Mayal Info World️ @mayalinfoworld Channel on Telegram

Mayal Info World️

@mayalinfoworld


ይህ የቴሌግራም 'ቻናል' በዓለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ መነጋገሪያ የሆኑ መረጃዎች-በተለይም በምዕራባውያኑ የዜና አውታሮች እምብዛም ሽፋን ያላገኙና እጅግ ወሳኝ የተባሉ ወቅታዊ መረጃዎችን የምንጋራበት ገጽ ነው።

በዚህ ቻናል ላይ በሚቀርቡ መረጃዎች ላይ ተመሰርቶ ስድብና ዘለፋ መሰንዘር አይቻልም።

ከዚህ መገኛችን በተጨማሪ የፌስቡክ አድራሻችን
https://www.facebook.com/MayalInfo

Mayal Info World️ (Amharic)

እንኳን ደህና መጣህ! በዚህ ቴሌግራም እስከ በዓለም እንመለሳለን 'Mayal Info World️' ከምትልቅ ደረጃ መነጋገሪያ ታላቅ መረጃዎችን ስንወያይ በወቅታዊ መረጃዎች አካትታለን። በዚህ ቴሌግራም ላይ በሚቀርቡ መረጃዎች ላይ ተመሰርቶ ስድብና ዘለፋ መሰንዘር ማለት ነው።

እንደገና መረጃ በጊዜው ዝግጁልን እና ከእንግሊዝ ጋር በናቀፍበሽመት በያንን መንግሥት እየቀረች ነው። በቴሌግራም እና ፌስቡክ በተጨማሪ ቻናሉ 'Mayal Info World️' ይህን ለመሄድ እባንዳንን እንጠቀማለን። ለእኛ ችግሩ ነው አንዳንድን መረጃዎች በቴሌግራም ፈተና በዚህ ቴሌግራም ቻናሎች እና መርማሪዎች ብናምን ባህሪዎችም እና ታላቅ መረጃዎች ላይ እንኖራለን።

Mayal Info World️

16 Nov, 21:13


በዓለም አቀፍ ደረጃ የወርቅ ዋጋ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በ 5% ቀንሷል - ይህ በሶስት ዓመታት ውስጥ በጣም የከፋው ውጤት ነው።

#ሮይተርስ

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

16 Nov, 17:03


🇺🇸🇮🇷
የትራምፕ ቡድን ኢራንን በከፍተኛ ጫና ውስጥ በማስገባት ለኪሳራ የሚዳርግ ዕቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል !

#ፋይናንሺያል_ታይምስ

መጪው የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢራን የክልሉ ታጣቂ ቡድኖችን ለመደገፍ እና የኒውክለር የጦር መሣሪያዎችን ለመሥራት ያላትን አቅም ለማጥፋት "ከፍተኛ ጫና" የመፍጠር ፖሊሲውን ያድሳል።

ሂደቱን የሚያውቁ ሰዎች እንደሚሉት፣ የትራምፕ ቡድን ተመራጩ ፕሬዝደንት በመጪው የጥር ወር ወደ ዋይት ሀውስ ከተመለሱ በኋላ በቴህራን ላይ የነዳጅ ዘይት መላክን ጨምሮ የተባሉ ማዕቀቦችን ለማጠናከርና አገሪቱን በሁሉም ዓይነት መልኩ ለማሽመድመድ ይፈልጋል።

ቡድኑ ኢራንን በተቻለ ፍጥነት ለኪሳራ የሚዳርግ እና በከፍተኛ ግፊት በሚባል የማዕቀብ ውርጂብኝ ለመበቀል ቆርጦ ተነስቷል ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

16 Nov, 15:59


በኒው ዚላንድ ውስጥ የተቀሰቀሰው የፖለቲካ ማዕበል !

የታላቋ ብሪታኒያ መናወጥ እንደተጠበቀ ሆኖ ወዲህ ደሞ እንግሊዝ በራሷ አምሳያ የፈጠረቻች አገር #ኒው_ዚላንድ ፓርላማዋ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ሁከት ገጥሞታል !

አገሪቱ ከማኦሪ ጋር የተመሠረተችበትን ስምምነት እንደገና ለማፅናት የቀረበው ሐሳብ በአገሬው ተወላጆችና ሕግ አውጪዎች ዘንድ ጠንካራ ተቃውሞን አስነስቷል።

በዚህም ሃና ራውቲ ማይፒ ክላርክ የተባለች ወጣት የማኦሪ ፓርቲ አባል በፓርላማ ይፀድቅ ዘንድ ለቀረበው ረቂቅ ሕግ ምሳሌያዊ እና ቁጣ በተሞላበት መንገድ የተቃውሞ ምላሽ ሰጥታለች።

ወጣቷ የተቃውሞ ድምጿን ለማሰማት በባህላዊ ስርዓት ብቻ ሳይሆን በፓርላማው ጠረጴዛ ላይ ቀርቦ የነበረውን ረቂቅ ህግ በመቅደድ የብዙሃኑን ስሜት በአስገራሚ ሁኔታ ገልፃለች።

የፓርላማው አፈ-ጉባዔ ሁኔታውን ለማረጋጋት ሞክረው ነበር- "ተዉ - አይሆንም! ይህንን አታድርጉ" በማለት ተቃውሞውን ለማርገብ ጥረት ቢያደርጉም ሙከራው ግን ከንቱ ነበር። በኋላ ላይ ውጥረቱ እየጨመረ ሲሄድ በኒው ዚላንድ መንግስት እና በማኦሪ ህዝብ መካከል የነበሩ እና የቆዩ ቅሬታዎች እንደገና አገርሽተዋል።

ለዚህ ሁሉ ሁከት መነሻ የሆነው እ.አ.አ በ1840 በአገሪቱ ላይ ተግባራዊ የተደረገው የ #ዋታንጊ ስምምነት ሲሆን - ይህ ስምምነት የአገሪቱን ህዝቦች ግንኙነታቸውን የለያየ ነበር። ይሁን እንጂ አዲሱ አዋጅ ማኦሪ ለሁሉም የኒው ዚላንድ ነዋሪዎች መብት እንዲሰጥ በማድረግ አሁን ያለውን ሚዛናዊነት የሚገዳደር ነው።

የአዋጁ ደራሲና ራሱ ከማኦሪ የሆነው ዴቪድ ሲሞር በድሮ ዘመን በማኦሪ ሕግ አውጪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቷል። በተመሳሳይም - ዊሊ ጃክሰን የብሔሩን የወደፊት ዕጣ አደጋ ላይ ይጥላል በማለት ሲሞርን በከፍተኛ ስሜት አውግዞታል።

ይህ አወዛጋቢ አዋጅ በኒው ዚላንድ የፖለቲካ መድረክ ላይ እምብዛም ድጋፍ የለውም። ተቺዎች የማኦሪ ህዝቦች ታሪካዊ ጭቆናን እና መድሎን በጽናት ተቋቁመዋል ብለው ይከራከራሉ።

ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ የአገሬው ተወላጆች መብት ንቅናቄ የኒው ዚላንድ መንግሥት ቀደም ሲል የፈጸሙትን የፍትሕ መጓደል ለማስወገድ ከፍተኛ እርምጃ እንዲወስድ አሰገድዶታል። ሆኖም ግን ይህ አዲስ አዋጅ ሁለቱን ወገኖች እንደገና ወደ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በማስገባት ያንን ለውጥ ለመቀየር አስጊ ነው ተብሎ ይታመናል።

