🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦 @al_islam_media_et Channel on Telegram

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

@al_islam_media_et


🇸🇦ቅድሚያ ለተውሂድ🇸🇦

🕋ቁርአን እና ሀዲስ🕋

✍️የሰሀቦች ታሪክ⚔️🛡️🏹

✍️ የሰለፎች ታሪክ

✍️የኡለሞች ታሪክ📝

👑የሙስሊም_መንግስታት_ ታሪክ⚔️

⚔️የሙጃሂዶች_ታሪክ🛡️

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦 (Amharic)

የ🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦 ቤት ነው የሰማይ አባቶችና እድሜያቸውን ለመቀነስ ያላቸው የሰማይ ታሪኮችን ዳገት ሊጠቀመው ይችላሉ። በዚህ ቤት የሚሰነጥቅ የሰማይ ታሪኮችን በተመለከተ ቀጥታ ማንም እንዴት ታሪኩን ለቀቃይ እንደጥሩ ደብዳቤ እንደሆነ ማስታወቂያ እየሰጠ ሲያስችል የምንድን ነው። የሰማይ ታሪኮች ፣ ተስፋዬን እና ተመለከባቸውን አዳም ማዝናበትን አስታውቅ የተሻለ ይደረጋል። ማንኛውም ሰᎮን ኮልፊሽን በሚሰጣበት ቀን ተይዞ ካናዳው ወዲህ አስተዋወቃል።

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

10 Jan, 11:06


በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?

📌በሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች ሕንፃዎች ተቃጥለዋል።

📌በግዙፉ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።

📌በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።

Al Ain

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

10 Jan, 08:10


የጋዛ እጣ ያለ ምንም ቦንብ በአሜሪካ ላይ እየደረሰ ነው። አላህ ሆይ እሳቱን መቆሚያ የሌለው አድርገው።

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

06 Jan, 10:22


ኹጥባ

በቀን 26/05/15 በወራቤ ከተማ በአዩበል አንሷሪይ መስጂድ የተደረገ የእለተ ጁሙዐህ ኹጥባ!!!


🎙 ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ)

ርእስ:- የረጀብ ወርን በተመለከተ!
https://t.me/abdulham/2356

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

06 Jan, 10:12


👉 የረጀብ ቢዳዓዎች

       በረጀብ ወር በጣም ብዙ ኢሳላም የማያውቃቸው በዒባዳ ስም የሚሰሩ ቢዳዓዎች አሉ ። ከእነዚህ ውስጥ ሶላቱ ረጛኢብ የሚባሉ በወሩ የመጀመሪያ ጁማዐህ በመጝሪብና ዒሻእ መካከል የሚሰገዱ 12 ረካዓዎች እንዲሁም ረጀብ 27 ለይለቱል ኢስራእ ወል ሚዕራጅ ብለው የሚያከብሩት ባጠቃላይ ኢስላም የማያውቃቸው ቢዳዐዎች ናቸው ። ኢስራእና ሚዕራጅ በትክክል በየትኛው ለሊት እንደነበር በትክክል አይታወቅም ። ቢታወቅም አይከበርም ። ምክንያቱም መልእክተኛውም ሶሓቦችም አልሰሩትም ።
     የአላህ መልእክተኛና ሶሓቦቻቸው የማያውቁት ወደ አላህ መቃረቢያ ተብሎ የሚሰራ ዒባዳ ትርፉ ድካም ነው ። አላህ ባሮቹ ወደርሱ የሚያቃርባቸው ለመልእክኛው ያላሳወቀውና መልእክተኛው ለኡመታቸው ያላደረሱት መልካም ስራ የለም ። ከአላህ ምንዳ የሚያስገኝና ወደርሱ የሚያቃርብን የዒባዳ አይነት በሙሉ ወደኛ ተላልፏል ። ሶሓቦቻቸው በተግባር ሰርተው አሳይተዋል ። ስለሆነም ነው አላህ በሚከተለው ቃሉ ሶሓቦችን እንድንከተል ያዘዘን ።
  « وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ »
                         التوبة   ( 100)
  " ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል ፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው ፡፡ "

      የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – የሳቸው ትእዛዝ የሌለበት ዒባዳ ወደ ባለቤቱ ተመላሽ መሆኑን በተለያዩ ሐዲሶች ነግረውናል ከእነዚህ ውስጥ ለማሳያ የሚከተለውን ሐዲስ እንመልከት : –

 " مَن أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو ردّ "
                 متفق عليه
   በዚህ ጉዳያችን ( እስልምናችን) ላይ ከርሱ ያልሆነን ያመጣ እሱ ተመላሽ ነው " ( ስራው ወደ አላህ አይደርስም በባለቤቱ ላይ ተመላሽ ነው )  ።
        እነዚህና ሌሎችም ኑሱሶች በረጀብም ሆነ በሻዕባን መረጃ ያልመጣበት የተለየ ምንም አይነት ዒባዳ እንደማይፈቀድ ያስረዳሉ ። አላህ  አውቀው ከሚጠቀሙ ባሮች ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

02 Jan, 07:44


ከሕመም ጋር አራት ልጆችን ያለአባት የማሳደግ የእናትነት ብርቱ ፈተና…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጸሃይ ተሻለ ትባላለች፤ የአዲስ አበባ ነዋሪ ስትሆን ሕመምተኛ እና የአራት ልጆች እናት ናት፡፡

የሕይወት መልኩ ብዙ ነው፣ አንዴ ጥሩ የሆነው ሌላ ጊዜ መጥፎ ገጽታውን ሊያሳይ ይችላል፡፡

ጸሃይ ተሻለም ከባለቤቷ ጋር ትዳር ስትመሰርት ደስተኛ ነበረች፤ ትዳራቸው የሰመረ ሆኖም ጥንዶቹ በልጅ ተባረኩ፡፡ ልጅ ሲመጣ ትዳር ይደምቃልና የጸሃይና ባለቤቷ ፍቅርም በልጆች ፍቅር ታጅቦ ዓመታትን አሳለፈ፡፡

ይሁን እንጂ ጸሃይና ባለቤቷ ሶስት ልጆችን ከወለዱ በኃላ በተለያዩ ምክንያቶች ትዳራቸው እክል አጋጠመው፤ ጥንዶቹ ልዩነትን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ወደ ግጭት አካላዊ ጉዳት አመሩ፣ በዚህ ሁኔታ ላይም ጸሃይ አራተኛ ልጇን ነፍሰ ጡር እያለች ባለቤቷ ልጆቹን አደራ እንኳን ሳይል ጥሏት ጠፋ፡፡

ጸሃይ ከባለቤቷ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በመለያየታቸውም አሁን ላይ አራት ልጆችን ብቻዋን የማሳደግ ሃላፊነት ተሸክማለች፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት ከባለቤቷ ጋር ልጆችን ለማሳደግ እና ሕይወትን ለማሸነፍና በርካታ ውጣ ውረድ እንዳሳለፈች ትናገራለች፡፡

ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ.. በአሁኑ ወቅትም አባት የት እንዳለ ባለመታወቁ ከማይድን ሕመም ጋር አራት ልጆችን ለማሳደግ ብርቱ ችግር ውስጥ እንደምትገኝ አንስታለች፡፡

ልጆቹን ለማሳደግና ትምህርት ለማስተማር ልብስ ከማጠብ ጀምሮ የተለያዩ አድካሚ ሥራዎችን እንደምትሰራ ነው የገለጸችው፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ መሰል ሥራዎችን በህመም እየተሰቃየች ሰርታ አራት ልጆችን ማሳደግ ከአቅሟ በላይ መሆኑን ለፋና ዲጂታል አስረድታለች።

ይህን ተከትሎም ልጆቿ ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ እና የእለት ጉርሳቸውን ለማግኘት ጎዳና በመውጣት ለልመና መዳረጓን አብራርታለች፡፡

''ያን ቀን እንደወትሮው ቤት ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ የለም፤ልጆቼን እያለቀስኩ አየኋቸው፤ ፊታቸው ጠውልጓል፤ እርቧቸዋልም፤ ከዛም የልጆቼን ርሃብ ለማስታገስ እግሬ ወደ አመራኝ ጎዳና ወጣሁ'' ትላለች ልመና የወጣችበትን ቅጽበት ስታስታውስ።

በእርግጥ ጎዳና ወጥቶ እንደመለመን ከባድ ፈተና የለም የምትለው ጸሃይ÷ አማራጮቿን ሁሉ ሞክራ የልጆቿን ቀጣይ ሕይወት አደጋ ላይ ላለመጣል የቀራት ብቸኛ አማራጭ የሰዎችን ትብብር መጠየቅ እንደሆነ ተናግራለች፡፡

7ኛ ክፍል የሆነው የመጀመሪያ ልጇ እንደ እርሷ የማይድን ሕመም ተጠቂ መሆኑን ስትናገር እንባዋ ይተናነቃታል፡፡

ሁለተኛ ልጇ 2ኛ ክፍል፣ ሶስተኛ ልጇ የቅድመ መደበኛ ተማሪ እንዲሁም የመጨረሻ ልጇ ደግሞ የ1 ዓመት ከሶሶት ወር ዕድሜ እንዳላት ገልጻለች፡፡

እናትነት፣ አቅም ማጣት እና የልጅን ቀጣይ እጣ ፈንታ የመወሰን ከባድ ፈተና ከሕመሟ ጋር ተዳምረው በንግግሯ መሃል የምትለው ይጠፋታል፡፡

ከሁሉም በላይ ልጆቼን አስተምሬ ጥሩ ደረጃ እንዲደርሱ ፍላጎት አለኝ የምትለው ምስኪኗ እናት፤ ልጆችም በጥሩ ሁኔታ ትምህርታቸውን ተከታትለው የተቸገሩ ሰዎችን የመርዳት ሕልም እንዳላቸው እንደሚነግሯት አንስታለች፡፡

አሁን ላይ ከልጆቿ ጋር የምትኖርበት ቤት ለአደጋ የሚያጋልጥ ከመሆኑ በላይ ውሃ እና መብራት እንደሌለው እና ምቹ አለመሆኑን አብራርታለች፡፡

ልጆችን ተከታትሎ ማስተማርና የእለት ጉርስ መፈለግም የእናትነት የእለት ጭንቀቷ መሆኑን በተሰበረ ልብ ታስረዳለች፡፡

ስለሆነም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያለባትን ጽኑ ችግር ተረድተው እጃቸውን እንዲዘረጉላት እናት ጸሃይ ተማጽናለች፡፡

ባለታሪኳን ማግኘትና መርዳት ለሚፈልግ👉ጸሃይ ተሻለ ዘሪሁን፤ስልክ፣0923149392

በመላኩ ገድፍ

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

01 Jan, 19:59


"አንድ አሳዛኝ እውነታ አለ እሱም መጅሊሱ የሚመራው በዱኒያ ሰው እንጂ በዲን ሰዎች አይደለም። ለዚህም ምስክር ስራቸውን ተመልከቱ ቁርአን ሀዲስን ነገር ችላ ብለውት በራሳቸው ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ለዱኒያቸው በሚመች መልኩ እንደፈለጉ በዲን ስም ይጨማለቃሉ። እና ከዚህ ነጂስ ማለቴ መጅሊስ ምን አይነት ተስፋ ነው የምታደርጉት?"

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

27 Dec, 13:50


ድብቁ የሙስሊም እህቶቻችን የእርቃን ፎቶ ንግድ!

