ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy) @liquism Channel on Telegram

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

@liquism


ሊቅነት ለኢትዮጵያዬ
This is a High Performance industry that creates ICON'S through SUCCESS SYSTEM that never never fails.I.e

(Liquism/ሊቅነት)
Consult Us
+251910369257
+251929192323

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy) (Amharic)

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy) የኢትዮጵያዬውን ሰው የሚሰጥን ሥራ ነው። ይህ የለቀቀ ስራ አስተዋይ ነው እና መልኩም አሉ። የሊቅነት ለውጥ (Liquism) ተማሪዎችን ከሚሰክሩ ሃይሎች ጋር የደረሰን ስራ ነው። በሌላው አለም። ሊቅነት ለማህበረሰብ መዉከልና አስተናወታሁም አለን። እናሺን። ሊቅነት፦ ሊቅነት፦ሊቅነት
አስማሙበት

+251910369257
+251929192323

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

12 Nov, 16:36


Never STOP ሊቅ!

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

10 Nov, 07:32


ከElon Musk የተማርኳቸው አሪፍ ባህሪዎች
ሙሉውን በዩቱብ ተከታተሉ!
https://youtu.be/yUFmGiG6sZY?si=dP6qDO3fdbged3oL

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

07 Nov, 04:46


አስተሳሰባችንን ነን።

  🎯 እኔ እና እናንተ የገዛ አስተሳሰባችን/አመለካከታችን ድምር ውጤት ነን።  

☑️አመለካከት =
          ሀሳብ + ስሜት + ተግባር

👉🏾 ይህ ሲባል ደሞ በሁለቱም በኩል የሚሰራ ነው ማለትም በአሉታዊም በአወንታዊም በኩል።
 
🎯ስለዚህ አሁን ባለህበት ህይወት የፍርሀት ፣ የጭንቀት ስሜቶች እየተፈጠረ ከሆነ እነዚህን ስሜቶች የምታሸንፍበት ብቸኛውን መንገድ ልንገርህ ወዳጄ። እኛ የሰው ልጆች በልዩነት በተሰጠን አዕምሯችንን በመጠቀም ስሜታችንን የመቆጣጠር ነፃ ፍቃድ አለን።

ይህን በመጠቀም አሁን ላይ ከሚሰማን የማንፈልገው ስሜት ወጥተን በምርጫችን የምንፈልገውን ስሜት መፍጠር እንችላለን።

👉🏾 አሉታዊ አስተሳሰቦቻችንና የአእምሮ ስእሎችን ከማስተናገድ ልንቆጠብ ይገባል።

        ⚠️ ልብ እንበል
                
   🌑ጨለማን ማስወገጃው መንገድ ብርሀን ነው።
🥶ቅዝቃዜን የመቋቋሚያው መንገድ ሙቀት ነው።

😡አሉታዊ የሆኑ አስተሳሰቦችን የማስወገጃው መንገድ ደግሞ በመልካም አስተሳሰብ መተካት ነው።

   🎯 መልካም ነገርን በእርግጠኝነት እንቀበል። የዚያኔ መጥፎው ነገር ደብዛው ይጠፋል።

    ስለዚህ ምን እናድርግ

🎯እለት እለት ለራሳችን ጊዜ በመስጠት ከእኛ የሚጠበቀውን እናድርግ ይህም ሲባል፦
                  🎯
    ሰው አንድን መልካም ነገር
በአይምሮው አስቦ ፣
በልቡ ማመን ከቻለ
በእጁ ይጨብጠዋል።
                
  🎯እለት እለት ሆን ብለን በአምስቱ የስሜት ህዋሳችን መልካም ነገሮችን እንፍጠር።
    መልካም ነገር ይታየን
መልካም ድምፅ ይሰማን
መልካም ነገር እንዲሸተን እናድርግ
መልካም ስሜት እንዲሰማን እናድርግ
መልካም ነገር የመቅመስ ያክል ይሰማን።

አስተሳሰባችንን በመቀየር ህይወታችንን እንቀይር።

ይምጡ።ይማሩ።ይደጉ።
Paradigm Shift Trainin
ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ ስልጠና
በአካል/በኦንላየን
በ 0929192323 ይደውሉ።

አድራሻ
ቄራ ዳውንታውን
4ኛ/#307
    
        ሊቅነት ማይንድሴት
እምቅ አቅም፣ጀግንነት፣ ሃብት

ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያካፍሉ
    እናመሰግናለን!መልካም ቀን!🙏

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

05 Nov, 05:30


የአመለካከት ለውጥ

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

01 Nov, 05:40


ሚስቴ ስታስተዋውቀኝ...

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

24 Oct, 05:48


አሪፍ መላበስ ያለባችሁ ባህሪዎች

ውጤታችን የባህሪያችን ነፀብራቅ ነው። ባህሪህ ከተበላሸ ውጤትህ ይበላሻል ከተስተካከለም እንደዛው። የተወሰኑትን እንይ።

ታማኝነት
በጣም አስፈላጊ ከሆኑት የባህርይ ገጽታዎች አንዱ ታማኝነት ነው.
ታማኝነት ሐቀኛ መሆን እውነት መሆን ቃላችንንና ቃልኪዳናችንን መጠበቅ ማለት ነው።
ጠንካራ ታማኝነት ያላቸው ሰዎች እምነት የሚጣልባቸውና  አስቸጋሪ ወይም ተወዳጅነት በማይኖርበት ጊዜም እንኳ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ሁልጊዜ የሚጥሩ ሰዎች ናቸው። ታማኝ ሁን።

ርህራሄ
ሌላው አስፈላጊ የባህርይ ገፅታ ነው። ይህ የሌሎችን ስሜት የመረዳት እና የመጋራት ችሎታን ያመለክታል. ርህሩህ ሰዎች ሩህሩህ እና ተንከባካቢ ናቸው፣ እና በጥልቅ ደረጃ ከሌሎች ጋር መገናኘት ይችላሉ። ርህራሔ መብዛት ግን የለበትም። ርህሩህ ሁን።

