ጉባኤ ሐዋርያት @apostolic_council Channel on Telegram

ጉባኤ ሐዋርያት

@apostolic_council


እንኳን ወደ ጉባኤ ሐዋርያት በደህና መጣችሁ ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት "ሐዋርያት በሰበሰቧት ከሁሉ በላይ በምትሆን በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን"

ከእግዚአብሔር ቃል የተጣረሱ ሐዋርያዊ ወንጌልን የሚጻረሩ አስተምህሮዎችን ሁሉ እያነሳን በቃሉ ሥልጣን እንለያቸዋለን ከሐዋርያት የተቀበልነውን ቅዱሱን ወንጌል አጽንተን እንቀጥላለን።

ጉባኤ ሐዋርያት (Amharic)

ጉባኤ ሐዋርያት በሃኪማት እንደሚሆን ቅዱሳን ወራሪዎች ላይ አስተማማኝ እና አስተምህሮዎችን መንፈሳዊ መልዕክቶች እንሻገናለን። በሌላም በተከለከለው ኳስ ፈጽሞ እርጋቹን መስለጥ እንደሆነ እንደዚህ ውሰድ ይችላል ሐዋርያት ከቁስለምለስ ቤተክርስቲያን፣ መልክምን አርግቼ እንቀርባለን። ሐዋርያት የተቀበለበት የእንግሊዝ ርሑስ ወንጌልን በቀን እናምናለን።

ጉባኤ ሐዋርያት

17 Nov, 06:32


መዝሙር 30
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ቅዱሳን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
⁵ ቍጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፤ ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።

መልካም የምሥጋና ቀን፤መልካም ሰንበተ ክርስቲያን ይሁንልን🙏

ጉባኤ ሐዋርያት

10 Nov, 06:42


የምሥጋና ቀን።

መዝሙር 118
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፤ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች።
¹⁷ አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ።
¹⁸ መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤ ለሞት ግን አልሰጠኝም።
¹⁹ የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
²⁰ ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ ወደ እርስዋ ጻድቃን ይገባሉ።
²¹ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
²² ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤
²³ ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች፥ ለዓይናችንም ድንቅ ናት።
²⁴ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።

ዕድሜን ለጨመረልን ምህረቱን ላበዛልን እግዚአብሔር ምሥጋናን እናቅርብ እንዲሁ መሽቶ አልነጋምና ቀናቶች የምህረቱ ውጤቶች ናቸው ሰይጣን የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ሲዞረን ሊያጠፋን ወድዶ ግን ያልጠፋነው በእግዚአብሔር ምህረት እና ጥበቃ ብዛት የተነሣ ነው ገናም እንደምህረቱ እና እንደ ጥበቃው ብዛት ዕድሜን ይጨምርልናል ለጠላት ኀሳብ አሳልፎ አይሰጠንምና።ምሥጋና ይገባዋል ምሥጋና ለሥላሴ ይገባል።

መልካም ዕለተ ሰንበት ሰንበተ ክርስቲያን። መልካም የምሥጋና ቀን ይሁንልን አሜን።🙏

ጉባኤ ሐዋርያት

03 Nov, 07:15


"ወደ አባቴ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ..." ዮሐንስ ወንጌል 20፥17

የኢየሱስ ክርስቶስ ልጅነት የማይመረመር በዚህ ጊዜ ተገኘ በዚህ ጊዜ ያልፋል የማይባል ነው ልጅነቱም የባሕርይ እንደመሆኑ ቅዱሳን ከተቀበሉት ልጅነት ይለያል እኛስ በጸጋ በኵል የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል እርሱ ግን ለአብ የባሕርይ ልጁ ነውና አብን አባቴ አለው። ወበእንተ ህላዌ መለኮትሰ ይቤ አቡየ( የባሕርይ ልጅ ነውና አባቴ አለው)።