ሰሞኑን ከአንድ የስራ ባልደረባዬ ጋር ስናወራ ዲጂታል መፅሄት ላይ የሠፈረ አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ ላከልኝ።
ጸሀፊው ምንተስኖት ደስታ ይባላል በሥነ-ሕብረተሰብ (ሶሲዮሎጂ) ከሐረማያ ዩንቨርስቲ የተመረቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት በስንቅ ዩዝ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት ማናጀር ነው ጥናታዊ ፅሁፉም ቴሌግራም ላይ ቻናል ግሩፕ ከፍተው የታዋቂ ሴቶችን ወይንም የድሮ የዝሙት ጓደኞቻቸውን እርቃን ፎቶ እየለቀቁ ብር ስለሚያስከፍሉ የቻናብ ባለቤቶች ያትታል።

ለአንድ እርቃን ፎቶ ከ 3000- 6000 እንደሚያስከፍሉም በጥናታዊ ፅሁፉ ሰፍሯል። እኔን ቀልቤን የሳበኝ እና ከባልደረባዬ የሰማሁት የሙስልም እህቶቻችን ከዚህም በላይ ከፍ ያለ ዋጋ እንዳለው ነው። በእርግጥ ለማመን ቢከብደኝም በገበያው ብዙም ስለማይገኝ ይሁን ለሙስሊም እህቶች ያላቸው መጥፎ እሳቤ በውድ ዋጋ እንደሚቸበቸብ ለዚህ ዋነኛ ተጠቂዎች የአረብ ሀገር እህቶች እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሆኑ ነው የሰማሁት።

በእርግጥ ግቢ ውስጥ በነበርንበት ሰአቶችም ይሁን ከግቢ ከወጣን በኋላ አንዳንድ ሽምግልናዎችን ታዝበናል። ከዛም አልፎ ህግ ደረጃ የደረሱም ነበሩ። ሽያጭ ደረጃ ይደርሳል የሚል ምንም አይነት ግምት አልነበረኝም።
በእርግጥ በሰላም ጊዜ ፍቅር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ የሚላላኩዋቸው ልቅ ምስሎች ናቸው በኋላ በጠብ ጊዜ ህይወታቸውን የሚያመሰቃቅሉት።

ከሁሉም የከፋው ደግሞ. . .

🔴 እህቶቻችን በማያውቁት መንገድ አብረው ከሚኖሯቸው ሙስሊም ካልሆኑ እህቶች ወይንም ዲናቸውን ጠንቅቀው በማያውቁ ሙስሊም እህቶች ተቀርፀው የሚላኩ ምስሎች ናቸው። በተለይ ሙተነቂብ ሲሆኑ ደግሞ በካሜራ ያድኗቸዋል አሳልፈው ለባዕድ ወንድ ይሰጧቸዋል።

🟢 ይሁን እና ብዙ ኡዝታዞች እና መሻይኾች ይህንን ጉዳይ ዘርዘር አድርገው ህዝበ ሙስሊሙን ቢያነቁበት ባይ ነኝ።

ኮፒ

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

21 Dec, 10:52


"የክፋት መንገዶች 3 ናቸው።

አመፀኛ ጠባይ ፣ ቅናት እና ስስት።

አመፀኝነት ሰይጣንን ከመታዘዝ ከልክሎታል ።

ቅናት ቃቢል ወንድሙን ሀቢልን እንዲገል አድርጎታል ።

ስስት አደምን ከጀነት አባሮታል።"

🗣:-ሀሰን አል-በስሪ(ረ.ዐ)

Copy

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

19 Dec, 10:35


አይቶ መለፍ እጅግ በጠም ይከብደል፡፡
እባካቹ እናንተ ደጋጎች ሼር ሼር አድርጉላቸው

ወዳጆቼ በዚ ከበድ ወቅት የበረከት ስራ እንስራ መርዳት ቢያቅተን ሼር ማድረግ እራሱ ትልቅ እርዳታ ነው:: ይህ የምትመለከቱወት ህፃን የሁለት አመት ከሶስት ወር ህፃን ነት የካንሰር ታማሚ ነት ካንሰር በሽታ የያዘውት ከተወለደች ከሶስ ወር  ጀመሮ የካንሰር ታማሚ ነት ይሄው እሷም እናቱወም አባቱወም ሁለት አመት ሙሉ አሚን አጠቀለይ ሆስፒተል ንብረታቸውን ሸጠው እሷን በማስታመም ላይ ይገኛሉ ህፃኑወን ካንሰሩ አይንወን አሳውሮታል አንደኛው አይንወ በቀዶ ጥገና ወጥቶለት አንደኛውንም አይኑወ ከሰሞኑ እንደሚወጣ ከዶክቶሮቹ ሰምቻለው በዚያ ላይ አንድ አፍንጫወን ደፍኖታል እናትና አባትወ  ለሁለት አመት ከልጃቸው ጋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ አሁን ላይ ከስቃዩም በላይ የህክምና እና የመድሀኒቱ ወጪ ሌላ ስቃይ ነው የሆነባቸው  ለመድሀኒቱና ህክምና ለአስራ አምስት ቀን ሰባ ሺ ብር ይፈልጋሉ አሁን ላይ ውጪ ሄደ የመታከም እድልም አለት ለህክምናወ ወጪ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈልጋልጋሉ እና ልጅቷም በስቃይ ውስጥ እናትና አባትም በስቃይና ጭንቀት ውስጥ ናቸው እንድረስላቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነው የቻልነውን  አነሰም በዛ ሳንል እጃችንን እንዘርጋላቸው ስል በፈጠሪ   ስም እንማፀናለን መርዳት ለምትፈልጉ
ንግድ ባንክ 1000603332346 እስማኢል ሀሠን አብደላ (Ismail Hassen)
ስልክ ቁጥር 0960067157

የማትችሉ በፀሎትና ሼር ሼር ሼር በማድረግ እንርዳቸው
ሼር ሼር ሼር በማድረግ አይከፈልበትም


☞ ሁለችንም 5 ብር ብንረደት ልነሰክመት እንችለለን፡፡




☞ ሁለቹም ለፈጠሪ ብለቹ  ሲትረዱ የረደቹበትን መረጀ በዚ  profile  አስቀምጡልን፡፡

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

14 Dec, 04:28


#የዓለማችን_አስገራሚ_ሶላት 💔💔

በሲድናያ እስር ቤት ታሳሪ የነበረ የተጅዊድ መምህር ሸይኽ እንዲህ ይተርካል ፦

ሙሉ እርቃን አድርገው አራቆቱኝ። ፀጉሬንም ላጩት ። በአንድ ክፍል ያጎሩን ሁሉ እርቃናችንን ነበርን። ከሴራሚክ ውጭ የምንቀመጥበት ነገር የለም። ልብሳችን ሀዘን፣ ህመም፣ርሃብና ማቃሰት ነበር። ቦታው ጠባብ ስለነበር እድሌ ሆነና ማደሪያዬ ሽንት ቤቱ ጋር ሆነ። የምበላው የምቀመጠውና የምተኛው እርሱ ጋር ነው።

አንድ ሰው ውሃ ሽንት ሲጠቀም ከሽንቱ የተወሰነው ይረጭብኝ ነበር። ደግነቱ ጥቂት ምግብ እንጅ ስለሌለ «ትልቁን ሽንት» በቀን አንድ ጊዜ ወይም በ2 ቀን ወይም በ3 ቀን አንድ ጊዜ ነበር እስረኞች የሚጠቀሙት። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ሶላት የምሰግደው አይኔን በማንቀሳቀስ ብቻ ነበር ።ሙሉ ለሙሉ እርቃን ሆኜ።

ምክንያቱም በእስር ቤቱ ህግ ሶላት የሚሰግድ ሰው ቅጣቱ የሚገለፅ አይደለም! ሞ* ት ከርሱ ይሻላል። የአሰድ የእስርቤት ጠባቂዎች ሲሰግድ ያገኙትን ሰው ወይ ወገቡን ሰብረ* ውት፣ ወይ 5 የጎን አጥንቱን ሰብረ* ውት ፣ ወይ አይኑን አጥ* ፍተ* ውት ወይ አጥንቱን ሰብ*ረው* ት ወይ እጁን ሽ* ባ አድርገውት ወይ እግሩን አንካ* ሳ አድርገውት እንጅ አይገኝም!

ስለሆነም ለሁለት ወር በሽንት ቤት ፣ ሙሉ እርቃን ሆኜ በነጃሳ ቦታ ወደ ቂብላም ሳልዞር አይኔን በማንቀሳቀስ ብቻ ሰገድኩ! አንዳንዴ እየሰገድኩ የአንዱ እስረኛ ሽንት ሲንጠባጠብብኝ ይሰማኝ ነበር! ይላል።

#ላ_ኢላሃ_ኢለላህ!
የዚህ አይነት ሶላት ሰምታችሁ ታውቃላችሁ! ?
የዚህ አይነት ጨ*ካ*ኝ አምባ*ገነ*ን ስርአትስ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

10 Dec, 20:57


👉 ራቁት ሆኖ ከመዝፈን በአላህ ላይ ማጋራት ይበልጣል !

