መዝሙር ዘ ተዋሕዶ @mezmur_z_tewahdo Channel on Telegram

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

@mezmur_z_tewahdo


እናመስግነው በአንድነት መሰዋትም ነውና
በመዝሙር እናወድሰው ይገባዋልምና
ከመላክት ጋር ባንድነት ከፃድቃን ጋር ሆነን
ቅዱስ ቅዱስ እንበል እናመስግን ስሙን
@GlorytoGod_Bot
. 🔷
🔷
🔶🔸🔶
🔷
🔷
🔷
https://telegram.me/https:/mezmur_z_tewahdo

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ (Amharic)

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ (Mezmur Z Tewahdo) በአማርኛ በዜናዊ መዝሙር ታሪኬችን አማርኛ ውስጥ ያንጸባረቃል፣ የካቲት መዝሙር ትዕቢት ከሚከተለው መንደር በተመለከተ እናስታውሳለን። በምርጫ እና ለበለጠ መልዕክቶች፣ መቼም ተጠቃሚ እና በእቃዎች መቀጣጠል አስፈላጊ ሆኑ። ከእንግዲህ እንችላለን: መዝሙር ዘ ተዋሕዶ ለሆዋ ምህረት ሳልበል፣ ስለሆዋ ስለ መነቅልህል፣ መዝሙር ዘ ተዋሕዶ የአንድ ህግ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር፣ መሠረት፣ ማብራሪ፣ የአባቶች ላይ እና በከልተኛ ብሄራዊነት መና አስተማሪ፣ የእግዚአብሔርን ኃያሉን ውሃውን በቃል አስታውሱ።

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

02 Jan, 14:22


https://www.youtube.com/live/YYYN803BN9s?si=kWVDnHKcM7Usk-hd

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

30 Dec, 12:39


ናሁ ሰማናሁ በኤፍራታ

ናሁ ሰማናሁ በኤፍራታ/2/


በኤፍራታ ኧኸ
በኤፍራታ ኧኸ
ተወለደ ኧኸ
ያለም ጌታ ኧኸ
ከንፅህት ኧኸ
ከድንግል ኧኸ
ስጋን ነሳ ኧኸ
አማኑዔል ኧኸ
የሰይጣንን ኧኸ
ጥበብ ሊሽር ኧኸ
ሰው ሆነልን ኧኸ
እግዚዐብሄር ኧኸ

አዝ___

በኤፍራታ ኧኸ
በኤፍራታ ኧኸ
በኤፍራታ ኧኸ
በበረት ኧኸ
ተወለደ ኧኸ
መድሀኒት ኧኸ
ዘመሩለት ኧኸ
መላዕክት ኧኸ
ከእረኞች ጋር ኧኸ
በአንድነት ኧኸ

አዝ___

በኤፍራታ ኧኸ
በኤፍራታ ኧኸ
ጥበበኞች ኧኸ
ሊሰግዱለት ኧኸ
ኮከብ አይተው ኧኸ
ተከተሉት ኧኸ
ደስ አላቸው ኧኸ
ሲያገኙት ኧኸ
ሲቀበሉ ኧኸ
በረከት ኧኸ

አዝ__

በኤፍራታ ኧኸ
በኤፍራታ ኧኸ
አቀረቡ ኧኸ
እጅ መንሻውን ኧኸ
ከርቤንና ኧኸ
ወርቅ እጣኑን ኧኸ
እመቤቴ ኧኸ
ደስ ይበልሽ ኧኸ
መዳኒቱን ኧኸ
ስለወለድሽ ኧኸ

አዝ__

በኤፍራታ ኧኸ
በኤፍራታ ኧኸ
በጨለማ ኧኸ
ለሚኖሩ ኧኸ
በመርገም ውስጥ ኧኸ
ለነበሩ ኧኸ
ብርሀን ወጣ ኧኸ
በእውነት ኧኸ
በምስራቅዋ ኧኸ
እመቤት ኧኸ

አዝ_

በኤፍራታ ኧኸ
በኤፍራታ ኧኸ
ድምፅ ተሠማ ኧኸ
በበረቱ ኧኸ
ሲዘምሩ ኧኸ
መላዕክቱ ኧኸ
ዛሬም እኛ ኧኸ
እንደነርሱ ኧኸ
ዘመርንለት ኧኸ
በመቅደሡ ኧኸ

