♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂 @yekeberedaha Channel on Telegram

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

@yekeberedaha


♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂 (Amharic)

ልዩ የፍቅር እና ጨዋታ ቻናል የተከለከለ ነው። በዚህ ቻናሉ የፍቅርና ጨዋታ መረጃዎችን እና የብልጽግና እንቅስቃሴ እናምርጧል። በዓለም ላይ እና በየአቅጣጫ እንዲሁም በእኩልነት እጋብዛለን። ይህ ቻናል ላይ በተነሳሱ የፍቅርና ጨዋታ እና የሴቶችን መፅሀፍ ይከብራል። የተለያዩ እውነቶችን በቻናሉ ማስፈጸም እና ማስተካከል እንደሚችለው ከቻናሉ ላይ መጠን ይችላሉ። የፍቅር እና ጨዋታ ቻናሉን እባክዎ ይግባ።

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

13 Jul, 10:42


በጥፋቱ የሚኮራ ሰው በበዛ ቁጥር እንደማህበረሰብ ለሃዘን መቀመጥ አለብን!

ብቻ በማያኮራው የሚኮሩ፥ በነውር ማጌጥ ቁም ነገር የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ።

🌹 🌹 🌹 🌹 🌹 🌹 🌹

ለመቀላቀል👉 @yekeberedaha

ለአስተያየት 👉 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

11 Jul, 17:20


​​🌺♦️ምኞት♦️🌸

💠ክፍል አስራ ስድስት  ((16))🍃🍃



አንብቦ እንደጨረሰ ፅናት አጠገብ መጥቶ እየተቀመጠ•••
"ፅናት እህቴ " አላት እንባ ባቀረሩ አይኖቹ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ እያያት " ወዬ ሚኪዬ" አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ እሱ ተጠጋች " እኔኮ ከሀዲ እና እምረባ ሰው ነኝ ልህልቴን ጎድቻታለሁ
ችኩል ባህሪዬ ፍቅሬንም ደስታዬንም አስጥቶኛል። ሰው ሆኜ ተፈጥሬ አውሬ ያደረገኝ ምን ይሆን ፅኑዬ? አንቺ እና ብሩኬ የማታውቁት ለራሴም ከቶ ያልገባኝ ሌላ የአውሬነት ባህሪ አለኝ
ፅኑዬ ለበደልኩት በደል ቅጣቴን ዛሬ መቀበል ጀምሪያለሁ ግን ቅጣቴ የረዘመ እና የበደልኳትን ይቅርታ ጠይቄ የማይፈታ እንዳይሆን ፀልይልኝ ፅኑዬ! እኔም የማላውቀው ሌላ ማንነቴ
በፈፀመው በደል አንቺም እኔም የምናውቀው ትክክለኛው ማንነቴ
እየተቀጣ ነው። ሰው እንዴት መንፈሱን የሚያጠግብ የፍቅር ረሀቡን ገፍቶ ለግዚያዊ እና ለስሜታዊ የስጋ ረሀቡ ቅድሚያ ይሰጣል ። የኔ መማር እና ትልቅ ቦታ መድረስ ስሜቴን ለመግዛት
ተው ተረጋጋ እሄ ልክ አይደለም በማለት ለፀፀት ከሚዳርግ መንገድ መቆጠብ ካልቻለ የእውቀት ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው።
ዛሬ አውቃለሁ ተምሬአለሁ እያሉ አካሄዳቸው ሁሉ ለስተት እና
ለፀፀት ከተጋለጡ እውቀታቸው ጭንቅላታቸው ላይ ሳይሆን
በተሰጣቸው ሰርተፍኬት ላይ ብቻ ካስቀመጡ ሰዎች ተርታ መሰለፌን አረጋግጫለሁ። በዚህ ሁኔታ አልነበረም ስለምኛቴ ልነግራችሁ ያሰብኩት ግን ሁሉም የኔ ጥፋት ነው። አለና ስለምኛት
እና ስለሱ ያለውን እውነት ከጅምሩ ጀምሮ አወራላቸው።
" አይዞህ ሚኪዬ ሁሉም ነገር በግዜው ይስተካከላል አንተ ግን መረጋጋት አለብህ ልጅቷን የምታገኝበትን መንገድ ነገሮችን ዳግም የምናስተካክልበት መንገድ ማሰቡ ነው ሚሻለው ያለፈው
አልፋል ሚኪዬ" አለችው ። እስሩ ገብታ በስስት እያየችው ።
" ማስተካከል ያለብኝ እኔው እራሴ ነኝ ምኛቴን በሁለት ቀን
አሳቅቄ እንዳባረርኳት ከገባችበት ፈልጌ አመጣታለሁ። የኔ ምኞት ፣ የኔ ስስት ማንንም ስለማታውቅ ወደ ሀገሯ
ከመመለስ ውጪ የትም ልትሄድ አትችልም " ብሩኬ "የት ነው
ሀገሯ?" አለው ፅናትን ወደ ጎን እያየ " ድሬዳዋ ነው የትም ቢሆን
የኔን ልእልት ሄጄ ይቅርታ ጠይቄ አመጣታለሁ ሳልይዛት እንደ
ማልመለስ ቃል እገባለሁ" አላቸው።
ብሩኬ ቢያንስ ፅናት እንደማይሳካላት በማወቁ የሰማው ነገር
እጅግ አስደስቶታል።
" ግን ብሩኬ ደብዳቤው በምን ልካው ነው አንተ ጋር እንዴት ዛሬ ደረሠ ?" አለው ሚኪ ብሩክን ..... ደብዳቤው እጁ ላይ እንደቆየ ብታውቅም ማን ሰጠው እሚለው የፅናትም ጥያቄ ነበርና መልሱን ለመስማት ቀና አለች " ዛሬ እዛ
ኮንደሚንየም አረፍ ለማለት ሄጄ ነበር እዛ አስቀምጣልህ ነው የሄደችው ሳገኘው ከላይ አድራሻ ስላልነበረው ከፍቼ ሳነበው ነው ላንተ መሆኑን ያወኩት ወድያው ይዤልህ ምጣሁ አለውና " ቀድሞ
የተዛጋጀበትን ሚኪን ካጠገባቸው የማብረር ውሸት ነገረው ። ሄዳለች ማለት ነው የኔ ምኛት ነገሩ ሂጂ ብዬ ያባረርኳት እራሴ ማን አለኝ ብላ እዚህ ትቀመጣለች ።" ምናለ ምኛቴ ደብዳቤሽን
ከቁልፉ ጋር በትንሹ ልከሽልኝ ቢሆን ምን ነበረበት " አለና ብቻዬን
መሆን ስለምፈልግ እዚሁ ጠብቁኝ መጣሁ " ብሎአቸው ሲወጣ ።
ፅናት በብሩኬ ውሸት አንጀቷ ቢቃጠልም ምንም ማለት አልቻለችም ።
ልትከተለው ስትነሳ ብሩክ ተይው እስቲ ፅኑ ብቻዬን ልሁን አለኮ! አላት እጇን ያዝ አድርጎ። በብስጭት መንጭቃው ተመልሳ ቁጭ በማለት ወደ መሬት አቀረቀረች ።
ሚኪ እንደወጣ ብሩኬ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ፅናት ተጥግቶ ተቀመጠና " ይገርማል!" አለ ዝም አለችው " እውነቱን ለመናገር ለ ሁለቱም በጣም
አዝኛለሁ አለ" አሁንም መልስ አልሰጠችውም "እና ምን አሰብሽ
ፅኑ? እያለ በተደጋጋሚ ሲጠይቃት በንዴት••
"ዘወር አለችና " እሄውልህ ብሩኬ ፍቅር ማለት እኮ ካፈቀርነው
ሠው ጋር ለመሆን ከተሳካልን የምንቀጥለው ካልተሳካልን ደግሞ
የምናቆመው በኛ ቁጥጥር ስር ያለ መኪና አይደለም ሚኪን የማፈቅረው የኔ ስለሚሆን ብቻ ይመስልሀል ፍቅር ከመቀበል ይልቅ መስጠትን የተላበሰ ቅዱስ መንፈስ ነው ገባህ እሱ ሌላ
የሚያፈቅራት ሴት ስላለች ብቻ ጠላሁት የምልህ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል ስትለው አፈጠጠባት...

ክፍል 17 ይቀጥላል.........

አካውንቱን በአዲስ መልኩ እንድንጀምር ሼር በማድረግ ይተባበሩን @yekeberedaha

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

11 Jul, 17:09


በጥፋቱ የሚኮራ ሰው በበዛ ቁጥር እንደማህበረሰብ ለሃዘን መቀመጥ አለብን!

ብቻ በማያኮራው የሚኮሩ፥ በነውር ማጌጥ ቁም ነገር የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ።

ለመቀላቀል👉 @yekeberedaha

ለአስተያየት👉 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

11 Jul, 08:22


​​​♦️ምኞት

♠️ክፍል አስራ አምስት ((15))💞🍃


" ብሩኬ እኔ.......ኮ.....ሚኪን አ ፈቅረዋለሁ!!! ሥትለው ብሩክ
የራሱን ጆሮ ተጠራጠረው
"ም......ምን አልሽ ፅናት ምን...ድን ነው የሰማሁት" እየቀለድሽ
ነው ?" አላት እጅግ በሚያሳዝን አነጋገር
" እዉነቴን ነው ምነው? ግን ብሩኬ ደብዳቤውን አንብቦ ውሳኔውን
ሳናውቅ እባክህ አትንገረው አለችው ።
ሚኪ ይፈልጋታል ብሎ ከመጠራጠር ውጭ እሄን ያልተጠራጠረው
ብሩክ እንደ ነፍሱ የሚሳሳላትና ያፈቀራት ፅናት ጓደኛውን
እንደምታፈቅረው መስማት እጅግ አሳመመው ፅናት እንኳንስ እሱ
እንደሚያፍቅራት ልታውቅ ለደቂቃ ተጠራጥራም አታውቅም
የብሩኬ ድንጋጤ ግን አብራው በፍቅር ያለችና የሚያፈቅራት
ፍቅረኛው ከድታው ሌላ ሰው እፍቅሬአለሁ ብላ የነገረችው ያክል
ነበር ባንዴ ከሰው ባህሪነት ተቀይሮ እየተንቀጠቀጠ እፍጥጦ
እያያት ካፉ ባይወጣም በውስጡ ካሁን ቡሃላ ትልቁ ስራው
ሁለቱን በተቻለው መንገድ ሁሉ ህይወታቸውም ሲኦል ለማድረግ
እቅድ ምውጣት እንደሚሆን ለራሱ ቃል የገባው።
ፅናት እያየችው ሲለዋወጥ አስፈራት ምንም ሳትለው ከመኪናው
በመውረድ ወደ ወንድማ ጋር ሄደችና ተያይዘው ወደ ሸገር በረሩ።
አዲስ አበባ እንደገቡ ወድያው ተጣጥባ ልብሷን ቀየረችና ወደ
ሚኪ ቤት ሄደች ስትደርስ ሚኪ ከእንቅልፉ አልተነሳም ቀጥታ ወደ
መኝታ ክፍሉ ሄደችና የአልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣ ቀሰቀሰችው
ተገላብጦ ተነሳ
" ምነው እስከዚህ ሰአት ሚኪዬ?" አለችው
"ወዬ ፅናቴ መቼ መጣችሁ ደሞ ስልክሽ ዝግ ነው ቡሩኬስ እንዴት
ሆነ ከደብዳቤው በስተቀር ሀዋሳ የተፈጠረውን ሁሉ ነገረችውና "
ተነስ ታጠብ ሳሎን እጠብቅሀለሁ" ብላው ወጣች
ሣሎን ሳትቀመጥ ወደበረንዳው በመውጣት ቁጭ ብላ ከዚህ
በፊት ከሚኪ ጋር ያወሩትን ነገር አይኗን አንድ ቦታ ላይ ተክላ
ማስታወስ ጀመረች ........
አንድ ቀን ብቻቸውን ቁጭ ብለው ሲጨዋወቱ " ሚኪዬ እስከመቼ
ነው ግን በዚህ ትልቅ ቤት ውስጥ በብቸኝነት የምትኖረው"
ስትለው " ፅናቴ አንቺና ብሩኬ ለመደገስ ተዘጋጁ እንጂ ሳታስቡት
ነው የኔን ልእልት ድንገት በመምጣት እሄን ቀዝቃዛ ቤት የምታሞቀው" ይላትና ይስቃል።
ያኔ ከሚኪ ፍቅር የያዛት ግዜ ነበር አሁንም ትንሽ ግዜ ትጠብቅና "
ታድያ ያንተ ልእልት መቼ ነው እምትመጣው? ነው ገና
አልተወለደችም?" ትለዋለች ከልቧ እውነቱን ለማወቅ ፈልጋ
ቢሆንም እንዳይታወቅባት ቀልድ እያስመሠለች።
" እሁንማ ፅናቴ ሙች እውነቴን ነው መምጫዋ እየቀረበ ነው"
ይላትና እሱም ሳቅ ብሎ ወሬውን ያሳጥርባታል ።
እንደሚለው የሱ ልእልት የእውነት ካለች ላይሳካላት ፍቅሯን ነግራው ወንድምነቱን ፈፅሞ ማጣት አትፈልግም ነበርና ውስጥ
ውስጡን ስትብከነከን ቆየች።
ብሩኬ መንገዱን በሙሉ ተንኮል እና ሸር ሲበትን እና ሲሰበስብ
ሲዘራ እና ሲያጭድ አዲስ አበባ ደረሰ።
ፅናት ስልኩን አላነሳ ሲላት ሚኪ ቤት እየጠበቀችው እንደሆነና
እንደደረሰ እንዲመጣ መልእክት ብትልክለትም መጠጥ ቤት
ገብቶ እስከማታ ሲጠጣ ቆይቶ ብዙ ካሰበበት ቡሀላ ለራሱ
ተንኮል እሚመቸው ደብዳቤውን መስጠቱ ግድ እንደሆነ ወሰነና
ወደ ሚኪ ቤት አመራ።
እንደደረሰ ሁለቱም ውጪ በረንዳው ላይ ቆመው አገኛቸው ቀጥታ
ደብዳቤውን አወጣና ለሚኪ ሰጠው
"ምንድን ነው ብሩኬ?" አለ ሚኪ " ገብተህ ብታነበው አይሻልም"
አለው ምፀት ባዘለ አነጋገር ሚኪ ወደ ሳሎን ገብቶ ማንበብ ጀመረ።
ሚኪ ሳሎን ገብቶ ማንበብ እንደጀመረ ብሩክ ወደ ፅናት ጠጋ አለና
" ፅኑ በቃ ምን ነክቶኝ እንደሆነ ባላውቅም ጥዋት ልረዳሽ
ስላልሞከርኩኝ ይቅርታ የተፍጠረውን ነገር በሙሉ እርሽው በኔና
ባንቺ ይቀራል በይ ነይ አሁን እንግባ" አላትና ተያይዘው ወደ
ውስጥ ገቡ የውስጡን በውስጡ ይዞ የውሸት ፈገግታ እያሳያት ።
ቢሆንም ሚኪ ደብዳቤውን አንብቦ ሲጨርስ ምን እንደሚፈጠር
እስክታውቅ እጅግ ጨንቋት ሥለነበረ የብሩኬን ሁኔታ ለማንበብ
ግድ አልነበራትም
ሚኪ ቀና ሳይል ደብዳቤውን አንብቦ እንደጨረሰ እዛው እንዳቀረቀረ እሚለውን ነገር አጣ ምን እንደሚያረግ ወዴት
እንደሚሮጥ ግራ ገባው ትንሽ ቆየና ስልኩን በማውጣት ምኞት
ጋር ደወለ ስልኳ አይሰራም ሲም ካርዷን ሰብራ ከጣለችው ሁለት ቀን ሆኗታል...
.
ይቀጥላል... 
ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።