     ወንጀል በየትኛውም ሀገር በማንም ቢሰራ ወንጀል ነው ። የሆነ ሀገር ስለተሰራ ከወንጀልነት አያወጣውም ። ሪያድ ላይ በሆነ ፕሮግራም ላይ የነበረ አሳዛኝና አስቀያሜ ተግባር ሶሞኑን ሰዎች ሲያወሩ ሰምቼ ምንድነው ብዬ ለማየት ሞከርኩ ። ድርጊቱ በጣም ፀያፍና አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ነው ። የካዕባ ምስል ተሰርቷል ለብሰዋል ለማለት የማያስደፍር ዘፋኝ ሴቶች በምእራባዊያን አኳኋል ያብዳሉ ። የዚህ አይነቱ ተግባር ፍፁም ከኢስላም አስተምሮ የራቀ አስቀያሚ ተግባር ነው ። ይህን ክስተት በተለይ የግብፅና የፍልጢን አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች የሳውዲን መሪዮች ለማክፈርና ለመርገም ምቹ አጋጣሚ ሆኖላቸው አየሁ ።
     በጣም የሚገርመው አንድ የእናቱን ፊት የተዋሰ የሚመስል የግብፅ ጋዜጠኛ ከሱረቱል ق የተወሰኑ አንቀፆችን ቀርቶ አላህ ፊት የቂያማ ቀን ስለመቆምና ስለሚኖረው ጭንቅ ከተናገረ በኋላ ለሳውዲ መሪዮች ጥያቄ ያቀርባል ። ሱብሓነላህ እንዴት የሚገርም ለዲን መቆርቆር ነው በጣም ደስ ይላል ። በዚህ መልኩ ወንጀልን መፀየፍና ማውገዝ ከኢስላም መርሆች ውስጥ ዋነኛው ነው ።
      ነገር ግን እኔ ለእነዚህ አካላት ጥያቄ አለኝ እነዚህ ወንጀሎች ሳውዲ ውስጥ ሲሰሩ ነው በዚህ መልኩ የምትቆረቆሩትና የምታወግዙት ወይስ ሀገራችሁም ላይ ? ለመሆኑ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ለአላህ እንጂ የማይገቡ የአምልኮ አይነቶችን መስጠት አሁን እያወገዛችሁት ካለው ወንጀል እንደሚበልጥ ታውቃላችሁን ? በግብፅ ምድር ላይ የአሕመደል በደዊ ቀብር ከ3 · 5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ጠዋፋ ሲያደርግበት ፣ የቀብሩን አፈር በጥብጦ ሲጠጣ ፣ ከአላህ እንጂ የማይጠየቁ እንደ ከጭንቅ አውጡኝ ፣ አፍያ ስጡኝ ፣ ርዝቄን አስፉልኝ ፣ ዘር ስጡኝ ፣ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ለአሕመደል በደዊና ለዱሱቂ ፣ ለዘይነብና ለመሳሰሉ ሙታኖች ሲጠይቁ የት ነበራችሁ?  የዚህ አይነቱ የቀብር አምልኮ መንግስታችሁ ባጀት መድቦ ሰራዊት አሰልፎ እንደባአል እንዲከበር ሲያደርግ ታወግዛላችሁ ? ወይስ ይህ በናንተ ሀገር ሲሰራ ወንጀል አይደለም ? ቤቱ በመስታወት የሆነ ሰው በሰው ቤት ላይ ድንጋይ አይወረውርምና ተረጋጉ እንላለን ።
     ሳውዲ ላይ የሚሰራ የትኛውም ወንጀል ከወንጀልነት ሊወጣ አይችልም ። በወንጀልነቱ ይወገዛል ። ነገር ግን መሪዮችን ለማክፈር መንገድ አድርጎ መጠቀም የኸዋሪጆች አካሄድ ነውና ተጠንቀቁ ነው የሚባለው ። የሳውዲ መሪዮች ደማቸው አረንጓዴ ነው አይነኩም ለማለት አይደለም ። ከመሪዮች የሚሰራ ስህተት የሚታረምበት መንገድ መልእክተኛው ነግረውናል ። ሰለፎችም ተግብረው አሳይተውናል ። የመሪዮችን ስህተት በኹጥባ ፣ በሙሓደራ ፣ በጋዜጣ ፣ በመፅሄት ፣ በተለያዩ ሚዲያዎች ማሰራጨት የነብዩና የሶሓቦች መንገድ የሚከተሉ ሰዎች አካሄድ አይደለም ።
     መጥፎን ነገር ስንለካ በሸሪዓ መለኪያ እንጂ  በስሜታችን መሆን የለበትም ። የወንጀሎችን ክብደትና ቅለትም እንደዚሁ ይህን መሰረት አድርገን ነው ሁሉንም በልኩ ማውገዝ ያለብን ። ሳውዲ በሽርክ ጉዳይ አንገት እየቀላች ድግምተኞችንና መተተኞችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣች ከተለያየ ሀገር መውሊድ ለማክበር የተሰበሰቡ ሱፍዮችን እየበተነችና አሰተባባዮችን በቁጥጥር ስር እያዋለች ማየት ያልቻሉት ወይም አይተው አላየንም የሚሉት በሀገራቸው ላይ ከሚሰራው አመፅና ወንጀል ሊወዳደር የማይችል ወንጀል ሳውዲ ላይ ሲሆን መሪዮች ለማክፈር መንገድ አድርጎ መጠቀም በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ።
    መሪዮች ሲያጠፉ በግል ይመከራሉ ዱዓእ ይደረግላቸዋል ። እንጂ በአደባባይ ከበሮ አይደለቅም ። ምክንያቱም የዚህ አይነቱ ተቃውሞ መሪዮቹ አፀፌታውን እንወስዳለን ብለው የበለጠ ጥፋት ሊመጣ ስለሚችልና መሪና ተመሪ መካከል ያለው መተማመን ጠፍቶ ሀገር ስለሚበጠበጥ ነው ። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ወንጀል ማንም የትም ቢሰራው ወንጀል ነው ይጠላል ይወገዛል ። ነገር ግን የሚወገዝበት መንገድ ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ መሆን አለበት ነው ትልቁ ነጥብ ።
    በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የሆነ ሰው ነፍሰጡር ሴትን ገደለ ፣ እናቱን ተገናኘ ፣ ከእህቱ ወለደ ፣ አስገድዶ ደፈረ ፣ ህፃን አረደ ሲባል ቢሰሙ ይሰቀጥጣቸዋል ይዘገንናቸዋል በጣም ያወግዙታል እንደ ጭራቅ ያዩታል ። ይህ ባልከፋ ነበር ። ከባድ ወንጀል ስለሆነ ሊወገዝ ይገባልና ነገር ግን እገሌ የሚባል ሰው የቀብር አፈር በጥብጦ ጠጣ ፣ ቀብር ጋር ሄዶ ጫማውን አውልቆ ስልኩን ዘግቶ እያለቀሰ የሞተውን ሰው እርዱኝ ድረሱልኝ አለ ፣ ሌላኛው ለጂኒ አርዶ ደሙን ጠጣ ፣ ሌላኛው ልጅ ፍለጋ ጠንቋይ ቤት ሄደ ቢባሉ ምንም አይመስላቸውም ። ይህ ሊስተካከል ይገባል ሙስሊሞች በሽርክና በቀባባድ ወንጀሎች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲያውቁ ማስተማር ያስፈልጋል ።
    አላህ በሱ ላይ ማጋራትን በፍፁም አልምርም ሲል ከሽርክ በታች ያሉ ወንጀሎችን ለሻው ሰው እንደሚምር ነግሮናል ። ሽርክ ስራን በሙሉ አበላሽቶ የዘላለማዊ ጀሀነም ባለቤት ሲያደርግ ከባባድ ወንጀሎች ግን አላህ ለሻው ሰው የሚምር ሲሆን ከቀጣውም በወንጀሉ ልክ ተቀጥቶ ከእሳት እንደሚወጣና የጀነት እንደሚሆን ኢስላም ያረጋግጣል ።
    ታዲያ ግብፅ ውስጥ ያለው የቀብሮች አምልኮ ሳውዲ ውስጥ ከተሰራው የሴቶች ተራቁቶ መዝፈን ጋር ሲነፃፀር የሰማይና የምድር ያክል ልዩነት አለው ። ነገር ግን ሁሉም ወንጀሎች በመሆናቸው ይወገዛሉ ይሁን እንጂ አይገናኙም ።

https://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

09 Dec, 19:07


"ሴት ልጅ  ገላዋን በኒቃብ በጅልባብ እስካልሸፈነች ድረስ እርክሰት ውስጥ ነው ያላቸው።"

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

08 Dec, 19:33


ስንፈልግ ትልቅን ነገር መፈለግ ይገባል

ስናልም የምናልምለትን ነገር ጥቅሙን መረዳት አስፈላጊ ነው ሂማችን ከፍ ማለቱ ነገራችንን ከፍ ያደርጋል ።

إِنَّما تنَالُ المَطالِب علَى قدرِ همَّةِ الطَّالب

እንደሚሉት በትንንሽ ነገር መጠመድ ትንንሽ ሆኖ መኖር እና በውዳቄ ነገር ውስጥ ተሳስሮ የመኖርን ችግር ይፈጥራል ።

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

06 Dec, 13:11


#ሱብሃነላህ

በብሪታንያ መሀመድ የሚለው ስም ቁጥር አንድ የህጻናት ስም ሆነ

በብሪታንያ በአንድ ዓመት ውስጥ ከተወለዱ ህጻናት ውስጥ ከ4 ሺህ 600 በላይ ያህሉ ስማቸው መሀመድ ተብሎ ተመዝግቧል

ለዓመታት ለብዙ ህጻናት ይሰጥ የነበረው ስም ኖህ የሚለው ነበር

ምንጭ ፦አል አይን አማርኛ

ሼር ማድረግ እንዳይረሱ
https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

02 Dec, 20:28


ምክር ቢጤ ለኒቃብስቷ ¡

ዲን በተግባር ነው
አንዳንድ እህቶች ኒቃብ ይለብሳሉ ለካሜራ ያላቸው ፍቅር ግን የተለየ ነው ።
በፎቶ አይኗን ከኒቃቡ ጋር ቀርፃ ኒቃብስቷ እያለች ትለጥፋልች ፣ አንዳንዴ ባይተዋሯ ፅኚ እያለች ፣ ዲናዊ ምክር ትለጥፋልች!
ከስር አንዱ ወንድ ይገባና ጌታዬ ሆይ እንደሷ ያለችን ሚስት ዘውጀኝ እያለ ይኸርፋል ! ልብ በሉ የፊትና በር እንዴት ሊከፈት እንደሚችል ሳታውቅ ለፊትናው ሰለባ ትሆንና ለአሏህ ብለው መካሪዎቿ ሲመክሯት እበካችሁን አትጩሁብኝ ፣ መብቴ መሰለኝ፣ ገና አሳያቹሃለው ወዘተ ነው መልሷ!

እንዲህ አይነት የቀለጠ አካሄድ በጣም ደባሪ ነው " ዲን –ሱና ማለት በትግበራ እንጂ በሽለላ በጓንት በኒቃብ ሽፋን ስርዓት የሌላቸው ታግባሮችን እንጠንቀቅ ።

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

24 Nov, 19:05


🔷  የተብሊግ ጀማዓዎች ማን ናቸው

              ክፍል ስድስት

          ዳዕዋ ኢለላህ

       የተብሊግ ጀማዓዎች ትልቁ ትኩረታቸው ኹሩጅ ፊ ሰቢሊላህ የሚል ነው ። እንደሚታወቀው እነዚህ ጀማዓዎች የዳዕዋቸው ዋናው ነጥብ ፈዳኢልን ( ቱሩፋትን ) ማሳወቅ ነው ። ዳዕዋቸው ትኩረቱ ፈዳኢል ላይ ያተኩራል ። ይህ ማለት ደግሞ አላህ የሰው ልጆችን ከኩፍርና ሽርክ ጨለማ ለማውጣት 124 ሺህ ነብያት የላከበትን መርህ ይቃረናል ። ምክንያቱም አላህ ነብያቶች የላከው ለህዝቦቻቸው አልህን ብቻ እንዲያመልኩና ጣኦታትን እንዲርቁ እንዲያስተምሩ ስለሆነ ነው ። ይህን አስመልክቶ ቁጥር ስፍር የሌለው የቁርኣን አንቀፆች መጥቷል ። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን እንይ : –

« وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ ۖ فَمِنْهُم مَّنْ هَدَى اللَّهُ وَمِنْهُم مَّنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ الضَّلَالَةُ ۚ فَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ »
                 النحل    ( 36 )
" በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል ፡፡ ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ ፡፡ ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ "፡፡

  « لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ »
             الأعراف  ( 59 )
ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡»

« وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ قَدْ جَاءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ فَأَوْفُوا الْكَيْلَ وَالْمِيزَانَ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ »
            الأعراف  ( 85 )
" ወደ መድየንም (ምድያን) ወንድማቸውን ሹዓይብን (ላክን)፤ አላቸው ፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም ፡፡ ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ በእርግጥ መጥታላችኋለች ፡፡ ስፍርንና ሚዛንን ሙሉ፡፡ ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) አታጉድሉባቸው ፡፡ በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ ፡፡ ይህ ምእምናን እንደኾናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው ፡፡»

«  وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ »
                 هود ( 61 )
" ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን) ፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ ፡፡ ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ (ለለመነው) ተቀባይ ነውና» አላቸው " ፡፡

