ISLAMIC SCHOOL️ @islam_in_school Channel on Telegram

ISLAMIC SCHOOL️

@islam_in_school


ኢስላም በትምህርት ቤት

ISLAMIC SCHOOL️ (Amharic)

ይህ የቴሌግራም ኮንትን የቴሌግራም ክትክብ እና የቴሌግራም መረጃ ፕራኤሽን ነው። "ኢስላም በትምህርት ቤት" እስከዚህ ቆጵሮ የዓለም ምርጥ እና እስከዚህ ሳይከተሉ የተለያዩ መረጃዎችን እና እንመለከታለን። ይህ መረጃዎችን በኢስላም በትምህርት ቤት ፈርተው ጸሎት እና ተመልክታ እንዲሆኑ አዝናኝ እንዲላኩ ናቸው። ከዚህ በቀላሉ አንድ ክስላም ፓትንስ ማድረግ ያለበት የቴሌረም መረጃው አዘንብልናል። ያለይቶ የቴሌግራም መረጃዎችን ለመለያያ ልምድ ይምረጡ።

ISLAMIC SCHOOL️

24 Jan, 04:44


የዳዕዋ ቲቪ አዲስ የዩቲዩብ ቻናል!

ውድ የዳዕዋ ቲቪ ቤተሰቦች ከ2ሺ በላይ የሚሆኑ የኪታብ ደርሶች፣ፈትዋዎች እንዲሁም የሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን የቁርአን ተፍሲርና የተለያዩ ኢስላማዊ እውቀትን የሚያስጨብጡ ትምህርቶችን ስናስተላልፍበት የነበረው የዩቲዩብ ገፃችን ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በመጠለፉ ጥልቅ ሀዘናችንን እየገለፅን በምትኩ አዲስ ቻናል ከፍተናል።

ስለሆነም እርሶም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን አዲሱን የዩቲዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ እንዲያደርጉና ለሌሎችም እንዲያስተላልፉ እንጠይቃለን!!!
👉 https://youtube.com/@daewatv1?si=AyREhvSL0jc-JgSn

ISLAMIC SCHOOL️

24 Jan, 04:27


ኢትዮጵያዊው ሙጃሂድ
ፍልስጤም ድረስ ዘምቶ የአል-ዐቅሳ ሰማዕታት ብርጌድ ወታደራዊ ስልጠናን ወስዶ፣ የወራሪዋ እስራኤል ጦር በ1980ዎቹ በአሪያል ሻሮን እየተመራ ሊባኖስ ቤይሩት ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት ሙጃሂዶችን በመክበብ ያካሄደውን ዘመቻ ለመመከት በተካሄደው የሞት ሽረት ፍልሚያ ላይ ተሳታፊ የነበረው ወጣት ዐብዱልመሊክ ፉጂሳ ታሪኩ እንዴት ይረሳል?! አላህ የእዝነት ካባውን ይደራርብለት።


Mahi Mahisho

ሰሉ አለ ረሱል🥰

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

23 Jan, 18:15


"ኒቃብ ሳታወልቁ አትወጡም!" - ዲላ ዩኒቨርሲቲ

ኒቃቢስት ተማሪዎችን አስታኮ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ጥግ የደረሰ የጥላቻ እና ንቀት ጦርነት የከፈተው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ቀን ተቀን እንግዳ የሆኑ ጭቆናዎችን እየፈፀመ ነው:: ኒቃቢስት ተማሪዎችን ከግቢ አባሮ ከትምህርት ከምግብ እና ከመኝታ ካራቀ 6 ቀናት ዛሬ ደፍኗል:: ከትምህርት ሚኒስቴር ጀምሮ ከሀገሪቱ ህዝብ ግብር ደመወዝ የሚተነፍሱ ተቋማትም ፀጥ ረጭ ብለዋል::

የሚገርመው ዛሬ ለራሱ ከሌላ ቦታ የEXIT EXAM ሞዴል ለመውሰድ በመኪና የገቡ ኒቃቢስቶችን ፈተና እንደጨረሱ ኒቃብ መልበሳቸውን አስተውሎ "ኒቃባችሁን ካላወለቃችሁ ከዩኒቨርሲቲው አትወጡም!" የሚልን ክልከላ አስተላልፎ በብዙ ጭቅጭቅ ነበር ተማሪዎች የወጡት::

ጥላቻ ሲያውር እንዲህ ነው ••• ከውጭ ያሉትን ካላወለቃችሁ አትገቡም በማለት በምግብ በትምሀርት እና በማደሪያ ያስፈራራል:: ከውስጥ ያሉትንም ካላወለቃችሁ አትወጡም ብሎ የቁም እስረኛ በማድረግ ለማስፈራራት ይሞክራል::

ሆኖም አይሳካላቸውም ••• አግጥጦ የመጣን ጭቆና ከእነርሱ በተሻለ ተምሮ አስተምሮ በሰለጠነ መንገድ የሚታገል ትውልድ መጥቷል::

ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

23 Jan, 15:18


አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ
ውዶች ዛሬ አንድ ቻናል ላስተዋውቃቹ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ሳይኮሎጂ ተማሪዎች አንድ ላይ በመሆን ስለ ሳይኮሎጂ እና ስለ አእምሮ ጤና በኢስላም መነፅር ሊያስቃኙን የከፈቱት ነው።
በተለያየ የህይወት ዘርፍ ላይ እገዛ ለምትፈልጉ፣ ስለ ራሳቹ በኢስላም እይታ በደንብ ማወቅ እና ራሳቹን ማሻሻል ለምትፈልጉ በጣም ጠቃሚ ነው።
በተለያዩ ጉዳዮች ግንዛቤ ለማግኘትና ጥያቄ ካላቹም ለመጠየቅ ቤታቸውን ተቀላቀሉ።
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/islamicpsychologycommunity

ISLAMIC SCHOOL️

23 Jan, 14:43


"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡" (አል-ሑጁራት 6)

ዛሬ ከዙህር ጀምሮ ከላይ ያለው ምስል ብዙ ተከታይ ባላቸው ቻናሎችና ግሩፖች ጭምር ሲሰራጭ አስተውለናል። የመስጂዱ ጀመዓዎችም ጉዳዩን ለማብራራት የሞከሩ ቢሆንም ያዳመጣቸው አልነበረም።

ለማንኛውም ጉዳዩ እንዲህ ነው፦
የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 6 አመራሮች ታቦት የሚወጣበትን ሰዐት ጠብቀው በቄራ መስጂድ ስም ከላይ ያለውን ባነር አሰርተው በቄራ መስጂድ አጥር ያለማንም እውቅና እና ፈቃድ ለጥፈው የመስጂዱን ክብር ደፍረዋል። የመስጂዱ አስተዳደሮች ጉዳዩ እንደደረሳቸው ጉዳዩን በማጣራት ባነሩን ወዲያው ያነሱት ሲሆን ይህንን ባደረጉ አካላትም ላይ ክስ እንደሚመሰርቱ አሳውቀዋል። አላህ ያግዛቸው! ጥጋበኞችንም የአላህ ቅጣት ይውረድባቸው!

ነገር ግን በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ አንድ የታዘብነው ነገር እስካሁን በኸይር የምናውቀውን መስጂድ እና ጀመዓ በቅጡ ባልተጣራ ጉዳይ ታላላቅ ከምንላቸው ሳይቀር ትችቶችን ታዝበናል። የሙዕሚን ቀልብ አላህ ዘንድ ከዱንያ እና በዱንያ ውስጥ ካሉ ነገሮች ሁሉ የበለጠ ዋጋ አለውና ያለአግባብ ወንድሞቻችንን ከመተቸት መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

23 Jan, 08:00


የደቡብ ክልል መጅሊስ ስለ ዲላ ዩኒቨርስቲዎች ጉዳይ ለፌዴራሉ መጅሊስ በደብዳቤ አሳውቋል። የፌዴራሉ መጅሊስ ምን ያደርግ ይሆን? ወይንስ ይተኛበት ይሆን?

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

22 Jan, 18:56


ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ በዲላ ከተማ ነው ••• የዚህን ያክል ተጨካክነናል?

ተመልከቱት ••• ሁሉም ያውቀው ዘንድም Share አድርጉት!

ኒቃቢስቶቹን በጨለማ ያለምንም ርህራሄ ሲመልሷቸው ይታያል:: አትገቡም ብለው ••• እስከዛሬ ገብተው ሲማሩበት ሲኖሩበት ከነበረው ግቢ መለሷቸው:: የት ይደሩ? የት ይማሩ? ይህንን እንኳን አያስቡም? ሰብዓዊነት የለም? የዚህን ያክል አውሬ ሆነዋል::

ለእስልምና እና ለሙስሊሞች በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከባድ የጥላቻ ክምር ተቆልሏል::

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

22 Jan, 17:46


የወራሪዋ እስራኤልን ጦር የፈረካከሰ ደግማ ደጋግማ ገድዬዋለሁ ያለችው የበይት ሀኑን ዕዝ ጠቅላይ መሪ የቀሳሞች ጦር አዛዥ ኮማንደር ሁሴን ፈያድ ዛሬ ከፍርስራሹ መሐል ብቅ ብሏል።
አላህ ይጠብቀው


Mahi Mahisho

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

22 Jan, 06:55


ትውልዱ ሞሮኮ የሚኖረው አሜሪካ ነው። ቃዲ አብዱል አዚዝ ይሰኛል። ከሚኖርበት የድሎት ከተማ ከአሜሪካ ተሳፍሮ ቴል አቪቭ ደረሰ። ስለፍልስጤም ወንድሞቹ እያሰበ ለበይኪ ያ አቅሳ ብሎ ስል ቢላዋ አዘጋጀ። እምነት በሞላው የልቡ ማሰሮ ወደ ፊት ገሰገሰ። በንጹህ እጁ አራት ሰፋሪዎችን በያዘው ቢላ ጨቀጨቀ። ከመሬቱ ተዘረሩ። ሁሉም ወደቁ።

አለመቻል ያላሸነፈው፣ የድሎት ህይወቱን ትቶ ከቤቱ የወጣው ቃዲ አራቱን ጥሎ እሱም ወደቀ። ይህ የሆነው ትላንት ማታ ነው። አለይሂ ረህመቱላህ።


Mahi Mahisho

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Jan, 18:52


ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎችን ማሠር ጀምሯል!

ላለፉት አመታት በነፃነት ሲለበስ የነበረውን ኒቃብ ከልክሎ ሙስሊም ተማሪዎችን ማንገላታት የጀመረው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደማስፈራራት እና ማሳሰር እንደተሸጋገረ ተገልፇል:: እስካሁንም ከኦዳያ ካምፓስ አንድ ሙስሊም ተማሪ ታስሯል:: ኒቃብ ለባሽ እህቶች ግቢ መግባት አትችሉም ከተባሉ ከዛሬ ጋር 4ተኛ ቀናቸውን የያዙም ሲሆን መስጂድ ውስጥ ከተማሪዎች እና ከትምህርት ርቀው እንደሚውሉና እንደሚያድሩም ታውቋል::

  የነፃነት እና እኩልነት ጥያቄን በማስፈራራት እና በማሰር ማቆም አይቻልም::

ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Jan, 13:40


ኧረ እነዚህ ሰዎች😳😳

ከሳአዲ ተልዕኮ ተቀብላቹሃል😳😳

ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ ክልከላ አድርገዋል የተባሉት በአክሱም ከተማ የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች

10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ከአክሱም ከተማ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በተዘረጋ የውጭ ተፅእኖ ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸው ፎርም አልሞሉም። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ' 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እንዲስተጓጎሉ ተደረገ ' እየተባለ ነው የሚወራው። 142 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻችን የሌሉ የፈጠራ ድርሰቶች ናቸው።

የተቀሩት 10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ቢሆኑ ፎርም መልተው ለመፈተን ፍላጎት አላቸው ፤ ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፣ ከመቐለ ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በየቀኑ እየተደወለ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ የቆየውን አብሮነት እና መቻቻል የሚጎዳ ለህዝብ እና አገር የማይጠቅም መወገዝ ያለበት ተግባር ነው። "

... ሲሉ ትምህርት ቤቶቹ በጥምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በላኩት የፅሁፍ ምላሽ ገልጸዋል።

ኧረ ሼር አርጉት

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Jan, 07:19


እህቶቻችን ለእህቶቻችን

«አክሱም ሒጃብ ብቻ አይደለም የተከለከለው እስልምና እንጂ»‼️

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Jan, 06:08


ሒጃቤ ክብርና ከፍታዬ!
መገለጫና ውበቴ
ኢስላማዊ ዓርማዬ ነው


Mahi Mahisho

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Jan, 06:01


በትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ በአክሱም ትምህርት ቤቶች የተጣለውን የሒጃብ ክልከላ የሚቃወም ሠልፍ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 13/2017 እየተካሔደ ይገኛል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Jan, 18:38


ዲላ ዩኒቨርሲቲ ••• Update!

የዲላ አናብስቶች 3ኛ ቀናቸውን በእምቢታ ቀጥለዋል:: ዛሬም ኒቃብ ለብሳችሁ ከግቢ አትገቡም የተባሉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኒቃቢስት እህቶቻችን ከግቢ ውጭ ከመስጂድ አድረዋል:: በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ግብር የተነባ የልሕቀት ማዕከል የሀገሪቱ ግማሽ የሆነውን ሙስሊም ማህበረሰብ ልጆች በእምነታቸው ሳቢያ ማደሪያ እንኳን ነፍጎ ከውጭ ያሳድራል::

በአላህ ፈቃድ ግን ይህን መሠሉ በራስ ሀገር በራስ ተቋም የሚፈፀም ግፍ ፍፃሜውን ያገኛል ••• ነፃነት በነፃ አይገኝም!

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Jan, 11:05


"ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ስለሆነ መልበስ አይቻልም!" - ዲላ ዩኒቨርሲቲ

ላለፉት 3 አመታት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በነፃነት ይለበስ የነበረውን ኒቃብ ያለ ሕግ እና መመሪያ ከወር በፊት ከልክሎ የነበረው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር ግብግብ ውስጥ እንደነበር ይታወቃል:: በሰሞኑም ለብሳችሁ አትገቡም በማለቱ ሙስሊም ተማሪዎች ከግቢ ውጭ ከመስጂድ ማደራቸው ይታወሳል::

የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም በዛሬው እለት ከሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረገው የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር "ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ስለሆነ በግቢ ውስጥ ለብሶ መግባትም ሆነ መንቀሳቀስ አይቻልም!" የሚል መልስ እንደሰጣቸው ተማሪዎች አሳውቀዋል::

በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ተጨባጭ ያልሆነ እና እምነቱን የሚዳፈር ምክንያት በማቅረብ የሚደረግ የመብት ጥሰት መቆም እንዳለበት:: ኒቃብንም ሆነ የትኛውንም ኢስላማዊ አለባበስ የደህንነት ስጋት አድርጎ ማሰብም ሆነ ማቅረብ ሀይማኖቱን ከማንቋሸሽ ተለይቶ አይታይም:: ኒቃብ በሐይማኖት እንዲለበስ የታዘዘ የእምነት ልብስ ሲሆን በሕግ ደግሞ የማይከለከል የነፃነት መገለጫ ነው::

በአላህ ፈቃድ መሠል ጥላቻ ተኮር የመብት ጭቆናዎች በዚህ ትውልድ ታሪክ ይሆናሉ ••• ነፃነት በትግል እንጅ በነፃ አይገኝም!

©️EHEMSU

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

11 Jan, 14:54


"...ሂጃባችሁን ካላወለቃችሁ ፎርም አትሞሉም በመባላችን የ12 አመት ልፋታችንን መና ሊቀር ነው።"

-የአክሱም ከተማ የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ተማሪዎች!

ሀሩን ሚዲያ፣ጥር 3/2017

በትግራይ ክልል የአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች "ወይ ሂጃባችሁን አውጣችሁ ፎርሙ ሙሉ አሊያ ከፈተና ውጪ ትሆናላችሁ" በመባላቸው የአስራ ሁለት አመት ድካማችን ሜዳ ላይ ሊቀር ነው ሲሉ ለሀሩን ሚዲያ ገልጸዋል።

የዘንድሮው አመት የትምህርት ዘመን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፎርም የሚሞላበት ቀን በመጭው ሰኞ ጥር 5/2017 ዓ.ል የሚጠናቀቅ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን 159 የሚሆኑ የአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ፎርሙን አለመሙላታቸውን ገልጸዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ሁለት አመት ወደኋላ መቅረታቸውን የሚናገሩት ተማሪዎቹ አሁን ደግሞ በሂጃባችን ምክንያት ከፈተና ውጪ ልንሆን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

"ትምህርታችሁን ወይም ሂጃባችሁን"አንዱን ምረጡ ተብለን ሰብዓዊ ክብራችን ሀይማኖታዊ ማንነታችን ተገፎ ከጓደኞቻችን በታች እንድንሆን እየተደረግን ነው ሲሉ ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በከተማዋ 159 የሚሆኑ ሙስሊም ሴት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጨምሮ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙስሊሞች ተማሪዎች በተመሳሳይ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ ከሆኑ ከወር በላይ ሆኗቸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚሰሩ ተቋማት እንዲሁም የሰብዓዊ መብትን በተመለከተ የሚሰሩ ተቋማት አስካሁን ያሉት ነገር የለም።

© ሀሩን ሚዲያ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

11 Jan, 09:19


📸
በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት የደረሰበት በገቢ ረሱ ዞን ዱለሳ ወረዳ የሚገኘው ሳጋንቶ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

Via FBC

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

11 Jan, 08:07


እሳቱን እዛው ለናንተ ይጨማምርላችሁ።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

10 Jan, 19:10


አንድ ክርስትያን ወይም የሌላ እምነት ተከታይ ሰለ ቁረዓን ማወቅ ፈልጎ ቁርዓኑን ይዞ ቢያነብ አይፈቀድም እንዴ?

ISLAMIC SCHOOL️

10 Jan, 16:32


መቱ በደሌ ካምፓስ ተማሪዋም ተማሪዎቹም ለዛሬ ገብተዋል!