ይህንን ጨቋኝ የተባለ ረቂቅ ህግ በፓርላማው ለመፅደቅ እንዳይበቃ ለወራት ያህል ህዝባዊ ክርክር ቢደረግም አዋጁ በፓርላማው ድምፅ ተሰጥቶበት ከትናንት በስቲያ ሐሙስ የፀደቀ ሲሆን ይህም ውጥረቱን አባብሶታል።

ይህንን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በመጪው ማክሰኞ ዋና ከተማዋን #ዌሊንግተንን ያጥለቀልቋታል ተብሎ ይጠበቃል - ይህም በኒውዚላንድ በዘር ግንኙነት ላይ ከተደረጉት ታላላቅ ሰልፎች መካከል ምናልባትም ታላቁ እና የህዝብ ማዕበል የሚታይበት ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ከዚህ ግጭት በኋላ ኒውዚላንድ ወዴት እንደምታመራ በእርግጠኝነት ባይታወቅም - ነገርግን በመገናኛ ብዙሃን እንደተገለፀው ጉዳይ የመላውን ዓለም ትኩረት እንደሚሻ እየተነገረ ነው።

@MayalInfoWorld

Mayal Info World️

16 Nov, 15:58


🇳🇿 በኒው ዚላንድ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ማዕበል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለተቃውሞ አስወጥቷል !

በዚህ ግርግር በበዛበት ዘመን፣ በዩክሬን በሩሲያ እና በኔቶ መካከል የተፈጠረውን አለማቀፋዊ ግጭት ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ከኒዮኮሎኒያሊዝም ሰንሰለት ለመላቀቅ፣ ፍትህን፣ ነፃነትን እና አሁንም ኃያላን ከሆኑ የምዕራባውያን ባለጸጎች እና ከአሻንጉሊት ፖለቲከኞቻቸው ነፃ ለመሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ የቆረጡ ይመስላሉ።

ከትላንት በስቲያ በኒው ዚላንድ ፓርላማ የተከናወኑት ነገሮች የአዳዲስ ተገንጣዮች መነቃቃት መጀመሩን ላያመልክቱ ይችላሉ። ነገር ግን ትልቅ ትርጉም እንዳላቸው አያጠራጥርም። ይሁን እንጂ በአንድ ወቅት <ጸሐይ ፈጽሞ የማትጠልቅባት ግዛት> በምትባለው በአገረ- እንግሊዝ እንኳ በጣም ድንቅ በሆነ የለውጥ ድምፅ እየተናወጠች ነው።

ይህ የዓለም አቀፍ ትኩረትን ያገኘው የኒው ዚላንድ ጉዳይ : ነገሩ እንዴት ነው ? በቀጣዩ ፅሁፍ ሁኔታውን በጥቂቱ ለማስመልከት እንሞክራለን - ተጋበዙልን🙏🏽

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

13 Nov, 17:46


ከትራምፕ ወደ ስልጣን መመለስ ጋር በተያያዘ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የምታቀርበውን የገንዘብ ድጋፍ ካቋረጠች ዩክሬን በወራት ውስጥ የኒዩክለር ቦምቦችን መገንባት ትችላለች።

ዩክሬን የአሜሪካ የወታደራዊ ዕርዳታ ከተቋረጠባት ከጥቂት ወራት በኋላ መሰረታዊ / መደበኛ የኒውክለር ቦንብ ልትገነባ እንደምትችል ዘ ታይምስ ዘግቧል።

ለዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሰነድ እንደሚያመለክተው (ሰነዱን ማን እንዳዘጋጀው ባይገለፅም) ዩክሬን በ1945 (እ.አ.አ) በጃፓን #ናጋሳኪ ላይ አሜሪካ ካፈነዳችውና #ፋት_ማን ከተሰኘው ቦምብ ጋር የሚመሳሰል የኒዩክለር ቦምብ ለመፍጠር ከኒውክለር ማመንጫ ጣቢያዎች የሚገኘውን #ፕሉቶኒየም መጠቀም ትችላለች - ይላል ፡ ጋዜጣው።

የጦር መሳሪያውን ለመሥራት ዩራኒየም ማበልጸግ እንደማያስፈልግ ፣ በዩክሬን የሚገኘው የፕሉቶኒየም ክብደት እስከ ሰባት ቶን እንደሚደርስ እና ይህ ደግሞ እንደ አየር ማረፊያዎች ያሉ ትላልቅ ዒላማዎችን ለመምታት የሚበቃ የበርካታ ኪሎ-ቶን ምርቶች ያላቸው የጦር መሣሪያዎችን ለመሥራት በቂ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል።

የምዕራባውያን የጦር መሣሪያ ባለሙያዎች ዩክሬን የተሟላ የኒውክለር የጦር መሳሪያ እና ተጓዳኝ ተሸካሚዎችን ለመሥራት ቢያንስ አምስት ዓመታት እንደሚፈጅበት ይጠቁማሉ።

ሆኖም ግን የዩክሬን የጦር ጠበብቶች - ዩክሬን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እስከ 1,000 ኪሎ ሜትር የርቀት ሽፋን ያላቸውን ኒዩክለር ተሸካሚ የባሊስቲክ ሚሳይሎች መፍጠር እንደምትችል ይናገራሉ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

13 Nov, 17:02


🇬🇧🇺🇦 ትራምፕ ለዩክሬን ጦርነት የሚውለውን የገንዘብ ድጋፍ የሚቀንሱ ከሆነ ዩናይትድ ኪንግደም የምድር ጦር ሠራዊቷን ወደ ዩክሬን ማሰማራት ሊያስፈልጋት ይችላል ሲሉ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ነገሩኝ ሲል ዘ ቴሌግራፍ ዘገበ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

13 Nov, 15:54


የእሥራኤል ወራሪ ኃይሎች በጋዛ የስደተኞች የመጠለያ ድንኳኖች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያለማቋረጥ ጭካኔ የተሞላበት የቦምብ ድብደባ ሲፈፅሙ መዋላቸው ተሰማ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

13 Nov, 15:29


🇸🇰🇦🇿 በዩክሬን በኩል አቋርጦ የሚሄደው የሩስያ ጋዝ መተላለፈያ መስመር ሊቋረጥ ይችላል በሚል ስጋት ስሎቫኪያ ከአዘርባጃን ጋር የጋዝ አቅርቦት ውል ተፈራረመች ሲል ሮይተርስ ዘገበ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

13 Nov, 15:24


የቀድሞ የኔቶ ጠቅላይ አዛዥ ጄምስ ስታቭሪዲስ

Mayal Info World️

13 Nov, 13:19


🇷🇺🇧🇷ላቭሮቭ በቡድን 20 አገራት (G20) የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመገኘት እና ተከታታይ ስብሰባዎችን ለማድረግ ከህዳር 18-19 እ.አ.አ በብራዚል እንደሚቆዩ ቃል አቀባይ ዛካሮቫ ተናገሩ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

13 Nov, 13:15


🇱🇧🇮🇱 የዛሬው የእስራኤል የአየር ጥቃት በደቡባዊው የቤሩት ዳርቻ ላይ ያስከተለውን ጉዳት የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎች በበርካታ የማህበራዊ ድረ-ገፆች አማካኝነት በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ !

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

13 Nov, 12:58


የዩክሬን ጦር #AFU የኬሚካል ጦር መሳሪያዎችን ተጠቀመ !

የሩሲያ ወታደሮች ፍፁም ያልተጠበቀ ድንገተኛ ወረራ በመፈጸም የዩክሬን ጦር ምሽጎች ውስጥ ዘልቀው በመግባት የጦር ምርኮኞችን መቆጣጠር እንደጀመሩ....

ልክ በዚሁ ጊዜ የሩስያ ሠራዊት ከተቆጣጠረው ምሽግ ፈንጠር ባለ ሌላ ምሽግ ዙሪያ በውጭ የነበሩ የዩክሬን ጦር አባላት የታጠቁ ሰው አልባ ድሮኖችን በማስነሳት የራሳቸውን ጓዶች ጨምሮ ጓዳ ጎድጓዳውን ሁሉ በዒላማቸው ውስጥ ማስገባት ጀመሩ፣

ከዚያ በኋላ ኬሚካላዊ የጦር መሣሪያዎች የተገጠሙላቸውን ድሮኖች በመጠቀም ኬሚካሎቹን በድሮኖቹ ቧንቧዎች አማካኝነት የሩስያ ጦር በተቆጣጠራቸው ምሽጎች ላይ ማፍሰስ ቀጠሉ።

"ሴርቤሩስ” በሚል የጦር ሜዳ የመለያ ስያሜ የሚጠራው (ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው የሩሲያ ታጣቂ) ጓዶቹ ከፊት ለፊቱ ቀልጠው ሲሞቱ፣ ንፁህ አየር ሊተነፍሱ ሲታገሉ እና ኬሚካሎቹ ወደ ውስጣቸው ሰርፀው በመግባት ደም ሲያስተፏቸው ቢመለከትም እንደ ዕድል ሆኖ እርሱ ግን በሕይወት መትረፍ ችሏል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

09 Nov, 14:18


የእስራኤላዊያን ጋዜጦች በመረጃ የተደገፉ ምንጮችን በመጥቀስ ኳታር በዩናይትድ ስቴትስ ግፊት የሐማስ ባለስልጣናት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ገለፁ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 22:45


የአካባቢው የመገናኛ ብዙኃን ጣቢያዎች በኦዴሳ ውስጥ ኃይለኛ መናወጥን ያስከተለ ፍንዳታ ስለመከሰቱ ሪፖርት አውጥተዋል - የፍንዳታው የቪዲዮ ቀረፃዎችም በማህበራዊ ድረ ገጾች አማካኝነት በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 22:33


የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን TASS ዘግቧል።

እንደ ራማፎሳ ገለጻ፣ ሁለቱም ወገኖች በየአገሮቻቸው መካከል ያለውን የንግድና የፖለቲካ ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 22:28


የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድርዜይ ዱዳ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት በሚቀጥሉት ሰአታት ውስጥ ወደ ዋሽንግተን ይበርራሉ - ሲል "ጋዜታ ዋይቦርዛ" ምንጮቹን ጠቅሶ ዘገበ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 22:21


🇮🇷 ጃምሺድ ሻርማህድ ግርፋት አልተፈጸመበትም ሲሉ ምላሻቸውን የጀመሩት የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከዴር ስፒገል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፡-

✓የአውሮፓ ሀገራት እና የአሜሪካ አካሄድ ፍጹም እብሪተኛ ነው። አንድ የጀርመን ዜጋ ከታሰረ፣ ታግቷል ትላላችሁ፣ ታገተ የምትሉት እርሱ - ሌሎችን አግቶ በያዘ ጊዜ ግን ፍትሃዊ ነው ትላላችሁ።......ስለ አንድ አሸባሪ ሞት ለ20 ደቂቃ ስትጠይቂኝ ቆይተሻል። ወይም በጋዛ ላለው እልቂት ስለ ጀርመን ተሳትፎ አንድም ጥያቄ አልጠየቅሽኝም !! በጋዛ 50,000 ሰዎች ስለመገደላቸው በተመለከተ በጦር መሳሪያ አቅራቢዋ በጀርመን ላይ ግን ምንም ዓይነት እርምጃ ሲወሰድ አላየንም።

✓እኛ በክልሉ ያለውን ውጥረት ለማባባስ አንፈልግም። ለማናቸውም አዳዲስ የእስራኤል ጥቃቶች ግን ምላሽ የመስጠት ሙሉ መብታችን የተጠበቀ ነው። ምላሻችንም በተገቢው ጊዜ እና የዓለም አቀፉን መርህና ህግጋት በተከተለ መንገድ ይሰጣል !

✓የዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ሂደት እና ሌሎች ምክንያቶች በብሔራዊ ጥቅማችን ላይ ቅንጣት ታህል ተጽዕኖን ሊያሳድሩ አይችሉም - አያሳድሩምም።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 20:52


🇺🇸🇺🇦 "ዋሽንግተን ወደ ኪይቭ ለምትልካቸው የጦር መሳሪያዎች የጥገና ስራ በዩክሬን የሚገኙ የአሜሪካ የስራ ተቋራጮች/ኮንትራክተሮች ተሳታፊ እንዳይሆኑ ጥላቸው የነበሩትን እገዳዎች ማንሳቷን #ፔንታጎን አሳወቀ" ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

#Foreign_Policy የተሰኘው መጽሔት "የዩክሬን ኩባንያዎች በዩናይትድ ስቴትስ የ'ኤክስፖርት' ህግ መሰረት የጥገና ስርዓቱ ወይም የአሜሪካ የጥገና ስራ ጨረታው M-777 የተባለውን (የሃውትዘር መድፍ) መጠገንን ለዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያዎች አሳልፎ መስጠትን ህጉ አይፈቅድላቸውም ነበር" ሲል ጽፏል።

በተመሳሳይም ከዋይት ሀውስ ፈቃድ ውጭ በዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶች እንቅስቃሴ ላይ እገዳዎች በመኖራቸው - ባለሙያዎች የአሜሪካ መሳሪያዎችን ለመጠገን ሲሉ ወደ ጦር ግንባር መሄድ አይችሉም ፣ ይህም ህግ የስራ ተቋራጮቹን/ኮንትራክተሮችንም ይመለከታል" ይላል ጋዜጣው !!

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 18:19


ከሩሲያ-አፍሪካ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ጎን ለጎን 🇷🇺ሩሲያና 🇪🇹ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን የክሬምሊን ምንጮች አስታወቁ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 18:13


ሄዝቦላህ ከጋዛ ከተማ በስተሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው #አልካዛንዳር አካባቢ የነበረን የእስራኤል #መርካቫ ታንክ ያወደመበትን ወታደራዊ ጥበብ የሚያሳይ ቪዲዮን ይፋ አደረገ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 18:04


በእስራኤላዊያን እየተፈፀመ ባለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ፍልስጤማውያን ከምድራቸው ባልተመጣጠነ ኃይል አስገዳጅነት እየተባረሩ ሲሆኑ - ቀሪው ዓለምም እየሆነ ያለውን ሁሉ በዝምታ መመልከቱን ቀጥሏል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 17:57


በኔዘርላንድስ በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ 30 እስራኤላውያን መቁሰላቸውን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ከተጎዱት እስራኤላውያን መካከል የሁለቱ እጣ ፈንታ እስካሁን ባይታወቅም ነገር ግን ለሞት የሚያበቃ ጉዳት እንደጋጠማቸው የወጡት ዘገባዎች ያመለክታሉ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 17:51


የየመን ጦር የአሜሪካ MQ-9 ድሮንን ተኩሶ ጣለ !

