Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو @ustaz_yasin_nuru_chanal Channel on Telegram

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

@ustaz_yasin_nuru_chanal


Wel-come to the official channel of TG Ustaz Yasin Nuru.
🇵🇸 Free Palestine 🇵🇸
My FB channel is ☟︎︎︎ https://www.facebook.com/ustazYassinNuru?mibextid=ZbWKwL

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو (Amharic)

ለተከታታይ ተናጋሽ ከሆነ፣ በቴሌግራም የወላጅያስ ያስእያውን ስለመረጣቸው አስተዳደርን.
📹ብካባኣዊ እና ዀድቃ እንቃያለን፣ አምስተርኪሱን እና ወታደርቋ ቅማሉን እንገናኝ።
🇵🇸 ኮምፒ ፐለርሲን ከፍተኛ 🇵🇸
የእኔን ኦርቶጎፍ ሊካንኖክ ቻናል ያለባቸው መረጃዎች፣ ከፈለገ፣ ሊንክነክመንም አሳያቸው።
እታኮት እናመሰጋህ፣ ፍቅረውን በፓለለ ወሲብ ቘማጌ ☟︎︎︎ https://www.facebook.com/ustazYassinNuru?mibextid=ZbWKwL

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

01 Dec, 17:40


حرقوا النازحين في خيامهم !!!

ህመምተኞቻችንን አቃጠሉ 😭
የአሏህ ጋዛን.......🤲🤲🤲🤲

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

04 Nov, 04:33


تشريح جثة يحيى السنوار أظهر أنه لم يأكل شيئا خلال الـ 72 ساعة التي سبقت وفاته .

የያህያ አል-ሲንዋር የአስከሬን ምርመራ ከመሞቱ በፊት በነበሩት 72 ሰዓታት ውስጥ ምንም ነገር እንዳልበላ አሳይቷል።
😭😭😭😭😭😭😭😭

ሰው ደፋር ሲሆን ተኩላ ይባላል።
ሲበረታ አንበሳ ይባላል።
ሲምር ሰው ይባላል።
በእሱ ውስጥ ሁሉም ባህሪያት ሲጣመሩ, እሱ ያህያ ሲንዋር ይባላል ::

ጀነት የማግኘት መብት የተጎናፀፈ እውነተኛ ጀግና እና የህዝቡ ተከላካይ። በጀነት እንገናኝ ወንድማችን.🦁🦁💪💪🇵🇸🇵🇸🇵🇸

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

29 Oct, 17:56


ሙስሊም ተማሪዎች በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ...

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ ካለፋት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መኖሩን ማስተዋላቸውን ተናግረዋል።

ከፍተኛ ምክር ቤቱ ችግሩ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙበት ወረዳና ክፍለከተማ የመጅሊስ መዋቅሮች  አመራር አማካኝነት ችግሩን ለመፍታት ጥልቅ ውይይት በማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡በዚህም መሰረት ከተወሰኑ ት/ት ቤቶች ጋር በተደረገ ስምምነት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ነገር ግን ከቀናት በኋላ ከውይይቱ ስምምነት በመውጣት ተማሪዎችን ማስክ እንኳ ቢሆን አድርገው እንዳይገቡ መከልከላቸውን በደብዳቤው ላይ አስፍሯል፡፡

የአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ ባወጣው የተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ ክልከላ የሌለበት አለባበስ ስለመሆኑ ባደረግነው ውይይት የተማመንበት ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ኃላፊነት በጎደላቸው አመራሮች ምክንያት ችግር በሚፈጥር መልኩ እየተሄደበት ያለው አካሄድ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ያላግባብ እንዲታገዱ መደረጉና የስነ-ልቦና ጫና መፈጠሩ የየትኛውም ህግ ድጋፍ የሌለውና ህዝበ ሙስሊሙንና መንግስትን ለማጋጨት የሚደረግ ጥረት መሆኑን በመገንዘብ በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥና ተማሪዎቹም መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት እንዲካካስላቸው አጥብቀን እንጠይቃለን ማለቱን ከአዲስ አበባ መጅሊስ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

01 Oct, 21:12


ምንበሩን ማን ሰራው?