  "ኒቃብ ለብሰሽ አትገቢም!" ብሎ ያገደውን በደሌ ካምፓስ በመቃወም "ኒቃብ ካለበሰች እኛም አንገባም!" በማለት ከዝሁር እስከ 11:00 ድረስ የመቱ ዩኒቨርሲቲ በደሌ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች ከግቢ ውጭ በር ላይ ቆመው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእህቶቻቸው መብት አሰምተው ነበር:: መጀመሪያ ላይ "ወይ ከትምህርቷ ወይ ከኒቃቧ ትምረጥ!" የሚልን መልስ የሰጠው የበደሌ ካምፓስ ፕሬዚዳንትም በስተመጨረሻም ከብዙ ውይይት እና ተፅዕኖ ቡሃላ "ለዛሬ ግቡ:: ሰኞ ላይ ተወያይተን ዘላቂ ውሳኔ እንወስናለን::" በማለት ኒቃቢስቶቹም ተማሪዎቹም እንዲገቡ ሆኗል::

በአላህ ፈቃድ የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጭቆና በዚህ ትውልድ ታሪክ ይሆናል •••• ነፃነት በነፃ አይገኝም::

የምን ፍትህ ማለት ነው መብታችንን ራሳችን እናስከብራለን

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

10 Jan, 08:04


ሰላም ከሎስ አንጀለስ ሰማይ ስር🫡


وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

وما يعلم جنود رَبِّكَ إلا هو وما هِيَ إلا ذكرى لِلْبَشَرِ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

09 Jan, 11:12


#Update

የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ለፈተና ፎርም ለሞሙላት ብቻ ሒጃባቸው አድርገው እንዲሞሉና ነገሩ በኃላ እንሚታይ ተነግሯቸዋል። ይህ ግን በፅሑፍ በደብዳቤ አይደለም። ችግሩን በህጉ መሰረት የሚፈታም አይደለም። ከግዝያዊ ጫና ለማምለጥ የተደረገ ይመስላል። ለደረሰባቸው በደልም እውቅና አይሰጥም። ህጉ መሰረት ያደረገ መብታቸው ገና ስለአልተፈቀደላቸው አልተቀበሉትም።

ስለዚህ ያለው ብቸኛው አማራጭ ህጉን ማክበርና ቀጣይም እንደሚከበር የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ የሚመለከተው አካል መስጠት ሲችል ነው።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

09 Jan, 10:50


🤲 በታላቁ አላህ ስሞችና መገለጫዎች ተማፅኖ ማድረግ ለዱዓእ ተቀባይነት ወሳኝ ነው!

ከቡረይዳ (📿) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦

ነቢዩ (📿) አንድ ሰው እንዲህ በማለት አላህን ሲማፀን ሰሙት፦

﴿اللهم إني أسألُك بأني أشهدُ أنك أنت اللهُ لا إلَه إلا أنتَ الأحدُ الصمدُ الذي لم يلدْ ولم يولدْ ولم يكن له كُفُوًا أحدٌ. قال فقال والذي نفسي بيدِه لقد سألَ اللهَ باسمِه الأعظمِ الذي إذا دُعيَ به أجابَ وإذا سُئِلَ به أعطى﴾

“‘አላህ ሆይ! (ጉዳዬን ትሞላልኝ ዘንድ) አንተ አላህና ከአንተ ውጪ ሌላ አምላክ የሌለ መሆኑን፣ አንድና ብቸኛ፣ የፍጡራን ሁሉ መጠጊያ፣ ያልወለድክም ያልተወለድክም፣ አንድም ቢጤ የሌለህ አምላክ መሆንህን በመመስከሬ እማፀንሃለሁ።’ ይህን ግዜ ነቢዩ (📿) እንዲህ አሉ፦ ‘ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ! በርግጥም አላህን ትልቅ በሆነ ስሙ (መገለጫው) ተማፅንከው (ጠየከው)፤ የጠየከውን ዱዓእ መልስ በሚያሰጥና የጠየከውን የሚያሰጥ በሆነ።’”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 3475

▫️▫️▫️▫️🎀🎀▫️▫️▫️▫️

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

08 Jan, 17:41


📍ጉዳዩን ወደ ሕግ ወስደነዋል

ከዚህ ቀደም ባወጣነው መግለጫ እንደገለጽነው ያለ ምንም ህጋዊ መሰረት ከትምህርት ገበታ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአክሱም ከተማ ተማሪዎች በአፋጣኝ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ሕጋዊ ክስ እንደምንመሠርት ማሳወቃችንን ይታወሳል። በመሆኑም አሁን ጉዳዩን ወደ ሕግ ወስደነዋል ።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

08 Jan, 16:55


ነገ ሀሙስ ነው ከቻልን እንፁም ካልቻልን ሌሎችን እናስታውስ 😊

ISLAMIC SCHOOL️

08 Jan, 11:06


አስቸኳይ ጥሪ !!

በአክሱም ከተማ 159 ሙስሊም ተማሪዎች በተለይም ሙስሊም ሴቶች በሒጃባቸው ምክንያት ከትምህርታቸው ተገለዋል። እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መመዝገቢያ ፎርም እንዳይሞሉ ተከልክለዋል።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ምን እየሰራ ነው? ለሙስሊሙ ሲሆን ጆሮ ደባ ብሎ ማለፉን ያውቅበታል !

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

08 Jan, 06:22


🚫 ያጠፋችሁ ነበር!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَوْ لَمْ تُذْنِبُوا لَذَهَبَ اللَّهُ بِكُمْ، وَلَجَاءَ بِقَوْمٍ يُذْنِبُونَ، فَيَسْتَغْفِرُونَ اللَّهَ فَيَغْفِرُ لَهُمْ﴾

“ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ!  እናንተ ሀጢያት የማትፈፅሙ ቢሆን ኖሮ አላህ ያጠፋችሁ ነበር። ከዛ ሀጢያት የሚፈፅሙ ህዝቦችን ያመጣና በሀጢያታቸው ምክንያት አላህን ምህረት ይጠይቁታል እሱም ይምራቸዋል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2749

☹️☹️😭🙁😭🙁☹️🙁

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

07 Jan, 18:40


ስንፍና ባንተ አያምርም!
----------------------
ወጣት ሆነህ ካልተለወጥክ መቼ ልትለወጥ ነው?አቅም ባለህ ሰዓት ካልሰራህ መቼ ልትሰራ ነው? ካልዘራህ እኮ አታጭድም፤ ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ይሄን ወርቃማ ዕድሜዬን ተዓምር እሰራበታለው በል!!

ከ ❿ ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልገው? ከራስህ አልፈህ የምትወዳቸውን ሰዎች መቀየር አትፈልግም? እርግጠኛ ነኝ ትፈልጋለህ አይደል!?......  ስለዚህ ተነስ! የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ቁጭ አትበል! የማይጠቅምህን ፕሮግራም አትይ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ንቃ ወዳጄ! ስንፍና ባንተ አያምርም!              

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

07 Jan, 08:26


ዝምታ...!

«ዝም ያለ ድኗል» ይላሉ ታላቁ መልዕክተኛ። ለዚያም ይመስለኛል ሱፊያን "ረጅም ዝምታ የአምልኮ ክፍል ነው" ብሎ የተናገሩት።

إبنِ الوردِ رحمه اللهُ، قال كان يقالُ: الحِكمةُ عَشَرةُ أجزاءٍ: فتِسعةٌ منها في الصَّمتِ، والعاشِرةُ عُزلةُ النَّاسِ
ኢብኑል ወርድ እንዲህ ይላሉ:- «ጥበብ አሥር ክፍሎች አሉት፣ ዘጠኙ በዝምታ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። አስረኛው ደግሞ እራስን ከሰዎች ማግለል ነው።»

አቡ ደርዳዕ እንዲህ ብለዋል:- «ንግግርን እንደምትማረው ሁሉ ዝምታንም ተማር። ዝምታ እጅግ ውድ የሆነ ጥበብ ነውና። ከመናገር ይልቅ ዝምታን አብዛ። ከተናገርክም የሚመለከትህን ብቻ አውራ። ያለ አላማም አትራመድ።

أفضَلُ الإسلامِ الصَّمتُ حتَّى يسلَمَ النَّاسُ منك
«ጥሩ እስልምና ብሎ ማለት ዝምታ ነው። ሰዎች ካንተ ዝም እስኪሉ ድረስ (ዝም በል)።

ጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ እንዲህ አለው:- «ልጄ ሆይ ! ሰዎች በንግግር ችሎታቸው ከተኩራሩ አንተ ደግሞ በዝምታህ ኩራ።»

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

06 Jan, 06:26


"አክሱም ላይ የተከለከለው ሂጃብ ብቻ አይደለም እስልምናም ጭምር ነው"

▣ በፌደራል መጅሊስ የትግራይ ክልል ተወካይ እንዲሁም የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ ለሀሩን ሚድያ ከገለፁት

- ሀሩን ሚድያ፣ ታህሳስ 27/2017

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ እንዳሉት ሂጃብ እና እስልምና የማይነጣጠሉ መሆናቸውን አንስተው በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ይህን ያደረጉት አካላት የእስልምና ጥላቻ ያለባቸው መሆኑን ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል።

በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ መገለላቸውን አስመልክቶ ፌደራል መጅሊሱ ምን እየሰራ ነው ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄም ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በጋራ በመሆን ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ እየሰራን ነው ብለዋል።

ሙስሊም ተማሪዎች ላይ በየጊዜው የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን ለማስቆም የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።

- ሀሩን ሚድያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠሪ ከሆኑት ከኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በቀጣይ ወደ እናንተ ምናደርስ ይሆናል።

© ሀሩን ሚድያ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

05 Jan, 16:24


ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ 👐

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

05 Jan, 14:02


ረመዷን ስንት ቀን ቀረው?

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

05 Jan, 05:16


#Update

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ስለሆነም ምዝገባ ያላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድማችሁ እንድታጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

አገልግሎቱ የ2017 ዓ.ም ፈተናዎች ይዘትን በተመለከተ ባስተላለፈው መልዕክት፤ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ 9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው ሊዘጋጁ እንደሚገባ አገልግሎቱ ጠቁሟል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

04 Jan, 15:53


ፖለቲከኛ ሆደ ሰፊ ሲሆን ጥሩ ነው
~
በዚህ ባንዲራ ሰበብ ወንድሞች እየታሰሩ እንደሆነ ከአንድ ወንድም መረጃ ደረሰኝ። በዚህ ፖስት አንዱ ማስተላለፍ የፈለግኩት ነጥብ ይሄ ነው። ጥንቃቄ እንድታደርጉ።
በርግጥ ይህንን ባንዲራ እኔም አልወደውም። ይህን ብቻ ሳይሆን ቢጫውና ቀዩ ቀለማት የተጣመሩባቸው ባንዲራዎች ሁሉ የየትኛውም አካል ቢሆኑ አልወዳቸውም፡፡ ይሄ የግል ስሜቴ ነው።

ግን ፖሊቲከኞች (ፖሊሶች) በዚህ ሰበብ ሰዎችን ማሳደድ ለምን? መንግስትን በምትወክሉበት ስልጣን ላይ ሆናችሁ ግለሰባዊ የሚመስል እልህ ባታሳዩ መልካም ነው። በተለጠፈው ምስል በዋናነት ማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት "በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው በደል ይቁም። ፍትህ ይስፈን" የሚል ነው። በዚህ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ አይኑን የጨፈነ አካል ኮከብ አለ የለም እያለ ሰው ሲያሳድድ ማየት የሚገርም ነው።

IbnuMunewor

ፖሊስ አንላይን ላይ ነው😁😁

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

04 Jan, 14:11


የሐረሪ መጅሊስ መግለጫ

ISLAMIC SCHOOL️

04 Jan, 09:05


ጃዋር ሙሐመድ ስለ ሒጃብ ክልከላ ገጠመኙን በዚህ መልኩ በመጽሐፉ ላይ አስፍሮታል
=====================================
(የሒጃብ ጉዳይ የማይገባቸውን ድንዙዛን በዚህ መልኩ ማስረዳት ሳይጠበቅብን አይቀርም!)

||
«… የሀይማኖት ተጽዕኖ መኖሩን ለመጀመሪያ ጊዜ የተረዳሁት አዳማ በምማርበት ወቅት ነበር። አንድ ቀን ትምህርት ቤት በር ላይ ስደርሰ መግቢያው ፊትለፊት ቆመው የሚያለቅሱ ሴቶችን ስላየሁ በድንጋጤ ምን እንደሆኑ ጠየኳቸው።
«ሂጃብ ካላወለቃችሁ አትገቡም አሉን» በማለት ነገሩኝ። «እናንተ ብታወልቁ ምን ችግር አለው?» ስላቸው፤ ሀይማኖታችን ይከለክለናል አሉኝ። በወቅቱ የሂጃብን አሰፈለጊነት ሰለማላውቅ ነበር የጠየኩት።

እስከማሰታውሰው ድረስ ባደኩበት አካባቢ አንዲት ሴት ጸጉሯን የምትሸፍነው ማግባቷን ለማሳየት ነው። ያላገባች ሴት ጸጉሯን አትሸፍንም፡
ሹሩባ ተሰርታ፣ ጸጉሯን አያዘናፈለች፡ የወጣቱን ልብ አያሸበረች ትሄዳለች። ስታገባ ራሷ ላይ ሻሽ ጣል ማድረግ ትጀምራለች፡ ልጆች ወልዳ ዕድሜዋ ሲገፋ ደግሞ ጉፍታ የሚባል ታስራለች። ያገባች እና ያላገባች ሴት መለየት የሚቻለው ጸጉሯን በመሸፈኗ እና ባለመሸፈኗ ነው።


የተማሪዎቹን ቅሬታ እና ሂጃብ ማውለቅ የማይችሉበችትን ሰበብ ከተረዳሁ በኋላ የትምህርት ቤቱየዲሲፕሊን ኃላፊ ጋር ሄጄ «ለምን አታስገቧቸውም? የሀይማኖት መብት ለምን ትጋፋላችሁን?› ስለው፡ «ከትምህርት
ቢሮ የመጣ መመሪያ አንጂ የትምህርት ቤቱ ውሳኔ አይደለም» አለኝ። ወደ ዳይሬክተሩ ሰሄድም ተመሳሳይ መልስ አገኘሁ። ወንድ እንደመሆኔ የሂጃብ ክልከላው በቀጥታ ባይጎዳኝም በሴት ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና በጣም አሳዘነኝ።


መታገል አለብኝ ብዬ ወሰንኩ። ከግቢ ውጪ ወዳሉት ሴት ተማሪዎች ተመልሼ «ነገ ሌሎቹንም ጨምራችሁ ሁላችሁም ሻሽ አድርጋችሁ በተመሳሳይ ሰዓት ኑ» አልኳቸው። በዕረፍት ሰዓት ሻሸ የማይለብሱ ወይም አውልቀው የገቡ ሴቶችን
ሰብሰቤ አወያየሁ። ክርስቲያን የሆኑትም ከሙስሊም አሀቶቻቸው ጋር ለመተባበር በማግሰቱ ሻሽ አስረው መምጣት
እንደሚችሉ ተወያይተው ወሰኑ። ወንድ ተማሪዎች በፊናችን ሴቶቹ እስከሚገቡ ድረሰ ውጪ ቆመን ባለመግባት
ትብብር ለማሳየት ተስማማን።

በማግስቱ እንዳቀድነው ብዙ ሴት ተማሪዎች ጸጉራቸውን ተሸፋፍነው በመምጣት አውልቁ ሲባሉ አሻፈረኝ በማለታቸው መግባት ተከልክለው ውጪ ላይ ቆሙ። ወንዶቹም ከአነሱ ጀርባ ቆመን«አናንተ እለፉና ግቡ ስንባል ሴቶቹ ካልገቡ አንገባም አልን። ለተቃውሞው ተዘጋጅተው የመጡ ብቻ ሳይሆኑ ቦታው ላይ የሰሙ ተማሪዎችም
መግባቱን ትተው ተቀለላቀሉን። እኛን ለማናደድ እና ሰሜት ውስጥ ለማስገባት በሚመስል መልኩ የግቢው ጥበቃ ባለፈው ከተማሪዎቹ የሰበሰበውን ሻሽ ማቃጠል ጀመረ። ተማሪዎቹ ሰሜት ውስጥ አንዳይገቡ አረጋግተን ዓላማውን አከሸፍነው።

በሩ ላይ ግርግር በዝቶ ፓሊሶች ተጠርተው ሲመጡ ሄጄ ያለውን ነገር አሰረዳኋቸው። ምንም ዓይነት ፀብ እንደማንፈልግና ያለንን ቅሬታ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደምናቀርብ ቃል ገብቼ አሳመንኳቸው። አዚያ የነበረው ፖሊስ አዛዥ ረብሻ ፈጥራችሁ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አሰካላደረሳችሁ ድረስ አንነካችሁምን በማለት ፓሊሶች ከእኛ ራቅ ብለው መንገድ ተሻግረው አንዲቆሙ አዘዘ። ጥበቃው እንዲያባርሩን ሄዶ ቢነግራቸውም ፖሊሶቹ እሺ አላሉም።


የት/ቤቱ ዳይሬክተር መጥቶ ጥቂቶቻችንን ለብቻ አናገረን። «መመሪያው የመጣው ከላይ ነው፡ ምን ማድረግ አንችላለን?» ብሎ ተማጸነን። እኛም «ከላይም ይምጣ ከታች ትክክል ያልሆነ እና የተማሪውን መብት የሚጋፋ ነገር
ሥራ ላይ መዋል የለበትም» ብለን ሞገትነው። ሊያሳምነን ሞክሮ ሲያቅተው ትቶን ሄደና ትንሽ ቆይቶ እንደተመለሰ
«ይህን ጉዳይ ተረጋግተን በውይይት እናሰተካክላለን። ለአሁኑ ሁላችሁም ወደ ክፍል ግቡ፡ ሴቶቹም ሻሻቸውን ሳያወልቁ
ይግቡ» አለን። ሁሉም ተማሪዎች ገብተን መደበኛው ትምህርት ቀጠለ።


