የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC @egbcc Channel on Telegram

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

@egbcc


ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC (Amharic)

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC የቴሌግራም ቻናል ነው። ይህ ባለምንም ክስደት ወንጌላዊ ለማስተማርም እና በወንጌላዊነት በእንግሊዝ ግንባታ ለማዋልና ለምን አነሳስነው ብሄራዊ ችግርን ለመጠቀም ዋጋውን ማስኬትና የሚመልከት መገኛው ቴሌግራም ምንጮቻችንን እንቀበል። ለወንጌል አማኞች ጸጋን በማስቀመጥ ሰኞ እሁድ አሉታዊ ማህበሩን በመመልከት ዋጋውን እና መረጃውን ማራዘም መክፈት ነን። ስለሆነ ለወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ያልዘወትር የቴሌግራም ቻናላችንን ትክክለኛ መረጃለሽ።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

20 Nov, 06:45


https://youtu.be/5wKJ8LfGHOU

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

19 Nov, 14:25


https://youtu.be/I-QyXNcypSE

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

19 Nov, 13:13


#የሮሆቦት_አብያተክርስቲያናት_ህብረት_2ተኛ_መደበኛ_ጠቅላላ_ጉባኤዉን_አካሄደ

በጉዲና ቱምሳ ፋዉንዴሽን አዳራሽ በተካሄደዉ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ እና የኢትዮዽያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት ፓ/ር ፃዲቁ አብዶ እንዲሁም የሌሎች ኀብረት መሪዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

የሮሆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት መጋቢ ካሳሁን እምሩ ለጉባኤዉ የእንኳን ደህና መጣቹ ንግግ ያደረጉ ሲሆን የህብረቱ የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ አየለ ወርቁ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል እንዲሁም ም/ፀሃፊ እና የፅ/ቤቱ ሃላፊ ፓ/ር አዲስ አዳነ ፀሎት በማድረግ ፕሮግራሙን አስጀምረዋል ዘማሪ ፀሀይ ዘለቀ በዝማሬ ስታገለግል የገሊላ ኢንተርናሽናል ባይብል ሰሚነሪ ም/ፕረዚዳንት  ዶ/ር ብርሃኑ ያደታ የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል አገልግለዋል።

በጉባኤዉ የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ከቀድሞ ይልቅ ተያይዘን አብረን መስራት አለብን በማለት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት ፓ/ር ፃዲቁ አብዶ ትኩረታችንን በቃሉ ላይ የተመሰረተ አስተምህሮ አድርገን ወንጌል እንስራ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሮሆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረትን በገንዘብ እና በልዩ ልዩ አስተወፅኦ ለደገፉ ለህብረቱ መስራች እና አስፈፃሚዎች የእዉቅና እና የሰርተፍኬት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

በ2ተኛ መደበኛ ጉባኤ ህብረቱ በተለያየ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ በዋናነት ቀድሞ የነበረዉን መተዳደሪያ ደንብ የበለጠ በስፋት ለመንቀሳቀስ ያመች ዘንድ አሻሽሎ ልዩ ልዩ ዉሳኔዎች አስተላልፏል።

በመጨረሻም ለጉባኤ መሳካት የበኩላቸዉን ላደረጉና ሲያስተባብሩ ለነበሩ የአዲስ አበባ ፅ/ቤት ሰብሳቢ ነብይት ሮዛ አድማሱ እንዲሁም ዋና ፀሃፊ ነብይ ኤልያስ እና ከዋናዉ ፅ/ቤት ፓ/ር አዲስ አዳነን ኅብረቱ አመስግኗቸው የጉባኤ ፍጻሜ ሆኗል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://t.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

18 Nov, 14:28


https://youtu.be/6TS6ZXswSFE

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

18 Nov, 13:43


#የኢትዮዽያ ቲር ፈንድ ቢሮ ቤተክርስቲያን እና የማህበረሰብ ለዉጥ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ቦርድ አቋቋመ። በኢትዮዽያ የቦርዱ ሰብሳቢ የካዉንስሉ ተወካይ የሆኑት ፓስተር አሸብር ከተማ ሆነዉ ተመርጠዋል።

ከህዳር 3 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017ዓ/ም በኬኒያ በተካሄደዉ ስብሰባ የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓ/ር አሸብር ከተማ ጨምሮ አራት ተወካዮች በስብሰባዉ ተካፍለዋል።

በስብሰባዉ ከሯንዳ፣ቡርንዲ፣ከዲሞክራቲክ ሪፐፕሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ከደቡብ ሱዳን እና ኢትዮዽያን ጨምሮ ከስድስት ሀገራት የተወጣጡ ወደ 30 የሚሆኑ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ስብሰባዉ የትኩረት አቅጣጫዉን ያደረገዉ ቤተክርስቲያን ማህበረሰቡን መለወጥ እንደምትችል እና በሰላም፣ተስፋ በማደስ እነዚህን እና በመሳሰሉ ጉዳዮች የለዉጥ ሐዋሪያ ሆና ማገልገል እንደምትችል በዋነኝነት ተወያይተዋል። ከዉይይቱ ባሻገር የስልጠና ጊዜ እና በሌሎች ሀገራት የተሰሩ ስራዎች የግምገማ ጊዜ ተከናዉኗል።

በመጨረሻም በኢስት አፍሪካና በሴንትራል አፍሪካ ሪጅን ምርጫ ተካሂዶ የካዉንስሉ አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓስተር አሸብር ከተማ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዉ ተመርጠዉ ስብሰባዉ ተጠናቋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://t.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

15 Nov, 12:57


https://youtu.be/o6RyZ4hYHic