ድፍረት
የሚያመለክተው ፈተናዎችን ለመጋፈጥ እና መሰናክሎችን በጀግንነት እና በቆራጥነት ለማሸነፍ መቻልን ነው። ደፋር ሰዎች ችግር ቢያጋጥሟቸውም አደጋን ለመቀበል እና ለሚያምኑት ነገር ለመቆም ፈቃደኞች ናቸው። ደፋር ሁን።

ለአንድ ሰው ባህሪ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሌሎች ጠቃሚ ባህሪያት ደግነት, ልግስና, ትህትና, ጽናት, ጥንካሬ, ራስን መግዛት እና ኃላፊነትን መውሰድን ያካትታሉ.

ባህሪ ብዙ የተለያዩ ባህሪያትን  የሚያጠቃልል ውስብስብ ጽንሰ-ሐሳብ ነው. እንደ ግለሰብ የማንነታችን አስፈላጊ አካልና ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት የሚቀርጽ ነው።

ጠንካራ ባህሪን ማዳበር ራስን ለማወቅና ለግል እድገት ዋነኛው መሰረት ነው።

ይምጡ የተሻለ ባህሪ ይገንቡ የተሻለ ውጤት ይቀዳጁ።
ሊቅነት የአስተሳሰብ ለውጥ

ራስን የማሳደግ ስልጠና
ለ2 ወራት የሚሰጥ ኢንተርናሽናል ስልጠና በኦንላየንና በአካል።
0929192323 ይደውሉ

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

20 Oct, 13:08


እውቀትን በጥበብ!!!

“አዋቂ ሰው ምን እንደሚናገር ያውቃል፣ ጥበበኛ ሰው ግን መቼ መናገር እንዳለበት፣ እንዴት መናገር እንዳለበት እና ነገሩ ሊነገር የሚገባው መሆኑንና አለመሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል” - ካልታወቀ ምንጭ

የሕይወታችሁ አብዛኛው አበሳ እንዲቀንስ ከፈለጋችሁ የምትናገሩትን ነገር ማወቃችሁ ብቻ በቂ እንዳልሆነ አምናችሁ መቀበል የግድ ነው፡፡

“ጥሬ” እውቀት እንደ አፈር በበዛበት የመገናኛ ብዙሃን ዘመን ውስጥ ነን ያለነው፡፡ ከዚህ በፊት ቀድተን ውስጣችን ካጠራቀምነውም (Save ካደረግነው) ሆነ እዚያው በዚያው እየቀዳን (Copy-Paste በማድረግ) መርጨት የምንችለው እውቀት እጅግ ብዙ ነው፡፡

ይህ እድል በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውም እውቀት ብቻውን ረጅም ርቀት እንደማያስኬደን ማስታወስ ግን ጠቃሚ ነው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ አዲስ ጎዳናን መጀመር እንችላለን፡፡ ይህ ጎዳና በእውቀት ላይ ጥበብን የጨመረ ጎዳና ነው፡፡ ይህንን ጎዳና መጓዝ ስንጀምር አንድን መረጃ ስላገኘን፣ አንድን ነገር ስላነበብንና አንድን ቀድሞ የማናውቀውን እውቀት ስላወቅን ብቻ አንናገረውም፡፡ በእውቀታችን ላይ ጥበብን ገዢ የማድረግንም ልምምድ እናዳብራለን፡፡

ማንኛውንም ሃሳብ ከመሰንዘራችን በፊት የሚከተሉትን ጥያቄዎች የመጠየቅ ልማዱ ይኑረን . . .  

1.  ይህንን ነገር መናገር አስፈላጊና ተገቢ ነው?

2.  ይህንን ነገር ለመናገር ትክክለኛው ጊዜ ነው?

3.  ይህንን ነገር በምን መልኩ ነው መናገር ያለብኝ?
         Liqnet Mindset
         Your Freedom

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

14 Oct, 04:43


ድንቅ የሊቅ ምክሮች..ሂሳቧንም በዛው..#share
🙉 እንደ ዳዊት ሊያነግስህ ሲፈልግ ጎልያድን የሚያክል ችግር ይሰጥሃል!

 🙉 አንተ ጎንበስ ካላልክ ማንም ጀርባህ ላይ አይወጣም!

 🙉 የወደቁትን ለማንሳት አቅሙ ከሌለህ ፣ ቢያንስ ለሚዋደቁት ምክንያት አትሁን!

 🙉 ያለምክንያት የሚወድህን ፈጣሪ እያሰብክ ፤ ያለምክንያት የሚጠሉህን ሰዎች እርሳቸው!

🙉 በህይወት መንገድህ አታርፍድ ፣ ካረፈድክም አትቅር ፣ ምክንያቱም ካረፈድክ ትቀጣለህ ፣ ከቀረህ ግን ታጣለህ!

🙉 ያልሆነልህ ነገር ካለ ለኔ አልተጻፈም በል እንጂ፣ የበታችነት ስሜት አይሰማህ። ማንም የፈለገውን ህይወት ሳይሆን፣ ፈጣሪ የፃፈለትን ነው የሚኖረው።

🙉 ለፈጣሪ የሚንበረከክ በማንም ሰው ፊት መቆም ይችላል።

🙉 የምትፈልገውን ህይወት ለማግኘት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፍ ይጠበቅብህ ይሆናል፤ ካንተ የሚጠበቀው ግን ተስፋ አለመቁረጥ እና ታጋሽ መሆን ነው።

🙉 አስታውስ! የምትወድቀው ሌሎችን ለመጣል ስትሞክር ነው!

