🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹 @south_wllo_zone_education_dept Channel on Telegram

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

@south_wllo_zone_education_dept

🇪🇹SWE "ይህ የቴሌግራም ቻናል በደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የሚከናወኑ ሁነቶችን የምናሥተዋውቅበት ገጽ ነው። ተቀላቀሉን አብረን እንሠራለን እንማማራለን ለችግሮቻችን አብረን መፍትሔ እንፈልጋለን::" 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹 (Amharic)

የ🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹 ቻናል የተማሪዎች ወሽብ ትምህርት መከታተያ አቅም ነው። ይህ ከቴሌግራም በደቡብ ወሎ ዞን የእንስሳ መምሪያ የሚከናወኑ የቻናሎችን እድሜዎችን የመፍታታዊ ድምፅ ለማግኘት ለመፍታተን መመልከት እንችላለን ። እኛም እናስተዋላለን እናመከብራለን እናማረጋጋለን ለዓለም ላይ መከታተያ ይሁን። የ🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹 ቻናል እናመሰግናለን የቻናሎችን መቆያ ከሆነ ጠበቆዎቹን የመገናኛ ችግር በማስመልከት ለእርስዎ ሰዎች መብት እናስፈትላለን ።

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

06 Jan, 18:42

እንኳን ለጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል አደረሳችሁ!!
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የትምህርት ባለሙያዎች፣ የትምህርት አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና የትምህርት ማህበረሰብ በሙሉ  እንኳን ለ2017 ዓ.ም ለጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የአብሮነትና አንድነት በዓል እንዲሆን ይመኛል።

   መልካም የገና በዓል!!

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

02 Jan, 07:39

ውድ መምህራን
መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ
https://forms.gle/NTMzLQK6pohUpvkq6

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

28 Dec, 03:27

ተስፋችንን አታጨልሙብን

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ርቀዋል። ይህን ተከትሎም ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠዋል።

ትምህርት ቤቶችም በጦርነቱ ምክኒያት መጎዳታቸው፣ መምህራን ላይ የተለያዩ ጫናዎች መድረሱ እና መሠል ችግሮችም አሳሳቢ ኾነዋል።

"ማን ይናገር የነበረ፤ ማን ያርዳ የቀበረ"ነውና ብሂሉ በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር በለሳ ወረዳ ጓኋላ ከተማ የምትኖረው የ16 ዓመቷ ታዳጊ ስለጉዳዩ ለአሚኮ ሃሳቧን ሰጥታለች።

በ2015 የትምህርት ዘመን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነበረች። እንደ ክልል ያጋጠመው የጸጥታ ችግር ወላጅ አባቷን በሞት አሳጥቷታል።

የአባቷን ሞት ተከትሎም የእርሻ በሬዎቻቸው ቀንበር ፈቱ። ያ ባቄላ፣ ጤፍ እና ማሽላ ይመረትበት የነበረው የእርሻ መሬት ጦም አደረ። ህይወት ለእርሷ እና ለቤተሰቧ ፈታኝ ኾነ።

በአካባቢው በገጠመው ግጭት ምክንያትም በበለሳ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ያስታዎሰችው ተማሪዋ ጦርነቱ ቤተሰባቸው ላይ ያሳረፈው በትር ድርብ ኾነ።

ወላጅ እናቷም የበኩር ልጃቸው ቤተሰቡ የገጠመውን ክፉ ቀን እንድታሳልፍላቸው ፈረዱባት እና ከሰው ቤት አስገቧት።

ሌላው ባለታሪካችን በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በጭስ ዓባይ ዙሪያ የድንጋይ ደባሎ ቀበሌ ነዋሪ ነው።

በሰላም እጦት ይማርበት የነበረው ትምህርት ቤት በመዘጋቱ አሁን ላይ የዘጠነኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጦ ከብት እየጠበቀ እና የእርሻ ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

ጠንክሬ በመማር ሳይንቲስት የመኾን ራዕይ ነበረኝ የሚለው ይህ ተማሪ ግጭቱ ከልጅነት ሕልሙን እንዳያሳካ እንቅፋት እየኾነብኝ ነው አለን።

ሌላዋ ባለታሪካችን በሰሜን ጎጃም ዞን የደቡብ አቸፈር ነዋሪ ናት። ባለታሪካችን በ2015 የትምህርት ዘመን የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን በመውሰድ ጥሩ ውጤት በማምጣት ወደ ዘጠነኛ ክፍል አልፋለች።

"ሳይንቲስት"የመኾን ራዕይ አላት። ይሁን እና በአካባቢው የተከሰተው ግጭት ለመማር ጉጉ የኾኑ ተማሪዎችን ሕይዎት ተስፋ ማደብዘዙን ነው ተማሪዋ የምትናገረው።

ግጭቱ ጠንክሮ ትምህርት ቤት እንደማይከፈት የተረዱት አክስቷ ወላጆቿን አስፈቅደው ወደ ባሕር ዳር ከተማ ወሰዷት። ጣና ሐይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ገባች።

በ2016 የትምህርት ዘመንም ጉብዝናዋን አስቀጥላ በመማር ከ53 ተማሪዎች ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ወደ 10ኛ ክፍል አለፈች።

"በቅርቡ ወደ ትውልድ ቀዬዬ ደውየ ነበር" የምትለው ባለታሪካችን "ስለእነዚያ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ደስ የሚል ዜና አልሰማሁም።

አንዷ የደብተር ቦርሣ በመያዥያ ጀርባዋ ልጅ ማዘሏን ሰምቻለሁ። ሌሎቹ እንዲኹ መማርን ቢሹም የሰላም እጦቱ ተስፋቸውን አጨልሞታል" ብላለች።

የኾነው ኾኖ ግጭቱ በሰላም ተፈትቶ የተማሪዎች የነገ ተስፋ ላይ የተጋረጠው ችግር እንዲቀረፍም ጠይቃለች።

በሰሜን ጎጃም ዞን የይነሳ ሦሥቱ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት የተማሪ ወላጅ አሁን በአካባበቢያቸው አንጻራዊ ሰላም መኖሩን መስክረዋል።

"መምህራንም ወደ ትምህርት ቤት እየመጡ ነው፤ ነገር ግን ወላጆች የልጆቻቸውን ጉልበት ለሰብል ሥብሠባ ስለሚፈልጉ ግጭቱን አሳበው ተማሪዎችን አስቀርተዋቸዋል" ብለዋል።

"እኔ በበኩሌ ለማስተማር ዝግጁ ነኝ። ሌሎችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ አለባቸው ነው ያሉት።

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

28 Dec, 03:27

“ሕዝቡ ልጆቼ እንዳይማሩ የሚከለክል ሁሉ ጠላቴ ነው ሊል ይገባል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ኾነዋል፡፡ ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታ ውጭ የኾኑ ለቀናት፣ ለሳምንታት እና ለወራት ብቻ አይደለም ለዓመታት ኾኗል እንጂ፡፡

በልጆቻቸው ተስፋ ያደረጉ ወላጆች የተስፋቸውን ፍሬ በዘመኑ እንዳይበሉ እንቅፋት ኾኗል፡፡ ነገን ለማሳመር ተስፋ የሰነቁ ልጆች ያለ በደላቸው ከዕድሜያቸው ላይ ተሠርቀዋል፡፡

ከእኩዮቻቸው ጋር እንዳይወዳደሩ ኾነዋል፡፡ ከትምህርት ርቀው በቁዘማ እንዲኖሩ ተገድደዋል፡፡

ሕጻናት የመማር መብታቸውን ተነፍገዋል፡፡ በትምህርት ቤቶቻቸው እንዳይንቀሳቀሱ ገደብ ተጥሎባቸዋል፡፡ መምህራን ሠርተው እንዳይኖሩ ተደርገዋል፡፡

