Letenah Ejigu Wale

@letenahejiguwale


Letenah Ejigu Wale

31 Jul, 15:42


አማራ ባንክ

ሃረር ቅርንጫፍ

Letenah Ejigu Wale

30 Jul, 16:43


የድሬ ትዝታየ ሲደመር አዲሷ ሃረር ፤

ድሬዳዋ ከ13 አመት በኋላ መጣሁ ፤ ይገርማል ።በፈረንጆች 2010 ወይም በእኛ 2002 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ድሬ መጣሁ ።

በወቅቱ ወደ ድሬ የመጣሁበት ጉዳይ ወዲህ ነበር ። በወቅቱ በህንድ አገር ፓንጃብ ዩኒቨርሲቲ የፒኤቺዲ ተማሪ ነበርኩና በአገር አቀፍ የማይክሮ ፋይናንስ ኮንፈረንስ ላይ የምርምር ወረቀቴን ላቀርብ ወደ ድሬ መጣሁ ። ኮንፈረንሱን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ማህበር ነበር (Association of Ethiopian Microfinance Institutions, AEMFI). በወቅቱ ደግሞ የAEMFI ዳይሬክተር የነበረው ነፍሱን ይማረውና ዶር ወልዳይ አምሃ ነበር ። ዶር ወልዳይ አምሃ ለኢትዮጵያ ማይክሮ ፋይናንስ ዘርፉ እድገት ብዙ አስተዋፅኦ ያደረገ በጣም ትጉህ እና ቅን ሰው ነበር ። ዶር ወልዳይ አምሃ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር (Ethiopian Economics Association, EEA) ፕሬዝዳንትም ነበር ። ከሆኑ አመታት በፊት ነው እጅግ አስደንጋጭ በሆነ የመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈው ። RIP Dr Wolday Amha 😭

እናማ ድሬ የምርምር ወረቀቴን አቅርቤ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የቦርድ አባላትን እና ዋና ስራ አስፈፃሚዎችን አግኝቸ ስለ ዘርፉ ብዙ ሃሳቦች የተቀያየርኩበት ወቅት ነበር ። በነገራችን ላይ የኔ የፒኤቺዲ ትምህርት ፋይናንስ ነው ። እናም ለፒኤቺዲየ ምርምር ርዕስ በወቅቱ ስመርጥ በአእምሮየ የመጣው ጥያቄ እንዴት ነው የኔ ትምህርት ለድህነት ቅነሳ ትግሉ አስተዋፅኦ የሚያደርገው ብየ ማሰብ ጀመርኩ ። ይህንን ሃሳብ ደጋግሜ ሳውጠነጥነው የመጣልኝ ነገር በቃ ስለ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ማጥናት አለብኝ ብየ ነው ። ከዚያ በዚያው ዘርፍ ጥናቴን ሰራሁና ጨረስኩ ።

እንደኛ አይነት ድሃ ለሆነ አገር የማይክሮ ፋይናንስ ተቋሞች ለኢኮኖሚው እጅግ ሲበዛ ቁልፍ ተቋማት ናቸው ፤ መደገፍና በጣም ማደግ አለባቸው ። እያንዳንዱ ትምህርት ለለውጥ እና ለፀረ ድህነት ትግሉ ካልዋለ ወይም አስተዋፅኦ ካላደረገ ፋይዳ ቢስ ነው ። ያ የፒኤቺዲ ጥናቴም ትምህርቴን ለህዝብ ጥቅም እንዲውልና በተለይም ለድሃው ማህበረሰብ እንድቆረቆር የገፋኝ ይመስለኛል ። አሁን ላይ ሆኘ ሳስበው ደግሞ የፒኤቺዲ ጥናቴን በድሃ ተኮር ፋይናንስ (ማይክሮ ፋይናንስ) ላይ መስራቴ የህዝብ የፋይናንስ ተቋም የሆነውን አማራ ባንክ እንድንወልድ አስተዋፅኦ አድርጓል ብየ እንዳስብ ያስገድደኛል ። ተመልከቱ የሆነ ጊዜ በሆነ ነገር ከተለከፋችሁ በቃ ተለከፋችሁ ነው ። ብዙ የፋይናንስ የምርምር ዘርፎች ቢኖሩም እኔ ሁሌም የሚመስጠኝ የጥቃቅን እና አነስተኛ ፋይናንስ (Micro and Small Enterprises Finance) ነው ። እኔ የማምነው ልማት የሚመጣው ከታች ያለው ህዝብ ሲነቃነቅ ነው ብየ ነው ። I honestly beleive in grass root movement and bottom up approach to development. አገራችን ድሃ ናት ስለዚህ ሁሉም ሙያ ለፀረ ድህነት ትግሉ አስተዋፅኦ ማበርከት አለበት እላለሁ። ተማርን የምንል ሰዎች ትምህርት ዝም ብሎ ጉራ የምንቸረችርበት ሳይሆን አንተም ተቀይረህ ማህበረሰብ የምትቀይርበት መሆን አለበት ። ይህ የሁልጊዜም ፍልስፍናየ ነው ። ከዚህ ውጭ ከሆነ ለኔ ትምህርት ጉራ ብቻ ነው እለዋለሁ ።

የኔ ነገር ወደ ሌላ ነገር ገባሁ ፤ በሉ ወደ ድሬ ትዝታ ልመልሳችሁ ።

እናማ በወቅቱ ድሬ ሳምንት ያክል ቆይተን ብዙ ትዝታ ነበረን ። በዛን ጊዜ የድሬዳዋ ከንቲባ የነበሩት በአሁኑ ሰአት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ሃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ነበሩ ። ገና ወደ ድሬ ስንመጣ እንዴት በክብርና በማርሽ ባንድ እንደተቀበሉን አስታውሳለሁ ። ድሬዎች እንግዳ መቀበል ላይ 1ኛ ናቸው ። በየቀኑ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮንፈረንሱ አባላትን በድሬ የተለያዩ ምርጥ ሆቴሎች ከባድ የእራት ግብዣ ከሙሉ የሙዚቃና የመዝናኛ አገልግሎት ጋር ሲያቀርቡልን ነበር ። የምስራቁ ኢትዮጵያን ሙዚቃና ባህል ያየሁት ያኔ ነበር ። ከሰሜኑ ጋር ያለው ልዩነቱ ይገርመኝ ነበር ። ለመጀመሪያ ጊዜ ግመል ያየሁትም ያኔ ነበር ። ኢትዮጵያ ግን ምን ያክል ሰፊና በጣም ብዙ ልዩነቶች (diversity) እንዳላት የተረዳሁበትም ወቅት ነበር ። የድሬ ገብያዎችን ጎብኝተን ብዙ ነገርም (ለምሳሌ የሴቶች ድሪያ) ሸምተን ነበር ። ብቻ ድሬዎች ፍቅራቸው ልዩ ነው ።

ዌል እንግዲህ ይህን ሁሉ የድሬ ትዝታ ከ13 አመት በኋላ የመጣብኝ ዛሬ ከአአ ተነስተን ድሬዳዋ ኤርፖርት አርፈን በከተማው ወደ ሃረር ስናልፍ ነው ።

አሁን ሃረር ገባን ። ሃረር ለመጀመሪያ ጊዜ መምጣቴ ነው ፤ ዞርዞር ብየ ሃረርን ካየኋት በኋላ ስለ ሃረር ደግሞ አስቃኛችኋለሁ ። ከድሬ ሃረር እንዲህ ቅርብ ነው ለካ ። በመሃል ያሉ ከተሞችን አየኋቸው ። ከድሬ እንደወጣህ ደንገጎን ታገኛለህ ። ደንገጎ ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ሃረር የሚሄደው መንገድ የሚገነጥልባት ናት ። ቀጥሎ ሌሎች ትናንሽ ከተሞች አሉ ። ቀጥሎ ሃረምያ ዩኒቨርሲቲ ያለበት የሃረምያ ከተማ እና የሃረምያ ሃይቅን አየሁት ። ደርቋል የተባለው የሃረምያ ሃይቅ መመለሱ ደስ ይላል ።