ለአስተያየት 👉 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

24 Oct, 15:53


​​​​♦️ምኞት♦️

♠️ክፍል 14

.
.
.
ምክንያት የማያልቅበት ብሩኬ እቃዉን እንዲያቀብላት ሊነግረው
ጓደኛው ጋር ሲደውል እናቱ ሞተው ሀዘን ላይ እንደሆነ ሰምቶ
ድንገት እንደመጣ ነገራት ባይዋጥላትም ለማንኛውም ምናልባት
ዋስ ካስፈለገ ብላ ሚኪ ጋር እንደደወለች ስትነግረው ፊቱ
ተቀያየረ "ምን ሆንክ?"አለችው••
እኔ ከቆይታ ቡሀላ እወጣለሁ ዋስ አያስፈልገኝም እሱ ጋር
መደወል አያስፈልግሽም ነበር " አላት ቀጠል አርጎም ሚኪ ከእሷ
እና ከሱ የደበቀውን ሚስጥር
እንደደረሰበትና በሚኪ በጣም እንዳዘነ ለሷም ከስር ቤት
እንደወጣ እንደሚነግራትና ሚኪ ምን ያህል ጨካኝ መሆኑን ስትረዳ
በእርግጠኝነት ለሡ ያላት አመለካከት እንደሚቀየር እያጋነነ አወራላት።
ስለሚኪ ጭካኔ ካንተ አፍ መስማቴን ማመን አልችልም እኔኮ
ጭንቅላቱን የተመታው ወንድሜ ብቻ ነበር የመሰለኝ ለማንኛውም
ስትወጣ ደውልልኝ " ብላው ካጠገቡ ሄደች ።
ማታ እራሷን እንዳመማትና ሁሉንም ነገር ስገናኙ እንደሚያወሩ
ብሩኬም ስለተፈታ መምጣት እንደሌለበት ለሚኪ ደውላ
ስትነግረው እባክሽ የጓደኛዬን ድምፅ አሰሚኝና ልረጋጋ ሲላት እኔ
ከወንድሜ ጋር ነው ያለሁት እሱ አጠገቤ የለም ብላ ስልኩን
ዘጋችና"አይ ሚኪዬ ጓደኛ አግኝተህ ሞተሀል አንተ ድምፁን ልስማው ትላለህ እሱ ድምፅህን ለማጥፋት ይሯሯጣል ።
አለች ለራሷ።
ፅናት ከንቅልፋ እንደነቃች ሞባይሏን አንስታ ሰአት ተመለከተች
ከጥዋቱ 2:30።
ዛሬ ጥዋት ወደ አዲስ አበባ ለመብረር ትኬት ቆርጠው ነው
ያደሩት ። ወንድሟ ወደ ተኛበት ክፍል በመሄድ ቀሰቀሰችው "
ተነስ ተዘገጃጅ 3:30 ላይ እኮነው በረራው ተነስ " ብላ
ቀሰቀሠችውና ወደክፍላ ተመለሰች።
ሚኪ ከተፈታ ቡሀላ ሊያገኛት ፈልጎ ቢደውልም ሁኔታው
ስላልጣማትና ስለሚኪ መጥፎ ነገር መስማት ስላልፈለገች
ስልኩን አላነሳችለትም።
ከወንድሟ ጋር ከሆቴሉ ሲወጡ የብሩክን መኪና ራቅ ብላ
ቆማለች።
ሰውየሽ በጥዋት መጥቶ ተገትሮልሻል ።
አላት ወንድሟ። ጥሎቦት ብሩኬን አይወደውም።
እንዴ እንደውም እስከ አየር ማረፊያው እሱ ይሸኘናል" መኪና
ይዘን እንምጣ ስልሽ ይቅር ያልሽው እሱ እንዲሸኘን ነው እንዴ "
እኔ በዚህ ሰውዬ መኪና መሄድ አልፈልግም" አላት ወንድሟ
ጥሎበት ብሩክን አይወደውም " እሺ በቃ ቻው ብየው ልምጣ"
በማለት ብሩክ ጋር ሄዳ በመኪናው መስኮት ተሰናብታው ልትሄድ
ስትል "ነይ ግቢ እንጂ ስለ ሚኪ እነግርሻለሁ ያልኩሽን ልንገርሽ
አላት ስለ ሚኪ እነግርሻለሁ ያልከኝ ምን ነበር ብላ ስላልጠየቀችው ተናዶ " አዲስ አበባ አይደርስም? አስቸኳይ
ነው?" ስትለው ይበልጥ "አዋ መኪና ውስጥ ግቢ ብዙም አትቆይም"አለ መስማት ባለመፈለጓ ይበልጥ ውስጡ እየተቃጠለ።
ወንድሟን ዘወር ብላ አየችውና መኪና ውስጥ ገባች ወድያው
ምኞት ለሚኪ የፃፈችለትን ደብዳቤ አወጣና ሰጣት ትንሽ
እንዳነበበች እምባዋ ደብዳቤው ላይ መንጠባጠብ ጀመረ።
ብሩክ ግራ ተጋባ "እቺ ልጅ ልጅቷ በመጎዷቷ ነው ወይስ ሚኪ
ሌላ ፍቅረኛ እንደነበረው ማወቋ ነው ለማንኛቸው ነው እምታነባው? አለ በውስጡ። ፅናትን በስስትና በትኩረት
እየተመለከታት የለቅሶዋ ምክንያት ግን አንደኛው ብሩኬ እንዳሰበው አዝናላት
ቢሆንም ሁለተኛው ግን ብሩኬ በህይወት እያለ መስማት የማይፈልገውና የሦስቱን ግኑኝነት ዳግም ላይመለስ ሊያፈራርሰው
የሚችል ነገር መሆኑን አልጠረጠረም እንደጨረሰች " አንተ ግን
እንዴት ሳያነበው እዚህ ይዘህ ትመጣለህ" አለችና ከነ እምባዋ
አፈጠጠችበት.....
ብሩኬ ያልጠበቀው ጥያቄ ስለነበር ተደናገጠ " እሱ ምን ለውጥ
አለው ልጅቷ እኮ ወደ መጣችበት ሄዳለች ደሞ ስደውልለት
አያነሳም ከዛ ያው ታውቂያለሽ እኔም አጋጣሚ ነው እዚህ የመጣሁት " አለ " ለውጥማ ሊኖረው ይችል ነበር ሚኪ በዚህ ሳምንት ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ትናንት ስላንተ ልነግረው
ስደውል ነው የተረዳሁት እሄ ደብዳቤ ቶሎ ቢደርሠው እራሱን በፀፀት ከሚጎዳ ወይ ሀሳቡን ሊቀይር ይችል ነበርኮ " አለች በተቆራረጠ ድምፅ።
ብሩክ ሁኔታዋን ለመረዳት ተቸገረ " ቆይ ፅኑ እስቲ ተረጋጊና ንገሪኝ የልጅቷ ነው ወይስ የሚኪ መጎዳት ነው ያሳዘነሽ እሄ እኮ እኛ ሳናውቅ ብቻውን የፈፀመው ነገር ነው " አላት።
" እኔ .......እኔ...........እኔ" አለችና በመኪናው መስታወት ወደ
ወደ ውጪ አይናን ወርውራው ተተክላ ቀረች።
" አንቺ.....አንቺ ምን...." እላት ብሩኬ ልትናገር ያሰበችውን
ለማስማት ከመቸኮሉ የተነሳ ቃሏን በግድ ፈልቅቆ ያስወራት
ይመስል አገጯን ቀና እያረጋት "የልጅቷንም ህይወት እንዲበላሽ
በፍፁም አልፈልግም ግን ስለ ሚኪ ደግሞ ከዚህ ሁሉ ግዜ ቡሀላ
የመጨረሻውን እውነቱ የማውቅበት ግዜ ሥለሆነ...." ብላ ዝም
አለች።
የምን እውነት ነው እምትይው እውነቱ እጅሽ ላይ ያለው ደብዳቤ
አይደል እንዴ እሡ በደፈናው አንድ ቀን ንግሥቴን ልእልቴን
ሣታሥቡት ነው እዚህ ቤት ይዣት የምመጣው ከማለት ውጪ
ምን ነግሮን ያውቃል አሁን ደሞ እሄው እውነቱን አወቅነው !"
ሲላት
" የእውነቱ መጨረሻ ግን እሄ አይደለም ገና አለየለትም" አለችው
ጮክ ብላ
" ታዲያ ከዚህ ውጪ ምን እውነት አለ ያችን ሚስኪን አምጥቶ
ሜዳ ላይ ጣላት እሷም የስንብት ደብዳቤ ፅፋ ወደ መጣችበት
ሄዳለች "
ፅናት " ግን ሚኪ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም እያልኩህ እኮ ነው
ብ..ሩ..ኬ ያለውን ስሜት ዛሬ እንደገባን እሄንን ደብዳቤ
ሰጥተነው ካነበበ ቡሀላ ብቻ ነው ልናውቅ የምንችለው ያኔ እኔም
ቁርጤን አውቄ ውሳኔውን በማክበር ከጎኑ እሆናለሁ" ስትለው
ብሩክ ከመደንገጡ የተነሳ ጉሮሮውን እሚያረጥብበት ምራቅ
አጠረው "ምን....ምን..አልሽ ፅናት ስለምን ቁርጥ ማወቅ ነው
እምታወሪው አንችን ደግሞ ከዚህ ጋር ምን አገናኘሽ!" አላትና በጭንቀት ወደ እሷ ጠጋ ብሎ መልስን ይጠባበቅ ጀመር
እምባ ባቀረሩ አይኖቿ ዝም ብላ አይን አይኑን እያየች ዝም አለች
በሁለት እጁ ግራና ቀኝ ትከሻዋን ይዞ " ንገሪኝ ፅኑ ምንድን ነው"
እያለ አወዛወዛት
" ብሩኬ እኔ.......ኮ.....ሚኪን አፈቅረዋለሁ!!!
" ብሩኬ እኔ.......ኮ.....ሚኪን አፈቅረዋለሁ!!! ሥትለው ብሩክ
የራሱን ጆሮ ተጠራጠረው
"ም......ምን አልሽ ፅናት ምን...ድን ነው የሰማሁት" እየቀለድሽ
ነው ?" አላት እጅግ በሚያሳዝን

🌺ክፍል 15 ♥️ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍 ማድረግ አይርሱ።

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

21 Oct, 18:31


​​​​♦️ምኞት♦️

♠️ክፍል 13

.
.
.
ሮጣ እታች እንደደረሰች እሷ ካለችበት ቀጥሎ ባለው
ኮንደሚንየም ጨለማ ውስጥ ግድግዳ ተደግፋ በመቆም ትንፋሽ
ወስዳ ከተረጋጋች ቡሀላ ወደላይ ቀና ብላ አየች መብራቱ
እንደጠፋ ነው ።
" ማን ይሆን ውስጥ ያለው የውጪ እገር ዜጋም ይመጣል እንዴ
ወይ ፈጣሪ ! " አለች በሩን ልትከፍት በምትሞክርበት ወቅት
"ማነው? ካለ ቡሀላ ያወራው ምን እንደሆነ በደንብ ባይሰማትም
ከአነጋገሩ ግን ኢትዬጲያዊ እንዳልሆነ ገምታ።
"አሁን የት ላድር ነው " አለችና ሸርተት በማለት እግሮቿ ላይ
ተቀመጣ ማሰብ ጀመረች።
በቅርብ ወዳለ ቤተ እምነት ለመሄድ አስበች። ግራ መጋባትና
ፍርሀት ውስጥ እንደተዋጠች እዛው ጭለማ ውስጥ ተቀምጣ
አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ወደ ግራ ደሞ ወደ ላይ በየተራ
እየተመለከተች ቆየች።
በመሀል ካቀረቀረችበት ቀና ስትል እሷ ተደብቃ ከምትኖርበት ቤት
መብራት ሲበራ ተመለከተች ወድያው በሩ ተከፍቶ አንድ ወጣት
ሴት ወጣች ብዙም ሳይቆይ አንድ ወንድ ተከትሏት ወጣና
ተመልሶ በመግባት መብራቱን አጥፍቶ ብዙ ሞባይል ብርሀን በሩን
ቆለፈ "እየወጡ በሆነ አምላኬ" አለች ወደላይ እንዳንጋጠጠች ...
ጨለማው ውስጥ እንዳደፈጠች እታች እስኪደርሱ መጠባበቅ
ጀመረች ከተወሰኑ ሠከንዶች ቡሀላ አንድ አጭር ወፍራም
ቻይናዊና አንዲት ኢትዬጲያዊት ወጣት በአጠገቧ እያወሩ አለፉ ...
ልጅቷ ውብ ነገር ነች ቻይናዊው እየተኮላተፈም ቢሆን አማርኛ
ያወራል ልጅቷ ዛሬ ባትችልም በሚቀጥለው ተዘጋጅታበት
በመምጣት እንደምታድር ለቻይናዊው ቃል ስትገባለት ሰማች ።
እንደሄድ " ወይ ጉድ እስቲ ባልጠፋ ቦታ ሴቶቹን እየጎተቱ እዚህ
ማንም እማይደርስላቸው ቦታ እሚያመጧቸው የሆነ ተንኮል
ቢያስቡ ነው እንጂ እሄ የተሻለ ቦታ ሆኖ አይደለም መቼስ" አለች
ምኞት ልጅቷ ሳምንት መጥቼ አድራለሁ ስትል በመስማቷ ከወዲሁ
ስጋት ገብቷት...
" እይ ሚኪ" አለች ቤቱን እምንጠቀምበት እኔና ሁለት ጓደኛቼ ነን
ብሏት እንደነበር እስታውሳ ወድያው ሚሞሪውን የሰረቀችው
ሰውዬ ቁልፍ ከአንዱ ወደ ሌላው እየተቀባበለ እዚህ ቤት
የሚመጣው የሰው ብዛት እንደማይታወቅ ለቀጭኗ ልጅ ሲነግራት የሰማችውን ትዝ አላትና እውነቱን ያወራው እሱ
እንደሆነ እያሠበች እሁንም ውስጥ የቀረ ሌላ ሰው እንዳይኖር በሚል ውስጧ ፈራ ተባ እያለ ደረጃውን ወጥታ ጨረሰች ።
በሩ ጋር እንደደረሠች ትንሽ ቆማ ካዳመጠች ቡሀላ አመሠግናለሁ
ያገሬ ልጅ ለማደር ብትስማሚ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር እያለች
ከፍታ በመግባት ክፍሎቹን አየት አየት አድርጋ ወደ እቃ ቤቷ
በመግባት ተጠቅልላ ተኛች ።
ፅናት ከወንድሟ ጎን እስከ እሁድ ሆስፒታል ቆየች እሁድ
ከጥዋቱ 3:00 ላይ ከእንደወጡ ወንድማን አልጋ ወደ ያዙበት
ሆቴል አድርሳ ብሩክ ወደ ታሠረበት ፖሊስ ጣብያ እየሄደች
ምናልባት ለመለቀቅ ዋስ ከተጠየቀ ብላ በማሰብ ወደ መኪ
ደወለች....
ሥልኩን በማንሳት " "ሄሎ ፅናቴ እንዴት ነሽ " አለ ሚኪ "ወይኔ
ጉዴ አሞሀል እንዴ ሚኪዬ " አለች ድምፁ እንደሰማች "
አላመመኝም ፅናቴ " አለ ሰሞኑን በተከታታይ የጠጣው መጠጥ
ባደከመው ድምፁ " ሚኪዬ ዝርዝሩን አሁን አትጠይቀኝ ሀዋሳ ነው
ያለነው ። ወንድሜ በፀብ ምክንያት ተጎድቶ እሁን ከሀኪም ቤት
መውጣታችን ነው ብሩኬ እዚህ ታስሯል።
የሚለቁት ይመስለኛል ነገሩን ካከበዱበትና ዋስ የሚያስፈልገው
ከሆነ መልሼ እደውላለሁ ቻው "ስትለው •••
ሚኪ በመደናገጥ " እንዴት በምን ምክንያት እዛ እንዴት ሄደ"
በማለት የሸሸችውን መልስ የሌለው ጥያቄ አክተለተለባት።
እደውልልሀለው ብቻ ብላ ስልኩን ከመዝጋት ውጪ መልስ
አልነበራትም ። ብሩኬ ወንድሟ ሲጣላ ፀቡ ውስጥ ድንገት
ከመከሰቱ ውጭ ሌላው ለሷም እንቆቅልሽ ነበርና።
ሚኪ ወድያው ከተኛበት በመነሳት ለጓደኛው ሊደርስለት
በመዘጋጀት የፅናትን ስልክ ቢጠባበቅም እስከ ማታ አልደወለችም
ቢደውልም ስልኳ ጥሪ አይቀበልም። ለጓደኛው እጅግ ከመጨነቁ
የተነሳ እስከማታ የመፈታቱን ዜና ካልሰማ በጥዋት ሊሄድ ወሰነ።
ፅናት እሥር ቤት ብሩኬን እንዳገኘችው እንዴት ሀዋሳ መጥቶ እዛ
ሆቴል ውስጥ ሊከሰት እንደቻለ በጥያቄ ታጣድፈው ጀመር....