ባሕርየ መለኮቱን ሳይለቅ ወደ እኛ አንድነት ወይም ባሕርይ መጥቷልና ወይም የእኛን ባሕርይ ነሥቷልና አምላኪየ አምላኬ ሊል ተገባው «ወደለወ ይእዜ ከመ ይብል አምላኪየ በእንተ ምጽአቱ ኀቤነ እምኀበ እግዚአብሔር አቡሁ»
ግን ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር ሳይለይ ወደ እኛ አንድነት ስለመጣ ዛሬ አምላኪየ ሊል ተገባው።

ስለዚህ እንዲህ እንበል፦እግዚአብሔር አብ አምላኩ ውእቱ ለወልድ ውእቱ በእንተ ትስብእቱ ወአቡሁ በእንተ መለኮቱ ቀዳማዊ። «ሰው ስለሆነ እግዚአብሔር አብ ለወልድ አምላኩ ነው ስለቀዳማዊ ባሕርዩ ደግሞ አባቱ ነው»

ለእኛስ..? እርሱ በሰጠን ጸጋ በኵል ልጆች ተብለናል «በእንተ ጸጋ ዘጸገወ ለአርዳኢሁ ይቤ አቡክሙ» ለደቀ መዛሙርቱ ስለ ሰጣቸው ልጅነት አባታችሁ አለ።

ስለዚህ የኢየሱስ ልጅነት ቀዳማዊ ልጅነት የባሕርይ በባሕርየ መለኮት በመተካከል ጅማሬ የሌለው በመሆኑ ከቅዱሳን የጸጋ ልጅነት ልጅነት ፍጹም የተለያየ ነው።

መልካም ዕለተ ሰንበት 🙏

ማጣቀሻ
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ  ኤጵፋንዮስ ገጽ 177 ምዕራፍ 54 ከቍጥር 8-10

ጉባኤ ሐዋርያት

27 Oct, 06:05


«እርሱስ ፈጽሞ አልተወንም»

እርሱስ  ፈጽሞ አልተወንም በከሀሊነቱ ተቀበለን እንጂ  በይቅርታው በቸርነቱ ብዛት  ወደ እርሱ  አቀረበን  እንጂ እንግዲህ ወዲህ  የእጆቹ  ፍጥረቶች  ወድቀን እንድንቀር  አልወደደም  በቸርነቱ  በይቅርታው  ብዛት  የሚታየውን የማይታየውን  ሁሉ  የፈጠረበትን አካላዊ ቃሉን  ላከልን  እንጂ  የሚታዩት ያላቸው የሚዳሠሡ ፍጥረቶች ናቸው  የማይታዩ  ያላቸውም  ረቂቃን  መላእክት ናቸው።

ወውእቱሰ ኢገደፈነ  ለግሙራ  አላ ተወክፈነ በክሂሎቱ ወአቅረበነ ኀቤሁ  በዕበየ  ሣህሉ ወምሕረቱ ወኢፈቀደ አንከ ንትገደፍ  ግብረ እደዊሁ ዳእሙ  በብዝኀ  ሣህሉ ወምሕረቱ ፈነወ ለነ ቃሎ  ዘገብረ ሎቱ  ኵሎ  ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ  እለሰ ያስተርእዩ ፍጡራን እለ  ይትገሀሡ  እሙንቱ  ወእለኒ ኢያስተርእዩ ፍጡራን መንፈሳውያን እሙንቱ

ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ገጽ 124 ምዕራፍ 36 ቍጥር 15-16

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🙏

ጉባኤ ሐዋርያት

25 Oct, 18:36


𝐅𝐨𝐫 𝐦𝐞, 𝐇𝐞 𝐢𝐬 𝐆𝐨𝐝, 𝐛𝐨𝐫𝐧 𝐢𝐧 𝐭𝐡𝐞 𝐟𝐥𝐞𝐬𝐡, 𝐟𝐫𝐨𝐦 𝐭𝐡𝐞 𝐡𝐨𝐮𝐬𝐞 𝐨𝐟 𝐃𝐚𝐯𝐢𝐝, 𝐞𝐯𝐞𝐧 𝐚𝐬 𝐇𝐞 𝐬𝐮𝐟𝐟𝐞𝐫𝐞𝐝 𝐨𝐧 𝐭𝐡𝐞 𝐂𝐫𝐨𝐬𝐬.

