Berbir Mereja / በርብር መረጃ @berbirmereja Channel on Telegram

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

@berbirmereja


Welcome back to our channel, where we bring you the latest updates and news from around the world.

Berbir Mereja / በርብር መረጃ (Amharic)

በርብር መረጃ የሚበልጥ ምርጫ ጥቅምት መነሻ እያንዳንዱ በቀጥታ የሚመረጥ እና ለሁለት ደቂቃና የዛሬ ዕድል የተከበረ ቦታ ነው። ይህን መከታተል የሚያስፈልጋቸው አስተዋጽዖ ሌላ ደረጃ እና አገልግሎታው ነበር። በአንድነት ለተለያዩ የአሳፋሪ መረጃዎችና አተም ታሪኬዎች መሠረት ፍየልን ለማቆየት ዋና ዘገባዎችን ተጠቀሙባቸው። በመሆኑ ብዙ ቦታዎችን ይጣሜ ወይም እንዴት በራስ ያሔደች ማየት እንዳለ በዚህበላይ መረጃ ድረስባን ጥረት ሲደረግ አዩ። የባለእንግሊዝኛ ጉዳይ እና መረጃችንን በቀላሉ አልበጣም። በበርብር መረጃ ከመጀመሪያ እንቅስቃሴ እስከ 7ፊንደል እስከ 1 ሰብኃ ከሚመለስ መንገድ እስከ ሳታከሚ ምንም በመጠቀም ሳያበቃል። በበርብር መረጃ በጥቅምት ብቻ እንዳለ ጥቅምት ምስል አምላክን የመማሪያ ነገር እንሆናለን።

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

21 Nov, 14:38


ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃት ፈጸመች

ጥቃቱ ዩክሬን በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይሁንታ በአሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎች በሩሲያ ላይ ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃቱ የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ÷ሩሲያ በዛሬው ዕለት አዲስ የሮኬት አይነት ወደ ዩክሬን ማስወንጨፏን አረጋግጠዋል፡፡

ሮኬቱም የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ባህሪያት እንዳሉት ፕሬዚቱዳንቱ መናገራቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ሩሲያ ወደ ዩክሬን ያስወነጨፈችው የባላስቲክ ሚሳዔል ሳይሆን እንዳልቀረ ስማቸው ያልተጠቀሱ ምዕራባውያን ባለስልጣናት መግለጻቸው ተጠቁሟል፡፡

🎆      🎆     🎆     🎆      🎆     🎆  

⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ         

  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                          

  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/           

  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

21 Nov, 13:36


የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ

የሶማሊያና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ፍጥጫ በተካረረበት ዛሬ ላይ በፑንትላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች የሶማሊያ ወታደሮችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉ ተሰምቶ በግብፅ የሚነዳዉ የሼክ መሀሙድ መንግስት ተደናግጧል፡፡

ሶማሌላንድን አይቶ ከዛሬ ጀምሮ እኔም እራሴን የቻልኩ ሪፐብሊክ ሃገር ሆኛለሁ ያለው የጁባ ላንድ መንግስት እንደ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላደርግ ነው ማለቱን ተከትሎ ሃሰን ሼክ መሃመድ ግዙፍ ጦር ወደ ጁባላንድ መላካቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ወታደሮች ጁባላንድ ግዛት ዶሎ አየር ማረፊያ ላይ ስድስት የሱማሊያ ወታደሮችን እንዳሠሩ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግቧል፡፡ ከሞቃዲሾ የተነሱት ወታደሮች በታሠሩበት ወቅት ሲቪል ለብሰው እንደነበር ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ወታደሮቹ ታሠሩ የተባለው፣ የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት ጁባላንድ በቅርቡ ልታካሂደው ያሰበችውን ቀጥተኛ ያልኾነ ምርጫ ኃይል በመጠቀም ለማስተጓጎል እንዳቀደ እየተነገረ ባለበት ወቅት ላይ ነው።

ከኢትዮጵያ ጋር ልዩ ግንኙነት ፈጥራለች የምትባለው ጁባ ላንድ የራሴን ፕሬዝዳናት እመርጣለሁ ሃሰን ሼክ መሃመድ የእኔ መሪ አይደለም በማለት ምርጫውን ለማድረግ ስትወስን የሶማሊያ ጦር ጁባ ላንድ ካለው ጦር ጋር ለመፋለም ትላንት ጁባላንድ ደጅ ደርሷል።