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

30 Dec, 12:35


❤️ወዳንቺ የመጣው ❤️

ወዳንቺ የመጣው በብሩህ ደመና
ከሶስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና
የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ
ባንቺ ተፈጸመ የሰው ልጆች ደስታ

በደይን የተጣለች ሄዋን ተደሰተች
የደስታ መፍለቂያ አንቺን ስላገኘች
የበረከት ፍሬ ካንቺ ተገኘልን
የወይን ቦታ ነሽ ድንግል እናታችን

ወልድም ባህሪሽን ባህሪይ አድርጎት
ለፍጥረታት ጌታ ባህሪይሽ ተስማምቶት
ካንቺ ይወለድ ዘንድ ፍጹም ሊላላክሽ
በጥቂት አደገ ተልኮና ታዞሽ

ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሃሊብ
በሩካቤ ሳይሆን በብስራት እንደንብ
ከሆድ መጥበብ ጋራ የመለኮት ስፋት
አንቺ ሆነሽ ሳለሽ ታናሿ ሙሽሪት

በፍጡር ህሊና የማይመረመር
እጹብ ነው ድንቅ ነው የመጽነሷ ነገር
እሳት ነበልባል በሆድሽ ወስጥ ሲያድር
ነደ ነበልባሉ አልፈጀሽም ነበር

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

29 Dec, 06:03


https://www.youtube.com/live/0RKV3eHknoo?feature=shared

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

25 Dec, 05:53


https://www.youtube.com/live/LF3KvHBi2UQ?feature=shared

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

21 Dec, 03:16


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ታህሳስ 12(፲፪)

✟ የታላቁ ኢትዮጵያዊ መናኝ ገዳማዊ
የእመቤታችንንም ውዳሴዋን ሲደግሙ ክንድ ከስንዝር ያህል ከምድር ከፍ ይሉ የነበረ የዱር አራዊትም ሁሉ ይገዙለት ጻዲቅ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እረፍታቸው ይዘከራሉ።✞

👉አቡነ ሳሙኤል ጻድቁ የተወለዱት በአክሱም ጽዮን ነው፡፡ ነገዳቸው የአክሱም ገበዝ ከነበረው ከጌድዮን ነው፡፡ የአባታቸው እስጢፋኖስና እናታቸው አመተ ማርያም ምግባር ሃይማኖታቸው የቀና ትሩፋት ተጋድሏቸው የሰመረ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡
👉 አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ገና በ12 ዓመቱ ማይ ሹም በተባለው ባሕር ገብተው ሲጸልዩ ባሕሩ በብርሃን ተከቦ ይታይ ነበር፡፡ ከባሕር ወጥተው ወደ ቤ/ክ ሲገቡ ካህናት የእኛ ኃጢያት ታይቶት ነው?ወይስ ምን ኃጢያት ኖሮበት ነው እያሉ ያደንቁ ነበር።
👉ምግብ አይቀምስም ነበር ይልቁንም የሚሰጡትን እንጀራ ለሕጻናትና ለውሾች እየሰጠ ቅጠል ይመገብ ነበር፡፡

እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን አስተምረውና አመንኩሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አባት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡

አባቶች ታሪካቸውንና የጽድቅ ሕይወታቸውን አስታውሱት፡-
እነርሱም
➨አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣
➨ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣
➨አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣
➨አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣
➨አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣
➨ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና
➨ አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ

አቡነ መድኃኒነ እግዚእ እነዚህን ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን ደብረ በንኮልን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡

እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት የጣናን ባሕር በእግራቸው ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን ደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው ወደ ደሴት የገቡ አሉ፡፡ በእግራቸውም እየረገጡ ባሕሩን የተሻገሩ አሉ፡፡ በሌላም ቦታ በየብስ የተሰማሩትም ቢሆኑ መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፡፡

አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባንም አመንኩሰው መርቀው ሲሸኟቸው እንዲያገለግሏቸው አንበሶችን ከጫካ ጠርተው ያዘዙላቸው አባታቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡
የዋልድባው አቡነ ሳሙኤል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ከመነኮሱ በኋላ በደብረ በንኮል 12 ዓመት አባታችንን ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ እሳት እስከማያቃጥላቸው ድረስ ከብቃት ደረጃ ላይ ሲደርሱ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ መርቀው በማሰናበት በዓት እንዲያጸኑ ሲያደርጓቸው አቡነ ሳሙኤል በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ጣና ደሴት ገብተው ሱባኤ ያዙ፡፡

