ቤተ ሊባኖስ ₃ @abalibanos333 Channel on Telegram

ቤተ ሊባኖስ ₃

@abalibanos333


የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮ ና ስርዓት የጠበቁ

👉 መንፈሳዊ መዝሙሮች
👉 መንፈሳዊ ትምህርቶች
👉 መንፈሳዊ ግጥሞች
👉 መንፈሳዊ ታሪኮች
👉 ምንፈሳዊ ምክር ነክ ፁፎች
👉 ንግሶች ስኖሩ እናሳዊቃለን
👉ለመናፍቃለ የተለያዩ መልሶችን እንሰጣለን
ግሩፕን ለመቀላቀል @zemariwochu3

ለተለያየ ጥያቄ ና @DA121922 ካላቹ አናግሩኝ

ቤተ ሊባኖስ ₃ (Amharic)

ቤተ ሊባኖስ ₃ አሳሽነው የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን እችግ መዝሙራትን እና መግለጫዎችን ያሳያል፡፡ በቅናት የዳግም ጥሩ መጽሐፍና በሌሎች የቲብርክ መምሪያዎችም ይጠቀሙበታል፡፡ በማለት ምርጥ መዝሙራትን እና መልክያቸውን እንዲያውቁ በማውረድ ይህን ቦታዎች ትክክለኛ እንዲሆኑ ለመረዳት እንወዳለን፡፡ ከአንዱ ሱማይ መነሻክሽን ስለሚጠቀሙ ላይ ሁኖ የሚገኝበት አገልግሎት ነው፡፡ ለተለያዩ ጥያቄ መልሶችን ከቱም መናፍቃችሁ አሉ፡፡ የቤተ ሊባኖስ ₃ በተመሳሳይ በአልጋሽኛም በሚወድም በመስርት መሳሪያዎች እና በመጣል የሚገባበት ምላሽ ነው፡፡

ቤተ ሊባኖስ ₃

22 Jan, 14:34


💰ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ

አዋ ከሆነ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
                 👇👇

ቤተ ሊባኖስ ₃

22 Jan, 14:24


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜

ቤተ ሊባኖስ ₃

20 Jan, 04:18


❖✟ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮና ስርአትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ከነዜማቸው በየቀኑ ወደናንተ ያቀርባል፡፡ ✟❖

ቤተ ሊባኖስ ₃

18 Jan, 07:54


የከተራና የጥምቀት መዝሙሮችን ለማጥናት 👇👇
🎶 እግዚኡ መርሐ ♡

🎶 ከድንግል ተወልዶ ✞

🎶 በዮርዳኖስ የተጠመቀው ✧

🎶 ዘወይን ዘወይን ✞

🎶 ጥምቀተ ባሕር ♡

🎶 እርሱ ፍጹም ሊልቅ ✞

🎶 ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠመቀ

🎶 ዮሐንስ አጥመቆ ♡

🎶 ዮሐንስኒ_ያጠመቀ ♡

🎶 እንዘስውር ✧

እነዚህን ለማጥናት ከስር Join አድርጉ
    join join join
     Join join join

ቤተ ሊባኖስ ₃

18 Jan, 04:14


https://youtu.be/mJGF4HdnoaY?si=Si3EQqw3x7nHPYz2

ቤተ ሊባኖስ ₃

18 Jan, 03:57


​​ጥምቀት

የሰው ልጅ ሕገ እግዚአብሔርን በመተላለፉና ለኃጢአት ተገዢ በመሆኑ ንጽሕት ነፍሱ አደፈች፤ ረከሰችም፤ በኃጢአቱም ምክንያት ከአምላኩ ተጣላ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ ምድርም በእርሱ የተነሣ ተረገመች፤ እሾህና አሜከላንም አበቀለች፡፡ እርሱም ለብዙ ዘመን አዝኖና በሥቃይ ኖረ፡፡

ቸርነቱ የማይልቅ መሐሪና ይቅር ባይ አምላካችን እግዚአብሔር በኀዘኑ አዝኖና ሥቃዩን ተመልክቶ ለእርሱ፤ ስለ እርሱ መከራና ሥቃይ ይቀበልለት ዘንድ ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሊያድነው በገባለት ቃል መሠረት ተፈጸመ፡፡ ከዚያም በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮርዳኖስን ብርህት ማኅፀን እንድትሆን፣ ምእመናንም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግም ተወልደው መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ  እንደዚሁም ሥርዓተ ጥምቀትን ለማስተማርና አብነት ለመሆን በጥር ዐሥራ አንድ ቀን ተጠምቋልና ይህችን የተከበረች ቀን ሕዝበ ክርስቲያን ያከብር ዘንድ ይገባል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትጠራላችሁ›› ተብሎ አስቀድሞ በተነገረው መሠረት ጌታችን በውኃ ተጠመቀ፡፡ የዚህም ምክንያት ሊቀውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስረዱት ውኃ ለሁሉ አስፈላጊ በመሆኑና ያለ ውኃ መኖር የሚችል ባለመሆኑ  ያለ ጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አይቻልምና ጥምቀትም ለሁሉም የሚገባ ሥርዓት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ውኃ መልክ ያሳያል፤ መልክ ያለመልማል (ያጠራል)፡፡ ጥምቀትም መልክዐ ነፍስን ያሳያል፤ መልክዐ ነፍስን ያለመልማልና (ያጠራልና)፡፡ (ሕዝ.፴፮፥፳፭)

በዘመነ ሥጋዌ ‹‹ጌታችን  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስ  በዮሐንስ  እጅ  ይጠመቅ  ዘንድ  ከገሊላ  ወደ ዮርዳኖስ መጣ›› (ማቴ.፫፥፲፫፣ማር.፩፥፱፣ሉቃ.፫፥፳፩፣ዮሐ.፩፥፴፪)፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ግን አገልጋይ በጌታው እጅ ይጠመቃል እንጂ ጌታ በአገልጋዩ አይጠመቅም፤ ‹‹እኔ በእንተ ልጠመቅ እሻለሁ፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?›› ብሎ አይሆንም አለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ‹‹አሁንስ ተው፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናልና›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ተወው፡ ጌታችን ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆ ሰማይም ተከፈተለት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፤ እነሆም ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው››የሚል ድምጽ ተሰማ፡፡(ማቴ.፫፥፲፫-፲፯)

መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል መውረዱም ምሥጢር አለው፡፡ ርግብ ኃዳጊተ በቀል ናት፤ መንፈስ ቅዱስም ኃዳጌ በቀል ነውና፡፡ ርግብ በኖኅ ጊዜ ‹‹ሐጸ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ፤ የጥፋት ውኀ ጎደለ›› ስትል ቆጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ተገኝታለች፡፡ መንፈስ ቅዱስም ተስፋ መስቀልን ያበሥራልና፡፡

እኛም የሐዲስ ኪዳን ሕዝቦች ይህን ምሥጢር በመረዳት፣ መከራ መስቀሉን በመሸከምና እምነት በመጽናት እንድኖንር አስፈላጊ በመሆኑ ነገረ ድኅነቱን በመረዳት በልደቱ እንደዘከርነው ሁሉ በጥምቀቱም እንዲሁ እናደረግ ዘንድ ይገባል፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀውም በሠላሳ ዓመቱ ነው (ሉቃ. ፫፥፳፫)፡፡ በሠላሳ ዓመቱ የተጠመቀበት ምሥጢርም አዳም የሠላሳ ዓመት፤ ሔዋን የዐሥራ አምስት ዓመት ሰው ሆነው ተፈጥረው አዳም በዐርባ ቀን፣ ሔዋን በሰማንያ ቀን ከሥላሴ የተቀበሉትን ልጅነት በምክረ ከይሲ ዕፀ በለስን በልተው አስወስደው ነበረና በሠላሳ ዓመቱ ተጠምቆ መልሶላቸዋል፡፡ በሠላሳ ዓመት የመጠመቁ ምሥጢር ይህ ሲሆን እኛ ዛሬ ወንዶች በዐርባ ቀን፣ ሴቶች በሰማንያ ቀን በዕለተ ዓርብ ከቀኝ ጎኑ በፈሰሰው ማየ ገቦ ተጠምቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ሁለተኛ የምንወለድበት ምክንያትም አዳም በዐርባ ቀኑ፣ ሔዋን በሰማንያ ቀኗ ከሥላሴ ያገኙትን ልጅነት መሠረት በማድረግ ነው /ኩፋ. ፬፥፱/፡፡ የምንጠመቀውም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፡፡  ‹‹ወእንዘ ታጠምቅመው በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ስታጠምቋቸውም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው፤›› እንዲል(ማቴ. ፳፰፥፲፱)፡፡

በአሁኑ ጊዜም ታቦታቱን ወደ ጥምቀተ ባሕር በማውረድ በዓለ ጥምቀቱን ለሚያከብሩ ክርስቲያኖች በሙሉ ከታቦታቱ ሁለት ሺህ ክንድ ርቀው መከተል እንዲገባቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፤ ‹‹ሕዝቡን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሠፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት፡፡ በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት በስፍር ሁለት ሺህ ክንድ ይሁን፡፡ በዚህ መንገድ በፊት አልሄዳችሁበትና፤ የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አቅርቡ፡፡›› (ኢያ.፫፥፩-፲፯)

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀትም ከተጠመቀበት ከ፴ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በየዓመቱ ጥር ፲፩ ቀን ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሲከበር ይኖራል፡፡

ከበዓለ ጥምቀቱ ረድኤት፣ በረከት ይክፈለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

17 Jan, 19:49


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

ቤተ ሊባኖስ ₃

16 Jan, 19:11


አንድ ቀን የአንድ ገበሬ አህያ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀች። እና እንስሳዉ ለሰዓታት ጮክ ብላ እያለቀሰች ነበር። ገበሬዉ አህያዋን ለማውጣት ቢጥርም አልቻለም።

በመጨረሻም ገበሬው አህያው አርጅታለች እናም ጉድጓዱ ደርቋል ስለዚህ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት ጉድጓዱ መሸፈን ያስፈልገዋል ብሎ ወሰነ።

አህያውን ከጉድጓዱ ውስጥ ለማውጣት ሳያስብ ጎረቤቶቹን በጠቅላላ ኑና እርዱኝ ብሎ ጠራቸው። እያንዳንዳቸውም አካፋ ያዙና ቆሻሻ ወደ ጕድጓዱ ይጥሉ ጀመር።

አህያው እየሆነ ያለውን አውቃ በአሰቃቂ ሁኔታ አለቀሰች። ከዚያም ሁሉም ሰው የተወሰኑ ቆሻሻዎች ከጣሉ በኋላ ገበሬው በስተመጨረሻ ወደ ጉድጓዱ ተመለከተና ባየው ነገር ተገረመ። በእያንዳንዱ የቆሻሻ ክምር አህያዋ የሚገርም ነገር እየሰራች ነው። በአካፋው የሚጣልባትን በጠቅላላ እየረገጠች ከቆሻሻው አናት ላይ እየቆመች ነበር። በዚህም ወደላይ ከፍ እያለች ነበር። ይህን የተመለከቱት ሁሉም ሰዎች አህያዋ ከጉድጓዱ አፋፍ ላይ እንዴት እንደደረሰች በማየት ተደነቁ።

ህይወት ቆሻሻ ልትደፋባችሁ ነው። እና ሁሉም አይነት ቆሻሻ ከጉድጓዱ የመውጣት ዘዴ ነው። እያንዳንዳችን ችግሮቻችን መወጣጫ ደረጃዎች ይሆኑናል። ተስፋ ካልቆረጥን ብቻ ከጥልቁ ጉድጓድ መውጣት እንችላለን። እናም ህይወትም ሆነ ሌሎች ሰዎች የሚጥሉባችሁን እያንዳንዱን ቆሻሻ እናንተን ከመቅበሩ በፊት ቀድማችሁ ቅበሩት እላችኋለሁ!።


ይህን 5ት ህጎች ሁሌም አስታውሱ፦

1.ልባችሁን ከጥላቻ ነፃ አርጉ

2.አእምሮአችሁን ከሚያዘናጋና ከሚረብሽ ነገር ነጻ ይሁን

3.የሚያጋጥማችሁን ነገሮች ቀለል አድርጋችሁ ተመልከቱት

4.ብዙ ስጡ ትንሽ ጠብቁ

5.አብዝታችሁ ውደዱና ቆሻሻውን አራግፉ። ምክንያቱም በዚህ ህይወት ውስጥ "ችግር" መቀበርያ ሳይሆን መወጣጫ መፍትሔ ነው!።
#ለኔ ና ለእናተ ምክር ነክ ፁሑፍ

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

13 Jan, 19:40


ዘንድሮ ከተራ ቅዳሜ ነው የሚውለው ፤ ጥምቀት ደሞ ገሀድ ጾም አለው

ጥያቄ ዘንድሮ እንዴት ነው ገሀድ ሚጾመው?

መልሳችሁን በ comments ላይ ይላኩ ዋና ምላሹን ነገ ይዘን እንመጣለን 🙏

ቤተ ሊባኖስ ₃

11 Jan, 04:57


የከተራና የጥምቀት መዝሙሮችን ለማጥናት 👇👇
🎶 እግዚኡ መርሐ ♡

🎶 ከድንግል ተወልዶ ✞

🎶 በዮርዳኖስ የተጠመቀው ✧

🎶 ዘወይን ዘወይን ✞

🎶 ጥምቀተ ባሕር ♡

🎶 እርሱ ፍጹም ሊልቅ ✞

🎶 ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠመቀ

🎶 ዮሐንስ አጥመቆ ♡

🎶 ዮሐንስኒ_ያጠመቀ ♡

🎶 እንዘስውር ✧

እነዚህን ለማጥናት ከስር Join አድርጉ
    join join join
     Join join join

ቤተ ሊባኖስ ₃

10 Jan, 20:14


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

ቤተ ሊባኖስ ₃

10 Jan, 20:05


🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️

         

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Jan, 20:43


​​ በጥር ወር የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት


ሐሙስ ጥር 1 -ቅዱስ እስጢፋኖስ - ልደቱ እና እረፍቱ

ቅዳሜ ጥር 3 -አባ ሊባኖስ - በዓለ እረፍታቸው
በእንጦጦ ኪዳነ ምህረት እና በጣፎ ገብርኤል

እሁድ ጥር 4 -ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ - የተሰወረበት መታሰቢያ እለት

ሰኞ ጥር 5 -አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ - በዓለ ልደታቸው ከታህሳስ 29 ወደ ጥር 5 የተዘዋወረ

ማክሰኞ ጥር 6 -ኢየሱስ - ግዝረቱ  - በገዳመ ኢየሱስ እና በፈርንሳይ ገነተ ኢየሱስ
በለገዳዲ መንበረ ኢየሱስ
            - ነብዩ ኤልያስ - በእሳት ሰረገላ ያረገበት
            -  ቅድስት አርሴማ - በዓለ ልደቷ

እሮብ ጥር 7 -ቅድስት ሥላሴ - የባቢሎን ግንብ ያፈረሱበት መታሰቢያ እለት

ቅዳሜ ጥር 10 - ከተራ

እሁድ ጥር 11 - በዓለ ጥምቀት

ሰኞ ጥር 12 - ቅዱስ ሚካኤል - ቃና ዘገሊላ

ማክሰኞ ጥር 13 - ቅዱስ እግዚአብሔር አብ

                     - ቅዱስ ሩፋኤል

እሮብ ጥር 14 - አቡነ አረጋዊ - ልደታቸው

ሐሙስ ጥር 15 - ቅዱስ ቂርቆስ - እረፍቱ

አርብ ጥር 16 - ቅድስት ኢየሉጣ - እረፍቷ

እሁድ ጥር 18 - ቅዱስ ጊዮርጊስ - ስባረ አፅሙ

እሮብ ጥር 21 - እመቤታችን -እረፍቷ በዓለ አስተርእዮ

ሐሙስ ጥር 22 - ቅዱስ ዑራኤል - በዓለ ሲመቱ

ቅዳሜ ጥር 24 - አቡነ ተክለሃይማኖት -በፀሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት (የተነሳበት) መታሰቢያ እለት

እሁድ ጥር 25 - ቅዱስ መርቆርዮስ - በስዕሉ ላይ አድሮ ታምር የሰራበት - በጎፋ መብራት ሀይል

ሰኞ ጥር 26 - አቡነ ሃብተ ማርያም - ቅዳሴ ቤት- አስኮ ቃሉ ተራራ

ማክሰኞ ጥር 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም - ቅዳሴ ቤት - በአለም ባንክ ጀሞ ተራራ መድኃኔዓለም
      -በ ቀበና መድኃኔዓለም

እሮብ ጥር 28 - ቅዱስ አማኑኤል - 2 አሳ እና 5 እንጀራ አበርክቶ የመገበበት መታሰቢያ እለት

አርብ ጥር 30 - ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ - ቅዳሴ ቤት - በቤላ በጣፎ እና በምንጃር ሸንኮራ ዮሐንስ

ቸር ያገናኘን አሜን !!!

https://t.me/zemariwochu3

👉 @DA121922

ቤተ ሊባኖስ ₃

03 Jan, 18:01


💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

ቤተ ሊባኖስ ₃

03 Jan, 17:46


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

ቤተ ሊባኖስ ₃

02 Jan, 15:29


የስልክ ቁጥሮን የመጨረሻ ቁጥር በመምረጥ እድሎን ይሞክሩ 🤩

ቤተ ሊባኖስ ₃

02 Jan, 15:08


🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️

⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

ቤተ ሊባኖስ ₃

01 Jan, 18:58


✅️አንድ ወጣት ስራ ለመቀጠር ፈለገ በድርጅቱ ውስጥም ትልቅ ቦታ ለማግኘት ወደ አንድ ድርጅት አቀና ።

✔️ወጣቱ ቃለ መጠይቁን በጥሩ ሁኔታ አለፈ ።ለመጨረሻ ቃለ መጠይቅ ለማድረግም ከዳይሬክተሩ ጋር ተገናኘ። ዳይሬክተሩ የመጨረሻውን መጠይቅ ካረገለት በኋላ ...

የወጣቱን የትምህርት፣ችሎታ የሚያሳየውም ሰነድ (ሲቪ)አገላብጦ ካየ በኋላ በጣም ጥሩ መሆኑን ገለፀ።

✔️ ዳይሬክተሩ:- ከአሁን በፊት የተሻለ የትምህርት እድል አግኝተሃል ሲል ጠየቀው ?

ልጁም:-  "አይ" ሲሳ መለሰ
ትምህርትህን እንድትከታተል እና የትምህርት ቤት ክፍያዎችን ከፍሎ ያስተማረህ አባትህ ነው?
'ወጣቱ :-  አዎ.' ብሎ መለሰ።
ዳይሬክተሩ :- አባትህ ምንድነው  የሚሰራው?
ወጣቱ:- አባቴ አንጥረኛ ነው"

✔️ ዳይሬክተሩ:-  ወጣቱ እጆቹን እንዲያሳየው ጠየቀው።
ወጣቱ :-  ለስላሳ እና ፍጹም የሆነ እጆቹን አሳየው

ዳይሬክተሩ:- ወላጅ አባትህን በሥራ ረድተሃቸው ታውቃለህ? ወጣቱ:- በጭራሽ፣ ወላጅ አባቴ  መጻሕፍቶችን እንዳነብና እንዳጠና ነበር ፍላጎቱ ። እና ደግሞ ከኔ በተሻለ ሁኔታ ስራውን መስራት ይችላል።

ዳይሬክተሩ እንዲህ አለ፡-

ለዛሬ ወደ ቤትህ ትመለሳለህ እቤት እንደደረስክም የአባትህን እጅ በደንብ አርገህ ታጥብና ነገ ጥዋት ተመልሰህ አግኘኝ  ብሎ ቀጠሮ ያዘለት ።

ጣቱ ስራውን የማግኘት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ተሰማው።
ወደ ቤቱ እንደተመለሰም የአባቱን እጅ እንዲያጥብለት አባቱን ፍቃድ ጠየቀው
?

አባቱ በልጁ እንግዳ ተግባር ተገረመ ደስም አለው , ነገር ግን የደስታ ስሜቱ  የተደባለቀ ነበር።
ከዚያም እጆቹን ለልጁ አሳየው. ወጣቱ ቀስ እያለየአባቱን እጆች አጠበ። ይህን ጊዜ የአባቱ እጆች የተሰነጣጠቁ እና በጣም ብዙ ጠባሳ እንዳለባቸው አየ ። ይህን ያስተዋለው ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር።

በአባቱ እጆች ላይ አንዳንድ ቁስሎቹ ነበሩ ፣እነዚህ ቁስሎች በጣም ያሙት ስለነበር ቆዳውን ሲነካቸው ያመው ነበር ።

ወጣቱ እነዚህ  እጆች የእርሱ ትምህርት ገንዘብ ለመክፈል በየቀኑ መሥራት ምን ማለት እንደሆነ ሲያውቅም ይህ የመጀመሪያው  ነው።

የአባቱ እጆች ላይ ያሉት እብጠቶች አባቱ ለእርሱ ትምህርት መሰረታዊ፣ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ለወደፊት ህይወቱ የከፈለው ዋጋ ነው!!!

ወጣቱ የአባቱን እጅ ካጸዳ በኋላ ለጠቂት ያክል በዝምታ ቆመ ።ከዚያም የአባቱን የስራ መስሪያ ቁሳቁሶች ማፅዳት ጀመረ። በዚያ ምሽት ላይ አባትና ልጅ ለረጅም ሰዓታት ተነጋገሩ፣ አብዛኛውን የምሽቱን ክፍለ ጊዜ በጨዋታ እና በውግ አሳለፉ ።

በማግስቱ ጠዋት ወጣቱ ወደ ዳይሬክተሩ ቢሮ ሄደ።
ዳይሬክተሩ የወጣቱ አይን እንባ ሲያቀር አስተዋለ ።

ዳይሬክተሩ:- ትናንት ቤትህ ውስጥ ያደረግከውን ሁሉ ልትነግረኝ ትችላለህ?
ልጁም 'የአባቴን እጅ አጥቤ ስጨርስ የአባቴን የስራ መገልገያ( አውደ ጥበቡን )አጸዳሁ' ሲል መለሰ።

ዳይሬክተሩ :- ከዚህ ምን ተማርክ ?
ወጣቱ :- ወላጆቼ ባይኖሩ ኖሮ ዛሬ ላይ እኔ
[እኔ እንደማልሆን]  ተረዳሁ ።በዚህም አባቴን በመርዳት አንድ ነገር በራሴ ማድረግ ምን ያህል ከባድ እና ከባድ እንደሆነ አሁን ተገነዘብኩ። ቤተሰቤን የመርዳትን አስፈላጊነት እና ጥቅም ተገነዘብኩ አለ ።

ዳይሬክተሩም "በድርጅቴ የምቀጥረው እና በድርጅቴ ውስጥ እንዲኖር የምፈልገው ይህንን ነው,።እርሱ የሌሎችን እርዳታ የሚያደንቅ፣በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ለእኛ ሲሉ ብቻ የእነሱ ያልሆኑ ሌሎች ነገሮችን ለማከናወን ሲሉ የሚደርስባቸውን ችግር እና ስቃይ የሚያውቅ ሰው መቅጠር እፈልጋለሁ አለ ።


ሁላችንም የራሳችንን ሸክም መሸከም ስንጀምር ለወላጆቻችን ልፋት ዋጋ መስጠት እንጀምራለን

✔️ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ በርህራሄ እንዳሳደጉኝ ሁሉ ምህረትን ስጣቸው በል

ወላጆችን  ሁለቱንም ውደዱ። "ለእናንተ ጉልበታቸውን አጥተዋል።


ለእኔ ና ለእናተ ምክር ነክ ፁሑፍ

ቤተ ሊባኖስ ₃

01 Jan, 18:23


የመዳን ትምህርት
(ነገረ ድኅነት) ክፍል ~ 4

አሁን እንዴት እንድናለን?

፫. ሥጋውን መብላት ደሙን መጠጣት

ሰው ካመነ ከተጠመቀ በኋላ ማድረግ ያለበት ቅዱስ ሥጋውን መብላት፣ ክቡር ደሙን መጠጣት ነው፡፡ ሥጋ ወደሙ ሕይወት የሚገኝበት የእምነት እና የጥምቀት ማተሚያ መደምደሚያ ነው፡፡ እምነት መሠረት፤ ጥምቀት መሰረት የሚጸናበት ከእግዚአብሔር የምንወለድበት፤ ሥጋው እና ደሙ ማረጋገጫ ነው፡፡ ያመነ በጥምቀት ይወለዳል፤ የተወለደ ደግሞ የሚያድግበት ምግብ ያስፈልገዋል፡፡ ምግቡም ሥጋውና ደሙ ነው፡፡ ይህን በልቶ ጠጥቶ የሚኖር የእግዚአብሔር ልጅ፣ የእግዚአብሔር የመንግሥቱ ወራሽ፣ የስሙ ቀዳሽ ይኾናል፡፡

“የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና … የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ፤ ለዓለም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና …” ተብሎ እንደ ተጻፈ (ዮሐ. ፮፥፳፯-፶፬፤ ሮሜ. ፭፥፱፤ ኤፌ. ፩፥፯፤ ፩ኛ ዮሐ. ፩፥፯)፡፡ ስለዚህ አምነን ተጠምቀን ሥርየት የተገኘበትን እና የሚገኝበትን ሥጋውን መብላት ያፈልጋል፡፡ በሃይማኖት ከብረን፣ በጥምቀት ተወልደን፣ በሥጋው በደሙ ታትመን ድኅነትን ገንዘብ እናደርጋለን፡፡

፬. መልካም መሥራት (ዐቂበ ሕግ)

ያመነ፣ የተጠመቀ፣ ሥጋውን የበላ፣ ደሙን የጠጣ ዂሉ በመልካም ሥራ መኖር አለበት፡፡ መልካም ሥራ የሌለው እምነት፣ ጥምቀት፣ ቊርባን ብቻውን አያድንም፤ ያመነ የተጠመቀ ሰው ፈጣሪውን በሃይማኖት መከተል በግብር መምሰል አለበት፡፡ “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፤” (ማቴ. ፭፥፲፮)፡፡ የሰው ልጅ ከላይ የተዘረዘሩ ተግባራትን ከፈጸመ እንንደየሥራው መጠን ዋጋውን እንደሚቀበል ቅዱሳት መጽሐፍት ምስክሮች ናቸው፡፡ “እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱ እንደየሥራው መጠን እከፍለው ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር ነው፤” (ራእ. ፳፪፥፲፪፤ ያዕ. ፪፥፳፮)፡፡

አምላካችን ለፍርድ ሲመጣ የሚጠይቀው ሃይማኖት ብቻ ሳይኾን ሥራ መኾኑን መዘንጋት ሞኝነት ነው፡፡ “… ብራብ አላበላችሁኝም፤ ብጠማ አላጠጣችሁኝም፤ ብታረዝ አላለበሳችሁኝም …” እንዳለ ጌታችን (ማቴ. ፳፭፥፴፭-፵፭)፡፡ ስለዚህ ለድኅነቱ ተግባር አስፈላጊ ነው፡፡ ከተግባር ጋር ዐቂበ ሕግ (ሕግ መጠበቅ) ተገቢ ነው፡፡ “የዘለዓለም ሕይወትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?” ብሎ ለጠየቀው ጐልማሳ ጌታችን የሰጠው ምላሽም “… ትእዛዛትን ጠብቅ” የሚል ነው (ማቴ. ፲፱፥፲፮-፲፯)፡፡ የዘለዓለም ሕይወትን ለመውረስ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚቀበለው መልካም ሥራ ወሳኝ ጉዳይ ነውና፡፡

፭. መጽናት

ለመዳን ከማመን፣ ከመጠመቅ፣ ሥጋውን ከመብላት፣ ደሙን ከመጠጣት በተጨማሪ በዚሁ ጸንቶ መኖር ያስፈልጋል፡፡ ገብተው የወጡ፤ አምነው የካዱ ዂሉ ድኅነት የላቸውም፡፡ “በዂሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትኾናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል፤” (ማቴ. ፲፥፳፪፤ ፳፬፥፲፫፤ ማር. ፲፫፥፲፫)፡፡ “እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትን ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን … የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ የክርስቶስ ተካፋዮች ኾነናል …” (ዕብ. ፫፥፮-፲፬)፡፡ “እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ኹን፤ የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ፤” (ራእ. ፪፥፲)፡፡

“ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻ ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልኩ በአሕዛብ ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ፡፡ በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላ ይቀጠቅጣቸዋል፤” (ራእ. ፪፥፳፮)፡፡ የሰው ልጅ የሚድነው በእምነት፣ በጥምቀት፣ በሥጋው በደሙ፣ በመልካም ሥራ ጸንቶ ሲኖር ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ጸንተን እንድኖር እና መንግሥቱን እድንወርስ፤ ስሙን እንድንቀድስ አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን፡፡ እንግዲህ ዂላችሁም ወደ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመመለስ (በመምጣት) ድኅነታችሁን በመፈጸም የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የተዘጋጃችሁ ኹኑ መልእክታችን ነው፡፡

የመጨረሻዉ ክፍል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤

ቤተ ሊባኖስ ₃

30 Dec, 07:03


የመዳን ትምህርት
(ነገረ ድኅነት) ክፍል ~ 3

ክርስቶስ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ሞት ኃይሉን አጥቷል፤ ከዚያ በፊት ሞት ሰውን ዂሉ ወደ ሲኦል ወደ ሁለተኛ ሞት የሚያጓጉዝ ነበር፤ አሁን ግን ሰውን ወደ ሕይወት የሚያደርስ ነው፡፡ ሞት ወደ ገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት የምንጓዝበት መንገድ ኾኗል፡፡ ሰዎች የሚፈሩት ሳይኾን የሚፈልጉት ኾኗል፤ ወደ እግዚአብሔር የምንሔድበት ስለ ኾነ፡፡ ከአዳም ጀምሮ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ድረስ የበደሉትም ያልበደሉትም በመስቀል ላይ በተከፈለው ዋጋ ድነዋል፡፡ ጌታችን ይህን ድኅነት የሚናገሩ፣ የምሥራቹን የሚያወሩ፣ ላለፈው ይቅርታ መደረጉን፣ ለሚመጣው ሕግ መሠራቱን የሚመሰክሩ ሐዋርያትን መርጦ ሾመ፡፡ ለወደፊቱ ለሚመጣው ትውልድ ድኅነት እንደሚገኝ ለማስተማር በዓለም ዂሉ ላካቸው፤ በቃላቸውም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር (ሐዋ. ፪፥፵፯)፡፡

አሁን እንዴት እንድናለን?

የታመሙት ድነዋል፤ ሲኦል የነበሩት ወጥተዋል፡፡ እኛስ ድነናል ወይስ እንድናለን? እኛማ እንድናለን፡፡ ካሣው ለዂሉም ተከፍሏል፤ አምላካችን የሞቱትን አድኗልና፡፡ በሕይወተ ሥጋ ያለን እኛ ግን ድኅነቱን ተቀብለን በሃይማኖት (በእምነት)፣ በጥምቀት፣ ቅዱስ ሥጋውን በመብላት፣ ክቡር ደሙን በመጠጣት የተሠራውን ሕግ በመጠበቅ ድኅነትን እናገኛለን፡፡ ድነናል ብለን የምናወራ ከኾነ ሕግ ለምን አስፈለገን? በገነት ለሚኖሩት ከሲኦል ለወጡት ሕግ አያስፈልጋቸውም፡፡ በተጻፈ ሕግ አይመሩም፤ እኛ ግን በተጻፈ ሕግ ከኦሪት ወደ ወንጌል የተሸጋገርነው የምንጠብቀው እና የሚጠብቀን የሚያድነን ሕግ ተሠርቶልናል፡፡

በዚህ እንድናለን፤ በሕጉ ካልኖርን ደግሞ እንቀጣለን፡፡ ከዚህ ላይ ‹‹የሚድኑትን›› የሚለውን ቃል ልብ ማለት ያሻል፡፡ ‹‹የዳኑትን›› አይደለም ያለው፤ ‹‹የሚድኑትን›› አለ እንጂ፡፡ ስለዚህ ክርስትና ወይም ሕገ ወንጌል የዳኑትን ለማዳን የተሰጠ ሕግ ሳይኾን ያልዳኑት እንዲድኑ የተሰጠ ሕግ ነው፡፡ የኦሪት ሕግ (የኦሪት መሥዋዕት) ማዳን የሚችል አልነበረም፤ ወንጌል ግን ለዓለም ድኅነት የተሰጠ ሕግ ነው፡፡ ሐዋርያት ዓለም እንዲድን የሕይወትን ወንጌል ይዘው ዞሩ፤ አስተማሩ፡፡ ወንጌል የተሰበከው ለዳኑት ሳይኾን ለሚድኑት ነው፡፡ ስለዚህ ለመዳን ምን ያስፈልጋል? የሰው ልጅ ለመዳን የሚስፈልጉት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፤

፩ኛ ማመን
የሰው ልጅ፣ ከዂሉ አስቀድሞ የዓለም መደኀኒት ክርስቶስ ሕግን እንደ ሠራለት አምኖ መመለስ ያስፈልገዋል፡፡ “ለሰው ዂሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም (ወደ ሰው) የመጣው ነው፡፡ በዓለም ነበረ፤ ዓለሙም በእርሱ ኾነ፤ ዓለሙ ግን አላወቀውም፡፡ ወደ ወገኖቹ መጣ፤ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፡፡ ለተቀበሉት ዂሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ከእግዚእሔር ተወለዱ …፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ (ዮሐ. ፩፥፱)፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ድኅነት ለተቀበሉትም ላልተቀበሉትም የተደረገ፤ ላመኑትም ላላመኑት የተፈጸመ ድኅነት ነው፡፡ አሁን ግን ላመኑ እንጂ ላላመኑ የሚሰጥ ድኅነት የለም፡፡

፪. መጠመቅ

“ያመነ የተጠመቀ ይድናል” (ማር. ፲፮፥፲፮) ተብሎ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረው ለመዳን እምነት ያስፈልጋል፤ ከእምነት ቀጥሎ መጠመቅ ያሻል፤ ይህን ካሣ ተፈጽሞ የተሠራውን ሕግ መፈጸም ግዴታ ነው፡፡ ለመዳን ማመን ብቻ አይበቃም፡፡ እምነትማ አጋንንትም አላቸው፡፡ ዕለት ዕለት የሚድኑበት፣ የሚጨመሩበት መንገዱ እምነትና ጥምቀት ነው፡፡ የቅዱሳን ሐዋርያት ተግባርም ይህ ነበር፡፡ ሕይወትን ድኅነትን መስበክ፤ ያመነውን ማጥመቅ፤ የድኅነቱ ተሳታፊ ማድረግ ወደ ድኅነቱ ማስገባት፤ የሕይወትን ቃል ለዂሉ መመስከር ነው፡፡ ዓላማው ለማሳመን፣ ለማጥመቅ፣ ለማዳን ነው፡፡ ለመዳን አምኖ መጠመቅ የግድ አስፈላጊ መኾኑን በሐዋርያት ሥራ የተመዘገበው የጃንደረባው ታሪክ ያስረዳናል (ሐዋ. ፰፥፴፭-፴፯)፡፡

ማመን ብቻውን ስለማያድን ጃንደረባው ‹‹አምናለሁ›› ብሎ ከማመን አልፎ ሃይማኖቱን መስክሯል፤ ፊልጶስም ‹‹ድነሃል፤ ሒድ›› አላለውም፤ አጠመቀው እንጂ፡፡ ስለዚህ ከእምነት ቀጥሎ መጠመቅ ለድኅነት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ዓለምን ለማዳን የመጣው አምላካችን ሐዋርያትን ወደ ዓለም ዂሉ የላከው (ማቴ. ፳፰፥፲፱)፡፡ ተልዕኮውም በቃ ‹‹አድኛቸዋለሁ›› አይደለም፤ እንዲያምኑ፣ እንዲጠመቁ፣ ትእዛዙን እንዲጠብቁ፣ ደቀ መዛሙርት እንዲኾኑ ነው፡፡ ድኅነት የሚገኘው በዚህ መንገድ ነው፡፡ በማውራት ብቻ ‹‹ድኛለሁ›› ብሎ ተዘልሎ በመቀመጥ አይደለም፡፡ “… እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፤ የሕይወትንም መንገድ ያስተምሯችኋል …” ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሐዋ. ፮፥፲፯)፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት የመዳንን መንገድ የሚነግሩን እንድናየው አይደለም፤ እንድንጓዝበት ነው እንጂ፡፡ “… ‹ጌቶቼ፥ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፤ አንተ እና ቤተሰቦችህ ትድናላችሁ› አሉት፡፡ የእግዚአብሔርንም ቃል ለእርሱና በቤቱ ላሉት ዂሉ ነገሩአቸው … በዚያው ጊዜ ከቤተ ሰቡ ዂሉ ጋር ተጠመቀ፤” (ሐዋ. ፲፮፥፴-፴፬)፡፡ ከዚህ ላይ ‹‹ድናችኋል›› ሳይኾን ‹‹ትድናላችሁ›› የሚለውን ቃል ልብ ይሏል፡፡ “ዳግመኛ ከውኃ እና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” እንዳለ (ዮሐ. ፫፥፭)፡፡ ስለዚህ ሰው አምኖ ይጠመቃል፤ ከእግዚአብሔርም ይወለዳል፤ በዚህ ድኅነትን ገንዘብ ያደርጋል፡፡ ከእግዚአብሔር ካልተወለደ በፍጹም ሊድን አይችልም፡፡ መዳን ማለት የእግዚአብሔርን መንግሥት ወርሶ ስሙን ቀድሶ መኖር ነው፡፡ ስለዚህ የሕይወት እና የድኅነት ወንጌል ለዓለሙ ዂሉ ይሰበካል፤ ዂሉም ይድን ዘንድ (ማር. ፲፮፥፰)፡፡

ክፍል 4 ይቀጥላል

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

29 Dec, 02:01


የመዳን ትምህርት
(ነገረ ድኅነት) ክፍል ~ 2

የሰው ልጅ ትእዛዘ እግዚአብሔርን በማፍረሱ ከእግዚአብሔር ተለየ፤ በዲያብሎስ ቁራኝነት ተይዞ በዲያብሎስ ክፋት ተመርዞ አምስት ሺ ከአምስት መቶ ዘመናትን ኖረ፡፡ ከሰው ልጅ ውድቀት ጀምሮ የሰው ልጅ ፍላጎት ድኅነትን ማግኘት ነበር፡፡ የሰው ልጅ የመዳን ተስፋውን ከፈጣሪው ተቀብሎ በተስፋ ኖረ፡፡ የሰው መዳን የእግዚአብሔር ማዳን በሰጠው ተስፋ መሠረት በነቢያት ትንቢት ተነገረ፤ ሱባዔ ተቈጠረ፡፡ ከዚህ ከደረሰበት መከራ ፍጡር ሊያድነው አይችልምና በእሩቅ ብእሲ (በሰው) ደም ነጻ ሊወጣ አልተቻለውም፡፡ የሰው ልጅ ባቀረበው መሥዋዕት፣ ባደረሰው ጸሎት የነበረበትን ዕዳ መሠረዝ ተሳነው፡፡ ነቢያት፣ ካህናት ለዘመናት የበሬ፣ የላም፣ የበግ መሥዋዕት የፍየል፤ የእኽል፤ የዋኖስ እና የርግብ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ስብ አጤሱ፤ የእንስሳትን ደም አፈሰሱ፤ ሰውን ግን ማዳን አልተቻላቸውም፡፡ ‹‹ጽድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ኾነ›› እንዳለ ነቢዩ ኢሳይያስ (ኢሳ. ፷፬፥፮)፡፡

ለአዳም በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ድኅነት የናፈቀውን፤ መከራ ያስጨነቀውን የሰውን ልጅ ያድነው ዘንድ ነቢያት በተናገሩት ትንቢት፣ በቈጠሩት ሱባዔ፣ እግዚአብሔር አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ ድኅነት ርቆት፣ መከራ በዝቶበት መዳን ሲፈልግ ከነበረው ሥጋ ጋር ወሀቤ ሕይወት (ሕይወት ሰጭ) አዳኝ ይኾነው ዘንድ መለኮት ተዋሐደ፡፡ ድኅነትን አጥቶ ሲሰቃይ ለነበረው የሰው ልጅ ፈጣሪ የተዘጋ ርስቱን (ገነትን)፣ የተቀማ ልጅነቱን፣ ያጣውን አንድነቱን መለሰለት፡፡ ስለዚህም የምሥራች ተነገረ፤ ድኅነት ተበሠረ፡፡ በዚህም የሰው ልጅ ተጠቀመ፤ የነቢያት ትንቢትም ተፈጸመ፡፡

ሰው የዳነው ከምንድን ነው?

፩. ከበደለው በደል (ጥንተ አብሶ)

የሰው ልጅ በአምላክ ሰው መኾን የበደሉትንም ያልበደሉትንም ያስቀጣ ከነበረው በደል ነጻ ኾኗል፡፡ አሁን ማንም ሰው በአዳም በደል አይጠየቅም፡፡ በራሱ ፈቃድ ሕግ ጥሶ፣ ትእዛዝ አፍርሶ የተከፈለለትን ዋጋ መጠቀም ባለ መቻሉ ይቀጣል እንጂ፡፡ “ከባላጋራችን የተነሣ በትእዛዝ የተጻፈዉን የዕዳችንን ደብዳቤ ደመሰሰልን፤ ከመካከላችንም አራቀው፤ በመስቀሉም ቸነከረው፤” (ቈላ. ፪፥፲፬፤ ራእ. ፩፥፭)፡፡ ለነበረብን በደል ይቅርታ አድርጎ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቈርሶ ይቅርታ ሰጠን፡፡ ባሮች ነበርን፤ ልጆቹ አደረገን፡፡ የነቢያት ጩኸት ይህን የተመለከተ ነበር፤ “… የቀደመ በደላችንን አታስብብን፤ አቤቱ፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፤ እጅግ ተቸግረናልና፤” የሚል (መዝ. ፸፰፥፰)፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ጩኸቱን አይቶ ልመናውን ሰምቶ በደሉን አስወግዶለታል፡፡

፪. ከዘለዓለም ሞት (ፈርሶ በስብሶ ከመቅረት፣ ከሞተ ነፍስ)

ሞት ማለት አንደኛ የነፍስና የሥጋ መለያየት ነው፤ የነፍስና የሥጋ መለያየት በትንሣኤ አንድ ኾነው እንደሚነሡ ክርስቶስ በሥጋ ወደ መቃብር፣ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ በሲኦል የነበሩትን ከሞተ ነፍስ ከመከራ ነጻ አወጣ፤ ሙስና መቃብርን አጠፋ፡፡ ለሰው ልጅ፣ ከሞት በኋላ ሕይወት፣ ከመቃብር ባሻገር ትንሣኤ መኖሩን አሳየ፡፡ “ሞት ሆይ፥ እንግዲህ መውጊያህ ወዴት አለ? መቃብር ሆይ፥ አሸናፊነትህ ወዴት አለ?” እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ (፩ኛ ቆሮ. ፲፭፥፶፭)፡፡ “ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፤ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤” (ሆሴ. ፲፫፥፲፬) ተብሎ የተነገረው የነቢዩ ቃል ይፈጽም ዘንድ የሰው ልጅ ከሞት (ከዲያብሎስ) ባርነት ከሲኦል ግዛት ድኗል፡፡ “ከጨለማ አገዛዝ አዳነን፤ ወደ ተወደደው ልጁ መንግሥትም መለሰን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ (ቈላ. ፩፥፲፫)፡፡

የሰው ልጅ በተከፈለለት ዋጋ ከሞተ ነፍስ የሚድንበትን መንገድ አገኘ፤ ፈጣሪው ሰው ኾኖ ከሞት የሚያመልጥበትን መንገድ አስተማረው፡፡ ሞተ ሥጋን በትንሣኤው ድል ነሣለት፤ የተዘጋውን ገነት ከፍቶ ለዘለዓለም በሕይወት መንገድ መራው፡፡ ስለዚህም ነው ጌታችን “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛል፡፡ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይሔድም፤” በማለት ያስተማረን (ዮሐ. ፭፥፳፬)፡፡ ይህም በእኛ ሥራ ሳይኾን በእግዚአብሔር ቸርነት የተደረገልን የማዳን ሥራ ነው፡፡ ራሱ ባለቤቱ በይቅርታው ብዛት ያደረገልን ነው፡፡ አምላካችን ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አስወገደልን፤ ከሞተ ነፍስም አዳነን፡፡ ሞተ ነፍስ ከእግዚአብሔር መለየት ነበር፤ እግዚአብሔር ሰው ሲኾን ይህ ሞት ተወገደ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ኾኗልና (ሮሜ. ፰፥፴፩)፡፡

በዚህ መንገድ ከእግዚአብሔር መለየት ቀረልን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኗልና፤ ማለት ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ በተዋሕዶ ከእኛ ጋር ተዛምዷል፤ ስለዚህ የእኛን ሞት እርሱ ሞተልን መከራችንንም ተቀበለልን፡፡ “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ ስለ እኛም ታመመ፤” እንዳለ ኢሳይያስ (ኢሳ. ፶፫፥፬)፡፡ ደዌያችንን ተቀብሎ ሕመማችንን ተሸክሞ ሞታችንን ሞቶ ሕይወትን ሰጠን፤ ከሞት አዳነን “ዘዚአነ ሞተ ነሥአ ወእንቲአሁ ሕይወተ ወሀበነ፤ የእኛን ሞት ሞቶ የእርሱን ሕይወት ሰጠን፤” እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም፡፡


ክፍል 3 ይቀጥላል..