ዕረፍት ሰዓት ላይ የትምህርት ቤቱ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት በማግስቱ ቀጠሮ መያዙ ተነገረን። በታቀደው ውይይት ላይ ሂጃብ መከልከል እንደሌለበት ኮሚቴውን ማሳመን የምንችልበትን ነጥብ አዘጋጅተን እኔ
አንዳቀርበው ተወሰነ። ሰብሰባው ላይ መምህራን፣የተማሪ ተወካዮች፣ ወላጆች እና የትምህርት ቢሮ ተወካዮች ተሳትፈዋል። ከሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ውስጥ አንድ መምህር ከትምህርት ቢሮ የመጣውን መመሪያ አነበበ። መመሪያው ሂጃብ የተከለከለበት ምክንያት የተማሪዎችን የጸጉር ንጽሕና ለማረጋገጥ፣ በሀይማኖት መካከል የሚፈጠር ልዩነት እና
ግጭት ለማስቀረት አንዲሁም ጽንፈኝነት አንዳይሰፋፋ ለመከላከል እንደሆነ ይዘረዝራል።

ምላሽ ለመስጠት ዕድሉ ሲሰጠኝ ተነሳሁና «በሀገራችን ሕገ-መንግሥት እና ዓለም አቀፍሕጎች መሠረት አንድ ድርጊት፣ ቃልና ምልክት ትምህርት ቤት ውስጥ መከልከል የሚችለው ሁለት ጉዳቶችን የሚያስከትል ከሆነ ነው'’ አልኩ።

እነሱም፣
1. የተማሪውን እና የአስተማሪውን መብት እና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ እና
2. የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያስተጓጉል ከሆነ።
የመጀመሪያውን ነጥብ ብዙ ማብራራት አላስፈለገኝም። «ጸጉር መሸፈን በትምህርት ቤት ውስጥ የደህንነት ችግር እንደማይፈጥር ግልጽ ነው። ሴቶች ሻሽ ሰላሰሩ የተፈጠረ የሀይማኖት ግጭት አላየንም አልሰማንም። ሻሽ ግጭት
ፈጥሯል የሚል ሰው ካለ ይናገር» ብዬ አዳራሹ ውስጥ ስመለከት ሐሳብ የሚሰጥ ጠፋ።
ሁለተኛው ነጥብ ወሳኝ ስለሆነ እና መመሪያውን ለማክሸፍ ስለሚጠቅም ተዘጋጅቼበታለሁ።

ከአኔ ጋር የሚማሩ ሁለት ሴት ተማሪዎችን አንዷ በሂጃብ አንድትሸፋፈን፡ ሌላኛዋ እንደ ከተማ ዱርዬ ከጉልበት በታች ተቆርጦ ያጠረ ዩኒፎርም
አንድትለብስ አድርጌ ወደ አዳራሹ አስገባሁ።
ሁለቱን ልጃገረዶች ጎን ለጎን አሰቁሜ በጣቴ ሂጃብ ወደለበሰችው ልጅ እየጠቆምኩኝ ከተሳታፊዎች መሀል አንዱን
ተማሪ «ይህቺ ልጅ ክፍል ውስጥ አጠገብህ ከተቀመጠች ወይም ግቢ ውስጥ ፊት ለፊትህ ከቆመች ትረብሽካለችን»
አልኩት። «ምኗን አይቼ ነው የምትረብሸኝ» ብሎ እንደመቀለድ አለ።

ቀጥሎ አጭር ልብስ የለበሰችዋን አሳይቼው
«ይህቺ ልጅ ሂጃብ ከለበሰችው አጠገብ ክፍል ውስጥ ፊትለፊትሀ ብትቆም የትኛዋ ናት የበለጠ የምትረብሽህ?› ብዬ ሰጠይቀው ልጁ እንደማፈር ብሎ አቀረቀረ፡ አዳራሹ ውስጥ የነበሩ ተሳታፊዎች ነገሩ ገብቷቸው ቤቱን በሳቅ
አናጉት። ዕድሜው ለገፋ አንድ አስተማሪም ለተማሪው ያቀረብኩለችን ጥያቄደገምኩለት «ሂጃብ የለበሰች ልጅ ክፍል
ውስጥ ማየትሀ የማስተማር ሥራህን ያውካል?›» ስለው «አሷን ካፈናት ነው አንጂ የሚረብሽ ነገር የለውም» አለ።

አጭር ልብስ የለበሰችውን፤ አሥነስቼ ስጠይቀው ደግሞ «አኔ ሽማግሌ ነኝ አይረብሸኝም። ለአንዳንተ ያለ ጎረምሳ
ግን አደጋ ነው፡ ጭኗን አንጂ ሰሌዳ አታዩም› ብሎ ሰውን አሳቀው።

«እንደምታዩት ጸጉርን መሸፈን የመማር ማስተማሩን ሂደት እንደማያውክ ተማሪውም አስተማሪውም መስክሯል።
መጀመሪያ ሕገ-መንግሥቱን ጠቅሼ እንደተናገርኩት አንድ ድርጊትም ሆነ አለባበስ ሊታገድ የሚችለው የመማር
ማስተማሩን ሂደት ካወከ ስለሆነ ሂጃብ የሚከለከልበት ምክንያት የለም። ከትምህርት ቢሮ የመጣው መመሪያም
ስሕተት ነው» ብዬ ቁጭ አልኩ።

በቀረቡት አስተያየቶች ላይ ውይይት ተደርጎ ሂጃብ አንዳይከለከል ስምምነት ላይ
ተደርሶ ለትምህርት ቢሮ አንዲገለጽ ተወሰነ።»
Via ሙራድ ታደሰ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

04 Jan, 08:19


_ _ _ _ _ _ _ 🍃🍂

{واتل ما أوحي إليك من كتاب ربك لا مبدل لكلماته jولن تجد من دونه ملتحدا}

[ ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ለቃላቶቹ ለዋጭ የላቸውም፡፡ ከእርሱም በቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም፡፡]


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

03 Jan, 09:27


ሙስሊም ሴት ተማሪዎች መበረታታት እንጂ በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ሊስተጓጎሉ አይገባም - የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት

ሰሉ አለ ረሱል🥰🥰

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

02 Jan, 16:46


"ከትምህርት እና ሃይማኖታችሁ አንዱን ምረጡ" የአክሱም ከተማ ፖሊስ ለአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች የሰጣቸው ማስጠንቀቂያ

በአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ትምህር ቤት መግቢያ በር ላይ BBC News Amharic ያነጋገራቸው ተማሪዎች እና ወላጆች ኃይማኖታዊ መብታችንን በመጠየቃችን ለእንግልት እና እስር ተዳርገናል ይላሉ።

ወ/ሮ ናአራይሚ መሐመድ ልጃቸው ከትምሕርት ቤት ተወስዳ ስለመታሰሯ ተናግረዋል።

ልጃቸው ትምሕርቷን ወይም ኃይማኖቷን እንድትመርጥ በፖሊስ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

"'ልጆቻችሁ የትምሕርት ቤቱን ህግ አክብረው ይመለሱ ወይም ወደ መስጊድ ይሂዱ፤ አንዱን ምረጡ' አሉን" ብለዋል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

02 Jan, 04:04


የአክሱም ከተማ ፖሊስ ሒጃብ ለብሰው ለማማር ወደ ትምህርትቤት የሄዱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት

"ለምን ሒጃብ ለብሳችሁ ለማማር መጣችሁ?" በሚል ወደ ፖሊስጣቢያ በመውሰድ ተማሪዎቹን ሲያስፈራሩ የሚያሳይ በድብቅ የተበረፀ አጭር ቪድዮ ደርሶናል።

ተማሪዎቹ የለበሷት ስካርፍ ሒጃብ ተመልከቱ። It's just a piece of cloth እኮ።

Uma

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

01 Jan, 16:47


መጅሊስ መግለጫ አውጥቷል

«በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፀሙትን የመብትና የሃይማኖት ጥሰቶችን በሚመለከት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!»

@yasin_nuru_hadis

ISLAMIC SCHOOL️

01 Jan, 08:29


«የአክሱም እህቶቻችን ዛሬም ወደ ትምህርታቸው መመለስ አልቻሉም። ዛሬም ከየት/ቤቱ በራፍ መግባት ተከልክለው ወደየቤታቸው ተደብድበው ተመልሰዋል። ሁሉም ያየውን የትናንቱን የዶ/ር ጉዕሽ ደብዳቤ «አልደረሰንም፣ አንቀበልም!» ብለው ከልክለዋቸዋል።»

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

01 Jan, 05:28


ከ1400 ዓመታት በፊት ትግራይ ውስጥ ከዛሬው የተሻለ የሃይማኖት ነፃነት ነበር።

መካ ውስጥ በገዛ ወገኖቻቸው የተገፉ የተንገላቱ ሙስሊሞች ባህር አቆራርጠው የተሰደዱት ወደ ሐበሻ ነበር። "እዚያ ከሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት ፍትሃዊ መሪ አለ" ተብሎ በነብዩ ﷺ የተመሰከረለት ድንቅ መሪ ነበር፣ ነጃሺ። ያኔ በግዛቱ ውስጥ ማንም እንዳይነካቸው ዋስትና ሰጥቷቸው ነበር ለስደተኛዎቹ ሙስሊሞች።

ዛሬ ከ1400 ዓመታት በኋላ በ21ኛው ክ/ዘመን ሙስሊም ለጋ ልጆች፣ ከሩቅ የመጡ እንግዶች ሳይሆኑ ተወላጆች፣ ሻሽ ካልጣላችሁ ተብለው በእምነታቸው ተለይተው ከትምህርት ገበታ ተገፍተዋል።

ይበልጥ መሰልጠን ሲገባ ጭራሽ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ መሄድ የሚያሳዝንም፣ የሚያሳፍርም፣ የሚገርምም ነው።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

31 Dec, 15:28


"...በደብዳቤው መሠረት በዚህ ሶስት ቀን ውስጥ ተማሪዎች ተመልሰው ችግሩ ካልተፈታ ከህዝባችን ጋር በመመካከር የምንወስዳቸውን ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች እናሳውቃለን.."

- የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ አደም አብዱልቃድር እና የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሐጂ ሙሓመድ-ካሕሳይ ከተበዳዮች ጎን ለቆሙት ሁሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ይህ በትምህርት ቢሮ የተፃፈው ደብዳቤ በሶስት ቀናት ውስጥ ተተግብሮ የሂጃብ ክልከላው በአዎንታዊ መልኩ ካልተፈታ በቀጣይ እንደ እስልምና ጉዳዮች ከህዝቡ ጋር በመመካከር የሚወሰዱ ሰላማዊ እርምጃዎች እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

የትምህርት ቢሮ ችግሩ ይፈታ በማለቱ መግለጫ መስጠታችን አሁን ላይ ትርጉም የለውም ያለው ከፍተኛ ም/ቤቱ እስካሁን በትግል እና ትዕግስት እንደመጠበቃችን መጠን ይህ ደብዳቤ ከተፃፈ ጋዜጣዊ መግለጫው አስፈላጊ አለመሆኑን ገልጸዋል። ነገር ግን በዚህ ሶስት ቀን ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታቸው ካልተመለሱ ከህዝባችን ጋር በመመካከር የምንወስዳቸው ሰላማዊ እርምጃወች እናሳውቃለን ሲሉ ገልጸዋል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

31 Dec, 11:55


የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በአክሱም ትምህርት ቤቶች የተጣለው የሒጃብ እገዳ ከመመሪያ ውጪ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን ደብዳቤው ላይ ሕግ እና መመሪያ በመጣስ በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥሰት በፈፀሙ አካላት ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሚጠይቅ የለውም። ተማሪዎቻችን ሒጃባቸውን ለብሰው ይማራሉ ወንጀሎችን ተጠያቂ እስኪሆኑ እንታገላለን። ሒጃብ መሰል (መብት) እዩ (ነው)


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

31 Dec, 03:55


ስለ ተማሪዎች የአለባበስ ስርዓት

Tetemke Brhan Tesha

ተጠምቀ ገብረእግዚአብሔር ይናገራል፦

"በዚህ ሰአት በትግራይ ክልል ተማሪዎች ጩቤ ይዘው ወደ ትምህርት የሚሄዱበት፤  በአንድ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከሰአት ክፍለጊዜ ላይ ጠጥተው ሰክረው እየመጡ ስላስቸገሩ  "ከ6ኛ-8ኛ ክፍል ያሉት ተማሪዎች በጧት ክፍለ ጊዜ ላይ ብቻ እንዲማሩ የተደረገበት ሁኔታ ፤  መምህር እያስተማረ ፊቱን ወደ ሰሌዳ ሲያዞር ድንጋይ የሚወረወርበት፤ ተማሪ ያልሆኑ ጎረምሶች መምህር ክላስ ዘግተው የሚደበድቡበት፤ ሴት ልጆች ወደ ትምህርትቤት ብለው ወጥተው በየጫካው እና በየሰፈሩ እድሜአቸውን በማይመጥን አስነዋሪ ስራ ላይ የሚውሉበት...አረ ስንቱን ልጥቀስ! ባሉበት ወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታ እንዲህ አይነት [ሒጃብ የለበሱ] ሴቶች እንደወንጀለኛ በተቆጠሩ ነበር?

📍 ጉዳዩ ሌላ ነው። ይህ የትግራይ ስቃይና ሕመም ቀጣይነት ማሳያ እንደሆነ ግልፅ ሊሆን ይገባል። ይህ የሃይማኖት ሽፋን በማድረግ ትግራይ ወደ ሌላ አዘቅት ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት ስለሆነ ካሁኑ በቃ ሊባል ይገባል።"

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

30 Dec, 15:43


አሁን የደረሰን መረጃ
ሒጃብ ለብሰን ነው የምንማረው ካሉ 159 የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች መካከል 20 ታስረው እንደነበረ ለማረጋገጥ ተችሏል። 17ቱ ከሰዓታት በፊት ተፈተዋል። ሶስቱ (3ቱ) በእስር ላይ ናቸው።

@መሀመድ ሀጎስ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

30 Dec, 14:09


በአክሱም ከተማ በሒጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ የታገዱ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከ150 በላይ መሆናቸው ተገለፀ!

በዛሬው ዕለት ሰኞ ታሕሳስ 21/2017 አዲስ ነገር ይኖራል ብለው የጠበቁ 159 የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ተፈታኝ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃባቸውን ለብሰው ወደ የትምህርት ቤቶቻቸውን ሄደው የነበረ ቢሆንም ዛሬም ሒጃቦችሁን አውልቃችሁ ካልሆነ መግባት አትችሉም ተብለው እንደተመለሱ ተማሪዎቹ ለሀሩን ሚድያ ገልፀዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ በበላ ሀገሪቱ ከ499 ሺህ በላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል ያለ ቢሆንም በአክሱም ከተማ ግን አንድም ሙስሊም ሴት ተማሪ ምዝገባ አለማድረጉን ተማሪዎች ተናግረዋል።

የ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ፎርም መሙያ የቀሩት ቀናት ጥቂት በመሆናቸው የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

© ሀሩን ሚድያ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

30 Dec, 09:06


ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ሌሎችም ባጠቃላይ እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ ለመስገድ የሚቸገሩበት ሁኔታ ከገጠማቸው ዙህርን እና ዐስርን በአንዱ ወቅት፤ መግሪብን እና ዒሻእንም እንዲሁ በአንደኛው በሚመቻቸው ወቅት መስገድ ይችላሉ። መንገደኞች ባይሆኑ እንኳ ማለቴ ነው። ስለዚህ ለምሳሌ አንድ ተማሪ ከመግሪብ ሶላት ቀደም ብሎ 12:00 ላይ ለፈተና እንዲቀመጥ ቢገደድና የፈተናው ጊዜ እስከ ዒሻእ ወቅት የሚረዝም ከሆነ ፈተናውን ካጠናቀቀ በኋላ በመጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ እንደገና ዒሻእን ይሰግዳል። ይሄ ሶሒሕ ሐዲሥ የመጣበት ነው። ለተጨማሪ የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚንን ድምፅ አያይዣለሁ።

ተጨባጭ ምክንያት ካልገጠመው ግን ሁሉንም ሶላት በወቅቱ ነው መስገድ ያለበት። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتۡ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِینَ كِتَـٰبࣰا مَّوۡقُوتࣰا }
''ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና።" [አኒሳእ፡ 103]


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

29 Dec, 18:25


ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ 👐

ISLAMIC SCHOOL️

29 Dec, 05:24


በዓለማችን ታዋቂውና የተሻለ የሚባለው የእንግሊዝኛ ቁርኣን ትርጉም Sahih International ሲሆን የተዘጋጀውም በ3 ሰለምቴ አሜሪካውያን ሴቶች ነው።

♦️የመጀመሪያዋ ❝ኤምሊይ አሳሚ❞ ወይም አሚናህ ዑሙ-ሙሐመድ ትባላለች። የተወለደችው ካሊፎርንያ ሲሆን ቤተሰቦቿ እምነት የለሾች ናቸው። ኢስላም ሴቶችን እንደሚጨቁን ስትሰማ ለማጣራት ቁርኣንን ማንበብ ጀመረች። ከዚያ በወቅቱ በአሜሪካ በቂ የኢስላም መጽሐፍ ስላልነበሩ ወደ ሶርያ በመሄድ ከደማስቆ ዩኒቨርስቲ ዐረቢኛን አጥንታ ክሱ ቅጥፈት መሆኑን ስታረጋግጥ ኢስላምን ተቀበለች። ከዚያም በ1981 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

♦️ ሁለተኛዋ ❝ሜሪ ኬኔዲ❞ የተወለደችው በኦርላንዶ ሲሆን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ምሩቅ ናት። ቤተሰቦቿ ክርስቲያኖች ናቸው። በኋላም ወንድሟ ኢስላምን ሲቀበል በእሱ ምክንያት በ1985 ኢስላምን ተቀበለች። ከዚያም በ1987 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

♦️ ሶስተኛዋ ❝አመቱላህ ባንትሌይ❞ ስትሆን የካቶሊክ እምነት ተከታይ የነበረችና ከሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ የቢዝነስ ማኔጅመንት ምሩቅ ናት። የሰለመችው በ1986 በዓለምአቀፍ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር አማካኝነት በ20 ዓመቷ ነው። ከዚያም በ1987 ወደ ሳዑዲዓረቢያ ሄደች።

👉 በ1990 አካባቢ በሳዑዲ ሳሉ በአጋጣሚ ተገናኝተው ተዋወቁ። በዚያው ሰሞን ሙስጠፋ የተባለ ሰው ቁርኣንን በቀላል እንግሊዝኛ ለመተርጎም ጀምሮት እንደሞተ ሲሰሙ ስራውን ለመጨረስ ተነሱ። በዚህም ከዚያ በፊት ፍፁም አስበውት የማያውቁትን የቁርኣን ትርጉም በ1994 ጀምረው በሶስት ዓመቱ በ1997 አጠናቀቁት።

በኋላም መጽሐፉ በዓለም ላይ ቀላሉና የተሻለው የእንግሊዝኛ ትርጉም ለመሆን የበቃ ሲሆን ሶስቱም በህይወት በመኖራቸው የስራቸውን ፍሬ ለማየት ታድለዋል። ዑሙ-ሙሐመድ ኤምሊይም ከዚያ በኋላ ከ80 በላይ ኢስላማዊ መጽሐፍት አዘጋጅታለች። እነዚህ እህቶችም ኢስላም በቁርኣን ጭምር የሴቶችን እውቀት የሚተማመን መሆኑን ማሳያ መሆን ችለዋል።

ሰልማን

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

28 Dec, 16:43


በዛሬው እለት በ6 ኪሎ ጀመዓ አዘጋጅነት በአል-አቅሷ መስጂድ በተካሄደው የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ከተማሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የተመለሱ መልሶች

🎙 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

28 Dec, 01:47


#ፈጅር

ለፈጅር ሰላት ወደ መስጂድ ስትገባ ጥቂት ሰጋጆች ስትመለከት ዕወቅ ... አላህ ነው ከእነርሱ(ከባሮቹ) እንድትሆን የመረጠህና አመስግን!!