ለአባቱም መምህር ሆኖ ልጁን ሳሙኤልን ተከትሎ ወደ እርሱ መጥቶ በአባ መድኃኒነ እጅ መነኮሰ፡፡ ዋሻ እየገባ ብዙ ጊዜ 40 ቀንና 40 ሌሊት በጾም በጸሎት እየኖረ እንቅልፍም እንዳያሸንፈው። አባታችን አባ ሳሙኤል በሕይወተ ሥጋ ሳለ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን አድርጓል፡፡
፦ እንደሙሴ ባሕርን የከፈለበት ጊዜ አለ
👉በልዑልም ዙፋን ፊት እየቀረበ ከቅዱሳን መላእክት ጋር የሚያመሰግንበት ጊዜ አለ፣ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይም ጋር ሆኖ የሚያጥንበት ጊዜ አለ፤
👉 በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ሆኖ ከእነ ቅዱስ ጴጥሮስና ከሁሉ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ጋር በአንድ ላይ ማዕድ የሚቀርብበት ጊዜ አለ።
👉 እመቤታችንንም ሲያመሰግናት ከምድር ወደ ላይ አንድ ክንድ ያህል ከፍ የሚልበት ጊዜ አለ፤ በቤትም ውስጥ ሆኖ ምስጋናዋን ሲጀምር የቤቱ መሠረት እየተናወጠ ዝናብ እንደያዘ ደመና ቤቱ ከምድር ከፍ ብሎ
👉አባታችን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ መቅደስ በሚገቡ ጊዜ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ይወርድላቸው ነበር፡፡
👉የእመቤታችንንም ውዳሴዋን ሲደግሙ ክንድ ከስንዝር ያህል ከምድር ከፍ ይሉ ነበር፡፡ እመቤታችንም እየተገለጠች ንጹሕ ዕጣንንና የሚያበራ እንቁን ሰጥታቸዋለች፡፡

👉አባ ሳሙኤልን የዱር አራዊትም ሁሉ ይገዙለት ነበር፡፡ ታላቅ የሆነ ዘንዶ፣ ነብር፣ ጅብ፣ ቶራህ፣ ዝሆን፣ አንበሳና ሌሎችም የዱር አራዊት ሁሉ እየመጡ እግሩን እየላሱት ወደ ቦታቸው ይመለሱ ነበር።
ጌታችንም ተገልጦ እንዲህ አላቸው
👉ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፣ ደስ ይበልህ፡፡ በጥቂቱ የታመንህ ባሪያዬ ሆይ በብዙ እሾምሃለሁ፡፡ እኔን በመውደድ ብዙ ደክመሃልና የመስቀሌንም መከራ በመሸከም እኔን መስለሃልና እኔም በመንግሥቴ መልካም የሆነውን የድካምህን ዋጋ እሰጥሃለሁ፡፡ እነሆ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የተካከለ መቀመጫህንና አክሊልህን አዘጋጀሁልህ፣
👉 ዕድል ዕጣህም ከአሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያቶቼ ጋር ነው፡፡ አፅምህ በተቀበረበት፣ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት፣ መታሰቢያህ በተደረገበት፣ ሥፍራ ሁሉ ምሕረትና ድኅነት ይሁን፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👉
በጸሎትህ የሚታመነውን፣ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ ለአንተ አሥራት ሰጥቼሃለሁ፡፡ ስለ እኔ የተቀበልከውን ድካም ሁሉ ዛሬ ያገኘኸውን የአንዲት ቀን የደስታ ልክ አይሆንም
ረድኤታቸው በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር!!!