🙉 ከእንቅልፍህ ስትነሳ ፈጣሪህን ማመስገንህን አትርሳ ምክንያቱም እሱም አንተን ማንቃት አልረሳምና!

🙉 ብቻህን ስትሆን ራስህን፣ ከሰው ጋር ስትሆን ደግሞ ምላስህን ጠብቅ!

🙉 አልሳካ ሲልህ መንገድህን እንጂ ዓላማህን አትቀይር፤ ዛፍ ቅጠሉን እንጂ ስሩን አይቀይርምና!

🙉 ጥሩ ሰው ከመፈለግ ጥሩ ሰው መሆን ይሻላል!

🙉 ሦስት ነገሮችን እመን፦ ፈጣሪህን፣ ስህተትህንና ያየኸውን።

#ሼር#Share አርጉ!
#ሊቅነት #የአስተሳሰብ #ለውጥ #inspire #fyp  #motivation #fyp #foryoupage #LikeShareFollow #ሊቃውንት #foryoupage #motivation #LikeShareFollow

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

13 Oct, 06:54


✍️ራስን መውደድ፣ ራስን ማክበር፣ ለራስ ክብር መስጠት ካስተዋልክ ሁሉም  የሚጀምሩት በ"ራስ" ነው ምክንያቱም ካንተ ውጪ በማንም ሰው ውስጥ ልታገኛቸው ስለማትችል ነው።

✍️ለሚንቁህ ዝቅ አርገው ለሚያዩህ መልስ የምትሰጠው በተግባር ብቻ ነው! እንደዚህ አይነት ሰዎች የሚሰሙት በአይናቸው ነው፤ ለውጥህን በተግባር ካላሳየሀቸው የምትናገረው ነገር ብቻውን ዋጋ ቢስ ነው።

✍️በጥረትህ  ማንነትህን አሳይ!
አንተን ከምትፈልገው ነገር የሚያገናኝህ የአላማ ፅናት ነው፤በህይወት የሚያሸንፈው እስከ መጨረሻው የሚጓዝ ነው።

✍️ወዳጄ ኑሮ ሊያደክምህ፣ ነገሮች ሊሰለቹህ፣ ህይወት ተደደጋሚ ልትሆን ትችላለች፤ የደስታን ጥግ ማየት ከፈለክ ግን ለአላማህ መኖር ከዛ ለአላማህ መሞት አለብህ!

✍️አብሮነትህ ከአላማህ ጋር ይሁን፣ ስራ ፣ ልፋ ራስህን አሳድግ ሁልጊዜ ወደ አላማህ ተጓዝ የዛኔ ምርጡን አንተን ታገኘዋለህ።

ድምቅ ያለ የበዓል ዋዜማ!
ይምጡ ስልጠናዎችን ይካፈሉ።
አድራሻ
ቄራ ዳውንታውን/22 ፕ.ኮ
0929192323

Please join and share the links
👉https://www.facebook.com/104741878048545/
👉https://t.me/liquism
👉https://vm.tiktok.com/ZM8GV9Y7U/
👉https://youtu.be/5T-R1m4L_UU
             
           ሊቅነት-ማይንድሴት
እምቅ አቅም፣ ጀግንነት፣ ሃብት

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

12 Oct, 04:59


ድንቅ ታሪክ አሁናዊ ኩነትን የሚያሳይ.....ኑ እንረባረብ፣ ተባብረን እንስራ...ሊቅነት
ለጊዜው ቢመስልም፤
ለኔ የመጣ ጢስ ላንቺ አይመለስም፡፡


በአንድ ገበሬ ቤት የምትኖር አይጥ ነበረች። ታዲያ ከለታት አንድ ቀን ይህችው አይጥ ገበሬው እና ባለቤቱ እቃ ሸምተው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ትመለከትና ለእኔ የሚሆን ምን ገዝተው ይሆን? ብላ በቀዳዳ አጮልቃ ስታይ ፍፁም ያልጠበቀችው ነገር፡፡ የተገዛው ነገር የሚበላ ሳይሆን የአይጥ ወጥመድ ነበር፡፡

በድንጋጤ ውስጥ እንዳለች ከጉድጓዷ ወጥታ እየሮጠች በግቢው ውስጥ ወዳሉት የቤት እንስሳት ሄደች፡፡ መጀመሪያ ያገኘችው ዶሮን ነበር… እየጫረች ጥራጥሬ ስትለቅም፡፡ “ማነሽ አንቺ ዶሮ፣ ኧረ ጉድ አልሰማሽ፣ ቤት ውስጥ ወጥመድ ተገዝቷል፡፡” ብትላት ጊዜ ዶሮዋ እየተቆናጠረች “እና ምን ይጠበስ! አንቺ ተጨነቂበት እንጂ እኔን የሚያሳስበኝ ነገር አይደለም” አለቻት፡፡

አይጧ እየተበሳጨች ወደ በግ ሄደችና “ስማኝማ አቶ በግ፣ ቤት ውስጥ የአይጥ ወጥመድ ተገዝቷል፤ እባክህ አንድ ነገር እናድርግ!!” ስትል በተማፅኖ ብጠይቀውም በጉ ካቀረቀረበት ሳር ላይ ቀና ሳይል “በጣም ያሳዝናል! ግን ልረዳሽ አልችልም፤ ራስሽ ተወጪው” አላት፡፡
አሁንም አይጥ ቁና ቁና እየተነፈሰች፣ ወደ በሬ ዘንድ ሄደችና ቤት ውስጥ ስለተገዛው ወጥመድ ነገረችው፡፡ በሬውም ምንም ሳይመስለው እንዲህ ሲል መለሰላት፣ “እንዴው ምን ይሻልሻል? ባይሆን በግና ዶሮ ይርዱሽና አንድ ነገር አድርጊ፤ እኔን እንኳን ተይኝ፡፡”
አይጧ ተበሳጭታ፣ “ኧረ ተው አንድ ነገር ብናደርግ ይሻላል፤ ለጊዜው ቢመስላችሁም ችግሩ የጋራችን ነው!!” ስትል ተናገረች፡፡