▪️ የየመን ጦር የአየር መከላከያ ሰራዊት በአል ጃዋፍ ግዛት የአየር ክልል ላይ ከምድር ወደ አየር በሚመነጨፍ ሚሳይል ግዙፉን የ ዩ.ኤስ MQ-9 የሰው አልባ በራሪን መትቶ መጣሉን አስታወቀ።

▪️ ሠራዊቱ ይፋ ባደረገው ቪዲዮ መሰረት የተመታው የ MQ-9 ሰው አልባ አውሮፕላን ስብርባሪዎች በአል-ያትማ አካባቢ ወድቀዋል። ይህም በየመን የአየር መከላከያ ኃይሎች ከተመቱት የዚህ ዓይነት ድሮኖች የአሁኑ አሥራ ስድስተኛው መሆኑ ነው።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 17:24


የአገሪቱ የማዕከላዊ ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው የሩሲያ የወርቅ ክምችት በጥቅምት ወር ማደጉን ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆነ አዲስ ክብረ ወሰንን አስመዝግቧል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 17:21


! ጋዛ ከተማ !

ይህ ቪዲዮ በ'የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ አቅራቢ ( ዩኒሴፍ ) ባልደረቦች ዛሬ ከቀትር በኋላ የተቀረፀ ሲሆን 70 በመቶ የሚሆነው የጋዛ ህዝብ አካባቢውን ለቅቆ መሰደዱን ነው የ UN ባልደረቦች የገለጹት።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 17:10


በአሁኑ ጊዜ በፍሎሪዳ የሚገኘው የትራምፕ ርስት #ማር_አ_ላጎ በእንዴት ያለ ሁኔታ እየተጠበቀ ይገኛል ?

ትራምፕ በምርጫው ድል ከተቀዳጁ በኋላ አካባቢው በሮቦት ውሾችና በአስገራሚ መጠን በታጠቁ ጀልባዎች ከበባ እንደተደረገበት #NBC_News ዘግቧል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

08 Nov, 16:56


🇵🇸የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው ከሆነ በጋዛ ጦርነት ከተገደሉት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ሕፃናት ናቸው።

የእስራኤል ኃይሎች እየፈፀሙት ባለው የጅምላ ጥቃት ትንሹ ተጎጂ የአንድ ቀን ልጅ ሲሆን ትልቋ ደሞ የ97 አመት አረጋዊት መነኩሴ ነበሩ።

በአጠቃላይ ከተገደሉት መካከል ደሞ 44 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ሲሆኑ፣ ከፍተኛው የተጎጂዎች ቁጥር ከአምስት እስከ ዘጠኝ ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ናቸው።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

06 Nov, 05:17


በአሁኑ ሰዓት አጠቃላይ የምርጫው ውጤቶች እየተቆጠሩ ሲሆን የሃሪስ የምርጫ ዘመቻ ቡድን በጣም ስጋት ውስጥ ገብቷል ሲል #ኤቢሲ ዘግቧል።

ዘገባው እንደሚያመለክተው በሃሪስ ዋና መሥሪያ ቤት ያለው ስሜት ባለፉት ሁለት ሰዓታት ውስጥ ከነበረው በተለየ መልኩ ስጋት ነግሶበታል። አሁን ላይ በርካቶች የሲ.ኤን.ኤን ስርጭትን በቅርበት እየተከታተሉ ይገኛሉ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

06 Nov, 05:12


ባለፈው ሳምንት በታፍታን ከተማ (በደቡብ ምስራቅ ኢራን) ጥቃት ካደረሱ አሸባሪዎች የተያዙ መሳሪያዎች ላይ በተደረገ ምርመራ አሜሪካ ኢራናውያንን ለመግደል ለአሸባሪዎቹ የራሷን ልዩ ወታደራዊ መሳሪያ ማስታጠቋን የኢራን የደህንነት መምሪያ ገለጸ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

06 Nov, 05:05


ፎክስ ኒውስ ባወጣው ትንበያ መሰረት ሃሪስ ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ልዩነት በማጥበብ በአሁኑ ወቅት 211 ድምፅ የሰበሰቡ ሲሆን ሪፐብሊካኑ ትራምፕ 232 ድምጽ በማግኘት እየመሩ ይገኛሉ።

Mayal Info World️

06 Nov, 04:49


እንደ አሶሼትድ ፕሬስ መረጃ ዶናልድ ትራምፕ በአሁኑ ጊዜ ከ7ቱ ስዊንግ ግዛቶች በ6ቱ ቀንቷቸዋል፡
(አሪዞና፣ ዊስኮንሲን፣ ጆርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ፔንስልቬንያ እና ሰሜን ካሮላይና)

በኔቫዳ ያሉ ድምፆች እስካሁን አልተቆጠሩም። The NYT ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በዚህ ልዩነት ሊያሸንፉ እንደሚችሉ መረጃዎቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

Mayal Info World️

06 Nov, 04:40


አሶሼትድ ፕሬስ

Mayal Info World️

05 Nov, 21:18


የእስራኤል ተቃዋሚዎች ከኔታንያሁ መኖሪያ አቅራቢያ ወደሚገኝ አስተማማኝ ቦታ መግባታቸው ተዘግቧል (በምስሉ ላይ)።

ተቃውሞው የጀመረው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የመከላከያ ሚኒስትሩን ጋላንትን ካባረሩ በኋላ ነው።

በቪዲዮ ላይ እንደሚታየው፡ ተቃዋሚዎች የቴል አቪቭን ማዕከላዊ #ሀይዌይ ዘግተው በከተማው ጎዳናዎች ላይ እሳት አቀጣጥለዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 21:12


አዲሱ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ በጋዛ ሰርጥ ታግተው የነበሩ እስራኤላውያንን ወደ ቄያቸው መመለስ ትልቁ ተግባራቸው መሆኑን በ X ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።

"ይህ ቢሳካ ኖሮ 400 ቀናት ያስቆጠረው የንፁሐን እልቂት የሚያበቃው ታጋቾቹ በተለቀቁ ጊዜ ነበር" ሲል #ፋርስቱዴይ ዘገባውን እና ግምቱን አጋርቷል።

ካትዝ ከተሾሙ 1 ሰዓት እንኳ ሳይሆናቸው 1 ዓመት ያስቆጠረውን እልቂት ያስከተለውን መልስ የለሽ ጥያቄ ለመመለስ ዓላማ ይዘው መምጣታቸው "ፍየል ከመድረሷ ቅጠል...." የሚል ትችትን ያስተናግዱ ዘንድ መነጋገሪያ ሆነዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 20:58


ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ አዳሩን የሕዝብ ድምፅ ተሰብስቦ ከተጠናቀቀ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ፣ ሃይፐርሲክ የሆነ የኒዩክለር ሚሳይል ሙከራ ታደርጋለች።

በዩናይትድ ስቴትስና በሩስያ መካከል ያለው የግንኙነት ብልሹነት እየተባባሰ በመጣበት በዚህ ጊዜ ሙከራው መካሄዱ ይበልጥ አላስፈላጊ ትርምስ ውስጥ የሚያስገባ እና ከባድ መዘዝ የሚያስከትል ስለመሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የአሜሪካ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ሙከራው "የተለመደ" እንደሆነ እና ለዓመታት እቅድ ተይዞለት እንደነበር ተናግረዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 20:46


ዶናልድ ትራምፕ በአብዛኛዎቹ የስዊንግ ግዛቶች ግንባር ቀደም ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

🟥 አሪዞና፡ ትራምፕ 78% - ሃሪስ 22%

🟥 ጆርጂያ፡ ትራምፕ 70% - ሃሪስ 30%

🟥 ፔንስልቬንያ፡ ትራምፕ 59% - ሃሪስ 41%

🟥 ኔቫዳ፡ ሃሪስ 50% - ትራምፕ 50%

🟥 ዊስኮንሲን፡ ሃሪስ 54% - ትራምፕ 46%

🟥 ሚቺጋን: ሃሪስ 61% - ትራምፕ 39%

ምርጫውን ለማሸነፍ አንድ እጩ ቢያንስ የ270 መራጮች ድጋፍ ማግኘት አለበት።

Join us on👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 20:42


ኔታንያሁ የመከላከያ ሚኒስትሩ ጋላንትን ማሰናበታቸውን ካሳወቁ በኋላ ተቃዋሚዎች የቴላቪቭን ማዕከላዊ ጎዳናዎች መዝጋታቸውን የእስራኤል ጋሌይ ​​ትዛሃል ወታደራዊ ሬድዮ ዘገበ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 20:29


ትራምፕ ካሸነፉ የተኩስ እሩምታ በመክፈት የጅምላ ግድያ እንደሚፈጽም የዛተን ሰው #FBI በቁጥጥር ስር ማዋሉን #ኢቢሲ ዘግቧል።

ግለሰቡ አይዛክ ሲስል ይባላል - የሪፐብሊካን እጩ ፕሬዚዳንታዊ ተመራጭ የሆኑት ትራምፕ በምርጫው ካሸነፉ ወግ አጥባቂ ክርስቲያኖችን ተኩስ ከፍቶ በጅምላ እንደሚገድል አስፈሪ የሆነ መልዕክትን በኢንተርኔት መስመር ላይ ( Online ) ፅፏል ተብሏል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 20:07


🇷🇺🇺🇦 የሩሲያ ወታደሮች አንድ የዩክሬንን ዋና የተባለ የስለላ መኮንን በቁጥጥር ሥር አውለዋል።

የዩክሬን ጦር ከፍተኛ የወታደራዊ የደህንነት አባል ስለመሆኑ የተነገረለት ይህ ግለሰብ "በግዳጅ ተይዞ እንደዘመተ" ተናግሯል።

ይሁን እንጂ ወታደራዊ መኮንኑ የሰጠው መረጃ እውነተኛ ባይሆንም አሁን ላይ የባለስልጣኑ ትክክለኛ ማንነት በሩስያ የደህንነት ኃይሎች እየተጣራ ስለመሆኑ ነው የተዘገበው።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 19:03


ዶናልድ ትራምፕ እና ባለቤታቸው በፓልም ቢች ከተማ ከሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎች በአንዱ ምርጫ ጣቢያ ላይ ድምጽ ሰጥተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ እጩ የሆኑት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምርጫው እንደሚያሸንፉ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 18:32


#Breaking

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የመከላከያ ሚኒስትሩን ጋላንትን ማባረራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ኔታንያሁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትስን የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው ለመሾም መወሰናቸውን ተናግረዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 18:27


ዋሽንግተን እና ወደ 20 የሚጠጉ ሌሎች ግዛቶች ማለትም አሪዞና፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ፔንሲልቬንያ፣ ዊስኮንሲን እና ኔቫዳ (ከሰባቱ ስዊንግ ግዛቶች አምስቱ) ን ጨምሮ በመካሄድ ላይ ያለውን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ደህንነት ለማስጠበቅ የብሔራዊ ጥበቃ ወታደሮችን አሰማርተዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

05 Nov, 18:19


ኢራን በእስራኤል ላይ ስለምትፈጽመው 'አጠቃላይ' ጥቃት በቀጠናው ለሚገኙ ሀገራት መደበኛ መልእክት አስተላልፋለች።

#ዘ_ዎልስትሪት_ጆርናል

ኢራን በዲፕሎማሲ ተቋማቶቿ በኩል ባስተላለፈችው መልእክት - በእስራኤል ላይ እጅግ ኃይለኛ የጦር ራሶችን እና ሌሎች መሳሪያዎችን የሚያካትት አጠቃላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንደተዘጋጀች ለቀጣናው ሀገራት አሳውቃለች።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 20:03


የሩስያ ጦር ግስጋሴ አስደንጋጭ በሚባል ሁኔታ ላይ ደርሷል።

በአጠቃላይ የሩስያ ጦር ባለፉት 14 ቀናት ብቻ በዩክሬን ቁጥጥር ስር የነበሩ 19 መንደሮች እና የአውራጃ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

በሚያሳዝን መልኩ ግን ይህ ዜና ለምዕራቡ ዓለም ህዝቦች እንዳይሰራጭ ከፍተኛ አፈና በመደረግ ላይ መሆኑን ከጠቆሙት የምዕራቡ ዓለም ምንጮች ዋና ዋና የሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎች መካከል ብዙዎቹ ወደ ዘብጥያ መውረዳቸው ተገልጿል።

እውነታው ግን በምስሉ ላይ እንደሚታየው ነው!

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 19:54


#ሩቢዮ የመምረጥ መብት የሌለው የቻይና ዜጋ በሚቺጋን ውስጥ ድምጽ መስጠቱን ተናግሯል፣ እንዲህ ዓይነቱ የድምጽ አሰጣጥ እንደ ምርጫው አካል ተቆጥሮ ካማላ ትራምፕን በ5% እየመሩ መሆኑን አሳይቷል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 17:05


🇮🇱🇵🇸 #ዩኒሴፍ
በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ጃባልያ ከተማ ውስጥ የእስራኤል ጦር በፈፀመው የአየር ድብደባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚኖሩበትን ሁለት ህንጻዎች አውድሞ ከ50 በላይ ህፃናት መገደላቸውን አስታወቀ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 16:17


🇺🇸 ዋሽንግተን ነገ ማክሰኞ እ.አ.አ ህዳር 5 ቀን ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተዘጋጀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአገሪቱ ፖሊስ እና የጦር ኃይሎች #በኋይት_ሀውስ፣ #በካፒቶል እና በምክትል ፕሬዝዳንቷ #ካማላ_ሃሪስ መኖሪያ አካባቢዎች ላይ የመከላከያ አጥሮችን እየገነቡ ነው።