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

27 Dec, 02:19


የመዳን ትምህርት
(ነገረ ድኅነት) ክፍል ~ 1
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነገረ ድኅነት ትምህርት እንዲህ ይላል ...

♦️ "የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና »፡፡ ሉቃ. 19፡10

♦️" . . . ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው።" 1 ዮሐ. 1፡1-2 ፤ 2፡25

♦️"በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።" 1 ዮሐ. 4፡9

♦️“ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” ዮሐ. 3፡16

♦️“ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤ በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።”1 ጴጥ. 1፡10-11

♦️"ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል።" ዮሐ. 20፡30-31

♦️"ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉ ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል፡፡ » 1 ጢሞ. 3፡15

♦️“ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” ማር. 16፡15-16

♦️« . . . ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ » 1 ጴጥ. 1፡2-3

♦️"አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር" ብሎታል። ቲቶ 2፡21

♦️“ጌታ ሆይ፣ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ . . . አለው። እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።” የሐዋ. 9፡5-“አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። … ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።” የሐዋ. 10፡5

ክፍል 2 ይቀጥላል

ቤተ ሊባኖስ ₃

27 Dec, 02:19


አጭር ተከታታይ ኮሪስ #ነገረ ድኀነት በምል በአንድ ሳምንት እንጨርሰዋልን በዚህ

ቤተ ሊባኖስ ₃

25 Dec, 09:19


. ቅዱሳን ማንን ይመስላሉ
#ቅዱሳኑ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
ቅዱሳኑን ልንቀበል : ልንመለከት : ልንሰማ : ልናይ : ልንመስላቸው ይገባል ።
#ቅዱሳን ነብያቱ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱሳን ሀዋርያቱ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱሳን ሰማእታቱ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱሳን መነኮሳቱ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱስ ጳውሎስ የሚመስለው ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት የሚመስሉት ክርስቶስን ነው::
#ቅዱስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው::
ስለኾነም እነርሱን መከተል ክርስቶስን መከተል ነው።
እነርሱን ማየት ክርስቶስን ማየት ነው
እነርሱን መስማት ክርስቶስን መስማት ነው ።
እነርሱን መምሰል ክርስቶስን መምሰል ነው ።
እኔ ጳውሎስ (ሳውል) ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ ይላል...
እኛም ይሄንን ያለማመንታት እና ያለማወላወል እንቀበለዋለን በዚህ ደግሞ መናፍቃኑ ይከሱናል
"ቅዱሳኑን አትመልከቱ ይላሉ"
"ቅዱሳኑን አትምሰሉ ይላሉ"
"ቅዱሳኑን አትከተሉ ይላሉ"
ይከሱናል ። ይወነጅሉናል ።
እውነት ክርስቶስ ስለሆነ
ቅዱሳን ነብያቱ ተነበዩለት
ቅዱሳን ሃዋርያቱ ሰበኩት
ቅዱሳን ሰማእታት ተሰውለት
ቅዱሳን መነኮሳት በፍቅሩ ተማርከው መነኑለት እነዚህ ሁሉ ህይወታቸው ክርስቶስ ነው። ታሪካቸው ክርስቶስ ነው ።
መጽሀፋቸው የክርስቶስ መጽሐፍ ነው ። ቃላቸው የክርስቶስ ቃል ነው።እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ሰርቷል በመሆኑም እነርሱን ማየት እነርሱን መከተል እነርሱን መስማት
ክርስቶስን ማየት መስማት መከተል ማለት ነው ።
ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል [ እኔን ምሰሉ ]፡፡
1ኛ ቆሮ 11፥1 ያለው እኮ ለዚህ ነው
እንዲሁም በ ፊልጵስዩስ ሰዎች። 3:17
ወንድሞች ሆይ፥ [ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ]፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ
የሚመላለሱትን ተመልከቱ በማለት ይገልጠዋል:: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ይሄንኑ
በራሱ ቃል ሲያጸናው
"እናንተን [ ቅዱሳኑን] የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይን ዋጋ ይወስዳል፥ፃድቅንም በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን
ዋጋ ይወስዳል።ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ጽዋ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም።"(ማቴ.10:40-42) አለን
ስለዚህ
[ ቅዱሳንን ስንቀበል ]የምንቀበለው ክርስቶስን ነው ።
ለቅዱሳኑ የተሰጣቸው ክብር እጅግ ከፍ ያለ ነው ። ቤተ ክርስትያን ማነጽ እነርሱን ማሰብ መከተል እና መስማት ብቻም አይደለም የማቴዎስ የምሥራች ምእራፍ 19 ቁ 28 እንዲህ አለ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተከተሉት ቅዱሳኑ ሲናገር
“እውነት እላችኋለሁ፤ በሚመጣው አዲስ ዓለም የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ
በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም የተከተላችሁኝ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ
በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ [ትፈርዳላችሁ]።በማለት ቅዱሳኑ ምን ያህል የላቀ እና የመጠቀ ክብር በአሁኑ ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም ጭምር እንዳላቸው አስረግጦ
ነው የተናገረው ።
ስለኾነም ክብር ለሚገባው ክብርን መስጠት ያስፈልጋል መፈራትም ለሚገባው እንዲሁ የሚገባውን መፈራት ማስረከብ ተገቢ ነው..
ለኹሉ የሚገባውን አስረክቡ ፣ ግብር ለሚገባው ግብርን ፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ፤
መፈራት ለሚገባው መፈራትን ፤ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ፡፡(ሮሜ 13÷7)
ተብለናልና..
ይሄም ለቅዱሳን የሚሰጣቸው ክብር እና መታሰቢያ ለዘለዓለም የሚኖር ነው :: በመጪውም
ዓለም የሚቀጥል ነው የቅዱሳን እና የቅዱሳት ኑሯቸው ሕይወታቸው ፤ ክርስቶስ ነው እና በፍርድ ጊዜም አብረውት ይመጣሉ ።
የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል:: (መዝ 111÷6)
አሜን አሜን አሜን ።

ቤተ ሊባኖስ ₃

23 Dec, 04:10


ጥያቄ :- ጌታችን በወንጌል "ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም።" ዮሐ. 3:5 ያለው ምሳሌያዊ እንጂ  ጥምቀትን አይደለም የሚሉ አሉ፦

መልስ

👉 ውሃና ከመንፈስ መወለድ የተባለው በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅ መሆንንና ለመዳን የሚያስፈልግ መሆኑን የሚያመለክት ነው። እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ ለመቀበል በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ካልተወለድን በስተቀር  ከእናት ከአባት በተወለድነው ተፈጥሮአዊና ሥጋዊ ልደት መንፈሳዊና ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ አንችልም።

ሐዋርያትና ከሐዋርያት የተማሩ ቅዱሳን ሊቃውንት ያስተማሩት በጥምቀት ዳግም ልደት መንግስቱን መወረስ የሚያስችል ምስጢር እንደሆነ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጥምቀት መንግስተ ሰማያት የሚያስወርስ ምስጢር እንደሆነ ሲገልጽ "ለማያምኑት አልቅሱላቸው የጥምቀትን ማሕተም ሳያገኙ ለሞቱት አልቅሱላቸው። እነርሱ ከመንግስተ ሰማያት ውጪ ናቸውና ልናለቅስላቸው ይገባናል። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ  በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" ተብሏልና።" [ትርጓሜ ፊልጵስዩስ
ክፍለ ትምሕርት 3]

ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌምም "ማንም ሰው ካልተጠመቀ በቀር መዳንን አያገኝም፣ በውኃ ሳይሆን በደማቸው ከተጠመቁ ከሰማዕታት በስተቀር። ጌታችን ዓለምን በመስቀሉ ባዳነ ጊዜ ጎኑን ተወጋ ያን ጊዜም ደምና ውኃ ከጎኑ አፈለቀልን። ይህም በሰላም ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች በውኃ ይጠመቁ ዘንድ በስደትና በመከራ ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በደማቸው ይጠመቁ ዘንድ ነው።..."።[ በእንተ ጥምቀት ትምሕርት 3 ቁ.10] ብሏል።"

👉 ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይዘው ውኃው የተባለው ጥምቀት ሳይሆን በተቃዋሚዎች ዘንድ አንዳንዶቹ ውኃው ምልክት (symbolic) ነው ሌሎቹ  የእምነት ማጽኛ ነው ሌሎቹም የእግዚአብሔር ቃል ነው  የእምነት መመስከሪያ [አንዳንዶቹም ውኃ የተባለው ምሳሌያዊ ሲሆን መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል ይላሉ።] በማለት ይተረጉማሉ።

ማስረጃ 1:-ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ በመድሎተ ጽድቅ መጽሐፉ ይህን አስመልክቶ "በተቃዋሚዎች ዘንድ ርስ በርሳቸው እንኳ ይህ ሁሉ የአረዳድ ልዩነት የተፈጠረው ግን ሁሉም አንብቦ መተርጎም ይችላል በሚል የተሳሳተ ትምህርታቸው የተነሳ ነው። ይህን የጻፈልን የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረው የቅዱስ ፖሊካርፕስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ሄሬኔዎስ "እኛ በኃጢአት ምክንያት አካላችን የተቆማመጠብን እንደመሆናችን የእግዚአብሔርን ስም በመጥራትና በተቀደሰው ውኃ በመጠመቅ ከክፉ በደሎቻችን ሁሉ እንነጻለን፤ አዲስ እንደተወለዱ ሕጻናትም በመንፈሳዊ ልደት ዳግመኛ እንወለዳለን ራሱ ጌታችንም እንዲህ ብሎ እንደተናገረ፦ "እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" ዮሐ 3:5 (ቅሬታት፣ 34)

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ፖሊካርፕስን ያስተማረው እንደዚህ ነበር። ቅዱስ ሄሬኔዎስም ከመምህሩ ከቅዱስ  ፖሊካርፕስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ የተማረው ይህንኑ ነበር፣ በተግባር ያየውም እንደዚህ ነበር። ስለዚህ ቅዱስ ሄሬኔዎስም ሆነ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ሁሉ የተረዱት ጌታችን በውኃ መጠመቅ ለዳግመኛ ልደትና መንግሥተ ሰማያት አስፈላጊ ነው ያለ መሆኑን ነው።በኒቂያውና በቁስጥንጥንያው የእምነት መግለጫ አንቀጽ ላይም "ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።" ተብሎ የተገለጸው ከእነርሱ በፊት ከነበሩ አባቶችና እነዚያም ከሐዋርያት፣ ሐዋርያት ደግሞ ከጌታ የተቀበሉት አተረጓጎምና አረዳድ ነው። ከዚህ የቤተ ክርስቲያናዊ አረዳድ የወጡና መጽሐፍ ቅዱስን በራሳችን መንገድ እንተረጉመዋለን የሚሉ ፕሮቴስታንቶች ግን ከዚህ ተቃራኒ የሆነ ነገር ይዘው ብቅ በማለት አንዳቸው ትክክለኛው ይኸኛው ነው፣ ሌላቸው ደግሞ እርሱ ሳይሆን እንደዚህ ነው እያሉ ሁሉም የራሳቸውን ግምት በሰዎች ላይ ለመጫን ይደክማሉ። (መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2. ገጽ 99)


ይቀጥላል...

ተክለ ማርያም

ቤተ ሊባኖስ ₃

23 Dec, 04:10


ከላይ እንደተገለጸው ተቃዋሚዎች "ውኃ" የተባለው ምሳሌያዊ እንጂ በቀጥታ አካላዊውን ውኃ አይደለም በማለት ተቃውሞን ያቀርባሉ። ውኃ ለመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሆኖ "በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህ ግን በርሱ የሚያምኑት ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ" ዮሐ. 7:38-39 ቀርቧል። ዳግመኛም "ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት..." ዮሐ. 4:10-14 ውሃ በምሳሌያዊ መልኩ ተገልጿልና "ከውሃና ከመንፈስ ያልተወለደ..." ሲልም ውኃ" የተባለው ቀጥታ ውኃ ለማለት  ሳይሆን ምሳሌያዊ ነው መንፈስ ቅዱስን ወይም ጌታን ነው የሚያመለክተው ይላሉ

ማስረጃ 2:-  በዮሐ. 3:5 ላይ "ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም።" የተባለው በውኃ ስለሚፈፀመው ጥምቀት እንጅ በምሳሌነት መንፈስ ቅዱስን ለማለት የተጠቀሰ አይደለም።

ይህን ለመረዳት ጌታችን ይህን ለኒቆዲሞስ ሲነግረው "ውኃ" የተባለው በውኃ ስለሚፈጸመው ጥምቀት  ውጪ  ሌላ ትርጉም ቢኖረው ኖሮ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ  አብራርቶ በጻፈልን ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጽፍ የተሳሳቱ ወይም ግራ የሚያጋቡ ሃሳቦች ሲኖሩ አስተካክሎ አርሞ ያልፋል እንጂ እንዲሁ አይተወውም። "...እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር" ዮሐ. 2:19-21፤ "...ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም።" ዮሐ.8:25-27 "እንቅልፍ ስለመተኛት የተናገረ መስሏቸው ነበር" ዮሐ. 11፡13:: "የአትክልት ጠባቂ መስሏት ነበር" (ዮሐ. 21፡33)  በማለት አብራርቶ ስሕተትም ካለ አርሞ የሚጽፍ ሐዋርያ ነው።

ስለዚህም ከላይ 'ውኃ' የተባለው "መንፈስ ቅዱስ" ቢሆን ኖሮ በዮሐ. 7:37-39 ላይ እንደሰፈረው አብራርቶ ይጽፍልን ነበር።
በዮሐ. 7:38 ላይ "የሕይወት ውሃ"  የተባለው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን አብራርቶ ገልጾ ነበርና።

ማስረጃ 3:-
በዮሐ. 3:5 ላይም የተጻፈው በቀጥታ በውኃ ስለሚፈጸመው ጥምቀት ባይሆን ኖር አብራርቶ ይገልጸው ነበር። "በውኃና በመንፈስ"  የተባለው በቀጥታ በውኃ ስለመጠመቅ እንጂ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሆኖ አለመቅረቡን ለመረዳት:-

1ኛ.  በዮሐ. 4:10-14 እና በዮሐ. 7:38-39 ላይ የሕይወት ውኃ (living water) እያለ ሲናገር በዮሐ. 3:5 ላይ ግን "ውኃ" በማለት ብቻ ነው የተባለው። ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር የሕይወት ውሃ እያለ ሲገልጸው በዮሐ.3:5 ላይ ደግሞ "ውኃ" ብቻ በማለት ምሳሌያዊ እንዳልሆነ ያስረዳናል።

2ኛ. በዮሐ. 4:10-14 እና በዮሐ. 7:37-39 ላይ በውኃና በሕይወት ውኃ (living water) መካከል በማነጻጸር ሲያስቀምጥ በዮሐ. 3:5 ግን እያነጻጸረ አልገለጸም ምክንያቱም "በውኃና በመንፈስ" በማለት የተገለጸው ምሳሌያዊ ሳይሆን በቀጥታ በውኃ ጥምቀት የሚፈጸመውን የሚያመለክት ነውና።

3ኛ. "በውኃና በመንፈስ" የተባለው ላይ "ውኃ" የተባለው ዮሐ. 7:38-39 ላይ "የሕይወት ውኃ" ተብሎ እንደተገለጸው መንፈስ ቅዱስን ለማመልከት ቢሆን ኖሮ "እና" በሚል አያያዥ ቃል ባልተጠቀመ ነበር። ምክንያቱም ውኃ የተባለው መንፈስ ቅዱስ ቢሆን ኖሮ "በውኃና በመንፈስ" በማለት አይገልጽም ነበር። ድግግምሽ ይሆናልና። ይልቁኑ በውሃና በመንፈስ የተባለው በጥምቀት የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን የምናገኝበትን የሚያመለክት ቃል ነው።


ተክለ ማርያም

https://t.me/zemariwochu3

ቤተ ሊባኖስ ₃

17 Dec, 13:00


📌 ያሳደገን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ደረሰ!
ዘክረን ለበረከት እንረባረብ። በዓይነት፣ በጉልበት በገንዘብ በማገዝ የአቅምዎን ያድርጉ።
ለበለጠ መረጃ :-0987166180
0953125078

Your account
አሑዱ ባንክ #0065068310101 DAGNE  LEMU AND AZEB GEBREMICHAEL
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000438455632

ቴሌ ብር 0953125078 Emebet tekle

ቤተ ሊባኖስ ₃

17 Dec, 05:00


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ቅዱስ ኒቆላዎስ (የገና አባት)
🎉🎊🎉🎊🎉🎊🎉🎊🎊🎉🎊🎊

🌷የገና አባት (ቅዱስ ኒቆላዎስ) ለድኆች ሥጦታ ይለግስ የነበረ ቅዱስ አባት ነው። ታሪኩም በስንክሳር ታኅሣሥ 10 ላይ ተጽፎአል። "የገና ዛፍ ባሕላችን አይደለም እነርሱ ክረምታቸውን የሚያስታውሱበት ነው ከእኛ ጋር አይገጥምም" "የተወለደውን ክርስቶስ የበዓሉ ማዕከል እንዳናደርግ ያደርገናል" ማለት ትክክለኛ ነገር ነው። Pagan Origin (የባዕድ አምልኮ መነሻ) አለው ብሎ ጣዖት አምልኮ ነው ማለት ግን ከገደብ ያለፈ ድምዳሜ ነው።

☀️በከዋክብት ያመልኩ የነበሩት የጥበብ ሰዎች በሚያመልኩት ነገር ወደ ክርስቶስ ተጠርተዋል ፣ የዙሐል ጣዖት ይከበርበት የነበረውን ዕለት ከክርስትና በኋላ በእስክንድርያ የቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን ሆኗል።

🌿የራሳችንን የገና ባሕላዊ አከባበሮች የገና ጨዋታን ፣ ቀጤማ መጎዝጎዝ የመሳሰሉትን ማክበር ይገባናል። ከዚያ ውጪ በክርስትና መንፈስ እስከተቃኘና የጌታን በበረት መወለድ ፣ የሰብአ ሰገልን ጉዞ ፣ ከዋክብቱን ፣ የመላእክትን ዝማሬ ፣ የእረኞችን ደስታ ፣ የሰብአ ሰገልን እጅ መንሻ የሚያሳይ እስከሆነ ድረስ የኛ ባሕል ያልሆነውን ሁሉ ጣዖት ነው ብሎ ማንቋሸሽ ፣ የሚያምር ነገርን ሁሉ ማውገዝ ያስመስላል። ቅዱስ ኒቆላስም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምትዘክረው ቅዱስ ስለሆነ አጋጣሚውን ጻድቁን ለማስተዋወቅም ልንጠቀምበት ይገባል።

🌲ሥጦታም የምንሠጣጠው የሰብአ ሰገልን ሥጦታ መነሻ አድርገን ሲሆን ልግስናውን ለነዳያን ብናደርገው የበለጠ በረከት እንቀበልበታለን።

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

ቤተ ሊባኖስ ₃

16 Dec, 19:21


👉 አስተማሪ

ዶክተሩ በድንገት ተደውሎለት ለአስቸኳይ የቀዶ ህክምና በጥድፊያ ወደ ሆስፒታሉ እየገባ ነው።

በተቻለው አቅም የስልክ ጥሪውን በአግባቡ አስተናግዷል። የህክምና ልብሱን በአስቸኳይ ቀይሮ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እያመራ ሳለ ኮሪደሩ ላይ የዶክተሩን መምጣት እየተንጎራደደ ይጠብቀው የነበረውን ሰው አገኘው።

"እንዴት ለመምጣት ይህን ያህል ግዜ ይፈጅብሀል? የልጄ ህይወት ልትጠፋ አደጋ ላይ እንዳለች አይታይህም? ህሊና የለህም?" ብሎ ዶክተሩ ላይ ጮኸበት።

ዶክተሩም በትንሹ ፈገግ አለና ,,,,
"አዝናለሁ ሆስፒታል ውስጥ አልነበርኩም። የስልኩን ጥሪ ከተቀበልኩ በሗላ በቻልኩት ፍጥነት እዚህ ለመድረስ ጥሬያለሁ አሁን አንተም ብትረጋጋ እኔም ስራዬን ብሰራ መልካም ነው" ብሎ ሊያረጋጋው ሞከረ።

ሰውየው ግን ,,,
"ተረጋጋ ነው ያልከው? ያንተ ልጅ ቢሆንስ አሁን እዚህ ክፍል ውስጥ ሆኖ ትረጋጋ ነበር? ልጅህ ቢሞት ምን ታደርግ ነበር?" አለ አባት በቁጣ።

ዶክተሩ አሁንም በትንሹ ፈገግ አለና እንዲህ መለሰለት
"የአምላክ ፈቃድ ይሁን። ዶክተር ህይወት ሊያራዝም ሊያጠፋም ሊተካም አይችልም ግን የቻልነውን ያህል እንጥራለን። እንደ አምላክ ፍቃድ ልጅህም ይድንልሀል አንተ ብቻ ተረጋጋ" አለው አሁንም ፈገግ እያለ።

ሰውየውም ,,,
" ባልገቡበት ጭንቀት አስተያየትና ምክር መስጠት ቀላል ነው" እያለ አጉረመረመ። ቀዶ ጥገናውም የተወሰነ ሰዓታትን ወስዶ በሰላም ተጠናቀቀ ዶክተሩ በደስታ እየተጣደፈ ከቀዶ ጥገናው ክፍል ውስጥ ወጣ።

ለአባትየውም ,,,,
"ፈጣሪ ይመስገን ልጅህ ተርፏል።" ብሎት የአባትየውን መልስ ሳይጠብቅ "ማንኛውም ጥያቄ ካለህ ሌሎች ረዳት ዶክተሮችን መጠየቅ ትችላህ።" ብሎት ዶክተሩ መንገዱን በሩጫ ቀጠለ።

የልጁም አባት "ለምንድነው ዶክተሩ እንደዚህ ስሜታዊና ችኩል የሆነው? ምናለ አሁን አንድ ደቂቃ ስለ ልጄ ሁኔታ ብጠይቀው?" ሲል ተናገረ።

ይህን የሰማችው ነርስ እንባ በጉንጮቿ እየጎረፈ ,,,,
"ትላንት ነበር የዶክተሩ ልጅ በመኪና አደጋ የሞተው። ለልጅህ ህክምና ስንደውልለት የልጁ ቀብር ላይ ነበር አሁን ያንተን ልጅ ህይወት ታደገ የራሱን ልጅ ደግሞ የቀብር ስርዓት ሊጨርስ በሩጫ ሄደ።" አለችው።

አባት ከሰዓታት በፊት ዶክተሩ ያሳየውን ፈገግታ እያሰበ ተንሰቀሰቀ። የፀፀት ለቅሶ

አንድ ሰው ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ሳታውቅ
ለመፍረድ አትቸኩል

"ቀድሞ መፍረድ ለህሊና ፀፀት ይዳርጋል"
https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

16 Dec, 19:00


#ለምንድነው_መኖር_የደከመህ??
.
ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ

☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡
☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡
☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን አነበብክ ታስፈልገናለህ፡፡

ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡

፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::"
በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ይሄ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት መሞክር ማለት ነው፡፡

ለኔ ና ለእናተ

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

13 Dec, 04:33


ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

(የምክር ቃል ለኔ ና ለእናተ)

ቤተ ሊባኖስ ₃

11 Dec, 12:19


✞በሦስተኛ ዓመቷ✞

በሦስተኛ ዓመቷ ታኅሣሥ ሦስት ዕለት(፪)
የገባችው ድንግል መቅደሰ ኦሪት(፪)

ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቦና
በሥላሴ ዙፋን በክብር ተሥላ
ድንግል ማርያም በቅድመ ሕሊና
ለእኛ ለአዳም ልጆች ታስባለችና
አዝ= = = = =
ሐናና ኢያቄም አምላክን ለምነው
በጾምና ጸሎት ብዙ ተፈትነው
ልጅ እንዲሰጣቸው ዘወትር ሲመኙ
በመልአከ ብሥራት ድንግልን አገኙ
አዝ= = = = =
መልአኩ ፋኑኤል ከአምላክ ተልኮ
ሰማያዊ መና ለድንግል አቅርቦ
የጸጥታ መጠት እንድትጠጣ ብሎ
ያገለግላታል ውዳሴን አቅዶ
አዝ= = = = =
ሐርና ወርቅን ተፈትላ አስጊጣ
በቤተ መቅደሱ መጽሐፉን ገልጣ
ስታገለግል በትህትና ሆና
ቃል ሥጋ ሆነ በእርሷ አደረና

መዝሙር
ቴዎድሮስ አለማየሁ

"ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ"
መዝ ፵፭፥፲
https://t.me/zemariwochu3

👉 @DA121922

ቤተ ሊባኖስ ₃

10 Dec, 04:21


✞ #ታህሳስ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ማክሰኞ ታህሳስ 1 - የነብዩ ኤልያስ ልደቱ - በእንጦጦ እና በጎፋ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 3 - ባዕታ ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን
                      -ቅዱስ ፋኑኤል - በዓለም ባንክ
      _በአያት መሪ ቅዱስ ፋኑኤል
                      -ዜና ማርቆስ - በጣፎ

እሁድ ታህሳስ 6 - ቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤቷ - የቅድስት አርሴማ ታቦት ባለበት

ማክሰኞ ታህሳስ 8 - አባ ኪሮስ ልደታቸው - አለምባንክ ጀሞ ተራራ መድኃኔዓለም ቤ/ክ - በጣፎ

ረቡዕ 9 - እስትንፋሰ ክርስቶስ ልደታቸው - በቦሌ ቡልቡላ ዋሻ ተክለሃይማኖት

አርብ 11 - ቅዱስ ያሬድ - ጎተራ አጎና ሲኒማ ፊት ለፊት

ቅዳሜ ታህሳስ 12 - አባ ሳሙኤል እረፍታቸው - በአቃቂ አባ ሳሙኤል ቤተ ደናግል ገዳም ፣ በቦሌ ቡልቡላ አባ ሳሙኤል እና በሲኤሚሲ ሚካኤል

እሁድ ታህሳስ 13 - ቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ - በሸጎሌ

ረቡዕ ታህሳስ 16 - ፍቅርተ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበለችበት እለት - በአንቆርጫ መድኃኔዓለም ከፈርንሳይ ጉራራ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ጋር ባጃጅ እና ታክሲ አለ የአንቆርጫ

ቅዳሜ ታህሳስ 19 - ቅዱስ ገብርኤል - ሶስቱን ህፃናት ያዳነበት

ማክሰኞ ታህሳስ 22 - ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እደምትወልድ ያበሰረበት - በብስራተ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 24 - አቡነ ተክለሃይማኖት - ልደታቸው

ሰኞ ታህሳስ 28 - ቅዱስ አማኑኤል - የልደቱ መታሰቢያ - በመሳለሚያ

ማክሰኞ ታህሳስ 29 - ባለወልድ - የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በዓል - በ4 ኪሎ ባለወልድ ቤተክርስቲያን - በለቡ መብራት አብርሃም ገዳም

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞

         https://t.me/zemariwochu3

ቤተ ሊባኖስ ₃

09 Dec, 17:40


"የበቃሁ ነኝ" የሚባለው መቼ ነው?

በአንድ ገዳም ውስጥ የሚኖር መነኩሴ ነበር። ከገዳሙ አበምኔት ጋርም ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እያነሱ ሲወያዩ " አባቴ እኔ ዛሬ የዓለምን ኋጢአት ግፍና በደል አየሁ፡፡ ስለዚህ የበቃሁ ሆኛለሁ።" ብሎ አጫወታቸው፡፡ አበምኔቱም " ወንድሜ ሆይ እስቲ በርትተህ ጸልይ ፥ገና ነህ።" ብለው መለሱለት።

እንዲሁም በሌላ ግዜ ወደ አበምኔቱ ቀርቦ " አባቴ አሁንስ በቅቻለሁ ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ ሲወጡና ሲወርዱ የሕዝቡንም ኋጢአት ሲያስተርዩ አይቻለሁ።" አላቸው። " ልጄ ሆይ ገና ነህ፥ አሁንም በርታና ጸልይ።" ብለው ሸኙት፡፡ ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ ኣብዝቶ ይጾምና ይጸልይ ጀመር። ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ አብዝቶ ይጾምና ይጸልይ ጀመር። ለሶስተኛ ጊዜ ስላየውም ራእይ ለአበምኔቱ እንዲህ ሲል ገለጠላቸው፡፡ " አባቴ ሆይ ዛሬስ በዓለም ሳለሁ የሰራሁትን ኋጢአት ሁሉ አንድ በአንድ አሳየኝ።" አላቸው እርሳቸውም " ልጄ የበቃኸው አሁን ነው።" ብለው አሰናበቱት።

ክርስቲያናዊ ሕይወት ምድራዊ ፍላጎቶችንና የሰይጣን ሸንገላ በመቃወም ሰማያዊ መንግስት የሚወረስበት ምስጢር በመሆኑ ፈተናውን የዛኑ ያህል ከበድ ይላል። ብዙ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ ቃለ #እግዚአብሔር መማር ሲጀምሩ የራሳቸው ኋጢአት እያሰቡ ከማልቀስ እና ንስሓ ከመግባት ይልቅ የሌላውን በደል መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ " እነ እገሌ እንኳን እንዲህ አደረጉ ጉድ ነው!" ማለት ያበዛሉ። ሌላውን ሲመለከቱ ሊዱኑበት የሚችሉበትን ወርቃማ የንሰሓ ጊዜ በኮንቱ ያበላሹታል። መጽሓፍ ግን "ለዚህ ዓለም ከማይመችና የአረጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ"(1ኛ ጢሞ 4 ፡ 7) ይላል። ይህ መነኩሴ የተገለጠለት ራእይ ለመዳኑ የጠቀመው የራሱን ኋጢአት ያየ ጊዜ መሆኑን ከታሪኩ መረዳት እንችላለን፡፡ እኛስ የሚታየን የማን ኋጢአት ነው? የራሳችን ወይስ የሌላው?

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Dec, 17:51


🍃🍃የአባቶች ምክር 🍃🍃
ልጄ ሆይ ፤ ዋዘኛና ቀልደኛ አትሁን ፡፡ በመከራ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታዝንና የምትራራ ሁን ፤ በድኃ ላይ አትጨክን ፤ ርስቱንና ቤቱንም በምክንያት አትውሰድበት ፤ ለመጨረስም የማትችለውን ነገር አትጀምር ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ በልተህ ስትጠግብ ረኃብን ፤ ስትበለጥግ ድኅነትን ፤i ስትሾም ሽረትን ፤ ሌላውንም ይህን የመሰለውን ሁሉ አትርሳ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ለሞተው ወዳጅህ ከማልቀስ ይልቅ በሕይወቱ ሳለ የክፋት ሥራ ለሚሠራ ወዳጅህ አልቅስለት ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ባለ ጠጋ ሰው ሁሉ ይደግፈዋል ፤ ድኃ ሲወድቅ ግን ሰው ሁሉ ወዲያው ይገፋዋል ፡፡ ባለ ጠጋ ሲከሰስ በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይሟገትለታል ፤ ድሀ ሲከሰስ ግን በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይፈርድበታል ፡፡ መልካም ዳኛ በመካከላቸው የተቀመጠ እንደ ሆነ ግን ፍርዱ እንደ ፀሐይ ያበራለታል ፡፡ ስለዚህ በምትኖርበት ሀገር መልካም ዳኛ አያጥፋብህ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ በማናቸውም ነገር ቢሆን ሞት አይቀርም ፡፡ ነገር ግን በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላል ፡፡

ለአፍህ መሐላ አታልምደው ፤ እግዚአብሔር ስሙን ከንቱ ያደረገውን ሳይቀስፈው አይቀርምና ስሙን በከንቱ አትጥራ ፡፡ ልጄ ሆይ ፤ የምትሠራውን ሥራ ሁሉ ሰው ቢያየው ቢሰማውም አይጎዳኝም ብለህ እንደ ሆነ ነው እንጂ አይታይብኝም ፤ አይሰማብኝም ብለህ አትሥራው ፡፡ አንተ ምንም ተሰውረህ ብትሠራው ከተሠራ በኋላ መታየቱና መሰማቱ አይቀርም ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት ፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር ፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ
ሆነ ግን ፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም ።

ልጄ ሆይ ፤ በጌታህም ቤት ቢሆን በሌላም ስፍራ ቢሆን ገንዘብ ወይም ሌላ እቃ ወድቆ ብታገኝ አታንሣ ፡፡ ብታነሣውም መልሰህ ለጌታህ ወይም ለዳኛ ስጥ እንጂ ሰውረህ አታስቀር ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ በፍፁም ልብህ ለማትወደው ሰው ቤትህንና የቤትህን ዕቃ አታሳይ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ንፁሕ አለመሆንህን እግዚአብሔር ያውቃልና በእርሱ ፊት ንፁሕ ነኝ አትበል ፡፡ በንጉሥ ፊትም ብልህ ነኝ አትበል ፤ የብልሃት ሥራ ሠርተህ አሳየኝ ያለህ እንደ ሆነ ታፍራለህና ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ጠላት በዛብኝ ፤ ምቀኛ አሴረብኝ ብለህ እጅግ አትጨነቅ ፡፡ በዓለም የሚኖር ፍጥረት ሁሉ ጠላትና ምቀኛ አለበት እንጂ ባንተ ብቻ አይደለም ፡፡ ከዚሁም በጥቂቱ
እጽፍልሃለሁ ፡፡ በፍየል ነብር ፤ በበግ ተኩላ ፤ በአህያ ጅብ ፤ በላም አንበሳ ፤ በአይጥ ድመት ፤ በዶሮ ጭልፊት አለባቸው ፡፡

ይህንንም የመሰለ ብዙ አለ ፡፡ ሰውም እርስ በርሱ እንዲሁ ነው ፡፡ ስለዚህ የሚመጣብህን ነገር ሁሉ በትእግሥት ሆነህ ተቀበለው ፡፡ በመጨረሻው ግን ሁሉ አላፊ ነውና ጠላቶችህ ሁሉ ያልፋሉ ፡፡ ወይም አንተ አስቀድመህ ታልፍና ከዚህ ዓለም መከራና ጭንቀት ታርፋለህ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው ፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች ፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች ፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች ፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁiሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ ፣ ሲያዝኑ ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ ፣ ሲራቡ ፣ ሲጠሙ ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል ፡፡

ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል ? የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡

‼️ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን ፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት & የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን



ለኔ ና ለእናተ

ቤተ ሊባኖስ ₃

07 Dec, 16:59


በማርያም አማላጅነት ያምናሉ 🥰

ቤተ ሊባኖስ ₃

07 Dec, 16:05


📝መንፈሳዊ ታሪኮች፣ልቦለድ፣ ስነ ፅሁፍ ፣እና መዝሙሮችን ፣የሚያቀርብ አዲስ ቻናል ተከፍቷል አሁኑኑ ተቀላቀሉ 👇

https://t.me/+yL-AeCQris9jZGY0
https://t.me/+yL-AeCQris9jZGY0

ቤተ ሊባኖስ ₃

07 Dec, 15:25


📷 እርግጠኛ ነኝ ፕሮፍይሎን ለመቀየር ፈልገው ፕሮፍይል የሚያደርጉት ጠፍቶ  ተቸግረው ያውቃሉ።

የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ መንፈሳዊ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇📷

https://t.me/addlist/gpX29GzfGs43MWE0

ቤተ ሊባኖስ ₃

07 Dec, 10:10


3 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ለፈተና በቂ ዝግጅት ስላላደረጉ ለመሸወድ ፈለጉ። በዚህም ምክንያት አንድ መላ ዘየዱ። ራሳቸውን ግሪስ ቀቡና ራሳቸውን በሚገባ በማቆሸሽ ከሌክቸረሩ ፊት በመቅረብ እንዲህ ሲሉ ምክንያታቸውን አቀረቡ፦

ኢንስትራክተር በጣም እናዝናለን፤ ፈተናውን ለመፈተን የማያስችል እንከን ገጥሞናል። ምክንያታቸውን አስከተሉ፦

አንድ ሰርግ ላይ ታድመን ነበር፤ እናም ከፕሮግራሙ በኋላ በመመለስ ላይ እያለን በመንገዳችን ላይ መኪናችን ብልሽት ገጠማት። የመኪናችንን ብልሽት ለመጠገን እንደምትመለከተን በአስቀያሚ ሁኔታ ቆሽሸናል።

#ሌክቸረሩም ከምክንያተቸው በመነሳት ተረዳቸውና ወደቤታቸው እንዲመለሱ ለፈተና ዝግጅት 3ት ቀን ሰጣቸውና አሰናበታቸው።

ከ3ት ቀን በኋላ ለተዘጋጀላቸው ፈተና በበቂ ሁኔታ አጥንተውና ተዘጋጅተው መጡ።

ሌክቸረሩ አንድ ውሳኔ ወሰነና እንዲህ አደረገ ...

ሶስቱም ተራርቀው የተለያየ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ተማሪዎቹም በጣም ተራርቀው ተቀመጡ፤ የፈተና ወረቀትም ተሰጣቸው። ጥያቄዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፦

ጥያቄ ቁጥር 1 - ማን ነበር ያገባው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 2 - የት ነበር የሠርግ ፕሮግራሙ የተካሄደው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 3 - መኪናዋ የተበላሸችበት ትክክለኛ ቦታ የት ነው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 4 - የተበላሸችው መኪና ሞዴሏ ምን አይነት ነው ? (25% ማርክ)

ከጥያቄዎቹ መጨረሻም #ማስጠንቀቂያው እንዲህ ይላል - መልሳችሁ የግድ ተመሳሳይ መሆን አለበት !!!
___

ውሸት መጨረሻው አያምርም

https://t.me/Abalibanos333
ለኛ ና ለእናተ ምክር ነክ ፁሑፍ

ቤተ ሊባኖስ ₃

06 Dec, 14:39


📡 በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️🀄️
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥

🔑 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘማሪዎች ውስጥ የማንን ዝማሬ ማግኘት ይፈልጋሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔴የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
⚫️የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
ዝ?የቀዳሜጸጋ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔴የኪነጥበብ መዝሙር
⚫️የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔴የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ እና      ወ.ዘ.ተ......
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️🀄️
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥


         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █       

 
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ቤተ ሊባኖስ ₃

04 Dec, 14:10


✟ እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?


የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት ተጀምሯል።
መዝሙሮቹን በ" ጃን ያሬድ " የቴሌግራም ገጽ ላይ
ያገኙታል ይቀላቀሉ። ⬇️


📎 https://t.me/+1rCQMEj6K2kzM2E8
📎 https://t.me/+1rCQMEj6K2kzM2E8

ቤተ ሊባኖስ ₃

04 Dec, 13:15


ኦርቶዶክስ ኖት ?

ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።

➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

ቤተ ሊባኖስ ₃

04 Dec, 09:46


#እንኳንም_ተሳሳትኩ

በአንድ ወቅት አንዲት #የሒሳብ_መምህርት የሚከተለውን በሰሌዳ ላይ ጻፈች፦

👉 9×1= 7
👉 9×2= 18
👉 9×3= 27
👉 9×4= 36
👉 9×5= 45
👉 9×6= 54
👉 9×7= 63
👉 9×8= 72
👉 9×9= 81
👉 9×10= 90

ጽፋ እንደጨረሰችም ወደ ተማሪዎቿ ዞራ ስትመለከት ሁሉም #እየሳቁባት ነው፣ የመጀመሪያውን #እኩልታ (equation) #ተሳስታለችና።

ይህን ጊዜ #መምህርቷ እንዲህ አለች፦ "የመጀመሪያውን #ስህተት_የጻፍኩት በዐላማ ነው፤ ከነገሩ ጠቃሚ ትምህርትን እንድትወስዱ ስለፈለኩኝ። ይኸውም፥ በውጪ ያለው ዓለም እንዴት እንደሚቀበላችሁ ታውቁ ዘንድ ነው። 9 ጊዜ #ትክክለኛ ነገር እንደጻፍኩ ማየት ትችላላችሁ ይሁንና አንዳችሁም ስለዛ አላበረታታችሁኝም፤ ነገር ግን ሁላችሁም ስለ ሠራሁት አንድ ስህተት ሳቃችሁብኝ፣ ነቀፋችሁኝ!

#ትምህርቱም_ይህ_ነው፦
የሰው ልጅ ሚሊዮን መልካም ሥራን ብትሠሩ አያበረታታችሁም ግን አንድ የሠራችሁትን ስህተት ይዞ ይነቅፋችኋል። በዚህ ግን ተስፋ ልትቆርጡ አይገባም... ሁልጊዜም ቢሆን ከሳቅና ከነቀፋ በላይ ወጥታችሁ ቁሙ፣ ጽኑ፣ በርቱም!"