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

12 Sep, 11:18


ሰበር፡ የአሸባሪው የጽዮናውያን ወረራ የተባረከውን የአል-አቅሳ መስጊድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊያቃጥል እንደሆነ ዝተዎል።
እሄም ተንቀሳቃሽ ምስል በማጋራት "coming soon" በማለት ማንም ሊያስቆማቸው እንደማይችል ዝተዎል
الدعاء
ፍልስጢየም ውስጥ ለምገኙ ወንድሞቼ ዱዓ አድርጉ እንዳትተኙ !! 🤲

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

09 Sep, 03:28


"ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" የሚሉ ሙስሊሞችን ማየት በጣም ልብ የሚያደማ ነው።

ተመልከቱ ለዛፉ ሲሰግዱ! ተመልከቱ የሚሰሩትን። ሙስሊሙ ወንድሜ ሆይ! የብሄር አጀንዳ አቅልህን አስ፞ቶ ጀሀነም እንዳይከትህ ተጠንቀቅ። አላህን ፍራ!! መስቀልን የምንቃወመው የአማራ የወሎ የኦሮሞ ወዘተ ስለሆነ አይደለም። የኩፍር በአል ስለሆነ እንጂ። ኢሬቻ የኦሮሞ ስለሆነ በተለየ አይን አናየውም። የኩፍር ቡላና ዳለቻ የለውም። ሁሉም ኩፍር ነው። ሁሉም የጣኦት አምልኮ ነው። ሁሉም ተውሒድን በጥብቅ ከሚያስተምረው ኢስላም ጋር ፈፅሞ የሚፃረር ነው። ሁለቱም ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ የለየት ክህደት ነው።
ዛሬ የብሄር አጀንዳ እራሱን የቻለ ጣኦት ሆኗል። ሰዎች ለብሄር ሲሉ ካፊርን ይወዳሉ። ሙስሊምን ይጠላሉ። ለብሄር ሲሉ ለመስቀል፣ ለኢሬቻ ወግነው ይሟገታሉ። የኩፍር በአል ያከብራሉ።
የሚያሳፍረው ሸይኾችና ዱዓቶች ጭምር በዘረኝነት መለከፋቸው ነው። እስኪ የመስጂድ ኢማም ሆኖ፣ ጥምጣም ጠምጥሞ የኦርቶዶክስ ሰልፍ የሚያደምቅ፣ በዘራቸው የተነሳ ሙስሊም ትግሬዎችን ጭምር የሚያጥላላ፣ ለኢሬቻ "የእንኳን አደረሳችሁ" መልእክት የሚያስተላልፍን ልክፍተኛ አስቡ። ዘረኝነት አደዛዥ እፅ ነው። በዚህ በሽታ የተለከፈ ሰው እይታው ቁንፅል ነው። አርቆ ማሰብ አይችልም። ይህንን ሀሺሽ፣ ይህንን ጣኦት አጥብቀን ካልተዋጋነው ብዙ ነገር ያሳጣናል።
የያዝኩት ቪዲዮ ኢሬቻ የሚያከብሩ ሰዎችን ድርጊት ነው።

https://t.me/ustaz_yasin_nuru_chanal

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

08 Sep, 19:24


أسماء الجنة الاثنا عشر

استعرض ابن القيم في كتابه "حادي الأرواح في بلاد الأفراح" تحت عنوان: "الباب الحادي والعشرون في أسماء الجنة ومعانيها واشتقاقها" بقوله: الجنة لها عدة أسماء باعتبار صفاتها والجنة مسماها واحد باعتبار الذات فهي مترادفة من هذا الوجه وتختلف باعتبار الصفات، فهي متباينة من هذا الوجه، وهكذا أسماء الرب سبحانه وتعالى، وأسماء كتابه وأسماء رسله وأسماء اليوم الآخر وأسماء النار.

1- الجنة
وهو الاسم العام المتناول لتلك الدار وما اشتملت عليه من أنواع النعيم واللذة والبهجة والسرور وقرة الأعين واصل اشتقاق هذه اللفظة من الستر والتغطية ومنه الجنين لاستتاره في البطن والجان لاستتاره عن العيون والمجن لستره ووقايته الوجه والمجنون لاستتار عقله وتواريه عنه والجان وهي الحية الصغيرة الرقيقة.