     እነዚህ ከብዙ ነብያቶች ለምን እንደተላኩ ከሚገልፁ አንቀፆች ጥቂቶቹ ናቸው ። ነብያቶች ስራቸው ዳዕዋ ነበር ስለዚ ዳዕዋ አደርጋለሁ የሚል አካል ዳዕዋው ነብያቶች ያደረጉት ዳዕዋ መሆን ይነርበታል ። ወደ ተውሒድ መጣራትና ከሽርክ ማስጠንቀቅ ። የተብሊግ ጀማዓዎች ግን በተቃራኒው ወደ ተውሒድ የሚጣሩትን ጠላት አድርገው ሰው እንዳይሰማቸው ያስጠነቅቃሉ ። ወሀብይ እያሉ ያጠለሻሉ ። ዳዕዋ ብለው ይወጡና መሻኢኾች ያስቀመጡት አዳብ ብለው በስድስቱ የሶሓባ ባህሪይ በሚሉዋቸው ነጥቦች ብቻ ሙሓደራ ያደርጋሉ ።
      አብዛኞቹ ዳዕዋ ብለው የሚወጡ ሰዎች ከተለያየ ቦታ የሚሰበሰቡ ስለሆኑ ስለእስልምና እንኳን በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ናቸው ። እነዚህ ሰዎችን አሳምነው እንዲወጡ ያደርጉዋቸውና ተመድበው የሆነ መስጂድ ይሄዳሉ ። እዛ ከደረሱ በኋላ አሚር ተብሎ በተመደበው ሰው አማካይነት የስራ ክፍፍል ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በስንት ጭቅጭቅ የወጣውን ሰው ዛሬ በያን ( ሙሓደራ)  አንተ ታደርጋለህ ይባላል ። ሰውየው ላብ በላብ ሆኖ እኔ ምንም አላውቅም እንዴት ሰው ፊት እቆማለሁ ሲል አብሽር አላህ ያናግርሃል መርሀባ በል የአሚር ትእዛዝ ነው ይባላል ።

           አላህ ካለ ይቀጥላል ።

     ክፍል አንድን ለማግኘት

   https://t.me/bahruteka/5508

      ክፍል ሁለትን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5510
      
         ክፍል ሶስትን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5519

        ክፍል አራትን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5530
      
        ክፍል አምስትን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5537

https://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

20 Nov, 19:43



ለአሏህ ስንት ሴት አለችው !

ሸይኽ አብዱልዐዚዝ አብዱሏሂ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ ፦


" فَكَمْ لِله مِنْ امرأة فوقَ كثيرٍ مِنَ الرجال في عَقلها ، ودِينها ، وضَبْطِها ".

"ለአሏህ ስንት ሴቶች በአስተዋይነታቸው፣ በዲናቸው እና ራሳቸውን በመግዛት ከብዙ ወንዶች የበላይ የሆኑ ?!"

መጁሙዑል ፈታዋ - ٢٩٣/٤

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

18 Nov, 18:43


አላህ በሸኽ ሙሀመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሀብ ዱኑን እንዴት ህያው እንዳደረገው ለአሁኑ ትውልድ መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ይቆጠራል ታድያ እነዚህ ሰዎች ብዙ ሆነው ሳይሆ ተዓምር የሰሩት በአላህ እርዳታ ታግዘው በነበራቸው ፅናት ነው።

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

13 Nov, 10:53


ተወጣጥራ ትወጣለች ወንድ ትስባለች
ዝሙት ተሰርቶባት ረክሳ ትቀራለች
ልጁም ጥላት ሄዶ ንፅህናዋንም ጠፍቶ ባዶዋን ትቀራለች
አሁን  ይቺህ ልጅ ሴት ትባላለች?

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

12 Nov, 20:27


"ከሰዎችም እንስሶች አሉ። እነሱም ወንድ ዝሙተኞች እና ሴት ዝሙተኞች ናቸው። ምክንያቱም በስሜታቸው እንጂ በአእምሮአቸው ስለማይመሩ። እንስሳቶች በስሜት እንደሚመሩት ሁሉ ዝሙተኞቾም በስሜት ነው ሚመሩት። አላህ ከዚህ አፀያፊ ነገር ይጠብቀን"

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

12 Nov, 19:11


#ኢማም_ኢብኑ_ባዝ ረሂመሁሙላህ

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

10 Nov, 10:38


ጅልባብ እና ኒቃብ ካለበሽ
አንቺኮ ከሴቶች ሁሉ ርካሽ ነሽ
ምክንያቱም ተገላልጠሽ ተወጣጥረሽ ስላለሽ

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

06 Nov, 18:53


እዚህ ጋር አንድ ገጠመኝ ላካፍላችሁ :– አንድ ቀን ሰፈራች ያለ መስጂድ ላይ ፓኪስታኖች መጥተው ነበር ። ከዙህ ሶላት በኋላ አንድ ፓኪስታኒ ተነስቶ ዳዕዋ ማድረግ ጀመረ ። ከጎኑ አንድ የኛ ሰፈር የተብሊግ ጀማዓ አባል የሆነ ልጅ ተነስቶ ማስተርጎም ጀመረ ። እኔ ተነስቼ እየወጣሁ ነበርና በጣም ገርሞኝ ይሄ ልጅ እንዴት ፓኪስታንኛ አወቀ እያልኩ ሳስብ አንድ ሌላ ሰው ተከትሎኝ ወጣ ። እኔም ይሄ ልጅ ፓኪስታንኛ የት አወቀ ብዬ ጠየቅሁት እሱም እየሳቀ ተብሊጎች እኮ የአለም ቋንቋ ያውቃሉ አለኝ ። እንዴት አልኩት ምክንያቱም የእነርሱ ዳዕዋ በይትኛውም ቋንቋ ቢደረግ አንድ አይነት ስለሆነ ተነስተው ያስተረጉማሉ ። በዚህም ሁሉንም ቋንቋ የሚችሉ በማስመሰል ሰውን ይሸውዳሉ አለኝ ።

        አላህ ካለ ይቀጥላል ።

https://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

06 Nov, 18:53


🔷  የተብሊግ ጀማዓዎች ማን ናቸው

               ክፍል ሶስት

               ስድስቱ የሶሓባ ሲፋዎች

       የተብሊግ ጀማዓዎች በዐለም ላይ በየትኛውም ሀገር በየትኛውም ቋንቋ በየትኛም ደረጃ የዳዕዋቸው መሰረት አድርገው የሚጠቀሙበት 6 የሶሓባ ባህሪዮች ከነ መክፈቻቸው የሚሏቸው ነጥቦች አሉ ። እነዚህ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው : –

አንደኛ – ላኢላሃ ኢልለላህ  ( ሚፍታሑል ጀናህ)
              ሙሐመድ ረሱሉላህ ( ሚፍታሑል
                 ሂዳይ )  
ሁለተኛ – ሶላት በኹሹዕና ኹዱእ ( ሚፍታሑል
               ኸዛኢን) 
ሶስተኛ – ዒልምና ( ሚታሑል መዕሪፋ) 
                ዚክር ( ሚፍታሑል ኸሺያ) 
አራተኛ – ሙስሊሞችን ማክበር ( ሚፍታሑል
               ቁሉብ )
አምስተኛ – ንያን ማስተካከል ( ሚፍታሑል
                 ቀቡል)
ስድስተኛ – ወደ አላህ መጣራት ( ሚፍታሑ
                 ዲን)
                ኹሩጅ መውጣት ( ሚፍታሑ ነሽሪ
                 ዲን) 
     እነዚህ ስድስት ባሕሪዮች የተብሊግ ጀማዓዎች ዘንድ ዳዕዋ የሚደረግባቸው ነጥቦች ሲሆኑ በየትኛውም የእውቀት ደረጃ ላይ ያለ ሰው ከዚህ መውጣት አይችልም ። መውጣት አለመቻል ብቻ ሳይሆን በጀማዐው መመሪያ መሰረት ከተቀመጠው ማብራሪያ ውጪ ማብራራትና ትርጉም መስጠት አይቻልም ። ለዚህ ማሳያ የመጀመሪያውን ሲፋ ( ባሕሪይ)  ብንመለከት : –
– ላ ኢላሃ ኢልለላህ ማለት :–
     ኢኽራጁ የቂኒልፋሲዲ ዐኒል አሽያዪ ወኢድኻሉል የቂኒ ሳዲቂ ዓለላህ ( የተበላሸ የቂን ከነገሮች ላይ ማውጣትና እውነተኛ የቂን በአላህ ላይ ማድረግ ) የሚል ነው ። ለዚህ ነው በየትኛውም ዐለም ያሉ የተብሊግ ጀማዓዎች በየትኛውም ቋንቋ ላ ኢላሃ ኢልለላህ ማለት የፈጠረን አላህ ነው ማለት ነው ፣ የሚገለን አላህ ነው ማለት ነው ፣ የሚቀሰቅሰን አላህ ነው ማለት ነው ። የሚያበላን አላህ ነው ማለት ነው ፣ የሚሉት ። ይህ በየትኛውም እምነት ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚያምኑበት ሲሆን የመካ አጋሪያኖችም በዚህ ያምኑ እንደ ነበር አላህ በተከበረው ቃሉ በተለያዩ አንቀፆች ላይ ነግሮናል ። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የተብሊግ ጀማዓ ዘንድ አንድ ሰው በየትኛውም የእውቀት ደረጃ ላይ ቢሆን ከዚህ መውጣት አይችልም ። በሌላ አባባል ተብሊጎች ጋር ሁሌም አንደኛ ክፍል ነህ ሁለተኛ ክፍል የሚባል ነገር የለም ። ከላይ የተጠቀሱት የላ ኢላሃ ኢልለላህ ትርጉም የሚሉት ፍልስፍና ከቁርኣንና ሐዲስ አስተምሮ ጋር የማይሄድ ሲሆን ነባራዊው ሁኔታ ውድቅ ያደርገዋል ። የአላህ መልእክተኛ የመካ አጋሪያኖችን ላ ኢላሃ ኢልለላህ በሉ ሲሏቸው በመገረም የሰጡዋቸው መልስ አላህ ሲነግረን እንዲ ይለናል : –

« أجَعَلَ الْآلِهَةَ إِلَٰهًا وَاحِدًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيْءٌ عُجَابٌ»
             ص   ( 5 )
«አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው» (አሉ)፡፡
       ይህ ማለት ሙሽሪኮቹ የላ ኢላሃ ኢልለላህ ትርጉም :–
" ከአላህ በስተቀር በእውነት የሜመለክ ሌላ አምላክ የለም " የሚል መሆኑን ያውቁ ነበር ማለት ነው ። ምክንያቱም ፍጥረተ ዐለሙን የሚያስናብረው አላህ መሆኑን ያውቁም ያምኑም ስለነበር ። ይንም አስመልክቶ ከመጡ አንቀፆች ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል : –

« وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ ۖ فَأَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ»
           العنكبوت  ( 61 )
" ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ " ፡፡

« وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّن نَّزَّلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَحْيَا بِهِ الْأَرْضَ مِن بَعْدِ مَوْتِهَا لَيَقُولُنَّ اللَّهُ ۚ قُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ »
                     العنكبوت   ( 63 )
" ከሰማይም ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ምስጋና ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም " ፡፡
       የመካ አጋሪያኖች አላህ ሰማይና ምድርን የፈጠረ ከሰማይ ዝናብ አውርዶ ከምድር ቡቃያ የሚያበቅለው አላህ እንደሆነ ያምኑ ነበር ። ላ ኢላሃ ኢልለላህ ማለት ትርጉሙ ይህ ቢሆን አንቀበልም አይሉም ይልቁንም ታዲያ ከአላ ሌላ ማን ነው ይሉ ነበር ። ነገር ግን ትርጉሙ ከአላ ሌላ የሚመለክ እርዳኝ ፣ ድረስልኝ ፣ ጠብቀኝ ፣ አድነኝ ፣ አክብረኝ ተብሎ የሚመለክ የለም ሲባሉ አይ አለ እነ ሁበል ፣ ላት መናትና ዑዛ ይደርሳሉ ፣ ይረዳሉ ፣ ይሰጣሉ ፣ ያከብራሉ ለጠራቸው ይደርሳሉ የሚል እምነት ስለነበራቸው ነው አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸው ( ከአላህ ሌላ የሚሰጥ ፣ የሚጠብቅ ፣ የሚደርስ ፣ የሚሰማ ፣ ከጭንቅ የሚያወጣ የለም)  አለ ብለው የተገረሙት ።
      የተብሊግ ጀማዐዎች በየመስጂዱ በየቋንቋው ተነስተው ቆመው የፈጠረን አላህ ነው ማለት ነው የሚገለን አላህ ነው ማለት ነው ሰማይን የፈጠረው አላህ ነው ማለት ነው እያሉ ከቆጠሩ በኋላ ላ ኢላሃ ኢልለላህ ይላሉ ። ይህ የተሳሳተ ከሽርክና ኩፍር የማያወጣ አስተምሮ ነው ። ዑለሞች ይህ አስተምሮ ተሕሲሉል ሓሲል ( የሚታወቅን ነገር ማሳወቅ ) ነው ይሉታል ። ወይም ይህ ማለት ለአንድ ዑብዱላሂ ፣ አሕመድ,  ሰዒድ,  ኸድር የሚባሉ ልጆች ላሉት አባት ሄዶ አንተ እኮ ዐብዱላሂ የሚባል ልጅ አለህ ማለት ነው ፣ አሕመድ የሚባል ልጅ አለህ ማለት ነው ፣ ሰዒድ የሚባል ልጅ አላህ ማለት ነው ፣ ኸድር የሚባል ልጅ አለህ ማለት ነው ። እንደማለት ነው ምክንያቱም አባት ልጆቹን ያውቃቸዋል ። አንተ መጥተህ የልጆቹን ስም እንደማያውቅ አድርገህ ስትነግረው ምናልባት አእምሮህ ትክክል አይደለም ሊልህ ይችላል ።
      የዚህ የተሳሳተ የላ ኢላሃ ኢልለላህ ትርጉም ነው የተብሊግ ጀማዓዎችን ቀብር አምላኪዮች እንዲሆኑ ያደረጋቸው ። ምክንያቱም አንድ ሰው የነገሮች ፈጣሪ አላህ መሆኑን ካመነ ሙስሊም ነው ኢማን አለው ብለው ስለሚያምኑና የተለያየ የአምልኮ አይነት ከአላህ ውጪ ላለ አካል መስጠት ችግር የለውም ብለው ስለሚያምኑ ። ይህ በመሆኑ ነው የተለያዩ ወልይ ተብለው የሚመለኩ መሻኢኾች ሀድራዎች ላይ ዋና ኻዲም ሆነው የምናገኛቸው ። የተብሊግ ጀማዓዎች ዳዕዋ ወጥና የማይቀየር በመሆኑ የትም ሀገር ሄደህ ዳዕዋ ስታደርግ የዛ ሀገር  ቋንቋ ተናጋሪ ተነስቶ ለማስተርጎም ከጎንህ ይቆማል ። ይህ ማለት አስተርጓሚው ያንተን ቋንቋ አውቆ ሳይሆን በየትኛውም ቋንቋ የሚነገረው ዳዕዋ አንድ ስለሆነ ነው ።

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

04 Nov, 18:56


ፍቅረኛ
ዝሙተኛ የዝሙት  አጋር

ከኒካህ በፊት ፍቅር ሚባል ነገር የለም ዝሙት እንጂ። በዚህ መንገድ ያላቹ ወንድም እና እህቶቼ አላህን ፍሩ ከዚህ መንገድ ራቁ መጨረሻው ዝሙት ላይ መዘፈቅ ነው። ዝሙት ደግሞ በዱኒያ ላይ ገላቹን ልክ በስሜት እንደሚነዱት እንስሶች ያረክስባቹዋል ገላቹ በዝሙት ይነጀሳል። ከዚህ የከፋው ሴት ከሆናቹ ያ አላህ በሀላል የተከበረው የሰው ልጅ እዲፀነስበት የፈጠረው ማህፀን ዲቃላ ሚባል የዝሙትልጅ እንዲረገዝበት ሰበብ ትሆናላቹ። ወንዶች ደግሞ በዝሙት ሴት ልጅ ዲቃላ እንድታረግዝ ሰበብ ትሆናላቹ። በእናንተ  የቅፅበቶች ስሜት ማብረጃነት ምክንያት አንዱ ምንም የማያውቅ ልጅ ህይወት ይበላሻል። ከተወለደም በኃላ በሸሪአችን በአባቱ ስም አይጠራም። አቤት የዚና ክፋትሲቀጥል ዝሙተኞች ከቀብር ጀምሮ እስከ ጀሀነም ድረስ በእሳት የተደገሰ ድግስ አለላቸው። አያቹ ይሄ  ሁላ ለአመታት የሚዘልቅ የዱኒያ እና የአኼራ ቅጣት የሚመጣው በጥቂት ደቂቃ በተሰራችው ዝሙት የተነሳ ነው። እና ለጥቂት ደቂቃዎች ብለን ለምን አመታቶችን እንከስራለን? ቢቀርብን አይሻልም? ከዚህ ሁሉ ጣጣ አቅም ካለ  በሀላሉ መሰተር ነው አቅም ከሌለ ግን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ያልቻለ ይፁም እንዳሉት መፆም ነው። በተረፈ ውዶቼ በዱአ ላይ በርቱ አላህ እሱ ከማመፅ እንዲጠብቀን ከዱኒያ ከአኼራ  ጭንቀት እንዲጠብቀን ዱአ ላይ በርቱ። አላህ እኔንም እናንተንም ከዱኒያ ከአኼራ ጭንቀት ነጃ ይበለን በተውሂድ እና በሱና ላይ ቀጥ ያድርገን እስከ እለተ ሞታችን ድረስ።

Abu Umer

ሼር ማድረግ እንዳይረሳ
https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

04 Nov, 18:28


🚫 የተብሊግ ጀማዓዎች ማን ናቸው

          ክፍል አንድ

      የተብሊግ ጀማዓ የዛሬ 98 አመት አካባቢ ህንድ ውስጥ በሙሐመድ ኢልያስ አማካይነት የተመሰረተ ሲሆን,  ሙሐመድ ኢልያስ ዐቂዳው ሱፍይ ስለነበረ በአራት የሱፍይ ጠሪቃዎች ነበር የመሰረተው ። እነዚህ ጠሪቃዎች የሚከተሉት ናቸው : –
1ኛ – ነቅሸበንዲያ
2ኛ – ቃዲሪያ
3ኛ – ጁሽቲያ
4ኛ – ሳሀርወርዲያ
        ነቅሸበንዲያ ማለት ነፍስ በአቡበከር አማካይነት ከነብዩ ጋር ትገናኛለች የሚል እምነት አላቸው ። ዚክር በልብ እንጂ በምላስ ማለት አያስፈልግም የሚሉ ሲሆኑ አንድ ሰው ዚክር ሲያደርግ አይኑን ጨፍኖ ከሸይኹ በሚሰጠው አይነት አቀማመጥ ተቀምጦ በልቡ ማለት አለበት ይላሉ ። ይህ ኢማን በልብ ነው ከሚለው የሙርጂዓ ዐቂዳ የተወሰደ ነው ። በዚህ መልኩ አላህን እያወሳ በሂደት መጋረጃው ተከፍቶ ከአላህ ጋር ይገናኛል ብለው ያምናሉ ። እንደሚታወቀው አብዛኛው የሱፍይ ጠሪቃዎች ቁርኣንና ሐዲስ ላይ የመጡ ሸሪዓዊ ድንጋጌዮችን አይከተሉም ።
        ቁርኣንና ሐዲስን መከተል የአዋሞች ዐቂዳ ነው ብለው ነው የሚያምኑት ። በመሆኑም ሁሉም የሱፍያ ጠሪቃዎች የራሳቸው የሆነ ዚክርና አዳብ አላቸው ። ከሸይኻቸው የሚሰጣቸውን መመሪያ በትክክል ፈፅመው ሲወጡ መቃም ደርሰናል ይላሉ ። በመጨረሻም በኛ ላይ ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች ውድቅ ናቸው እስከማለት ይደርሳሉ ። በዚህ መልኩ ሸይጣን ወሕይ እያደረገላቸው መቃም ደርሳችኋል በሚል ሸይኻቸውን እንዲያመልኩ ያደርጋቸዋል ።
      የነቅሸበንዲ ጠሪቃ በዚህ ስም የተጠራው ሸይኻቸው ሙሐመድ በሃኡዲን ሻህ አላህን መዘከር ከማብዛቱ የተነሳ በልቡ ጀርባ ላይ አላህ የሚል ጠቅ ጠቅ ተደርጎ ተፅፎ ታትሞበታል ከሚል እምነት በመነሳት ነው ።  እንዴት የልቡን ጀርባ እንዳዩት ግን አይታወቅም ። የነቅሸበንዲዮች ዐቂዳ የሚከተሉትን ነጥቦች ያካትታል : –
– ጠሪቃቸው ከአቡበከር ሲዲቅ የተወሰደ ነው የሚል እምነት ።
– አንድ ሰው ከሶስት እስከ አርባ ቀን ከሰው ተገልሎ ምላሱን ሳያንቀሳቅስ አይኑን ጨፍኖ በልቡ አላህን መዘከር አለበት ይላሉ ።
– ሸይኻቸው የሩቅ ሚስጢር ያውቃል ሲጠሩት ይደርሳል የጠየቁትን ይሰጣል ብለው ያምናሉ ።
– የጠሪቃ ሸይኽ የሌለው ሸይኹ ሸይጣን ነው ይላሉ ።
– የነቅሸበንዲ ተከታይ የሆነ ሰው ከሸሪዓ ዑለሞች ጆሮዉን መጠበቅ አለበት ከእነርሱ መስማት የለበትም ይላሉ ።
– አንድ ሙሪድ መቃም የሚደርሰው የሩቅ ሚስጢር ሲገለጥለት ነው ብለው ያምናሉ ።
– የመጨረሻ ግባቸው አላህ በእነርሱ ላይ መስፈር አለበት የሚል ነው ። ይህ ከሆነ መመለክ ስለሚችል ለዚህም ነው ሸይጣን ሸይኻቸውን እንዲያመልኩ የሚያደርጋቸው ።
      ስለ ነቅሸበንዲያ ይህን ያክል ካልን በሚቀጥለው አላህ ካለ ስለ ቃድርያ እናያለን ።

              አላህ ካለ ይቀጥላል

      https://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

03 Nov, 19:50


አዲስ pdf
➚➚➚➚
↩️ شرح رسالة قبح الشرك بالله عز وجل من ثلاثة عشر وجها
↪️በአላህ ﷻ ላይ የማጋራት አፀያፊነት በ13 አቅጣጫዎች የሚለው ሪሳላህ ማብራሪያ