#ልብ_እንበል፦
#መሳሳትን ከፈራን #መሞከር አንችልም፤ መሳሳት መጨረሻችን አይደለም የማወቅ መነሻ እንጂ። ምናልባት #የተማርነውን እንረሳ ይሆናል፣ የተሳሳትነውን ግን አንረሳም። ከብዙዎች የስንፍና ፍፁምነት ይልቅ የእኛ የመሥራት ስህተት እንደሚሻል እናስብ።

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

03 Dec, 04:23


የትግስት ዋጋ

ስመጥሩ ግሪካዊ ኤዞፕ አንድ ዝነኛ ተረት አለው፡፡ በዚህ ታዋቂ ተረት ደሃ ና ሞኝ ገበሬ ገጸ ባህሪ አለ፡፡
ይህ ገበሬ ከእለታት አንድ ቀን የእለት ተእለት ስራውን አከናውኖ ወደቤቱ ሲመለስ በመኖሪያው ያልተለመደ ነገር ጠበቀው፡፡ ገበሬው ግራ ተጋባ፡፡ ገበሬውን ግርታ ውስጥ የከተተው
የገበሬው ንብረት የሆነችው ዶሮ የወርቅ እንቁላልን መጣሏ ነበር፡፡
ከዚህ ያልተለመደ ክስተት በኋላ ገበሬው እንቁላሉ የእውነት መሆኑን ሊያጣራ የተለያዩ መንገዶችን ቢሞክር እንቁላሉ እውነተኛ ወርቅ ሆኖ አገኘው፡፡ ይሄኔ ደስታውን ይበልጥ ከፍ ለማድረግ የወርቅ እንቁላሉን በውድ ዋጋ ሸጠወ፡፡

በቀጣይ ተከታታይ ቀናትም ዶሮዋ የወርቅ እንቁላል መጣል የቀጠለች ሲሆን ገበሬውም የወርቅ እንቁላሉን ወደገበያ እያወጣ መሸጡን ቀጠለ፡፡ ኑሮውም በከፍተኛ ፍጥነት ተለውጦ በአካባቢው ቀጭን ጌታ ለመሆን ቻለ፡፡

አንድ ቀን ታዲያ ገበሬው በየእለቱ አንድ እንቁላል ብቻ እየጠበቀ መሸጡ አዋጭ አልመስልህ አለው፡፡ ስለዚህም ዶሮዋን በማረድ በሆድዋ ያለውን እንቁላል በሙሉ ወስዶ ለመሸጥና ሐብቱንም በአንድ ጊዜ እጥፍ ሊያደርግ ወሰነና ዶሮዋን አረዳት፡፡

ይሄኔ ሰውዬው ተደናገጠ፡፡ ምክንያቱም ዶሮዌ ሆድ ውስጥ ምንም እንቁላል ሊያገኝ አልቻለም፡፡

ይህ የብዙዎቻችን ህይወት ነው፡፡
ልክ እንደገበሬው በአንድ ጊዜ የስኬት ቁንጮ ላይ መቀመጥ ስለሚያምረን የስኬት መንስኤ ሊሆነን የሚችለውን ነገር እናርዳለን፡፡
በሂደት የሚመጣን አዎንታዊ ለውጥ በትእግስት መጠበቅ ስለሚያቅተን አተርፍ ባይ አጉዳይ ህነን ባዶ እንቀራለን፡፡

እናስተውል፡፡ ለመታገስ ፈቃደኛ ካልሆንን በገዛ እጃችን ስኬታችንን አርደን ባዶ እንቀራለን፡፡

#ለኔ ና ለእናተ ምክር ነክ ፁሑፍ
https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

30 Nov, 04:29


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች በቅድሚያ እንኳን አደረሳችሁ እያልን አገልግሎታችንን ተደራሽ ለማድረግ በ  tiktok ም መተናል ።
እንደተለመደው የናንተን ድጋፍ እንሻለን
follow , share , like በማድረግ ይተባበሩን    
👇
https://www.tiktok.com/@da121922?_t=8qLMpESxmcf&_r=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ቤተ ሊባኖስ ₃

26 Nov, 20:46


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ‼️

በአንድ ወቅት በድህነት ውስጥ የሚኖር አንድ ቤተሰብ ነበር፡፡ በቤተሰቡ ውስጥ እናት፣ አባት እና አንድ ሴት ልጅ ነበረች፡፡ ከቤተሰቡ ውስጥ ገቢ የነበረው አባት ብቻ ነበር፤ ነገር ግን መሰረታዊ ፍላጎትን (ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያ) ለማሟላት በቂ ነበር፡፡

አባት ምንም እንኳን በቂ ገንዘብ ባይኖረውም ሁሌም የሚያልመው ልጁን የአለማችን ምርጥ ዶክተር ማድረግ ነበር፡፡ እጅግ ከሚባለው በላይ ይወዳታል፡፡ እሷም መልካም ልጅ ነበረች፡፡

የHigh School ውጤቷን በተቀበለችበት ቀን አባት ከሚባለው በላይ በመደሰቱ "ዛሬ በአንቺ ኩራትና ደስታ ተሰምቶኛል፤ እንድገዛልሽ የምትፈልጊውን ማንኛውንም ነገር ጠይቂኝ" አላት፡፡

ልጅ መለሰች"Papa ባለፈው ያሳየውህን ቀሚስ እፈልጋለው፤ ግን ዋጋው 1500 Dollar ነው፤ የዛኔ እንድትገዛልኝ አልጠየኩህም፤ ነገር ግን አሁን ተገዛልኛለህ?" አለች፡፡

አባት በመደሰቱ እና ልጁ ተከፍታ ማየት ስለማይፈልግ ብቻ ያን ቀሚስ የሚገዛ ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ እንኳን እንደሚገዛላት ቃል ገባ፡፡

በቀጣዩ ቀን አባት ያንኑ ቀሚስ ገዝቶ ስጦታ ሰጣት፡፡ እናት ይህን ስትመለከት ያን ያህል ገንዘብ እንደሌለው ስላወቀች ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው ጠየቀችው፡፡

አባት እንዲህ ሲል ተደመጠ "ያጠራቀምኩት ትንሽ ገንዘብ ነበር፤ በተጨማሪ ደሜን ሸጬ ባገኘውት ገንዘብ ነው፡፡ ምክንያቱም ልጄን ማናደድ አልፈልግም፡፡"

ከግዚያት በኀላ ልጁ የጤና ትምህርት ቤት ገባች፡፡ አባትም ለእሷ የሚያስፈልጉ ክፍያዎችን መክፈል ያስችለው ዘንድ ከወትሮው በበለጠ ጠንክሮ መስራት ጀመረ፡፡

የመጨረሻ አመቷ ላይ ደረሰች፡፡ ለሁሉም ነገር የሚከፈል 80000 Dollar ያስፈልጋታል፡፡ አባት በቂ ገንዘብ ባይኖረውም እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ያን ገንዘብ ከፈለ፡፡

እናት አሁንም ያን ያህል ገንዘብ እንደሌላቸው ስለምታቅ "ያን ገንዘብ ከየት ነው ያመጣኸው? ያን ገንዘብ ለማግኘት መጥፎ ነገር አረክ እንዴ?" በማለት ጠየቀች፡፡

"አይደለም የሆነ ኩላሊቱ ከጥቅም ውጭ የሆነበት ሰው ነበረ፤ እና አንዱን ኩላሊቴን ሸጥኩለት፡፡ አደራ ለልጃችን እንዳትነግሪያት፤ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማታል፡፡" አለ አባት፡፡

ዛሬ የልጃቸው የመመረቂያ ቀን ነው፡፡ እናትና አባት ሴት ልጃቸው ለመጀመሪያ ግዜ #ዶክተር ሁና ወደ ቤቷ ልትመጣ በጉጉት እየጠበቋት ነው፡፡ ነገር ግን ልጃቸው ዶክተር ሆና ሳይሆን አሰከሬን ሆና ወደ ቤት መጣች፡፡ የምታፈቅረው ሰው በእሷ ላይ ከሌላ ሴት ጋር ስለማገጠባት እራሷን አጠፋች፡፡ እስቲ መልሱልኝ አሁን የሞተው ማነው? እሷ ወይስ ቤተሰቦቿ? በተለይ አባቷ የሞት ሞትን ነው የሞተው፡፡

ወዳጄ ህይወትክ ያንተ ብቻ መስሎክ ከሆነ ተሳስተሀል፡፡ መኖርክ እንኳን ባይጠቅማቸው መሞትክ የሚጎዳቸው ቤተሰቦች አሉክ፡፡ ስለዚህ PLS እራስክን በሲጋራ፣ ጫት፣ አልኮል ውስጥ ደብቀህ በቁም ሙተክ በቁም አትቅበራቸው፡፡

ወዳንቺ ደሞ ልምጣ እህቴ፤ አንቺ እራስሽን ብታጠፊ ፍቅረኛሽ ሌላ ሴት ያገኛል፤ ቤተሰቦችሽ ግን ሌላ ልዕልት ልጅ አያገኙም፡፡

ስለዚህ ሁሌም በህይወታችን ላይ ለመወሰን ስንነሳ እኛን በማሳደግ የጎበጠችው እናታችን፤ እኛን በማሳደግ በውርጭና በፀሀይ ፊቱ የከሰመው አባታችን ይታወሱን፡፡

#መልካም ምሽት

https://t.me/Abalibanos333

ለኛ ለወጣቶች ምክር ነክ ፁሑፍ

ቤተ ሊባኖስ ₃

26 Nov, 20:40


የሰው ልጅ የተፈጠረበት አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ምሳሌነታቸው እንደምንድን ነው ቢሉ፦

#እሳት️ ፡- በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ይመሰላል። ለምን ቢሉ እሳት ፈቃድ ፈጻሚ ነው አንድ ቦታ ላይ ብንጭረው ሃገርን ሊያወድም ይችላል እግዚአብሔርም ሁሉን ማድረግ የሚችል ምንም ማይሳነው አምላክ መሆኑን።

#ውሃ ፡- በእግዚአብሔር ርህራሄ ይመሰላል። ውሃ እድፍን እንደሚያጠራ በኃጥያታችን ተጸጽተን ንስሐ ብንገባ ይቅር ሊለን፣ ከኃጢአታችን ሊያነጻን የታመነ መሆኑን።

#ንፋስ፡- በእግዚአብሔር ፈራጅነት ይመሰላል። ንፋስ ገለባውን ከስንዴ እንደሚለይ እግዚአብሔርም በዳግም ምጽዓት ጊዜ ኃጥኡን ከጻድቁ በእውነተኛው ፍርዱ የሚለይ መሆኑን።

#መሬት (#አፈር):- በእግዚአብሔር ታጋሽነት ይመሰላል። መሬት ጥቁር፣ ቀይ፣ ወፍራም፣ ቀጭን ፣ ኃጥእ፣ ጻድቅ ሳትል ሁሉንም ችላ ትኖራለች ፈጣሪም እንዲሁ በማንነታችን ሳይለየን የሚታገሰን መሆኑን።

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Nov, 17:47


የልደት የገና ድራማዎችን ና ጭዉዉት የምትፈልጉ አባላት ካላችሁ በዉስጥ መስመር አዋሩኝ ግን በፁሑፍ የለንም በድምፅ ነዉ አስገራም ጭዉዉትም አሉ @DA121922

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Nov, 17:12


የእግዚአብሔር ጊዜ


እግዚአብሔርን የሚጠብቁ እጆች አያፍሩም እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ባሟላልን ጊዜ እርሱን የምንረሳበት ምክንያት የእግዚአብሔርን እጅ አለመጠበቃችን ነው ባርክልኝ አለማለታችን ነው።

ተመልከቱ እግዚአብሔር እርሱን ተስፋ ያደረጉትን መቼም አይጥልም

አሁን ባሳለፍነው ሳምንት አንድ የውጪ ዜጋ አሜሪካዊ በአሜሪካ በተነሳው አውሎ ነፋስ ምክንያት ሁሉም ሰው ሀገሩን ለቅቆ በሚሄድበት ጊዜ እርሱ ግን አንድ እግር የሌለው ቢሆንም ተስፋው በእግዚአብሔር ነበረ።

ሰማይ ምድሩን ያናውጽ የነበረው አውሎ ነፋስ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ስለሆነ ምንም አልሆነም ያመንኩት አይጥለኝም ሲል ለሀገሩ ነዋሪዎች ምላሽ መልሶ ወደ አንድ ጀልባ ወጥቶ በዚያ ተጠቀመጠ ይህ አውሎ ነፋስ ብዙ ነፍሳትን ሲቀጥፍ ይህ እግዚአብሔር ተስፋዬ ነው አይጥለኝም ጋሻዬ ነው

መከታዬ ነው
ኃይሌ ነው
ጉልበቴ ነው
ሙላቴ ነው እንዳለው ሰው ሁሉ ስለ እርሱ ሲጨነቅ ምንም ማድረግ ባይችልም እርሱ ተስፋውን የጣለበት አምላክ ተስፋውን አለምልሞ ዛሬ ለምስክርነት በህዝቡ ፊት ቆሞ አምላኳን የረሳች አሜሪካ ፊት ስለ እግዚአብሔር በሙሉነት ይመሰክራል እግዚአብሔር በህይወቱ የሰራለትን በኩራት ይናገራል ።

እግዚአብሔር በህይወታችን ሲሰራ የእውነት ነው
እግዚአብሔር በህይወታችን ሲገባ በበረከት ነው አይሆንም ያልነው እያስገረመን ይፈጸማል ።

ብዙ አላልፍም ያልነው ፈተና እንደቀላል ወደኋላ ይቀራል
አሁንስ ተስፋዬ ማነው እግዚአብሔር አይደለምን ያለው ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በህይወቱ የተደረገውን ድንቅ እውነት ተመልክቶ ነው

እኔ ኃጢተኛ ነኝ የሰው ደም በእጄ ፈሷል ብሎ ተስፋ ሲቆርጥ እግዚአብሔር በልጅህ መቅደሴ ይሰራል ብሎ ተስፋ ሰጠው እግዚአብሔር መቼም ቢሆን በህይወታችን በሰጠነው ቦታ በሚያስደንቅ ለውጥ ይሞላናል

የልባችንን መሻት ያያል ቅዱስ ጳውሎስ ያስገርመኛል እግዚአብሔር ግን ዓላማ ነበረው በርሱ እርሱ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲወገር የወጋሪዎቹ ልብስ ያዥ ነበረ እግዚአብሔር ግን ያየው ልቡን ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲወገር እያሰበ የነበረው የእግዚአብሔር ፈጣሪ ተቃዋሚ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተወገረ እግዚአብሔር ከበረ ብሎ ነበረ እያሰበ የነበረው እግዚአብሔር በአገልጋዩ የፈጸመውን በድል ሳይሆን ያየው የልቡን ለእግዚአብሔር ተገዢነት ነው ለዚህም ነው በደማስቆ በፍቅር የማረከው

እኛም በእግዚአብሔር ተስፋ ከመቁረጣችን በፊት ለእግዚአብሔር በልባችን ቦታ እንስጥ የዚያኔ ህይወት በአዲስ መልክ ይጀምራል ይፈካል

በህይወት እስካለን በጸሎት እንትጋ ከወዳጅ መሳይ ጠላት ዲያብሎስ ይጠብቀን አሜን


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

23 Nov, 19:10


https://www.tiktok.com/@da121922?_t=8qLMpESxmcf&_r=1

ቤተ ሊባኖስ ₃

23 Nov, 05:54


🧲 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቻናል

📚 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት ብራና እና ወረቀት በpdf
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ
📜 ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች
የግእዝ ቋንቋ ትምህርት
🎶 የኦርቶዶክስ የመዝሙር ግጥሞች
📙 ተከታታይ ትምህርቶች
📘 ስንክሳር የእየለቱ
📗 ብሂለ አበው
📓 መንፈሳዊ ተረኮዎች
📔 የአበው ምክር
📚 የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች
🤵‍♂የመምህር ምህረተአብ አሰፋ ቻናል

የፈለጉትን መርጠው ይቀላቀሉ

🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖

ቤተ ሊባኖስ ₃

22 Nov, 18:04


🟣ፊላታዎስ ሚዲያ🟣

⛪️የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ስረዓቱን እና ደምቡን ጠብቀው የተዘጋጁ ዝማሬዎች እንዲሁም የተለያዩ ትምህርቶችን መንፈሳዊ የቅዱሳን አባቶች ታሪኮችን የሚያገኙበት ፊላታዎስ ሚዲያ
በዚህ ሚዲያ እግዚአብሔር በረዳን መጠን
👉 የተለያዩ የአውደምህረት ስብከት ዝማሬ
👉  አዳዲስ ዝማሬ የሚያገኙበት
👉 የቅዱሳን አባቶች ታሪክ የሚያገኙበት ሚዲያ ነው‼️

የተዋህዶ ልጆች  ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ አገልግሎቱንም ያበረታቱ
              👇🏽👇🏽
https://youtu.be/qE-CX-_SDY4

ቤተ ሊባኖስ ₃

22 Nov, 17:35


⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
                      ይቀላቀሉን                   

ቤተ ሊባኖስ ₃

18 Nov, 20:10


+ እርግጠኛ ነበርኩ +


ከአንድ ከባድ ጦርነት በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፡፡

አለቃውም "ይኑር ይሙት ለማይታወቅ ሰው ብለህ
ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም"
በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡

ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ ከፍለጋው በኋላ እጅግ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል።

አለቃውም በንዴት "ይሞታል ብዬህ አልነበረም?
ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ.. አንተ ራስህ ልትሞት እኮ ምንም አልቀረኽም?"  በማለት ይወቅሰዋል፡፡

ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበርና ወቀሳውን ከምንም ሳይቆጥር አለቃውን "
አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም
ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሼ ያለኝን ብትሰማ እንዲህ ባልተናገርከኝ ነበር " ይለዋል።

አለቃውም "ምን አለህ?" ሲለው

ወታደሩም በፈገግታ እና በሀዘን
" እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ"



በእውኑ ልብ የሚነካ ጓደኝነት ነው። ወዳጄ ያንተስ ጓደኛህ የት ነው? በሀጢያት ሞቶ

" አረ እሱንስ ተወው ቢመጣም መንፈሳዊ ህይወት የለውም "

ተብሎ  ተስፋ የተቆረጠበት  በሜዳ ላይ የወደቀ ይሆን? ምን አልባት ልክ ሆኜ ከሆነ ከመሞቱ በፊት ተስፋ ያረጋሀልና ድረስለት ለምን ብቻህን ትኖራለህ እሱን ማታስበው እስከ መቼ ነው? ሄደህ ፈልገው ምን አልባት ብዙ መስዋት ያስከፍልህ ይሆናል ምን አልባትም ቆስሎ አልያም ሞቶ ታገኘው ይሆናል አንተ ግን ከመፈለግ አትስነፍ አንተ ብቻ እሱን ይዘኸው ለመምጣት ያብቃህ እንጂ እናትህ ቤተክርስቲያን ቢቆስልም ታክመዋለች ቢሞትም ሞትን ድል የነሳ ጌታ አሷጋ ነውና ከሞተ ታነሳዋለች ብቻ አንተ ይዘኽ ለመምጣት ያብቃህ!!

ወይስ ወዳጄ  ወዳቂው ራሱ አንተ ትሆን?
 
ምን አልባት አንተ ራሱ ወዳቂው ሆነህ ከተገኘህ ሰዎች የሞተ ነው ተስፋ የለውም ብለውህ ከሆነ እኔ መፍትሔ ልንገርህ።  አኪያ ብለህ ተጣራ መፍትሔ ታገኛለህ። አኪያ ማለት እግዚአብሔር ጓደኛዬ ነው ማለት ነው። አየህ ሰው ራሱን ራሱን እያለ ፈፅሞ ላያስታውስህ ይችላል ፈፅሞ የማይረሳ እግዚአብሔር ነውና እሱን ጓደኛ አድርግ እሱስ ይከብደኛል ካልከኝ  እሺ ይሁን ለሁሉ አዛኝ የሆነች በርህራሄዋ ና በትህትናዋ አምላክን እስከ መውለድ የበቃች አንዲት የህያዋን እናት አለች። እሷን እናት አድርጋት

"ድንግል ሆይ አለም ከተባለች የጦር ሜዳ በኃጢያት ቁስል ወድቄ ለሞት ቀርቤያለሁና ድረሽልኝ። ድንግል ሆይ ወደ ልጅሽ መሄዱን መች ጠላሁ ነገር ግን በአለም ሀሳብ ዝዬ ደክሜያለሁ ለዚህም ደጋፊ ጓደኛ ረዳት የለኝምና እናቴ ሆይ ደግፊኝ። ከሁሉ የደከምኩ እኔን አስቢኝ ምነው ልጄን ብትጠይቀው  ምትመጣበትን ጉልበት አይሰጥህም ትዪኝ ከሆነ አሱ መች ከበደኝ ነገር ግን በልጅ ፊት እንደኔ አይነት ሀጣኖች ፀሎታቸው ይሰማላቸው ዘንድ ሞገስ የላቸውምና   አይቻለኝም ባይሆንስ በእግዚአብሔር ፊት ፀጋን የተሞላሽ ታናሿ ብላቴና አንቺ ነሽና በሱ ፊት ወዳጅህ ሜዳ ላይ ወድቋል ወደ አንተ መምጣት አቅቶታልና መምጣቱን ስጠው ብለሽ አደራ አሳስቢልኝ።  ድንግል ሆይ እኔስ እንደ ኤልሳቤጥ በእግዚአብሔር ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ የሄድኩ ሆኜ አይደለም አንቺን ማውራቴ ይልቁንም ፅድቅ የሌለኝ በእግዚአብሔር ፊት የተዋረድኩ ነኝ

ግን ቢሆንም አዛኚት ነሽና  እኔነቴን አይተሽ ፀሎቴን እንደማትተዪ አምኜ ነው አንቺን ማውራቴ። ድንግል ሆይ ከሰው ይልቅ ያንቺን እናትነት እሻለሁ እና ወዳለሁበት ነይ። ከቁስሌ እንድድን ምን አልባት ሞቼ ቢሆን እንኳን ልጅሽ አላዛር ከሞት እንዳነሳው ታነሽኝ ዘንድ እማፀነሻለሁ እንደ ምትመጪም ተስፋ አደርጋለሁ ""

ብለህ ተማፀናት ያኔ ፈጣኗ ደመና ሩሩህ የሚሆን ሚካኤልን ፍሱህ የሚሆን ገብርኤልን አስከትላ እንደ ዘመዳ ኤልሳቤጥ ልትጎበኝህ ተራራን አቋርጣ ትመጣልሀለች። አንተ ብቻ በእምነት በላት!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/Abalibanos333


ቃለ እግዚአብሔር በአቅሜ ለማድረስ እንደበረታ ስለኔ ፀልዪ።
ይህቺ ትንሽ ፅሁፍ ለሌሎች ይዳረስ ዘንድ Share በማድረግ አግዙኝ🙏

ቤተ ሊባኖስ ₃

18 Nov, 20:06


+ ትህትና +

👉 ለአንድ መነኩሴ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ተገለጸለትና "እኔ ገብርኤል ነኝ ወደ አንተ ተልኬ መጣኹ" አለው::

በዚኽ ጊዜ መነኩሴው "እስኪ ወደ ሌላ ተልከኽ እንደኾነ ልብ አድርግ፤ እኔ እንኳንስ አንተን የገዛ ኃጢኣቴን እንኳ ለማየት የበቃኹ አይደለኹም" አለው::

ይኽን ሲሰማ ከትሕትናው ፊት መቆየት የተሳነው ጠላት እንደ ትቢያ በኖ ጠፋ:: 

በእግዚአብሔር ፊት የተዋረደ ስብዕናን አላብሶ ፀሎታችንን ምፅዋታችንን ፆማችንን እና ድካማችንን ተቀባይነት የሚያሳጣው ትዕቢት ነው። እግዚአብሔር እንደ ትዕቢት የሚፀየፈው ነገር የለም።  በዚህ ምክንያት ነው ከዛ ተመፃዳቂ ፈሪሳዊ ይልቅ ያንን ልቡ የተሰበረ ኃጢያተኛ ፀሎት የተቀበለው።

ትህትና እግዚአብሔር እስከ መፀነስ ያበቃች ታላቅ መንፈሳዊ ልብስ ናትና እሷን እንልበስ። የለበስነውም የትዕቢት ልብስ ለባለቤቱ ለዲያብሎስ እንመልስ ያኔ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተን መሻታችን ይፈፀማል።

"ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።" ምሳ.፲፰፥፲፪

ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏


https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

18 Nov, 20:04


የቀጠለ


መነኩሴውም በመልሱ ቢደነቁም ንዴት ገና አለቀቃቸውምና በቁጣ እሺ " ያ ብላቴና ምን አርጎህ ነው የጎደልከው?

ወጣቱም መነኩሴም ፦  አይ ልጁ ምንም አልበደለኝም ግን እናትና አባቱ እግዘብሔርን በድለዋል ልጁን የወለዱት ያለ ህግ በዝሙት ነውና የእግዚአብሔር መንፈስ የተለየው ነው። በዚህ ምክንያት ሲያድግ እናቱን እና አባቱን ገዳይ ቤተክርስቲያንን አስጨናቂ ይሆናል!
በዚህም ምክንያት ገደልኩት በመገደሌም ልጁን ከኩነኔ ሳድነው እናቱንና አባቱን ደግሞ ተፀፅተው ንስሐ እንዲገቡ ማድረግ ችያለው " ብሎ መለሰ።


እሳቸውም ፦  እሺ ለመጠጥ ቤቱ ሰግደህ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋይ መወርወርህስ??


ወጣቱም መለሰ ፦  " ቤተ ክርስቲያኑን እንዳዩት አርጅቷል አገልግሎት ካቆመ ዘመናት አልፎታል ። ይህን አይተው አጋንንት ሲሳለቁ ባያቸው ጠጠርን ሰብስቤ አማትቤ ወረወርኩ እነሱም እንደ ጢስ ተነው ጠፉ። በአንፃሩ ደግሞ መጠጥ ቤት ውስጥ የነበሩ 2ት ሰዎች ይቺን ቤተ መቅደስ ለመስራት እየተወያዩ ነበር። ይሄንን የተቀደሰ ሀሳባቸው እንዲፈፀምላቸው ለእግዚአብሔር ስገድኩ አላቸው።

መነኩሴው በመልሱ ተደንቀው  " ይሄ ከአንድ ወጣኔ የማይጠበቅ የቅድስና መብቃት ነው ማን ነህ ማንነትህን ንገረኝ አሉት"

መነኩሴዎም ፦ "የኔን ተውትና እርሶ ሳምንቱን ሲረብሾት የነበረው ነገር ይልቅ ይንገሩኝ"  አላቸው።


መነኩሴውም ጉዳዪን አዝነው አስረድተው ሳይጨርስ ካፋቸው ከበል አድርጎ " ያ ጨካኙ ንጉስ ምንም ጨካኝ ቢሆን የሰራው ጥቂት መልካም ነገር ነበረ እና ለዛች መልካምነት ምድር ላይ ቀብሩን ባማረ መልኩ አደርጎ ከፈለው። በሰማይ የሞት ሞት ይጠብቀዋል። እኚያ ወንድምህ እድሜ ዘመናቸውን እግዚአብሔርን ቢያገለግሉም ጥቂት በደልን በድለዋልና ያቺን ኃጢያት ምድር ላይ የተዋረደ ሞትን እንዲሞቱ አድርጎ ለዘለአለም ፍሰሀ የደስታ ህይወት አዘጋጃቸው አሁን ለዘለአለም በደስታ ሊኖሩ ገነት ናቸው ብሎ መለሰላቸው። ከመልሱ ብኋላም በቁጣ "እግዚአብሔርን እንዴት እንደዚህ ታደርጋለህ ተብሎ የማይመረመር በስራው ስህተት የማይገኝበት አምላክ ነውና ወደ ራስህ ተመለስ! ይሄ የኔ ተገፃፅ ነው

ጌታ እግዚአብሔርም ደግሞ እንዲህ የሚል መልክት ልኮልሀል "እኔን ወንጅለህ አንተ ፈራጅ ሆንክ አሁን ያደረኩበትን ምክንያት ሰማህ ስንት አመት ምን ልትቀጣኝ አስበሀል " ብሏቸው ያ ወጣት መነኩሴ ከፊታቸው ተሰወረ።


እሳቸውም ፦ ተንበረከኩ እንባ እያፈሰሰ ያለውን ፊታቸውን ቀና አርገው ጌታ ሆይ ታዘብኩህ ብዬ ነበር። አይ አለማወቄን አይህ የጠበበ አእምሬዬን

ታዘብከኝ አይደል ይቅር በለኝ አሉት።

¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤

እኛስ እግዚአብሔርን ያደረገበትን ምከንያት ሳናውቅ ስንቴ ወንጅለነዋል ስንቴስ ከሰነዋል? እንዲህ አይነት ስብዕና ያለን ሰዎችስ በሀሰት ከሚወንጅሉ ከአይሁድ በምን ተሻልን? ክርስቶስን ከሰደቡ ከሮማውያንስ በምን በለጥን? እነሱ አምላክን ፍጡር ብለው ሰደቡ እኛ ደግሞ ፍትሀዊውን አምላክ ፍትህ የጎደለው ለአንዱ የሚያዳላ አንዱን ሚበድል በከንቱ የሚመራ ንጉስ አላደረግነውምን? ከዚህ ተግባራችን እንደ መነኩሴው ታዘብከኝ አይደል ብለን መመለስ ይገባናል! 


ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

18 Nov, 20:03


+ ታዘበከኝ አይደል +


15 መቶ ክፍለ ዘመን በግብፅ ቤተክርስቲያን ምንኩስናን ከተቀበሉ መነኮሳት መካከል አባ ሙሴ ሚባሉ አንድ መነኩሴ ነበሩ። 
መነኩሴው የእለት ተግባር የሆናቸውን በበረሀው ለሚኖር ለአንድ ባህታዊ ቁራሽ እንጀራ ለማቀበል በሚሄዱበት ወቅት የሀገሩ ንጉሥ ሞቶ ህዝቡ እያለቀሱ ካህናቱ በፀሎት አስክሬኑን በማረ በተዋበ ስርዐት ለመቅበር ሲሄዱ ያያሉ። በልባቸውም ይሄ ጨካኝ ምንም ርህራሄ የሌለው ንጉስ ነው እንዴት እንደዚህ ያለ ስርዐት ይገባዋል እያሉ ያጉረመርሙና መንገዳቸውን ይቀጥላሉ።  መንገዱ እጅግ አድካሚ ነበር ቢሆንም ካሰቡበት በስንት መከራ ይደርሳሉ።  ሲደርሱም እንደተለመደው እንደምን አሉ የሚል የደከመ ድምፅ ሳይሆን የጠበቃቸው የአራዊት ጩኸት የጅቦች ኮቴ እና በደም የተለወሰ ዋሻ ነበር። እሳቸውም ደንግጠው ምን እንደተፈጠረ ሲያዩ ያ ሁሌ ምግብ ሚያመላልሱለት ባህታዊ ሞቶ ስጋውን አራዊት በጫጭቀው በልተው ዋሻውንም በደም አቦራጭቀው መሄዳቸውን ተረዱ።
ውስጥቸው ነደደ። ንዴታቸው ገደብ አለፈ እና ወደ እግዚአብሔር ከባድ ቃላት መሰንዘር ጀመረ።

" በእውኑ ይሄ ፍትህ ነውን? አንተን የማይወድ በጭቃኔው ወደር የሌለውን ያ ርጉም ንጉስ በማረ ስርአት ሲቀበር። እኚህ አባት ከልጅነታቸው ጀምሮ አንተን ሲያገለግሉ የነበሩ ለአንተ ሲሉ ሁሉ ነገራቸውን ትተው ራሳቸውን ላንተ ሰተው ለኖሩ አባት ይሄ መገባት ነበረበት። በእውነት ታዘብኩህ ""

ይሄን ማጉተምተማቸውን ከጨረሱ ብኋላ የያዙትን ትተው ባዶ እጃቸውን ተመለሱ። 

በማለዳውም በፀሎታቸው መሀል ይህ ትናንት የነበረ ብስጭት ፍሬ አፍርቶ ይረብሻቸው ጀመር። ፀሎትን ሁሉ ለምን እፀልያለሁ ከኔ የበለጡ እኚህ አባት እዲህ ተዋርደው ከሞቱ እኔማ እንዴት እሆን ብለው ጭራሽ የሞቱት አባት በዚህ ሁኔታ የመሞታቸው ምክንያት ብዙ በመፀለያቸው ነው እያሉ በሀሳባቸው ማዕበል ለ 7 ቀናት ሲዳክሩ ከራሳቸው ጋርም ሲጣሉ ከረሙ።

በ 7 ተኛው ቀንም የገዳሙ አበ ምኔት እኚህን አባት ወደ ዮስጦስ ገዳም ንዋየ ቅዱስ አሲዘው እንዲያደርሱ ይልኳቸዋል። መነኩሴውም ትዕዛዙን ተቀብለው ጉዞዋቸውን በሚሄዱበት ወቅት አንድ ወጣት ያገኛሉ ወጣቱም በፍፁም የእግዚአብሔር ሰላምታ ሰላም ብሏቸው ወዴት እንደሚሄዱ ይጠይቃቸዋል።  እሳቸውም የገዳሙ አለቃ ወደ ዮስጦስ ገዳም ንዋየ ቅዱስ አድርሱ ብሎ እንደ ላካቸው ያስረዱታል። እሱም እጅግ ደስ ብሎት ንዋየ ቅዱስ ለማድረስ ከበቁማ ታላቅ አባት ኖት ስለዚህ እኔን በጣም ይረዱኛል አባኮት እሺ ይበሉኝ አጋዥ የሚያስፈልገኝ ወጣኔ (ጀማሪ መነኩሴ ነኝ ) እያለ ይማፀናቸዋል። እሳቸውም ችግር የለውም ምን ልርዳህ አሉት። እሱም እንደሚያውቁት ከምንኩስና ስርዐት አንዱ አርምሞ(ዝምታ)  ነውና እሱን ማድረግ አቅቶኛል ይላቸዋል። እሳቸውም ለዚህ ነው በል ለዚህስ ከሆነ ችግር የለውም ከዚ እስከ ዮስጦስ ገዳም የ 3 ቀን መንገድ ነው በዚህ መንገድ ላይ አብረኸኝ ሂድ 3 ቱንም ቀን እኔም አንተም ለሰዎች የእግዚአብሔር ሰላምታ ከመቅረብ በቀር በአርምሞ እንቆያለን ለዚህም ደግሞ በመሀላ ቃል እንፈፅማለን አሉት።    እሱም በእውነት ደስ ብሎኛል በዚህ 3 ቀንም ጥሩ አርጌ አርምሞን እማራለሁ ስለዚህ ቃሉን መፈፀም እንችላለን ሲል የደስታ ቃሉን ሰጥቶ ቃለ መሀላውን እሱው ይጀምራል። እሳቸውም መልካም ብለው  ቀሪውን ቃለ መሀላን ፈፅመው ጉዞዋቸውን ይጀምራሉ።

ቀን 1

እኚህ ተጓዦች በመጀመሪያ ቀን ብዙዎን መንገድ ተጉዘው አመሻሹ ላይ ከአንድ ክርስቲያን መንደር ጎራ ይላለሉ። ክርስቲያኖቹም ምግባራቸው ያማረ ነበር እና እግራቸውን ባማረ የብር ሰሀን አጥበው ምግብ እና መኝታን አቅርበው ያስተናግዷቸዋል። እነሱም አመስግነው ወደ መኝታ ይሄዳሉ። እኩለ ሌሊት ላይ ግን ይሄ ወጣቱ  መነኩሴ ከተኛበት ተነስቶ ያን የብር ሰሀን ሰርቆ ይወጣል። ይህን ድርጊቱን ያዪ እኚያ መነኩሴ ሊያስጥሉት ተከትለውት ይወጣሉ እሱ ግን ወጣትነት ረድቶት ጥሏቸው ሮጦ ከባህር ዳርቻ ጠበቃቸው እሳቸው ሲደርሱም ያንን የብር ሰሀን አይናቸው እያየ ባህር ውስጥ ወረወረው። ተበሳጩ

"ይሄ ሰይጣን ! ሌባ መነኩሴ እኔ ሰው መስሎኝ እስከትዬው ብመጣ የሰው ሰሀን ለዛው የብር ብዙ ገንዘብ የሚያወጣ እቃ ይሰርቃል። ቆይ ምን አረጉት በተቀበሉት ባበሉት ርጉም " ይላሉ በልባቸው። ዛሬ ያ መሀላ ባይዛቸው ቃል አውጥተው ሺ ቃል በተናገሩት ነበር። ነገር ግን ምንም ሊያረጉ ይችላሉ ጉዞዋቸውን ከመቀጠል በቀር !

ቀን 2

በዚህ ቀን ደግሞ ጉዞዋቸው ከትላንቱ የባሰ አድካሚ ነበር ምከንያቱ ደግሞ እጅግ አስጀጋሪ መንገድ ስለነበር ነው ። አመሻሹ ላይ እንደተለመደው ሚያድሩበት ቤት ፈልገው ተጠጉ እግዚአብሔር ረድቷቸው እንደ ቀድሞው ስነምግባራቸው ያማረ ሰዎች ገጠሟቸው። ሰዎቹም በእንግድነት ተቀብለው አብልተው አጠትተው ማደሪያን ሰጣቸው። እኑሱም ወደ ማደሪያቸው አቀኑ። እንደተለመደው በእኩለ ሌሊት ላይ ይሄ ወጣት መነኩሴ ተነስቶ ከማደሪያው ወጣ ና ወደ ዋናው ክፍል አቀና በመኝታ መደብ ላይም ያማረ ህፃንን አገኘ። ድምፁን ሳያሰማ በሁለት እጆቹ በተኛበት አነቀው።

ይህን ድርጊት ያዪት ሽማግሌው መነኩሴም እንደ እብድ ሆኑ ሊያስጥሉ ታገሉት ግን ሳይሰካ ልጁን ያ ወጣቱ መነኩሴ ገደለው። ይባስ ብሎም እጃቸውን ይዞ እጎተተ ከቤቱ ይዟቸው ወጣ።
በልባቸውም

"ሌባ ስል ጭራሽ ነፍሰ ገዳይ ነው። ወይ ጌታ ሆይ ከምኑ አገናኘኸኝ ይሄ መነኩሴ ሳይሆን ስጋ ለበስ ሰይጣን ነው። ደሞ እጄን ይይዘኛል " እያሉ ተበሳጩ። ግን አሁኑም ምንም ሊያረጉ አልቻሉም!

ቀን 3

በመጨረሻው ቀንም ይህን ወጣኔ (ወጣት መነኩሴ) በአይናቸው እየገላመጡ በሰውነታቸው ተፀይፈው ከአንድ ካረጀች ቤተ ክርስቲያን ደረሱ ወጣኔውም ከመሬት ለይ ጠጠር ለቃቅሞ ወደ ቤተ መቅደሱ ወረወረው።  በአንፃሩ ወደ ሚገኘው መጠጥ ቤት ደግም በግባሩ ተደፍቶ ሰገደ።

እኚህ መነኩሴ ከአቅማቸው በላይ ሆነና ጥለዉት እቃቸውን ይዘው ወደ ገዳሙ በብስጭት እና እጅግ በታላቅ ቁጣ ሄዱ በሩ ላይም ሲደርሱ ዞረው ቆመው ጠበቁት። ወጣኔውም መጣ።
"አንተ እርጉም የተረገምክ መነኩሴ የሚባል ማዕረግ አለኝ ምትል ስጋ ለበስ ሰይጣን .... እና የመሳሰሉትን  ንግግሮች አከታተሉበት። መነኩሴውም ምን አረኩ ይሄን ያህል ሚናገሩኝ አላቸው። ጭራሽ ጥፋተኝነት ስሜት አለመሳየቱ ይበልጥ አናዷቸው ፊታቸው ፍህም ሆነ። "ቆይ ምን ልሁን ብለህ ነው ያበሉንን ሰው ብለው የተቀበሉንን የእነዚያን ሰዎች የብር ሰሀናቸውን የሰረከው " ብለው ጮሁበት።

ወጣቱ መነኩሴም  ፦ እነዚያ ሰዎች መልካምና ደግ ቢሆኑም አያቶቻቸው ግን ርኩሳን ነበር። ከመጥፎነታቸውም የተነሳ በቤተመቅደስ በቅዳሴ ሰአት ካህኑ እጁን ሚናፃበትን(ሚታጠብበትን) ሰሀን ሰርቀው ለቤታቸው አርገዋል።  ልጆቻቸውም (የሰዎቹ አባቶች) ባለማወቅ ያን ቅዱስ እቃ ሲበሉበት ሲጠጡበት እንግዳ ሲቀበሉበት በመኖራቸው ነፍሳቸው ታላቅ ስቃይ ላይ ናት ። ስለዚህ እኔም ይህንን ንዋየ ቅዱስ ወስጄ ባህር ላይ ወረወርኩት ። ያ ወንዝ በ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ስለሚያልፍ የቤተክርስቲያኑ ዘበኛ ያገኘዋል። በጎኑ ያለውን "ይህ ንዋየ ቅዱስ ለጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተሰጠ ነው " የሚል ፅሁፍ አንብቦ ለካህኑ ያስረክበዋል። ካህኑም ዳግም አፅድተው በሜሮን አክበረው ወደ ቀደመ አገልግሎቱ ይመለሳል። በዚህም ነገር የሰዎቹ አባቶች እና የሰዎቹ ነፍስ ሰላምን ታገኛለች " ብሎ መለሰላቸው።

ይቀጥላል...

ቤተ ሊባኖስ ₃

18 Nov, 20:02


+ መመንኮሱንም አላውቅም +

ወጣት መነኩሴ ወደ አባ እንጦንዮስ መጣ። እየተማረረ እንዲህ አለ "አባቴ ሆይ ከመነኮስሁ ዓሥር ዓመታት አለፉኝ። ነገር ግን የዲያቢሎስን ፈተናውን መታገስ አቃተኝ ፣ እጅግ እየታገለኝ ነው" አባ እንጦንስም ለዚህ መነኩሴ የሚገባውን ምክርና ተግሣፅ ሠጥቶ አሰናበተው። መነኩሴው ከወጣ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ አባ እንጦንስ ቀርቦ እንዲህ አለ። "በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ ፣ ይኼ ሰው መመንኮሱንም አላውቅም"

እኛ በዲያቢሎስ ተፈተንሁ ለማለት ራሱ ገና ነን ፣ ምክንያቱም የራሳችንን ድካምና ምኞት ገና ድል አልነሣንም።

"ምንም እንደ መቅደሱ መንጻት ባይነጻ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው"  (2 ዜና 30: 19)

@Abalibanos333

ዲ/ን ወገን

ቤተ ሊባኖስ ₃

15 Nov, 15:47


#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_5

#ርዕስ ፦ ጉዞ ወደ ምድረ ግብፅ

➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ወደ ምድረ ግብጽ ሲጓዙ ሦስት ቀን ጫካ ውስጥ ሰነበቱ። በጣም ተራቡ፣ ተጠሙ። በበረሃ በረሀብና በውሃ ጥም እንዳይሞቱ እመቤታችን ጸለየች። ወዲያው የተሠራ ማዕድ የተዘጋጀ ምግብ መጣላቸው በልተው ጠገቡ። ከዚህ በኋላ #ኢንፍሎን ወደተባለ አገር ሄዱና #ርግባዳ ከተባለ ሰው ቤት ተቀመጡ። ብዙ ሰዎች ዕውቀት ፈልገው ወደ እመቤታችን ይመጡ ነበር። እመቤታችን ከጥበበኞች ከእስራኤል ሀገር ስለመጣች ብዙ ጥያቄዎችን ይጠይቋት ነበር። እመቤታችንም ብዙ ምሳሌ እየመሰለች ጥያቄዎቻቸውን ስትመልስላቸው እያደነቁ ይሄዱ ነበር።

➯ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዚያች ሀገረ ገዥ ሞተ። ቤተሰቦቹ መጥተው ለእመቤታችን ነገርዋት፡፡ እመቤታችን ስትሄድ ሞቶ አገኘችው፡፡ የሚያለቀሱትን ሰዎች "ዝም በሉ አለቻቸው።" አልቃሾቹ ዝም አሉ። በቀኝ እጅዋ ይዛ "በእግዚአብሔር ስም ተነስ አለችው።" የሞተው ሀገረ ገዥ ሕያው ሆኖ ተነሣ ለልቅሶ የተሰበሰቡት ሰዎች የጣዖቶቻቸውን ስም የመጥራት አጵሎንና አርዳሚስ ሰው ተመስለው መጡ አሉ። እመቤታችንም "እናንተ የምትሏቸው ጣዖታት አይደለሁም። ከይሁዳ ምድር ተሰድጄ የመጣሁ ሰው ነኝ" ካለቻቸው በኋላ የሞተውን ሰው ማስነሣት የሚቻለው እግዚአብሔር መሆኑን እንዲያውቁና በእግዚአብሔር፡ እንዲያምኑ፡ አስተማረቻቸው።

➯በሀገራቸው ውስጥ የሚኖሩ በሽተኞችን እየፈወሰችላቸው ጥቂት ወራት ተቀመጠች። ምድራችውን ውሃ አፈለቀችላቸውና፡ "በዚህ ተፈወሱ አለቻቸው።" የታመመ ሰውም ሆነ እንስሳ አመቤታችን ባፈለቀችው ውሃ ሲታጠብ ይፈወስ ነበር፡፡

➯ከዚህ በኋላ #ራፋን ወደተባለ ሀገር ሄዱ፡፡ የራፋን ሰዎች መለከት እየነፉ ወጥተው እመቤታችንን ዮሴፍንና ሰሎሜን በድንጋይ ቀጠቀጧቸው፡፡ እነዮሴፍም ከዚያ ሀገር ወጥተው ሄዱ፡፡ በአረብ #አንፃር_ቄድሮስ ከተባለ አገር ደረሱ፡፡ በተቃራኒው የሚጾሙ የሚጸልዩ ደጋግ ሰዎችን አገኙ። ሀገሩም በጣም ደስ የሚያሰኝ ልምላሜ የተሞላበት ሀገር ነበር፡፡ #በቄድሮስ 8ወር ተቀመጡ፡፡ ዮሴፍም እመቤታችንን "ሁሉን ነገር ትተን ከዚህ ሀገር እንቀመጥ አላት።" ሀገር ለሀገር ዋሻ ለዋሻ መንከራተቱን ትተን እንረፍ ማለቱ ነው፡፡ እመቤታችንም "ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ እዚህ መቀመጥ አንችልም" አለችው ዮሴፍን፡፡

➯በዚያች ሌሊት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ እመቤታችንን ከዚህ አገር ውጪ አላት፡፡ ከዚያች አገር ወጥተው ወደ #ደብረ_አሞር ሄዱ፡፡ የተለያየ ደዌ የያዛቸው ሰዎች ወጥተው ተቀበሏቸው። እመቤታችን ሁሉንም ፈወሰቻቸው እነዮሴፍ በደብረ አሞር በዙ ጊዜ
ተቀመጡ፡፡

➯በደብረ አሞር ወጥተው ሲሄዱ #ሌላውዳ ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በዚያም ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው አገኙ። ርኩስ መንፈስ ከያዘው 70 ዓመት አልፎታል፡፡ ሰውየው አይተኛም ሥጋውን በድንጋይ ይቦጫጭቃል በሰንሰለትም ሲታሰር ሰንሰለቱን ይሰባብራል። እመቤታችንን ባያት ጊዜ "ይቅር በይኝ" ብሎ ከእግሯ ስር ወደቀ፡፡ እመቤታችንም ርኩሱን መንፈስ "በእግዚአብሔረ ስም ውጣ አለችው፡፡" ርኩሱ መንፈስ ወጣ፡፡ ርኩሱ መንፈስ ጦጣ ይመስል ነበር፡፡ ክፉ አራዊት የርኩሳን መናፍስት መገለጫዎች ናቸው። #ዮሐንስም በእባብና በዘንዶ ዲያብሎስን ሲገልጸው እንዲህ ይላል፡፡ "«ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ»" (ራዕይ 12፥9) ርኩሱ መንፈስ የወጣለት ሰው አልለይም ብሎ እየሰገደ እመቤታችንን ተከተላት። እመቤታችንም "ወደ ዘመዶችህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ነገር ንገር" አለችው፡፡

➯እመቤታችን የተለያዩ ተአምራትን እንደምታደርግ በአካባቢው ተሰማ፡፡ አንድ ሆዱን የነፋው ሀገረ ገዢ መጥቶ "ፈውሺኝ" አላት፡፡ እመቤታችንም "በልጄ እመን ትድናለህ" አለችው፡፡ እርሱም "አምናለሁ" አለ። ከሆዱም እባብ ወጣለት፣ ከበሽታው ተፈወሰ፡፡ እነዮሴፍን ዘጠኝ ወር ያህል ከቤቱ አስቀመጣቸው፡፡

➯ከዘጠኝ ወር በኋላ ከቤቱ ወጥተው ሲሄዱ #ሌበ የሚባል ባሕር ካለበት ሀገር ደረሱ፡፡ የዚያ ሀገር ሰዎች በጅራፍ እየገረፉ አባረሯቸው፡፡ እነዮሴፍ #ቤልቤል ከሚባል ዛፍ ስር አደሩ፡፡ ነገር ግን መልአክ ወርዶ በሰረገላ ወስዶ ካሳደዷቸው ሰዎች ሀገር መካከል አስቀመጣቸው።

➯እመቤታችንም ከእንቅልፏ በነቃች ጊዜ ያደሩበት ሀገር በጅራፍ እየገረፉ ያሳደዷቸው ሰዎች ሀገር እንደሆነ አወቀች። እመቤታችንም የቅናቱ ጅራፍ ተመልሶ እንዳይመጣ ወደ እግዚአብሔር አጥብቃ ጸለየች፡፡ በጅራፍ የገረፍዋቸው ሰዎችም ከሰውነት ወደ ውሻነት ተለወጠው ውሻ ሆኑ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ሰዎች የሚቀጣበት መሣሪያው የተለያየ ነው፡፡ አእምሮ ያለውን ሰው አእምሮ የሌለው እንስሳ ያደርገዋል፡፡ ይህ አይነት ቅጣት በጣም የሚታበዩ ሰዎች የሚቀጡበት ነው።

➯የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በትዕቢቱ ምክንያት ወደ አውሬነት ተለውጦ ቤተ መንግሥቱን ለቆ ከአራዊት ጋር ሣር እየበላ ሰባት ዓመት ኖርዋል፡፡ (ዳንኤል 4፥28-34፡፡)
https://t.me/Abalibanos333

#ክፍል_ስድስት_ይቀጥላል

ቤተ ሊባኖስ ₃

15 Nov, 15:46


#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_4

#ርዕስ ፦ ተአምረ ማርያም በምድረ ጋዛ

➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲዘዋወሩ #ጋዛ ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በጋዛ የሚኖሩ ሰዎች እጅግ ክፉዎች ነበሩ፡፡ ዮሴፍ በጋዛ የሚኖሩትን ሰዎች እንዲሀ አላቸው። "በአገራችሁ ውሃ የለምን?" የጋዛ ሰዎችም እንዲህ አሉ "በሀገራችን ውሃ የለም ውሃ የምንቀዳበት ቦታ ርቀት በእግር 27 ቀን ይወስዳል፡፡ 27 ቀን ተጉዘን በግመል ጭነን አምጥተን ትንሽ ትንሽ እንጠጣለን አሉት።" የጋዛ ሰዎች ክፉዎች ስለሆኑ እንዲህ አሉ እንጂ በሀገራቸው ውሃ የሌለ ሆኖ አይደለም፡፡ የጋዛ ሰዎች ውሃ ከቀዱ በኋላ የውሃውን ጉድጓድ ዝግባ በተባለ ታላቅ እንጨት ይገጥሙታል፡፡ መንገደኞች ውሃ ሲጠይቋቸው ወይም ሲለምንዋቸው ውሃ የለንም ይላሉ፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ሕይወት ይሆን ዘንድ የፈጠረውን ውሃ የሚከለክሉ ጨካኞች ነበሩ፡፡

➯የውሃ ልመናው ያልተሳካለት ዮሴፍ እመቤታችንን እንዲህ አላት፡፡ በዚህ ሀገር የምንጠጣው ውሃ የለም፡፡ እመቤታችንም አተር የአሚወቁ የሚያበራዩ! ሰዎችን አየች። አተር ወደ ሚወቁት ሰዎች እንሂድና አተር ስጡን እንበላቸው አለችው ዮሴፍን እመቤታችን የጋዛን ሰዎች ጭካኔና ርኅራኄ ማወቅ ፈልጋለች ፡ አተር ወደሚያበራዩት / ወደሚወቁት ሰዎች ሄደው "ይህን ሕፃን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለራው ትንሽ አተር ስጡት ብለው ለመንዋቸው። የጋዛ ሰዎች ውሃ እያላቸው ውሃ የለንም እንዳሉ ሁሉ የአተሩን ልመናም አልተቀበለትም። ይልቁንም "ይህ የምታዩት አተር ሳይሆን ድንጋይ ነው" በማለት ቀለዱባቸው።"

➯ከዚህ በኋላ ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን "እንደቃላችሁ ይሁንላችሁ በያቸው አላት፡፡" እመቤታችንም "እንደቃላችሁ ይሁን አለቻቸው።" ወዲያው የሚወቁት አተር ድንጋይ ሆነ፡፡ ውሃ እያላቸው ውሃ የለንም ስላሉ ውሃቸውም ደረቀ። አገራቸውም እህልን ዕፅዋትን የማያበቅል ደረቅ ሆነ። ምንጊዜም ቢሆን ለከፉ ሰዎች የተንኮላቸው ዋጋ ይከፈላቸዋል፡፡

➯ኢየሱስ ክረስቶስ ወንጌልን በሚያስተምርበት ጊዜ ተንኮለኞች በተንኮላቸው እንደሚጠፉ እንዲህ ሲል ተናግሯል ፡ "ወራት ይመጣብሻልና ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኩሉም ያስጨንቁሻል" (ሉቃ 19፥43-44) ኢየሱስ ክርስቶስን ግብዞች ፈሪሳውያን ስለአሉባት ከተማ የተነገረ ቃል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን ሰቅለው የገደሉ የአይሁድ ከተማ ኢየሩሳሌም ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በ10 ዘመን በሮማውያን ጠፍታለች።
https://t.me/Abalibanos333

#ክፍል_አምስት_ይቀጥላል.....