እናስተምራለን ባሉ መገፋት ደርሶባቸዋል፡፡ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የሚልኩ ወላጆች የግድያ ዛቻ ደርሶባቸዋል፡፡

ከአሚኮ ወቅታዊ ጋር ቆይታ ያደረጉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የመማር መብት መጣስ ከሕጻናት መብት ጥሰት ጋር ይያያዛል ነው የሚሉት፡፡

የነገዋን ኢትዮጵያን ለማሳመር የዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ግድ ይለናል፤ ዛሬ የሚገነባው ትውልድ የነገውን የኢትዮጵያ ገጽታ የሚያንጸባርቅ ነው ይላሉ፡፡

በአማራ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ሕጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ አድርጓል፡፡ በ2017 የትምህርት ዘመን ሰባት ሚሊዮን ተማሪዎችን እናስተምራለን ብለን አቅደን አፈጻጸማችን ዝቅተኛ ነው ይላሉ፡፡

ለትምህርት ዘመኑ ከወረሐ ነሐሴ/2016 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች እንዲመዘገቡ ጥረት ቢደረግም በሚፈለገው ልክ አልኾነም ነው የሚሉት፡፡ በጸጥታው ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ርቀዋል፡፡

ትምህርት ቤቶችም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከትምህርት ገበታ ርቀው የቆዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት እንዲመጡ ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

በዘመናት መካከል፣ በተለያዩ ሀገራት እና ፖለቲከኞች የፖለቲካ ልዩነት ይኖራል የሚሉት ኀላፊዋ ትምህርትን ግን ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ እና ትውልድን መጉዳት የተገባ አይደለም ነው የሚሉት፡፡

በግጭቱ ምክንያት ተማሪዎች እና መምህራን በሥነ ልቦና ተጎድተዋል ነው ያሉት፡፡ ዕድሜያቸው ባክኗልም ብለዋል፡፡

ልጆችን ከትምህርት ቤት ማስቀረት ሚሳኤል ከመወርወር ያልተናነሰ ጥቃት ነው፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ሁሉም ሊያግዝ ይገባዋል ነው የሚሉት፡፡

እታገላለሁ የሚሉ አካላትም የሚታገሉት ለሕዝብ ከኾነ ሕጻናትን ያለ ሐጥያታቸው ጨለማ ውስጥ እንዲኖሩ መፍረድ የለባቸውም ነው ያሉት፡፡ በሕጻናት ሕይዎት ላይ መቀለድ የተገባ አይደለም ብለዋል፡፡

ሕጻናትን ከትምህርት ቤት አስቀርቶ መታገል ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የማይመጥን የትግል ስልት መኾኑንም አንስተዋል፡፡ የትምህርት ተቋማትን ከመዝጋት እና ተማሪዎች እንዳይማሩ ከማድረግ የበለጠ ጥፋት የለም ነው ያሉት፡፡

የትኛውም አካል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚያደርገውን አካሄድ በቃህ ሊለው ይገባልም ብለዋል፡፡

“ሕዝቡ ልጆቼ እንዳይማሩ የሚከለክል ሁሉ ጠላቴ ነው ሊል ይገባል” ነው ያሉት፡፡ ሕዝቡ በትምህርት ጉዳይ የሚመጣበትን በቃህ ሊለው ይገባል፤ ትምህርት ቤቶችን መጠበቅም አለበት ብለዋል፡፡

አንዳንድ አካባቢዎች ላይ እንሞታለን እንጂ ድጋሜ ልጆቻችን ከትምህርት ገበታ ውጭ አይኾኑም እያሉ መኾናቸውንም አንስተዋል፡፡ ሁሉም ኅብረተሰብ በዚህ ልክ በቃችሁ ሊል ይገባል ነው ያሉት፡፡

ተማሪዎችን እናስተምር ያሉ መምህራን ችግር እንደደረሰባቸውም አንስተዋል፡፡ መምህር ራሱን እንደሻማ እያበራ ለሌሎች ሕይዎት የሚኖር ነው ብለዋል፡፡

ኅብረተሰቡ መምህራንን መጠበቅ እንደሚገባውም አመላክተዋል፡፡ ያለፈው ዓመት ይበቃል ዘንድሮ ተማሪዎች ሳይማሩ እንዲከርሙ መፍቀድ አይገባም ነው ያሉት፡፡

በትምህርት ላይ የሚደርስ ጉዳት በትውልድ ላይ ክፍተት የሚፈጥር መኾኑንም አንስተዋል፡፡ የትምህርት ስብራት የትውልድ ሥብራትን ይፈጥራል፤ ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ የኾኑበትን መንገድ በቃ ሊሉ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ታጣቂ ኀይሎች መጠለያ ያደረጓቸው በርካታ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንም አስታውቀዋል፡፡ የትኛውም አካል በቃችሁ ብሎ ሊነሳ ይገባል ብለዋል፡፡

የሰበዓዊ መብት ተሟጋቾች በለሆሳስ ከመጻፍ ባለፈ በአደባባይ ወጥተው ማውገዝ አለባቸው ነው ያሉት፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት ሁሉም ማገዝ እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡

ትምህርትን መደገፍ ትውልድን መደገፍ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ መሥራት መኾኑንም አመላክተዋል፡፡

ታህሳስ 18/2017_ባህርዳር

አሚኮ

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

27 Dec, 06:19

ለ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል በሄራዊ ፈተና ለሚወስዱ የግል ተፈታኞች የተላለፈ መልእክት
==========
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለሚወስዱ የግል ተፈታኞች መመዝገቢያ መተግበሪያ ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች ዝግጁ መሆኑን ሀገር አቀፍ የፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት አሳውቋል፡፡በመሆኑም የመመዝገቢያ መተግበሪያውን register.eaes.et በመጠቀም እንድትመዘገቡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

26 Dec, 12:51

https://t.me/ab12_ef

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

26 Dec, 12:46

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

20 Dec, 19:01

https://selectacademy.edu.et/
መማሪያ መጻሕፍት እና የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናዎች በጥራትና በብዛት ያካተተ እንድሁም በርካታ አጋዥ ማጣቀሻ መጻሕፍት የተጫኑበት አድራሻ ስለሆነ ይጠቀሙበት

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

17 Dec, 07:26

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከዚህ በታች በተገለፁት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ብቁ የሆኑ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ

• አመልካቾች ከታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አስፈላጊ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ፣
- በአዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ እናት ህንፃ አጠገብ በሚገኘው የተቋሙ ቢሮ፣
- በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣
- እንዲሁም በሁሉም ክልሎች የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
• ስራ ልምድ ለሚጠይቁ የሥራ መደቦች አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• ዜሮ ዓመት ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ለሚጠይቁ ስራ መደቦች ላይ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም የዩኒቨርስቲ መመረቂያ ውጤት ለወንድ 2.5 እና ለሴት 2.00 መሆን አለበት፣
• የትምህርት ደረጃ /Level/ ለሚጠይቁ ስራ መደቦች የCOC ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
• ዜሮ ዓመት ለሚጠይቁ ስራ መደቦች ላይ የሚያመለክቱ ተወዳደሪዎች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁ መሆን አለባቸው፣
• መስፈርቱን አሟልተው ለሚመረጡ ተወዳዳሪዎች ተቋሙ የሚሰጠውን ስልጠና ለመውሰድ ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል፣
• ዜሮ ዓመት ለሚጠይቁ ስራ መደቦች ዕድሜያቸው 35 ዓመት እና ከዚያ በታች ሆነው የ8ኛ ክፍል የት/ት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
• ተቋሙ በሚመድባቸው የትኛውም ስራ ቦታ ላይ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ፣
• የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቋንቋ ክህሎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ፣
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፣
• መሠረታዊ የኮምፒዩተር ክህሎት (Basic computer skill) ያላቸው ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ፣
• ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ማስታወቂያውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ሊሰርዝው ይችላል፣

ዝርዝሩን በድረ ገፃችን ላይ ያንብቡ
👉 https://ics.gov.et/job/national-job-opening

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

——

Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

17 Dec, 07:20

t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref668035518
🥳 Hey, want to visit the Zoo together?
🦒 Here, you can buy animals, upgrade enclosures, and take part in an Airdrop!
🎁 Claim your welcome bonus and pick your first animal!

