስ ሾው ላይ ሁለት ግዜ ቀርቧል ገራሚ ቫይራል ነበር ስለ ኢትዮጱያ አይሁድ የተናገራ አስገራሚ ነበር በዩቲዩብ እስከአሁን 21 ሚሊየን እይታን አግኝቷል።


ሲጠቃለል፡ ፒርስ ሞርጋን እንደ ምዕራቡ mainstream ሚዲያ ሁሉንም እንግዶቹን Do you condemn Hamas..?  በሚል አሰልቺ ጥያቄ ቢያሰለችም፣ የተዳፈነዉ የፍልስጤማውያን ድምፅ እንዲሰማ ብርቱ ተናጋሪዎችን ይጋብዛል።ካቀረባቸዉ እንግዶች መካከል ከሀዲ ፍልስጤማዊ አለ ለዛዉም ሀማስን ከመሰረቱት ታዋቂ ሰዉ ጭራሽ ለእስራኤል የሚሰልል ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ

የዛሬዉን ለመከታተል በዚህ መስፈንጠሪያ ይጠብቁhttps://youtube.com/@piersmorganuncensored?si=4d9rdAkgwQWN6ORh

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

23 Oct, 18:07


ያህያ ደማቅ ታሪክ ፅፎ ተለየን የነስሩ ቀን ተቃርቧል

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

23 Oct, 16:15


የተመድ የንግድ እና ልማት ኮንፈረንስ ማክሰኞ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ጦርነቱ ነገ ካበቃ እና ጋዛን ወደ ቅድመ ጦርነት ደረጃዋ ለመመለስ 350 አመታት ሊወስድ እንደሚችል አስታውቋል። 
 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ እጅግ ገዳይ እና አውዳሚ ወታደራዊ ዘመቻዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለትን የጋዛ ጦርነት ለመልሶ ግንባታ አስርተ አመታትን ሊወስድ እንደሚችል ሲያስጠነቅቁ እንደሰነበቱ ይታወሳል፡፡
አሁን ጦርነቱ ከተጀመረ ከአንድ አመት በኋላ እየወጡ የሚገኙ አዳዲስ ሪፖርቶች ደግሞ የጋዛን ኢኮኖሚ መልሶ ለመገንባት መቶ አመታተን ሊወስድ እንደሚችል እያመላከቱ ነው፡፡
 የመልሶ ግንባታው እና ኢኮኖሚውን ድጋሚ ለማነቃቃት የሚወስደውን ጊዜ ለማሳጠር እስራኤል የጣለችው የእንቅስቃሴ እገዳ ሊነሳ ይገባል ተብሏል፡፡
ከጦርነቱ በፊት ሀማስ በ2007 ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ጋዛ በእስራኤል እና በግብፅ ኢኮኖሚያዊ እገዳ ስር ነበር፡፡
 በሃማስ እና በምዕራቡ ዓለም የሚደገፈው የፍልስጤም አስተዳደር በዌስት ባንክ መካከል የተደረጉ አራት ጦርነቶች እና መከፋፈል እንዲሁ በጋዛ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫናን አሳድረዋል፡፡
@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

23 Oct, 14:59


እስራኤል በሊባኖስ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ በፈፀመቺው የአየር ጥቃት ቄስ አባ ግሪጎሪዮስ ሳሎምን ጨምሮ 8 የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮችና ባለቤታቸው ተገደሉ።
ይህ የሆነው ከቀና በፊት ነው።
በደቡባዊ ሊባኖስ ናባቴህ በምትባለው የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በሚኖሩባት ከተማ ቤተክርስቲያን ላይ በፈፀመቺው የአየር ጥቃት ነው እስራኤል ቤተክርስቲያኗን አውድማ ቄሱን ከየተከታዮቻቼውና ባለቤታቸው የገደለቻቼው።

ሊባኖስ በመካከለኛው ምስራቅ በርካታ ክርስቲያኖች የሚገኙባት ሀገር ስትሆን በእስራኤል ድብደባ በርካቶች ተገድለዋል።ቤተክርስቲያናትም የእስራኤል የጥቃት ኢላማ ከመሆን አልተረፉም።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 17:14


የምንወደው የምናከብረው ትዉልደ ግብፃዊ አሜሪካዊዉ ኮሚዲያን ጋዜጠኛ ባሲም የሱፍ እንደተለመደው ነገ ከ ፕሪስ ጋር የጦፈ ክርክር አላቸዉ በጣም ጓጉቻለሁ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 14:26


ሰበር ዜና
እንደሚመረጥ አቅ ነበር ኻሊድ ማሻል የሸሂድ ያህያ ሲንዋር ተተኪ እሱ ሆኖል
ከ36 ዓመት በፊት ከእስራኤል ግድያ ያመለጡት ካሊድ ማሻል ሐማስን በጊዜያዊነት መምራት ጀመሩ፡፡ከዚህ ቀደም ሲመረጥ በህመም ምክንያት አልተቀበለም ነበር
ለያህያ ሲንዋር ግድያ ሐማስ እስራኤል ይበቀላል ሲሉ ዝተዋል

የፊዚክስ መምህር የሆኑት ካሊድ ማሻል ሐማስን ከመመስረታቸው በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 1996 እስከ 2017 ድረስ የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ሀላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 09:17


ባለጸጋ እስራኤላዊያን በሐማስ የታገቱ ዜጎችን ለሚለቁ የገንዘብ ጉርሻ ማዘጋጀታቸውን ገለጹ
😁
ዳንኤል ብረንቡም የተባሉት ከአልኮል ነጻ መጠጥ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ከታገቱበት በህይወት ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ላደረጉ አጋቾች 100 ሺህ ዶላር እንደሚሰጡ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ባለጸጋው ገንዘቡን በካሽ አልያም በቢትኮይን መልክ እከፍላለሁ ያሉ ሲሆን እስካሁን ከ100 በላይ ስልክ እንደተደወለላቸው ተናግረዋል፡፡
ከ100 ሺህ ደዋዮች ውስጥ አብዛኛው የሹፈት ስልኮች ሲሆኑ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑት ግን ትክክለኛ ደዋዮች መሆናቸውን ተከትሎ ጉዳዩን ለእስራኤል መንግስት አሳውቄያለሁም ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በአሜሪካ የሚኖሩ ሌሎች እስራኤላዊን ታጋቾችን ለሚለቁ ሰዎች በተመሳሳይ የገንዘብ ማዋጣት መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 07:16