በመጨረሻም ጥያቄ ፤

ውድ አንባቢዎቸ ፤ ከድሬ እስከ ሃረር ያለው አካባቢ ኢኮኖሚው በአብዛኛው የተመሰረተው በምንድን ላይ ነው ? መቸም ይህ ጥያቄ Exit Exam ቢመጣ ማንም ይደፍነዋል ብየ አስባለሁ ። ይህን ጥያቄ ስጠይቅ ግን ለምንድን ነው ሰይፉ ፋንታሁን ትዝ ያለኝ 😁

የጥያቄው መልስ በአረንጓዴ ወርቅ ወይም በርጫ የሚል ይሆናል 😁 አወዳይ የምትባልዋ የቀለጠች ከተማ ደግሞ የበርጫው ኢንዱስትሪ ዋና የአክሲዮን ገብያ ናት ኡዝቢላሂ 😁 ከበርጫ ሚኒስቴር መረጃ ካገኘሁ ስለ በርጫው ኢኮኖሚማ የምዳስሰው ነኝ (ፍላጎት ፤ አቅርቦት ፤ ምርት ፤ ፍጆታ ፤ ሽያጭ ፤ ዋጋ ፤ ትርፍ ፤ ሃብት ፤ እዳ ፤ ካፒታል፤ የፈጠረው የስራ እድል ፤የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማ ወዘተ)

ፅሁፌን በሙሃሙድ ሙዚቃ ልቋጨው ፤

የድሬ ልጅ ናት የከዚራ ፤
ስለውበቷ ምኑን ላውራ ።
የሀረር ልጅ ናት የአዋሽ ማዶ፤
ልቤ ተሠዷል እሧን ወዶ ።

ሻሎም ✌️✌️✌️

ለጤናህ ነኝ
ከሃኪም ጋራ ስር ፤ ሃረር

Letenah Ejigu Wale

30 Jul, 05:34


እርሳቸውም ከእነዚህ አንዱ እንዳልሆኑ እንዲህ መልሰዋል።

“እኔ ሚሊዮነር ሆኛለሁ፤ 20 ጊዜ የታተመ መጽሐፍ አለኝ። ሌላ 12 ጊዜ የታተመ መጽሐፍ አለኝ። 6.6 ሚሊዮን ሕብረት ባንክ አክሲዮን አለኝ፤ የማከራየው ቤት አለኝ፤ ገንዘብ መሥራት የጀመረ ዩቲዩብ አለኝ። ምን ትፈልጋለህ?”

ስለዚህ ሞቲቬሽን ይሠራል ነው የሚሉኝ?

“አዎ! የሰው ልጅ ዋናው ሃብቱ አስተሳሰቡ ነው። የሰው ልጅ ሃብቱ የመሬት ስፋት ቢሆን ሲንጋፖር አትኖርም ነበር። ምቹ መሬት ቢሆን ጃፓን አትኖርም ነበር። ዋናው ነገር ከአንገት በላይ ያለን አካል በአግባቡ መጠቀም ነው።

“እኔ ያን ሥልጠና ባልሳተፍ አሁን ጡረታ ወጥቼ ዳማ ስጫወት ነበር የምታገኘኝ። መሠልጠን በመቻሌ ግን ገና የ30 ዓመት ሕልም አለኝ።”

የናትናኤል አማራጭ መንገድ

ዶ/ር ወሮታው ከሚሉት በተቃራኒው የሚቆመው ናትናኤል እንደ ግለሰብም እንደ አገርም ለገባንበት ቀውስ መፍትሄው የሞቅታ ሞቲቬሽን አይደለም ይላል።

ታዲያ መፍትሄው ምንድነው ሲባል “ኮንሽየስ መሆን” ብሎ በድፍኑ ይመልሳል።

ከቀልብ መሆን፣ መንቃት፣ ያለንበትን ማወቅ ማለቱ ነው።

ሞቲቬሽን ያልነቃ ሕዝብ ኪስ ውስጥ ገብቶ ገንዘብ ለማውጣት ይሰራል። ለፖለቲከኞችም ሕዝብን ለመንዳት ይጠቅማል።

ምንጊዜም ያልነቃ ሕዝብ አእምሮ ውስጥ የሞቲቬሽን ጠብታ በመጨመር ማስከር ይቻላል። ለውጥን በሞቲቬሽን ማምጣት ግን ፍጹም አይቻልም ይላል።

“ጃፓን ድምጽ የለም፤ ሥራ ግን ይሠራል። እኛ ጋር ግን አገሩ ሁሉ በሞቲቬሽን ቀረርቶ ተሞልቷል። ለምን ይመስልሃል?”

ሞቲቬሽን መር ፍልስፍና እንደ አገር አይበጀንም የሚለው ናትናኤል፣ ይህ ያልተጨበጠ ባለጸጋ የመሆን ዲስኩር ከአስተዳደር አልፎ ወደ እምነት ቤቶች መግባቱን ይተቻል።

“ብዙ ቸርቾች ውስጥ አሁን አሁን ወንጌል ሳይሆን ሞቲቬሽን ነው የሚሰበከው። ኢየሱስ ምን ሊያመጣልኝ ይችላል እንጂ መቼ ይመጣል የሚል ሰው ከምዕመኑ ዘንድ የለም።”

“አገራችን ካለችበት ቀውስ ለመውጣት ሞቲቬሽን አይሠራም። እንችላለን፣ ታላቅ ነበርን፣ ታላቅ ነን በሚል ፉከራ አገር አይለወጥም። ከባድ ቀውስ ውስጥ ነን። ሞቲቬሽን ለዚህ መፍትሄ አያመጣም።”

ናትናኤል በተደጋጋሚ አሁን አማራጩ ‘ኮንሺየስነስ’ን መሞከር ነው ሲል አበክሮ ይሞገታል።

ምንድነው ኮንሺየስነስ ሲባል ግን የተፍታታ መልስ መስጠትን ገሸሽ ያደርጋል።

“መንቃት። በአእምሮ ሰላም ውስጥ መሆን። ከቀልብ መሆን። አሁን ላይ መሆን።”

ይህ ማለት ምን ማለት ነው?

“አጠገብህ የሚሻክር ነገር አለ?”

“አዎ!”

“ካለ ስሜቱን በቃላት ግለጽልኝ?”