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

15 Dec, 12:29

ሕጻናትን መዳር ነገአቸውን ማበላሸት ነው።
===================
ታኅሣሥ 5/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) ዓለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት "ከቅሸነ" ቲያትር እና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር "ልጆችን በትምህርት እናሳድግ" በሚል መሪ መልዕክት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በሰቆጣ ከተማ በተለያዩ ኩነቶች አክብሯል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ሕጻናትን በመወከል የሕጻናት ፓርላማ ምክትል ሠብሣቢ ተማሪ ዓለም አወቀ ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ያሉ ሕጻናት ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ገልጻለች።
እየተስፋፋ የመጣውን ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ እና የሴት ልጅ ጥቃት እንዲቆም የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርባለች።
ሕጻናትን ያለ ዕድሜ መዳር ነገአቸው እንዲበላሽ መወሰን ነው ያለችው ተማሪዋ ወላጆች ከዛሬው ደስታ ይልቅ የነገውን ሰቆቃ በመገንዘብ ሕጻናትን ወደ ትምህርት እንጂ ወደ ትዳር ሊያስገቡ እንደማይገባ አስገንዝባለች።
በከተማ እየተስፋፋ የመጣው ሱሰኝነት ለሴት ልጅ ጥቃት እንደምክንያት ነው ያሉት ደግሞ የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጌትነት እሸቱ ናቸው።
ዓለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት ባለፉት ሁለት ዓመታት በከተማዋ የሠራው የንቅናቄ መድረክ ለውጥ እያመጣ ነው ብለዋል ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው።
የሴት ልጅን ጥቃት፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻን እና የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛን ማስቆም ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር ባለመኾኑ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
ዓለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት በዓለምም ኾነ በኢትዮጵያ ሕጻናት ላይ የሚደርሱ የጉልበት ብዝበዛዎችን፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻን እና መሰል ጭቆናን ሊከላከል የመጣ ግብረሰናይ ድርጅት መኾኑን በሰቆጣ ቅርንጫፍ የድርጅቱ ሥራ አሥኪያጅ ምህረት ሞላ ገልጸዋል።
በቀጣይም መሰል መርሐ ግብሮችን በማካሄድ የግንዛቤ ማስጨበጡን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የነገሩን።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በጋብቻ 112 ሕጻናት፣ በሱስ 413፣ በወቅታዊ የሰላም እጦት እና በድርቁ ሳቢያ ከ59ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ማቋረጣቸውን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይ ገልጸዋል።
ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ችግር ለመከላከል አሥተዳደር ምክር ቤቱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መኖሩ ሕጻናት ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡ አጋዥ ድርጅቶችም በነጻነት እንዲያግዙ የሚያስችል በመኾኑ ያለውን ሰላም መጠበቅ ይገባል ነው ያሉት።
በመርሐ ግብሩም የጎዳና ላይ ሩጫ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ አስተማሪ ድራማዎች እና መልዕክቶች ተላልፈዋል።
አሚኮ
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

13 Dec, 12:50

የትምህርት ሚኒስቴር ከICDL Africa እና kepler ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
-------------------------- // ----------------------------
(ታህሳስ 04/2017 ዓ.ም) ስምምነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃንን የዲጂታልና ሶፍት ሰኪል በማጎልበት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በሂደትም የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትብብርን በማሳደግ ምሩቃን የተሻለ ክህሎት እና የስራ እድል የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃን ያለባቸውን የዲጂታልና ሶፍት ስኪል ክህሎት ክፍተቶች በመለየት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

ሚኒስተር ድኤታው አክለው እንደገለጹት የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪ ዘርፉ ጋር ያላቸውን ትስስርና ትብብር በተለየ መልኩ ለመደገፍ እገዛ እንደሚኖረውም አብራርተዋል።

የአይሲዲኤል አፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሶሎንዥ ኢሚዩሊሳ በበኩላቸው ድርጅታቸው አፍሪካውያን ተገቢውን የዲጂታል ክህሎት የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚሰራ ደርጅት መሆኑን በመጥቀስ ባለው አቅም ድጋፍ ለማድረግና አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የኪፕለር ዳይሬክትር በበኩላቸው የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃንን በመደገፍና በማሰልጠን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

01 Dec, 14:00

በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግስታት መካከል በትምህርት መስክ ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን የፈረንሳይ እና የአውሮፓ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን ኖኤል ባሮት አስታወቁ፡፡
-------------------- // ------------------------
(ህዳር 21/ 2017 ዓ.ም) ሁለቱ አገሮች በሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት አስር በመቶ ነጻ የትምህርት እድል የሚያስገኝ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ https://www.facebook.com/share/158icUGCJB/

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

30 Nov, 08:40

ዉድ የወሎ ዩኒቨርሲቲ መዉጫ ፈተና /exit exam/የምቶስዱ ተማሪዎች
የመዉጫ ፈተናዉ በጥር እሚሰጥ መሆኑን አዉቃችሁ የተሻለና ጥሩ ዉጤት ለማስመዝገብ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እድታደርጉ ሲል የተማ/ህብ/ፅ/ቤት ያሳስባል።

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

30 Nov, 03:05

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

27 Nov, 10:58

ከደቡብ ወሎ ዞን ሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመለመሉ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደረገላቸው።

ደሴ:- ህዳር 18/2017 ዓ/ም (ደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

በደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ከሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመለመሉ 320 ግንባር ቀደም የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በወሎ ዩንቨርስቲ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውና በዞኑ ከተመረጡ መምህራን ጋር በጋራ በመሆን የተሻለ ድጋፍ እንደሚደሚያገኙ እና ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የማጠናከሪያ ትምህርት በተመረጡ የዩንቨርስቲው መምህራን እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ዩንቨርስቲው ለተማሪዎቹ የተለየና ራሱን የቻለ የዶርምተሪና የቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ተጠቃሚ እንድሆኑ ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ገልጾ በቀጣይ ሁሉም ተማሪዎች የዘመኑን የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና የተሻለ ውጤት አምጥተው እንደሚያኮሩትና ለራሳቸው እና ለሃገራቸው ኩራት እንደሚሆኑ ገልጾ መልካም የትምህርት ዘመን እንድሆንላቸው በመመኘት በዩንቨርስቲው ግቢ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ ማድረግ ስላለባቸው እና ስለሌለባቸው ነገሮች ዙሪያ ምክር ተሰጥቷቸዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያም የወሎ ዩንቨርስቲ ላደረገው ትብብር ከፍ ያለ ምስጋናውን በቅድሚያ እየገለጸ በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በግንባር ቀደምነት እንደሚሰራ ገልጿል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

15 Nov, 16:15

🟣 ወሎ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እንድማሩ በወረዳ ተመልምለው በዞን ደረጃ የተመረጡ ተማሪዎች የህሊና ዝግጅት እንድያደርጉ መደገፍና እነዚህን የተመረጡ ተማሪዎች የሚያስተምሩ ብቃት ያላቸው መምህራንን በተሰጠው መመልመያ መስፈርት መሰረት ፍላጎት ያላቸውን መምህራን መመልመልና በዞን ደረጃ እንድወዳደሩ ለዞን ማሳወቅ፡፡

🔵 ተማሪ ምዝገባ ያልጀመሩ ተቋማትን ምዝገባ ማስጀመር ፣ ትምህርት ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ ትምህርት ቤቶችን ትምህርት ማስጀመር ፣ ያልተመዘጉ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ምዝገባና የተመዘገቡ ተማሪዎችን በሙሉ ትምህርት ማስጀመር የወቅቱ የትኩረት ተግባር አድርጎ መፈጸም ፣

