ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]• @ktebiban_meder Channel on Telegram

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

@ktebiban_meder


°| ✍ከአፍቃሪያን ገጽ በፍቅር ቀለም |°

•[ ከጠቢባን ምድር! ]•
🌴 دار الحكمآء

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]• (Amharic)

በአፍቃሪያን ገጽ ላይ በፍቅር ቀለም እየጠቢባነት ያለ አዝናኝ ምድር ከጠቢባን ምድር ሆነን ለራስ አብዱ ሩሚ ትንሽ ለመሆን የሚችል ተግባር። የራስ አብዱ ትንሽ በሆነው በዓለም ላይ ብቃት እንዲሆን አፈር ብሎአል። እስኪ መግባት ስሚዎችም ለምስል ካደንም በላይ አይዘወት እያጠቡ ስልኩ በሞኝ ምድር እንቆማለን። ከጠቢባን ምድር ከቤቶቻችን እንጠቀማለን።

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

07 Jan, 18:48


መቼስ..
ደቂቁ እኔ
ከእጥፋቴ ባልቀና
ጥፋቴ ለቃል ቢጠና
ውስጠቴ ቢሆንም ኦና ፡
መተስፈይ አልተው
መማፀን አልተው
ጌታዬ  አንተ ነህና ፡

እኔ እኔ ነኝ
እልፍ መሰበር ያላደከመኝ
አንተ አንተ ነህ
በሰፊ እዝነትህ
ውድህ አድርገኝ
እኔን ከነፍሴ ገላግለኝ፤

እንደ ነጭ እርግብ ክንፌን ላማታ
ከእኔነቴ ላ'ንተ ልፋታ ፡
ይሰማኝ ስጠራህ እፎይታ
ስማልኝ የነፍሴን ዋይታ ፡

•[ አብዱ ሩሚ ]•

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

07 Jan, 18:34


ልቤ ባ'ንቱ ፡ ከኔ ሸሸ ❤️‍🔥

አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ!❤️‍🔥

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

06 Jan, 20:38


https://vm.tiktok.com/ZMrunAVYv/
#Follow

@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

05 Jan, 10:18


አንድ አሊም ተጠየቁ አንድ ሰው ተውበት ሲያደርግ ተውበቱ ተቀባይነት ያግኝ አያግኝ ይታወቃልን?
" ይህ እንኳን በእርግጠኝነት ሚታወቅ ነገር አይደለም። ነገር ግን ምልክቶች አሉት። ተውበቱ ተቀባይነት ሲኖረው ነፍሱ ከሰራው ሀጥያት መላቀቁ፣ ደጋጎችን መቀማመጡና ከመጥፎ ሰዎች መነጠሉ አንዱ ምልክት ነው። ለዱንያ ሚሰራት ትንሽ ስራ ስትበዛበት። ለአኼራ ሚሰራው ብዙ ስራው ሲያንስበት። ቀልቡ አላህ በደነገጋቸው ነገራቶች ላይ ሲተሳሰር። ሰዐቲቱን ከሚጠባበቁት ሲሆን። ሁሌም በሰራው ጥፋት ሲብሰለሰልና ፀፀት ሲሰማው ቅቡልነቱን ማወቅ ይቻለናል። "  በማለት መለሱ...!
:
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

05 Jan, 10:14


" ሰላትህ እንዴት ነበር?"

• "በምንም አይነት ሁኔታ ላይ ብሆን ፡ በቀን አምስት ጊዜ የልቤን የማወያየው ማንም እንደማሌለኝ ተገነዘብኩ፡
ባዝን፣ ብሰበር ፣ ብደክም፣ ብታመምም...ከአዛኙ እጅግ በጣም አዛኝ ከሆነው አሏህ በስተቀር። "•

#አሏህ
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

01 Jan, 17:24


አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ!
😭

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

31 Dec, 21:30


ያ አላህ❤️‍🩹

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

31 Dec, 20:47


ታላቁ ዓሊምና የአላህ ወዳጅ ሰዪዲ ሸይኽ ዐብዱል ቃድር አል ጀይላኒይ(قدس سره)በመጀመሪያው የረጀብ ወር ሌሊት ይህንን ዱዓ እንድናደርግ በእውቁ "አል ጙንያህ"ኪታባቸው ውስጥ ጠቅሰዋል፤ዱዓውን ከነ ትርጉሙ አስቀምጨዋለው:–
إِلهِي : تَعَرَّضَ لَكَ فِي هذه اللَّيْلِة المُتَعَرِّضُونَ ،وَقَصَدَكَ القاصِدُونَ ،وَأَمَّلَ فَضْلَكَ وَمَعْرُوفَكَ الطَّالِبُونَ ؛وَلَكَ فِي هذه اللَّيْلِة نَفَحاتٌ وَجَوائِزُ ،وَعَطايا وَمَواهِبُ ،تَمُنُّ بِها عَلى مَنْ تَشاءُ مِنْ عِبادِكَ ،وَتَمْنَعُها مِمَّنْ لَمْ تَسْبِقْ لَهُ العِنايَةُ مِنْكَ، وَها أَنا ذا عّبدُكَ الفَقِيرُ إِلَيْكَ، المُؤَمِّلُ فَضْلَكَ وَمَعْرُوفَكَ؛ فَإِنْ كُنْتَ يا مَوْلاي تَفَضَّلْتَ فِي هذِهِ اللَّيْلَةِ عَلى أَحَدٍ مِنْ خَلْقِكَ ،وَجُدْتَ عَلَيْهِ بِعائِدَةٍ مِنْ عَطْفِكَ ،فَصَلِّ عَلى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ وآلِهِ وَصَحبِهِ، وَجُدْ عَلَيَّ بِطَوْلِكَ وَمَعْرُوفِكَ، يا رَبَّ العالَمينَ .
አላህ ሆይ! በዚህች ሌሊት ቀራቢዎች ወዳንተ ቀረቡ፣አሳቢዎችም አሰቡህ፣ፈላጊዎች ትሩፋትና መልካምህን ተስፋ አረጉ፣በዚህች ሌሊት ውስጥ እድያዎችና ሽልማቶች፣ልገሳዎችና ስጦታዎች አሉህ፤በነሱም ከባሪያዎችህ የፈለግከውን ባሪያ ትመነዳለህ፤ካንተ የሆነች እገዛ ካያልቀደመችለትም ሰው ትከለክላለህ፤ይሄው እኔ ወዳንተ ፈላጊ፣ችሮታህንና መልካምህን ከጃይ ባርያህ!
ረዳቴ ሆይ! በዚህች ሌሊት በአንዳች ፍጡርህ ላይ ችሮታህን ለግሰህ፣በእዝነትህ ውለታን ውለህ ከሆነ፣አንተ የአለማት ጌታ ሆይ  በሰዪዳችን በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ እዝነትህን አውርድ፤ከፀጋህና ከመልካምህ ለኔም ለግሰኝ"
_
© t.me/hamidabuhamid

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

30 Dec, 17:43


የሰዎች ልብ ውስጥ በይበልጥ የገዘፈው ነገር "ጌታ" ለመኾን የቀረበ ነው። ሰዎች ራሳቸውን ለማወቅ ካልታገሉ። የፈለገ ቢማሩ፣ የፈለገ ሐይማኖተኛ ቢኾኑ አንደበታቸውና ገጽታቸው እነርሱን አይገልጽም። ሰዎች በሌሎች ዘንድ የሚፈልጉትን የቅቡልነት ፍላጎት፣ ሌሎችን የመቆጣጠር ስሜት፣ ሁሉንም ነገር ይገባኛል የሚል ነፍሲያ ሐቅ ላይ እንዳሉ በማሳየት ይጋርድባቸዋል። ይህ በነፍሲያ የመታለል አባዜ አላህንም ጭምር መርሳትን ያለማምዳቸዋል።

ሰዎች መስጂዶችን ሞልተው፣ ልዩ አልባሳትን ለብሰው አሸብርቀውና ደምቀው መላእክት መስለው ሲታዩ በክፋት በኩል የሚያልፉም አይመስሉም። ግና ከነጫጭ ጀለቢያዎች ጀርባ ያለውን ሰውን የመጥላት፣ ሰው ላይ የማሴርን፣ ሰው ላይ የመመቅኘትን ወኔ ማን ይኾን ያለበሳቸው?!

ሸይጣን???

መስጂድ ገብተው፣ ሰግደው፣ አንዳንዴም ጾምው፣ ከዚህም አልፎ ዑምራና ሐጅ ተመላልሰው?!