............ይቀጥላል..........

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

20 Oct, 18:12


​​​​😘ምኞት😘

ክፍል 12
.
.
ከመደንገጡ የተነሣ ሥልኩን እንሥቶ እየደወለ ልብሡን
ሣይለብሥ ከቤት ሊወጣ ዳዳው ልጅታ ሥልክ አ አታነሣም
ደግሞ መከረላት አነሳችው.....
"በሂወት መኖር ካልፈለግሽ በሥተቀር የራሥሽን ቪድዮ አጥፍተሽ
ሚሞሪውን ብትመልሺ ይሻላል!" አላይ•••
ግራ ገባት "የምን ሚሞሪ" አልችው እምታላግጥበት መሠለው
በሷ ባህሪ ማሥፈራራቱ እንደማያዋጣው እሥቦ " እየውልሽ የኔ
ወፍ እኔ በፍፁም አንቕችን የመጉዳት ሀሳብ የለኝም በቃ የራሥሽን
አጥፊና ሌሎቹን ግን በጣም የምፈልጋቸው የግል ነገሮች ሥለሆኑ
እባክሽ መልሽልኝ አንቺ አድርግ ወይም ክፈል በይኝ ብቻ ደሥ
ያለሽን ነገር እቀጣለሁ"
ሢላት..
የበለጠ ግራ ብትጋባም ከሁኔታው ግን የሆነ ነገር እንደተፈጠረ
እየተጠራጠረች " እኔ ሥለ ምን እንደምታወራ አላውቅም ብላ
ሥልኩን ዘጋችና ምናልባት ከኔ ለመደበቅ ኪሡ አሥቀምጦት
ወድቆ ጠፍቶበታል ምለት ነው" "ጠፍቶ በቀረ!" አለች።
"ሠውየው ግራ ተጋባና ማታ ሠክሬ ሥለነበር ቦታውን ተሣሥቼ
ይሆን እንዴ? " ብሎ ምንጣፉን እየገላለጠ መፈለግ ጀመረ የለም።
ቀጭና ልጅ አንድ የሴት ጒደኛዋ ጋር ለመሄድ ታክሢ ውሥጥ ነች
ሂሣብ ለመክፈል ዝርዝር ፈለጋ የቦርሳዋን ኪሶች ስትበረብር
በወረቀት የተጠቀለለውን ነገር አገኘችና ግራ በመጋባት ገላልጣ
ሥታየው ወይኔ ጉዴ ብላ ጬኸቷን አቀለጠችው ታክሲ ውስጥ
ያሉት ግራ በመጋባት ሲገላምጧት ወራጅ አለችና ሳትደርስ ወርዳ
ወደ አንድ ካፌ ገባችና ሚሞሪውን ስልኲ ውስጥ በማስገባት
የሷን ጨምሮ ብዙ ሚስጥሮችን ተመለከተችና ጭንቀታ ሁሉ
እንደጉም በኖ ሲሄድ ታወቃት በሱ ቤት ምናልባት ጥዋት በግዜ
አትነሣም ብሎ እኔ እማልጠረጥርበት ቦታ ደብቆ ጥዋት ጥዋት
ሊወሥድ እሥቦ ነበር አለችና ሥልኲን አንሥታ ደወለችለት።
ስልኩን ወድያው ነበር ያነሳው አንተ ዝሆን ፈጣሪ ሀያል ነው እጄ
ላይ ጣለህ ደሞ ሚጣ ትሙት ትላለህ ልጅህን ብትወድ ኖሮ
የልጅህ እኩያ ከምትሆን ሴት ጋር እያስፈራራህ ባልተጋደምክ ነበር
እሄን ጉድህን ለዛች ብሯን አይተህ ለምታገባት እጮኛህ በስጦታ
መልክ እልክላታለሁ ብላው ስልኩን ዘጋችው ።
እባክሽ አትዝጊው ቆይ እንነጋገር እያለ በሩን ቆልፎ እየተጣደፈ
ሢሄድ ምኛት ሚሞሪውን ወሥዳ ጥላው ቢሆን ኖሮ ልጅታ
መጥፋቱን ብትሰማም ከሠቀቀን እንደማትድን አሥባ ቦርሳዋ
ውስጥ ለመክተት በወሠነችው ውሳኔ እንደ ህፃን ልጅ በመዝለል
ጮቤ ረገጠች••
ደስታዋን አጣጥማ እንደጨረሰች ወጣ ብላ ቁርስ ቢጤ
በመግዛት ከቀማመሠች ቡሀላ ለሊቱን ሣትተኛ ሥላደረች ገላዋን
ታጥባ ተኛች።
ከቀኑ 11 ሰአት ከ 40 ደቂቃ ሆኗል ንፋስ ለመቀበል ከቤት
ወጣች ከኮንደሚንየም የሚያሥስወጣውን ዋና አሥፓልት በመያዝ
ቁልቁል ወደ ቀለበት መንገድ ሄደችና ፊቷን ወደ ደብረዘይት
መውጫ አድርጋ ብዙ ከተጓዘች ቡሀላ ስትመለስ ዛሬም እዛ ቤት
ሌላ ባለታሪክ እንዳይይመጣና በሰላም እንድትተኛ ፈጣሪዋም
እየተማፀነች ሰፈሯ እንደደረሰች ድሬ ድሬ በማለት የሚጣራ የሰው
ድምፅ ሰምታ ዘወር ከማለታ የሆነ ባጃጅ አጠገባ ደርሶ ቀመ
ወድያው ነበር ያወቀችው ባለፈው እቃ ለመግዛት የወሰዳት ባጃጅ
ሹፌር ነበር አንተ እንዴት ነክ አለሁልሽ ጠፋሽ እኮ የገዛሽው
አስቤዛ ካላለቀ ከቤት አትወጭም እንዴ አላት ፈገግ አለች
ሰላምታ ከተለዋወጡ በሃላ ኬት እየመጣች እንደሆነ ጠየቃት ኬት
እንደምትመጣና አሁን ግን ወደ ቤት ልትግባ እንደሆነ ስትነግረው "
በይ ነይ ግቢ እሷን አድርሰናት እሸኝሻለሁ አላት አንድ ወፈርራምና
ክብ ፊት ያላት እጭር ወጣት ሤት ጭኗል ምኛት ባጃጁ ውስጥ
ገባች።
ተሳፋሪዋ መውረጃዋ ደርሶ ወረደችና ከያዘችዉ ትልቅ ቦርሳ
ውስጥ የመጣችበትን ሂሳብ ለመክፈል ብር በመፈለግ
ስለቆየችበት " አልታይ ካለሽ ለምን መብራቱን አታበሪውም?"
አላት "የምኑን?" አለች ተሳፋሪዋ "የቦርስሽን ነዋ መብራቱ ጠፍቶ
ነው ዛሬ ተረኛ ነሽ እንዴ "? የምን ተራ ? አለች ይበልጥ ግራ
በመጋባት ማለቴ መብራት በፈረቃ አደል ከዚህ ቤት ከሚያህል
ቦርሳሽ ብር ፍለጋ ስትደናበሪ ተረኛ ሆና መብራት ጠፍቶ ካልሆነ
ለምን አታበራውም ብዬ ነው ወይ ባትሪ ልስጥሽ እንዴ ሲላት
እንኳን ለኔ ቦርሳ ላንተም ኩርኩር መብራት አላስፈለጋት እቤት
ውስጥ የተሰቀለው መብራት ንፋስ ውስጥ እንደለኮሱት ሻማ
እየተስለመለመ ተቸግረናል! ጭራሽ ቦርሳሽ መብራት የለውም
ይላል እንዴ ! ቀልደኛ !ለከፋ መሆኑ ነው? ብላ ስትንጣጣበት ።
አረ የምን ለከፋ ለጎፋ ነው ስሚ እኔ ጥዋት ካላየኋት ቀኑን ሙሉ
የሚያፋሽገኝ ምርጥ ፍቅረኛ አለችኝ እሷን በሳምኩበት አፌ አንቺን
መልከፍ አይከብድም ሲላት •••
ወሬ አለብህ ዝም ብለህ የጫንካትን ሸኝ "ሆሆ..." ብላ ሂሳቡን
ወርውራለት ስትሄድ ምኛት ያፈነችውን ሳቋን ለቀቀችው•••
"አንተ ምን አርጊ ነው ምትላት?" አለችው ሳሳቋ መሀል
"አላየሽውም እንዴ የያዘችውን ቦርሣ ከመሸ ቡሀላ ከውሥጡ ብር
ለማውጣት እኮ ወይ መብራት ወይ ባትሪ ያሥፈልግዋል ለመሆኑ
እሄ ቦርሣ ምን እንደሚባል ታውቂያለሽ?" አላት ወደ ምኛት ፊቱን
አዙሮ "ያው የሴት ቦርሣ ነዋ ደሞ ሌላ ምን ይባላል" አለች ምኛት
እየሳቀች " ስንት አይነት የሴት ቦርሳ አለ አንዳንዶቻቹማ ቤቱን ከነ
ሙሉ እቃው አይደል እንዴ ይዘው የሚንቀሳቀሱት ለማንኛውም
እሄ አሁን ልጅታ የያዘችው አይነት ቦርሳ ባለ ባለሶስት መኝታ ቤት
ኮንደሚንየም ይባላል" ሲላት" አቦ አታብዛዋ አንተ ደሞ !
እየሳቀች። እስቲ ድገሚው አሁን ያልሽውን አፍሽ ሲጣፍጥ አላት።
ሂድ ወደዛ ሀይይ! አለችው።
ምኛትን ሢሸኛት ሠአቱ 2: 20 ሆናል ተደብቃ ወደ ምትኖርበት
ኬንደሚንየም ለመግባት ቁልፏን አንገቷ ላይ ጣል ከረገቻት ሻርብ
ጫፍ ላይ ነበርና ያሰረቻት ቋጦሮውን እየፈታች በሩ ላይ ደርሳ
ለመክፈት ስትሞክር ቤቱ ከውሥጥ ተቆልፎ ቁልፍ ሥላልተነቀለ
አልከፈት ብሏት ስትታገል ማነው የሚል የተኮላተፈ የወንድ ድምፅ
ከውሥጥ ሠማች አመዳ ቡን እለ ወድያው በሩ ከመከፈቱ በፉት
ጫማዋን አውልቃ በእጃ በመያዝ ቁልቁል ከነፈች..

🌺ክፍል 13 ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍 ማድረግ አይርሱ።

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

19 Oct, 06:51


​​​🔷ምኞት🔹

♠️ክፍል 11


.
.
.
ሚሞሪውን ከደበቀ ቡሀላ በፍጥነት ወደ ቦታው በመመለሥ
"እሄው አጥፍቼልሻለሁ አንቺ ነዝናዛ ወፍ " አላት ሻወር ቤት በር
ላይ ሆና ገላዋን እያደራረቀች " እሥቲ ማል"? አለችው " ሚጣ
ትሙት አጥፍቼዋለሁ" ሚጣ ፈረንጆቹ አገር እያለ የውለዳት ሤት
ልጁ ነች። እሥቲ አለችና ሞባይሉን ተቀብላ ያሉትን ቪድዮዋችና
ፎቶዋች በየተራ እያየች ምንም እንኳን ውጪ ብዙ ግዜ ብትቆይም
ኢትዮጲያዊ ነህ እሄ ነገር በኖርክበት አገር ምንም ማለት ላይሆን
ይችላል እዚህ ግን ኢትየጲያ ነው ሰው ከምንም ነገር በላይ
ለራሡ እና ለሀገሩ ክብር አለው እንደዚህ አይነት ነገር ደግሞ
የአንድን ሠው ክብር ብቻ አይደለም የሚያቆሽሸው" ሥትል እፍፍፍ
ፍልሥፍናሽን ተይን እንግዲህ" አለና ወደ ሽንት ቤት መሄድ
ሲጀምር እውነቴን ነው እናንተም ብትሆኑ የክብርን ጣእም
የምታጣጥሙት በሀገራችሁ ነው ከምንም ነገር በላይ ደግሞ
አባቢ እሄን ነገር ቢያውቅ አንተንም እኔንም ከመግደል ወደ ሃላ
አይልም ነገሩ እሡ በዚህ ነገር ቀሥሙ ሢሠበር ከማይ ሞቴን
እመርጣለሁ" አለች በሚያሣዝንና በሚያባብል የንግግር ቃና።
ምኛት ሠውየው ወደ ሽንት ቤት ሢገባ ተክለ ሠውነቱን በደንብ
አየችውና "እሄ አሣማ " አለች ከተደበቅሽበት ውጭና እነቂው
እነቂው የሚል ሥሜት እየተናነቃት ሢመለሥ ልጅታ አሁንም
ሞባይሉ ላይ ነች በቃ እንተኛ ግን ዛሬ ባለፈው እምቢ ያልሽኝን
ነገር ማረግ አለብን አለብን" ሢል
እባክህ እንድዛ አይነት ነገር አድርጌም አላውቅም ማረግም
አልፈልግም አታሥገድደኝ" አለች አይን አይኑን እያየች " ምንድን
ነው ቆይ ያ አፈቅረዋለሁ አገባዋለሁ የምትይው ፍቅረኛ ተብዬሽ
ወጣ ያለ ነገር አያሣይሽም እንዴ"? አላት እያላገጠ
እሱ ለሤት ልጅ ፍቅርም ክብርም ያለው ንፁህ ኢትዮጲያዊ ነው
እንደ አንተና መሠሎችህ በባእድ ሀገር እሥነዋሪ ድርጊቶች
አልተመረዘም "
አገጯን ይዞ ቀና እያረገ ምን ምን ፍቅር ክብር ደሞ እሄ ወይ
ገንዘብ የለው ወይ ንቃት የለው ደሀ ደሞ እሡ ለምን ተነካ ነው
እምታፈጭብኝ " አለ በውሥጡ ቆይ ያንን ቪድዮ ልኬ
እገላግልልሽ የለ አለና የፌዝ ሣክ ሣቀባት
ተብከነከነች የቪድዮው ነገር ይዛት እንጂ ልጅታ በቀላሉ
እምትበገር እይደለችም "እናንተ ብር ያላችሁ ምን አረጋችሁ
በብራችሁ ሀይል በሚሥኪኖች ሥቃይ ከመደሠትና የሠይጣንን
ፍላጎትና እቅድ ከማሥፈፀም ውጪ "
ሥትለዉ "አንቺ ያባቷ ልጅ !! አለና ባንድ እጁ አንገቷን ባንድ እጁ
ሁለት እግሯን በመያዝ ከተቀመጠችበት ብድግ አድርጎ
ከተሸከማት ቡሀላ ወደ ምኝታ ቤት ይዟት በመግባት ንዴት እና
እልሁን ይወጣባት ጀመር።
ምኛት ሠውነታን ውርር አደረጋት ሠውነታቸው ከፍራሽ ጋር
ሢፋተግና ትንፋሻቸው ሢቆራረጥ ይሠማታል ልጅታ ከአቅሟ በላይ
እንደሆነባት የምታወጣው የታፈነና የተጨነቀ ድምፅ ይመሠክራል
ምኛት ከዛ በላይ ቆማ መሥማት አልቻለችም ወደ ፍራሻ በመሄድ
ጆሮዋን ይዛ ተቀመጠች ።
መሥማት የሌለባትን ነገር በመሥማታ የጥፋተኝነት ሥሜት
ተሠማት ግን እዛ ቦ ታ ላይ የተገኘችዉ ተጥላ እና ተገፍታ እንጂ
ፈልጋ አልነበረም መርጣ ሣይሆን አማራጭ ሥላልነበራት ነበር
ተከፍቶ በማያውቅ እና በተረሣ ጭለማ ቤት ውሥጥ የምትኖረው