የፈጅርን ሰላት በጀምዓ ለመስገድ ስለበቃህ እንኳን ደስ አለህ!
በአላህ ጥበቃ ውስጥ ነህ .... በእውኑም በመንፈስም ቤትህ ከሌሎች ቤቶች ብርሀን ነው።

«ጌታዬ ሆይ ጉዳዮቼን ወደ አንተ አቀርባለሁ፣ እንደምታሳካልኝም ተስፋ አደርጋለሁ!» ከሚሉ ባሮቹ ውስጥ ያድርገን!!


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

27 Dec, 11:28


በቻይና በተካሄደ አለም አቀፍ የሮቦ ሮቦቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል የተወዳደረው ተማሪ አክረም ሙሀመድ 3ኛ በመውጣት የዋንጫ አሽናፊ ሆነ!

- ሀሩን ሚዲያ፣ ታህሳስ 17/2017

በአዲስአበባ የሚገኘው መወዳ ትምህርት ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ አክረም ሙሀመድ በቻይና በተካሄደ የአለም አቀፍ የሮቦ ሮቦቲክስ ውድድር 3ኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

ከ36 በላይ የአለም ሀገራት ተሳታፊ በነበሩበት ውድድር ላይ ጠንካራ ፉክክር እንደነበር የገለፀው ተማሪ አክረም ሙሀመድ በአላህ እገዛ ማሸነፍ ችያለሁ ብሏል።

ተማሪ አክረም በውድድሩ ላይ የሀገሩን ሰንደቅ አላማ ከፍ በማድረጉ በሚማርበት መወዳ ትምህርት ቤት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ተማሪ አክረም ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለፈጠራ ስራዎች ልዩ ቦታ እንዳለው የገለፁት ወላጆቹ በቻይና በነበረው አለም አቀፍ የሮብ ሮቦቲክስ ውድድር ወቅት የነበረው የምግብ አለመቸት እና የአየር ፀባይ መቀያየር ጫና ባይፈጥርበት 1ኛ ሊወጣ ይችል እንደነበር ገልጸዋል።

ለፈጠራ ስራ ልዩ ቦታ እንዳለው የገለፀው ተማሪ አክረም ሙሀመድ ወደፊት ሀገሩን የሚያስጠራ ኡማውን የሚጠቅም ስራ የመስራት ራዕይ እንዳለው ገልጿል።

- ሀሩን ሚዲያ በዚህ ዙሪያ ከተማሪ አክረም፣ ከቤተሰቦቹ እንዲሁም ከመምህራኖቹ ጋር ቆይታ በማድረግ ያሰናዳውን ዝግጅት በቅርቡ ወደእናንተ ያደርሳል!

© ሀሩን ሚዲያ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

27 Dec, 05:37


"..ሂጃብ አልከለከልንም ጸጉራቸውን እንዳይሸፈናፈኑ ነው የከለከልነው.."

- የአክሱም አሉሙናይ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ


በአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸውን እንዳይሸፍኑ የሚከለክል መመሪያ መኖሩን የአክሱም አሉሙናይ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ ገለፁ!

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም መባላቸው ይታወቃል።

ይህንኑ ጥያቄ ይዘን ሂጃብ ለብሶ መማር ክልከላ ከተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች አንዱ ወደ ሆነው የአሉሙናይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ርዕሰ መምህር አቶ ብርሃኔ ጋር ሀሩን ሚዲያ ባደረገው የስልክ ቆይታ ርዕሰ መምህሩ ምንም እንኳን ሂጃብ ብለው በግልጽ ባይናገሩም ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸዉን ተሸፋፍነው መማር አይችሉም የሚል መመሪያ እንዳላቸዉና በመመሪያው መሰረት ፀጉር መሸፋፈኛና ጌጣጌጥ ለብሶ መማር አይቻልም በማለት አጭር ምላሽ ሰጥተውን ስልኩን ዘግተውብናል።

ርዕሰ መምህሩ ምንም እንኳን ሂጃብ መልበስ አልከለከልንም ቢሉም ፀጉራቸውን ሸፍነው የሚማሩት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች እንደሆነ‍ም ይታወቃል።

በዚህ ጉዳይ ወደ አክሱም ከተማ ከንቲባ ወደሆኑት አቶ አበበ መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ የእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ስልካቸው ባለመመለሱ ምክንያት ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።

© ሀሩን ሚዲያ

#ᴊᴏɪɴ_and_share_ᴏᴜʀ_ᴘᴀɢᴇ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

26 Dec, 06:48


የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሰቆቃ
==========================

ሙስሊም በመሆን ብቻ ንጹሐን የሚጨቆኑባትና መብታቸው የሚረገጥባት የትግራይዋ አክሱም!

ጸጉራችሁን ገልጣችሁ ካልተማራችሁ መማር አይቻልም ከተባሉት የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች መካከል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ የማትሪክ ፈተና ፎርም መሙላት አልቻሉም። ፎርም መሙላት የሚቻለው ደግሞ ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 16 ድረስ ነበር።

ስለዚህ ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ በግልፅ ከትምህርት እንዲያቋርጡ ተደርገዋል። ይህን የፈጸሙት አካላት የሙስሊሞችን ጸጉር ማየት አምሯቸው አይደለም፤ ይልቁንም ሙስሊም መሆናቸው አስጠልቷቸው ነው። ጸጉራቸውን ገልጠው ቢገቡ እንኳ አሁንም ሌላ ከትምህርት ማስቆሚያ ዘዴ ከመፈለግ ወደ ኋላ አይሉም። ለዛም ነው ሙስሊሞች ከናካቴው በማይደራደሩበት የሒጃብ ጉዳይ የመጡት። እያወራን ያለነው ስለ ኒቃብ ወይም ጂልባብ ሳይሆን ስለ ትንሿ ሒጃብ ነው።

የመቃብርና የመስጅድ ቦታ መነፈጋቸው ሲገርመን፤ ጭራሽ ጸጉር ሸፍነው መሄድ ተከለከሉ። ኡማውና ተቋሙ ግን እስካሁን ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ነው። እስከዛሬ «ተቋም ቢኖረን!» እያልን ነበር መሰል ነገሮችን ስንመለከት። ግና አሁን ተቋምም አለን ብለን ከጭቆና ሊታደገን አልቻለም።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

25 Dec, 15:51


ነገ ሀሙስ ነው ከቻልን እንፁም አልቻልን ሌሎችን እናስታውስ 😊


ᴊᴏɪɴ and share ᴏᴜʀ ᴘᴀɢᴇ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

25 Dec, 09:36


💜 ወፍ የፈለገ ያህል ሰማይ ላይ
ብትበርና ብትበር መሬት ላይ
ማረፏ አይቀሬ ነው‥
๏ የሰው ልጅም የፈለገ ያህል
ቢኖርና ቢኖር መሞቱ አይቀሬ ነው ።
አላህ አሟሟታችንን ያሳምርልን

#መልካም_ቀን

#ᴊᴏɪɴ_and_share_ᴏᴜʀ_ᴘᴀɢᴇ

          @islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

25 Dec, 08:49


የትግራይ ተወላጆች ሆይ!

ያኔ በጦርነቱ ወቅት አብረዋችሁ ከጎናችሁ ቆመው የነበሩ ሙስሊም የክልሉን ተወላጆች ዛሬ ላይ ሒጃብ አትለብሱም ብላችሁ ስትከለክሏቸው ልታፍሩ ይገባል።

የክልሉ ንጹሐን ተወላጆችና በዚህ የጽንፈኝነት መርዝ ያልተጠቃችሁ አክቲቪስቶች፣ ወጣቶች፣ የመብት ተሟጋቾች፤ ይህንን ነውረኛ ተግባር የፈጸሙ ወንበዴዎቻችሁን ከኛ በላይ መቃወም ያለባችሁ እናንተው ናችሁ። ጸብ ሲኖር ያለ ልዩነት ከፊት ታጋፍጧቸዋላችሁ፤ የተመቻችሁ ሲመስላችሁ ታገሏቸዋላችሁ። ነገሮች በዚሁ ላይቀጥሉ ይችላሉ፤ የምታፍሩበት ቀን ሊኖር ይችላልና በደል ባትፈፅሙ ይሻላል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

24 Dec, 06:25


መርሃብ መርሃብ ያ ሂላል🥰

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

06 Dec, 06:53


🦋ልቡ እንዲከፈትለት ፣ወንጀሉ እንዲማርለት ፣ ችግሩ እንዲነሳለት፣ጭንቁ እንዲወገድለት የፈለገ ሰው በሠይደልዉጁድ[ﷺ]🩵 ላይ አብዝቶ ሶለዋት ያውርድ

اللّهُمّ صَلّ عَلَىٰ سَيّدِنا مُحَمّدٍ عَدَدَ حِلْمِكَ🤍  وَصَلّ علَىٰ سَيّدِنا مُحَمّدٍ عَدَدَ عِلمِكَ🤍 وَصَلّ علَىٰ سيّدِنَا مُحَمّدٍ عَدَدَ كَلِمَاتِك🤍 وَصَلّ علَىٰ سَيّدِنَا مُحَمّدٍ عَدَدَ نِعْمَتِكَ.

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

05 Dec, 15:57


🚨 ማዝራዊ የዩናይትድን ሀሳብ አስቀይሯል‼️

ማንችስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን ጨዋታ በፊት ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ድጋፍ ያዘጋጀውን ጃኬት ተጫዋቾቹ ለብሰው ወደ ሜዳ እንዲገቡ ጠይቆ ነበር።

ሞሮኳዊው ተጫዋች እምነቱ ስለማይፈቅድ ጃኬቱን መልበስ እንደማይፈልግ በማሳወቁ ጃኬቱን በሌላ ቀይረው ወደ ሜዳ መግባታቸው ተዘግቧል።


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

05 Dec, 10:01


♡ የተኛ ሰው ህልም ላይ እንዳለ
ከነቃ በኋላ እንጂ አያውቅም ...
⇨ እንደዛውም ከአኺራ የተዘናጋ ሰው
ሞት ሲመጣበት እንጂ ያከሰረውን
ነገር አያውቅም ።


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

05 Dec, 01:19


ለፈጅር ባልተቤቶች ሽልማቶች አሎቸዉ
የሚተኙ ሰወች የማያገኙት!

ያረብ እሷን ከሚጠብቁ አርገን

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

04 Dec, 17:53


ነገ ሀሙስ ነው ከቻልን እንፁም አልቻልን ሌሎችን እናስታውስ 😊

ISLAMIC SCHOOL️

04 Dec, 05:42


የኔ ስም ተጠርቶ ሰላዋት ያላወረደ
ሰዉ ስስታም ነው አሉ ረሱላችን ❴ﷺ❵

ISLAMIC SCHOOL️

04 Dec, 01:39


ሁልጊዜ የፈጅርን ሶላት በጊዜ መስገድን አላህ
እድሉን ከሰጠህ አብሽር  ከዱንያና በሷ ዉስጥ ካሉ ነገራቶች በላጭ የሆነዉን ሶላት የሰጠህ አላህ
በዱንያ ዉስጥ ያሉ ነገራቶችን ለመስጠት ቻይ ነዉና ታገስ

የፈጅር ሱና ከዱንያና በሷ ዉስጥ ካሉ ነገራቶች በላጭ ነዉ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

03 Dec, 03:46


♡ ዱንያ ላይ እስካለን ድረስ
ሀዘን መቼም ቢሆን አያልቅም
ደስታም መቼም አይዘወትርም ...
⇨ ከኛ ማድረግ ሚጠበቀው
በሀዘን ጊዜ ነፍሳቸንን ሰብር
በደስታ ጊዜ ደግሞ ሹክርን
ማለማመድ አለብን ። 

#ሶባሐል_ኸይር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

03 Dec, 00:46


ፈጅርን በጊዜ የሚሰገድ ሰዉ
አላሁ ሱብሐነሁ ወተአላ ዱንያዉና አኼራዉ እንዲያምርለት የመረጠዉ ሰዉ ነዉ

አህባቢ ከየትኞቹ ነን!❤️

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

02 Dec, 00:58


ከፈጅር ሶላት የተኙ ሰወች
የፈጅርን ሱጁድ ጠዓም ቢቀምሱ ኑሮ  እንቅልፍቸዉ
ቅጣት ብቻ እንደሆናቸዉ ያቁ ነበር

"ጀነት ፈላጊወች ሶላተል ፈጅር"

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

01 Dec, 18:57


ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ 👐

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

01 Dec, 03:19


♡ በሁለቱም ሀገር ደስተኛ መሆን ከፈለክ
በረሱል ሰ,ዐ,ወ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዛ
⇨ዱዓህ ተቀባይ እንዲሆን ከፈለክ
በረሱል ሰ,ዐ,ወ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዛ
⇨ ወንጀሎችህ ስፍር ቁጥር ከሌላቸው
በረሱል ሰ,ዐ,ወ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዛ
⇨ ስትሞት ደስ የሚሉ ነገሮችን ማየት ከፈለክ
በረሱል ሰ,ዐ,ወ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዛ
⇨ ቀብር ውስጥ ደህንነት ከፈለክ
በረሱል ሰ,ዐ,ወ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዛ
⇨ ቂያም ቀን ሸፈዓቸውን ማግኘት ከፈለክ
በረሱል ሰ,ዐ,ወ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዛ

#ሶባሐል_ኸይር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

01 Dec, 01:40


ይህን ውድ ጊዜማ በዋዛ እንዳታሳልፈው። እንደምንም ተነስ፣ የተሟላ ውዱዕ አድርግና ወደመስጂው ተጓዝ።
“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም” “ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች”
“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም” “ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች”

#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

30 Nov, 06:55


ተቆጥታ ለባሎ እንዲህ አለቺው..

በኔ እናት እና ባንተ እናት መሀል ያለውን ልዩነት ብሎ ብታቅ ኑሮ..?

ባልም በንግግሮ ፈገግ ብሎ በቆንጆ መልስ እንዲህ አላት..☺️

እናቴ ለህይወት ወለደቺኝ
እናትሽ ደሞ ህይወትን ወለደቺልኝ 🙌

በቆንጆ ንግግር ሀይለኛውን ጦርነትን
ረጂሙን የጦርነት ጊዜ አጠፍ!☺️

መታሰቢያነቱ ባሎቻቸውን መንከባከብ ለማይችሉ ሴቶች ይሁንልኝ በቅድሚያ ግን ባሎቻቸውን አስርበው የባሎቻቸውን ሀቅ ሲነጋ አሙቀው ለሚበሉ ይሁን🙌🙌😂

ISLAMIC SCHOOL️

30 Nov, 02:37


ከሙናፊቅነት ነጃ ይባላል

አቢሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“በመናፍቃን ላይ ከባድ ሰላቶች የሱብሂና የኢሻ ሰላቶች ናቸው የእነዚህን ሰላቶች ጥቅም ቢያውቁ ኖሮ በዳዴም ቢሆን ወደሰላቱ ይመጡ ነበር።”  አህመድ፣ቡኻሪ እና ሙስሊም

#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ

ISLAMIC SCHOOL️

29 Nov, 16:33


🥹ነገ ካንተ የሚሸሸው ጠላትህ ሳይሆን የቅርብ ወዳጅህ ነው።
እናትህ ...እናትሽ
አባትህ ...አባትሽ
ወንድምህ ...ወንድምሽ
ሚስትህ ...ባልሽ
ጓደኛህ ...ጓደኛሽ
ነፍሲ ነፍሲ!
.
.
አንድ ሰው ግን ስለ አንተ/አንቺ ይጮኻል።
ስለ አንቺ አምላኩን ይማፀናል።
ኡመቲ ኡመቲ!🥹

🥰አላሁመሰሊ ወሰሊም ዓላ
ሀቢቢና ሙሀመድ🥰

❤️‍🩹
ሳይደክሙና ሳይሰለቹ ያረብ..ያረብ ያሉ ምላሶች...
ምላሽን ማግኘታቸው አይቀሬ ነው!
አላህ የማይሰለች ምላስ፣ የማይደክም ልብ ይስጠን 🤲

ያማረ ጁምአ ተመኘው😊
በዱአችሁ 🥰

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

29 Nov, 01:37


➚ከፈርድ ሰላቶች ሁሉ በላጭ ሰላት፤ የጁምዓ ቀን ሱብሂ/ፈጅር ሰላት ነው ➚»ረሱል ❴ﷺ❵ 💚

➘ተነሱ ስገዱ💫💫

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

28 Nov, 18:45


🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋

ISLAMIC SCHOOL️

28 Nov, 10:41


♡ ከዱንያ በኋላ አኺራ እንዳለ
⇉ ከህይወት በኋላ ሞት እንዳለ
⇉ ቂያም ቀን ሂሳብ እንዳለ
⇉ በዛ ሲራጥ ላይ መጓዝ እንዳለ
የምታውቁ ውድ የአኺራ ወንድም እህቶቼ
አሁኑኑ ዛሬ ነጌ እያልን ጊዜው ሳይሄድብን
ወደ አላህ እንመለስ
እባካችሁ ተውባ እናድርግ ...