𝑀𝑎𝑟 𝐽𝑎𝑐𝑜𝑏 𝑜𝑓 𝑆𝑒𝑟𝑢𝑔𝑒 ܡܪ ܝܝܥܩܘܒ, 𝑆𝑦𝑟𝑖𝑎𝑛 𝐶ℎ𝑢𝑟𝑐ℎ 𝐹𝑎𝑡ℎ𝑒𝑟.

@Apostolic_Council

ጉባኤ ሐዋርያት

20 Oct, 06:31


<< ከድንቅም ድንቅ >>
"መንክረ-መንክራት"

የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ባስልዮስ እንዳስተማረው።

የእግዚአብሔር ገቢረ ተኣምራት ሁሉ ግሩማን ናቸው አይመረመሩም። ቅዱስ ዳዊት ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው ይላልና....

ግና ከድንቅም ድንቅ አምላክ በሥጋ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት የተወሰነበት ከሃሊነቱ አይደንቅም..?? አይረቅም..? ኢሳይያስ ስለ ነገረ ትሥጉቱ ሲናገር የተወለደው ሕጻና ድንቅ መካር ኀያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ይለዋልና..(ኢሳይያስ 9፥6)  መንክር(ድንቅ) የሚባል ከሕሊናት ሁሉ የሚያልፍ የማይመረመር ሥራ ነው።

የአንጾክያ ሊቀ ጳጳሳት ባስልዮስ ሲናገር "እስመ ኢሳይያስ ነቢይ ክቡር በውስተ ነቢያት ሰመዮ መንክረ መንክርኒ ውእቱ ግብር ዘኢይትረከብ..." 'ከነቢያት መካከል የከበረ ነቢይ ኢሳይያስ መንክር(ድንቅ) ብሎታልና መንክር(ድንቅ) የሚባልም የማይመረመር ሥራ ነው። (ሃይ-አበው ዘባስልዮስ ም 96 ቍጥር 27)

ዓለማትን በእጁ የያዘ አሕዛብ ሁሉ በፊቱ በገንቦ እንዳሉ የውሃ ጠብታ የሆኑለት ሰማይ ዙፋኑ ምድርም መረገጫው የሆነ አምላክ ሥጋ ሆነ አበው እንደ ተናገሩትም <<ወልደቱሂ ኮነ ብርሃነ መድኀኒትነ>> (ልደቱም የደኅንነታችን መታወቂያ ሆነልን) ሃይ-አበው ዘባስልዮስ ምዕ 96 ቍጥር 23)

መልካም ዕለተ ሰንበት 🙏

ጉባኤ ሐዋርያት

13 Oct, 06:12


የአምላክን ሰው መሆን ባሰብን ጊዜ ይህ የማይመረመር ታላቅ ደስታ ለዓለሙ ሁሉ የሚሆን እንደሆነ ቅዱሳት መጽሐፍት ያስተምሩናል ይህ ምክንያተ ፍሰሓ ግን ለሰብአውያን ብቻ ሳይሆን ለዓለመ መላእክትም ጭምር እንደሆነ አክለው ይነግሩናል ይህ ፍጹም ደስታ አምላክ በመወለዱ ያመሰገኑበት (ሉቃስ 2፥13) ሊያዩት የሚመኙት (1ጴጥሮስ 1፥12) ኀጥእ ንሰሐ በገባ ጊዜ የሚደሰቱበት ፍሰሐ ነው (ሉቃስ 15፥10) ። ጌታ መድኀኔ ዓለም ከኀጢአት የሚያድን ዕረፍተ ሥጋ ዕረፍተ ነፍስ ነው።


ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ   ገጽ 292 ክፍል 34 ምዕራፍ 75    ቍጥር 24