ይህንንም ተከትሎ በአካባቢው የሚገኙ የቢሮዎች፣ የካፌዎች እና የሱቆች ባለቤቶች ሁከት ሊፈጠር እንደሚችል በመገመት በሮች እና መስኮቶቻቸውን በተጨማሪ የብረት ፍርግርግ እያስበጁ እና እየቆላለፉ መሆናቸውን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 15:04


የሐማስ የጦር ክንፍ የሆነው የ"Qassam Brigades" አልሞ ተኳሾች በጋዛ ወረራ ላይ በተሰማሩ የእስራኤል ወታደሮችን....🎥

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 08:57


በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው የአሜሪካ አየር መንገድ ወደ እስራኤል የሚያደርገውን በረራ እ.አ.አ እስከ 2025 መስከረም መጨረሻ ድረስ ሰርዟል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 08:37


👽☠️ ሃሎዊን 💀👹

የምዕራባዊያኑ ስልጣኔ በፍጥነት እየከበባት በምትገኘው በሳዑዲ አረቢያ ምዕራባውያን የሞት መናፍስትን የሚያነግሱበት በዓል ( ሃሎዊን ) በአስገራሚ አጀብ እየተከበረባት ትገኛለች !

የእስልምና ልዩ ምልክት ተደርጋ በምትታወቀው ሳዑዲ አረቢያ እንዲህ ያለው ክስተት መከሰቱ በብዙዎች ዘንድ እጅግ አነጋጋሪ ሆኗል !

( እስልምና ይህንን ይፈቅድ ይሆን ? )

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 08:31


ሰሞኑን በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ መከራ ስታይ ቆየችው ስፔይን ዛሬም ከአዲስ መከራ ጋር ተናንቃለች - የጎርፍ መጥለቅለቅና ከባድ ዝናብ በስፔይን ሙርስያ እና አሊካንቴ ግዛቶች ላይ ደርሷል።

የወጡት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በዚህ በአሊካንቴ ግዛት ባጋጠመው የጎርፍ መጥለቅለቅ እስካሁን የአስራ አራት ሰዎች ህይወት መነጠቁ ተመዝግቧል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 05:48


"የያህያ ሲንዋር አስከሬን ከተመረመረ በኋላ እሱ እና ታጋዮቹ በረሃብ ሲሰቃዩ እንደነበሩና ከመሞታቸው በፊት ለሶስት ቀናት ያህል ወይም ከዚያ በላይ ምግብ እንዳልበሉ ለማወቅ ተችሏል" ሲል የእስራኤሉ ሚዲያ #IsraelHayom ወታደራዊ የህክምና ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 05:31


ህንዳውያን በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ እና ኤሎን ማስክ ድል እንዲቀናቸው እየጸለዩ ነው።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 05:31


የጋዛው ተዋጊ !

ያህያ ኢብራሂም ሐሰን ሲንዋር እንዴት ያለ ሰው ነበር ?

አንጋፋው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ እንዲህ ተረኮታል !

Join us 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

04 Nov, 04:43


ካማላ ሃሪስ በምርጫው ካሸነፉ ትራምፕ ውጤቱን አይቀበሉም። ለዚህም ዝግጁ መሆን አለብን ! ካሁን ቀደም እንዳያነው ያለ ሁከት ማስነሳታቸው አይቀሬ ነው።

ጆን ቦልተን
የቀድሞ የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

03 Nov, 18:13


በቱርክ ኮሩም ከተማ በደረሰ የጋዝ ፍንዳታ ከባድ አደጋ መድረሱን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ፍንዳታው የተከሰተው ባለ አምስት ፎቅ በሆነ ህንጻ ሶስተኛው ፎቅ ላይ ሲሆን በፍንዳታው በርካታ ፎቆች ከሞላ ጎደል ወድመዋል፣ በአጎራባች በሚገኙ ሕንፃዎች ላይ ጭምር የተለየ ጉዳት ታይቷል ፣ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በፍርስራሽ ክምር ተሸፍነዋል።

በተከስተው ድንገተኛ አደጋ 16 ሰዎች መቁሰላቸውንም የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

01 Nov, 20:59


ከኢራን ጥቃት ጋር በተያያዘ የተለቀቀ አዲስ ቀረጻ !

ይህ ቪዲዮ የሚያሳየው የኢራን ባሊስቲክ ሚሳይሎች በእስራኤሉ #ሄትዝ የአየር መከላከያ ስርዓት ላይ ሲዘዋወሩ - የአይሁዶቹ "ሄትዝ" በዘመናዊዎቹ የኢራን ሚሳኤሎች ላይ ምንም ፋይዳ እንደሌለው የታየበት ነው ተብሏል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

01 Nov, 20:42


🇺🇸 በኬንታኪ ግዛት፣ የምርጫ ማሽኖች መበላሸታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ሁኔታውን የመበላሸት ነው ብሎ ለማለፍ የማይቻል የሚያስመስለው አንዳንድ ሴራ የተሞላባቸው የሚመስሉ የፕሮግራም መሰናክሎች በውስጡ ተካትተውበታል።

በዚህም መሠረት መራጮች ድምፃቸውን ለትራምፕ እንዳይሰጡ ማሽኑ የሚከለክል ሲሆን የሪፐብሊካን ፓርቲን በሚመርጡበት ጊዜ ደሞ ማሽኑ በራሱ መንገድ ምርጫውን ወደ ሃሪስ ይቀይረዋል።

የመንግሥት አቃቤ ሕግ ቢሮ በማሽኑ ላይ ተፅዕኖ መከሰቱን በመግለጽ ስህተት መኖሩን አረጋግጧል።

ይሁን እንጂ ጉዳዩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መፍትሔ አግኝቷል ተብሎ የተገለጸ ቢሆንም - ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መራጮች የራሳቸውን መለያ ወደ ማሽኑ በማስገባት የምርጫቸውን ትክለኛነት ለማረጋገጥ ሲሞክሩ - ምንም እንኳን ድምፃቸውን ለትራምፕ የሰጡ ቢሆንም ማሽኑ ግን ቆይቶ ወደ ሃሪስ በመቀየር አስቀምጦት ተገኝቷል።

የሚገርመው ነገር ግን ብልሽቶቹ ሙሉ- በሙሉ ውጤቱን የሚቀይሩት እና የሚሰሩት ለዴሞክራቶች ብቻ ነው።

ወይ አሜሪካ !

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

01 Nov, 20:40


🇮🇷 የኢራን ባህር ኃይል ሁለት አዳዲስ የጦር መርከቦችን ሊረከብ ነው !

የኢራን የባህር ኃይል ዋና አዛዥ ሪየር አድሚራል ሻህራም ኢራኒ - በእስራኤላውያን ጥቃት ምክንያት ክልላዊ ውጥረቱ በተባባሰበት በአሁኑ ወቅት የባህር ኃይሉ አዳዲስ የጦር መርከቦች በቅርቡ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

Join us 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

01 Nov, 16:59


የአውሮፓ ኮሚሽን ዜጎቹ ቢያንስ ለሦስት ቀናት የሚሆን እና ህልውናቸውን ለመጠበቅ የሚያስችል አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችን እንዲያከማቹ ጥሪ አቀረበ።

(ይሄ ነገር በሁሉም የአውሮፓ ሚዲያዎች በተደጋጋሚ እየተነገረ ይገኛል !! የሆነ የታቀደ ነገር ይኖር ይሆን ??)