ሸይጣን አይደለም ያስቸገረን በዋናነት ያስቸገረን የገዛ ነፍሲያችን ነው። የአምልኮ ግብ ሳይገባን መስጂዶችን አጨናነቅን፣ በሰለዋትና ዚክር የሚለዝበውን ማንነታችንን በሚድያ ዲን ቀየርን። ለልባችን የሚጠቅሙ ሙረቢዎችን (መምህራንን) ኋላ ቀር ብለን የሚያብረቀርቁ የቲክቶክና የሚድያ ሸይኾችን ተከተልን። ውጪያችን የሚያበራ ውስጣችን የጨለመ ማንነት ወረስን።

ፖለቲከኞች እየተቀደሱ መንፈሳዊ ግለሰቦችን በንቀት ከቦታቸው በውርደት እንዲገፈተሩ ተደረገ። በፍጥነትም የገፈቱ ቀማሽ ኾንን ዛሬ መንፈሳዊነት ርቆናል፣ ኪታብ ብንሰበስብ፣ ዕውቀት ብናከማች ኢጃዛ (ፈቃድ) ከሌለ ዘውቁ ከየት ይመጣል። ዛሬም አልረፈደም በመረጃ ብዛት ያከማቸነው ሐይማኖት በሕይወታችን ውስጥ እንዲሰራ ከፈለግን ለልብ የሚኾነንን ዑለማ እንፈልግ። ፊታችንን ወደ ሰለዋት፣ ዱዓ እና ዚክር እንመልስ። ከልባችን ውስጥ ከገቡ ጣኦቶች ንሰሐ እንግባ።

አላህ ያስረዳን

© Best Kerim🩵

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

29 Dec, 17:17


ወሃብ ኢብኑ ሙነቢህ እንዲህ ብለዋል፡- “ከንባቦቼ መረዳት እንደቻልኩ የሰው ልጅ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው እውቀት ሁሉ በአንድ ሆኖ ቢሰበሰብ ከነብዩ ﷺ እውቀት ጋር ሲወዳደር እንደ ነጠላ የአሸዋ ቅንጣት ብቻ ቢሆን ነው። "
(አሽ-ሺፋ)

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

29 Dec, 17:15


ቃል አያክመው የልቤን ህመም
አብሽር አያሽረው
ረግፏልና የነፍሴ ለምለም፡
እምቡጧ ሩሄ ጠውልጋ
ንጋቷ ከስሞ
ድቅድቅ አለም ውስጥ መሽጋ ፡
ተላምዳ ከፅልሙ አለም
ወድቃለች
ጠፍታለች
ጭላንጭል ብርሀኗ የለም ፡

ማንም መሆኗን እስክታውቅ
ምንምነቷ እስኪገባት
መንገድ ለጠፋት ብክነት ለበዛት ፡
ድኩሟ ነፍሴን
አንተው ወዳንተ አድርሳት፤

ኸልቅ ሲዘክር
ወዱድ እያለ ሲከርር ፡
..
ሌላው ጋር ብርሀን ወግጎ
እኔ ጋር ፅልመት ሲወጣ ፡
ከወደቅኩበት ዝቅታ
ምርኩዜ ሁነኝ ልወጣ ፡

መቼስ..
ደቂቁ እኔ
ከእጥፋቴ ባልቀና
ጥፋቴ ለቃል ቢጠና
ውስጠቴ ቢሆንም ኦና ፡
መተስፈይ አልተው
መማፀን አልተው
ጌታዬ አንተ ነህና ፡

እኔ እኔ ነኝ
እልፍ መሰበር ያላደከመኝ
አንተ አንተ ነህ
በሰፊ እዝነትህ
ውድህ አድርገኝ
እኔን ከነፍሴ ገላግለኝ፤

እንደ ነጭ እርግብ ክንፌን ላማታ
ከእኔነቴ ላ'ንተ ልፋታ ፡
ይሰማኝ ስጠራህ እፎይታ
ስማልኝ የነፍሴን ዋይታ ፡

ላግኝህና መኖር ልጀምር
ቅፅበት ዘመኔን
ልኑር ስምህን ስዘምር።
_
•[ አብዱ ሩሚ ]•

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

28 Dec, 19:40


ጌታህ እነዛ ፡ ደጃቸውን ጠንተህ ከሚመልሱህ ሰዎች በላይ ቸር ነው። ደጁን አጥበቀህ ያዝ።

' የሰው ልጅ ስትጠይቀው ይቆጣል። ከሪሙ ግን ካልጠየቅከው ይቆጣብሀል። '
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

28 Dec, 04:46


| ልጄ ሆይ ~3 |

< የተከዳ ልብህ። ሰዎች እንደ ድልድይ አድርገው የተረጋገጡበትን ፣ በየዋህነትህ ለዕባብ ስትቀልበው የነበረን ደግነትህ አትጥላው። አንዳንድ ትምህርቶች መራር ናቸው። ልክ እንደ መድሀኒት! ካላዋቂነት በሽታ ይፈውሱሀል ፡ ሁሉም ያንተ ልብ የተገባው አይደለም። ለራስህ አዝነህ ሰው ምረጥላት። በጨላለመ ጊዜ ክንዶቿን አጥበቀው ሚዩዙ! በሰላሙ ወቅትም እቅፋቸው ሚሞቅ። ከነውር የፀዳን ሰው ፈልግ እያልኩህ አይደለም። ሰው ነንና ጉድለት መገለጫችን ነው። ግን ደግሞ ከአድከሚው ክህደትና ራስወዳድነት ልብህን ጠብቃት። >

ውብ ማለዳ❤️‍🔥
. . .
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

27 Dec, 05:46


ጁምዓኩም ሙባረክ🖤

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

26 Dec, 17:03


አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐለይህ💚

@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

26 Dec, 15:19


በዱዓችሁማ😊
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

23 Dec, 20:58


ሰላም ይድረሶት ሰላሜዋ❤️‍🔥

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

23 Dec, 19:11


አላህ❤️‍🔥 አላህ ❤️‍🔥

አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ! 🩵
ከሶለዋት አንገፍልማ!
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

22 Dec, 14:03


مناجاة آخر اليل ❤️‍🩹

#الإمام_عبد_القادر_الجيلاني
قدس الله سره 🤍
_ ሙናጃ!❤️‍🩹 የሩህ ሰላም! _
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

22 Dec, 13:55


ስክነትን ስሻ
መርጋትን ስሻ
መሸሻዬ ነው እርሱ
መጠግያዬ ነው ከትርምሱ፡
አዋጅ ለልቤ..
ሞገድ ማይንጠው ፅናትን ከሻህ
እርሱን አድርገው ሁሌም መሸሻህ፤
እርሱን ፈልጎ ፡ወደርሱ የሸሸ
ሀሉ ሰመረ እንጂ፡ መቼ ተኮላሸ?
እርሱን የከጀለ ለፍቅሩ የዋለ
መች ባ'ዘን ዋለለ?
:
ልሳኑን አቃንቶ ስሙን እየጠራ
ያደፈን ልቦናው በዚክሩ ሊያጠራ፤
የጨለመ ሩሁን
የታበየች ነፍሱን በፍቅሩ ሊገራ
የተቀማመጠ ከሙኽታሮች ጋራ፤
ራህመትህን እያለ
ራህመት የከጀለ፡
መች አፍሮ ከሰረ? መቼ ተሰበረ?
.
እጁ ሲተሳሰር ሲለው አልዘረጋ
ቃላት ሲሰወረው ልሳኑ ሲዘጋ፡
በእምባ እንክብሎቹ
የልቡን ሲያወጋ፡ መሽቶ ሚያነጋ
መች ተከፍቶ አየህ
መች ውድቀቱን አየህ እርሱን የተጠጋ!
:
[ አብዱ ሩሚ! .... 08/04/2015 ]
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

21 Dec, 10:48


ልጄ ሆይ ~2

[ አብዱ_ሩሚ ]

<  ልጄ ሆይ በጌታህ ቻይነት አትዘናጋ። በዝንግታህ ላይ ሆነህ የቀብር ልብስህን ልታጠልቅ ትችላለህና። ልጄ ሆይ! የጌታህ ቅጣት አሳማሚና ከሁሉ ሚልቅ ነው። ልብህን እንዲህ ካደነደነብህ ወንጀል መች ትታቀባለህ? መመለሻህን የሚጠባበቅ አዛኝ ጌታ ነው ያለህና ፡ ና ወደ ደጁ።
. . .
የኔ ልጅ በማዕሸር ዕለት ሰው ሁሉ የሚሸበረው ወንጀሉን አይቶ ሳይሆን የወነጀለውን ፈጣሪ ታላቅነት አይቶ ነው። የወንጀልህን ትንሽነት ሳይሆን ማንን እንደወነጀልክ አስተውል። በዚህ መልኩ ከጥፋቶች ሁሉ ልብህን ለማቀብ ጣር።
. . .
በሰላትና በጎ ነገር ላይ የምትታትረዋ ፡ ለለይል ሰላት ማትሰንፈዋ ነፍስህ የትኛው ወንጀል እንዲህ አጠወለጋት. . ? ምናልባትም 'ትናንሽ' ፡ ብለህ የናቅካቸው ይሁኑ?...
ትንሹ ወንጀልህ ፡ ልብህ ላይ ምን ያህል ተፅኖ አለው?
ትልቁ ጥፋትህ ፡  በምን ያህል እምባህ አበስከው? ነው ወይስ እምባን ተነፍገሀል? ከተነፈግክ ስለ ተነፈግከው ፀጋ ተዋደቅ። እምባን ጠይቀው! ዘለላ እምባ. .ስለ እርሱ የምትፈስ ዕንቁን >

@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

21 Dec, 10:41


ልጄ ሆይ~1

[  አብዱ_ሩሚ ]

< በዚህች ምናባዊ አለም ላይ ያለን ቁስ ፈላጊ  በቁጥር አይገደብም። በውስጧ ያሉ መጋጌጫዎች ፣ ሀብትን ዝናን ፣ ድሎትና ምቿቷን ሽቶ ነፍሱን ሊመፀውት የተዘጋጀ አንድ ተብሎ አይዘለቅም። ከመሻቷ ተናጥቦ ስለ ዘልዓለማዊው አለም ፡ ስለ ሲራጥ ፣ ስለ ሂሳብ ፣ ስለ በርዘኹ አለምና ስለማዕሸር የሚጨነቅና ስለርሱ የሚለፋ ደግሞ እጅግ አናሳ ነው። ብዙኋኑ በስካር ላይ ያሉና ነፍሶቻቸው መርጋት ተስኗት የምትንገዳገድ ናት። ከኚህ አኼራዊ ሰዎች ፣ በዘመናቸው እንግዳ ከሆኑ ሰዎች በስተቀር። 
በዚህች አለም ላይ ከዱንያውም ይሁን አኼራዊ ጉዳዩች አስበልጠው አላህን(አዘ ወጀል) የሚሹና ውዴታውን የሚከጅሉ ፣ ከጥቂትም ያነሱ ጥቂት ሆነው ታገኛቸዋለህ።

ምንኖርባት ምድር አንድ ናት። አኗኗራችንና በልባችን ላይ ያለው ፍፁማዊ መሻት ግን የኑሮዋችንን መልክ ይወስናል። ታድያ የኔ ልጅ. .
የኑሮህ ቀለም በጥቁረት የተላወሰ ነው ወይስ በብርሀን የተሽቆጠቆጠ? >