አብዱረህማን እንደፃፈዉ ለወደፊት ሲንዋር የተሰኘ ፊልም መሰራቱ አይቀርም። ስክሪፕቱንም ይሁን የእውነተኛውን ሙሰልሰል ፍፃሜ ደራሲ ደግሞ ራሱ ሲንዋር ነው። አሸውክ ወል ቁሩንፉል (እሾህና ቁርንፍድ) የተሰኘ እውነተኛ ታሪኩን ከልጅነት እስከ ሸሂድነቱ እዚያው ወራሪዋ ቢእር አስ-ሰበእ ወህኒ እያለ ፅፎታል።

ፅዮናውያኑ የድሮኗን ፉቴጅና የየሕያን ፍፃሜ መልቀቃቸው የግዛታቸውን ስረ-መሰረት አናግቶታል። እንደዚህ ስህተታቸውም የሚበሳጩበትና የሚፀፀቱበት ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም ዓለማቀፍ ምልክት ነው ያደረጉት።

አረበኛ የገራላችሁ አንብቡት

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

22 Oct, 07:11


ሲንዋር ያቺን ሰዓት

እንዳወሩበት ሳይሆን እንደ ወንዶቹ ፊት ለፊት ከመሬት በላይ ሆኖ ሲዋጋና ሲያዋጋ ቆየ። በአንድ አጋጣሚ ከሁለት አጃቢዎቹ ጋር በቅኝት ላይ ሳለ የወራሪ ሀይሎች ታንክ ሳይቀር ታጥቀው ሲንቀዋለሉ አይን ለአይን ተፋጠጡ። ሶስቱ ጀግኖች ከባድ መሳርያ የታጠቁትን ወራሪዎች ለመጋፈጥ ደጀን ፍለጋ ወደ አንድ ህንፃ ገቡ። ቦቅቧቆቹ ግን ለሶስት ነፍስ አንሰው ህንፃውን በታንክ ደጋግመው መቱት። ህንፃው በከፊል ፈረሰ። ውስጥ ያሉት ጀግኖች ቆሳሰሉ። ብዙም ሳይቆይ በድጋሜ ሌላ የታንክ አረር ህንፃውን መታው ያኔ ሁለቱ አጃቢዎቹ በክብር ተሰዉ። የህንፃው ውስጥ ከነቤት እቃው በአቧራ ተሞላ። ሲንዋር ቀኝ እጁ እና ወገቡ ገደማ ላይ በታንክ ፍንጥርጣሪ ክፉኛ ቆሰለ። እናም የስንብቱን ታሪካዊ ክዋኔ ጀመረ።

ሲንዋር ወታደራዊ ዩኒፎርሙን እንደለበሰ ክላሹን ተደግፎ በቤቱ ጥቅ ያየውን በትር አነሳና በሱ ተመርኩዞ የወንድሞቹን ፊት ሸፍኖና ዱዓ አድርጎላቸው ክህንፃው ብዙም ወዳልተጎዳው ክፍል አዘገመ። በተረጋጋ መንፈስ የሸሀዳውን ፅዋ ለመጨለጥ አቧራ ለብሶ አቧራ ለበሱ ሶፋ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ። ወታደራዊ ዩኒፎርሙን ከነ ጥምጣሙ በአንድ ሙጃሂድ ኩነት አስተካከለ። ጀርባውን ለወራሪዎች መግቢያ በር ሰጥቶ ፊቱን ደግሞ ወደ ቁድስ አቅጣጫ አቅጣጭቶ ጉዞውን ሊቋጭ ዝግጁ ሆነ። የቆሰለውን እጁን በቅዳጅ ጨርቅ ግጥም አርጎ አሰረ። ክላሹን በእግሮቹ መሀል አፈሙዙን ውደላይ ሰድሮ አቆመው። በትሩን ባልተጎዳው የግራ እጁ ያዘው። በተጎዳ እጁ ከወራሪ ኮረኔል የማረከውን ሳይለንሰር የተገጠመለት ሽጉጥ ይዟል። በከፍተኛ ተመስጦ ደረቱን ነፍቶ ከጌታው ጋር እያወራ ወራሪዎችን መጠባበቅ ያዘ። ነገር ግን 24 ሰአት ሙሉ ዝር ያለ የጠላት ወታደር የለም። ፍርሀታቸው ካልሞቱስ በሚል እሳቤ ደጅ አቁሟቸዋል።

ሙሉ ቀን ከነ ለሊቱ ካለፈ በኋላ በአስርት የሚቆጠሩት ወታደሮች ሲንዋር ወዳለበት ለመግባት አልደፈሩም። በስተመጨረሻም ፈሪ ወደ ህንፃው ከመግባቱ በፊት ውስጡን ለመሰለል ድሮን ካሜራውን ላከ። ሲንዋር በእርጋታ በተቀመጠበት የጠላቱን ድሮን ድምፅ ሰማ። ደሙ ለ 24 ሰአት ሲፈስ እና ያለምንም የህክምና እርዳታ ቢቆይም ባለ በሌለ ሀይሉ በእጁ የያዘውን በትር ወደ ድሮኑ ወረወረ። የመጨረሻውን አቅሙን ለጥቃት ተጠቀመበጥ እስከመጨረሻው ተጋደለ። ድሮኑን የሚያበረው ፈሪ የወራሪ ወታደር ከፍርሀቱ ብዛት ድሮኑን ለቀቀው። ትዝ ሲለው ቦታው ላይ ያለው ድሮኑ እንጂ እሱ አይደለም። እናም መልሶ ድሮኑን ተቆጣጥሮ ተረጋጋ። ውስጥ ያለው ሲንዋር መሆኑን ገና አሁን ማወቃቸው ነበር። እስከዚህ ቅፅበት ድረስ ተራ የሃማስን ወታደሮች እየተዋጉ እንጂ ሲንዋርን መጋፈጣቸውን አያውቁም ኖሯል። ፈሪነት ቤት ሲሰራ የእስራኤልን ወታደር ይመስላል። ለአንድ ነፍስ ድሮን እና ታንክ የሚተኩስ ወታደር የእስራኤል እንጂ የሌላ አይደለም። ወታደሮቹ ሲንዋርን ከበነዋ ብለው አሳወቁ ቴላቪቭ ውሸት አለች። ሲንዋርኮ በቀላሉ አይገኝም አሉ። እንደነሱ መስሏቸው። ቢሆንም ህንፃውን ምቱትና ግደሉት ከዛ ጣቱን ቆርጣቹ ላኩት ብለው ትዕዛዝ አስተላለፉ። ሲንዋር እንደዚያ ተጎድቶም ሊጠጉት አልደፈሩም። ከርቀት በታንክ ህንፃውን ደጋግመው መትተው ናዱት። የሲንዋር ሶፋ ሲንዋርን ይዞ ፍርስራሽ ውስጥ ገባ። ናዳ ተጫጫነው። ሲንዋን እንደ ጀኛ ፊት ለፊት ተጋፍጦ ሞተ። የጀግናውን ወኔ ድሮኑ ነግሯቸዋል። ቢገቡ አስሩን ጥሎ እንደሚወድቅ አውቀውታል። እነሱ ህይወታቸውን በሚወዱት ልክ ሲንዋር ሞቱን ይመኘው ነበር። እናም ተሳካለት። ታላቁ ሙጃሂድ ትጥቁን እንደታጠቀ ሰማዕትነትን ተቀበለ። ታሪክ ፅፎ አለፈ። ህያው ትግልበአስረክቦ ነጎደ። በኋላም ከፍርስራሽ መሃል ሲንዋርን አዩት። ለአንድ ሰው በሚሊዮን ዶላር የሚገመት መሳርያ ማፍሰሳቸው አሳፈራቸው። ለአንድ ሰው ታንክ መተኮሳቸውን ዓለም አውቆ እንዳያፌዝባቸው ሰጉ። እናም የሞተውን የሲንዋር ግንባር በጥይት ነደሉት። በተኩስ ልውውጥ የሞተ ለማስመሰል። ጀግናው ግን ህይወቱን ለሰጠለት ዓላማ የመጨረሻ ህቅታውን ሰጠ። ዘመን የማይረሳው ደናቅና አክብሮት የሚያስቸር አሟሟት። ታሪካዊ ማንነት። የጀግና ምሳሌ። የህያ ሲንዋር። ድል ለፍልስጤማውያን!