ገለጽኩለት።

“አሳምረህ በቃላት ስሜቱን ገልጸኸዋል፤ እኔን ግን አልሻከረኝም።”

ለማለት የፈለከው አልገባኝም።

“ኮንሺየስነስ እንደዚያ ነው። ትኖረዋለህ እንጂ ቃላት በመደርደር አትገልጸውም። ወሬ ሳይሆን ተግባር ነው።”

***

*ይህ ጽሑፍ ባለፈው ዓመት “ሚሊየነር የመሆን ጥበብን የሚሰብኩን ሰዎች ለምን ‘ድሆች’ ሆኑ?” በሚል ርዕስ በቢቢሲ አማርኛ ላይ ወጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ከጥቂት ማሻሻያ ጋር በድጋሚ የቀረበ ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Letenah Ejigu Wale

30 Jul, 05:34


ዛሬ ደግሞ ለቲክቶክ ዘመን በሚስማማ መልኩ በሚጻፉ፣ ቶሎ ተጥደው፣ ቶሎ በሚገነፍሉ፣ ቶሎ ተነበው ቶሎ የሚጣሉ (Use and throw) መጻሕፍት ብቅ ብለዋል።

ገበያ የሚወዳቸው ሞቲቬሽኖች

የሚገርመው በዓለም የገነኑት የማነቃቂያ መጻሕፍት አብዛኞቹ በሚሊዮኖች ቅጂ የታተሙ ናቸው።

ከየትኛውም የመጻሕፍት ዘውግ (Genre) ባልተናነሰ ሁኔታም ወደ አማርኛ ተመልሰዋል።

በኢትዮጵያ ገበያ ሌሎች መጻሕፍት 3 ሺህ ቅጂን ለማለፍ ፍዳቸውን በሚያዩበት ጊዜ፣ እነሱ እንደዋዛ በ20 እና 30 ሺህ ቅጂ ይታተሙም ነበር።

አሁን ግን መጻሕፍቱ በመድረክ ዲስኩሮች እየተተኩ ይመስላል።

ፋይዳቸው ዘላቂ ነው? ብለን ብንጠይቅ አልዘገየንም ለማለት ነው።

እውን ናትናኤል እንደሚለው ሞቲቬሽኖች ‘የብድር ደስታ’ መፈልፈያ ፋብሪካዎች ናቸው? ወይስ ዶ/ር ወሮታው እንደሚሉት ሰዎችን ወደላቀ ልዕልና የሚያደርሱ አውራ ጎዳናዎች?

በሙግቱ ትንሽ እንግፋበት እና እናገባድ።

“በስድስት ዓመት ውስጥ ራሴን አፍርሼ ሠራሁት”

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ያመቻቸላቸው ሥልጠና አዲስ የብርሃን ዘመን የከፈተላቸው ዶ/ር ወሮታው፣ ከዚያ ወዲያ የሞቲቬሽን መጻሕፍትን እያሳደዱ ማንበብ ጀመሩ።

እሳቸው ወጣት ሳሉ የቭላድሚር ሌኒን እንጂ የናፖሊዮን ሒል መጻሕፍት አልነበሩም።

ስለ ግል ቢዝነስ ማሰብም ነውር ነበር።

የወላጅ ዘመድ የመጨረሻ ሕልምም ልጄ ተቀጥሮ ደመወዝ ይበላል ወይስ አይበላም የሚል ነበር።

ከ1992 ዓ.ም. ወዲህ ግን እነ ናፖሊዮን ሒል ብቅ አሉ። እሳቸውም "Think and Grow Rich"ን ነበር መጀመሪያ ያነበቡት።

ከፍተኛ መነቃቃት ፈጠረላቸው። ከዚያ ወዲያ የሞቲቬሽን መጽሐፍት አደን ውስጥ ገቡ።

ዘመኑን መለስ ብለው ሲያስታውሱ “ከዚያች ሥልጠና ወዲህ በነበሩ ስድስት ዓመታት ነበር ራሴን አፍርሼ እንደ አዲስ የሠራሁት” ይላሉ።

ሞቲቬሽን የሚሠራው እንዴት ነው?

አእምሯችን ከልጅነታችን ጀምሮ የሐሳብ ድር ሲያደራ ነው የኖረው።

በቀን በአማካይ ከ60 ሺህ በላይ የሐሳብ ዘለላዎችን ይመዛል፤ ይፈትላል። እያነሳ ይጥላል።

ከዚህ ሁሉ ሺህ የሐሳብ ደውር አብዛኛው ፀፀት እና ተስፋ ነው። ትናንት እና ነገ።

በሌላ አነጋገር አእምሯችን ወይ ወደ ትናንት ይንሸራተትብናል፤ አሊያ ደግሞ ወደ ነገ ይስፈነጠራል።

ዛሬ ላይ፣ አሁን ላይ ሁን ስንለው እሺ አይልም።

ለዚህም ነው “ከቀልቡ የሆነ ሰው ማግኘት አስቸጋሪ የሚሆነው” ይላል ናትናኤል።

ከቀልብ መሆን ምን ማለት ነው?

ክፍል ውስጥ አስተማሪ ስም ሲጠራ በአካል የተገኘውን ተማሪ ለመቁጠር ነው። ከቀልቡ የሆነ ሰውን ‘አቴንዳንስ’ ቢይዝ ግን አስተማሪው ራሱ ‘አብሰንት’ ሊባል ይችላል።

ከቀልብ መሆን ቀላል ነገር አይደለም። ሐሳብን ማቆም የዋዛ አይደለም።

ሌላ አብነት፤ ሰዎች መለኪያ ውስኪ የሚጎነጩት ኋላ እና ፊት የሚፈነጭን ሐሳብ ለማስቆም ነው። የሆነ መለኪያ ቁጥር ላይ ስንደርስ ይህ ይሳካል።

ፊልም የምናየውም ለተመሳሳይ ግብ ነው። ሐሳብን ለማስቆም። በምንወደው ፊልም ውስጥ እጅግ ፍሰሐ የምናደርገው ያ ቀዥቃዣው ሐሳብ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ስለሚቆም ነው።

አለበለዚያ በ5 ደቂቃ የ15 ዓመት ፀፀት እያሰብን ሕመም ውስጥ እንገባለን፤ እናረጃለን።

ወደ ዋናው ነጥባችን እንምጣ።

አነቃቂ (ሞቲቬሽን) ንግር ስንሰማ ወይም ጽሑፍ ስናነብ ከፍታ ላይ እንወጣለን፤ የስሜት ማማ ላይ።

ብዙዎቹ በቁማችን ቂቤ ያጠጡናል። ምኞታችንን እንድናመነዥግ ያግዙናል፤ በዲስኩር፣ በመጽሐፍ የሕልም ዓለም ውስጥ ያንሳፍፉናል።

ስለዚህ ከፍተኛ የስሜት መነቃቃት ይፈጠርብናል።

በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ ከሰዎች መማር፣ ጥልቅ የንባብ ፍቅር ውስጥ መግባት፣ በራስ ማመን ሊፈጠሩ ይችላሉ።

“ሞቲቬሽን ወደ ጠንካራ ዲሲፕሊን የመራቸው ሰዎች አሉ፤ ይህ በጎ ገጽታው ነው” ይላል ናትናኤል።

ክፋቱ ግን ሞቲቬሽን በራሱ ሱስ ሊሆን ይችላል።

ወደ እውነታው ስንመለስ ስለሚያመን እዚው መቅረት እንመርጣለን። ከሞቲቬሽን ወደ ሞቲቬሽን።

በማነቃቂያ መድኃኒት የምንሠራ ከሆነ የዚያ መድኃኒት ጥገኛ መሆናችን አይቀርም። ሞቲቬሽን ሱስ ነው። ሁሉም ሱስ ሃንጎአር አለው፤ ሞቲቬሽንም ቢሆን፣ ይላል።

ናትናኤል በሞቲቬሽን አብዮት ጊዜ ብዙ በጎ ነገሮች እንደተፈጠሩ አይክድም።

ሰዎች ንባብን ለምደዋል። ከአዲስ ሐሳብ ጋር ተዋውቀዋል። የጊዜ አጠቃቀማቸው ተሸሽሏል።

የሞቲቬሽን መሠረታዊ ችግሩ ግን አንድ ነው ይላል፤ “የብድር ደስታን መፍጠሩ።”

ሞቲቬሽን የደስታ ወረፋ ውስጥ ያሰልፈናል ይላል።

“ወደፊት ይህ ዓይነት መኪና፣ እንዲህ ዓይነት ቤት፣ እንዲያ ዓይነት ትዳር ሲኖረኝ ደስተኛ እሆናለሁ…” ካልን የደስታ ወረፋ ውስጥ ነን ማለት ነው።

ከአነቃቂ ንባብ/ዲስኩር በኋላ ሰዎች መጠነኛ ድብርት ውስጥ ይገባሉ የሚለው ናትናኤል ምክንያቱ “የብድር ደስታ ውስጥ ስለነበሩ ነው” ይላል።

“እኔም በሞቲቬሽን ሙሉ ጉባኤ ሙሉ ቁጭ ብድግ የማደርግበት ጊዜ ነበረ። ይሄ እኔ ሳልሆን ተማሪዎቼ የሚመሰክሩት ነገር ነው። ስህተት እንደሆነ ለመረዳት ግን ጊዜ ወስዶብኛል።”

ታዲያ መፍትሄው ምንድነው?

