Yasin nuru's hadis @yasin_nuru_hadis Channel on Telegram

Yasin nuru's hadis

@yasin_nuru_hadis


This is not Official
ይሄ ቻናል የያሲን ኑሩ ትምህርት የሚሰጡበት እንጂ የያሲን ኑሩ አይደለም!

"በጃሂሊያ (ብሄርተኝነት) ጥሪ የተጣራ እርሱ በእንብርክክ ጀሃነም የሚገባ ነው ፤ ቢፆምና ሙስሊም ነኝ ብሎ ቢሞግት እንኳን።

Yasin nuru's hadis (Amharic)

የያሲን ኑሩ አዝናኝ ቻናል

የይህን ቻናል ለመደበኛ ያሰገዱት ተከታይ ስለእናንተና ስለእኛ ምንጭ። በጃሂሊያ (ብሄርተኝነት) ጥሪ የተጣራ እርሱ በእንብርክክ ጀሃነም የሚገባ ነው ፤ ቢፆምና ሙስሊም ነኝ ብሎ ቢሞግት እንኳን። ስለዚህ እናንተን ለእናንተ የያሲን ኑሩ ትምህርት ቻናል እና በተለያዩ መረጃዎች እንዲሰጡ ተለቅቻለው። የኑሩን በየከተማው ለምስላከንም መረብ ከሆኑ፣ ስለጎና መረጃዎች ማስጫን እንዲችሉ በቴሌግራም መልክም በሁለቱም ተቀብለው ማድረግ።

Yasin nuru's hadis

21 Nov, 09:30


አይናችሁ የቱ ጋር አረፈ🥹?

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

20 Nov, 17:31


ነገ ሐሙስ ነዉ የቻለ ይፁም
.
ያልቻለ ለመቻል ይሞክር ☺️
.
.
መልካም ነገርን የጠቆመ ከሰሪው እኩል አጅር ያገኛል እና ሌሎችንም አስታውሱ 🙌

መልካም ለይል

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

20 Nov, 11:33


100 days until Ramadan!
اللهم بلغنا رمضان
ረመዷንን 100 ቀናት ቀሩት

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

20 Nov, 05:32


የማንንም ልብ ለማሸነፍ ስትይ
ማንነትሽን አትቀይሪ   አንችን የሚወድሽ ሰዉ
ከነ ማንነትሽ ይቀበልሻል

Yasin nuru's hadis

20 Nov, 05:30


﴿للهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا فِيهِنَّ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ﴾.

«سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ ، أشْهَدُ أنْ لَا إلَهَ إلَّا أنْتَ ، تَبَارَكْتَ وَتَعَالَيْتَ ، أسْتَغْفِرُكَ وَأتُوبُ إلَيْكَ ، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِكَ».

Yasin nuru's hadis

19 Nov, 18:49


ሐላል ትዳር እና ሐላል ሥራ ላሳሰበው ሁሉ ቆንጆ ዱዓዕ -
~
"አልላሁምመ-ክፍኒ ቢሐላሊከ ዐን ሐራሚከ ወአግኒኒ ቢፈድሊከ ዐምመን ሲዋከ"
ትርጉም:–
ጌታዬ ሆይ ከሐራምህ በሐላልህ አብቃቃኝ። በችሮታህም ካንተ ውጭ ያለውን እንዳላስብ ብቃኝ ።

Yasin nuru's hadis

19 Nov, 03:47


በሁሉ ነገራችን አላህ ባይሠትረን ኖሮ ከእፍረት              ብዛት አንገታችን ተሰብሮ በቀረ ነበር ።
 
ሲትራከ ያ ረሕማኑ


@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

19 Nov, 03:47


﴿قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ﴾.

«اللَّهُمَّ إنَّا نَسْألُكَ إيمَانًا دَائِمًا وَيَقِينًا ثَابِتًا وَعِلْمًا نَافِعًا وَهَدْيًا قَيِّمًا».

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

18 Nov, 15:14


ማስታወሻ 

1- ሸሪዓዊ ስርዓቶችን ባማከለ መንገድ መተራረም በሙስሊሞች መካከል ሊሰፍን የሚገባ የወንድማማችነት መገለጫ ነው! አላህ እንዲህ ብሏል፦
{وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنْكَرِ..}
«ወንድ አማኞችም ሴት አማኞችም ከፊላቸው የከፊላቸው ረዳት ናቸው፤ በበጎ ያዛሉ፤ ከመጥፎም ይከለክላሉ…» [አት-ተውባህ ፡ 71]

2- ምክር በመሰረቱ በግል መተላለፉ ቢመረጥም በተሰራጩና በይፋ በሚተገበሩ ጉዳዮች ዙሪያ እውቀት ላይ የተመረኮዘ ገንቢ ምክር በይፋ መለገሱ ብዙዎችን የሚያርምና የሚያስተምር ይሆናል። ሆኖም፦