@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

20 Dec, 11:23


አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ🖤😊

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

19 Dec, 19:17


@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

17 Dec, 18:16


ተጓዝ . . . እግሮችህ አፈሩን ይዳብሱ
ተራመድ. . .ተመልከት ባህርና የብሱ'ን
አድማሱን . . .ፅጌውን
ጥኡም ዜማን ከአዕዋፋቱ የሚቀዳን ፡
ስሱን ንፋስ . . የማለዳን ፣

ሁሉን ቃኘው. . ሁሉን እየው ፣
መረዳት ስትጀምር ፡ የርሱን ታላቅነት ፣
ይገለጥልሃል. .
የአንተነትህ ፡  ትንሽነት ፤

| Abdu Rumi  |

@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

17 Dec, 17:40


°

የልብ ጉዞ ለማድረግ ሂማ ያስፈልጋል። ከገፍላው ተነሳሽነት እንዲኖር የሚያደርገው አላህ (ሱወ) በልብ ላይ የጣለው ቀስቃሽ ስሜት ነው። ይህ አንቂ ስሜት
"ባዒስ" ይሰኛል።

ለአንድ የሰርግ ድግስ የጥሪ ወረቀት የደረሰው ሰው በቀጠሮ ሰዐት ለመሄድ ይነሳል። ድግሱን ይታደማል።
ያን ድግስ እንዲታደም ተነሳሽነት እንዲኖረው ያደረገው የጥሪዋ ወረቀት ናት።

የጥሪዋ ወረቀት እንደ "ባዒስ" ናት ጥሪው ከደረሰን ቡኋላ ለመሄድ የሚኖረን ተነሳሽነትና ለመጓዝ መሰናዳታችን ደግሞ ሂማችን ነው።

ለልብ ጉዞ ስንሰናዳ ሂማ እንዲኖረን ይህ "ባዒስ" እጅግ ያስፈልገናል።  የተነሳሽነትና የመልካም ጉጉት ስሜታችን እንዲያብብ የሚያደርገንን  " ባዒስ " በሶስት አይነት መልኩ ልናገኘው እንደምንችል አሊሞች ይናገራሉ።

አንደኛው በ #ተርሂብ ሲሆን የአላህን ቅጣት ፈርተን ካለንበት ጥፋት እንድንታቀብና በኢባዳ ላይ እንድንቻኮል ያደርገናል።

እንደ ምሳሌ አንድ ሰራተኛ በቢሮ ውስጥ በተደጋጋሚ እያረፈደ በመምጣቱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውና " ነገ ካረፈድክ ከስራ ትባረራለህ" ቢባል። ንጋት ላይ ማልዶ ቢነሳና ነፍሱ እንቅልፍ ቢያምራት እሺታውን ይቸራታል? የነፍሱን ፍላጎት ከተከተለ የሚደርስበትን ቅጣት ያውቀዋልና ነፍስያውን ተቃርኖ ከቅጣት ይድናል።

ሌላኛው መንገድ ደግሞ #ተርጊብ ይሰኛል። አላሁ (ሱወ) ለአማኞች ያዘጋጀውን ምንዳን ስናደምጥ። የጀነት ውስጥ ፀጋ. . ወንዞቹ ፣ ፍራፍሬዎቹ ፣ ሁረል ዐይኖቹ . . .የተለየዩ የማይከስሙ የአኼራ ፀጋዎችን ስናስተውል ለኢባዳ ሂማ እንዲኖረን የሚያደርገንን ባዒስ እናገኘዋለን።

ምሳሌ . . .አባት ለልጁ ይህን አመት አንደኛ ከወጣህ ብስክሌት እገዛልሀለሁ ቢለው ያ ልጅ ማጥናት ሲሰለቸው ወይም ጫወታ ሲያምረው ከጥናቱ ጀርባ የሚያገኘውን ስጦታ እያየ በነፍሱ ሳይሸነገል ሽልማቱን ለማግኘት ይጥራል።

አላህ (ሱወ) ዘንድ ስላለው ዘውታሪ ኒዕማ መስማትና ማሰብ በኢባዳችን እንዳንሰናፋና በነፍስያ መዳፍ እንዳንጨፈለቅ የሚያደርገንን ሂማ እንዲኖረን ይረዳናል።

ሶስተኛው. . . #ሸውቅ ነው። አላህን ሱወ መናፈቅ . . ማፍቀር። የዋለልንን ፀጋ በማስተንተን ፣ ፍጥረተ ዐለሙን በማጤን ፣ በተለያዩ የቁርዐን አያዎችና አሀዲሶች ውስጥ የርሱን ፍቅር መፈለግ።
የራስን ብዙ ጥፋት . . .የርሱን ሰፊ እዝነት ማሰብ።

በአንድ ጦርነት ላይ አንዲት እናት ከልጇ ጋር ትጠፋፋለች። በትርምሱ መሀል ያገኘችውን ህፃን እቅፍ አድርጋ ከደረቷ እያስጠጋች ልጇ መሆኑን ታረጋግጣለች። ካልሆነ አስቀምጣው ፍለጋዋን ትቀጥላለች። በዚህ መሀል ልጅና እናት ይገጣጠማሉ። እናት ተንሰፍስፋ ልጇን እቅፏ ውስጥ ሸሸገችው።
ይህንን ትዕይንት እየተመለከቱ የነበሩ ሰሀባዎች ልባቸው ተነክቶ አለቀሱ።
በዚህ መሀል ረሱላችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ምን እንደሚያስለቅሳቸው ሲጠይቋቸው የልጅዬውና የእናቱ ሁነት እንደሆነ ይናገራሉ።
ረሱላንችንም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም " ይህች ሴት ልጇን እሳት ውስጥ ትጥላለች ብላችሁ ታስባላችሁን? " ብለው ጠየቋቸው።  በፍፁም  አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሲሉ መለሱ።
ረሱለሏህም " አላህ ይህች ሴት ለልጇ ከምታዝነው በላይ ለእናንተ አዛኝ ነው። " ሲሉ ተናገሩ።

ይህን አዛኝ ጌታ አዛኝነቱን ማወቅ። ችሮታውን ፣ ፍቅሩን ፣ መሀሪነቱን ፣ ሰታሪነቱን ፣ ገፋርነቱን ፣ ይቅር ባይነቱ ከልብ ማሰብ ወደ አላህ ለምናደርገው ጉዞ ሂማ እንዲኖረን የሚያደርገውን " ባዒስ"ን ይቀሰቅሳል።

ሳሊሆችን መቀመጥም ለኸያራት ሂማ እንዲኖረን ያደርገናል። ከቀደምት ሳሊሆች
" ሙሀመድ ኢብኑ ዋሲዕን ስመለከት ለወር ያህል ኢባዳ እንድሰራ በሚያስችለኝ ሂማ እሞላለሁ። " የሚል ነበር።


እንደው ስናጠቃልለው . . .
በማዕሲያ የተጠመዱ ሰዎች የሚደርስባቸውን ቅጣት በማስታወስ አልያም ለሙተቆች የተዘጋጀውን መስተንግዶን ስናደምጥ ወይም አላህን ሱወ ስንናፍቅና ከደጋጎች ጋር ስንቀማመጥ ለልብ ጉዞ የሚሆነንን ሂማ እናገኛለን።
____
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

17 Dec, 10:34


| የነፍሳችን ነፍሶች! |
ረሂመሁላህ💔

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

28 Nov, 20:02


ብኩኗ ነፍሴ . . .
ለአንዲት ቅፅበት ፡
ለአንዲት አፍታ ፡
እዚህ ስፍራ ላይ ፡ መሆን ምኞቷ ፡
ያኔ. . .
ይገታል ፡ እልፍ መሻቷ! -

አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ❤️‍🩹
ሀቢቤዋ🥺!

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

28 Nov, 18:43


|  ሩሄ ወዳንቱ ትከንፋለች🕊    |

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

27 Nov, 18:15


| ሀቢቢ ያ ረሱለላህ!💚 |

አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ!💜
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

27 Nov, 17:08


ዝምታ. . !
:
ክርታሴ ላይ ቀለም አኖርኩ ፡
ሞነጫጨርኩ ፡
ከእምባዬ መድ እየነከርኩ ፤

ገለባዬ ከኔ በላይ ሚዛን ደፋ
ብናኝ ሆንኩኝ እፍፍ ቢሉኝ የምገፋ ፤

ቃል ቀለሙ ተደማምሮ
አልገልፅ አለኝ የሀዘኔን እንጉርጉሮ ፤
.
ከዛም. . .በዝግታ
ዘለቅኩኝ ወደ ዝምታ

ዝምታ ውስጥ ተኳለ አይኔ፡
ደማመቀ የሩህ ከውኔ

በቃል ሠጠር
ስለ ልቤ ፡ ላስስ ስጥር
( ገባኝ ዛሬ . . .)
ከቃል በላይ
ዝምታ ውስጥ
አለ ሰላም ፡ አለ ሚስጥር !
_
•[ አብዱ ሩሚ ]•
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

27 Nov, 15:06


• - ኪምያን - እንደ አላህ ፍቃድ ጊዜ ካገኘሁ ሰኞ ምንቀጥለው ይመስለኛል። ትንሽ ሀጃዎቼ ተደራርበው ነውና በዱዓችሁ! •

[ ወሰላም! ]

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

27 Nov, 04:10


| የምትወደው ነገር ሁሉ የማንነትህ ትንሹ ነፀብራቅ ነው። |

ጀላሉዲን አል-ሩሚይ💜

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

25 Nov, 08:24


| ከመሞትህ በፊት ፡ ሙት! |

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

23 Nov, 16:05


| ትርምስ ነው. . .
ግርግር ነው. . .
ፍጥረታቱ በምድር ገፅ ይራወጣል ፡
. . . ይባዝነል
ደጋግሞ ያዝናል ፡
ደግሞ ይስቃል ፡ ይፈግጋል
ስትወጣለት ትንሽ ብስራት ፡
ይዘነጋል ሺህ ስብራት !

