ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚 @booksshelf22 Channel on Telegram

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

@booksshelf22


😌 አለማወቅን መቀበል እውቀትን ለማግኘት የመጀመሪያው እርምጃ ነው።
:
:
:
:

ልጅ አባቱን ካልበለጠ እንዳልተወለደ ይቆጠራል፤ መወለድ ከወላጅ ለመብለጥ ካልሆነ አለመወለድ ይሻላል።
:
:
ለሰውዬው አሳ ስጠው ለውሎው ይመገበዋል፤ አሳ ማስገርን አስተምረው በህይወት ዘመኑም ሲመገብ ይኖራል፤ ሃይማኖትን ስጠው እስኪሞት አሳ እንዲያገኝ ሲፀልይ ይኖራል።




ሀሳብ፣ አስተያዬት @ABKOO1996

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚 (Amharic)

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚 አዲስ አመትን ተግባራቸውን ለማረጋገጥ የመጀመሪያው መልእክት ነው። እናትና ንግድና ኃይለኛ ወለድ፦ አባትን በራሱ መንገድ ካልበለጠ እንዳልተወለደ እንዴታቸው ይቆጠራል። ስለሌላ መወለድ ምን እንደሚደረግ እንዴታቸው ይሻገራል። ለሰውዬው አሳ እናውቃለው በውሎው ስሠለው ይመገበዋል። አሳው ማስነፍርን ለሁሉም እንዴታቸው በህይወት የጠራውን እንዴታቸውም ሲመገብ እንችላለን። ሃይማኖታቸውን እንዴታው ማስነፍር ወደ ማግኘት የሚችልን ባለሙያ ሲዘምናቸው እንደማጠየቅ ይመልሳል። በመሆኑም ሀሳብ፣ አስተያዬት @ABKOO1996 እናትና ንግድ።

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

25 Oct, 17:18


ሰላም እንደት ናችሁ? አንድ ልጅ በውስጥ መስመር በኩል የሆነ ቪድዮ ልኮልኝ ነበር እናም ቪድዮን ለማን እንደሚላክ ባይነግረኝም ግን እሯሷ ታውቀዋለችና አንተ ብቻ መልዕክቱን አስተላለፍልኝ ብሎኛል።

እኛም ቪድዮውን ስንመለከተው ቆንጆ ስለመሰለን ወደ እናንተ አቅርበንላችኋል፤ ተጋበዙልን 🙏🙏🙏🙏🙏

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

28 Sep, 19:05


ውድ እቃ ያለቦታው ርካሽ ነውና የእናንተ ትክክለኛ ቦታችሁ የት ነው???????





Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

16 Sep, 21:05


Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

11 Sep, 07:43


🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻2017🌻መልካም🌻አዲስ አመት🌻

            🌻🌻🌻
     መልካም🌻አዲስዓ መት
  መልካም🌻     አ🌻🌻
መልካም 🌻        ዓ🌻🌻
ለወዳጄ 🌻          ዓ🌻🌻
🌻🌻🌻🌻        አ🌻🌻
                         ዓ🌻🌻
                       አ🌻🌻
                     አ🌻🌻
                   ዓ🌻🌻
                 አ🌻🌻
            ዓ🌻🌻
        አ🌻🌻
      ዓ🌻🌻
   አ🌻🌻
🌻🌻ት               🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

            🌻   🌻   🌻
      🌻መል🌻🌻🌻ካም🌻
  አ🌻🌻ስ          ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ            ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ            ዓ🌻🌻
  አ🌻🌻ስ          ዓ🌻🌻
       🌻🌻🌻🌻🌻
             🌻  🌻  🌻

                    
                🌻🌻አዲስ
           🌻🌻🌻አመት
        🌻🌻🌻ልካም
   🌻🌻አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
  🌻መልካም  🌻 አዲስዓመት
  🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
   አዲስዓመት🌻ለወዳጄ🌻🌻
  🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

🌺🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌼
🌻🌻🌻🌻🌻አመት🌻🌷
🌻🌻🌻🌻🌻አመት🌻🌷
                               የ🌻ሞገስ 🌻          
                             የ🌻ክብር  🌻        
                            የ🌻ሹመት🌻
                           የ🌻ታላቅነት🌻        
                            🌻ዓመት 🌼
              🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻🌷🌹
   🌻🥀🌹🌷🌼🌹ሁ 🌾  
               🌻🥀 🌼    🥀🌹🌺       
                        🌻የበረከት 🌻
                       🌻የሹመት 🌻
                      🌻የምርቃት 🌻
                     🌻የመግዛት 🌻
                    🌻የከፍታ 🌷🌻
                    🌻ዓመት 🌷🌻
                    🌻 ይሁን 🌻🌻
                   🌻🌻🌻🌻🌻
                   🌻🌻🌼🌼🌼


🌻🌻🌻  ያሰብነው የሚሳካበት          🌻🌻
🌻🌻🌻                                         🌻🌻
🌻የካሳ🌻የሰላም🌻የጤና🌻የበረከት🌻🌻
🌻🌹🌾ዓመት 💐🌷ይሁንልን።🌻🕊🌻🌻


🌼@Booksshelf22🌼

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

26 Aug, 11:17


ቁጥር - 2


በህይወቴ አይሆንም ያሉኝን ሰዎች ሁላ
ላመሰግን እወዳለሁ; ምክንያቱም እነሱ እምቢ ስላሉኝ እኔ እራሴ ሄጄ አደረኩት።
በፈገግታ የተሞላ ፊት ሁላ ችግር የለበትም ማለት አይደለም። ችግራቸውን የሚወጡበት መንገድ አላቸው እንጂ።
በብርሃን ስትሆን ሁሉ ነገር ይከተልሃል:: ጨለማ ውስጥ ከሆንክ ግን ጥላህ እንኳን አይከተልህም።
ሳንቲም ብዙ ድምፅ ያሰማል:: ገንዘብ ግን ምንም አያሰማም:: ስለዚህ ዋጋህ ሲጨምር ወሬህን እየቀነስክ ና!
ደሀ ሆነህ ብትወለድ ጥፋቱ ያንተ አይደለም ደሀ ሆነህ ብትሞት ግን ጥፋቱ ያንተ ነው።