እፎኑ ኢንመልእ ፡ ፍሥሓ  እንዘ ፡ ንሬእዮ  ለእግዚእነ  መድኃኔ  ዓለም ተወሊዶ እምድንግል ፡ ቅድስት  ወእሙንቱ ዓዲ ፡ ያብዕሉ፡ ሶበ ይሬእዩ ፡ ፩ደ[አሐደ] ፡ ብእሴ ፡ኃጥኣ ፡ እንዘ ይኔስሕ፡ በከመ ይቤ፡ መድኃኒነ ፡ ኵሎሙ ፡ ቅዱሳን ፡ መንፈሳውያን ይሴብሑ ።

እንዲህ  ከሆነ ፡ የዓለም መድኃኒት ጌታችን ፤ ከንጽሕት  ድንግል ' ተወልዶ ፡ ስናየው እንደምን ደስ  አይለን? ዳግመኛ መድኃኒታችን ክርስቶስ ፡ ቅዱሳን መንፈሳውያን መላእክት ደስ ይላቸዋል ፡ እንዳለ እነርሱ ፡ አንድ ኃጥእ ሰው ንስሐ  ሲገባ ፡ ባዩ ፡ ጊዜ ፡ ደስ ፡ ይላቸዋል


መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🙏

ጉባኤ ሐዋርያት

08 Oct, 08:24


በከመ መሀረ ፊላታዎስ ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ሃይ አበው ምዕራፍ 105 ቍጥር 3 ገጽ 472

ምሥጢረ ፡ ሥላሴ ፡ ይትከፈል ፡ ወኢይትከፈል ፤ ይትከፈሉ ፡ በአካላት ፡ ወበገጻት ፡ ወኢይትከፈሉ በመለኮት ፡ በከመ ፡ መሀሩነ ፡ አበው ንሰግድ ለአብ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አሐተ ፡ ስግደተ..

የሦስትነት ፡ ምሥጢር ፡ ይለያል ፤ አይለይም ፤ በአካላት ፤ በገጻት ፡ ይለያሉ ፤ በመለኮት ፡ ግን ፡ አይለ ዩም ፤ አባቶች ፡ እንደ ፡ አስተማሩን ፡ ለአብ ፡ ለወ ልድ ፡ ለመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አንዲት ፡ ስግደትን ፡ እንሰግዳለን

ጉባኤ ሐዋርያት

06 Oct, 08:20


አብ ከወልድ ፡ ተለይቶ ፡ የኖረበት ፡ ዘመን ፡ የለም ፥ወልድም ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ተለይቶ ፡ የኖረበት ፡ ዘመን ፡ የለም፤ መንፈስ፡ ቅዱስም ፡ ከአብ ፡ ከወልድ፡ ተለይቶ ፡ የኖረበት ፡ ዘመን ፤ የለም ሥሉስ ቅዱስ በዘመኑ ፡ በቀኑ ፡ ሁሉ ፡ በግብርም ፡ በስምም ፡ ሳይለ ወጥ ፡ ሳይፋለስ ፡ ጸንቶ ፡ ያለ  ነው ፡ እንጂ ።

ጥንት ፡ የሌለው ፡ ቀዳማዊ ፡ ልጅ  ያለው ፡ እግዚአብ ሔር ፡ አብ ፡ ብቻ  ነው ፡ ዳግመኛ ፡ እርሱ ፡ ወልድም፡ አይመረመርም ፡ ማንም  መርምሮ አያገኘውም ።

አብ ፡ ከዘመን፡ በኋላ አልወለደውም ፡እርሱ ቀዳማዊ ወልድ፡፡ ከአብ ፡ ጋር ፡ በቅድምና  የነበረ ፡ ነው ፡ እንጂ የማይሞት  ነው ፡ ከማይሞት ፡ ከአብ ፡ ጋር ፡ ፈጣሪ ፡ ነው ፤ እንደ፡ አብም፡ ሁሉን የፈጠረ ' ነው ።