ከለሊቱ 8: 30 ሆኗል የቀጭና ልጅ ትንፋሽ ባይሠማም ሰውየው
ግን እያንኮራፋ ነው ምኛት ከተደበቀችበት እቃ ቤት በጥንቃቄ
ወጣች የሳሎኑ መብራት አልጠፋም ቀጥታ ሚሞሪው ከተደበቀበት
ካነሣች ቡሀላ ቆም ብሏ በማሠብ በሠከንዶች ውሥጥ ምን
ማድረግ እንዳለባት ወሠነችና ሶፋው ላይ የተቀመጠውን የልጅታን
ቦርሳ ከፍታ ሚሞሪውን ውሥጡ በማረግ ብ
በጥንቃቄ ወደ ክፍላ በመመለሥ ተኛች።
ሰውየው ማታ መጠጥ አብዝቶ ሥለነበር ለመሽናት ተነሥቶ ወደ
ሽንት ቤት ሢሄድ..
ተነሥቶ ወደ ሽንት ቤት ሢሄድ ምኛት ወድያው ነበር የሠማችው
ፍርሀት ሥላለበት በደንብ እራሣን ጥላ አልተኛችም "አምላኬ ሆይ
አውጣን አለች ሢመለሥ ሚሞሪው አለመኖሩን ካየ ምን ሊፈጠር
እንደሚችል እያሠበች።
ቀስ ብላ ተነሣችና ለማንኛውም ብላ ያሥቀመጠችውን ርዝመቱ
አንድ ሜትር የሚሆን ወፍራም ዱላ አንሥታ በመያዝ ወደ በሩ
ተጠጋች ሢያጣው አምጪ ይላታል፡ አልወሠድኩም ሥትለው
ቢያንቃት ማንም እንደማይደርሥላት አሠበችና "መቸሥ ሢገላት
ዝም አልልም ለሁለት አያቅተን" እያለች ወደ እቃ ቤቱ በር
ተጠጋች።
ሠውየው አይኑን እንኲን በአግባቡ ሣይገልጥ ነበር ሽንቱን ሸንቶ
ወደ መኝታው የተመለሠው ወድያው ማንኮራፋቱን ቀጠለ።
ቀጭና ልጅ ጥዋት መነሣት እንደማትወድ ሥለሚያውቅ ሢነሣ
እንደሚያገኛት እርግጠኛ ቢሆንም ልጅታ ግን ቀድማ የሥልኲን
ማንቂያ በጣም ዝቅተኛ በሆነ ድምፅ ከጥዋቱ 12፡30
እንዲቀሰቅሳት ሞልታው ሥለነበር ገና ማቃጨል ሢጀምር ተነሥታ
ማንቂያውን ካጠፍች ቡሀላ ማታ የሠውየውን ሥልክ ሥትፈትሽ
ሚሞሪ እንዳልነበረው አሥተውላ ሥለነበር "እሥቲ ዝም ብዬ
ከምወጣ ምናልባት ብላ" የሠውየው ልብሶች ኪሥ ውሥጥና
የሶፋውን መቀመጫዎች እያነሣሣች ብትፈልግም ሥላጣች " በቃ
የለውም ይሆናል ሣይነሣ ብሄድ ይሻላል" አለችና ቦርሣዋን
አንሥታ በሩን ቀሥ ብላ በመክፈት ተፈተለከች።
ምኛት ሠውየው ሢያንኮራፋ ሥለሚሠማት የወጣችው ልጅታ
እንደሆነች እርግጣኛ በመሆኗ ጋደም ካለችበት ቀና ብላ
በመንበርከክ ፈጣሪዋን አመሠገነች።
ከእንቅልፉ ብንን ሢል ከጥዋቱ 2:30 ሆኗል አጠገቡ አለመኖሯን
አሥተዋለና ቀና ብሎ ማታ እያወለቀ ያሽቀነጠረውን የልጅታን
ልብሥ መሬት ላይ ፈለገ ልብሣም የለም እንዴት ነው ዛሬ
በጥዋት የነቃችው እያለ ተነሥቶ ወደ ሣሎን ሚሞሪውን ወደ
አሥቀመጠበት በመሄድ ምንጣፉን ገለጠው በድንጋጤ አድሮበት
የነበረው ሥካር ለቀቀው....

..........ይቀጥላል........

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

16 Oct, 13:47


​​😘ምኞት😘

♠️ክፍል 10

.
.
.
ሚኪ ከትንሹ አጠገብ ወዳለው መሥስኮት ሄደና ወደ ውጪ
እየተመለከተ እኔኮ እማረባና እራስ ወዳድ ሠው ነኝ አለና አቀረቀረ ።
ትንሹ ሚኪ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ምኞት ደብዳቤ
ልካ እንደነበርና ብሩክ ጋር እንደሆነ መናገር ፈራና ቁልፉን
ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦለት ወጣ። እቤት ገብቶ ቢተኛም ሚኪ
ሥለ ምኞት የጠየቀውን ጥያቄዎችና፡ ፊቱ ላይ ያየውን የፀፀትና
የጥፋተኝነት ስሜት ግን መርሳት አቃተው።
ምኞት እሥከ ቅዳሜ ጠዋት ብትጠብቀውም ሚኪ አልደወለም
ተሥፋ ቆረጠች ሞባይላን በመውጣት
ያቀደችውን በሙሉ አደረገችው።
ዛሬ ቅዳሜ ሥለሆነ ሠው ሊመጣ እንደሚችል እያሠበች እቃ
ቤቱን በመዝጋት እዛው ቤት ውድጥ
የነበረ አንድ ተጀምሮ ያላላቀ ግማሽ ከረጢት ስሚንቶ ጎትታ
በማሥደገፍ ቀኑን ሙሉ የሰው ኮቴ እያዳመጠች ሥትጨነቅ
ብትውልም የመጣ ሰው የለም ።
መሸ ልክ ከምሽቱ 5፡15 ሲሆን እንቅልፍ ሸለብ እንዳረጋት በሩ
ውስጥ ቁልፍ ሲገባ ድምፅ ሰማችና ተመንጭቃ በመነሳት
በጭንቀት እቃ ቤቱ በር ላይ ተለጥፋ ስታዳምጥ አንድ ጎርነን ያለ
ድምፅ ያለው ወንድ ሲያወራና አብራው ያለችው ሴት ስትስቅ
ሰማች ወድያው በሩን ከፍተው ወደ ሳሎን ሲገቡ በቀዳዳ እንዲት
ቀጭን ወጣት ሴት የሰማይ ስባሪ ከሚያክል ወፍራም ወንድ ላይ
እንደ ጨርቅ ተለጥፋ እየተጓተቱ ሲገቡ አየችና የልቧ ትርታ
ድምፅ ለሠዎቹ የሚሰማ እስኪመስላት ድረስ ፍርሀት ወረራት።
እንደገቡ ትልቁ ሶፋ ላይ ጎን ለጎን ተቀመጡና የያዙትን ውስኪ
መጠጣት ጀመሩ "እዚህ ቤት በቅርብ መተሀል እንዴ "? አለችው
ለምን ጠየቅሽኝ"? አላት ጎርነን ባለ ድምፁ" ልክ ባለፈው ስመጣ
እንደነበረው የተዘጋ ቤት ጠረን የለውም " ስትለው " እዚህ ቤት
እኮ የሚመጣው ሠው አይታወቅም ቁልፍ ያለው አራት ሠዎች ጋር
ቢሆንም ሁሉም በየፊናዉ ለተለያየ ሠው እየሰጠ ለተለያዩ የግል ጉዳዮች ይጠቀሙበታል" አላት።
"ካንተ እና ከዛ አረመኔ ጓደኛህ ዉጪ የሚመጣ አለ ማለት ነው
ደሞ ምን ጉዳይ ኖሯቸው ያውቃል ዲያስቦራው ከውጪ ወደ ሀገሩ
ገብቶ ለአገር በሚጠቅም ነገር ላይ ኢንቨሥት ያረጋል ያ ጓደኛህና መሰሎቹ የሀገራቸውን ሴቶች መጫወቻ ያደርጋሉ"
ስትለው•••
አሁን አንቺ ምንሽ ተነካ ነው ለዛች በረሮ ጓደኛሽ መቆርቆርሽ ነው
ምላሷን እና እግሯን ብትሰበሰብ ኖሮ እዚህ አምጥተው እንደ ህፃን
ልጅ አይገርፏትም ነበር" አለ ።
አረመኔዋች ናቸው በእዉነት ለሳምንት ያክል ቁጭ ለማለት እኮ
እስክትቸገር ነው የገረፏት እኔኮ ሚገርመኝ እንደዛ ስትጮህ ሰው
የሚባል ሊያስጥላት አለመምጣቱ ነው" እለች ።
"ቤቱ ኮ ኮንደሚንየም ነው ረሳሽው እንዴ ሁሉም ቤቱን ዘግቶ
የራሱን ኑሮ ነው እሚኖረው እሄ መንደር ውስጥ ያለው ማህበራዊ
ኑሮ እዚህ የለም ጉርብትና ብሎ ነገር ታሪክ ሆኗል መንግስት
በቋንቋ ላይ ከተመሰረተው ፌደራሊዝም ቀጥሎ ህዝቡን የከፋፈለው በኮንደሚንየም ይመስለኛል ሳስበው። አጠገብ ለአጠገብ እየኖሩ ሰላም አይባባሉም ።
በተለይ ብዙ ግዜ በሩ የሚዘጋ ከሆነ እሚኖረውና እንግዳ ሆና
የመጣው ተለይቶ አይታወቅም በዛ ላይ ከዚህ ቤት ቀጥሎ ያሉት
ተከታታይ ሁለት ቤቶች ጒደኞቻችን ናቸው የያዙአቸው ታዲያ
እንጥሏ እሥኪወርድ ብትጮህ ማን ይደርስላታል" አለ።
ምኞት የለሊቱ ፀጥታ የሚያወሩት በሙሉ በደንብ እንዲሰማት
ረድቷቷል "ወይ ጉድ ለካ እነዚህ ሁለት ቤቶች ተከፍተው የማያውቁት ለዚህ ነው እነዚህ አውሬዎች" አለች
ነገሩ አንተም የጓደኛህ በህሪ አየተጋባብህ ነው አለች ቀጭኗ
ወጣት "እንዴት እኔ እና እሱን ምን አንድ አረገን " አለ ቆጣ ብሎ
" በቃ ተወው" አለች ፈርታ " ተናገሪ ስለ ቪድዮው ለማውራት ነው አይደል እኔ ሆነ ብዬ ነው እንዴ ያንን ቪድዬ የቀረፅኩት እኔም አንቺም በጣም ሰክረን ነበር ግንኙነት እያደረግን ዝም ብዬ
እንደቀልድ ሪከርድ አረኩት አለቀ ያለፈ ነገር ነው" አለ እያፈጠጠባት።
"አስበህበት ካልሆነ እንደ ቀልድ ከተቀረፀ እንዴት የኔ ሁለመናዬ እየታየ የአንተ ከወገብ በታች ብቻ ሊገባ ቻለ ደሞ ዛሬ ለመገናኘት እንደማይመቸኝ ስነግርህ ያንን ቪድዮ ዩቲዩብ ወይም ፌስቡክ ላይ
ላይ እንድለቀው ትፈልጊያለሽ ብሎ ማስፈራራቱ ለምን አስፈለገ"
አለች።
አሁን ማልቀስሽን አቁሚ በቃ ካሁን ቡሀላ እኔም ላገባ ስለሆነ
እሄ የመጨረሻችን ነው ቩድዮውንም አጠፋዋለሁ" አላት
ምኞት ፡ ወይ ፈጣሪዬ በቀረፀው ቪድዮ እየስፈራራ ነው እቺን አንድ ፍሬ ልጅ እሚጫወትባት " አለችና ፍርሀቷ ወደ እልህ እና ንዴት ተቀይሮ በቆመችበት መንቀጥቀጥ ጀመረች።
"አሁን ማላዘንሽን አቁሚና ጠጪ" ሲላት " እኔ በራሴ እጅግ አፍራለሁ ያንን ቪድዮ ሳስበው ቆሻሻነት ይሰማኛል ያን ቀን ምን
አዳስነካከኝና እዚህ ቅሌት ውስጥ እንደገባሁ አላውቅም ያባዬ
የቅርብ ጓደኛና ባለውለታው ነክ ብዬ ነበር ግብዣህን የተቀበልኩት•••
እባክህ አጥፋው እኔ ከዛ ውጪም ቢሆን እንደፈለከው እሆንልሀለሁ
ካለበለዝያ ግን በዚህ ምክንያት ምንም ነገር ለማድረግ ብትሞክር እራሴን እንደማጠፋ እወቅ " እለችው እና አይኗን እየጠራረገች ሻወር ለመውሠድ ገባች።
[የሻወር ቤቱን በር መዝጋቷን ካረጋገጠ ቡሀላ ቪድዮው ያለበትን
ሚሞሪ ካርድ ከሞባይሉ በማውጣት ኮርነር ላይ የመሬት
ምንጣፉን በመግለጥ ሲደብቅ ምኛት አየችው•••

ይቀጥላል ........

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

10 Oct, 16:02


"ስንወለድ ሰዎችን ሁሉ አውቀን አይደለም፡፡ ከሰዎች ጋር በብዙ መንገዶች እንተዋወቃለን፡፡ ለሁሉም ሰው ተገቢውን ቦታ ስንሰጥ ለህይወታችን ትክክለኛውን ሰው እናገኛለን፡፡"

🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹

🅙🅞🅘🅝 🅤🅢👉 @yekeberedaha

🅒🅞🅜🅜🅔🅝🅣👇👇
📩 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

10 Oct, 06:57


ታሪክ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ወደ ቻናሉ ጓደኞቻችሁን በመጋበዝ ይተባበሩን🙏

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

10 Oct, 06:46


​​​​😘ምኞት😘

♠️ክፍል 9
.
.
.
ከራሱ ሲጨቃጨቅ ግዜ ቢፈጅም ከማያሸንፈው የፍቅር ስሜት ጋር
ትግል መጀመሩ ሲታወቀው ሚኪ አፍቅራሀታል እንዴ ብሎ እራሱን
ጠየቀው•••
አለፈቀርካትም ብሎ ለመመለስ ድፍረት አጣ እሄን ግዜ ከራሱ ጋር
የመጨረሻውንና አስታራቂ የማይፈታውን ጥል ተጣላ።
ይህን ፀብ በድል ለመወጣት ያለው አማራጭ ብርጭቆ ውስጥ
መደበቅ ነበር ።
ለተከታታይ ቀናት ብርጭቆ ውሥጥ ተደበቀ ነገር ግን መጠጡ
እውነቱ የበለጠ ጎልቶ እንዲታይ በማረግ የበለጠ
ከራሡ ጋር እንዲጣላ አረገው እንጁ እንዲረሣው አልረዳዉም።
ብሩኬ መጀመሪያ ትንሹ ሢደውልለት ለምን እንደደወለ ስለገባው
ባያነሳም ቆይቶ መልክት ሲደርሰው ከፍቶ አነበበው የትንሹ
መልክት ነበር•••
አ..ይይይይ ትንሹ እሥቲ ተወኝ አንተ ጋደኛህ ምናምን የምትለው
ሚኪ የንተን ባለ አደራ ሚስኪኗን ልጅ ሜዳ ላይ ጥሎ እኔ
ከማፈቅራት
ከፅኑ ጋር ከኔ ተደብቆ እዚህ አለሙን እየቀጨ መሆኑን ሥታውቅ
ይቅር ትለኛለህ አለ።
ብሩኬ ሀዋሳ ከደረሰ ቡሀላ እነ ፅናት ይዝናኑበታል ብሎ
የሰባባቸው አንዳንድ ቦታዋች ላይ ቢፈልጋቸውም ሊያገኛቸው
አልቻለም 9፡00 ሰአት ሆናል ድካም እና ረሀብ ስለተሠማው
ሊበላ አረፍ አለ።
ቁጭ ብሎ ምሳ እየበላ አንድ ሀሳብ ሢመጣለት ደስ አለው ብዙ
ግዜ እራሡን ማድነቅ የሚወደው ብሩኬ " አይ ብሩኬ አናታም እኮ
ነህ በዚህ አናትህ እምታመጣው ሀሣብ ይገርማል "አለና ሣቀ።
አንዳንዴ ለጨነቀን ነገር መፍትሄ የሚያመጣ ሀሳብ ብልጭ
ሢልልን መደሠቱ የጤነኛ ሰው መገለጫ ነው ብሩኬ ግን ብዙ
ግዜ ደሥተኛ የሚሆነው የተንኮል ሀሳብ በሚምጣለት ሰአት ነው

