Fresenbet G.Y Adhanom @fresenbett Channel on Telegram

Fresenbet G.Y Adhanom

@fresenbett


Fresenbet G.Y Adhanom (English)

Are you a fan of sports betting and looking for a reliable and exciting platform to place your bets? Look no further than Fresenbet G.Y Adhanom! This Telegram channel is dedicated to providing sports enthusiasts with the latest updates on upcoming matches, expert betting tips, and exclusive promotions. Whether you're a seasoned bettor or just starting out, Fresenbet G.Y Adhanom has something for everyone. With a team of experienced professionals behind the scenes, you can trust that you're getting top-notch advice and analysis to help you make informed decisions. What sets Fresenbet G.Y Adhanom apart is its commitment to transparency and fairness. You can rest assured that all information shared on this channel is accurate and reliable. So why wait? Join Fresenbet G.Y Adhanom today and take your sports betting experience to the next level!

Fresenbet G.Y Adhanom

08 Feb, 13:16


"ለደካሞች ኃይልን ይሰጣል፥ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴናዎች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጎበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።" (ኢሳ 40:29-31)

የሥዕል ሥራው ባለቤት - BI NI

Fresenbet G.Y Adhanom

27 Jan, 16:36


+ እምነትን በእውቀት +

በዚህች ምድር ላይ ከእምነታችን የበለጠ ዋጋ ያለው ነገር የለንም። ገንዘብ ያለ እምነት፥ እውቀት ያለ እምነት፥ ዝና ያለ እምነት ሁሉም ጤዛ ናቸው። በእውነት ማጌጥ የፈለገ፥ በእውነት መዋብ የፈለገ፥ በእውነት መክበር የፈለገ እምነቱን ጠንቅቆ ያውቃታል፥ አውቋትም በሕይወቱ ይገልጠጣታል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እምነትን ሲገልጣት "እምነት ግን መሠረት ናት" የሚለው ለዚህ ነው። መሠረት ጽኑ ከኾነ፥ በላዩ የሚገነባውም ጽኑ ይኾናል።

ማኅበረ ቅዱሳን መሠረታዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ትምህርትን በኦንላይን (ኢ-ለርኒንግ) እና በርቀት መርሐ ግብር በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋ መስጠት ጀምሯል። እንግዲህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እምነታችንን ለመማር ያለው መሰናክል እየቀለለ መጥቷል። እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እድሉን መጠቀም ይመከራል።

Fresenbet G.Y Adhanom

26 Jan, 05:55


+ ዝምታ እና እምነትን መኖር +

አንድ በአይሁድ መምህራን የተከተበ ድንቅ መጽሐፍ አለ። ፒርቄይ አቮት (פִּרְקֵי אָבוֹת) ይሰኛል። በተለያዩ ጊዜያት የኖሩ የአይሁድ ሊቃውንት በግብረገባዊ ጉዳዮች ላይ የተናገሯቸውን አጫጭር ብሂሎች ሰብስቦ የያዘ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ከጫፍ እስከጫፍ ሳይሰለች የሚነበብ አይነት ነው። በውስጡ እጅግ ብዙ ሊጠቀሱ የሚገባቸው ትምህርቶች ቢኖሩም፥ ለዛሬ ጊዜውን ይዋጃል ብዬ ያሰብኩትን አንዱን ለቅምሻ ያህል ላጋራ።

ከዚህ በታች ያለውን የተናገሩት ሊቅ የአይሁድ ምሁር የሆነው የገማልያል ልጅ ናቸው። ስምዖን ወልደ ገማልያል ይባላሉ። ሊቅነቱ እንደ አባታቸው እንደሆነ ይነገራል። ዮሲፎን "የአይሁዶች ጦርነት" በተሰኘው ሥራው ላይም ስማቸውን ያነሳል። እኚህ ሊቅ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ስለመናገራቸው በፒርቄይ አቮት ሰፍሮ ይገኛል፦

שִׁמְעוֹן בְּנוֹ אוֹמֵר, כָּל יָמַי גָּדַלְתִּי בֵין הַחֲכָמִים, וְלֹא מָצָאתִי לַגּוּף טוֹב אֶלָּא שְׁתִיקָה. וְלֹא הַמִּדְרָשׁ הוּא הָעִקָּר, אֶלָּא הַמַּעֲשֶׂה. וְכָל הַמַּרְבֶּה דְבָרִים, מֵבִיא חֵטְא:

"ሕይወቴን ሙሉ በጠቢባን መካከል አድጌያለሁ፥ ለሰው ልጅ ግን ከዝምታ የተሻለ አንዳች ነገር አለመኖሩን፥ ከመማር ይልቅ ማድረግ [በድርጊት መግለጥ] የተሻለ መሆኑን እና ንግግርን የሚያበዛ ኃጢያትንም እንደሚያበዛ ተረድቻለሁ።"

ይህ ብሂል ከመጽሐፉ ውስጥ ከሰፈሩት ምናልባትም እጅግ አብልጬ ከወደድኳቸው እና ዘወትር ከማስታውሳቸው መካከል ቀዳሚው ነው። ምክሩ ዘመናችንን ያማከለ ጥበብን በውስጡ ያዘለ መኾኑ እሙን ነው። ይህም ስለ ዝምታ እና እምነትን ስለመኖር ነው።

በተለምዶ ዝምታ ወርቅ ነው ይባላል። በግሌ ከወርቅም በላይ መሆኑን አምናለሁ። ዝምታ ከብዙ ስህተት የሚጠብቅ ቁልፍ ነው። አንደበትን ሲከፍቱ አእምሮ ይታያል የሚባለውን ያገናዘበ በሚመስል መልኩ፥ ጠቢቡ ሰለሞን ዝምታ የሰነፍን ውርድት ሳይቀር እንደምታርቅ ሲነግረን “ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቈጠራል፥ ከንፈሩንም የሚቈልፍ፦ ባለ አእምሮ ነው ይባላል።” (ምሳ 17፥28) ይለናል። መልካም ነገርን የሚናገረው ንጉሥ ዳዊት ስንኳ አንደበቱን ስለመጠበቅ ሲናገር “አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።” (መዝሙር 141፥3) ሲል እንሰማዋለን። በኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትም፥ የቅድስናን መንገድ ፈጥኖ ለመውጣት የሚረዳ መንገድ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል።

በአሁኑ ዘመን፥ ሰዎች ስለማያውቁት ነገር ብዙ ይናገራሉ። በተለይ ደግሞ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሁሉም ሰው ስለሁሉም ነገር ሲናገር፥ በሁሉም ነገር ላይ አሳቡን ሲሰጥ፥ በሚያውቀውም በማያውቀውም ጉዳይ ላይ ሲተነትን ይታያል። ይህ እጅግ አደገኛ ነው። በሁሉም ላይ ደርሶ ተንታኝ መሆኑን ለስህተትም መጋለጥ፥ ራስንም ማልፋት፥ ትዝብት ላይም መውደቅ ነው። በዝምታ ውስጥ ጥበብን እናገኝ። መቼ መናገር እንዳለብን እንወቅ። መናገር ስለምችል ብቻ አንናገር፥ መመለስ ስለምንችል ብቻ መመለስ ይቅርብን። በዝምታ እያሰላሰልን ጥበብን መፈለግ እንልመድ።

ሌላኛው ነጥብ እምነትን ስለመኖር የተጠቀሰው ነው። መምህሩ ከእውቀት ይልቅ ያወቁትን መኖር እንደሚበልጥ ይናገራሉ። ይህ እውነት ነው። እምነታችንን ካልኖርነው ትርጉም አልባ ይሆናል። ወንጌሉም ሆነ የቀደምት አባቶቻችን ትምህርት አስረግጦ የሚያስረዳን ይህንን እውነት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” (ማቴዎስ 5፥16) በማለት ክርስትናን በተግባር የመኖርን አስፈላጊነት ሲነግረን፥ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ "ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥ ከእናንተ አንዱም፦ በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል? እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።" (ያዕቆብ 2:15-17) በማለት ይነግረናል።

በአሁኑ ጊዜ ብርሃናችን በሰው ፊት ማብራት አልቻለም። እምነታችንን ልንኖረው አልተቻለንም። ይህ ክርስትናችንን ፉርሽ ያደርገዋል። መማሩን እንማር፥ ነገር ግን እንተግብረው። ሮማዊያን ይሉ እንደነበረው "Non scholæ sed vitæ discimus" (የምንማረው ለአስኳላ ሳይሆን ለሕይወት ነው) የሚለው ቃል መርሕ ይሁነን።

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://www.facebook.com/fre.asalib

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1

Fresenbet G.Y Adhanom

23 Jan, 16:48


+ ሊኖሩበት የሚገባ መርህ +

በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ከብጽዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ንግግር የተሻለ መርህ ለማግኘት ከባድ ነው። ይህንን መርህ ሁላችንም ብንከተል እግዚአብሔር የሰጠንን መክሊት ተጠቅመን ያለምንበት መድረስ እንችላለን። የአባት ምክር እነሆ:-
.
.
.
"እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል፤ ያንን መሥራት የእሱ ፈንታ ነው፡፡ ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያቢሎስ ሥራ ነው፡፡ በእርግጥ ሥራው እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል፡፡ ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፡፡ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል፡፡የሐሜት ጐርፍ ያስወርድብሃል፡፡

ደራስያን እንዲጠይቁህ፥ እጅግ ስመ ጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ጲላጦስ፣ ሄሮድስ፣
ሐናንያ፣ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ፡፡ ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሠላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል፡፡ ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዘብ አትችልምን?

አንተ ግን ሥራህን ሥራ!

አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፣ የሰይጣንን ውሻዎች ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎቹንም በማባረር ጊዜህን አታጥፋ፡፡ ሥራህን ሥራ! ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኀበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ፣ አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈጸም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ፡፡

ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልነገረህም፣ ሰይጣንና አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅክም፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሰራ አትችልም። ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለእግዚአብሔር አልሠራህም፡፡

ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን ፤ ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ፣ ይጨቃጨቅ፣ ጥቃት ይደርስብህ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፣ ትቆስልና፣ ትናቅ ይሆናል፡፡ ኃይለኛ ያጐሳቁልህ፣ ወዳጆች ይተውህ፣ ሰዎችም ይንቁህ ይሆናል፡፡

አንተ ግን በጸና ውሳኔ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ጸንተህ፣ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጸምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል!"

ብጽዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

Fresenbet G.Y Adhanom

21 Jan, 13:10


+• ጊዜው ገና ነው •+

አንድ ምንጩ የማይታወቅ አስተማሪ የሆነ አፈ-ታሪክ አለ። በዚህ አፈ-ታሪክ መሠረት፥ ከእለታት በአንዱ ቀን አጋንንት ስብሰባ አደረጉ ይባላል። ይህንን ስብሰባ የጠራው የአጋንንቱ አለቃም “ዓለምን ሁሉ ከእኔ ጋር ለማሰለፍ እፈልጋለሁ። ምን ይደረግ? ማንንስ ልላክ?” ብሎ ጠየቀ። ከሥሩ ያሉትም አንድ በአንድ እየተነሱ አሳቦችን ማቅረብ ጀመሩ። 

አንዱ ተነሳና፥ “እኔን ብትልከኝ፥ ፈጣሪ የለም ብዬ ሰዎችን ማሳመን እችላለሁ!” ብሎ ተናገረ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱ አይሠራም። ብዙዎቹ አያምኑህም። ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ። 

ሌላኛው ተነሳና፥ “እኔን ከላክኸኝ፥ ገነትም ሆነ ሲኦል የሚባል ቦታ እንደሌለ አሳምናቸዋለሁ!” አለ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱም አይሠራም። ብዙዎቹ ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ። 

ሌላው ደግሞ ተነሳና፥ “እኔን ላከኝ። ፈጣሪም አለ፥ ገነትም አለ፥ ሲኦልም አለ፤ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ ለማሰብ ጊዜው አሁን አይደለም ብዬ አሳምናቸዋለሁ።” አለ። የአጋንንቱ አለቃም ደስ እያለው “ይህ ጥሩ መንገድ ነው!” በማለት አሳቡን ተቀበለና ላከው ይባላል።

ሰይጣን ማዘግየት ጥሩ ስልት መሆኑን ስለሚያውቅ፥ ለማዘግየት ይፋጠናል። በሐዲስ ኪዳን ላይ ቅዱስ ጳውሎስ "ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፥ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።” (1 ተሰ 2:18) ሲል እናገኘዋለን። ሰይጣን ላያስቀረን ይችላል፥ ግን ቢያንስ ሊያዘገየን ብዙ ይሞክራል።

እርሱ ዓለማዊ ጓዞቻችንን ለአፍታ ስንኳ አውርደን ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት እንድናስብ አይፈልግም። ስለ ጸሎት ብታስብ፥ "አሁን ደክሞሃል። ጊዜው አይደለም። ሌላ ጊዜ ትጸልያለህ" ይልሃል። ለመጾም ብትዘጋጅ "አሁን ጉልበት ስለሚያስፈልግህ ብላ። የምትጾምበት ጊዜ አይደለም፤ ሌላ ጊዜ ትጾማለህ።" ይልሃል። ለመስገድ ብትዘጋጅ "ኧረ ተረጋጋ፤ ጊዜው አይደለም፥ ጾም ሲገባ ትሰግዳለህ" ይልሃል። ንስሃ ልትገባ ብትዘጋጅ "ቆይ እንጂ፥ ዘልለህ ጨርሰህ አንዴ ብትታጠበው አይሻልም?" ለማለት የሚቀድመው የለም። ቅዱስ ቁርባን ልቀበል ነው ካልክ "አንተኮ ገና ነህ፥ ለወደፊት ጣጣህን ስትጨርስ ቀስ ብለህ አመቻችተህ ትቆርባለህ" ብሎ ያዘናጋሃል።

በዚህ ሁሉ መዘግየት ውስጥ መልአከ ሞት መቼ እንደሚመጣ ማን ያውቃል? ለመንፈሳዊ ነገር ስንነሳ፥ ሰይጣን "ጊዜው ገና ነው" ማለቱ አይቀርም። እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል“ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።” (2ኛ ቆሮ 6፥2) እንደሚል እናስታውስ። ለመዳናችን ቀጥሮ አንስጥ።

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://www.facebook.com/fre.asalib

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1

Fresenbet G.Y Adhanom

13 Jan, 08:34


+• አሥራት ለምን ታወጣለህ? •+

አባ ታድሮስ ማላቲ “Stories for the Youth” በሚል ርዕስ ለወጣቶች ባዘጋጁት መጽሐፍ ላይ፥ ስለ አሥራት ጥቅም አንድ አጭር ታሪክ ጸፈዋል፤ እንደሚከተለው ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ።
--
ከሃያ ዓመት ቆይታ በኋላ፥ በካሊፎርኒያ ከተማ አንድ የመንፈስ ልጄን አገኘሁት እና ወደ ቤቱ ወሰደኝ። ቤቱ እጅግ ግዙፍ እና ውብ ነበር። አብረን ተቀምጠን ሳለም፥ “አባ፥ የዛኔ በካሊፎርኒያ መኖር ስጀምር ትዝ ይልዎታል? ኑሮን ለማሸነፍ ትግል ላይ ነበርኩ፥ አሁን ግን እግዚአብሔር ከጠየቅሁትም በላይ ሰጥቶኛል።” አለኝ።

እኔም “ይህ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው። በእውነቱ አምላካችን ያስብልናልና እናመሰግነዋለን።” አልኩት።

እርሱም ቀጠለና፥ “እግዚአብሔር ምን ያህል ቸርነት እንዳደረገልኝ ያውቃሉ? ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ጀምሮ ‘እዚህ በምድር ላይ ስኬታማ ብሆን፥ መንግሥተ ሰማያትን ግን ካጣሁ ምን እጠቀማለሁ?’ እያልኩ መብሰልሰል ጀመርኩ። ከዚያ አንድ ቀን፥ በአምላኬ ፊት ተንበርክኬ፥ ሁኔታዬ ምንም ያህል ቢከፋ፥ ከማገኘው ገቢ ላይ አሥራቴን ላለመንካት ቃል ገባሁለት። አሥራት የእግዚአብሔር ነዋ! ቀጠልኩና ‘ጌታዬ ሆይ፥ ሁሉም ያንተ ስጦታ ነውና፥ ከዘጠኝ እጁ ላይ ደግሞ በእዚህ በአሜሪካም ሆነ በግብጽ ላሉ ነዳያን እመጸውታለሁ።’ አልኩት።

“ከዚያም በልግስና መስጠት ጀመርኩ፤ የገነት በሮችም ተከፈቱልኝ! በእውነቱ እግዚአብሔር ከሚያስፈልገኝ በላይ ሰጠኝ። አንዳንዴ፥ ተንበርክኬ እያለቀስኩ፥ ‘እባክህ በቃህ አምላኬ! ከዚህ በላይ ከሰጠኸኝ የሃብት ብዛት ነፍሴን እንዳያጠፋት እፈራለሁ’ ብዬ እለምነው ነበር። እርሱ ግን እንዲህ እያልኩም የበለጠ ይሰጠኝ ነበር።”

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://www.facebook.com/fre.asalib

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1

Fresenbet G.Y Adhanom

12 Jan, 07:45


+• የሐዋርያው የመጨረሻ አደራ •+

በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የሚነገር አንድ ትውፊት አለ:: ይህንን ትውፊት ቅዱስ ሄሬኔዎስ በሥራዎች ውስጥ አካትቶት እናገኛለን :: በትውፊቱ መሠረት የተወደደው ሐዋርያ ሊለያቸው መሆኑን የተገነዘቡት ደቀ-መዛሙርቱ ተሰብስበው "ለእኛ ምን መልእክት ተተውልናለህ?" ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ልጆቼ ሆይ፥ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ" አላቸው:: ይህንንም እጅግ ብዙ ጊዜ ደጋገመው:: ደቀ-መዛሙርቱም "ከዚህ ሌላስ የምትለን አለ?" ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ይህ ይበቃችኋል፤ የጌታ ትእዛዝ ይህ ነውና" ብሎ መለሰላቸው::

የክርስትና መነሻው፥ ማዕከሉም ሆነ መጨረሻው ፍቅር ነው:: ከክርስትና ውጪ "አምላክ ፍቅር ስቦት ኃጢአተኛ የሆነውን ሰውን ለማዳን እርሱ ራሱ ሰው ሆነ" የሚል ሃይማኖት የለም:: ክርስትና በአንድ ቃል ይገለጽ ቢባል "ፍቅር" የሚለው ቃል ይገልጸዋል:: የእውነተኛ ክርስቲያኖች መገለጫ ምንድር ነው ቢባል "ፍቅር" ተብሎ ሊጠቀለል ይችላል:: ጌታችንም ይህንን ሲያስረዳ "እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።" (ዮሐ 13:35) ብሎን ነበር:: ሰዎች ዛሬ ላይ አይተውን የክርስቶስ ደቀ-መዛሙርት ስለመሆናችን ቢጠረጥሩን አትደነቁ - እንደኛ ፍቅር ያጣ የለምና!

አንዳንዴ እድሜ ልካችንን ክርስቲያን መሆናችንን እያወጅን እግዚአብሔርን ግን ላናውቅ እንችላለን:: 'ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?' ልትሉኝ ትችላላችሁ:: ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ የዚህን መልስ ሲሰጠን:- "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።" (1 ዮሐ 4:8) ይለናል:: ክርስቲያን መሆናችንን ለዓለም ሁሉ ልናውጅ እንችላለን፤ ፍቅር ከሌለን ግን አዋጁ ሁሉ ከንቱ ነው:: ይህ ምን እንደሚያሳጣን ልብ በሉ:: ሐዋርያው "ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።" (2 ዮሐ 1:9) ይለናል:: እንግዲህ የክርስቶስ ትእዛዝ ፍቅር ከሆነ፤ እኛ ደግሞ ፍቅር ካጣን፤ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል ብለን እየፎከርን ክርስቶስን አጣነው ማለት አይደለም? ክርስቶስን ካጣን ደግሞ አብም ሆነ መንፈስ ቅዱስ አጣን ማለት አይደለም?

