ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ @elaftube Channel on Telegram

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

@elaftube


ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ (Amharic)

ኢላፍ ቲዩብ የቴሌግራም ክፍል ነው አሁን ለማስተካከል እባኮት ተጠቃሚው። ጠቃሚ በመሆን ኢላፍ ቲዩብ ለሃገሮችና ጥራቄዎች ራሳቸውን ለማስወገድና ለማክበር ተጠቃሚ ይዞት ያላቸው። ይህ ቦታ ያውቃሉ እና አዝናኝ አስተያየቶች አጋርርዋል። ELAF TUBE አንድ አገር ደግሞ ትክክለኛ የመረጃ ገዳጅ በዚህ ቦታ ነው እና ሌሎችም እንዲሁም በውስጥ የተለያየ ንብረት ለመክፈልና ገለጹለትን እንዲሆን ቱቦትን በቀኝ ፈላጊ ይገኛል። ይህ ቦታ በፍጹም ሀገር ውስጥ ይቆማቸዋል። ይህ ቦታ ስንት ላይ እንዲባል ሊከታተሉ ይችላል።

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

21 Nov, 11:38


https://youtu.be/5DD5ZXWbWek

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

20 Nov, 21:08


ሰከን፣ ጎጆ እንዳይበተን
~
ፍቺ ላይ መጠንቀቅ ይገባል። ሚስት በትንሽ በትልቁ ፍቺ ልትጠይቅ አይገባም። ባልም ፍቺን ማስፈራሪያ ሊያደርግ አይገባም። ህይወት የጋራ ነው። ፍቺ በድንገተኛ ብስጭት ሳይሆን አስቦና አሰላስሎ ነው መወሰን ያለበት። እለታዊ ግጭትን መነሻ በማድረግ ለፍቺ መቻኮል ኋላ ፀፀት ላይ ይጥላል። ትዳር ተቋም ነው። ጤነኛ ሰው ተቋምን በቅፅበታዊ ግጭት አይበትንም። ይልቁንም ከማፍረሱ በፊት ጊዜ ወስዶ ደግሞ ደጋግሞ ያስብበታል።

መታወቅ ያለበት በኢስላም ፍቺ ገደብ የለሽ አይደለም። ልቅ በሆነ መልኩ እንደፈለጉ እየፈቱ መመለስ፣ እየፈቱ መመለስ የሚባል የለም። ዳግም መመላለስ የሚቻልበት ፍቺ ቁጥሩ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። ሶስተኛ የፈታ ሰው በቀላሉ መመለስ አይችልም። በረባ ባልረባው ፍቺ እየፈፀሙ ኋላ ሲጨንቃቸው መፍትሄ ፍለጋ የሚባዝኑ ብዙዎች ናቸው። እንደዋዛ የቀለዱበት ትዳር እንደዋዛ አይጠገንም። ኋላ ለከባድ ፀፀት ከመጋለጥ በፊት በጊዜ መጠንቀቅ ነው የሚበጀው። በተለይ ደግሞ ልጅ ሲኖር ጉዳቱ ጥልቅ ስለሚሆን ይበልጥ መጠንቀቅ ይገባል።

በነገራችን ላይ ሚስት የወር አበባ ላይ እያለች ፍቺ መፈፀም አይቻልም። እንደዚሁም ከወር አበባ ከጠራች በኋላ ግንኙነት ተፈፅሞ ከሆነም ፍቺ አይፈፀምም። ይህንን ሱና መጠበቅ በድንገተኛ ስሜት ፍቺ እንዳይፈፀም ይረዳል። አብዛኞቹ ትዳሮች የሚፈርሱት ጥንዶቹ የጦዘ ብስጭት ላይ በሚሆኑ ጊዜ ነው። ብስጭታቸው እስከሚበርድ ውሳኔያቸውን ቢያቆዩት ብዙ ኒካሕ ከመፍረስ ይድናል።

||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//elaftube

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

19 Nov, 13:44


https://youtu.be/qAXkgVeLiA4

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

18 Nov, 12:29


✍️የኢማን መስታወት፣ የዲን ነፀብራቅ፣ የሐያእ ልብስ፣ የውበት ቀንዲል፣ የዩኒቨርሱ ሚዛን መጠበቂያ፣ ዘመን ተሻጋሪ የሴት ልጅ ውበት ነው። ሰትሮ ይሰትራል። ራስንም ሆነ ሌሎችን ከወንጀል መጠበቂያ ጋሻም ነው። ሴትና ሒጃቧ፣ እንቁና ዘውድ ናቸው፤ አይነጣጠሉም።
-
ሰውነትን በኣደባባይ ተራቁቶ መሔድ ጥንት በጋርዮሽ ዘመን የነበረ ልማድ እንጅ ዘመናችን ያመጣው ነፃነት ወይም ስልጣኔ ኣይደለም። ይልቁንም ሂጃብ ያልሰለጠ'ነውን የጃሒሊያን ስርዓት የሻረ በመሆኑ ዘመን የማያልፍበት የተላቀና የተከበረ የኣለባበስ ስርዓት ነው።
*
ሒጃብ/ኒቃብ ሴት ልጅ ሐፍረተ-ገላዋን የምትሸፍንበት፣ ውበቷን የምትጠብቅበት፣ እምነቷን የምታንጽባርቅበት፤ ከራስ ጸጉር እስከ ታች ጥፍር የሚሸፍን ወፍራምና ሰፋ ያለ፣ የሰውነት ቅርጽ የማያሳይ፣ ዕይታ የማይስብ፣ ፋሽን ያልሆነ፣ ለኢ-አማኒያን ርጋጽኻነት ማሳያ፣ ሰማያዊ እሴትና ትዕዛዝ ያለበት ትልቅ ኣምልኮ ነው።

یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّبِیُّ قُل لِّأَزۡوَ ⁠جِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاۤءِ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ یُدۡنِینَ عَلَیۡهِنَّ مِن جَلَـٰبِیبِهِنَّ ذَ ⁠لِكَ أَدۡنَىٰۤ أَن یُعۡرَفۡنَ فَلَا یُؤۡذَیۡنَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمࣰا۝
አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
📒አል-ኣሕዛብ (59)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//elaftube

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

18 Nov, 12:22


https://youtu.be/e4eWpC8UHrs

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

18 Nov, 12:21


ወዳጅ ልብ እና ውዴታው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍️አቡበክር (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) በረሱላችን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነበር። ውድጅታቸው ድሮ ነበር። ሆደ በሻሻ፣ ዝምተኛ ነበር። ውዴታ ራሱን ሲ'ያህል ይወዳቸዋል። ከጎናቸው አይጠፋም። ጉዳያቸውን ያዋዩታል። ያማክሩታል።
-
የወዳጅነት ትርጉሙ አቡበክር ነቢዩን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሚወዳቸውን አይነት ነው ማለት ይቻላል። ሲወዳቸው ሙሐባ ሙሽራ ስትሆን፤ መሕሯ ነፍስ ናት ያህል ለነፍሱ አይሳሳም ነበር።

ሆኖም ወደ አኼራ ሲሄዱ አጠገባቸው አልነበረም። በመዲና ዳርቻ ላይ በምትገኝ አስ-ሱና በምትባል መንደር ባለቤቱን በመጎብኘት ላይ ሳለ ነበር፤ ወደ አኼራ የመሄዳቸው ዜና የደረሰው። 

ወዲያው ወደ መዲና ተመለሰ። እንደደረሰም በቀጥታ ወደ ነብዩ ክፍል ሄደና ተሸፍነው ተኝተው አያቸው።

የመለ'የት ሕመሙ እንዴት`ስ አድርጎት ይሆን⁉️
የልብ ወዳጅን እንደማጣት ምን ከባድ ነገር አለ⁉️
የድምፅ ፀጥታን እንደመቻል ምን ኃይል አለ⁉️

በዚያች ቀን ለአቡበክርም ሆነ ለሶሐቦች ሞት በቅርበት ሲመጣ የመጀመሪያው ነበር። ዓለም በፍርሃት ነገሰች። መዲና በሃዘን ተናጠች። በዚህ ዑማ ላይ ሐዘን ርብርብ አለ።
*
ተልዕኳቸውን ለማስቀጠል፣ ወዳጅነትን በተግባር ለማሳየት፣ የአላህን ዲን ለመጠበቅ ሲል አቡበክር ተረጋግቶ አረጋጋቸው። በርትቶ አበረታቸው። ጠንክሮ የማጠንከሩ፤ በርትቶ የማበርታቱ ፍጥነት ከአውሎ ንፋስ በኋላ እንዳለው የንፋስ መረጋጋት አይነት ነበር።

ይሁን እንጅ በርሳቸው ሞት ብዙዎች ወደ ክህደት እና ወደ ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብተዋል። አቡበክርም፦ «ሙሐመድን ሲያመልክ የነበረ ሙሐመድ በርግጥም ሞቷል፤ አላህን ሲያመልክ የነበረ ግን አላህ ሕያው ነው አይሞትም።» የሚል ጠንካራ አዋጅ አሰሙ።
من كان يعبد محمداً فإن محمداً قد مات، ومن كان يعبد الله فإن الله حي لا يموت.
በዚህ ንግግራቸው ሶሓቦችን በማረጋጋትና ከታላቅ የሐዘን ስሜት ወደ እምነታቸው እንዲመለሱ አደረጉ።
--
ሐዘን አይረሳም ልብ ውስጥ ይቀበራል እንጂ እንዲሉ፤ የነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሞት ለዚህ ኡማህ ለሶሓባዎችና ለተከታዮቻቸው እጅግ ትልቅ ሐዘን ጥሎ ቀጠለ። በርግጥም ከባድ ናፍቆት፤ ከመሬት ታች ላለ ሰው ነው።
(ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም!)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//elaftube

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

17 Nov, 13:47


https://youtu.be/FGEsX6GZuaI

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

17 Nov, 08:46


https://youtu.be/wXdnvNu73f4

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

16 Nov, 17:25


https://youtu.be/Chd948QEaws

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

16 Nov, 09:10


https://youtu.be/9doKZHo4Dko

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

16 Nov, 00:35


የዱንያን እና የአኺራን ደስታ ሰብስባ የያዘች ዱዓ
اللهم إني اسألك العفو العافية
አላሁመ ኢኒ አስአሉከ አልዓፍወ ወልዓፊያ

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

13 Nov, 09:35


https://youtu.be/PSbh4mxiCbY

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

11 Nov, 09:00


https://youtu.be/e3p4PZIIVHA

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

09 Nov, 13:47


https://youtu.be/p2DQ8AmtuAA

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

09 Nov, 13:06


https://youtu.be/lhPJrACCaao

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

08 Nov, 10:48


https://youtu.be/q84fGO2Rs9E

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

07 Nov, 21:33


https://t.me/elaftube

ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

05 Nov, 19:01


https://youtu.be/e_t76O-l1Fo

10,507

subscribers

101

photos

29

videos