ለመላመድ. . .
ለመዛመድ ከነፍሱ ጋር ፡
ልቡ ጠፍቶት . .
የልብ አጋር ፡
አይኑን ሰዶ ፡ ከወደ ሩቅ
ያማትራል . .
እምባ ይዘራል ፡

' ወዳጅ ' አንተ
' አካሚ ' አንተ. . .


ለዚች ልቡ ሁን ብስራት ፡
በ'አንተ' ፍቅር ፡ ነፍሱን ስራት ፣
ወዳጅ ሁናት ፡
ሰርክ ሀሴት ፡
፡ ሁሌም ደስታ
ማይደፈርስ ጥልቅ እርጋታ
የማይከስም አደይ ፌሽታ ፤

ላንዴ ይቸር ፡
እልፍ ታሟል ፡
እልፍ አምብቷል ፡
ዛሬ ይንጋለት ፡
ላንዴ ይዘንጋ ፡ ሺ ብሶቱን
ካ' ንተ ይመገብ ፡
የመሀባን ወይን እሸቱን ፡     |

[ አብዱ ሩሚ ]
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

22 Nov, 14:48


• ኪ ም ያ ~ 9 •

| አብዱ ሩሚ  |


ሸሪዓ እንደ ፋኖስ ነው። በጨለማ ውስጥ የሚዳክርን ነፍስ እየገራ ከውድቀትና ስብራት ይጠብቃል። ወደ ምንሻው ቦት ያለ ምንም መደናገር ያስጉዘናል። ግና ፋኖሱን የለገሰንን ዘንግተን ፡ ትኩረታችንን ሙሉ ፋኖሱ ላይ ማድረጋችን ወዴት ያደርሰናል?


የውሸት ተጣሪዎችና እኩይ መምህሮች ከሰማይ ከዋክብት በላይ በምድራችን ላይ ተበትነዋል። ትክክለኛ ሙረቢ ወደ ነፍሱ ባለቤት እንጂ ወደ ራሱ አይመራህም። ጣቶቹን ቀስሮ ወደ ብርሀን ሲያሳይህ ፣ የጣቶቹን ነውር አትመልከት። ይልቅ ወዳመላከተህ አይኖችህን ስደዳቸው። ትክክለኛ ሙረቢ እንደ መስታወት ነው ፡ ብርሀን ከርሱ አልፎ ወዳንተ እንዲዘልቅ በር ይሆንልሀል።

|    ኮ ብ ላ ዩ [2]    |

በእሳት የተለበለበ ፊቱን ሳይሆን በመገፋት የቆሰለ ልቡ አይኖቹ ላይ ይታየኛል። ዙሪያው ያሉ ሁሉ ለገንዘቡ የቀረቡት ናቸው። ራሱም እራሱን የሚፀየፍ አይነት ሰው ነው። በሰው ቢከበብም የሚሰማው ባዶነት አለ። ይህን ሁሉ ያወቅኩት ፡ ወደ መመገቢያው ቦታ ካመራሁ ቡኋላ እየተንደረደረ ፡ ልክ እንደ ሩቅ ወዳጁ ሲያቅፈኝ ነው።
የፊት ገፅታዬ ከርሱ የበፊት መልኩ ጋር እጅግ እንደሚመሳሰል ፈገግ እያለ ነገረኝ። የሚያወራኝ እንደ አንድ ባለ ሀብት ተኩራርቶ ሳይሆን እንደ ልጅ እየተፍለቀለቀ ነበር። ልቡ ንፁህ ነው። ኩራት ከሚሉት መርዛማ በሽታ የጠራ ይመስለኛል። ኩራት እሳት ነው። የተረገመው ኢብሊስ በአንዲት ኩራት ነው የዘመናት አምልኮው አፈር የለበሰው። ጀነት ውስጥ ኗሪ መሆኑ ፡ ከመላዒካዎች ጋር መሆኑ ፡ እጅግ አምላኪ መሆኑ ለኩራቱ ከመቀጣት አላገደውም።  ቅጣቱም እጅግ የከፋ ነበር።

አባታችን አደም አለይሂ ሰላም ጥፋት ባጠፉ ጊዜ ወድያውኑ ተውበት አደረጉ። ራሳቸውን በጥፋት ፈረጁ። ተናንሰው ወደ አላህ ተዋደቁ። ምህረቱን ለመኑት። ውስጣቸው በፀፀትና ጥርት ባለ የምህረት ተስፋ ተሞላ። መሀሪው አላህም ይቅር አላቸው። ጥፋታቸውን በይቅርታው ሻረው።

ኢብሊስ ራሱን በጥፋተኝነት አልወቀሰም። በሰራውም ስህተት ወቀሳ አልተሰማውም። ፀፀት አልነካውም። በጥፋቱ ላይ ፀና። የጥፋቱ ምንጭ ኩራት ነበርና መመለሱ ከባድ ሆነበት።

አንድ ሰውም ሲያጠፋ የጥፋቱ መነሾ ኩራት ካልሆነ ፀፀት ከልቡ ዘልቆ የተውባ እንባ ከዐይኖቹ እየረገፉ ምህረትን ለመጠየቅ ይቀርባል። የጥፋቱ ምንጭ ከኩራት ከሆነ ግን መመለሻው ዳገት ይሆንበታል።

አንድ ቀን ኢብሊስ ወደ ሙሳ(ዐሰ) መጣ። አንተ ማለት አላህ ለመልዕክተኝነቱ የመረጠህና ማናገርን ያናገረህ ሙሳ ነህ አይደል? ሲል ጠየቃቸው። ሙሳም " አዎን ማን ነህ አንተ ምንስ ፈልገህ ነው? " ሲሉ ጠየቁት። እኔ ኢብሊስ ነኝ ፡ " ከፍጥረታቶችህ መሀል  አንዱ ፍጡርህ ንሰሀን ጠይቋል።  ብለህ ለጌታህ ንገርልኝ። " ሲል ጠየቃቸው

አላህም ወደ ሙሳ (ዐሰ) ወህይን አወረደ። " እኔ የምትለውን ተቀብያለሁ ነገር ግና ሙሳ ሆይ ወደ አደም ቀብር ሄዶ እንዲሰግድ ንገረው። "
ኢብሊስ ይሄን ሲሰማ ንዴት ውስጡን ሞላው። ኩራቱ ዳግም ጠፍንጎ አሰረው።  " በህይወት እያለ ያልሰገድኩለት ከሞተ ቡኋላ እንዴት ለቀብሩ እሰግድለታለሁ።" በማለት በአመፁ ላይ ቀጠለ።

የኩራቱም ቅጣት ለዘልዓለሙ መረገም ነበር! እድለቢስነት።
ከዚህ አይነት በሽታ ልቡ የጠራችለትን ሰው ማውጋት አብዝቼ እወዳለሁ።እሱም ብዙ ዘመናት ሲናፍቀው የነበረውን ወዳጁን ያየ ይመስል ከአንዱ ጥግ ላይ አስቀምጦ የልቡን ያወጋኛል።

  
     የነበረበትን የድህነት ህይወት ያለ ምንም መሸማቀቅ አወጋኝ። ስለሰዎች ያለው ምልከታና ለዱንያ ስላላቸው የገዘፈ ቦታ በአግራሞት አወራኝ። ዙሪያው ያሉ ሁሉ ዱንያውን እንጂ እርሱን ፈልገው እንዳልተሰበሰቡ ፈገግ እያለልኝ ነገረኝ። በግራ ፊቱ በኩል ያረፈው ጠባሳ ከግራ ጆሮው አንስቶ እስከ ከንፈሩ የግራ ክፍል ይደርሳልና ፈገግታው ግማሽ ነው። ቢሆንም ግን የጥርሶቹ ንጣት ፈገግታውን ያደምቁታል። ግልፀኝነቱ ለአንድ ባዳ ሰው ሳይሆን ፡ ከዚህ በፊት ለነበረው እርሱነት የሚያወጋ ነው ሚያስመስለው።

እንዴት ከችግርና መከራ ተላቆ ወዳለበት ሀብትና ዝና እንደተደላደለ ሲነግረኝ። ልቤን ነዘረኝ። ዱንያን ስለፈቱት ሁለት ሰዎች!  ያላቸውን ሁሉ መፅውተው ከበትራቸው ጋር ስደት ስለገቡት ሰዎች! 
ልቤም ከጆሮዎቼ  ጋር ተከፍተዋል። ሚያወራውን በጉጉት ይለቅማሉ። የምሰማው ሁሉ በነበር ከሚዘገብ የቀደምቶች ታሪክ ጋር ተመሳሰለብኝ።
በወንጀል ልባቸው የቆሰለ እኚህ ሰዎች የንስሀቸውን ርቀት ታዘብኩ። ዝህድና እና አምልኮዬ ከብናኝም አነሰብኝ።
ወዴት እንደሚሄዱ ሲጠይቃቸው ፡ ያ ደራሲው የተናገረውን ነገረኝ
" . . .ብዙ ርቀን አንሄድም ! አታስብ መድረሻችን ወደ ልባችን አድራሽ ነው። የትም ይሁን ምኞታችንን ሚጋራንን እስካገኘንና ወደ ተፈቃሪያችን የሚያዘልቀንን መንገድ እጃችንን ይዞ ሚገራን ካለ እንሰክናለን። የእግር ሳይሆን የልብ ጉዞ ላይ ነን። እጅግ ርቀነው ስለ ነበረው ወዱድ ስንል ልባችን ላይ የገዘፈ ቦታ ያላትን ዱንያን መፅውተናል። በኸይር የምታውላት ይሁን! . . "

   ልቤ ክንፏን አማታች። እኚህን ድንቅ ሰዎች ለመገናኘት ጓጓች። በዘገየሁ ቁጥር ሳላገኛቸው የሚያመልጡኝ መሰለኝ። እጅግ የወደቀ የነበረ ሰው ከውድቀቱ በብርቱ ንሰሀ ሲነሳ ፡ ከሺ ደጋጎች በላይ ደግ ይሆናል። እጅግ ጌታውን ወዳጅና ፈሪ ይሆናል። እኔ እንደሁ ፡ የመንገድ ልጅ ነኝ። መሄድ አያደክመኝም።
ኮብላይ ነኝ!

