✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖ @haymanoteabew Channel on Telegram

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

@haymanoteabew


ስለ ሐይማኖታችን እንወቅ


ያለንበት የማያልፍ የሚመስል መከራ ቢመስለንም
ትላንት ከሱ የባሰውን አልፈን ነው ዛሬን ያየነው
ትላንታችንን አንርሳ ! ሒወት የደስታና የሀዘን ናት
ሁለቱም ማለፋቸው አይቀርም በሚያልፉ ቀናቶች
መሀል የማያልፍ መዋደድን ይስጠን !!

ሁሌም እላለሁ ሃይማኖታችንን ልንጠብቅ ያስፈልጋል አምላከ ቅዱሳን
በቸርነቱ ይጠብቀን!

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖ (Amharic)

ሐይማኖተ አበዉ ከተማን ደግሞ የሚጠብቁ መከላከያዎችን በመልኩ አንዳንድ ሰዎች ወደ የሃይማኖት አበዉ ቤት አምላክ ቅዱሳን ይጠብቁን። ሃይማኖታችን እያላከ ያስፈልጋል አምላከ ቅዱሳን ለቸርነቱ እንዴት ተጠብቀን፣ በቸርነቱ ያሉ መኪናዎችን ያስፈልጋል። ሁሉንም መልኩ ልንጠብቅ በመግባት እንደተወደደ በተጠቃሚነት ለብርቱ ግንኙነቱ፣ በሀይማኖት አበዉ የተጋለጠ ሰው እንዲሆነ ድምፃችንን ለማስተማር ፡፡

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

01 Nov, 18:57


በቅርብ ቀን አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
ይጠብቁን
https://vm.tiktok.com/ZMhChDeTk/
#profile_picture
#add to_story
#timeline
#share
   #share
   #share

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

13 Oct, 15:14


ወዳጄ ሆይ!

ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ። ከአገሬ በቀር አገር የለም ፣ ከእናቴ በቀር እናት የለም ፣ ከእኔ በቀር ሰው የለም ፣ ከእገሌ በቀር አገልጋይ የለም አትበል። ጨርሶ መናገር ለዚህ ዓለም ነዋሪ ትዝብት ያተርፍለታል። በክረምት ለመዝራት ዝናቡን የተሰቀቁ የአጨዳ ዘመን የላቸውም። ሌላው ሲያለቅስ የሳቁ በኀዘናቸው አጋር አያገኙም። ካልገዛ በቀር ስጦታውን የሚያቃልል የእግዚአብሔርና የሰው ወዳጅ መሆን አይችልም። ፍላጎት መልካም ነው ፣ ከልክ ያለፈ መሻት ግን በቀን ሰላም ፣ በሌሊት እንቅልፍ የሚነሣ ነው።

ወዳጄ ሆይ !

ሲሰበክ እየተኛህ ፣ ሲወራ የምትነቃ ከሆነ አእምሮህን ጠላት እያደባበት ነውና በስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተዋጋ። የዛፍ የመጀመሪያ አካሉ ለስላሳ ነው። የመጀመሪያ ግንኙነትህም ዕድገት እንዲኖረው በመልካም ፍቅርና ትሕትና ወጥነው። ሀብታቸውን ሊያሳዩህ ለሚሹ እዘንላቸው። ከእነርሱ ይልቅ የሠሩት ቤት ዕድሜ አለውና። አንተም ተመክተህ ያለህን ለማሳየት በተነሣህ ቀን መጀመሪያ መቃብርህን ቆፍረህ ሂድ።

ወዳጄ ሆይ !

የታረሰ መሬት የዘር ሞትና ትንሣኤ ነው። የተከፈቱ ልቦችም የቃሉን ዘር ሲያገኙ እኔነትን ቀብረው ፣ አዲስ ሕይወትን ያወጣሉ። የግል ንግግርን አደባባይ ላይ አታውለው ። ስሜትህን ለማያውቁህ አታስነብበው። ጥረትህ ኪሣራ ቢያመጣም በዚህ ዓለም እስካለህ ጣር። የጉባዔ ታላቅነት የሚለካው በሰው ብዛት ሳይሆን በእግዚአብሔር መገኘት ፣ በታላላቆች መታደም ሳይሆን በእውነተኛ አምልኮ ነው። የሚወጥኑ ፣ የሚገነቡ ብቻ ሳይሆን የሚተቹም ያስፈልጉሃል። ተቺዎች በነጻ የሚያገለግሉህ የጥራትና ደረጃ ባለሙያዎች ናቸው። ችላ ተብለህ አድገህ ከሆነ ችላ የተባሉትን አስባቸው። የእምነት ሰዎች ሲወድቁ ብታይ በጣም አትፍረድ ፣ የመነሻውን ምሥጢርም ያውቁታልና። ያሉ የመሰሉ ነገር ግን የሌሉ ፣ የሌሉ የመሰሉ ነገር ግን ያሉ ብዙ ሰዎች ናቸው።

ወዳጄ ሆይ !