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

28 Nov, 06:24


♡ ሴት ልጅ 3 ነገር ያለውን
ወንድ ትወዳለች ...
① ያለሷ የማያይ አይን ያለው
② ክህደት የማያውቅ ልብ ያለው እና
③ ሁሌም የሚያሞግሳት ...

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

28 Nov, 03:26


እስከ መጨረሻው አንብቡት‼️

ማክሰኞ በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ

የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊት ተጋጭተው ነበር..

"አምቡላንስ አየሁ ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ፣

አንድ ወጣትን ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየው፡፡

ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል አካላቱ ተቆርጠዋል፣ እግሩም ጭምር ተቆርጧል እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል

"መሞት አልፈልግም፣በጣም ፈርቻለሁ ፣ እሳት ነው ምገባው እኮ" ይለዋል

እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔኮ አልሰግድም ነበር ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም፣ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል

ሰወችም ተሰበሰቡ፣ እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ፣ በጣምም ፈርቻለሁ፡፡

በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል

የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ ጩኸቱም _ ቀጠለ ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ፡፡

ሊያድኑት ግን አልቻሉም

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሀዳ በል ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም

አላሁ አክበር፣ በጣም ፈርቶ ነበር፣ ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ

ግን....ግን ሸሀዳውን ማለት አልቻለም ነበር

ከዚያም አልተንቀሳቀሰም፣ ሰውነቱም ደርቆ ቀረ

ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት

ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት፡፡

ዘጋቢውም ይለናል፦" በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው፣ ሰላታችሁን ግን ጠብቁ፣ በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡

የመጨረሻ ቀናችሁ መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም እኔም ከዚህ ክስተት ቡሃላ መተኛት አልቻልኩም እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...” እሰግዳለሁ፣ ወላሂ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ መሞት ግን አልፈልግም..….”🥹🥹

ያ አላህ መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን

አንብባችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉ ምናልባትም በዚህ ታሪክ የ1 ሰውን ህይወት ማቃናት እንችል ይሆናል፡፡
© #Copied

ISLAMIC SCHOOL️

28 Nov, 03:07


ህይወት እንደ  መኪና ነች የተፈጠረቺው ወደ ፊት እንድትሄድ ነው ..
ነገር ግን አንዳንዴ ወደ ኋላ መመለስ ያስፈልጋል የምንሄድበትን መንገድ ለማቅለል!

#ሶባሐል_ኸይር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

27 Nov, 16:22


ነገ ሐሙስ ነው ከቻልን እንፁም ካልቻል ሌሎችን እናስታውስ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

27 Nov, 13:46


♡ አቡ ለሐብ ከተከበረው ሐሸሚይ
ቁረይሽ ጎሳ ነው ነገር ግን
የመንቀልቀል ባለቤት የሆነችን ጀሀነም
በእርግጥ ይገባል ።
ቢላል ኢብኑ ረባህ {ረ,ዐ}
ጥቁር ባሪያ ሐበሻ ነበር
ረሱል {ሰ,ዐ,ወ} የጫማውን (ኮቴ) ሹክሹክታ
ጀነት ውስጥ ሰምተዋል ።
......... ......... ......... ሐሳቡን ለናንተው

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

27 Nov, 03:12


ቀልቡን አሏህን በማውሳት ያረጠባት በህይወት ድርቅና አይንገላታም/አይደክምም‥

⇘ ሱብሃነሏህ
⇘ወልሀምዱ ሊሏህ
⇘ወላኢላሀ ኢለሏህ
⇘ወሏሁ አክበር

#ሶባሐል_ኸይር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

27 Nov, 02:34


✍️የመጀመሪያው እቅድህ ፈጅር ሰላት መነሳት ካልሆነ ቀሪው ቀንህ ብታቅድም ምንም ዋጋ የለውም የስኬትን ጅማሮህን ከስርሀልና

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

26 Nov, 09:14


ምድርን ጠባብ የሚያደርጓት ወንጀሎች ሲሆኑ ሰፊ የሚያደርጓት ደግሞ ኢስቲግፋሮች ናቸው ።

.
.
استغفرالله واتوب اليه



@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

26 Nov, 03:05


♡ ወንድ ልጅ የሴት ልጅን ሩህ ካፈቀረ
ከአንድ ውጪ ሌላን አያይም አያስብም ..
# ሁልሽም_ሩህሽን_አሳምሪ
"
"
"
▼ ነገር ግን የሴትን ልጅ ፊት እና
መልኳን ካፈቀረ
ምድር ላይ ያሉ ሴቶች አይበቁትም ።

#ሶባሐል_ኸይር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

26 Nov, 01:03


አጅሩ ሙሉውን ለሊት እንደቆመ ይቆጠርለታል

አቢሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“የኢሻን ሰላት በጀመአ የሰገደ ግማሹን ለሊት እንደቆመ ሲሆን ሱብሂን በጀመአ የሰገደ ሙሉውን ለሊት እንደቆመ ይቆጠራል።” ሙስሊም

“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም” “ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች”
“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም” “ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች”

#የፈጅርሶላትን_በመስጂድ


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

25 Nov, 12:16


#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ

ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

25 Nov, 08:37


ስብራታችንን በመታገስና በዝምታ ስላሳለፍነው ምንም የተጎዳን የማይመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ አንዳንድ ጊዜ ሁሉንም ህመም ለማውራት ህሌናችን አይፈቅድልንም ህመማችንን ለሰዎች ከማውራት ይልቅ #የተሰበረችን_ልብ ለሚጠግነው ጌታ በሚስጥር መናገር ትልቅ እረፍት አለው።

የማያልፉ የመሰሉ ቀኖችን አልፈን ዛሬ ላይ ደርሰናል አልሃምዱሊሏህ 😊

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

25 Nov, 03:19


♡ በእያንዳንዷ ሰከንድ
መመለስ የማንችለው እስትንፋስ
ከአፋችን ትወጣለች
▼ በዚህች ውድ እስትንፋስህ ሰው አምተህ
ዑለማእን ሰድበህ እራስህን ኪሳራ ውስጥ
አትጣል ... ባይሆን
▼ ለወዲያኛው ሀገርህ { አኺራ }
የሚጠቀምህን ነገር ተናገርበት ።


#ሶባሐል_ኸይር

ISLAMIC SCHOOL️

21 Nov, 07:22


💜 እንደ ዌስተርኖች እየኖሩ
እንደ ነቢያቶች መሞት የሚፈልጉ
ማህበረሰብ ውስጥ ነው ያለነው ።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Nov, 07:09


ሁሉንም ሰው አትመን አንዳንድ ሰዎች
ሊረዱህ እየሞከሩ እንደሆነ ያስመስላሉ።😒

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Nov, 04:08


በሁለት ፀጋወች መሀል ነኝ
የትኛው የተሻለ እንደሆነ አላቅም
አላህ የደበቀልኝ ወንጀሎቼ ማንም የማያነውረኝ
በባሪያወቹ ልቦች ላይ ያስገባልኝ ውዴታ ስራወቼ የማይደርሱበት


#ሶባሐል_ኸይር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Nov, 01:32


በመስገጃህ ላይ ታገስ፤ ስኬት፣ ደስታና እርጋታ ከደጃፍ ይፈለፈላሉ።

#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Nov, 18:22


የነገሮችን በፍጥነት መለዋወጥ ስናይ የአሏህን ኃያልነትና ችሎታ እንረዳለን፡፡ ለርሱ ምንም ነገር አይሳነውም፡፡ ለርሱ ሁሉም ነገር ቀላል ነው፡፡ ከባዱም ቀላል፣ ቀላሉም ቀላል ነው፡፡

የባሮችን ሁኔታ በፍጥነት እና በማይታመን ሁኔታ ይቀያይራል፤ ሁኔታቸውን ይለዋዉጣል፡፡ ከሕይወት ወደ ሞት፣ ከዉድቀት ወደ ስኬት፣ ከስኬት ወደ ዉድቀት፣ ከጤና ወደ በሽታ፣ ከበሽታ ወደ ጤና፣ ከደስታ ወደ ሐዘን፣ ከሐዘን ወደ ደስታ፣ ከማጣት ወደ ማግኘት፣ ከማግኘት ወደ ማጣት …

ነገሮችን በቅጽበት የምትለዋዉጥ አምላካችን አሏህ ሆይ! ሁኔታችንን ይበልጥ ወደተሻለ ሁኔታ ለውጥልን ያረብ🤲

#መልካም_ምሽት

ISLAMIC SCHOOL️

20 Nov, 17:55


ነገ ሐሙስ ነው ከቻልን እንፁም ካልቻል ሌሎችን እናስታውስ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Nov, 11:33


100 days until Ramadan!
اللهم بلغنا رمضان
ረመዷንን 100 ቀናት ቀሩት

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Nov, 09:45


በአላህ እጆች ስር በተቀመጥክ ጊዜ
የህፃናት ባህሪ አሳይ
ህፃን የሆነ ነገር ፈልጎ ካልተሰጠው እስከሚሰጠው ያለቅሳል!😥

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Nov, 05:22


አቡ አብዱራህማን አብደሏህ ኢብኑ ዑመር አል ኸጧብ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹የክብርና የልዕልና ባለቤት የሆነው አላህ አንድ ሰው በሞት አፋፍ ላይ እስካልሆነ ድረስ ተውበቱን ይቀበለዋል፡፡››

ሐዲሱን ቲርሚዚይ ዘግበውታል

‹‹ ሞት ከመድረሱ (የመጨረሻ ሰዓት ከመድረሷ በፊት) ተውበት ማድረግ መስፈርት መሆኑን፡፡

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Nov, 04:51


አላህ ሆይ! የከለከልከውን ከመዳፈር አንተው ጠብቀን!

#ሶባሐል_ኸይር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Nov, 02:31


ንቁ፣ ስገዱ...የአሏህ(ሱ.ወ) ጥሪ ነውና!
“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም”
“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም”

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

19 Nov, 18:05


እንደማገባት ንገሮት
አራት ቀለበት አለብሳታለሁ
ሸሪዓውን በሷ ላይ ይተገበራል
ከሷ በፊት ሌላ የለም ከሷ ብኋላም ሌላ የለም!🙌

ISLAMIC SCHOOL️

19 Nov, 16:47


ይህ ብራዚላዊ እሰረኛ ለ5 ዓመታት ያህል ጊዜ የማምለጫ ጉድጓድ(ቀዳዳ) ቆፍሮ የወጣው ግን የእስር ቤቱ ጠባቂዎች የሚቀመጡበት ክፍል ውስጥ ነበር ።

የመጨረሻ እድለቢስ ስቶን😂

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

19 Nov, 14:23


ጓደኞች ከሌሉህ ችግር የለም☺️

የሴት ጓጀኛ ከሌለህ ችግር የለም☺️

ካሽ ከሌለህ ግን ከባድ ችግር😂😂

እውነት ነው🤔

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

19 Nov, 10:31


ሙስሊሞች ከደረሰባቸው ፈተናዎች ሁሉ ትልቁ

የረሱል ((ﷺ)) 🖤 ሞት ነው!!

ISLAMIC SCHOOL️

19 Nov, 02:40


እነሆ ዛሬም ሌላ እድል፣ እነሆ ሌላ ተጨማሪ የመኖር ተስፋ••• አልሀምዱሊሏህ እልፍ ምሥጋና ይገባሓል።

ምሥጋናህን በሶላት፣ በሱጁድ፣ በኢስቲግፋር... አካበው። አልሀምዱሊሏህ•••

#የፈጅርሶላትን_በመስጂድ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

18 Nov, 17:41


የሰው ልጅ ልክ እንደ ሳንቲም ሁለት ፊት ሲኖረው በሰዎች ኪስ ውስጥ ከአንዱ ወደ አንዱ እየተገለባበጠ ይኖራል።


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

18 Nov, 13:33


አንዲት ሴት ከባሌ ጋር ከተጋባን ከስድስት ወራት ብኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አለመግባባት ተፈጠረ ።

ባልተቤቴ ፊቱ ተቆጥቶ ከቤት ወጣ
ከባሌ ጋር ከተጋባን ጀምሮ አብረን የጀመርነው ኪታብ ኘበር አብረን የምንማማረው። ለባሌ የተወሰኑ የሚያስፈልጉኝን ቁሳቁስ ገዝቶልኝ እንዲመጣ ነግሬው ነበር ።

  ኪታብ የምንቀራበት ጊዜ ሲደርስ ባሌ ያልኩትን ይዞ መጣ ምንም እንዳልተፈጠረ ፊቱ ፈገግ ብሎል ❤️

የምትፈልጊውን ኢሄው ትናንት ያቆምነው የት ጋር ነበር አለኝ ፈገግ ብሎ.. ☺️

እኔም የማትመጣ መስሎኝ ነበር አልኩት?
እሱም በአእምሮየ መቼም የማይጠፍ ቃል ነገረኝ!
ቁጣ ሰአታት ነው ፍቅር ግን እድሜ ልክ ነው

ያኔ የዱዓየን ልክ ተረዳሁ "የማይሰለች መከታን  "የኔ መከታም ይህ ነው ።
اللهم نسألك بسند لا يميل ❤️


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

18 Nov, 01:34


አሏህ ሆይ እዝነትህን•••
በእዝነትህ አካበን፣ በእዝነትህ አድነን፣ በእዝነትህ ምራን•••

የእርሱን እዝነት ትፈልጋለህ?፥ ይኸው ጊዜው አሁን ነው። ተነስና የፈጅርን ሶላት ስገድ። ጌታህ ፈጽሞ ብቻህን አይተውህም።•••

#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

17 Nov, 16:44


በአሁን ሰዓት ምን እንደናፈቀኝ ታቃላችሁ🥲

ድሮ ትንሽም ቢሆን የነበረኝ ኢማን🥺🥺ወላህ

ሰላት ራሱ በስነ-ስርዓት መስገድ አቃተኝ

ዱዓ አርጉልኝ

ISLAMIC SCHOOL️

14 Nov, 02:58


ሙሳ አለይሂ ሰላም
ህፃን እያለ ደካማ በነበረበት ጊዜ አልሰመጠም ነበር ።

ፊርአውን ግን ሀይለኛ በነበረበት ጊዜ ከነ ጉልበቱ ሰመጠ ።
አላህ እሱ ጋር የሆነለት ደካማነቱ አይጎዳውም።
አላህ እሱ ጋር ያልሆነለት ሀይሉ አይጠቅመውም ።

#ሶባሐል_ኸይር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Nov, 19:18


" ለምንድነው እናትህ አሁንም ከአንተ ጋር የምትኖረው?"

ክሪስቲያኖ ሮናልዶን ጋዜጠኛው ክሪስቲያኖ ሮናልዶን እንዲህ ሲል
ጠየቀው:- ለምንድነው እናትህ አሁንም ከአንተ ጋር የምትኖረው? ለምን የራሷን ቤት አትገዛላትም?’

ክሪስቲያኖ መለሰ:- እናቴ የራሷን ህይወት መስዋዕት አድርጋ ነው እኔን ያሳደገችኝ፡፡ እራቴን በልቼ እንድተኛ ፆሟን ታድር ነበር፡፡

ገንዘብ የሚባል ነገር ጭራሽ አልነበረንም፡፡ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ ትጥቄን አሟልቼ እንድጫወት በሳምንት ሰባት ቀን፤ እና ምሽቱን ጽዳት ሠራተኛ ሆና አሳልፋለች፡፡

የኔ ጠቅላላ ስኬት ለእሷ የተሰጠ ማስታወሻ ነው። እኔ በህይወት እስካለሁ ሁልጊዜም ከጎኔ ትኖራለች፡፡ ከእኔ ማግኘት ያለባትን ሁሉ እሰጣታለሁ:: መሸሸጊያዬና የህይወቴ ታላቋ በረከት ናት።

ክብር ለእናቶች


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Nov, 18:12


ተከታታይ የፆም ቀናት...
ነገ ሀሙስ ፆም
ጁመዓ 13፣ቅዳሜ14 ና እሁድ15 አያመልቢድ ሰኞ
የቻልን እንፁም! አላህ ይወፍቀን

ISLAMIC SCHOOL️

13 Nov, 18:12


ነገ ሐሙስ ነው ከቻልን እንፁም ካልቻል ሌሎችን እናስታውስ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Nov, 17:11


#ጥቆማ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች መካከል በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዐረብኛ ቋንቋና ሥነ - ጽሑፍ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ከሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በመኾኑም መስፈርቱን የምታሟሉና ፍላጎቱ ያላችሁ አመልካቾች ከ8ኛ-12ኛ ክፍል ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ይዛችሁ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ዋናው ሬጅስትራር  በአካል በመቅረብ ከኅዳር 05 - 20/2017 ዓ.ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መኾኑ ተገልጿል።

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ወደ ፍሬሽማን ፕሮግራም ያለፋችሁ ተማሪዎች የዕድሉ ተጠቃሚ መኾን ትችላላችሁ ተብሏል።

ለበለጠ መረጃ:-
                     📱0920114937
(ሙሐመድ፣ የዐረብኛ ትምህርት ክፍል ኃላፊ)
(Muhammad, head Department of Arabic Language & Literature)

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Nov, 17:09


#ፔሬግሪን_ጭልፊት(peregrine falcone) በፍጥነት(320 ኪ.ሜ. በሰአት) በሚጠልቅበት(በሚበርበት) ጊዜ ወደ አፍንጫው ውስጥ የሚገባው አየር ሳንባው እንዲፈነዳ ሊያደርግ ይችላል፣ ነገር ግን በአፍንጫው ውስጥ ያሉት የአጥንት መጋጠሚያዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የአየር መተላለፊያን ይቆጣጠራሉ። ታዲያ የአውሮኘላን መሐንዲሶች አየርን ወደ አውሮፕላን ሞተሮች የማስተላለፍን ችግር በተመሳሳይ መንገድ ነበር የፈቱት ።
#ሱብሃን_አላህ

"هَٰذَا خَلْقُ اللَّهِ فَأَرُونِي مَاذَا خَلَقَ الَّذِينَ مِن دُونِهِ...
"ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡"
#سبحان_من_خلق_وصور_وأبدع_سبحانه
@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Nov, 10:17


ጌታየ እንዴት ልጀምር ስል ጠየኩት
"በኔ ስም ጀምር አለኝ"
ጌታየ ልቤን እንዴት አርጌ ረፍት ልስጠው ስል ጠየቁት?
"እኔን በማስታወስ ሲል መለሰልኝ"
ጌታየ አጠገቤ ማንም አልቀረም አልኩት
"አትፍራ እኔን ታገኘኛለህ አለኝ"
ጌታየ ልቤ ባዶ ነው አልኩት
"በውዴታየ ሙላው አለኝ"
ጌታየ ችግሮቼስ ስል ጠየኩት?
"በኔ ላይ ተመካ አለኝ"
ጌታየ ምኞቶቼስ ስል ጠየኩት
"ሰበብ አድርስ ከዛ እኔን ጠይቀኝ አለኝ"
እኔም ጌታየ ሁሉንም ነገር ስጠይቅህ እኔ አልከኝ አልኩት..!
"ጌታየም ከአፈር ፈጥሬህ ሩህ ያስገባሁት እኔ ነኝ አለኝ"


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Nov, 02:16


ቀንህን ለጌታህ ታማኝ በመሆን ጀምር። ጅምሩን ለእርሱ በመንበርከክ ካደረግክ፣ ቁጥር ስፍር የሌለው ችሮታውን ትቋደሳለህ።

#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

12 Nov, 18:55


በአላህ ስጧታ አፍራለሁ አንዳንድ ሰወችን ስመለከት እኔን በጥሩ እይታ ተመልክተው ቆንጆ የሆነን ደግነት ይመለከቱና እኔ በራሴ ላይ የማልመለከተውን ። አልሀምዱሊላህ መጥፎውን ነገር ደብቆልን በባሪያወቹ ዘንዳ ምንም ወንጀለኛ ብንሆን ለሰተረን። ,ይህ ነገር ከአላህ ጥቂት ውበቱ ነውና ለፈለገው ሰው የሚሰጠው አልሀምዱሊላህ መጀመሪያና መጨረሻ!


