ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ከቀናት በፊት ከጀርመን ድምፅ ራዲዮ (DW) ጋር ቆይታ ማድረጉን ጠቆም አድርገናችሁ አልፈን ነበር። ያን ማለታችን ስለአሟሟቱ ያልጠሩ መረጃዎች ስለደረሱን ነው። እንደደረሰን መረጃ ከሆነ አርብ ዕለት ከ5 ቀናት በፊት ከጀርመን ድምፅ ራዲዮ ከጋዜጠኛ ታምራት ዲንሳ ጋር ኢንተርቪው መስጠቱን ተከትሎ ጋዜጠኛው ቁጥሩን ለአገዛዙ ሰዎች ሳይሰጥ እንዳልቀረ የሚጠቁም መረጃ ነው የደረሰኝ። ይሄን መረጃ እንዲህ በቀላሉ ማለፍ አልፈለኩም። ከዚህ በፊት አርበኛ ውባንተ አባተ በተመሳሳይ ኢትዮጵያኒስት ነን ለሚሉ አካላት ኢንተርቪው በሰጠ በአጭር ቀናት ነው ተለይቶ የተመታው። የፋኖ ዩሃንስም ግድያ ከዚህ ጋር የተያያዘ እንደሚሆን ይገመታል። ይሄ ዝም ተብሎ የሚታለፍ ተራ መላምት አይደለም።
#Amhara #Ethiopia
የቲክቶክ ቻናላችን➲ tiktok.com/@amhara_gion