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

19 Dec, 12:58


አይሰለቸኝም ከቶ

አይሰለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚአብሄር በዘመኔ2×

                 አዝ://

ቸርነትና ፍቅሩን ያላራቀ ከባሪያው
ከለመለመ ስፍራ ልጆቹን ሚያሠማራው
ታራቅ ነው የኛ ንጉስ ታላቅ ነው የኛ ጌታ
መፅሀፉን የዘረጋ ማህተሙን የፈታ

                 አዝ://
አንገቱን ፍፁም ደፍቶ ቀና አንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በህይወት አቁሞኛል
አልችልም የሡን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ዉለታውን ለመግለፅ የለኝም ብርቱ ቃላት

                  አዝ://
ያንተ ክንድ የማይንደው ተራራ ጋራ የለም
ወጥቻለው ከጥልቁ ታላቅ ነህ ዘለአለም
የተከፈተ ደጃፍ ሠተኸኛል ከፊቴ
ተመስገን ክበርልኝ ንገስልኝ አባቴ

                  አዝ://
ለይተህ የጠራኸኝ ያበዛህልኝ ፀጋ
ትዝታዬ ነህ ጌታ ሲመሽና ሲነጋ
ወዳጅ እና ዘመዴ ብዬ ስጠራህ ልኑር
እየሡስ የእግዚአብሄር ልጅ ለወጠኝ ያንተ ፍቅር

                       አዝ://
አንገቱን ፍፁም ደፍቶ ቀና እንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በህይወት አቁሞኛል
አልችልም የሡን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ዉለታውን ለመግለፅ የለኝም ብርቱ ቃላት

                     አዝ://

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

19 Dec, 12:57


እንዴት ተገኘህ እኔ ቤት

እንዴት/፪/ብለህ ተገኘህ እኔ ቤት/፪/
እንዴት አልሰለቸህ መተኛት ከበረት/፪/እንዴት


አበሰሩን መላእክቱ ተወለደ ሂዱ እያሉ
ግርግም መሃል ተጠቅልሏል የምስራች ለአለም ሁሉ
ተነስቼ ገሰገስኩኝ ከበጎች ጋር ከበረት
የማይንቀኝ መድሃቱን አይኔ አየችው በሊሌት

ቀና ስል ከሰማይ ኮከብ ይመራኛል
የፍቅሩ መዓዛ ልቤን ይጠራኛል
እንደ አጭሩ ቀራጭ ሾላ ላይ ብወጣ
ከቤቴ ሊገባ መምህሩ መጣ እንዴት

አዝ-----------

ፈሪሳዊው ቢጸየፈኝ አመንዝራ ቀራጭ ብሎ
አልፎኝ ሲሄድ ያ ሌዋዊ ተጸይፎ ተነጥሎ
አግሬን ሲያጥብ ተመልከቱ በኔ ምትክ ሲሰቀል
ይሄን ብርቱ ፍቅር እዩ አለም ሁሉ ጉድ ይበል

ቀና ስል ከሰማይ ኮከብ ይመራኛል
የፍቅሩ መዓዛ ልቤን ይጠራኛል
እንደ አጭሩ ቀራጭ ሾላ ላይ ብወጣ
ከቤቴ ሊገባ መምህሩ መጣ እንዴት

አዝ-----------

እኔ ማን ነኝ የምትገባ ከጣሪያዬ ከቤቴ ስር
እሰማለሁ እድናለሁ ጌታዬ ሆይ ቃል ተናገር
አቴርሳታ የኔ ገዢ የኑሮዬ የመንገዴ
የማይቀሙኝ በጎ እድሌ እኔ ባንተ መውደዴ

ቀና ስል ከሰማይ ኮከብ ይመራኛል
የፍቅሩ መዓዛ ልቤን ይጠራኛል
እንደ አጭሩ ቀራጭ ሾላ ላይ ብወጣ
ከቤቴ ሊገባ መምህሩ መጣ እንዴት

                  

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

19 Dec, 12:52


አይሰለቸኝም ከቶ

አይሰለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚአብሄር በዘመኔ2×

                 አዝ://

ቸርነትና ፍቅሩን ያላራቀ ከባሪያው
ከለመለመ ስፍራ ልጆቹን ሚያሠማራው
ታራቅ ነው የኛ ንጉስ ታላቅ ነው የኛ ጌታ
መፅሀፉን የዘረጋ ማህተሙን የፈታ

                 አዝ://
አንገቱን ፍፁም ደፍቶ ቀና አንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በህይወት አቁሞኛል
አልችልም የሡን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ዉለታውን ለመግለፅ የለኝም ብርቱ ቃላት

                  አዝ://
ያንተ ክንድ የማይንደው ተራራ ጋራ የለም
ወጥቻለው ከጥልቁ ታላቅ ነህ ዘለአለም
የተከፈተ ደጃፍ ሠተኸኛል ከፊቴ
ተመስገን ክበርልኝ ንገስልኝ አባቴ