ሃብታም ሳይሆኑ ሃብታም የመሆን ምሥጢርን ማስተማር አይከብድም?

በአሜሪካ ብዙዎቹ የብልጽግና ሰባኪዎች፣ የይቻላል አቀንቃኞች ቢያንስ የሃብት ጥያቄያቸውን መልሰዋል።

ሚሊዮን ቅጂዎችን ሽጠዋል። ሕዝብ አነቃንቀዋል።

በእኛ አገር ይህ ብዙም አይታይም።

የሃብትን ምሥጢር፣ የብልጽግናን ቁልፍ እንካችሁ የሚሉን ሰባኪዎች ለራሳቸውም ያወቁ የማይመስሉበት አጋጣሚ አለ።

ይህን ጥያቄ ለዶ/ር ወሮታው አንስተንላቸው ነበር።

ሁሉንም በአንድ ቅርጫት ማስቀመጥ አግባብ እንዳልሆነ ጠቀሱ።

በልምድ እና በሕይወት ተሞክሮ አልፈው የሚያሠለጥኑ አሉ። አዳራሽ ሕዝብ ሰብስበው ያለ ምንም የሕይወት ልምድ፣ ሕዝብ ላይ ቴአትር የሚሠሩም አሉ።

“ለምሳሌ ናፖሊዮን ሒል ‘ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች’ን ሲጽፍ 25 ዓመት ነው የወሰደበት።”

ስለዚህ እያሉን ያሉት ዶ/ር፣ ችግሩ ከሥልጠናው ሳይሆን ከአሠልጣኞቹ ነው?

“አዎ! ለምሳሌ የእኔ አሠልጣኞች ያሰብከውን ስላለምክ ብቻ ትደርስበታለህ አላሉኝም። ለስኬት የምከፍለው ከፍተኛ ዋጋ እንዳለ ነው ያስተማሩኝ።”

ባልተፈተነ ሕይወት፣ በጣፈጠ ቋንቋ ብቻ በሰው አእምሮ መጫወት ትክክል አይደለም የሚሉት ዶ/ር ወሮታው “ሙሉ አዳራሽ አስፈንጥዞ ማስወጣት ይቻላል። እኔ ያንን አልከተልም።”

ዶ/ር ግን የማነቃቂያ ሥልጠና በመስጠት ሰውን ከድህንት ማውጣት ይቻላል? የምር ይህ ዘዴ ይሠራል ብለው ያምናሉ?

“እንዴታ! ሰው ከዋሻ የወጣው ከችግር ለመውጣት ነው። ቁርጠኝነት እና ዓላማ ካለ ምን የማይሠራ ነገር አለ። ደግሞም በኢትዮጵያ። አንድ ሰው 8 ሰዓት ቢሮ ከሠራ ሌላውን 8 ሰዓት ባጃጅ ቢነዳ ምንድነው ችግሩ። የመለወጥ ቁርጠኝነት ካለ ማለቴ ነው።”

ዶ/ር ሌላው ጥያቄ ሰዎችን አትቀጠሩ እያላችሁ ለምን በተሳሳተ መንገድ ታበረታታላችሁ?

“ተቀጥረህ አትቅር እናለለን እንጂ አትቀጠር አንልም። ሰው ልምድ ማግኘት አለበት እኮ።”

የመጨረሻ ጥያቄ ዶ/ር፣ ሃብት እና ብልጽግናን የምትሰብኩ ሰዎች ለራሳችሁም ሃብት አልፈጠራችሁም ይሏችኋል?

“ይህ የተሳሳተ ነው። የእነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አሰልጣኝ ሯጭ ሳይሆን ለምን ያሰለጥናል ይባላል እንዴ? አዋቂ ያወቀውን ቢያስተምር በቂ ነው።”

ዶ/ር ወሮታው ይህን ካሉ በኋላ ግን በልምድ እና በዕውቀት ያልዳበረ ሕይወት ሌላውን ለማብቃት ባይደፍር መልካም እንደሆነ አልሸሸጉም።

Letenah Ejigu Wale

30 Jul, 05:34


አነቃቂ ንግግሮች ወዴት ያደርሱናል?

* ወደ የማይጨበጥ ተስፋ ወይስ ወደ ስኬት?

#Ethiopia | መካሪና ሰባኪ በዝቷል። ከመገናኛ እስከ ኢኒስታግራም፤ ከዩትዩብ እስከ ድልብ መጻሕፍት፣ ከመድረክ እስከ ታክሲ፤ በተለይ አራተኛ ወንበር ላይ።

የሁሉም መልዕክት አንድ ነው፤ ‘የብልጽግና ባቡር ቀርባለችና ተሳፈሩ’ የሚል።

በየዓመቱ መቶ ሺዎች እየተመረቁ ሥራ ያጣሉ። ‘የሥራ ፍጠሩ’ ሰባኪዎች ይቀበሏቸዋል።

በስንት ደጅ ጥናት የተገኘን ሥራ ‘ጥላችሁ ውጡ’ ይላሉ። ዛሬውኑ የራሳችሁ አለቃ ሁኑ እያሉ ያስጎመዣሉ።

ከእጅ ወደ አፍ ቀርቶ፣ እንደ ወፍ - ከአፍ ወደ አፍ በሆነ የዛሬ ኑሮ፣ ‘ከቆጠባችሁ ከነገ ወዲያ ሚሊዮነር ትሆናላችሁ’ ይላል።

አነቃቂ መጻሕፍት ሕይወት ይለውጣሉ? የመድረክ ዲስኩሮች ያበለጽጋሉ?

አንዳንዶች ‘አዎና! እኛን ነው ማየት!’ ይላሉ።

ሌሎች ደግሞ በአነቃቂ መጻሕፍት የሚለወጥ ሕይወት ካለ የደራሲው እና የዲስኩረኛው ብቻ ነው ብለው ያፌዛሉ።

በሁለቱም ጎራ የካበተ ልምድ ያላቸውን አሰልፈን ጉዳዩን ብናብላላውስ?

ዶ/ር ወሮታው፡ “የአንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ሕይወት ለመለወጥ እየሠራሁ ነው”

በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ግንኙነት ሦስተኛ ዲግሪ አላቸው። የእርሳቸው ሥራ ግን የሰዎችን አእምሮ ከብልጽግና ጋር ማዋደድ ነው። ወጣቶችን ወደ ሃብት ማማ ማውጣት።

የትኛውንም አእምሮ በመግራት ስኬት እና ልዕልናን ማጎናጸፍ ይቻላል ብለው ያምናሉ።

እንደተመረቁ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ተቀጠሩ፣ ከዚያም ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ሆኑ።

ከዕለታት አንድ ቀን “ሕይወቴን የሚለውጥ አጋጣሚ ተፈጠረ” ይላሉ ዶ/ር ወሮታው።

ቀን እና ወሩን ሁሉ አይረሱትም። በ1992 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ከዩኒቨርስቲው ከጋና በመጡ አሠልጣኞቹ በሚሰጥ ሥልጠና ላይ እንዲሳተፉ ተላኩ።

ሥልጠናውን ሲጨርሱ ከባድ የአስተሳሰብ ነውጥ ገጠማቸው። የአስተሳሰብ ነውጡ፣ የሕይወት ለውጥን አስከተለ።

“በዚያች ቅጽበት የራሴን ነጻነት አወጅኩ፤ ከዚያ በኋላ በጭራሽ አልተቀጠርኩም፤ በጭራሽ!” ይላሉ።

“ተቀጥሮ መሥራት አንገሽግሾዎት ስለነበር ነው ዶ/ር?”