ለክርስቲያን ከዚህ በላይ ኪሳራ ምን ይኖር ይሆን?

እንኳን ለወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://www.facebook.com/fre.asalib

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1

Fresenbet G.Y Adhanom

11 Jan, 09:17


+ የማዋረድ ሩጫ +

የእንግሊዙ መሪ የነበሩት ዊንስተን ቸርችል እጅግ አንደበተ ርቱዕ፥ ሲናገሩ የሚያፈዙ፥ ጨዋታም ጭምር አዋቂ ናቸው ይባልላቸዋል። እርሳቸው ንግግር ሊያደርጉ ነው የተባለ እንደሆነ፥ ሰው ሁሉ ካለበት መጥቶ ተሰብስቦ ያዳምጣቸው ነበር። በአንድ ወቅት አንድ ጋዜጠኛ ሲጠይቃቸው፥ “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር፥ እርስዎ ንግግር ሲያደርጉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ የሚያዳምጥዎት መሪ ነዎት። ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስቦ ሲያዳምጥዎት ምን ይሰማዎት ይኾን?” ብሎ ጠየቃቸው። እርሳቸው ግን የሰውን ስነልቡና በደንብ ጠንቅቀው የተረዱ ብልህ ስለነበሩ፤ “ተፈርዶበታል ይሰቀል ቢባል ከዚህ በላይ ሕዝብ አይሰበሰብም ብለህ ነው?” ብለው መለሱለት ይባላል።

ታላቁ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ወልደሕይወት ሲመክር እንደ ንብ ሁኑ ይላል። ንብ መልካም መልክ እና መዓዛ ካላቸው አበቦች ስትደክም ውላ ማር ትሠራለች። እርሷ የሠራችው ማር፥ ከራሷ አልፎ ሌላውን ይመግባል። የራሷን እድሜ ተሻግሮ ከአንድ ሺህ ዓመት በላይም ሳይበላሽ ይቆያል። በዚህ ‘ዘመናዊ’ በተባለው ዘመን ግን የሰው ልጅ ከንብ ይልቅ የዝንብን ጠባይ እየተዋረሰ መሄዱን ማሰብ ያሳዝናል። ይህንን ለማወቅ ወደ ዩቲዩብ ጎራ ብሎ በብዙ መቶ ሺህ እይታዎች ያላቸውን ቪዲዮዎች ርእስ ማንበብ በቂ ነው። ከሚጠቅመን ምክር ይልቅ የሚጎዳንን አሉባልታ፥ ከሚያንጸን ትምህርት ይልክ የሚያውከንን ዜና ለመስማት እንከጅላለን። የተወደዱት ሲጠሉ፥ የተከበሩት ሲዋረዱ፥ የተመረቁት ሲረገሙ ለማየት ያለን ጉጉት ያስፈራል። የሰው ልጅ በታሪኩ ውስጥ የተከበሩትን ለማዋረድ የሮጠበት ጊዜ ብዙ ነው። ሰው አንዳንዴ ለጌታም አይመለስም። “ሆሳዕና” ያለ ሕዝብ መልሶ “ይሰቀል” ለማለት ብዙ ጊዜ እንዳልፈጀበት ማስታወስ መልካም ነው።

አንድ መምህር ወረቀት ላይ ነጥብ አስቀምጦ “ምን ይታያችኋል?” ብሎ ተማሪዎቹን ሲጠይቅ፤ እነርሱም “ጥቁር ነጥብ” ብለው መለሱለት። ሰፊ ቦታ የያዘው ነጩ ወረቀት ሆኖ ሳለ፥ ተማሪዎቹ ግን ያዩት ጥቁሩን ነጥብ ነው። ከብዙው መልካም ትንሿን ሕጸጽ አጉልቶ ማየት የሚያስገርም ነው። እኛም ብዙ ሰዎች ከመልካም ጎናቸው ሰዋዊ ድካማቸው ጎልቶ ይታየናል። የብዙ ዓመት ድካማቸውን በአንድ ቀን የተዛነፈ ሚዛን አሽቀንጥረን እንጥላለን። በመረቅናቸው አፍም መልሰን ስንረግማቸውም ለነገ አንልም። ዛሬ የመረቀ አንደበት፥ ነገ ተሳዳቢ ሆኖ ሲገኝ ያሳፍራል። ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ “ከአንድ አፍ በረከት እና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።” (ያዕ 3፡10) ብሎ ይመክረናል። እኛም እንዲህ ብለን እንለምናለን - ጌታ ሆይ፥ ዛሬ መርቀውን ነገ ከሚሰድቡን፥ ዛሬ አልብሰውን ነገ ከሚገፍፉን፥ ዛሬ አቅፈውን ነገ ከሚነክሱን ጠብቀን!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
----------
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/fre.asalib
ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett
ሊንክድኢን፡ https://www.linkedin.com/in/fresenbet-g-y-adhanom/
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/fresenbet_et/

Fresenbet G.Y Adhanom

09 Jan, 10:44


+ የተስፋ ጉንጉን +

በአንድ ዘመን ላይ የተሻሉ የሚባሉት ሰዎች ካማረሩ ችግር በርትቷል ማለት ነው። አዋቂው ስለ እውቀት መጥፋት ከተናገረ፥ አማኙ ስለ እምነት መድከም ካዘነ፥ ሀብታሙ ስለ ኑሮ ውድነት ካነሳ የዘመኑን መክፋት ልክ ያሳያል። ከጌታ ልደት የቀደመውን ዘመን ስንመረምረው፥ እጅግ የከፋ የጨለማ ዘመን እንደነበር የምንገነዘበው “የነቢያት አክሊል” የሚባለው ነቢዩ ኢሳይያስ ስንኳ “ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።” (ኢሳ 64፡6) እያለ ሲያዝን ስናገኘው ነው። ከፈጣሪው ጋር ቃል በቃል የሚነጋገር ነቢይ እንዲህ ካለ፥ ‘ለምዕመኑማ ምን ያህል በርትቶበት ይኾን?’ ያሰኛል።

የሀገራችን ሰው ሲተርት ‘ሲያልቅ አያምር’ ይላል። እውነትም ዘመኑ እያለቀ ነው መሠል፤ ነገሮች ሁሉ እየተበላሹ ነው። ዓለማችን እንደ ሃያኛው እና ሃያ አንደኛው ክፍለዘመን ስለ ሰላም የጮኸችበት ጊዜ የለም። በዚያው ልክ እንደ እነዚህ ዘመናትም ሰላምን ያጣችበትም ጊዜ የለም። የብዙ ሰው ሕይወት መከራ ተዘርቶ መከራ የሚታጨድበት አውድማ ሆኗል። ጦርነት ባይኖር ስንኳ፤ በልቶ መጥገብ፥ ጠጥቶ መርካት፥ ተኝቶ ማረፍ ያልተቻለበት ሕይወት የቁም ስቃይ መሆኑ አይቀርም። አንዱ የዚህ ማሳያ በተለያየ ምክንያት ራሱን የሚያጠፋው ሰው መበራከት ነው። ‘እገሌኮ ራሱን አጠፋ’ ሲባል፥ አንዳንድ ሰው ‘በራሱ ላይ እንዴት እንዲህ ጨከነ?’ ብሎ ይገረማል። ሰው ሁሉ ነገር ሐዲድ ሲስተበት ራሱን ባያጠፋ ስንኳ ሞቱን ይመኛል። ዘመን ሲከፋ፥ ጊዜ ሲጠም፥ አቅም ሲከዳ፥ የእግዚአብሔር ነቢይ ስንኳ “አቤቱ፥ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና፥ ነፍሴን ውሰድ” (1 ነገ 19፡4) ብሎ ሞትን በፈቃዱ ይጠራል።

እንዲህ ያለን ዘመን ያለ ተስፋ መሻገር አይቻለም። ተስፋ ከመጀመሪያው ዘመን ጀምሮ የሰው ልጅ ስንቅ ሆኖ እስከዛሬ አለ። አዳምና ሔዋን እግዚአብሔርን ከመሠለ አባታቸው እና ገነትን ከመሠለ ቤታቸው ሲለዩ፥ እግዚአብሔር “ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔዴን ገነት አስቀመጠ” (ዘፍ 3፡24) ተብሎ ተጽፏል። ሊቃውንት ይኽንን ሲተረጉሙት እግዚአብሔር በመላእክት ያስጠበቀበት አንዱ ምክንያት አዳም "እግዚአብሔር ፈጽሞ ቢጣላኝ ኖሮ ገነትን ለሌላ ይሰጥብኝ ነበር እንጂ በመላእክት አያስጠብቀውም ነበር ብሎ ተስፋ እንዳይቆርጥ ነው" ይላሉ። ተስፋ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ታላላቅ ስጦታዎች መካከል አንዱ ነው። ዙሪያ ገባችን ሲጨልም ብርሃን እንዳለ የሚያስታውሰን ተስፋ ነው። ሐዘን ሲበረታበን እንደሚያልፍ ሹክ የሚለን ተስፋ ነው። ሰው በብዙ ነገር ‘ክፉ ነው’ ሊባል ይችላል፤ ተስፋን ከሌላው እንደሚነጥቅ ያለ ክፉ ግን በየትም የለም።