ኩራት ልጃገረዶችን ይስባል፣
ድፍረት ከልጅአገረዶች ያቀራርባል፣
እውቀት የሴትን ልጅ ይገዛል፣
ጥንካሬ ከሴት ልጅ ጋር
በትእግስት ያቆያል ነገር ግን ታማኝነት ከሴት ልጅ ጋር እንዲዘልቁ ያስችላል፡፡



Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

25 Aug, 04:33


ወንድሞቼ ምክሬን ስሙኝ ቁ 1

🌹በዚህች አለም ላይ እንደነበረ የሚቆይ ምንምነገር የለም
ዛሬ ስምህ ማንም ቢሆን ነገ ግን ሬሳ ትባላለህ፣
ዛሬ የቱንም ሀብት ቢኖርህ ነገ 1 ሜትር ከፈን ብቻ ነው ይዘህ የምትሄደው።
ዛሬ የተንደላቀቀ አልጋ ላይ ብትተኛ ነገ አፈር ውስጥ ትተኛለህ፣
ዛሬ የቱንም ያህል ስልጣን ቢኖርህም ነገ ከሁሉም ጋር እኩል ነክ፣
ዛሬ የምትናፈቀ ቢሆን ነገ ሬሳ ሆነህ እንዳትሸት ሰዎች ቶሎ ያሸሹካል፣
🌟ስለዚህ ዛሬ ላይ ለነገ የሚጠቅምህን ስራ ብትሰራ መልካም ነው!!!
🌷መልካም መሆን ቢያቅትህ መጥፎ አትሁን መልካምነት ለራስ ነውና!!




Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

20 Aug, 15:59


....😭 ፍትሕ ለሰማዩ ዳኛ 🙏🙏


የድሆቹን በደል አንድ ባንድ አይቼ
ስሞታውን ሁሉ በዝርዝር ሰምቼ
ከጨረስኩ በኋላ ከዕለታት አንድ ቀን
ከጅረት አጠገብ ጥቅጥቅ ወዳለ ደን
ሄድኩና ቁጭ ብዬ ከትልቅ ቋጥኝ ላይ
እገረም ጀመረ ስለሰዎች ስቃይ

ትግል እንደያዝኩኝ ከሐሳቤ ጋራ
ትልቅ ሽማግሌ ግርማው የሚያስፈራ
ለሁሉም ጊዜ አለው እያለ ሲያወራ
ሳያስብ ደረሰ ከአለሁበት ስፍራ
እኔም ሁኔታውን እንደተመለከትኩ
ፈላስፋ መሆኑን ስለተገነዘብኩ
.....ጊዜ ጊዜ ጊዜ ጊዜ የምትለው
አሳየኝ በል እስቲ ከወዴት ነው ያለው


ላለው ለሚያመጣ ከሌለው ለሚሰርቅ
ለወሽካታ ጊዜ ምነው ባትጨነቅ
ብዬ ሳጉረመርም ባይኑ እያተኮረ
አዳምጠኝ እያለ መናገር ጀመረ
ምንም እንኳን ለሰው፣ እንደተፈጠረ፣ የሚቀር ቢመስለው
ጠቢቡ ሰሎሞን፣ ተናግሮታልና፣ ለሁሉም ጊዜ አለው

የትዕግስትን ፍሬ፣ ከኑሮ ላይ ስጠኝ ቢውጡት ቢመርም
ቀን ይወስዳል እንጂ፣ የታቀደ ዓላማ፣ እንደቀረ አይቀርም
ለሁሉም ጊዜ አለው፣ ወዳላዩት ዓለም ቀስ በቀስ ለመግባት
በኑሮ ሸለቆ፣ ዳግመኛ ተወልዶ፣ አብቦ ለማፍራት
አስተውለው እስቲ፣ ባሻገር ያለውን፣ የተራራ ውበት
የዕፅዋቱን ቀለም፣ የፀሐይዋን ግርማ፣ የገደሉን ርቀት

የዛፉን አቋቋም፣ የሣሩን መተኛት፣ የመስኩን ፀጥታ
ልብ በልና እየው፣ የጅረቱን ጉዞ፣ የሐይቁን እርጋታ
ልብህ ይረዳዋል ግዑዛን ሲበሉ ብታስተውል ሁሉን
የመኖራቸው ስልት ከተፈጥሮ መስመር አለመዛነፉን
ነገር ግን የሰው ልጅ መሆን ከሚገባው ከመስመሩ ወጥቶ
በእኩልነት ፋንታ ኃይለኛ ደካማ የሚል ዘዴ አምጥቶ
በብልጠት መከታ እኖራለሁ ይላል ኑሮን አበላሽቶ

ኑሮውም ከንቱ ነው የተስፋና ሐዘን አዘቅት የሞላበት
የማይሆነው ሆኖ የሚሆነው ሳይሆን መክኖ የሚቀርበት
ሆኖም በሥራ ኃይል እንዲህ ያለው ኑሮ በርግጥ ይሸነፋል
ጊዜ ያዘዘው ለት ደወሉ ሲደወል እንደጥላ ያልፋል
ያኔ ነው እንግዲህ ዕውነት ኃይል ስትሆን ማጭበርበር ተረስቶ
ኑሮ የሚለመልመ ከጠወለገበት ከትቢያ ተነስቶ