ሙሴን ሰው እንዳልቀበረው አስታውሰህ፣ ጌታችንን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ እንደገነዙት አስበህ ሞትህ ሰርግ እንዲመስል አትጓጓ። ክፉ ሰዎችን እየተመለከትህ ታዝናለህና ለሚመለከቱህ ኀዘን ላለመሆን ፈሪሀ እግዚአብሔር ይኑርህ። እግዚአብሔር ለሁሉም ጾታና ወገን ክብር እንዳለው አስብ። በወንዱም በሴቱም ላይ ይሠራልና ምሉዕ እግዚአብሔርን አታጥብበው። ሕይወቴ እግዚአብሔር ነው ማለት ቀርቶ ሕይወቴ ሌላ ነው የሚል ሰው ፣ ለመግደል የማይመለስ ጨካኝ ነው። አንተ የምታስፈልገው ለጠወለጉ ሰዎች ፣ ለተጎሳቆሉ ነፍሶች ነው። ቃላትህ የድምፅህ አቅም ከሞት የሚመልስ እንጂ ወደ ሞት የሚሰድድ አይሁን።

ወዳጄ ሆይ !

የጠነከሩ ልቦችን እንደ ወርቅ የሚያቀልጥ የፍቅር እሳት ነው። ልትደርስበት ያቃተህን ነገር ባዶ ነው ብለህ አትናቀው። ሲኖርህ ድሀን ካላሰብህ ሳይኖርህ ልታስብ አትችልም። ስለማንም ሰው ክፉም ደግም በእርግጠኝነት መናገር አትችልም። የመናገር ብቻ ሳይሆን የመኖር ድፍረትህ እግዚአብሔር ነው። አንድ የካደ ሰውን ስታሳምን የክርስቶስን መስቀል አገዝከው ማለት ነው። ንግግር ማብዛት በራስ ላይ ወጥመድ መታታት ነው።

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

22 Aug, 11:26


ጥር አርፋ በነሐሴ ወር ሁለት ሱባኤ ይዘው ሲጨርሱ በነሐሴ 14 መልአኩ ቅዱስ ሥጋዋን ከገነት አምጥቶ ሰጥቷቸው በጸሎትና በምሕላ ቀብረዋታል፡፡ በዚህ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም፡፡ በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ተነሥታ ስታርግ፣ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል፡፡ በዚህ ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው፣ ለእርሱ የቀረበት መስሎት አዝኖ ‹‹በፊት የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ፤ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ ከደመናው ለመውደቅ ተመኘ፡፡ በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አጽናናችው፡፡ ከእርሱ በቀር ትንሣኤዋን ሌላ እንዳላየ ነገራው ለምስክር እንዲሆነው ሰበኗን/መግነዝ ሰጥታው ዐረገች፡፡

ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ ክብርት እናቱ እመቤታችም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስና መቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጇ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷን ትንሣኤዋ ‹‹እንደ ልጅዋ ትንሣኤ›› ነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡

ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት፡፡ እርሱም ምስጢሩን ደብቆ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› አላቸው፡፡ ሐዋርያትም ‹‹አንተ ተጠራጣሪ ነህ›› ብለው መቃብሩን ሊያሳዩት ሲከፍቱ አጧት፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹እመቤታችን ተነሥታ አርጋለች›› ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው፡፡ ‹‹ለምስክር ይሁንህ›› ብላ የሰጠቸውንም ሰበኗን አሳያቸው፡፡ ሐዋርያትም ይህን አይተው ትንሣኤዋን አመኑ። ሰበኗን ቆራርጠው ለበረከት ተከፋፍለው ወደየሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል፡፡ ዛሬም በመጾር መስቀልና በካህናት እጅ መስቀላቸው ላይ የሚያስሯት ‹‹መሀረብ›› የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው፡፡ በዓመቱም ሐዋርያት ‹‹ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን!›› ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባኤ ገቡ፡፡ በነሐሴ 16 ቀንም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አሳርጎ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቅዳሴ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም የመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገቷን በዓይናቸው አይተውና በሚገባ ተረድተው ዓለምን ዙረው አስተምረዋል፡፡

በድጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለኃጥአን ሁሉ እጅግ እያዘነች ኖረችና አምላካችን ተወዳጅ ልጇ የሰጣትን ዘላለማዊ የድኅነት ቃልኪዳን ባሰብን ነፍሳችን ሀሴት ታደርጋለች፡፡ ቃልኪዳኗንም ዘወትር በማሰብ እንጽናናለን፡፡ ክብርት እመቤታችን አምላካችንን ተወዳጅ ልጇን "... በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ ከሲኦል ነጻ አድርገው፡፡ ከአንተ ጋራ የደረሰብኝን ረኀቡንና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ›› አለችው፡፡ ተወዳጅ ልጇ መድኃኔዓለም ክርስቶስም ‹‹ወላጅ እናቴ ሆይ! እንዳልሽው እንደወደድሽ ይሁንልሽ፡፡ ጣፋጭቱ ከመዓር ከሸንኮር የሚጥመው ንጹሕነቱ ከኤዶም ምንጭ ውኃ ንጣቱ ከበረዶና ከወተት የበለጠውን ወተት መግበው ባሳደጉኝ ጡቶችሽ ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ትእዛዜንና ሕጌን ባስተማሩ ዓስራ አምስቱ ነብያት፣ ሄሮድስ ባስገደላቸው ዓስራ አራት እልፍ የቤተልሔም ሕፃናት ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ የወንጌልን መንግሥት ለዓለም በሰበኩ ሐዋርያት፣ ስለእኔ ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፈው ስለሰጡ ሰባ ሁለቱ አርድእት ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ዙፋኔ በተዘጋጀባት ሉዓላዊት ሰማይ፣ የእግሬ መረገጫ በሆነች ታህታዊት ምድር ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ነደ እሳት በሆነ የእሳት ነጋረጃዬ ፍጹም ማደሪያዬ በሆነ በአርያም ሰማይ ቃል ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ በተሰቀልኩበት ዕፀ መስቀል፣ እጅና እግሬ በተቸነከረበት ቅኖት ችንካር፣ በጦር በተወጋው ጎኔ ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ በዕለተ ዓርብ በፈሰሰው ደሜ በሕመሜና በሞቴ፣ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊትም በከርሰ መቃብር ባደርኩበት ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ከመቃብር ወጥቼ አዳምን ከነልጆቹ ከሲኦል ለማውጣት ወደሲኦል በመውረዴ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቼ ሙስናን መቃብርን አጥፍቼ በመነሳቴ፣ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ በማረጌ ዳግመኛም ዓለምን ለማሳለፍ በታላቅ ምስጋና በምመጣበት ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ክቡር በሆነ ደሜ ቅዱስ በሆነ ሥጋዬ ቃልኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ብርክት እናቴ ድንግል ማርያም ሆይ! የሰጠሁሽም ቃልኪዳን እንዳይታበል አማንዬ ብዬ በራሴ ማልኩልሽ›› አላት፡፡
~~~~
እናቱን ለሁላችን ለምንታመንባት እናታችን አድርጎ ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን፣ በምልጃዋ ይማረን፡፡
~~~~
              
©በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

22 Aug, 11:26


ነሐሴ ፲፮

የብርሃን እናቱ የክብርት እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ በክብር ወደ ሰማይ ያረገበት ዕለት ነው፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ በሥጋ ከመሞቷ በፊት በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መቃብሩ ቦታ ትጸልይ ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስም ለእመቤታችን ከዚህ ዓለም እንደምትለይ ነገራት፡፡ ጌታችንም በደብረ ዘይት ላሉ ደናግላን ነግሯቸዋልና ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፍጥነት መጡ፡፡ እርሷም መንፈስ ቅዱስ የነገራትን ለእነርሱ ነገረቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን እንዲህ ብላ ጸለየች፡- ‹‹ልጄ ወዳጄ፣ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ልመናየን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም ሕያዋን የሆኑትን ሐዋርያትን ሁሉንም ነፍሶቻቸውን የለየሃቸውንም ሁሉ ወደ እኔ አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋን አምላክ ነህና ለአንተም ምስጋና ይሁን አሜን›› አለች፡፡

በዚያን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ ቅዱስ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ወደ እመቤታችን አደረሰችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በፊቷ ሰገደላትና እንዲህ አላት፡- ‹‹ሰላምታ ይገባሻል፣ ጌታችንን ፈጣሪያችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለድሽው ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ከዚህ ዓለም ተለይተሽ በክብር በምስጋና ወደ ዘለዓለም ሕይወት ትሄጃለሽና፡፡ ይህም ስሙ ክቡር ምስጉን የሆነ ጌታችንና ፈጣሪያችን ድንቅ ድንቅ ተአምራቶችን በአንቺ ላይ ከገለጠ በኋላ ነው›› አላት፡፡ እመቤታችንም ይህን በሰማች ጊዜ እጅግ ደስ አላት እግዚአብሔርንምእንዲህ ብላ አመሰገነችው፡- ‹‹ፈጣሪዬ ጌታዬ ላንተ ምስጋና ይሁን፣ የለመንኩህን ሰጥተኸኛልና፡፡ አሁንም ነብሴን ተቀብለው ወደ ሰማይ ወደ አንተ ሊይሳርጓት ከሚመጡ ቅዱሳን መላእክቶችህ ጋር በመምጣትህ የምለምንህን ሁሉ ስጠኝ›› አለችው፡፡ በዚያም ጊዜ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡- ‹‹እነሆ አሁን መላእክት ይደርሳሉ፡፡ ሐዋርያትም ሁሉ ከምድር ዳርቻ በደመና ተጭነው ለሰማይና ለምድር ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ወደሆነች ወደ ቅድስት ድንግል ይደርሳሉ፡፡ ወዲያውም ሁሉም ሐዋርያት የሞቱት ከመቃብራቸው ተነሥተው በሕይወት ያሉትም ሁሉም ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ ‹‹አምላካችን ከአንቺ የተወለደ ጸጋን የተመላሽ ሆይ! ደስ ይበልሽ፣ እርሱ ከዚህ ዓለም ለይቶ ቃል ኪዳን እንደሰጠሽ በክብር በምስጋና ከእርሱ ጋር ያሳርግሻልና›› አሏት፡፡

በዚያንም ጊዜ እመቤታችን በዐልጋዋ ላይ ተቀመጠችና ሐዋርያትን እንዲህ አለቻቸው፡- ፈጣሪዬ ፈጣሪያችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እንደሚመጣ እናንተንም እንዳየኋችሁ እንደማየው አሁን ዐወቅሁ፡፡ ከዚህ ከሥጋዬ ወጥቼ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እሄዳለሁ፡፡ ነገር ግን ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፣ እኔ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ዐወቃችሁ?›› ብላ የጠቀቻቸው፡፡ በመጀመሪያ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚያም ሁሉም ሐዋርያት ‹‹ወደ አንቺ እንመጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፣ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አሏት፡፡