                  አዝ://
ለይተህ የጠራኸኝ ያበዛህልኝ ፀጋ
ትዝታዬ ነህ ጌታ ሲመሽና ሲነጋ
ወዳጅ እና ዘመዴ ብዬ ስጠራህ ልኑር
እየሡስ የእግዚአብሄር ልጅ ለወጠኝ ያንተ ፍቅር

                       አዝ://
አንገቱን ፍፁም ደፍቶ ቀና እንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በህይወት አቁሞኛል
አልችልም የሡን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ዉለታውን ለመግለፅ የለኝም ብርቱ ቃላት

                     አዝ://

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

10 Dec, 14:58


https://www.youtube.com/live/LPfM9ceg_Cg?feature=shared

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

08 Dec, 16:39


💫የታህሳስ ወር አመታዊ በአላት

ቅዳሜ 1 - ነብዩ ኤልያስ - እንጦጦ ኤልያስ

ሰኞ 3 - በአታ ለማርያም - 4ኪሎ በአታ
ማርያም እና አብነ ዜና ማርቆስ በአለ እረፍት

ሀሙስ 6 - ቅድስት አርሴማ - የቅድስት አርሴማ ታቦት ባለበት ሁሉ

ቅዳሜ 8 - አባ ኪሮስ - ጣፎ

ማክሰኞ 11ቅዱስ ያሬድ ፦ አጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር የሚወስደው መንገድ

ረቡዕ 12 - አባ ሳሙኤል - አልታድ ሚካኤል፣ ቡልቡላ አባ ሳሙኤልእና አቃቂ አባ ሳሙኤል ቤተ ደናግል

ሀሙስ 13 - ሩፋኤል - ሸጎሌ

እሁድ 16 ፍቅርተ ክርስቶስ - ፈረንሳይ ጉራራን አለፍ ብሎ በአንቆርጫ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን


ረቡዕ 19 ፦ ቅዱስ ገብርኤል  የቅዱስ ገብርኤል ታባት ባለበት እና አባ ሰላማ በንብ ሚካኤል

ቅዳሜ 22 :.ብስራተ ገብርኤል፦ሳር ቤት   
ብስራተ ገብርኤል ቤ/ክ

ሰኞ 24.ተክለሐይማኖት፦አሉላ.መርካቶ...

ማክሰኞ 25 ኖላዊ ኄር በደብረ ምህረት አፍሪካ ህብረት.