2- دار السلام
وقد سماها الله بهذا الاسم في قوله: "لَهُمْ دَارُ السَّلَامِ عِندَ رَبِّهِمْ ۖ وَهُوَ وَلِيُّهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ (127)"، (الأنعام)، وقوله: "وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَىٰ دَارِ السَّلَامِ وَيَهْدِي مَن يَشَاءُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ (25)"، (يونس).
وهي أحق بهذا الاسم فإنها دار السلامة من كل بلية وآفة ومكروه، وهي دار الله واسمه سبحانه وتعالى السلام الذي سلمها وسلم اهلها "دَعْوَاهُمْ فِيهَا سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَتَحِيَّتُهُمْ فِيهَا سَلَامٌ ۚ وَآخِرُ دَعْوَاهُمْ أَنِ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ (10)"، (يونس)

3- دار الخلد
وسميت بذلك لأن أهلها لا يظعنون عنها أبدا كما قال تعالى: "وَأَمَّا الَّذِينَ سُعِدُوا فَفِي الْجَنَّةِ خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۖ عَطَاءً غَيْرَ مَجْذُوذٍ (108) "، (هود)

4- دار المقامة
قال تعالى حكاية عن أهلها: " الَّذِي أَحَلَّنَا دَارَ الْمُقَامَةِ مِن فَضْلِهِ لَا يَمَسُّنَا فِيهَا نَصَبٌ وَلَا يَمَسُّنَا فِيهَا لُغُوبٌ (35)"، (فاطر).

5- جنة المأوى
قال تعالى: "عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ (15)"، (النجم)، والمأوى مفعل من أوى يأوي إذا انضم إلى المكان وصار إليه واستقر به.

6- جنات عدن
إحدى الجنان والصحيح أنه اسم لجنة الجنان وكلها جنات عدن قال تعالى: "جَنَّاتِ عَدْنٍ الَّتِي وَعَدَ الرَّحْمَٰنُ عِبَادَهُ بِالْغَيْبِ ۚ إِنَّهُ كَانَ وَعْدُهُ مَأْتِيًّا (61)"، (مريم)

7- دار الحيوان
قال تعالى: "وَمَا هَٰذِهِ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا لَهْوٌ وَلَعِبٌ ۚ وَإِنَّ الدَّارَ الْآخِرَةَ لَهِيَ الْحَيَوَانُ ۚ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ (64)"، (العنكبوت)، والمراد الجنة عند أهل التفسير، قالوا وأن الآخرة يعني الجنة لهي الحيوان لهي دار الحياة التي لا موت فيها.

8- الفردوس
قال تعالى: "أُولَٰئِكَ هُمُ الْوَارِثُونَ (10) الَّذِينَ يَرِثُونَ الْفِرْدَوْسَ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ (11)"، (المؤمنون).
اسم يقال على جميع الجنة، ويقال على أفضلها وأعلاها كأنه أحق بهذا الاسم من غيره من الجنات. وأصل الفردوس البستان والفراديس البساتين.

9- جنات النعيم
قال تعالى: "إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتُ النَّعِيمِ (8)"، (لقمان)، وهذا أيضا اسم جامع لجميع الجنات لما تضمنته من الأنواع التي يتنعم بها من المأكول والمشروب والملبوس والصور والرائحة الطيبة والمنظر البهيج والمساكن الواسعة... وغير ذلك من النعيم الظاهر والباطن.

10- المقام الأمين
قال تعالى: "إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي مَقَامٍ أَمِينٍ (51)"، (الدخان)، والمقام الأمين موضع الإقامة، والأمين الآمن من كل سوء وآفة ومكروه وهو الذي قد جمع صفات الأمن كلها، فهو آمن من الزوال والخراب وأنواع النقص وأهله آمنون فيه من الخروج والنغص والنكد، والبلد الأمين الذي قد أمن من أهله فيه مما يخالف منه سواهم.
11–12 مقعد الصدق وقدم الصدق
قال تعالى: "إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَنَهَرٍ (54) فِي مَقْعَدِ صِدْقٍ عِندَ مَلِيكٍ مُّقْتَدِرٍ (55)"، (القمر). فسمى جنته مقعد صدق، لحصول كل ما يراد من المقعد الحسن فيها.
ومدخل الصدق ومخرج الصدق هو المدخل والمخرج الذي يكون صاحبه فيه ضامنا على الله وهو دخوله وخروجه بالله ولله وهذه الدعوة من أنفع الدعاء للعبد فإنه لا يزال داخلا في أمر وخارجا من أمر فمتى كان دخوله لله وبالله وخروجه كذلك كان قد أدخل مدخل صدق واخرج مخرج صدق... والله المستعان.

╭┈───────  ↷ ⇣🌹⇣↷ೄྀ࿐ 🇵🇸
╰┈➤𝐉𝐎𝐈𝐍:☞ https://t.me/ustaz_yasin_nuru_chanal

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

07 Sep, 04:42


◾️አጠር ያለች ምክር ለጧሊበል ዒልሞች!

➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩
ከጧሊበል ዒልም አደቦች መካከል አንዱ ባወቅከው ነገር ላይ መስራት ነው ይህንን አስመልክቶ አብዛኞቻችን የተዘናጋንበት ነጥብ ስለሆነ በትንሹ ወንድምና እህቶቼን ማስታወስ እፈልጋለሁ።

እንደሚታወቀው ዒልም በጣም ትልቅ ደረጃ እንዳለው ይታወቃል ይህን አስመልከቶ የመጡ ቁርአናዊ ና ሐዲሳዊ መረጃዎች በርካታ ናቸው።

ይህንም መሰረት በማድረግ ብዙ ዑለማዎች ስለ ዒልም ደረጃ በተለያየ መልኩ ገልፀዋል።

➭ ከነዚህም ውስጥ ኢማሙ ኢብኑ አል-ቀይም ረሒመሁሏህ
ስለ ዒልም ሲናገር እንዲህ ይላል
"የዒልም ሱራ ቢኖረው ኖሮ ከፀሀይ እና ጨረቃ ሱራ የበለጠ ያማረ ይሆን ነበር"

እናም ብዙ ወንድምና እህቶች ይህን በመረዳት አልሐምዱ ሊላህ ዒልም በመፈለግ ላይ እንገኛለን።
ነገር ግን የቀሰምነውን ዒልም ተግባር ጋር ካላቆራኘነው ምንም ጥቅም አይኖረውም።
ከዚህም አልፎ በሰዎች መመሳሰል ነው የሚሆነው በህዝቦች (በየሁዳ እና ነሷራ) የተመሳሰለ ደሞ ከእነሱው ነው ብለዋል። ነብያችን ዓለይሂ ሰላቱ ወሰላም እዚህ ጋር የፈለግኩበት የሁዳን ነው። ምክንያቱም የሁዳዎች ዒልም ኣላቸው ነገር ግን ስለማይሰሩበት ዒልም ከመኖራቸውም ጋር ጠማዋል ።
አላሁ ሱብሐነሁ ወተዓላ ሰረቱ አል-ጁሙዓህ ላይ እንዲህ ይላል
" مثل الذين حملوا التوراة ثم لم يحملوها كمثل الحمار يحمل أسفارا ... "
" እነዚያ ተውራትን የተጫኑ (የወረደላቸው) ከዚያም ተውራት በሚለው ነገር ያልሰሩ ሰዎች ምሳሌያቸው ብዙ መፅሀፍት እንዲሚሸከም አህያ አምሳያ ነው ..."

ተውራትን ያነባሉ ነገር ግን ወደ ተግባር ስላልቀየሩት አልጠቀማቸውም ። እኛን (ሙስሊሞችን) አስመልክቶ ደሞ
ተፍሲር ኢብኑ ከሲር ላይ ይህንን አንቀፅ ሲያብራራ ያመጣው ከኢብኑ ዓባስ ተይዞ የተወራ መርፉዕ የሆነ ሀዲስ አለ
ነብያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ " የጁሙዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ እያለ የተናገረ ሰው ብዙ መፅሀፎችን እንደተሸከመ አህያ ቢጤ ነው።" ምክንያቱም ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ማውራት ክልክል እንደሆነ እውቀቱ እያለው ነገር ግን አልሰራበትም

➧ እንዲሁም ስለ ዚክር ጠቀሜታ የተወሩ ብዙ መረጃዎች አሉ ከማወቃችን ጋር እስኪ ስንቶቻችን ነን ራሱን የቻለ ሰአት ሰጥተን ዚክር የምናደርገው አይደለም ራሱን የቻለ ሰአት ሰጥተን ትንሽ ሰአት ያለውን አዝካረ ሰባሕ ወል መሳእን ቋሚ በሆነ መልኩ የምናደርገው ራሳችንን እንፈትሽ !!