እመቤታችንም ይህን ነገር ከሐዋርያት በሰማች ጊዜ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፡- ‹‹ጌታዬና ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈጽሜ አመሰግናለሁ፣ የእኔን የአገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ ኃይልን አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ወዲያ ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሰግኑኛል›› አለች፡፡ ጸሎቷንም ስትጨርስ ሐዋርያትን ‹‹ዕጣን አምጥታችሁ በማጠን የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ጥሩት›› አለቻቸው፡፡ እነሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ፡፡ በዚያም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክቱ አጅበው እያመሰገኑት መጣና እመቤታችንን አረጋጋት፡፡ ያዘጋጀላትንም ተድላ ደስታ ነገራት፡፡ በዚያም ጊዜ ድንቆቸ የሆኑ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ዓይነ ሥውራን ማየት ቻሉ፣ ደንቆሮች መስማት ቻሉ፣ ዲዳዎች ተናገሩ፣ ለምጻሞች ነጹ፣ ሐንካሶች መሄድ ቻሉ፣ ደዌ ያለበትም ሁሉ ዳነ፡፡ የብርሃን እናቱ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ወደ አለችበት ቤት በቀረቡ ጊዜ ከደዌአቸው ሁሉ ይፈወሳሉና፡፡

ከዚህም በኋላ እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ‹‹በአየር ውስጥ ተበትነው ከሚኖሩ ከሚያስነግጡ ግሩማን መላእክት የተነሣ ከእሳት ባሕርም የተነሣ እፈራለሁ›› ባለችው ጊዜ እርሱም ‹‹እናቴ ሆይ ከእነርሱ ለማንም በአንቺ ላይ ሥልጣን የለውም›› አላት፡፡ ከሥጋዋም የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሐዋርያትንና ደናግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኗት፡፡ እመቤታችንም እጇን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ጌታችን ቅድስት ንጽሕት ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሃን ልብስ አጎናጽፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከእርሱ ጋር አሳረጋት። ሥጋዋን ግን እንደሚገባ ገንዘው፤ ወደ ጌቴ ሰማኒ ተሸክመው እንዲወስዷ ሐዋርያትን አዘዛቸው፡፡ ነፍሷ ከሥጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር ብርሃን እያየች ነበር፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችንም ‹‹እንግዲህ ሥጋሽን ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት አፈልሳለሁ፡፡ ዳግመኛም ሥጋሽን ከነፍሽ ጋር አዋሕጄ አስነሥቼ መላእክት በፊትሽ ሆነው በሚያመሰግኑበት አምሳያ በሌለው ተድላ ደስታ ባለበት መኖሪያ አኖርሻለሁ›› አላት፡፡

እመቤታችንም እንዲህ አለች፡- ‹‹አቤቱ በረቀቀ ጥበብህ ይህን ሁሉ የሠራህ አመሰግንሃለሁ፤ ሁለተኛም ልመናየን ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ሁሉ፤ ልመናውን ተቀበለው በመከራም ውስጥ ሁኖ ስሜን ጠርቶ ወደ አንተ የሚለምነውን ከመከራም ሁሉ አድነው፤ በሰማይም በምድርም በሥራው ላይ ሁሉ አንተ ከሃሊ ነህና መታሰቢያየን በውስጧ የሚያደርጉባትን ቦታ ሁሉ ባርክ፣ በእኔ ስም የሚያቀርቡትን የሁሉንም መሥዋዕታቸውን ተቀበል›› አለችው፡፡ ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰላት፡- ‹‹የለመንሽኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ፤ ደስ ይበልሽ፣ ከእኔ ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ጸጋ ክብር ባለሟልነት ተሰጥቶሻልና ስምሽንም ጠርቶ የሚለምን ሁሉ በዚህ ዓለምም በወዲያኛው ዓለምም ከቶ አይጠፋም›› አላት፡፡ እመቤታችንም በታላቅ ክብር ካረፈች

ኋላ ጌታችን እንዳዘዘ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሊወስዷት ሐዋርይት ገንዘው ተሸከሟት፡፡ አይሁድም በሰሙ ጊዜ ሥጋዋን ሊይቃጥሉ ወጡ፡፡ ከእርሳቸውም አንዱ ከምድር ይጥላት ዘንድ የእመቤታችንን አልጋዋን ያዘ፡፡ ያን ጊዜም ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ መልአክ እጆቹን በእሳት ሰይፍ ቀጣውና እጆቹ በአልጋው ላይ ጠንጠለጠሉ፡፡ ያን ጊዜ በጌታችን አምኖ ወደ እመቤታችን እያለቀሰ እንዲህ ብሎ ለመነ፡- ‹‹የእውነተኛ አምላክ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ሆይ! አንቺ በእውነት ድንግል ይሆንሽ በእኔ ላይ ይቅርታ ታደርጊ ዘንድ አለምንሻለሁ፡፡›› በሐዋርይትም ልመና እጆቹ ተመልሰው እንደቀድሞው ደኅነኞች ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም እመቤታችንን በቀብሯት ጊዜ ከዚያ ሶስት ቀን ኖሩ፣ ዕረፍቷም የሆነው እሑድ ቀን ጥር ወር በ21 ቀን ነበረ፡፡ ጌታችንም ብርሃናውያን መላእክትን ላከ፣ እነርሱም ሥጋዋን ከመቃብር ወስደው በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር አኖሯት፡፡ በጌታችን ትእዛዝ መልአኩ የእመቤታችንን ቅዱስ ሥጋ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር በክብር አኑሮታል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት ዮሐንስ ከተመለሰ በኋላ ‹‹እመቤታችን እንደምን አለች?›› አሉት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም «ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች» አላቸው፡፡ እነርሱም ዮሐንስ ዐይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ፡፡

