Grace @amazing_grace_minister Channel on Telegram

Grace

@amazing_grace_minister


ሮሜ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ወንጌሉም ስለ ልጁ፣ በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ሆነ፣
⁴ በቅድስና መንፈስ ደግሞ ከሙታን በመነሣቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በኀይል ስለ ተገለጠው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

Grace (Amharic)

ግራሩ ከማህበረሰብ ሄዘን አዲሱ መት ጋር የሚሰራ እና ቴሌግራም ማህበረሰብ፡ ይህ ተስፋው እና መደምሰሲያዊ እንቅስቃሴን እንደማያዩ ጊዜ ደግማችሁን አመሽና እሬ አውጪ በገንቢ በሚሰራበት ቦታ ተስፋውን ቆዳለች። በእኛው የቴሌግራም ክፍሎችን ተመለከተና እናቶችን ከእርቀት ጋር በባህርይ ተመከረን። ለዚህም ማዳመቂያዎች ለማስከበር እባክዎ አስቡተው።

Grace

11 Oct, 07:21


#ሉተር ስለ #ጽድቅ የነበረው አቋም፦

• ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ብቻ ነው። (Justification by Faith)
• በእምነት የተገኘው ጽድቅ፣ ሂደታዊ ሳይሆን ቅጽበታዊ ነው።
• በእምነት የተገኘው ጽድቅ፣ በሥራ የምናሟላው አይደለም። በራሱ ሙሉ ወይም ፍጹም ነው።

Grace

06 Oct, 07:58


“እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።”
— መዝሙር 105፥4

Grace

02 Jul, 02:43


https://youtu.be/wYMlFUOYRGg?si=mlEomaOXaWqbBv7Q

Grace

18 Jun, 04:26


#መጽሐፍ ቅዱስ #ለጥቂት ሰዎች #ፍላጎትና #ጥቅም ሰባል #ተቀይሯል ሲሉ መምህሩ ተናገሩ!
=======================================
ቤተክርስቲያን እውነተኛው የእግዚአብሔርን ቃል አጥቃ አነድትይዝ አባቶችን አሳስባለሁ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/100036933507231/posts/1237735007467604/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Grace

10 Jun, 22:05


#የክርስቶስ_ደም

በብሉይ ኪዳን ሆነ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የኀጢአት ስርየት የሚደረገው #በደም ብቻ ነው። የብሉይ ኪዳን ጊዜ የኀጢአት ስርየት የሚደረገው በእንስሳት ደም ሲሆን  በአዲስ ኪዳን ጊዜ ደግሞ የኀጢአት ስርየት የሆነው የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ነው። የኀጢአት ይቅርታ የሚደረገው በደም እንጂ በጸሎት አይደለም።

በምድር ኑሮአችን ደሰ እንዳለን መኖረ አንችልም በዋጋ ስለ ተገዛን በሥጋችን እግዚአብሔርን ማክበር ይኖርብናል ምክንያቱም በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ #ደም በክቡር #የክርስቶስ ደም ስለ ተዋጀን።(1ኛ ጴጥሮስ 1፥18-19)

የተገዛንበት ዋጋ የከበረ የክርስቶስ ደም ነው። አንተ የራስህ አይደለህም የእግዚአብሔር ነህ ።የእግዚአብሔር ከሆንክ ደግሞ እንደ ቃሉ እንጂ እንደ አንተ ፍላጎት አትኖርም። የእውነት በተከፈለልን ዋጋ ልክ እንድንኖር እግዚአብሔር ጠርቶናል።

ከሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ የተወሰደ መልዕክት👇👇👇👇👇👇

የኢየሱስ ደም ከሞተ ስራ ለዘላለም ያነጻናል!

ምድር ላይ ያሉት ሁሉ ደሞች ሰማይ ሄደው እግዚአብሔርን ማርካት ያልቻሉት ከሃጢአት ጋር ስለተነካኩ ሲሆን የኢየሱስ ደም ግን የራሱ የእግዚአብሔር ደም ነው። እግዚአብሔር እራሱ የላከው ሕይወት ስለሆነ እራሱን አረካው፤ ደሙን ለማፍሰስ የታረደልን ኢየሱስ ሃጢያት የሌለበት ነው፤ የዓለምን ሃጢያት ያፀዳው ለዚህ ነው።

የማንም ሰው ደም ከተወሰደ ከ42 ቀን በኋላ ምንም ስራ የለውም ወይም  ይበላሻል። 42 ቀን ያለፈውን ደም ለሆነ ሰው ቢሰጠው የተሰጠውን ሰው ይገድለዋል። የበሽተኛ ደም ለጤነኛ አይሆንም፤ የበሽተኛ ደም ለበሽተኛም አይሆንም!