📂 የኪታቡ 𝙥𝙙𝙛 ከላይ ተያይዟል።
https://t.me/shakirsultan/1903

➼ ኮርሱ የሚሰጠው፦
🎙 أستاذ شاكر بن سلطان - حفظه الله تعالى
🎙 በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (አላህ ይጠብቀው)


📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
 👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

03 Nov, 19:50


👆👆👆
#በአላህ ﷻ ላይ የማጋራት አፀያፊነት በ13 አቅጣጫዎች የሚለው ሪሳላህ ማብራሪያ ክፍል 1

የኪታቡን PDF ለማግኘት
https://t.me/shakirsultan/1903

🔶
በማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ቃጥባሬ ቀበሌ ታላቁ አሊፍ መስጂድ የተሰጠ ኮርስ ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

🌐 https://t.me/shakirsultan

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

03 Nov, 18:56


"ሰላማዊ ሰልፍ ከምእራባውያን መጥቶ  በኢኽዋኖች አማክኝነት ሙስሊሙ ውስጥ የገባ ሸሪአ ሚፃረረው የትግል መንገድ ነው። በቁርአን በሀዲስ የሌለ የትግል አይነት ነው።"

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

02 Nov, 10:19


ወርሃዊ ደመዎዝ - የመረጥነው ባርነት

ቻይናዊው ጃክ ማ በዓለማችን ከሚገኙ የናጠጡ  ሐብታሞች መካከል ከፊት ረድፍ ላይ ይሰለፋል። የሃብቱ መጠን በቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሆነ ይገመታል። ጃክ ማ እንዲህ ይላል: - « ከዝንጀሮ ፊት ገንዘብ እና ሙዝ ባስቀምጥ ዝንጀሮው የሚመርጠው ሙዙን ነው። ምክኒያቱም ዝንጀሮው ገንዘቡ ብዙ ሙዝ ሊገዛ እንደሚችል አይረዳምና»

በተመሳሳይ መልኩ ወርሃዊ ደመዎዝ የሚያስገኝ ስራ እና ሌላ ፕሮጀክት አቅርበህ ለሰዎች ብታማርጣቸው ብዙኋኑ የሚመርጠው ወርኃዊ ደመዎዝ የሚያስገኘውን ስራ ነው። ምክኒያቱም ፕሮጀክቶች ከወርሃዊ ደመዎዝ እጅግ በተሻለ መልኩ ገንዘብ ማስገኘት እና ህይወትን ሙሉ በሙሉ መቀየር እንደሚችሉ ስለማይገነዘቡ ነው።

ሰዎችን ደሃ ከሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል ከፕሮጀክቶች የሚገኙትን መልካም አጋጣሚዎች እንዲመለከቱ የሚያስችል ትምህርት አለመቅሰማቸው ነው። ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሩት ነገር «ስራ ሁሌም ወርሃዊ ደመዎዝ ማግኛ መንገድ» እንደሆነ ነው። 

ወርሃዊ ደመዎዝ ምናልባት ድህነትን ቢከላከልልህም ሃብታም ከመሆን ግን ያቅብሃል። ሙሰኛ ካልሆነ በቀር በወርሃዊ ደመዎዝ ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ ሰርቶ «ሃብታም» የሆነ ሰው በህይወቴ አጋጥሞኝ አያውቅም...¡

መንቁል

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

02 Nov, 06:59


👉  ሸይኽ አልባኒን ያስለቀሰ ታሪክ

   ዒሳም ሃዲይ የተባለ ተማሪ ሸይኽ አልባኒን በተኽሪጅ ያግዛቸው ነበር ። ከሳቸው ጋር ወደ አምስት አመት አካባቢ አሳልፏል ። የኢብኑ ሒባንና ኢብኑ አሳኪርን ኪታቦች ተኽሪጅ እየሰራ በነበረበት ጊዜ ሸይኽ አልባኒ በእነዚህ ኪታቦች ውስጥ ለየት ያለ ጠቃሚ ነገር ስታገኝ ንገረኝ አሉኝ ይላል ።
    የሲቃት ኢብኑ ሒባንን ኪታብ እያነበብኩ ሳለ የአቡ ቂላባን ታሪክ በአምስተኛው ሙጀለድ መጀመሪያ ላይ ለሸይኻችን ማንበብ ጀመርኩ ። በጣም አስገራሚ ሶብሩን ይናገራል ወደ መጨረሻ አካባቢ ደርሼ ቀና ብዬ ሳይ ሸይኻችን በእንባ ታበዋል ። የለቅሶ ሀይል ከውስጣቸው ገንፍሎ ድምፃቸው እንዲወጣ ስላደረገው ተነስተው ወደ ቤት ገቡ ። ከቆይታ በኋላ ተመልሰው መጥተው በጎረነነ ድምፅ ሰላም ብለውኝ ስራቸውን ቀጠሉ ። ታሪኩ ጠቃሚ ስለሆነ ላቅርብላችሁ ይላል የሸይኽ አልባኒው ተማሪ ዒሳም ታሪኩ እንዲህ ነው ።
     ኢብኑ ሒባን ከዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ይዞ እንዲህ ይላል : –
      " አንድ ጊዜ ወደ ዳርቻ ሄጄ ዒባዳ ለማድረግ ወጣሁ ። ዳርቻ ላይ ማረፊያችን ከቅጠላቅጠል የተሰራ ዳስ ቢጤ ነው ። ወደ ዳርቻ ስደር አሸዋማ በሆነው በባሕር ዳር ባለው ዳርቻ ላይ የሆነ ድንኳን አየሁ ። ወደ ድንኳንኩ ጠጋ አልኩኝ ። በውስጡ የሆነ ሰው አለ ይህ ሰው ሁለቱም እጅና እግሮቹ የሉም ። አይኑም ተይዟል ፣ ጆሮውም ያስቸግሯል ፣ ከአካሉ ሙሉ ጤነኛው ምላሱ ብቻ ነው ። ጠጋ ስል እንዲህ እያለ ዱዓእ ያደርጋል : –
       " አላህ ሆይ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋና ከብዙ ፍጥረታቶችህ ለማስበለጥህ የማሸኩርበት ምስጋና እንዳመሰግንህ አድርገኝ  " ።!!!
    ዐብዱላህም በአላህ ይሁንብኝ ይህን ሰው ቀርቤ መጠየቅ አለብኝ የትኛው ፀጋ ነው አላህ ከሌሎች አስበልጦ የሰጠው ? ፈህም ነው ወይስ እውቀት ወይስ ኢልሃም ነው አላህ በልቡ ላይ የጣለለት አለ ። ዐብዱላሂ ሄደና ሰላም ካለው በኋላ ስታደርገው የነበረውን ዱዓእና ምስጋና ሰምቻለሁ ከአላህ ፀጋዎች የትኛውን ነው የምታመሰግነው አልኩት ይላል ። እንዲህ ብሎ መለሰልኝ : –
     " አላህ በኔ ላይ የዋለውን ፀጋ አታይምን አላህ ሰማይን እሳት እንድታዘንብብኝ አዞ ቢያቃጥለኝ ፣ ተራራን አዞ ቢያጠፋኝ ፣ ባሕርን አዞ ቢያሰምጠኝ ፣ ምድርን አዞ ቢውጠኝ አሁን ካለሁበት ምስጋና አልወገድም ነበር ። እሱን የማመሰግንበት ምላስ እስከሰጠኝ ድረስ !!!!! ነገር ግን እስከመጣህ ድረስ ካንተ አንድ ሀጃ አለኝ ። እንደምታየኝ እኔ ራሴን መጥቀም አልችልም አንድ ልጅ ነበረኝ የሶላት ሳአት ሲደርስ ውዱእ የሚያስደርገኝ ፣ ሲርበኝ የሚያበላኝ ፣ ሲጠማኝ የሚያጠጣኝ,  ነገር ግን ከሶስት ቀን ጀምሮ አጣሁት እኔ እንደምታየኝ ነኝና እስኪ ፈልግልኝ አለኝ ። በአላህ ይሁንብኝ አንድም ሰው በሰው ሀጃ አይሄድም በምንዳ የላቀ በሆነ ባንተ ሀጃ ከመሄድ የበለጠ ብዬው ፍለጋ ቀጠልኩ ።
ብዙም ሳልቆይ በሁለት ኮረብታዎች መካከል አሸዋማ በሆነ ደለል ላይ አውሬ በልቶት አየሁ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብዬ በምን መልኩ ነው ቀርቤ የሆነውን የምነግረው ብዬ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ ። የተወሰነ ጊዜ በሀሳብ ከተሰወርኩ በኋላ መመለስ ጀመርኩ ።
    መንገድ ላይ እያለሁ የነብዩላሂ አዩብ ታሪክ ትዝ አለኝ ። ከዛም ደርሼ ሰላም አልኩት መለሰልኝ ቀጥሎም አንተ ጓደኛዬ ነህ አይደል አለኝ አው አልኩት ። ጉዳዬን ምን አደረከው አለኝ ።
እኔም አላህ ዘንድ አንተ ነህ ወይስ አዩብ ነው የበለጠ ቦታ ያለው አልኩት ።
እሱም አዩብ አለኝ ።
እሺ ጌታው ምን እንዳደረሰበት ታውቃለህ አይደል በአፍያው ፣ በልጆቹና በሀብቱ ፈትኖታል አይደል አልኩት ።
እሱም አው አለኝ ።
ታዲያ ጌታው እንዴት አገኘው አልኩት ።
እሱም ታጋሽ ፣ አመስጋኝ ሆኖ አገኘው አለኝ ።
አዩብ ጌታው በሱ ላይ ያደረሰበትን ቤተሰቦቹንና ጓደኞቹን እስከሚያስገርም ወዶ ተቀብሏል አይደል አልኩት ።
እሱም አው አለኝና አሳጥረው አላህ ይዘንል አለኝ  ።
ልፈልገው የላክኸኝ ልጅ አውሬ በልቶታል አላህ አጅርህን ያብዛልህ ትእግስቱንም ይስጥህ አልኩት ።
የመከራው ባለቤትም እንዲህ አለ " ምስጋና ለዚያ ከዘሬ ውስጥ እሱን አምፆ በእሳት የሚቀጣው ያልፈጠረ ለሆነው ጌታዬ የተገባ ይሁን " ብሎ  ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን አለና የማቃሰት ድምፅ አውጥቶ ሩሑ ወጣ ። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብዬ ትካዜ ውስጥ ገባሁ ።
     ትቼው ከሄድኩኝ አውሬ ይበላዋል ቁጭ ካልኩም ምን እንደማደርግ አላውቅም ብዬ በላዩ ላይ በነበረው ፎጣ ሸፍኜው ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ። ብዙም ሳይቆይ አራት ሰዎች ሲያልፉ አዩኝና መጡ ። ምንድነው ነገርህ አሉኝ ታሪኩን ነገርኳቸው ። እስኪ ክፈተው አሉኝ ከፈትኩት ። ተንበርክከው በአይኖቹ መካከል ይስሙት ጀመር ሐራም ያላየ አይን ይላሉ ። እጅና እግሮቹን እየሳሙ ሰው ሲተኛ ለጌታቸው በመስገድ ያልተኙ አካሎች ይላሉ ። አላህ ይዘንላችሁ ለመሆኑ ይህ ሰው ማን ነው አልኳቸው ። እነርሱም አላህና ነብዩን በጣም ይወድ የነበረው አቡ ቂላባ የኢብኑ ዐባስ ባልደረባ ነው አሉኝ ። 
     አጥበን እኛ ጋር በነበረ ልብስ ከፍነን ቀበርነው ። ሰዎቹም ሄዱ እኔም ወደ ዒባዳ ቦታዬ ሄድኩ ። ማታ ላይ ጋደም አልኩኝ የተኛ ሰው እንደሚያየው ያን የአላህ ባሪያ በጀነት ጨፌ ላይ የጀነት ልብስ ለብሶ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ ሲቀራ አየሁት :–