ቅዱስ ጳውሎስ “እምነት፥ ተስፋ፥ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ” (1 ቆሮ 13፡13) በማለት ሦስት ጸንተው ከሚኖሩ ነገሮች መካከል ተስፋን ያካትተዋል። ተስፋን ለየት የሚያደርገው ግን ከእምነትም፥ ከፍቅርም ጋር ተገምዶ የሚገኝ በመሆኑ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እምነትን በራሱ “ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ” (ዕብ 11፡1) መሆኑን በመናገር ተስፋን ከእምነት ይገምደዋል። በሌላ መልእክቱ ደግሞ “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ፥ ተስፋ አያሳፍርም።” (ሮሜ 5፡5) ብሎ ፍቅርን ከተስፋ ይገምደዋል። ጠቢቡ “በሦስት የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም” (መክ 4፡12) እንዳለ፤ እምነትን ከተስፋ፥ ተስፋን ደግሞ ከፍቅር ጎንጉኖ የሚኖር አማኝም ክፉ ዘመንን የሚሻገርበትን ብልሃት ይዟል ማለት ነው። ሦስቱም ደግሞ በእግዚአብሔር ላይ ሲሆን ይጸናል። እምነትህን በእግዚአብሔር ላይ ከሆነ፤ ክፉውን ጊዜ ታልፈዋለህ። ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ ካደረግህ፥ በወደቁት መካከል ትቆማለህ። ፍቅርህ ለእግዚአብሔር ከሆነልህ፤ የጽድቅን ብርሃን ትለብሳለህ።

ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ፥ በዚህ ዘመን፤ የሰው ልጅ በስልጣኑ፥ በሀብቱ፥ በትምህርቱ ይቅርና በቆመበት መሬት ላይ ስንኳ ተስፋ ማድረግ እንደማይችል እያየ ነው። በድንግዝግዙ ውስጥ የምናይበት የማይጠፋ ብርሃናችን፥ በመናወጹ ውስጥ የምንቆምበት የማይናወጽ ዐለታችን አንተ ብቻ ነህ። ለአዳም በሐዘን፥ ለኖኅ በቃልኪዳን፥ ለአብርሃም በስደት፥ ለሙሴ በበረሃ፥ ለዮሴፍ በእስር ቤት፥ ለሩት በሰው ሀገር የሰጠኸውን ተስፋ ለእኛም በያለንበት አትንሳን።

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/fre.asalib
ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett
ሊንክድኢን፡ https://www.linkedin.com/in/fresenbet-g-y-adhanom/
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/fresenbet_et/

Fresenbet G.Y Adhanom

07 Jan, 05:47


+• ምላሽዎ ምንድር ነው? •+

የጌታን መወለድ ሰምቶ የተግባር ምላሽ አለመስጠት ከባድ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የጌታን መወለድ የሰሙ ሰዎች ሁሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ይህ ምላሽ ግን በጎም ሆነ ክፉ ሊሆን ይችላል። ንጉሥ ሄሮድስ ስለ አይሁድ ንጉሥ በሰማ ጊዜ፥ በቅናት አብዶ በሕጻናት ላይ ሰይፉን አነሳ። ሰብዓ ሰገል የንጉሡን መወለድ ባወቁ ጊዜ ግን፥ ሀገር አቆራርጠው ለንጉሡ ሊሰግዱ ሄዱ።

ለንጉሡ መወለድ የእኛስ ምላሽ ምን ይሆን? ይህ ዜና ለጆሯችን የምስራች ነው ወይስ መርዶ? የምስራች ከሆነ፤ ስጦታን ይዘን መሄድ ይገባል። እንኳን ለንጉሥ ልደት ይቅርና፥ የትኛውም ሕጻን ሲወለድ ስጦታን ይዞ መሄድ ነባር ዓለምአቀፍ ባህል ነው። ባዶ እጅ መሄድም ነውር ነው።

የተወለደው ንጉሥ ከእኛ ወርቅ፥ እጣን እና ከርቤን አይጠብቅም። እርሱ ከእኛ የሚፈልገው እኛነታችንን ነው። ሐዋርያው "ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ" (ሮሜ 12፥1) ያለውን ብንሰማ፥ ሰውነታችንንም በንስሃ ንጹህ አድርገን በቅዱስ ቁርባን ጌታን ወደ ሕይወታችን ብንቀበል፥ በንጉሡ ዓይን ሞገስን እናገኛለን።

እርስዎም የጌታን መወለድ ሰምተዋል። ታዲያ ለዚህ በጎ ዜና ምላሽዎ ምን ይሆን?

እንኳን ለጌታችን ልደት በሰላም አደረሰን!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://www.facebook.com/fre.asalib

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1

Fresenbet G.Y Adhanom

06 Jan, 09:42


+ ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ +

ልደቱን በባለ ልደቱ ቤት ለማክበር በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከ 8:00 ጀምሮ እንገናኝ!

በቤተክርስቲያኑ ስንገኝ አሥር ጧፎች ይዘን እንምጣ። ሦስቱ በዝማሬው ጊዜ የምናበራቸው ሲሆኑ፥ የተቀሩት ሰባቱ ደግሞ በገጠር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት የሚላኩ ናቸው።

የቻለ ሁሉ ደግሞ ከዝማሬው በኋላ በቤተክርስቲያኒቷ በማደር ድንቅ የሆነውን ማኅሌት ይሳተፍ፤ ቅዳሴውንም ያስቀድስ።

#ኑ_በብርሃኑ_ተመላለሱ!
#የአእላፋት_ዝማሬ

Fresenbet G.Y Adhanom

05 Jan, 17:36


+ አንዷን የእንባ ዘለላ ይቀበል ይኾን? +

አባ አንቶኒ ኮኒያሪስ የተሰኙ የግሪክ ኦርቶዶክስ ካህን በጻፉት "ፊሎካሊያ: የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት ቅዱስ መጽሐፍ" (Philokalia: The Bible of Orthodox Spirituality) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ለማስተማሪያነት ያሰፈሩት እንዲህ የሚል አንድ ጥንታዊ አፈታሪክ አለ:-

እግዚአብሔር ከዕለታት በአንዱ ቀን ቅዱሳን መላእክቱን "ወደ ምድር ወርዳችሁ ከሁሉ ይልቅ እጅግ ብርቅዬ የሆነውን ነገር ይዛችሁልኝ ኑ" ብሎ ያዛቸዋል::

አንድ መልአክ ሌላ ሰው ለማዳን ብሎ ራሱን መስዋእት ያድረገን ሰው የደም ጠብታን ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በእርግጥ ይህ በእኔ ዓይን እጅግ የተወደደ ነው:: በዓለም ያለው እጅግ ብርቅዬ ነገር ግን አይደለም::" አለው::

ሌላኛው መልአክ ደግሞ ሌሎችን ስታስታምም በያዛት በሽታ ምክንያት ያረፈችን የአንዲት ነርስ የመጨረሻ እስትንፋስ ይዞ መጣ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በእርግጥ ስለሌሎች የሚከፈል መስዋእትነት በእኔ ዓይን እጅግ ታላቅ ዋጋ አለው:: ሆኖም ግን በዓለም ያለው እጅግ ብርቅዬው ነገር ይህ አይደለም" አለው::

በመጨረሻም አንድ መልአክ ንስሃ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰን ኃጢአተኛ አንድ ዘለላ እንባ ይዞ መጣ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በዓለም ላይ ያለውን እጅግ ብርቅዬ ነገር አመጣህ - ይኸውም የገነትን በር የሚከፍት የንስሃ እንባ ነው!" በማለት ተናገረ::

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር ከአእላፋት ዝማሬ በፊት በብዙ አጥቢያዎች መሐረነ አብ እንዲደርስ ያደርጋል። ሰዎች ጸሎቱን እየተከታተሉ በእንባ "ማረን፥ ይቅር በለን" እያሉ መሐረነ አብን ይጸልያሉ። የአንዳንዱ እንባ ያስደነግጣል፤ ያስፈራልም። የባለፈው ዓመት ዝማሬ ላይ ስንቱ በእንባ እየታጠበ እንደዘመረ መድኃኔዓለም ያውቀዋል። በአእላፋት ዝማሬ ቤተክርስቲያን መጥቶ፥ "ይህቺ ናት ለካ ቤተክርስቲያን!" ያለው እልፍ ነው። በዚያው ትምህርት ተምሮ ወደ ቤተክርስቲያን አገልግሎት የገባውም ብዙ ነው! የዚህ ዝማሬ አንድምታው ቀላል አይደለም!

ቅዱስ መድኃኔዓለም ለምህረት ይኾንልን ዘንድ ከሚፈሰው እንባ አንዷን የእንባ ዘለላ ይቀበልልን ይኾን? እርሱ እንደ ቸርነቱ ያድርግልን! ሐዋርያው "ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ" (ፊል 4፡4) ብሎናልና፤ ሁኔታ ሳይገድበን እናመሰግንሃለን! እንዘምርልሃለንም!

እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር፥ ነገ ታህሳስ 28 2017 ዓ.ም ልደቱን በባለ ልደቱ ቤት በዝማሬ ለማክበር በቦሌ መድኃኔዓለም ከ 8፡00 ጀምሮ እንገናኝ!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/fre.asalib
ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett
ሊንክድኢን፡ https://www.linkedin.com/in/fresenbet-g-y-adhanom/
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/fresenbet_et/

Fresenbet G.Y Adhanom

29 Dec, 15:40


+ መቃብራችን ምን ይላል? +

በሁላችንም ሕይወት ውስጥ ወደድንም ጠላንም የምንቀበለው አንድ እንግዳ አለ። ይህ እንግዳ ‘ላይህ አልፈልግም’ ብለው የሚደበቁት አይደለም። ይህ እንግዳ ‘ዛሬ የለም፥ ነገ ተመለስ በለው’ ብለው ሰው ልከው የሚሸኙት አይደለም። ይህ እንግዳ ‘ሒድልኝ፥ ከቤቴ ውጣልኝ’ ብለው የሚያዋርዱትም አይደለም። እርሱ ‘በዘገየ’ እንጂ ‘በቀረ’ የማንለው ከባድ እንግዳ ነው። ይህ እንግዳ እንደሌላው አስተናግደው የሚሸኙት ሳይሆን ሁሉን ጥለው ወደመጣበት የሚከተሉት ልዩ እንግዳ ነው። ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፥ እውቀት ያለው በእውቀቱ፥ ውበት ያለው በውበቱ ሊደልለው አይችልም። ‘ተወለደ’ የተባለለት ሰው ሁሉ ‘ሞተ’ ሊባልለት በውዴታ ግዴታ ይቀበለዋል። ስሙ ማን ይባላል? ምዕራባዊያኑ ‘ሁሉን እኩል አድራጊ’ የሚሉት፥ ዐረቦቹ ‘የእንቅልፍ ታላቅ ወንድም’ ብለው የሰየሙት ሞት ነው!