ሠዋችን እንዴት ሊሸውድ ወይም ሊያጠቃ እንደሚችል
የሚያመላክት ሀሣብ ሢመጣለት ልቡ ጮቤ ይረግጣል በባህሪው
የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት በሚወሥደው እርምጃ የሌላውን
ጉዳት ሚዛን ላይ ማሥቀመጥ ብሎ ነገር ያልፈጠረበት እርኩስ
የሚባል አይነት ሠው ነው።
ሥልኩን አወጣና ወድ ፅናት ደወለ " ስልኳ ተከፍታል" አለ ሢጠራ
ከተወሠነ ጥሪ ቡሀላ አነሣችው።
ፅኑ ሀኒ እንዴት ነሽ"? አለ ።
አለሁልህ ሠላም ነው አለች ወንድማ አጠገባ ነው
እንዴት ነው ዘና እያልሽ ነው አለ
አየሩ አልተመቸኝም ግን ወጣ ማለቱ ደስ ይላል አለች።
ወሬ ማብዛት አልፈለገም ቀጥታ ወደ ገደለው ገባ
እኔ ምልሽ የሆነ ሠው ለኔ ይዘሽልኝ እምትመጭው እቃ
ያቀብልሻል የቱ ጋር ነሽ አላት
ንፋስ ለመቀበል ወደ አሞራ ገደል እየሄድን ነው እዛ መጥቶ
እንዲሠጠኝ ንገረው አለች ፅኑ
ሚኪዬ ግን ደና ነው ምን ሆኖ ነው? እ ማ ይ ደ ው ል ል ኝ አለች
ፅኑ ሙዝዝ እያለች
እኔም እለገኘሁትም በማለት በፍጥነት ተሠናብታት ሥልኩን ዘጋው

ኧረ በናንተ ቤት ሙድ መያዛችሁ ነው ሚ..ኪ ምናምን ትላለች
አጠገባ ሆኖ አለና ቀጥታ ወደ አሞራ ገደል በመሄድ እሡ
ሳያያቸው ቀድመው እንዳያዩት ዛፎቹን በመጠቀም እየተጠነቀቀ
መፈለግ እንደጀመረ ብዙም ሳይቆይ ፅኑና ወንድማ ምንጣፍ ላይ
ተቀምጠው አያቸው ሚኪ የት ሄዶ ነው አለ አጠገባቸው
አለመኖሩን ቢያይም አላመነም ተደብቆ ሲከታተላቸው መሸ ፅኑ
የወንድማን ባህሪ ስለምታውቅ በግዜ ገብታ መተኛት ፈልጋ ነበር
ወንድማ ወጥተው መጨፈር እንዳለባቸው ባትፈልግም ተጫናትና
ወጡ።
ከምሽቱ 5፡30 ሆኗል ጭፈራ ቤቱ የተለያየ አይነት የብርሃን
ነፀብራቅ ባላቸው የጭፈራ ቤት መብራቶች ድምቅምቅ ብላል
ሙዚቃው ለጉድ ይጮሀል ብሩኬ ፡ ፅኑና ወንድማ ከተቀመጡበት
ቦታ ራቅ ብሌ ኮርነር ላይ ጨለም ያለ ቦታ መርጦ በመቀመጥ
ይከታተላቸዋል አሁን ድረሥ ሚኪ አለመኖሩን አምኖ የተቀበለ
እይመስልም ፅኑ በመሀል እንዴ ብሩክ ይምጣል ያልው ሠውዬ
ቀረ ለካ አለች ባክሽ ተይው አላት ወንድማ ደስ አይልም ደውዬ
ለብሩክ መንገር አለብኝ ብላ ስልኳን ስታወጣ ወንድማ ሥልኩን
ቀማትና ሠከርሽ እንዴ ፅኑ ሠአቱም ሄዷል ደሞ ሚዚቃውን
አስበሽዋል እንዴት ልታወሪው ነው አላት ።
ጮክ ብለው በማውራት ነበር እነሡም የሚግባቡት ከደቂቃዋች
ቡሀላ ውንድሟን እንደንስ ብትለውም እምቢ ሥላላት ፅናት
ብቻዋን ተነሥታ መውረግረግ ጀመረች በነሡ ትዩዩ ያሉ ሶስት
ጠብደል ጠብደል ወጣቶች አይናቸው እሷ ላይ ነው።
አንድ ተነሥቶ ወደሣ በመጠጋት አብሯት ለመደነሥ ሢሞክር
የወንድሟን ባህሪ ሥለምታውቅ ዳንሷን አቁማ መቀመጥ
እንዳለባት ወሠነች ልትቀመጥ ሥትል ወጣቱ ክንዳን ያዝ አርጎ
ጎተት አረጋት ወንድማ ከመቅፅበት በመነሣት ጠርሙሡን
ጭንቅላቱ ላይ አፈነዳው ወደቀ ተቀምጠው የነበሩት ሁለቱ
ጒደኛቹ እንደ አራሥ ነብር የፅኑ ወንድም ላይ ሰፈሩበት ቤቱ
ድብልቅልቅ አለ ፅኑ የሞት ሞቷን ወንድሜን ብላ በመጮህ
ጠርሙሥ አንሥታ ሥትሠነዝር አንደኛው እጃን ይዞ እንዳፈጠጠባት
ብሩኬ ከተደበቀበት ተነሥቶ በመምጣት ከጀርባው ያዝ እንዳረገው
ልጅ በፍጥነት በመዞር ሲወረውረው ብሩኬ ተሽቀናጥሬ መሬት
ከመድረሱ በፊት ፅኑ አየችውና እንዴ ብሩክክክክ ብላ ጮኸች።
ኬት መጡ ሣይባል ፖሊሶች ጭፈራ ቤቱን ወረሩት
ከሶሥቱ ወጣቶች መጀመሪያ የተመታውንና የፅኑን ወንድም ወደ
ሀኪም ቤት ሢወሠዱ እንደኛው
ወጣት እምጥ ይግባ ሥምጥ ካቦታው ተሰወረ
ብሩኬን እና አንደኛውን ወጣት ወደ እሥር ቤት ይዘዋቸው ሥሄዱ
ብሩኬና ፅናት ተያዩ ጥያቄ ባዘሉ አይኖቻ አፈጠጠችበት።
ምኛት ቀኑን ሙሉ አይና ከሥልኳ ላይ ሣይነቀል ኤር ፎኗን ሠክታ
ኤፍ ኤም ሥታዳምጥና የሚኪን ሥልክ ሥትጠብቅ ውላ
ብታመሽም ሚኪ አልደወለም።
ልትተኛ ሥትል ፌሥ ቡክ አካውንታን ማቋረጥ እና ሢም ካርዳን
ሠብራ ለመጣል በውሥጧ የተፈጠረውን ስሜት ፡ እሥከ ነገ
ብጠብቂውሥ የሚለ ሀሣብ እጃን ጠፍንጎ ያዛት።
አጠገቧ ሠው ያለ ይመሥል "በቃ እሥከ ነገ እጠብቀዋለሁ ነገ
ግን የመጨረሻ ነው" አለችና ተጠቅልላ ተኛች።
ትንሹ ምኝታው ውሥጥ ሆና ይብሰከሠካል ቀን ለብዙ ሠአት
ድንጋይ ላይ ከተቀመጠ ቡሀላ ሚኪን ቤቱ ሄዶ እንዳገኘው•••
" ምኛት ምን አለች?እንዴት ነበር ሁኔታዋ?እሥቲ በዝርዝር ንገረኝ"
እያለ ከተቀመጠበት ተነሥቶ አጠገቡ በመምጣት አይን አይኑን
ሢያየው በጣም ታሣዝን ነበር ፡ ልቧ የተሠበረ ሤት ምን
እንደምትመሥል እሣዋ ላይ ነው ያየሁት " አለው ትንሹ።

ከ100👍 በኋላ
.............ይቀጥላል........


🌹💞💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹

🅙🅞🅘🅝 🅤🅢👉@yekeberedaha

🅒🅞🅜🅜🅔🅝🅣👉 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

05 Oct, 13:40


ስለዘገየሁ ይቅርታ

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

05 Oct, 05:42


​​​​😘ም..................ኞ...................ት😘

🔥ክፍል 8

.
.
.
በይ ነይ 50 ብር ይበቃኛል
አለና 50 ብሩን መለሠላት ተሣሣቁና ተቀብላው ሄደች።
ለማንኛውም ሀገራችንን ለማለማመድ በምንኛውም ሰአት ዝግጅ
ነን " አላት
ጮክ ብሎ ። ቆም አላችና " ለሊትም ቢሆን" ? አለች ፈገግ
እያለች።
"ችግር የለውም" እለ እየሣቀ። ሀዬባባ . .ብላው ፍቷን እዙራ
ሄደች ትንሽ ራቅ እንዳለች
በጃጁን አስነድቶ ሲሄድ ድምፅ ሰማች። የአዲስ አበባ ሰው
አይቀርብም ብለው የሚያወሩት ወጣቶቹን አይመለከትም ማለት
ነው አለች ልብ ራሷ።እቤት እንደገባች የገዛቻቸውን ነገሮች እቃ ቤት አስቀምጣ በመውጣት ሳሎን ተመለሠችና ተናዳ
ስትወረውራት ከግድግዳው ጋር ተጋጭታ የተበታተነችውን ሞባይል ኪዷኗንና ባትሪዋን ከሶፋው ስር ቀሪ አካሏን ደሞ ከትልቁ
ሶፋ ላይ ለቃቅማ ገጣጥማ ስታስነሳት ነቃች ተርፈሻል ማለት ነው
አንቺ ሞት እንቢ ስንቴ ወድቀሽ ተነሳሽ አለች ። የመልክትም ያልተሳካ ጥሪም ያለመኖሩን ስታይ በረጅሙ ተነፈሰች ። በጣም ከፋት። እስካሁን ይመጣል ይደውላል እያለች የምታፅናናት የተስፋ
ብርሀን ንፋስ ሊያጠፋት እንደሚያስፈራራት ሻማ ትስለመለማለች
ጨርሳ ተስፋ አልቆረጠችም።
ሚኪ አለች አጠገባ ያለ ይመሥል
እስከ ማታ እማትደውል ከሆነ አንተን መርሳት ቀላል ባይሆንም አንተን ለመርሳት የማደርገውን ጥረት ከዛሬ ማታ እጀምራለሁ አለች የምታረገውን ነገር እያሰበች የመጀመሪያው ከሚኪ እና
በፉት ከማውቃቸው ሰዋች ያገናኘኝን ፡ ፌሥ ቡክ አካውንቴንማጥፋት(ዲ አክቲቬት ማረግ)
ሁለተኛው ሚኪና ዘምድ አዘማድ እንዲሁም የድሬ ዳዋ ጒደኞቿዋ
በሙሉ የሚያውቁትንና አሁን የምትጠቀምበትን ፡ ሢም ካርድ
ሠባብሬ መጣል ብላ አሠበችና እምባዋ በአይኗ ሙሉ ግጥም አለ።
ትንሹ ከእንቅልፉ እንደነቃ ከአልጋው ላይ ሴይነሳ ነበር ምኞት ትዝ ያለችው። ፖስታዉን ለመውሰድ ፍራሹን ገለጥ ሲያደርግ የለም።በድንጋጤ በፍጥነት ተነሳና ፍራሹን ሙሉ በሙሉ
ከእልጋው ላይ አነሳው ፡ የለም። ክው አለ ፡ የሠራተኛቸው ሥም፡ ጠፋበት " እንትና..ማነሽ . ምኞት እለ በጩኊት የሠራተኛዋ ሥም
ግን ጌጤ ነበር ሰራተኛዋ ድምፁን ሰምታ መጣች "ከነጋ እዚህ ገብተሽ ነበር"?
አላት "እንደውም" አለች ጌጤ
ከላይ ሣይለብስ በዛው ለብሶ ባደረው ቁምጣ ወደ ሚኪ ክፍል ገሠገሠ በርግዶ ሢገባ የለም መቼ እንደወጣ ቢጠይቅም ሢወጣ አየሁም ሠማሁም የሚል ሠው አጣ።
ደወለለት አያነሳም ፡ ልብሡን ለብሶ ከቤት እየወጣ
መልክት ፃፈለት፡ እባክህ ብሩኬ በምንወዳት እናታችን ይሁንብህ
የአደራ ፖስታ ነው እንዳትከፍተው ላንተ ምንም አይጠቅምህም ደሞ ሚኪ ጒደኛህ ነው ከሠጠሁት ቡሀላ ማወቅ እምትፈልገውን ብትጠይቀው ይነግርሀል
ከፍተህ አንብበህ ከሆነ ግን እማዬ ትሙት ካሁን ቡሀላ ብሩክ የሚባል ወንድም የለኝም ብሎ ፅፎ ላከለት።
ቁርሱንም ሳይበላ ወደ ሚኪ ቤት ገሰገሰ።
ሚኪ ቤት ደርሶ ብሩኬ ፖስታውን ሠጥቶት እንደሆነ እስኪያጣራ
ቸኩሏል እንደደረሠ በሩ ክፍት ስለነበር ዘው ብሎ ግቢ ውሥጥ ሲገባ ሠራተኛዋን አገኛት።
ጠጋ አለና ሚኪ መኖሩን ጠየቃት መኖሩንና ግን ሊነጋጋ ሲል
ሥለገባ መተኛቱን ገለጠችለት "ከነጋ ጋደኛው ወይም ሌላ ሠው መጥቶ ነብር እንዴ" ማንም የመጣ ሠው የለም አለችው።
ትንሹ ፦ ጭንቅ አለው ሆነም ቀረ የተፈጠረውን ነገር ለሚኪ መናገር እንዳለበት አሠብና " ከብሩኬ ጋር ቢጣሉስ ኡፍፍ " አለ
"በሰላም ነው ግን ሊነጋጋ ሢል የገባው ትናንት እኮ እሥከ 3፡00
ሠአት ይገባል ብለሽኝ ነብር" ሢላት
ሚኪ ላይ ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ባህሪ አይታበት እንደማታውቅና ሠሞኑን ያመጣው አዲሥ ባህሪ እንደሆነ
ሥትነግረው ፡ እሺ በቃ እኔ ጋር ቁልፍ ሥላለው ልሠጠው ነው ትንሽ ቆይቼ እመለሣለሁ ብሏት ወጣ።
ትንሹ ከግቢው እየወጣ ምናልባት የሚኪ ለውጥ ከምኞት ጋር የተያያዘ ይሆን እንዴ ፡ ወይኔ!! እኔ ለአደራ የማልበቃ
ሠው ይሄኔ እኮ ደብዳቤውን ሠጥቸው ቢሆን ሊታረቁም ይችላሉ አለና
ከሚኪ ቤት ራቅ ብሎ ካለ አንድ ድንጋይ ላይ ግራ በተጋባና በተረበሸ መንፈሥ ቀኝ እጁን ከቀኝ ጉንጩ ጋር አጣብቆ ቁጭ
አለ።
ሚኪ የመሳፈሪያ ብር በትንሹ በኩል ልኮ ምኞትን እንድትሄድ ከነገራት ቡሀላ ወድያው ነበር ከራሡ ጋር የተጣላው ።
በህይወት ውስጥ ሠው ከሠው ጋር ይጣላል፣ ሠው ከተፈጥሮ
ጋርም ይጣላል ፡ የከፋው እና ከባድ ፀብ ግን ከራሥ ጋር መጣላት ነው።
ከራሡ ጋር ያልተሥማማ ሠው ከማንም ጋር መሥማማት
አይችልም፡ እራሡን ማሣመን ያልቻለ ሠው ማንንም ለማሣመን
አቅም አይኖረውም።
ሚኪም በምኛት ላይ ያደረገው ነገር ፍፁም ምቾት እና እረፍት
ሊሠጠው አልቻለም ለሷ ያለውን ፍቅር
ደረጃው እሥከምን እንደሆነ ማወቅ አልቻለም ነበር ሥጋዊ ፍላጎቱ የተኮረው ግዜያዊ በሆነው ውጫዊ ውበቷ ላይ
ነበር
እውነተኛ ፍቅር መንፈሣዊ እንጂ ሥጋዊ አይደለም እሄን ባለመረዳት ብዙዋቻችን አንድን ሠው አብረነው ሥንሆን እና
እምንፈልገውን ነገር በሙሉ ያገኘን ሢመሥለን ብንለየውም
የምንጎዳ አይመሥለንም ነገር ግን ገና ካጠገባችን ራቅ እንዳለ
ለሡ ያለን ፍቅር ይታወቀናል ምክንያቱም ፍቅር እሚጠገብ ነገር
አይደለም ሁሌም እንደ አየር ብንተነፍሠውም የሚሰለች ፍቅር
የለም ሚኪ ልቡን ለማዳመጥ እድል ሳይሰጥ ስሜቱን አድምጦ
በወሰነው የተጣደፈ ውሳኔ ብዙም ሳይቆይ ነበር ግራ በተጋባ እና
ፀፀት ባዘለ ስሜት መጣደፍ የጀመረው ሁሉም ነገር ባንድ ግዜ
ሲያስጠላው ምክንያቱ በምኞት ላይ የፈፀመው ክህደት ስለመሆኑ
እንኳን ለማስተዋል ሳይችል ምን ሆኜ ነው ውስጤ ርብሽብሽ ያለው እያለ ከራሱ ሲጨቃጨቅ ግዜ ቢፈጅም ከማያሸንፈው የፍቅር ስሜት ጋር ትግል መጀመሩ ሲታወቀው ሚኪ አፍቅራሀታል
እንዴ ብሎ እራሱን ጠየቀው ።

ይቀጥላል.......

🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹

🅙🅞🅘🅝 🅤🅢👉 @yekeberedaha

🅒🅞🅜🅜🅔🅝🅣👇👇
@mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

02 Oct, 02:27


​​😘ምኞት😘

🔥ክፍል 7
.
.
.
እንደገባ ክፍሉ ውሥጥ ለሚኪ የተላከውን ነገር ድምፅ ሳያሰማ
መፈለግ ጀመረ የልብሥ ማስቀመጫውን፣ መፃፍ መደርደሪያውን፣
ትንሹ አውልቆ የተኛውን ልብስ በየተራ በረበረ ምንም የለም ወይ
ፋኑኤል ደረቅ እኮ ነህ እስቲ ብትነግረኝ ምን ነበረበት" አለ ፋኑኤል የትንሹ የትምህርት ቤት ሥም ሲሆን በባህሪው ሠው ማስቀየም እማይፈልግ ፡ ላመነበት ነገር ሟች፣ ታማኝ እና ሲበዛ
ወግ አጥባቂ እንደሆነ ስለሚያውቅ ቢያስገድደውም መልክቱን
እንደማያሳየው ያውቃል።
ቆም አለና አሰበ ቁልቁል ትንሹን ሲያየው ትራስ ደራርቦ በቀኝ እጁ
የፍራሹን ጠርዝ ጭብጥ አድርጎ መተኛቱን አስተዋለ ከልጅነቱ
ጀምሮ ሰው ይወስድብኛል ብሎ ያሰበውን ነገር ይዞ ከተኛ እስኪነጋ እጁን ሣያነሳ በአንድ ጎኑ ሳይገላበጥ የማደር ባህሪ
እንደነበረው አሠበና
ፍራሹ ሥር መሆን አለበት አለ
በቀሥታ እጁን ከፍራሹ ላይ አላቀቀና ዳር ላይ የተኛውንና ከተኛ
ብዙ እማይሰማውን ትንሹን ወደመሀል ገልበጥ አደረገው ። ፍራሹን ገለጥ ሢያደርግ ፖሥታውን አየው " ተገኘሽ አይ ትንሿ አለና እየሳቀ ወደ ክፍሉ ሄደ።
ክፍሉ እንደገባ ፖሥታውን አገላብጦ አየው የላኪም ሆነ የተቀባይ
አድራሻ የለውም።
ሊከፍተው ካለ ቡሀላ ፈራ በፅናት ካልመጣበት በስተቀር በሌላ
ጉዳይ አብሮ አደጉና ጓደኛውን ሚኪን ማስቀየም አይፈልግም ።
ጋደም ብሎ ማሰብ ሢጀምር ለሊት ሢያንቆራጥጡ ያሳደሩት
ሀሳቦች ፡ተራ በተራ አእምሮው ውስጥ መክተልተል ጀመሩ
"ምናልባት እኮ ፅናት ወደ ሀዋሳ አብሯት እንዲሄድ ፈልጋ እቤት አጥታው፡ ስልኩንም ሳያነሣ ቀርቶ፡ ከቤት ሠራተኛቻቸው ለአንዷ
መልክት አሥቀምጣለት ሄዳ ይሆናል"
በቃ እሄን ፖሥታ ሳይወሥድ በመሀል ተደዋውለው በዛው ሄደው
ይሆናል" የቅናት አባዜው ሰፈረበት ፡ ተብከነከነ የያዘውን ፖሥታ
በረጨቀው!
ደጋግሞ አነበበው፡ ውስጡ በተለያየ ሀሳብ ግራ ተጋባ ባንድ በኩል ማየት ያልነበረበትን ያየ በጓደኛው በሚኪ ላይ ክህደት የፈፀመ መስሎ ሲሰማው ባንድ በኩል ደግሞ ስለሚኪ ምንም
ያለማወቅ ስሜት ስለምኛት የማዘን ስሜት ውዝግብግብ አለ
"ምንድን ነው እሄ ?እኔ ሣላውቅ መቼ ተጀምሮ ነው አሁን ያለቀው
ምን አይነት እምታሳዝን ልጅ ነች " አለ።
ትንሹን ቀስቅሶ ስለ ምኛት ሊጠይቀው ፈለገ ግን ትንሹ ብሩኬ
ፖስታውን ወስዶ እንዳነበበው ቢያውቅ በዛ በለሊት ኡኡ ብሎ
ከመጮህ እንደማይመለሥ አሠበና ተወው
እችን ሚስኪን ልጅ ከቤት አውጥቶ ሜዳ ላይ የጣላት ከፅኑ ጋር
ለመሆን ነው በቃ ወደ ሀዋሳ አብረው እንደሄድ እርግጠኛ ነኝ " አለና ውስጡን የሆነ ነገር ሲነዝረው ተሰማው።
ወድያው ከአልጋው ተፍናጥሮ በመነሳት ልብሱን ለባበሰ።
"መጣሁልችሁ ሚኪና ፅናት አንተ ሚኪ እሄን ጉድ እዛው ፅናት ፊት
ስሠጥህ ምን እንደምትል አያለሁ! እሷም እሄን ስታቅ ምን
እንደምትል አያለሁ ፡ ያኔ ፡ ወደ እኔ ፡ ወይ ወደ እሱ ፡ መንገዷን
ትመርጣለች እያለ መኪናውን አስነሥቶ ወደ ሀዋሳ ነጎደ።
ምኞት ከእንቅልፏ ሥትነቃ 2፡00 ሰአት ሆኗል ገላዋን ተጣጥባ
ልብስ ቀየረችና እሷ ካለችበት ክፍል ቀጥሎ ያሉት ሁለት
ተከታታይ ቤቶች ከመጣች ጀምሮ ሲከፈቱም ሱዘጉም አልያም
ከውስጥ ምንም አይነት ድምፅ አለመስማቷን እያስብች በሩን
በመክፈት አንገቷን ወጣ አድርጋ ውጪ ሰው አለመኖሩን አረጋገጠች።
ሚኪ ከላከላት ሳንቲም የተወሰነ ቀንሳ ቀሪውን በማሥቀመጥ
ሻርፗን ተከናንባ ከቤት ወጣች።
ሠፈር ውስጥ ብዙም መታየት ስላልፈለገች ቀጥታ ኮንዶሚንየም
መውጫ ዋናው አስባልት
ላይ ወደ ተኮለኮሉት ባጃጆች አመራች እንደደረሰች አንድ ባዶ
ባጃጅ ውስጥ ዘው ብላ በመግባት ቁጭ አለች።
ወዴት ነሽ እናቱ አላት ጠየም ብሎ ረዘም ያለ ወጣት ባጃጅ ሹፌር ምኞት የት እንደምትለው ግራ ገባት አቦ ወንድም እቃ ለመግዛት ነው የወጣሁት ግን እንኳንስ የምሄድበትን ያለሁበትንም ሠፈር አላውቀውም ለመሆኑ እሄ
አከባቢ ምንድን ነው እሚባለው"? ስትለው ኧረ ሙድ መያዝ ! በጥዋት ቀልድ ገና ኮ ቁርሥ አልበላሁም "አለ

እዉነቴን ነው ወንድም አለችው
ፉታን ሢመለከተው እየቀለደች እንዳልሆነ ተረዳና ከመጣሽ ስንት ግዜ ሆነሽ "?አላት።
3 ቀን አለችው ከየት ነው የመጣሽው?ከድሬ እንዴ የድሬ ልጅ ድሬን እኮ ትንሽ
ትንሽ አውቃታለሁ የት ሰፈር ነሽ?" አላት። ጎሮ አለች
እንዴ......ጎሮ ..ጎሮ ..ደሞ እንደዚህ እሚባል ሠፈር አለ እንዴ?
የቱጋ ነው? እኔ ከዚራን ነው እማውቀው፡ልጅ ሆኜ ነበር የሄድኩት
አላት እሺ ሣብያን ወይም ሠይዶንሥ ታውቀዋለህ ሠይዶ !!!!!! ሠይዶ ደሞ ማነው ? ሲላት
ለ3 አመት ከልባቧ ሥቃ የማታቀውን ምኞት አሳቃት
ሠይዶ እዛ አከባቢ ህንፃ በሰሩ ሰው ስም የተሠየመ የሠፈሩ ሥም
ነው ሠይዶ ህንፃ ይባላል አለችው
ሳብያንን ካላወክ እዛ አከባቢ የሉትን ሠፈሮች ማወቅ አትችልም
ስትለው እሱም አውቃታለሁ ያለት ድሬ ተምታታችበትና
ቆይ አንቺ ማን ፡ ጋ ፡ ነው የመጣሽው እሥካሁን ማለቴ 3 ቀን
ሙሉ እንዴት ሥለሠፈሩ አልጠየቅሽም አላት።
አንዳንዴ ግድ መዋሸት የሚኖርብን ግዜ አለ ውሸታችን ማንንም
እማይጎዳ ከሆነ ክፋት የለውምና
ምኞትም የግድ መዋሸት ነበረባት
እኔ የመጣሁት አጎቴ ጋር ነው ብርድን ሥላልቻልኩት ከመጣሁ
ጀምሮ ስተኛ ነበር ከማንም ጋር ስለሠፈሩ አላወራሁም አለችው ።
እሺ ለማንኛውም እሄ አካባቢ ቃሊቲ ይባላል የሠፈሩ ሥም ገላን ኮንደሚንየም ሢባል አንቺ በመጣሽበት ጋር
ያለው አዲሡ ገላን ኮንደሚንየም
ሢባል እሄኛው በዚጋ ያለው ደሞ አሮጌው ገላን ኮንደሚንያም ይባላል አላት።
እና አሁን የት ልውሠድሽ ገበያ ያለው አቃቂ ወይም ቶታል ጋርም አለ
የሚቀርብህ ቦ ታ ውሰደኝ አለች ወደ ቶታል ይዛት ሄደ እየሄዱ እሺ የድሬ ልጅ እሄ ምን ነበር ያልሽው የሰፈሩ ሥም እኔ
ሠምቸውም አላውቅ እኔ ከከዚራ ዉጪ እማውቀው ግሪክ ካምፕ እሚሉትንና እሄ ገበያው ምን ነበር....ቀፊራ እሚባለውን ነው
ሣቀችና አንተ እምታውቀው ከዚህ ሢኬድ መግቢያው አከባቢ ያሉትን ሠፈሮች ነው
ሣብያን ማለት አሁን ባቡር ጣብያው ወደ ተሠራበት ወደ መልካ መሄጃ መሥመር ላይ ያለ ሢሆን ጎሮ ማለት ደግሞ ከሣብያን
በሥተ ግራ ወደ ላይ ሥትገባ ያለው ሠፈር ነው አለች።
ሽፌሩ የባጥ የቆጡን ሢያወራ በግድም ቢሆን አሥቋታል ለአጭር ግዜም ቢሆን ሀሣብ እና ጭንቀቷን አሥረሣት።
ገዛዝተው እንደተመለሡ
ብሎክ ሥንት ነው ያጎትሽ ቤት አላት አላውቅም አለችው ግራ
በመጋባት ባጃጃን ድንገት አቁሞ እና የት ልውሰድሽ አላት " እዚሁ ጋር አለችና መቶ ብር ሰጥታው ስትወርድ•••
እንዴዴዴ! ወይ የድሬ ልጆች አለ ግራ በመጋባት..........

ክፍል 8 ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍 ማድረግ አይርሱ።


🅙🅞🅘🅝 🅤🅢 👉 @yekeberedaha

🅒🅞🅜🅔🅝🅣👇👇
📩 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

30 Sep, 13:35


​​​😘ምኞት😘

ክፍል 6


.
.
.
በሩ ላይ እንደደረሰች ቆም አለችና ማዳመጥ ጀመረች ፀጥ ረጭ
እንዳለ ነው፡ ከቦርሳዋ ያስቀረፀችውን ቁልፍ አወጣችና በሩን ከፍታ በመግባት ከውስጥ ቆልፋ ቁልፉን እዛው ላይ ተወችው ፡
ጨለማ ቢሆንም መብራት ማብራት አልፈለገችም ባሞባይሏ
ብርሀን ፡ሣሎኑን፣ ምኝታ ቤቱን፣ሽንት ቤቱን፣ ተራ በተራ አየች
ሁሉም ነገር እሷ ስትወጣ እንደነበረው ነው ወድያው የሚኪ ጋደኞች
ቢመጡም ቅዳሜ እና እሁድ እንደሆነ የሚመጡት የነገራትን
አሰበችና ዛሬ እቃ ቤት ገብቶ መደበቁ አስፈላጊ አይደለም ብላ
በማሰብ እዛው ሳሎን ዉስጥ ትልቁ ሶፋ ላይ ጋደም ብላ ከብዙ
ትግል ቡሀላ እንቅልፍ ጣላት።
መልክተኛው ልጅ የምኞትን ሁኔታ እና ያዘነ ፊቷን ከጭንቅላቱ
ማውጣት ተስኖታል።
ሰፈር እንደደረሠ ቀጥታ ወደ ዲያስፖራው ወደ ሚኪ ቤት
በማምራት ደብዳቤውን እስከሚሰጠው ድረሥ ልቡ ተሰቅሏል።
እነ ሚኪ ቤት ሲደርስ ከምሽቱ 1:30 ሆኖ ነበር ፡ የውጪ በር ደውሉን አንቃጨለው ።
የሚኪ ሠራተኛ በሩን ከፍታ ማነው, አለች።
ሚኪ አለ? አላት።
አልገባም። አለችው ሀሞቱ ፍስስ አለ ቀጥታ ወንድሙ ጋር በመደወል ሚኪ አብሮት እንደሆነ ጠየቀው።
ዛሬ አላገኘሁትም ምነው? አለው
አይ ምንም እሺ ስልኩን ስጠኝ? አለው
ወንድምየው ብሩክ ሲባል የሚኪ በጣም የቅርብ ጋደኛ ነው።
ዛሬ ታናሽ ወንድሙ፡ ሚኪን ለምን አጥብቆ እንደጠየቀው ግራ
ተጋብቶ ለምን ፈለከው በሰላም ነው? አለው በድጋሚ ሰው መልእክት ልኮኝ ነው።
አለ ታናሽ ወንድሙ ሠው ማለት ?ወንድ ሴት? አለ ብሩኬ እረ ሴት ነች እለ ትንሹ።
ብሩኬ ወድያው ጭንቅላቱ ሌላ ነገር አሰበ እሡና ሚኪ ሁለቱም
በጣም የሚቀርቧት እሷም ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ሁለቱንም እጅግ የምትቀርባቸው አብራ ብዜ ግዜ ከመታየቷ የተነሳ ሠው የማንኛቸው ነች እያለ እንዲወዛገብ ያደረገችው ሞልቃቃዋ የሀብታም ልጅ ፅናት ነች ።
ምክንያቱም ሁለቱም በጣም ቢቀርቧትም የብሩኬ ቅርበት ግን
ወደ ፍቅር ተቀይሮ መብሰክሰክ ከጀመረ ቆይቷል ግን ሚኪም እሚፈልጋት ስለመሰለው ለሷም ለጒድኛውም ሚስጥሩን አልተነፈሰም።
ነገር ግን አንድ ቀን እንኳን ሳያገኛት መዋል አይችልም እሱ በሌለበት ሚኪና ፅናት አብረው እንደሆኑ ካወቀ ወይም እዚህ ቦታ ነን ና ብለው ከደውሉለት ባይታወቀውም ቅናት ቢጤ
ሥለጀማመረው ደስ አይለውም ወይ ያኮርፋል ግን ሚኪን በጣም
ስለሚወደው ኩርፊያው ውስጥ መቆየት አይችልም።
ታናሽ ወንድሙ ሚኪ ጋር ሰው እንደላከው ሲነግረው ወድያው
ፅናት መሆን አለባት ግን ምን ልካለት ይሆን ብሎ አሰበና
እሺ ስልኩን ሰጥሀለሁ ግን አሁን አንተ የት ነህ? አለው ወደቤት እየገባሁ ነው። አለው ትንሹ መጣሁ ጠብቀኝ አለና ስልኩን ዘጋው ወድያው እቤት እንደደረሰ
ትንሹ እቤት የለም ደወለለት
አያነሳም ፡ ተናደደ ሚኪ ጋር ሄደ ማለት ነው ፡ ሚኪ ጋር ደወለ እሱም አያነሳም መኪናውን አሥነሥቶ ወደ ሚኪ
ቤት በረረ ። ትንሹ አላሥችል ሢለው ወደ ሚኪ ጋር ተመልሶ ሄዶ ነበር።
እንደደረሰ ትንሹ እቤት መግባት ስላልፈለገ ውጭ ብርድ ላይ ቁጭ ብሎ ሚኪን ሲጠብቅ አገኘው ።
እንዴ አንተ እዚህ በጭላማ ምን እየሰራህ ነው"? አለው።
መልክቱን ዛሬ ማድረሥ ሥላለብኝ ሚኪን እየጠበኩት ነው "
ማን ነው መልክተኛው ?መልክቱስ ምንድን ነው"?
አይ በቃ የሆነች ልጅ እዚህ መጥታ ሚኪን እንዳጣችው እንድነግርላት ሥልለመነችኝ ነው በማለት መልህክቱንም የላከውንም ሰው ለወንድሙ መንገር ክህደት መሥሎ
ሥለታየው ደበቀው።
ብሩክ ግን አልተዋጠለትም ።
"ፅናት ብትሆን ትደውላለች እንጂ መልክት አትልክም
ስልኩ እምቢ ቢላት እንኳን እኔ ጋር ትደውለለች እንጂ ሰው እትልክም" ብሎ አስበና
"ቅድም እኮ መልክት ልሰጠው ነው እንጂ ልነግረው ነው አላልክም" አለው
ኧረ ልነግረው ነው ያልኩህ" መለሰ ትንሹ
እና እዚህ እሥከ ስንት ሠእት ነው እምትጠብቀው"?
ሠራተኛዋ ብዙ ግዜ እሥከ 3፡00 ሰአት እንደሚገባ
ነግራኛለች" መለሰ ትንሹ
ለኔ ንገረኝ በቃ ሥልኩን ካነሳ እነግረዋለሁ" አለው።
አይ ተው ወንድሜ ነገ ሳገኘው እነግረዋለሁ" አለ ትንቩ
ወደ ቤት እየሄዱ ብሩኬ ለሚኪ ደጋግሞ ቢደውልም ስላላነሳለት ተናደደ።
ፅኑ ወደ ሀዋሳ ዛሬ ጥዋት ከመሄዳ በፊት
"ሀዋሳ አብሬሽ ብሄድ ደሥ ይለኛል " ስላት ወንድሜ ነው እንሂድ
ያለኝ የሱ ፕሮግራም ነው ያለችኝ ያንን ጉረኛ ወንድሟን ብዙም እንደማልወደው ሥለምታቅ እኔን ደብቃ ከሚኪ ጋር ብቻቸውን ለመሆን ነው ማለት ነው"
እያለ በውሥጡ መብከንከን ይዟል።
ወድያው ሥልኩን በማውጣት የነ ፅኑ የቤት ሥልክ ላይ ደወለ
እይነሳም። ወደ ፅኑ ሞባይል ደወለ ፡ ጥሪ
አይቀበልም "በቃ ይሄማ አጋጣሚ ሊሆን አይችልም" አለ ጮክ ብሎ ሳይታወቀው
ምኑ አለ ትንሹ እሱን ያናገረ መሥሎት ስለተናደደ መልሥ አልሠጠውም ።
ገብቶ ቢተኛም እንቅልፍ ሳይወሥደው በራሱ ሀሳብ ከፈጠራቸው
ቅዠቶች ጋር ሥያወራ፣ ሢጋጭ ፣ ሲስማማ ከለሊቱ 11፡00 ሆነ
በመጨረሻም ወንድሙ የሆነ ነገር እንደደበቀው ማታ ተጠራጥሮት
እንደነበረ ትዝ ሲለው
ከተኛበት ተፈናጥሮ በመነሳት ወደ ትንሹ ምኝታ ቤት አመራ•••

