Nolawi ኖላዊ

@nolawii


ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ!

0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኮንን

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:26


እንኳን ደስ አላችሁ !



እግዚአብሔር ሆይ ተመስገን !

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:26


እንደገመትነው አይደለም

ያኰረፈን ስለ ኮራ፣ ዝም ያለን ጊዜው የእኔ ነው ብሎ አይደለም፤ እኛ ከማናውቀው ከራሱ ችግር ጋር እየታገለ ስላለ ነው። ፊቱ የተጨማደደው ፣ ዝም ብሎን የሄደው እኛን ጠልቶ አይደለም፤ የሕክምና ውጤቱ ደስ የማያሰኝ ስለ ነበረ ነው። እርሱ ስለ ካንሰር ያስባል፣ እኛ ስለ ፈገግታ እናስባለን። ያልመጣው፣ ቀጥሮን መንገድ ላይ ያቆመን የተሻለ ስላገኘ አይደለም። አደጋ ገጥሞት ፣ ራሱን ስቶ ነው። ስልካችንን ያላነሣው ይለምኑኛል ብሎ ሰግቶ አይደለም ፣ በአካል ለማግኘት ፈልጎ ነው።

ያልመጣው ጥሪያችንን ንቆ አይደለም፣ ያሠራልን ያገር ልብስ አልደርስ ብሎት ነው። የእናቱን ሞት ሰምቶ ከምቾት አገር ያልመጣው፣ አልነገረንም እንጂ በወረቀት ምክንያት ስለ ታሰረ ነው። ያላገለገለው ትንሽና ድሀ ስለሆንን ንቆን አይደለም፤ ልጁ ሞታበት ቀብር ላይ ስለ ነበረ ነው። ያልሰጠን ስለ ሰሰተ አይደለም፣ ንብረቱ ሁሉ ታግዶ ችግር ላይ ስለነበረ ነው። ጠይቀነው ዝም ያለን የራሳቸው ጉዳይ ብሎ አይደለም፣ ስለ እኛ ሰዎችን እየለመነ ስለ ነበረ ነው። ልቅሶአችንን ያልደረሰው ውለታ በላ ስለሆነ አልነበረም፣ የስምንት ዘመዶቹን መርዶ ሰምቶ ኀዘን ላይ ስለ ነበረ ነው። እየጠጣ ወደ ቤቱ የሚገባው በጣም ስለ ተመቸው አይደለም፣ መደበቅ የሚፈልገው ውስጣዊ አባራሪ ስለ መጣበት ነው። ሳይነግረን የመጣው ቀጠሮ ማስያዝ እንደሚገባው ረስቶ አይደለም፣ ከሞት ጋር እየታገለ ስለ ነበረ ነው። የጠባይ ለውጥ ያመጣው ምን ያመጣሉ ብሎ በእጁ ስላስገባን አይደለም፣ ከፍተኛ የአእምሮ ጭንቀት ገጥሞት ለመዋል ለማደር ተቸግሮ ነው። ዝምታን ያበዛው አስጠልተነው አይደለም፣ ብነግራቸው ይጎዳሉ ብሎ ነው ። ለመክፈል የዘገየው ብልጥ ሆኖ አይደለም፣ ከሥራ ስለ ተባረረ ነው።

ከሰው የሚሸሸው በደሉኝ ብሎ አይደለም፣ የገጠሙት ክፉዎች ሁሉን እንዳያምን ስላደረጉት ነው። አገር ካገር የሚዞረው ስለ ደላው አይደለም፣ የገዛ ትዳሩና ልጆቹ ጠላት ሆነውበት ነው፡፡ የሚነጫነጨው ሌላ ለምዶ አይደለም፣ ትሞታለህ የሚል ድምፅ ሰምቶ ነው። የሚቆጣው ሥራችን ስላላስደሰተው አይደለም፣ ከራሱ ጋር ያለውን ትግል ማንም ስላልተረዳለት ነ ው። ያመሸው ትዳሩ ላይ እየባለገ ስለ ነበር አይደለም፣ የደረሰበትን አደጋ ቢነግረን ይደነግጣሉ ብሎ ነው።

እንደገመትነው አይደለም። እርሱን ብንሰማውና እውነቱን ብናውቀው ራሳችንን ክፉ ነህ እንለው ነበር። ራስን ብቻ ማዳመጥ ትንሽ ሰው እንደሚያደርግ ይገባን ነበር። እኛን ስለ ልጃችን ጠባይ የሚመክረን እርሱ ልጅ ቀብሮ ነው። በነጻ የሚፈልገን ያለሁላቸው እኔ ብቻ ነኝ ብሎ ስላሰበ ነው ። እንዳላውካቸው ብሎ የሚሸሸን እርሱ የእኛን ችግር ሲካፈል የኖረ ነው። የዛሬውን ሳይሆን የትላንቱን ፣ ተራራ አብረን የገፋንበትን ቀን እናስብ ። ሃያ ዓመት የሳቀልን አንድ ቀን እንዲያኮርፍ እንፍቀድለት ። ዛሬ ደክሞት ነው ፣ መፈለግ የኛ ተራ ነው እንበል። ወዳጅ እንዲሁ አይጣልም። ወዳጅ በገንዘብ አይለወጥም። ደጉን ቀን እያሰቡ ያልፉታል እንጂ በአንዲት ሰባራ ቃል አይሸኙትም። ብቻ እንደገመት ነው አይደለምና እግዚአብሔር ሆይ ይቅር ይበለን !