ቤተ ሊባኖስ ₃

12 Nov, 20:17


እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

አዲስ የአእላፋት መርሙራት ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@janyared

ቤተ ሊባኖስ ₃

12 Nov, 11:39


#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_3

#ርዕስ ፦ ጉዞ ወደ ጥብርያዶስ

➯ከዚህ በኋላ የእመቤታችን ዘመድ የኬፋዝ ንጉሥ ወደ አለበት ወደ ጥብርያዶስ ሄዱ፡፡ እመቤታችንም ሄሮድስ እንደ ሚያሳድዳት ዘመዷ ለሆነው ንጉሥ ነገረችው:: "ንጉሡም ሄሮድስ የሚያሳድድሽ ለምን ምክንያት ነው ብሎ ጠየቃት።" "ይህን ሕፃን ለመግደል ስለሚፈልግ ነው አለችው::" ንጉሡም እመቤታችንን "ከዚህ ከእኔ ቤት ተቀመጪ አላት።" ቤተሰቦቹንም "ማርያምን ከእርሱ ቤት መኖርዋን ለማንም እንዳይነግሩ አስጠነቀቃቸው።" ሄሮድስ ግን በብዙ አገሮች እየዞረ ቢፈልጋት ሊያገኛት አልቻለም፡፡ ሄሮድስ እንዲህ ይል ነበር ማርያምን ምድር ዋጠቻትን።

➯ሄሮድስ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ያደረገው ጥረት የደከመው ድካም እጅግ ብዙ ነው። ያለውን ኃይል አሟጦ ተጠቅሟል የሚፈልገውን አለማገኘቱ ደግሞ ድካሙን ውጤት አልባ አድርጐታል።

➯ከብዙ ቀናት በኋላ ሄሮድስ ጥብርያዶስ በሚባል አገር እመቤታችን መኖርዋን ሰማ፡፡ እመቤታችን ወደ አለችበት ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ መልእክተኛ ላከ፡፡ ሄሮድስ የጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል "ንጉሥ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል #ማርያምን_ከነልጅዋ ያዝልኝ ብዙ ወርቅ እና ብር እሰጥሃለሁ በእኔ እና በአንተ መካከል ጽኑ ፍቅር ይሆናል።" ንጉሡም የሄሮድስን ደብዳቤ አንብቦ በጣም ተገረመ። እንዲህም አለ "ማርያም በእኔ ቤት መኖርዋን ለሄሮድስ ማን ነገረው መቼም ሰው አልነገረውም ሰይጣን ነግሮታል እንጂ።" የእመቤታችን ዘመድ የሆነው ንጉሥም ሄሮድስ የላከውን መልእክት ለእመቤታችን ነገራት። እመቤታችንም በጣም ደነገጠች።

➯ንጉሡም "እኔ ከሞትኩ ትሞቻለሽ እኔ ከዳንኩ ትድኛለሽ አትፍሪ ለሄሮድስ አሳልፌ አልሰጥሽም አላት፡፡" "ወትቤ ማርያም ዘፈቀደ አምላከ እስራኤል ለይኩን /ማርያምም የእስራኤል አምላክ የፈቀደው ይሁን አለች፡፡"

➯በዚያች ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ "ሲነጋ ይህን አገር ለቀሽ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሂጂ አላት፡፡ በዚያም እኔ መጥቼ ተነሺ እስክልሽ ድረስ ተቀመጪ አላት።" በነጋ ጊዜ መልአኩ የነገራትን ለንጉሡ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ደስ ብሎት የሦስት ቀን መንገድ እስከ ዛብሎን እና እስከ ንፍታሌም ድረስ ሸኛት። ከዚህ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡


#ክፍል_አራት_ይቀጥላል.....

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

11 Nov, 17:16


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

ቤተ ሊባኖስ ₃

11 Nov, 16:41


❤️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።❤️

"ማንበብ የሚችል ሁሉ ያንብ"
✏️በቀን 3 ጊዜ ትበላለህ።
✏️ገላህን መሸፈኛ ልብስ አለህ።
✏️ቀን ደክመህ ውለህ ማታ የምታርፍበት ጎጆ አለህ።

🔑እንግዲያውስ እወቅ አንተ በአለም ላይ ካሉ ከ75% በላይ ሰዎች የተሻለ ኑሮ ላይ ነህ!!!
🔑ኪስህ ውስጥ አንዳንድ የምትፈልጋቸውን ነገሮች የምትገዛበትና የምትፈልግበት ቦታ የምትንቀሳቀስበት ገንዘብ ካለህ………አንተ በአለማችን 18% ሀብታሞች ውስጥ አንዱ ነህ!!!

📌ይህችን ቅፅበት ያለ ምንም ህመም በሙሉ ጤንነት እያሳለፍክ ነው።
➡️በዚህ ሰአት በአለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ በሞት አፋፍ ላይ ሆነው የሚያጣጥሩና አልጋ ላይ ከሚሰቃዩት ውስጥ አይደለህምና እድለኛ ነህ።
🌈ይህንን መልዕክት እያነበብክና እየተረዳክ ነው???

♥️ልብ በል በአለም ላይ ከ1 ቢሊዮን በላይ ማየት ማንበብ የማይችሉ እንዲሁም የአእምሮ ህመተኞች ይህን ማድረግ አይችሉምና ከእነሱ ውስጥ አንዱ ባለመሆንህ ትልቁ እድለኛ ነህ።
💵ስለ ሌለህ ነገር እያሰብክ ከማዘን ይልቅ ቆጥረህ በማትጨርሰው የፈጣሪህ ስጦታ ደስተኛ ብትሆን ህይወትህ ደማቅ ይሆናል።

"ሁሌም ፈጣሪን እናመስግን።"
"የሰጠንን ብናውቅ የጎደለን የለም"
"አመሰግንህ ዘንድ ምክንያቴ ብዙ ነው።"

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!

ቤተ ሊባኖስ ₃

11 Nov, 16:39


የእመቤታችን የስሟ ክብር!

በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም

በአንድ ወቅት ወደ ወሎ አካባቢ ሁለት የቆሎ ተማሪዎች ሲከራከሩ አንድ አባት የይሰማሉ፡፡ መከራከሪያ ነጥባቸው አንዱ የቆሎ ተማሪ ማርያምን ብሎ ሲምል ይሰማዋል፡፡ ይህን የሰማው ተሜም ‹‹ማርያምን ብለህ፣ በሙሉ አፍህ ጠርተህ መማል ቀርቶ ስሟን መጥራት አይገባህም›› ይለዋል፡፡ ምላሽ ሰጪ ተሜ ደግሞ ‹‹እናቴ ናት ስሟን ብጠራ፣ በስሟ ብምል ምን ገዶህ››ይለዋል፡፡ ተከራካሪ ተሜም ‹‹ትሰማለህ ውዳሴዋን ሳታደርስ፣ ፍቅሯን በልቦናህ ሳታሳድር ማርያም ስትል አታፍርም? አባቶች እመቤታችን ድንግል ማርያም ብለው ቢጠሯት ውዳሴዋን አድረሰውላት፣ በፍቅሯ ብዙ ሆነውላት ነው የከበረ ስሟን የሚጠሩት›› ይለዋል፡፡

ለመሸነፍ የዳዳ ተሜ የራሱን ባዶነት የእመቤታችንን የስሟን አክብሮት በመገንዘብ ‹‹ታዲያ በስሟ ካልጠራኋት ምን ብዬ ልጥራት›› ይለዋል፡፡ አዛኜ ብለህ ጥራት ይለዋ፡፡ የእነዚህን የፍቅር ክርክር የሰሙት አባት በመሃላቸው በመግባት ‹‹ትሰማለህ ተሜ አንተም ስሟን መጥራት ፈርተህ አዛኜ ብትላት የከበረ ስሟን አክብረህላት ነው፡፡ አንተም እመቤቴ ማርያም ብትላት የከበረ ስሟን ወደህላት ነው፡፡ ስለዚህ ሁለታችሁም ልክ ናችሁ›› ብለው ሃሳባቸውን በማስታረቅ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡

ለብቻቸው እየሄዱ ‹‹አይ እመቤቴ እንኳን ለምስጋናሽ ለከበረው ስም አጠራርሽ የማልበቃ ኃጢአተኛ ነኝ›› ብለው የእመቤታችንን የሥም አጠራር ተረድተው በተማሪው ትህትና ተገርመዋል፡፡ የእመቤታችን ስም የክርስቶስን ፍርድ የሚያራራ ነው፡፡ ኃጥአን በምድር በሥጋ በሠሩት በደል፣ ጌታችን በሰማይ በነፍስ ብድራቸውን ሲከፍል፣ እነዛ በእሳት ዙፋን ፊት የቆሙ ምስኪን ነፍሳት ጌታችንን ‹‹እባክህን ስለ እናትህ ብለህ ማረን ይቅር በለን፡፡ ስለ ስሟ ተለመነን›› ይሉታል፡፡ ጌታችንም ስለ ስሟ ፍርዱን ያቀላል፡፡ በእሷ ጸጋ ያጸድቃል፡፡

ጌታችን እንኳን ለሙሉ ክብሯ፣ ለስም አጠራሯ ልዩ ቦታ አለው፡፡ የእመቤታችን ስሟ መድኃኒት ነው፡፡ አባቶቻችን እናቶቻችን ለፍቅሯ ለስም አጠራሯ ከመሳሳታቸው የተነሳ አዛኜ፣ ወለላይቱ፣ እማዋይሽ፣ ወይኒቱ ወዘተ… በማለት
ይጠሯታል፡፡

እመቤታችን እንኳን ያደረባት የመለኮት ጸጋ ቀርቶ፣ስሟ የአጋንንት መዶሻ፣ የሰይጣን ድል መንሻ፣ የዲያብሎስ ማሸሻ፣ ነው፡፡ ስሟ ሲጠራ አጋንንት ረአድ፣ በድንጋጤ መርበድበድ ስለሚይዛቸው ስም አጠራሯን ይፈሩታል፡፡

እናውቃለን ዛሬ በዘመናችን ድንቅ ሠሪ፣ አጋንንት አባራሪ የሆነችው ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ስሟ ሲጠራ አጋንንት ይቃጠላሉ፣ መሄጃ መሮጫ ያጣሉ፣ በድንጋጤ ባህር ገደል ይገባሉ፡፡ እመቤታችን በወለደችው በክርስቶስ ስም መከራ እና በአንገቷ ካራ የተቀበለችው የቅድስት አርሴማ ስም ተዓምር ከሠራ የቅድስት አርሴማን አምላክ የወለደችው የእመቤታችን ስሟ ምን ይሠራ ይሆን?

እመቤታችን በሥጋ አርፋ ቅዱሳን ሐዋርያት ለቀብር ወደ ቤቴሴማኔኒ ይዘዋት በሄዱበት ሰዓት በትዕቢት የደነዘዘ፣ የአልጋዋን ሸንኮር ለመጣል እጁን የመዘዘ ታውፋንያ በቅዱስ ገብርኤል የእሳት ሰይፍ እጁ ተጎምዶ ነበር፡፡ የእመቤታችንን የስሟ ክብር ያወቀው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የታውፋንያን እጅ በልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ በተአምራት ሊገጥምለት አላሰበም፡፡ ይልቁኑም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በድንግል ማርያም ስም በማለት ወደ ነበረበት ቦታ መልሶለታል፡፡ ቅዱስ ጴጥረስ በጌታችን ስም ሙት እያስነሳ፣ ድውያንን እየፈወሰ ድንቆችን የሚያደርግ ሊቀ ሐዋርያት ነው፡፡ ነገር ግን ከጌታው ስም በተጨማሪ የእናቱ ስም ተአምር እንደሚያደርግ ስላወቀ በተግባር አሳይቶናል፡፡

የበላዔ ሰብዕ የመዳን ምክንያት፣ የእመቤታችን የስሟ መጠራት ነው፡፡ በላዔ ሰብዕ በስሟ ተለመነ ጥሪኘ ውሃ ሠጠ፣ ከሰባ ስምንት ነፍስ ዕዳ አመለጠ፡፡ ጌታችን ለቅዱሳን ቃል ኪዳን ሲገባ የመጀመሪያው ‹‹ስማችሁን የጠራ፣ በስማችሁ የተማጸነ›› በማለት ነው፡፡ ለካ ስም መጥራት ያስገባል መንግስተ ሰማያት፡፡

በአገራችንም በውጭም ያሉ ቅዱሳኖች የተትረፈረፈ የጸና ቃል ኪዳን ከፈጣሪያቸው ተቀብለዋል፡፡ ከተቀበሉት ውስጥ አንዱ ‹‹ስማችሁን የጠራ፣ በስማችሁ የተማጸነ፣ ስሙን በስመማችሁ የሰየመ›› የሚል ነው፡፡ ጌታችንም እመቤታችንን ‹‹ስሙን /ስሟን/ በስምሽ የሰየሙ በመላእክት ፊት የከበሩ፣ በመንግስቴ ለዘላለም የሚኖሩ ናቸው›› ብሎ በስሟ ብቻ ቃል-ኪዳን ገቶላታል፡፡ ወገኔ አማላጅነቷ አይድነቀን ስሟ ብቻ መጽደቂያችን ነው፡፡ በእርግጥ ለመጽደቅ ሥራ ያስፈልጋታል፡፡ ግን ብዙዎች በስሟ ገነት ገብተዋል፡፡

ማርያም የሚለው ስሟ ብዙ ትርጓሜ ቢኖረውም እንደ አባቶቻችን አስተምህሮ ማርያም የሚለውን ስሟን በሁለት ከፍለው ትረጉሙን ይነግሩናል፡፡ ማር እና ያም!፡፡

ማር ፡- በምድር ካሉ ጣፋጭ ምግቦች አንዱ ነው፡፡ ማር በጣፋጭነቱ ብቻ ሳይሆን በመድሃኒትነቱም ይታወቃል፡፡

ያም፡- በሰማይ ያሉ ቅዱሳን የሚመገቡት እጅግ ጣፋጭ ምግብ ነው፡፡

ስለዚህ የእመቤታችን ስም በምድርም በሰማይም ላሉት ሁሉ እንደ ምግብ ጣፋጭ እና መድሃኒት ነው፡፡ ማርያም የሚለውን ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ከእመቤታችን በፊት እና በኋላ የተጠሩበት ሴቶች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-

1/ ማርያም፡- የሙሴ እህት - ዘፀ. 15-20

2/ ማርያም፡- የዮቶር ልጅ የእዝራ የልጅ ልጅ 1 ዜና.መ 4÷17

3/ ማርያም፡- የማርታና የአልዓዛር እህት - ዮሐ. 11÷1

4/ ማርያም መግደላዊት፡-ሰበት አጋንንት የወጣላት ሉቃ. 8÷2,፣ ማር. 15÷40-41

5/ ማርያም፡- የታናሹ የያዕቆብና የዮሳም እናት ማር.16÷1፣ ሉቃ. 24÷10

6/ ማርያም፡- የቀለዮጳ ሚስት- ዮሐ. 19÷25

7/ማርያም፡- የማርቆስ እናት - ሐዋ.ሥራ 12÷12

እነዚህ ከላይ ያሉት በማርያም የተጠሩ ቢሆንም የእመቤታችን የድንግል ማርያም ስም ግን ግብሯን ይጠቅሳል፡፡ ያ ማለት ቅድስናዋን ንጽህናዋን፣ መድኃኒትነቷን፣ በምድርም በሰማይም የከበረች መሆንዋን ስለሚገልጽ ልዩ ያደርጋታል፡፡

ውድ የእመቤታችን ልጆች እኛም ስሟን ልናከብር እንጂ በሆነውም ባልሆነውም ስሟን መጥራት አልያም በስሟ መማልና መገዘት የለብንም፡፡ ማርያም የሚለው ስም ለእኛ ለልጆቿ እንደ ማርዳ በአንገታችን የሚጠለቅ ጌጣችን፣ እንደ ቅቤ ከሰውነታችን የሚዋኃድ፣ ኋላም የሚያድን ከፍርድ ነው፡፡ ስለዚህ የከበረ ስሟን በአግባቡ ጠርተን አክብረን ለመክበር ያብቃን፡፡

‹‹በስምሽ ያመነውን ማን ያስፈራዋል፡፡ በልጅሽስ ያመነውን ማን የስፈራዋል፡፡ የአንበሳም ጩኸት እንደ ውሻ ጩኸት ይመስለዋል፡፡ የነብሮችም ኃይል እንደ ድመት ደካማ ነው›› አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ይቺን ቅድስት እናት እናክብር፣ እንውደዳት በፍቅር!
‹‹ስለ እመቤታችን ክብር፣ያላስተዋልነው ነገር›› ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ፡፡

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

11 Nov, 16:38


ይህን ያውቁ ኖሯል
1) በቅብዓ ሜሮን የማይከብር እርሱ ቅዱስ ሆኖ ሌላውን የሚቀድስ ክቡር ሆኖ
ሌላወን የሚያከብር መጽሐፍ ቅዱስ አንደሆነ ያውቁ ኖሯል?
2) የመጀመሪያው የብሉይ ኪዳን ነብይ አዳም ሲሆን የሐዲስ ኪዳን ደግሞ መጥምቀ
መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መሆኑን ያውቃሉ?
3) የእግዚአብሔር ስም ያልተጠቀሰበት መጽሐፍ መጽሐፈ አስቴር አንድ ጊዜ ብቻ
የተጠቀሰበት መኃ.መኃ 8፡6 ላይ መሆኑን ያውቃሉ?
4) ሃሌ ሉያ የስሙ ትርጉም አግዚአብሔር የተመሰገነ ነው ምሥጋና ለአምላክ ማለት
መሆኑን ያውቃሉ?
5) /ጴንጤ/ የሐገር ስም መሆነን ያውቃሉ? 1ኛ ጢሞ 6፡13
6) በዕለተ ዓርብ ጌታን ጐኑን የወጋው ከጌታችንም ጐን በፈሰሰ ደም በተዓምራት
የታወረው ዐይኑ የበራለት አይሁዳዊ ሰው /ሌንጊኖስ/ እንደሚባል ያውቃሉ?
7) ሊቀ ሐዋርያት ቅድስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲመረጥ ዕድሜው 55 እንደነበር ያውቁ
ኖሯል?
8) 8ቱ መጽሐፍተ ኪዳን በቤተክርስቲያን ስም በተለያዩ ጊዜያት በወጡ የመጽሐፍ
ቅዱስ ሕትመቶች ያልተመደቡበት ምክንያቱ የቀኖና ቤተክርስቲያን /የቤተክርስቲያን ሕግ
ሥርዓት/ በመሆናቸው እና በውስጣቸው በያዟቸው ምሥጢራት ምክንያት /ከካህናት
በስተቀር/ ለምዕመናነ እንዳይሠራጩ የሚል ትዕዛዝ አብነት ስለሚገኝ መሆኑን
ያውቃሉ? /መ. ሲኖዶስ ገጽ 9ዐ ረሰጠአ 81፡85 ሐዋርያዊት ቀኖናት/
9) የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ሕጋዊ ባለቤት ሄኖክስ እንደምትባል ከእርሷም 7 ልጀችን
እንደወለደ ያውቁ ኖሯል? ማቴ 13፡55 4 ወንዶችን ዮሳ፤ሳምሶን፤ ይሁዳ፤ ያዕቆብ እና
3 ሴቶችን ልጆች ወልዷል፡፡
10) ነብዩ ኤልያስ ከሞት ያስነሣው የሠራተኛዋ መበለት ልጅ ዮናስ አንደሆነ ኤልያስንም
ያገለገለው የትንቢት ጸጋ የተሰጠው መሆኑን ያውቃሉ? /መስከረም 25 መጽሐፈ
ስንክሳር/

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

10 Nov, 10:00


#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_2

#ርዕስ ፦ ሁለቱ ወንበዴዎች

➯ሁለቱ ወንበዴዎች ማለት ጥጦስ እና ዳክርስ ይባላሉ በእግዚአብሔር ቀኝና ግራ የተሰቀሉት ማለት ነው። መተዳደሪያቸው ቅሚያ ነበር፡፡ እነዮሴፍ ከገሊላ በወጡ ጊዜ ወንበዴዎች ተከተሏቸው:: በበረሃ ቢፈልጓቸው እስከ ስድስት ቀን አላገኟቸውም። በሰባተኛው ቀን አገኟቸውና ዛሬስ እግዚአብሔር ከእጃችን ጣላችሁ ብለው እየሮጡ ሄዱባቸው ስሎሜ አስቀድማ ልብሷን ጥላላቸው ሸሸች።

➯ወንበዴዎቹ ከእነዮሴፍ እጅ የተገኘውን ቀምተው ከሄዱ በኋላ ጥጦስ ዳክርስን እንዲህ አለው። ይቺ ቤት የነገሥታት ወገን ትመስለኛለች። ሕፃኑም ከነቢያት አንዱ ይመስለኛል። የቀማናቸውን እንመልስላቸው ዳክርስም ጥጦስን እንዲህ ያለውን ርኅራሄ ከየት አገኘኸው ይህን ውንብድና ያስተማርከኝ አንተ ነህ። ሊላው ደግሞ ዛሬ የቀማነው የእኔ ድርሻ ነው የራስህን ድርሻ ወስደህ የእኔን ድርሻ እንመልስላቸው ትላለህ አለው።

➯እነዚህ ሁለት ቀማኞች አንድ ቀን የቀሙትን አንደኛው ሲወስድ በሌላ ቀን የቀሙትን ደግሞ ሁለተኛው ይወስድ ነበር። በዚህ ዕለት የቀሙት የዳክርስ ድርሻ ነበር። ጥጦስም ከገሊላ እስከዚህ የቀማነውን አንተ ውሰድ ይህን ለእኔ ስጠኝና ልመልስላቸው አለው፡፡ ዳክርስም በዚህ ሐሳብ ተስማማ፡፡ ዳክርስ የልታደለ ሰው ነው። ጥሩ እድል ገጥሞት ነበር አልተጠቀመበትም፡፡ በትንሽ ርኅራኄ ብዙ በረከት አመለጠው ወደ እርሱ ያንዣበበውን ፀጋ ለጓደኛው ሰጠው።

➯እመቤታችን ሁለቱ ወንበዴዎች ቆመው በዚህ ሐሳብ ሲወያዩ እይታ ፈራች። ወንበዴ አዩኝ አላዩኝ ብሎ የቀማውን ይዞ ይሄዳል እንጂ ለምን ቆሞ ይማከራል : ምን አልባት ልጆቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ይሆናሉ። በዚህ ሕፃን ምክንያት ልጆቻችን ሞቱብን ብለው ልጄን ሊገሉብኝ ይሆናል ብላ ጽኑ ለቅሶን አለቀሰች። ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስም እናቱን ድንግል ማርያምን እንዲህ አላት አይዞሽ እናቴ አታልቅሺ አይገሉኝም እንመልስላቸው እያሉ ነው። እኔ በቀራንዮ ስሰቀል እነሱም በቀኜ እና በግራዬ ይሰቀላሉ አንዱ አምላክነቴን አምኖ ይድናል ሁለተኛው ግን አይድንም፡፡

➯ከዚህ በኋላ ጥጦስ የተባለው ወንበዴ ገንዘባቸውን መለሰላቸውና ጌታን አቅፎ ይዞ ሲሄድ ሰይፉ ወድቆ ተሰበረበት፡፡ በጣም አዘነ፡፡ ጌታ የሰይፍህን ስባሪ ሰብስብ አለው፡፡ ጥጦስ የሰይፉን ስባሪ ሰበሰበ፡፡ ጌታም እንደቀድሞው ይሁንልህ አለው፡፡ ሰይፉም እንዳልተሰበረ ሆነ፡ጥጦስ ሕፃኑ ከነቢያት ወገን : ይመስለኛል ብሎ የገመተው ግምት እውን ሆነለት፡፡ ተአምራቱን አየና አደነቀ፡፡

➯ጌታም ጥጦስን እንዲህ አለው አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ፡፡ ጥጦስም ሄዶ ጌታ የነገረውን ሁሉ እና ያደረገለትን ተአምራት ለጓደኛው ነገረው ግን ጓደኛው ዳክርስ አላመነም፡፡ ጥጦስ የተባለው ወንበዴም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ በጌታ ቀኝ ( ተሰቅሎ : ፀሐይ : ስትጨልም : አይቶ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት አምኖ «ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ» አለው። "ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው።" (ሉቃ 23:42) ጌታ አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ ብሎ በጫካ የሰጠውን ተስፋ በመስቀል ላይ ፈጸመለት፡፡

➯ከዚህ በኋላ እነዮሴና ገዳመ ጌራራል ገቡ ጌራራል ከተባለ ጫካ ገቡ በገዳመ ጌራራል መላእክት እየመጡ እያጽናኗቸው 40 ቀን ተቀምጠዋል። ከ40 ቀን በኋላ አንድ አውሬ አዳኝ አያቸው እርሱም በፍጥነት ሄዶ ማርያምን እና ዮሴፍን ሰሎሜንም በጌራራል ጫካ ትናንት አየኋቸው ብሎ ለሄሮድስ ነገረው፤ ሄሮድስም በጌራራል ጫካ መኖራቸውን በሰማ ጊዜ በጣም ደስ ተሰኘ። ይህን ወሬ ላመጣለት አውሬ አዳኝ እነዮሴፍን ካሳየኸኝ የመንግሥቴን አኩሌታ እሰጥሃለሁ ብሎ በጣዖቱ ማለለት፡፡ ሄሮድስ በሀገሩ ሁሉ አዋጅ ነገረ መልእክተኛ ላከ፡፡ አዋጅ ነጋሪው በየሀገሩ እየዞረ "ሁላችሁም የሄድሮስ ወታደሮች ነገ በሄሮድስ ቤተ መንግሥት እንድትገኙ" በማለት አስጠነቀቀ።

➯ወታደሮቹ የሄሮድስን ቤተመንግሥት አጥለቀለቁት። ሄሮድስም ወደ ጌራራል ጫካ ላካቸው፡፡ የሄሮድስ ወታደሮች የጌራራልን ጫካ ከበቧት፡፡ ነገር ግን እነዮሴፍን አላገኝዋቸውም፡፡ ወታደሮቹ እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ እነዮሴፍ የት ሄዱ ምድር ዋጠቻቸውን እነዮሴፍን ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ የሄሮድስ ሠራዊት በማያውቁት መንገድ ወሰዳቸው።

https://t.me/Abalibanos333

#ክፍል_ሦስት_ይቀጥላል.....

ቤተ ሊባኖስ ₃

09 Nov, 16:15


🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ቤተ ሊባኖስ ₃

09 Nov, 02:40


#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_1

#ርዕስ ፦ የእመቤታችን ልደትና ስደት

➯እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችው በደብረ ሊባኖስ ተራራ ነው:: ድንግል ማርያም በእናቷ በሐና ማሕፀን ከተጸነሰችበት ቀን ጀምሮ የተለያዩ ተአምራትን ታደርግ ነበር። በማሕፀን ሳለች ካደረገቻቸው ተአምራት ሁለቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡

➯ - በአንደኛው ዓይኗ ማየት የተሳናት ቤርሳቤህ የተባለች የሐና አክስት ጐረ ቤት ነበረች። እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን የጸነሰችውን የሐናን አካል በእጅዋ ነክታ /ዳብሳ/ እጅዋን መልሳ ማየት የተሳነውን ዓይኗን በነካችው ጊዜ ቦግ ብሎ በራላት፡፡ ይህ አንደኛው ተአምር ሲሆን።

➯ - ሁለተኛው ደግሞ እንደሚከተለው ነው፡፡ የሐና የአጐቷ ልጅ የሚሆን ሳምናስ የተባለ ሰው ሞተ፡፡ ሐና ለልቅሶ ተጠራች። ሐና ከሞተው ሰው ቤት በገባች ጊዜ ጥላዋ በሞተው ሰው ላይ ወደቀበት። የሞተው ሰውም ሕያው ሆኖ ተነስቶ እንዲህ አለ "«ኦ እሙ ለፀሐየ ጽድቅ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ» ሰማይን እና ምድርን የፈጠረ ጌታን የምትወልድ የቅድስት ድንግል ማርያም እናት የሆንሽ ሐና ሆይ ሰላምታ ይገባሻል፡፡" ለልቅሶ የተሰበሰቡት እስራኤላውያን ይህን ተአምር አይተው በቅንዓት ተቃጠሉ፡፡

➯ኢያቄም እና ሐና የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን እንደሚወልዱ ባያምኑም እንኳ አንድ ተአምረኛ ልጅ እንደሚወልዱ ገምተዋል። ቀናተኞች እስራኤላውያን እንዲህ አሉ ከዚህ በፊት ከነገደ ይሁዳ የተወለዱ እነዳዊት እነሰሎሞን በእኛ ላይ ነግሠው አርባ አርባ ዓመት ገዝተውን ነበር። ዛሬም ከኢያቄም እና ከሐና የሚወለደው እኛን ሊገዛ ይችላል። ስለዚህ ተአምረኛውን ልጃቸውን ከመውለዳቸው በፊት ኢያቄምን እና ሐናን እንግደላቸው በማለት መከሩ።

➯የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ኢያቄምን እና ሐናን ይህንን አገር ለቃችሁ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሂዱ አላቸው:: ኢያቄም እና ሐና ወደ ደብረ ሊባኖስ ተሰደዱ፡፡ በስደት ላይ እያሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ሊባኖስ ተወለደች። ከወላዶቿ ጋር ሦስት ዓመት ተቀመጠች። ከዚህ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ተወሰደች። በቤተመቅደስ 12 ዓመት ኖረች። የ15 ዓመት ልጅ ስትሆን ሽማግሌው ዮሴፍ ይጠብቃት ዘንድ ወደ ዮሴፍ ቤት ሄደች። በዮሴፍ ቤት ሳለች የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶን በመንፈስ ቅዱስ ጸነሰችና በቤተ ልሔም ወለደች። ብዙ መከራና ሥቃይንም ተቀበለች፤ የአባቷ ዕጣ ፋንታ ደረሰባት።

➯የእመቤታችን ወላጆች የኢያቄም እና ሐና በማሕፀን ሳለች ሙት ያስነሳችላቸውን ልጃቸውን ለመውለድ ወደ ደብረ ሊባኖስ እንደተሰደዱ ሁሉ ቅድስት ድንግል ማርያምም የሰማይና የምድር ፈጣሪን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለወለደች ወደ ግብፅ ተሰደደች።

➯ኢያቄምና ሐና ልጃቸው በማሕፀን ተምራትን ስለአደረገች ከቀናተኞች ጐረቤቶቻቸው ዓይን ለመራቅ ነበር የተሰደዱት፡፡

➯እመቤታችን ደግሞ ልጅዋ በሰባሰገል አንደበት የአይሁድ ንጉሥ ስለተባለ ከቀናተኛው ከሄሮድስ ዓይን ለመሠወር ስደተኛ ሆነች። ከዮሴፍ እና ከሰሎሜ ጋር ሀገር ለሀገር ተንከራተተች

➯እንደ ዛሬው የፖለቲካ ስደተኛ በአውሮፕላን፣ በመኪና ወይም በባቡር አይደለም የተሰደደችው። በእሾህ እና ድንጋይ እግሮቿ እየደሙ ቀን በፀሐይ ፊቷ እየተቃጠለ ሌሊት በብርድና በውርጭ ቆዳዋ እየተሰበሰበ በረሃብ እና በጥም ውስጧ እየተጐዳ መራራውን በመከራ ጸዋ እየጠጣች ሦስት ዓመት በመንፈስ ኖራለች።

https://t.me/Abslibanos333

#ክፍል_ሁለት_ይቀጥላል......

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Nov, 19:37


💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Nov, 19:12


⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
                      ይቀላቀሉን                   

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Nov, 15:41


"ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ያላችሁ
ኦርቶዶክሳዊ Wave ውስጥ መግባት የምትፈልጉ"

❤️‍🩹=================❤️‍🩹



👇👇👇 በዚህ አዋሩኝ...🖤
@Maryamn_27
@Maryamn_27
@Maryamn_27

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Nov, 13:33


ኦርቶዶክስ ኖት ?

ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።

➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Nov, 11:58


❤️ የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ 👇

👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

👤 ሊቀ መዘምራን . ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ

👤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

👤 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

👤 ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

👤 ዘማሪ| በሱፍቃድ አንድአርጋቸው

👤 ዘማሪት ሲስተር ሊዲያ ታደሰ

👤 ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ

👤 ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ

👤 ዘማሪ ዲያቆን ብርሃኑ በቀለ

👤 ዘማሪት አዜብ ከበደ

👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ

👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ

👤 ዘማሪት ሰላማዊት በርታ

🔗የሁሉንም ዘማሪዎች ለማግኘት🎚
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ቤተ ሊባኖስ ₃

06 Nov, 15:59


+++ "አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው?" +++

በሕይወትህ ውስጥ በጣም የሚያስፈራህ ነገር ምንድር ነው? ተብለህ ብትጠየቅ ምን ትመልሳለህ? "ሞት" ልትል ትችላህ። በእርግጥ ላልተዘጋጀን ኃጥአን የሞታችን ቀን መጠየቅን ወደሚወድ አምላክ የምንሄድበት ዕለት በመሆኑ እጅግ የሚያስፈራ ቀን ነው። ይሁን እንጂ ለሰው ከተስፋ ቢስነት በላይ የሚያስፈራው ነገር የለም። ሰው ተስፋውን ያጣ ቀን ሁሉ ነገሩን ያጣል። የሚያየው ሁሉ ትርጉም የለሽ ይሆንበታል። እሳቷ ፀሐይ ጥቁር ዐለት ትመስለዋለች፣ ጣፋጩ ይጎመዝዘዋል፣ የቀናው ይጎረብጠዋል። የመኖር ጉጉቱ ሁሉ ይጠፋል። ተስፋ ስትቆርጥ ሞት ወደ አንተ እስኪመጣ ድረስ አትጠብቅም። አንተ ወደ ሞት ትገሰግሳለህ። ታዲያ ለሰው ልጅ "ተስፋ ከመቁረጥ" በላይ ምን የሚያስፈራ ጠላት ሊኖረው ይችላል?

በሰው ሕይወት ውስጥ "ተስፋ" ትልቅ ገፊ ኃይል ነው። ማናቸውንም የዕለት ሥራዎቻችንን የምናከናውነው ባለ ተስፋ ፍጥረት ስለሆንን ነው። ለዚህም ነው መዝሙረኛው "ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች" ሲል የሚዘምረው።(መዝ 16፥9) ደስታም ያለው በተስፋ ውስጥ ነው። ሰው በወደቀ ጊዜ አዝኖ የማይቀረው "እነሣለሁ" ብሎ ተስፋ ስለሚያደርግ ነው። በገጠመው ከባድ ኃዘን የማይሰበረው የተስፋን ምርኩዝ ስለሚይዝ ነው።  ይህ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ሊደገፈው የሚገባ የማይሰበር የተስፋ ምርኩዝ ማን ነው? ይህ ሊጠፋ የሚጤሰውን የተስፋ ጥዋፍ እንደ አዲስ የሚያበራው፣ ተቀጥቅጦ የደቀቀውንም የተስፋ ሸንበቆ ጠግኖ ወደ ቀድሞ ማንነቱ የሚያድሰው ኃያል እርሱ ማን ነው?

"መድኃኒታችን እግዚአብሔር ተስፋችን ኢየሱስ ክርስቶስ" አይደለምን!!! (1ኛ ጢሞ 1፥1)

ክርስቲያኖች በራሳቸው ማስተዋል ወይም በሀብታቸው አይደገፉም። እንደ እነርሱ ተሰባሪ በሆነ ሰው ላይም ተስፋቸውን አያደርጉም። የክርስቲያን ተስፋው "የተስፋ አምላክ" ክርስቶስ ነው።(ሮሜ 15፥13) ክርስቶስን ለምን ተስፋ እናደርጋለን? "ሁሉ በእርሱ ስለሆነ፤ ከሆነውም አንዳች እንኳን ያለ እርሱ የሆነ" ስለሌለ፣ ኃይልና ችሎታ በእጁ ስለሆነ፣ ያጎበጠንን ሸክም አራግፎ ሊያሳርፈን "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሎ ስለ ጠራን፣ ወደ ጠራን አምላክ ቀና እንላለን።(ዮሐ 1፥3፣ 2ኛ ዜና 20፥6፣ ማቴ 11፥28) እርሱን ተስፋ ብናደርግ እንደ ሰው አይለወጥብንም። እስከ ሽበት እንኳን ተሸክሞን አይሰለቸንም።(ኢሳ 46፥4) ነፍሱን እስኪሰጥ ስለወደደን፣ በብዙ ሕማም በእጁ መዳፍ ላይ ስለቀረጸን ፍቅሩ ቀዝቅዞ ጨርሶ ሊረሳን አይችልም።(ኢሳ 49፥16)

በቸገረህ ጊዜ ብርና ወርቅ የለኝም ብለህ ተስፋ አትቁረጥ። "ሁሉን የሚችል አምላክ ወርቅና የሚብለጨለጭ ብር ይሆንልሃል"።(ኢዮ 22፥25) ስትታመምም "ማን ይረዳኛል?" አትበል። እግዚአብሔር በሕመም አልጋ ሳለህ ይረዳሃል። በበሽታህም ጊዜ አልጋህን እያነጠፈ ይንከባከብሃል።(መዝ 41፥3) እርሱ ካልተውከው አይተውህም፣ ካልሸሸኸው ከአንተ አይርቅም። ተስፋ ቆርጠህ ከሕይወትህ ካላስወጣኸው አንተን መፈለግ አይደክመውም።

ሰይጣን በአንድ ኃጢአት ደጋግሞ በጣለህ ጊዜም ፈጥነህ ተስፋ አትቁረጥ። የፈጣሪህንም መሐሪነት አትጠራጠር። ለጠላትህም እንዲህ በቀላሉ እጅ አትስጥ። ስለዚህ ነገር በገነተ አበው (Paradise of fathers) የተጻፈን ታሪክ እስኪ  እናስታውስ። ሰይጣን በተመሳሳይ ኃጢአት  ብዙ ጊዜ እያሰነካከለ የሚጥለው አንድ መነኩሴ ነበር። ታዲያ ይህ መነኩሴ ሁል ጊዜ በአንድ ኃጢአት እየደጋገመ መውደቁ ቢያሳዝነውም፣ መልሶ ንስሐ እየገባ ፈጣሪውን "አውጣኝ" ብሎ መማጸን ግን አላቆመም ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን መነኩሴው ቆሞ መዝሙረ ዳዊት ሲጸልይ ሳለ ድንገት ሰይጣን ወደ እርሱ መጣና:- "ፊቱ ቆመህ በእነዚህ ንጹሕ ባልሆኑ ከንፈሮችህ የእግዚአብሔርን ስም ስትጠራ አታፍርም?" አለው። ያም መነኩሴ "አንተ እኔን ጨክነህ ታሰናክላለህ። እኔ ደግሞ መሐሪውን አምላክ እንዲያዝንልኝ ሳላቋርጥ እለምነዋለሁ። እስኪ ከአንተ ጭካኔ እና ከአምላክ ምሕረት የቱ እንደሚበልጥ እናያለን።" ሲል መለሰለት። ሰይጣንም የመነኩሴውን ተስፋ አለመቁረጥ ባየ ጊዜ ከእርሱ ሸሽቶ ሄደ።

የፈተና ማዕበል በሚበዛባት በዚህች ዓለም ስንኖር፣ ዐውሎና ወጀቡ ከሚያመጣው ጥፋት ለመዳን መልሕቃችንን የምንጥልበት የተስፋ መሬታችን አምላካችን እግዚአብሔር ነው።

"ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመ ቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ"

"ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ አባቶቻችን አልነገሩንም። እኛም አልሰማንም፤ አላየንምም!"

"አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን?    ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።"
                                              መዝ 39፥7

ዲያቆን አቤል ካሳሁን


https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

06 Nov, 15:58


+++ "እግዚአብሔርን የተጠማች ነፍስ" +++

ቅዱስ ባስልዮስ "ሰውነታችን ያለ እስትንፋስ መኖር እንደማይችል፣ ነፍሳችንም ፈጣሪዋን ሳታውቅ ሕያው ሆና ልትኖር አትችልም። የነፍስ ሞቷ እግዚአብሔርን አለማወቋ ነውና" ይለናል፣ እውነት ነው፤ እግዚአብሔር ሕያው ነፍስ ላለው የሰው ልጅ ሁሉ የሰጠው ትልቁ ጸጋ "እርሱን ማወቅ" ነው። ነፍስም ያለዚህ መኖር እንደማትችል ታውቃለችና ዘወትር ይህን ስትጠማ ትኖራለች። 

እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ስለ እርሱ የተጻፉ መጻሕፍትንና የተነገሩ ትምህርቶችን ማንበብ፣ መስማት ብቻ አይደለም። እነዚህ ብቻቸውን "ስለ እግዚአብሔር እንድናውቅ" እንጂ "እግዚአብሔርን እንድናውቀው" አያደርጉንም። "ስለ እግዚአብሔር ማወቅ" የመጨረሻው ዓላማችን  ወደ ሆነው "እግዚአብሔርን የማወቅ ሕይወት" የምንገሰግስበት መንገድ እንጂ ራሱን ችሎ መዳረሻና ማረፊያ ወደብ አይደለም።

"እግዚአብሔርን ማወቅ" ግን በተግባር የሚገለጥና ከፈጣሪ ጋር የምናደርገው የአንድነት ሕይወት ነው። እኛ በእርሱ፣ እርሱም በእኛ የሚኖርበት ልዩ ምሥጢራዊ ውሕደት ነው። "እግዚአብሔርን ማወቅ" ማለት ስለ እርሱ ሲነገር በጆሮ የሰሙለትን አምላክ ከብቃት ደርሶ ማየትና በፍጹም ልብ መውደድ ነው። ይህ ደግሞ ራሱ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረው የዘላለም ሕይወት ነው።(ዮሐ 17፥3)

ይህን ሕይወት ቀምሶ ያጣጣመው ቅዱስ ዳዊት "ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም። ስለዚህ ልቤን ደስ አለው" እያለ በሐሴት የከንፈሩን መሥዋዕት ለአምላኩ ያቀርባል።(መዝ 16፥8) በሌላ ጊዜ ደግሞ ይኸው መዝሙረኛ አይቶት እንደማያውቅ ነገር "ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?" እያለ በናፍቆት ይዘምራል።(መዝ 42፥1-2) ምን ማለቱ ይሆን?

የዋልያ መኖሪያ ከፍ ካለ ኮረብታ ላይ ነው። ታዲያ ይህ የበረሃ ፍየል ውኃን በተጠማ ጊዜ ምንጭ ያለው ከተራራው ግርጌ ስለሚሆን እርሱን ፍለጋ ወደታች ይወርዳል። ወርዶም ምንጩን ካገኘና ከጠጣ በኋላ፣ ወደ መጣበት ኮረብታ ሲመለስ ገና ከተራራው ወገብ ሳይደርስ አካሉ ይደክምና ውኃ ይጠማል። መልሶ ከምንጩ ወርዶ ይጠጣል። ወደ ተራራው ሲመለስ አሁንም ይጠማዋል። እንደ ገና ወደ ምንጩ ይመለሳል።(ስለ ዋልያ ውኃ መጠማት የሚሰጥ ሌላው ሐተታ እንደ ተጠበቀ ሆኖ) ታዲያ ይህን ያየ ክቡር ዳዊት ዋልያ እንዲህ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፣ ነፍሴም ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? ብሎ ዘመረ። (መዝ 41(42)፥1-2)

ይህም የቅዱስ ዳዊት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ያወቀችና ፍቅሩን የቀመሰች፣ እርሱንም መዘከር የማትጠግብ ነፍስ ሁሉ የዘወትር መዝሙር ነው።

እኛስ ስለ እግዚአብሔር ከማወቅ አልፈን፣ እርሱን በሕይወታችን ተዋውቀን፣ ፍቅሩን ቀምሰን "ተጠማሁ" እያልን በመናፈቅ የምንዘምርበት ቀን መቼ ይሆን?

በዲያቆን አቤል ካሳሁን


https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

06 Nov, 15:57


ሰውን የሚጥለው መመካቱ ነው

ወንድሜ ሆይ በሥራህ ሁሉ የታመንህ ሁን አገልጋይ ባልንጅሮችህን ውደዳቸው። ንጹሑን አረጋዊ መቼም መች አክብረው።

ወንድሜ ሆይ በታላላቆች መሃል አትቀመጥ። ተቀመጥ እስኪሉህ ድረስ ቁም እንጅ በሽማግሌዎች መካከል አትቀመጥ፤ በዝቀተኛው ማዕርግ ተቀመጥ እንጅ።

ወንድሜ ሆይ ቁጡ ወይም አንጎራጓሪ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ሐኬተኛ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ምንም ተግባር ለመፈጸም ወዲያና ወዲህ አትናወጽ። እንዳትዋረድ በሊቅ በአዋቂ መሃል አትናገር።

ልጄ ሆይ በጽድቅህ አትመካ፤ ራስህን አታመስግን፤ ሰይጣን ትምክሕትን እንዳያመጣብህ ራስህን በፈቃድህ አዋርድ እንጅ። በትዕቢትና ትምክሕት ሰዶምና ገሞራ ወደቁ። ከእግዚአብሔር መንገድም ተሰናከሉ። ትምክሕተኛውን መነኩሴ ፈተና ያገኘዋል፤ መንፈስ ቅዱስም ይለየዋል፤ የዲያብሎስ መንፈስም ያድርበታል። በሥራችሁ ሁሉ አትመኩ፤ ሁሉም ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ይሠራል እንጅ ከራሱ የሆነ ምንም የለምና። ነቢይ የተናገረውን አልሰማችሁምን? ፈጽማችሁ አትመኩ ታላላቅ ነገርንም አትናገሩ፤ ክፉ ነገርም ከአንደበታችሁ አይውጣ።

መጽሐፈ ወግሪስ - ገጽ 84-85

ቤተ ሊባኖስ ₃

06 Nov, 15:56


+++###በትሯን_ግያዝ_ያዛት###++

++++++++++++++++++++++++

በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 4፥8 ጀምሮ ስናነብ ሱማናዊቷን ሴት እናገኛለን። በእርግጥ የዚህች ታላቅ ሴት ታሪክ ጥልቅ ምሥጢራት የሚያስተላልፍ እጅግ አስደናቂ ታሪክ ነው። ይህቺ ሴት የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳዕን በሱማን ባለፈ ጊዜ ከእርሷ ጋር ተገናኝቶ እንጀራ ይበላ ዘንድ አቁማዋለች። እርሱም ብቻ ሳይኾን ባለሀብት ስለነበረች ለእርሱ ማረፍያ የሚኾን ቤት ሠርታ ሰጥታዋለች። ይህቺ ሴት ባሏ ያረጀ እርሷም መውለድ የማትችል መካን ነበረች። የሆነው ሆኖ በቅዱስ ኤልያስ ጸሎት በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ልጅ ወለደች። ይህ ልጇ ሞተ ወዲያውኑ ወደ ኤልሳዕ ሄዳ የኾነውን ሁሉ ነገረችው። ኤልሳም ደቀ መዝሙሩ ግያዝን በትሩን ሰጥቶ በሞተው ልጅ ፊት እንዲያደርግ ነገረው፤ ነገር ግን ልጁ ሊነሣ አልቻለም። የዚህችን ሴት አስደናቂ የኾነውን የታሪኳን ምሥጢር እናቆየውና ግያዝ ወደ ያዛት በትር አእምሯችንን እንላከው።

++++++++++++++++++++++++

ግያዝ የያዘው በትር የቅዱስ ኤልሳዕ በትር ነው። ጉዳዩን በእርጋታ ስንመረምረው በአእምሯችን ውስጥ አንድ ጥያቄ ሊፈጥር ይችል ይኾናል። የሙሴ በትር ባሕር ከፍሎ አልነበረምን? የኤልያስስ መጎናጸፊያ ይህን አስደናቂ ነገር ፈጽሞ አልነበረምን? እንግዲህ እንዴት የኤልሳዕ በትር ሙት ማሥነሣት አልቻለም? በእርግጥም ይህን ጥያቄ ማንሣት በእጅጉ ተገቢ ነው። በጣም የሚያስገርመው ኤልሳዕ በቅዱስ ኤልያስ በእኔ ላይ ያለው መንፈስ እጥፍ ይሁንብህ የተባለለት ሰው ሲኾን በትሩ ባሕርን ከፍሎ ከማሻገር የሚያንሰውን ሙት ማስነሣት አለመቻሉ ነው!! ይህቺ በትር ተአምር ያላደረገችው የያዛት ግያዝ በስብሐተ ብጡል ወይም በከንቱ ውዳሴ ስለተወጋ ነው። የሞተው ቢነሣ እኔ አስነሣው የሚል ስለኾነ ነበር። ይህን ስናስበው በእኛም ሕይወት ውስጥ በእንዲህ ዓይነት ምክንያት እንዳይፈጸሙ የተከለከሉ ብዙ ነገሮች መኖራቸውን ማሰብ እንችላለን። አገልግሎታችን ፍሬ ሊያፈራ ያልቻለው ስለምን ይመስላቸዋል!? የምናደርገውን የምናደርገው ለራሳችን ክብር ብቻ ከማሰባችንና እኔ እንዲህና እንዲያ አደረግሁ ስለምንል አይደለምን?

++++++++++++++++++++++++

ሊቁ አውግስጢኖስ ይህቺን በትር ከእግዚአብሔር በነቢያት በኩል የተላከችው ሕግ ናት ይለናል። በእርግጥም የብሉይ ኪዳኗ ሕግ የሞተውን አዳምን ከሞት የማስነሣት ኃይል የላትም። በሕገ ልቦና የነበሩ አበው የጸለዩት ጸሎት ያቀረቡት መሥዋዕት አዳምን ማዳን አልቻለም። በብሉይ ኪዳን ያለችዋ ቤተ እስራኤልም ከኢሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ማለትም ከጽድቅ ወደ ኃጢአት የወረደውን አዳምን ማዳን ስላልቻለች ደጉ ሳምራዊን ትጠብቀው ነበር። በዘመነ አበው የተደረገው የአበው ጸሎት፣ በዘመነ ካህናት የተደረገው የካህናት ጸሎትና መሥዋዕት፣ በዘመነ ነቢያት የተደረገው የነቢያት ጸሎት የመጀመርያውን ርግማን አጥፍቶ ሰውን ወደ ፍጹም ድኅነት መመለስ አልቻሉም። እንግዲህ ይህቺ በትር ይህን አገልግሎት የምታሳይ ናት። አማናዊው ኤልሳዕ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ሥጋና ነፍስ ነሥቶ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ኾኖ በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስ ተፈርዶበት በሲዖል ያለውን አዳምንና ልጆቹን አዳነ!!!

++++++++++++++++++++++++

ይህቺ በትር የቃል ኪዳኑን ታቦት የምታሳይ መኾኗን ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ይግለጣል። የቃል ኪዳኗ ታቦት እስራኤል ዘሥጋን ብዙ ጊዜ የታደገች የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ መኾኗ አጠያያቂ ባይኾንም፥ የሚይዛት ሰው ግን በእጅጉ ወሳኝ ነው። ይህን ለማጠየቅ ነው የእግዚአብሔርን ታቦት የያዙ እስራኤላዊያን በኃጢአታቸው ሲከፉ በፍልስጥኤማዊያን እጅ እንዲወድቁ የኾነው ለዚህ ነው። ሊቁ እንዳለው ግያዝ የእግዚአብሔር ጸጋ የሌለው ነው። የማዳን ኃይል ያለውን በትር ይዞ ማዳን ያልቻለው በትሩን የያዘው እርሱ ውስጡ ባዶ ስለኾነና የቅድስና ፍሬ የሌለው መኾኑ ይታወቀው ዘንድ ነው። በትሩ ሳይኾን ኃይል የሌለው በትሩን የያዘው ግያዝ ነበር! በእርግጥ ይህን የግያዝን የመሰለ ጠባይ አንድ ወቅት ላይ የጌታችን ደቀ መዛሙርትም አሳይተው ነበር። በእምነታቸው ጉድለት ምክንያት ማዳን አቅቷቸው ጌታችንን ለምንድነው ማዳን ያልቻልነው ሲሉ የእምነታቸውን ጉድለት ነግሮ ገስጿቸዋልና። በእምነታችን ጉድለት ብዙ ኃይል ያላቸውን ነገሮች ኃይላቸው እንዳይገለጥ እንዳደረግን ብናውቅ ወደ ልባችን ተመልሰን ለመስተካከል ይጠቅመን ነበር። ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ነገሮች የሚደረጉት እኛ ራሳችንን ራሳችን በያዝነው በኩል እንድንረዳ ለማድረግ ነው። ጉድለትን ማወቅ ወደ ቀናው መንገድ ለመምጣት በጣም አስፈላጊ ነው።

++++++++++++++++++++++++

ብዙዎቻችን በአንገታችን ላይ ያለውን መስቀል የተባለውን የኤልሳዕ በትር  ኃይሉን እንዳይገልጥ አድርገነዋል። ኃጢአታችንን የማያስወግድ ኾኖ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በኃጢአት ላይ ኃጢአት በማብዛት በእኛ እንዳይሠራ፤ የሞተ አሳባችንን አጥፍቶ የአሳብ ልዕልና እንዳይሰጠን አድርገነዋል። በእርግጥ ሰዓታቱን፣ ማኅሌቱን፣ ቅዳሴውን ይዘነዋል ኾኖም ከሞታችን መነሣት አልቻልንም። ምክንያቱም የማይገባን ሰዎች ይህን መልአካዊ አገልግሎት ይዘን በክፉ ድርጊታችን ምክንያት በእኛ ላይ እንዳይሠራ አደረግነው። በእርግጥም ከክርስትና የበለጠ በትር ምን ነበር!? ክርስትና በክርስትና ራስ በኢየሱስ ክርስቶስ መሪነት እየተመሩ የሚኖሩት የጽድቅ ሕይወት ነበር፤ እኛ ግን ገለበጥነውና ለመጠላላት፣ ለመነቃቀፍ፣ ለመለያየት፣ ለመቀናናት፣ ለመሰዳደብ አደረግነው!!! የያዝናቸው ታላላቅ በትሮችን በሕሊናችን ፈጽሞ ካድናቸው፤ ከእነርሱም ይልቅ በጣም ተራ የኾኑ ነገሮችን ተማመንን። ብዙ ሙታን ሲነሱ ያየንበትን ጠበል የተባለውን በትር እኛ ያዝነውና የእኛን ሙት አስተሳሰብ ማስነሣት አቃተን! ሩቅ መሄድ አያስፈልገንም፥ እኛው ጋ ያሉት የእግዚአብሔር በትሮች እንዴት ኃይላቸው መገለጥ እስኪያቆም ድረስ ግያዝን እንደኾን ታስተውላላችሁን? እንግዲያውስ ከምንም አስቀድመን በትራችንን በበጎ ሥራዎቻችን ይዘን እንደ ዮሐንስ ሐፂር እናለምልማት። እርግጥ ነው 19.2 Km እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ተጉዘን ውኃ እየቀዳን በትርነታችንን ፍሬ እስኪያፈራ ልንተጋ ያስፈልገናል። ያም ሆኖ ሦስት ዓመት መታገስንም ሊጠይቀን ይችላልና ከቀቢጸ ተስፋ ፈጽሞ መራቅና መልካም ሥራችንን ሠርተን በትር ሃይማኖታችንን፣ መስቀላችንን፣ ክርስትናችንን አብቦ እንዲታይ ማድረግ አለብን። እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን አሜን!!

ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

https://t.me/zemariwochu3

ቤተ ሊባኖስ ₃

06 Nov, 04:44


🥰ምን አይነት መዝሙር ማግኘት ይፈልጋሉ  የምት ፈልጉትን መዝሙር በመምረጥ ተቀላቀሉ 👇👇👇

ቤተ ሊባኖስ ₃

06 Nov, 04:20


📚 ውዳሴ ማርያምን የደረሰው ሊቅ ስም ማን ይባላል



✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ቤተ ሊባኖስ ₃

03 Nov, 20:54


+  መልአኩ ነው +

       ሰዓቱ ሌሊት ነው ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዚያ ሌሊት መላው የቤተሰባችን አባል አምሽቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ከዚህ የቤተሰብ ስብስብ መካከል ሳይገኝ የቀረው አንድ በወኅኒ ቤት የታሰረ ወንድማችን ብቻ ነበር፡፡ ድንገት ግን የጊቢው በር በተደጋጋሚ ተንኳኳና ሁላችንም ጨዋታችንን አቋረጥን፡፡ በሌሊት ደግሞ የሚያንኳኳው ማን ነው ? አልን በልባችን

ሠራተኛችን ሮጣ ሔደች:: ወዲያው ግን በሩን ሳትከፍተው ተመልሳ እየሮጠች መጣች፡፡ በደስታ ሰክራ ‹‹የታሰረው ልጃችን በር ላይ ቆሟል!›› ብላ ተናገረች፡፡ "በድምፁ አወቅኩት!› እያለች ዘለለች፡፡ ከሁኔታዋ የተነሣ ‹አብደሻል እንዴ!?› አላት ቤተሰቡ ሁሉ፡፡

እስዋ ግን በእርግጠኝነት ተናገረች! በቀን የታሰረው ልጅ በሌሊት ተፈቶ መምጣቱ ፈጽሞ ሊታመንን የማይችል ነገር ነው፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ የታሰረው ልጅ መጣ ብሎ አላመነም፡፡ ባይሆን የመንግሥት ወታደሮች የቀረነውን ሊወስዱን ይሆን? ማን ሊሆን ይችላል? ብሎ ተብሰለሰለ:: በመጨረሻም የሁሉም ግምት አንድ ነገር ላይ አረፈ:: ሁሉም ሰው በአንድ ድምፅ አንድ ቃል ተናገረ "መልአኩ ነው!"

  መልአኩ የሰው ስም አይደለም:: ቤተሰቡ የተስማማው "ደጅ የቆመው የታሰረው ልጃችን ሳይሆን እሱን ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር የተሠጠው ጠባቂ መልአኩ ይሆናል›› ብሎ ነበር፡፡ የበሩ መንኳኳት አሁንም ስላልቆመ ቤተሰቡ ግር ብሎ ወጣና ተቻኩሎ በሩን ከፈተ፡፡ በደጅ የቆመው ግን እንደተባለው የታሰረው ልጅ ራሱ ነበር፡፡ ሁሉም ተደሰተ!!!

      ይህ ገጠመኝ በአሁን ዘመን የተፈጸመ ነው ብዬ ብናገር ማን ያምነኛል? እውነት በሌሊት የቤታችን በር ሲንኳኳ  መልአክ ነው ብለን እንገምታለን? ይህን የገመተው ቤተሰብ ምን ዓይነት ቤተሰብ ነው?

በሌሊት ሲንኳኳ በብዙዎቻችን አእምሮ ውስጥ መጀመሪያ የሚመጣው ጥርጣሬ ‹ሌባ ሊገባ ይሆን?› የሚል ስለሚሆን ዱላ ፍለጋ እናማትራለን፡፡ ወይ ደግሞ ሌሊቱ ወደ መንጋቱ እየተቃረበ ከሆነ ‹‹የምን መርዶ ሊያረዱኝ ይሆን? የቱ ዘመዴ ሞቶ ይሆን?› የሚል ጭንቀት ይፈጠራል፡፡

‹የሚያንኳኳው የእግዚአብሔርመልአክ ይሆናል› ብሎ የሚጠረጥር ሰው ግን በዚህ ዘመን ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ እንዲህ ብሎ ግምቱን የሚናገር ሰው ከቤተሰባችንመካከል ቢገኝ እንኳን እንደ ዕብድ ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ታዲያ ይህን ገጠመኝ ከየት አመጣኸው ትሉኝ ከሆነ መልሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚል ነው፡፡

      በሐዋርያት ዘመን ሔሮድስ የተባለው ንጉሥ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ወኅኒ ቤት ውስጥ ወርውሮት ነበር፡፡ የቀሩት ደቀመዛሙርትና ክርስቲያኖች በዚያ ሰሞን ሲጸልዩ ከርመዋል፡፡ በአንድ ሌሊት በማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ተሰብስበው አምሽተው ነበር፡፡ ድንገት የቤቱ በር ሲንኳኳ ሮዴ የምትባል የቤት ሠራተኛ ደጁን ልትከፍት ወጣች፡፡ ማነው ብላ ስትሰማ የቆመው እስረኛው ቅዱስ ጴጥሮስ መሆኑን በድምፁ አወቀች፡፡ ደስታ ግራ ሲያጋባት በሩን መክፈትን ረስታ ወደ ውስጥ ሮጠችና ጴጥሮስ መምጣቱን ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን አላመኑአትም፡፡ ጤንነቷን ተጠራጥረው ‹አብደሻል› አሏት፡፡ እርግጠኛ ሆና ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን መልሰው ‹‹የቆመው ጴጥሮስ ሳይሆን መልአኩ ነው፡፡›› አሉ፡፡ ይደንቃል የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንዲህ በር ሲንኳኳ ‹መልአክ ነው› ብለው የሚገምቱ መንፈሳዊያን ነበሩ፡፡ (ሐዋ. 12፡12-15)

ክርስትናን ከመላእክት ውጪ አይታሰብም:: ከመጽሐፍ ቅዱስም እንደ ትንቢተ ሐጌና መጽሐፈ አስቴር ያሉ ጥቂት መጻሕፍት በቀር ስለ መላእክት የማይናገር መጽሐፍ የለበትም:: ክርስትና የጀመረው በገብርኤል ብሥራት ነው:: ልደቱ በመላእክት የታጀበ ነው:: ስቅለቱ ትንሣኤውም ከመላእክት ጋር ነው:: የጌታ ምጽአቱም በመላእክት የታጀበ ነው::
     

ቅዱሳንመላእክት እኛ የሰው ልጆች ከመፈጠራችን ቀድመው የተፈጠሩ ታላቅ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም ምድርና የሰው ልጅ ሲፈጠር ደስ እያላቸው ‹‹እልል›› ይሉ ነበር፡፡ (ኢዮ. 38፡6) ቅዱሳን መላእክትን እግዚአብሔር ለእንዳንዳችን ጠባቂዎች አድርጎ ሠጥቶናል፡፡ መላእክት ለሰው ባልተናነሰ ቁጥር ምድር ላይ አሉ:: እነርሱን ለማየት ግን ቅድስና ይጠይቃል::

ከክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብለው የተማሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መላእክት ጠባቂነት ጋር ይህን ያህል እምነት ከነበራቸው እኛም የመላእክቱን ጠባቂነት ማመን ለዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ምን ያህል ይገባን ይሆን? ቅዱሳን መላእክት በክርስትና ሕይወት ለሚኖርሰው ሁሉ የመላእክት ረዳትነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለሁሉ ብርታት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሥጋው ወራት በተያዘባት ምሽት ሲጸልይ ‹‹ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ሉቃ. 22፡43) ይህም ቀርበው አገለገሉት‹ለከ ኃይል› እያሉ አመሰገኑት ማለት ሲሆን ለእኛም የመላእክት ርዳታ አያስፈልገኝም እንዳንል የሚያስተምረን ነው፡፡

ቅዱሳን መላእክት በምድር የሚሆነውን ያውቃሉ:: (2 ሳሙ 14:20) በበደላችን ስንጸጸት "ኃጢአትህ ተሠረየችልህ" ይላሉ (ኢሳ 6:7) በክፋታችን ጸንተን ከቀጠልን ደግሞ "ይቅር አይሉም" (ዘጸ 23:20)
ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ቆመው "የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?" ብለው ያማልዳሉ:: (ዘካ 1:12)

አንዳንድ ሰዎች መላእክትን ለረዳትነት ስንጠራ ሲሰሙ እነርሱ በምን ያውቃሉ በሁሉ ቦታ የሉም እኮ ሊሉን ይሞክራሉ:: ሰይጣን "ፈተነኝ" ስንል ግን "እሱ በሁሉ ቦታ የለም ምን ያውቃል አይሉም:: እኛ ግን መላእክት በሁሉ ባይሞሉም ለትንሽዋ ፕላኔት ምድር ግን እንደማያንሱና አንዱ መልአክ ብቻ ለምድር እንደሚበቃ እናምናለን:: (ራእ 18:1)
ለመላእክት ስንዘምር የሚቃወሙ ሰዎች "ጠላቴ ሆይ" ብለው ስለ ሰይጣን ክፉነት እያነሱ ብዙ መዝሙር ሲዘምሩ ስንሰማ ግራ እንጋባለን::

እኛ ግን በመላእክቱ ረዳትነትና ምልጃ እናምናለን:: ባለንበት ዘመን በየሆስፒታሉ በዓለም ሁሉ በበሽታ የሚሠቃየው ብዙ ነው::  በሕመም ለሚሠቃየው ሁሉ

"መልአክ ቢገኝለት እየራራለት [ለእግዚአብሔር] ፡— ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው፡ ቢለው፥ ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል፤ ወደ ጕብዝናውም ዘመን ይመለሳል" ኢዮ 33:23-25

ቤተ ሊባኖስ ₃

30 Oct, 19:35


በወይን መጥመቂያው ውስጥ ስንዴን ሲወቃ የእግዚአብሔር መልአክ ያገኘው ሰው ማነው ?

ቤተ ሊባኖስ ₃

30 Oct, 19:29


አሁን የምንፆመው ፆም ምን ይባላል?

ቤተ ሊባኖስ ₃

30 Oct, 15:04


በእንተ ዐርክ ምእመን (ስለ ታማኝ ወዳጅ)
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

“የታመነ ወዳጅ ስለ ወንድሙ ብሎ ኹሉን ይከፍላል፤ ነፍስን እስከ መስጠትም ቢኾን፡፡ ይኽን የሚያደርገውም ነፍሱን እንዲሰጥ ስለተጠየቀ አይደለም፤ እንደ ስጦታ ለመስጠት በራሱ ውዴታ ይሰጣል እንጂ፡፡ ይኽን ከመሰለ ፍቅር በላይ ምንም ጣፋጭ ነገር የለም፡፡
የታመነ ወዳጅ የታመነ መድኃኒት ነው፡፡ መድኃኒት ሲውጡት ይመራል፡፡ ኋላ ግን አድኖ ደስ ያሰኛል፡፡ የታመነ ወዳጅም ተቆጥቶ የልብ ምክር ሲመክር ያሳዝናል፤ ኋላ ግን ደስ ያሰኛል /ሲራክ.፮፡፲፮/፡፡
የታመነ ወዳጅ እንዳላባሽ አግሬ ጋሻ ነው፡፡ ጋሻ ከተጣለ ጠጠር ከተወረወረም ጦር ያድናል፤ የታመነ ወዳጅም እንዲኹ ነው /ሲራክ.፮፡፲፬/፡፡ የታመነ ወዳጅ የማያደርገው ነገርስ ምን አለ? ከደስታው ኹሉ የማይሰጠውስ ምን አለ? ከጥቅሙ የማይሰጠው ምን አለ? ከደኅንነቱ የማይሰጠውስ ምን አለ? እጅግ ብዙ ነገሮችን ብንጠቅስም የታመነ ወዳጅን ሊገልጠው የሚችል ነገር ግን ፈጽመን አናገኝም፡፡…
የታመኑ ወዳጆች ከፀሐይ ብርሃን በላይ ተናፋቂዎች ናቸው፡፡ እንዲኽ መኾናቸውም አልደነቅም፡፡ የታመኑ ወዳጆችን ከምናጣ የፀሐይ ብርሃን ብናጣ እመርጣለኹና፡፡ የታመነ ወዳጅ ከምናጣ የታመነ ወዳጅን አግኝተን በጨለማ ብንኖር እመርጣለኹ፡፡ ለምን ይኽን እንደምልም ምክንያቱን አስረዳችኋለኹ፡፡ ብዙ ፀሐይን እየተመለከቱ በጨለማ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አሉ፡፡ የታመነ ወዳጅ ያላቸው ግን ደግሞ አንዳች የጐደላቸው ነገር የለለ ሰዎችም አሉ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወዳጆች ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን የተመለከትን እንደኾነ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች ነፍሱን እንኳን ሊሰጣቸው እንደሚችል ተናግሯል /፩ኛ ተሰ.፪፡፰/፡፡ ይኽም የሚለው የተሰሎንቄ ሰዎች ነፍሱ እንዲሰጣቸው ስለጠየቁት አይደለም፤ ወደ ሲዖል ውረድልን ብለዉትም አይደለም፤ ስለ ታማኝ ወዳጅነቱ እንጂ፡፡ …
የወዳጅነት ምሳሌ ልሰጣችኁ እወዳለኹ፡፡ በክርስቶስ የኾነ ወዳጅ ከአባትም ከልጆችም በላይ ወዳጅ ነው፡፡ በዚኽ ዘመን ስላሉት ወዳጆች አትንገሩኝ፡፡ እንዲኽ ዓይነቱ ወዳጅነት ከጥንትም ነበር፡፡ ነገር ግን በዘመነ ሐዋርያት የነበረውን ወዳጅነት አስታውሱ፡፡ በሐዋርያት ዘንድ የነበረው ብቻ አይደለም፤ በተራው ምዕመንም ጭምር እንጂ፡፡ ወንጌላዊው ሉቃስ በግብረ ሐዋርያት መጽሐፉ ላይ ሲነግረን “ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ ገንዘባቸውም ኹሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ከላው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደኾነ ማንም አልተናገረም፡፡ … ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር” /ሐዋ.፬፡፴፪/፡፡ በእነዚኽ የታመኑ ወዳጆች መካከል “የእኔ” “የአንተ” የሚሉ ቃላት አይታወቁም፡፡ የታመነ ወዳጅነት ማለት ይኼ ነው፤ አንድ ሰው ያለውን ነገር የራሱ ብቻ እንደኾነ ሳያስብ ይልቁንም የገዛ ወዳጁም ጭምር እንደኾነ ሲገነዘብ፡፡ በሌላ አገላለጥ የታመነ ወዳጅ ያለው ነገር ኹሉ የራሱ ብቻ እንደኾነ አያስብም፡፡ ምናልባት ከእናንተ መካከል “ይኽ ነገር በእኛ ዘንድ እንደምን ይቻላል?” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ የማይቻል ኾኖ አይደለም፤ ፈቃደኞች ስላልኾንን ነው፡፡ የማይቻልስ ቢኾን ኖሮ ክርስቶስ አድርጉት ብሎ ባላዘዘን ነበር፤ ከምንም በላይም ስለ ፍቅር ባላስተማረ ነበር፡፡
ወዳጅነት እጅግ ታላቅ ነገር ነው፡፡ እስከ ምን ድረስ ታላቅ እንደኾነ ግን በቃላት ተምረን ወይም አስተምረን መጨረስ አንችልም፡፡ ወዳጅነት እስከ ምን ድረስ ጥልቅ እንደኾነ የሚገባን ስንኖረው ብቻ ነው፡፡ መናፍቃን እንዲኖሩ እንኳን ያደረጋቸው ይኽ ፍቅር ነው፡፡ ክርስቶሳዊ ፍቅር ባይኖር ኖሮ ማን በሕይወት ቆሞ ክሕደትን ያስተምር ነበር? አሕዛብ ስንኳ አሕዛብ እንዲኾኑ ያደረጋቸው ይኸው ነው፡፡ የታመነ ወዳጅ አንድን ነገር የሚፈጽመው ስለ ታዘዘ ወይም በሕግ እንዳይቀጣ አይደለም፡፡ ፍቅሩ ነው የሚያስገድደው፡፡
የታመነ ወዳጅ ከመቀበል ይልቅ መስጠት ያስደስቷል፡፡ መስጠቱም የመውደዱ መገለጫ ነው፤ ቢሰጥ ቢሰጥ አይረካም፡፡ የታመነ ወዳጅ እጅግ ብዙ ነገር ሲደረግለት ከሚደሰተው በላይ እጅግ ብዙ ነገር ለገዛ ወዳጁ ሲያደርግ ይደሰታል፡፡ የታመነ ወዳጅ ከራሱ በላይ የገዛ ወዳጁ መልካም ነገር ደስ ያሰኟል፡፡ ዓቅም አግኝቶ እጅግ ብዙ ነገር ቢያደርግ ምንም አይከፋውም፡፡ የታመነ ወዳጅ ዓቅም ካገኘ በበጐ ነገር ኹሉ የመዠመሪያ ነው፡፡ …
የምናገረው ነገር ምናባዊ ሊመስላችኁ ይችላል፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ የምናገረው ሰማያዊ ምሥጢር ስለኾነ ነው ምናባዊ የሚመስለን፡፡ እኛ የማንኖረው ከኾነ ምናባዊ ይመስለናል፡፡ ነገሩ ምናባዊ ኾኖ ሳይኾን እኛ ስላቀመስነው፤ ወይም በዚያ ሕይወት ውስጥ ስለሌለንበት፡፡ ለምሳሌ አንድ በሕንድ ብቻ ስለሚገኝ ዛፍ ብነግራችኁና ያንን ዛፍ ካላያችኁት በቀር እልፍ ቃላት ብደረድርም አይገባችኁም፡፡ የምነግራችኁ ነገር እንዲገባችኁ ያንን ዛፍ አስቀድማችኁ ማወቅ አለባችኁ፡፡ ስለ ታማኝ ወዳጅ ያወራነውም የሚገባችኁ እናንተው በዚያ ውስጥ የምትኖሩ ከኾነ ብቻ ነው፡፡…
የታመነ ወዳጅ ከማር በላይ የጣፈጠ ነው፡፡ ማር ይሰለቻል፤ የታመነ ወዳጅ ግን አይሰለችም፡፡ እንደዉም በቀረብነው ቁጥር ጣዕሙ ይጨምራል፤ ስልቹነት የሚለው ቃልም ጭራሽ ይጠፋብናል፡፡…”
የታመንን ወዳጆች እንድንኾን አንድም የታመነ ወዳጅን እንድናገኝ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡



በግ በውሻ ቀና

ሊቁ ብላቴን ጌታ ኅሩይ “ ስኳርና ወተት” የሚል ከእንግሊዘኛ የተተረጎመ በ1922ዓ.ም ከፃፉት ተረት መጽሐፍ ላይ የጠቀሱትን እንመልከትና እንማርበት፡፡ ምሳሌ ማስተማሪያ መንገድ ነው፡፡
ብዙ በጎች ያሉት አንድ ሰው ነበር እርሱም በጎቹን ሲጠብቅ በብዙ ጥንቃቄ ነው፡፡ የለመለመ ሳር ይመግበቸዋል፣ የጠራ ውሃ ያጠጣቸዋል ሲመሽም ወደ ጉሮኗቸው ያስገባቸዋል፡፡ በዚህ መልኩ በጣም ይንከባከባቸዋል፡፡ ከአንዱ ግልገል በቀር ሁሉም ጠባቂያቸውን ይወዳሉ፡፡ ያ አንዱ ግልገል ግን ጠባቂውን አይወድም፡፡ አንድ ቀን ወደ እናቱ ቀርቦ “እናቴ ሆይ እኛ ማታ ማታ ለምን ይዘጋብናል እነሆ ውሾች ሳይዘጋባቸው እየተጫወቱ ያድራሉ፡፡ እኔም ከአሁን በኃላ እንደ ውሾች ማታ ማታ መጫወት እፈልጋለሁኝ” አላት፡፡ እናቲቱም “ልጄ ሆይ አርፈህ ተቀመጥ ጠባቂያችን እጅግ መልካም ነው እርሱ እንዳዘዘን ውለን ብንገባ ይሻለናል፡፡ እንቢ ያልክ እንደሆነ በራስህ ላይ ጥፋት ታመጣለህ” አለችው፡፡

ግልገሉም ይህን በሰማ ጊዜ “እናቴ ሆይ መልካም ምክር አልመከርሽኝም እኔስ እንደ ውሾቹ መሆኔን አልተውም” አለ፡፡ ከዚህ በኃላ ጠባቂያቸው እንተለመደው ሲመሽ ሲያስገባቸው ያ ግልገል ተደብቆ ቀረ ጠባቂው ሁሉም የገቡ መስሎት ቤቱ ገባ፡፡ ጊዜው ሲጨልም በውሾች የቀናው ግልገል ከተደበቀበት ወጥቶ ከውሾች ጋር መሯሯጥ ጀመረ፡፡ ከጉረኖውም እየራቀ ሄደ በድንገትም አንድ የተራበ ተኩላ አይቶት አባረረው ውሾቹም ተበታተኑ በጉም ርቋልና ወደ ጉረኖው መድረስ ተቸገረ ተኩላውም ደርሶበት አቅፎ ወስዶ ወደ ጉድጓድ አግብቶ ገነጣጠለው፡፡
“ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው” እንዲሉ በጎ ምክር የማንሰማ ከከበረ ኑሮ ይልቅ የጨለማውን ለእኛ የማይገባ የኃጢአት ኑሮ የምንመርጥ እየበዛን ነው፡፡ ከመንፈሳዊ መዝሙር ይልቅ በዘፈኑ፣ ከቅዱሳን ይልቅ በሀጥአን የምንቀና እንደነሱ ካልሆንን የምንል እንደ በጉ ግልገል ሳይገጥመን በቤተክርስቲያን እንጽና፡፡ “ሕዝቤ ሆይ ወደ ቤትህ ግባ ደጅህንም በኃላ ዝጋ” አሳ 26÷20
@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

29 Oct, 19:04


አባ ዮሐንስ ሐፂር
ጥቅምት ሃያ በዚች ቀን ክቡርና ገናና የሆነ አባ ዮሐንስ ሐፂር አረፈ ።
የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ ከላይኛው ግብጽ ናቸው እነርሱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው ግን ከእርሱ በቀር ልጅ የላቸውም የዚህ ዓለምም ብልጽግና ቢሆን የላቸውም ነገር ግን በበጎ ሥራ ባለጸጎች ናቸው ይህንንም ቅዱስ እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት ።
የዚህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ሲሆነው የእግዚአብሔር ቸርነት አነሣሥታው የመላእክት የሆነ አስኬማን ይለብስ ዘንድ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ ይኸውም የምንኵስና ልብስ ነው ።
ከዚያም በደረሰ ጊዜ አባ ባይሞይ የሚባለውን አንዱን አረጋዊ አባት ተገናኘው ዮሐንስም ሰገደለትና ወደ እርስ እንዲቀበለው ለመነው ሽማግሌውም አባት ልጄ ሆይ ያንተ በዚህ መኖር ልክ አይደለም በዚች ገዳም የሚኖሩ በእጆቻቸው ይሠራሉ በቀንና በሌሊት ይጾማሉ ይጸልያሉ በሚተኙም ጊዜ ያለ ምንጣፍ በምድር ላይ ይተኛሉ አንተ ወጣት ጎልማሳ ስለሆንክ ይህን ሁሉ ችግር አትችልም ። ነገር ግን ወደ ዓለም ተመልሰህ እንደ ሰው ሁሉ በጎ አኗኗርን ትኖር ዘንድ ይሻልሃል የዚች ገዳም ኑሮ ጭንቅ ነውና አለው ።
አባ ዮሐንስም እንዲህ አለው እኔ በጥላህ ሥር ልኖር መጥቼአለሁና ስለ እግዚአብሔር ብለህ ተቀበለኝ እንጂ አትመልሰኝ ይህም አባ ባይሞይ እግዚአብሔርን ሳይጠይቅ ምንም ሥራ አይሠራምና በዚያን ጊዜ ሥራውን ይገልጥለት ዘንድ ስለ ዮሐንስ ሐፂር እግዚአብሔርን ለመነው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦለት እርሱ የተመረጠ መሳሪያ ይሆናልና ተቀበለው ብሎሃል አለው ።
ከዚህም በኋላ ዮሐንስ ሐፂርን ወስዶ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገባው የምንኵስና ልብሶችንም አምጥቶ በላያቸው ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ጸለየ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾ በመስቀል ምልክት በልብሶቹ ላይ አማተበ ሽማግሌውም እነዚያን ልብሶች ለአባ ዮሐንስ አለበሰው ።
ከዚያቺም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ ተጋድሎንና አገልግሎትን ጀመረ አባ ባይሞይም ሊፈትነው ወደደ በአንዲትም ቀን ደብድቦ ከአንተ ጋር መኖር አልሻም ብሎ ከበዓቱ አስወጥቶ አባረረው የከበረ አባ ዮሐንስም ከሜዳ መካከል በውጭ ቆመ በየቀኑም በጥዋት እየወጣ ከእዚህ ላይህ አልሻም እያለ ይመታዋል እርሱ ግን አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ ብሎ ከእግሩ በታች ይሰግዳል ።
በሰባተኛዪቱም ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊሔድ ሽማግሌው አባ ባይሞይ ወጣ አባ ዮሐንስንም ሰባት መላእክት ከበው አክሊላትን ሲያቀዳጁት አያቸው ከዚያንም ጊዜ ወዲህ መፈተኑን ተወው ወደ መኖሪያውም አስገባው ።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን አባ ባይሞይ የደረቀ ዕንጨት አግኝቶ ወስዶ ለአባ ዮሐንስ ሰጠውና ይህን ዕንጨት ትከለው እስከሚበቅልና እስከሚአፈራ ድረስ ውኃን አጠጣው አለው ። አባ ዮሐንስም ለአባቱ ታዛዥ በመሆን ተቀብሎ ወስዶ ተከለው በየቀኑም ሁለት ሁለት ጊዜ ያጠጣዋል ውኃውም ዐሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል የራቀ ነው።
ከሦስት ዓመትም በኋላ ያ ዕንጨት አቈጥቊጦ በቀለ ታላቅም ዛፍ ሁኖ አብቦ ጣፋጭ ፍሬን አፈራ ። አባ ባይሞይም ከፍሬው ለቅዱሳን አረጋውያን ወሰደላቸውና የታዛዡንና የትሑቱን ፍሬ እነሆ ብሉ አላቸው እነርሱም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው አደነቁ ለመምህሮቻቸው ለሚታዘዙ እንዲህ ያለ ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ።
አባ ባይሞይም ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል በጽኑዕ ደዌ ውስጥ ተይዞ ኖረ አባ ዮሐንስም ያገለግለው ነበር አባ ዮሐንስን እንደፈተነው የተመረጠ መሥዋዕትን ይሆን ዘንድ በዚህ ደዌ እንዲፈተን እግዚአብሔር ፈቅዷልና ።
በሚሞትበትም ጊዜ አባ ባይሞይ ቅዱሳን አረጋውያን መነኰሳትን ሰበሰባቸውና አባ ዮሐንስንም እጁን ይዞ እርሱ ሰው ያይደለ መልአክ ነውና ተቀብላችሁ ጠብቁት ብሎ ሰጣቸው ። እርሱንም ደግሞ እንዲህ አለው ከእረፍቴ በኋላ ያን ዕንጨት ወደ ተከልክበት ቦታ በዚያ ኑር እግዚአብሔር ላንተ ያዘጋጀልህ ነውና ብዙዎችም በአንተ እጅ ይድናሉ መታሰቢያህም በዚያ ጸንቶ ይኖራል ዜናህም በዓለም ሁሉ ይወጣል ይህንንም ተናግሮ አረፈ አክብረውም ቀበሩት ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባ ዮሐንስ አረጋዊ አባቱ አባ ባይሞይ እንደነገረው ወደዚያ ቦታ ሒዶ ኖረ ዜናውም በዓለም ሁሉ እጅግ እስከ ተሰማ ድረስ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ።
በራሱ ቤተ ክርስቲያንም አበ ምኔት ሁኖ ተሾመ በሹመቱም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ እጆቹን በራሱ ላይ ሲጭን አክዮስ አክዮስ አክዮስ የሚል ቃል ከሰማይ ተሰማ ይህም ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል ማለት ነው ። የቊርባን ቅዳሴን በሚቀድስ ጊዜ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል የማይገባቸውን ይለያቸዋል ዛሬስ ሒዳችሁ ንስሓ ግቡ ከዚያም በኋላ ተመልሳችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ ይላቸዋል ።
ይህን አባ ዮሐንስንም ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ የቅዱሳን የሠለስቱ ደቂቅን ሥጋቸውን እንዲአመጣለት ወደ ባቢሎን ልኮታል ይህም በግንቦት ወር በዐሥረኛው ቀን ተጽፎአል ። በአንዲትም ዕለት አንድ መነኰስ ሊጎበኘው ወደ በዓቱ ቢመጣ አባ ዮሐንስን ተኝቶ አገኘው የእግዚአብሔርም መላእክት በላዩ ይጋፉ ክንፎቻቸውንም ያርገበግቡ ነበር አንዱም ሌላውን ተወኝ ክንፌን በላዩ ላኑር ይለዋል ይህንንም አይቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው ።
ከዚህም በኋላ የመነኩሳቱን መንደር ሊበረብሩ የበርበር አረማውያን ወደ አስቄጥስ ገዳም በመጡ ጊዜ አባ ዮሐንስም ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ወደ ቁልዝም ሔደ በዚያም በአባ እንጦንስ ገዳም በጎኑ በአለ ቦታ ተቀመጠ እስከ ሚያርፍባትም ቀን ድረስ የሚያገለግለው አንድ የታመነ ሰውን እግዚአብሔር አመጣለት ።
ከዚህም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ እግዚአብሔር ቅዱሳን ጻድቃኖቹን አባ እንጦንስን፣ አባ መቃርስን፣ አባ ጳኵሚስን ከእርሳቸውም ጋር መንፈሳዊ አባቱ አባ ባይሞይን ያረጋጉትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መለየቱን ይነግሩት ዘንድ ወደርሱ ላካቸው ። እነርሱም እንዲህ ብለው አረጋጉት ደስ ይበልህ እግዚአብሔር የማያልቅ ተድላ ደስታን አዘጋጅቶልሃልና ክብር ይግባውና ጌታችንም እንዳዘዘ በእሑድ ቀን ሁለተኛ ወዳንተ መጥተን ወደ ዘላለም ሕይወት እንወስድኻለን ባርከውትም ከእርሱ ዘንድ ተመለሱ ።
በዐርብ ቀንም አገልጋዩን ወደ አንድ ቦታ ላከው ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ በእሑድም ቀን ሌሊት ዶሮ ሲጮህ እሊያ ቅዱሳን ከሁሉም ቅዱሳን ማኅበር ጋር መጡ የመላእክትም ሠራዊት ሁሉ ወደርሱ መጡ በአያቸውም ጊዜ ደስ ብሎት በእግዚአብሔር እጅ ነፍሱን ሰጠ መላእክትም እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ነፍሱን አሳረጓት በዚያንም ጊዜ ረድኡ መጣ ነፍሱንም ከበው እያመሰገኑ ሲያሳርጓት የጻድቃንና የመላእክትን ማኅበር አይቶ እያደነቀ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ። ከመላእክትም አንዱ ወደርሱ መጥቶ የቅዱሳንን ስማቸውን በመጥራት በጣቱ እያመለከተ ይህ አባ ዕገሌ ነው ብሎ አስረዳው ረድኡም መልአኩን እንዲህ ብሎ ጠየቀው ይህ በፊታቸው ያለ ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚበራ ማን ነው መልአኩም የመነኰሳቱ ሁሉ አባት አባ እንጦንስ ነው ብሎ መለሰለት ።
ወደ በዓቱም ያ ረድእ በገባ ጊዜ በምድር ላይ ሰግዶ እንዳረፈ አባ ዮሐንስን አገኘውና ታላቅ ልቅሶን በላዩ አለቀሰ ከዚያም በኋላ ወደ መነኰሳቱ መንደር ፈጥኖ በመሔድ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐፂር እንደ አረፈ ነገራቸው ። እነዚያም መነኰሳት አክብረው ገንዘው ሥጋውን ተሸክመው ወስደው በቦታቸው አኖሩት ።
የደረቀ ዕንጨት ተክሎ በአበቀለበት ላይ በሠራት የራሱ በሆነች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልጆቹ ከዚህ አፍልሰው ወስደው እስከ አኖሩት ድረስ በዚያ ኖረ ።
 