የዕውቀት አፈርሳታ ታማኝ አቅመኛ የሚመረጥበት
ያኔ ስለሆነ የታሸገ ምላስ የሚላቀቅበት
ይታየኛል አለ ጊዜ ነው ወሳኙ ለሁሉም ነገር ይህንን ተናግሮ ሽማግሌው ፈላስፋ ከፊቴ ሲሰወር
ከሐሳብ እንቅልፌ ተመልሼ መጣሁ ከሄድኩበት አገር፤
ለካስ ልክ ነበሩ አባባ፡ ፈጣር ይዳኛል
ቀኖች ብቆዩም ሁሉም በየስራው ቅጣቱን ያገኛል። 🧘‍♀🧘‍♀


Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

20 Aug, 09:22


#ይድረስ_ለተከፋች_ሴት
.
.
ይኸውልሽ የኔ አይናማ፤
አንዴ ብቻ እኔን ስሚኝ አታለቃቅሺ እርሺው እንባሽን፤
ሰው ከመሆንሽ ሳትሸራርፊ እጥፍ ውደጂው ያስለቀሰሽን።
ልብሽን በእምነት አፅኚው የዛሬ ቀንሽም ያልፋል፣
ችግርሽ ምን ቢደራረብ በእግዜር እጆች ይገፋል።
የምታምኚው አምላክሽ እኮ፤
ከሞት መንጋጋም ነፍስ ያስተርፋል።
"ተሳሳትኩ " ??

አልተሳሳትኩም !!!!!
የተስፋ መሃረብ ይዘሽ ትኩስ እንባሽን በይ አደራርቂው፣
መደነቃቀፍ ብርታት ከሆነ ገፊሽን ሁሉ ወደሽ መርቂው።
ወርቅን እራሱ፤
"ወርቅ ሆነ" እንዲባል የተጋጋመ እሳት በልቶታል፣
ታድያ አምላክሽ ይመካብሽ ዘንድ ሺ ቢፈትንሽ ክፋቱ የታል ????
"እኔ አልታየኝም"።
.
.
እናምልሽ ውድ ዓለሜ መፈተንሽን እንዳትጠዪው፣
ይልቅናሽስ ፈገግ ብለሽ "ፈጣሪዬ ሆይ ተመስገን" በይው።


👆👆👆 በማንኛውም ግዜ ስትከፉ ይህን ታሪክ አድምጡ


                        



Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

19 Aug, 20:34


ሰዎች ከእናንተ ጋር እንዲስማሙ የሚያደርጉ ከ50 በላይ የሳይኮሎጂ ትሪኮች__Psychology Tricks  እስከ መጨረሻ ስሙ🙏🙏

                        



Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

19 Aug, 20:05


🧾📑🗒 ትምህርት ክፍል 1

1.1 የሥነ ምግባር ፍልስፍና ምንነት –

በተለምዶ የፍልስፍና ጥያቄ ሁልጊዜ የፍልስፍናን ምንነት በመፈተሸ ነው የሚጀምረው፡፡ እኛም ይሄንን ኮርስ ስንጀምር በሞራል ፍልስፍና ሥር የሚነሱ ጥያቄዎችና መልሶቹ የሚቀርቡበትን የተለያዩ መንገዶች ከማየታችን በፊት የሞራል/የሥነ ምግባር ፍልስፍናን ከሌሎቹ የፍልስፍና ዘርፎች የሚለዩት ባህሪያት ምን እንደሚመስሉ በመዳሰስ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ‹‹ለመሆኑ የሞራል/የሥነ ምግባር ፍልስፍና ምንድን ነው?›› የሚል ጥያቄ በማንሳት እንጀምር፡፡ ዛሬ እዚህ ጥያቄ ላይ አጠር ያለ ውይይት እናደርግና ወደ ዋናዎቹ የሞራል ፍልስፍና ህልዮቶች (ቲዮሪዎች) እንሄዳለን፡፡

እስቲ ውይይታችንን ‹‹Ethics›› እና ‹‹Moral Philosophy›› ከሚሉት ሁለት ቃላት ፍቺ እንጀምር፡፡ ሁለቱም ቃላት አንድ ዓይነት ምልከታ ስላላቸው <<Ethics>> እና <<Moral Philosophy>>  የሚሉትን ቃላት እየቀያየረን (interchangeably) መጠቀም እንችላለን:: Ethics is the philosophical study of morality ወይም የበለጠ ግልጽ ለማረግ ቀጣዩን ገለጻ እንመልከት Ethics is a study of what are good and bad ends to pursue in life and what it is right and wrong to do in the conduct of life.
ማለትም ‹‹ሥነ ምግባር ልንከተላቸው የሚገቡና የማይገቡ የህይወት ግቦችን የሚያጠና እንዲሁም በተግባራዊው ህይወታችን ልናደርጋቸው የሚገቡና አግባብ ያልሆኑ ድርጊቶችን የሚያጠና የፍልስፍና ክፍል ነው፡፡››

Ethics የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል መሠረቱ ‹‹Ethos›› የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን፣ Morality የሚለው ቃል ደግሞ ምንጩ ‹‹Mores›› ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ነው፡፡ ሁለቱም አንድ ዓይነት ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ በእንግሊዝኛው

<<custom>>፣ <<behavior›› ወይም ‹‹habit›› እንደ ማለት ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ ቃሎቹ ለፍልስፍና የተለየ ምልከታ አላቸው፡፡ ይህም ማለት ምንም እንኳን በተለምዷዊ አነጋገር ሁለቱን ቃላቶች በተቀያያሪነት የምንጠቀማቸው ቢሆንም በጥብቅ ትርጉማቸው ግን የተለያዩ ናቸው፡፡

በሥነ ምግባር ፍልስፍና ውስጥ ከሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ውስጥ የሚከተሉትን ማንሳት እንችላለን፣

ምን አይነት ህይወት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ? ምን ዓይነት ህይወትስ ነው የሚገባኝ?