  «سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ»
             الرعد  ( 24)
«ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡

    አንተ ያ ጓደኛዬ አይደለህምን አልኩት ። አው አለኝ ። ታዲያ ይህን ደረጃ እንዴት አገኘኸው አልኩ ። አላህ ደረጃዎች አሉት በመከራ በመታገስ ፣ በደስታ በማመስገን ፣ አላህን በድብቅም በግልፅም በመፍራት እንጂ የማይገኝ አለኝ " ።

    አስሲቃት ሊብኒ ሒባን የአምስተኛው ሙጀለድ መጀመሪያ የአቡ ቂላባ ታሪክ

https://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

01 Nov, 05:55


ሴት ልጅ ከባሏ ዘመድ ጋር መገለልና እሱ ፊት ፊቷን መግለጥ ክልክል ስለመሆኑ፦

ይህቺኛዋ ማግለል ከሌላዋ(ከተለመደው ማግለል) ከባድ አደጋ ያላት ናት። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦

{ إياكم والدخول على النساء، فقال رجل من الأنصار: يا رسول الله أفرأيت الحمو ؟ قال: الحمو: الموت } البخاري النكاح (4934) ، مسلم السلام (2172) ، الترمذي الرضاع (1171) ، أحمد (4/149) ، الدارمي الاستئذان (2642) . رواه أحمد والبخاري والترمذي وصححه .

“በሴቶች ላይ መግባት ተጠንቀቁ፤ ከአንሷሮች አንድ ሰው የአላህ መልክተኛ ﷺ ሆይ! ስለ ዋርሳ ምን ይላሉ?” ብሎ ሲጠይቃቸው ዋርሳ ሞት ነው። (ከሞት የበለጠ ሀገር አጥፊ) ነው።” (አሕመድ፤ ቡኻሪና ቲርሚዝይ ዘግበውታል) ዋርሳ ማለት የባል ወንድም ነው። ይህንም ያሉበት ዋርሳ ብቻውን ይዟት እንዳያገል በመጥላት ነው።

አል ሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር ፈትሑ ልባሪ ውስጥ ጥራዝ 9 ገፅ 331 ላይ እንዲህ ይላሉ፦ “ኢማሙ አንነዋውይ እንደሚሉት “አል አሕማእ” (لحمو) ማለት የባል ቅርብ ዘመዶቹ እንደ አባቱ፣ አጎቱ፣ ወንድሙ፣ የወንድሙ ልጅ፣ የአጎቱ ልጅ እና የመሳሰሉት እንደሆኑ የቋንቋ ምሁራን ይስማማሉ ይላሉ። አክለውም እንደተናገሩት፦ “በዚህ ሐዲስ የተፈለገበት አባት እና ልጁ ሲቀሩ የባል የቅርብ ዘመዶች ማለት ነው። የባል አባት እና የባል ልጅ ለእርሷ “መህረም” ስለሆኑ እርሷን ይዘው ማግለል ስለሚችሉ በሞት አይመሰሉም። በተለምዶ በማግራራት ወንድም የወንድሙን ሚስት ይዞ ስለሚያገል በሞት ተመስሏል።የባል ወንድም በመከልከል ደረጃ ቅድሚያ የሚይዝ ነው።

ኢማሙ አሽሸውካኒ “ነይሉል አውጧር” በሚባለው ኪታባቸው ጥራዝ 6 ገፅ 122 ላይ እንዲህ ይላሉ፦ “ዋርሳ ሞት ነው” ማለታቸው ሞት ከሌሎች አስፈሪዎች የበለጠ እንደሚፈራ ሁሉ ከዋርሳም የሚመጣው መጥፎ ነገር ከሌሎች ከሚመጣው መጥፎ ነገር የበለጠ አስፈሪ ነው ለማለት ነው።

አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! አላህን ፍሪ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰዎች ችላ ቢሉትም አንቺ ችላ አትበይ፤ምክንያቱም የአንድ ነገር መገለጫ በሸሪዓ ያለው ፍርድ እንጅ የሰዎች ልምድ አይደልም።

https://t.me/sunah123

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

31 Oct, 19:55


🟢ለአላህ የሆነው ይፀናል

አልኢማም ማሊክ "ሙወጠእ" የተባለውን ኪታብ በፃፉ ጊዜ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ "ሌሎች ተመሳሳይ ኪታቦች እያሉ ያንተ መፃፍ ምን ጥቅም አለው ? " ታሪክ በማይረሳው ድንቅ  ቃል እንዲህ ብለው መለሱ :
(ما كان لله يبقى = ለአላህ የሆነው ይቀራል)

وقال ابن عبد البر : (وبلغني عن مطرف بن عبد الله النيسابوري الأصم صاحب مالك أنه قال: قال لي مالك: ما يقول الناس في موطئي فقلت له: الناس رجلان محب مطرٍ وحاسدٍ مفتر، فقال لي مالك: إن مد بك العمر فسترى ما يراد الله به)
التمهيد لا بن عبد البر (1/85).
ኪታቡ ተጠናቆ ሰዎች ጋር ከደረሰ በኃላ ደግሞ ባልደረባቸውን ሰዎች ስለ ሙወጠእ ምን እንደሚሉ ጠየቁት:: እርሱም ሲመልስ:
"ሰዎች ሁለት አይነት ናቸው።አድናቂ ወዳጅ እና ምቀኛ ቀጣፊ።" ኢማም ማሊክ እንዲህ አሉ: "እድሜህ ረዝሞ ከቆየህ አላህ የተፈለገበትን ታየዋለህ።"

{...كَذَلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْحَقَّ وَالْبَاطِلَ فَأَمَّا الزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَاءً وَأَمَّا مَا يَنْفَعُ النَّاسَ فَيَمْكُثُ فِي الأَرْضِ كَذَلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الأَمْثَالَ ﴾[الرعد ١٧]
{ልክ እንደዚሁ አላህ ለሀቅና ለባጢል (ምሳሌ) ያደርጋል።ኮረፉማ (ተንሳፋፊው ቆሻሻ) ተበታትኖ ይጠፋል። ሰዎችን የሚጠቅመውማ መሬት ላይ ፀንቶ ይቀራል። ልክ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ያደርጋል።}

  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ)
http://t.me/Abuhemewiya

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

31 Oct, 05:15


ትክክለኛዉ ሸሪአዊ ሂጃብ(ኒቃብ) ማለት
1ኛ, ሰፊ የሆነ
2ኛ, ጠባብ ያልሆነ
3ኛ, ሙሉ አካልን የሚሸፍን
4ኛ,አጭር ያልሆነ
5ኛ, ሙሉ አካል የሚሸፍን ከአካልም ምንም ነገር የማያስገኝ

6ኛ,ሂጃቡ ላይ ጌጣጌጥ መኖር የለበትም
7ኛ, ከወንዶች ልብስ ጋር መመሳሰል የለበትም
8ኛ, ከካፊሮች ልብስ ጋር መመሳሰል የለበትም!!

👍ይሄ ነዉ የአሏህ ድን(ሀይማኖት)
ይሄ ነዉ የነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሱና!!

Copy #Share

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

29 Oct, 04:55


☀️አላህ ካዘነላቸው ባሮቹ ስትሆን አምሽተህ ካነጋህ በኃላ አይንህን በቁርአን እንድከፍት ትደረጋለህ። ስንቱ አለ አይደል አይኑን ሀራም ነገር በማየት ቀኑ ምትከፈትለን? እና ሀቢቢ አላህ ለኸይር ነገር ስለወፈቀህ አልሃምዱሊላህ አትልምን?


#አልሃምዱሊላህ

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

27 Oct, 05:14


🔷 የሰለፍያን ዳዕዋ ለምን ይፈሩታል ?

     ሰለፍያ ማለት ትክክለኛው እስልምና ማለት ነው ። የሰለፍያ ዳዕዋ ሲባል ወደ ትክክለኛው ኢስላም  ነብዩ ፣ ሶሓቦች ፣ ታቢዒኖች ፣ አትባዑ ታቢዒኖችና እነርሱን በመልካም የተከተሉ የኢስላም ሊቃውንቶች ያስተማሩት ኢስላም  ማለት ነው ። ሰለፍያ ዳዕዋው ሲሆን ዳዒው ( ወደዛ ተጣሪው)  ሰለፍይ ይባላል ። ቃሉ የተወሰደው ሰለፍ ( ቀደምት)  ከሚለው ሲሆን ሰለፎች የሚባሉት የመጀመሪያወቹ ኢስላምን በቁርኣንና ሐዲስ አስተምሮ ተግብረው ያሳዩት ናቸው ።
      ከዚህ የምንረዳው የሰለፍያ ዳዕዋ ማለት የመጀመሪያው ወደ ትክክለኛ ኢስላም በነብዩና ሶሓቦቻቸው የተደረገው ዳዕዋ ማለት ነው ። ታዲያ ለምን ይሆን ዛሬ የሙስሊም መሪዮች ነን እያሉ ይህን ዳዕዋ የሚፈሩትና የሚጠሉት ? ለምን ይሆን ሁሉም ሙስሊም ነን የሚሉ አንጃዎች ይህን ዳዕዋ ማሰናከል የመጀመሪያ ግባቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱት ? ለእስልምና ታስቦ ወይስ ለሙስሊሙ ? ሁለቱም አይደለም ነው መልሱ ። ምክንያቱም እስልምና ማለት ከሰባት ሰማይ በላይ በጅብሪል አማካይነት በነብዩ ላይ ወርዶ ለተከታዮቻቸው በንግግርና በተግባር ያስተማሩት ስለሆነና የሰለፍያም ጥሪ ወደዛው በመሆኑ ። ለሙስሊሞች ታስቦ ነው የሚለው ውድቅ የሚሆነው ሙስሊሞች በቅርቢቱም ሆነ በመጪው ዐለም ስኬት የሚጎናፀፉት የመልእክተኛውን ፈለግ ተከትለው አላህን በብቸኝነት ሲያመልኩ ነውና ።
     ስለዚህ የትኞቹም የኢስላም አንጃዎች የሰለፍያን ዳዕዋ የሚፈሩትና የሚዋጉት ዝንባሌያቸውንና ጥቅማቸውን ስለሚነካ ነው ። እነዚህ አካላት ለእስልምናና ለሙስሊሙ ነው የምንሰራው የሚሉት ለሽፋን መሆኑ ይፋ የሚወጣው በኢስላም ስም ቀብር ሲመለክ ፣ በኢስላም ስም መውሊድ ሲደለቅ ፣ በኢስላም ስም ሽርክና ቢዳዓ ሲስፋፋ መብት ነው እያሉ የተውሒድን ዳዕዋ ማሰናከል ግብ አድርገው ሲሰሩና ለዚህም ዋጋ ሲከፍሉ ነው ።
     በኢስላማዊ ዳዕዋ ስም ህዝብ ተሰብስቦ ጫት በአይሱዙ በሰለፍ ሲራገፍ እያዩ ምንም ሳይመስላቸው ሰዎችን ከፉጡራን ጋር ሳይሆን ከፈጣሪ ጋር የሚያስተሳስረውን የተውሒድ ዳዕዋን ማጨናገፍን ለኢስላምና ለሙስሊሞች ብለን ነው ማለት ምን የከፋ ቅጥፈት ነው  ነው ?
      የተውሒድን ዳዕዋ ለማስቆም መሞከር ፀሀይን በእጅ መዳፍ ብርሃንዋን ለመጋረድ እንደሞመከር ነው ። የተውሒድ ዳዕዋ ተቀናቃኞቹ በበዙ ቁጥር እያበበ ይሄዳል ። በደቆሱት ልክ እየጠነከረ ይሄዳል ። ስለዚህ የሰለፍያን ዳዕዋ መዋጋር ትርፉ የሁለት ሀገር ክስረት ነውና ከፍርሃትና ጠላትነት ወጥታችሁ ወደ ሰፉ ግቡ ለበላይነቱ ስሩ እንላችኋለን ።

https://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

25 Oct, 19:48


የአካውንቱ ባለቤት ወንድሙ ነው ። ስሙ ዐ/ሰመድ አሕመድ ይባላል ።

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

25 Oct, 19:48


👉 የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሰበብ መሆን የሰውን ልጅ ሕይወት ሁሉ እንደማዳን ነው ።

