🍀 ጋብቻ የመደጋገፍ ፤ የመተጋገዝ ግዴታን ቤተሰብን በጋራ የማስተዳደር ፤ በጋራ አንድ ላይ የመኖር ግዴታዎችን ያቅፋል ፨
🍀 ጋብቻ ማለት ፦
1.ጋብቻ ማለት መስማማት ማለት ነው፠
# በተጋቢዎች መካከል ስምምነት መኖር አለበት። ከመጋባት በፊት መስማማት ያሻል፨ ሳትግባቡ አትጋቡ ፨
2.የጋብቻ ትርጉሙ አንድ መሆን ነው፨
# ስለዚህ ሰው አባቱን እና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ ማቲ 19:5
# 1+1=1 ባልና ማስት በትዳር ላይ አንድ ነው የሚሆኑት ሁለት አይደለም ፨
3.ትዳር ማለት የራስ ወዳድነት ስሜት መተው ማለት ነው፨
# አንዴ ካገቡ በሓላ " እኔ " ወደ " እኛ " የሚቀየርበት የጋብቻ እውነት ነው፨
4.ጋብቻ ማለት አዲስ ትውልድ መቅረፅ ማለት ነው ፨
# ከትዳር በሓላ ልጆች መውለድ ስለሚከተል ልጆችን በመፅሀፍ ቅዱስ እውነት ቀርፆ መልካም ቤተሰብ የመፍጠር ትልቅ ሀላፊነት አለው፠
5.ጋብቻ ማለት መለወጥ ፤ መማር እና ማደግ ማለት ነው ፠
# ተጋቢዎች ሁል ጊዜ ትዳራቸውን የመነከባከብ የመጠበቅ የጋራ ሀላፊነትን ያዘለ ነው ፠ ለመማር ፤ ለመታረም ለመለወጥ ተነሳሽነት እና ዝግጁነትን ይጠይቃል ፠ ተጋቢዎች የጋራ ቁርጠኛ የማደግ ፍላጎት ሊኖራቸውና ሊያዳብሩ ይገባቸዋል፠
ይቀጥላል ..
https://t.me/httpstme8RjldnZsNIM4YmE02015