🔵 የመጀመሪያ ዙር የነባርና የተለዩ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ 15 / 03 / 2017 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ስለሆነ በዚህ የግዜ ገደብ ምዝገባውን ለማጠናቀቅ ተቀናጅቶ መሥራት

🔵 የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ልየታ በመማር ላይ ካሉ ተማሪዎች መካከል ያልተለዩትን እስከ 15/03/2017 ዓ.ም ድረስ የልየታ ሥራው እንድጠናቀቅ ለትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን ተልዕኮ መሥጠትና መረጃውን ማደራጀትና ሪፖርት ማድረግ

🔵 የልተማዘገቡ ነባርና የተለዩ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በሥምና በመኖሪያ ጎጥ በመለየት የማጣሪያ የቤት ለቤት ቅስቀሳ ማካሄድና የማይመዘገቡትን ተማሪዎች መረጃ በምክንያት መለየት

🔵 የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ (ያልተዛወሩ) የክልል አቀፍ ተፈታኝ የሆኑ የ6ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በስም በመለየት የማጣሪያ የቤት ለቤት ቅስቀሳ ማካሄድና የማይመዘገቡትን ተማሪዎች መረጃ በምክንያት መለየት

🔵 ዘግይተው ለተመዘገቡ ተማሪዎች ያለፋቸውን ትምህርት ማካካሻ የሚሆን በፕሮግረም የተደገፈ የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጥበትን ሥርዓት በወረዳው በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንድካሄድ ድግፍና ክትትል ማድረግ

🔵 የሴት/ እናቶች አደረጃጀት ፣ የሀገር ሽማግሌዎችን ፣ ተጽኖ ፈጣሪ ታዋቂ ግለሰቦችን ፣ የዕድር ዳኞችን ….. ወዘተ በመጠቀም ከታጣቂ ቡድን አመራሮች ጋር በመወያየት ትምህርት እንድጀመር ጥረት ማድረግ

🔵ትምህርት ያልጀመሩና አቋርጠው የሚጀምሩ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ ቢሆን ትምህርት ቤት ከመጣ የማስተማር ሥራውን ሳይቆራረጥ መጀመር ያለባቸው መሆኑን በማስገንዘብ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

🔵 በመስክ ሥምሪት ላይ ከሚገኘው የዞን አመራርና ባለሙያዎች ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ይገባል፡፡

*መልካም አዳር

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

15 Nov, 16:15

በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ያልተመዘገቡ ነባር ተማሪዎች በተመለከተ

🔴 ወግዲ 8,962 ፣ ቦረና 7,333 ፣ አምሃራ ሳይንት 5,204 ፣ መቅደላ 5,014 ፣ አምባሰል 4,881 ፣ ለጋምቦ 4,474 ፣ ጃማ 4,058 ፣ ደላንታ 3,546 ፣ ቃሉ 3,571 ፣ ከላላ 3,472 ፣ ተሁለደሬ 2,440 ፣ ተንታ 1,955 ፣ ወረኢሉ 1,877 ፣ ወረባቦ 1,810 ፣ ኩታበር 1,680 ፣ ለገሂዳ 1,694 ፣ መሀልሳይንት 1,373 ፣ ደሴ ዙሪያ 1,112 ፣ አልብኮ 1,060 እና አርጎባ 823 በድምሩ 66,339 ያልተመዘገቡ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች አሉ፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያልተመዘገቡ ነባር ተማሪዎች በተመለከተ

🔴 ቦረና 2,629 ፣ ፣ ተንታ 2,312 ፣ ደላንታ 2,323 ፣ አምባሰል 2,165 ፣ ደሴ ዙሪያ 2,058 ፣ ቃሉ 1,810 ፣ ወግዲ 1,803 ፣ ለጋምቦ 1,510 ፣ መቅደላ 1,339 ፣ ጃማ 1,368 ፣ ኩታበር 1,165 ፣ ወረኢሉ 1,168 ፣ አምሃራ ሳይንት 992 ፣ ለገሂዳ 888 ፣ ተሁለደሬ 883 ፣ አልብኮ 867 ፣ ከላላ 851 ፣ ወረባቦ 694 ፣ መሀልሳይንት 641 እና አርጎባ 336 በድምሩ 27,802 ያልተመዘገቡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አሉ፡፡

**ክፍል 2****

የተመዘገቡ ተማሪዎችን ትምህርት ከማስጀመር አኳያ (06/03/2017)፡-

✍️ የተሻለ አፈፃፀም ያላችው ወረዳዎች

1️⃣ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች(≥ 80%)

👉ቃሉ 100%
👉ደሴ ዙሪየ 93.65%
👉ተሁለደሬ 87.58%
👉ወረባቦ 84.22%

2️⃣ በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች(≥90)

👉ቃሉ 99.36%
👉ድሴ ዙሪያ 99.03%
👉አርጎባ 96.9%
👉ተሁለደሬ 96.18%
👉ወረባቦ 92.54%
👉ኩታበር 90.77%

3️⃣ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች

👉አልብኮ 100%
👉ወግድ 100%
👉ቃሉ 99.93%
👉ደሴዙሪያ 99.91%
👉ወረባቦ 100%
👉ወረኢሉ  99.85%
👉አርጎባ 99.12%
👉ተሁለደሬ 99.11%

✍️ መካከለኛ አፈፃፀም ያላችው ወረዳዎች፡-

1️⃣ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች( ≥50)

👉ለገሂዳ 67.31%
👉አ/ሳይንት 63.08%
👉ተንታ 56.12%
👉ቦረና 53.69%
👉መቅደላ 53.22%
👉አልብኮ 50.65%
👉ወረኢሉ 50.53%

2️⃣ በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች(≥70)

👉ተንታ 85.26%
👉ወረኢሉ 78.95%
👉ለገሂዳ 78.30%
👉አልብኮ 77.03%

3️⃣ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች(≥90)

👉አ/ሳይንት 95.38%
👉ተንታ 94.26%
👉ከላላ 95.4%
👉ኩታበር 89.05%
👉መቅደላ 91.74%
👉አምባሰል 84.75%
👉ቦረና 83.99%

✍️ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላችው ወረዳዎች፡-

1️⃣ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች (≥35)

👉ኩታበር 43.48%
👉አርጎባ 45.77%
👉ከላላ 43.88%
👉ለጋምቦ 40.29%
👉አምባሰል 38.08%
👉ወግድ 35.69%

2️⃣ በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች(≥40)

👉ለጋምቦ 66.57%
👉አ/ሳይንት 61.03%
👉መቅደላ 61.92%
👉ወግድ 52.67%
👉አምባሰል 47.85%
👉ከላላ 47.85%

3️⃣ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች

👉ለገሂዳ 76.85%
👉ደላንታ 73.72%
👉ለጋምቦ 65.6%
👉ጃማ 57.16%

✍️ በጣም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላችው ወረዳዎች፡-(≤34)

1️⃣ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች

👉ደላንታ 27.54%
👉ጃማ 17.22%
👉መ/ሳይንት 11.74%

2️⃣ በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች(≤39)

👉ቦረና 30.56%
👉ደላንታ 25.46%
👉ጃማ 19.71%
👉መ/ሳይንት 11.51%

3️⃣ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች

👉መ/ሳይንተው 10.71%

ትምህርት በማስጀመር ለውጥ ያላቸው ወረዳዎች በተማሪ ቁጥር፡-

✍️ ቅድመ አንደኛ፡- አልብኮ 8፤አምባሰል 219፤አ/ሳይንት 123፤ ፤ደላንታ 163፤መ/ሳይንት 22፤መቅደላ 227፤ ተሁለደሬ 14፤ተንታ 1539፤ወረባቦ 116 ድምር 1666