ሞት የተባለ እንግዳ መጥቶ ለጎበኘው ወዳጃችን የምንሰጠው የመጨረሻ ስጦታ ለቅሶ እና የመቃብር ድንጋይ ነው። ለቅሶው ጊዜያዊ፥ የመቃብር ድንጋዩ ዘላቂ እንደሆነ ይታሰባል። ታዲያ ወዳጅ ሲሞት የመቃብር ድንጋዩ ሕይወቱን ያንጸባርቃሉ በተባሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያሸበርቃል። ሕይወቱ ከፋም ለማም፥ የአንዱ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ” (2 ጢሞ 4፡7) የሚል ይጻፍበታል። የሌላዋ “በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው” (ራእ 14፡13) የሚል ይኖርበታል። የሌላው ደግሞ “ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ” (ፊል 1፡23) ይለናል። እነዚህን እና መሠል ጥቅሶችን ሁሉም ያለ አድልዖ ይጠቀምባቸዋል።

መቃብራችን ስለ ሕይወታችን እውነቱን ቢናገር ኖሮስ? የመቃብር ድንጋያችን ባይዋሽ ስለ ሕይወታችን ምን ይል ነበር?

እግዚአብሔርን በመፍራት እና በማገልገል ኖረን፥ መቃብራችን “የእግዚአብሔር አገልጋይ የሁሉ ወዳጅ ሆኖ አለፈ” ይል ይኾን? “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” (ማቴ 25፡21) የሚለውን ጥቅስ እናገኝበት ይኾን?

በዓለም ላይ በመዳከር ሕይወታችንን አሳልፈን፥ መቃብራችን “ኹሉ አለኝ እያለች፥ አንዳች ሳይኖራት ተሸኘች” ይል ይኾን? “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?” (ማር 8፡36) የሚለው አሳዛኝ ጥቅስ ተጽፎበት እናገኝ ይኾን?

ኑሯችንን በስስት እና በስግብግብነት አሳልፈን፥ መቃብራችን “እርሱን እንዳትመስሉት፤ ትምህርት አድርጉት እንጂ!” ይል ይኾን? “በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ ወዮላችሁ!” (ማቴ 23፡25) የሚለው ጥቅስ ይኖርበት ይኾን?

ዛሬ ብንሞት፥ ነገ መቃብራችን ምን ይል ይኾን? መቃብራችን ባይዋሽ፥ ምን ተጽፎበት ይገኝ ይኾን?

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------
ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ሊንክድኢን፡ https://www.linkedin.com/in/fresenbet-g-y-adhanom/

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/fresenbet_et/

Fresenbet G.Y Adhanom

25 Dec, 11:24


ከወጣቷ የሥነ-ልቡና ባለሞያ ሕይወት ጋር "ራስን መውደድ" በሚለው አሳብ ማዕከልነት አድርገን በተለያዩ ሥነ-ልቡናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረግነው ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል ጋብዣችኋለሁ።

https://youtu.be/FAimU1zjlds?si=iPbwhiLYkqUpGd7N

Fresenbet G.Y Adhanom

21 Dec, 15:12


በአርጋኖን ሚዲያ ላይ በሚዘጋጀው "አርጋኖን ፖድካስት" ላይ ከዲ/ን ከሣቴብርሃን (ዶ/ር) ጋር በኢአማኒነት ዙሪያ ጥሩ ቆይታ አድርገናል። የኢአማኒነት ጉዳይ ቤተክርስቲያን ትኩረት ልትሰጠው የተገባውን ያህል ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ አይደለምና፥ ስለዚህ ብለን ጉዳዩን ወደ ብርሃን ለማምጣት ሞክረናል።

ተጋብዛችኋል!

https://youtu.be/K7tDet51fp0?si=ade8btNUiJmjh2gC

Fresenbet G.Y Adhanom

12 Oct, 05:57


በልደቴ ቀን የቤተሰብነት ስጦታ ስጡኝ!

ዛሬ ልደቴ ነው። የዚህን ዓመት ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ሠላሳ ዓመት መድፈኔ ነው። ከሰሞኑ ጀምሮ "ለመሆኑ እስከ ዛሬ ድረስ በሃያዎቹ እድሜዬ ምን ሠራሁ?" ብዬ መጠየቅ ጀምሬያለሁ። ለራሴ የሰጠሁት መልስ መልካም ነው። መሥራት የምፈልጋቸውን ሁሉ ሠርቻለሁ ባልልም፥ ሃያዎቹ ዓለማዊም ሆነ መንፈሳዊ ትምህርቶችን የተማርኩበት፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት በደንብ የቀረብኩበት፥ ቤተክርስቲያንን ያገለገልኩበት፥ ያገባሁበት እና የወለድኩበት ነው። ሃያዎቹን ከሞላ ጎደል በደንብ እንደተጠቀምኩ ይሠማኛል። በብዙ ቸር የሆነልኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይኹን!

አሁን ደግሞ ሠላሳዎቹን 'ሀ' ብዬ ጀምሬያለሁ። በዛሬዋ የልደቴ ቀን አዲሱን የአገልግሎት መሥመሬን ላስተዋውቃችሁ መጥቻለሁ። በአሁን ጊዜ ለብዙዎች ለመድረስ ከሚዲያ የተሻለ አማራጭ የለምና፤ እነሆ 'ቴዎሎጊያ' በተሰኘ ዩቲዩብ ቻናሌ መጥቻለሁ። ይህ ቻናል ጥናትና ምርምር የተደረገባቸውን መንፈሳዊ ቪዲዮዎች የምለቅበት ይሆናል።

በልደቴ ቀን ለወደፊት በብዙ የምትገለገሉበትን ቻናሌን ቤተሰብ ትሆኑኝ ዘንድ ስጦታ ሰጠኋችሁ፤ እናንተም በልደቴ ቀን 'Subscribe' በማድረግ ቤተሰብ የመሆንን ስጦታ ትሰጡኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

https://youtube.com/@theologiaortho?si=1NXLiOOi2bA37WNy

Fresenbet G.Y Adhanom

14 Sep, 17:08


በእቁብ እናንብብ!

ከጥቂት ጊዜ ወዲህ ሁኔታዬን ሳስተውለው፥ ድሮ መጻሕፍትን በምገዛበት መጠን እየገዛሁ አይደለም። ይህ የሆነው የመጻሕፍት ዋጋ እጅግ እየተወደደ ስለመጣ ነው። መጻሕፍት እጅግ ሲወደዱበትን "ይህንን ነገር ለቤቴ ላሟላ ወይስ መጽሐፉን ልግዛ?" የሚል አጣብቂኝ ውስጥ መግባት ጀመርን። ጉዳዩ እንዲህ መሆኑ ቢያሳዝንም፥ አሪፍ መፍትሔ ይዘው የመጡትን አሪፍ መጻሕፍት ተዋወቋቸው!

አሪፍ መጻሕፍቶች የመጻሕፍት እቁብ ይዘውልን መጥተዋል። ኪሳችን እንዳይጎዳ ደግሞ እንደ አቅማችን በ400 ብር፥ በ700 ብር፥ በ1000 ብር እና በ5000 ብር አማራጭ አቅርበውልናል። እቁቡ በየወሩ የሚጣል ሲሆን፥ በስድስት ወር ውስጥ ይጠናቀቃል። እቁብ ሲወጣልን ደግሞ በቅናሽ መጻሕፍትን ከመግዛት ባሻገር፥ ካለንበት ቦታ በነጻ ዲሊቨሪ ሊያደርሱልን ቃል ገብተዋል።

አኔ ኪሴን የማይጎዳውን አማራጭ በመምረጥ ተመዝግቤያለሁ። እርስዎስ? እስቲ በአዲሱ ዓመት በእቁብም ቢሆን የንባብ ሕይወታችንን እናስቀጥል!

https://forms.gle/8FvLNHsqY1LJ9hzPA ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

አሪፍ መጻሕፍት እናመሰግናለን!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

Fresenbet G.Y Adhanom

11 Sep, 14:37


https://youtu.be/FqLG4hz48sw?si=5WsAJ5Oja_D5l9WY

Fresenbet G.Y Adhanom

11 Sep, 14:36


+ ሀብታም አይጸድቅም? +

ቤተክርስቲያን ለረዥም ዘመናት ሰይፍና ጦርን ብቻ ሳይሆን ሐሰተኛ ትርክቶችንም እየተቋቋመች ዛሬ እስካለንበት ዘመን መዝለቅ ችላለች። ከእነዚህ የሐሰት ክሶች መካከል ቤተክርስቲያን ሥራን ጠልታ ስንፍናን እንደምታገዝፍ፥ ሀብታምን ገፍታ ድሃን ብቻ እንደምታቅፍ፥ ሠርቶ መክበርን ሳይሆን የፈቃድ ድህነትን ብቻ የምትሻ እንደሆነች ተደርጎ የሚነገርባት አንዱ ነው።

ይህንን እና መሠል ጉዳዮችን በተመለከተ ከወንድሜ ዮኒ (Yonas Moh) ጋር ዘለግ ያለ ቆይታ አድርገናል። የአዲስ ዓመት ግብዣ ትሁንልኝ።