Ⓒሳሊህ አስታጥቄ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

21 Oct, 15:09


“በእሳት እየተቃጠልን እያያችሁ ዝምታን መረጣችሁ” - እናት እና ልጆች በእሳት ቃጠሎ ያጣው ቤተሰብ




ማሳሳቢያ፡ ይህ ታሪክ አንባቢያንን የሚረብሽ ገለፃ ይዟል

ሰብዓዊነት የጠፋ ይመስላል። አቅም ያላቸው የሚባሉ መሪዎች እንኳ እያዩ ምንም እያደረጉ አይደለም።

አሕመድ አል-ዳሉ እንዲህ ነው እምነቱ። ቤተሰቡ በእሳት ሲቃጠል ተመልክቷል። ይህ ምሥል መቼም ከአእምሮው የሚጠፋ አይመስልም።

“ከአሁን በኋላ ሕይወት የለኝም” ይላል።

ሰኞ ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም. ወንዶች ልጆቹ እና ሚስቱ ጋዛ ውስጥ አል-አቅሳ በሚባል ስፍራ በእሳት ተቃጥለው ሞቱ። ከዚህ በኋላ በሕይወት ላይ ተስፋ ቆርጧል።

ከፊት ለፊቱ በጨርቅ የተጠቀለለ አስከሬን አለ። የ12 ዓመት ወንድ ልጁ አብዱልራህማን አስከሬን ነው። የመጨረሻ ልጁ።

በእስራኤል ጥቃት በተነሳ እሳት ምክንያት ነው ልጁ ተቃጥሎ የሞተው። በቃጠሎው ተጎድቶ አራት ቀናት ሆስፒታል ቆይቷል። ከመሞቱ አንድ ቀን ቀድሞ አሕመድ ሆስፒታል ተገኝቶ ልጁን አይቶት ነበር።

“አባዬ አታስብ፤ ደኅና ነኝ። ደኅና ነኝ አባዬ። አትፍራ” ለመጨረሻ ጊዜ ከልጁ የሰማው ድምፅ ነበር።

አሕመድ እንባ እየተናነቀው ነው የሚናገረው።

“ሦስት ጊዜ ከእሳት ውስጥ ላወጣው ሞከርኩ። ነገር ግን ሰውነቱ ወደ እሳቱ ወደቀ” ይላል።

ታላቅ ወንድሙ የ19 ዓመቱ ሻባን እና የ37 ዓመት እናቷ አላ በዚሁ ምሽት በተነሳው እሳት ሞተዋል።

ሻባን የጋዛ ስቃይ መለያ ምልክት ሆኗል። በሕይወት ሳለ በእሳት ሲቃጠል የሚያሳይ ዘግናኝ ምሥል በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ተሠራጭቷል።

አሕመድ ፊቱ እና እጁ በእሣት ተቃጥሏል። ሚሳዔሉን የተኮሰው ፓይለት እና ትዕዛዙን የሰጡት መሪዎች “ልቤን ሰብረውታል፤ ቅስሜን ሰብረውታል. . . እሳቱ ቢበላኝ ይሻል ነበር” ይላል።

የምስሉ መግለጫ,አሕመድ አል-ዳሉ ከእሳት ቃጠሎው ቢተርፍም ፊቱ እና እጁ ላይ ጉዳት ደርሶበታል

ጥቃቱ የተፈጸመው ሰኞ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ለሊት 7፡15 ሰዓት አካባቢ ነው።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል (አይዲኤፍ) ዒላማ ያደረግነው የሐማስን “የዕዝ እና የቁጥጥር” ማዕከል ነው ይላል። ጥቃቱ የደረሰው ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በአል-አቅሳ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ነው።

ሐማስ ሆስፒታሎች ውስጥ አልገኝም ሲል ወቀሳውን ያስተባብላል።

በጥቃቱ ምክንያት አራት ሰዎች ወዲያውኑ ሲገደሉ በርካቶች ከፍተኛ የተባለ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የእስራኤል መካለከያ ኃይል ሁኔታውን “እያጣራሁ ነው” ብሏል።

የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ የእሳት ቃጠሎው ምሥሎች “እጅግ የሚረብሹ ናቸው” ብለው እስራኤል ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ የበለጠ ጥንቃቄ እንድታደርግ አሳስበዋል።

“እስራኤል ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የመጠበቅ ግዴት አለባት። አሁን የተፈጠረው ነገር በጣም የሚረብሽ ነው። ሐማስ በሆስፒታሉ አካባቢ ሰላማዊ ዜጎች እንደ ምሽግ ቢጠቀም እንኳ የሆነው ነገር የሚረብሽ ነው።”

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታኒያ እና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት በጋዛ ጦርነት ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት አሳስቦናል ብለዋል።