“አይደለም፤ በዚያች ቅጽበት የምኖርለትን ሕልሜን ስላገኘሁ ነው።”

“የሚኖሩለት ሕልም ምንድን ነበር?”

“ማሠልጠን፤ ባለጸጎችን ለኢትዮጵያ ማፍራት።”

“የምር ይሳካል ብለው ያምናሉ?”

“ያለጥርጥር! አንድ ሚሊዮን ባለጸጎችን ለኢትዮጵያ እናፈራለን።”

“መቼ ነው ይህን ሁሉ ሰው ባለጸጋ የሚያደርጉት?”

“የዛሬ 20 ዓመት፤ በነሐሴ 2023 ዓ.ም።”

ዶ/ር ወሮታው ይህን የሚሉበት እርግጠኝነት የእምነታቸውን ጥንካሬ ያሳብቃል። እንዴት ያለ ሥልጠና ቢሆን ነው?

“...በዚያ ሥልጠና ወሮታው ላይ ሳቅኩበት፤ ወሮታውን ነጻ አወጣሁት። ለሕልሜ ታማኝ እንድሆን፣ ሃብቴ አስተሳሰቤ እንደሆነ፣ የማምንበትን እየሠራሁ እንድኖር ያደረገኝ አጋጣሚ ነበር።”

የእሳቸው ሕይወት በአንድ ሥልጠና ከተለወጠ የሌሎች ሕይወት ለምን አይለወጥም?

ናትናኤል ፋንታ፡ “የሞቲቬሽን ሥልጠና በብድር መደሰት ማለት ነው”

‘ናትናኤል ሜሞሪ’ በሚለው የንግድ ስሙ በርካቶች ያውቁት ይሆናል።

የሕይወቱን እኩሌታ በአእምሮ ሥልጠና ላይ አሳልፏል።

ናትናኤል በተለይ በማስታወስ ጥበቡ በ90ዎቹ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እየቀረበ ብዙ ሰዎችን ሲያስደምም አንዳንዶች ዛሬም ድረስ ያስታውሱታል።

ናትናኤል ከማስታወስ ጥበብ በኋላ በቀጥታ ወደ ‘ሞቲቬሽን’ [ማነቃቃት] ተሸጋገረ።

ብቻ በጥቅሉ ባለፉት በ21 ዓመታት በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከአእምሮ ጋር በተያያዘ አሠልጥኗል።

የእሱን ልብ አንጠልጣይ ‘ሞቲቬሽን’ ቃል ለመስማት ብዙዎች አዲስ አበባ 22 አካባቢ ደጅ ጠንተዋል።

እሱም ያንን ዘመን በመለስተኛ ፀፀት እያስታወሰ፣ “...ሙሉ ጉባኤ ቁጭ ብድግ አስደርግ ነበር” ይላል።

አሁን ግን ፍጹም በተቃራኒው ቆሟል። የአነቃቂ ንግግሮች አድናቂ አይደለም። እንዲያውም ‘ሞቲቬሽን’ አይሠራም ሲል አውጇል።

“ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ያረጋገጥኩት አንድ ነገር ቢኖር፣ የሰዎችን ሕይወት ለመለወጥ ትክክለኛው መንገድ ያ እንዳልነበረ ነው” ይላል።

ለምን? በ21 ዓመት ውስጥ ምን ተፈጠረ? ትክክለኛው መንገድ ያ ካልሆነ ታዲያ የቱ ነው?

በዓመታት ጥናት ደረስኩበት የሚለውን ይነግረናል።

የአነቃቂ መጻሕፍት አጭር የሕይወት ታሪክ

ራስ አገዝ መጻሕፍት፣ የይቻላል ዲስኩሮች እና መሰሎቻቸው በጅምላው ‘ሰልፍ ዴቨሎፕመንት ኢንዱስትሪ’ ውስጥ ይካተታሉ።

በአሜሪካ በአንድ ወቅት ከሙዚቃ ኢንዱስትሪው ቀጥሎ ሚሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ዘርፍ ነበር። በተለይ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ወዲህ።

የአነቃቂ መጻሕት አባት የሚባለው ቻርልስ ሃናል ነው።

ኋላ የመጡት ገናናዎች የእርሱ ደቀ መዛሙርት ናቸው።

በዘመኑ የጻፈው ነገር አእምሮን የሚያሸፍት ነበር።

“…ኋላ ላይ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን መጽሐፎቹን ለቅማ አቃጥላበታለች” ይላል ናትናኤል።

ከእርሱ በኋላ አብረሃም ማስሎው መጣ። “አእምሮን በመግራት ማንም ሰው ምንም መሆን ይችላል” ብሎ ተነሳ።

ቀስ በቀስ ሞቲቬሽን ከቤት እና ከቢሮ ወጥቶ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሰተት ብሎ ገባ።

የይቻላል መንፈስ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንቀጾች ጋር ስምም ተደርጎ በሰባኪዎች አንደበት ተነገረ።

ሚሊዮኖች በተስፋ ራሳቸውን ሳቱ። ያለስስት ጥሪታቸውን ለሰባኪያን ሸለሙ።

ከአፋቸው ማር ጠብ የሚልልላቸው ሰባኪያን መቅደስ ጠበባቸው። በቲቪ መስኮት መጡ።

‘ቴሌቫንጀሊስቶች’ ተወለዱ። በስብከት ጉባኤ መዋጮ የግል ጄት ገዙ። ምዕመናን የታክሲ እያጡ፣ እየነጡ መጡ።

ካፒታሊዝም ፋፋ። የገበያ ትንቅንቅ ተፈጠረ።

‘ሞቲቬሽን’ ሽያጭን የሚያስመነድግ ሁነኛ መሣሪያ እንደሆነ ተደረሰበት።

ሰዎች የስቶክ ማርኬት የድርሻ ገበያ እንዲገዙ ማሳመን ፈተና ሆኖ ነበር።

ለዚያም ነው በሞቲቬሽን አእምሯቸውን ማጦዝ፣ በተስፋ ካውያ ማጋል አስፈላጊ ሆኖ የተገኘው።

እንዲህ፣ እንዲያ እያለ በ80ዎቹ እና በ90ዎቹ የሞቲቬሽን ኢንዱስትሪ ጣሪያ ነካ። ደራሲያን መጻሕፍትን በሚሊዮኖች ቅጂ መሸጥ ጀመሩ።

በእኛም አገር ‘ኔትዎርክ ማርኬቲንግ’ በስፋት ዘልቆ ገባ።

የ’ጎልድ ኩዌስት’ ዘመን፣ የፒራሚድ ገበያን ለማሳለጥ ሁነኛ የ’ሴልስ’ ስትራቴጂ ኾኖ አገለገለ።

ሐኪሞች ሆስፒታልን፣ መምህራን አስኳላን ጥለው ወጡ፤ ወደ ሀብት ይወስዳል የተባለው አውራ ጎዳና በሕዝብ ታመቀ፣ ተጨነቀ።

ብዙዎች “አይቤን ማን ወሰደው”ን እያነበቡ አይባቸውን ፍለጋ ባዘኑ። አንዳንዶች አገኙት። ብዙዎች አጡት።

ናትናኤል ያን ዘመን የነበረውን አስደማሚ መነቃቃት ሲያስታውስ፣ “አዳራሽ ውስጥ ‘I believe I can fly’ የሚል ሙዚቃ ተከፍቶ ሰዎች በተስፋ ብቻ ሲያለቅሱ አይቻለሁ” ይላል።

ይህን ነው እሱ “የብድር ደስታ” የሚለው። ምን ማለቱ እንደሆነ ቆየት ብሎ ያስረዳናል።

የዴል ካርኒጌ ዘመን

እርግጥ በእኛ አገር ብቻም ሳይሆን አሜሪካ ገበያ እነ ዴል ካርንጌ፣ እነ ናፖሊዮን ሒል የጻፏቸው መጻሕፍት ከባድ የአስተሳሰብ አብዮት አስነስተዋል።

በተለይ ናፖሊዮን ሒል ለ25 ዓመታት 500 የሚሆኑ እጅግ የናጠጡ ባለጸጎች ላይ ጥናት ሠርቶ “Think and Grow Rich” የሚለውን መጽሐፉን ከጻፈ በኋላ ምድረ አሜሪካ በ‘ይቻላል’ ተነቃንቋል።

ከዚያ ወዲያ ‘ሞቲቬሽን ዘርፍ’ ሳይከስም እየጎመራ ነው የቆየው።

በርካታ በዓለም ዙሪያ የተሰራጩ የማነቃቂያ መጻሕፍት ታትመው ሚሊዮኖች ጋር ደርሰዋል።

Letenah Ejigu Wale

29 Jul, 13:39


የገቢ ስትራቴጅ (Revenue Strategy)

1. በላብህ በደምህ (Active Income)

2. በብርህ (Passive Income)

Letenah Ejigu Wale

29 Jul, 13:38


የአንድ ሰው የገቢ ኡደት (Revenue Cycle) ምን ይመስላል?

(ለጤናህ እጅጉ ዋለ)

የአንድ ሰው የገቢ ኡደቱ እንደሚከተለው ከ ሀ ወደ ፐ ይፈሳል ። ማለቴ ከለፍተህ ጥረህ ግረህ ብላ (Active Income) ወደ ብዙ ሳትለፋ ብላ (Passive Income) የሚቀየረው በሚከተለው ዘዴ ነው ።

1. በመጀመሪያ የሆነ የሚያበላ 😂 ትምህርት ወይም ሙያ ተማሩ ። የሚያበላ ትምህርት ወይም ሙያ ምንድን ነው ከተባለ እንጃ ራሳችሁ ተወያዩበት 😂 እውቀትና ሙያ ነፃ ያወጣል የምንለው ለዚያ ነው ። የአንድ አገር እድገትና ብልፅግና መሰረቷ ትምህርት ነው ። ያልተማረ ሰውኮ ገንዘብ ቢኖረውም እየኖረ አይደለም ። ያልተማረ ሰው በጨለማ ውስጥ የሚኖር ሰው ነው ። በኔ አተያይ ህዝባችን ቢያንስ በዝቅተኛ ደረጃ ወይ ቴክኒክ እና ሙያ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ መያዝ አለበት ። ከዚያ በላይ ያለው እንኳን ለጥቂቶች ብቻ ነው መሆን ያለበት ። አገሪቱ እንዳይን የጠፋችው ሁሉም በግድ ማስተርስና ዶክትሬት ካልያዝኩ ብሎ ገግሞ ነው 😁

2. ቀጥሎ በተማራችሁበት ትምህርት እና ሙያ የሚያበላ ቦታ 😂 ተቀጠሩና ገቢ አግኙ ፤ ይህ በላብ የሚገኘው ገቢ Active Income ይባላል ። አዳም ሆይ ለፍተህ ጥረህ ግረህ ብላ ብሏል ታላቁ እና ቅዱሱ መፅሃፍ ። የሚያበላ መስሪያ ቤት የቱ ነው እንጃ እራሳችሁ ተወያዩበት😂

3. ቀጥሎ ተቀጥራችሁ ከምታገኙት ገቢ ውስጥ ቆጥቡ ሁሉን አታውድሙት ፤ የብዙ ሰው ችግር ይኸ ነው ፤ ሁሉን ማውደም ። በአለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ቢያንስ የገቢያችንን 20% መቆጠብ አለብን ይባላል ። እኛ ግን ያለንን ሁሉ አውድመን ከዛ ወይ እንበደራለን ወይ እንለምናለን ። በቁጠባ ላይማ አነቃቂ ስልጠና መስጠት አለብኝ 😂

3. ቀጥሎ ቁጠባችሁን ይዛችሁ ባንክ ሂዱና ተበደሩ ። ብድር አትፍሩ ። ስለብድርም ስልጠና መስጠት አለብኝ 😂

4. ቀጥሎ የራሳችሁን ቁጠባና የባንክ ብድሩን ይዛችሁ ብዙ ሳትለፉ ገቢ የሚያስገኝላችሁ ንብረት ግዙ ። ያ ንብረት የሚከራይ ህንፃ መገንባት ወይም የሚያበላ አክሲዮን መግዛት ሊሆን ይችላል ። Look back again all kind of passive income strategies I wrote.

5. ህንፃውን አከራዩ ወይም አክሲዮን ግዙና ቀስ በቀስ ከመቀጠር ወጡ እና ሳትለፉ ገቢ አግኙ ። ይህ ብዙ ሳትለፉ ገቢ የምታገኙበት ዘዴ Passive Income ይባላል ። ህንፃው ወይም አክሲዮኑ ይሰራል አንተ አትሰራም ግን ትበላለህ 😁 Passive Income ማለት ሳትሰራ መብላት ነው ። በነገራችን ላይ ይህ ህጋዊ እና ታክስ የሚከፈልበት ስራ ነው ። አንዳንዱ እንደ ህገወጥ ስራ ሊያየው ስለሚችል ብየ ነው ይችን ነጥብ የጨመርኳት 😁

በአጠቃላይ ይኸው ነው ፤ እና ግልጥ ነው ጓዶች 😂

ይህን ሁሉ እንድለፈልፍ ያደረገኝ ዶር GM Melaku ከአሜሪካ ህንፃው እንዴት ይሰራል ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ ነው ። እግዞ ተው እንጂ ብዙ አታስለፍልፉኝ 😁

ሻሎም

ለጤናህ ነኝ
ከአባይ ወንዝ ዳር

Letenah Ejigu Wale

29 Jul, 12:17


ብዙ ሳንለፋ ገቢ የምናገኝባቸው ዘዴዎች (Passive Income Strategies)

(ለጤናህ እጅጉ ዋለ )

1. ህንፃ ማከራየት

2. የትርፍ ክፍፍል የሚከፍሉ አክሲዮኖችን መግዛት

3. ለጓደኛህ ማበደር (Peer to Peer Lending)

4. በዌብሳይት ምርቶችን ማስተዋወቅ (Affilate Marketing)

5. ዲጂታል ኮርስ ወይም ኮንቴንት መፍጠር

6. ከአእምሮአዊ ንብረት የሚገኝ ሮያሊቲ

7. ከፍተኛ ወለድ የሚያስገኙ የባንክ ቁጠባዎች

8. ንብረት ማከራየት ፤ ለምሳሌ መኪና ፤ ማሽን ሌላም እቃ

Letenah Ejigu Wale

28 Jul, 17:38


የማዳበሪያ ስርጭት ምርመራ ይካሄድ !!!

በኔ ግምት በማዳበሪያ ስርጭት ጉዳይ ላይ ማዳበሪያው ጥቁር ገብያ ገብቶ አርስአደሩ እንዲበዘበዝ ያደረጉ ማንኛውም ከላይም ሆነ ከታች ያለ አመራር ሆነም ባለሙያ ሆነ ነጋዴ ካለም ነጋዴ በሚመለከታቸው የህግ አካላት (ፀረ ሙስና ፤ አቃቢ ህግ ፤ ፖሊስ ወዘተ) ምርመራ መደረግ አለበት እላለሁ ። ለዚህም በየሶሻል ሚዲያው የህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ የሚለው አክቲቪስቱ ወጥሮ መቀስቀስ አለበት እላለሁ ። በማስቀጠል የህዝብ የቴሌቪዢን ጣቢያዎችም (ኢቢሲ ፤ አሚኮ ፤ ፋና ፤ ዋልታ ወዘተ ) serious የሆነ የምርመራ ጋዜጠኝነት (Investigative Journalism) ዘገባ መስራት አለባቸው ። ይህን ካልሰሩ ምን ሊሰሩ ነው ? ዋ !

ባጭሩ ከዚህ በላይ አገርና ህዝብን systematically መግደል የለምና ሁሉም ተረባርቦ አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረግ አለበት እላለሁ !!!

Letenah Ejigu Wale

27 Jul, 18:02


ጥቂት ስለ ጉምቱ አርክቴክቶች ፤

ዌል እንግዲክ የተለያየ ፕሮጀክት እና አጋጣሚ እያገናኘን ውሎየ ከጉምቱ አርክቴክቶች ጋር ከሆነ ሰነባበተ። እናማ የሚቀጥለው የዝውውር መስኮት ሲከፈት ከአካውንቲንግና ፋይናንስ ወደ አርክቴክቸር በከፍተኛ ሳምንታዊ ደሞዝ ሳልዘዋወር አልቀረሁም 😁

ወደ ፎቶው ስመጣ በቀኝ በኩል ያለው አርክቴክት ወሰን አወቀ ሲሆን በግራ በኩል ያለው ደግሞ አርክቴክት ገናነው ዓለምነው ዳምጤ ነው ።

ስለ እነዚህ ጉምቱ አርክቴክቶች በጣም ትንሽ ልበላችሁ ።

👉አርክቴክት ወሰን ማለት በጣም senior አርክቴክትና በአአዩ አስተማሪ የነበረ ነው ። የወሰን አርክቴክት www.wossen.com ባለቤት ነው ። አርክቴክት ወሰን
በጣም ብዙ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ሰርቷል ። መዘርዘር ከባድ ነው ። እሱ የሰራውን አንድ iconic ኘሮጀክት ብቻ ልንገራችሁ ። የባህርዳር ፈርጥ የሆነው Blue Nile Avanti Hotel Resort የተሰራው በእሱ ነው ።

👉አርክቴክት ገናናው ማለት የ Shigez Architects መስራችና CEO ነው ። በተጨማሪም የImpact Real Estate ባለቤትም ነው ። በጣም ትላልቅ አገራዊ ፕሮጀክቶችን ሰርቷል ። ለምሳሌ ግዙፉ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስታድየም የተሰራው በእርሱ ነው ። በተጨማሪም በጣም ብዙ እና ግዙፍ የመንግስት ፤ የዩኒቨርሲቲ እና የግል ባለሃብቶች ፕሮጀክቶች ሰርቷል ። መዘርዘር ከባድ ነው ።

እነዚህ ድንቅ አርክቴክቶች ለመጭው የአርክቴክቸር ትውልድ ምሳሌ ስለሚሆኑ ወደፊትም ስለ እነሱ ስራ እፅፋለሁ ።

Architects with Beautiful Minds!

ሳጠቃልለው ሰው የሚመስለው ውሎውን ነው ። እናማ አርክቴክቸር በጣም እየከየፈኝ ስለሆነ በዚህ ዘርፍ የሆነ አጭር ኮርስ በonline ቢሆንም መውሰዴ አልቀረም ዋ 😁

ሻሎም ✌️✌️✌️

ለጤናህ ነኝ
ከአባይ ወንዝ ዳር

Letenah Ejigu Wale

19 Jul, 17:58


የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት (Exit Exam Results) ጉዳይ ፤

(ለጤናህ እጅጉ ዋለ)

1. መግቢያ

ዌል እንግዲህ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተማሪዎች በአገር አቀፉ የዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ላይ ለምን ዝቅተኛ ውጤት አመጡ የሚለውን ወቅታዊ ጉዳይ በመጎርጎር ላይ እንገኛለን ። ለዚህም መረጃ መሰብሰቡ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። በየዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ተማሪዎችም ጉዳዩ በትምህርት ሚኒስቴር እንዲመረመር እየጠየቁ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው ።

ነገሩ አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል ነውና በየቀኑ አዲስ ነገር ሳይኖር አልቀረም ። ተከተሉን እስቲ ።

እናላችሁማ በደረሰኝ መረጃ መሰረት ከታች ያያዝኩትን ሰንጠረዢ ሰራሁ ። ሰንጠረዡ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተማሪዎችን የመውጫ ፈተና ውጤትን ከተቀራራቢ ዲፓርትመንት ተማሪዎች ውጤት ጋር ለማወዳደር ተሞክሯል ። ለአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተቀራራቢ የሚባሉት ደግሞ የኢኮኖሚክስ እና ማኔጅመንት ዲፓርትመንቶች ናቸው ።

2. መጠነኛ ትንታኔ

የንስር አይን ላለው ሰው ሰንጠረዡ ብዙ ነገር ይናገራል ። ይህ ጥናት የናሙና ብዛት 21 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው ። ናሙናው 21 ብቻ ስለሆነ ጥናቱ ባለ ትንሽ ናሙና ጥናት (Small Sample Research) ይባላል። በሰንጠረዡ ያስቀመጥኩት ብዙ የስታቲስቲክ መረጃዎች ቢሆንም የትንሽ ናሙና ጥናት የሚጠቀማቸውን የስታቲስቲክስ መረጃዎች ብቻ ለይታችሁ ተንትኗቸው ። ለማንኛውም በሰንጠረዡ ያስቀመጥኩት የሚከተሉትን የስታቲስቲክስ መረጃዎችን ነው ።

2.1 አማካኝ ነጥቦች (Measures of Central Tendency) ፤

በዚህ ውስጥ የምታዩት Mean እና Median ናቸው ። Median ሌላ ስሙ Quartile 2 (Q2) ነው ።

2.2. የመረጃው ቅርፅ (Measures of Shape)

በዚህ ውስጥ የሚታዩት ደግሞ Minimum, Maximum, Quartle 1 (Q1), Quartile 3 (Q3), The difference between Median and Mean, Skewness and Kurtosis ናቸው ።

2.3. የመረጃው መለያየት(Measures of Dispersion) ፤
በዚህ ውስጥ የሚታዩት Range and Inter-Quartile Range(IQR) ናቸው ።

አንድ ትንታኔ ብቻ ላቅርብ ፤

ከላይ እንዳልኩት ይህ የትንሽ ናሙና ጥናት ነው ። በእንደዚህ አይነት ጥናት አማካኝ መለካት ያለበት በMedian ነው ። የኢኮኖሚክስ እና ማኔጅመንት ተማሪዎች አማካኝ የማለፍ ምጣኔ 85% ሲሆን የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ግን 19% ነው ። ልዩነቱ 60% ነው ። ይህም ማለት ከባድ ውድቀት ነው ። ይህን 60% ውድቀት ደግሞ በስታቲስክስ አይን ትልቅ ወይም ትንሽ ቁጥር መሆኑ Non-Parametric Tests ተወስደው ይፈተሻል ፤ ከፍ ወዳለው ወደዚያ ትንታኔ ግን አልሄድም ። በግርድፉ ግን የ60% ውድቀት ከባድ ቁጥር ስለሆነ ይህን ችግር የፈጠረውን ምክንያት ፈልፍሎ ማጥናት ይጠይቃል ።

ነገርየው ሳይከፈለኝ ሙሉ የምርምር ወረቀት ሊሆን ስለሆነ 😁 ላሳጥረውና ሌላውን ትንታኔ ቀጥሉበት 😁 ትምህርት ሚኒስቴር ከከፈለኝ ግን እቀጥላለሁ 😁

3. ለአሁኑ ምን ይደረግ ?