3- ስህተት የፈፀመን ለይተው ሳይጠቅሱ ጥቅል ምክሮችን በይፋ ማስተላለፍ የመልዕተኛውን ፈለግ የተከተለ አንድ ስልት ነው። የሙእሚኖች እናት ዓኢሻህ እንዲህ ትላለች፦
كَانَ النَّبِيُّ -صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- إِذَا بَلَغَهُ عَنِ الرَّجُلِ الشَّيْءُ لَمْ يَقُلْ: مَا بَالُ فُلَانٍ يَقُولُ؟ وَلَكِنْ يَقُولُ: مَا بَالُ أَقْوَامٍ يَقُولُونَ كَذَا وَكَذَا؟
= «ነብዩ (ﷺ) ስለ አንድ ግለሰብ አንድ ወሬ ሲደርሳቸው “እገሌ ምን ሆኖ ነው እንዲህ የሚለው!” አይሉም ነበር! ነገር ግን “እንዲህ የሚሉ ወገኖች ምን ሆነው ነው?” ይሉ ነበር።»
[አቡ ዳዉድ (4788) በትክክለኛ ሰነድ ዘግበውታል፤ (“ሲልሲለቱ’ል-አሓዲሥ አስ-ሶሒሓህ” ቁጥር 2064)]

ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑ ሐዲሦች እጅግ ብዙ መሆናቸው ይታወቃል።
እንዲያውም ለአስር አመታት የነብያችን አገልጋይ (ኻዲም) የነበሩት አነስ ኢብኑ ማሊክ ስለ እርሳቸው እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፦
"وَكَانَ لَا يَكَادُ يُوَاجِهُ أَحَدًا فِي وَجْهِهِ بِشَيْءٍ يَكْرَهُهُ.."
«አብዛኛውን ጊዜ አንድን ሰው በሚጠላው ጉዳይ ፊት ለፊቱ አይጋፈጡትም ነበር።» [(አህመድ (12573)፣ (12367)፣ (12628) አቡ ዳዉድ (4182)፣ (4789)] (በሰነዱ ውስጥ ያለው “ሰልም አል-ዐለዊ” የተባለውን ግለሰብ በተመለከተ የሐዲሥ ሊቃውንት ዘንድ ውዝግብ ያለ ሲሆን ብዙሃኑ ደካማ እንደሆነ ፈርደዋል።)

4- በትምህርታዊ ምክር ተጠቃሚ እንዳንሆን ከሚያግዱን እንቅፋቶች አንዱ መልዕክቱን አገናዝቦ ራስን በመፈተሽ ፈንታ “ለማን ታስቦ ነው? ማንን ደግፎ ነው? ማንንስ ነቅፎ ነው?..” በሚል ሀሳብ መዋለልና አልፎም በዚህ ላይ መነታረክ ነው። ከዚህ ይልቅ ለሁሉም የሚበጀው፦
" فإمَّا أَن تنطق بِعِلم، وَإِمَّا أَن تسكت بحِلم "
((ወይ በእውቀት ተናገር፤ አሊያም ችለህ ዝም በል!))
[ከአል-ኢማም አዝ-ዘሀቢይ ንግግሮች ነው።]

5- ከአንድ ሰው ንግግር በተዘዋዋሪ የተረዳነውን ግንዛቤ ከአንደበቱ እንደወጣ ቀጥተኛ ንግግር ወይም አቋም መቁጠር እንደማይፈቀድ የኢስላም ሊቃውንት አስፍረዋል! [ለምሳሌ፦ “መጅሙዑ’ል-ፈታዋ” (20/217) ይመልከቱ!]
አደራ! ያልተፃፈ አይነበብም፤ የተፃፈውም ያለ አግባብ አይመነዘርም!

6- የመካሪም ሆነ የሌላ ስህተት ባለቤቱን እንጂ ሌላን አይመለከትም፤ በግልፅ መረጃዎች ያልተቋጨ ጉዳይ ላይ የሚሰነዘርም ቃል ተናጋሪውን እንጂ ሌላን አይወክልም!

7- በፌስ ቡክ ላይ የሚፃፉ አስተያየቶችና መልዕክቶች ለሺዎች እንደሚደርሱና እንደሚዳረሱ አንዘንጋ! በዚህ ላይ የተለያዩ አመለካከቶች፣ አላማዎች፣ የግንዛቤ ደረጃዎችና ስሜቶች ያሏቸው ተጠቃሚዎች የሚስተናገዱበት መድረክ ነው።

===================
በምፅፋቸው መልዕክቶች የማቅደው ጥቅል ትምህርታዊ ምክርን እንጂ ወቀሳንና ተራ ትችትን አይደለም፤ ገለፃዎቹም ገንቢ እንጂ አፍራሽ ቃና እንደሌላቸው ተስፋ አለኝ፤ ለዚህም ነው በአብዛኛው የዑለማዎችን ንግግር በማጣቀስ ላይ የምገደበው።
{إِنْ أُرِيدُ إِلَّا الْإِصْلَاحَ مَا اسْتَطَعْتُ وَمَا تَوْفِيقِي إِلَّا بِاللَّهِ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ}
አላህ ለርሱ ብለው ከሚዋደዱ ያድርገን!
أخوكم في الله: إلياس أحمد

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

18 Nov, 08:06


Mohammed Ali👊👊

አላህን ከያዝክ ምንም ነገር አያስፈራክም

@yasin_nuru_hadis‌‌‌‌

Yasin nuru's hadis

17 Nov, 18:26


የሰነፍ ወንድ ህልም
ሀብታም ሴት ማግባት ነው

አንተ ምታገባት ጠብ እርግፍ ብለህ
    ልታስቱዳድራት  እንጂ
ልታስተዳድርህ መሆን የለበትም

ወንድ ሁን

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

17 Nov, 14:03


አንድ ሰው ካማኸው ምንድን ነው መፍትሄው?