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

26 Jul, 08:33


#ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ (#ሐምሌ_19)

ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው። 

ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው። 

ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ። 

መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። 

በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 

ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው። 

ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። 

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። 

ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ ➛ ስንክሳር ዘተዋሕዶ

@haymanoteabew

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

03 May, 08:30


#ዓርብ /የስቅለት ዓርብ/፦
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥንተ ተፈጥሮ አዳምን በዕለተ ዓርብ ፈጥሮታል፤ ዳግመኛም በዕለተ ዓርብ ሊያድነው መሥዋዕት ሆኖለታል። ከዕለተ ሐሙስ ምሽቱ ሦስት ሰዓት እስከ ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ማኅበረ አይሁድ በጌታ ላይ መከራን አብዝተውበታል፡፡ ይህን አብነት በማድረግ አንድ ቆራቢ (የጌታን ሥጋና ደም ለመቀበል የተዘጋጀ) ሰው 18 ሰዓታት መጾም እነደሚገባው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች፤ ምክንያቱም ከሐሙስ ምሽት ሦስት ሰዓት እስከ ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ 18 ሰዓት ነውና። ክርስቶስም ሥጋውን በበላን ጊዜ ደሙንም በጠጣን ሰዓት መከራውንና ሞቱን ልናስብ ይገባል።
   ከሐሙስ ምሽት ሦስት ሰዓት እስከ ዓርብ መዓልት ስድስት ሰዓት ብዙ መከራና እንግልት አፈራርቀውበታል፡፡ ከዚያም ዓርብ ከቀኑ ስድስት ሰዓት በመስቀል ላይ ሰቅለውታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለበት ጊዜ ብዙ ገቢራትና ተአምራት ተፈጽመዋል፡፡ እነዚህም፦
- ፀሐይና ጨረቃ የፈጣሪቸውን ዕርቃን ላለማየት ብርሃናቸውን ከልክለው ደም ለብሰዋል።
- ከዋክብት ከሰማይ ረግፈዋል።
- የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፍሏል።
- መቃብራት ተከፍተው ሙታን ተነሥተዋል፤ (ማቴ 27፥45-52)።
   በመጨረሻም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሁሉ እንደተፈጸመ ተመልክቶ እናቱ ድንግል ማርያምን ታጽናናን ዘንድ በወንጌላዊው ዮሐንስ አማካኝነት ለእኛ ሰጥቶናል። ከዚያም ‹‹ሁሉ ተፈጸመ›› (ዮሐ 19፥30) በማለት ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በገዛ ፈቃዱ ለይቷል።
(በዕለተ ዓርብ በጌታ ላይ የተደረገበትን ግፍና መከራ በስፋት በመጽሐፈ ግብረ ሕማማት ላይ ያንብቡ)።
      ▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝  ▭▭▭ 

@haymanoteabew

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

02 May, 10:25


ምሴተ ሐሙስ እና ጉልባን

ጉልባን ከባቄላ ክክ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ እና ከሌሎችም የጥራጥሬ እህሎች ጥሬውን ተከክቶ እንደ ንፍሮ ተቀቅሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በዕለተ ሐሙስ የዕለቱ ሥርዓተ ጸሎት እና ስግደት አልቆ ቅዳሴው ተከናውኖ ከተፈጸመ በኋላ ምእመናን ወደ ቤታቸው ሄደው የሚመገቡት ነው  ይሄውም ስለ ሦስት ነገር ይደረጋል

፩ የኦሪትን ምሳሌ ለመፈጸም
እስራኤላውያ ከግብጽ ባርነት በዘጠኝ መቅሰፍት በአስረኛ ሞተ በኩር መውጣታቸውን እናሳታውሳለን በመጨረሻው ሞተ በኩር ግን ፈርኦን እነርሱን  ማስቀረት አልቻለም ነበር  እሥራኤላውያንም ተቻኩለው ሲወጡ በቤተ ያለውን እህል ያልተፈጨውን ንፍሮ ቀቅለው የተፈጨውን ቂጣ ጋግረው በልተው ነው ጉዞ የጀመሩት ፡፡ ይህንን በዓል ( ፋሲካን ) ሲያከብሩ በግ አርደው ያልቦካ ቂጣ ጋግረው ንፍሮ ቀቅለው ከባርነት በወጡ ዕለት የነበረውን ሁኔታ ያስቡ ዘንድ ታዘዋል ፡፡ዘዳ 13፡-1 
እኛም አስቀድሞ በሙሴ ላይ ህገ ኦሪትን የሠራ ህዝቡንም መርቶ ከነዓን ያስገባ እርሱ እግዚአብሔር የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ በሥጋዌ መገለጡን በማመንና ጌታ ራሱ አዲሱን ኪዳን  ከመሥራቱ አስቀድሞ  ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን እንዳከበረ ሁሉ  እኛም ሐዲስ ኪዳን የተመሰረተባትን ዕለት ስናስብ  ቀድሞ የነበረውንና ለሐዲስ ኪዳን ጥላ (ምሳሌ) የሆነውን ሥርዓት ለመታሰብያ እናደርጋለን፡፡
ሌላው እስራኤላውያን ጉልባን በልተው ግብጽን ተሰናብተው እንደወጡና ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደገቡ እኛም ከሰሙነ ሕማማት በኋላ የመከራውን ዘመን ተሰናብተን አማናዊውን ሥጋና ደም ተቀብለን ርስት መንግስተ ሰማያትን ለመውረሳችን ምሳሌ ነው ፡፡