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

12 Nov, 18:13


🦋ህይወት ልክ እንደ መርፌ ቀዳዳ ያህል
ብትጠብህ አንተም ልክ እንደ ክር ሆኖ የማለፍ ብቃት ይኑርህ።


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

12 Nov, 16:01


በኢትዮጵያዊው ወጣት የተሰራ ድሮን

ሙሳ ከድር ይባላል። ነፍሱ ለቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በተለይ ደግሞ ለስፔስ ሳይንስ እጅግ የቀረበች ናት።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪው ሙሳ ከድር ይበል የሚያሰኝ በርካታ የድሮን ቴክኖሎጂ ሥራዎች እየሰራም ይገኛል።

በልጅነቱ ስፔስ ሳይንስ ነክ ዶክመንታሪዎችን እያየ ማደጉ ወደዚሁ ሳይንስ እንዲሳብ እንዳደረገው ይናገራል። በአሁኑ ወቅት ለተለያየ ዓላማ የሚውሉ ድሮኖችን አምርቷል።

ከጓደኛው ጋር በመሆንም የእሳት ማጥፊያ እና የሕንጻ መስታወት ማጽጃ ድሮን በመስራት ወደ ገበያ ለማቅረብ በሥራ ላይ ናቸው።

የእሳት አደጋ ሲነሳ ለማጥፋት የሚያስችል እና ለማጽዳት አደገኛ የሆኑ ረጃጅም ሕንጻዎችን፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መስኮቶችን ለማጽዳት አገልግሎት ላይ የሚውል ድሮን በስፋት ለማምረት ነው እቅዳቸው።

የሚሰራቸው ድሮኖች አንድን እቃ የተፈለገበት ቦታ ላይ አድርሶ (ጥሎ) የመመለስ አቅም እንዳላቸው የሚናገረው ሙሳ የህክምና እና የተለያዩ እቃዎችን ለማድረስ እንደሚያግዙም ይገልጻል።

ታዳጊው ሙሳ ከድር በ2019 በነበረው የጎላ አስተዋጽኦ እና ባሳየው ድንቅ ብቃት የኢትዮጵያ ወጣት የአስትሮኖሚ አምባሳደርነትን አግኝቷል።

በአሁኑ ወቅት ከድሮን በተጨማሪ ራሱን መንዳት የሚችል መኪና መፍጠር እንደቻለም ይናገራል።

ሙሳ ከእነዚህ ሥራዎቹ በተጨማሪም ሌሎች የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በመስራት ላይ ይገኛል። ወደ ፊትም በዘርፉ የተሻሉ ሥራዎችን የመስራት እቅድ ሰንቋል።
ዋልታ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

12 Nov, 06:35


አንቺን ካላየው መኖር አልችልም፣
ብሌኔ ነሽ😂😂

@islam_in_school @islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

11 Nov, 17:19


#ሊብያ በሀገሪቷ አዲስ ህግ አውጥታ መነጋገሪያ ሆኗል

☞ካፌዎች ለቤተሰብ ብቻ የተፈቀዱ ናቸው ጓደኛ ፣ሰራተኛ፣ የስራ ባልደረባ ሚባል ነገር የለም!👌🏻

☞ ሒጃብ ግዴታ ነው ነፃነት የሚል ካለ ወደ አውሮፓ ሄዶ መኖር ይችላል።

☞መኪና 🚘ይዛ ፀጉሯን ግማሽ ክፍት አድርጋ የምትሄድ ሴት መኪናዋ ይቀማል ትታሰራለች የተጠባበቀ ልብስ ለብሳ ምትሄድም እንዲሁ ትታሰራለች

☞ወጣት ወንድ ሱሪውን ዝቅ አድርጎ ከተገኘ ወንድነቱ እስኪመለስ ይታሰራል ።

☞ፀጉሩን አበላልጦ የተቆረጠ ✂️ ከተገኘ ፀጉሩ ይላጫል
ይህ ህግ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

ጀግናው የሊቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

10 Nov, 18:54


ታላቅ የምስራች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ስር ከሚገኘውና ከዚህ በፊት በሐገራችን የሸሪዓ በተለይም የተውሂድ እውቀትን በማስፋፋት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከነበረው ነሲሃ አካዳሚ ጋር በመተባበር ልዩ የሆነ ተከታታይ የሸሪዓ ትምህርት እንዳዘጋጀ ሲገልፅ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው:: አጠቃላይ ትምህርቱ ለሶስት ወራት የሚቆይ ሲሆን የፊቂህ፣ ሀዲስ፣ አቂዳ እና ተጅዊድን የመሳሰሉ ወሳኝ እና ቁልፍ የሆኑ እስላማዊ የትምህርት ዘርፎችን አካቶ ይዟል።

አጠቃላይ ትምህርቱ በበይነ- መረብ (Online) የሚሰጥ ሲሆን ትምህርቱን በተገቢው ሁኔታ ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ከAAU ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት እና ከነሲሃ አካዳሚ የጋራ የምስክር ወረቀት የሚያገኙ ይሆናል።

ለመመዝገብ፡ https://forms.gle/3tfAJdYGjjx7i1p39

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት በ @Aaumuslimstudentsunion1 ያናግሩን።

የዚህ ልዩ የእውቀት ማዕድ ተቋዳሽ በመሆን እወቅትዎን ያሰፉ ዘንድ ጋበዝንዎ። ለሚወዱት ሁሉም በማጋራት ውዴታዎን ይግለፁ።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

10 Nov, 07:55


ሳዑዲ ዓረቢያ ለአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ፕሮጀክት ግንባታ 100 ቢሊዮን ዶላር በጀት መድባለች። !

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

09 Nov, 09:13


ይሄንን ያውቁ ኖሮዋል? በኢትዮጵያ በቀን 300 አህዮች ይታረዳሉ...

የቻይና ኩባንያዎች ከፍተኛ በጀት መድበው ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል!

ጓደኞቻችንን እንደብቅ በቃ ተስፋም አይኖራቸው ከዚ ቦሀላ  😫

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

09 Nov, 07:41


•በሰው ቀልብ እየተጫወቱ አላህ ጌታ ሆይ ቀልቤን አረጋጋልኝ ብለው ይለምናሉ። አይታሰብም

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

08 Nov, 18:59


ኪሳራ የሌለው ትርፋማ ንግድ 👌👌

ሳዑዲ ሄዶ #አልቤክ(AL BAIK) 🍗🍗ያልበላ ይኖር ይሆን?
አንድ ሰው አልቤክ ለመግዛት ረጅም ሰልፍ መሰለፍ ይኖርበታል።
#የአልቤክ ባለቤት አላህ ይርሃመውና ከሚያገኘው ገቢ 5% ሰደቃ ይሰጥ ነበር ፣ታዲያ ይህ ሰው ወደ አኼራ ሲሄድ ሁሉም ሰው ይህ ሰደቃ ይቆማል ብሎ አስቦ ነበር ነገር ግን ልጃቸው ድርጅቱን ሲረከብ ሰደቃው እጥፍ አርጎ 10% አደረገው ታዲያ ገቢያቸውም እጥፍ እያደገ እስካሁን እንደተወደደ አለ።

👌👌👌ሁሌም ትርፋማ መሆን ከፈለክ ንግድህን ከአላህ ጋ አድርግ
الَّذِي يُقْرِضُ اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَاعِفَهُ لَهُ أَضْعَافًا كَثِيرَةً
ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ (አላህ) ብዙ እጥፎች ያደርግለታል

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

08 Nov, 05:51


እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጁምአ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ ። ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡
(ሱረቱ አል-ጁሙኣህ 62:9)

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا نُودِىَ لِلصَّلَوٰةِ مِن يَوْمِ ٱلْجُمُعَةِ فَٱسْعَوْا۟ إِلَىٰ ذِكْرِ ٱللَّهِ وَذَرُوا۟ ٱلْبَيْعَۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

07 Nov, 07:28


ሁላችን ጉዞ ላይ ነን፣ ወደ ኣኺራ!
ሟቾች እንደሆንን ሁላችንም በርግጠኝነት እናውቃለን። የማናውቀው የቀጠሮውን ቀን ነው።

ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

"ሁሉም ይጓዛታል - ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን - ያለው ስንቁን ይዞ።"

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

06 Nov, 10:04


Maths question🚩

📚This will help you to do more question in suitable way for entrance examination.

Don forget math is about doing more questions.😉


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

06 Nov, 07:40


ኩሉ ነፍሲ ዛኢቀቱል መዉት።:
💠 💠 #አንዲት #እናት #ወደ #አንድ #ሸይኽ #ፈትዋ #ለመጠየቅ #ትመጣና

↪️ለሸይኹ
" ሸይኽ ሆይ የልጆቼ እንቅልፍ በጣም ከባድ ነው ፣ #ለፈጅር #ሰላት እነሱን
መቀስቀስ ደከመኝና ምንድነው መፍትሄው? " በማለት ጠየቀች ።


↪️  #ሸይኹም " ሙቀት መቆጣጠሪያው ተቃጥሎ እሳት ቢተፋ ኖሮ ምን
ታደርጊ ነበር? " አላት

↪️ #እናት " #እቀሰቅሳቹኋለሁ " አለች

↪️ #ሸይኹ " ግንኮ እንቅልፋቸው ከባድ ነው " አላት

↪️ #እናት " በአላህ ይሁንብኝ አንገታቸውን እየጎተትኩ ቢሆንም
እቀሰቅሳቸዋለሁ " አለች

↪️ #ሸይኹ " ይህን የምታደርጊው #ከዱንያ #እሳት ልታድኚያቸው ነው ፣ ልክ
#እንደዛውም #ከአኺራ #እሳት🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ለማዳን ቀስቅሺያቸው " አላት ።
( ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻗُﻮﺍ ﺃَﻧْﻔُﺴَﻜُﻢْ ﻭَﺃَﻫْﻠِﻴﻜُﻢْ ﻧَﺎﺭًﺍ ﻭَﻗُﻮﺩُﻫَﺎ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﻭَﺍﻟْﺤِﺠَﺎﺭَﺓُ ﻋَﻠَﻴْﻬَﺎ
ﻣَﻠَﺎﺋِﻜَﺔٌ ﻏِﻠَﺎﻅٌ ﺷِﺪَﺍﺩٌ ﻟَﺎ ﻳَﻌْﺼُﻮﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻣَﺎ ﺃَﻣَﺮَﻫُﻢْ ﻭَﻳَﻔْﻌَﻠُﻮﻥَ ﻣَﺎ ﻳُﺆْﻣَﺮُﻭﻥَ )

💎💎💎" #እናንተ #ያመናችሁ #ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ
ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነች እሳት ጠብቁ ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች ፣
ኀይለኞች የሆኑ መላእክት አልሉ ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ)
አያምጹም ፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ ፡፡" 🍃🍃🍃

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

05 Nov, 10:32


«የታሰሩ ሙስሊም ተማሪዎች ዜና!
እለተ ማክሰኞ ጥቅምት 2017 E.C.

   በኒቃብ ጉዳይ ከታሰሩት የአዲስ ከተማ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ተማሪ አሚር አ/ከሪም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፤ ተማሪ አሚር በት/ቤት ውስጥ ት/ቱን በአግባቡ በመከታተል እና ተማሪዎች በአካዳሚም ይሁን በዲናዊ ህይወታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ በመምከር የሚታወቅ አርአያ ተማሪ ሲሆን፤ ከት/ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር አብሮ እህቶቻችን ለምን ኒቃብ መልበስ ይከለከላሉ ብሎ በሰላማዊ መንገድ በመጠየቁ ብቻ ት/ቤቱ በከፈተው የውሸት ክስ እለተ አርብ በትምህርት ገበታ ላይ እያሉ ስም ዝርዝራቸው ለፖሊስ ተሰጥቶ በየክፍላቸው እየተዞረ ከተለቅሙት ሙስሊምች ተማሪዎች አንዱ ነበር።

  በዛሬው እለት በዋለው ችሎት አቃቢህጉ ት/ቤቱን በማስረበሽ እና የት/ቤት ንብረትን በማውደም የሚል የውሸት ክስ በተማሪ አሚር አ/ከሪም ላይ ያቀረበ ሲሆን ከአዲስ አበባ መጅሊስ ተወክሎ የቆመለት ጠበቃ ሁሴንም በችሎቱ ላይ ባቀረበው ብርቱ ክርክር የዋስ መብቱ ተጠብቆ በመጨረሻም በ5ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ ተወስኗል፤ በቅድሚያ አላህን እናመሰግናለን በመቀጠል ለአዲስ አበባ መጅሊስ እና ለጠበቃ ሁሴን ምስጋናችን ይድረስ።

  ይህ በእንዲህ እንዳለ ተማሪ ነቢል እና ተማሪ ሰሚር በመጪው ሀሙስ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሲሆን የክስ መዝገብ ላይ ስማቸው ሰፍሮ ያልተያዙ ሙስሊም ተማሪዎች አሁንም ድረስ በፖሊስ እየተፈለጉ በመሆኑ ሁሉም የት/ቤታችን ሙስሊም ተማሪዎች በነፃነት የመማር መብታቸው ተከብሮ ወደ ቀድሞው የትምህርት ገበታቸው እስኪመለሱ ድረስ ሁሉም ሙስሊም የሚችለውን አስፈላጊ ትብብር እንዲያደርግልን በአላህ ስም እንጠይቃለን።

ኒቃቧንም ትለብሳለች‼️
ትምህርቷንም ትማራለች‼️»

©: የአዲስ ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

05 Nov, 05:14


📵ዋናው አጠቃቀምህ ነው

🌐አጠቃቀሙን ላወቀበት ኢንተርኔት ከጊዜው የአላህ ፀጋዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ደዕዋ ይደረግበታል፣ መረጃ ይሠጥበታል፣ ንግድ ይነገድበታል፣ ጓደኛ ይፈራበታል፡፡

♻️ ካልቻሉበትና አጠቃቀሙን ካላሳመሩ ጉዳቱም በዚያው ልክ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ፌስቡክ የብዙ ወጣቶችን ጊዜ እየበላ ነው፣ ዕድሜያቸውን እንክት እያደረገ ነው፡፡ ቁርኣን ተዘግቷል፣ ሐዲሥ ተረስቷል፣ ቁምነገር ተዘንግቷል፡፡

📵ጉዳቶቹ

1- ከመጥፎ ጓደኞች ጋር ሊያገናኝ ይችላል፣
2- እምነትና አመለካከትን የሚፈታተኑ መረጃዎች ይለቀቁበታል፣
3- ሞራልና ሥነምግባርን ይሸረሽራል፣
4- ከዚክር እና ከሶላት ያዘናጋል፣
5- ይበልጥ ጠቃሚ የሆነውን ነገር ከመሥራት ወደኋላ ያስቀራል፣
6- ለስንፍና እና ድክመት ያጋልጣል፣
7- ጊዜና ዕድሜን ወደማባከን ያደርሳል፣
8- ከትምህርትና ጥናት ያርቃል፣
9- ለአልባሌ ሱስ ይዳርጋል፣
10- የትዳር ሕይወትን ለአደጋ ያጋልጣል፣
11- ሥራ ያስፈታል

🔆ከጥቅሞቹ መካከል

1- ወደ እስልምና ለመጣራት፣
2- ትክክለኛውን የእስልምና አስተምህሮ ለማሳወቅ፣
3- ወደ መልካምነትና ሰላም መጣራት፣
4- በእስልምና ዙሪያ የሚነዙትን የሐሰት ወሬዎች ለማክሸፍ፣
5- የዲን ዉስጥ ፈጠራዎችንና የሐሰት አስተምህሮዎችን ለመዋጋት፣
6- ጠቃሚ ትምህርትንና መልካም ሥነምግባር ለማስፋፋት፣
7- የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን ለመቀበልና ለማስተላለፍ፣
8- ሌሎችም ብዙ ጥቅሞች

ስለዚህ ይህን አላህን ፀጋ ጠቃሚ ነገር ላይ በማዋል እንጠቀምበት።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

04 Nov, 18:11


አልገባኝም
==========
ኒቃብ የለበሱ ተማሪዎች ትምህርት ከተከለከሉ፣ አሸባሪና ጽንፈኛ ተብለው ከተወነጀሉ፣ አትከልክሉ ብለው የተቃወሙ ተማሪዎች ሴት ወንድ ሳይባል በጅምላ ከታሰሩና በሽብር ወንጀል ከተከሰሱ፣ የእምነቱን ትዕዛዝ ጠብቆ ጺም ያሳደገ መምህር አታስተምርም ተብሎ ደመወዙን ከ3 ወር በላይ ከተከለከለ…

እንደት ነው የአሁኑን ስርዓት ከያኔው ከጨቋኙ የወያኔ ስርዓት የተሻለ ነው ልንል የምንችለው?
ዳግም ወደዛ ስርዓት እየተመለስን አይመስልም? ምናልባት በዚሁ ከቀጠለና ነገሮች ከተወሳሰቡ ከዛ የከፋስ ላለመምጣቱ ምን ዋስትና አለ?
ይሄው ይህ አሸናፊ የተባለ ሰለምቴ ወንድማችን ጺምህን አሳድገሃል ተብሎ ከአስተማሪነት ደመወዙ ተከልክሏል። ምን ይሻል? መጅሊስ እነዚህን መሠረታዊ ነገሮች ለምን ተከታትሎ አያስከብርም? ከአቅሙ በላይ ከሆነ ለምን ለህዝበ ሙስሊሙ አያሳውቅም?