✍️ በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች፤- አልብኮ 6፤አምባሰል 832፤አ/ሳይንት 339፤ ቦረና 410፤ ደላንታ 292፤መቅደላ 952፤ተሁለደሬ 78፤ወረባቦ 42 ፤ድምር 2957

✍️ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች፤አምባሰል188፤ለገሂዳ 21፤መቅደላ 77፤ ድምር 289 በመሆኑ ሊበረታቱ ይገባል፡፡

ችግሮች ሰፊ በመሆናቸው ሁሉም የተመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ትም/ገበታቸው ለማምጣት ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም በየደረጃው በቅንጅት በመስራት ከችግራችን መውጣት ተገቢ ነው፡፡

ዘግይተው ወደ ት/ቤት ለሚመጡ ተማሪዎች ት/ቤቶች በየደረጃው ልዩ የድጋፍ ስርአት ዘርግተው እንድሰሩ መግባባት አስፈላጊ ነው፡፡
የትኛውም የተማሪ ቁጥር ቢሆን ት/ቤት ተማሪዎች እስከመጡ ድረስ መማር እንዳለባቸው መግባባት ያስፈልጋል፡፡

*ክፍል 3**
የትኩረት ነጥቦች

🔵 ተማሪ ምዝገባ ያልጀመሩ ተቋማትን ምዝገባ ማስጀመር ፣ ትምህርት ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ ትምህርት ቤቶችን ትምህርት ማስጀመር ፣ ያልተመዘጉ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ምዝገባና የተመዘገቡ ተማሪዎችን በሙሉ ትምህርት ማስጀመር የወቅቱ የትኩረት ተግባር አድርጎ መፈጸም ፣

🔵 የመጀመሪያ ዙር የነባርና የተለዩ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ 15 / 03 / 2017 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ስለሆነ በዚህ የግዜ ገደብ ምዝገባውን ለማጠናቀቅ ተቀናጅቶ መሥራት

🔵 የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ልየታ በመማር ላይ ካሉ ተማሪዎች መካከል ያልተለዩትን እስከ 15/03/2017 ዓ.ም ድረስ የልየታ ሥራው እንድጠናቀቅ ለትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን ተልዕኮ መሥጠትና መረጃውን ማደራጀትና ሪፖርት ማድረግ

🔵 የልተማዘገቡ ነባርና የተለዩ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በሥምና በመኖሪያ ጎጥ በመለየት የማጣሪያ የቤት ለቤት ቅስቀሳ ማካሄድና የማይመዘገቡትን ተማሪዎች መረጃ በምክንያት መለየት

🔵 የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ (ያልተዛወሩ) የክልል አቀፍ ተፈታኝ የሆኑ የ6ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በስም በመለየት የማጣሪያ የቤት ለቤት ቅስቀሳ ማካሄድና የማይመዘገቡትን ተማሪዎች መረጃ በምክንያት መለየት

🔵 ዘግይተው ለተመዘገቡ ተማሪዎች ያለፋቸውን ትምህርት ማካካሻ የሚሆን በፕሮግረም የተደገፈ የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጥበትን ሥርዓት በወረዳው በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንድካሄድ ድግፍና ክትትል ማድረግ

🔵 የሴት/ እናቶች አደረጃጀት ፣ የሀገር ሽማግሌዎችን ፣ ተጽኖ ፈጣሪ ታዋቂ ግለሰቦችን ፣ የዕድር ዳኞችን ….. ወዘተ በመጠቀም ከታጣቂ ቡድን አመራሮች ጋር በመወያየት ትምህርት እንድጀመር ጥረት ማድረግ

🔵ትምህርት ያልጀመሩና አቋርጠው የሚጀምሩ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ ቢሆን ትምህርት ቤት ከመጣ የማስተማር ሥራውን ሳይቆራረጥ መጀመር ያለባቸው መሆኑን በማስገንዘብ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

🔵 በመስክ ሥምሪት ላይ ከሚገኘው የዞን አመራርና ባለሙያዎች ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ይገባል፡፡

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

15 Nov, 16:15

ግብረ - መልስ ቁጥር - 23
06 / 03 / 2017
*ክፍል 1**
የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተማሪ ምዝገባ አፈጻጸም በተመለከተ

የተማሪ ምዝገባ በትምህርት ተቋማት አፈጻጸም
አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች
🔵 ጠቅላላ ትምህርት ቤቶች ብዛት 1,210
🟢 ምዝገባ ያካሄዱ ትምህርት ቤቶች ብዛት 1140
🔴 ምዝገባ ያላካሄዱ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብዛት 70 ( አልብኮ 1 ፣ አምባሰል 2 ፣ ቦረና 19 ፣ ደላንታ 1 ፣ ጃማ 6 ፣ መሀልሳይንት 8 ፣ መቅደላ 1 ፣ ወግዲ 32)
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች

🔵 ጠቅላላ ትምህርት ቤቶች ብዛት……….68
🟢 ምዝገባ ያካሄዱ ትም/ቤቶች ብዛት……64
🔴 ምዝገባ ያላካሄዱ ትም/ቤቶች ብዛት…..4 (አምባሰል 1 ፣ ቦረና 1 ፣ ደላንታ 1 ፣ ወግዲ 1)

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ዞናዊ የተማሪ ምዝገባ አፈጻጸም በእያንዳንዱ ፕሮግራም ሲታይ ፡-

🔹 ቅድመ አንደኛ……77.43% ፣
🔹 ንጥር ቅበላ……….52.58% ፣
🔹 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ….61.90% ፣
🔹 ሁለተኛ ደረጃ……………26.21% ፣
🔹 አንደኛናመካከለኛ ደረጃ ልዩፍላጎት….62.35 %
🔹 ሁለተኛ ደረጃ ልዩ ፍላጎት……..47.49 % እና
🔹 ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ …..57.40%
🔹ጎልማሶች ትም/ት 55.1% ሲሆን

ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ የወረዳዎች አፈጻጸም እንደሚከተለው ነው

1ኛ. አርጎባ………75.91%
2ኛ. ተንታ..........72.07%
3ኛ. ተሁለደሬ.....71.27%
4ኛ. ቃሉ............70.77%
5ኛ. ወረባቦ …….67.53%
6ኛ. ወረኢሉ……66.87%
7ኛ. ከላላ……….66.05%
8ኛ. ኩታበር……66.36%
9ኛ. ለገሂዳ……..63.35%
10ኛ. ጃማ……...62.05%
11ኛ. ደሴዙሪያ…61.66%
12ኛ. ለጋምቦ…..58.8%
13ኛ. አልብኮ…..58.45%
14ኛ. መቅደላ…..57.88%
15ኛ. መ/ሳይንት...54.15%
16ኛ. አ/ሳይንት...44.32%
17ኛ. ደላንታ…....44.50%
18ኛ. ቦረና……...41.88%
19ኛ. ወግዲ……...37.66%
20ኛ. አምባሰል…..29.29% ናቸው፡፡

በ06 / 03 / 2017 ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ፕሮግራሞ ዕለታዊ የተማሪዎች ምዝገባ ለውጥ ያላቸው 7 ወረዳዎች

1ኛ. ኩታበር...234 ተማሪዎች
2ኛ. ደላንታ...209 ተማሪዎች
3ኛ. መቅደላ …147 ተማሪዎች
4ኛ. ለገሂዳ ....10 ተማሪዎች
5ኛ. ወረባቦ …12ተማሪዎች
6ኛ. ደሴዙሪያ ..4 ተማሪዎች
7ኛ. ወግዲ …….2 ተማሪዎች ናቸው፡፡

በ05 / 03 / 2017 ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ዕለታዊ የተማሪዎች ምዝገባ ለውጥ የሌላቸው 13 ወረዳዎች