ትምህርት ሚኒስቴር ገለልተኛ ኮሚቴ አዋቅሮ ነገሩን በጥልቀት ያስጠናው እና ኮሚቴው በሚደርስበት የውሳኔ ሃሳብ መሰረት የማስተካከያ እርምጃ ይወሰድ ።

4. ለወደፊት ምን ይደረግ ?

ይህ ግርድፍ መረጃ ለወደፊቱ ብዙ ነገር እንድናጠና ያደርገናል ። ለምሳሌ የእያንዳንዱን ተማሪ ውጤት እና የተማሪው ሌሎች መረጃዎች በመውሰድ እና ሌሎችንም የመምህራን ፤ የዩኒቨርሲተዎች መረጃዎች በመጨመር በትልቅ ናሙና ጥናት (Large Sample Research) አሪፍ ግብአት የሚገኝበት የምርምር ስራ ይወጣዋል ። የዚህ ምርምር ስራ ደግሞ ወደፊት ለሚደረጉ የመውጫ ፈተና አዘገጃጀቶች እና ይህን ተከትሎ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መስራት ስለሚኖርባቸው የቤት ስራ ብዙ ግብአት ይገኝበታል ።

እውቀት ነፃ ያወጣል !

ሻሎም ✌️

ለጤናህ ነኝ
ከአባይ ወንዝ ማዶ

Letenah Ejigu Wale

15 Jul, 11:59


የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአገራችን ያለው የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲስፋፋ ሴክተሩን በፋይናንስ መደገፍ የሚያስችል ስርዓት የዘረጋው የፖሊሲ ማሻሻያ አድርጎ ወደ ተግባር ከገባበት እ.አ.አ. ነሐሴ 2022 ጀምሮ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጤናው ሴክተር በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አገልግሎት ሥርዓት የሚያካትታቸው አገልግሎቶች፣

• በገበያ አዋጪ የሆኑ እጅግ ዘመናዊ (tertiary) ሆስፒታሎችን ፋይናንስ ያደርጋል፤
o የሜዲካል ቱሪዝምን የማስፋፋት አቅም የሚኖራቸው፣
o ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ፣
o አገልግሎት በሚሰጥባቸው የሕክምና ዘርፎች እጅግ ብቁ የሆኑ ጤና ባለሙያዎችን የያዙ፣
o ልዩ ሕክምና (highly specialized medical care) አገልግሎት መስጠት ላይ ትኩረት ያደረጉ፣ 

በፕሮጀክት ፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች፣

• የሚገነቡት ሆስፒታሎች በሚመለከተው የመንግሥት አካልና በባንኩ የሚጠበቅባቸውን ዝቅተኛ መመዘኛዎች ያሟሉ ሆነው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
• ሆስፒታሎች በቂ ሀብት (አቅም) ሊኖራቸው ይገባል፣
o ሦስት የሙሉ ሰዓት ሐኪሞች፣ እንዲሁም አንድ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ ፈቃድ ይዞ የሚገኝ ማለት ነው፡፡
o ሪፈራል ለመቀበል የሚያበቃ በቂ ሀብት (አቅም) ያላቸው

በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት የጤናው ሴክተር በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓት

• ልዩ ልዩ የሕክምና መስጫ መሣሪያዎች፤ 
o የሕክምና ላብራቶሪ መሣሪያዎች (laboratory equipment)፣
o የምርመራ መሣሪያዎች (diagnostic equipment)፣
o የሕክምና ንጽህና መጠበቂያ መሣሪያዎች (medical sanitation equipment) እና ሌሎች የሕክምና መሣሪያዎች ናቸው፡፡

Letenah Ejigu Wale

14 Jul, 19:45


College of Medicine and Health Sciences organizes training on Entrepreneurship to Female academic Staff.
=======================================================================
(July 14, 2023, Bahir Dar): Bahir Dar University College of Medicine and Health Sciences organized today training on entrepreneurship to female academic staff.

The training was offered by Dr. Letenah Ejigu, Assistant Professor of Accounting and Finance at Bahir Dar University.

The college organized the training to equip female academic staff members with the knowledge and skills necessary to start and run successful businesses.

Speaking during the start of the training, Almaz Mamaru, Director of Gender, HIV and Inclusive office at the college, said that the training was organized in an effort to help female academic staff have a practical understanding of what it takes to launch a business and grow it to profitability.

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website:
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t…
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences-bahir-dar-university-ethiopia/

Letenah Ejigu Wale

14 Jul, 17:21


ከላይ እንዳልኳችሁ ይህን 27 ቡና በቀን እንዴት እናምርተው የሷ የቡና መሃንዲሷ ስራ ነው ። ቡናው እንዴት ይቆላል ፤ እንዴት ይፈላል ፤ እንዴት ሰክኖ ይቀዳል የሷ ስራ ነው ። የቡናዋ ኢንጂነር ልጅ 😂 በቀን 27 ቡና ለማን ልሽጥ የማርኬቲንግ ስራ ነው ። ማርኬቲንጓም እሷው የቡና ኢንጂነሯ ናት ። እኔ እንደ አካውንቲንግ እና ፋይናንስ ባለሙያነቴ የምነግራት በቀን ዝቅተኛ ስንት ቡና ብትሸጥ አትራፊ እንደምትሆን ነው ። በቃ 27 ቡና አልኩ ።

5. ተጨማሪ ትንታኔ ፤

ትንሽ ነገር ልጨምራችሁ በቀን 27 ቡና ስትሸጥ ትርፏ ዜሮ ይመጣል ። Break Even Point ማለትም ትርፍም የለም ፤ ኪሳራም የለም ዜሮ ትርፍ ማለት ነው ። በቀን ከ27 ስኒ ቡና በላይ ከሸጠች ግን እነዚያ ተጨማሪ ቡናዎች በቀጥታ ወደ ትርፍ ይሄዳሉ ማለት ነው ። ለምሳሌ በወሩ ውስጥ በሁሉም ቀን 27 ስኒ ቡና ሸጠች እንበል ። በአጋጣሚ ግን ከወሩ በአንድ ቀን 30 ስኒ ቡና ሸጠች እንበል ። ስለዚህ በሆነች እንዷ ቀን የሸጠቻቸው ተጨማሪ ሶስት ስኒ ቡናዎች በቀጥታ ትርፏ ናቸው ። ያ ማለት ትርፏ 3 ስኒ ቡና * 5 ብር ትርፍ በአንድ ስኒ ቡና = 15 ብር ይሆናል ።

በክፍል ሁለት ነገሩን ላለማወሳሰብ የዘለልኳቸውን ፅንሰ ሃሳቦች አብራራላችኋለሁ ። ሌላ ተጨማሪ ምሳሌም እሰጣችኋለሁ ።

አካውንቲንግ እና ፋይናንስ ያማልዳል 😂

ሻሎም ✌️✌️✌️

ለጤናህ ነኝ

ከአባይ ወንዝ ዳር