ምን ዓይነት ሰው መሆን አለብኝ?

በህይወት ውስጥ ትልቁና የመጨረሻው ግብ ምንድን ነው?

ሐብት (ገንዘብ) ነው?

መሰረታዊ ፍላጎቶችን ብቻ ማሟላት ነው?²

ሥልጣን ነው?

ታዋቂና ዝነኛ መሆን ነው?

➢ መንፈሳዊ መሆን ነው? ወይስ

➢ ደስተኛ መሆን ነው? ደስታ ከሆነስ እንዴት ነው ደስታ የሚገኘው?

➢ ወይስ ሌላ ነገር አለ? (What is that ultimate purpose and goal of life then?)

አንድን ድርጊት ‹‹ጥሩ›› እና ‹‹መጥፎ››፣ ‹‹ትክክለኛ›› እና ‹‹ስህተት››፣ ‹‹ፍትሐዊ›› እና ኢፍትሐዊ››፣ ‹‹ሞራል›› እና ‹‹ኢሞራል›› የሚያስብለው መለኪያ መስፈርት (Criteria/Standard) ምንድን ነው?



➢ <ጥሩ - መጥፎ››፤ ‹‹ትክክለኛ — ስህተት››፣ ‹‹ፍትሐዊ – ኢፍትሐዊ››፣ ‹‹ሞራል — ኢሞራል›› የሚያስብለውስ የድርጊቱ ውጤት (መጨረሻው) ነው ወይስ ሌላ ‹‹ትክክለኛ መርህ ወይም መስፈርት›› አለ?³

➢ እንደዚህ ዓይነት መርህ ወይም መስፈርት ካለስ፣ ይሄ መስፈርት (መርህ) በጊዜ፣ በቦታና በባህል አንፃራዊ ነው ወይስ በእነዚህ ሁኔታዎች የማይለወጥ ቋሚ ነገር ነው?

➢ የዚህ የሞራል መርህ (መስፈርቱ) ምንጭስ ምንድን ነው እግዚአብሔር (ሃይማኖት) ነው? አመክንዮ ነው? የተፈጥሮ ህግ ነው? ማህበረሰባዊ ስምምነት (ህግ/ህገ መንግስት) ነው? ወይስ ባህል ነው?

እነዚህ ጥያቄዎች በሙሉ የፍልስፍና ጥያቄዎች ናቸው፡፡ እነዚህን የሞራል ፅንሰ ሐሳቦችንና የሞራል ፍርዶችን (Moral Judgments) የሚያጠናና ለመመለስ የሚሞክር የፍልስፍና ቅርንጫፍ ደግሞ ‹‹የሞራል ፍልስፍና›› እንለዋልን፡፡ እነዚህ የሞራል ጥያቄዎች ዘላለማዊ ሲሆኑ፣ መልሶቹ ግን በየዘመኑ እንደሚነሱት የፈላስፋዎች አሰላስሎት ሁኔታ ይለያያሉ፡፡ ይሄ ነገር ለሥነ ምግባር ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የፍልስፍና ቅርንጫፎች የሚሰራ ነው፡፡

እንቀጥላለን


👇👇👇👇👇👇
Join @&Share

💠 Philosophy education
🌐 Learning Philosophy

For more 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

31 Jul, 10:20


«አሁን ቀጥሎ ለምጠይቃችሁ ጥያቄ መልሳችሁን በየራሳችሁ ወረቀት ላይ አስፍሩ›› አለና ቀጣዩን ጥያቄ አቀረበ፦
   .......................‹‹ዳቦ ምንድነው?››


የመጀመሪያው፡- ‹‹ዳቦ ምግብ ነው?››

ሁለተኛው፡- ‹‹ከዱቄትና ውሃ ቅልቅል የተሰራ ነው››

ሦስተኛው፡- ‹‹የፈጣሪ ስጦታ ነው››

አራተኛው፦ ‹‹የተጋገረ ሊጥ ነው››

አምስተኛው፡- ‹‹ዳቦ እንደያንዳንዱ ሰው ትርጓሜ የሚቀያየር ነው››

ስድስተኛው፡- ‹‹ሰውነት ገንቢ ንጥረ ነገር ነው››

ሰባተኛው፡- ‹‹ማንም በእርግጠኝነት አያውቀውም››

‹‹እንግዲህ ንጉሥ ሆይ!›› አለ ናስሩዲን የሁሉንም ምላሽ ንጉሡ አንብቦ ሲጨርስ፡- ‹‹በየዕለቱ የሚመገቡትን ዳቦ ምን እንደሆነ እንኳን በጋራ ለመወሰን የማይችሉ ሰዎች እንዴት በእኔ ላይ የተመሰረተውን ክስ በአንድ ላይ ተስማምተው መፍረድ ይችላሉ?›› በማለት ንጉሱን ጠየቀ::

ናስሩዲን አስከትሎም፡- ‹‹እነዚህ ሰዎች በየቀኑ ለሚመገቡት ዳቦ ምንነት የጋራ የሆነና የሚያስማማቸውን ትርጉም መስጠት ሳይችሉስ እኔ ስም አጥፊ ነህ ተብዬ ለቀረበልኝ ክስ የጋራ የሆነ ስምምነት ላይ እንዴት ይደርሳሉ ብለህ አሰብክ?››