@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

29 Oct, 18:50


👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 ግብረ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ወደ ቦቱ ይግቡ 👇👇

ቤተ ሊባኖስ ₃

29 Oct, 18:48


መላእክት ቁጥር አላቸዉ

ቤተ ሊባኖስ ₃

27 Oct, 17:48


*"* *የጠፋው* *ልጄ* *ተገኘ* *"*

🙎🏽‍♂ አባቴ ልንገርክ ኧኽ ብለክ ስማኝ
ንብረቴን እሻለሁ ለኔ የሚደርሰኝን አካፍልና ስጠኝ
ከህል ከከብት ከገንዘብም ቢሆን ሁሉን አስረክበኝ
ሆኖም አደራክን ዛሬ ነገ እንዳትል አሁኑኑ ይሰጠኝ
ሽማግሌዎች ጥራ ጉልማዬን ልወቅ ሸንሽነው ያካፍሉኝ
ድርሻዬን ለይተክ እንድታስረክበኝ እፈልጋለሁኝ

👴🏽 *በወላዲትዋ*!
ምንድነው የምትል የሆንከው አለ እንዴ?
እንዲህ ተበሳጭተክ የምታናግረኝ ምን ነክቶክ ነው ውዴ?
ማነው የስቀየመክ ክፉ የተናገረክ ወይስ ምን በደልኩክ
ገንዘብስ ለምንክ ምን ሊጠቅምህ ገና ልጅ አይደለክ?
ችግርም እንዳለ ንገረኝ አትፍራ አንተ በምን አቅምክ ትቋቋመዋለክ
እኔ እስካለሁ ድረስ አደራ እንዳይኖር ከቶ የሚያስጨንቅክ

🙎🏽‍♂ እንደዚህ ስላልኩክ አይክፋክ አትናደድብኝ
ነገር ግን አሁን ደግሜ ዕልካለሁ ድርሻዬን አካፍለኝ
ያለኝን ስጥና ለኔ የሚደርሰኝ መርቅና ሸኘኝ
ተትረፍርፎ ሳለ አውድማ ጎተራው ለምን አሰሰተክ?
ብታካፍለኝም በእጥፍ ይገባል በወሰድኩት ምትክ
ይልቅ አባዬ ሳታመነታታ አሁኑኑ ስጠኝ ነው ደግሜ ምልክ


👴🏽 እሺ በቃ ልጄ እጅግ ከባሰብክ
እሰጥሀለሁኝ አትናደድ አሁን ውሰድ እሄው ድርሻክ
ሳልል ወደኋላ አስረክቤካለሁ ሁሉም ያልፋልና አትከፋ አይዞክ
ባገር ሽማግሌ ከንብረቴም ሁሉ አካፍዬካለሁ
ሰርተክ ጨምርበት አምላክ ይባርክልክ ብዬ መርቄሀለሁ

🙎🏽‍♂አመሰግናለሁ ደህና ሰንብቱልኝ
እንደዚህ ይሻላል በማያቁት ሀገር ዝና እላለሁኝ
መኖር እንዲህ እንጂ ቀብረር ፀዳ ብሎ
የት ነበርኩ እስካሁን እሄንን ለማየት ያልነቃሁት ቶሎ
በይ ነፍሴ ተደሰች ያሻሽን አድርጊ
ገንዘብ እንደው አለኝ በአንዳች አትስጊ
ብይ ጠጪ በቃ ሀሴት አድርጊ
ለስጋሽ እርካታ ለአይንሽም ደስታ ከቶም አትንፈጊ

💗 ከአባትህ ኮብልለህ ከፈሩ ወተሃል
አክብር የሚለውን ህጌንም ጥሰሃል
የልብህን ምኞት ስትፈፅም ኖረሃል
አላፊ ጠፊውን አለሙን መርጠሃል
መሰረት የሌለው ህወት ገንብተሀል
በዘፈን ጭፈራ በሱስይሁንህ ደንዝዘካል
ለሰራህው ስራ ደመወዝ ልክፈልህ
ተዘጋጅቻለው መማርያ

🙎🏽‍♂ ወይኔ ጉዴ ፈላ ተራብኩኝ ተጠማው
ገንዘብ አለኝ እያልኩ ያኔ እንዳላቅራራው
አለቀ ገንዘቤ እሄው እጄ ባዶ ነው
የአባቴን ንብረት
ተድላን የለመደው የቀድሞ ሕይውቴ
ጭራሽ ይባስ ብሎ ድንገት ተጎሳቁሎ ጠፋ ማንነቴ
ኪሴ ተራገፈ እጄ ባዶ ቀረ እኔም ሆንኩ ዋተቴ
ደስታ ሰላም ጠፋ እራቀ ከፊቴ
እርሀብ ፀናብኝ እጂግ ተንገላታሁ እስኪዝል ጉልበቴቤቴ
ከማር ከወተቱ የበላው አንጀቴ
ትዝ ይለኝ ጀመረ ፍቅሩ የአባቴ

ጥፋቴ ከባድ ነሁ አውቃለሁ ጠንቅቄ
ወደ አባቴ ልሂድ ልኑር በግ ጠብቄ
ይቅርታ ልጠይቅ እግሩ ላይ ወድቄ

💗 መመለስ አለብህ መልካም አስበሃል
ስህተት መስራትክ አሁን አስታውሰሃል
አባትክን ይቅርታ መጠየቅ ይገባሃል ስላንተ ያስባል ሁሌም ይወድሀል
ልጁን የሚጠላ አባት የት አይተሀል ?
ከልብህ ሁንና ጠይቀው ይቅርታ
ዳግም ለመበደል ልብህ አያመንታ

👴🏽 ገና ከሩቅ ሳይክ ሀሴት አገኘሁኝ
የጠፋውን ልጄን ጌታ ምልሶልኝ
ለብዙ ጊዜያት ደስታ ከኔ ርቆኝ
ሀዘን ሰፍኖ ቤቴ ሰላምም ሳላገኝ
ዛሬ መጣህልኝ ፍሪዳ ጣሉለት ጥሩ ዘመድአዝማድን
እጅግ ደስ ብሎና የጠፋው ልጃችን ስለተገኘልን
ለግሩ ጫማ አምጡ ለዕጆቹም አንባር
ከጠፋበት ቦታ ስለተመለሰ አምላክ ተመስገን

🙍🏿‍♂ ምንድነው ይህ ሁሉ ትላንት ንቆን አይደል?
ዛሬ ተመልሶ ድርሻውን ሲጨርስ
ዳግም ደሞ መጣ ሌላውን ሊያፈርስ
እንዳሻው ሲቦርቅ ሲፈነጥዝ
ከርሞ የትም ሲልከሰከስ
ሲቸግረው መጣ የኛንም ሊካፈል ሳናስበው ድንገት
እንዴት ለዚህ ብኩን ለሆነብክ ሽፍታ
ንብረቱን አጥፍቶ ለመጣ ከርታታ
እንዴት ተቅበልከው በፍቅር በደስታ
ለኔም አላሳየህኝ እሄንን ፈገግታ?
አገልጋይህ ለሆንከህ ጠዋትና ማታ

👴🏽 ልጄ ተው እባክህ የስጋዬ ክፋይ
ላንተም እንደዛው ነኝ ለያይቼም አላይ
የኔ ያልኩት ሁሉ ነው ግድ የለም ያንተ
ሳትለያዩበኝ አንድላይ ኑሩ እንጂ በፍቅር በሰላም
ወንድምክም አንተ
ተገኘልን ከሞት ከጥፋት
ዛሬ
ፀልይለት አንተም
ጥፋቱን እንዳይደግም
እናም እናመስግን ጌታን በዝማሬ


🙎🏽‍♂ ወይ አቤቴ ደጉ የቀዶሞ ስራዬን በደሌን ሳይቆጥር
ይልቁንም አባብሎ እሄው ተቀበለኝ በሰላም በፍቅር
ዕውነት ለውለታው ለታላቅ ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ
ስለቸርነቱ
ስለዕርሕራሄው በሒወቴ ሁሉ አመሰግናለው
ዳግም ላልባድለው ገፍቼውም ላሌድ ቃል ገባለታለሁ።
@Abalibanos333
አሜን ወስበሀት ለእግዚአብሔር

ቤተ ሊባኖስ ₃

26 Oct, 17:37


🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ቤተ ሊባኖስ ₃

26 Oct, 17:11


✥ ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ

በማኅሌተ ጽጌ "አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ክበበ ጌራ ወርቅ" እያልን እንዘምራለን። ግን ለምን እንዲህ እንላለን?

በቅድሚያ ሙሉ የማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱን ከነ ትርጉሙ ላስቀምጥ:- "ክበበ-ጌራ-ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ፣ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፣ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፣ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፣ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።"

ትርጉም:- "ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት፣ (የጊዮርጊስ) የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ፣ ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ፣ አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ፣ እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል።"

ቅዱስ ጊዮርጊስ የ7 ዓመታት ተጋድሎውን የጀመረው በ20 ዓመቱ ነበር። ለሰባት ዓመታት ያክል እየሞተ እየተነሣ ተጋድሎውን ፈጽሞ በ27 ዓመቱ፣ በሚያዝያ 23፣ በ304 ዓ.ም. ዐረፈ። እስከዚያው ጌታችን ቃል እንደ ገባለት 3 ጊዜ ሞቶ 3 ጊዜ ተነሥቷል። በዐራተኛው ሞቱ ፈጽሞ ዐረፈ። ያረፈውም በዕለተ ዓርብ በ9 ሰዓት ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ጊዜ መሞቱን "ማርያም" ከሚለው ባለ 4 ፊደል ቃል ጋር ያመሣጠረው ደራሲው "ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ - የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ" ሲል እመቤታችንን በማኅሌተ ጽጌ አመሰገናት። ቅዱስ ጊዮርጊስን ያንገላታ የነበረው ንጉሥ ዱድያኖስ ንግሥት እለስክንድርያ የምትባል ሚስት ነበረችው። መሳፍንቱና መኳንንቱ ኹሉ ለእርሷ ይሰግዱ ነበር። በሰማዕቱ ትምህርት አምና ለቅዱስ ጊዮርጊስ የፀጋ ስግደትን ሰገደችለት። በዚህም ምክንያት በሚያዝያ 15 አንገቷን በሰይፍ እንድትቆረጥ ተደርጋለች። ያቺ ሣር ቅጠሉ ኹሉ ይሰግድላት የነበረች ንግሥት

ያቺ ሣር ቅጠሉ ኹሉ ይሰግድላት የነበረች ንግሥት ለቅዱስ ጊዮርጊስ መስገዷን ያስተዋለው ሊቁ ግን በማኅሌተ ጽጌው "አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ - አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ" ሲል በእመቤታችንና በሰማዕቱ ምስጋና ላይ ዘከራት። ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍጥረት ኹሉ "ብፅዕት" ለሚላት ለድንግል እንደሚሰግድም "ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ - እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል" ሲል ገልጾአል። "የደናግል መመኪያ፣ የሰማዕታት አክሊል፣ ..." የምትባለው እመቤታችን: ቀደም ሲል ባነሣናቸው ምክንያቶች የተነሣ: ይልቁንስ ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ የከበረች አክሊሉና ዘውዱ መኾኗን ሲገልጽም "ክበበ-ጌራ-ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ... አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ - ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት... ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ" ብሏል። እኛም እንደ አባ ጽጌ ድንግልና እንደ አባቶቻችን በማኅሌተ ጽጌ "ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ" እያልን እመቤታችንንና ሰማዕቱን እንዘክራለን።
@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

26 Oct, 17:10


ይህንን ዓይነት እርማት ላድርግ ብሎ የሚነሣ ሰው መጽሐፍ ቅዱስንም ማረም ሊኖርበት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የተነገረን ቃል ለቅዱሳን ሲሠጥ በተደጋጋሚ እናገኘዋለን፡፡

ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት ፡-

‹‹ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው›› ሲባል ‹‹የዓለም ብርሃን ክርስቶስ ብቻ ነው›› ብሎ የሚቃወም ቢኖር ራሱ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ‹‹እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ፤ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ›› ብሏል፡፡ የእርሱ ብርሃንነት የባሕርይው የቅዱሳን ብርሃንነት ግን ከእርሱ የተሠጠ ነው ብለን እንከፍለዋለን እንጂ የቅዱሳንን ብርሃንነት አንክድም፡፡ (ማቴ. 5፡14)

አንዳንድ ምእመናን ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ሲመሰክሩ ‹‹ለእመቤቴ የሚሳናት ነገር የለም›› ሲሉ የሚሰማ ሰው ራሱን እየነቀነቀ ‹የእኛ ሰው Bible ላይ ብዙ ይቀረዋል› ብሎ ሊመጻደቅ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያውቅ ከሆነ ግን ‹‹እምነት ቢኖራችሁ የሚሳናችሁ ነገር የለም›› የሚለውን የጌታ ቃል ፣ ‹‹ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› የሚለውን የጳውሎስ ቃል በሰማበት ጆሮው ‹ያመነችው ብፅዕት› ‹የልዑል ኃይል ያደረባት› ድንግል ‹የሚሳናት የለም ሲባል ከመቆጣት ይልቅ ለምእመናን የተሠጠውን እምነትና ማስተዋል ያደንቃል፡፡ (ማቴ. 17፡20 ፣ ፊል. 4፡13 ፣ ሉቃ.1፡35፣45)

ለእግዚአብሔር የተነገሩ ቃላት ለቅዱሳን ተደግመው ብናገኛቸው እንኳን ትርጉሙን እንረዳለን እንጂ የእግዚአብሔርን ክብር ቅዱሳን ወሰዱ አንልም፡፡ ለምሳሌ ጌታ መጥምቁ ዮሐንስን ‹የሚያበራ መብራት ነበር ፤ በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ› ሲለው ወንጌላዊው ደግሞ ‹‹እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ብርሃን አልነበረም›› ብሎታል፡፡ የማንን እንቀበል? የጌታችንን ንግግር ወይስ የወንጌላዊውን? ዮሐንስ ብርሃን ነው ወይንስ አይደለም? መልሱ ግልጥ ነው ዮሐንስ ብርሃን ነው ፤ የዮሐንስ ብርሃንነት ግን ከክርስቶስ ብርሃንነት ጋር ሲተያይ የሻማና የፀሐይ ብርሃን ያህል ነውና ብርሃን አልነበረም ተብሏል ብለን እንረዳዋለን፡፡(ዮሐ. 1፡8 ፤ 5፡35)

ይቀጥላል.....


#ኦርቶዶክሳውያን_ለቅዱሳን_ለምን_ይዘምራሉ?
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ክፍል ፬ (የመጨረሻ ክፍል)

የእግዚአብሔርን ክብር አስጠብቃለሁ ብሎ የትርጉም ልዩነቱን ሳይረዳ ለቅዱሳን የሚቀርብን ምስጋና የመተቸት ዝንባሌ ያለው ሰው ግን ይህ አካሔዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያጣላው ነው፡፡ ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች ‹የአዳም ፋሲካው ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ› የሚለውን ቃል በመጥቀስ እንዴት ድንግል ማርያም ፋሲካ ትባላለች ‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል› ይል የለምን እንዳሉ ሰማን፡፡ ስለ እንክርዳድ ማውራት እንክርዳድን ዝነኛ እንጂ ስንዴ ስለማያደርገው ተናጋሪዎቹን ትተን ጉዳዩን እናስተውለው፡፡

ወደ ሌላ ዝርዝር ሳንገባ አንድ ጥያቄ እናንሣ ፤ ክርስቶስ ፋሲካ ነው ወይንስ የፋሲካ በግ? ፋሲካ የሚባለው በዓሉ ነው? ወይንስ በጉ ነው? የታረደው በዓሉ ነው? ቢባል ምን ይመለሳል? "ፋሲካን እረድ" ሲል በጉን ነው (2ዜና 35:5)፣ "ይህ ፋሲካ ለእግዚአብሔር ተፈሰከ" ሲል በዓሉን ነው። (2ነገሥ 23:23)

ፋሲካ ሲል በዓሉን ከሆነ መሻገሪያ ፣ ደስታ ማለት ነውና ለድንግል ማርያምም ሊነገር ይችላል፡፡ ‹ታርዶአል› የተባለው ግን በጉን ነውና እመቤታችንን እመ በግዑ (የበጉ እናት) እንጂ የታረደችው በግ ብለናት እንደማናውቅ ግልጥ ነው፡፡ ጨርሶ ለክርስቶስ የተነገረ ቃል ለእርስዋ ለምን ይደገማል? ከሆነ ደግሞ እስቲ የቅዱስ ጳውሎስን ንግግር እንመልከት፡-

ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 2:20 ላይ ፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ›› ብሏል፡፡ አልፎ ተርፎም ‹‹እኔ ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› ብሏል፡፡ (ገላ. 6፡14)

የዚህ ንግግር ትርጉም ምንድን ነው? ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎ ነበር ማለት ነው? የተሰቀለው በቀኙ ነው የግራው?"ለዓለም ተሰቀልኩ" እንዴት አለ? እውን ለዓለም የተሰቀለው ጳውሎስ ነውን? ክርስቶስ አይደለምን? የፋሲካው ሲገርምህ ለዓለም ተሰቅዬአለሁ ያለ መጣ? ጳውሎስ የተሰቀለውን የክርስቶስን ክብር መሸፈኑ ነውን?

እንደዚያ እንዳንል ደግሞ ራሱ ጳውሎስ ‹‹ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ብሎ አሳርፎናል፡፡ (1ቆሮ 1፡13) ስለዚህ መተርጎም መብራራት አለበት እንጂ ቃሉ ተመሳሰለ ተብሎ አይብጠለጠልም። ጫማ ይስተካከላል እንጂ እግር አይስተካከልም እንደሚባለው መስተካከል ያለበት የእኛ አረዳድ እንጂ የመጽሐፉ ቃል አይደለም።

ሐዋርያው ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ሲል የክርስቶስን የመከራ መንገድ ተከትያለሁ ፣ የመከራው ተሳታፊ በመሆን የክብሩ ተካፋይ እሆናለሁ ሲል ነው። "ለዓለም ተሰቅልኩ" ያለው ደግሞ በክርስቶስ መከራ በማመኔ ለዓለማዊ የኃጢአት ሥራ ሙት ሆኜአለሁ ማለቱ ነው ብለን እናብራራለን እንጂ ጳውሎስ የጌታን ክብር ተጋፋ አንልም፡፡

ቅዱሳንን የምናመሰግናቸው የእግዚአብሔር ስለሆኑና ነቢዩ እንዳለው "እግዚአብሔርም በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ስለሆነ ነው" ሥዕሉ ሲደነቅለት የሚበሳጭ ሠዓሊ እንደሌለ ሁሉ የእርሱ ድንቅ ሥራዎች ሆነው ፣ እርሱን አገልግለው ሲወደሱ ፈጣሪን ደስ ይለዋል እንጂ አያዝንም። ጠርሙስ ሰብራ ሽቱን በእግሩ ላይ ላፈሰሰለች ሴት "ወንጌል በሚነገርበት ሥፍራ ሁሉ ያደረገችው ነገር ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል" ብሎ የተናገረ ጌታ አንገታቸው ተሰብሮ ደማቸውን ስለ ስሙ ስላፈሰሱ ቅዱሳን በዓለም ሁሉ ቢነገርና ቢዘመር የሚከለክል አይደለም። (ማቴ 26፥13)

ምስጋና እንኳን ለቅዱሳን በሃይማኖታችን ከጸናን ለእኛም ለደካሞቹም አልተከለከልንም ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና :–

"ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ" ቆላስ 2፥7

ቤተ ሊባኖስ ₃

26 Oct, 17:07


#ኦርቶዶክሳውያን_ለቅዱሳን_ለምን_ይዘምራሉ?
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ክፍል ፪

ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ላላቸው ሰዎች ብቻ ዘምሮ አላቆመም ፤ ለማትናገረውና ከእንጨት ከድንጋይ በሰው እጅ ለተሠራችው ከተማው ለጽዮን የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆንዋ ዝማሬን አዝንሞላታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል ፤ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዷታል፡፡ እንዲህ ሲል ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፣ መርጫታለሁና በእርስዋ አድራለሁ››
‹‹እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የከበረ ነገር ይባላል››
‹‹በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን ፤ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን ፤ የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ጋር ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ›› ብሎ ስለ ቅድስቲቱ ከተማ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ ከራሱ አልፎም በዙሪያው ላሉት በመዝሙሩ እንዲህ ሲል ጥሪ አቀረበ ‹‹ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ ፤ ግንቦችዋን ቁጠሩ ፤ በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ ፤ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ›› የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንን ለማይወድዱ ደግሞ በመዝሙሩ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ›› ብሎ ዘምሮአል፡፡

ዳዊት ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮት ለሚውልና ለሚያድርባት ከተማ የእግዚአብሔር ማደሪያው እንድትሆን እንደ መረጣት አውቆ እንዲህ ሲዘምር ማየቴ ‹መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል› ለተባለችዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹የጌታዬ እናት ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ› ብዬ ለመዘመር እንድችል ኃይል የሚሠጥ ሆነልኝ፡፡ ባቢሎን በተባለ በኃጢአት ሥፍራ ሆኜ ድንግልን ባሰብኳት ጊዜ እንዳለቅስና ‹‹ድንግል ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ›› ብዬ እንድዘምርላት ድፍረት ሠጠኝ፡፡

የዳዊት ሲደንቀኝ ልጁ ሰሎሞን ደግሞ ‹ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር› (መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) በተባለ ውብ ድርሰቱ ከአባቱ የባሰ የመዝሙር ቅኔን ሲቀኝ አገኘሁት፡፡ በዚህ ዝማሬው ላይ በፍቅረኛሞች መካከል የሚደረግን የፍቅር ቃል ልውውጥ ሰበብ አድርጎ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሙሽራው ስላደረጋትና እርስዋም ‹ውዴ› ብላ ስለምትጠራው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውብ ስንኞችን ጽፎ አገኘሁት፡፡

በዚህ ዝማሬው ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውድዋ የሆነውንና ነፍስዋ የወደደችውን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ስትፈልገው ፣ በከተማ የሚጠብቁ ጠባቂዎች የተባሉ መላእክትን ስትጠይቅ ፣ ቤተ ክርስቲያን በቀዳም ስዑር የምትዘምረው ‹እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት› ብላ አልጋ በተባለ መቃብር ስለ ሰው ልጅ ፍቅር የተኛውን ክርስቶስን እርሱ ወድዶ ሞትን ድል አድርጎ እስከሚነሣ በእምነት እንዲጠብቁ ስትናገር ፣ ውዴ ወደ ገነቱ ወረደ ብላ ነፍሳትን ይዞ ወደ ገነት ስለ መውጣቱ ስትዘምር በሰሎሞን ዝማሬ ውስጥ አገኘሁ፡፡ በዚህ ዝማሬ ላይ ሙሽራው ስለ ሙሽራዪቱ ቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ውበት ፣ ጡቶችዋ ስለተባሉ የቃሉ ወተት ስለሚፈስስባቸው ብሉይና ሐዲስ ኪዳን ማማር ፣ ድንቅ ቅኔ ሲዘምር አገኘሁት፡፡

በሰሎሞን መዝሙር ላይ ‹ወዳጄ ሆይ ነይ ውበቴ ሆይ ተነሽ› ‹ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም› የሚሉት ውብ ዝማሬዎች ለፍጡር እንጂ ለፈጣሪ የቀረቡ ምስጋናዎች አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ውብ ዝማሬ ሁለተናዋ በቅድስና ለተዋበችው ድንግል ማርያም መዝሙር አድርጋ የምትዘምረው፡፡ አባቱ ዳዊት ‹ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽን አዘንብዪ› ብሎ ለጠራት ድንግል ልጁ ሰሎሞን ‹እኅቴ ሙሽራ ሆይ› ብሎ መዘመሩን የምንቀበለውም ከዚህ ተነሥተን ነው፡፡

ይቀጥላል.....
@Abalibanos333

#ኦርቶዶክሳውያን_ለቅዱሳን_ለምን_ይዘምራሉ?
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ክፍል ፫

ቅዱሳንን ማመስገን በዳዊትና በሰሎሞን አላበቃም ፤ መላእክትም ለቅዱሳን ሲዘምሩ ታይተዋል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ‹ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ› ብሎ ለድንግል ማርያም ያቀረበው ሰላምታ ‹ከእንዴት ውለሻል› ሰላምታ ያለፈ ምስጋና አይደለምን? ለዘካርያስ ‹አንተ ከካህናት ተለይተህ የተባረክህ ነህ› ያላለው ይህ መልአክ ለድንግል ለይቶ ያቀረበው በእርግጥም ምስጋና ነበር፡፡ ስለሆነም የገብርኤልን ሰላምታ ተውሰን ድንግሊቱን ለዘወትር እናመሰግናታለን፡፡ ገብርኤል ያቀረበውን እኛ ማቅረብ አያስፈልገንም የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም ድንግሊቱ ‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል› ብላ መናገርዋ ለማመስገናችን ምክንያት ነው፡፡ ‹ትውልድ ሁሉ› አለች እንጂ ሰው ሁሉ አላለችምና ከየትውልዱ የማያመሰግኗት ቢገኙ አይደንቅም ፤ ከእኛ የሚጠበቅብን እንደ ኖህ ‹በትውልዳችን ጻድቅ› ሆኖ መገኘት ብቻ ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል ‹ደስ ይበልሽ› ቢላትም እኛ ‹ደስ ይበልሽ› አንላትም የሚሉ ሰዎች መላእክት ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› የሚሉትን እግዚአብሔርም ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› ለማለት እንዴት ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ?

ለቅዱሳን የሚቀርበው ምስጋና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን የምንደመድመው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው ምስጋና ነው፡፡ ‹‹ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን … እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም›› (ሉቃ. 7፡26-28) ከዚህ በላይ ምስጋና ከየት ይመጣል? በዜማ መሆኑ ከሆነ ችግሩ በንባብ እንለዋለን።

የመጥምቁ ምስጋና በቅዱስ ገብርኤልም አንደበት ተነግሮ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የዮሐንስን ልደት ሲገልጥ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነበር ፤ ወደ መዝሙር ሲለወጥ ‹ዮም ፍስሓ ኮነ በእንተ ልደቱ ለዮሐንስ› እንደማለት ነው፡፡

አባቱ ዘካርያስ ደግሞ ‹‹አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ›› ብሎ ነበር ይህም ‹ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ፤ አርኩ ለመርአዊ ትሰመይ›› የሚለው መዝሙር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዱሳን ስትዘምር ቃላትና ግጥም የምትዋሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

‹‹ሐውፅ እምሰማይ ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ›› (ፀሐይ ተክለ ሃይማኖት ሆይ ከሰማይ ሆነህ ጎብኝ)
የሚል መዝሙር ቢዘመር ‹‹ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ›› የሚለውን የተስፋ ቃል ይዞ ነው፡፡ (ማቴ. ፲፫፥፵፫)

‹‹ጊዮርጊስ ኃያል ኮከበ ክብር›› ተብሎ ቢዘመር ‹‹ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ›› የሚለውን ይዞ ነው፡፡ (ዳን. 12፡3)

‹‹አቡነ አረጋዊ ሆይ ነፍሴ ዛሬ በአንተ ፊት የከበረች ትሁን!›› ‹‹ትክበር ነፍስየ በቅድሜከ ዮም ፤ ወባርከኒ አባ አረጋዊ›› ተብሎ ሲዘመር ብንሰማ አንድ የመቶ አለቃ በነቢዩ ኤልያስ ፊት ተንበርክኮ ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ነፍሴ አሁን በፊትህ የከበረች ትሁን›› ብሎ ካቀረበው ልመና ተወስዶ ነው፡፡ (2ነገሥ. 1፡13)

በአንዳንድ ሥፍራ ለቅዱሳን በሚቀርቡ ምስጋናዎች ላይ ለፈጣሪ የቀረቡ የምስጋና ቃላት ተወስደው ለቅዱሳን ሲቀርቡ ይታያል፡፡ ይህንን የሚያዩ ሰዎች ቅዱሳን የተመለኩ ፣ የፈጣሪ የባሕርይ ክብሩ ለቅዱሳን የተሠጠ መስሏቸው ይተቻሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለቅዱሳን በሚዘመሩ መዝሙራት ሁሉ ላይ የሚታረም ነገር አያጡም፡፡ ሆኖም

ቤተ ሊባኖስ ₃

26 Oct, 17:02


🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ቤተ ሊባኖስ ₃

25 Oct, 09:09


ጋብቻ እና ቃልኪዳን

ቃል ኪዳን ምንድነው? ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ለሆኑ ሰዎች መካከል የሚደረግ የጋራ ስምምነት ስምምነት ነው። ቃል ኪዳን ሰዎች በህግ ማዕቀብ ውስጥ እንዲሆኑና በስነስረአት እንዲመሩ የሚያደርግ አሰራር ነው ። እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳንን በጥንዶች መካከል ትዳራቸውን የመጀመር ዋዜማ ላይ ቆመው በነበረ ሰአት እንዲፈፀም የፈቀደው ተግባር ነው። ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ጋብቻቸውን ለመፈፀም በተቀደሰው ሚስጥር አንድ የሚሆንበትን የጋብቻ ህይወት የሚጀምሩበትን ባሉበት ሰአት እርሱም እርሶም በቤተክርስትያን ውስጥ እርሶም መግባት በሚገባት በር እርሱም መግባት በሚገባበት በር ከገቡ በሆላ እግዚአብሔር አምላክ አንድ ሊያደርጋቸው የሚችል ሁለቱም አንድ የሚያደርግ ቃል ኪዳን ነው ። ቃል ኪዳን በመሰረታዊነት ጋብቻችን ሲጀመር ለጋብቻችን አስፈላጊ ከሆኑ ግባኦታችን አንዱ ነው።ሴቶ ጋብቻዋን ልትፈፅም ባለችበት ቤተክርስትያን ውስጥ ስረአቱ ሲፈፀም በካህኑ አማካኝነት የምትገባው ቃል ይሔ ነው እኔ እገሊት እገሌን የህግ ባል ይሆነኝ ዘንድ ወድጄ ተቀብየዋለው ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ በስራው ሁሉ እረደዋለው በህመምና በጤናው በሀዘንና በደስታው ግዜ ከእርሱ ጋር እሆናለው መከነ ሰነፈ በማለት ይህንን በመሳሰለ ምክንያት ሁሉ ላልለየው በልኡል እግዚአብሔር ከእርሱ በሞት እስከምለይ ወድጄ ተቀብየዋለው ስለዚህ በእግዚአብሔር እና በተቀደሰችው በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ጉባኤ ፊት በመሀላ ቃሌን እሰጣለው ትላለች ። እርሱም ደግሞ የህግ ሚስቱ አድርጎ ሊቀበላት ያላትን ሴት ከእርሶ ጋር የሚኖረውን የልጅነት ኑሮ እንዴት በአግባብና በእንክብካቤ እና በፍቅር እንደሚኖር ገና የትዳሩ መግቢያ ምዕራፍ ላይ በኦርቶዶክስ አማነዊ ቤተክርስትያን ጉባኤ ፊት እና የእግዚአብሔር መሰውያ በሆነው በቤተመቅደሱ ፊት በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብሎ ቃል ይገባላታል ። ወድጄ ተቀብያታለው እስከ እለተ ሞት ድረስ ላልተዋት ብሎ ቃል ኪዳን ይገባል ።


ታድያ ስንቶቻችን ቃል ኪዳናችንን ጠብቀናል ??

ስንቶቻችን ለቃል ኪዳናችን ታማኝ ሆነናል ????

ስንቶቻችን የእግዚአብሔር ቃል አክብረናል ????

ስንቶቻችን የቃል ኪዳናችንን ቀለበት አውልቀት ፍትወት ( ዝሙት ) ሰርተናል ?

አንቺስ እህቴ ቃልሽን አክብረሽ ይሆን?????

ወደ ቃል ኪዳን ከመግባታችን በፊት ወጣቶች አውጥተው አውርደው ሊያስቡበት እና ሊያሰምሩበት ይገባል
@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

25 Oct, 09:09


« ሚስት እንዴት እንምረጥ? »
( ከቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ )
. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .
"እኔ ወደ ጋብቻ ለመግባት ለሚፈልጉ ሰዎች
ምክር ለመስጠት እወዳለሁ። እኛ ቤተሰቦችንና
ባሪያዎችን ልንገዛ ስንል:- ስለሚሸጡልን ሰዎች፣
ስለ ቀደሙት ባለቤቶችና ስለምንገዛቸው ሰዎች
ለማወቅ በጣም እንጓጓለን። በዚህ ዙሪያ ወሬ
ማነፍነፍም እንወዳለን። ስለ ሰውነቶቻቸው
ሁኔታና ስለነፍሶቻቸው ጠባይም ለማወቅ
እንፈልጋለን። ☞አንዲት ሚስት ልናገባ ስንፈልግ
ግን ከዚህ በበለጠ አርቆ አስተዋይነት
ልንመለከት ግድ ነው። አንድ ቤት የተበላሸ ከሆነ
እንመልሰዋለን። አንድ ባሪያ ልፍስፍስ ከሆነ
ደግሞ ለሸጠልን ሰው እንመልስለታለን። ሚስትን
ካገባን በኋላ ግን ወደ ቤተሰቦቿ ልንመልሳት
አንቺልም። እስከ መጨረሻው ከእኛ ጋር ልናቆያት
ግድ አለብን። ስለመጥፎነቷ የምንተዋት ከሆነ
እንደ እግዚአብሔር ሕግ በዝሙት እንወነጀላለን።
ስለዚህ ሚስት ልትወስዱ (ልታገቡ) ስትሉ
የመንግሥትን ሕግጋት ብቻ አታንብቡ።
እግዚአብሔር አምላክ የሚፈርድባችሁ
በመንግሥት ሕግ ሳይሆን በራሱ ሕግ ነውና።
አብዛኛውን ጊዜ የገንዘብ ቅጣት
የሚያስከትለውን የመንግሥት ሕግ እርሱት።
የእግዚአብሔርን ሕግ መርሳት ግን ነፍስ
ልታመልጥ የማትችለውን ቅጣት ከማምጣቱም
በተጨማሪ የማይጠፋ እሳት ያስከትላል።
እናንተ ሚስት ልታገቡ ስትሉ በጉጉት ፈጥናችሁ
የምትሄዱት መንግሥታዊ ወደ ሆነው የማዘጋጃ
ቤት ሕግ ነው። ....... የሚስታችሁ ንብረት
ከሆነው ውስጥ አንዱም ወደ እርሷ ዘመዶች
እንዳይገባም ማንኛውንም አይነት ምርመራ
ታካሂዳላችሁ። .............. ታዲያ ይኼ ጅልነት
አይደለም እንዴ?
እኔ ሚስት ለማግባባት ለተዘጋጁ ሰዎች ምክር
የምሰጠውና አጥብቄ የማሰማው ወደ ተባረከው
ሐዋርያ ጳውሎስ በመቅረብ ጋብቻውን
አስመልክቶ የዘገባቸውን ሕግጋት እንዲያነቡ
ነው።"
@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Oct, 09:21


ፍትወትን ለመግታት ጾም፣ጸሎት፣ ስግደት የሚባሉ ልጉዋሞች አላቸውና፡፡ ጾም፣ጸሎት፣ስግደት ቢኖረንም ፍትወት ፈተና ሆኖ ለመነሳት ትንሽ ነው የሚበቃው፡፡ ለዛም ነው ፍትወት የሁሉም የፈተና ሕይወት የሆነው፡፡

ታድያ ፍትወት ለባልና ለሚስት ፈተና ቢሆን የሰውን የሥጋ ጾር ሳያገናዝቡ ቀኖናን ብቻ ተገን አድርገው ‹‹ሥጋዬ የራሴ ነው ስለዚህ ሥልጣኑ ስላለኝ ሩካቤ አልፈልግም›› በማለት በራስ ገላ በመመካት ትዳሩ ችግር ውስጥ እንዳይገባ ሐዋርያው ሁነኛ መፍትሔ አስቀምጧል፡፡ ይህ መፍትሔው የአንዱን መብት ለአንዱ በመስጠት ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ መብቱም ቀኖናን የጣሰ ሳይሆን ፈተናችንን የተንተራሰ መፍትሔ ነው፡፡ ይህም ‹‹ሚስት በገዛ ሥጋዋ ልይ ሥልጣን የላትም፣ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፣ሥልጣን ለሚስት ነው እንጂ›› በማለት ዘግቶታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 7÷4

ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን ከሌላት መብቱ ሥልጣኑ የባል ነው፡፡ ስለዚህ ሥልጣን በሌላት ገላዋ ላይ ማዘዝ አትችልም አዛዡ ባል ነው፡፡ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን ከሌለው ሥልጣኑ መብቱ የሚስቱ ነው፡፡ መብት እና ሥልጣን በሌለን ገላ ላይ አዛዥ መሆን አይቻልም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ መብት እና ሥልጣን አለኝ በማለት አንዱ በአንዱ ላይ መንፈሳዊ እንቅፋት እና ፈተና መሆን የለበትም፡፡ በመነጋገር በመመካከር የሚደረግ ነገር ነው፡፡

እንግዲህ ሩካቤን እርስ በእርስ ለመከላከል የፍትወት ሰጣ ገባ ውስጥ የገባችሁ ልብ በሉ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ አንዱ በአንዱ ላይ ሥልጣ አለው ያለው ለተቸገሩት ያዘጋጀው የፈተና በር መውጫ ነው፡፡ አስቡት እስኪ ስንት ባለ ትዳሮች አንዱ የአንዱን ፈተና ባለመረዳት፤ቀኖናን ብቻ በማየት ሩካቤን ሲከላከሉ፤ለፍቺ ይዳረጋሉ፡፡ ሐዋርያው እያለን ያለው ፈተና በሚገጥማችሁ ጊዜ ሕገ እግዚአብሔር የሆነው ትዳሩ ሳይሆን ሕገ ሥጋ የሆነው ጾሙ ይፍረስ ዓይነት ነው፡፡

ለማንኛውም ሩካቤን እንደ መድኃኒት መጥነው ቢወስዱት እመክራለሁ፡፡ ምክንያቱም የትኛውም ፈዋሽ መድሃኒት ከሐኪሙ ትዕዛዝ ውጭ ቶሎ እድናለሁ በማለት ጨማምረው ቢወስዱ መድኃኒቱ ከመፈወስ ይልቅ አደጋ ላይ እንደሚጥል ሁሉ ሩካቤም ከቤተ ክርስትያን ቀኖና ውጪ እንደፈለጉት ቢሆኑበት ከደስታው ይልቅ መሰላቸቱ፣ከክቡርነቱ ወደ ተራነቱ ይሄድብናል፤ቅድስናውንም ያጣል፡፡

ስለዚህ ሩካቤያችን ፈተናችንን፣ችግራችንን ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ባለ ትዳሮች በትዳራቸው መሃል የአንዱ የፍትወት ፍላጎት በሥጋ ባሕርይ ይሆን በሰይጣን ፈተና ያይልና አንዳቸው ሩካቤን ለእግዚአብሔር ሕግ ታማኝ ከመሆንና፣ለቀኖና ዘብ ከመቆም አንጻር ሩካቤ ሥጋን ይከላከሉና መጨረሻ ወደ ፊቺ ይሔዳሉ፡፡ ስለ እውነት በእንደዚህ ዓይነት የተፋቱ ባለ ትዳሮች ካሉ ስለ እግዚአብሔር ሕግ መከበር የፈቱ መስሏቸው ከሆነ ትልቅ ስህተት ሰርተዋል፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋና ሰማያዊ ክብር የሚያገኙት ለትዳር አጋራቸው መስዋዕት ቢሆኑና ችግሩን ቢጋሩ ነበር፡፡

@Abalibanose333

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Oct, 09:20


የሩካቤ ነገር የነፍስና የሥጋ ነገር ነው

ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈውን ገለጥለጥ አድርገን ስናየው!