የምስሉ መግለጫ,የተፈናቀሉ ሰዎች የተጠለሉበት ቦታ ላይ የደረሰውን የሚሳዔል ጥቃት ተከትሎ የተነሳው እሣት

በጋዛው ጦርነት ሰዎች በእሳት እየተቃጠሉ ነው፤ በከባድ የጦር መሣሪያ እየተገደሉ ነው፤ በየቀኑ እየተተኮሰባቸው ነው።

ከፍርስራሶሽ ውስጥ የተረፉ ሰዎችን ለማውጣት የሚደረግ ጥረት፣ ሆስፒታሎች ውስጥ ያለው መረበሽ፣ መጨረሻ የሌለው ቀብር በካሜራ ዕይታ ውስጥ ገብተው ይሆናል። ብዙውን ጊዜ ግን እነዚህ ግድያዎችን በካሜራ ስላልተቀረጹ ዓለም አላያቸውም።

የሻባን አል-ዳሉ አሟሟት ይለያል። እጆቹ ከእሳቱ ለመውጣት ሲሞክሩ ይታያሉ። በፍም እሳት የተከበበ ሰው ይታያል። የሚደርስለት ግን አጥቷል።

ከቃጠሎው በኋላ የሻባን ቪድዮዎች እና ፎቶዎች በማኅበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት መሰራጨት ጀምሯል። ሻባን ታዳጊ ነበር። የማኅበራዊ ሚድያን ኃይል ያውቀዋል። የየዕለት ተግባሩን በስልኩ ካሜራ ያስቀምጣል።

ስልኩ ውስጥ የተገኙት ቪድዮዎች እና ፎቶዎች ብዙ ነገር ያሳያሉ። ደም ሲለግስ ይታያል። ሌሎችም እንዲለግሱ ያበረታታል።

ቢቢሲ ከቃጠሎው የተረፉትን የሻባንን ቤተሰቦች አናግሯል። ቢቢሲ አካባቢው ባሉ ወኪሎች አማካይነት ነው ይህን ማድረግ የቻለው። ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ወደ ጋዛ ሄደው እንዲዘግቡ ከእስራኤል ፈቃድ አልተሰጣቸውም።

ሻባን በጋዛው ጦርነት ምክንያት ከቤተሰቡ ጋር ሦስት ጊዜ ተፈናቅሏል። ሁለት እህቶች እና ሁለት ታናናሽ ወንድሞች አሉት።

“የምንኖርበት ሁኔታ አስከፊ ነው” ሲል በቀረጸው ቪድዮ ላይ ይታያል። “ቤት የለንም፣ ምግብ አጥሮናል፣ መድኃኒትም የለንም” ይላል።

ይህን ቪድዮ ሲቀርጽ ከኋላው የእስራኤል ድሮን ድምፅ ይሰማል። ድሮኗ አካባቢውን ትሰልላለች። ይህ የጋዛ ነዋሪዎች የዕለተ ዕለት እውነታ ነው።

የሻባን እና አብዱልራህማን ወንድም ሞሐመድ አል-ዳሉ ታላቅ ወንድሙን ለማዳን ወደ እሳቱ ውስጥ ገብቶ እንደነበር ለቢቢሲ ይናገራል። ነገር ግን ሌሎች ሰዎች ይዘውት ነው የተረፈው። የዚያን ዕለት ውጪ ነው ያደረው። መንገድ ላይ ተኝቶ የወንድሞቹን ዕቃ እየጠበቀ።

የምስሉ መግለጫ,የሻባን እና አብዱልራህማን ወንድም የሆነው ሞሐመድ አል-ዳሉ

ሞሐመድ ወንድሞቹ ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ አቅራቢያ አነስተኛ ጥላ ዘርግተው ምግብ ይሸጡ እንደነበር ያስታውሳል።

“ጠንክረን ሠርተን ያገኘውን ነገር በጥንቃቄ እንጠቀማለን። ያለን ነገር ሁሉ ሠርተን ያገኘነው ነበር። ሠርተን እንበላለን፤ ሠርተን እንጠጣለን። አሁን ግን ያለ ነገር ሁሉ ወድሟል።”

ሞሐመድ የቤተሰቡን የተቃጠለ አስከሬን ቢመለከትም ማወቅ የቻለው የእናቱን ብቻ ነው። ምንም እንኳ የእናቱ ሰውነት በእሳት ክፉኛ ቢጎዳም እጇ ላይ ባደረጉት አምባር ምክንያት ለይቷቸዋል።

“አምባሩን ባላየው ኖሮ እናቴ መሆኗን እንኳ መለየት አልችልም ነበር። እጇ ከሌላው የሰውነት ክፍሏ ተለያይቶ ነበር። ነገር ግን አምባሯ አለ። ከእጇ ላይ ወስድኩት።”

የእናቱ አንድ የቀረው ማስታወሻ ከእሳት ከተረፈው አስከሬኗ ላይ ያገኘው አምባር ነው።

የአል-ዳሉ ቤተሰብ ድንጋጤ ላይ ነው። የተረፉት ሐዘን ላይ ናቸው። “መግለፅ ይከብደኛል” ይላል ሞሐመድ።

“ለሰዎች ለማስረዳት እሞክራለሁ፤ ነገር ግን አይሆንልኝም። የገዛ ወንድሜ በእሳት ሲቃጠል አየሁት። እናቴም በእሳት ተቃጥላ ስትሞት አየኋት” ይላል።

“ምን እስኪሆን ነው የምትጠብቁት? ምን እስኪሆን ነው ዝም የምትሉት? በእሳት ስንቃጠል እያያችሁ ዝምታን መረጣችሁ?” ሲል የዓለም ማኅበረሰብን ይጠይቃል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

21 Oct, 14:52


አጫጭር መረጃ

ዬዲዮት አህሮኖት በጀባሊያ በቀጠለው ውጊያ ውስጥ የሚገኙትን የእስራኤል መኮንኖች ጠቅሶ እንደዘገበው "ቀደም ሲል በእስራኤል ጦር የተመቱ የሃማስ ሃይሎች ዋሻዎች እንደገና መገንባታቸው አስገርሞናል" ሲሉ ገልጿል።

- 7 እስራኤላውያን አይሁዶች ለኢራን ሲሰልሉ እንደነበር በመግለጽ በቁጥጥር ስር አውላለች። የእስራኤል ጦር የደህንነት ተቋማት ፎቶግራፎችን አንስተው ለኢራን ሲያስረክቡ ነበር ተብሏልም።