ሁሉም ተያይተው ተሳሳቁባት፡፡ “ቀልደኛ ነሽ!” እየተባባሉ፡፡ አይጥም ተስፋ ቆርጣ ወደ ጉድጓዷ ገብታ ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ሳይወስዳት አደረች፡፡

ማታ ወጥመዱ ተጠምዶ እያለ ቀጭ የሚል ድምፅ ሲሰማ የገበሩው ሚስት ተስፈንጥራ ተነሳች. . . ወጥመዱ የያዛትን አይጥ ለማየት፡፡ ጭለማ ስለነበረ በዳበሳ ወደ ወጥመዱ ሄዳ ወጥመዱን ስትነካው በአይጥ ፋንታ የተያዘው መርዘኛ እባብ ስለነበረ ነደፋት፡፡ በነጋታው የገበሬው ሚስት ከሀኪም ቤት ስትመለስ ራስምታት እንዳያስቸግራት ተብሎ ዶሮዋ ታረደችና ሾርባ ተዘጋጀላት፡፡ የገበሬው ሚስት ህመሙ እየጠናባት ሲሄድ በቶሎ እንድታገግም ተብሎ በግ ታረደላት፡፡ ሆኖም ግን ሴትዮዋ ማገገሟ ቀርቶ ሞተች፡፡ ይህንን ተከትሎ ዘመድ አዝማድ ለለቅሶ ሲመጣ ለተስካር በሚል በሬውም ታረደ፡፡

አይጥም ቁጭ ብላ እያለቀሰች ሶስቱም ሲታረዱ አየች።

ችግር ሲመጣ ለጊዜው አንድ ሰውን ብቻ የሚጎዳ ይመስላል፡፡ ሁሉም አያገባኝም ይላል፤ ቆይቶ ግን ሁላችንንም ይበላል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ሚዲያዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ በስልጣን ላይ የሚገኙ አካላትም ሆነ ተራው ዜጋ እዚህ አገር በሚከሰቱ ችግሮች ላይ በጋራ እስካልተንቀሳቀሱ ድረስ ለሁላችንም የመጣውን ችግር ከሥሩ ነቅለን መጣል አይቻለንም፡፡

ትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተ ችግር የትግራይ ብቻ ከመሰለን፤ አማራ ክልል ውስጥ ችግር ሲከሰት ኦሮሞን ካላስደነገጠው ወይም ሶማሌው በሀረሩ ችግር፣ ጋምቤላው በቤንሻንጉሉ ካልበረገገ፤ ሲዳማው በወላይታው፣ ጉራጌው በከንባታው፣ ሙስሊሙ በክርስቲያኑ ችግር ካልተረባረበበት ነገ የእሱን ቤት ማንኳኳቱ አይቀርም፡፡ በተለይም አሁን ላይ ብሄርና ሀይማኖት ተኮር ችግሮች የቱም ጋር ቢለኮሱ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በወላፈኑ የማይለበለብ በጢሱ የማይታፈን ሰው አይኖርም፡፡

ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ወይም ቡድኖች ልዩነቶቻቸውን በሌሎች ምክንያታዊ የውድድር ሜዳዎች ቢያስተናግዱ ይበጃል፡፡ ልዩነት ሊኖረን ቢችልም የጋራ የሚያደርገንም ነገር አለ፤ እሱም ‹የጋራ ቤታችን የሆነችው ኢትዮጵያ ናት›፡፡ የአገር ጉዳይ ነጥብ የማስቆጠርና ያለማስቆጠር አይደለም፤ የአገር ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ነው፡፡ አንዱን ክልል ከአንድ ፓርቲ ጋር አስተሳስረን በአገር ላይ የተደቀነ አደጋን ዝም ብንል ያለፍነው እንደሆን እንደሞኙ በግ፣ እንደ ቸልተኛው በሬ እና እንደ ሆድ አደሯ ዶሮ ከመበላት አናመልጥም፡፡
ያቺ አይጥ እንዳለችው. . .

“ለጊዜው ቢመስልም፤
ለኔ የመጣ ጢስ ላንቺ አይመለስም፡፡”
ተቀላቀሉን።
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/liquism
ቴሌግራም
https://t.me/liquism
ዩቱብ
https://youtu.be/4ipVPZQaUwI
For those who want trainings use
0910369257 ሊቃውንት
0929192323  ጀሚላ

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

03 Oct, 08:31


በህይዎትህ ሁለት ነገሮችን መንከባከብ አለብህ።

ብቻህን :… ብቻህን ስትሆን ሃሳብህን አስተሳሰብህ ተንከባከብ… ብዙ ሰዎች ሃሳብ አታብዛ አትተክዝ ይሉሃል አትስማቸው ህይዎትህን በራስህ መንገድ መኖር ካለብህ አእምሮህን በራስህ ሃሳብ መሞላት አለበት…

ምንም ያህል ጎበዝ ብትሆን አስተሳሰብህ ድንቅ ቢሆን ነገሮች በቦታቸው ላይ አይመጡልህ… ለምሳሌ የሆነ ሰው የሆነ ነገር ቢጠይቅህ በጠየቅህ ደቂቃ አእምሮህ መልስ አያፈልቅም process አለው ያንን process አንተ ብቻህን ልመደው አንዱን አንስተህ ሌላውን ጣል አንዱን ሃሳብ ገምብተህ ሌላውን አፍርስ የሃሳብ ድርዳራ የሃሳብ ግንባታ ከራስህ ጋር ሆነህ ተለማመድ…