፪ የሐዘን ሳምንት መሆኑን ለመግለጽ

እንደ ሀገራቸችን ባህል ንፍሮን  ዕንባ አድርቅ ይሉታል ብዙ ጊዜ ለለቀስተኞች ይዘጋጃል ምክንያቱም ሞት ተናግሮ አይመጣምና በድንገት ሲመጣ ለእንግዳ መሸኛ ቶሎ ሊደርስ የሚችል ምግብ ንፍሮ ስለሆነ ለለቅሶ ቤት ይሰራል ስለዚህ ክርስቲያኖችም በክርስቶስ ሞትና በድንግል ማርያም ኃዘን ምክንያት ኃዘንተኞች ስለሆንን  ይህንን ለማመልከት ጉልባን እናዘጋጃለን

፫ የጌታን መከራ እና ሕማም ለማሰብ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ብሎ ከተቀበላቸው ሕማማተ መስቀል መካከል አንዱ ሆምጣጤን መጠጣቱ ነው በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሰናል፡፡

@haymanoteabew

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

28 Apr, 11:55


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ሰንበት ያደረጋቸው ነገሮች የየራሳቸው ትንቢትና ምሳሌ አላቸው፤ አህያዋና ውርንጫዋ የሁለቱ ኪዳናት (የሐዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን) ምሳሌ ናቸው፡፡

አህያ የተመረጠችበት ምክንት
1. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ፡- ‹‹አንቺ የጽዮን ልጅ እጅግ ደስ ይበልሽ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ የሆነው ትሑትም ሆኖ በአህያዋ በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል›› (ዘካ 9፥9)፡፡
2. ትሕትናን ለማስተማር፡- አህያ በብዙዎች ዘንድ የተናቀች እንስሳ ነበረች፤ በአህያ መቀመጥም ራስን ማዋረድ ነውና ጌታም ትሕትናን ለማስተማር በተናቀችው አህያ ተቀምጧል፡፡ አንድም የዓለም ጥበብና ክብር በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነትና ውርደት መሆኑን ለማስረዳት ዓለም የሚያደንቃቸውን ትቶ ዓለም የናቀውን ተጠቅሞበታል፡፡
3. እኔ የሰላም አምላክ ነኝ ሲል፡- አህያ የሰላም ምሳሌ ነች፡፡ በጥንት ዘመን ነቢያት በአህያ ተቀምጠው የመጡ እንደሆነ መልካም የምሥራች ትንቢት ሊናገሩ መሆኑ ይታወቃል፤ በፈረስ ተቀምጠው ከመጡ ደግሞ ስለመቅሰፍት ወይም መአት ትንቢት እንደሚናገሩ ይታወቅ ነበርና፡፡
4. እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል፡- በአህያ ላይ የተቀመጠ ሰው ቢያሳድዱት አያመልጥምና ብትፈልጉኝ እኔ ቅርባችሁ ነኝ ታገኙኛላችሁ ሲለን ነው፤ (ኤር 23፥23)
5. በትሑት ሰው ልቦና አድሬ እኖራለሁ ሲል፡- አህያ ብዙ ጫንክብኝ፣ ጎዳኸኝ ብላ ሳታማርር ራሷን ዝቅ አድርጋ ባለቤቷን ታገለግላለችና እኔም ራሱን ዝቅ አድርጎ በሚገዛልኝ ትሑት ሰው ልብ አድሬ እኖራለሁ ሲል ነው፡፡
አህዮቹን ፈትታችሁ አምጡ ለምን አለ?
   አባታችን አዳም ከዲያብሎስ እስራት የሚፈታበት ጊዜ መድረሱን ለማመልከት ነው፤ አንድም ለደቀ መዛሙርቱ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን (ሥልጣነ ክህነት) መስጠቱን ለማጠየቅ ነው፤ (ማቴ 16፥18-19 ፣ ዮሐ 20፥22-23)፡፡
ሕፃናቱ ለምን አመሰገኑት?
   አስቀድሞ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ ለራስህ ምስጋና አዘጋጀህ›› (መዝ 8፥2) ብሎ የተናገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ይህ የመዝሙር ክፍል የዚህች ሰንበት ምስባክም ነው፡፡

ሕፃናቱ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት ምክንያት
ሀ. ዘንባባ በእስራኤል ባሕል የሰላም የደስታ ምልክት ስለሆነ፤ (ነህ 8፥14-15)
ለ. የዘንባባ የሚዋጋ እሾህ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው፤ ‹‹እግዚአብሔር ተዋጊ ነው›› ይላልና ዘጸ 14፥14፡፡
ሐ. ዘንባባ የመለኮት ምሳሌ ነው፤ ዘንባባ ቢደርቅ እንኳ በእሳት ይለበለባል እንጂ አይነድምና፡፡ የመለኮትንም ምጥቀቱንና ጥልቀቱን የሰው ኅሊና ሊመረምረው አይችልም፡፡
            ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጾምና ምጽዋት፣ ሰባቱ አጽዋማት
        ═══•꧁🌿🌿🌿꧂•═
@haymanoteabew