የጌታ የኢየሱስ ደም ከሌላ ደም ክቡር የሆነበት ምክንያት ከሁሉም ደም የተሻለና የበለጠ ቆሻሻ የሌለበትና ንፁህ ስለሆነ ነው። የኢየሱስ ሕይወት ንጹህና የተቀደሰ ስለሆነ የእርሱ ደም የዓለምን ሀጢያት የማስወገድ ታላቅ አቅም ስላለው ነው።

የኢየሱስ ደም ክቡር የሆነበት ምክንያት ስለሚያድን፣ ስለሚፈውስ፣ ነጻ ስለሚያወጣ፣ ከሃጢያት ስለሚያጥብና ስለማያረጅ ነው።

https://t.me/abundant_grace_church

Grace

04 May, 05:28


ሮሜ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ ለሚቈጥርልን፣ ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው በእርሱ ለምናምን ለእኛም ጭምር ነው።
²⁵ እርሱ ስለ ኀጢአታችን እንዲሞት ዐልፎ ተሰጠ፤ እኛን ጻድቅ አድርጎ ለማቅረብም ከሞት ተነሣ።

የትንሣኤው መገለጥ አማኞች ለማጽደቅ ነው፤ ትንሣኤ ኢየሱስ ከሙታን ተነስቷል ብለን የምናከብረው በአል ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በሙታን መነሳት (የትንሣኤ መገለጥ ) አማኞች የእግዚአብሔር ጽድቅ የተደረጉበት ትክክለኛ ማንነታችን ነው።

ትንሣኤ አማኞች በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሆኖ የተገለጠበት ትክክለኛ ማንነታችን ነው።

ትንሣኤ አማኞች በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተብለን የተጠራንበት ድንቅ መገለጥ ነው።

ትንሣኤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳት አማኞች ለማጽደቅ ተነሣ እንጂ ኢየሱስ ተነስቷል ብለን የምናከብረው በዓል አይደለም።

#ትንሣኤ_በየአመቱ_የሚከበር_መንፈሳዊ_በአል_አይደለም፤ #ትንሣኤ_አማኞች_የእግዚአብሔር_ጽድቅ_ሆኖ_የተገለጡበት_ድንቅ_የምስራች_ነው።

አማኞች የእግዚአብሔር ጽድቅ ናቸው ብለን ስንናገር ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት አማኞችን ለማጽደቅ ነው።

#Messager_Ephraim_Gebreyesus
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

30 Apr, 03:11


#እግዚአብሔር_ልጆች

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ የሚለው የሐዋርያው ዮሐንስ አባባል በግሪኩ ቋንቋ የተገለጠበት ሐረግ ማነጻጸሪያ በሌለው ባልተለመደ ዓይነት ፍቅር እንደወደደን የሚገልጽ ነው።

የእግዚአብሔር ፍቅር በእግዚአብሔር አባትነት፤ የእግዚአብሔር አባትነት በእግዚአብሔር ፍቅር መጠን እንዲገለጡ እርስ በራሳቸው በእጅጉ የተሳሰሩ ናቸው።

የእግዚአብሔር ፍቅር ጥልቀት ኃጢአተኛ፣ ደካማና ጠላቶች የነበርነውን እኛን ዳግም ለመዋጀት በማይመጠነው መልካምነቱ ልጁን ስለ እኛ በመስጠቱ የተገለጠ ነው። እግዚአብሔር ከአምላካችን ባሻገር አባታችንም ነው! (ሮሜ 5፥6)

ሬቨረድ. ተዘራ ያሬድ


Join and subscribers👇👇👇👇
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

17 Apr, 01:40


#በሰራነው_ሳይሆን_ክርስቶስ_በሰራው
===============================

✍️በአንዱ አዳም አለመታዘዘ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ (በኢየሱስ) መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ፡፡ (ሮሜ 5፥ 19)

✍️ኃጢአተኞች የተባልነው እኛ በሰራነው ሳይሆን አዳም በሰራው እንደ ሆነ ጻድቃን የተባልነውም እኛ በምሰራው ሳይሆን በክርስቶስ ሥራ ነው፡፡

✍️ስራችን ኀጢአተኞች ካላደረገን ስራችን ጻድቃን ሊያደርገን አይችልም፡፡ ስለዚህ በአንዱ አዳም ሃጢያተኞች ሆነናል ብለን ለመናገር ካላፈርን በአንዱ በክርስቶስ ጻድቅ ነን ማለት እውነት እንጅ ከንቱ ድፍረት አይደለም ፡፡ (ሮሜ 5፡12-21)

📌 በክርስቶስ ላላችሁ ጸጋና ምህረት ይብዛላችሁ።

የወንጌል እውነት

Join and subscribers👇👇👇👇
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

12 Apr, 15:23


በዚህ የመዝሙር ግብዣዬ ትነካላቹ
የተባረኩበት የፀሎት መዝሙር ግብዣ
#ፀጋ ይብዛልኝ
👇👇👇👇
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

09 Apr, 04:12


#ተከፍሏል_ነቢይ_እዩ_ጩፋ_Shorts_(720p).mp4

ሙሉ ስብከቱ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው ሊንክ መሠረት ተጭናችሁ እንድትሰሙ እጠይቃለሁ።

ስብከት ርዕስ፦ ተከፍሏል.mp4
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

07 Apr, 15:19


ስለ 3ኛው የአለም ጦርነት የተነገረ ትንቢት... - Christian Promotion - CP
https://www.facebook.com/GospelMusicEthiopia/photos/a.1335101486618309/4729852057143218/?type=3

Grace

01 Apr, 02:15


“እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 2፥4-5
"አገልጋይ ነኝ።" ባይ ግን በሰዎች ዘንድ ለመወደድ ሲባል ዋጋ ሌለው ውሸት ዋጋ የሚተምን እውነትን ግን የሚሰውር፤ብሎም ለግል ጥቅም የሚያሸረግድ የጌታ አገልጋይ ሊሆን አይችልም።
“ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።”
— ገላትያ 1፥10

የዚህ መልዕክት የጸሐፊ Milka Yonatan

Join and subscribers👇👇👇👇
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

24 Mar, 05:30


በወንድም ዳዊት ፋሲል

በማቴዎስ ወንጌል ም.25 ላይ በተመለከተ የሰጠው ማብራሪያ ይመልከቱ።

Join in the group👇👇👇👇👇
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

23 Mar, 22:41


Salvation/መዳን/
ክፍል አንድ

መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ

“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሐዋ. 4፡12)

ከላይ ያለው መልዕክት ስለ መዳን የተነገረን አንድ እውነት አለ፤ መዳን የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው።

✍️ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤” የሚለው ቃል መዳን በሰው ሆነ በመላዕክት ዘንድ ሊገኝ የማይችል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ የምትቀበለው የዘላለም ድነት ነው።

✍️ “እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” የሚለው ቃል ድነት የተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝው የዘላለም ህይወት ሰዎች ሁሉ አምኖ እንዲድኑ የተሰጠ ስም ሲሆን ከዚህ ስም ውጭ ሌላ የመዳን መንገድ እንደሌለ አስረግጦ ይናገራል።

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያዘጋጀው ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘላለም ህይወት እንዲቀበሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።

“ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
  — ዮሐንስ 14፥6 (አዲሱ መ.ት)





ኢየሱስ ያድናል! 


📖📖📖ይቀጥላል📖📖📖

Join in the group👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

21 Mar, 21:34


ንቧ🐝 ና ሲሳይ ተፋጠጡ😄
#የልፍለፍ ፕሮግራም
#ለታዳጊዎች ና #ለወጣቶች
#ምክር
#አስቂኝ ና ቁም ነገር
ከሲሳይ አዙዛ ጋ
@SisayAzusaRevivall

Grace

15 Mar, 20:43


የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ የሚለው የሐዋርያው ዮሐንስ አባባል በግሪኩ ቋንቋ የተገለጠበት ሐረግ ማነጻጸሪያ በሌለው ባልተለመደ ዓይነት ፍቅር እንደወደደን የሚገልጽ ነው።

የእግዚአብሔር ፍቅር በእግዚአብሔር አባትነት፤ የእግዚአብሔር አባትነት በእግዚአብሔር ፍቅር መጠን እንዲገለጡ እርስ በራሳቸው በእጅጉ የተሳሰሩ ናቸው።

የእግዚአብሔር ፍቅር ጥልቀት ኃጢአተኛ፣ ደካማና ጠላቶች የነበርነውን እኛን ዳግም ለመዋጀት በማይመጠነው መልካምነቱ ልጁን ስለ እኛ በመስጠቱ የተገለጠ ነው። እግዚአብሔር ከአምላካችን ባሻገር አባታችንም ነው! (ሮሜ 5፥6)

📌 የእግዚአብሔርን ፍቅር መረዳት ከሚለው አዲስ መጽሐፍ የተወሰደ!

ሬቨረድ. ተዘራ ያሬድ
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

02 Mar, 04:43


ኤፌሶን 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
¹⁰ እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

ወዳጄህ በኢየሱስ ክርስቶስ ተሰርቶ ያለቀው የመስቀል ስራ በጸጋው እምነት መቀበል ስለቻለን ሀይማኖት አያስፈልግም። ሀይማኖት በመስቀል ላይ የተሰራው ስራ ሳይሆን በአንተ ጥረት እና ትግል እንድትኖር የሚያድርግ ከባድ ቀንበር ነው።

ሀይማኖትን መከተል ትተህ የሕይወት ቃል ያለው ኢየሱስ ብትመርጥ ይሻላል።
ኢየሱስ ያሳርፋል እንጂ እንደ ሀይማኖት ስርአት ሸክም አትሆንም።

ኢየሱስ በጸጋው አካል ስለሆነ ያሳርፋል እንጂ በሀይማኖት ቀንበር ስር አይቀመጥም።
https://t.me/abundant_grace_church

Grace

24 Feb, 04:19


#አማራጭ_የሌለው_ምርጫ_ኢየሱስ_ብቻ_ነው_ይሄን_ድንቅ_መልዕክት_ላልሰሙ_አሰሙልኝ_የመዳን_ቀን_ዛሬ_ነው።

Join and subscribers👇👇👇👇
https://t.me/abundant_grace_church