ብቻህን መሆን ብቸኛ መሆን ከመሰለህ ተሸውደሃል እራስህን የምታገኘው ብቻህ ስትሆን ብቻ ነው…

ብቻህን መሆን አትፍራ መዝናናት ከራስ ጋር ሲሆን ጣዐሙ ልዩ ነው ማሰብ ከራስህ ጋር ሲሆን ጥልቅ ነው የሚያቆምህ የሚረብሽህ ተሳስተሃል ትክክል ነህ የሚልህ ሳይኖር ማሰብ ጣዐሙ ልዩ ነው…

ከራስህ ጋር ተከራከር ተሟገት አንድ የምታምንበት የራስህን ማንነት ጨምቀህ ታወጣለህ… የራስህ የማትቀይረው ማንነት ከሌለህ የሌሎች ሰዎች ሃሳብ ፌርማታ ነው የምትሆነው ተጠንቀቅ።

ከሰው ጋር :… ከሰው ጋር ስትሆን ምላስህን ቃላቶችህ ተቆጣጠር… አንዳድ ሰዎች ከሰው ፊት ሲቀርቡ ይለዋወጣሉ ያለእውቀታቸው አዋቂ ያለንፁህነታቸው ንፁህ ፃዲቅ መሆን ያበዛሉ…

እሰዎች ፊት ስትቀርብ ተረጋግተህ ውስጥህን አዳምጣህ የተነገራህን ሰምተህ የምትናገረውን መርጠህ ወደንግግርህ ስትገባ ጥሩ ቃላትን ከጥሩ አነጋገር ጋር ለሰዎች ትሰጣለህ።

የምትሽቀዳደም ለማውራት የምትጓጓ ከሆነ ግን ትሳሳታለህ ከራስህ ጋር ያልተግባባህበትን ነገር ትናገራለህ ያን አደረክ ማለት ደሞ ሰዎች ጋር ያለህን ቦታ ታጣለህ ሰዎች ጋር ያለህን ቦታ ካጣህ ደሞ ላራስህ ያለህን ትልቅ አመለካከት ታጣለህ በራስ መተማመንህ ይቀንሳል…

ለራስህ ያለህን ጥሩ አመለካከት አጣህ ማለት ደሞ ከሰው ጋር አብረህ መቆም ይከብድሃል።

አሁን አሁን ሰዉ ሁሉ የአስገራሚ ባህሪ ባለቤት እየሆነ ነው ሳይሰማህ ሳትጠይቀው የሚመልስ የሚያወራ ሰው እየበዛ…

አንዳዴ ሁለት ሰዎች እያወሩ የሚጣሉ ነው የሚመስለው እኩል ያውራሉ የጯጯሃሉ በቃ መደማመጥ መወያየት የለም ይሄን ባህሪህን ተወው።

ቃላቶችን ቆጥብ ሃሳብህን ቀምመህ መልስህን አዘጋጅ ከዚያ ታወራለህ።

ታላቁ ሊቃውንት ሊቅነት

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

01 Oct, 05:03


"ነገ ትሞታለህ ብትባልስ.. ? ዛሬህን እንዴት ልታድራት ነው የምትመኘው?"  ብዙ ጊዜ እንደማስተምረው

“የህይወት ስኬት ማለት በሙያ ወይም በገንዘብ ወይም በሌላ በዓለም በታወቀ መለኪያ የምትቀዳጀው ቁርጡ የታወቀ ነገር ሳይሆን፣ ራስህ የምትወስነው ደስተኛ ህይወትን መምራት መቻል ነው። ''

ከልጅነቴ ጀምሮ ከተወሰነ የቤተሰብና ጓደኝነት ግፊት ውጪ የማምንበትንና ትርጉም የሰጠኝን ህይወት ኖሬአለሁ! ለዚህም እኔንና ፈጣሪን አመሰግናለሁ!

አንተስ/ አንቺስ? እንዴት ነው Life!

የህክምና ዶ/ር የሆነው ሊ ሊፕሰንታል በጥሩ ቁመናና ብርታት ላይ በሚገኝበት በ52ኛ ዓመቱ ላይ ድንገት አንድ ገጠመኝ ቀሰቀሰው። አፉ የዶለው የዳቦ እምቡጥ ከጉሮሮው አልወርድ ብሎ መከራውን ያበላዋል። አየር ያጥረዋል። ደረቱ በህመም ይቀሰፋል። እንደምንም ተንደፋድፎ ግን ዋጠውና አየር ለመሳብ በቃ። 

ሚስቱ (ኬቲ) ስትመጣ ያጋጠመውን ይነግራታል። አብራው በህክምና ኮሌጅ የተማረች የህክምና ዶክተር ነች።  ሁለቱም ሀኪሞች ናቸው። 30 ዓመት በትዳር ኖረዋል። ወንድና ሴት ልጆች አፍርተዋል።

ሊ ሊፕሰንታልን ምን እንደገጠመው ከታዩት ምልክቶች ህመሙ ምን ሊሆን እንደሚችል ሁለቱም ጠርጥረዋል። የፈሩትን ግን ሳይነጋገሩ ተቃቅፈው ያድራሉ። 

በማግሥቱ ዶ/ር ሊ ይመረመራል። ካንሰር ተገኘበት። የጉሮሮ ካንሰር። ለካ ሳያውቀው የጨጓራው አሲድ ወደ ጉሮሮው እያሻቀበ ለዓመታት ሲያነደው ኖሯል። እና ካንሰሩ ወደ ሳንባውና ሌሎች አካላቱም ተሰራጭቷል። መርዳት የማይቻልበት ወቅቱ ላይ ነው ጫን ባለ የዳቦ ትንታ የባነነው።

እና በህይወት ለመቆየት ያለህ ዕድል ከዓመት ሁለት-ዓመት ያነሰ ነው የሚል ቁርጥ ያለ (ኮንክሪት) የምርመራ ውጤት ይነገረዋል። 

በዚህ ከምርመራው ውጤት እስከ ሞቱ መሐል ባለችው ጊዜ ውስጥ ነው ዶ/ር ሊ ሊብሰንታል ይህን እጅግ ልብ የሚነካ፣ እና ማንንም የሰው ፍጡር በጠንካራ መንፈስ የሚያበረታ፦ 

"Enjoy Every Sandwitch - Living Each Day As If It Were Your Last" የሚል መፅሐፍ የፃፈው። የሚያሳዝነው ዶ/ር ሊ መፅሐፉ ከመታተሙ በፊት ቀድሞ (በሴፕቴምበር 20/ 2011 ላይ) ህይወቱ አለፈ። 

ከወራቶች በኋላ ዶ/ር ሊ ሊፕሰንታል የሪሰርች ፕሮግራም ዳይሬክተር ሆኖ ለአሰርት ዓመታት የሠራበት  የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ፕሮፌሰር የሆነ የብዙ ዓመት ወዳጁ ዶ/ር ዲን ኦርኒሽ የመፅሐፉን መግቢያና ስንብት ክፍሎች ፅፎለት፣ መፅሐፉ ሊታተምለት በቃ።


የህይወት ስኬት ማለት አንተ ነህ! ስኬት በሙያ ወይም በገንዘብ ወይም በሌላ በዓለም በታወቀ መለኪያ የምትቀዳጀው ቁርጡ የታወቀ ነገር ሳይሆን፣ ራስህ የምትወስነው ደስተኛ ህይወትን መምራት መቻል ነው ይላል።

ኖረህ ኖረህ የሞትህ ቀን ላይ ስትደርስ፣ አሁን ብሞትም ዝግጁ ነኝ፣ ደስተኛ ነኝ፣ ብለህ ከፀፀትና ትካዜ ነፃ ሆነህ መገኘት የምትችልበት ህይወት ካለህ አንተ በትክክል ህይወትን ሙሉዋን ኖረሀታል ማለት ነው ይለናል።

I think I am doing it! If you want to do it too....

ቀጥሎ ያሉትን ሀሳቦች እያቸው...

1. ሞትህ ፊትህ ሲቆም እንዳይቆጭህ የምትማረርበትን የህይወት መስክ ጊዜ ሳታባክን ቀይረው በሊቅነት። 

2. ሪስክ ውሰድ፣ ለውጥን አትፍራ፣ ለውጥ የሚያመጣልህ ነገር ወይም የሚወስድህ ሥፍራ ምን እንደሆነ ባታውቀው እንኳ ያን ካማረረህ ህይወት ፈቅ ለማለት የምትደፍር የህይወት ጀግና ሁን። 

3. የህይወትህ ጀንበር ሳለች አፍቅር። ከሰው ተግባባ። ከማህበረሰብህ ተቀላቀል። 

4. ለሰዎች ምስጋና ይኑርህ። ለህይወት ምስጋና ይኑርህ። ለሰዎች የምታስተርፈው ርህራሄ አትጣ።

5. መንፈሳዊ እሴቶችን በህይወትህ ሳለህ ቋሚ ልምዶችህ እንዲሆኑ መለማመድ፣ ንዴትና ቁጣዎችህን ወደ ፈጠራና መልካም ነገሮች መለወጥ፣ ብዙ ዘመኔን ፈጀሁበት ብዙ ነገሬን አባከንኩበት ብለህ የተሳሳተ መሆኑን የምታውቀውን የህይወት መንገድ ሙጭጭ ብለህ ሞት ፊት እንዳትቀርብ ደግሞ ደጋግሞ የሚናገራቸው ቁምነገሮች ናቸው።

6. ይቅርታ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይቅር በል፣ ግን አትርሳ ለሌላ ጊዜ ትምህርት እንዲሆንህ

7. ከታጠርክበት መጥፎ ሳጥን ደሞ በፍጥነት ውጣ። ከመጥፎ የአስተሳሰብ ሳጥን ወጣ በልና ህይወትን ተመልከተው።  

I know it hard but you got to choose! So Chhose the best!

Safe Life
Likawunt Z Great I

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

30 Sep, 03:57


ምናብ!Imagination is the Marvelous gift humans have, but zey dont use it!
ሁለም ህልሞቼ ወደ መሬት የወረዱት በምናብ አማካኝነት ነው።

ምናብ በሕይወታችን የምንፈልገውን ማንኛውንም ነገር በሀሳብ፣ በምስልና በስሜት የምናመነጭበት፣ የምንቀርጽበትና የምንፈጥርበት ልዩ የአዕምሮ ክፍል ነው።

ምናብን ባለመረዳት ብዙዎች አይጠቀሙትም ወይም በትክክል Positively አይጠቀሙትም።
በሕይወትህ ላይ ለውጥ እንድታመጣ፣ በትክክል ስትጠቀምበት ደግሞ ተዓምር እንድትፈጥር የሚያግዘህ ስጦታ ነው።

ሁሌ ጠዋት ለ30 ደቂቃ አይንህን ጨፍነህ አስብ!Sit down Every morning. Close your eyes and think for 30 minutes! ምናብን ትረዳዋለህ!

አንድ ሰው ምናቡን በትክክል ሲጠቀም፣ ኪሳራን አሸንፎ  ትርፍ ማግኘት ይጀምራል። ምናባችንን በትክክል ስንጠቀምበት፣ ችግር ውስጥ ሆነን  ያልታየን “መፍትሄ” በምናባዊ መንገድ ማየት እንችላለን።

👉 ብዙ ጊዜ ህይወት የምናያቸው ነገሮች ጋር ብቻ የተቆራኘ ይመስለናል። No!

Everything አሁን በ3D የምናያቸው የሚመነጩት ከድንቁ የሰው ልጅ ምናብ ውስጥ ነው። ትልልቅ ግኝቶች የሚወጡት ከሰው ልጅ ምናብ ውስጥ ነው።

ምን ያደርጋል ሰው ምናብ እንዳለው ራሱ አያውቅም! እንዴት እንደሚጠቀምበትም አያውቅም።So They Waste it!

ማንኛውም ለችግራችን የሚሆነውን መፍትሄ በዐይናችን አላየነውም ወይም በጆሯችን አልሰማነውም ማለት፣ ችግራችን ትክክለኛ መፍትሄ የለውም ማለት አይደለም።

በነገራችን ላይ Reality! አንድን ነገር በዐይንህ አላየህም ማለት፣ ምንም ነገር የለም ማለት ወይም ውስጣዊ በሆነው ምናብ የአዕምሮ ክፍል አታይም ማለት አይደለም።

አሪፍ ላይፍ አሪፍ ገንዘብ ስለማግኘትም ስናወራ፣ ልትረዳው የሚገባህ ዋናው ቁም ነገር የምትፈልገውን ስራ ለመጀመር የሚያስፈልግህን ገንዝብ በዐይንህ አላየኸውም ማለት፣ ገንዘቡ የለም ማለት አለመሆኑን ነው።

ማንኛውንም ነገር በትክክለኛው መንገድ ስትፈልግ፣ የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ ማየት ከዚያም ማግኘት ትጀምራለህ። የሚያስፈልጉህ ነገሮች በአምስቱ የስሜት ህዋሶችህ ባይታዩህም፣ ማየት ግን ትችላለህ፤ በምኔ ብትል፣ በምናብህ። የሚያስፈልግህን ነገር በምናብህ ካየኸው፣ በአዕምሮህ ታስበዋለህ። በአዕምሮህ ስታስበው ደግሞ በልብህ ታምነዋለህ።

If you believe! Its Yours then you will translate it it to reality!
This is how the world works!

You must know this principle to change your Results! Do It!

Likawunt Z Great I

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

29 Sep, 09:19


ዕውቀት ያንሰናል ትስማማላችሁ?

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

28 Sep, 06:31


Confidence- በራስ መተማመን አስፈላጊ ነው?!በራሳችን ሳናምን ሰዎች በእኛ ማመን ይችላሉ?

1ኛ አው እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። 2ኛው በፍፁም። እኛ በራሳችን ሳናሞን ማንም በኛ ሊተማመን አይችልም።

👉 ሰዎች በእኛ ካላመኑብን ደግሞ በየትኛው የሕይወት መስክ ውስጥ ምንም አይነት የሰዎችን አጋርነትም ሆነ የስራ ስኬት ማግኘት ያስቸግረናል፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ መስራት ያለብን በራሳችን የማመናችን ጉዳይ ላይ ነው፡፡

👉 በራስ መተማመን ማለት ክህሎት ሲሆን አንድ ሰው ባለው አቅምና ችሎታ፣ ግቦቹን ለማሳካትና ውጤቶችን ለማስተካከል ተግዳሮቶች ቢኖርም አሸንፋለው የሚል እምነትን ማዳበር ነው።

👉 በዚህ መልኩ በራሳችን ላይ ያለንን አመለካከት ከፍ ያለና የላቀ ስናደርገው ከሁሉም በፊት በራሳችን ላይ ያለን የመተማመን ደረጃ እጅጉን ይጨምራል፡፡ ይህን የመተማመን ሁኔታ ለሚያገኘን ሰው ሁሉ በግልጽ እስከሚታይ ድረስ መደበቅ አንችልም፡፡ ሰዎች ምላሽ የሚሰጡት ለዚህ ሁኔታ ነው፡፡

👉 Confidence ለምን ያስፈልጋል?
1.  ያወጣነውን ግብ እና እቅድ ተከትለን በወቅቱ ለማከናወን፡፡

2.  አንድን የለውጥ መንገድ ጀምረን ለውጡ እስከሚከናወን ድረስ ለመቀጠል፡፡

ወጥፎ ልማድን ለማቆም፣ ወይም አንድን መጀመር ያለበትን መልካም ነገር ለመጀመር ጉዞን ከጀመረ በኋላ ዲሲፕሊን በመለማመድ ለማሳካት Confidence ግድ ነው። 

3. ቃላችንን ለማክበርና ለመጠበቅ
ብዙ ሰው ላይ ያለ ክፍተት ነው።
በራስ መተማመን ይህንን ለማስተካከል ሁነኛ መፍትሔ ነው።
4. አሉታዋ ትችትን ለመቋቋምና ያመንበትን ለማድረግ
5. በህይወታችን ትልቅ ስኬትን ለመቀዳጀት። ስኬት በራስ መተማመን ከሌለን ከባድ ነው።

       እናንተስ? ሀሳባችሁን Comment አርጉ።
              ሊቅነት-Mindset
              Your Freedom

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

27 Sep, 16:26


https://youtu.be/LYuATdL7wQg?si=9_JlDoa7ZRsbiK60

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

24 Sep, 11:31


ለመማር ዝግጁ ነህ?
ቻይና ውስጥ አንድ በጣም ጠቢብ የዜን ፍልስፍና (Zen Philosophy) መምህር ነበር።  ሰዎች የእርሱን እርዳታ ለማግኘት እና ጥበብ ለመቅሰም  ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ይጓዙ ነበር።  

አንድ ቀን አንድ የተማረ (ምሁር) ምክር ለማግኘት መምህሩን ይጎበኛል።   ምሁሩም ስለ ዜን የህይወት ፍልስፍና ለመማር እንደመጣ ይናገራል።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ውይይቱ ተጀመረ። ምሁሩ አእምሮው ‘በሁሉን አውቃለሁ ባይነት’ የተሞላ እና በእራሱ አመለካከት፣ አስተሳሰብ  እና እውቀት ፍፁምነት  ያምን ነበርና በንግግራቸው ወቅት መምህሩ የሚናገረውን እና የሚያስተምረውን ከመስማት እና ትኩረት ከመስጠት ይልቅ የራሱን ታሪክ እና ስለ ምሁርነቱ በማውራት መምህሩን የመናገር እድል ይነሳዋል። 

መምህሩም በእርጋታ አንድ ላይ ሻይ እንዲጠጡ ሐሳብ ያቀርባል። ለእንግዳው (ምሁሩ) ባቀረበው ብርጭቆም ሻይ ይቀዳለታል።  ብርጭቆው ሞላ። 

ነገር ግን መምህሩ እየፈሰሰም ቢሆን ሻይውን መቅዳቱን አላቆመም። ጠረጴዛው ላይ እስኪፈስ ድረስ ሻይ እየቀዳለት ነበር።  ሻይው ወለሉ ላይ ብሎም በምሁሩ ጃኬት ላይም ይፈስ ነበር።   ምሁሩም በመገረም እየተመለከተው ‘’“ተው እንጅ!  ብርጭቆው እኮ ሞልቷል።  ማየት አትችልም እንዴ ” ይላል።

መምህሩ በፈገግታ “ብርጭቆህን ባዶ አድርግ! አንተም  ልክ እንደዚህ ብርጭቆ ሁሉ አእምሮህ ባረጁ ሃሳቦች እና እምነቶች የተሞላ ስለሆነ ከዚህ በላይ ምንም አዲስ እውቀትና ሃሳብ መቀበል አቁመሃል። ‘’ በማለት ተናግሮ ብርጭቆውን ባዶ አድርጎ እንዲመለስ መከረው።  .

እኛም በህይወታችን ውስጥ በየቀኑ ተመሳሳይ ታሪክ ይከሰታል። ሁሉንም የምናውቅ ይመስለናል እናም ‘በትህትና ማዳመጥ እንዲሁም ከሌሎች መማር አያስፈልገንም!’ ብለን አእምሮአችንን ሞልተን ባዶ ማድረግ አቅቶናል!!!

መማር ከፈለክ ዙሪያህ ሁሉ አስተማሪ ነው!

ለመማር ዝግጁ ከሆንክ ማወቅ የፈለከውን አታጣም፤ ባገኘሀው አጋጣሚሁ ለመማር ተዘጋጅ፣ ለእወቀትህ ንቁ ሁን፤ ለእድገት እራስህን አመቻች፤ ተገደህ ሳይሆን ፈልገህ የእውቀት ባህር ውስጥ ግባ፤ ዋናም ባትችል ገብተህ በጥቂቱ ተለማመድ። ትምህርት ክህሎት አይጠይቅም ፤ ገንዘብ አይፈልግም፤ ካለህ ጊዜ ጥቂቱን ብቻ ይፈልጋል ።

መድረስ የምትፈልግበትን ካሰብክ ለመማር ጊዜ አታጣም፣ እድገትን ከተመኘህ እለት እለት ከመማርና ከማወቅ በላይ የሚጠቅምህ ነገር የለም። እድገት በእውቀት ውስጥ ነው። በንብረትና በገንዘብ ብቻ መትረፍረፍ እውቀትና ጥበብ ካልታከለበት ከብልፅግና ወደ ጥፋት፤ ከደስታ ወደ ጭንቀት መቀየሩ የማይቀር ጉዳይ ነው ።

ለመማር ዝግጁ ስትሆን፤ ለገዛ ህይወትህ አዋቂ፣ እውቀትህን ለማካፈል የማትሰስት፣ በየጊዜው እራስህ ላይ ጥራትንና እሴትን የምትጨምር፣ የእድገትና የለውጥ ጥማተኛ ትሆናለህ።

አዎ! ትምህርትን ፈልገህ ተማር፣ እውቀትን አሳደህ ያዘው፣ ከስራህ በላይ እራስህ ላይ ለመስራት የተጋህ ሁን። አለማወቅን ተጠየፍ፣ ከአዋቂነት ተዛመድ። የአዋቂነትን አቅም በእራስህ ላይ ሞክረው፤ እውቀትህ ያረጋጋሃል፤ በእራስ መተማመንህን ይጨምራል፤ ከጊዜ በፊት የምትቀድም ያደርግሃል፤ የሚመጥንህ ቦታ ያደርስሃል፤ የሚገባህን ይሰጥሃል፤ መቼም የምታጋራው ነገር አያሳጣህም ።

መማር አታቁም፣ እድገትህን አትግታ፣ እራስህን አሻሽል፤  በአዳዲስ እውቀቶች እራስህን አንፅ!

ብርጭቆህን ባዶ አድርግ!!!!

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

23 Sep, 11:19


How to Beat Procrastination!
የቸልተኝነት መፍትሔዎች

1. Set Clear Goals: Define your tasks and establish specific, achievable goals for yourself. Break down big tasks into smaller, more manageable chunks.

2. Prioritize and Plan: Create a to-do list or a schedule, prioritizing tasks based on their urgency and importance. This will help you stay focused and organized.

3. Use Time Management Techniques: Implement techniques like the Pomodoro Technique, where you work for a set amount of time (e.g., 25 minutes) and then take a short break. This can help you stay motivated and reduce the tendency to procrastinate.

4. Eliminate Distractions: Identify and remove or minimize distractions in your environment. Turn off notifications on your phone, close unnecessary tabs on your computer, and find a quiet and comfortable space to work.

5. Find Accountability: Share your goals and progress with someone you trust, such as a friend, family member, or coworker. Their support and regular check-ins can help keep you accountable and motivated on your job!

Join Us for High Performance Training
Mindset and Entrepreneurship Training
Contact 0929192323