ንጉሡም በናስሩዲን ሃሳብ ተደንቆ በነፃ እንዲሰናበት ከፈረደለት በኋላ- “ለመሆኑ እነዚህን ሰዎች እውነት አላዋቂ ናቸው ብለህ ስብክሃል?›› በማለት ጠየቀው::

ናስሩዲንም እየሳቀ፡- ንጉሥ ሆይ! ፈላስፋውም ሆነ ሰባኪው እንዲሁም የሕግ ባለሙያው ሁሉም አላዋቂዎች ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን እንኳን የማያውቁ ናቸው:: ለዚህም ነው ከእነሱ የቀደሙት ሰዎች የገለጡትን እውቀት እንደበቀቀን እየደገሙ አዋቂነታቸውን ለማሳየት የሚደክሙት.. በማለት ተሰናብቶት ሄደ::

በሱፊው ቢስታሚ ይህን ወግ መሠረት አድርገው የሚነግሩን ቁም ነገር ብኖር  <<ታላቅ ሚስጥር ማለት የራስ ኣድርገው ነው፤ ይህን ምስጢር የገለጠም በእርግጥ አዋቂ ነው›› ይሉናል::

ሱፊው ሩሚ ደግሞ ይህን ሐሳብ ሲያጠናክሩልን፡- ‹‹ፈጣሪህን ፈልግ ራስህን ታገኛለህ፤ ራስህን ስትፈልግ ግን ፈጣሪህን ታገኛለህ›› ይሉናል።
ራስን መፈለግና ራስን መውደድ  ግን ታላቅ ልዩነት እንዳለው ልብ እንድንል ሩሚ አክለውም ያሳስቡናል::

የዚህን ምዕራፍ ጉዟችንን የምንቋጨው በቀጣዩ የናስሩዲን ወግ ይሆናል::

የናስሩዲን አህያ ይጠፋና በየመንደሩ እየዞረ በጩኸት ማስታወቂያ መንገር ይጀምራል፡- «ማንም አህያዬን ያገኘና ያመጣልኝ እሷኑ መልሼ እንደምሸልመው አስታውቃለሁ!››

ይህን የናስሩዲንን ማስታወቂያ የሰማ ጎረቤቱ፡- ‹‹ዕብድ ትመስለኛለህ፤ እንዴት አህያዬን ላገኘ መልሼ እሸልመዋለሁ ትላለህ?›› በማለት ሳቀበት::

በዚህ ጊዜ ናስሩዲን፡- ‹‹አየህ! ማንኛውም ነገር የአንተ ከመሆኑ በላይ ጠፍቶ ሲገኝ የሚሰማህ ደስታ ከፍተኛ መሆኑን ተረዳ›› አለው::

በቀጣይዋ ድንቅ የሱፊዎች አባባል ልሰናበት፡-
‹‹አንተን ከፈጣሪህ የሚሰርቅህን ነገር ሁሉ ፈጣሪ ከአንተ በመስረቅ ፍቅሩን ያሳይሃል::››

ውድ ቤተሰቦች ሁላችሁንም የዓለም መድኃኒት በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርሲቶስ በንፁህ ፍቅር እወዳቸዋለሁ
መልካም ቀን ይሁንላችሁ🙏🙏🙏




👇👇👇👇👇👇
Join @&Share

💠 Philosophy education
🌐 Learning Philosophy

For more 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

29 Jul, 22:43


በሚኒሊክ ዘመን የተሰሩ
1882 ዓ.ም. ---------------------ስልክ
1885 ዓ.ም. ---------------------ወፍጮ
1886 ዓ.ም. ---------------------ፖስታ
1886 ዓ.ም. ---------------------ባህር ዛፍ
1886 ዓ.ም. ---------------------ገንዘብ
1886 ዓ.ም. ---------------------የውሃ ቧንቧ
1887 ዓ.ም. ---------------------ጫማ
1887 ዓ.ም. ---------------------ድር
1887 ዓ.ም. --------------የሙዚቃ ት/ቤት
1887 ዓ.ም. -------------የፅህፈት መኪና
1889 ዓ.ም. ---------------------ኤሌክትሪክ
1889 ዓ.ም. ------------ዘመናዊ ህክምና
1889 ዓ.ም. ---------------------ሲኒማ
1889 ዓ.ም. ------------የሙዚቃ ሸክላ
1889 ዓ.ም. ------------ቀይ መስቀል
1890 ዓ.ም. ---------------------ሆስፒታል
1893 ዓ.ም. ---------------------ባቡር
1893 ዓ.ም. ---------------------ብስክሌት
1896 ዓ.ም. ---------------------መንገድ
1897 ዓ.ም. ---------------------ፍል ውሃ
1898 ዓ.ም. ---------------------ባንክ
1898 ዓ.ም. ---------------------ሆቴል
1898 ዓ.ም. ---------------------ማተሚያ
1898 ዓ.ም. ---------------------ላስቲክ
1899 ዓ.ም. -------------አራዊት ጥበቃ
1899 ዓ.ም. ------------የጥይት ፋብሪካ
1900 ዓ.ም. ---------------------ጋዜጣ
1900 ዓ.ም. ---------------------አውቶሞቢል
1900 ዓ.ም. ----------የሚኒስትሮች ሹመት
1901 ዓ.ም. --------------ፖሊስ ሰራዊት
1904 ዓ.ም. -----------የመድሃኒት መሸጫ ሱቆች

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደሀገራችን ያስገቡት ታላቁ አባታችን እምዬ ሚኒሊክ ናቸው!!!
ውድ አንባቢዎች ከላይ ከተገለፀበት መካከል የተሳሳተ መረጃ ካለ፡ እባካችሁ በውስጥ መስመር አናግሩኝ።





Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

29 Jul, 18:54


ጸሃፊው አኒስ መንሱር ተጠየቀ፡-

"የሰዎችን እውነታዊ መልክ እንዴት እናውቃለን?"