የፍቅር ኮብላይ .  . .

@ktebiban_meder
__

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

22 Nov, 09:04


| ጁምዓኩም ሙባረክ🩵 |

አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐለይህ!🩵
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

21 Nov, 13:41


•| አላህ♥️ |•

@ktebiban_meder
አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐለይህ!

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

20 Nov, 15:00


|      ኪ ሚ  ያ  ~8        |

-አብዱ ሩሚ-

   ብዙዎች ያኔያቸውን ይረሳሉ። በተለይም ነበራቸው ውድቀትና ድህነት ከነበር። ሰው ሀዘኑን ሽሽት ራሱን ያታልላል። ያለፈ ማንነቱን በደግነቱ ከርሱ ይወገድ ይመስል! ማጣት ውስጥ ያለው ችግር አይታየኝም። ለኔ ነፍሴን መቅጫ በትሬ ነው! ለሚቀርበኝ ፈገግታን እሰድቃለሁ ፡ አንደበቴ በዚክር የረጠበ ሆኖ ሳለ ፡ ነፍሴ እየፋፋች ስለ አካሌ መክሳት ስለምን የሁሌ ሀሳቤ ይሁን! ክምር አፈር ብቻ ነኝ! . . .!


|   ኮ ብ ላ ይ [1]    |

ይህች ነፍሴ በነጋዴዎች ከታጨቀችው መስጂድ በላይ የኮንያ ተራሮችን ትወዳለች። እዛ ድምፄን ከፍ አድርጌ አዜማለሁ። የልቤን እስክስታ አወርዳለሁ። ከተራራው አናት ላይ ሆኜ የከተማውን ትርምስ እያየሁ
" ኦ! የሰዉ ብክነት! እነዚህ ተራራዎች ላይ የሚያገኙትን ፡ የገበያ ሱቆች ላይ ለመሸመት ይተራመሳሉ! "

እውቁ የፍቅር ምሶሶ አፍጋን ውስጥ  ፡ ከበልኽ አውራጃ ሩማ ከምትባል መንደር በልጅነታቸው ወዲህ ነበር የከተሙት። በብዙ ልቦናዎች ላይ የፍቅራቸውን ችካል አኑረው ያለፉት።
እያወራሁ ያለሁት ስለ ጀላሉዲን -አል ሩሚይ ነው። ነፍሱን ለነፍሱ ባለቤት ስላስረከባት ፍጡር። ማሰቡን ትቶ ሀሳብን ስለፈጠረው ፈጣሪው ያሰበ።
በሁለቱም ክንፎች መብረር የተቻለው አፍቃሪ። ንግግሩና ግጥሞቹ በልብ የሚዳሰስ ሚስጥራትን ያጨቀ ነውና ያለ ደረጃቸው ለመረዳት በሚሞክሩት ላይ ግራ መጋባትን ብቻ ያተርፋል። ለተረዱትና በልባቸው ብርሀን ለተመለከቱት በሚስጥራት ስር ያስዋኛል።

  እኔም የእርሱ ኮብላይ ነኝ። የሩሚ ደረሳ! ምንም እንኳ ህልፈቱ ቢዘገይም አሁንም ድረስ አይኖቼ የናፍቆት እምባን ያንጠለጥላሉ። ይህ ፍቅር ነው ፡ ከኢርዙሩም ወደ ኮንያ ያመጣኝ። የኮንያ ተራራዎች ላይ ወጥቼ ስለ ወዱድ ፍቅር እንዳዜም ያደረገኝም ይሄው ፍቅር ነው። በሸይኽ ፍቅር ያለ ፈናዕ ፣ ከፍ ይልና ወደ ታላቁ ፍጡር በሀቢበላህ አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ፈናዕ ያዘልቃል ፡ ከዛም ወደ ወዱድ!
ፈናዕ ራስን መስጠት ነው። መሻትን ሁሉ ስለተፈቃሪህ ስትል ማጣት። በተፈቃሪህ ስር አንተነትህ ደብዝዞ እርሱነቱን ማጉላት።

በሱረቱ ዩሱፍ ላይ የተጠቀሰውን አንቀፅ ላይ መክተም ነው መሻቴ። አንቀፁ የሚስር እንስቶች በዩሱፍ ውበት ተደምመው ጣቶቻቸውን በስለት ሸረከቱ። ህመሙ ግን ለአፍታ አልተሰማቸው። ነፍሳቸው በውበት ስር ሰጥማ ነበርና! ይህ ነው ፈናዕ! እኔም ህመሜን እንደሽልማት ፡ ምቆጥርበትን መቃም ላይ መደላደል ነው ምኞቴ! ጥረቴም. . . .!

በልጅነቴ ነው ስለ ፍቅር የተሰበክኩት። ያውም ከባባ ኢልያስ ውብ አንደበቶች።

< ከዘመናት በፊት አንድ ባለ ሀብት ነበር። ይህ ባለ ፀጋ ድንገት በአንዱ እለት ፡ አንዲት ውብ ባሪያን ይመለከታል። ባለ ፀጋው በውበቷ ስር ወደቀ። በነጋ በጠባ ቁጥር ምስሏ በምናቡ ይመላለሳል። ትውስታዋ ከልቦናው ሊፋቅ ተሳነው። የፍቅሯ ታሳሪ ሆነ። በፍቅርና በናፍቆት መሀል የምትናወጥ ልቡን ይዞ ወደ አሳዳሪዋ አመራ። ባሪያይቱን ከፍ ባለ ገንዘብ ሊገዛት ጠየቀው። የባሪያዋ አሳዳሪም ፡ ባለ ፀጋው ከባሪያዋ ጋር በፍቅር መውደቁን ከአይኖቹ ተረዳ። አሰብ አደረገና። " አይ በዚህ ዋጋ አትሸጥም! " በማለት ያለውን ሁሉ አስረክቦ ባሪያይቱን እንዲገዛው አደረገ። ባለሀብቱ የለበሰውንም ባርኔጣና ኩታ ሳይቀር አስረክቦ ተፋቃሪውን ይዞ ተጓዘ። >
   አየህ አይደል የኔ ልጅ! አፍቃሪ ላፈቀረው ነገር ያለውን ሁሉ ይሰዋል። ሚሰዋው ቢጠፋ የቀረችው አንዲትን ነፍስ እንኳን ብትሆን እርሷንም አይሰስትም። የርሱ መሻት የተፈቃሪው ደስታና ውዴታን መጎናፀፍ ነው። ታድያ በፍጡራን መካከል ላለ አላቂ ፍቅር ይህን ያህል ቤዛ የሚደረግለት ከሆነና ሀብትና ንብረትን እስከማጣት ካስደረሰ ፡ ስለምን የጌታህን ፍቅር ያለ ምንም ክፍያ ትሻለህ? ክልከላውን ስትዳፈር ፡ ልብህ ላይ ያለው የማፍቀር ሂማ እየሞት እንደሚጠፋ አይሰወርህ። የትዕዛዙን በትር ስትይዝ ፡ የኩራትን ኩታን ካደረግክም በራስህ ላይ የፅልመት ካባን ነው የደረብከው። እኔነትህን ጥለህ ቅረበው። መሻትህን ግደለው። ምንምነትህን ገልጠህ ፡ ከዱንያ ፍቅር ተራቁተህ ቅረበው። ጣላት ይህችን ነፍስ! ተዋድቀህ የእውነት ፡ ሚስኪንና አሳዛኝ ባሪያ ሁንለት። እንዲያ ነው ፍ ቅ ሩ ን የምታገኝ!  >

በእኚህ ቃላት ነፍሴ ተሰደደች። ተፈቃሪዋን አፍቃሪው ሰው ወደነበረበት ከተማ።
ኮንያ ከኢልምና ሲያሳ መዓከልነቷም ባሻገር ደጃፋቸው ላይ ለምንተነፍሰውም አየር ሊያስከፍሉ የሚዳዳቸው ስግብግብ ነጋዴዎችንም ይዛለች።

በእርግጥ መጥፎና ጥሩ የምንላቸው ነገራቶች ብዙ ጊዜ በጣምራ ይገኛሉ። ደግነት ካለ የሆነ ቦታ ላይ የበዛ ንፉግነት ይኖራል። ለዛም ይመስለኛል ከነዚህ ስግብግብ ነጋዴዎች አቅራቢያ የተራቡትን መቀለብያ ቤት የተከፈተው። የዚህ በጎ ስራ ባለቤት ልበ ብሩህና ቀና ሰው እንደሆነ በመሳኪኖች አንደበት ሲመሰከርለት ሰምቻለሁ። ስለ ፊቱ ገፅታ አስፈሪነትም ያንሾካሽካሉ። እኔም ይህን ደግ ሰው ላገኘው ወደ ምግብ ቤቱ ሄድኩኝ። የጠበቀኝ ግን ያላሰብኩት አቀባበል ነበር። በኺድማው ላይ ከሚሳተፉ ደረሶች ለየት ያለን ልብስ ያጠለቀ ሰው በትኩረት ተመለከተኝ። አይኖቹን ባለማመን ግራ ቀኝ አዙሮ ድጋሚ ወደኔ ተቅጣጨ።

ወዳለሁበት ስፍራ ተቻኮለ . . .