➼ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ከሱብሒ በኋላ አዝካረ ሰባሕ ማድረግ ነው የሚበልጠው ወይስ ቁርአን መቅራት ነው የሚበልጠው ተብለው ተጠይቀው እንዲህ ብለው መልሰዋል
" ቁርአን መቅሪያ ሰአቱ ሰፊ ስለሆነ የአዝካረ ሰባሕ ሰአት ደሞ ጠባብ ስለሆነ አዝካረ ሰባሕ ማድረጉ ይበልጣል ። "
ባወቅነው ነገር የምንሰራ ከሆነ የተማርነውን እውቀት የመርሳት እድሉ ጠባብ ነው የሚሆነው ስለዚህ ወንድም እና እህቶቼ እለት ተ እለት በምንማረው ነገር ለመስራት ቆርጠን መነሳት አለብን የሚል መልእክት አስተላልፍላቹሃለው።

╭┈─────── ↷ ⇣🌹⇣↷ೄྀ࿐ 🇵🇸
╰┈➤𝐉𝐎𝐈𝐍:☞ https://t.me/ustaz_yasin_nuru_chanal

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

05 Sep, 18:17


🧿በቅፅል ስማቸው እንጂ በዋናው ስማቸው በብዛት የማይታወቁ ስመ ጥር ዑለሞች በጥቂቱ :-

❶➤ኢብኑ ተይሚያህ =አህመድ አብዱልሀሊም

➋➤ኢብኑል ቀዪም =ሙሐመድ አቡበክር

❸➤ኢብኑ ረጀብ =አብዱራህማን አህመድ

➍➤ኢብኑ ሀዝም =አሊ አህመድ

❺➤ኢብኑ ሀጀር =አህመድ አሊ

❻➤ኢብኑ ከሲር =ኢስማዒል ዑመር

❼➤ኢብኑል ጀውዚይ =አብዱራህማን አሊ

ኢማም አል ቡኻሪ =ሙሐመድ ኢስማኢል

❽➤ኢማም አት-ቲርሚዚ =ሙሐመድ ኢሳ

❾➤ኢማም አን-ነሳዒ =አህመድ ሹዓይብ

❿➤ኢማም ኢብኑ ማጃህ =ሙሐመድ የዚድ

❶❶➤ኢማም አቡ ሀኒፋ =ኑዕማን ሳቢት

❶➋➤ኢማም አሽ-ሻፊዒ =ሙሐመድ ኢድሪስ

❶❸➤ኢማም አዝ-ዘሃቢ =ሙሐመድ አህመድ

❶➍➤ኢማም አስ-ሱዩጢ =አብዱራህማን አቡበክር

╭┈─────── ೄྀ࿐ 🇵🇸ˊˎ-
╰┈➤𝐉𝐎𝐈𝐍:☞ https://t.me/ustaz_yasin_nuru_chanal

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

31 Aug, 20:02


ሙስሊም ያልሆኑ ምሑራን ስለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ ዐ ወ)

ጆርጅ በርናርድ ሻው

ክፍል-0⃣2⃣
(የኖቤል እና የኦስካር ተሸላሚ እየርንዳዊ ጸሐፌ ተውኔት፣ ሐያሲ፣ ተከራካሪ እና በምዕራቡ ዓም በትያትር፣
በባሕል እና በፖለቲካ ዘርፍ ታላቅ ተጽእኖ ካሳረፉ እሠላሣዮች አንዱ)

‹‹የሙሐመድን ሃይማኖት ለድንቅ ጥንካሬው ሁልጊዜም ሳከብረው ቆይቻለሁ።

ለእኔ ከሃይማኖቶች ውስጥ የመቀየር/የመቀየጥ ኃይል ኖሮት ለተቀያያሪው የተፈጥሮ ዑደት በሁሉም ዘመን የሚያገለግል ብቸኛው ሃይማኖት ሆኖ ይታየኛል።

... (ሙሐመድን) አጥንቼዋለሁ - ድንቅ ሰው ነው።
በእኔ አመለካከት እሱ ‹ጸረ-ክርስቶስ, ሳይሆን የሰው ልጆች መድኅን ተብሎ ሊጠራ ይገባዋል።››

ክፍል ሦስት ይቀጥላል........................... ።

Collected Letters, 1926-1950 (1988), Dan H. Laurence, P. 305
╔════════════╗
🌕JOIN: shere shere shere🌙
https://t.me/ustaz_yasin_nuru_chanal
🌕JOIN: shere shere shere🌙      ╚════════════╝

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

30 Aug, 08:28


ሙሐመድ ﷺ በፍቅሩ ዓለምን የገዛው ነብይ
اللَّهُمَّ صل عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ
.
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