ተጻፈ በቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም በትዳር ላሉት በጾሙ በሩካቤ ሥጋ ለሚወዛገቡት

እስኪ ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ እምነት ያለ ምግባር ዋጋ እንደሌለው ስላወቀ እኛ እንረዳው ዘንድ ‹‹በሞት›› መስሎ ነው ያስተማረው፡፡ የመልእክቱን ምዕራፍ ሁለትን አጋማሽ እምነትንና ምግባርን እያጣመረ፤አስረጅ ምሳሌን እየደረደረ ጽፏል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው›› የሚለውን ልዋሰውና ወደ ትዳር ላምጣው፡፡ ያዕ 2÷16

ሩካቤ የተለየው ትዳር ልክ ነፍስ እንደ ተለየው ሥጋ ትዳሩም ይሞታል፡፡ እምነትንና ምግባርን መለየት እንደማይቻል ቢለይም እንደማያጸድቅ ሁሉ ሩካቤ የተለየውም ትዳር የሞተ ነው፡፡ ሩካቤ ቢለየውም ትዳር ሳይሆን ምነና ነው የሚሆነው፡፡ ታድያ አንዳንዶች ከተጋቡ በኋላ በቤት ውስጥ አንዳቸው ይጰጵሱና ባገኙት አጋጣሚ ሩካቤን ይከላከላሉ፡፡ እኔ አጸዋማትና የግዝት በዓላት፤ ሰንበታትን አርብ ረቡዕን ካልሆነ በስተቀር በየምክንያት ሩካቤን የሚከላከሉ ለእኔ አጥፍቶ ጠፊ ናቸው፡፡ እራሳቸውንም፣ የትዳር አጋራቸውንም፣ ክቡር ትዳሩንም ያጠፋሉ፡፡

ሩካቤና ትዳር እንደ ነፍስና ሥጋ የተጣመሩ፤ እርጅና እስካልገደባቸው ድረስ አብረው የሚኖሩ፣የፈጣሪ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ነፍስ ሥጋ ሲያረጅባት ወደ ሰማያዊው ቤት በሞት ምክንያት እንደምትሔድ ሁሉ ሩካቤ ሥጋም፤ ሥጋ ሲያረጅ ስሜት ከሥጋ ይለያል፤ ያኔ ሥጋም ለሩካቤ ይሞታል፡፡
አንዳንድ ባለ ትዳሮች መንፈሳዊነትን ብቻ ተገን በማድረግ እንደ ነፍስና ሥጋ፤እንደ ሰምና ጧፍ በባሕርያቸው የተጣበቀውን ሩካቤ በቀኖና ምክንያት ለመለየት ይሞክራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በትዳር ያልኖረው፣ ጣዕመ ሩካቤን ያላወቀው ቅዱስ ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት የከተበልንን አላወቁም ማለት ነው፡፡

ወዳጆቼ የከረረ ገመድም ስለሚበጠስ አክርረን ሳይሆን አጥርተን አፍታተን በደንብ እናየዋለን፡፡ ምክንያቱን ብዙዎች የመንፈሳዊ ሥርዓተ ጋብቻን ከሚፈሩበት አንዱ ሩካቤው በራሱ ጦም/ማዕቀብ/ ይበዛዋል ከሚል መነሾ ስለሆነ እያጠራን እንየው፡፡ ስለ ሩካቤ ጉዳይ ከቅዱስ ጳውሎስ ይልቅ በትዳር የኖረው ቅዱስ ጴጥሮስ በጻፈልን ነበር፡፡ ግን የሩካቤ ነገር፤የቅዱስ ጴጥሮስ ልምድ የታከለበት፤እግዚአብሔር የተጨመረበትን መልእክት ከሚጽፍልን ይልቅ በተግባር ያላወቀው፣በመንፈስ ቅዱስ የተረዳው ቅዱስ ጳውሎስ መጻፉ ይገርማል፡፡ ስለ ሩካቤ ጣዕም ያላወቀው ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አውቆ፤እንደ ሕግ አርቅቆ በትእዘዝ ስለ ጻፈልን በእግዚአብሔር እንገረማለን፡፡ ህቡእ የሆነውን ተገልጧልና፡፡

ታድያ ከሁለት አንዱ የቤት ውስጥ ጳጳስ በመሆን ትዳሩ በሩካቤ ምክንያት እንዳይቃውስ፤ በማክረር ሳይሆን በማለዘብ፣አንደ ቀንበር ሳይሆን እንደ ቀሊል ሸክም ቆጥሮ ሩካቤን እርስ በእርስ መፈቃቀድን፣መከላከልን ከነ ምክንያቱ በማስቀመጥ ጽፎልናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እናመሰግንሃል! ነገረ ሩካቤያችንን እንደ ልጅ እያባበለልን ‹‹ዳሩ ግን ይህን እንደ ፈቃድ እላለሁ እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም›› እያለ ይለማመጠናል፡፡ 1ኛ ቆሮ 7÷6 በነገረ ሩካቤ ዙርያ ከቅዱስ ጳውሎስ ሐሳብ ጋር ካልተስማማን ከቤተ ክርስትያኒቱ ቀኖናና ከትዳር አጋራችን ጋር እንጣላለን፡፡ በቤተ ክርስትያናችን በምንም ምክንያት በተለይም በፍትወት ተግባርና ጽንሰ ሐሳብ ምክንያት መለያት አይቻልምና፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ነገረ ሩካቤ የትዳር ጦስ እንደሚሆን ስላወቀ ነው ትእዛዝ ሳይሆን በመፈቃቀድ ይሁን ያለው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ነገረ ሩካቤያችንን መከላከል ያለብን በነገር ሳይሆን ለጾም ለጸሎት ክብር መሆን እንዳለበት እንዲህ ይለናል፡፡ ‹‹ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር እርስ በእርሳችሁ አትከላከሉ፤ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈትናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ›› ብሎ ብዙ ሐሳቦችን በዚህ ጠቅልሎ ጽፎልናል፡፡ 1ኛ ቆሮ 7÷5

ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ሰብሰብ አድርጎ የነገረንን እኛ ደግሞ ግልጥልጥ አድርገን እንየው፡፡ በመጀመርያ ‹‹ለጸሎት ትተጉ አንድ›› ያለን ማታ፣ሌሊትና ጠዋት በጸሎት እንድንተጋ እንጂ እዛ ነገር ላይ ብቻ መትጋት የለባችሁም ሲለን ነው፡፡ እሱ ነገር ላይ መትጋት፤ለመንፈሳዊ ዝለት ስለሚዳርግ ነው፡፡

ሩካቤን ለመጋራት ጠበቅ አድርገው ከያዙ፣ እንደ ምግብ ካበዙ፣ ከጸሎት፣ከኪዳን፤ከቅዳሴ ብሎም ከቁርባን ያርቃልና ነው፡፡ በሩካቤ መትጋት ለመንፈሳዊ ስንፍና ይዳርጋልና ‹‹ለጸሎት ትተጉ ዘንድ›› አለን፡፡ ‹‹ተስማምታችሁ›› ያለን በጾም ወቅት ፍትወት ይፈትናልና፡፡ ምክንያቱም እኛ የሰው ልጆች ጥንት የገነት ታሪካችንን ስንመለከት የተከለከለ ነገር ለማድረግ እንቸኩላለንና፡፡ በጾም ወቅት የፍትወት ጾር ስለሚበዛ መስማማት ፍትወትን ለመፈጸማና ላለመፈጸም ወሳኝ ነውና፡፡

‹‹ለጊዜው ካልሆነ በቀር›› የተባለው የአዋጅ አጽዋትን የተመለከተ ነው፡፡ ጾሞቹ ጊዜያዊ ስለሆኑ በእነዛ ቀናት፣ወራት ፍትወትን በጾም በጸሎት አስታግሱት ነው፡፡ ‹‹እርስ በእርሳችሁ አትከላከሉ›› ያለው ‹በቀር› የምትለዋ አፍራሽ ስለሆነች አጽዋማት የግዝት በዓላት ከሌሉ ፍትወትን ተጋሩ፣ እንጂ አንዱ አንዱ ላይ ማዕቀብ አይጣል፤ እንቢኝ አይበል ነው፡፡

‹‹ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈትናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ›› ያለው ሦለት ትርጓሜ ይኖረዋል፡፡ አንደኛው በጾም ወራት ጾር እንዳይፈትነን በመስማማት ከምናደርጋቸው ነገሮች ውስጥ አልጋ መለየት ነው፡፡ ግን አልጋ በመለየት የፍቅር የትዳር ሙቀት መቀዛቀዝ ከመጣ አልጋ ከመለየት አብሮ መተኛት ይሻላል ነው፡፡ ምክንያቱም ፍትወትን የምናሸንፈው አልጋ በመለየት ሳይሆን እራስን በመግዛት ነውና፡፡ ለበረቱት ለተጉት፣መንፈሳዊነትን አሟሽተው ለሚኖሩት፣የሥጋን ነገር ትተው ለነፍስ ያደሉት እንኳን አልጋ መለየት ፍትወትን ማጥፋት ስለሚችሉ ቢለዩም ይችላሉና፡፡ ግን ለወጣንያን ቢከብድም መሞከሩ አይከፋም፡፡

ሁለተኛው ትርጉም ፍትወትን ለመግታት አልጋ መለየት ፍቱን መድኃኒት ነው ብላችሁ ለመስማማት እራሳችሁን/ሥጋችሁን/ መግዛት ካልቻላችሁ አብራችሁ ሁኑ፡፡ ምክንያቱም የናንተን የቀናት፣የወራት በጾም ምክንያት መለያየትን ያየው ሰይጣን እንዳይፈትናችሁ አብራችሁ ሁኑ ነው፡፡ ሦስተኛው ሥጋችሁን መግዛት ባለመቻላችሁ ሰይጣን የዝሙት ምክንያት እንዳይሆናችሁ ከሚስታችሁ፣ከባላችሁ ጋር ሁኑ ነው፡፡

‹‹ዳሩ ግን ይህን እንደ ፈቃድ እላለሁ እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም›› ያለውን ልብ በሉ፡፡ ‹ፈቃድ› በመስማማት እና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ድርጊት ነው፡፡ ‹ትእዛዝ› በሕግ የተደነገገ፣ የተወሰነ፣ግዳጅ ማለት ሲሆን ግሱ መከናወን ያለበትን ነገር ለመግለጽ የምንጠቀምበት ነው፡፡ ስለዚህ ነገረ ሩካቤያችን ጾር በሚነሳ፣ፍትወት በሚያገሳ ጊዜ እንኳን አብራችሁ ብትሆኑ የሕግ ግዴታ ውስጥ የማእቀብ ማዕቀፍ ውስጥ አትገቡም ሲለን ነው፡፡ ስለዚህ ነገረ ሩካቤ በሕግ የታሰረ ሳይሆን በቀኖና በፈቃድ የተመሠረተ ነው፡፡ ለዚህም ነው እግዚአብሔር በቅዱስ ጳውሎስ አድሮ የሩካቤ ምሬት ውስጥ እንዳንገባ ትእዛዝ ሳይሆን ፈቃድ አድርጎ የሰጠን፡፡

ምክንያቱም በመንሳዊ ሥርዓት ስላገባን መንፈሳዊ ሩካቤ የለም፡፡ ፈተናው በዓለማዊም በመንፈሳዊም ያገባው ላይ እኩል ነው፡፡ ሁለቱም ሥጋ ነው የለበሱት፡፡ በዓለማዊ ያገባ ሰው፤ በመንፈሳዊ ሥርዓት ያገባው መልአክ አይደለምና፡፡ ልዩነቱ መንሳውያን ተጋቢዎች

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Oct, 08:49


በወር አበባ ወቅት መከልከል የሚገባው ከምን ከምን ነው ?



ሀ ከሩካቤ ፦ የወር አበባን የምታይ ሴት ባለ ትዳር ከሆነች በደሟ ወቅት ምንም እንኳን ባሏም ቢሆን ሩካቤ መፈፀም በመንፈሳዊ ህግ አይፈቀድላትም ። የህክምና ባለሙያዎችም ቢሆኑ በደም ወራት የሚደረግ ሩካቤ በአብዛኛው ለአባላዘር ፣ ለልዩ ልዩ ተላላፊ በሽታዎችና ለኢንፌክሽን በቀላሉ ሊያጋልጥ እንደሚችል ይናገራሉ። መፅሐፍ እንዲህ ይላል "እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልፅ ዘንድ ሴት አትቅረብ " (ዘሌ 18:19) ምንም እንኳን የወር አበባ በአዲስ ኪዳን መርገም ወይም ርኩሰት ስላለልሆነ በዚህ ወቅት ሩካቤ የሚፈፅሙ ሰዎች እንደ ኦሪቱ በድንጋይ ተወግረው ባይሞቱም ተገቢው ቀኖና ግን ይሰጣቸዋል

ለ.ከመጠመቅ ፦ ሐዋርያው ጴጥሮስ "ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ... የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም ። ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ " በማለት ተናግሯል ። ( 1ኛ ጴጥ 3:21) ስለዚህ ጥምቀት ሥጋዊ እድፍ ማስወገጃ ስላልሆነ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው ከአፍአዊ እድፍ ከጠሩ በሁዋላ መጠመቅ ይገባል ። አንዳንድ ጊዜ በጠና የታመሙ ሴቶች በፀበል ለመፈወስ ክትትል ሲጀምሩ ልዩ ልዩ ፈተና ያጋጥማቸዋል ከፈተናዎቻቸውም ውስጥ አንዱና ዋነኛው ያለ ወሩ ያለ ማቋረጥ ወይም በተደጋጋሚ መከሰቱ ነውይህን የመሰለ ነገር ሲከሰት ከሰይጣን ጋር እልህ መጋባትና ዝም ብዬ ብጠመቅ ምን አለበት ? ማለት ሞኝነት ነው

ሐ.ከመቁረብ ፦ ምንም እንኳን ለቁርባን የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቁ ቢሆኑም ሴቶች ከደመ ፅጌ ሳይነፁ ሥጋና ደሙን መቀበል አይችሉም ይህን ሥርዓት ተላልፎ ሴቶችን ከወር አበባ ሳይነፁ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡና ሥጋውን ደሙን እንዲቀበሉ ያደረገ ቢኖር ዲያቆን ሆነ ቄስ ከክህነቱ እንዲሻር ፍትሐ ነገስት እንዲህ ሲል ይደነግጋል "ከግዳጅዋ ያልነፃችውን ሴት በደሟ ወራት ከቤተ ክርስቲያን አግብቶ ሥጋውን ደሙን ያቀበላት ከመዓርጉ ይሻር " (ፍት.ነገ 6)

መ.ቤተ መቅደስ ከመግባት ፦ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ሆና መማር መፀለይ ትችላለች መቅደስ መግባት ግን ክልክል ነው ።

@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Oct, 08:49


የወር አበባ ርኩሰት ነውን ?


ምንጩ ባይታወቅም በወር አበባ ላይ ያሉ አንዳንድ ሴቶች መስቀል ሊያሳልሟቸው ሲሉ ርኩስ ነኝ አያሳልሙኝሲሉ ይደመጣሉ። ሌሎች ደግሞ ደመ ፅጌ ሲታያቸው ከፀሎት ፣ ቅዱሳት መፃህፍትን ከማንበብ ፣ አልፎ ተርፎም ለዝክርና ለፀዲቅ የሚሆን ማንኛውንም ሥራ ከመስራት ይከለከላሉ

ማለትም ስንዴ ከመልቀም ፣ አሻሮ ከመቁላት ፣ እንኩሮ ከማነኮር እስከ መከልከል ይደርሳሉ ። በእርግጥ የወር አበባ ርኩሰት ነውን ? ርኩስስ ያሰኛልን ? በእርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር ። መፅሐፍቅዱስ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የምታይን ሴት ለመጥቀስ "በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች " እና "ባለ መርገም ሴት "ሲል ይገኛል ። ከወር አበባ የነፃችን ሴት ለመጥቀስ ደግሞ "ከርኩሰቷ ነፅታ" ነበርና በማለት ይገልፃል

በዘመነ ኦሪት የመርገምና የርኩሰት ምልክት ነበር ። ይህ የሆነበት ምክንያት ዕፀ በለስን ሔዋን ስትቆርጣት ስለደማች "የዚህችን ዕፀ በለስ ደሟን እንዳፈሰስሽ የአንቺም ደም በየወሩ ይፍሰስ " ብሎ ፈጣሪ ስለረገማት ነው ። ይሁን እንጂ የረከሰ በተቀደሰበት የተረገመ በተባረከበት በዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን የወር አበባን ርኩሰት ነው ማለት ቀርቶ መታሰብም የለበትምየወር አበባ ርኩሰት መሆኑ ቀርቷል ርኩሰት አይደለም ርኩስም አያሰኝም

በአዲስ ኪዳን ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈፀመው ቤዛነት መርገምነቱና ርኩስነቱ ተወግዷልና ። አንድ መዘንጋት የሌለበት ነገር የወር አበባ ርኩሰት ባይሆንም አደፍ ነው ። አደፍ (እዳሪ) ነው ማለትና ርኩሰት ነው ማለት ከፍተኛ ልዩነት አላቸው ። ርኩሰት ውሳጣዊ ነው በንስሀ እንጂ በውሀ አይጠራም ። አደፍ ግን አፍአዊና የሚታይ ነው ። ስለዚህ ውሀ ያጠራዋል ። የወር አበባ እዳሪ ነው ሲባል ሰውነታችን እንደሚያስወግዳቸው ማንኛውም ሌሎች ነገሮች አፍአዊ ቆሻሻ ነው ማለት ነው ። የወር አበባ ከሴቶች ባህሪ ሳለ እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም ሰውነት ሲያስወግደው ግን ይቆጠራል

ለምሳሌ ፦ ዛህል (ንፍጥ) ፣ ሽንት ፣ ምራቅ፣ ዓይነምድር፣ ላብ እነዚህ ሁሉ በሰው ባህሪ በሰውነት ውስጥ ሳሉ ጠቃሚና አስፈላጊ ነበሩ ። ሰውነት ሲያስወግዳቸው ግን እንደ ጉድፍ ይቆጠራሉ። የወር አበባም እንዲሁ ነው ። ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳለም ፣ ከመፀለይ ፣ ቅዱሳት መፃህፍትን ከማንበብና ከመድገም አያግድም በቀጣይ ደሞ በወር አበባ ወቅት ከምን ከምን መከልከል ይገባል ? የሚለውን እናያለን
@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Oct, 08:48


የወር አበባ



በመንፈሳውያን መፃህፍት የወር አበባ ልዩ ልዩ ስያሜዎች አሉት ። ሙሴ ስለ አብርሃምና ሳራ በሚተርክበት ጊዜ " አብርሃምና ሣራም በዕድሜያቸው ሸምግለው ፈፅመው አርጅተው ነበር ፤ በሴቶችም የሚሆነው ልማድ ከሳራ ተቋርጦ ነበር " በማለት ተናግሯል ። በዚህም ትረካው ሙሴ የወር አበባን በሴቶች የሚሆነው ልማድ በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ሰይሞታል (ዘፍ 18:11)ከዚህም በመነሳት ሌሎች ቅዱሳት መፃህፍትና መምህራነ ቤተክርስቲያን ልማደ አንስት ሲሉ ይገኛሉ

የወር አበባ "የወር" የተባለበት ምክንያት ወር ጠብቆ የሚመጣ ስለሆነ ሲሆን "አበባ " የተባለበት ምክንያት ግን ሴቶች በዕፅ ፣ በየወሩ የሚያዩት ደም በአበባው ፤ የሚወልዷቸው ልጆች ደግሞ በፍሬው ስለሚመሰሉ ነው መፅሐፈ ስነፍጥረት ከመፅሐፈ ምስጢር ጠቅሶ እንዲህ ይላል ፦ "ለአንድ ተክል አበባው ቀድሞ ፍሬው እንዲከተል ለሴቶች ደሞ በመጀመሪያ የወር አበባ ቀድሞ ይታያቸውና በሁዋላ ልጅ ለመውለድ ይበቃሉ" ይላል ።

አዳምና ሔዋን በገነት በነበሩበት ጊዜ ምንም እንኳን በሔዋን የወር አበባ ባህርይ የነበረ ቢሆንም ደሟ በአፍአ አይታይም ነበር ዕፀ በለስን በልተው በበደሉ ጊዜ ግን ሔዋን ስትቆርጣት እፀበለስን አድምታታለችናፈጣሪ ደሟ በየወሩ እንዲፈስ በሔዋን ፈረደባት ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከገነት ውጪ ሆና ስትኖር ደሟ በየወሩ ይፈስ ጀመር እንደሚታወቀው ዝናብ መዝነብ የጀመረው በምድር ላይ ኃጢአት እየበዛ መጥቶ እግዚአብሔር ዓለምን በጥፋት ውኃ እንድትጠፋ ካደረገ በሁዋላ ነው

ከዚያ አስቀድሞ ውስጥ ለውስጥ በሚሄድ ጉም ምድር ትረሰርስ ነበር እንጂ አይዘንብም ነበር ። ከዚህ ቡሃላ ውስጥ ለውስጥ ያረካት የነበረው ውኃ ዝናብ ሆኖ እየመጣ ምድርን ከውጭ ያጨቀያት ጀመር ። ምድር ለሔዋን ምሳሌ ናት ። ሰው ምድር ይባላልና ዝናብ ደሞ የወር አበባ ምሳሌ ነው ከውስጥ ለውስጥ ይሄድ የነበረው ውኃ ከጊዜ ቡሃላ በውጭ ተገልጦ ምድርን ማጨቅየቱ በሔዋን የነበረ ደም ከጊዜ በሁዋላ በአፍአ መታየት መጀመሩን ያስረዳል ለዐቅመ ሔዋን የደረሰች ሴት ደመ ፅጌ በምታይባቸው ዕለታት የጡንቻና የአጥንት መልፈስፈስ(ድካም) ያጋጥማታል

በተጨማሪ የጀርባ ህመም ፣ሆድ ቁርጠት ፣ የምግብ መሸርሸር ችግርና የምግብ ፍላጎት ማጣት ለመሳሰሉት የሕመም ስሜቶች ስለምትጋለጥ በአመጋገብና በቂ ዕረፍት በማግኘት ረገድ ምቾት ያስፈልጋታል ዕረፍት ሲባልም ተኝቶ መዋል ሳይሆን ከከባድ ስራና ፈጣን እንቅስቃሴ ሚጠይቅ ስራን ከመስራት መቆጠብ ማለት ነውከሚኖረው ህመም በተጨማሪ ትዝብት ላይ እስከ መውደቅ የሚያደርስ መቅበጥበጥና አንዳንድ ጊዜም የመደበር እና በሆነው ባልሆነው በቀላሉ የመከፉት ሁኔታ ሊንፀባረቅ ይችላል

በዚህ ወቅት የሚገኙ ሴቶችን መንከባከብ እንደሚገባ ከቀደሙት መፃህፍት መረዳት ይቻላል ላባ የተባለ ሰው የጠፋበትን ዕቃ በሚፈልግበት ጊዜ በወር አበባ ላይ ትገኝ የነበረችውን ልጁን ራሄልን ከተቀመጠችበት ቦታ ላለማስነሳት የተቀመጠችበትን ስፍራ ከመበርበር ተቆጥቧልበምን አውቆ ቢባል እርሷም አባቷን " በፊትህ ለመቆም ስላልቻልኩ አትቆጣብኝ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛል" አለችው ስለሚል ። (ዘፍ31:35) ይሄ ታሪክ የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶችን መንከባከብ እንዳለብን ያስረዳል በቀጣይ ደሞ የወር አበባ ርኩሰት ነውን ? የሚለውን እናያለን

@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Oct, 08:48


​​​​ግለ ወሲብ / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ይገባዋል?

#ካለፈው_የቀጠለ

ቤተ ፈት የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈትታ የኮበለለች ሴት ናት። ከሄደችበትም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በምትኖርበት ጊዜ የነበራት ምቾትና ክብር ነው። አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም። ማለትም ኃጢአት ሠርቶ ከገነት በተባረሩ ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀምኩት እያለ ስለ በደሉ ያለቅስ ነበረ እንጂ የገነት ተድላ ደስታ ቀረብኝ እያለ ስላጣው ነገር አያዝንም ነበር።

" አልቦቱ ካልዕ ሕሊና ለአዳም ዘእንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ" ሰለ ኃጢአቱ ከማልቀስ በቀር ለአዳም ዘእንበለ ብካይ አልነበረውም። የተባለው ሰለዚህ ነው።

እንደዚህ ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ የዝሙት ኃጢአት በተስነካከለ ጊዜ "ድንግል ነኝን? ተክሊልስ ይገባኛል? " እያለ ያጣውንና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ " አንተን ብቻ በደልሁ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ ።" (መዝሙረ ዳዊት 51: 4) ማለት ኃጢአቱን እያሰበ ቢያለቅስ በንስሐ አዳምን መስሎታልና የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ይባላል።

በመጨረሻ ከማስተርቤሽን እና ይህንን ከመሰሉ የዝሙት ርኩሰት መንገዶች የምታመልጠው በተቀደሰው ጋብቻ አማካኝነት ነው። ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ፦ " ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7: 2) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዝሙትን ጠንቅ ብሎ ነው የጠራው በወጣትነት ወራታችን ከዲያብሎስ ከሚወረወሩ ፍላጻዎች መካከል አንዱ የዝሙት ፍላጻ ነው ይህንን ፍላጻ ለመመከት ጋብቻ መመከቻ ጋሻ መሆኑን ከገጸ ንባቡ እንረዳለን።

በእውነት ከሴጋ የኃጢአት ዓለም ወጥተን በተቀደስ ጋብቻ ለመኖር ማሰባችን የሚመሰገን መንፈሳዊ ውሳኔ ቢሆንም ጋብቻችንን ግን በትህትና በተሰበረ ልብ ልንፈጽም መዘጋጀት ይኖርብናል።

አንዳንድ ሰዎች ማስተርቤሽን ሲፈጽሙ ከኖሩ በኋላ የንስሐ አባቴ ፈቅደውልኛል በማለት ተክሊል ለመፈጸም ሲዳፈሩ ይታያል። እነዚህ ሰዎች ሰለ ማስተርቤሽን በጥልቀት ለንስሐ አባታቸው ሳይናገሩ በሥጋ ብቻ ድንግል መሆናቸውን አጉልተው በማምታታት /በማድበስበስ/ ኑዛዜ ፈጽመው ወደ ተክሊል ለመምጣት የሚያደርጉት ጥረት ለመአት ካልሆነ የበረከት መንገድ አለመሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነውና መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ተወዳጆች ከድፍረት የሚገኝ ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የለም። ድፍረት መንፈሳዊ ኪሳራን ያስከትላል ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ያለው " የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።" (መዝሙረ ዳዊት 19: 13) ምን አልባት አንዳንድ ካህናት ሰለዚህ አይነት ኃጢአት ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ተክሊል ፍጽሚ ተክሊል ፈጽም ቢሉን እንኳን ራሳችንን ዝቅ በማድረግ አይገባኝም ልንል ያስፈልጋል።

#ሼር
@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

24 Oct, 08:48


​​ግለ ወሲብ / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ይገባዋል?

በወጣትነት ወራት ሰለ አባል ዘር ሥራና ውጤት ለማወቅ ካለ ጉጉትና ለተቃራኒ ፆታ የሚኖር ዝንባሌ ከመጨመሩ የተነሣ ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች የመራቢያ አካላቸውን በመነካካት ጾታዊ ሰሜት እንዲሰማቸውና የስሜት እርካታ እንዲያገኙ ሆን ተብሎ የሚፈጸም ተግባር ሴጋ ወይም ግለ ወሲብ በመባል ይታወቃል።

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሰለ ግለ ወሲብ በዝርዝር ማብራራት ሳይሆን ማስተርቤሽን የተባለውን የዝሙት ኃጢአት የፈጸመ ሰው ተክሊል መፈጸም ይችላል ወይስ አይችልም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው። ተወዳጆች እያወራን ያለነው ከወንድ ጋር በአካል ዝሙት ፈጽማ የማታውቅ ነገር ግን የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሷን በራሷ ለማርካት ማስተርቤሽን ቪዲዮ ሰለፈጸመች ኦርቶዶክሳዊ ሴት ወይም ከሴት ጋር በአካል ዝሙት ፈጽማ የማያውቅ ነገር ግን የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሱን በራሱ ለማርካት ማስተርቤሽን ሰለፈጸመ ኦርቶዶክሳዊ ወንድ ነው።

እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ከተቃራኒ ጾታ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሳያደርጉ ለእንደዚህ አይነት የዝሙት ተግባር በመጋለጣቸው ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከወንድ ጋር በምንጣፍ አንድ አልሆንኩም ነገር ግን ማስተርቤሽን ፈጽሚያለሁ ድንግል ልባል እችላለሁ ለደናግላን የሚፈጸመው ሥርዓተ ተክሊልስ ለእኔ ልፈጸምልኝ ይችላል? የሚለው ዋነኛ ነው።

ይህ ጥያቄ በራሱ ተገቢነት የሌለው ትሕትና በማጣት ዲያቢሎስ እየፈተነን መሆኑ ማስረጃ ነው። አንድ ኦርቶዶክሳዊ ከማንኛውም የዝሙት ተግባር እርቆ ከኖረ በኋላ ተክሊል ሊፈጽምለት ሲል አረ አይገባኝም በማለት ራሱን ዝቅ ያደርጋል። ከዚህ በተቃራኒ ራስን በራስ የማርካት የዝሙት ኃጢአት የኖረ ሰው ተክሊል ይገባሃል ቢባል እንኳን አረ እኔ አይገባኝም ብሎ በተሰበረ ልብ ሊርቅ ሲገባው በማስተርቤሽን ኃጢአት የዝሙትን ተግባር ሲፈጽም ከኖረ በኋላ ተክሊል ይገባኛል ብሎ መጠየቅ ልባችን በፈጸምነው ኃጢአት አለመሰበሩን ማረጋገጫ ነው።

አንዲት ሴት ራሷን የዝሙትን የኃጢአት እርካታ የመራቢያ አካሏን በመነካካት እያረካች ከኖረች በኋላ እንዴት ባለ ድፍረት ነው ተክሊል ይገባኛል ብላ የምትጠይቀው? ይቺ ሴት ከወንድ የምታገኘውን የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ከራሷ እያገኘች ከሆነ ከጋብቻ ውጭ ከወንድ ጋር ዝሙት ከሰሩት ሴቶች በምን ትለያለች? ምንም ከወንድ ጋር በምንጣፋ አንድ ባትሆን በሕሊናዋ ወንድ ከማሰብ አልፋ በፈቃዷ አፈ ማኅፀኗን እየነካካች የዝሙትን ተግባር ሰለፈጸመች ድንግል ተብላም አትጠራም።

በሉቃስ ወንጌል ላይ የሚገኝ አንድ ታሪክ አለ። ይህ ሕያው ታሪክ ከአባቱ ተለይቶ የኮበለለው ልጅ ሕይወትን ያስነብበናል። ይህ ልጅ ከአባቱ ለመለየት መወሰኑ ስህተት መሆኑ ገብቶታል። ሰለዚህም የሰራውን ስህተት ለማረም ሲነሳ ወደ አባቱ ለመመለስም ሲወስን እንዲህ ብሎ ነው ያሰበው " ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።" (የሉቃስ ወንጌል 15:18-19 )

ይሄ ልጅ በአባቱ ላይ ማመጹ ኃጢአት መስራቱ ፈጽሞ እንደጸጸተው የምንረዳው " ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም" በሚለው ንግግሩ ነው። ወደ አባቱ ቤት ሲመለስ ሰለመብቱ እያሰበ አልነበረም በልጅነት ክብር መጠራት እንደማይገባው አምኖል ወደ አባቱ ቤት የተመለሰው በአባቱ ቤት ከሚሰሩት ሙያተኞች መካከል እንደ አንዱ ሁኖ በባርነት ለማገልገል ነበር። ማስተርቤሽን ሲፈጽም የኖረም ሰው ኃጢአቱን አምኖ ወደ እግዚአብሔር ሲመለስ ድንግል ልባል የደናግልና ሥርዓትም ሊፈጸምልኝ አይገባም በሚል የተሰበረ መንፈስ ነው እንጂ በይገባኛል የሚል የትዕቢት ሐሳብ በልቡ ከያዘ መንፈሳዊ ኪሳራ ውስጥ መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ማሽተርቤሽን ቪዲዮ ሴክስ ፎን ሴክስ ከፈጸሙ በኋላ " በአካል ከተቃራኒ ጾታ ጋር ግንኙነት አላደረኩም ተክሊል መፈጸም ይፈቅድልኛል?" የሚል ጥያቄ በአእምሮቸው የሚፈጠረው ፍቅር እግዚአብሔር ሲጎድልብንና ራስ ወዳድ ስንሆን ነው። ምክንያቱም ማሽተርቤሽን ቪዲዮ ሴክስ ፏን ሴክስ የመሰለ ብዙ ኅብረ ዝሙት እየፈጸምን ያሳሰበን በደልነቱ ሳይሆን ተክሊል መፈጸም አለመፈጸም መሆኑ ነው። እንዲህ አይነት አስተሳሰብ " የቤተ ፈት" አስተሳሰብ ይባላል።

#ይቀጥላል
#ሼር
@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

22 Oct, 18:31


#ሕይወት_እነዚህን_10ሩን_ናት!

#1_ሕይወት_ምስጢር_ናት

በሕይወታችን ብዙ ያልተረዳናቸው ነገሮች አሉ፣ ቢሆንም የሕይወት ምስጢር በጣም አስደሳች የሚያደርገው አካል ነው።

#2_ሕይወት_ጉዞ_እንጂ_መድረሻ_አይደለችም

ሕይወት ወደ መጨረሻው መድረስ ሳይሆን በጉዞው ስለመደሰት ነው። ስለዚህ ፍጥነትህን ቀንስ፣ ጊዜህን ወስደህ እያንዳንዷን ቅጽበት አጣጥም።

#3_ሕይወት_በፈተና_የተሞላች_ናት

ፈተናዎች እኛን ለመጣል ሳይሆን ጠንካራ እንድንሆን የታሰቡና የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ ተግዳሮቶችን አትፍራ፣ ተጋፈጥ።

#4_ሕይወት_ስለ_ግንኙነቶች_ነው

በሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር የምንወዳቸው ሰዎች ናቸው። ስለዚህ ለምትወዳቸው ሰዎች ጊዜ ስጥ እና ምን ያህል እንደምታስብላቸው አሳውቃቸው።

#5_ሕይወት_ስለ_መስጠት_ነው

በሰጠነው መጠን ብዙ እንቀበላለን። ስለዚህ ጊዜህን፣ ገንዘብህን እና ፍቅርን ለግስ።

#6_ሕይወት_ለውጥ_ማምጣት_ነው

ሁላችንም በአለም ላይ ለውጥ ለማምጣት አቅም አለን። ስለዚህ የምትወደውን ነገር ፈልግ እና ለውጥን ፍጠር።

#7_ሕይወት_በአሁን_ውስጥ_ስለ_መኖር_ነው

ስላለፈው ነገር አታስብ፤ ስለወደፊቱም አትጨነቅ። አሁን ባለው ቅጽበት ላይ አተኩር እና በተሟላ ሁኔታ አጣጥመው።

#8_ሕይወት_አላማህን_ማግኘት_ነው

ለምንድነው እዚህ ያለኸው? ለምትኖርባት ዓለም ያበረከትከው ልዩ አስተዋጽዖ ምንድን ነው? አላማህን ፈልግ እና በተሟላ ሁኔታ ኑር።

#9_ሕይወት_በተስፋ_ስለመኖር_ነው

ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ብትሆን እንኳን፣ ሁልጊዜ ተስፋ አለ። ስለዚህ ምንም ቢሆን ተስፋ አትቁረጥ።

#_10_ሕይወት_ስለ_ፍቅር_ነው

በአጽናፈ ሰማይ ውስጥ ታላቁ ኃይል ፍቅር ነው። እንግዲያውስ ፍቅር በሕይወትህ ውስጥ ይምራህ።

ቤተ ሊባኖስ ₃

22 Oct, 18:30


#ሕይወትን_በዛሬ_ልክ_ኑር!

ኢትዮጵያዊው የበረሃ መልእክተኛ አባ ሙሴ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ ‘ለነገ አትጨነቁ፤ (ማቴ ፮፥፴፬) ተብሎ የተጻፈው ለማን ነው?’

ሽማግሌውም መለሱ፣ “ስቃዬ ምነው በዛ መቼስ ነው የሚያበቃልኝ፣ ብሎ ለሚጨነቅ ሰው ነው የተጻፈው። ከዚህ ይልቅ ለራሱ “ዛሬ” ማለት አለበት”

ብዙውን ጊዜ አዲስ አመት በመጣ ቁጥር፣ ከቀደመው ጠባያችን ሳንላቀቅ፣ የኃጢአት ኮተቶቻችንን እንደያዝን፣ “ይሄኛው አመት የተለየ ይሆናል፣ የተሻለም እሆናለሁ!” እንላለን፣ ሆኖም አባ ጴሜን እንዳሉን...

ህይወትን በዛሬ ልክ መኖር አለብን። ከውድቀት ራሳችንን ማስቀረት ባንችል እንኳ፣ ብንወድቅም የሚያነሳን አባት አለንና አስቀድመን መጨነቅ አያስፈልገንም፤

ጭንቀታችን ሁሉ ለአምላካችን ሰጥተን ዛሬ ላይ ብቻ የምንችለውን ማድረግ ይኖርብናል፤ ነጋችንን እሱ ብቻ ያውቃልና።

ማለዳችንን እግዚአብሔርን በማመስገን ከጀመርን፣ ስቃያችን በአዲስ ህይወት የሚቀየርበት ቀን ይሆንልናል።

@Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

22 Oct, 18:26


አዜብ ወደ ሰሎሞን ስትሔድ ስንት ደናግላን አስከተለች???

ቤተ ሊባኖስ ₃

20 Oct, 20:38


🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

         ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █          
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ቤተ ሊባኖስ ₃

20 Oct, 20:27


👳‍♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
            እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
    ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ

ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
    ⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️

ቤተ ሊባኖስ ₃

20 Oct, 18:05


#ወደ_ተሳሳተ_ምንጭ_አትሂድ

በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር ገበሬ አንዲት ላም ነበረችው። ላሟን እጂግ ከመውደዱ የተነሳ አብዝቶ ይንከባከባታል። ጥሩ ሳር ባለበት ቦታ እየወሰደ ይመግባታል። በአካባቢው ወዳለ ንጹህ ምንጭ እየወሰደም ውኃ ያጠጣታል።

ነገር ግን ላሟ ሁልጊዜ ትከሳለች። ከቀን ወደ ቀን የበለጠ ቀጭን ትሆናለች።

ሰውዬውም እጅግ እየተገረመና ግራ እየገባው

"ላሜ እንዲህ እየተንከባከብኳት ለምንድን ነው የምትከሳው?" ይል ነበር።

መልሱን ለማግኘትም ብዙ ጊዜ አልወሰደበትም። አንድ ቀን፥ ድንገት ውኃ ጠምቶት ከምንጩ ለመጠጣት ዝቅ ሲል አንድ ነገር አስተዋለ። ውኃው ውስጥ የሆኑ አስፈሪ ነፍሳት ነበሩ። አዎ ምንጩ በአለቅት ተወሩ ነበር።

ስለዚህም ላሟ በየቀኑ ከምንጩ በጠጣች ቁጥር ከውኃው ጋር አለቅቶች ወደ ሆዷ ይገቡ ነበር። ገብተውም ደሟን እየመጠጡ ያዳክሟታል።

የዚህ ዘመን ሰው መንፈሳዊ ሕይወትም እንደዚህ ዓይነት ነገር ነው ያጋጠመው። ጥሙን ለማርካት ውኃ የሚጠጣው ወደ ተሳሳተ ምንጭ በመሄድ ነው።

ወዳጄ አንተም ጥምህን ለማርካት ወደ ተሳሳተ ምንጭ አትሂድ!

@Abalibanos333

ምክር ነክ ፁፍ

ቤተ ሊባኖስ ₃

19 Oct, 21:25


የንስሐ አባታችን በክፉ ምግባር ቢገኝ ኃጢአት እየሰራ ለርሱ መናዘዝ ተገቢ ነው ወይ?


በመጀመርያ መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአትን ለካህናት መናዘዝ እንዲገባ በግልጽ ያስተምራል። ጌታችንም በወንጌል ይህን ስልጣን ለሐዋርያት ሲሰጥ እንዲህ ብሏል። "እውነት እውነት እላችኋለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል። በምድር የምትፈቱት በሰማይ የተፈታ ይሆናል።" ማቴ.18:18

በዮሐንስ ወንጌል 20:22-23 ላይም "ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል። የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው።" በማለት ተገልጾአል። ስለዚህ ይህን ስልጣን መድኃኔዓለም ሰጥቷቸዋል። ለዚህም ነው በሐዋርያት ስራ 19:18 ላይ "አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር። " በማለት ኑዛዜ ንስሐ እንደሚያስፈልግ የተናገረው።

በማቴ. 3:6 ላይም "ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።" በማለት ለመጥምቁ ዮሐንስ ይናዘዙ እንደነበር ይናገራል። ስለዚህ ይህን ስልጣን ለካህናት የሰጣቸው እግዚአብሔር መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል።

የምናዘዝለት ካህን ኃጢአተኛ ቢሆንስ ለሚለው ጥያቄ በንስሐ ጊዜ ኃጢአትን ለካህን ብንናዘዝም በካህኑ በኩል ይቅርታን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። ለዚህም ነው ካህኑ "እግዚአብሔር ይፍታህ" የሚለው። ከኃጢአት እስር የሚፈታ እግዚአብሔር ነውና።

የምንናዘዝለት ካህን ኃጢአተኛ ወይም ምግባረ ብልሹ ቢሆን ንስሐ በሚገባው ሰው ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። በራሱ በካህኑ ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ ከማምጣቱ በቀር። ይህን በምሳሌ ስንረዳው፦

👉 አንድ የምስራች የሰፈረበትን ደብዳቤ ይዞ የመጣ መልእክተኛ መልከ ጥፉ ይሁን መልከ መልካም ጸባየ መልካም ይሁን መጥፎ ይዞት በሚመጣው መልዕክት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። የምንናዘዝለት ካህኑም ምግባሩ ብልሹ ቢሆን ኃጢአተኛ ቢሆን የኃጢአት ስርየት ምናገኘው በካህኑ ኃጢአት አይወሰንም።

👉 ሌላ ምሳሌ እንጨምር አንድ ገበሬ ጠባዩ ጥሩ ይሁን መጥፎ በሚዘራው እህል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። ጥሩ ዘርን በጥሩ መሬት ላይ ከዘራ ጥሩ ምርት ይገኛል። ኃጢአተኛ ገበሬ ዘራው ጻድቅ ገበሬ በምርቱ ላይ ለውጥ አያመጣም። በእርግጥ በእግዚአብሔር የተሾመ ነውና ካህን ለሌላው ምዕመን አርአያ ሊሆን ይገባዋል እንጂ ምግባረ ቢስ ሊሆን አይገባውም። ኃጢአተኛ ቢሆን ግን ፍርዱን ራሱ ይቀበላል እንጂ ለካህኑ በመናዘዛችን ላይ ችግር አያመጣም። ቀድሞም ስርየተ ኃጢአት የሚሰጥ እግዚአብሔር ነውና።

👉 አንድ የከተማ አስተዳዳሪ እንደ ሁሉም ነዋሪዎቹ በምግባሩ መልካም ላይሆን ይችላል። ነገር ግን አስተዳዳሪው ነዋሪዎቹ የሌላቸውን ስልጣን ይዟል። ካህኑም እግዚአብሔር የሾመው ስለ ተሰጠው ክህነት ከምዕመናኑ ይበልጣል የእግዚአብሔር መሳርያም ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
በወንድም ተክለማርያም
https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

19 Oct, 21:24


#ኦርቶዶክሳዊ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_አነባበብ

🔸ኦርቶዶክሳዊው የመጽሐፍ ቅዱስ አነባበብ አራት መገለጫዎች አሉት፡፡

➊ #መጽሐፍ_ቅዱስን_በመታዘዝ_መንፈስ_ማንበብ

መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ጥበቃ የተጻፈ በመሆኑ አንድነት ያለው መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ቅዱሳን ሰዎች የተጻፈ ቢሆንም መሪያቸው መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ አንድ ዓይነት መልዕክት ያለው በመሆኑ በብዙ ቁጥር "The biblia" ተብሎ ሳይሆን በነጠላ ቁጥር "The bible" እያልን እንጠራዋለን፡፡

#በመታዘዝ_በመገዛት_ማንበብም_ሲባል፦

♦️መጽሐፍ ቅዱስን በመደነቅ መንፈስ ሆኖ ማንበብ

ይሀውም መጽሐፍ ቅዱስን ደግመን ደጋግመን ብናነበው እንኳ ሁሌም አዲስ የሆነ መጽሐፍ ሁሌም አዲስ ምስጢር ያለው መሆኑን ማወቅ መረዳት ነው፡፡ ያነበብነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልም ቢኖር አንድ ጊዜ አንብቤዋለሁ ብሎ ደግሞ ደጋግሞ ከማንበብ መሰልቸት የለብንም፡፡ ይልቁኑ ባነበብኩት ምን ያህል ተለውጫለሁ በማለት ራሳችንን መጠየቅ ፡፡

♦️በመጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረንን ቃለ ይገባናልእግዚአብሔር በመስማት

ብዙዎቻችን ለመስማት የዘገየን ለመናገር ደግሞ የፈጠንን ነን፡፡ መስማትን ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሕይወት እንማራለን፡፡ "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች፡፡" ሉቃ. 1:38፤ "ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡" ሉቃ. 2:19፤ ሉቃ. 2:51 እንዲል:: እኛም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሕሊናን ገንዘብ ለማድረግ ከመናገር ይልቅ መስማትን ልናስቀድም ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ሲናገረን በመታዘዝ መንፈስ ሆነን መስማት የኦርቶዶክሳዊ አነባብ መለያው ነው፡፡

➋ #መጽሐፍ_ቅዱስን_በቤተክርስቲያን_በኩል_መረዳት

መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ማስረገጫችን በቤተ ክርስቲያን ስለተላለፈልን ነው፡፡ መናፍቃን መጽሐፍ ቅዱስን ለመበረዝ በሚሰሩበት ጊዜ ቆጥራ ሰፍራ እኚህ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው መጻህፍት ናቸው በማለት በቀኖና ያስረከበችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ መጻህፍቱን ቆጥራ ሰፍራ ያስረከበችን ቤተ ክርስቲያን ከሆነች የመተርጎሙም ስልጣን ያላት አንዲቷ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቅዱስ ሄሬኔዎስ መጽሐፍ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን ብቻ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ውጪም ያሉት መብት የላቸውም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉ ሁሉ በራሳቸው ግልጥ ያሉ አይደሉም፡፡ በምናነብበት ጊዜም ለሚከብዱን ቃላቶች ትርጓሜውን ለመረዳት የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ጎልቶ እንድንረዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን መቅረብ አለብን፡፡ ቅዱሳን አባቶችን አነሳስቶ ያጻፈ መንፈስ ቅዱስ ያለባት ናትና ታሪክ ባህልን አገናዝባ የመተርጎም ስልጣን ያላት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡

➌ #የመጽሐፍ_ቅዱስ_ማዕከሉ_ክርስቶስ_መሆኑን_በማወቅ_ማንበብ

መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ጊዜ እያንዳንደዱን የመጽሐፍ ክፍል ነጥሎ በማየት ሳይሆን በአንድነት የመረዳት መንፈስ ሊኖረን ይገባል፡፡ የብሉይ ኪዳኑን ጥቅስ በሐዲስ ኪዳን የሐዲሱንም በብሉይ ኪዳን ውስጥ አድርጎ መተርጎም ያስፈልጋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ሙሴ በምድረ በዳ የሰቀለው የነሀሱ እባብ ዮሐ. 3:14 የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ቀርቧል፡፡ እስራኤል ዘስጋ የጠጡበት አለት በክርስቶስ ተመስሏል፡፡ 1ኛ ቆሮ. 10:4 መልከጼዲቅም የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ቀርቧል፡፡ ዘፍ. 14:18 እኛም አነባበባችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ሊሆን ይገባል፡፡

➍ #በመጽሐፍ_ቅዱስ_ውስጥ_ራሳችንን_በማየት_መንፈስ_ማንበብ

አንዱ መነኮስ "በሐሳቡ ትሁት የሆነና በመንፈሳዊ ስራዎች የተጠመደ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ባነበበ ጊዜ እያንዳንዱን ቃለ እግዚአብሔር ለራሱ ሕይወት ሰጥቶ ይረዳዋል (ለራሱ እንደተነገረ ያስባል) እንጂ ለባልንጀራው ሰጥቶ አይተረጉመውም" ብሏል፡፡ የደጉ ሳምራዊን ታሪክ ስናነብብ "በወንበዴዎች መካከል የወደቅኩት እኔ ነኝ" በሚል መንፈስ መሆን አለበት፡፡ የጠፋው ልጅ ታሪክንም ስናስብ "ታናሽ ልጅህ የምሆን እኔ የሰጠሀኝን ሐብት ገንዘብ አባከንሁ... አሁን ግን ተርቤያለሁ" በሚል የንስሐ መንፈስ ሆኖ ማንበብ ነው፡፡

ዋቢ፦ How to read Bible ,Fr kallistos ware
https://t.me/Abalibanose333
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ቤተ ሊባኖስ ₃

17 Oct, 04:30


ጥያቄ:- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ነው ስንል እንዴት ነው? ማለት በምን ላይ ነው የሚፈርደው በዳግም ምፅዐት ሲመጣ ስለሚፈርደው ፍርድ ነው እያልን ያለነው ወይስ ከዚያ በፊት ፍርድ አለ?