🔶 አልብኮ ፣ አምባሰል ፣ አም/ሳይንት ፣ አርጎባ ፣ ቦረና ፣ ለጋምቦ ፣ ጃማ ፣ ቃሉ ፣ ከላላ ፣ መ/ሳይንት ፣ ተንታ ፣ ተሁለደሬና ወረኢሉ ናቸው፡፡

በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ያልተመዘገቡ ነባር ተማሪዎች በተመለከተ

🔴 ወግዲ 8,962 ፣ ቦረና 7,333 ፣ አምሃራ ሳይንት 5,204 ፣ መቅደላ 5,014 ፣ አምባሰል 4,881 ፣ ለጋምቦ 4,474 ፣ ጃማ 4,058 ፣ ደላንታ 3,546 ፣ ቃሉ 3,571 ፣ ከላላ 3,472 ፣ ተሁለደሬ 2,440 ፣ ተንታ 1,955 ፣ ወረኢሉ 1,877 ፣ ወረባቦ 1,810 ፣ ኩታበር 1,680 ፣ ለገሂዳ 1,694 ፣ መሀልሳይንት 1,373 ፣ ደሴ ዙሪያ 1,112 ፣ አልብኮ 1,060 እና አርጎባ 823 በድምሩ 66,339 ያልተመዘገቡ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች አሉ፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያልተመዘገቡ ነባር ተማሪዎች በተመለከተ

🔴 ቦረና 2,629 ፣ ፣ ተንታ 2,312 ፣ ደላንታ 2,323 ፣ አምባሰል 2,165 ፣ ደሴ ዙሪያ 2,058 ፣ ቃሉ 1,810 ፣ ወግዲ 1,803 ፣ ለጋምቦ 1,510 ፣ መቅደላ 1,339 ፣ ጃማ 1,368 ፣ ኩታበር 1,165 ፣ ወረኢሉ 1,168 ፣ አምሃራ ሳይንት 992 ፣ ለገሂዳ 888 ፣ ተሁለደሬ 883 ፣ አልብኮ 867 ፣ ከላላ 851 ፣ ወረባቦ 694 ፣ መሀልሳይንት 641 እና አርጎባ 336 በድምሩ 27,802 ያልተመዘገቡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አሉ፡፡

ግብረ - መልስ ቁጥር - 23
06 / 03 / 2017
የተማሪ ምዝገባ አፈጻጸም በተመለከተ
የተማሪ ምዝገባ በትምህርት ተቋማት አፈጻጸም

✍️ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች

🔵 ጠቅላላ ትምህርት ቤቶች ብዛት 1,210
🟢 ምዝገባ ያካሄዱ ትምህርት ቤቶች ብዛት 1140
🔴 ምዝገባ ያላካሄዱ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብዛት 70 ( አልብኮ 1 ፣ አምባሰል 2 ፣ ቦረና 19 ፣ ደላንታ 1 ፣ ጃማ 6 ፣ መሀልሳይንት 8 ፣ መቅደላ 1 ፣ ወግዲ 32)

✍️ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች

🔵 ጠቅላላ ትምህርት ቤቶች ብዛት……….68
🟢 ምዝገባ ያካሄዱ ትም/ቤቶች ብዛት……64
🔴 ምዝገባ ያላካሄዱ ትም/ቤቶች ብዛት…..4 (አምባሰል 1 ፣ ቦረና 1 ፣ ደላንታ 1 ፣ ወግዲ 1)

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ዞናዊ የተማሪ ምዝገባ አፈጻጸም በእያንዳንዱ ፕሮግራም ሲታይ ፡-
🔹 ቅድመ አንደኛ……77.43% ፣
🔹 ንጥር ቅበላ……….52.58% ፣
🔹 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ….61.90% ፣
🔹 ሁለተኛ ደረጃ……………26.21% ፣
🔹 አንደኛናመካከለኛ ደረጃ ልዩፍላጎት….62.35 %
🔹 ሁለተኛ ደረጃ ልዩ ፍላጎት……..47.49 % እና
🔹 ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ …..57.40%
🔹ጎልማሶች ትም/ት 55.1% ሲሆን

ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ የወረዳዎች አፈጻጸም እንደሚከተለው ነው

1ኛ. አርጎባ………75.91%
2ኛ. ተንታ..........72.07%
3ኛ. ተሁለደሬ.....71.27%
4ኛ. ቃሉ............70.77%
5ኛ. ወረባቦ …….67.53%
6ኛ. ወረኢሉ……66.87%
7ኛ. ከላላ……….66.05%
8ኛ. ኩታበር……66.36%
9ኛ. ለገሂዳ……..63.35%
10ኛ. ጃማ……...62.05%
11ኛ. ደሴዙሪያ…61.66%
12ኛ. ለጋምቦ…..58.8%
13ኛ. አልብኮ…..58.45%
14ኛ. መቅደላ…..57.88%
15ኛ. መ/ሳይንት...54.15%
16ኛ. አ/ሳይንት...44.32%
17ኛ. ደላንታ…....44.50%
18ኛ. ቦረና……...41.88%
19ኛ. ወግዲ……...37.66%
20ኛ. አምባሰል…..29.29% ናቸው፡፡

በ06 / 03 / 2017 ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ፕሮግራሞ ዕለታዊ የተማሪዎች ምዝገባ ለውጥ ያላቸው 7 ወረዳዎች

1ኛ. ኩታበር...234 ተማሪዎች
2ኛ. ደላንታ...209 ተማሪዎች
3ኛ. መቅደላ …147 ተማሪዎች
4ኛ. ለገሂዳ ....10 ተማሪዎች
5ኛ. ወረባቦ …12ተማሪዎች
6ኛ. ደሴዙሪያ ..4 ተማሪዎች
7ኛ. ወግዲ …….2 ተማሪዎች ናቸው፡፡

በ05 / 03 / 2017 ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ዕለታዊ የተማሪዎች ምዝገባ ለውጥ የሌላቸው 13 ወረዳዎች

🔶 አልብኮ ፣ አምባሰል ፣ አም/ሳይንት ፣ አርጎባ ፣ ቦረና ፣ ለጋምቦ ፣ ጃማ ፣ ቃሉ ፣ ከላላ ፣ መ/ሳይንት ፣ ተንታ ፣ ተሁለደሬና ወረኢሉ ናቸው፡፡

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

12 Nov, 09:30

ቀን 03/03/2017 ዓ.ም
👉የተማሪ ጥሪ ማስታዎቂያ
ለደብረ ታቦር  ዩኒቨርሲቲ  አንደኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ፤

በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ፣ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥታችሁ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ትምህርት ምዝገባ ህዳር 9-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ:-
👉 ከ8ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ፣ አራት 3x4 የሆነ ፎቶ ግራፍ፣ ትራስና ብርድ ልብስ እንዲሁም የስፖርት አልባሳት ይዛችሁ እንድትመጡ።

👉በ2016 ዓ.ም የፍሬሽማንን የመጀመሪያ ሴሚስተር ወስዳችሁ የሴሚስተር ውጤታችሁ ከ1.0 -1.49 የሆነ ተማሪዎች ከC በታች ያስመዘገባችኋቸውን ኮርሶች በድጋሜ ለመውሰድ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡

👉በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ በሌላ ማስታዎቂያ እስክንገልፅላችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

👉ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ መግባት አይቻልም፡፡
👉ለበለጠ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድህረገጽ www.dtu.edu.et ን ይጎብኙ፡፡

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

07 Nov, 08:26

https://telega.io/channels/south_wllo_zone_education_Dept/card
Advertising in the Telegram channel «South Wollo Zone Education Department» fa28e - Telega.io

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

06 Nov, 10:06

አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ

“አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ'' መርሃ ግብር በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥታት የተጀመረ የዲጂታል ሥራ ክሂሎቶችን የማሳደጊያ የትብብር ፕሮጀክት ሲሆን በማደግ ላይ ባለው ዲጂታል ኢኮኖሚ ከባቢ የመጪው ትውልድ ኢትዮጵያዊያንን ለማብቃት ታልሞ የተጀመረ ነው።

በመርሃ ግብሩ መሰረት እ.ኤ.አ በ2026 አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክሂሎት የሚያስጨብጥ ይሆናል።

እርስዎስ በዚህ መርሃ ግብር ላይ ለመሰልጠን ተመዝግበዋ? ካልተመዘገቡ ዛሬውኑ በመመዝገብ የዚህ ታላቅ እድል ተቋዳሽ ይሁኑ!!

