ከአብደላህ ቢን መስዑድ (📿) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦
“የአላህ መልዕክተኛ (🤍) ሰሌን ላይ ተኙና ጀርባቸው ላይ የሰሌኑ ፋና እየታየ ተነሱ። እኛም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የተመቸ ምንጣፍ ብናደርግሎትስ? አልናቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ፦ ‘እኔና ዱንያ ምን አገናኘን። እኔኮ ዱንያ ውስጥ ልክ ዛፍ ስር እንደተጠለለና ትቷት እንደሄደ መንገደኛ እንጂ ሌላ አይደለሁም።’”
📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 2377
@muhamedunresulullah