ታድያ አንድዋ ተዘያሪ ኮዬ ንፋስልክ የምትገኝ የሶስት ልጆች እንት ስትሆን አባታቸዉ በጎሮሮ ካንሰር ታሞ ጳዉሎስ ከተኛ ሰንበት ብሎዋል።
ለልጆችዋም የለት ዳቦ እንዳያጡ ስትል ልብስ እያጠበች ዳቦ ትገዛላቸዋለች። እናት
አይዞሽ ባይ ሚላት እንኪ ኢሄ ለዛሬሽ ሚላት ቤተሰብ አጠገብዋ የላት ።
ይችን እህታች መጪዉ ረመድዋን ነዉ እና ሰዎችን ለምኜ ለመብራት ሳምቡሳ ለመጥበስ አስብያለዉ ብላን ነበር። ታድያ መጥበሻዉ አለሽ ወይ ብለንም ስንጠይቃት የለኝም እንደዉ ካገኘሁ አለችን።
ሙዕሚናትም ከደጋግ ሙዕሚኖች ጋር በመሆን ለዚች እናት ለልጆችዋ ዳቦ መግዣ የሳምቡሳ መጥበሻዉን ማሽን ገዝቶ ለመስጠብ አስቦዋል።
ሌላኛዉ ተዘያሪ ከዚ ቀደም ህፃን መሀመድ ይመር አስተዋዉቀናቹ ነበር የእግር ካንሰር ታማሚ ነዉ ወደ ህንድ ሀገር ሄዶ እግሩ በጨረር ስለተጎዳ ብለዉ መዳኒት አዘዉ ለት 3 ወር ቀጥረዉት ተመልሶዋል። አልሀምዱሊላህ በአላህ ተስፋ አይቆረጥ………………
ቤታቸዉ ጠባብና የቀለም እድሳት ሚያስፈልጋት ናት። ታድያ ይቺን ቤት ለረመዷናቸዉ ፏ ለማድረግ ሙዕሚናት አስቦዋል ከሙዕሚን እህት ወንድሞች ጋር በመሆን።
ታዲያ በነዚ ቀላል ኸይር ስራዎች ላይ መሳተፍ ምትፈልጉ ደጋግ የአላህ ባሮች በገንዘብ ፣ በልብስ፣ በቁስ፣ በሌሎችም እራሳቸዉንም ቤተሰቦቹን በግል ማግኘት ምትፈልጉም @umi_asiya አናግሩኝ።
አማኝ ጎሮቤት ተርቦ እርሱ ጠግቦ አያድርም።
የሙስሊም እህት ወንድሞች ችግር የኛም ችግር ነዉ። የነሱ ደስታ ደስታችን ነዉ።
ሙዕሚናት የጅልባብና ኒቃብ በጎ አድራጎት ጀምዐ