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

28 Apr, 09:06


🌿 #ሆሣዕና
  
ሆሣዕና ማለት አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ይህች ሰንበት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሲገባ የእስራኤል ሕዝብ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በማለት እየዘመሩ ያጀቡበት ዕለት መታሰቢያ ሰንበት ናት፡፡

ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ፋጌ በደረሰ ጊዜ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ልኮ የታሰረች አህያና ውርንጫዋን ይዘው እንዲመጡ አዘዛቸው፤ ካመጡለት በኋላም ጌታ ተቀመጠባቸው፤ ሕዝቡም ልብሳቸውን ሌሎችም ዘንባባን እየዘነጠፉ በመንገድ ላይ እያነጠፉ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ (ማቴ 21፥1-17)፡

@haymanoteabew

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

14 Apr, 05:17


ጥንዶች አንዳቸው ለሌላኛቸው የሚያደርሱት ጸሎት

በቅዱሱ ሐዋርያህ [በተወዳጅ] ጳውሎስ በኩል አንዳችን የሌላኛችንን ሸክም እንሸከም ዘንድ ያስተማርከን እግዚእነ ወአምላክነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ቅዱስ የኾነውን ትእዛዝህን እፈጽም ዘንድ፥ እንደ ምሕረትህ የሚስቴን ሸክም በ[መንፈሳዊት] ፍቅር መሸከም ይቻለኝ ዘንድ ጸጋህን አትንሳኝ፤ ትሰጠኝ ዘንድ እማልድሃለሁ! ፍጹምና ሰላምን የሚያጎናጽፍ ፍቅርህን ወደ እኛ በመላክም፣ በአንድ ልብ በአንድ አሳብ በመጠበቅም፣ በአሚን እንድንጸና በማድረግም ትዳራችንን ባርክልን። አንተ በምትሰጠው ደስታ ደስ እንድትሰኝና በነገሮች ኹሉ አንተን ደስ ማሰኘት ይቻላት ዘንድ በሚስቴ (የክርስትና ስሟ ጥቀስ) ላይ ፍቅርህን አሳድርባት። ለዘለዓለም ቅዱስ የኾነውንና አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተሰኘ [የሦስትነት] ስምህን በአንድነት ማክበር ማግነን ይቻለን ዘንድም ከጸብ ከክርክር ከፈተናም [ኹሉ] ጠብቀን፤ በሰላምና በአንድነት አጽናን፤ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ፥ አሜን!

@haymanoteabew

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

08 Mar, 17:03


ስንናደድ ለምን እንጮሃለን ?

አንድ ብልህ አረጋዊ አባት በገዳም የሚኖሩ ደቀ መዛሙርትን ሰብስበው እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው :-

" ስንናደድ ለምን እንጮሃለን ? ሰዎች ሲበሳጩ ስለምን እርስ በእርሳቸው ይጯጯሀሉ ?"

ደቀ መዛሙርቱ ለጥቂት ደቂቃ ዝም ብለው ካሰቡ በኋላ ከመካከላቸው አንዱ ተነስቶ እንዲህ ሲል መለሰ :-

" ስንናደድ መረጋጋት ስለሚያቅተን እንጮሀለን "

አረጋዊው አባትም ቀጠል አድርገው '' አብሮህ ያለው ሰው ከአጠገብህ ሆኖ ሳለ ታዲያ ስለምን ትጮህበታለህ ? በለሰለሰ ድምፅ መነጋገር የማይቻል ነገር ነውን ? ስትበሳጭ ስለምን ሌላኛው ሰው ላይ ትጮሀለህ ? "

ደቀ መዛሙርቱ በየተራ እየተነሱ የመሰላቸው ኹሉ መለሱ ። ነገር ግን አንዱም የደቀ መዛሙርቱ ምላሽ እኚህን ብልህ አረጋዊ አባት ስላላረካቸው የራሳቸውን ጥያቄ እንዲህ ሲሉ መለሱ:-

" ሁለት ሰዎች በሚበሳጬበት ሰዓት ልባቸው እጅግ ይራራቃል ይህን ርቀት ለመቀነስ እና ለመደማመጥ ደግሞ የግድ መጮህ አለባቸው ! አምርረው በተቆጡ መጠን በመካከላቸው ሰፊ መራራቅ ስለሚፈጠር ለመደማመጥ ይበልጡን መጮህ ግድ ይላቸዋል ።

አረጋዊው አባት ሌላ ጥያቄም አስከተሉ :-

"ሁለት ሰዎች ሲዋደዱስ ምን ይፈጠራል ? ይልቅ በለሰለሰ ድምፅ ያነጋገራሉ፡፡ ' ለምን ካላችሁኝ ምክንያቱ ልባቸው በጣም ስለሚቀራረብ ነው ! በመካከላቸው ያለው ርቀት ጥቂት ስለሚሆን እጅጉን እየተዋደዱ በመጡ ቁጥር ቃል ማውጣቱንም ትተው በሹክሹክታ ያወራሉ ። በመጨረሻም መንሾካሾክም ሳያስፈልጋቸው ዓይን ለዓይን በመተያየት ብቻ ይግባባሉ። እንዲህ ነው ሁለት የሚዋደዱ ሰዎች የሚቀራረቡት ።"