🎆      🎆     🎆     🎆      🎆     🎆  

⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ         

  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                          

  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/           

  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

21 Nov, 10:56


Major ማከፋፈል ጀመረ👏

Major ስትሰሩ የነበራችሁ የበርብር ቤተሰቦች የለፋችሁበትን chek አድርጉ Token መከፋፈል ተጀምርዋል።

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

21 Nov, 10:31


“በአስር ወራት ብቻ 20ሺ የሚሆኑ ኤርትራውያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል” - የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን

ከጥር ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አስር ወራት 20ሺ የሚሆኑ ኤርትራውያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አስታወቀ።ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ጥገኝነት በመጠየቅ የሚኖሩ ኤርትራውያን የተጠናከረ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቋል።
"ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች በአፋር እና ትግራይ ክልሎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡት አለም አቀፍ ከለላ እና መሰረታዊ እርዳታ ለማግኘት ነው" ሲል ኮሚሽኑ ትላንት ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በአስር ወራቱ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ከተሰደዱ 20ሺ ኤርትራውያን በተጨማሪ በኢትዮጵያ ከ70 ሺ የሚበልጡ በኮሚሽኑ የተመዘገቡ ስደተኞች መኖራቸውንም የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በመግለጫው አመላክቷል።
በስደት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኤርትራውያኑ ስደተኞችን እንደደረሱ ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል ያለው ኮሚሽኑ ስደተኞቹን መመዝገብ እና ሰነድ እንዲዘጋጅላቸው ማድረግ ለሚሰጣቸው ከለላ የመጀመሪያው እና ወሳኙ እርምጃ ነው ሲል አሳስቧል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ጥገኝነት የሚጠይቁ ኤርትራውያንን ለመመዝገብ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል፤ ምዝገባ መካሄዱ ኤርትራውያን ስደተኞች ማግኘት የሚፈልጉትን የጤና፣ የትምህርት አገልግሎቶች፣ ከቤተሰብ ጋር የመገናኘት እድሎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ለመስራት የሚያስፈልጋቸውን ፈቃድ ለማግኘት መመዝገባቸው ወሳኝ ነው ሲልም አስታውቋል።ስደተኞቹ በአፋጣኝ እንዲመዘገቡ ማድረግ የህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እጅግ አስፈላጊ ነው ሲልም አመላክቷል።



🎆      🎆     🎆     🎆      🎆     🎆  

⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ         

  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                          

  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/           

  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

21 Nov, 10:30


የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስወረድና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ዛሬ ተጀመረ።

የመጀመሪያው ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝድ በማድረግ ወደ ስልጠና ማእከላት የማስገባት ስራ በመቐለ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

በመጀመሪያ ዙር በክልሉ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ስልጠናና የማቋቋምያ ገንዘብ በመስጠት ወደ ህብረተሰቡ የማቀላቀል ስራ ይሰራል።

በአሁን ሰዓት ታጣቂዎች የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የትግራይ ክልል የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ አመራሮች ፣ የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪዎች እና ሚድያዎች ፊት የታጠቁትን ቀላል መሳሪያ እያስረከቡ ነው።

በዛሬው ዕለት 320 የትግራይ ተዋጊዎች ቀላል መሳሪያዎችን አውርደው በማስረከብ ወደ ተሃድሶ ያስልጠና ማዕከል አቅንተዋል።

ዛሬ በተካሄደ ይፋዊ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያው ፤ " የዴሞብላይዜሽን አሰራር ሴት ተዋጊዎችን ፣ አካል ጉዳተኞችን እና በአደረጃጀት ውስጥ ያሉ አመራሮችን በማስቀደም ይፈፀማል " ብለዋል።

በዴሞብላይዜሽን አሰራር በየቀኑ 320 ታጣቂዎች ወደ ስልጠና ማእከላት የማስገባት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በመጀመሪያ ዙር 75 ሺህ ታጣቂዎች እንደሚስተናገዱ አክለዋል።