እንኳን ለ 2017 ዓ.ም በቸርነቱ አደረሰን!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://lnkd.in/e2NNiGH4

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://lnkd.in/eU7d2X_Q

Fresenbet G.Y Adhanom

08 Sep, 05:45


+• ውሃ የሚያናውጥ መልአክ •+

በጥንት ዘመን በኢየሩሳሌም ውስጥ በሽታ የጸናበት ሰው ሁሉ የሚናፍቃት አንዲት መጠመቂያ ነበረች። ይህቺ መጠመቂያ ጤናማ ሰው ቢመለከታት የተለየ ነገር ላያይባት ይችላል። ታሞ ያያት ሁሉ ግን በውስጧ የመዳን ተስፋን ያይባታል። ስሟ ቤተ-ሳይዳ ይባል ነበር። በዚህች መጠመቂያ ቦታ ደዌ የበረታባቸው ሁሉ በዙሪያዋ ቁጭ ብለው አንዳች ነገር ይጠባበቃሉ።

ይህ የሚጠባበቁት አንዳች ነገር የውሃውን መናወጥ ነበር። ሰላምና የተረጋጋ የነበረው ውሃ ድንገት ከተናወጥ፥ አካባቢው በአንዴ ይረበሻል። ሁሉም ይሯሯጣል። እድል ቀንቶት መጀመሪያ የገባ ካለበት በሽታ ሁሉ በአንዴ ይፈወሳል። የመዳን ሎተሪ እንደማለት ነው። ለአንድ ሰው ብቻ ይወጣል። ሐኪም ቤት ለመታከም ሄደን ቀድሞ የደረሰው ሰው ብቻ ታክሞ ቢድን፥ ሌላው ሁሉ ወደ ቤቱ ቢሸኝ ማለት ነው። ለአንዱ ፈንጠዚያ፥ ለሌላው ግን እንደገና ሌላ የመዳን ጥበቃ።

ውሃው ግን የሚናወጠው በተፈጥሮ ምክንያት አልነበረም። የዮሐንስ ወንጌል "አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና" (ዮሐ 5፡4) ይለናል። ለመሆኑ ይህ ውሃውን የሚያናውጥ መልአክ ማነው? በዚህ ዙሪያ ሁለት ምልከታዎች አሉ። አንዱ ወገን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነው ሲል ሌላው ደግሞ ቅዱስ ሩፋኤል መሆኑን ይገልጻል።

ከሁለቱ ትውፊቶች ምናልባትም "ቅዱስ ሩፋኤል ነው" የሚለው ቢያመዝን ስንኳ የሚገርም አይሆንም። ቅዱስ ሩፋኤል ብዙ ነገሩ ከፈውስ ጋር የተጣመረ ነው። ሊቃውንት ስሙን ሲተረጉሙት "ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ" ብለው ቢሆንም፥ የዕብራይስጡ የስሙ ፍቺ ግን የመልአኩን እውነተኛ ማንነት ይበልጥ አጉልቶ ያሳያል። በዕብራይስጥ ስሙ ራፋኤል (רָפָאֵל‎) ሲሆን፥ የስሙ ዋና ሥር የሆነው ረፈአ (רפא) እንደ ግሥ ስንጠቀመው "ፈውስ" ማለት ነው። በመሆኑም ራፋኤል የሚለው ስም ፍቺ "እግዚአብሔር ፈወሰ" ወይም "እግዚአብሔር ፈውሷል" ማለት ይሆናል።

በአንድ የጥንት የአይሁድ ትውፊት ላይ አብርሃም ከተገረዘ በኋላ እግዚአብሔር ቁስሉን ይፈውስለት ዘንድ ቅዱስ ሩፋኤልን እንደላከለት ያትታል። መጽሐፈ ሄኖክም ስለዚህ መልአክ "በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው"(ሄኖ 10፡13) በማለት ይገልጻል። ሊቃውንትም ሕሙማንን የሚፈውስ (ፈዋሴ ዱያን) ይሉታል። እንግዲህ "ውሃውን እያናወጸ ሰዎች እንዲፈወሱ ያደርግ የነበረው ቅዱስ ሩፋኤል ነው" ቢባል የማይገርመው ለዚያ ነው፤ እንዲያውም ከስሙም ሆነ ከግብሩ የሚስማማ ይሆናል።

ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ፥ የእኛ ደዌ ለሠላሳ ስምንት ዓመት ከተኛው ከመጻጉዕ ይጸናል። በቤተሳይዳ ከተሰበሰቡት ድውዮች ሕመምም ሁሉ ይከፋል። የእነርሱ ደዌስ ለራስና ለአስታማሚ ብቻ ተረፈ። የእኛ ውስጣዊ ደዌ ግን መዘዙ ለሀገር ሁሉ ሆነ። ታላቁ መልአክ ሆይ፥ በተሾምህባት በዚህች ዕለት፥ የተጨነቁትን ነፍሳት ሁሉ አስብ። ደመናቱን አናውጸህ፥ ዝናቡንም ባርከህ በጠበልነቱ ክፉ በሽታችንን ፈውስልን።

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

ሥዕሉን በትውፊቱ መሠረት የሣለው ሠዓሊ Gigar Negusse ነው።

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://www.facebook.com/fre.asalib

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1

Fresenbet G.Y Adhanom

06 Sep, 09:38


+ የክፉ ቀን ‘ተመስገን’ +

አንዱ ሰው “የሰው ልጅ ሕይወት ውጣ ውረድ የበዛው ነው” ሲሉት “የኔ ሕይወት ታዲያ ምነው ውረድ ብቻ ሆነብኝ? ውጣው የታለ?” አለ ይባላል። ይህ ሰው እውነት አለው። አንዳንዴ የሰው ልጅ በመከራ ተወልዶ፥ በመከራ ኖሮ፥ በመከራ ሲያልፍ እንመለከታለን። በሕይወታችን ውስጥ መከራቸው ከመብዛቱ የተነሣ “ምነው ባለፈላቸው” ብለን የምንለምንላቸው ሰዎች አይጠፉም። በዚህ ጊዜ ‘ብርቱ ትግል የሚሰጠው ለብርቱ ወታደር ነው’ የሚለውን እያሰብን እንጽናናለን። በእርግጥ ትግሉ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ብቻ አይደለም፤ ይህንን ደግሞ ከኢዮብ ታሪክ በላይ የሚያስረዳ ላይኖር ይችላል።

ጻድቁ ኢዮብ ሰይጣን የሚቀናበት፥ ሰዎች ለመሆን የሚመኙት፥ እግዚአብሔር ደግሞ እጅግ የሚወድደው ሰው ነበር። ሰዎች የሌሎች ሰዎችን ሙገሳ በሚፈልጉበት ዓለም፥ ከፈጣሪው ዘንድ “በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹማና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም” (ኢዮ 1፡8) ተብሎ የተመሰከረለት ነው። ይህ መሆኑ ግን ከመከራ አልሸሸገውም። ከአሥር ሺህ በላይ የሆኑት ከብቶቹ የተወሰኑት ተማርከው፥ የተወሰኑት ተገድለው፥ የተቀሩት ደግሞ ከሰማይ በወረደ እሳት ተበልተው መጥፋታቸው ተነገረው። ሦስቱንም መርዶ የሰማው በተከታታይ ከመሆኑ የተነሳ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ‘እርሱም ገና ሲናገር ሳለ ሌላ መጥቶ እንዲህ አለው’ እያለ ተገልጿል። አንዳንድ መርዶ የቀደመውን መርዶ ሰምተህ እስክትጨርስ ስንኳን አይጠብቅህም። ኢዮብ ይህንን ሁሉ ሰምቶ መጮኽ ሳይጀምር ሌላው ደርሶ ልጆቹ የነበሩበት ቤት በድንገተኛ ነፋስ ተንዶ አሥሩም ልጆቹ እንደሞቱ ነገረው።

ይህ ሁሉ ሆኖበት ኢዮብ ምን አለ? መጎናጸፊያውን ቀድዶ፥ ራሱን ተላጭቶ፥ በምድር ተደፍቶ ሰግዶ “እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔር ነሣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ፈቀደ ሆነ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን” (ኢዮ 1፡21) ብሎ እግዚአብሔርን አመሰገነ። ንብረቱን ሁሉ ያጣው ኢዮብ እግዚአብሔርን አከበረ! አሥር ልጆቹን በአንዴ የተነጠቀው በምድር ላይ ሰግዶ እግዚአብሔርን አመሰገነ!

ልጆቿን ሁሉ በማጣቷ “የወላድ መካን” የሆነችው የኢዮብ ሚስት ወደ ባሏ ስትመጣ ጤናውንም ሳይቀር አጥቶ ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ በቁስል ተሸፍኖ አገኘችው። ደህና መካሪ መስላ ‘እግዚአብሔርን ስደብና ሙት’ (ኢዮ 2፡10) አለችው። ብዙዎቻችን ቢሆን “እውነትሽን ነው! በጽድቅ ሆኜ በኖርኩ እንዴት እንዲህ ያደርገኛል!” ብለን ለስድፍ አፋችንን በከፈትን ነበር። ኢዮብ ግን ቀና ብሎ አይቷት “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ!” ብሎ ገሰጻት። ከዚያም በኋላ ለሁላችንም ምክርና መጽናኛ የሚሆን ነገርን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” (ኢዮ 2፡10)

ይህ ጥያቄ ለእኛም ነው። ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ከተቀበልን፥ ክፉውን አንታገሥምን? እግዚአብሔርን በሕይወታችን ውስጥ ባሉ ስኬቶች ብቻ መመዘን አይበቃንምን? እግዚአብሔር ቢከፋም ቢለማም፥ ቢደላም ቢጨንቅም የሚመለክ ታላቅ አምላክ አይደለምን?

እግዚአብሔርህ ሆይ፥ ለውጣውም ለውረዱም ተመስገን!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://lnkd.in/e2NNiGH4

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://lnkd.in/eU7d2X_Q

Fresenbet G.Y Adhanom

19 Aug, 15:14


+ በሕጻን ሄቨን ጉዳይ ምን እናድርግ? + (አንዳንድ የመፍትሔ ሃሳቦች)

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጆሮን ጭው የሚያደርጉ፥ ሰውነትን የሚወሩ፥ 'አይ ሰው መሆኔ' የሚያስብሉ፥ በፍትሕ ሥርዓቱ ተስፋን የሚያስቆርጡ ዘግናኝ ወንጀሎች እየተበራከቱ መጥተዋል። የወንጀሎቹ ሰቅጣጭነት ሳያንስ፥ ሁሉም የአንድ ሳምንት አጀንዳ ከመሆን አለመዝለላቸው ደግሞ እጅጉን ያማል። "ፍትሕ" የሚለው ጩኸት ከሳምንት በላይ ሊዘል አለመቻሉ፥ ጥልቅ ማኅበረሰባዊ ልምሻ እያጠቃን መሆኑን አመላካች ነው። የዚህ ልምሻ ክትባትም ሆነ መድኃኒት በቶሎ ካልተገኘ መዘዙ አደገኛ ነው።

ከሰሞኑ የሕጻን ሄቨንን ጉዳይ ሰምቶ ያልታመመ ያለ አይመስለኝም። በግሌ የእናቷን ቃለ መጠይቅ ስንኳ ጨርሼ መስማት አልቻልኩም። ለሚስቴ ባል፥ ለእህቶቼ ወንድም፥ ለልጄ አባት እንደመሆኔ የእናቷን ሕመም ለመጋራት "በእኔስ ቤተሰብ ደርሶ ቢሆን?" ብሎ ራስን መጠየቅ ብቻ በቂ ነው። በእውነቱ ይህንን ማሰብ እስከማልችል ድረስ የሚዘገንን ነው። የሕጻን ሄቨንን ጉዳይ ግን የአንድ አረመኔ ጉዳይ ብቻ አድርገን ካሰብነው ተሳስተናል። ሥልጣንን ለወንጀለኛ ሽፋን መስጫ የሚጠቀሙ ባለሥልጣናትን፥ ማስረጃ ለማጥፋት የሚሞክሩ የጤና ባለሞያዎችን፥ ወንጀልን የሚያደባብሱ የፖሊስ አባላትን፥ ለገዳይ የሚወግኑ ሴቶችን ያየንበት ነው። ይህ ጉዳይ በዳይ እየተዝናና ተበዳይ ሲሳደድ ያየንበት የፍትሕ ሥርዓት እንቆቅልሽ ነው።

በእርግጥ ፍትሕን መጠየቃችን መልካም ነው። ከዚያ ባለፈ ግን “ሌላስ ምን ማድረግ እንችላለን?" ብለንም መጠየቅ ይኖርብናል። በዚህ ደረጃ ሁለት መፍትሔ ይታየኛል። አንድኛው ወንጀለኛው ተገቢውም ቅጣት እንዲያገኝ የማድረጉ ጉዳይ ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ የሕጻን ሄቨን እናትን የመደገፉ ጉዳይ ነው።

1) የሕጻን ሄቨን ገዳይ ጉዳይ በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ነው። ከዚህ ባለፈ የሴቶች የሕግ ባለሞያዎች ማኅበር እና የሕጻናትና ሴቶች ጉዳይም ያለበትን የሕግ ሁኔታ እየተከታተሉ መሆናቸውን ሰምተናል። ይህ አበረታች ነው። ሆኖም ግን ጉዳዩ እንደሌሎች መሰል ክሶች በሕዝብ ዘንድ ተረሳስቶ እንዳይቀር ከፍተኛ ክትትልን ይጠይቃል። ከዚያ ባለፈ ደግሞ እውነተኛው የፍትሕ ባለቤት እግዚአብሔር ለወንጀሉ ፍትሕን፥ ለሕጻኗ የነፍስ እረፍትን፥ ለእናቷ መጽናናትን ይሰጥ ዘንድ ሁላችንም እንጸልይ። ከዚህ በተጨማሪ ግን ተከሳሹ ከፍተኛውን ቅጣት እንዲያገኝ እየተሰበሰበ ያለ ፐቲሽን ስላለ፥ እርሱን በመፈረም የበኩላችንን ማድረግ እንችላለን። የፕቲሽኑ ሊንክ የሚከተለው ነው፦ https://chng.it/8VRtxHHYZH

2) ሁለተኛው ጉዳይ ለሕጻን ሄቨን እናት የሚደረገውን ድጋፍ በተመለከተ ነው። በማኅበረሰብ ደረጃ በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ ለውጥ ማምጣት የምንችል ይመስለኛል። በአሁኑ ሰዓት ለእናቷ የሥነ ልቡና እና የገንዘብ ድጋፍ እጅጉን ያስፈልጋል። የሥነ ልቡና ድጋፉን በተመለከተ በተለይም ለሥነ ልቡና ቁስል እና ጥልቅ ሐዘን (Trauma and Grief) በሚሰጥ የሥነልቡና ሕክምና ላይ ልምድ ያላችሁ የሥነ ልቡና ባለሞያዎች አስፈላጊውን የሥነ ልቡና ድጋፍ ብታደርጉላት መልካም ነው። እናትየዋ በግፍ ከሥራዋ ተፈናቅላ ችግር ላይ እንደመሆኗ መጠን ደግሞ፥ የገንዘብ ድጋፉ እጅግ ወሳኝ ነው። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ሁላችንም የተቻለንን ድጋፍ በእናቷ የግል አካውንት ማድረግ እንችላለን። የንግድ ባንክ አካውንቷ የሚከተለው ነው፦ Abekyelesh Adeba Kassa – 1000177318934

እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ!
የሕጻኗንም ነፍስ በግፍ ከተገደሉ ሕጻናት ነፍስ ጋር በገነት ይደምርልን!
ለእናቷም እውነተኛው አጽናኝ መንፈስ መጽናናትን ይስጥልን!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://lnkd.in/e2NNiGH4

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://lnkd.in/eU7d2X_Q

Fresenbet G.Y Adhanom

29 Jul, 11:21


+• ደፋር ሟች እና ፈሪ ገዳይ •+

የብዙ ሰማዕታት አሟሟት የዓለምን ታሪክ ገልብጦ አሳይቶናል። በዓለም ታሪክ የሚታወቀው ሟቾች ሲሸሹ እና በፍርሃት ሲቅበዘበዙ፥ ገዳዮች ደግሞ በድፍረት ሲንጎማለሉ እና ሲኩራሩ ነው። የሰማዕታት ሞት ግን ይለያል። ሟች ሳይፈራ ወደ ሞት ሲገሰግስ፥ ገዳይ ወይም አስገዳይ ደግሞ በሟች ላይ የሚያየው ድፍረት ሲያስፈራው እና ሲያስደነግጠው የምናየው የሰማዕታትን ልዩ ሞት ስንመለከት ነው። አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም “አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ ያስጨክናሉ” የሚለንን በሰማዕታት ድፍረት ውስጥ እናየዋለን። ዛሬ የምናስታውሳቸው ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስም ወደ ሞት ሲገሰግሱ ያልፈሩ ሥላሴ ያስጨከኗቸው ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሰማዕት ናቸው።

ጣሊያን አቡነ ጴጥሮስን ሲከስሳቸው “ሕዝብ ቀስቅሰዋል፥ ራስዎም ዐምጸዋል፥ ሌሎችም እንዲያምጹ አድርገዋል” በማለት ነበረ። ይህንን አስታኮም ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ስንኳ ጣሊያንን ሲቀበሉ እርሳቸው ለምን እንዳመጹ ተጠየቁ። ሰማዕቱ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስም “አቡነ ቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን የሚገዳቸው ነገር የለም። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ። ስለዚህም ስለ አገሬና ስለ ቤተክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ። ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም። ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ። ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ።” በማለት ተናግረዋል።

ፓጃሌ የተባለ የኮርየሬ ኬላሴራ ጋዜጣ ወኪል ስለ ሰማዕቱ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ሲጽፍ፤ ከመሞታቸው በፊት መስቀላቸውን አውጥተው ሕዝቡን እንደባረኩ ይነግረናል። የሞታቸው ሰዓት መድረሱን አውቀው ሰዓታቸውን አውጥተው ሲመለከቱም ሰዓቱ “5፡15” ይል ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ምንም ፍርሃት እንዳልታየባቸው፤ በተቃራኒው ግን የሞት ፍርዳቸውን ያነብብ የነበረው ጣሊያናዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ እንደነበረ ዘግቧል። የአቡነ ጴጥሮስን የሞት ፍርድ ለማስፈጸም የተኮሱት ወታደሮች በስምንት ጥይት ቢመቷቸውም ስላልሞቱ ሌላ ወታደር የራስ ቅላቸውን በሽጉጥ መትቶ ገድሏቸዋል።

የአባታችን የሰማዕቱ የቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ በረከት በሁላችን ላይ ይደር!


🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

----------

የፌስቡክ ገጽ: https://lnkd.in/e2NNiGH4

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ቲክቶክ: https://lnkd.in/eU7d2X_Q

Fresenbet G.Y Adhanom

25 Jul, 06:45


+ ሸክላ ሠሪ +

በድሮ ዘመን ነው - መምህር አልዓዛር የተሰኙ አንድ የአይሁድ መምህር በአህያቸው ላይ ኾነው ከትምህርት ቤታቸው ወደ ሰፈራቸው እየተመለሱ ነው። በእለቱ በዛ ያለ የእግዚአብሔር ቃል ስላጠኑ ቀናቸው ብሩህ ኾኖላቸው ፊታቸው ፈካ ብሏል። በጉዞ ላይ እያሉ ግን አንድ ሰው ቀረበና፡ “መምህር ሆይ፥ ሰላም ለእርስዎ ይኹን!” ብሎ ሰላምታ ሰጣቸው። ከአህያቸው ላይ ሆነው ቁልቁል አዩትና ፊታቸው ጠቆረ። “አንተ የማትረባ! መልክህ ምንድር ነው? ለምንድር ነው እንዲህ መልከ ጥፉ የኾንከው? የአንተ አካባቢ ሰዎች ሁሉ እንዳንተው መልከ ጥፉ ናቸው እንዴ?” አሉት። ይህም ሰው “እርሱን አላውቅም። ባይኾን የሠራኝን ሄደው ‘የሠራኸው ሸክላ እንዴት መልከ ጥፉ ነው!’ ብለው ይንገሩት።” አላቸው።

መምህር አልዓዛርም ሰውየውን በመልኩ ብቻ ክፉ ንግግር እንደተናገሩት አስተዋሉና ከአህያቸው ወረዱ፤ በፊቱም ተደፍተው “እባክህ ይቅር በለኝ” ብለው ለመኑት። እርሱ ግን “እርስዎ ሄደው ለሠራኝ ‘የሠራኸው ሸክላ መልከ ጥፉ ነው!’ ብለው እስካልነገሩት ድረስ ይቅርታ አላደርግልዎትም አላቸው።

መምህር አልዓዛር ሰውየውን እየተከተሉ ይቅርታ እየጠየቁት ከሰፈራቸው ደረሱ። የሰፈሩ ሰው ኹሉም እየወጣ “እንኳን ደህና መጡ፥ መምህር ሆይ” እያሉ ሰላምታ ይሰጡዋቸው ጀመር። ሰውየውም “ማንን ነው መምህር ሆይ የምትሉት?” ብሎ ጠየቀ። ሰዎቹም “እርሳቸውን ነዋ! ታላቅ የኦሪት መምህር ናቸውኮ!” ብለው መለሱለት። እርሱም “እርሳቸው የኦሪት መምህር ከኾኑ፥ እንግዲያውስ ለዘለዓለም በእስራኤል ምድር እንደ እርሳቸው አይነት መምህር አይኑር!” ብሎ ተናገረ። የሰፈራቸው ሰዎችም ደንግጠው ለምን እንዲህ እንዳለ ጠየቁት፤ እርሱም የተፈጠረውን ነገራቸው። ሰዎቹም በማዘን “ቢሆንም ይቅርታ ጠይቀዋል፤ ስለዚህ ይቅር በላቸው። እርሳቸው ታላቅ የኦሪት ምሁር ናቸው።” አሉት። ሰውየውም “ከአሁን በኋላ እንዲህ አይነት ነገር እንደማያደርጉ ቃል ከገቡ፥ ለእናንተ ስል ይቅርታ አደርጋላቸዋለሁ።” በማለት ለመምህሩ ይቅርታ አደረገላቸው።

በእድሜ ዘመናችን ‘ሲያስጠላ፥ ስታስጠላ’ ብለን ያሸማቀቅናቸው ምን ያህል ይኾኑ? ለአንዳንድ ሰው ምርቃት እስኪመስል ድረስ እነዚህ ቃላት ከአንደበቱ አይለዩትም። እግዚአብሔር አስውቦ የሠራውን ሸክላ ለመንቀፍ የበቃነው፥ እኛም ‘ሸክላነታችንን’ ስለምንረሳ ነው። ሸክላነቱን ያልረሳው የዘለሰኛ ገጣሚ፦

‘እዚያ ዳር ያለች ሸክላ ሠሪ፥ ድሃ ናት አሉ ጦም አዳሪ
ማን አስተማራት ጥበቡን፥ ገል ዐፈር መኾኑን!’

… ብሎ አዚሞ ነበር። አንዳንዴ ኹሉ ሲሰምርልን ሥልጣን የሚሻር፥ ሀብት የሚጠፋ፥ መልክ የሚጠወልግ አይመስለንም። አንዳንዶች ጸጉራቸው መመለጥ ሲጀምር ‘ጸጉርኮ ባዳ ነው’ ይላሉ። ጸጉር ብቻ ሳይሆን አሉን የምንላቸው ሁሉ ባዳ ናቸው። በዚህ ሁሉ ውስጥ ጸንቶ የሚቀረው ‘ሸክላነታችን’ ነው፤ እርሱም ወደ መጣንበት ዐፈር እስክንመለስ ድረስ።

ሁላችንም ከአፈር የተሰራን ሸክላ ነንና፤ ሸክላውን በመልኩ ስንሳደብ፥ ሸክላ ሰሪውን እየነቀፍን መኾኑን አንርሳ!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
---------
የፌስቡክ ገጽ: https://www.facebook.com/fre.asalib

ቴሌግራም: https://t.me/fresenbett

ሊንክድኢን፡ https://www.linkedin.com/in/fresenbet-g-y-adhanom-7b316b312/

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1

Fresenbet G.Y Adhanom

22 Jul, 12:52


በአካባቢው 18 ምእመናን ብቻ የሚኖሩበትን የዋሽወራ ቅዱስ ቂርቆስ እና እናቱ ኢየሉጣ ቤተ ክርስቲያን ታግዙ ዘንድ የበረከት ጥሪ ቀርቦላችኋል።

Fresenbet G.Y Adhanom

22 Jul, 12:50


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!


ውድ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ እንኳን ለአፈ በረከት ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የእረፍት በዓልና ለሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ🙏🙏🙏


ከሥር በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በጉራጌ ሀገረ ስብከት በምሁርና አክሊል ወረዳ ቤተ ክህነት በአጣጥ ቀበሌ በልዩ ስሙ የዋሽወራ ቅዱስ ቂርቆስ እና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን በአካባቢው 18 ምእመናት ቢቻ ያሉበት አጥቢያ ነው ታዲያ አሁን እየተገለገሉበት ያለው ቤተ መቅደስ ከእርጅናና በክረምት ወቅት ከሚደርስበት የጎርፍ ጥቃት እየተሸረሸረና እየተቦረቦረ ቤተ መቅደሱ ሊፈርስ ከጫፍ ድርሷል ማለት ይቻላል ታዲያ ይህን ታሳቢ በማድረግ በአካባቢው በአሉት ምእመናት ተነሳሽነት ከሥር በምስሉ የምታዩትን ቤተ መቅደስ በአስቸኳይ እየተሰራ ይገኛል ግን በአጥቢያው ያሉት ምእመናት ከአቅማቸው በላይ እያደረጉ ይገኛሉ ግን አሁን ላይ የማቴሪያል እጥረት አጋጥሟቸዋል ይህን ደግሞ ለማድረግ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ የእኛን የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን እገዛ ይፈልጋሉ ታዲያ የሁላችንም ግዴታ ነው ይህን ቤተ መቅደስ ማነጽ ምክንያቱም የኃያሉ የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ ስለሆነ የሁላችንም በአርባና በሰማንያ ቀን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት ስለሆነ ዘወትር በጸሎት በቅዳሴ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ስለሆነ ቤተሰብ እንኳን እንመስርት ብንል የጋቢቻ ሥርዓታችን የምንፈጽምበት ስለሆነ በነፍስም በሥጋም ብንታመም የምንፈወስበት ቤት ስለሆነ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የምንቀበልበት ስለሆነ እንዲሁ ከሥጋ እረፍታችን በምናርፍበት ጊዜ እንኳን ጸሎተ ፍትሐት ተፈጽሞልን የሥጋችን ማርፊያ ስለሆነ ብናዝን ብንደሰት መጽናኛችን ማመስገኛችን ስለሆነ ይህ ሁሉ አገልግሎትና ፀጋ የምናገኘው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ስናንጽ ነውና ሁላችንም የአቅማችንን በመርዳት ይህን ቤተ መቅደስ እናስፈጽም እግዚአብሔር ዋጋ ሲሰጥ ብዙ የሰጠ ትንሽ የሰጠ አይልም የሁላችንም ዋጋ በሰማይ እኩል ነው ስለዚህ የአቅማችንን እንስጥና ቤቱን እናንጽ እያልን በአምላከ ቅዱስ ቂርቆስና በቅድስት ኢየሉጣ ስም እናሳስባለን🙏🙏🙏


አሁን ላይ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች

፩, ድንጋይ የውሃ ልኩ ማንሺያ የሚሆን
፪, ሲሚንቶ በጣም ፈተና የሆነ ነገር ነው።
፫, በርና መስኮት
፬, ቀለም እነዚህ ዋንኞችሁ ናቸው በዚህ ሁሉ በረከት መሳተፍ ያስፈልጋል ሌላው ለጸሎትና ለልዩ ልዩ አገልገሎቶች የሚውሉ ንዋየ ቅዱሳት እጣን፣ዘቢብ፣ጧፍና ሻማ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።


👉ድጋፍ የምታድርጉበት አካውንት በቤተ ክርስቲያኑ ስም የተከፈተ ያለው ንብ ባንክ ነው ቁጥሩም፦ 7000028803977 ነው።
ምን አልባት በንግድ ባንክ መላክ የምትፈልጉ የግለሰብ አካውንት አለ እሱም፦ 1000535092797 ዮሐንስ ጌቱ በዚህም ገቢ ማድረግ ይቻላል አደራውን ማድረስ ስለምችል ነው ወገኖቼ ታዲያ ገቢ ከአደረጋችሁ በኋላ እስሊፑን ላኩልን የግድ ለማድረስ ማወቅ ያስፈልጋል ማለት ነው።

ለበለጠ መረጃና ገቢ ማድረጋችሁን ለማሳወቅ፦ 0996990485 ቀሲስ ኃይለ ቂርቆስ የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ።

👉0945173873 ዲያቆን በረከት ሞገስ አስተባባሪና አገልጋይ ነው።

👉0937076125፣0912241064 ዮሐንስ ጌቱ በእነዚህ የስልክ አድራሻዎች መረጃ መጠየቅም መስጠትም ትችላላችሁ ማለት ነው።


ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን!

5,953

subscribers

111

photos

1

videos