" በምትከራከሩ ጊዜ ልባችሁ እንዲራራቅ አትፍቀዱለት ፣ ይበልጥ የሚያራርቃችሁንም ቃላት አትጠቀሙ !ምክንያቱም አንድ ቀን በመካከላችሁ ያለው ርቀት እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ዞሮ መመለሻው መንገድ ይጠፋባችኋል ! "

" ፍቅር ልብን የተረጋጋ እና ሕይወትን የሚሰጥ ሲያደርገው በአንጻሩ ጥላቻ ደግሞ የተረበሸ ያደርገዋል በዚህም ሌላውን የሚጠሉ ራሳቸውን ያሰቃያሉ ! ከፍቅር በላይ ምን ጣፋጭ ነገር አለ ? "
"ለእኛ ያለህ የማይቋረጥ ፍቅርህ ከአባትም፣ ከእናትም ፣ ከሚስት እና ከባልም የሚበልጥ አቤቱ ፍቅር የሌለን ባሪያዎችህን ማረን አሜን !!! "

ምንጭ :- አባ ዮሐንስ ክሮንስታት የተባሉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባት እንደጻፉት

@haymanoteabew

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

24 Aug, 05:53


" በጌጠኛው ቤት ልማት ይሁን " መዝ 122፥7

ብጹዓን አባቶች የሚታደሙበት የህንጻ ቤተክርስቲያን ምርቃት  ።

እንደ ቸሩ አባታችን መድኃኔዓለም መልካም ፈቃድ በደብራችን አስተዳዳሪ ሊቀ ጉባዔ አባ ህሩይ ደስታና እና በሰበካ ጉባኤ ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት  ቅዱስ ፓትርያሪኩና አቡነ ማቴዎስ ፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳሳ አቡነ ሄኖክ እንዲሁም ሌሎች ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በታደሙበት ነሐሴ 26  የህንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናውኖ ነሐሴ  ሰ 27  በደብሩ የሚገኙት ታቦታት በአንደነት ከብረው  ከጊዜያዊ ማረፊያ መቃኞ ወደ ቀደ መንበረ ክብራቸው የሚመለሱበት ልዩ በዓል ።

ቤተሰብ ፣ ዘመድ አዝማድና ጓደኛችሁን ጋብዛችሁ ልትገኙበት የሚገባ ልዩ ዕለታታ ስለሆነ በበዓሉ ዕለታት እንድትታደሙ እና የበረከቱ ተሳታፊ እንድት ሆኑ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን ፡

በእዚህ ታሪካዊ እና የበረከት ቀን ከመድኃኔዓለም ደጅ ማን ይቀራል  ?

#ኑ_አብሩን_ታቦታቱን_እናጅብ
#ኑ_አብረን_እንባረክ
#ኑ_የመቅደስ_መታደስ_በዓላችንን_እናክብር

 
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝  ▭▭▭
🔎ፌስቡክ ገፅ https://www.facebook.com/finotebrhans
@finote brhan
🔎ዩቲዩብ ገፅ፡ https://youtube.com/channel/
@finote brhan
🔎 ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@
@finotebrhan
🔎ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡ https://t.me/finottebirhan

@finotebrhan

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

15 Apr, 07:07


#ቀዳሜ_ስዑር /ቅዳሜ/


ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሄዱትን እና በክንፍ የሚበሩትን በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈበት ዕለት ነች፡፡

ይህች የመጀመሪያው ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት እግዚአብሔርን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ ስላረፈበት ሰንበት ዐባይ /ታላቋ ሰንበት/ ትባላለች ታላቋን ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል፡፡ ዘፍ.1፡3፡፡

#‎ዕለተ_ቀዳሚት  /ሰንበት ዐባይ/


👉በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ ተከናውኖባታል፡፡ ጥንት ሥነ ፈጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንደ ተደረገባት ሁሉ የፍጥረት ሁሉ ቁንጮ የሆነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው ቸሩ አምላክ በመቃብር አርፎባታል፡፡ ማቴ.27፡61፡፡

👉በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሜ ስዑር » ትሰኛለች፡፡ ስዑር ቀዳሜ የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ምትጾም ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱ በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታልከቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን በመጾምና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡

👉በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት ጀምረው እስከ ስቅለተ ዓርብ ድረስ በስግደት እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቅዳሜ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ «ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፡-

#በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ» የምሥራች እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምእመናን ቄጠማ ይታደላል ቄጠማው የምሥራች ምልክት ነው፡፡


#ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖህ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ሆነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ዘፍ.9-1-29፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል፡፡


«  #‎ቄጠማ »፣

👉ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደሆነ አሁንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የሆነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡


👉የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሚያቃጥለው ዋዕየ ሲኦል /የሲኦል ቃጠሎ/ ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው መመለሳቸውን በዚህ አኳሃን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ

@haymanoteabew

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

14 Apr, 10:57


የ6 ሰዓት ንባብና ፀሎት🙏🙏

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

14 Apr, 10:57


የ 6 ሰዓት ንባብ እና ፀሎት🙏🙏

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

14 Apr, 10:54


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

14 Apr, 10:52


🙏🙏🙏

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

14 Apr, 09:30


በእለተ አርብ ሚደገም መዝሙረ ዳዊት ክፍል

✞ ሐይማኖተ አበዉ ✞❖

14 Apr, 09:18


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

2,929

subscribers

153

photos

6

videos