25 Aug, 15:43


ይህ የወራሪዋ ጦር መስጂዱን አፈራርሰው ቁርአኑን እየቀደዱ ሲያነዱት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ነው

የምናየው ልብን ያደማል የምንሰማው ይሰቀጥጣል። የጀግኖቹም ትዕይንት ያስደምማል የቀሳሞቹ ገድል ልብን በወኔ ይንጣል። የወራሪዋ ጭካኔ ልብን ያንዘፈዝፋል ቁርአኑን ቀደው ሲያነዱት ስታይ አይንህ ይቀላል።

በቀስተኞች ተራራ ላይ ካንተ በቀር ማንም ባይኖር እንኳ ቦታህን አትልቀቅ።
ሰዎች ስለ ጋዛ መፃፍ ቢያቆሙ ህመም ብሶታቸውን ጀግንነት ገድላቸውን መመዝገብ ያለብህ አንተ ብቻ እንደሆንክ እያሰብክ ስለ ጋዛ ጻፍ።

ሲስቁ አብረሀቸው ሳቅ ሲያለቅሱም እንዲሁ አብረህ አንባ። እርዳታውን የነፈጋቸው ሁሉ ፈተናውን ወድቋልና ሰበብ ማድረስህን ለአላህ አሳይ!

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

09 Aug, 04:32


የጋዛ ሸሂዶች ስም ዝርዝር በአሜሪካ

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

08 Aug, 15:37


ዕድለኛ ትውልድ ነን ።

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

27 Jul, 03:49


📝 ሙስሊም ያልሆኑ ምሑራን
ስለ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ ዐ ወ) ስናገሩ፡

✓ ሞሃንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ (መሃተመ ጋንዲ ) ይባላል::

(ሕንድን ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ ያወጣ የሠላማዊ ትግል መሪ)

ክፍል-0⃣1️⃣

‹... በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦችን ልብ በጭብጡ ውስጥ ስላስገባው ሰው ምርጥ
የሕይወት ቅጽበቶች ለማወቅ ፈለግኩ፡፡
… (አንብቤ ስጨርስ) በዚያ ወቅት በነበረው
የሕይወት ማእቀፍ ውስጥ ለእስልምና ቦታ ያስገኘለት የሰይፍ ኃይል እንዳልሆነ ከምንም
በላይ አመንኩ፡፡
ይልቁንም ቦታ ያስገኘለት የነቢዩ (ሙሐመድ) ቅልል ያለ እና በመተናነስ የተሞላ ሕይወት፣ እንከን የለሽ ቃል ኪዳን አከባሪነት፣ ለጓዶቹ ያሳየው
ፍጹም መሰጠት (አጋርነት)፣ የተስተዋለበት ታላቅ ወኔ እና ፍርሃት አልባነት፣ እንዲሁም
በአምላክ እና በተልእኮው ላይ የነበረው ጥልቅ መተማመን ነበር፡፡
(ትግሉን) ያስኬደለት እና በየመንገዱ ያገኘውን እንቅፋት ያስገበረለት ሰይፍ ሳይሆን እኒህ ባሕሪዎቹ ነበሩ፡:
(የነቢዩ /ሙሐመድ/ን የሕይወት ታሪh መጽሐፍ) ሁለተኛ ጥራዝ አንብቤ ጨርሼ
ስዘጋው ስለታላቅ ሕይወቱ ተጨማሪ የማነበው ነር ባለመኖሩ እያዘንኩ ነበር፡፡»
ያንግ ኢንዲያ – 1924

ክፍል ሁለት ይቀጥላል........................... ።

╭┈─────── ೄྀ࿐ 🇵🇸ˊˎ-
╰┈➤𝐉𝐎𝐈𝐍:☞ https://t.me/ustaz_yasin_nuru_chanal

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

05 Jul, 11:18


🛑 የጁምዓ ሰላት አንደ ረከዓ እና ሁለት ረከዓ ያገኘ ሰው እንዴት እንደሚሰግድ ያውቃሉ?