የእውነት ዋናው ስርዓቱ ከምንጩ ይሄን አካሄድ ሆነ ብሎ ይደግፋል? ወይንስ መንግስት እንዲጠላ ለማድረግ ከታች ያሉ ፍናፍንቶች ሴራ እያሴሩ? የዋናው የመንግስት ስርዓት የዚህ ሙስሊም ጠልነት ሴራ እጁ የለበትም እንል ዘንድ አቤቱታ ሲቀርብለት በአስቸኳይ ተከታትሎ ስሙን አስጠፊዎችን ተጠያቂ በማድረግ የተበደሉ ወገኖችን መካስ አለበት።

ምን እየተካሄደ ነው? አልገባኝም

Murad

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

04 Nov, 12:41


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦

በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

በTelegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

04 Nov, 08:16


መህዲ ተብሎ በሚጠራው በዐባሲያው ኸሊፋ ዘመን አንድ ሰው ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ። ወታደሮች አሰሩትና ኸሊፋው ዘንድ አቀረቡት።

* ኸሊፋው፦ "አንተ ነብይ ነህ?" ብሎ ጠየቀው።

- "አዎ" አለ ሰውየው።

* ኸሊፋው፦ "ወደ ማን ነው የተላክከው?" አለው።

- ሰውየው፦ "ወደ ማንስ እንድላክ መቼ ፋታ ሰጡኝ። ረፋድ ላይ ተልኬ ከሰዓት በኋላ አሰሩኝ።

[ረቢዑል አብራር፣ አልባቡ ታሲዕ]

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

03 Nov, 06:38


ሐሰነ-ል-በስሪይ (ረሒመሁ-ል'ሏህ) «ዱንያን ቸልተኛ ያደረገህ ነገር ምንድነው?» ሲባሉ፦

√ ሪዝቄን ማንም እንደማይወስድብኝ አወቅኩኝ፤ ልቤ ተረጋጋልኝ፣

√ ሥራዬን ማንም እንደማይሰራልኝ አወቅኩኝ፤ ትኩረት ሰጥቼ ሠራሁኝ፣

√ ጌታዬ እንደሚጠባበቀኝ አወቅኩኝ፤ በወንጀል ልቀጣጨው ፈራሁኝ፣

√ ሞት እንደሚጠብቀኝ አወቅኩኝ፤ ጌታዬን ለመገናኘት ስንቄን ሰነቅኩኝ!

rio

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

01 Nov, 19:30


የመምህራን ምገባ በሸገር ከተማ ተጀመረ !

በሸገር ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪና መምህራን የምግብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህ ፕሮግራም የተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥን ማስወገድ የተቻለ ሲሆን መምህራንም በማስተማር እና በመማር የበለጠ እንዲተጉ አድርጓል ተብላል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

01 Nov, 09:32


☞የ6አመት ህፃን ልጅ ከአባቱ ጋር እየተጫወተ እንዲህ ሲል

ልጅ☞~አባቴ ቲቸር ስታስተምረን ምን እንዳለችን ታውቃለህ ...

አባት☞እስኪ ንገረኝ ልጄ

ልጅ☞ ሰላት የኢስላም ምሰሶ ነው አንድ ሰው ሰላቱ ከተበላሸ ስራውም ተበላሸ ማለት ነው አለች እውነቷን ነው አባቴ??

አባት☞ አዎ ልጄ ሰላት በኛ ላይ ግዴታ ነው ወቅቷንም ጠብቀን
ልንሰግድ ታዘናል

ልጅ ☞ደግሞ አባቴ ቲቸር እንዳለችን ሰላት የማይሰግድ ሰው በቀብር ውስጥ ቅጣት ይጠብቀዋል ፣አላህ ይቀጠዋል ፣ጀሃነብም ያስገባዋል አለች እውነቷን ነው ??

አባት ☞አዎ ልጄ ትክክል ናት ሰላት በኛ ላይ ግዴታ ከመሆኑ አልፎ ወቅቱን አሳልፈን ብንሰግድ እንኳ ይቀጣናል ፡፡

ልጁ☞~ጀሃነም ማለት የሚያቃጥል እሳት ነው??

አባት ☞አዎ ልጄ ከሃዲዎች አመፀኞች ከአላህ ትዛዝ ያፈነገጡ በስግደታቸው የሚቀልድ ሰዎች መግቢያ ናት ፡

ልጅ ☞ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ

አባት ☞ምነው ልጄ አንተኮ ገና ልጅ ነክ አይዞህ አለው

ልጅ ☞አንተ እኮ አንድም ቀን ስትሰግድ አይቼህ አላውቅም አላህ አንተንም የሚያቃጥለው እሳት ውስጥ ሊያስገባህ አይደል ?

አባት ☞ደነገጠ በልጅ ንግግር ልቡ ተነካ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ለራሱም እንዲ ሲል ተናገረ ወላሂ እነዛ በስግደታቸው የሚቀልድ የሚዘነጉ ሰዎችን እደሚቀጣቸው በግልፅ ተናግሯል ይህንም አውቃቸዋለሁ ግን እኔ አልሰግድም ዋ!ነፍሴ ሲል ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ከዚያም አስተግፉሩላህ ወአቱቡ ኢለይህ በማለት ወደአላህ ተመለሰ .....

የአባትና የልጅ ንግግር እጅጉን ልቤን ነካው አባት ለብዙ አመት ሰላት አይሰግድም ከአላህ ርቆ የነበረ ሆኖ ሳለ አላህ ሲመራው ይህንን ህፃን ልጅ ሰበብ አድርጎለት ወደ ጌታው ተመለሰ ፡፡

አላህ ሆይ መልካም እንዲህ አንተ ገዴታ አድርገህ ወደ አዘዝከን
መንገድ የሚመልሱ ሷሊህ ልጆች ለሁላችንም ወፍቀን !!!!!!
አሚንንንንንንንንንንንን


የተለያዩ  ጣፋጭ አስተማሪና  ኢስላማዊ ታሪኮች የሚቀርቡበት ምርጥ ቻናል ነው።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

31 Oct, 17:07


ትንሾቹ ሱመያዎች🔥🔥🔥

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

31 Oct, 05:42


በኒቃባቸው ምከንያት ከትምህርት ገበታ ታግደው የነበሩ ተማሪዎች ወደትምህርት ገበታ እንድመልሱ ከስምምነት መድረሱን የአዲስአበባ መጅሊስ ገለፀ!

-ሀሩን ሚዲያ፣ጥቅምት 21/2017፣አዲስአበባ

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰሞኑን በከተማችን በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በመዋቅሮቻችን አማካኝነት በየደረጃው ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱ ገልጿል።

በትላንትናው እለት ጥቅምት 20/2016 የከፍተኛ ምክር ቤታችን ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣የአ/አ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁም መሰረት ችግሩ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለና ዘላቂ መፍትሔ የሚያሻው ከመሆኑ አንጻር የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል መጅሊስ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ ዘላቂ እልባት የሚያመጣ የመፍትሔ ሀሳብ እንዲያቀርብ ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል።

ከያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው የተገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን በጊዜያዊነት ከመገለላቸው በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት ተደርሷል።

ከፍተኛ ምክር ቤታችን ቀሪውን ስራ በትኩረት የሚያከናውን ሲሆን በውይይቱ የተካፈሉ የከተማዋ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በሙሉ ችግሩን ለመፍታት ላሳዩትን ተነሳሽነት በከተማዋ ሙስሊም ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን ሲል የአዲስ አዲስ አበባ መጅሊስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባስተላለፈው መልክት አስተዋቋል።

@islam_in_school
@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

30 Oct, 12:33


ወይ ጥሩ ተናገር ወይም ዝምበል

የማስታወቂያው ንጉስ ባይስ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

30 Oct, 06:08


በጣም ቆንጆዋ እሷ ናት🥰🥰

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

29 Oct, 18:44


ጫማህን የምታወልቅበት ቦታ እስካልሄድክ ድረስ

ቀዳዳ ካልሲ ማድረግ ምንም ችግር የለውም😁

ልክ ነኛ ? 👇👇👇

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

29 Oct, 12:13


አዲስ ከተማ ት/ቤት ፖሊስ አስገብተው በሰላማዊ መንገድ በኒቃብ ጉዳይ የጠየቁ ተማሪዎችን እያስረበሹ ነው።

ፖሊስ ሰላማዊ ዜጎችን ትቶ ኒቃቢስቶችን አሸባሪና ጽንፈኛ ያለውን ርዕሰ መምህርና አጋሮቹ አይዝም እንደ? ወይንስ እነርሱም ይስማማሉ?

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

29 Oct, 09:03


በትምህርት ቤቶች በየጊዜው የሚያገረሸው የኒቃብ ክልከላ ጉዳይ ቋሚ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል።
«=» «=» «=» «=» «=»

ፊትን ከባዕድ ወንዶች መሸፈን ግዴታ መሆኑ የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች አቋም ነው።
ሆኖም ሴቶች ፊትና በማይሰጋበት ሁኔታ #ለአስፈላጊ_ጉዳይ ፊታቸውን ለወንዶች ማሳየት  እንደሚችሉ የሁሉም የፊቅህ ሊቃውንት ንግግር ያሳያል።

በዚህ መሰረት ተማሪዋ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ ወደ ፈተና ማእድ ስትገባ፣  አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር ወይም በማንኛውም ጊዜ ማንነቷን ማጣራትና ከመታወቂያዋ ጋር ማመሳከር ሲያሰፈልግ ፊቷን ገልጣ አሳይታ መልሳ መሸፈን ትችላለች።
«ሙሉ በሙሉ ተገልጠሽ ካልቆየሽ አትገቢም!» ማለት ግን ሀይማኖታዊ መብትን በግልፅ የሚጋፋ፣ ሴኪዩላሪዝም ራሱ የማይደግፈው… ምንም አግባብነት የሌለው የግለሰቦች ድርቅና ነው።

ኡስታዝ ኤሊያስ አህመድ حفظه الله

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች
#ትምህርቷንም_ትማራለች

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

28 Oct, 12:41


የሞተ ትውልድ ሲኖር እንዲህ የማንም መጫዎቻ ይሆናል።

ይህ በፎቶው የምትመለከቱት ደብዳቤ ኒቃብ ሲያስወልቋት ትምህርቷን ላለማቋረጥ በማስክ ለምትማር እህት የተሰጠ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው።

ይህኔ ከአንድ ተቃራኒ ፆታ ጋር አንድ ተማሪ ስትጃጃል ብትገኝ ምንም አትባልም። ከጉልበቷ በላይ አሳጥራ ብትለብስም ምንም አትባልም።

ኒቃብ ግን በጽንፈኞች ዘንድ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ እስከዚህ ደረጃ አድርሷል።

ይህ ለምን ሆነ ከተባለ ምንም እንደማታመጣ ይታሰባል። ምንም የማያመጣ ተቋም እንዳለም ታምኗል።

በጣም እየገረመኝና ትርጉም እያጣ የመጣብኝ ነገር የመጅሊስ ነገር ነው።
ይህኔ በፊት ቢሆን «የኡማውን መብት የሚያስከብር ጠንካራ ተቋም አጣን!» እንል ነበር። ዛሬስ? ምን አዲስ ተገኘ?

ለየትኛዋ ኒቃቢስት መብት መከበር መጅሊስ ምን ሠራ? በኒቃብ ምክንያት ለታገዱት የጉንችሬ እህቶች መፍትሄ አመጣ?
ዛሬስ በየ ሃይስኩሉና ካምፓሱ ለሚከለከሉት ምን አደረገ?

ለዚህ ለዚህማ የበፊቱስ ምን አጠፋ? በምን ተሻሉ?

ወይንስ ኒቃቢስቶች የሙስሊሙ አንድ አካል አይደሉም ብለው ያምናሉ? ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር ካለ ለምን ለህዝቡ አያሳውቁም?

መልስ እንሻለን

እህቶቻችን እንሰተር ባሉ እንደ ወንጀለኛ እየተቆጠሩ ተሳቀውና ተገልለው የሚኖሩባት ሃገር ማብቃት አለባት።

ፍትሕ ለኒቃቢስቶች

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

28 Oct, 06:37


ኔታኒያሁ በራሱ ህዝብ ሲዋረድ!

ዛሬ ኔታኒያሁ በጦርነቱ በሙጃሂዶች ከተገደሉ ወታደር ቤተሰቦች ጋር ፕሮግራም ነበረው።

በዚህ መድረክ ላይ ህዝብ በተሰበሰበት ንግግር እያደረገ እያለ የሟች ወታደር ቤተሰቦች እንዳለ በመጮህ
" በራስህ እፈር ልጆቻችንን አስጨረስካቸው አለቁ ህዝባችንን ለጦርነት ማገድከው" እያሉ ንግግሩን አስቋርጠውታል።

እርሱም በሀፍረት ምን ማለት እንዳለበት ግራ ገብቶት ንግግሩን አቋርጧል

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

27 Oct, 05:34


የቴሌግራም መስራች Pavel Durov እንዲህ ሲል ተናገረ

”የሚቆጨኝ ነገር ግን ማቆም ያልቻልኩት ነገር ቢኖር McDonald’s ገብቼ በርገር አዝዤ የምትጠቀው 5 ደቂቃ ነው። 5 ደቂቃ ሙሉ ያለምንም ስራ መቀመጥ ማለት ለ 5 ደቂቃ መሞት እንደማለት ነው።

ልጆች Game አጨዋወት ሳይሆን Game አሰራር ተማሩ!

ወጣቶች የፊልም Recommendation ሳይሆን የስራ ፈጠራ Recommendation ተመልከቱ ወደፊት ታመሰግኑኛላቹ”።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

26 Oct, 18:49


ስሙማ ሰዎች ድሮ ክላስ ውስጥ ወይም ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ኒቃብ ማድረግ ይቻላል እንዴ?

ISLAMIC SCHOOL️

26 Oct, 04:58


አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላለፍት ሶስት አመታት ኒቃብ ለብሰው ሲማሩ የነበሩ ተማሪወች ወይ አውልቁ ወይ ትምህርት ቤት አትምጡ ተብለዋል ።

ከትምህርት ከታገዱም ሳምንት አለፍቸው መጅሊሱም መረጃ ቢደርሰውም እየተባበረ አይደለም እዛ አከባቢ ያላቹህ የተማሪወች ወላጆች ወጣቶች ይህንን ችግር በኔነት ስሜት ተከታትላቹህ እህቶቻችን ዳግም ትምህርት እንዲመለሱ እንቅስቃሴ አድርጉ ።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

25 Oct, 05:19


#ተቀይሯል #Remedial

ከዚህ በፊት ለሪሚዲያል ተማሪዎች በተቋማት የሚሰጠው ውጤት 30% ሲሆን 70% ደግሞ የሚሰጠው ከት/ት ሚኒስቴር ነበር።

አሁን ግን ይህ አሠራር ተሻሽሎ 100% ከማዕከል(በትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጡ ምዘናዎች) በኩል እንዲሰጥ ተወስኗል።

ተማሪዎች በሚማሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠው 30% የውጤት ምዘና  አሰጣጡ ወጥነት ስለሚጎድለው ይሄን ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አክሎ ገልጿል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

24 Oct, 14:27


የ 2017 ዓ.ም የ Freshman Official Group ተከፈተ 🏆🙋‍♀🙋

💁‍♀ በ Groupኣችሁ ሀሳባችሁን ከመለዋወጥ እና ከ ትውውቅ ባሻገር  በሁለቱ ትምህርታዊ ቻናሎች አማካኝነት ግቢያችሁን የሚመለከቱ

🔥 Study materials!
🔥 Gbi Info.!
🔥 Mid Exam!
🔥 Final Exam!
🔥 Coc Exam!