እንዳማኸው ካወቀ በግልፅ ወዳማኸው ሰው ሂድና ይቅርታ (ዐውፍታ) ጠይቀው።

ካላወቀ፦ አላህ ወንጀሉን እንዲምርለት ዱዓእ አድርግለት፣ በዛ ባማኸው ቦታ ስለርሱ ጥሩ ጎን አውራና አወድሰው። መልካም ሥራ መጥፎን ያብሳልና!

ኢብኑ ዑሠይሚን

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

16 Nov, 07:25


እናቴ🥰🥰🥰

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

15 Nov, 17:41


☀️رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الآخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّار

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

15 Nov, 09:29


ሰሉ አለ ረሱል🥰🥰

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

15 Nov, 06:06


በነገራችን ላይላይ

ጁሙዐ ቀን ኹጥባ እየተደረገ ማውራት እንደማይፈቀድ ይታወቃል።

ሌላው ቀርቶ ወሬ የያዘን ሰው "ዝም በል" ብሎ ማናገር እንኳ አይገባም። "ታዲያ እንዴት አድርገን ዝም እንዲል እናድርግ?"

ከተባለ ያለ ንግግር በእጅ በማመላከት መጠቆም ይቻላል። የምልክት ጥቆማ በኹጥባ ቀርቶ በሶላትም ውስጥ ይፈቀዳል።

ኢብኑ ዑመር እና መጅዘአ ብኑ ዛሂር አልአስለሚይ - ረዲየላሁ ዐንሁም - ኹጥባ እየተደረገ በጥቆማ ያመላክቱ እንደነበር ተጨባጭ መረጃ መጥቷል። [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ፡ 3/225] [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ 2/117]

ኢብኑ ረጀብ አልሐንበሊይ ረሒመሁላህ "በጥቆማ ማመላከት እንደሚቻል በዑለማእ መካከል ልዩነት የለም" ብለዋል። [ፈትሑልባሪይ ፡ 5/496]

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

14 Nov, 07:39


እስልምና ፀጋ ነዉ
ኢብራሂም ለአባቱ ተመኘ ኑህ ለልጁ
ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለአጎቱ
አላህ ይህንን ፀጋ ሳናስበዉ ሳንጠይቀዉ ለኛ ሰጠን!

ይህንን ፀጋ እኛ ግን አስተንትነነዉ እናቃለን....?

አላህ በባሪያወቹ ላይ በርካታ መልካም ነገሮችን
ሰቶቸዋል በርካታ ሰወች ግን አያመሰግኑም!💔


@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

14 Nov, 07:32


አላህ ከጀሃነም ቅጣት ይጠብቀን🥹🥹

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

13 Nov, 04:36


እርሷ ንግስት ናት

ጌታዋን በብቸኝነት ያመለከች፣ ለርሱም ጊዜውን ጠብቃ ሰላቷን የሰገደች!!

ሂጃቧን በስርአት የለበሰች እና በሀያዕ ያሸበረቀች ሴት በርግጥም  እርሷ ንግስት ናት👌



               
@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

12 Nov, 12:07


ለነፍሳችን እንድረስለት

ሰሌን ደህና ማረፊያ አይደለም ። አካልን ምቾት የሚነሳ መሻከር እንዳለበት የታወቀ ነው ….

ነብዩ ይሄው ሰሌን ላይ ይተኙ ነበር ።  ሰሌኑም ጎናቸው ላይ ምልክትቱን ይጥል ነበር ።
ባልደረቦቻቸው “ ለምን የተሻለን ምንጣፍ አናደርግልህም ?”  ሲሏቸው

ما لي وللدنيا؟ ما أنا في الدنيا إلا كراكب
استظل تحت شجرة، ثم راح وتركها

“ እኔና ዱንያ ምንና ምንድን ነን ? እኔ እኮ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ( ለማረፍ ) እንደተጠለለ አንድ ( መንገደኛ ) ጋላቢ ነኝ .. ከዚያም ሄደ ተዋትም ….

አንዳንዴ ቤታቸው ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ይጠፋ ነበር … በርግጥ ነው አንዳንዴ በርከት ያለ ነገር የነብዩ እጅ ውስጥ ይገባ ነበር ። ነገር ግን እጃቸው ውስጥ የገባውን ሪዝቅ በአላህ መንገድ ላይ ያከፋፍሉት ነበር ….

የነብዩ ባልደረቦች የሚለበስ በማጣት ተፈትነዋል ፣ ረሃብን አብዝተው አስተናግደዋል … ግባቸው የአላህን ውዴታ ማግኘት ነበርና ታገሱ ፣ ፈተናውን በአግባቡ ተወጡ …  ግን ከነ ችግራቸው የደስታን ህይወት ገፍተዋል  …

የኛ ነገርማ

ትልማችን አለማዊ ሆኗል ! ህልማችን የዱንያው ሸቀጥ ብቻ ሆኖ አኺራን ዘንግተናል … ወጋችን ባንክ ነው .. ሚዛናችን ሃብትና ዘር ነው - አላህ ያዘነት ሲቀር ጠፍተናል  እየጠፋን ነው ።

ለነፍሳችን እንዘን ፣ ወደ አላህ መንገድ እንመለስ  …

አላህ ይመልሰን !!