ይቀጥላል........

❤️ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹

🅙🅞🅘🅝 🅤🅢👉 @yekeberedaha

🅒🅞🅜🅜🅔🅝🅣👇👇
📩 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

29 Sep, 06:46


​ "አንድ ቀን"

አፍቅሪኝ አልልም
እኔ እንዳፈቀርኩሽ
ተጎጂም አልልም
እኔ እንደደማሁት
አንቺን በኔ ቦታ ማየት አልፈልግም
ከቶ አያረካኝም…
ግን ብቻ አደራ…
ከልብሽ ውደጂኝ ከውስጥሽ አኑሪኝ
ከህሊናሽ ካልራቅኩ ቢቆጠሩ አመታት
ታፈቅሪኝ ይሆናል አንድ ቀን ምናልባት ።
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
🅙🅞🅘🅝 🅤🅢👉 @yekeberedaha

🅒🅞🅜🅜🅔🅝🅣👇👇
📩 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

29 Sep, 06:44


​​​😘ም................ኞ.................ት😘

ክፍል 5


.
.
.
ድጋሚ ተንኳኳ ማነው ብላ ለመጠየቅና ማንነቱን ለማወቅ አቅም አነሳት ፡ እራሱ ሚኪ መጥቶ ቢሆንስ አለች
አይ ፍቅር ፡ ፍቅር ተስፋ እይቆርጥም ፣ይሰጣል እንጂ አይጠብቅም፣
ፍቅር ሁሌም በደግነት የተሞላ እንጂ ቂም አያውቅም፣ምን
አረኩለት እንጂ ምን ተደረገልኝ አይልም፣ እንዴት ደስተኛ
ላርገው እንጂ ለራሱ ደሥታ አይጨነቅም፣ በፍቅር ዉስጥ
ማነው፣ ምንድን ነው፣ ምን አለው፣ ትናንት ምን ነበር፣ ነገ
ምን ይሆናል፣የሚል አሥተሳሰብ ቦታ የለውም ።
እና ምኞትም በቅፅበት የተፈጠረዉን ሁሉ ረስታ በሩን
እሚያንኳኳው እራሱ ሚኪ ቢሆንስ ብላ አሰበችና የልቧ
ትርታ ለራሷ እየተሰማት ፡በሩን ተነስታ ለመክፈት አቅም አጠራት
በሀይል ተንኳኳ ተንደርድራ ሥትከፍት•••
እንድ ቀጠን ረዘም ያለ ወጣት ቆሟል ፡።
አይኗን ጭፍን አድርጋ ላፍታ ቆየችና አቤት አለችው ምኞት ማለት
አንቺ ነሽ ፡አላት ። ለመልክተኛው ልጅ ጭንቅላቷን በማወዛውዝ
ምኞት መሆኗን አረጋገጠችለትና•••
"ምኞት ማለት አንቺ ነሽ ?" ብላ እራሷን ደግማ በመጠየቅ?
አዋ የቤተሰብ ፍቅር :ጣእም ያለው የተመጠነ ሂወት: ፍቅርና
መተሳሰብ የነገሰበት የፍቅር ሂወት ሁሉ እንደስሜ በምኞት እንጂ
በእውን እንዳጣጥመው ያልተፈቀደልኝ የት እንዳለሁና ወዴት
እንደምሄድ እንኳን የማላውቅ በአራቱም አቅጣቻ እየዞርኩ ብፈልግ
የኔ የምለው ሰው ያጣሁኝ ምኞት የተመኘሁትን ሁሉ እየተነጠኩ
ካቅሜ በላይ የሆነ መራር ሂወት የተሰጠኝ ምኞት ማለት እኔ ነኝ
አለች በውስጧ።
ልጁ አይኗ ላይ አቅርሮ የከበዳትን እንባ እንዳይመለከት ዞራ ወደ
ሳሎኑ እየገባች።
"ሚክያስ ነው የላከኝ አለ። ከኪሡ የታሸገ ፖስታ በማውጣት እንድትቀበለው እጁን በመዘረጋት።
በጨረፍታ ፖስታ መሆኑን ስትመለከት እልካለሁ ካለው የመሳፈሪያ
ብር ጋር የሆነ ነገር ፅፎ የላከላት ስለመሰላት ለቅሶዋን
ለመቆጣጠር ከውስጧ ያለውን እሳት በረጅሙ ተንፍሳ
በማቀዝቀዝ ዞራ ተቀበለችውና በፍጥነት ከፈተችው ከተደረደሩ
የመቶ ብር ኖቶች ውጪ ፖስታው ላይም ቦፖስታው ውስጥም
አንድም የተጫረ ፊደል የለም ። ልሙጥ ነጭ ፖስታ። ቢያንስ
ምክንያቱን ለመናገር ድፍረት ቢያጣ ይቅርታ እንኳን አለማለቱ
ውስጧን ያስነሳው የሀዘን ማእበል መላ አካላቷን አናወጠው።እራሷን ለማረጋጋት ወደ መታጠቢያ ቤት ገብታ ፊቷን በቀዝቃዛ ውሃ ካረጠበች ቡሀላ ቦርሳዋን በመየዝ ካልወጣሁ እያለ
የሚተናነቃትን እንባ ያሥቀረው ይመሥል በሻርፗ ተጠቅልላ ቀና
ሳትል እሄው ቁልፉ ቆልፈውና እንሂድ አለችው። በሁኔታዋ ግራ እየተጋባ ቆልፎ ተከተላት።
ትንሽ እንደሄድ እያለቀሰች እንደሆነ ሢረዳ ተጨነቀ ።
እህት ለምንድነው ምታለቅሽው ?በናትሽ ችግር አለ? ንገሪኝ !እያለ
ጨቀጨቃት። አይ ዝም ብዬ ነው አለችው። እስካሁን ችግሯን ተረድቶ የሚሸሻት እና እንደእህቷ ባል አይነቱ ደሞ ችግራን እንደጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀምበት የሚሞክር እንጂ የሚያቀልላት
የሚያፅናናት አለሁልሽ የሚላት ሰው እንዳላጋጠማት እያሰበች ።
ችግሬን ብነግርህ አንተም ለትራንስፖርት የሚቀርብሽ ቦታ አልጋ
እንድትይዢ የመውሰድ ግዴታ የለብኝም እየጠየቅሽ ድረሽበት ብለህ ጥለከኝ ትሄድ ይሆናል! ነገሩ የምሄድበትም የምሳፈረውም ትራንስፖርት ስለሌለ ከአጠገቤ ሂደህልኝ ለላከህ ሸኝቻታለሁ
ብትለው ግልግል ነበር አለች ለራሷ እንዳቀረቀረች።
ልጁ ግን የምሩን ነብር የተጨነቀው ለምን እንደሆነ ባይገባውም
በሩን እንደከፈተች በጉጉት የተንከራተቱት ውብ አይኖቿ መልሰው እንዴት ክስም እንዳሉ እና ወድያው ፊቷ ላይ ያየው የሀዘን ስሜት ድንገት ውስጡ የሆነ ስሜት ፈጥሮ ረብሾታል።
የት ነው እምትሳፈሪው የሚቀርብሽ ቦታ አልጋ ላስይዝሽ አላት
ችግር የለውም እዚሁ አካባቢ አድሬ ጥዋት በታክሲ እሄዳለሁ አለችው ። አሀ ቅርብ ነው አገርሽ ከነጋ ቡሀላም ብትሄጂ
ትደርሻለሽ ?አላት ።እህህ እለችዉ እሺ አንጪ ቦርሣውን ላግዝሽ
አለና ተቀበላት ትንሽ እንደሄድ ሠው ብዙ የሌለበትን ሆቴል አየችና እስቲ ግባና እልጋ ካለ ጠይቅ ብላው እሷ ፈንጠር ብላ ቆመች።
ፖሥታውን ከቦርሳዋ በማውጣት ትጠብቅው ጀመር ሆቴሉ በር
ላይ ቆሞ ፡አለ ነይ የሚል ምልክት ሲያሣያት መልሳ እንዲመጣ ምልክት አሳየችው ፡ግራ እየገባው ተጠጋትና ምነው አልጋ አለኮ አላት ፡እሺ ወንድም አንድ ነግር ላስቸግርህ ሚኪ
ዘመድህ ነው አለችው ኧረ አይደለም ግን የታላቅ ወንድሜ ጓደኛ
ነው አላት እሺ አልችና ፡በረጅሙ ተንፍሳ እኔን እንደእህትህ እየኝ
እና አለችና ነው እህት አለህ ?አለችው የለኝም አላት እህት
ባይኖርህም
እናት አለህ በናትህ እደራ እሄን ፖሥታ ለሚኪ ዛሬ ካልቻልክ
ደግሞ ነገ በጥዋት ትሠጥልኛልህ? አለችው ። እንዴ ኧረ ዛሬውኑ
እሰጥልሻለሁ ለዚህ ነው እንዴ አላት
እሺ እኔም ገብቼ አልጋውን እይዛለሁ
አንት ሂድ ስትለው ፡እሺ አላትና አይዞሽ እህቴ በሚል የማፅናኛ
አሥተያየት እያያት ፡ካጠገቧ በፍጥነት ሄደ ራቅ እንዳለ
ዞሮ ሲመለከት ወደ ሆቴሉ እቀርቅራ ሥትገባ አያት ምን ሆና ይሆን
አለ በውስጡ ፡እሥኪመሽላት ላስላሳ አዛ እዛው ከቆየች ቡሀላ ፡
ወጥታ ሚኪ ወደ አመጣት ኮንደሚንየም መገሥገሥ ጀመረች ፡
እንደደረሠች እሷ ከወጣች ቡሀላ ምናልባት ሠው ገብቶ ከሆነ ብላ
እሰበችና ፡ጨለማው ውስጥ ቆማ
መብራት አለመብራቱን እና እንቅሥቃሤ እለመኖሩን አረጋግጣ
ደረጃውን መውጣት ጀመረች ፡ደረጃውን ጨርሳ በረንዳው ላይ
ስትደርሥ ኮቴዋን አጥፍታ ወደ በሩ ተጠጋች......

🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹💞🌹

🅙🅞🅘🅝 🅤🅢 👉 @yekeberedaha

🅒🅞🅜🅜🅔🅝🅣👇👇
📩 @mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

27 Sep, 14:01


​​​😘ም................ኞ................ት

ክፍል 4


.
.
.
ጭንቅላቷ ጭውውውው ብሎ ሲጮህ ተሰማት ዞረባት ቤቱ
የሚሽከረከር መሰላት ።
ላለመውደቅ የሶፋውን ጠርዝ ይዛ በቀስታ ተቀመጠች ። ሸርተት ብላ ጋደም አለች ከቆይታ ቡሀላ ወደ እራሷ ስትመለስ
የትና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለች አምኖ መቀበል ቸገራት።
የህቷ "አንድ ነገር ተፈጥሮ ብትመለሽ መልሼ አላስገባሽም "
የሚል የዛቻ ድምፅ ድጋሚ ጆሮዋ ላይ አቃጨለባት ።
የሰፈሩ ወሬኞች ድያስቦራ ጠብሳ አዲስ አበባ ገባች እያሉ
የሚቀባበሉት ወሬ ከነወሬኞቹ ፊት ፊቷ ላይ በየተራ ተንጫጫባት።
ፌስ ቡክ ላይ በመልክት የላኩላትና ያነበበችው የጓደኛቿ እንኳን
ደስ አለሽ መልክት በ በጓደኛቿ አንደበት ኧእምሮዋ ውስጥ ሲነበብ
ተሰማት። ግን ለምን ለምን ለምን አለችና ያ የብሶት ማስተንፈሻ የመገፋት
እና የበደል ማስታገሻ እንባዋን መንታ መንታ ታወርደው ጀመር ።
ሚኪ ለስራ ሌላ ቦታ ልሄድ ነው ያላት ሰበብ እንደሆነ ሲደውል እና
ደርሳ በአካል ሲያገኛት የነበረው የስሜት ለውጥ እዚህ ኮንደሚንየም እስኪያደርሳት የነበረው ሁኔታ በአይነ ህሊናዋ በድጋሚ እያጠነጠነች ስታስበው ምን እንዳሰበ ሁሉም ነገር
የበለጠ ግልፅ ሆነላት እንደ እብድ እደረጋት ።
የህቷ ባል ክፋት ታወሳት።
ካልመጣሽ ብለህ መቆሚያ መቀመጫ እንዳላሳጣከኝ ሁለት ቀን
ሳይሞላኝ ተመልሰሽ ሂጂ ስትል ሌላው ቢቀር ግፍ እንኳን አትፈራም ሚኪ ።
ግን እንዳሰብከው ስትፈልግ ነይ ስትፈልግ ሂጂ የምትለኝ አይነት
እይደለሁም ሚኪ ብወድህም ስትገፋኝ የምወድቅበት ስለለኝ አልገፋልህም።
በፈለኩበት ሰአት ወጥቼ ካልተመቸኝ ተመልሼ የምገባበት ቤትም የለኝም ።
በፍፁም አልሄድም! የት ነው እምሄደው? ማን ጋ ነው ምሄደው ?
ከዚ ቤት ማንም አያስወጣኝም!
አለች ሢቃ ባዘለ ድምፅ ትንሽ ተቀምጣ ካሰበች ቡሀላ የእቃ ቤቱን በር ከፍታ በመግባት። ከጠረጴዛው ሥር ያለውን ቆሻ በማፅዳት ሻንጣዋን አሥቀምጣ
ወጣችና ከምኝታ ቤት እልጋው ግርጌ ሥር ተጣጥፋ የተቀመጣችውን ትንሽ ፍራሽ ወሥዳ እቃ ቤት ጠረጴዛው ሥር
እሥተካክላ ካነጠፈች ቡሀላ ከቤት በመውጣት መንደር ውሥጥ አንድ ጥግ ላይ ጫማ ወደሚጠርገው ልጅ በምጠጋት ይቅርታ ወንድም ለማባክንብህ ግዜ ሀምሣ ብር እሠጥሀለሁ የቤት ቁልፍ እሚቀረፅበት ቦታ ልትወስደኝ ትችላለህ ሀገሩን በደንብ
ስለማላውቅ ነው አለችዉ።
ሊስትሮው በቅፅበት እቃውን አንድ ሱቅ ውሥጥ አሥቀመጦ
ይዟት ሄደ ቁልፉን አስቀርፀው ሲመለሡ ከቀኑ 9፡30 ሆኗል እቤት
ገብታ ትንሽ እሰብ አረገችና ሱቅ ሄዳ ወረቀት እና ፖሥታ
በመግዛት ለድያሥፖራው ደብዳቤ መፃፍ ጀመረች•••
ይድረሥ ትናንትም ዛሬም ነገም ቢሆን ሁሌም ጥሩ
ነገር ለምመኝልህ ሚክያስ እንደምን እለህ፡እኔ መቼም ደና ነኝ አልልህም፡ ይገርማል ለምን እንደሸሸከኝ ሣሥበው ባንተ አለማሥተዋል ባዝንም ይበልጥ የሚያብከነክነኝ ግን ያለፈ ህይወቴ መጥፎ አሻራ አሁንም ያንተን ዉሳኔ ለማስቀየር ጉልበት እንዳለው መመልከቴ
ነው።
አሁን ያለው ውጫዊ ማንነቴ በሀዘን በብሥጭት በፊት የለመደውን ምቾት እና እንክብካቤ በማጣቱ የመጣ እንጂ ተፈጥሮአዊ ማንነቴ እንዳልሆነ ትረዳለህ ብዬ ነበር ያሠብኩት ።ምክንያቱም ሁሉንም በዝርዝር ባናወራም ለ 3 አመት በከባድ የህይወት ፈተና ዉስጥ እንደነበሩኩ ነግሬሀለሁ።
ሚኪ ሰው እኮ ኑሮውን ነው እሚመሥለው ፡አንተ ትግሥት ቢኖርህ
እና ዉስጤ ሰላም እንዲሰማው እና ያጣሁትን ፍቅርና እንክብካቤ
ብትሰጠኝ እንተ መጀመሪያ አይተህ የወደድካት ውጫዊ ማንነቷ
የጠፋው ምኛትን እሆንልህ ነበር።
አምስት ደቂቃ ቁጭ ብለን ብናወራ ሁሉንም ባስረዳህ ጥሩ ነበር
ግን አልሆነም።
ሚኪ እሁን እሄን መፃፌ እሚቀይረው ነገር ባይኖርም ካነበብከው
ይደረሰብኝንና የነበርኩበትን አስከፊ ሂወት ለማንም ሳላወራ
በውስጤ ይዤ የኖርኩትን ስቃይ እና እሳት ባትረዳኝም እንኳን
እንድታውቀው እሻለሁና እውነቱን እንደሚከተለው ፅፌልሀለሁ ።
የኔ እውነት እና ሂወት እሄ ነው•••
በተሠቦቼ እኔን እና ታላቅ እህቴን ብቻ ነበር የወለዱት እኔ
የወጣሁት በናቴ ሢሆን እናቴ በጣም ውብ ነበረች እባቴ ደግሞ
ከልክ በላይ የሚቀና ሠው ነበር በዚህ ጤነኛ ያልሆነ ቅናቱ የተነሣ
ከቤት እንካን እንድትወጣ አይፈልግም ነበር ፡በዚህ ምክንያት ብዙ
ግዜ እየተጋጬ ቤተሠቦቻ ጋር ስትሄድ ታርቀው እስክትመለሥ
ድረሥ በብስጭት በጣም ከመጠጣቱም በላይ ቤት በፍፁም
አያድርም ። ባጭሩ የያዘው የቅናት አባዜ ከእቅሙ በላይ ሆኖ ከ3
እመት በፊት ነበር የናቴንም የራሱንም ህይወት ያጠፋው ሁለቱንም
በእንድ ግዜ ማጣቴ ከባድ ሀዘን ውስጥ የከተተኝ ሳይበቃ እህቴ ጋ
በምኖርበት ሰአት ባሏ እህቴ እቤት የማትኖርበትን ግዜ እየጠበቀ
መከራዬን ያሳየኝ ጀመር በህቴ ላይ እንደዚ አይነት ነገር ከማረግ ፡
ሞቴን እንደምመርጥ ሲረዳ ፡ጠምዶ ያዘኝ በትንሽ በትልቁ ነገር
እየፈለገ ከህቴ ጋር መጨቃጨቁን የየእለት ሥራው አደረገው ፡እኔ
በምን እንደጠመደኝ ምክንያቱን ባውቅም እህቴ ለትዳሯ ያላትን
ክብር ፡ለሁለት ልጆቻ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ሥለማውቅ እውነቱን
ደብቄ ስብከነከን ኖርኩ ። ሚኪዬ እኔ ኮ ላለመሞት ብቻ ነበር
ምኖረው፡ ላለፉት 3 አመታት ከልቤ ሥቄ አላውቅም፡ደስ ብሎኝ
ያለ ሰቀቅን በልቼ አላውቅም፡በወላጆቼ ሀዘን እና በእህቴ ባል
ክፋት ፡እንኳንስ ውጫዊ ውበቴን ፡ ህይወቴንም በትግል ነበር
ያቆየሁት። ሁሌም ወላጆቼ የወደፊት ህይወቴ ብሩህና ደስታ የተሞላበት እንዲሆን እንደሚፀልዩልኝ ይነግሩኝ ነበር እሁን የሀዘን
ባህር ዉስጥ ብገባም አንድ ቀን ፀሎታቸው እውን ሆኖ አየው
ይሆናል። ወደፊት የተሻለ ወይም የባሰ ነገር ምን እንደሚገጥመኝ ባላውቅም ዛሬ ግን ወደ እዛ ህይወት ተመልሼ እልገባም። ራቂ
ብለሀልና እግሬ ወደ መራኝ በመሄድ እርቅልሀለሁ ። በመጨረሻ እንድ ነገር ልንገርህ ፡ቢያንስ ከነበርኩበት የሲኦል ህይወት እንድወጣ ምክንያት ስለሆንከኝ አመሰግናለሁ ።
እወድሀለሁ። ባንተ ሳይሆን የማዝነው በእድሌ ነው ።
ምኞት። ይላል •••
ደብዳቤውን ፅፋ ሥትጨርሥ
ከቀኑ 10፡45 ሆኗል በፍጥነት
ፖሥታ ዉሥጥ ከታ ካሸገች ቡሀላ ወደ እቃ ቤት በመግባት ፡ ከሻንጣዋ ውስጥ
እንዲት እነስ ያለች የተጣጣፈች ቦርሳ አውጥታ የተወሰነ ልብሥ ያዘች፡ ሻንጣዋን መልሳ ፡ እዛው ጠረጴዛው ስር ከመለሰች ቡሀላ ማንም ወደ እዛ ገብቶ እንደማያውቅ ከሁኔታው የተረዳች ቢሆንም ለማንኛውም ብላ
እዛው እቃ ቤት ያለውን የተበላሸ ፍሪጅ እንደምንም አንፏቃ
ጠረጴዛው ስር ያለው ሻንጣዋ እንዳይታይ በመከለል ትንሿን ቦርሳ
ይዛ ሣሎን ቤት ልጁን መጠበቅ ጀመረች። ልክ ከቀኑ 11፡20 ላይ
የቤቱ በር ተንኳኳ.....

🅙🅞🅘🅝 🅤🅢 👉 @yekeberedaha

🅒🅞🅜🅜🅔🅝🅣👇👇
@mood_zeki

♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ😂😂

24 Sep, 17:24


​​​😘ም..............ኞ..............ት😘


ክፍል 3
.
.
.
ከቆመችበት ሳትንቀሳቀስ ለደቂቃዋች ፈዛ በር በሩን ስትመለከት
ቆየች የሚኪ መሄድ እውን መሆኑን ስታረገግጥ ውስጧ
እርብሽብሽ ሲልባት እዛው እንዳለች ሸርተት ብላ ተቀመጠች።
ሚኪ አንጠልጥሎ ያማጣው ፌስታል አፉ እንደተከፈተ አጠገባ
ተቀምጧል።
ድንገት ዞር ስትል ውስጡ በወረቀት የተጠቀለለ ነገር
ተመለከተች።
እሄን ግዜ አባቷ ሊሞት ሲል ፅፎ ያስቀመጠው ደብዳቤ ፊቷ ለይ ድቅን
አለ ።
ፌስታሉ ውስጥ ያየችው ወረቀት የሆነ መጥፎ ዜና የያዘ መስሎ
ተሰማት ፈራች ። ወረቀቱን ከፌስታሉ ውስጥ አውጥታ
ለመመልከት አቅም አጣች።
እራሷን አረጋግታ ሚኪ ጋር መደወል እና ስለወረቀቱ መጠየቅ
እንደሚሻላት አሰበችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ሶፋው ላይ
ወዳስቀመጠችው ቦርሳዋ በመጠጋት ሞባይሏን አውጥታ ደወለች

አያነሳም ደግማ ደወለች አነሳውና ምንም ከማለቷ በፊት ቀድሞ
ገና እቤት መድረሴ እኮ ነው! አላት
አይ ቆየህ ብዬ አደለም ፌስታሉ ውስጥ ወረቀት ሳይ ግዜ ረስተክ
ሄደህ ከሆነ ብዬ ነው ስትለው
የቤቱ ቁልፍ ነው ምናልባት ከውስጥ መቆለፍ ከፈለግሽ ብዬ
ነው። መልሼ ደውላለሁ : ደውላለሁ እየነዳሁ ስለሆነ ነው ብሎ
ስልኩን ዘጋው።
ወረቀቱን ከፋፍታ ስትመለከተው ከቁልፉ በተጨማሪ ካስፈለገሽ
ከሚል ፅሁፍ ጋር ብር አስቀምጦላታል ደነገጠች!
የሚመለስ ከሆነ ብር ማስቀመጥ ለምን አስፈለገው አለች!
ያመጣላትን ምግብ ሳትቀምስ ለሰአታት በስጋት እንደተዋጠች ኮቴ
ስትጠባበቅ ብትቆይም ሚኪ ግን አልተመለሰም ጨነቃት ።ስልኳን
አንስታ ደወለች አያነሳም ። ቆይታ ሞከረች ስልኩ ጥሪ አይቀበልም መሸ ። እምትይዘው እምትጨብጠው ጠፋባት ፍርሀቷ ወደ እውነቱ የቀረበ መሰሎ ተሰማት ጉልበቷ ላይ ተደፍታ
ተንሰቀሰቀች።
6 ወር ሙሉ ምን እያለ ሲፅፍላት እንደነበር አስታውሳ ሞባይሏን
አነሣችና Fb ከፈተች የሱን የበፊት መልእክቶች ስታይ አዲሥ ዛሬ
የተላኩ 4 መልእክቶች እንዳሉ ምልክት አየች አንደኛዉን ከፈተችው
ከክፍለ ሀገር ጓደኛዋ ነች•••
"ወይ ምኞት እንዴት ነሽ ጒደኛዬ እኛ እዚህ ከማንም ባለጋሪ ጋር
ስንጃጃል እንቺ ዲያስቦራ ጠብሰሽ ሄድሽ እሉ ደስ ሢል "ይላል።
ድጋሚ ማልቀስ ጀመረች እየተንሰቀሰቀች ሁለተኛውን መልእክት
ከፈተችው ስልክሽን እታነሽም ምኞትዬ እንኳንም ከዛ ጨቅጫቃ የእህትሽ ባል ገላገለሽ ይላል ማንበብ እቃታት ጮክ ብላ ማልቀሥ ጀመረች •••
ማልቀሷን ድንገት እቁማ በሩን ከፍታ ወጣች አራተኛው ፎቅ
በረንዳው ላይ እንደቆመች ቁልቁል አፈጠጠች ዝለይ ዝለይ አላት
አይኗን ጨፍና ማሰብ እንደጀመረች•••
የመኪና ድምፅ ሰማች።
ውስጧ ሚኪዬ መጥቶ ቢሆንስ አለች ። የልቧ ትርታ በፍጥንት
መደለቅ ጀመረ። አይኗን ገልጣ ቁልቁል ስትመለከት መኪናው
የፊት መብራቱ ጠፍቶ እታች ካሉ ቤቶች በሚውጣው ጭላንጭል
ብርሀን አንድ ሰው የመኪናውን በር ከፍቶ ሲወርድ ተመለከተችና በፍጥነት ወደ ቤት በመግባት በሩን ከውስጥ ዘግታ በእንባ የራሰ ፊቷን ታጠበችና ፡ከቦርሳዋ መስታወት አውጥታ የተበታተነ ፀጉሯን
አስተካክላ፡ በድንጋጤ የደረቀ ከንፈሯን ቀባብታ በጉጉት እሷ
ወዳለችበት የሚመጣ የኮቴ ድምፅ መጠበቅ ጀመረች፡ ማንም
አልመጣም አስር ደቂቋ ያህል ከጠበቀች ቡሀላ የፈካው ስሜቷ
መደብዘዝ ጀመረ ትንሽ ጠብቃ አላስችል ሢላት በሩን ከፍታ በመውጣት፡
ቁልቁል መኪናው መኖሩን ስታይ ምንም ነገር የለም፡ ወደ ቤት
በመግባት ሞባይሏን በመያዝ ሩጫም እርምጃም በማይባል
ፍጥነት ቁልቁል ተምዘገዘገች፡ እታች እንደደረሰ ምንም የለም።ወይኔ ጉዴ ምኞት እያበድሽ ነው በቃ ለየልሽ እሄን ሁሉ ግዜ ብዙ መከራ ሲፈራረቅብሽ በፅናት ተወጠሽ በማታውቂው ሀገር
መጥተሽ በንድ ቀን ልታብጂ ነው እንዴ ተረጋጊ ምኛቴ ተረጋጊ
አለቻት እራሷን አይኖቿ እንባ እንዳዘሉ። ጭለማ ውስጥ አንድ ጥግ በመያዝ ተቀመጠች፡ ንፋሡ የተረበሸ ስሜቷን በመጠኑም ቢሆን ቀለል ሢያደርግላት ፡ወደታች እንደወረደችው ሣይሆን
በጣም በዝግታ ወደ ቤት ገብታ ተዘረረች ብንን ስትል ከቀኑ
አምስት ሠአት ሆኗል ስልኳን ሥትመለከት ከድያስቦራው አዲስ
መልእክት ሥታየው ""ለአሥቸኳይሥራ ተጠርቼ ሌላ ቦታ ሄጃለሁ
ሥለምቆይ አትጠብቂኝ ፡ለመሳፈሪያ የሚሆን ገንዘብ አንድ ልጅ
ዛሬ 11 :00 ሠአት ላይ ይዞልሽ ይመጣል :ለትራንስፖት
እሚቀርብሽ ቦታ አልጋ ያስይዝሻል የቤቱን ቁልፍ ለሡ ሥጭው"
ይላል ስልኩን ግድግዳው ላይ አፈነዳችው አበደች...

ይቀጥላል.........