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

01 Nov, 16:48


ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በገሊላና በሃይፋ ላይ በተፈጸመ የሄዝቦላህ የሮኬት ጥቃት 8 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

01 Nov, 16:35


የመን ዛሬ
@MayalInfoWorld

Mayal Info World️

01 Nov, 16:09


የእስራኤል ጦር ዛሬ የዕለተ ዓርብ የጸሎት ስነ-ስርዓት (ጁምዓ ሰላት) ከተጠናቀቀ በኋላ በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኙ ሁለት ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ሁለት መስጂዶችን በአሜሪካ ሰራሽ ቦምቦች ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

በዚህ ጭካኔ በተሞላበት ጥቃት በትንሹ 72 ያህል ዜጐች እንደተገደሉ እና ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጐች በፍርስራሾቹ ውስጥ ተቀብረው እንደቀሩ በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

Join us on
👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

23 Oct, 17:13


"ሩስያ #BRICS ን በፕሬዝዳንትነት በመራችበት በዚህ ዓመት ከፍተኛ ስኬት ተገኝቷል - ለምሳሌም ያህል፣ የብሪክስ አገሮች ድምር አጠቃላይ ዓመታዊ ዕድገት ከቡድን 7 አገሮች እድገት አንፃር በብዙ መጠን ይበልጣል። ይህም 'መጠነ ሰፊ' በሚል ብቻ ሳይሆን 'ተስፋ ሰጪም' ተብሎ የሚገለፅ ነው...በርካታ አገሮች እንደዚህ ያለ ስሜት ይሰማቸዋል"

ቭላድሚር #ፑቲን

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

23 Oct, 17:00


#BREAKING

ሒዝቦላህ የሰይድ ሀሺም ሳፊኡዲንን ህልፈተ ህይወት አረጋገጠ !!

▪️የሊባኖሱ ሒዝቦላህ መግለጫ አውጥቷል - የንቅናቄው ስራ አስፈፃሚ የምክር ቤቱ መሪ የሆኑት “ሰይድ ሀሽም ሳፊኡዲን” በእስራኤላውያን የአየር ድብደባ መገደላቸውን አረጋግጧል።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

23 Oct, 15:18


❗️#Breaking

🇹🇷በአንካራ ቱሳሽ ኤሮስፔስ ኩባንያ ግቢ ውስጥ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት ሁለት የጥበቃ አባላትን ጨምሮ 9 ሰዎች ተገድለዋል።

(የመጀመሪያዎቹ 5 ምስሎች የሚያሳዩት በህንጻው ላይ ጥቃት የሰነዘሩ አሸባሪዎችን ነው። ምስሎቹ በቅድሚያ ታጋቾችን በመያዝ ላይ መሆናቸውን ያሳያሉ።)

ታጣቂዎቹ መትረየስ፣ ሽጉጥ እና በልዩ ደረጃ ከፍተኛ መጠን ያለው ጥይት የታጠቁ ነበሩ።

ታጣቂዎቹ በታክሲ ወደ ስፍራው የደረሱ ሲሆን በቅድሚያ በሁለት ቡድን ተከፋፍለው፣ ከመካከላቸው አንዱ አጥፍቶ ጠፊ በፍተሻ ጣቢያው ላይ ራሱን በፈንጂ በማፈንዳት በፍንዳታው ምክንያት ሁለት ጠባቂዎችን ገደለ።

ሌላኛው ቡድን ታጋቾችን በመውሰድ በፍተሻ ኬላው በኩል አለፉ ሲል የቱርክ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በአሁኑ ሰዓት የተኩስ ልውውጡ በህንፃው ውስጥ እንደቀጠለ ይገኛል።

በተጨማሪም ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ፍንዳታ መድረሱ ተዘግቧል።
ዝርዝር ማብራሪያ እየተሰጠ ነው....

የአንካራ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት በአሸባሪዎቹ ጥቃት ላይ ምርመራ ጀምሯል ተብሏል።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

22 Oct, 15:43


የሩሲያ ኢኮኖሚ በ 3.6% በማደግ ላይ ይገኛል !!
#IMF

ምንም እንኳን ከሀያላኑ ስብስብ ጋር የዓለማችን አስከፊውን ጦርነት በማድረግ ላይ የምትገኘው ሩስያ ዛሬም ለምዕራባውያኑ ራስ ምታት መሆኗን እንደቀጠለች ትገኛለች !

ዓለም አቀፉ ተቋም የሩሲያን የዕድገት ግስጋሴ #አስደናቂ ሲል ገልፆታል !

እ.ኤ.አ. በ 2024 የሩሲያ ኢኮኖሚ እድገት ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ ሆኗል- ይህ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የደረሰበት መደምደሚያ ሲሆን ባሳለፍነው የሐምሌ ወር የሩስያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አቅርቦት የነበረውን የ3.2% ግምቱን እንዲያሻሽል አስገድዶታል።

በዚህም መሰረት ተቋሙ እ.አ.አ በ2024 በበርካታ ሀገራት ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ግምገማ በሚከተለው መልኩ ይፋ አድርጓል፡-

🇮🇳 +7.0% - ህንድ
🇨🇳 +4.8% - ቻይና
🇷🇺 + 3.6% - ሩሲያ
🇧🇷 +3.0% - ብራዚል
🇺🇸 +2.8% - አሜሪካ
🇨🇦 +1.3% - ካናዳ
🇬🇧 +1.1% - ብሪታንያ
🇫🇷 +1.1% - ፈረንሳይ
🇮🇹 +0.7% - ጣሊያን
🇯🇵+ 0.3% - ጃፓን
🇩🇪 +0.0% - ጀርመን

አይ.ኤም.ኤፍ እ.አ.አ በ2024 በበርካታ ሀገራት የነፍስ ወከፍ እድገትን በተመለከተ ባስቀመጠው ግምት፡-
🇮🇳 + 6.0% - ህንድ
🇨🇳 +4.9% - ቻይና
🇷🇺 + 3.8% - ሩሲያ
🇧🇷 +2.6% - ብራዚል
🇺🇸 +2.3% - አሜሪካ
🇫🇷 +0.8% - ፈረንሳይ
🇯🇵+ 0.8% - ጃፓን
🇮🇹 +0.7% - ጣሊያን
🇬🇧 +0.6% - ብሪታንያ
🇩🇪— 0.4% - ጀርመን
🇨🇦 —1.5% - ካናዳ

በተጨማሪም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል ምስራቅ አፍሪካዊቷ 🇪🇹 #ኢትዮጵያን በ13ኛ ደረጃ ላይ ያሰፈረ ሲሆን የዕድገት መጠኗንም በ6.2% አድርጎ አስፍሯል።

Mayal Info World️

22 Oct, 14:56


የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በ #BRICS የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሩስያ ( ካዛን ) መግባታቸውን የአገሪቱ የፕሬስ አገልግሎት አስታወቀ።

video credit #TASS

Join us 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

22 Oct, 14:52


🇱🇧🇮🇱የእስራኤል አየር ኃይል አውሮፕላኖች በምሥራቃዊ ቤይሩት በሚገኙ አካባቢዎች ላይ ጥቃት በመሠንዘር ላይ ይገኛሉ።

በአሁኑ ሰዓት የአየር ድብደባው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዚህም ጥቃት የሊባኖስ አጠቃላይ የደህንነት መምሪያ አቅራቢያ የሚገኝ ህንጻ ተመትቶ በርካቶች በፍርስራሹ ስር ተቀብረው እንደሚገኙ ታስ የዜና ወኪል ከስፍራው ባሰራጨው ቪዲዮ አመልክቷል።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