       መልስ
   
👉 ከዚህ በመነሳት የክርስቶስ ፈራጅነት ሲገለጽ በዳግም ምጽዓቱ ስላለው ፍርድ ብቻ አይደለም።  በዳግም ምጽዓት ያለው ፍርድ ለዘላለም ሕይወትና ለዘላለም ሞት የእግዚአብሔር ፍርድ ሲሆን በዓለም ላይ ስለሚፈጸመውም ኢፍትሐዊነት ግፍ የኃጢአተኞች ተግባር እግዚአብሔር በግፈኞች በኃጢአተኞች ላይ አሁንም ይፈርዳል። ለተገፉት የሚፈርድላቸው እርሱ ነው።

👉 አባታችን አብርሃም ሰዶምና ገሞራ እንዳይጠፉ ሲማልድ "ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?" ዘፍ. 18:25 ብሎአል። እግዚአብሔር በምድር ላይ ላሉት በቅን የሚፈርድ እንደሆነ ገልጿል።

👉 እግዚአብሔር አምላክ እሥራኤል ዘሥጋን ከግብጽ የባርነት አገዛዝ የማውጣቱን ነገር የእግዚአብሔር ፍርድ ተብሎ ተገልጿል። "ፈርዖንም አይሰማችሁም፥ እጄንም በግብፅ ላይ አደርጋለሁ፥ ሠራዊቴንም የእስራኤልን ልጆች ሕዝቤን በታላቅ ፍርድ ከግብፅ አገር አወጣለሁ።" ዘፍ.7:4። አሁንም ቢሆን ግፍን የሚያደርጉትን የሚመለከት በቅን የሚፈርድ አምላክ አለ።

👉 ዳግመኛም እግዚአብሔር "በቀልና ፍርድ የእኔ ነው። " ዘዳ.32:35 ብሎአል።

ዳግመኛም "ኃይላቸውም እንደ ደከመ፥  የተዘጋ የተለቀቀም እንደሌለ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ስለ ባሪያዎቹም ያዝናል።" ዘጸ.32:36 ይላል። እግዚአብሔር በእውነት ይፈርዳል የፈጠረውን ፍጥረት አንዴ ፈጥሮ የተወው አይደለምና። በትንቢተ አሞጽም እንደተጠቀሰው ከእግዚአብሔር መንገድ ለወጡ እስራኤላውያን እግዚአብሔር አሕዛብን አስነስቶ እንደሚያስጨንቃቸው ይናገራል። ይህ በኃጢአተኞች ላይ የሚያደርገው የእግዚአብሔር ፍርድ ነው።  "ፍርድን ወደ ሐሞት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ እሬት የለወጣችሁ፥ በከንቱም ነገር ደስ የሚላችሁ... የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ ሕዝብን አስነሣባችኋለሁ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር፤ እነርሱም ከሐማት መግቢያ ጀምረው እስከ ዓረባ ወንዝ ድረስ ያስጨንቋችኋል።"  አሞ.6:12-14


ይህ የእግዚአብሔር ፍርድ በሐዲስ ኪዳን የቀረ አይደለም።  ጌታችን በወንጌል "ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።" ዮሐ.3:17 ብሎአል። ጌታችን እኛን ለማዳን በሥጋ ማርያም ሲገለጥ አስቀድሞ በምክረ ከይሲ ሕግን ተላልፎ እጸ በለስን የበላውን ሞት የተፈረደበትን አዳምን ሊያድነው ነው የመጣው ሊፈርድበት ከድንግል ተወልዶ ሰው የሆነው አዳም አስቀድሞ ተፈርዶበት ነበርና።

ክርስቶስ በዚህ ምድር ከመጣ የመዳንን መንገድ ካስተማረን በኋላም በርሱ ያላመኑ ሰዎችም በዳግም ምጽአት ፍርድ  ሰዎችም የሚጠብቁ አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ ያላመነው አሁን ተፈርዶበታል ይላል። "በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።" ዮሐ.3:18:: ያላመነ ሰው ሁሉ አሁንም በፍርድ ነው ማለት ነው። ለዚህም ነው ቅዱስ ዳዊት " ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።" መዝ.1:5 ያለው። ክፉዎች ያላመኑ ኃጥአን ፍርድ ፊት አይቆሙም አሁንም በኩነኔ በፍርድ ናቸውና።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም ምጽዓት ሊፈርድ ይመጣል። በዚህ ዓለም ያለ ፍርድ ቀርቷል ማለት ግን አይደለም።

👉 በሐዋርያት ሥራ ገንዘባቸውን አስቀርተው መንፈስ ቅዱስን ለማታለል የሞከሩት ሐናንያና ሲጳራ ተቀስፈው ሞተዋል። ይህ የእግዚአብሔር ፍርድ ነው። "ጴጥሮስም። የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለ ምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው አንቺንም ያወጡሻል አላት።" ሐዋ.5:5፤ ሐዋ.5:9

👉 ንጉስ ሄሮድስ በአምላክ ቦታ መከበርን ስለሻተ በእግዚአብሔር ፍርድ ተቀስፎ በትል ተበልቶ ሞቷል።  "ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ።" ሐዋ.12፥23። ዛሬም እግዚአብሔርን የሚገዳደሩ ኃያላን ፍርድ አለባቸው።

👉 አሁንም የሚበቀል እግዚአብሔር ነው። ለተገፉት የሚፈርድላቸው እርሱ ነው።  በግፈኞች ምክንያት በድሆች ላይ የሚደርሰውን ግፍ እንደ ናቡቴ የሚፈሰውን ደም እግዚአብሔር ያያል ርሱም ይበቀላል። እግዚአብሔር አሁንም ይፈርዳል።  ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ይላል:- "ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።" ሮሜ.12:19 እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ እግዚአብሔር አሁንም ይፈርዳል።

👉  ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ ይላል
"ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?" 1ኛ ጴጥ.4:17።

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

17 Oct, 04:30


ጥያቄ:- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ነው ስንል እንዴት ነው? ማለት በምን ላይ ነው የሚፈርደው በዳግም ምፅዐት ሲመጣ ስለሚፈርደው ፍርድ ነው እያልን ያለነው ወይስ ከዚያ በፊት ፍርድ አለ?

መልስ:- ይህን ጥያቄ በአብዛኛው የሚያነሱት ክብር ምስጋና ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ እኛ ይማልዳል ይለምናል" የሚሉ ተቃዋሚዎች ናቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ስለመሆኑ በዳግም ምጽዓት ለፍርድ የሚመጣ መሆኑን ሲነገራቸው አሁን ታዲያ እየፈረደ ነው ወይ? የሚል ጥያቄን ያስከትላሉ። ቅዱስ ጳውሎስ ጌታችን ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ቤዛነት ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን በግርማው በቀኝ ተቀመጠ በማለት ይናገራል። እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤" ዕብ. 1:3። 'ቀኝ' የተባለው ለእግዚአብሔር ግራ ቀኝ ኖሮት ሳይሆን ስልጣኑን ሲገልጽ ነው። በግርማው ቀኝ መቀመጡም በክብር ለፍርድ መቀመጡን የሚያስረዳ ነው።

👉 ዳግመኛም ቅዱስ ጳውሎስ "ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን"  ዕብ.2:9 በማለት እኛን ለማዳን የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ መከራ መቀበሉ መሞቱ በባሕርያቸው ሞት ከማይስማማቸው መላዕክት እንኳ አነሰ ተብሎ ተነግሮ ነበር። ዳግመኛም "በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።" ፊልጵ.2:8 "ራሱን አዋረደ" እስኪባል ድረስ ተጻፈልን። ጌታችን በመስቀል ሞት እኛን ካዳነን በኋላ ዳግመኛ በምድር እንደሆነው አድርገን እንዳናስብ ቅዱስ ጳውሎስ "ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።" 2ኛ ቆሮ.5:16 አለ።

በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ እንደተቀመጠው  ፍርድ ማለት እውነትን ከሐሰት መለየት ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ፍርድን በአምስት መንገድ ይገልጠዋል።

1ኛ. ነገሩን ማስተዋል:- ምሳ.1:3፤ ምሳ.2:8 ሰውም በግብዝነት ማለትም ራሱ እየፈጸማቸው ባሉት ነገሮች ላይ በሌላው እንዳይፈርድም ተከልክሏል። ማቴ.7:1-6::

2ኛ. የሕዝብ አስተዳዳሪዎች ያለ አድልዎ እንዲፈርዱ ታዝዘዋል።ዘዳ.17:1

3ኛ. በዓለም ላይ የሚፈጸም የእግዚአብሔር ሥራም ፍርድ ተብሎአል። እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በግፈኞችና በኃጢአተኞች ላይ ይፈርዳል። አሞጽ.6፥12:14። መሳ.1:7:: እግዚአብሔር እሥራኤላውያንን ሲታዘዙለት ባረካቸው ከፈቃዱ ሲወጡ ግን ቀጣቸው። ሲቀጣቸው ግን እንዲቀደሱ እንጂ እንዲጠፉ አይደለም። ኤር.25:29፤ 1ኛ ጴጥ.4፥17::

4ኛ. በዳግም ምጽዓቱ በዓለም ፍጻሜ የሚሰጠው ፍርድ ነው። ኢሳ.2:12፤ ማቴ.12:36፤  ማቴ.25:31-46፤ 1ኛ ቆሮ.3:12-15፤ 2ኛ ቆሮ.5:10።

5ኛ. ኩነኔ ተብሎ የተገለጠው ሲሆን በክርስቶስ አምነው የነፍስን ፈቃድ የሚያደርጉ ፍርድ የለባቸውም ተብሏል። ሮሜ.8:1:: ያላመኑትን ደግሞ በዚሁ ዓለም በፍርድ ናቸው ተብለዋል።

ይቀጥላል...👆👇👆👇👆

ቤተ ሊባኖስ ₃

16 Oct, 19:06


የሳሙኤል አባት ስም ማን ይባላል?

ቤተ ሊባኖስ ₃

16 Oct, 19:04


ማህተባችችን ለምን አንገታችን ላይ እናስራለን

ቤተ ሊባኖስ ₃

16 Oct, 07:12


ማጠቃለያ

👉 "ምጽዋት በመስጠታችን እጽፍ ድርብ ዋጋ እንድናገኝ ሰው ሁሉ ማመን ይገባዋል። የተቻለውን ምጽዋት የማይሰጥ ሰው እንደ ከሐዲ እንደ ሌባ እንደ ወንበዴ ነው።" ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ.16

ስንቶቻችሁ ስለ ምጽዋት በተከታታይ የተላለፈውን ትምህርት ተከታተላችሁ?

ቤተ ሊባኖስ ₃

16 Oct, 07:12


በእንተ ምጽዋት [በአበው ትምህርት]

ምጽዋትን እንዲህ ላለውስ መስጠት ይገባል
            
           የመጨረሻ ክፍል

               ክፍል- 10

👉 በርግጥ የምንሰጠው ሰው ችግረኛ ይሁን አይሁን ላናውቅ እንችላለን። እርሱን መመርመር የእኛ ድርሻ አይደለም። ከእኛ የሚጠበቀውን ከሰጠን መድኃኔዓለም ዋጋውን አያሳጣንም። ይሁን እንጂ በግልጥ ቤተ ክርስቲያን ማታበረታታው ምጽዋት መስጠት አለ።

1⃣ኛ. ለኃጢአት ተግባር የሚሰጠውን- ለጫት ለሲጋራ ለመጠጥ ብሎ የሚጠይቀንን ሰው ግን መስጠት አግባብ አይደለም። ምጽዋት ምሕረት ማድረግ እንደመሆኑ ሥጋውና ነፍሱን የሚጎዳውን ነገር ለሚያደርግ ሰው አጋዥ መሆን ምሕረት ማድረግ ሳይሆን የጥፋቱ ተባባሪ ያደርገናል ስለዚህ ለእንዲህ ዓይነቱ ምጽዋት ልናደርግ አይገባም። እንዲህ ያለ ሰው ሳይፈልግ ከተያዘበት ሱስ የተነሳ የሚጠቅመውን ባለማወቅ አደንዛዥ እጾችን  ቢጠይቀን የሚጠቅመውን መርጠን ግን መመጽወት እንችላለን። የጫት ሲጋራ በሚጠይቁን ፈንታ የእለት ጉርሳቸውን መሙላት እንችላለን ከዚህ በላይ ካሉበት ክፉ ግብር እንዲወጡ ምክራችንን ልንመጸውታቸው እንችላለን።

2⃣ኛ . ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን። ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና።" 2ኛ ተሰ.3:10 በማለት እንዳዘዘን መስራት ሲችሉ አቅም ኖሯቸው በስንፍና ምክንያት ሳይሰሩ ከሌላ የሚጠብቁትን ሰዎች ምጽዋትን መስጠት የነርሱን ስንፍና ማበረታታት በኛ ላይ ጥገኛ ሆነው ሁሌም የተረጂነት ስሜት እንዲኖራቸው ማድረግ ነውና ልናበረታታው አያስፈልግም። "ሊሠራ የማይወድ  አይብላ" የተባለው ግን ሊሠሩ የማይችሉ ከሆኑት ጋር ልንለይ ይገባናል። ሕጻናት፤ አቅማቸው የደከመ አረጋውያን፤ የአዕምሮ ሕሙማን በደዌ (በሕመም) የተያዙ ሁሉ መሥራት ስለማይወዱ ሳይሆን እንደሌሎች ወጥተው ወርደው ለመሥራት አቅም የሌላቸው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

👉 ዮሐንስ ክሮንስታድ [Jhon Kronstadt] የተባለ የምስራቅ ሊቅ My Life in Christ በተባለ መጽሐፉ እንዲህ አለ:- "ብዙ ድሆች ለህልውናቸው አስፈላጊ ልብስና መጠለያ አጥተው ባለጠጎችም ከሚገባቸው በላይ ሀብትን ማከማቸታቸው ፍትሐዊ አይደለም። ይሁን እንጂ የሚሰራ (የሚደክም) አብዝቶ ሊያገኝ ይገባዋል ሰነፍ የሆነውም በድህነት በጉስቁልና ሊኖር ይገባዋል። ስለዚህም አንዳንዶች በራሳቸው ከስራ ፈትነትና ከሥንፍናቸው የተነሳ ድሃ እንደሆኑ ብናውቅ በሥራችን (በድካማችን) ያገኘነውን ልናካፍላቸው አንገደድም።  ጳውሎስ እንዳለው "ሊሰራ የማይወድ አይብላ"  2ኛ ተሰ.3:10 ይላልና። በእርጅና ላሉ ፣ በሕመም ላሉ ፣ ለፍተው ዝቅተኛ ደመወዝን ለሚቀበሉ፣ በሕይወታቸው ከባድ ችግር ለገጠማቸው፣ ብዙ ቤተሰብ ኖሯቸው ለተቸገሩ፣ የሚያመርቱት ላነሰባቸው ሁሉ በተለይም ባለጠጋ የሆንን ፈጥነን ልንረዳቸው ይገባናል። በሐዋርያት ጊዜ በነበሩ ታሪኮች በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌነት ልንመራ ይገባናል።" ይላል።" 

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

12 Oct, 04:30


በእንተ ምጽዋት [በአበው ትምህርት]

ምጽዋትን የመስጠት ቅደም ተከተል
             
           ክፍል- 9

1ኛ. በሃይማኖት ምክንያት ለታሠሩ ሰማዕታት
2ኛ.ለካህናት
3ኛ.ለተቸገሩ ዘመዶች
4ኛ.ለተቸገሩ ምዕመናን ሁሉ
5ኛ.ላላመኑ ችግረኞች


👉 ሃይማኖታችንን አንክድም ለጣዖት አንሰግድም ብለው መታሠር መደብደብ ለደረሰባቸው፣ የቤት ቃጠሎ፣ የሀብት ዝርፊያ እንዲሁም ውድመት ለደረሰባቸው ሰማዕታተ ጽድቅ ቅድሚያ ከሰጠን በኋላ

👉  በማስቀጠልም በችግር ውስጥ ሆነው ሰውና እግዚአብሔርን በማገናኘት፣ በማኅሌት፣ በሰዓታት፣ በቅዳሴ፣ በማጥመቅ፣ በማቁረብ፣ የበደለኞችን በደል በደስታ ተቀብለው ለሕመማቸው መድኃኒቱ ንስሐን በማቅረብ ያሉ ካህናትን በችግር ምክንያት ቤተሰብ እንዳይጎዳባቸው አገልግሎት እንዳይጓደልባቸው መጎብኘት እንዲገባ ያስረዳል። ግን ከተቸገሩ እንጂ ካህናት ስለሆኑ ብቻ ምጽዋት ሊሰጣቸው ይገባል ማለት አይደለም።

👉 ከዚህም በመቀጠል የተቸገሩ ምዕመናንን መጎብኘትን በቤተሰቦቻችን መጀመር ይገባናል። ይህም አድልዎ አይደለም መቸገራቸውን የሚያውቃቸው ውሎ አዳራቸውን የሚያውቅ የቅርብ ሰዋቸው ስለሆነ እንጂ ። ሲቀጥል ለሰጩ ዘመድ ከመሆናቸው ይልቅ የሚበልጠው የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸው ነውና የእግዚአብሔር ልጅ በመሆን ሁሉም አንድ ስለሆኑ፤ ደግሞም በእነዚህ የሚያቆም አይደለም ፀሐይ ስታበራ ከመስኮቷ እንደምትጀምር መስጠትን ከቤቱ ይጀምር አለ እንጂ፤ በእነዚህ ያቁም አላለምና። ምክንያቱም ከእነዚያ ቀጥሎ ለተቸገሩ ምዕመናን ሁሉ በማለት ሲያጠቃልለው እንመለከታለንና።
[ፍትሐ ነገሥት ምን ይላል?: የኔታ በጽሐ አለሙ]

ነገ የመጨረሻውን ክፍል
  ምጽዋትን እንዲህ ላለውስ መስጠት ይገባል? በሚል ርዕስ ትምህርቱን እንፈጽማለን!

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

12 Oct, 04:30


በእንተ ምጽዋት [በአበው ትምህርት]

ይልቁኑ ምጽዋትን ለእነማን እንስጥ?
          
              ክፍል- 8

👉 ምንም እንኳ ምጽዋትን ለሁሉም የምናደርገው ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ግን ልናስቀድም የሚገባውን ይነግረናል።
ቅዱስ ጳውሎስ "እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ።" ገላ. 6:10። 

ዳግመኛም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ አለ  "ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።" 1ኛ ጢሞ.5:8 እንዲል በሃይማኖት የሚመስሉንን መዘንጋት ከማያምነው ሰው የከፋ ነው ይለናል። በአንድ አካል ያሉ ብልቶች ያላቸውን ሊተሳሰቡ ይገባል። አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳልና::

👉 በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 16 ላይም እንዲህ የሚል አለ:- "ምጽዋት ምንም ለሚሻት ሁሉ የምትገባ ብትሆንም ከሰው ለይቶ ለሰው ሊሰጧት ትገባለች።" ይላል።

👉ርቱዓ ሃይማኖትም እንዲህ አለ:- "ለአንተስ ለሁሉም መልካም ነገርን አድርግ። ይልቁንም ለሃይማኖት ሰዎች። የሃይማኖት ሰዎችም በዋሻው፣ በተራራው በፍርኩታው፣ በምድር ጉድጓድ ያሉ ናቸው። ለእነዚህ ራሳቸውን ላስቸገሩ ገዳማውያን ስጦታን አብዛላቸው፤ በሚመጣው ዓለም በርግጥ ይነግሣሉና። ጻድቃኑም ከርስታቸው ይከፍሉሃልና። ስለ ኃጥአን ግን ጌታ ይከፍልሃል፤ አበድረኸዋልና። ብድርህም ከገንዘብህ መቶ እጥፍ ነው። [ርቱዓ ሃይማኖት ገጽ.105]

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

09 Oct, 14:48


  #ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ
#ዝቋላ #ገብረ መንፈስ #ቅዱስ #ገዳም

መነሻ ቀን -: ጥቅምት 04/02/2017ሰኞ
መመለሻ ቀን -:ጥቅምት 05/02/2017 ማክሰኞ


 መነሻ ሰዓት ና ቦታ ፦ ሰኞ ጥቅምት 04/02/2017 ከጠዋቱ 12:00 መነሻ ቦታችን አያት ጣፎ መካነ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ና አያት አደባባይ ጎሮ አደባባይ

መመለሻ ሰዓት ፦ 05/02/017ዓ.ም  ከንግስ በኃላ
 
የጉዞ ዋጋ 550

  ለበለጠ መረጃ ና ለመመዝገብ ከታች ያለዉን ስልክ 👇👇👇👇

+251953125078 ዳኜ

+251941137351 ፀጋ

+251952559464 በሱፍቃድ

     ትኬቶችን በአያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መግቢያ በሮች ና የደብሩ ሰንበት /ት/ት ሱቁ ላይ በሁለቱም መግቢያ በሮች ሱቁ ላይ ታገኛላችሁ                        
#ቦታ #ያስይዙ፣#ይመዝገቡ።
  
አዘጋጅ አያት ጣፎ መካነ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተክሌ ቴዎፍሎስ ሰንበት /ት/ት

በቴሌግራም @DA121922

ቤተ ሊባኖስ ₃

09 Oct, 14:44


በእንተ ምጽዋት [በአበው ትምህርት]

      ለነማን እንስጥ

          ክፍል- 7

"ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ" ሉቃ.6:30 እንዲል ለሁሉም እንድንሰጥ ጌታችን አዞናል።

"እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።" ማቴ.5:44-45 እንዲል የእግዚአብሔር ልጅነታችን የሚታወቀው ያለ አድልዎ ስንመጸውት ነው።

👉 በእረኛው ሔርማ [Shepherd of Hermas] ላይ እንዲህ የሚል አለ:- "እግዚአብሔር ከሰጠህ ከእጆችህ ፍሬ መልካም ሥራን አድርግ በየዋሕነት ያለ መጠራጠር ለተቸገሩት ሁሉ ቀድሞ ትሰጣቸው ለነበሩትና ላልነበሩትም ሁሉ ስጥ። እግዚአብሔር ስጦታው ለሁሉ እንዲደርስ እንደሚወደው አንተም እንዲሁ አድርግ። የሚቀበሉትም ለምንና በምን ምክንያት እንደተቀበሉት በእግዚአብሔር ፊት መልስ ይሰጡበታል። ተቸግረው የወሰዱ ፍርድ የለባቸውም። በሐሰት ምክንያት የተቀበሉት ግን ፍርድ አለባቸው።ስለዚህም ምክንያት ሰጪው ወቀሳ የለበትም። ምክንያቱም እርሱ ከእግዚአብሔር እንደተቀበለ ግዴታውን በየዋሕነት ያለ ጥርጥር ለተገባውና ላልተገባው ሁሉ ሰጥቷልና። [እረኛው ሔርማ]

👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንዲህ አለ:- "ምጽዋትን ለባልንጀሮቻችን ወይም በእምነት ለሚመስሉን ብቻ ልናደርግ አይገባም ለማያምኑም ጭምር እንጂ። በሕገ ኦሪት የወደቀ አህያን ብታገኝ የማን እንደሆነ ሳትጠይቅ ከወደቀበት ታነሳዋለህ። ይህ ለእንስሳት ማድረግ ያለብህ ኃላፊነት ከሆነ እንደምን አብልጠን ያለ ልዩነት ሰዎችን ለሰዎች ልናስብ ይገባን ይሆን?"

👉 በመጽሐፈ ገነት [Book of Paradise] ላይም እንዲህ የሚል አለ "አንድ አባት ልብሱን ለአንድ ድሃ ይሰጠዋል። ቅርጫትን ይዞ ለመሸጥ ምግብንም ለመግዛት ወደ ገበያ በወረደ ጊዜ አንዲት ዘማዊት የርሱን ልብስ ለብሳው ያያታል። እጅግ ተናደደ አለቀሰም:: እግዚአብሔር ሊያስተምረው ከሃሳቡም ሊያሳርፈው መልአክን ላከለት። የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጦ "አትዘን ለድሃው ልብስህን በሰጠህበት ቅጽበት ልብሱን ክርስቶስ ለብሶታል። ከዚህ በኋላ ስለሆነው ያንተ ኃላፊነት አይደለም።" አለው።


ምጽዋትን በሰጠንበት ቅጽበት ዋጋችንን እግዚአብሔር እንደሚሰጠን በማሰብ ምጽዋትን የሚቀበለውን ሰው ልንመራመር አይገባንም። በሰው ልቡና ያለውን የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነውና።

https://t.me/Abalibanos333

ይቀጥላል

ቤተ ሊባኖስ ₃

09 Oct, 14:43


በእንተ ምጽዋት [በአበው ትምሕርት]

እንደ አቅማችን ልንመጸውት እንደሚገባ 
      
        ክፍል- 6

👉 በአንድ በኩል የፍጽምና ደረጃ ላይ የደረሱ አበው ያላቸውን ሽጠው ከዚህ አልፈው ራሳቸውን ሽጠው ሲመጸውቱ በስንክሳር ተጽፎ ስናነብብ የደረሱበትን የብቃት ደረጃ ማሰብ ይገባናል። እኛ በመስጠታችን ብዛት የቅዱሳኑ ገድል እንዳንታበይ ልጓም የሚሆን  ፍጹም ለመሆን ከወደድንም በግብር እነርሱን ልንመስል እንደሚገባ የሚያስተምር ሕያው ወንጌል ነው። እኛ ቅዱሳኑ ከደረሱበት የብቃት ደረጃ ሳንደርስ በእነርሱ ልክ የፍጹማንን ሕግ ለመፈጸም መሞከር በራሱ ፈተና አለው። መንፈሳዊ ልምምድን በጥቂት በጥቂቱ እንጂ በአንዴ የሚደረስበት አይደለምና።

👉 ከዚህ  ውጪ መሠረታዊ ፍላጎታችንን ካሟላን ባልንጀሮቻችን ነዳያንን እንደ ራሳችን አድርገን ልንወዳቸው ይገባናል። ከአቅም በላይ መስጠት ከሕግ በላይ ማድረግ ትሩፋት ሆኖ ዋጋ የሚያሰጥ ቢሆንም በደካማ እምነት ያለችንን መጽውተን እግዚአብሔርን ለማማረር ግን ምክንያት ልናደርገው ግን አይገባም

👉 በመጽሐፈ ሐዊ እንዲህ የሚል አለ:-
"ጥያቄ- አባቴ ሆይ ተርጉምልኝ ንግግርህንም ግለጥልኝ ገንዘቡ ከዕለት ምግቡ የማይተርፍ ቢሆን ሰው እንደሚስማማው ሊሰጥ አይገባውምን እርሱ ራሱ እንዳያዝን ስላደረገውም ነገር እሱ ራሱ በፈቃዱ ስላደረጋት በጎ ሥራ ማዘን እንዴት ይገባል?

መልስ:- ሥራውን ሁሉ ለይተህ በማወቅ ትሠራ ዘንድ ይገባል በጎ ሐሳብንም በልቡናህ ታሳድር ዘንድ ይገባል ከሠራኸውም በኋላ እንዳትታወክ እንዳትጸጸት ሰው ከችሎታው የበለጠ ቢሠራ እርሱ በጎ ሥራን የሚሰራ ቢሆን ወይም የሆነውን ማናቸውንም ቢሆን ሥራውን ለይቶ ካለማወቅ ይቆጠራልና ከዚህም በኋላ ለሚሠራው ሰው ስህተትን መታወክን ያመጣል። ይኸውም ሥራ ክፉ አይደለም ሰው ከጉልበቱ በላይ የማይቻለውን አይደክምምና ነው እንጂ።

[መጽሐፈ ሐዊ ምዕራፍ.20 ገጽ.553]

በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 16 እንዲህ ይላል:- "ምጽዋት ከተሰጠ በኋላ እንዳይጸጸቱ መሆን ይገባዋል። ሰጭውም ምጽዋት በሚሰጠው ሰው ላይ የሚታበይ ያይደለ ሰው ወዳጅ ይሁን"

ከአቅማችን በላይ ለማድረግ ሞክረን በኋላ ላይ እግዚአብሔር ላይ የምናማርር እና የምንጸጸት እንዳንሆን ሲሉ በአቅማችን ልናደርግ እንደሚገባ አበው ይመክሩናል።

👉በእውነት ከራሳችን ያለፈ ገንዘብ አጥተን ነው ወይ ብለን ስንጠይቅ  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል ይገስጸናል። " ለአዝናኝ ተዋናዮች እና ዘማውያን ሴቶችን ለማየት ሌሎች የሚሰጡትን አትመለከቱምን? ሌሎች ለአዝናኝ ተዋንያንና ለዘማውያን ከሚሰጡት ግማሹን እንኳ ስጡ። ሌሎች ለዘፋኞች ከሚሰጡት ግማሹን እንኳ ለክርስቶስ ስጡ። ከትዕቢታቸው የተነሳ በአደባባይ ለሚተውኑ የሚሰጡትን ያህል ስንኳ ለተራበው ስጡ። የዘማዊቷን ልብስ በወርቅ ያስጌጣሉ አንተ ግን ክርስቶስ እርቃኑን ሆኖ እያየሀው የክርስቶስን ሥጋ በቁራጭ ልብስ መሸፈን አትፈልግም? በፈቃድህ ባዶ ለሆኑ ነገሮች ገንዘብህን ታባክናለህ ድሃውን ለማልበስ ሲሆን ግን ራስህን የድሆች ድሃ ታደርጋለህ።" በማለት አሳዛኙን የእኛን እውነታ ይገልጸዋል።

👉 በርግጥም ብዙዎቻችን መሠረታዊ ፍላጎታችንን አሟልተን ቅንጦትን ለማድረግ ስለምንወድ ነው የማንመጸውተው። ቅዱስ ጳውሎስ "አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል።" 1ኛ ጢሞ.6:8 ብሎናል። በመቀማጠል የሚኖሩ ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ሙታን ነው የሚላቸው " ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት።" 1ኛ ጢሞ. 5:6

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

09 Oct, 14:42


በእንተ ምጽዋት  [በአበው ትምህርት]

እንደ አቅማችን ልንመጸውት እንደሚገባ

                ክፍል- 5

ምጽዋት የኃጢአት ሥርየት ምታሰጥ በሰማያት ዋጋ የምታሰጥ ምግባር ስለሆነች ሀብታሙም ድኃው ሊሰጥ እንደሚገባ አይተናል። ከአቅማችን በላይ እስኪሆን ግን ልንጨነቅ አይገባንም።

👉 ቅዱስ ጳውሎስም እንደ አቅማችን ልንሰጥ እንደሚገባ እንዲህ ብሎ ተናገረ "እንደ ዓቅማቸው መጠን ከዓቅማቸውም የሚያልፍ እንኳ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁና።" 2ኛ ቆሮ.8:3

👉 ዳግመኛም ብጹዕ የሚሆን ጳውሎስ እንዲህ አለ:- "በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም።" 2ኛ ቆሮ.8:12

👉 ፍትሕ መንፈሳዊም እንዲህ ይላል:- "መላ ገንዘቡን ግን መመጽወት ለሰው ሁሉ አልታዘዘም። መጀመርያ መላ ገንዘብን መመጽወት ይገባል ያለው ፍጹም ልትሆን ከወደድክ ገንዘብህን ሁሉ ሽጠህ ለነዳያን ስጥ ብሎ ጌታ ስለተናገረ ነው። [ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 16]።

👉 መጽሐፊ ሐዊ ላይም እንዲህ የሚል አለ:- "ቅዱስ በርሱኑፍዮስ ከተናገረው ቃል የመጣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጅ የሚሆን ከሕዝቡ አንዱ የበርሰኑፍዮስ ደቀመዝሙር የሚሆን አባ ዮሐንስን እንዲህ ብሎ ጠየቀው ሰው ማናቸውንም ነገር ከእኔ ቢፈልግ ባይኖረኝ ተበድሬ ልሰጠው በውኑ ይገባልን? ስለዚህም ነገር መለሰለት ሰው ሰውን ከእጁ የሌለውን ገንዘብ ቢለምነው ተበድሮ ሊሰጥ አይገባውም። አንድ በሽተኛ  ምጽዋት ይሰጠው ዘንድ ሐዋርያው ጴጥሮስን ቢለምነው ወርቅ ብር የለኝም ብሎታልና ተበድሮ አልሰጠውምና ገንዘቡ ለዕለት ምግቡ ብቻ ያህል ቢሆን ግን ለሌላ ሊሰጥ አይገባውም እሱ ራሱም አጥቶ ሊያዝን አይገባውም። ሰው ለዕለት ምግቡ ለኑሮው የሚበቃው ገንዘብ ቢያጣ መታገሥም ባይቻለውለው ለማኝ በለመነውም ጊዜ ቢደነግጥ ቢታወክ የምሰጥህ የለኝም ይበለው እንጂ ሊሰጥ አይገባውም። ሐዋ.3:7 [መጽሐፈ  ሐዊ.ምዕራፍ 20 ገጽ.552]

👉 ዳግመኛም በመጽሐፈ ሐዊ እንዲህ የሚል አለ። "ይኸውም ሐሰት አይደለም ከዕለት ምግቡ በቀር ምንም ምን የሌለው ሰው ይሰጥ ዘንድ ነውር ነቀፋ የለበትም ማለት አይገባውም። የአምስቱ የደናግል ምሳሌ አስብ በፋናቸው ላይ ዘይት ይጨምሩላቸው ዘንድ ሰነፎች ብልሆቹን በለመኗቸው ጊዜ ለእኛም ለእናንተም አይበቃም እንዳሏቸው ሐዋርያው ጳውሎስም ስለ ደጎቹ ሰዎች ጽፎ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች በላከው መልዕክቱ ከእናንተ የተረፈውን ለዚህ ጉዳይ መሙሊያ ይሁን ብሎ እንዳሳሰበ። 2ኛ.ቆሮ 8:10-11፤ ማቴ.25:8-10:: [መጽሐፈ ሐዊ ምዕራፍ 20 ገጽ.552


https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Oct, 05:13


በእንተ ምጽዋት [በአበው ትምህርት]

እነማን ይስጡ

             ክፍል- 4

👉 "አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች። ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ። እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች።" ማር.12:43-44 እንዲል ጥቂት እንኳ ያለው ቢኖር ሊመጸውት ይገባል።

👉 ፍትሐ ነገሥት እንዲህ ይላል:- የምጽዋት ረብሀ ጥቅሟ ብዙ ነው፤ እያንዳንዱ እንደተቻለው ይስጥ ባለጸጎችም ነዳያንም። ሁለቱንም የጠቀሰው ከሁለቱ አንዳቸውንም ባይጠቅስ ላለመመጽወት ምክንያት በሆነ ነበርና ሁለቱንም  ጠቀሰ በእርሷ በኩል ክብር ማግኘት የሁሉም ድርሻ ነውና። ዋጋዋም እንደሰጭዋ ትጋት መጠን ነው። [ፍትሐ ነገሥት ምን አለ: ገጽ.178]

👉 መተርጉማን በወንጌል አንድምታ በጠበበው ደጅ ግቡ የሚለውን ቃል ሲተረጉሙ  "ሰፊ በር ሰፊ መንገድ የተባለ ባለጠጋን መጽውት ድኃን ጹም ማለት ነው። ጠባብ በር ጠባብ መንገድ ባለ ጸጋን ጹም ድኃን መጽውት ማለት ነው" በማለት ጠባብ የተባለው ድሃን መጽውት የሚል ነው ብለዋል።

👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም "ወንድሜ ሆይ የምጽዋት ነገር ባለጸጋና ታላላቅ ሰዎችን ብቻ የሚመለከት አይደለም ድሆችና የተቸገሩትንም ጭምር እንጂ ምክንያቱም በርሷ ታላቅ ዋጋና ለሁሉ ድኅነት አለና። ኑሮውን በልመና የሚገፋ ሰው ለርሱ ስለ ምጽዋት ማውራት የተገባ ነው። ይህም ሁለት ናስ እንኳ እስኪያጣ የተቸገረ ድሃና ችግረኛ እንደሌለ ነው።
" ብሎአል።

https://t.me/Abalibanos333

ይቀጥላል.

ቤተ ሊባኖስ ₃

08 Oct, 05:12


በእንተ ምጽዋት [በአበው ትምህርት]

ክፍል 3

   ውዳሴ ከንቱና ምጽዋት
                   

👉 በአንቀጸ ምጽዋት የወንጌል ክፍል ጌታችን  እንዲህ አለ "እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።" ማቴ.6:2። በሰማይ ዋጋን እንዳናጣ ከውዳሴ ከንቱ ርቀን ልንመጸውት ይገባል።

👉 ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ አለ "ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥
ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና። የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና።"
ቆላ.3:23-24

👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ስትመጸውት ለሌሎች እንዲያዩህ አትፈልግምና ስለዚህ ነገር አትጨነቅ። ለውዳሴ ከንቱ ብለህ አላደረግሀውምና ዓለም ሁሉ እንኳ ቢያወድስህ ማንም አያይህም።ጌታችን "ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤" ማቴ.6:1 ብቻ አይደለም ያለው  "እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤" ማቴ.6:2 ለታይታ ስትሉ አታድርጉት ጭምር እንጂ።" ብሎአል። ይህም ስንመጸውት የሰው መኖር አለመኖር  ሳይሆን ውዳሴ ከንቱ ፈልገን ነው ወይ የምንመጸውተው? የሚለው የልቡናችን ሃሳብ ነው ሊያስጨንቀን የሚገባው።

👉 ምጽዋትን ሲሰጥ በውዳሴ ከንቱ የሚፈተን መስጠቱ ጨርሶ ካለመስጠት ግን የተሻለ ነው።  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ውዳሴ ከንቱን ሽታችሁ አታድርጉ በማለት ሲያስተምር አንድ ባለጸጋ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቀርቦ "ምጽዋት መመጽወት እወዳለሁ ውዳሴ ከንቱም  እወዳለሁ አለው። ውዳሴ ከንቱውን ትተህ መጽውት አለው። አይሆንም ሁሉንም እወዳለሁ ይህ ከቀረ ምጽዋቱም ይቅር አለው። እንኪያስ አትተው መጽውት ሰው ዘር ይዘራል ባይጠብቀው የእሸት እህል ያጣታልን? አንተም የዚያን ያህል ጥቂት ዋጋ አታጣም ስጥ ብሎታል።" [የማቴዎስ ወንጌል አንድምታ]

https://t.me/Abalibanos333

ቤተ ሊባኖስ ₃

07 Oct, 18:08


በእንተ ምጽዋት [በአበው ትምህርት]

            ክፍል 2

 ስንመጸውት የሚቀበለን ጌታችን ስለመሆኑ

👉 ወንጌል እንዲህ ይላል:-  "ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?... ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።" ማቴ.25:45

👉 ታሪክ 1- በቁስጥንጥንያ የነበረ በመመጽወቱ ልዩ የሆነ አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱ በከተማው ጎዳና ሲዘዋወር ለድሆች ከመጸወተ በኋላ እንዳያውቁትና ምስጋናቸውንም ላለመስማት ፈጥኖ ከነርሱ ይሄድ ነበር፡፡ አንድ ወዳጁ እንዴት እንዲህ ለጋስ ሊሆን እንደቻለ በጠቀው ጊዜ አንድ ቀን በቤተ ክርስቲያን ካህኑ 'ለድሆች የሚመጸውት ለክርስቶስ ነው የሚሰጠው' ብለው ሲያስተምሩ ሰማሁ "ይህማ እንዴት ይሆናል? ክርስቶስ በሰማያት ያለ አይደለምን?"  በማለት ለማመን ተቸገርኩ፡፡ ከዕለታት ባንዱም ቀን ወደ ቤቴ እየሄድኩ ሳለ አንዱ ነዳይ ሲለምን ከራሱ ላይም የክርስቶስ ፊት ሲያበራ አየሁ፡፡ አንድ መንገደኛም ጥቂት እንጀራን በሰጠው ጊዜ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንጀራውን ተቀብሎ የሰጠውንም ሰው ሲበባርከው ተመለከትኩ፡፡ ከዚያች ጊዜ ጀምሮ በነዳያን ራስ ላይ የክርስቶስ ፊት ሲያበራ እመለከታለሁ፡፡ ስለዚህም በታላቅ ፍርሀት የሚቻለኝን ልግስና አደርጋለሁ፡፡" በማለት ተናግሯል፡፡ [ከምስራቃውያን አባቶች አንዱ]

👉 ታሪክ 2- ገና የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለሁ የቅዳሴ ጸሎት ልካፈል በሐዋርያው የቅዱስ ቶማስ ቤተ ክርስቲያን ተገኘሁ። አንድ አረጋዊ ካህን ለሕዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምር ነበር። በትምሕርቱ መካከል ስለምጽዋት ሲናገር 'ማንም ሰው ለተቸገረ የሚያደርገው ሥጦታ የጌታችን የተቀደሱ እጆች ላይ እንደማስቀመጥ ነው' ሲል ሰማሁት። የሰማሁት በጣም አስደነቀ። ለመሆኑ ጌታችን በክብር ያረገና በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ሆኖ ሳለ በምድር ለአንድ ችግረኛ የሚሰጥን ምጽዋት እንዴት ሊቀበል ይችላል? የማይመስል ነገር ነው። እንዴትስ እንዲህ ያለ የሐሰት ትምህርት ይሰጣል? ስል አረጋዊውን የእግዚአብሔር ሰው ተቸሁት።

የሰማሁትን በኅሊናዬ እያሰላሰልኩ ወደ ቤቴ ስመለስ በመንገድ ላይ አንድ እጅግ የተጎሳቆለ ችግረኛ ተመለከትኩ። በሚደንቅ ሁኔታ ጌታችን ቆሞ ይታያል።
አንድ ደግ ሰው ወደ ችግረኛው ሰው ቁራሽ ዳቦ ሊሰጠው ቀረበ። ሊሰጠውም እጁን ሲዘረጋ ጌታችን ቅዱሳት እጆቹን ዘርግቶ ዳቦውን ተቀብሎ ካመሰገነው በኋላ በድሀው እጆች ላይ አኖረው። የሆነውን ግን የሚለምነውም ሆነ ምጽዋቱን የሚሰጠው አላወቀም። እጅግ ተደነቅሁ ! ከዚያ ቀን አንሥቶም ማንም ለተቸገረ ወንድሙ እጁን በርኅራሄ ሲዘረጋ በክርስቶስ ቅዱሳት እጆች ላይ እንደሚያስቀምጥ በእርግጥ አመንሁ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሁልጊዜ ከተቸገሩት ሰዎች በላይ ቆሞ ስለማየው ድሆችን ማክበርን ተሞላሁ። ጌታንም እጅግ ደስ እንደሚያሰኘው ስለተረዳሁ በቻልኩት አጋጣሚ ሁሉ ለተቸገሩት የአቅሜን ለማካፈል ተጋሁ።

[ራዕየ ኒፎን ገጽ.119-120]

https://t.me/Abalibanos333

ይቀጥላል

36,667

subscribers

288

photos

44

videos