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

11 Nov, 08:32


🎖🎖ቢስሚላህ ብሎ የመጠጣትና የመብላት ጥቅሞች፡፡ነብዩ ሰዐወ ከ1400 አመት በፊት የተናገሩትን በዚህ ዘመን ሳይንቲስቶች ያረጋገጡት እዉነታ

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

10 Nov, 17:37


Imagine በባቡረያን የጀነት በር ሰብሰብ ብለን ስንገባ 😍
እኔ ከፊት ሆኘ 😁
ባቡ ረያን :- ፆመኞች የሚገቡበት የጀነት በር
.
ነገ ሰኞ ነዉ የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

10 Nov, 07:58


ዝነኛው የሲያትል Gum Wall በታሪኩ ለሁለተኛ ጊዜ ሊፀዳ ነው ።
.....

በ1990 ዎቹ መጀመሪያ ላይ በሲያትል በሚገኝ አንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ በሚገኝ  ሲኒማ ቤት ፡ ፊልም ለማየት የተሰለፉ ሰወች ያኝኩት የነበረውን ማስቲካ እንደቀልድ  በግድግዳው ላይ መለጠፍ ጀመሩ ።  በጥቂት ጊዜያት ውስጥም  ግድግዳው በሙሉ በማስቲካ ተሞላ
.....
በ2009 በተሰራው Love Happens በተሰኘው የፍቅር ፊልም ላይ ፡ ጄኔፈር አኒስተንና አሮን ኤከርት በዚህ ስፍራ ተገኝተው ያኘኩትን ማስቲካ በግድግዳው ከለጠፉ በኋላ ደግሞ ፡ ስፍራው ይበልጥ ዝነኛ ሆኖ ፊልሙን ያዩት ሁሉ እየሄዱ የማስቲካ አሻራቸው ያስቀምጡ ጀመር ።
.....
ሆኖም ፡ ከቀን ወደቀን  የሚለጠፈው ማስቲካ እየበዛ  በመሄዱና ግድግዳውን እንዳይጎዳው በማሰብ. .  በ2015 ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲፀዳ በተደረገበት ወቅት  እያንዳንዱ ሰው የሚለጥፈው  ተጠራቅሞ  2,350 ፓውንድ የሚመዝን ማስቲካ ከግድግዳው ላይ ተነስቶ የተጣለ ቢሆንም ፡ ብዙም ሳይቆይ ግድግዳው እንደገና በማስቲካ ተሸፍኖ የጎብኝዎችን ትኩረት ሲስብ ቆይቷል ።

......
በተናጠል ቀላል የሚመስሉ ድርጊቶች በህብረት አስደናቂ ነገር መፍጠር እንደሚችሉ ማሳያ የሆነው ይህ የማስቲካ ግድግዳ ከዚህ በተጨማሪም, ውበት እና ጥበብ ባልተመለዱና እንግዳ በሆኑ መንገዶች እንደሚፈጠሩ የሚያሳይ ነገር ነው ።

©መንቁል

የማይሰማ ጉድ የለም መቼስ

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

09 Nov, 07:49


🚫እንዲህ አይነቱን ሰው ከመሆን ተጠንቀቅ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿أَتَدْرُونَ مَا الْمُفْلِسُ ؟ " قَالُوا : الْمُفْلِسُ فِينَا مَنْ لَا دِرْهَمَ لَهُ وَلَا مَتَاعَ. فَقَالَ : " إِنَّ الْمُفْلِسَ مِنْ أُمَّتِي يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِصَلَاةٍ وَصِيَامٍ وَزَكَاةٍ، وَيَأْتِي قَدْ شَتَمَ هَذَا، وَقَذَفَ هَذَا، وَأَكَلَ مَالَ هَذَا، وَسَفَكَ دَمَ هَذَا، وَضَرَبَ هَذَا ؛ فَيُعْطَى هَذَا مِنْ حَسَنَاتِهِ، وَهَذَا مِنْ حَسَنَاتِهِ، فَإِنْ فَنِيَتْ حَسَنَاتُهُ قَبْلَ أَنْ يُقْضَى مَا عَلَيْهِ ؛ أُخِذَ مِنْ خَطَايَاهُمْ فَطُرِحَتْ عَلَيْهِ، ثُمَّ طُرِحَ فِي النَّارِ﴾

“ድሃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?! ሶሐቦችም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ ‘እኛ ውስጥ ድሃ ማለት ድርሃም (ገንዘብ) እና መጠቃቀሚያ የሌለው ነው።’ የዚህን ጊዜ ነቢዩ እንዲህ አሉ፦ ከኔ ህዝቦች ድሃ ማለት፦ በሶላት፣ በጾምና በምጽዋት (በዘካ) በተሰሩ መልካም ስራዎች የቂያም ቀን የሚመጣ ነው። በርግጥ አንዱን ሰድቧል፣ አንዱን አነውሯል፣ የአንዱን ገንዘብ በልቷል፣ የአንዱን ደም አፍሷል፣ አንዱን መቷል (ደብድቧል)። ለእዚያም ከመልካም ሥራው ይሰጠዋል፣ ለእዚያም ከመልካም ሥራው ይሰጠዋል። ያለበትን እዳ ሳይከፍል በፊት መልካም ሥራው ካለቀ፤ ከነርሱ ወንጀል ይያዝና እርሱ ጀርባ ላይ ይወረወራል። ከዚያም ወደ እሳት ይወረወራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2581

Yasin nuru's hadis

05 Nov, 04:36


ጨለማው ብቻ ሳይሆን ሲትሩም ሸፍኖን አድረናል።
የቱን፣ ስንቱን ፀጋዉን እናመስግን ?


አልሃምዱሊላህ❤️‍🩹🤍

Yasin nuru's hadis

04 Nov, 08:16


ያህያ ሲንዋር ማነው?