📌 ሶላቱል ጁምዓን በዑዝር ምክንያት መሳተፍ ያልቻሉ ሙሳፊር ያልኾኑ ሙስሊሞች፤ ሶላቱ-ዙህርን እንደተለመደው አራት ረከዓህ መስገድ ግዳጃቸው ነው፡፡ እንዲሁም ወደ ጁምዓ መስጂድ አርፍደው የመጡና፤ ከዚያም ኢማሙ ላይ ከሁለተኛው ረክዓህ ሩኩዕ መነሳት በኋላ የደረሱበት ሰዎች፤ ምንም ረክዓህ ስላላገኙ፤ የቀረውን የሱጁድ እና የተሸሁድ ስርአት ከኢማሙ ኋላ በመከተል ይሰግዱና፤ ኢማሙ ሲያሰላምት፤ እነሱ በመነሳት ባለ አራት ረከዓህ ሶላት (ዙህር) ይሰግዳሉ፡፡ ግን ኢማሙ በሁለተኛው ረክዓህ ሩኩዕ ላይ እያለ ከደረሱበትና እነሱም ያንን ሩኩዕ ኢማሙ ሳይነሳ በፊት ከደረሱበትና ሩኩዕ ካደረጉ አንድ ሙሉ ረክዓህ አግኝተዋልና፣ ኢማሙ ባሰላመተ ጊዜ፤ እነሱ ይነሱና የቀረውን አንድ ረክዓህ በመስገድ ያሰላምታሉ ማለት ነው፡፡ አንድን ሙሉ ረክዓህ ለማግኘት የመጨረሻው ጊዜ ኢማሙን ሩኩዕ ላይ እያለ መድረስና፤ ከሩኩዕ ቀና ሳይል እኛም አላሁ አክበር ብለን በቆምንበት ቦታ ከሐረምን በኋላ ወዲያው ሩኩዕ ማድረጋችን ነውና፡፡


ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ አንሁ) ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፡- "ከጁምዓ ሶላት አንድን ረክዓህ ያገኘ ሰው፤ የቀረውን ሌላ ረክዓህ ወደሱ ይጨምር፡፡ ሁለቱም ረክዓዎች ያመለጡት ሰው አራትን ረክዓህ ይስገድ" (አል-በይሀቂይ፡ ሱነኑል-ኩብራ 5531፣ ጦበራኒይ፡ አል-ሙዕጀሙል ከቢር 9545)፡፡

📌 ግለሰቡ የጁምዓ ሶላት ሁለቱም ረክዓዎች አምልጠውት ኢማሙ ከማሰላመቱ በፊት ቢደርስና፤ ከኋላቸው ነይቶ ቢቀመጥ፤ ኢማሙ ያሰላመተ ጊዜ እሱ ተነስቶ አራት ረክዓህ የሚሰግድ ከኾነ፤ መጀመሪያውኑ ነይቶ የሚቀመጠው ዙህርን ሶላት ነው ወይስ ጁምዓን? ለሚለው ጥያቄ፡- ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) የሰጡት ምላሽ፡- ግለሰቡ ሁለቱ ረክዓዎች አምልጠውት ኢማሙን በተሸሁድ ላይ ኾኖ ካገኘው፣ በዙህር ኒያ ከኢማሙ ጋር ተሸሁድ ይቀመጥና ኢማሙ ሲያሰላምት ተነስቶ አራት ይሰግዳል የሚል ነው፡፡ (አሽ-ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 4/160)፡፡

📌 የጁምዓ ቀን ሶላት (ሶላቱል ጁምዓ) ከበፊቱ የሚሰገድ (ሱንነቱል-ቀብሊያ) የለውም፡፡ ነገር ግን ከቤቱ ለጁምዓ ሶላት ተዘጋጅቶ መስጂድ የመጣ ሰው ኢማሙ ወደ ሚንበር እስኪወጣ ድረስ፤ አላህ ያገራለትን ያህል ሶላት መስገድ ይችላል፡፡ ይህ ሙጥለቅ (በመጠን ያልተገደበ የኾነ) የሱንና ሶላት ተብሎ ይጥጠራል፡፡ ከአዛን በኋላ ግን የሚሰገድ የኾነ የሱንና ሶላት የለውም፡፡ ሰልማኑል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አንድ ሙስሊም በጁምዓ ቀን ሰውነቱን የታጠበ ከኾነ፣ ጥሩ መዓዛ ባለው ቅባት የተቀባ ወይንም ሽቶን በልብሱ የነሰነሰ ኾኖ ወደ መስጂድ ኼዶ፤ በሁለት ሰዎች መሐል፤ በመሐላቸው በመለየት ሳይቀመጥ (ሳያስቸግር)፤ ከዚያም የተጻፈለትን (አላህ ያገራለትን ያህል) ከሰገደ፣ ኢማሙም መናገር ሲጀምር በዝምታ ካዳመጠ፤ ቀጣዩ ጁምዓ እስኪመጣ ድረስ በዚህ መሐል ያለው ኃጢአት ይማርለታል" (ቡኻሪይ 883)፡፡