" ማንኛውም ትጥቅ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ መያዝ የሀገሪቱ ህገ-መንግስት ይከለክላል ስለሆነም በትግራይ እየተፈፀመ ያለው የዴሞብላይዜሽን አፈፃፀም ህግና ስርዓት ተከትሎ የሚፈፀም ነው " ሱሉ ተናገረዋል።

#Tikva

🎆      🎆     🎆     🎆      🎆     🎆  

⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ         

  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                          

  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/           

  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

20 Nov, 16:35


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጋምቤላ ክልል የተገነባውን ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኩባንያው በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ በተከናወነው ትርጉም ባለው የኢንቨስትመንት ሥራም ለሁሉም አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሒደት ለብዙ ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገ-ወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ ለማዋል ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያሳይም ነው ያስረዱት፡፡


🎆      🎆     🎆     🎆      🎆     🎆  

⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ         

  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                          

  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/           

  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

20 Nov, 16:04


ሰበር ዜና☄️☄️

ሩሲያ የኒዉክለር መከላከያ ምሽግ እየገነባች

የአሜሪካ የኒዉክለር አዉሮፕላን ሚስጥራዊ በረራ

🩸ዛሬ አለም ሲፈራው የነበረው አርማጌዶን ደረሰ ያስባለ ልብ ቀጥ የሚያደርግ ጉድ ነው ከሩሲያ የተሰማው።

ሩሲያ ከኒውክለር ጥቃት ማምለጫ የሚሆኑ ባንከሮችን ለህዝቦቿ እያዘጋጀች መሆኑ ሲሰማ የአሜሪካ ኒውክለር አውሮፕላን ሚስጥራዊ በረራ ማድረጉ ተደርሶበታል።

አሜሪካ ላይ የኒውክለር ጥቃት ሊፈጸም ሲል ብቻ ሰማይ ላይ የሚታየው የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ከ አየር ማረፊያው ተነስቶ ሚስጥራዊ በረራ መጀመሩን ሚስጥር በርባሪ የዜና ገጾች ይፋ አድርገዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ወታደራዊ አውሮፕላን የኒውክሌር እንቅስቃሴዎችን ከሰማይ መለየት የሚችል የአየር ናሙና ተልዕኮ ወደ ህንድ ውቅያኖስ ሲያመራ ታይቷል።

🩸ከአሜሪካ ቤት ይሄ ከመሰማቱ ከሰዓታት ቀደም ብሎ ከሞስኮ በተገኘ መረጃ ሩሲያ የኒውክለር ጥቃት ሲፈጸም ህዝቦቿ የሚገቡበት ባንከር በድብቅ እየተገነባ መሆኑን ውስጥ አዋቂ ታማኝ የዜና ምንጮች ጠቁመዋል።

የሩሲያ ኒውክለር ሃይል በባህር፣ በየብስ፣ በጦር አውሮፕላን እና ከሳታላይት ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ቦታ ቢታ መያዛቸውን ቢልድን ጨምሮ ሌሎችም ዘግበዋል። ይሄን አይቶ ጭንቅ የገባው የአሜሪካ ጦር ኒውክለር ጥቃት አነፍናፊ አውሮፕላኑን ልኳል።

የአሜሪካ ጦር ይሄን ኒውክለር ጥቃት አነፍናፊ አውሮፕላን የለቀቀው ከምድር ብቻ ለሚፈጸሙ የኒውክለር ጥቃቶች ሳይሆን ከጠፈር ላይ ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ጭምር መሆኑን ያስታወሰው ዘገባው ለምን በዚህ ግዜ አሜሪካ ይሄን ማድረግ እንደፈለገች ከመግለጽ ተቆጥባለች ብሏል።

ኮንስታንት ፊኒክስ አሊያም "ኑውክለር ስኒፈር" በመባል የሚታወቀው ይህ የሰማይ ንስር ሬድዮአክቲቭ በቅጽበት ከከባቢ አየር ውስጥ የሚገኙ ብናኞችን እንዲሁም የጋዝ ልቀቶችን እና ፍርስራሾችን ሲለቀቁ አስቀድሞ በማሽተት በቀጥታ ለአሜሪካ ኒውክለር ጦር ምልክት በመስጠት አሜሪካ የአጸፋ ምላሽ እንድትሰጥ ማድረግ ዋነኛ ስራው ነው።

🎆      🎆     🎆     🎆      🎆     🎆  

⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ         

  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                          

  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/           

  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja