...የአስቴርን ዘፈን ስሰማ አንቺ ለእኔ ያዜምሽው ይመስለኛል <<ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ...>> እያልሽ።
ይበልጥ የሚሰማኝ መቼ እንደሆነ ልንገርሽ?
አንቺ የሆንሽውን መቀበል አቅቶኝ፤እኔ የምስላትን አይነት ሴት ካሆንሽ ብዬ አስጨነኩሽ።ስለምትወጂኝ ላንቺ አልከበደሽም ሁኚ ያልኩትን ሆንሽ...እንደዛም ሆኖ አልበቃኝም።
ይሄን ባሰብኩ ጊዜ መንፈሴ ይታወካል።አንቺ ከበቂ በላይ መሆንሽ ዘግይቶ፤የሌላ ከሆንሽ በኋላ እንደገባኝ ሳስብ...ፀፀት እጆቼን የኋሌት ያስረኛል፣ወፍራሙ በጎነትሽ እንደ ጅራፍ ይገመዳል፣አመለ ቢስነቴ፤ጥጋቤ እሾህ ይሆኑ እና ትዝታ በፈርጣማ ክንዱ ይገርፈኛል።
ልትሄጂ ስትይ እጅግ አዝነሽ የጠየቅሽኝ ጥያቄ ህሊናዬ ውስጥ ያስተጋባል።
<አንተ ሰው ምን አድርጊ ነው የምትለኝ?>
የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