አርብ 28 .አማኑኤል፦መሳለሚያ

ቅዳሜ 29 .ባለወልድ፦4ኪሎ፣ ለቡ አብርሀሙ ስላሴ

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

03 Dec, 14:10


https://www.youtube.com/live/HLR-MeVP7CM?si=08_QThKzVx5LKRsN

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

03 Dec, 05:50


https://www.youtube.com/live/rd_1mLN_x5I?feature=shared

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

01 Dec, 05:21


https://www.youtube.com/live/1cHK1QFsp28?si=ycQa7R4cnzfjq0ol

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

17 Nov, 11:39


https://www.youtube.com/live/d_v2bhuBm8c?si=CNn9lGzZhAHo9JWe

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

06 Nov, 04:31


https://www.youtube.com/live/c1f464WgW6o?si=8w2bUk2UtoLlN71H

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

05 Nov, 20:00


https://www.youtube.com/live/b9g4AYCXCrI?si=Q8FBZcXpKhLPCkaY

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

05 Nov, 15:09


https://www.youtube.com/live/3_8Vbmg6rtQ?si=erZQGeCthTEgoFqs

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

02 Nov, 20:06


https://www.youtube.com/live/rA_x7RaVfiU?si=h_7XPfvL1BPHmjmo

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

01 Nov, 05:57


https://www.youtube.com/live/SLSN0uA9_ag?si=9gcy7DvrXQLjDkI3

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

24 Oct, 05:25


https://www.youtube.com/live/b3M5DV-fJFE?si=s_qPg9ux0CSHUaSi

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

19 Oct, 17:50


https://www.youtube.com/live/z6rXWvAMmx8?si=C4ARAD_3zqsiuf6O

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

17 Oct, 06:10


https://www.youtube.com/live/BdvNB8Xs7jw?si=ntAm6A12-qVK5_Lz

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

16 Oct, 11:57


https://youtu.be/yd92dmoRyUc?si=h_1U_W5nJREHa_lX

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

08 Oct, 19:30


Live streem ቀጥታ https://www.youtube.com/live/Q-fsNfVEOhU?si=FHyqAZfAafd6WS3T

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

05 Oct, 20:19


https://www.youtube.com/live/MIKAc-unGEs?si=6DDrybjoQXs16waA

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

25 Sep, 21:29


https://www.youtube.com/live/DTepFqjM1Bc?si=5jVV3eiV-pcNYpnY

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

19 Sep, 20:47


https://www.youtube.com/live/up-MZKz8DOE?si=M7pU9LS7HGW3GRt0

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

19 Sep, 20:35


ጼዴንያ ማርያም✞

ጼዴንያ ማርያም(፪)
ታላቅ ነሽ ዘለዓለም(፪)
ክብርሽም ገነነ በዓለም

ገስግሼ መጣሁኝ - - - ንዒ ድንግል
ማለዳ ቤትሽ - - - ንዒ ድንግል
ዝክርሽን አስቤ - - - ንዒ ድንግል
ቀስቅሶኝ ፍቅርሽ - - - ንዒ ድንግል
      አዝ= = = = =
እንደ አባ ቴዎድሮስ - - - ቅዱስ ስዕልሽ
እንደ ደጓ ማርታ - - - ቅዱስ ስዕልሽ
ነፍሴ ተደሰተች - - - ቅዱስ ስዕልሽ
ስዕልሽን አይታ - - - ቅዱስ ስዕልሽ
      አዝ= = = = =
ሽፍታው ክንዱ ዛለ - - - በአንቺ ብርሃን
አንበሳው ተረታ - - - በአንቺ ብርሃን
በአስፈሪው በረሃ - - - ንዒ ድንግል
አዛኝቷ መጥታ - - - ንዒ ድንግል
      አዝ= = = = =
ሉቃስ የሳላት - - - ቅዱስ ስዕልሽ
ስመኛት ነበረ - - - ቅዱስ ስዕልሽ
ዛሬ ተሳለምኳት - - - ቅዱስ ስዕልሽ
ሀሳቤ ሰመረ - - - ቅዱስ ስዕልሽ

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

19 Sep, 03:55


መስከረም 10 - ጸዴንያ ማርያም

እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምትወድና በሚቻላትም ሁሉ የምታገለግላት፣ ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ መነኮስ ከእርሷ ዘንድ በእንግድነት አድረው በማግሥቱ ከቤቷ ሲወጡ ማርታ የሚሔዱበትን አገር በጠየቀቻቸው ጊዜ እርሳቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው ቅዱሳት መካናትን እንደሚሳለሙ ነገሯት፡፡ ማርታም ከእርሷ ገንዘብ ወስደው የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተው ይዘውላት እንዲመጡ ለመነቻቸው፡፡ መነኵሴውም በራሳቸው ገንዘብ ሥዕሉን ገዝተው እንደሚያመጡላት ቃል ገቡላት፡፡

አባ ቴዎድሮስ ኢየሩሳሌም ደርሰው ቅዱሳት መካናትን ከተሳለሙ በኋላ ሥዕሏን ሳይገዙ ወደ አገራቸው ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ?›› የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰምተው ተመልሰው መልኳ ያማረና የተወደደ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ገዝተው በሐርና በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ይዘው እየተጓዙ ሳሉ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ሲደርሱ ወንበዴዎች ተነሱባቸው፡፡ሊሸሹ ሲሉም ‹‹መንገድህን ሒድ››የሚል ቃል ከሥዕሏ ወጣ  መነኵሴውም መንገዳቸውን በሰላም ተጓዙ፡፡ ሁለተኛም አንበሳ ሊበላቸው በተነሣባቸው ጊዜ ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረላቸው፡፡

አባ ቴዎድሮስ ይህን ኹሉ ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜም ያቺን ሥዕል ለማርታ ከመስጠት ይልቅ ወደ አገራቸው ሊወስዷት ወደዱ፡፡ በመርከብ ተሳፍረው በሌላ አቅጣጫ ሲሔዱም ታላቅ ነፋስ ተነሥቶ ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያ ወሰዳቸው፡፡ ከመርከብም ወርደው ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ደረሱ፡፡ ነገር ግን ማንነታቸውን ለማርታ አልገለጡላትም ፤ እርሷም አላወቀቻቸውም ነበር፡፡