እንዲሁ መንፈስ ፡ ቅዱስም ፡ ከአብ  ከወልድ ፡ ጋር፡ በቅድምና ፡ የነበረ  ቀዳማዊ ፡ ነው ፤ በሥራውም ሁሉ ከአብ ከወልድ፡ ጋር፡ አንድ፡ ነው ።

ጉባኤ ፡ የቆመለት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን፡ የተቀበለችው፡ ሐዋርያት ፡ ያስተማሩት ፡ እውነኛ ትምህርት፡ ይህ፡ ነው ።

ሃይማኖተ አበው ዘሠለስቱ ምዕት ምዕራፍ ፲፱ ገጽ ፶፩  ቍጥር ፮ እስከ ፲

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን።🙏

ጉባኤ ሐዋርያት

29 Sep, 05:55


ዛሬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ለምን ፡ ተውከኝ ፡ ይል ዘንድ ፡ ምን ፡ አተጋው ! እኛስ ፡ ቀድሞ ፡ አዳም ፡ በበደለ ፡ ጊዜ ፣ የተሠራችለትን ፡ ትእዛዝንም ፡ በአፈረሰ ፡ ጊዜ ፤ ከተሠራችለትም ' ሕግ ፡ እርሱ ፡ በተለየ ' ጊዜ ፤ ስለዚህ ፡ ነገር ፡ እግዚአብሔር ፡ የሰውን ፡ ባሕርይ ፡ ከእርሱ ፡ አርቆት ፡ ነበርና ፤ በፍዳም ፡ ተይዞ ፡ ሞትም ፡ ድል ፡ ነሥቶት ፡ ነበርና ፡ ስለዚህ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኛን ፡ ባሕርይ ፡ ወደ አለመለወጥ ' ሊመልሰው ' ወደደ ። ዘፍጥረት 3፥1-19። ሮሜ 15፥14-20
(ሃይማኖቸ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ ገጽ 323 ምዕራፍ 79 ቍጥር 36)

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን።🙏

ጉባኤ ሐዋርያት

27 Sep, 06:39


'እልመስጦአግያ"

...ወበመስቀሉ ኮነ

እልመስጦአግያ የሚለው ቃል በግዕዝ ትምህርተ ኅቡዓት ማለት ነው። ትምህርተ ኅቡዓት በሥጋ ሕሊና የማይመረመረውን ነገረ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ በከሠተበት ልክ የምንማርበት ትምህርት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦“ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።”
(1ቆሮንቶስ 2፥14)
 
መንፈሳዊ ነገር በፈቃደ እግዚአብሔር ካልተገለጠ ዘወትር ኅቡዕ ነው ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ “መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው (1ቆሮንቶስ 2፥10)።” ብሎ እንደ ተናገረው ኅቡዕ የሆነው ነገረ እግዚአብሔር በምንችለው ልክ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ያስተምረናል።

በዚህ በሃይማኖተ አበው በእልመስጦአግያ ክፍል ላይ አበው ስለ ክርስቶስ መስቀል ማተኰር ያለብንን ሀሳብ በዚህ መልክ ያስተመሩናል፦ ተሰቅለ በእንቲአነ ፡ ወበመስቀሉ ፡ ኮነ፡ ሕይወትነ ፡ ጽንዕነ ፡ ቤዛነ።


ትርጓሜውም፦ ስለእኛ ፡ ተሰቀለ ፡ በመስቀሉም ጽናችን ፡ ቤዛችን ፡ ድኅነታችን ፡ ተደረገልን ።  ይኸውም ፥ከእግዚአብሔር ፡ የማትርቅ ፡ መቸም ፡ መች ፡ የማትለይ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ የማትመጠን  የቸርነቱን ፡ ብዛት ፡ በመናገር ፡ የማይፈጸም ፡ ደስታ ፡ ያለበት ፡ ረቂቅ ፡ ምሥጢር ፡ ነው ።