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

03 Nov, 16:42


ነገ ሰኞ ነዉ የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ 🤍

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

03 Nov, 06:35


የአለማት እዝነት🥰

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

02 Nov, 17:17


ጀነትን ተመኘሁላችሁ 🖤


ለኔም እስኪ ዱዓ አድርጉልኝ🥰

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

02 Nov, 04:37


.
አላህ ሆይ🤲

እነዛ ደስታን የናፈቁት ልቦች❤️‍🩹
ማዘናቸው ትዝ እስከማይላቸው ድረስ
በደስታ ሙላቸው....

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

01 Nov, 13:19


https://t.me/islamicprofilepicture1

Yasin nuru's hadis

01 Nov, 11:43


እኔ ቅርብ ነኝ🥰🥰

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

31 Oct, 12:43


አላህን የያዘ ምን ያጣል🥰

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

31 Oct, 07:09


ነገ መልካም ይሆናል ....ነገሮች ይስተካከላሉ ደስተኛም እንሆናለን ።

ኢንሻአላህ!

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

30 Oct, 18:32


ነገ ሐሙስ ነዉ የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ🤞

መልካም ለይል አህባቢ 🙌

Yasin nuru's hadis

30 Oct, 06:15


አንድ ፓስተር በነብዩ ﷺ እና ሙስሊሞችን በምሳሌ በመጥቀስ እንዴት አማኞችን እንደሚያተምር ይመልከቱ

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

30 Oct, 02:59


አላህ ለሊቱን ወደ ቀን መቀየር ከቻለ
ሸክማችንን ወደ ፅጋ ሊለውጠው ምን ይሳነዋል?


❤️‍🩹....


@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

29 Oct, 09:04


.
የተበዳይን ዱዐ ፍሩ! በሱ እና በአሏህ መካከል ግርዶሽ የለምና! ረሱል ﷺ 🤍

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

28 Oct, 13:07


- ላለፈው አታስብ

ያለፉት ቀናት ላይመለሱ ሄደዋል..💝
ላይመለሱ ለሚመጡት ቀናት አስብ🤍


@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

27 Oct, 05:34


የቴሌግራም መስራች Pavel Durov እንዲህ ሲል ተናገረ

”የሚቆጨኝ ነገር ግን ማቆም ያልቻልኩት ነገር ቢኖር McDonald’s ገብቼ በርገር አዝዤ የምትጠቀው 5 ደቂቃ ነው። 5 ደቂቃ ሙሉ ያለምንም ስራ መቀመጥ ማለት ለ 5 ደቂቃ መሞት እንደማለት ነው።

ልጆች Game አጨዋወት ሳይሆን Game አሰራር ተማሩ!

ወጣቶች የፊልም Recommendation ሳይሆን የስራ ፈጠራ Recommendation ተመልከቱ ወደፊት ታመሰግኑኛላቹ”።

@islam_in_school

Yasin nuru's hadis

27 Oct, 01:32


አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ እንዴት ናችሁ? ይህ መፅሀፍ በ @IbnuHashm channel የተዘጋጀ ሲሆን የመፀሀፉ ርዕስ ''በኢስላም ዉስጥ የሴትን ልጅ መብትና ግዴታ እና ማረጋገጫ'' የሚል ነዉ።

ይህ መፅሀፍ ዋናዉ ዓላማዉ ምዕራብያዉያን እንደሚሉት ሴት ልጅ በእስልምና ተጨቁናለች ለሚለዉ አጠር ያለች እና አጥጋቢ መልስ የያዘች መፀሀፍ ነች። እንድታነቡት ጋበዝኳችሁ።

ሁላችሁም ሼር አድርጉት በተለይ ለUniversity ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በጣም ያስፈልጋቸዋል።

የ University የተማሪዎች አሚሮች ይህንን መፅሀፍ በጀመአዉ ቻናል ወይም በግል አሰራጩት።

ጀዛኩመላሁ ኸይረን

Yasin nuru's hadis

27 Oct, 01:29


@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

26 Oct, 16:35


ሰላም ለነዛ 🖤



ቀጥሉት እስኪ 😌

Yasin nuru's hadis

26 Oct, 05:09


የቀኑ ሶስቱ ሃዲሶች

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐
1️⃣📚
"በጁምዓ ቀንም ሆነ በሌሊት የሚሞት ሙስሊም የለም አላህ ከቀብር ፈተና ይጠብቀዋል"

2️⃣📚
“አንድ ሰው ለቤተሰቡ አስቦ የሚያወጣው ወጪ ለሱ ሰደቃ ይሆንለታል።”


3️⃣📚
“አንዳችሁም አላመናችሁም ለራሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ።”

📚1️⃣【 ቲርሚዚ 1074】
📚2️⃣【ሳሂህ ሙስሊም 1002】
📚3️⃣【ሳሂህ ሙስሊም 45】


@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

25 Oct, 06:07


አንተ አሏህን ማመስገን እስካላቆምክ ድረስ ተመስጋኙም(አሏህ) አንተን ማስገረሙን አያቆምም💫

Yasin nuru's hadis

24 Oct, 14:39


ወንድ ልጅ ሴት ልጅን
ማፍቀሩ ተፈጥሮ ነው

በሃላል ሰትሯት ጠበቅ ማድረጉ ግን
ወንድነት ነው
              

Yasin nuru's hadis

24 Oct, 09:43


ዝነኛና ታዋቂዋ የ MMA (mixed martial arts) ተደባዳቢ አምበር ሊብሮክ (AMBER LEIBROCK) እስልምናን ተቀብላለች። ማሻአላህ!❤️🌷🥰

በሒጃብ ውበቷ እጥፍ ሆኗል!😊

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

23 Oct, 00:09


አላህ ከፍጥረታት ሁሉ መረጠንና የሰው ልጅ አደረገን...

ከሰውዎችም መካከል መረጠንና እስልምናን ለገሰን

ከሙስሊማች መካከል መረጠና የተወዳጁ ነብዬﷺ ኡመት አደረገን...

ወላሂ ወቢላሂ  ቆጥረን ማንዘልቀው ትልቅ እድል ውስጥ ነን።

አላህን በብዛት እናመስገን !🤲

{وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ}
"የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡"
                [ሱረቱ ነህል:18]

ብዙ ለሰጠን አላህ ብዙ ምስጋና የተገባው ነው🌱

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

22 Oct, 13:43


ተው ግን እየገባቹ ኮድ 56ን 👍 አርጉልኝ አላሳዝናቹም

Yasin nuru's hadis

22 Oct, 04:55


🦋❝ጀነት ስንገባ አንድም ሰው ከመካከላችን እንዲጎድል አንፈልግም..በሉ ተነሱ ልጆቼ❞ እያለች ልጆቿን ለሱብሒ ሶላት የምትቀሰቅስ አንዲት እናት ነበረች።

አሏህ ለልጆቻቹህ ምርጥ ዓርዐያ የምትሆኑ ያድርጋቹህ  ያድርገን🤲🦋

Yasin nuru's hadis

21 Oct, 06:23


➥ "በጥንቃቄና በእንክብካቤ ሊጠብቁት የሚገባ ሐብት ምንድን ነዉ?" የሚለዉን ጥያቄ ሶሐቦች (ረ.ዐ) ረሱልን (ሶ.ዐ.ወ) ጠይቀዉ ሲመልሱላቸዉ:-

"አላህን በማስታወስ(ዚክር በማድረግ) የተጠመደ ምላስ፤ አላህን የሚፈራ ልብ ፤ባሏን በዲን ሥራ ላይ ተግታ የምትረዳ ሚስት ናቸዉ" ሲሉ ገልፀዋል።

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

20 Oct, 05:35


ያ አላህ

ሰላም ፣እርዝቅ ለእነዚያ ይህንን ቻናል ሌት ከቀን ለሚከታተሉና <<ሼር>> ለሚያደርጉ🥰

Yasin nuru's hadis

19 Oct, 04:27


ሀቢቢ!
የጌታህን ፍቅር፣ የረሱሉን ውዴታ፣ የመልካም ሰዎችን ጉርብትና ከሻህ… በሰላትህ ጠንክር!

ነገ ብርሀንን፣ ኑርን፣ ምስክርን ከፈለክ ዛሬ ሰላትህን አስውብ!

ቅር ቢልህም አንድ ዕውነታ ልንገርህ!
ካልሰገድክ… ነገ ብርሀንም፣ ኑርም፣ ምስክርም አይኖርህም። ከዚያም ብሶ በዓለም ላይ እንደነሱ ክፉ ታይቶ ከማይታወቅ ከነ ፊርዖን፣ ከነ ሀማን፣ ከነ ኡብይ ኢብኑ ከለፍ ጋር ነው ምትጎዳኘው።

ወይኔ! እንዲህ ባረኩ ኖሮ ብለህ የምትፀፀትበትና ፀፀትህም የማይጠቅምህ ቀን ሳይመጣ በጊዜ ተዘጋጅ! በጊዜ ሰንቅ!

[[ሀቢቢ! ነገ ከዱንያ የበለጠ ዕጅግ ያማረ ቦታ ይጠብቀናልና… #ሰላትን_አደራ!]]

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

18 Oct, 03:54


ከሱረቱል ከህፍ የመጀመሪያ አስር አያዎችን የሀፈዘ ከደጃል ፈተና መጠበቂያ ይሆነዋል❗️

روى الحاكم في المستدرك مرفوعا إن من قرأ سورة الكهف يوم الجمعة أضاء له من النور ما بين الجمعتين. وصححه الألباني

📌ረሱል ﷺ በጁሙዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን ያነበበ በሁለት ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል ብለዋል።

📌ነብዩ ﷺ በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ የናንተ ሰለዋት እኔ ዘንድ ይቀርባልና ብለዋል።

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنّ في الجُمُعَةِ لَساعَةً، لا يُوافِقُها مُسْلِمٌ، يَسْأَلُ اللهَ خَيْرًا، إلّا أعْطاهُ إيّاهُ.﴾

“በጁምዓ ቀን አንዲት ሰዓት አለች። በዛች ሰዓት አንድ ሙስሊም አላህን መልካምን ነገር እየጠየቀ አይገጥምም፤ ለሱ የጠየቀው የሚሰጠው ቢሆን እንጂ።”

ሙስሊም ዘግቦታል

📌በጁሙዓ ቀን ኹጥባ በሚደረግበት ጊዜ ሰዎች ላይ መረማመድ እና ማውራት የተከለከለ መሆኑን አንዘንጋ።


እንዲሁም ከሚስተዋሉ ስህቶች አንዱ ጁሙዓ ሙባረክ መባባል ነው ይሄ መሰረት የለውም።

#ጁመዓ_ነው_ሰለዋት_እናብዛ

اللهم صلي على محمد وعلى آل محمد ،
كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم ،
وبارك على محمد وعلى آل محمد ،
كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم، في العالمين إنك حميد مجيد


@yasin_nuru_hadis
@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

18 Oct, 02:28


አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡



@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

17 Oct, 12:24


ሸይጧን ሸቀጡን በኸይር ገበያ ነው የሚሸጠው።

🔻ፆም ሁሉ ዒባዳ አይደለም። ፆም መዕሲያ ወንጀል የሚሆንበት ጊዜያቶች አሉ።

🔻ሶላት ሁሉ አምልኮ ታዛዥነት አይደለም። መስገድ ወንጀል ሀራም የሆኑባቸው ጊዜያቶች አሉ።

📌📌ደግሞ ስራው ልክ ሆኖ አርካኑ ሸርጦቹ በሙሉ አሟልቶ ተቀባይነት ያግኝ አያግኝ አይታወቅም።

📌📌📌ስራው ተቀባይነት ካገኘ እራሱ ሒስድ ካለ እሳት እንጨትን አመድ እንደሚያደርገው ስራው በሙሉ አመድ ይሆናል።

📌📌📌📌በብዙ ኢጅቲሃድ እራስህን ከሒስድ አጥርተ ተቀባይነት ያለው ዒባዳ መልካም ስራ ብትሰራ ከዛም የሰዎችን ክብር ብትነካ ነገ በአኼራ ለነሱ ይሰጣቸውዋል። ይህ እራሱ አላህ የተቀበለህ ኸይር ስራ ካለህ ነው።

🟢ምንም ባትሰራ የሰዎች ሀቅ ከሌለብህ ትልቅ ሸረፍ ነው። ሙፍሊስ ከመሆን አላህ ይጠብቀን።

🔰ዋናው ነገር አደብ ይኑርህ። ታላላቆችህ አንተ ስትወዳቸው ብቻ ሳይሆን ባትወዳቸውም አክብራቸው። አንተን ሲገጥሙ ብቻ ሳይሆን ሲኻልፉህም አክብራቸው። ለማክበር መውደድ መስፈርት ሆኖ አያውቅም። ታላቅ ማለት፦ በእድሜ፣ በዒልም ና በተለያዩ መልካም ነገሮች የሚበልጡህ ታላላቆችህ ናቸው። ብታከብራቸው ትከብራለህ።

🖍ትልቁ ነገር አደብ ነው። አደብ የሌለው እምነትም የለው።
ኡስታዝ ካሚል ሰልማን

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

16 Oct, 05:47


ጊዜ ምን አስተማረሽ?

* እኔ መቼም እንደዛ አልሆንም
* እኔ ላይ መቼም አይደርስም
* እኛ ቤት መቼም አይሆንም

  አለማለትን💔❤️‍🩹

©yuti

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

15 Oct, 17:14


ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

 ﴿أدِّ الأمانةَ إلى منِ ائتمنَكَ، ولا تخُنْ من خانَكَ﴾

“አምኖ ለሰጠህ አማናውን አድርስ። የካደህን አትካድ።”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 423

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

15 Oct, 06:44


🌷"የቆምኩ ያህል ይሰማኛል ከሶሓቦቹ ጎራ፣
የስንብት ቃሉ ሲናኝ አማናዎ ሲዘራ፣
ምን ባጎድል አደራዎን ባይሳካልኝም፣ አልሰማሁም የምልበት አንደበት ግን የለኝም።"🌷

🌺"ከተሰጡት ምን ቀርቶብኝ ካንቱ ምን አጥቼ፣
በጨለማ የምባክን ብርሃኖን ትቼ፣
የስንብት ሕያው ቃሎ ደርሷል ከኔም ደጅ፣
ምስክር ነኝ ባአደባባይ ነብይ የኔ ወዳጅ።"🌺


እኛም ድርሶናል መልእክቶ ያ ነቢየላህ!🌺

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

14 Oct, 11:41


የሰው መልኩ ልቡ ነው

አላህ ልብ ይስጠን 🤲

Yasin nuru's hadis

14 Oct, 08:04


قال رسول الله ﷺ :

اقرؤا سورة البقرة، فإن أخذها بركة، وتركها حسرة، ولا يستطيعها البطلة .
صحيح مسلم - ٨٠٤ -

البطلة : هم السحرة .

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

ሱራ አልበቀራን አንብቡ፣ እሷን መውሰድ በረካ ነው፣ እሷን መተው ፀፀት ነው፣ ሳሂሮችም(ጠንቋዮችም)  አይችሏትም።

ሳሂህ ሙስሊም - 804 -

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

13 Oct, 07:41


ሰው ለሚስቱ በ50 ሚሊዮን ዶላር ደሴት እየገዛ አንተ 50 ሺህ የወረቀት ብር መህር መክፈል ከበደኝ ትላለህ¡


ለአንዷ ደሴት መግዣ ብሎ ብር ከሚያባክን 3 አይጨምርበትም ነበር ወይ? የሚል አይጠፋም¡

Murad

@yasin_nuru_hadis

Yasin nuru's hadis

12 Oct, 06:03


ከዚህ በፊት ስለ ገንዘብ ፈተና እና ስለ ልጅ ፈተና አይተናል ። ሌላውና ትልቁ ፈተና ደግሞ "ሸህዋ" ነው ..