ከኮንያ ሰማይ ስር. . .
_____
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

20 Nov, 05:17


ፈገግታ

አንድ ኢማም ናቸው ይባላል... ኺድማ እማያውቁ ሰዎች መስጂድ ዘንድ ኢማምነት ተቀጥረው በእንግድነታቸው ለ3ቀናት ዳቦ በጨውዘይት ያበሉኣቸዋል
በ4ኛው ቀን በጣም ክፍት ብሉኣቸው ሱብሂ ሶላቱን እንዲህ አሰገዱ

ከፋቲሃ በኋላ " እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ አላህን ፍሩ ፡لا تطعمو إمامكم خبزا وملحا "ኢማማችሁን ዳቦ በጨው አትቀልቡ
بل أطعموه لحما طريا فإن لم تجدو فدجاجا مشويا فإن لم تجدو فسمكا سمينا
ትኩስ ስጋን አብሉት እሱን ባታገኙ የተጠበሰ ዶሮን ይሄም ካልተገኘ ሰባ ያለ አሳን
ይህንን ያልሰራ " ዶላለን ሙቢይን" ግልጽ የሆነ ጥመት ውስጥ ነው።
በሁለተኛው ረከዐም እንዲሁ ብፌያቸውን ቀራሩ

ሶላቱ እንዳለቀ ምስኪን ምስኪን አባቶች "አፉ በሉን አፉ በሉን ሸሆቹ " እያሉ ስራቸው ተደፉ '"ምንም አይደል እንዲሁ ላስታውሳችሁ ብዬ ነው "
"ግን አንቀጹስ የትኛው ምዕራፍ ላይ ነው ያለው አላወቅነውምኮ ሸሆችዬ" ሲሉኣቸው
"ሱረቱል ማኢዳ(የማእድ ምዕራፍ)ን አጣርታችሁ ቅሩ" አሉኣቸው ይባላል።

ያው እኛም ቁርዐን እና ሓዲስ ለስሜታችን ማስረጃነት ብቻ ስንገለገልባቸው ከዚህ ኢምም ብዙም አልተለየንም........

©Aymeni

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

19 Nov, 14:44


| ኪምያ~7 |


-አብዱ ሩሚ-


አብዛኞቻችን የምኞታችን ጣሪያ ላይ ስንደላደል ሌላን ከመመኘት ውጪ ፡ ረግቶ መስከንን አንችልበትም።  ምንገታው አይነት አይደለም መሻታችን። ሁሉ በእፍኛችን ቢሆን እንኳ የማጣትን ስሜት ምንመኝ ይመስለኛል።

|     ባ ለ   ሀ ብ ቱ [2]       |

የሰው መልክ ይገርመኛል። እጅግ አስመሳይ ፍጡር ነው። የሚፈልገውን ለማግኘት ያልሆነውን ይሆናል። የማይደፈረውን ያደርጋል። የማይታሰበውን ይፈፅማል። ነፍሱ አብዝታ ለምትጓጓለት ነገር ነፍሱንም ቢሆን ይገብራታል።
ምንም እንኳ ልቤ በጥላቻና በእልህ ቢጨልምም ። አይምሮዬ ግን ንፁህና አስተዋይ ነው። የማየውን እያንዳንዱን ነገር አገናዝባለሁ። ዛሬ ላይ ስደላደል ትላንቴን አልረሳም። ከሀዲ አይደለሁም። ለራሴ እጅግ ታማኝ ነኝ።

ታድያ ዛሬ ላይ እንዲህ የከተማው ባለ ሀብት ተርታ የተመደብኩት በምፅዋት ነው ብል ማን ያምነኛል? በዛች የተባረከች የምላት ምሽት ሆዴ የረሀብ ዜማውን ሲያደራብኝ ፡ ወደ ደራሲው ቤት ቆረቆርኩኝ። ያንኳኳሁት የደራሲውን ደሳሳ ጎጆ ቢሆንም የተከፈተልኝ ግን የሀብት በር ነበር። ችግርና ማጣት ያጎሳቆለኝ እኔ ሳላመነታ ገባሁበት።  ደራሲው ከባለ ወይኑ ጋር ሆነው ለሰደቃ በጆንያ ያዘጋጁትን የወርቅ ሳንቲም በሙሉ ለኔ ለገሱኝ። የህይወታችን መልክ ተቀያየረ። ሁለቱም ተመሳሳይ ቁመት ያላቸውን በትር ፣ አነስ ያለች ቦርሳና ኢብሪቃቸውን አንጠልጥለው ለመንገድ ተሰናዱ።
የኑሮን ቀለም ተቀያየርን። እኔ ወደ ድሎቱና ምቾቱ አለም እነርሱ ወደ ችጋርና ማጣቱ ተቀላቀሉ። የሰው ልጅ ጥጋብ ይህን ያህል ይሆናል ብዬ አስቤ አላውቅም። እነዚህ በመጠጥ ሱስ የተናወዘ አዕምሮ ያላቸው ሰዎች እንዲህ ቸር ይሆናሉ ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ለጉዞ ተሰናድተው ባሉበት ፡ ወዴት እንደሚሄዱ ልጠይቅ...አልጠይቅ እያልኩ አመነታሁ።
ድንገት ደራሲው ምናልባትም ልብ አውቃው አልያም ጠንቋዩ    " ብዙ ርቀን አንሄድም ! አታስብ መድረሻችን ወደ ልባችን አድራሽ ነው። የትም ይሁን ምኞታችንን ሚጋራንን እስካገኘንና ወደ ተፈቃሪያችን የሚያዘልቀንን መንገድ እጃችንን ይዞ ሚገራን ካለ እንሰክናለን። የእግር ሳይሆን የልብ ጉዞ ላይ ነን። እጅግ ርቀነው ስለ ነበረው ወዱድ ስንል ልባችን ላይ የገዘፈ ቦታ ያላትን ዱንያን መፅውተናል። በኸይር የምታውላት ይሁን! "

  የድሎት ወራቶች ተፈተለኩ። ምቾት ላይ ስንሆን ረዥሙ ጊዜ ለምን እንደሚያጥር አይገባኝም። አልያም ችግር ላይ የሆንባት ትንሽ ሰዓት ለምን የአመታት ያህል እንደሚረዝም።  ምናልባትም በአመስጋኝነትና በታጋሽነታችን ማነስ ይሁን ነገሩ የተገለባበጠው?
ትላንት ላይ አጠገባቸው ሆኜም መኖሬን እንኳን ልብ ማይሉና ማያስተውሉ ሁሉ ዛሬ ላይ በክብር ከወንበራቸው እየተነሱ ይቀበሉኛል። አንቱታን ተቸርኩ። የውሸት ውዴታና አድናቆት ወደ ጆሮዎቼ መንቆርቆር ጀመረ።

ምንም እንኳ ከነበርኩበት የብቸኝነትና የርሀብ ዘመን የተሻለ መስሎ ቢታየኝም ፡ ቀስ በቀስ ሁሉ ነገር እየሰለቸኝ መጣ። የምኖርለት አላማ ተሰወረኝ። የቀን ጉርሴን ብቻ አግኝቼ እብቃቃ የነበርኩት እኔ ዛሬ ላይ ጠረጴዛ ሙሉ ምግብ አላረካህ አለኝ። ምን እንዳጣሁ አልገባኝም። ብቸኝነቴን በሀሰት ፈገግታቸውና ጫወታቸው የሚያሶግዱ ጊዜያዊ ወዳጆችን አፍርቻለሁ። ምመኘውና ማልመው የሀብትና ዝና አናት ላይ ተቆናጥጬ መርጋት ተሳነኝ።

  የሆነው የልቤ ክፍል ያለፈ ማንነቴ አካል የሆኑትን ማገዝ እንዳለብኝ ይነግረኛል። ስግብግቧ ነፍሴ መስጠትን እንደማጣት እየቆጠረች ትከለክለኛል። በልቤና በነፍሴ ማሀል እንደዋዠቅኩ ሁለት ድፍን አመታቶች አለፉ። የልቤ እውነት እየጎላና የነፍሴ ጥማት እየቀነሰ መጣ።

መጀመሪያ በኢዝሚር ላይ ለየቲምና ለችግርተኛ በነፃ የሚቀልብ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከፈትኩ። ቦታውን በኢዝሚር ዳርቻ ላይ ከሚገኙ ሀሪማዎች አቅራቢያ አደረግኩት። የሀሪማው ደረሶች ያለምንም ክፍያ የቲሞችን ሊንከባከቡ ቃል ገብተው ድርጅቱን ተረከቡኝ። ትክታ የማይታይበት ፊታቸው እጅግ ሰው ይስባል። መሳኪኖችን ከምግብም ባሻገር ፍቅርና ፈገግታን ይመግባሉ። በዚህ ተግባር ላይ ከተሰማራሁባት ቀን አንስቶ መኖር ያጓጓኝ ጀመር።
ምክንያቱም ትልቅ አለማን አንግብያለሁና! የተራበን ነፍስ መመገብ። የአልቃሾችን እምባ ማበስ። የተሰበረን ልብ መጠገን። በአንዲት አማኝ ልብ ላይ ደስታን መጫር። ይህ ተግባር ከምንም በላይ ለኔ ትርጉም አለው። የመራብና የመገፋትን ጥግ አይቼዋለሁ። በርሀብ ራስን መሳት ምን ማለት እንደሆነ ፡ እየኖሩ አለመኖር። እየሳቁ አለመደሰት ፡ ሞትን በናፍቆት የመጠባበቅን ስሜት እረዳዋለሁ።

ነፍሴ በልቤ ውሳኔ ባገኘችው ሀሴት ላይ ሌላን ልታክል በኮንያና ካይሰሪም ለተመሳሳይነት አላማ ሚውሉ መመገቢያ ቤቶችን ከፈትኩ። ስክነትና እርካታ በራስ ዙሪያ ገንዘብን በማዋል እንደማይገኝ ተረዳሁ። ስክነት እንደ ወፍ ናት በተቸገሩ ሰዎች ልብ ስር  የምትገኝ። ሚያስደስታትን ስታገኝ ክንፏን እያማታች ያስደሰታት ልብ ላይ ታርፋለች።

   ገንዘብ ካለ. . .ወደ ልብ መንገድ አለ! ሆነ መርሄ። በገንዘቤ የሰዎችን ልብን መጠገኑን ተያያዝኩት። ያዘኑ ነፍሶችን ማስደሳቱን ስራዬ አደረግኩት። ምትደሰተው ግን የኔዋ ደስታ ለማኝ ነፍስ ብትሆንም።


   አመታቶች ነጎዱ! ሶስት  የድሎትና ምቾት ጊዜያቶች። ኢዝሚርን ለቅቄ ዋና ከተማ ወደሆነችዋ ኮንያ ላይ ወደገዛሁት ቤት አመራሁ። ከእለታት አንድ ቀን በከተማዋ መሀል ላይ ያሰራሁትን የመሳኪኖችን እምባ ማበሻ ቤት ላይ ግን አይኖቼ ሊያምኑት የከበዳቸውን እውነት ተመለከቱ።

. . .የ"ነበር" መልኬ!.....

@ktebiban_meder
__

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

18 Nov, 14:51


| ኪምያ ~ 6   |

- አብዱ ሩሚ -

ገፅታቸው ማይስብ ቢሆንም ውስጣቸው እጅግ የተዋበ የሆኑ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ፡ ልባቸው እጅግ አስቀያሚ የሆኑ ባለ ቆንጆ ፊቶች አሉ። እውነተኛ መልካችን ቢገለጥ ማን ሚቀርበን ይመስላችኀል? ምናባትም ራሳችንንም እንፀየፍ ይሁን!


|    ባ ለ   ሀ ብ ቱ [1]    |

የተራቆትኩ ነኝ። ልክ እንደ ረገፈ ዛፍ! ዕለት በዕለት እያንዳንዱ የሰውነት አካሌ ይከዳኛል። ማጣውን የማጣው ለዘልዓለም ነው። ሰዎች ከገዳይም ፣ ከአማፂም በላይ ተጠይፈው ይመለከቱኛል። አይኖቻቸው ድንገት ወደኔ ከተቅጣጨ ማን እንደሆንኩ ሳይሆን ምን እንደጎደለኝ ለማየት ያንከራትቱታል። ለኔ ፀደይ የለም ፡ ምፈካበት! ለኔ እኔው ጠበቃ ሆኜ መቆምም እስካልችል ድረስ በሰዎች ተገፍቻለሁ። እራሴንም ደጋግሜ ከመርገም ውጪ ከራሴ ጋር መታረቅ ተስኖኛል።
እኔን የተመለከቱ አይኖች ሞት በአስቀያሚ ገፅታ የቀረባቸው ይመስል ይደናበራሉ። አይኖቻቸውን ሚያሳርፉበት ሌላ ስፍራ ፍለጋ ይዟዟራሉ።
መፅዎቾቼ ፡ ፊቶቻቸውን አጨፍግገው ነው  ሽርፍራፊ ሳንቲም ሚለግሱኝ። እሱንም አሳዝኛቸው ሳይሆን ፈርተውኝ ይመስለኛል።

  
     የዛሬን አያድርገውና. . ብዙዎች የሚመኙት ውበት ተለግሼ ነበር። የዘመናችን ዩሱፍ የሚያስብልን ቁንጅና ፡ በአንድ መከረኛ ቀን አጣሁት። አካባቢያችን በሞንጎሎች እሳት በተያዛዘበት ወቅት ነው ፡ ዩስፍነቴ የረገፈው። መልከ ጥፉው እኔ የተፈለቀቅኩት።

ያ ሰዎችን ይማርክ የነበረው የላይ ገፅታዬ እንዲህ ሲቀየር የሚቀርበኝ አጣሁ። የሰዎች ውዳሴና አድናቆትን የለመደ ጆሮዬ ስድብና ማንቋሸሻቸውን መስማት ተሳነው። ክብርና ሙገሳን የለመደችዋ ነፍሴ ንቀትና ውርደትን መቋቋም አቃታት። በእሳት ከተለበለበው አስፈሪ ፊቴና ፡ ግራ እጄ ላይ ያረፈውን  ቁስል ይዤ ከኢርዝሩም ወደ ኢዝሚር አመራሁ። በአነስተኛ ንግድ የሞቀች ለአቅመ ከተማ ያልደረሰች መንደር ናት። እዚህ ማንም ስለኔ ግድ አይሰጠውም። ሁሉም ብልጭልጯ አለም ላይ ነው ልቡ ያለው። ከስንት አንዱ የተወሰነች ገንዘብ ጣል ያደርግልኛል ፡ ሌላ ከፍ ያለን ገንዘብ እንዲለግሰው በማሰብ እየመፀወተ መሆኑ ነው። በቃኝ የሌለበት ርብርብ ነው። ሁሉም ስግብግብ ነው ፡ አንድም ግን አመስጋኝ አላየሁም። ከኢማሙ ጀምሮ የአማራሪዎች ጥርቅም።

    ብዙ ጊዜ የኢማሙን ኹጥባ ከአንድ ጥግ ላይ ተሰይሜ አደምጥ ነበር። በዘመኑ ላይ ፡ በነዋሪው ላይ  ፣ በነጋዴው ላይ የኑሮ ምሬታቸውን በሀዲስ መሀል እያዋዙ ከመለፈፍ ውጪ ምን አደረጉ?
አንዳንዱ ልቡን ከጭንቀት ለማሳረፍ ወደ መስጂዱ ሲገባ ፡ ያላሰበውን እንዲያስብ እያደረጉ ፡ ጭንቀቱን ያድሱለታል።

    በእርግጥ ያሉበትን ጨለማ መርገም ትተው ፡ ጭላንጭል ብርሀን ለመለገስ ሚታትሩባት ደጋግ ሰዎችንም ትንሿ ኢዝሚር አቅፋለች። ግን ምን ያደርጋል ፡ እነርሱ ጋር ለልብ የሚሆን ቃል እንጂ ለሆድ የሚሆን ሳንቲም የላቸውም። ያገኙትን ሁሉ ላገኙት ሰው ይለግሳሉ። ስለ ነጌያቸው ብዙ አይጨነቁም።ዛሬን በደግነት ለመኖር ሲሉ ፡ ስግብግብ ማንነታቸውን እንደ በግ አጋድመውት ለማረድ ይታትራሉ። እንደ ሌላው እኔን አይጠየፉኝም። ከልብ መልካም ናቸው። ሰጋጅ ፡ ፆሚ የምላቸው ፊታቸውን በንቀት ሲያጨፈግጉብኝ ፡ እነዚህ ግን ፈገግታቸው ለልብ ይደርሳል።


በመስጂድና በሰጋጆች ፣ በሀሪማና በሙሪዶች ፣ በሱቅና በነጋዴዎች ብቻ አልታጠረችም። ኢዝሚር!
ይልቅ መጠጥ ቤት እና መጠጥ ጠጪዎቿንም ታቅፋለች። ምንም እንኳ ስለ መጠጥ ቤቱ አድራሻ የሚያውቁ ጥቂቶች ቢሆኑም መጠጥ ቤት እንዳለ ግን የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ከመጠጥ ቤቱ ደንበኞች ውስጥ ፡ እንደሆነ የሚጠረጠረው የአንድ ደራሲ ቤት ፡ እኔ ከምተኛበት በረዳ ብዙ አይርቅም። ታድያ አንድ አንዴ በስካር መንፈስ እየለፈለፈ በሌት ወደ ቤቱ ሲዘልቅ እመለከተዋለሁ። አንዳንዴ ደግሞ በቃሉ የጌታውን ቃል በውብ ድምፅ እያዜመ ይገባል።
ይህ ፍፁም የተለያየ ማንነት ያለው ሰው ፡ ሊገባኝ አልቻለም። እንዴት ሰው በቀናቶች ውስጥ መልዓክም ሰይጣንም መሆን ይቻለዋል! ዛሬ ላይ ደግሞ ከአንድ ፈርጣማ ሰው ጋር ወደ ቤቱ በዝምታ ገባ። ያ ፈርጣማ የቤተ መፅሀፍቱ አልያም የመጠጥ ቤቱ ባለቤት ይሆናል።

ሆዴ እንደ ወትሮው መታገስ ተሳነው። ሰርክ እንደሚደለቅ ነጋሪት ይጮህብኛል። ከናፍርቶቼ ደርቀዋሉ። በእንቅልፍ ላታልለው ግራ ቀኜን ተገላበጥኩ። የሚሆን አልሆነም። ብርዱም አጥንት ይሰረስራል። ጥርሶቼ በቅዝቃዜው ሳብ ይገጫጫሉ። በመጨረሻም ያለኝን እንጥፍጣፊ ጉልበት አሰባስቤ ቅርቤ ወዳለው ቤት አንኳኳሁ።  የደራሲው ቤት!

. . ምናልባት ዛሬ የደግነቱ ተራ ይሆን? በመተስፈይ ላይ. . .

ይቀጥላል . . .

@ktebiban_meder
__

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

16 Nov, 11:31


ልጅ ናት ነፍሴ . . !