እልመስጦአግያ ምዕራፍ 2 ቍጥር 2

በዚህ ምንባብ ላይ አበው በ1ጴጥሮስ 2፥24 ላይ ያለውን ምንባብ ዋቢ አድርገዋል እንዲህ ይነበባል፦“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”

ጌታችን ኢየሱስ ኀጢአታችንን በመስቀሉ በማስወገዱ የጥልን ግድግዳ በመስቀሉ አፈረሰ ነገረ መስቀሉን ስናስብ እጅግ የሚደንቀን እውነት ይህ ነው።

በዚሁ በእልመስጦአግያ ምዕራፍ 2 ቍጥር 2 ላይ
ዘውእቱ ፡ ምሥጢር ፡ ኅቡዕ ፡ ፍሥሓ፡ ዘኢይትዌዳዕ ፡ በነጊር ፡ በዕበየ ፡ ትሩፋት ፡ ኵሎ ፡ ጊዜ ፡ እንተ ኢትትኌለቍ ፡ ወኢትርኅቅ ፡ እም ፡ እግዚአብሔር ፡ ወትረ ፡ ኢትሴስል ።



ይኸውም ፥ከእግዚአብሔር ፡ የማትርቅ ፡ መቸም ፡ መች ፡ የማትለይ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ የማትመጠን  የቸርነቱን ፡ ብዛት ፡ በመናገር ፡ የማይፈጸም ፡ ደስታ ፡ ያለበት ፡ ረቂቅ ፡ ምሥጢር ፡ ነው ።

ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያይቱ በቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ፦“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።”
(1ኛ ቆሮንቶስ 1፥18)

የመስቀሉ ቃል የተባለው በቍጥር 23 ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን መስበክ እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ይናገራል በዚህ በመስቀሉ ቃል በኩል የዘላለም ሕይወት ድኅነት እና የኀጢአት ሥርየት ሁሉ አለ እግዚአብሔር መዳንን ሁሉ በልጁ በክርስቶስ አዘጋጅቶልናልና።
ስለዚህም ነው ዘውእቱ ምሥጢር ኅቡዕ የተባለው።

መልካም የመስቀል በዐል ይሁንልን።

ጉባኤ ሐዋርያት

22 Sep, 04:47


ወንአምን በእሉ አስማት ዘተጠመቅነ ቦሙ።አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ዘከመ አዘዘነ ቃል ሥግው እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ።

በከበርንባቸው በእሊህ ስሞች በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እንመን ሰው የሆነ ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዘዘን።

ሃይማኖተ አበው ዘባስልዮስ  ምዕራፍ 32

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን።

ጉባኤ ሐዋርያት

20 Sep, 05:49


መንክር ውእቱ ልደትከ ኦ ወልደ እግዚአብሔር ከመዝ። የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ መወለድህ እንዲህ ድንቅ ነው።

የሕጻናት ፈጣሪ-ፈጣሬ ሕጻናት በማኅጸነ ብእሲት አጥንትን የሚያገጣጥም ጅማትን የሚያስማማ ሥጋንም የሚያለብሳቸው በየጥቂቱም የሚያሳድጋቸው አምላክ መፍጠሩን በፈጸመ ጊዜ ጌትነቱን የሚገልጥበት አምላክ ለራሱ በድንግል ማኅጸን ሥጋን ፈጠረ ቅዱስ ኤፍሬም ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ ወእምኔሃ ነሥአ ሥጋነ ዘውእቱ ፈጣሪ እርሱም እናቱን ፈጠረ ከርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ።

መወለዱ እንዲህ ድንቅ ነው! ማሪ ያዕቆብ እንደ ተናገረው ትንንሽ ሕጻናትን የሚፈጠር ይዋሐደው ዘንድ ሥጋን ካንቺ ፈጠረ ሕጻናትን ልጆችን የፈጠረ እርሱ በማኅጸንሽ አደረ