#DIGITALETHIOPIA  
ለመመዝገብ፡http://www.ethiocoders.et

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

05 Nov, 21:12

አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ

በአገር አቀፍ፣ በክልል ወይም በአካባቢ ደረጃ ያለው የትምህርት ደረጃና ጥራት ከተጠበቀው በታች መወረዱ ሲረጋገጥ የሚመለከታቸው ፦
➡️ የፌደራል፣
➡️ የክልል
➡️ የአካባቢ የትምህርት አስተዳደር ኃላፊዎችን ተጠያቂ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ ቀርቧል።

የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለሰው ሀብት ልማት የሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ በአብላጫ ድምፅ ተመርቷል፡፡

ረቂቁ ምን ይዟል?

🇪🇹 የትምህርት ደረጃና ጥራት ከሚጠበቀው በታች የወረደ መሆኑ ሲረጋገጥ የትምህርት ተቋሙ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን፣ ሌሎች ለችግሩ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትና ግለሰቦች ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ ተደንግጓል፡፡

🇪🇹 በሒደቱ የትምህርት ደረጃና ጥራት መርማሪዎችን ሥራ ለማሰናከል የሚደረጉ ተግባራት የተከለከሉ መሆናቸው ተደንግጓል።

🇪🇹 የአጠቃላይ የትምህርት ደረጃ ጥራትን በባለቤትነት የሚያስጠብቅ የትምህርት ቁጥጥርና ክትትል አገልግሎት የሚሰጥ መንግሥታዊ ተቋም በትምህርት ሚኒስቴር ሥር እንደሚቋቋም ተካቶበታል፡፡

🇪🇹 የመንግሥት ዋነኛ ተግባር ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ማንኛውም ሕፃን ለአጠቃላይ ትምህርት ያለውን መብት ተግባራዊ ማድረግ፣ ተማሪውም የአንደኛና መለስተኛ ትምህርቱን ለመከታተል ያለበትን ግዴታ መወጣቱን ማረጋገጥ ያስችላል።

🇪🇹 በትምህርት ዘርፍ ለሚሳተፉ ባለሀብቶችና ሌሎች መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት፣ በአገሪቱ የኢንቨስትመንት ሕግና አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት ማበረታቻ ይሰጣል።

🇪🇹 ስለትምህርት ክፍያ አለመኖር በሚያብራራው አንቀጽ በማንኛውም የመንግሥት አጠቃላይ የትምህርት ተቋም ውስጥ በመደበኛው የትምህርት መርሐ ግብር ከሚማር ተማሪ ከወላጆች ወይም ከአሳዳሪዎች የትምህርት ክፍያ፣ የመማርያ መጻሕፍት ዋጋ ወይም የመመዝገቢያ ክፍያ መቀበል ክልክል ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡

🇪🇹 ክልሎች በሚያወጠት ሕግ መሠረት ለሌሎች የትምህርት መሣሪያዎች የሚውል መጠነኛ ክፍያ ከተማሪ ወላጆች የመክፈል አቅም ጋር በተጣጣመ መንገድ ሊያስከፍሉ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ድንጋጌው ቢኖርም ይህንን አላሟላህም ተብሎ ተማሪው ከትምህርት ገበታው እንዲለይ ማድረግ አይቻልም።

🇪🇹 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መግቢያ ከአራት ዓመት እስከ ስድስት ዓመት ሲሆን፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕድሜ ደግሞ ሰባት ዓመት ተደርጓል፡፡

🇪🇹 ተማሪዎች ቢያንስ ሦስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ እንደሚደረግ ተደንግጓል። እንግሊዝኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይሰጣል። እንዲሁም አንድ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ክልሉ በሚመርጠው መሠረት ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ በአማራጭነት እንዲሰጥ ይደረጋል።

🇪🇹 ማንኛውም ሰው ተገቢው የማስተማር ሥራ ፈቃድ ሳይኖርው በአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመምህርነት ሊሠራ እንደማይችል የተደነገገ ሲሆን፣ ለዚህ የሚረዳና የሥራ ፈቃድ አሰጣጥን የተመለከተ ስታንዳርድ መመርያ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ይወጣል።

🇪🇹 ከቅድመ ሥራ ሥልጠና በኋላ በመምህርነት የሚመደብ ሰው በቅድሚያ የሁለት ዓመት የትውውቅ ሥልጠና የመከታተልና ለዚህም የሚሰጠውን መመዘኛ ፈተና የማለፍ ግዴታ አለበት። ይህን ግዴታ ከተወጣ በኋላ በዚህ አንቀጽ የሥራ ፈቃድ እንደሚሰጠው ተደንግጓል፡፡

🇪🇹 የመምህራን የሙያ ፈቃዱ በየሁለት ዓመቱ መታደስ ያለበት ሲሆን፣ ዕድሳቱ ከማንኛውም የፈቃድ ክፍያ ነፃ ተደርጓል፡፡ ይህ ዕድሳት ለመምህራን ደረጃ ዕድገት እንደሚረዳ ተቀምጧል፡፡

🇪🇹 በውጭ አገር ማኅበረሰቦች የሚቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው በጀት በአገራቸው መንግሥት 30 በመቶ የሚደገፉ እንደሆኑ፣ ቀሪውን 70 በመቶ ራሳቸው መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማምጣት አለባቸው።

🇪🇹 ኢትዮጵያ ውስጥ በሚቋቋሙ የውጭ አገር ማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶችና ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ከሚመለከተው አገር የሥራ ፈቃድ ማምጣት እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡ (ሪፖርተር ጋዜጣ)

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

04 Nov, 14:18

የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት : https://placement.ethernet.edu.et 
➡️ በቴሌግራም : https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

04 Nov, 14:16

አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ

የ “አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ'' መርሃ ግብር በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥታት የተጀመረ የዲጂታል ሥራ ክሂሎቶችን የማሳደጊያ የትብብር ፕሮጀክት ሲሆን በማደግ ላይ ባለው ዲጂታል ኢኮኖሚ ከባቢ የመጪው ትውልድ ኢትዮጵያዊያንን ለማብቃት ታልሞ የተጀመረ ነው።

በመርሃ ግብሩ መሰረት እ.ኤ.አ በ2026 አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክሂሎት የሚያስጨብጥ ይሆናል።

እርስዎስ በዚህ መርሃ ግብር ላይ ለመሰልጠን ተመዝግበዋ? ካልተመዘገቡ ዛሬውኑ በመመዝገብ የዚህ ታላቅ እድል ተቋዳሽ ይሁኑ!!

#DIGITALETHIOPIA  
ለመመዝገብ፡http://www.ethiocoders.et

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

03 Nov, 06:34

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የ1ኛ ሩብ ዓመት ስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የቀጣይ እቅድ ላይ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ በ2017 የ1ኛ ሩብ ዓመት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊዎችና ምክትል ሃላፊዎች እንድሁም የትምህርት መምሪያ ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት በማካሄድ ላይ ነው፡፡

የመምሪያ የዕቅድ ዝግጅና ትግበራ ቡድን መሪ አቶ አህመድ አደፋ በሩብ አመት የተከናወኑ ስራዎችን ያቀረቡ ሲሆን አቶ አለምነው አበራ የመምሪያው ኃላፊ የቀጣይ ተግባራትን በማቅረብ ውይይት እየተደረገባቸው ነው። በዝርዝር ጉዳዩ ቀጣይ እንመለሣለን።

ደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው።

ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ!