📌 ጁምዓ ሶላት ከበኋላው የሚሰገድ የኾነ ሶላት (ሱነኑል በዕዲያ) አለው፡፡ ግለሰቡ እዛው መስጂዱ ውስጥ ከኾነ የሚሰግደው ባለ ሁለት ረክዓህ ሶላት ሁለት ጊዜ በመስገድ እስከ አራት ረክዓህ መስገድ ሲችል፤ በቤቱ መስገድ ከፈለገ ደግሞ ሁለት ረክዓህ ይሰግዳል ማለት ነው፡፡ ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከናንተ ውስጥ ከጁምዓህ በኋላ መስገድን የሚፈልግ ሰው አራት (ረክዓህ) ይስገድ" (ሙስሊም 2075)፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ሶላቱል ጁምዓን ከሰገደ በኋላ ወደቤቱ ሄደና ሁለት ረክዓህ ሶላትን ሰገደ፡፡ ከዚያም፡- ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ያደርጉ ነበር›› በማለት ተናገረ፡፡ (ሙስሊም 2076)፡፡

📌 በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባህ እያደረገ በዚህ መሐል መስጂድ የገባ የአላህ ባሪያ፤ መቀመጥን ከፈለገ ቅድሚያ ቀለል ያለ ሁለት ረክዓህ መስገድ ተገቢው ይኾናል፡፡ ሶላቱንም ቀለል እና ፈጠን በማድረግ፤ በቀሪው ጊዜ የኢማሙን ኹጥባህ ለመስማት መጓጓት አለበት፡፡ ምንም ሳይሰግድ መቀመጡ ሱንናን መቃረን ይኾንበታል፡፡ ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጁምዓ ቀን ለሰዎች ኹጥባ እያደረጉ አንድ ሰው ገባና (ተቀመጠ)፡፡ እሳቸውም ‹‹እንትና! ሰግደሀልን?›› አሉት፡፡ ሰውየውም፡- አልሰገድኩም! አለ፡፡ እሳቸውም፡- ተነስና ሁለት ረክዓህ ስገድ! በማለት አዘዙት" (ቡኻሪይ 930፣ ሙስሊም 2055)፡፡

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

05 Jul, 06:20


“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”

ረሱል (ﷺ)

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

04 Jul, 03:19


የካእባ ልብስ #ኪስዋ የአለማችን #ውዱ ልብስ 🕋

🕋 የልብሱ ክብደት 1000 ኪ .ግ የሚመዝን ሲሆን አጠቃላይ የካዕባን ልብስ ለማዘጋጀት #ከ20 ሚሊዮን ሪያል በላይ ይፈጃል።

🕋 ይህ የካዕባ ልብስ በንጉስ አብዱልአዚዝ ኮምፕሌክስ የሚዘጋጅ ሲሆን ኪስዋውን ለማዘጋጀትም 200ባለሞያዎች ይሳተፉበታል::

🕋 በአለም ረጅሙ እና ኮምፒውተራይዝ የሆነው የስፌት ማሽን ይህን የካዕባን ልብስ ለማዘጋጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን የስፌት ማሽኑም 16 ሜትር የሚረዝም ነው::

🕋 የካዕባ ልብስ ኪስዋ 670 ኪሎ የሚሆነው ጥቁር ሀር ሲሆን በሀሩ ላይ ለሚፃፈው የቁርኣን አንቀፆችም 120 ኪሎ 21ካራት #የወርቅ_ክር እና 100ኪሎ #የብር_ክር አገልግሎት ላይ ይውላል::

🕋 በልብሱ ላይ የሚፃፈው የቁርዓን አንቀፆችም በሰዎች እጅ በጥንቃቄ የሚጠለፍ ነው

🕋 የዘንድሮ አመት 1445 የካእባ ልብስ ኪስዋ የመቀየር ስነ ስርዓትም የፊታችን ቅዳሜ ሙሀረም 1 የሚከናወን ይሆናል ኘሮግራሙም በቀጥታ የቴሌቭዢን ስርጭት ይተላለፋል !!