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም.

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:26


Live stream finished (26 minutes)

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:26


Live stream started

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:25


አትበል /2

ቤቴን ሠርቻለሁ፣ ጡረታዬን አስተካክያለሁ፣ ልጆቼን ቦታ ቦታ አስይዣለሁ ከዚህ በኋላ ዐርፌ መብላት መጠጣት ነው አትበል። ቤትም ጡረታም መተዳደሪያ እንጂ ሕይወት አይሆኑም። ልጆች ቦታ ቢይዙም ይህ ዓለም ለአንድ ራስም አስጨናቂ ነው። ብኖር ለጌታዬ እኖራለሁ በል። ቢሳካ ደስታ ነው፣ ባይሳካ ምኞትህ ዋጋ ወደሚያገኝበት ዓለም ትሄዳለህ። እንኳን አንተ ታላላቅ ነገሥታት ግቢያቸውን ደሴት ላይ ፣ መታጠቢያ ቤታቸውን በወርቅ ሠርተው ነበር። እንኳን መኖሪያ መቀበሪያ አላገኙም። ማን እንዳረፈ ታርፈለህ? ደግሞም ንብረት አያሳርፍም ፣ ሰውም ልብ አይጥሉበትም። ወደ እኔ ኑ ያለው ወደ ልቡ የጋበዘን ክርስቶስ ብቻ ዕረፍት ነው።

እኔን ካልነኩኝ ስለ ማንም ግድ የለኝም ፣ ለእኔ ችግር ማን ደረሰ ? አትበል። ችግር አልቆ አይቆምም፤ ክፉዎችም ክፋትን በቃኝ አይሉም። በሩቅ ያየሃቸው ክፉዎች ወደ አንተም ይመጣሉ። አንድ ውሻ አንድ ነገር አይቶ ሲጮህ ያላዩት መቶ ውሾች እርሱን ሰምተው  ይጮኻሉ ። የሌላው ኀዘን እንዲያሳዝንህ ፣ የሌላው ጩኸት እንዲሰማህ ይሁን። ከውሻ እንኳ አትነሥ ።

ይህን ያደረገው እገሌ ሳይሆን አይቀርም አትበል። ባላየኸው ነገር በንጹሕ ሰው ላይ ዕዳ አታሸክም። እንኳን ግምትህ ዓይንህም ይሳሳታል። ሰውን ያለ ኃጢአቱ እንኳን በአፍህ በልብህም አትኰንነው። የበደል አውራው ንጹሕ ላይ መፍረድ ነው። በርኩሱም እንዳትፈርድ ገደብ ተጥሎብሃል። ደግሞም ግምትህና ፍርድህ ሐሰተኛ ሆኖ ስታገኘው በራስህ ታፍራለህ።

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:23


ሌላ አጽናኝ

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:23


Live stream finished (58 minutes)

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:23


Live stream started

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:23


ዛሬ እሑድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡00 ላይ
በቴሌግራም ቻናላችን የቀጥታ ቃለ እግዚአብሔር ስርጭት ለ50 ደቂቃ ይኖረናል:: ሌሎች ወዳጆቻችሁንም ጋብዙ ::

በክርስቶስ ሰላም!



https://t.me/Nolawii

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:22


Live stream finished (24 minutes)

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:22


Live stream started

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:22


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ነገ እሑድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም.
ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በቴሌ ግራም ቻናላችን የቀጥታ ቃለ እግዚአብሔር ትምህርት ይኖረናል::
የክርስቶስ ሰላም ከእናንተ ጋ ይሁን!



https://t.me/Nolawii

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:21


የማርቆስ ወንጌል ትርጓሜ 38

ማር.11፥ 1-10

#ዲያቆን #አሸናፊ #መኰንን

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:21


Live stream finished (1 hour)

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:21


Live stream started

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:21


Live stream finished (29 seconds)

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:21


Live stream started

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:20


የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ! ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከቀኑ
12: 00 ሰዓት የቀጥታ ትምህርት በቴሌግራም ቻናል በኖላዊ የማርቆስ ወንጌል ትርጓሜ ለ40 ደቂቃ ያህል ይሰጣል። ባላችሁበት እንድትሳተፉ እንጋብዛለን !

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:20


Live stream finished (49 seconds)

Nolawi ኖላዊ

21 Jan, 00:20


Live stream started

6,356

subscribers

733

photos

96

videos