ድንግል ታዝለው እና ታቅፈው ዘንድ በድንግል ማኅጸን ለራሱ ደረትን ፈጠረ በፍዳ ተይዞ ተጎድቶ የነበረ የአዳምን ባሕርይ ገንዘብ አደረገ የሚወደውን ደቀ መዝሙርንም በደረቱ አስጠጋው።


የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነገረ ክርስቶሳዊ መደነቅ ከሰፊ ማብራሪያ ጋር ይቀጥላል።

ጉባኤ ሐዋርያት

16 Sep, 21:36


ቃሌ Vs አክሊል።

ጉባኤ ሐዋርያት

16 Sep, 17:57


https://t.me/Hokhmahstudies?videochat

ሊጀመር ነው ግቡ

ጉባኤ ሐዋርያት

16 Sep, 08:00


ዛሬ ከምሽቱ 3:00 ላይ በወንድም ቃሌ እና አክሊል Sola Scriptura በሚል ርዕስ ውይይት ይኖራል።

ውይይቱን በቲክቶክ ለመከታተል ፦ https://vm.tiktok.com/ZMhRB4WtD/


ውይይቱን በቴሌግራም ለመከታተል።
https://t.me/Hokhmahstudies

ጉባኤ ሐዋርያት

15 Sep, 07:50


ወወልደ አብ ዋሕድ ይሰመይ ብርሃነ.. <<የአብ አንድ ያ ልጅ ብርሃን ይባላል>>

ወወልደ አብ ዋሕድ ይሰመይ ብርሃነ እስመ ብርሃን ዘተወልደ እምብርሃን ኡይትበሀል ተወልደ እምድኅረ ብርሃን አላ በጊዜ ዘኮነ ቦቱ ውእቱ ብርሃን ይትረከብ ብርሃን ዘተወልደ እምኔሁ ወኅልው ወትረ ምስሌሁ ወብርሃንሂ ያጤይቀከ አምሳሊሁ ለወልድ ዘውእቱ ህልው ምስለ አብ በኵሉ ጊዜ እምቅድመ ኵሉ ዓለም። ወንነግረከ ወናሌብወከ ዘንተ ስመ ዘውእቱ ወልድ ከመ ውእቱ አሐዱ ህላዌ ምስለ አብ። አሜን።

የአብ አንድ ልጅ ብርሃን ይባላል ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከብርሃን በኋላ የተገኘ ነው አይባልምና ያ ብርሃን በተገኘ ጊዜ ከርሱ የተወለደው ብርሃን ተገኝቶ ከርሱ ጋር ህልው ሆኖ ዘወትር ይኖራል እንጂ ብርሃንም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር በጊዜው ከአብ ጋር ህልው የሚሆን የወልድን ነገር ያስረዳሃል። ይህንንም ስም ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ እንደሆነ እንነግርሃለን እናስረዳሃለን ይኸውም ወልድ መባል ነው።  አሜን። ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎዶስጦስ ምዕራፍ 53 ቍጥር 10-11 ገጽ 172-173

ነአምን በሥላሴ (በሥላሌ እናምናለን)  መልካም ዕለተ ሰንበት

ጉባኤ ሐዋርያት

11 Sep, 03:47


እስመ ለዓለም ምህረቱ
ምህረቱ ለዘላለም ነውና..(መዝሙር 136)

የብርሃናት አባት የጊዜያት ሁሉ ባለቤት ታላላቅ ብርሃናትን ለጊዜያትና ለዘመናት ያበጃቸው በምህረቱ እና በቸርነቱ ብዛት መሻገርን አድርጎልናል እስመ ለዓለም ምህረቱ ብለን እንናገራለን..

መንገዳችንና ትንፋሻችንን ሁሉ በእጁ የያዘ አምላክ ዐዲሱን ዘመን እንደ ምህረቱ ብዛት ስላሳየን ምስጋና ይገባዋል።

እንኳን ለ2017 ዓም ዐዲስ ዐመት በሰላም አደረሰን።