በማግሥቱም ተሠውረው ወደ አገራቸው ሊሔዱ ሲሉ የቅፅሩ ደጃፍ ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ዋሉ በመሸባቸው ጊዜም ወደ ማደሪያቸው ተመለሱ፡፡ ማታ ማታ በሩን ያዩታል፤ ነግቶ መሔድን ሲሹ ግን የበሩ መንገድ ይሠወርባቸዋል፡፡ እንዲህም ኾነው እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቆዩ፡፡ ማርታም ‹‹አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን? ስትቅበዘበዝ አይሃለሁና ምን ኾነህ ነው?›› ሰትል ጠየቀቻችው፡፡ እርሳቸውም ከእመቤታችን ሥዕል የተደረገውን ተአምር ሁሉ ነገሯት፤ ራሳቸውንም ገለጡላትና ሥዕሏን ሰጧት፡፡ እርሷም የእመቤታችንን ሥዕል ተቀብላ የተጠቀለለችበትን ልብስ በፈታችው ጊዜ ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች፡፡ ከደስታዋ ብዛት የተነሣም የአባ ቴዎድሮስን እጃቸውንና እግራቸውን ሳመች፡፡ ሥዕሏም ቅዱስ ሉስ የሳላት ነበረች፡፡

ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር አኖረቻት፡፡ ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት፡፡ በቀንና በሌሊትም የሚያበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች፤ ከመቅረዞች ውጭም የሐር መጋረጃን ጋረደች፡፡ ከሥዕሊቱ በታችም እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች፡፡ እኒያ መነኰስም እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገሉ ኖሩ፡፡

የአገሩ ሊቀ ጳጳስም የእመቤታችን ሥዕል ሥጋ የለበሰች ሆና ባገኙና ተአምሯንም በተመለከቱ ጊዜ ከዚህ አምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ፡፡ ከሥዕሏ ከሚንጠባጠበው ቅባት ቀድተው ለበረከት ሲካፈሉም ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ መላ፡፡ ሥዕሊቱን ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜም ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ፡፡ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያች አገር በጸዴንያ ትገኛለች፡፡

እመቤታችን ኢትዮጵያን ሰላም ታርግልን አሜን

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

19 Sep, 03:53


የፀደኒያ ስመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም

ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ አቅጣጫ በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ አስተዳደር የምትገኘው የፀደንያ ስመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም በ1955 አ.ም የተመሠረተች ሲሆን ቤተክርስቲያኗን የመሠረቷት እማሆይ ስመኝ ተክሉ ይባላሉ፡፡እማሆይ ስመኝ በመናገሻ አምባ ማርያም በእመቤታችን ማርያም ስም ቤተክርስቲያን ለማሠራት አስበው
ለቤተክርስቲያኑ ማሠሪያ ገንዘብ እና የሚከራይ 6ክፍል ቤት ሠጥተዋል፡፡
በኅላም የነበረው ገንዘብ በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ በብፅዕ ወቅዱስ አቡነ
ባስልዮስ የመጀመሪያው ፓትርያርክ መልካም ፈቃድ ቤተክህነት ተጨማሪ ገንዘብ በጅቶ አሁን ላይ ያለው ህንፃ ቤተክርስቲያን ተገንብታል፡፡
የገዳሙ መጠሪያ ፀደንያ ስመኝ
ገዳሟን በመሠረታት እማሆይ ስመኝ ተክሉ ስም እንዲሆን በብፅዕ ወቅዱስ አቡነ
ባስልዮስ እንዲሆን በማሠብ ህንፃ ቤተክርስትያኑ ተገንብቷል፡፡
በዚህ ገዳም በየአመቱ መስከረም 10ቀን (መስከረም 10 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው) ጸዴንያ ማርያም ይባላል፡፡ 

ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ ገባ፤
ታሪኩ እንዲህ ነው የግብጽ ንጉስ ክርስቲያኖችን እንደሚያሰቃይ እና
ጳጳሱ አቡነ ሚካኤልን እስርቤት እንደከተታቸው አጼ ዳዊት
ሰሙ፤ጦራቸውን ወደ ግብጽ አዘመቱ ሱዳን ሲደርሱ ግን አንድ ነገር
ታሰባቸው፤አባይ ወንዝን መገደብ የዛኔ ለህይወቱ ሲል ጳጳሱን ይፈታቸዋል
ብለው አሰቡ አስበውም አልቀሩ ካርቱም ላይ አባይን ገድበው ወደ
በርሃ እንዲፈስ አደረጉት፤በዚህ ጊዜ የግብጽ ንጉስ ጳጳሳሱን ለቀቀ
ክርስቲያኖችንም ነጻ አወጣ፤ ይባሱን አጼ ዳዊት ይቅርታ
እንዲያደርጉለት የኢየሩሳሌም የሮም የአርመንና
የቁስጥንጥንያን ነገስታት ማለደ ደብዳቤም በተነ፤ለአጼ ዳዊት ብዙ
ወርቅ እጅ መንሻ አቀረበ፤ አጼ ዳዊትም ወርቅ አልፈልግም ይልቅስ
የጌታዬን መስቀል ስጠኝ ይሉታል፤ እርሱም መስቀሉን ብቻ ሳይሆን
ሌሎች ነዋያተ ቅድሳትን ጨምሮ ሰጣቸው፤መስከረም 10 ቀን
ኢትዮጰያ ገባ፤ ይህ ቀን አጼ መስቀል ተብሎ ይከበራል። መስከረም 21
ግሸን ያረፈበት ቀን ነው።
የእናታችን የድንግል ማርያም ረድኤት በረከቷ አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሄር

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

18 Sep, 19:19


ዩትዩብ ሰብስክራይብ አድርጋችኋል ግን¿¿ link 👈ንኩት በታማኝነት

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

14 Sep, 04:15


የመስከረም ወር የንግሥ በዓላት

መስከረም 1  -ቅዱስ ራጉኤል - በእንጦጦ ራጉኤል ወ ኤልያስ እና መርካቶ - በወይራ አርሴማ እና አጨጌ ዮሐንስ

መስከረም 2  - መጥምቁ ዮሐንስ - በቤተል ማርያም - በቦሌ መድኃኔዓለም እና ዮሐንስ መጥምቁ በአለበት ሁሉ

መስከረም 6  - ቅድስት አርሴማ -በአቃቂ አባ ሳሙኤል ቤተ ደናግል ገዳም

መስከረም 7 - ቅድስት ሐና - በኮተቤ ሐና እና በፉሪ(ቀለበት ሐና)

መስከረም 10 -ፀደንያ ማርያም - ቡራዩ

መስከረም 16 - ቅድስት ኪዳነምህረት - በጎፋ ካምፕ

መስከረም 17 - ቅዱስ እስጢፋኖስ

መስከረም 18 - አቡነ ኤዎስጣቴዎስ - በሰሚት ኮንዶሚኒየም በበዓታ ማርያም ቤተክርስቲያን

መስከረም 21 - እመቤታችን

መስከረም 24 - አቡነ ጎርጎርዮስ - ከቦሌ ሚካኤል አጠገብ

መስከረም 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም - ቅዳሴ ቤቱ - በአለም ባንክ - ትሮፒካል

መስከረም 29 - ቅድስት አርሴማ

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

11 Sep, 01:31


https://www.youtube.com/live/-yZ6yMsWNGU?si=NSgkcMkA6ry7TdWB

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

07 Sep, 05:35


https://www.youtube.com/live/WT6-VGw_tCM?si=XnhDHTeWGhkMQHy2

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

05 Sep, 05:05


https://vm.tiktok.com/ZMrEvDRaS/

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

02 Sep, 17:03


https://vm.tiktok.com/ZMrKu2NjF/
copylink share እያደረግን ለህዝበ ክርስቲያን በሙሉ እናድርስ።

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

01 Sep, 12:40


የሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ወዳጅ የሆናችሁ በሙሉ መልእክቱን ለወዳጆቻችሁ አጋሩልን

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

01 Sep, 12:37


https://vm.tiktok.com/ZMrwTGPjA/

መዝሙር ዘ ተዋሕዶ

31 Aug, 06:27


ደብረ ሊባኖስ
https://vm.tiktok.com/ZMrwh5Lf3/
https://vm.tiktok.com/ZMrwh5Lf3/
https://vm.tiktok.com/ZMrwh5Lf3/
የዓመት ሰው ይበለን
እሁድ ደግሞ በጋራ ጻድቁ ሃብተ ማርያምን እናከብራለን የሰንበት ሰው ይበለን።

4,526

subscribers

158

photos

12

videos