👩‍🏫 በ Pdf እና Zip file Organized🗞 ሁነው  ይቀርቡላችኋል!🛒

Click on your university’s link below and start your journey! 👇🏾

🔔  1. AA SCI. & TECH UNIVERSITY👇🏾
 https://t.me/AASTU2017_Freshman      

🔔  2. Adama science & technology University👇🏾
https://t.me/Astu2017_Freshman

🔔  3. Addis Ababa University👇🏾
https://t.me/AAU_freshman_2017

🔔  4. Adigrat University👇🏾
https://t.me/Adigrat_Freshman_2017

🔔  5. Ambo University 👇🏾
https://t.me/+6ZmSplCu4m9iNDNk

🔔  6. Arba Minch University👇🏾
https://t.me/AMU_freshman_2017


🔔  7. Arsi University 👇🏾
https://t.me/ARU_freshman_2017

🔔  8. ASOSSA UNIVERSITY👇🏾
 https://t.me/+plMoa60V8DtiYTA0

🔔  9. Axum University.👇🏾
 https://t.me/AXU_freshman_2017

🔔  10. Bahir Dar University👇🏾
https://t.me/+ULIv64ndQOc3NTA0

🔔  11  BONGA UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/+iKEqGSlPIFU1ODE0

🔔  12.  BULE HORRA UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/BHU_freshman_2017

🔔 13. DEBARK UNIVERSITY👇🏾
 https://t.me/+E-t2Q5Dpr3ZlZDE0

🔔 14 Debrebirhan University👇🏾
https://t.me/DBU_freshman_2017

🔔 15 Debremarkos University👇🏾
https://t.me/DMU_freshman_2017

🔔 16.  DEBRETABOR UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/+MbfJfqT5G0RjODE0

🔔 17.  DEMBI DOLO UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/+evd64Xk-1GE0MDJk

🔔  18  Dilla University👇🏾
https://t.me/+DejMScz8tkRiODM0

🔔 19  Dire Dawa University👇🏾
https://t.me/+Wnw49U1b60liY2I0

🔔  20 Gambella University👇🏾
 https://t.me/GMU_freshman_2017

🔔  21 Gondar University👇🏾
https://t.me/GU_freshman_2017


🔔  22 Haramaya University👇🏾
https://t.me/+fdwbWV-HWB9iODA0

🔔 23. Hawassa University👇🏾
https://t.me/+SQlv3k2kaYdiOTRk

🔔  24 INJIBARA UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/IU_freshman_2017

🔔  25. Jigjiga University👇🏾
https://t.me/+7OdaCxweyK05MzI8

🔔  26. Jimma University👇🏾
https://t.me/JU_freshman_2017

🔔  27.  JINKA UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/+_5VtjiX8MUsyODhk

🔔  28  KEBRI DEHAR UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/+CvEXMK1lMYdiMWY0

🔔  29 Kotebe Metropolitan University👇🏾
https://t.me/KMU_freshman_2017

🔔  30 Meda Welabu University👇🏾
https://t.me/+RfSoDggZzxQwMjU0

🔔  31 Mekelle University 👇🏾
https://t.me/MU_freshman_2017

🔔  32 MEKIDELA AMBA UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/MAU_freshman_2017

🔔  33 METU UNIVERSITY 👇🏾
https://t.me/MTU_freshman_2017

🔔  34 Mizan-Tepi University 👇🏾
https://t.me/+724vEfofCWQ0MTA0

🔔  35. Oda BultumOBU 👇🏾
https://t.me/+Ke2x3rPiNEJiYjVk

🔔  36 RAYA UNIVERSITY👇🏾
https://t.me/+6HZUVm0gQWNmM2Zk

🔔  37 Selale University 👇🏾
https://t.me/SLU_freshman_2017

🔔  38 Semera University 👇🏾
https://t.me/+Srg_Im1Z3dwyMGRk

🔔 39 WACHAMO UNIVERSITY 👇🏾
https://t.me/+jzYPxu_JpUFlNGJk

🔔  40 Welketie UNIVERSITY 👇🏾
https://t.me/+zkOierFEkso3ZDhk

🔔  41 WERABE UNIVERSITY 👇🏾
https://t.me/WRU_freshman_2017

🔔  42 Wolayita Sodo University 👇🏾
https://t.me/+QxTSX7CCaQViOTI0

🔔 43 Woldiya University 👇🏾
https://t.me/+sx3HWJhuU4tjNjQ0

🔔 44  Wollega University 👇🏾
https://t.me/+1DxvJ9T1HdRhYjk8

🔔  45 . Wollo University 👇🏾
https://t.me/Wou_freshman_2017

ISLAMIC SCHOOL️

24 Oct, 13:06


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

Good luck

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

24 Oct, 05:00


ሰላም ለእነዛ.....

ክፍል ውስጥ አስተማሪ እየገላመጣቸው፣ እያሳቀቃቸው፣ በውጤታቸው እየተጫወተ፣ አትችይም እያለ በተማሪ ፊት ክብራቸውን ዝቅ ሊያደርግ እየሞከረ፣ በማስክ አውልቂ ምክኒያት ቢሮ ለቢሮ እያንከራተታቸው ከዳይሬክተር እስከ ጥበቃ በስድብ ሊያንቋሽሿቸው እየሞከሩ........

ይሄን ሁሉ ችለው ሂጃባችንን አናስነካም ብለው አላማቸውን ሰንቀው ፣ በጌታቸው ተመክተው፣ ለካፊር እጅ አንስጥም ፤ተምረን ሙስሊሙን ኡማ እናገለግላለን ፤ ኢስላምን እንኻድማለን የሚል ትልቅ ተስፋ አንግበው ጥርሳቸውን ነክሰው ብዕር እና ማቅለሚያቸውን ይዘው በማለዳ ትምህርት ቤት ለሚመላለሱት ልእልት የhighschool ተማሪዎች


እነዚህን ጀግኒቶች ምን ብለን እንጥራቸው!!!

if

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

23 Oct, 17:20


በህይወት ውስጥ በጣም ደስ የሚል
ስሜት ማለት ከአይን ውስጥ ብዙ
እንባ ማፍሰስና በአላህ ፊት ስሜትን
መግለፅ ❤️‍🩹

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

23 Oct, 00:06


#ጣፋጭ_ስኬት🌼

ሰማይ ሩቅ መስሎ ቢታይም  ከሰማይ በላይ የሆነው ጌታ ግን ቅርብ ነው፡፡ እጅህን ከፍ አድርግና ተጣራ ችግሮች የሚፈቱት በዱአ ነው፡፡ ችግሮችህ አንዲፈቱና፤ የምትፈልገውን ነገር ለማሳካት ከባዱ መሳሪያ ዱዓ ነውና እጅህን ከፍ አድርገህ ጠይቀው አላህም የጠየከውን ለመስጠት ጥሪህንም ለመቀበል ቃል ገብቷል። አሰተውል የዚህ ምድር ትልቁ መሳሪያ ዱዓ ነው።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

22 Oct, 10:43


ሁልጊዜም የምላስህን ጫፍ ጠብቃት እናም በብዙ ቦታ ወጥመድ ውስጥ ጥለሽኛል በላት፡፡

አቡበከር ረ.ዐ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

21 Oct, 06:26


አላህ በአንዴ አያዋርድም
🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳

ኢብኑ ሐዝም ሲሰርቅ ተይዞ ወደሳቸዉ የተወሰደን ሌባ "እጁን ቁረጡት"በማለት ትዕዛዝ ሰጡ። ሌባዉ "ምሕረት ያድርጉልልኝ።

ከዚህ በፊት በ ፍፁም ሰርቄ አላዉቅም " እያለ ቢማፀናቸዉም አቡበክርለሌባዉ "በርግጥ እነዋሸህ ነዉ።

ነፍሴ በእጁ ባለችዉ አላህ እምላለሁ። አላህ አንድን ሙእሚን  ገና በበኩር ኀጥያቱ አያወርደዉም አሉት።

ዑመር የሌባዉ እጅ እንዲቆረጥ ያስተላለፉትን ትዕዛዝአፅንተዉ እጁ ተቆረጠ። በኋላሌባዉ ሐቁን እንዲያወጣ ዐሊይ ሲያግባቡት ሌባዉ"በርግጥ ሲሰርቅይህ ለ 21ኛ ጊዜዬ ነዉ"ብሏቸዋል።

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

20 Oct, 05:36


ለበርካታ ጊዜ ለመረዳት እየሞከርኩ ነበር
ነብዩላህ ሙሳ ከመድየን ሴት ምንን ቢመለከት ነበር......!
አስር አመታትን ለሷ መህር ሲል ያሳለፈዉ እነሱ
ዘንድ

መልሴን በአላህ ሱብሐነሁ ወተአላ ቃል ዉስጥ አገኘሁት

فَجَآءَتۡهُ إِحۡدَىٰهُمَا تَمۡشِي عَلَى ٱسۡتِحۡيَآءٖ

አንዷ ሀያእ (በአይናፍርነት ) ወደሱ መጣች

አላህ የሷን ቁመት ወይም መልኮን ሳይሆን
እሷ ዘንድ ያለዉን ዉዱን ነገር ነበር "ሀያእነቶን" የተናገረዉ

ለሴት ልጅ ዉዱ ነገር ሀያእነቷ ነዉ!

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

19 Oct, 04:24


#ከሀዲስ_ምህዳር

የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ ሰባት አጥፊ ወንጀሎችን ራቁ።" ሶሐቦች ምንድን ናቸው? ሲሉ ጠየቁ። የአላህ መልዕክተኛ: "በአላህ ማጋራት ፣ድግምት ፣በህግ ቢሆን እንጅ ያችን አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል፣ ወለድ መብላት ፣የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ የጦርነት ቀን  መሸሽ እና ጥብቅ፣ ከዝሙት የዘነጉ ምእምናትን መስደብ ናቸው።" አሉ። ]

📚ቡኻሪ ዘግበውታል

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

18 Oct, 03:55


ከሱረቱል ከህፍ የመጀመሪያ አስር አያዎችን የሀፈዘ ከደጃል ፈተና መጠበቂያ ይሆነዋል❗️

روى الحاكم في المستدرك مرفوعا إن من قرأ سورة الكهف يوم الجمعة أضاء له من النور ما بين الجمعتين. وصححه الألباني

📌ረሱል ﷺ በጁሙዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን ያነበበ በሁለት ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል ብለዋል።

📌ነብዩ ﷺ በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ የናንተ ሰለዋት እኔ ዘንድ ይቀርባልና ብለዋል።

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنّ في الجُمُعَةِ لَساعَةً، لا يُوافِقُها مُسْلِمٌ، يَسْأَلُ اللهَ خَيْرًا، إلّا أعْطاهُ إيّاهُ.﴾

“በጁምዓ ቀን አንዲት ሰዓት አለች። በዛች ሰዓት አንድ ሙስሊም አላህን መልካምን ነገር እየጠየቀ አይገጥምም፤ ለሱ የጠየቀው የሚሰጠው ቢሆን እንጂ።”

ሙስሊም ዘግቦታል

📌በጁሙዓ ቀን ኹጥባ በሚደረግበት ጊዜ ሰዎች ላይ መረማመድ እና ማውራት የተከለከለ መሆኑን አንዘንጋ።


እንዲሁም ከሚስተዋሉ ስህቶች አንዱ ጁሙዓ ሙባረክ መባባል ነው ይሄ መሰረት የለውም።

#ጁመዓ_ነው_ሰለዋት_እናብዛ

اللهم صلي على محمد وعلى آل محمد ،
كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم ،
وبارك على محمد وعلى آل محمد ،
كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم، في العالمين إنك حميد مجيد


@islam_in_school
@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

17 Oct, 12:24


قال رسول الله ﷺ :

اقرؤا سورة البقرة، فإن أخذها بركة، وتركها حسرة، ولا يستطيعها البطلة .
صحيح مسلم - ٨٠٤ -

البطلة : هم السحرة .

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

ሱራ አልበቀራን አንብቡ፣ እሷን መውሰድ በረካ ነው፣ እሷን መተው ፀፀት ነው፣ ሳሂሮችም(ጠንቋዮችም)  አይችሏትም።

ሳሂህ ሙስሊም - 804 -

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

16 Oct, 05:25


አነስ (ረዲየላሁ አንሁ) ስለ ሀቢባችን ውበት ሲገልፅ እንዲህ ይላል፦

"ጨረቃዋን አየኋት ከዛ ረሱልን አየኋቸው መልሼ ጨረቃዋን አየኋት ከዛም መልሼ ረሱልን አየኋቸው   
ወላሂ ረሱል ከጨረቃዋ በላይ ውብ ነበሩ። "

ሰሉ አለል ሀቢብ❤️
ሰሉ አለል ነቢይ ❤️

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

15 Oct, 06:43


አንድ የሳውዲ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ አንድ ተማሪ, አንድ አስተማሪ, አንድ ሱፐርቫይዘር እና ርዕሰ መምህር ማግባት ችሏል።

አጂብ!

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

14 Oct, 16:53


በኢትዮጵያ ከአምስት ሰዎች አንዱ በህይወት ዘመኑ የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥመው ተነገረ

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

14 Oct, 10:31


ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:-

በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን ::

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል :: ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን ::
    
📌 AAU MUSLIM STUDENTS UNION - 0909524252

Main and FBE Campus
📌 ኢስማዒል አብዱሮ - Main campus - 0936906322
📌 አብዱረሂም አሚን  - FBE Campus - 0995477358

AAiT (5 Kilo) Campus
📌 ማህፉዝ ነጋሽ - AAIT - 0996220264

4 Kilo Campus
📌 ዘይድ ሳዲቅ - 4kilo - +251992546811
📌 መስዑድ ውበቱ - 4kilo - +251905877461

Sefere Selam Campus
📌 ሙሐመድአሚን - s.selam campus - 0917046439
📌 ኑር አወል - s.selam campus - ++251951044287

Ldeta Campus
📌ያህያ አባ ረሻድ - Ldeta Campus - 0965435476 or 0777435476
📌 አብዱልዓዚዝ ሙሄ - Ldeta Campus - 0909534342 or 0777534342

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

14 Oct, 07:41


ኢብኑል ቀይም አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይሉ ነበር፡–

"ለአሏህ ተብሎ የሚመሰረት ወንድማማችነት ምሳሌው ልክ እንደ አይን እና እጅ ነው!

አይን ሲያለቅሰ እጅ  ይጠርገዋል እጅ በሆነ ነገር ከተጎዳ ለሱ ብሎ አይን ያለቅሳል”

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Oct, 16:12


የ ሳውዲው አልጋወራሽ ልዑል ቤተሰብ
80 ለሚሆኑ ጭልፊቶቹ 1(አንደኛ )ደረጃ መዓረግ የአውሮፕላን ቲኬት በመግዛትና በማጓጓዝ የዓለምን ህዝብ አጃኢብ አሰኝቷል


@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Oct, 11:05


ሙሉ ዓፊያ ያላቸው ተኝተው የምርኩዝ ባለቤቶች ደግሞ ምርኩዛቸውን ተደግፈው #ፈጅርን በጀመዓ ለመስገድ ሲሄዱ ባየህ ጊዜ ስንኩልነቱ ያለው አካል ላይ ሳይሆን ልብ ላይ መሆኑን እወቅ።

@islam_in_school
@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Oct, 09:20


ከዚህ አለም ጥቅም አይንህን ጨፍን፤ ቀልብህንም አዙር። አደራ ይህች ዱንያ
ካንተ በፊት የነበሩትን ሰዎች እንዳጠፋችው ሁሉ አንተንም እንዳታጠፋህ። አወዳደቃቸውን እና የተረፋቸውንም መጥፎ ነገር አይቻለው።


  ዑመር ኢብኑ አል ኸጣብ (ረ.ዐ.)

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

13 Oct, 07:39


  አንድ ቀን ውዱ ነቢያችን ሙሐመድ  ﷺ  አለቀሱ !
ሶሀቦችም ☞ለምን ያለቅሳሉ ያረሱለላህ?
➛ነብያችንም ﷺ ☞ወዳጆቼ ናፍቀውኝ
ሶሀቦች ☞እኛ ወዳጆቾ አይደለንም እንዴ ያረሱለላህ?
ነብያችን ﷺ ☞ አይ እናንተማ ጓደኞቼ ናችሁ !

ወዳጆቼ ግን ከእኔ በኃላ የሚመጡ እኔን ሳያዩ በእኔ የሚያምኑ ህዝቦቼ ናቸው።
ያ ማለት ደግሞ እኔ፣ አንተ፣ አንቺ፣ በአጠቃላይ እኛን በመናፈቅ ነው ያለቀሱት።

"አንተን ለማወቅ የማይፈልግ ታዋቂ ሰው አድናቂ አትሁን ይልቁንስ አንተን በመናፈቅ ከ1400 አመታት በፊት ያለቀሱልህን ዝነኛ ነቢይ አድናቂ ሁን"⇓

#ናፍቀናቸው ባለቀሱት ነብይ ላይ ሰለዋት አውርዱ
اللهم صـــــــلــــــى  وســــــــلــــــــم على نبـــيـــــنا محمدٍ

@islam_in_school
@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

12 Oct, 16:40


ጥናቶች እንደሚያሳዩት አንዳንድ ጊዜ ሕፃናት አዲስ ወንድም ወይም እህት እንዳይኖራቸው በእኩለ ሌሊት ማልቀስ ይጀምራሉ!

በተለይ አርብ ምሽት

ወይ አጥኚዎች🥺😂😂

@islam_in_school
@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

12 Oct, 11:13


ነብያችን ▫️ እንዲህ ብለዋል ፦
"አንድ ሰው እራሱን በረገመ ቁጥር መላኢካዎቹ አሚን ይላሉ። ስለዚህ መልካም ዱዓን አድርጉ እንጂ እራሳችሁን አትርገሙ።"

📃【ሙስሊም ዘግበውታል።】

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

12 Oct, 06:01


ሦስቱ ገዳይ ባህሪያት

⓵ ወሰን ማለፍ
"የሰዉ ልጅ ሆይ! በአመፃቹህ ተጎጂዎቹ እናንተዉ ናቹህ።" ቁርአን(10:23)

⓶ተንኮል መስራት
"መሠሪነትም ራሳቸዉን (መሠሪዎችን) እንጅ ሌላን ማንንም አይጎዳም።" ቁርአን (35:43)

⓷ቃልኪዳን ማፍረስ
"ቃልኪዳኑን ያፈረሰ የሚጎዳዉ ራሱን ነዉ።" (ቁርአን 48:10)

@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

11 Oct, 17:17


በህይወት የሌሉት የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ-ኢል ይፋዊ የህይወት ታሪክ ላይ የአየር ሁኔታን የመቆጣጠር ልዩ ሃይል እንዳላቸውና በህይወት ዘመናቸው ሽንት ቤት ገብተው እንደማያውቁ ተፅፏል።

ወይ ሰሜን ኮረያ😁🙌

@islam_in_school
@islam_in_school

ISLAMIC SCHOOL️

11 Oct, 16:21


አንድ ባንግላዲሻዊ 8 እህቶቹን ወደ ኡምራ ወስዶ የረጂም ጊዜ ህልማቸዉን አሳካላቸዉ!

@islam_in_school

5,245

subscribers

1,706

photos

321

videos