እርሱም አለ፦

"ባል ሚስቱ የታመመችበት እለት፤
ሚስትም ባሏ ድሃ በሚሆንበት ጊዜ ያውቃሉ፤
ወዳጅ በችግር ወቅት ይታወቃል፤
ልጆች ወላጆቻቸው ሲያረጁ ይታወቃሉ፤
ወንድሞች ውርስ በደረሰ ጊዜ ይተዋወቃሉ፤
እውነተኛ ፍቅርም ከእኛ በራቀ ጊዜ፤
አማኝም በፈተናው ሰዓት ይታወቃል።
"
                        



Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

07 Jul, 11:52


እንደምን ቆያችሁ ውድ የሀገረ ልጆች?
ሰላም፣ ጤና እና ጥበብ ሁሌም ከእንናተ አይለይ🙏 እያልኩ፤ አንድ አዲስ ዜና ይዠላችሁ መጥቻለሁ።

በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ወቅቱ ለተማሪዎች የእረፍት ማለተ ትምህርት የሚዘጋበት ጊዜ ስለሆነ፡ ተማርዎች ሰዓታቸውን በጥሩ ነገር ላይ እንዲያሳልፉ በማሰብ አንድ ነገር አዘጋጅቻለሁ፡ እርሱም................
Free Online Philosophy Course( ነፃ /ያለ ክፍያ የፍልስፍና ትምህርት) ስለዚህ እሄንን ዕድል መጠቀም የሚፈልግ እታች ባለው link መቀላቀል ይችላል 👇👇👇👇





👇👇👇👇👇👇
Join @&Share

💠 Philosophy education

🌐 Learning Philosophy

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

29 Jun, 19:20


የዜን ገዳም ውስጥ ነው። ዋናው የዜን ማስተር በጣም የተንደላቀቀ ህይወት ነው የሚኖረው። የሚኖርበት ቤት የሚበላው ምግብ የሚለብሰው ልብስ የቅንጦት ነው። የበታቾቹ ግን ቁሳዊ ምቾት የላቸውም። የሚጠቀሙት ነገር ሁሉ መደዴ ነው።

አንዱ መነኩሴ ይሄ ሁሌ ይነደዋል ለካ። ከዛ ወደ ማስተሩ ሄዶ እንዲህ አለው፦

"እንዴት እንዲህ አይነት ከፍተኛ የመንፈስ ብቃት ላይ ደርሰህ ሳለ ለቁስ ትገዛለህ? ለኛ ለበታቾችህም ጥሩ አርአያ አይደለም። በመንፈስ የበለፀገ ሰው ለምቾት ደንታ ሊኖረው አይገባም። ቁሳቁስን መናቅ አለብህ።"

ማስተሩም መለሰ፦

"አየህ እኔ መንፈሴ ስለበለፀገ ቁስ ምንም መስሎ አይታየኝም። ለኔ መገልገያ ነው ከዛ ያለፈ ትርጉም የለውም። በመንፈስ ያልነቃ ሰው ምቾት ቢለምድ ይሰናከላል ይሸወዳል። እኔ ያለሁበት የመንፈስ ብቃት ግን ቁሳዊ ምቾትን ያለ መሰናክል መጠቀም ያስችለኛል። እና መንፈሳዊ ብቃት ማለት ስጋን መበደል አይደለም"።
                         



Contact us 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

29 Jun, 13:28


"ራስህን በትክክል የምትወድ ከሆነ ሌላን የምትጎዳ አይነት ሰው አትሆንም "
/ ጉተማ ቡድሀ /

፨ ሰውን ለምን እንደሚጎዱ በሚጠየቁበት ሰአት "ስለምወደው" የሚል ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ስህተተኛ ብቻ ሳይሆን ሀሰተኛም ናቸው። ሰውን ለመጉዳት የምንነሳው ስለምንወደው ሳይሆን የወደድነውን የራሳችን ብቻ ለማድረግ የሚገፋን ራስወዳድነት ስለሚጫወትብን ነው።

የወደድከው ነገር ሁሉ ያንተ ካልሆነ አጥፋው የሚል ስሜት ውስጥህ ካለ...ስሜትህ ውሸት ነበር ማለት ነው። ፍሬ ከናፍር እወደዋለሁ ያልከው ነገር ያንተነቱን እንጂ እሱነቱን አልወደድከውም ማለት ነው...።
አንድን ነገር ስትወደው ተፈጥሮውን አድንቅለት...ነፃ አድርገው በቃ! ያንተ መሆን ያለመሆንን ምርጫ ለሱ ብቻ ተውለት...አንተ የመኖር መብት እንዳለህ ሁሉ የምትወደው ነገርም የመኖር መብት አለው...አንተ የመምረጥ መብት እንዳለህ ሁሉ የወደድከውም የመምረጥ መብት አለው...እዚህ መሀል ማስገደድ ካለ መውደድ የለም...!!

የራስህን አስተሳሰብ ስርአት ባላስያዝክበት ሁኔታ ሌላ ላይ ጣትህን ለመጠቆም እንደማትበቃው ሁሉ ራስህን መውደድህን በትክክል ባላረጋገጥክበት ሁኔታም ሌላን ልትወድ አትችልም ። የፍቅርን ትርጉም የማያውቅ እና ራሱን አፍቅሮ የማያቅ ሰው...ሥላፈቀርኳት የሌላ ሆና ማየት ሥለማልሻ አጠፋኋት ሲል ባደባባይ ይዋሻል...ራስህን አትዋሽ...!!