@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

15 Nov, 15:43


|        ኪምያ~5        |


-አብዱ ሩሚ-


     አዋላጆች ሚያዋልዷት ሴት ህመም ካልተሰማት፡ የልጁ መውጫ ሰላማዊ እንዳልሆነ ይገነዘባሉ። እንዲህ ነው ህይወትም ላይ ፡ እኛነታችን አዲስ ውልደትን እንዲያገኝ ህመም ግድ ይላል። ሸክላ እንዲጠነክር በእሳት ውስጥ ገብቶ እንደሚወጣው ሁሉ ፡ ፍቅርም ሚሞላው ከህመም ጋር ነው።

*

|      ደ ራ ሲ ው [2]      |


      . . .ጊዜ መውደድ ላይ ያለው ተፅኖ ምንም ነው። ለአመታት አብሮን ከሰነበተ ሰው ይልቅ ፡ ለአንድ ሰዓት ያወራነው ሰው ይበልጥ ለልባችን የቀረበ ሊሆን ይችላል።

በእምባ ብዛት ያባበጡ አይኖቼን ይዤ ወደ ባለ ወይኑ አቀናሁ። ወደ መግቢያው ስጠጋ እንደ ሁሌው ሳቅና ጫጫታ ይደመጣል። በሩን በርግጄም ብገባ ስለ መግባቴ ማንም ግድ አይሰጠውም ብዬ አሰብኩ። ለነገሩ ስለኔስ ማን ግድ ይሰጠውና! ባይሆን ባለ~ወይኑን ሰላም ብዬው እመለሳለሁ።

በሩን በቀስታ ገርበብ አደረግኩት. . .


*

አይኖቹ ከበሩ ላይ ነበር። የኔም አይኖች እግሮቼ ወደ ውስጥ ከዘለቁ ወዲህ ወደርሱ ተቅጣጭተው ነበር። ያየው እንዳስደነቀው ሰው ፊቱ በአግራሞት ተሞላ። ከሚያስተናግድበት ቦታ እየተጣደፈ ወደኔ ተቻኮለ ፡ ፊቱ ሀሴት ይረጫል። አይኖቹ አንዳች ብስራትን እንደደበቀ ያስታውቃሉ።

" ምነው ምን አጋጥሞህ ነው የጠፋሀው? " ደስታና ስጋት ያደረበት ፊቱን አስተዋልኩ።
ዝም ብዬው ወደ መቀመጭያዬ አዘገምኩኝ ፡
ተረጋግቼ ከተቀመጥኩ ቡኋላ ፡ ለአንዱ አስተናጋጅ ወይን እንዲያመጣልኝ ሲጠረው ፡ እጁን ይዤ አስተውኩት።
" ምነው ሰላም አይደለህም? " ግራ ገብቶት ጠየቀኝ።

ብልጭ ድርግም ስለሚለው ቅድስናዬ ፡ በዚህ የጥፋቴ ሜዳ ላይ ላወጋው አልፈለግኩም። የሆነውን ሁሉ ፡ ወደ ኸልዋዬ ወስጄ አስጎበኘዋለሁ። ምናልባትም ፡ የርሱም ልብ የኔን ፡ የኔን የርሱን ታቀና ይሆናል።


   ምንም እንኳን የእውነትን መንገድ ለመመራትና በርሱም ላይ ለመሰንበት ምትመኝ ልብ ብትኖረኝም። ነፍሴ ለዚህ መንገድ የሚከፈለውን ፡ የገንዘብ ፡ የፍላጎትና ምኞት እንዲሁም የነፍስን መስዋትነት ልትከፍል ፍቃደኛ አይደለችም። ልቤ የረታች ቀን ደጉ እኔነቴ ይጎላል። ሁኔታዬ ወደ ጌታዬ ያስጠጋኛል። አሳዛኝ አምላኪ እሆናለሁ። በጌታው ፍቅር እንደተነካ ከታቢም ያደርገኛል። አንደበቴ ላይ ስሙ ይገራል ፣ ያረካኛልም። መዴ ይለመልማል። ምከትበው ሁሉ ይዋባል።
ነፍሴ የምትረታበት እለት ላይ ድባቴና ምሬትን እጎነጫለሁ። የማላውቀው ብቸኝነት ይወረኛል። እንጥፍጣፊ እዝነት የሌለው ጨካኝ እሆናለሁ።  እርም የሆነውን ሁሉ እዳፈራለሁ። ጨለማ ገፄ በነፍሴ የተከተበ ድቅድቅ ነው። ብርሀኔን ለኳሽ ልቤ በፀፀት ትበራለች።


*

እግሮቻችን እየከታተሉ ፡ ከመጠጥ ቤቱ ርቀን ወደ ልቤ ጎጆ አመራን። ወደ ኸልዋዬ! ተነጥዬ ማነባበት። በፀፀት ጠብታዎች ወደረሰረሰው ምሽግ። ከነፍሴ መሻት ምደበቅበት ስፍራ!


የኸልዋው ግድግዳዎች ላይ ፡ በተለያየ ቀለም የተፃፉ ቃላቶች እጅግ ጎልተው ይታያሉ። የጌታዬን ስም በሚያማምሩ ፅሁፎች ከትቤ ፡ ከስሙ ግርጌ ፀፀቴን በቃላት ሞነጫጭርያለሁ። እምባዎቼ ግድግዳው ላይ ተዘርተዋል።
_

ወደ ኸልዋው እንደገባን ፡ ስለ እኔነቴ አወጋሁት። ሁለት ገፅ እንደሆንኩም ጭምር። በየሰሞኑ ምቀያየር ፡ ጨለማና ብርሀን የሰፈረብኝ ሰው እንደሆንኩ እየነገርኩት ሳለ . . .
" እርግጥ ብርሀንህ ፡ መርታት ሚቻላት ይመስለኛል! ብስራት አለኝ! " ሲል አቋረጠኝ።

የሚለውን ለመስማት ሙሉ ሰውነቴ ጆሮ ሆኖ የአንደበቱን ቃላት ይጠባበቅ ጀመር። ባለንበት እንደቆምን ፡ በሶስት ኩራዞች የምታበራዋ ፡ ጎጆ ስር ትልቅ ብስራትን ሊጋሩ ሁለት ነፍሶች ተሰይመዋል።

አብረን በተኛንበት ሌት ላይ ስላየው ህልም ያወጋኝ ጀመር።
". . . አይኖቿን ተከትሎ የእምባ መውረጃ ሚመስሉ መስመሮች ያሉባት ፡ ነጭ በነጭ የለበሰችመልከ መልካም ሴት አጠገብ. . ነበርክ! "

እምባዬ ያለ ፍቃዴ ረገፈ። ነፍሴ ተንሰቀሰቀች። ድብቅ ልጅነቴ ፡ ተፍለቀለቀ። የዘመን አቧራዬ ሲረግፍ ታወቀኝ ፡ ልቤን ቅልል አላት። የኔን ማልቀስ ፡ ተከትሎ እርሱም ያነባ ጀመር። እስኪበቃን ተንፈቀፈቅን. . ከዛም የለቅሶ ዜማችን ወደ ሳቅ ተቀየረ። ሁኔታችን ግራ እንደገባኝ አለሁ። ከጎጆው ግድግዳ ላይ ከዚህ በፊት የከተብኳት ፅሁፍ ተለይታ አንዲት ፅሁፍ እንደ ጨረቃ ደምቃ ታበራለች። አይኔ ፊደላቶቹ ላይ ነበር. . .

| <  በዚህች ምናባዊ አለም ላይ ያለን ቁስ ፈላጊ  በቁጥር አይገደብም። በውስጧ ያሉ መጋጌጫዎች ፣ ሀብት ፣ ዝናን ፣ ድሎትና ምቾቷን ሽቶ ነፍሱን ሊመፀውት የተዘጋጀ አንድ ተብሎ አይዘለቅም። ከመሻቷ ተናጥቦ ስለ ዘልዓለማዊው አለም ፡ ስለ በርዘኹ አለም የሚጨነቅና ስለርሱ የሚለፋ ደግሞ እጅግ አናሳ ነው። አብዛኛዎቻችን በስካር ላይ ያለንና ነፍሶቻችን መርጋት ተስኗት የምትንገዳገድ ናት። ከኚህ አኼራዊ ሰዎች ፣ በዘመናቸው እንግዳ ከሆኑት በስተቀር። 
በዚህች አለም ላይ ከዱንያውም ይሁን አኼራዊ ጉዳዩች አስበልጠው አላህን የሚሹና ውዴታውን የሚከጅሉ ፣ ከጥቂትም ያነሱ ጥቂት ሆነው ታገኛቸዋለህ።

• ምንኖርባት ምድር አንድ ናት። አኗኗራችንና በልባችን ላይ ያለው ፍፁማዊ መሻት ግን የኑሮዋችንን መልክ ይወስናል። ታድያ የኔ ልብ. . .
የኑሮህ ቀለም በጥቁረት የተላወሰ ነው ወይስ በብርሀን የተሽቆጠቆጠ? > |

አይኖቼን ከግድግዳው ላይ አንስቼ ወደ ባለ ወይኑ ላኩ። እርሱም እኔ ሳነብ የነበረውን እያነበበ ነበር። እነዚያ ፈርጣማ እጆቹ ፡ ተኮማትረው እርስ በእርስ ተቆላልፈዋሉ። አይኖቹ እምባ ያለቃቸው ይመስል ደርቀዋል። በወይን የወዙ ከንፈሮቹ ዛሬ ላይ ምድረ በዳ መስለዋል።

ፁሁፉን ያነበብነው በአይኖቻችን አልነበረም። የተገነዘብነውም በአይምሮዋችን አይደለም። ያየነውም ያነበብነውምና የተረዳነውም በልባችን ነበር። ገፀ ህይወታችን ጥቁረት ወርሶታል። ድቅድቃት ብቻ! ኋላችን የውድቀት ታሪካችን ተከትቦበታል። የክስረትና ራስን ማጣት አለም ታጭቆበታል። ሰላም የሌለው የርስክሰት ቅፅበታቶች ሰፍረውበታል።

ነበራችንን በአዲስ ገፅ ለመፋቅ ተነሳን። የነፍሳችንን ድቅድቃት በልባችን የብርሀን ሰደድ ልንረታ። ጥቁሩን ገፅ በነጭ ቡሩሽ ልንቀልም ፡  . . . .


እንደ አላህ ፍቃድ ሰኞ ይቀጥላል  . . .
@ktebiban_meder

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

15 Nov, 11:21


• ውብ አሁን!💚

# الشخ-جابر-بغدادي🌹
@ktebiban_meder

4,488

subscribers

894

photos

225

videos