ዛሬ ዘመናችን እንደውም የሸህዋ አብዮት ዘመን ተብሎ ቢጠራ ማጋነን አይሆንም ። ለምን ብትሉ ሸህዋን ተንኳሽ ፣ ቀስቃሽ የሆኑ ነገራት በየቦታው ያጋጥማችኋል .. ሰው መቼስ አይኑን ጨፍኖ አይሄድም ።

ሁለት አይነት ሰዎች ይመጣሉ ፥ እኔ አላየኋቸውም .. አንደኛው እንደ ከብት ጂራት የሚመስል አለንጋ ይዘው ሰውን በአደባባይ የሚገርፉ ፣ የሚቀጠቅጡ ሰዎች ወደፊት ይመጣሉ አሉ .. ሁለተኛው ደግሞ የለበሱ ግን የተራቆቱ ሴቶች ፥ የጠመሙ ሌላውን የሚያጠሙ ፣ ራሳቸው እንደተዘነበሉ የግመል ሻኛዎች ያጋደለ የሆኑ ሴቶች ይመጣሉ አሉ ።

“የለበሱ እርቃኖች” የሚለው አገላለፅ ራሱ ይአጅባል .. በሰውነታቸው ላይ የሚያንጠላጥሉት ልብስ ዋጋው ሲታይ ውድ ዋጋ ነው የወጣው ፤ ስለዚህ እንደነሱ ድንቅ ልብስ ነው የለበሱት .. ግን እርቃን ናቸው (መሸፈን ያለበት የሰውነት አካል ስላልተሸፈነ) ደረት ተገልጦ .. እስከ ባት ድረስ ተሰብስቦ .. ከዚያም የተለያየ ነገር ተቀብቶ .. በሚገርም ሁኔታ ይሄን ሁሉ አድርገው ምናልባት ወንዱ ላያየን ይችላል ብለው ደግሞ ጫማቸው ላይ ሚስማር ሰክተው ቋ ቋ እያደረጉ ይሄዳሉ ። ተጋልጬ ወጣሁኝ አላየኸኝም ቆርቁሬ አሰማሃለሁ እያሉ ነው :) አዳምጥ ¡

ይሄንን ያየ ትዳር አልባ ወጣት ይፈተናል .. አንዳንዱ ግብዝ ራሱንም አታሎ ሌላውንም ለማታለል ይፈልግና ምን ይልሃል? እኔኮ ራሴን እቆጣጠራለሁ ፤ ነፍሴን አውቃታለሁ ይላል .. ነፍስን መቆጣጠር መከላከያውን አበጅቶ ነው ። ረሱል እንዳሉት ሴት አይቶ በጣም ከማረከችው ቶሎ ቤት ይመለስ .. እቤት ባለትዳር ስለሆነ ከባለቤቱ ጋር ተገቢውን ነገር በማድረግ ያንን መስበር ይቻላል ። ውጭ ያለውና ውስጥ ያለው አንድ አይነት ነገር ነው ። መመለሻ የሌለውስ .. ወደ ቤት ይመለስ አሉ .. ቤት ሲመለስ ምንም የለም :(

ይሄን ፈተና ማን ይቋቋመዋል እስኪ?!
"ዙይነ ሊናስ ሁቡሸሃዋት" ብሏል አሏህ .. ይሄኮ አብሮን የተፈጠረ ነገር ነው ። ብዙወቹ ሳያገቡ የሚኖሩ ሰዎች ራሳቸውንም አታለው ሰውንም ለማታለል እኛ እራሳችንን እንቆጣጠራለን ይላሉ ። እዚህ ቦታ ላይ ራስን መቆጣጠር ከባድ ነው ። አይን ያያል የሱን ስራ ጨረሰ እሱ ፣ አይንህ እንዳይቃብዝ ረሱል ምን አሉ «መን ኢስተጧዓ ሚንኩም አልባዓተ ፈልየተዘወጅ» ከናንተ የጋብቻውን ጣጣ መክፈል የቻለ ሰው ቶሎ ያግባ ። አይኑን ይሰብርለታል!
አይን መጨፈን የሚቻለው አይንን በመክደን አይደለም (ያ ከሆነ አትራመድማ) ይልቅ መከላከያውን በማበጀት ነው ።

አጠቃላይ የሰው ልጆችን ከፊሉን በከፊሉ ፈትኗል «ወጀአልና በዕዶኩም ሊበዕዲን ፊትና አተስቢሩን» ይላል ። ሴቷ በወንዱ፤ ወንዱ በሴቷ .. ሀብታሙ በድኻው ፣ ድኻው በሃብታሙ .. ጤነኛው በበሽተኛው ፣ በሽተኛው በጤነኛው እየተፈተነ ነው ። የሸህዋው የሚለው ጊዜ አይሰጥም ፣ እንደ እሳተ ጎመራ ድንገት ነው ። ራሴን እቆጣጠራለሁ ይል የነበረው ሰውዬ ይወድቃል ። ነብዩም “ዲናቸው ጎደሎ ፣ አቅላቸው ጎደሎ ግን የጠንካራን ልቦና ባለቤት የሚያሸንፉ እንደናንተ አላየሁም” አሉ ሴቶችን .. በጦር ሜዳ ማይበገረው ጀግና በሸህዋ ላይ ጠብ ብሎ ታየዋለህ .. ያዳግታል ፣ ይፈታተናል

@yasin_nuru_hadis
@yasin_nuru_hadis

8,529

subscribers

38

photos

212

videos