በትክክል ራሱን የሚወድ ሌላን የሚጎዳ ስብዕና የለውም...!!

🎤 ግልፅ እንድሆንላችሁ አንድ ወግ ላውጋችሁ፦
ታላቁ ማስተር ቻንድራ ሞሃንጅ (ራጅነሽ ኦሾ) እንዲህ ይላል 👇👇👇👇👇👇

አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ እንደማሰብ መርዘኛ ነገር የለም ሰውን የግል የማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው ከእንዲህ አይነቱ ስሜት ቢያንስ ጥላቻ ይሻላል በጥላቻ ውስጥ ውሸት የለም ከዚያ በላይም ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል።
የሰውን ልጅ ግን የግል የማድረግ ፍላጎት ፈጽሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው ፍቅር ማለት ሞት ነው።

"If you love a flower, don’t pick it up. Because if you pick it up it dies and it ceases to be what you love. So, if you love a flower, let it be. Love is not about possession. Love is about appreciation."




አስተያዬት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ ካለብዎት Click here 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

25 Jun, 12:21


.... ዛሬም እደግመዋለሁ፦ በጽሑፌ ላይ ያለው ፍቅር...... ወንድና ሴት አፈቀርኩሽ አፈቀኩኽ የሚባባሉ ፍቅር ሳይሆን፤ ንጽሕ እና ተፈጥሯዊ ወንድና ሴት ብሎ በፆታ የማይለይ ነው፤ እንከታተል👇👇👇👇👇

🌘የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው ። ሕይወት ካንተ ውጪ ሳትሆን ከእናንተ ጋር ትሁን፡፡

💫 ራስህን ስጋት አታድርግ፡፡ መልካም ሰው ማንንም አያማርርም ። ያለፍቅር ሕይወት ዋጋ የለውም ፡፡ ፍቅር የሕይወት ውሃ ነው ፣ ፍቅርን የሚያቅ ሰው የነፍስ መብራት ነው። ሁሉም ነገር እና ሁሉም ሰው ከማይታዩ ብዙ ህብረቶች ጋር የተሳሰረ ነው።

☀️ምን ዓይነት ፍቅርን መፈለግ እንዳለብህ አትጠይቅ…የምስራቃዊ ወይም ምዕራባዊ እያልክ ክፍፍል አትፍጠር፣ ያንተ ክፍፍሎች ወደ ብዙ መከፋፈል ከማምራት በቀር አንተን አይቀይሩህም፡፡ ፍቅር ስያሜ የለውም ፣ ትርጓሜ የለውም፡፡ንፁህ እና ቀላል ነው።

💫የሰዎችን ልብ አትስበር ፡፡ከአንተ ይልቅ ደካማ እንደሆኑ አርገህ ቁልቁል አትመልከት፡፡በአንደኛው የዓለም ክፍል ውስጥ ያለ ሀዘን መላውን ዓለም ሊያሰቃይ ይችላል ፣በዛው ልክ ደግሞ የአንድ ሰው ደስታ እና ፈገግታ መላውን ዓለም ፈገግ ሊያደርገው ይችላል።

☀️ አብዛኛዎቹ ግጭቶች እና ውጥረቶች በቋንቋ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው።ለቃላቶች በጣም ትኩረት አትስጥ ፣ በፍቅር ሀገር ውስጥ ቋንቋ የራሱ የሆነ ቦታ የለውም።
ፍቅር ውብ ዝምታ ነው ፡፡

የሱፊው ሊቅ ሸምስ ታብሪዝ





አስተያዬት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ ካለብዎት Click here 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

25 Jun, 09:24


#ከህይወቴ ተምሬያለው
💥. አንዳንድ ሰው እንዲያፈቅራችሁ ማድረግ እንደማይቻል ተምሬያለሁ ፤ ማድረግ የሚቻለው ጥሩ አፍቃሪ መሆን ብቻ ነው ።

💥.ብስለት የሚመጣው ከሚያጋጥሙን ተሞክሮዎች ዓይነትና ከተሞክሮዎቹ ከቀሰምናቸው ትምህርቶች እንጅ ካከበርናቸው የልደት በዓሎች ብዛት እንዳልሆነ ተምሬያለሁ ።

💥.እንዳንዴ የቱንም ያህል ለሌሎች ብጨነቅ እና ግድ ብሰጥ አንዳንዴ አንዳንዶች በመልሱ ግድ ላይሰጡ እንደሚችሉ ተምሬያለሁ ።

💥.ጓደኞች ምንም ያህል ጥሩ ቢሆን አልፎ አልፎ ማስቀየማቸው እንደማይቀር ተምሬያለሁ ። ባስቀየምናቸው ሰዎች ይቅር መባል በቂ ያለመሆኑንና ራስንም ይቅር ማለትም እንደሚያስፈልግ ተምርያለሁ ።

💥.መታመንን ለመግንባት ዘመናት እንደሚያስፈልግ ፤ ለማውደም ግን ሰከንዶች ብቻ እንደሚበቁ ተምሬያለሁ ።

💥.አንዳንድ ጊዜ ተንሸራትተህ ስትወድቅ ይረጋግጡኛል ብለህ የምትጠብቃቸውና የምትፈራቸው ሰዎች ብድግ አድርግው በማንሳት እንደሚያስገርሙህ ተምሬያለሁ ።