-እስራኤል ኢራንን ለማጥቃት ያወጣችዉ እቅድ መረጃ ማፈትለኩን በተመለከተ አሜሪካ ጉዳዩን እንደምታጣራ አስታወቀች


-የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ በጋዛ የሚገኘውን የ401ኛ ጦር መሪ የነበሩት ኮሎኔል ኤሳን ዳክሳን ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
ወታደራዊ አዛዡን በሃማስ ያጣው የእስራዔል ጦር በዛሬው ዕለት የሃዘን ቀን አውጆ ውሏል፡፡ 

-እስራኤል ሄዝቦላህን ይደግፋሉ ያለቻቸውን በመዲናዋ ቤይሩት እንዲሁም በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ ባንኮች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች።
@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

20 Oct, 19:55


ይህቺ የሸሂድ ሲንዋር ስታይል በጣም ታስገርመኛለች ሶፋ ላይ ተቀምጦ በፈራረሰዉ ጋዛ የለቀቀዉ ፎቶ ዝነኛ ነበር ሲሞትም ሶፋላይ ተቀምጦ ነበር ታዲያ ወራሪዋ እስራኤል የያህያ ሲንዋር አስክሬን ፎቶ በወረቀት ስትበትን ነዉ የዋለችዉ ፁሀፋም ከዚህ ቡኋላ ሲንዋር የለም ሀማስ የለም ይላል በሰላም መኖር የፈለገ እጅ ይስጥ ይላል ለወራሪዋ ጋዛዊያን የሰጡት ምላሽ ፎቶዉን እንደምታዮት አጋርተዋል በዚህ የተበሳጩት አይሁዳዊያን የህያ ሲንዋር ጠላቶቹን እየተዋጋ የተሰዋበትን ቤት ከ ደቂቃዎች በኋላ አፈነደዋለሁ በማለት የወራሪዋ ጦር መግለጫ ማውጣቱን አልጀዚራ ዘግቧል።
በቀጣይ ልክ እንደ የህያ ሲንዋር አይነት ሚሊዮን ሲንዋሮችን እናያለን ኢንሻአላህ ።
@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

20 Oct, 15:20


ይህን አሳማሚ መረጃ ልንገራችሁ!!
የአረብ ሀገራት በተለይም ኢማራት የቀይ ጨረቃ በሚባለው የግብረሰናይ ድርጅታቸው አማካኝነት ወደ ጋዛ የእርዳታ አከፋፋይ ሰዎችን ይልካሉ።
ያው ሀማስም ሙሉ ውጊያ ላይ በመሆኑና የሚቆጣጠር አካል ስለሌለባቸው ገብተው የሚሰሩት ስራ እርዳታ ማከፋፈል አይደለም።

ከዚያ ይልቅ የሀማስ እዝ የት እንዳለ ፣ ሮኬቶችን ከየት ቦታ እንደሚያስወነጭፍ ፣ አመራሮቹ የት ሆነው እንደሚያዙ ፣ የእዝ ሰንሰለቱ ምን አይነት እንደሆነ ወዘተ ሁሉንም ነገር ለእስራኤሉ ሞሳድ ፣ ሺን ቤት እና ለአሜሪካው ሲአይኤ መረጃዎችን የማቀበል ስራ ይሰራሉ።
ይህ የተረጋገጠ ሀቅ ነው የምነግራችሁ። አረቦች በአንድ ነገር ደስተኛ አይደሉም እርሱውም እስራኤል ጦርነቱን ቶሎ ባለመጨረሷ ነው። በዚህ አሜሪካም ደስተኛ አይደለችም።

በአሁኑ ሰአት ለሙስሊሙ አለም ከአረቦ ነገስታቶች በላይ ጠላት የለውም። ነገርታቶቹ የህዝባቸውን አእምሮ ማጠብ የቻሉትን አጥበው የተቀረውንና አልሰማም ያለውን ደግሞ አሳማሚ ቅጣት እየቀጡ ባሪያ አድርገውታል።

አረቦች የገዛ ዜጎቻቼውን የሚሰልሉት በእስራኤል እና አሜሪካ የስለላ ተቋማት አማካኝነት ነው። ከነርሱ እይታ የሚወጣ አንድም ነገር የለም። የአረቦችና የእስራኤል የስለላ ተቋማት በጥምረት ነው የሚሰሩት። የጋራ ጠላቶቻቼው የሆኑትን የሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄና የኢራን መሩን የትግል ግንባር ለማፍረስና ለመቋቋምም አብረው ይሰራሉ።

እና የሙስሊሙ አለም ነፃ የሚወጣው እነዚህን ባሪያ መሪዎች ሲያስወግድ ብቻ ነው። እስከዚያ ዋጋ እየከፈለ ይቀጥላል!

የኢማራት አገዛዝ ፈራርሶ አላህ ያሳየኝ!
ይህች ሸይጧን ሀገር በሙስሊሙ ላይ ያደረሰቺው ውድመት ተገልፆ አያልቅም! በመካከለኛው ምስራቅ ሸይጧናዊነትን በማስፋፋት የሚቀድማት አንድም ሀገር የለም!

via sied mohamed
https://t.me/palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

20 Oct, 09:28


ማንኛውም የቴሌቪዥን የሚዲያ ሞስኮት የምመለከትበት ጊዜም ሰዓቱም የለኝም እኔ የሚቀናኝ በስልኬ የምመለከታቸዉ ፕላትፎርም የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ብቻ ነዉ እነዚህ የ NBC ETHIOPIA TV በ ዮቲዮብ አንዳዴ ይደርሱኛል እንደነዚህ ሰዎች የመካከለኛው ምስራቅ ኢሲያ ጂኦፖለቲካ የገባቸዉ የለም ይተነትኑታል አይገልፅም ያሰላም ።ከእዉነት ጋር የቆመ ጋዜጠኛ ይመቸኛል ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

19 Oct, 18:54


እነዚህ ቀሽም ኢማራቶች

አረብ ኤሚሬትስ በሶማሊላንድ እስራኤል ወታደራዊ ሰፈር እንድትገነባ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በአፍሪካ ቀንድ “ስትራቴጂካዊ” የእስራኤል ወታደራዊ ኃይልን ለመመስረት አቅዳለች።

ኤሚሬትስ ሌክስ እንደዘገበው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ይህን ሃሳብ በሚስጥር ያቀረበች ሲሆን ለእስራኤል ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግም ቃል ገብታለች።

አቡ ዳቢ የሶማሊላንድ ባለስልጣናትን እስራኤል ለሶማሌላንድ ይፋዊ እውቅና መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን በማቅረብ ማሳመን ችላለች።
ሶማሌ ላንድ ለሀገር እዉቅና ስትል ለእስራኤል ከፈቀደች ፍልስጤማውያን እንደካደች እቆጥረዋለሁ እስራኤል የመን ሀዉቲዎች የዘጉባትን ወደብ በሶማሊያ መጠቀም ስለፈለገች ነዉ እንዲሁም ኢራን እና ቱርክ የሶማሊያ ላንድ የባህር ሀይል ስላሰጋት ነዉ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

19 Oct, 11:33


ብሎ ነበር

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

19 Oct, 11:31


ሃማስ ከጋዛ ውጪ ከሚገኙ አባላቱ አዲስ መሪ ለመሾም እየተመካከረ ነው
የሞቱ መሪዎቹን በፍጥነት የመተካት ልምድ ያለው ሀማስ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል በሆነው የሹራ ካውንስል አዲስ መሪ እንደሚሾም ይጠበቃል። የሟቹ ያህያ ሲንዋር ወንድም ሞሀመድ ሲንዋር በጋዛ ከእስራኤል ጋር የሚደረገውን ውግያ በማስተባበር እና በመምራት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ግምት አግኝቷል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

19 Oct, 08:00


የኔታኒያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ።

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ቡድን በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል።

የድሮን ጥቃቱ በሰሜን ቴል-አቪቭ ኬሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ መፈጸሙ ነው የተነገረው።ግን በቤቱ ዉስጥ ከነቤተሰቡ አልነበረም

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

18 Oct, 16:43


ቀጣይ የሀማስ መሪ ማን ነዉ የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ነዉ ።መልሱ የሀማስ መሪ ከዚህ ቡኋላ ይፋ እንደማይሆን ተረጋግጧል ይህም ጠላትን ያስፈራል ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

18 Oct, 07:26


ሐማስ አንድ ግለሰብ አይደለም። ሐማስ ተቋም አይደለም። ሐማስ ግፍ እና ጭቆና የወለደው ብሶት ነው። ጭቆናው እስካልቆመ ድረስ በሰው መሞት ሐማስ አይሞትም ሊሞትም አይችልም። በመሪ መገደል ሐማስ አይከስምም አይነጥፍም። ሰው እንጂ ሀሳቡ አይሞትም። መሪ እንጂ ትግል እቅድ አይሞትም ..!በመላዉ አለም ሰላተል ጅናዛ ይሰገዳል ተብሎ ይታሰባል ሲንዋር የጀነት በር ይከፈትልህ የጀነት ምንጣፍ ይነጠፍልህ ያ ሸሂድ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

18 Oct, 05:57


This is how all the sons of the Palestinian people are, fighting until the last breath, because they are defending their land and their people to get rid of the terrorist Zionist occupation that is insanely supported by the European Commission, the United States of America and Britain, who claim false human rights and false democracy.

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

18 Oct, 05:25


የእስራኤል ጦር በለቀቀው የድሮን ፉቴጅ የመጨረሻ የሲንዋርን ሰአታት ማሳየት ችሎ ነበር። በታንክና ከባድ መሳርያ ተኩስ ባደረሱበት ጥቃት አንድ እጁን አጥቶ እንኳን በስናይፐር እስከተገደለበት ቅጽበት በጽናት እየተዋጋቸው ነበር። ህዝቡን ማግዶ ከኃላ የሚቀር መሪ አልፈጠሩም፣ ከዋሻ ጀርባም ወታደር እየላከ አልተዋጋቸውም። ፊት ለፊታቸው ተዋድቋል፣ አልሸሸም፣ አልዞረም። ሲያገኙት ከነ መሳርያው ነው። እየሞተ ሳይቀር ድል አደረጋቸው..!እናትማ እናንተን ወልዳለች..!

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Oct, 17:55


ያረብ 🫀

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Oct, 17:40


ኦሳማ ሐምዳን ከደቂቃዎች በኋላ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣሉ ።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Oct, 15:22


የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መግለጫ፡- 

377 ኛው ቀን የያዘዉ በጋዛ ጦርነት ላይ

የ"እስራኤል" ወረራ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ጭፍጨፋ የፈፀመ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 29 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 93 ቆስለዋል።

አንዳንድ ተጎጂዎች አሁንም በፍርስራሹ ውስጥ እና በጎዳናዎች ላይ ይገኛሉ, እናም አምቡላንስ እና የሲቪል መከላከያ ቡድኖች ሊደርሱላቸው አልቻሉም.

ካለፈው ጥቅምት 7 ጀምሮ በ"እስራኤል" ጥቃት 42,438 ፍልስጤማውያን ሰማዕታት ሲሆኑ 99,246 ቆስለዋል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Oct, 15:16


ያህያ ሲንዋርን እና መላዉ የፍልስጤም ሙጃሂዶችን አላህ ይጠብቃቸው

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Oct, 15:00


ከአሜሪካ እስርቤት ወጥቶ በሰላም ወደ ትዉልድ ሀገሩ አልጄሪያ ከቤተሰቦቹ ጋር ተቀላቅሏል ሀምዛ

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Oct, 13:40


https://t.me/palestine_quds/2101

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

17 Oct, 13:40


መረጃ መንታፊዉ ሀከር የምእራባውያን ራስምታት ሀምዛ ለ12 አመት የእስር ስቃይ በሰላም ተለቋል ከዚህ ቀደም በርካታ የአሜሪካ እና የአዉሮፓ ባንኮችን ሀክ አድርጎ ለፍልስጤማውያን እና በችግር ላሉ አፍሪካውያን መስጠቱ ይታወቃል በእስራኤል ላይም የሳይበርጥቃት አድርሷል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

15 Oct, 18:30


የእስራኤል እና የአረቡ አለም ሚዲያዎች እንደዘገቡት የሐማሱ መሪ የህያ ሲንዋር በቅርብ 'ከሳምንታት ዝምታ' በኋላ ከኳታር አደራዳሪዎች ጋር እንደገና መነጋገሩን ዘግበዋል።

በሲንዋር ሃሳብ ዙሪያ አንድ የእስራኤል ባለስልጣን ለዋላ ጋዜጣ እንደገለፀው በእስረኞች ልውውጥ እና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ  አሁንም ሲንዋር አቋሙን አላለሰሰም ሲል ገልጿል። አሁንም የእስረኞች ልውውጥ ለማድረግ  እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ከጋዛ ለቀው እንዲወጡ እና ጦርነቱ በዘላቂነት እንዲቆም ማድረግ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ሲንዋል አሳውቋል ብሏል የእስራኤሉ ባለስልጣን።

ዛሬ፣ የእስራኤሉ ጀሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ሲንዋር 'በድብቅ እንደሚንቀሳቀስ' እና በየወሩ አንድ ጊዜ በመውጣት ብቻ ስለ ውጊያው ሰፊ መመሪያዎችን ይሰጣል። ሪፖርቱ እንዳስቀመጠው "አጠቃላይ ፖሊሲዎችን እና ቀይ መስመሮችን ብቻ ያብራራል እንጂ ሁሉንም ቀጥተኛ ትዕዛዞችን እምብዛም አይሰጥም" ቀጥተኛ ትእዛዝ የመስጠት ኃላፊነቱን አሁን ወንድሙ መሐመድ ሲንዋር እየመራ ነው።

ይህ የሲንዋር የተጠና እንቅስቃሴ “በድርድሩ” ላይ የሚደረገውን ጥረት ያወሳስበዋል ብሏል። በተጨማሪም ሲንዋር በእስራኤል፣ በኢራን እና በሂዝቦላህ መካከል ባለው ሰፊ ግጭት ውስጥ ያሉትን ሂደቶችና ውጤታቸውን እየተመለከተ ነው ይላል።

ዘገባዎች በተጨማሪም ሲንዋር መልእክት የሚያስተላልፈው በብዕር እና በወረቀት ብቻ ሲሆን አንዳንዴ ብቻ በድምጽ መልእክት ያስተላልፋል እንጂ ምንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ በዙሪያው እንዳይኖር አድርጓል።
@Palestine_quds

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

13 Oct, 19:18


የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ አባል ዒዘት አልሪሽቅ:-

እነዚህ በጋዛና በሊባኖስ ሴቶችንና ሕጻናትን በቦምብ የደበደቡ ደማቸውን ከምግብ ጋር የቀላቀሉ የናዚ ጽዮናውያን ወታደሮች ናቸው። አሁን እነሱም በዚያው ጽዋ እየጠጡ ነው።

"ተጋደሏቸው። አላህ በእጆቻችሁ ይቀጣቸዋል፣ ያዋርዳቸዋል፣ በነሱም ላይ አሸናፊ ያደርጋችኋል፣ የምእመናን ሕዝቦች ልቦችም ይፈወሳሉ።"

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

13 Oct, 19:13


"ጋዛ ሆይ ደስ ይበልሽ የአላህ እውነተኛ ቃል ተቃርቧልና" በሚል ሂዝቦላህ የሚከተለውን ቪዲዮ ለቋል።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

13 Oct, 18:34


የመጨረሻው መጀመርያ          ክፍል 2
በማሂ ማሂሾ
አለም በእንቅልፍ ሰመመን ተውጣለች። በተለይ ሙስሊሙ በህልም አለም ውስጥ ይዳክራል። በቁሙ የተኛም ሞልቷል። እየሄደ የሚያንቀላፋም እንዲሁ። ብቻ ከአንድ አቅጣጫ ከእንቅልፍ የተራራቁ ሳቅ ደስታቸውን ዋጥ አርገው የገዘፈ አላማን ያነገቡ አይሁዶች ጉርጓድ ምሰው ሊቀብሩን ደፋ ቀና ይላሉ።

ለተከታታይ ሁለት ሺህ አመታት ሲጠባበቁት የከረሙት ቀያይ ላሞች ተወልደው ሁለት አመታት እስኪሞላቸው በጥብቅና በድብቅ ቦታ አኑረው አፈፃፀሙን አቅደው የአይሁድን ስርወ መንግስት ሊመሰርቱ ደፋ ቀና ይላሉ። የቀሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳ ከዛሬ ሶስት ወር በፊት በሰጠው መግለጫ ላይ የጠቀሳቸው ቀያዮቹ ላሞች ምንድነው አላማቸው

በሚሽናህ ገለፃ በኦሪት ማብራሪያ አንዲት የፀጉር ዘለላዋ በሌላ ከለር ያልቀለመ፣ ያልወለደች፣ ገመድ በአንገቷ ላይ ያልጠለቀ፣ ያልተጋለበች ንጹህ ሙሉ በሙሉ ቀይ ላም!

ተወልዳ ሁለት አመት እስኪሞላት ተንከባክበው አሳድገዋታል። አይሁዶችን ከርኩሰት ለማንጻትና መስጂደል አቅሳን በመቆጣጠር የአዲሱን ቤተመቅደስ ምሶሶ ለማቆም የዚህችን ቀይ ላም መወለድ ለበርካታ አመታት ሲጠባበቁ ከርመዋል።

የግዙፏ እስራኤል ምስረታ ይሉታል። አለም በአይሁድ መመራት የምትጀምርበት አመት ሲሉም ይጠሩታል። አይሁዶች ወደ መስጂደል አቅሳ እንዳይገቡ የሚከለክለው ድንጋጌ የሚሰረዝበት ወቅት ስለመሆኑ ደጋግመው ይለፍፉበታል።

ይህን በጥልቅ ለመረዳት አመታትን ወደኋላ ተጉዘን በሙሳ ክፍለ ዘመን ላይ እንክተም። ቁርኣን በሱረቱል-በቀራህ ከአንቀፅ 67 እስከ 73 በሰፊው ስለ ላሚቷ ያወሳል። አይሁዶች እንዲያርዱት የተጠየቁትን ላም ይዘቷንና ከለሯን በጠየቁ ጊዜ ቢጫ ስለመሆኗ ይናገራል። አዎ! አይሁዶች እንዲያርዱ የተጠየቁት ላም ቢጫ ነበረች። ከጊዜ ወዲህ በይተል መቅዲስን ለማውደም መሳሪያ ትሆን ዘንድ መልኳ ወደ ቀይነት ተለወጠች በዕብራይስጠኛ ሰፍራዕ የሚለው ቃል ደማቅ ቀይ ማለት ነው ይሉናል የቋንቋ ሊቃውንቱ።

አይሁዳዊያን ላልሆኑ ህዝቦች ጥፋትና ውድመት ክስረትና እልቂት ለአይሁዶች መዳኛዋን ላም ለማግኘት ጥልቅ ሙከራዎች ከተጀመሩ ሰነባበቱ። ታዋቂው የቤተመቅደስ ተቋም የሆነው temple institute በ1987 ከተመሠረተበት ዕለት አንስቶ ከሌሎች የጽዮናውያን ተቋማዊ ድጋፍ እየተደረገለት እነዚያን ቀያይ ላሞች ለማግኘት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ማነፍነፍ ጀመረ።

ከአስራ አምስት አመታት በፊት በወራሪዋ ሀገር አምስት ቀያይ ላሞች መወለዳቸው ተሰማ። በኔጌቭ በረሃ ወደሚገኝ ሚስጥራዊ እርሻ ተወሰዱ።  ግና ሁለተኛ ዓመታቸውን በቅጡ ሳይሞሉ ጥቋቁር ፀጉሮች ከጀርባቸው መሐል ተገኙ። በዚህም አይሁዶችን በደም በአመዳቸው የማጥራት ክብራቸው ተገፈፈ።

ሚስጥራዊው ፍለጋ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ እስከ 2022 ዘለቀ። በድንገት አምስት ቀይ ላሞች በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ባለ ዘመናዊ እርሻ ውስጥ የመወለዳቸው ዜና ዳግም ሲሰማ በልዩ እጀባ ከዮርዳኖስ ሸለቆ በስተሰሜን ወደሚገኘው በይሳን ከተማ ተወሰዱ። የቤተመቅደስ ተቋም በሆነው ምስጢራዊ እርሻ temple institute ውስጥ በአክራሪ አይሁዳዊያን ክትትል ይደረግላቸው ገባ።

የጀግና አቀባበል የተደረገላቸው እኚህ ላሞች በምንም መልኩ ያልታለቡ የተለመደው ፀጉራቸውን በሚቀይሩበት ወቅት ሌላ ቀለም ያለው አንዲትም ፀጉር ያልተቀላቀላቸው መሆኑ ተረጋገጠ።

በመፅሃፍ ቅዱሱ ገለፃ የሚታረዱበት ዕድሜ ሁለት ሲሆን ደማቸውና አመዳቸው ከምንጭ ውሃ ጋር ተቀላቅሎ አይሁድን ያድናል ያነጻቸዋል ሶስተኛው ቤተመቅደሳቸውን በተባረከው መስጂደል አቅሳ ፍርስራሽ ላይ ለመገንባት መሰረት ይጥላሉ እንዳይገቡ የተከለከሉት ትዕዛዝ በዚሁ የላሞቹ ደምና አመድ ይቋጫል ይላል።

ላሞቹ ተወልደዋል። ይስሃቅ ማሞ ከዛሬ አስራ ሁለት አመታት በፊት የእርድ ቦታውን አዘጋጅቷል። አል አቅሳ መስጂድን ቁልቁል እየተመለከቱ ከዘይቱን ተራራው ጫፍ ላይ ሊያርዱ እየተዘጋጁና የትግበራው ቀን እየተጠባበቁ በድንገት ቀሳሞቹ ጥቃት ፈፀሙ። መስዋዕትነት ከፍለው እቅድ ውጥናቸውን ሊያከሽፉ በፓራሹት እየታገዙ ጠመንጃቸውን ሰብቀው ብዙዎችን ገደሉ.....  ይቀጥላል

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

13 Oct, 17:33


የሂዝቦላ ሰው አልባ አውሮፕላኖች የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ስብስብ በመምታቱ የጅምላ አደጋ ተከስቷል።ከ25 በላይ ሰዎች መጎዳታቸው ተዘግቧል፣ በትንሹ 15 የሚሆኑ በአደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

የእስራኤል ጦር የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂ ለምን እንዳልጮኸ እየመረመረ ይገኛል።

እስራኤል ወታደሮቿን ከካምፑ በሄሊኮፕተር እያስወጣች ሲሆን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደታወጀ ተሰምቷል፤ ሃይፋ ሆስፒታል ታካሚዎችን እያስተናገደ ነው።

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

13 Oct, 04:39


"የእስራዔል መንግስት ፋሽስት እና ዘር ጨፍጫፊ ነው" - ኒካራጉዋ

ኒካራጉዋ ከእስራኤል ጋር ያላትን ድፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ አቋረጠች።

ላቲን አሜሪካዊቷ ሀገር እስራኤል በፍልሥጤም ግዛቶች የምትፈጽመው ጥቃት የሁለትዮሽ ግንኙነቷን እንድታቋርጥ ምክንያት እንደሆናት ገልፃለች።

ሀገሪቱ የእስራኤልን መንግስት "ፋሽስት" እና "ዘር ጨፍጫፊ" ስትል ጠርታዋለች።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መቋረጡን የሀገሪቱ ፓርላማ ባሳለፈው ውሳኔ ይፋ አድርጓል።  

Palestine 🇪🇹ኢትዮ🦋ፍልስጢን🇵🇸✌️

12 Oct, 19:24


በዛሬው እለት በመዲናችን አዲስአበባ
🇪🇹🇵🇸

የፍልስጤም ኤምባሲ ተወካይ እና የሊባኖስ ዲፕሎማት ጋር በመተባበር በቬንዙዌላ የቦሊቪያን ሪፐብሊክ ኤምባሲ ውስጥ የአንድነት ዝግጅ ተካሂዷል።

ዓለም አቀፍ የአብሮነት ቀን መሆኑን አስታውቋል; ሰላምን ለማራመድ እና ፋሺዝምን, ሽብርተኝነትን እና በፍልስጤም እና በሊባኖስ ውስጥ የዘር ማጥፋትን ወንጀል ለማውገዝ

በዝግጅቱ ላይ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የኢትዮ-ፍልስጤም ወዳጅነት ቡድን እና የቬንዙዌላ እና የፍልስጤም ወዳጆች ተገኝተዋል።
በዚህ ዝግጅት እጅግ በጣም የምናከብራቸው የምንወዳቸው የመካከለኛው ምስራቅ ኢዢያ የፖለቲካ ተንተኛ ደሪሲ የሆኑት አቶ አስናቀ ሲሳይ የተገኙበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል የተከበራችዉ ዉድ የኢትዮ ፍልስጤም ቻናል ተከታዮች የሰቆቃ ምድር ፍልስጤም በሚል ዝነኛ መፀሀፋቸዉ አቶ አስናቀ ማበርከታቸዉ ይታወቃል ከዚህ ቀደም በዚሁ ቻናል መፀሀፋቸዉን መዳሰሴ ይታወቃል እንድታነቡት እመክራለሁ በዚህ አጋጣሚ አቶ አስናቀ ሲሳይ በኢሜል አድራሻቸው 🇪🇹 በኢትዮጵያ ፍልስጤም🇵🇸 ቻናል ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቢያለሁ ለእዉነት የቆመ ሰዉ ምስጋና ሲያንስ ነዉ ።ድል ለፍልስጤማውያን

አብዱሰላም(አልዮ)🇵🇸✌️🇪🇹

2,753

subscribers

1,425

photos

877

videos