22 Oct, 14:44


#Breaking

🇮🇱🇱🇧 የእስራኤል ጦር በፈፀመው የአየር ድብደባ በቤሩት የሚገኝን ባለ 10 ፎቅ ህንጻ አፍርሶ የ20 አባውራዎች ቤቶችንና ውስጥ የነበሩ ጥቂት ኗሪዎችን ሙሉ ለሙሉ አወደመ።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

19 Oct, 18:45


የኢራን ፕሬዝዳንት ቢሮ፥ " ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያን በቀጣዩ ሳምንት (ማክሰኞ) ወደ ሩሲያ በመጓዝ በ16ኛው የብሪክስ+ ጉባዔ ላይ ንግግር ያደርጋሉ " ሲል አስታወቀ።

Join👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

19 Oct, 18:38


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በቂሳርያ የሚገኘው ቤታቸው ጥቃት ከተፈፀመበት በኋላ ባስቀረፁት የ24 ሰከንድ ቪድዮ ባሰራጩት መልዕክት ላይ ለጥቃቱ በሰጡት የመጀመሪያ ምላሽ ምላሻቸው " ወደፊት መግፋታችንን እንቀጥላለን - እናም በምድር ላይ ምንም ኃይል ሊያስቆመን አይችልም " ብለዋል።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

19 Oct, 08:10


#BREAKING

ሄዝቦላህ የሰው አልባ አውሮፕላን በመጠቀም የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር #ኔታንያሁን ለመግደል ሙከራ አድርጓል፡ - በጥቃቱም የኔታንያሁ የግል መኖሪያ ቤት የተመታ ( የተቃጠለ ) ሲሆን በወቅቱ ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ በቤት ውስጥ አልነበሩም ተብሏል።

ይህንንም ተከትሎ የሊባኖሱ ታጣቂ ሄዝቦላህ በሰጠው መግለጫ የትም የሁን የትም ነፍሰ በላውን ሚንስትር አድንን እንገላቸዋለን ብሏል።

Join us 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

19 Oct, 04:25


— በተናጠል የ #BRICS ምንዛሪ ለመፍጠር ጊዜው አሁን አይደለም - ይህ ከግምት ውስጥ አልገባም። #የBRICS አገሮች በራሳቸው መንገድ የስዊፍት ተተኪ የሆነ የገንዘብ የዝውውር ስርዓትን ለመፍጠር በርትተው እየሰሩ ነው።

— በሩሲያ፣ በቻይናና በሕንድ አዎንታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ቢጠበቅም በአፍሪካና በደቡብ ምሥራቅ እስያ አገሮች ግን ፈጣን ዕድገት እንደሚኖር አመላካች ፍንጮችን እያየን ነው።

—በአሁኑ ጊዜ ብሪክስ የምድሪቱን 33% ይዞታ እንዲሁም 45 በመቶ የሚሆነውን የፕላኔቷን ሕዝብ የያዘ ነው ! ብሪክስ "የፀረ-ምዕራባውያን ማኅበር አይደለም፣ ነገር ግን በቀላል አገላለፅ የምዕራባውያን ማኅበር አይደለም።

— ዩናይትድ ስቴትስ የቻይናን ዕድገት ማስቆም አትችልም፤ ይህንን ማድረግ ከሚችሉበት 15 ዓመት ያህል ዘግይታለች። በተመሳሳይም ዩናይትድ ስቴትስ አውሮፓውያንንና ኔቶን እንደ ትንንሽ ውሾች ከቻይና ጋር ወደሚያላትም ግጭት እየጎተተች ትገኛለች።

— የሩሲያና የቻይና ትብብር በዓለም ላይ የተረጋጋ ሁኔታ እንዲከሰት ከሚያደርጉት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ነው። በአገሮች መካከል በዓይነቱ ልዩ የሆነ የመተማመን ግንኙነት የዳበረ ሲሆን የንግድ መጠኑም ይህን ያረጋግጣል። በቻይና የንግድ ልውውጥ ላይ የሩሲያ ድርሻ እያደገ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በአራተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

— ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ሁለት መንግስታት - (እስራኤል እና ፍልስጤም) - እንዲፈጠሩ ያሳለፈው ውሳኔ ተግባራዊ መሆን አለበት ከሚለው እውነታ ጋር ሁሌም ቀጥላለች። እናም ፍልስጤማውያንም ከዚያ አይወጡም። ይህች ምድራቸው ናት። ይህን መረዳት አለብን። ፍልስጤማውያን በምድራቸው ላይ የመጡባቸውን ወራሪዎች መመልከትና ታግለው ነፃነታቸውን የማስከበር ሙሉ መብት አላቸው።

— ዩክሬን በምንም ዓይነት ሁኔታ የኒውክለር መሣሪያዎችን እንድትሰራ ሩሲያ አትፈቅድም !!

— በዩክሬን ውስጥ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለመፍጠር ለሚወሰዱ እርምጃዎች "ተገቢው ምላሽ" ይሰጣቸዋል። በተመሳሳይም ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት በተቻለ ፍጥነት ለማስቆም ፍላጎቱ አላት። ይሁን እንጂ ግጭቱን ለማስቆም የሚያስችል የጊዜ ገደብ ማውጣት ውጤታማ አይደለም።

—ዘመናዊው የጦርነት መንገድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚደረግ ግጭት ነው ፣ ይህም የሂሳብ ሊቃውንቶች ጦርነት ነው።

—ሩስያ በዩክሬይን ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ በማቆም ላይ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ናት። ሆኖም ግን በኢስታንቡል ስምምነቶች መሰረት ብቻ ከሆነ ነው።

— ድል የኛ ይሆናል !

Mayal Info World️

19 Oct, 04:25


⚡️ ዘመናዊው የጦርነት መንገድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚደረግ ግጭት ነው ፣ ይህም የሂሳብ ሊቃውንቶች ጦርነት ነው።

ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት

ፕሬዚዳንቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆፍጠን ብለው እንዲሁ ደግሞ ፈታ ብለው ታዳሚውን እያዝናኑ ፣ እያሳቁ ፣ እያስገረሙም በርካታ የሆኑ የዓለም አቀፍ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸው ውስጥ ያለው በራስ የመተማመን መንፈስ ከሌላው ጊዜ ለየት ያለ ሆኖ ተመልክተነዋል።

ፑቲን የብሪክስን ወቅታዊ ቁመና አስመልክተው በተናገሩት ንግግር ምዕራባዊያኑን " እንቁልልጭ " ከማለት በማይተናነስ ሁኔታ ምራቃቸውን ለማስዋጥ ሞክረዋል።

ፑቲን በሞስኮ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ የአገራት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ከየአገራቱ የሚዲያ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረው ነበር። ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል:- በቀጣዩ ይዘት እነሆ !
👇🏽👇🏽👇🏽