💥.እውነተኛ ጓደኝነት እንደዚህም እውነተኛ ፍቅር በቦታ ርቀት ሳይግደብ ማበብ መፍካቱ እንደማይቆም ተምሬያለሁ ።

💥.በአስተዋይነት "እምቢ" ማለት ሁልጊዜም የንፉግነት ምልክት ያለመሆኑን “እሺ” ማለትም ሁልጊዜ ምግባረ ሰናይነትን እንደማያሳይ ተገንዝቢያለሁ ።

💥.ራስን ከጥፋተኝነት ስሜት እንዲሁም ከጥላቻ የምንገላገልበት ብቸኛ መንገድም የአለፈውን ጊዜ ረስተን ከአሁን ጋር እርቅ ማድረግ ስንጀምር እንደሆነ ተምርያለው ።


💥. የማይፈፀም ቃል መግባት ከስጋ አልፎ፤ አጥንትንና ሕይወትን እንደሚጎዳ ተምረያለው።
ለዚህ አባባል የምሆን አንድ ታርክ ልንገራችሁ👇👇

:
:
:
•ንጉሱ በጣም ብርዳማ በሆነው ሌሊት ወደ ቤተመንግስቱ ሲገባ ስስ የሆነ ልብስ የለበሱ አንድ በእድሜ የገፉ የቤተመንግስቱን ጥበቃ ተመለከተ፡

ወደ እሳቸውም ተጠጋና አይበርዶትም? አላቸው፤

ሰውዬውም፦ይበርደኛል እንጂ ነገር ግን ብርድን የሚከላከል ልብስ የለኝም! አለ።

ንጉሱ፦ ወደ ህንጻው ከገባ በኋላ ከጠንካራው እና ብርድን የሚከላከል ከሱፍ የተሰራ ልብስ እንዲያመጣላቸው አንዱን አገልጋይ
ያዘዋል።

ጠባቂው፦ በንጉሱ ቃል በጣም ተደሰቱ። ነገር ግን የንጉሱ አገልጋይ ረስቶት ሊያመጣላቸው አልቻለም።

ሌሊቱ ሲነጋ ግን ንጉሱ ከቤተመንግስቱ ሲወጣ ሰውዬው ሞተው ያያል።

አንድ ብጣሽ ወረቀትም በእጃቸው ይዘው ነበር ንጉሱም ወረቀቱን ማንበብ ጀመረ።

ደብዳቤውም እንዲህ ይላል...............

"ብርዳማ ሌሊቶችን መቋቋም እችል ነበር ነገር ግን ለኔ ብርድ የሚከላከል ልብስ #ቃል መግባትህ ሀይሌን ነጠቀኝ" የምል ነበር ደብዳቤው።
.
~~~~~~~ ~~~
አያችሁ ቃል የምትገባላቸው ሰዎች ቃልህን ከምታስበው በላይ ቦታ ሊሰጡት
ይችላሉና እናስታውስ ቃላችንን አንጠፍ።
ሰናይ ቀን ተመኘሁላችሁ🙏🙏🙏
የእናንተው AB የዓለም ልጅ።





አስተያዬት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ ካለብዎት Click here 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲

ጥበብ ከፍልስፍና 📝📂📚

24 Jun, 18:49


1.ከሰነፍ ሰው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም፡፡አንድ አይነት ቋንቋ አናወራም፡፡ሰነፍ ከሆንክ አልረዳህም፡፡ ልረዳህም አልፈልግም፡፡ ”– kobe Bryant
+
2. “ጫናን ተግዳሮትንና አሉታዊ ነገሮችን ሁሉ የምወስዳቸው ሊያነሱኝ እንደ መጡ መልካም አጋጣሚ አድርጌ ነው፡፡
”– kobe Bryant
+
3. “ማረፍ መሃል ሳይሆን መጨረሻ ላይ ነው፡፡”– kobe Bryant
+
4. “በራስህ ተማመን ያለበልዚያ ሌላ ሰው ላንተ በራሱ ሊተማመን አይችልም፡፡”– kobe Bryant
+
5. “ ምን ያህል በማሸነፍ ሱስ እንደተጠመድኩኝ ሰዎች አይረዱም፡፡ ”– kobe Bryant
+
6. “ ቀጣዩ ማይክል ጆርዳን የመሆን እቅድ የለኝም፡፡ እኔ መሆን የምፈልገው ኮቢ ብርያንትን ብቻ ነው፡፡ ”– kobe Bryant
+
7. “ውድቀትን የምትፈራ ከሆነ አሁን የመውደቅ እድልህ ከፍ ያለ ነው፡፡”– kobe Bryant
+
8. “ እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር መሞከር እና ሰዎችን በማነቃቃት በመረጡት የስራ መስክ ታላቅ እንዲሆኑ መደገፍ ነው፡፡ ”– kobe Bryant
+
9. “ተስፋ ስትቆርጥ ሌላ ሰው እንዲያሸንፍ እየፈቀድክለት ነው፡፡ ”– kobe Bryant
+
10. “ዋናው የቡድንህ አባላት የምትጥረው ለእነሱ እንደሆነና እነሱ ስኬታማ እንዲሆኑ እንደምትፈልግ ማወቃቸው ነው፡፡”– kobe Bryant
+
11. “ የምችለውን ሁሉ ቆንጆ አድርጌ ከውኛለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ያለውን መንገድ ደግሞ እግዚአብሔር ይመራኛል፡፡ በዚህም ከልክ በላይ ደስተኛ ነኝ፡፡ ”– kobe Bryant





አስተያዬት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ ካለብዎት Click here 👉👉... 🌐  AB የአባቴ ልጅ 


#ሼር  #SHARE 🙏🙏
#ሼር #SHARE 🙏🙏

         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
         ☞ @Booksshelf22 ☜ 
━━━━━━✦✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