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

አስተያየት ለመስጠትና መረጃዎችን ሊያደርሱን ከፈለጉ ይህንን ግሩፕ ይቀላቀሉ የርስዎ ነው!!
🇪🇹 https://t.me/sweducation

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

31 Oct, 19:26

አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ

የ “አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ'' መርሃ ግብር በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥታት የተጀመረ የዲጂታል ሥራ ክሂሎቶችን የማሳደጊያ የትብብር ፕሮጀክት ሲሆን በማደግ ላይ ባለው ዲጂታል ኢኮኖሚ ከባቢ የመጪው ትውልድ ኢትዮጵያዊያንን ለማብቃት ታልሞ የተጀመረ ነው።

በመርሃ ግብሩ መሰረት እ.ኤ.አ በ2026 አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክሂሎት የሚያስጨብጥ ይሆናል።

እርስዎስ በዚህ መርሃ ግብር ላይ ለመሰልጠን ተመዝግበዋ? ካልተመዘገቡ ዛሬውኑ በመመዝገብ የዚህ ታላቅ እድል ተቋዳሽ ይሁኑ!!

#DIGITALETHIOPIA  
ለመመዝገብ፡http://www.ethiocoders.et

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

30 Oct, 22:04

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የዲጂታል አቅምዎን ያሳድጉ! ተጠቃሚነትዎን ያስፉ!

5 #ሚሊዮን_የኢትዮጵያ_ኮደርስ_ለምን?

የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው ዓለም ዜጎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘመን ክህሎቶችን ለማስታጠቅ ይፋ የተደረገ መርሃ ግብር ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ ዜጎች በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በአንድሮይድ ልማት መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ በማድረግ ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ጊዜ እንዲዘጋጁ የሚያደርጋቸውን ስልጠና በነፃ ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

በ5 #ሚሊዮን_የኢትዮጵያ_ኮደርስ_ማን_መመዝገብ_ይችላል?

የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በዲጂታሉ ዓለም ጊዜውን የዋጀ እውቀትና ክህሎት በመታጠቅ ራሳቸውንና ሀገራቸውን መቀየር የሚፈልግ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ስልጠናውን በነፃ መከታተልና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡  

#እንዴት_መመዝገብ_ይቻላል?

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የሚሰጠውን ሥልጠና ለመከታተል ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ተመዝግበው አሁኑኑ ስልጠናዎን መጀመር ይችላሉ፡፡ www.ethiocoders.et

#የዲጂታል_ሥራዎች_እንዴት_ማግኘት_ይቻላል?

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና የወሰዱትን ጨምሮ በዲጂታል ክህሎት መሰረታዊ እውቀትና ክህሎት ኖሯቸው በኦን ላይን የሚመጡ የሥራ ዕድሎችን ለመጠቀም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (https://lmis.gov.et)ላይ በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

27 Oct, 07:57

በየጊዜው በማደግ ላይ ባለው የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከዘመኑ ጋር አብረው የሚሄዱ እንዲሁም ራስን እና ሀገርን የሚጠቅም ሥራ ለመመስረት አስፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ክህሎቶችን በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲሺ የስልጠና እድሎች ያገኛሉ።

የስልጠና እድሎችን በዚህ ሊንክ በመግባት መውሰድ ይችላሉ። https://ethiocoders.et

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

25 Oct, 20:11

#የደቡብ_ወሎ_ዞን_ዋና_ሰራና_ስልጠና_

በዘንድሮው አመት ከ20ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን በኮደርስ ኢኒሸቲቨ ስልጠና ለማሳተፍ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ስራና ስልጠና አስታወቀ።

ደሴ- ጥቅምት 15/2017/ደሴ ፋና/የመምሪያው ሃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ እንደገለፁት እንደ አማራ ክልል 767 ሺ 963 በደቡብ ወሎ ዞን ደግሞ በ3 አመት ውስጥ ለ83ሺ 40 ለሚሆኑ ሰዎች ስልጠናውን ለመስጠት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

ከነዚህ መካከል 20ሺ 760 ለሚሆኑት በዚህ አመት የሚሰጥ ሲሆን እስካሁን በተሰጠው የኮደርስ ስልጠና ከ5ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞች እንዲወስዱ ተደርጓል።

አለም በሰለጠነችበት ግዜ የነገዋን ኢትዮጵያን ለመገንባት በተለይ ወጣቱ በቴክኖሎጅ የላቀ እንዲሆን ለማድረግ በቀላሉ እጁ ላይ ባለ ስልክ ስልጠናውን በመውሰድ ህይወትን ቀለል በማድረግ የስራ አማራጭን ለማግኘት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

እስካሁን 16ሺ 276 የመንግስት ሰራተኞችና ወጣቶች የግንዛቤ ፈጠራ የተፈጠረላቸው ሲሆን ስልጠናውን ከወሰዱት 294 የመንግስት ሰራተኞች 94ቱ ብቁ ሁነው ሰርተፍኬት ማግኘት ችለዋል።

ስልጠናውን በላቀ መልኩ ለመስጠት 30 የሚሆኑ አሰልጣኞች የተመደቡ ሲሆን 164 ኮምፒተሮችም ዝግጁ ሁነዋል።

እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ያለ ምንም መስፈርት መሰልጠን እንደሚችልም ተጠቁሟል።

ኢንተርኔት በሌለበት አንዳንድ ወረዳዎች ላይ ስልጠናውን ተደራሽ ለማድረግ እንቅፋት ቢሆንም ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ሁሉንም ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም አቶ ደምስ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሸቲቨ ስልጠና ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ጋር በመተባበር የተዘጃጀ ሲሆን እንደ ሃገር 5 ሚሊየን ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

ሰብለ አክሊሉ

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

25 Oct, 20:06

ትምህርት ለትውልድ - ሰኬቶች ደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

በደቡብ ወሎ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች "ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛል። አብዛኞቹም ተጠናቀው ሥራ ጀምረዋል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

24 Oct, 12:46

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተገለፀው የበይነ መረብ ወይም ቴሌግራም ጠቋሚ በመግባት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ ይችላሉ።

ምደባ ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፡-
http://placement.ethernet.edu.et
ቴሌግራም፡-
https://telegram.me/moestudentbot

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

24 Oct, 09:28

ትምህርት ለትውልድ - ሰኬቶች ደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

በደቡብ ወሎ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች "ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛል። አብዛኞቹም ተጠናቀው ሥራ ጀምረዋል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

23 Oct, 07:22

ትምህርት ለትውልድ - ሰኬቶች ደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ "ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

23 Oct, 07:22

ትምህርት ለትውልድ - ሰኬቶች ደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ "ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

23 Oct, 06:31

ትምህርት ለትውልድ - ሰኬቶች ደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

በደቡብ ወሎ ዞን በመቅደላ ወረዳ "ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

23 Oct, 06:27

ትምህርት ለትውልድ - ሰኬቶች ደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ|

በደቡብ ወሎ ዞን በተንታ ወረዳ "ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ናቸው። የተወሰኑትም ተጠናቀው የመማር ማስተማር ሥራው ተጀምሮባቸዋል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

🇪🇹🇪🇹ማህበራዊ ሚድያ ለበጎ አላማ🇪🇹🇪🇹

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ

Telegram_ https://t.me/south_wllo_zone_education_Dept

Facebook_ https://www.facebook.com/swed03 🇪🇹

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

22 Oct, 05:56

ትምህርት ለትውልድ - ሰኬቶች | ደቡብ ወሎ ዞን |

በደቡብ ወሎ ዞን በኩታበር ወረዳ "ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛል። በቅርቡ የመማር ማስተማር ሥራው ይጀምራል።

የላቀች ኢትዮጵያን ለመገንባት፤ ቀድመን የላቁ ትምህርት ቤቶችን እንገንባ!!