ውድ ቤተሰቦቻችን በየጊዜው የሚያጋጥሙ የህመም አይነቶች አንዱ ሌላውን እያስረሳ ውስጥን በሐዘን የሚሞላ አእምሮን የሚረብሽ ነው ። የተለያዩ ሰዎች በተለያየ በሽታ ይሰቃያሉ ። ከበሽታ ሁሉ አስከፊውና በአሁኑ ጊዜ እንደወረርሽኝ እየተዛመተ ያለው የካንሰ በሽታ ነው ። በዚህ በሽታ ሰበብ ብዙ ሰዎች ወደ አኼራ ይሄዳሉ ። የአላህ ውሳኔ እንዳለ ሆኖ ቤተሰብ በአቅም ማነስ ምክንያት ማሳከም ባለመቻሌ ነው በሚል ፀፀት ይሰቃያል ። ከእንደነዚህ አይነት ገጠመኞች አንዱ የሆነውን ዛሬ ወደናንተ ለማድረስ ወደድኩ ።
ይኸውም ወንድማችን ሙሀጅር አሕመድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በደም ካንሰር ተይዞ በአሁኑ ሰአት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይገኛል ። ይህ ወንድማችን የኬሞ መድሀኒት የጀመረ ሲሆን ያለበት ሁኔታ ሐኪሞች ተስፋ ሰጪ ነው ይላሉ ። ነገር ግን የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጅ በመሆኑ ለሕክምናው የሚያስፈልጉ ወጪዮችን መሸፈን የማይችሉ መሆኑን ሆስፒታሉ አረጋግጦ ፅፎለታል ።
ከሱ ጋር ያለው አርሶ አደር ወንድሙ በደረሰው ነገር ቅስሙ ከመሰበሩ ባሻገር የወንድሙም ህይወት በሱ ድጋፍ የነበሩ ቤተሰቦቹም ችግር ረፍት ነስቶት የይድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው ። ተስፋ የነበረውን ወንድሜ ሰበብ ሆናችሁ አድኑልኝ ይላል ። አይኑ ብቻ ሳይሆን ሁለመናው እያለቀሰ የደረሰበትን ሲናገር ማየት በጣም ይከብዳል ። በጣም ብዙ ጉዳዮች የሚመጡ ሲሆን ወደናንተ የማደርሰው በጣም አሳዛኝና ምንም ሰበብ ከሌላቸው ውስጥ ጥቂቶቹን ነው ። ስለዚህ በአላህ ፈቃድ ከተባበርን አላህ ካልቀደረበት ወንድማችንን ሰበብ ሆነን ማዳን እንችላለን ።
የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሰበብ መሆን የሰውን ልጅ ሁሉ ህይወት እንደማዳን ነው ። በመሆኑም ውድ እህትና ወንድሞች ለወንድማችን ጥሪ ምላሽ ሰጥተን ታማሚውን ለማዳን ሰበብ ሆነን የወንድሙን እንባ እንጥረግለት እላለሁ ። በምንም መልኩ አንብበን እንዳናልፈው የምንችለውን እናበርክት ።
የሆስፒታሉ የድጋፍ ደብዳቤ ላይ አካውንትና ስልክ አለ አብሬ አያይዘዋለሁ ።

https://t.me/bahruteka/5492

https://t.me/bahruteka

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

24 Oct, 20:05


ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿السَّاعِي عَلَى الْأَرْمَلَةِ وَالْمِسْكِينِ كَالْمُجَاهِدِ فِي سَبِيلِ اللَّهِ، أَوِ الْقَائِمِ اللَّيْلَ الصَّائِمِ النَّهَارَ﴾

“የምስኪንን ጉዳይ ለመሙላት የሚሯሯጥ ሰው፤ በአላህ መንገድ ላይ እንደሚታገል (ሙጃሂድ) ነው። ወይም ደግሞ ሌሊት በሰላት እንደሚቆምና ቀን በፆም እንደሚያሳልፍ ነው።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5353

ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿أكثِروا ذكرَ هاذمِ اللَّذّاتِ: الموتِ﴾

“ጥፍጥና ቆራጭ የሆነውን (ሞት) ማስታወስ አብዙ።”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 2307

በኸይር ነገር ላይ እንበረታታ ጀዛ ኹሙላሁ ኸይረን ለአላህ ብዬ እወዳችዋለሁ አላህ ይዉደዳቹ

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

22 Oct, 18:39


ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች

ቢድዓን “ቢድአቱል ሀሰናህ” (መልካም ፈጠራ) እና “ቢድዓቱ ሰይአህ” (መጥፎ ፈጠራ) በሚል የከፈለ እርሱ ስህተተኛ ፣ ተሳሳች እና ለሚከተለው የረሱል ንግግር ተቃራኒ ነው፡

“ማንኛውም ቢድዓ ጥመት ነው”

ምክንያቱም ቢድዓ በሁሉም አይነት ቢሆን ጥመት እንደሆነ ረሱል ﷺ በዚህ ንግግራቸው ወሰኑ፡፡

ይህ ሰው ደግሞ “ሁሉም ቢድዓ ጥመት አይደለም ፣ ይልቁንም የቢድዓ መልካም አለው” እያለ ነው፡፡

ሀፊዝ ብን ረጀብ “ሸርህ አልአርበዒን” በተባለው ኪታባቸው የሚከተለውን ተናግረዋል ፡

“ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው” የሚለው የረሱል ﷺ ንግግር አጠቃላይ ከሆነው ንግግራቸው ውስጥ ነው፡፡ ከእርሱም አንድም ነገር ተቀንሶ የሚወጣ የለም፡፡ እርሱ ከዲን መሰረቶች ትልቅ የሆነ መሰረት ነው፡፡ “በዚህ ጉዳያችን ከእርሱ ያልሆነ አዲስን የፈጠረ ፣ እርሱ ተመላሽ ነው” የሚለው የረሱል ﷺ ንግግርም ተመሳሳይ ነው፡፡ ማንኛውም ከዲን መሰረት የሌለውን አዲስ ነገር የፈጠረ ከዚያም ወደ ዲኑ ያዛመደ እርሱ ወደርሱ ይመለስበታል፡፡ እርሱ ጥመት ነው፡፡ ዲን ከእርሱ የጸዳ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በእምነት ጉዳዮችም ይሁን ወይም በተግባራት ፤ ከንግግር ግልጽም ይሁን ስወር ተመሳሳይ ነው”

'መልካም ቢድዓ አልለ' በማለት የተናገሩ ሰዎች በተራዊህ ሶላት ዙሪያ ኡመር 'ይህች ያማረች ቢድዓ ነች' በማለት የተናገረው ንግግር እንጅ ሌላ መረጃ የላቸውም፡፡

በተጨማሪ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡

ቀደምቶች ያላወገዟቸው በርካታ ነገሮች ተፈጥረዋል፡፡ ለምሳሌ ቁርዓንን በአንድ መጽሐፍ መሰብሰቡ ፤ ሐዲስ መጻፉና በጥራዝ ሆኖ መዘጋጀቱ ነው፡፡

ለዚህ ምላሽ ፡ እነዚህ ነገሮች አዲስ የተፈጠሩ ሳይሆኑ ፣ በሸሪዓ መሰረት ያላቸው ናቸው፡፡

“ያማረች ቢድዓ” በማለት ኡመር የተናገረው “ቢድዓቱ ሉገውያ” (ቋንቋዊ ቢድዓ) እንጅ ሸሪዓዊ ቢድዓን አይደለም የፈለገው፡፡ በሸሪዓ መሰረት ያለው ነገር ሁሉ ወደርሱ ይመለሳል፡፡

(የሸሪዓ መሰረት ኖሮት) “ይህ ነገር ቢድዓ ነው” ከተባለ ሸሪዓዊ ሳይሆን ቋንቋዊ ነው፡፡ ምክንያቱም ቢድዓ በሸሪዓ ወደርሱ የሚመለሱበት መሰረት የሌለው ነው፡፡

ቁርዓን በኪታብ ውስጥ መሰብሰቡ የሸሪዓ መሰረት አለው፡፡ ምክንያቱም ነብያችን ቁርዓን እንዲጻፍ አዘው ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ቁርዓን በተለያዩ በሚጻፍባቸው ነገሮች (ለምሳሌ ፣ በቆዳ ፣ በጣውላ ..) ተበታትኖ ተጽፎ ስለነበር ሶሃቦች እርሱን ለመጠበቅ ሲሉ በአንድ መጽሐፍ ተሰባስቦ እንዲጻፍ አድርገዋል፡፡

ነብዩ ﷺ የተራዊህ ሶላትን የተወሰኑ ሌሊቶችን ለሶሃቦች ኢማም ሆነው አሰግደዋል፡፡ ከዚያም በእነርሱ ላይ ፈርድ ይሆናል ብለው በመስጋት ወደኋላ ቀሩ፡፡ ሶሃቦቹ ግን ነብዩ በሂዎት እያሉ ከሞቱም በኋላ የተበታተኑ ሆነው ስግደታቸውን ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻ ኡመር በነብዩ ﷺ ጀርባ እንደሚሰግዱት ሁሉ በአንድ ኢማም ጀርባ ተሰባስበው እንዲሰግዱ አድርጓቸዋል፡፡ ይህ በዲን ቢድዓ አይደለም፡፡

በተመሳሳይ ሀዲስን በኪታብ መልኩ መጻፉ በሸሪዓ መሰረት አለው፡፡ የተወሰኑ ሶሃቦች ሐዲስ እንዲጻፍላቸው ሲፈለጉ ነብዩ ﷺ እንዲጻፍላቸው አዘዋል፡፡ ጥቅል በሆነ ሁኔታ እርሱን መጻፉ አደጋ የነበረው በረሱል ﷺ ዘመን ነበር፡፡ ምክንያቱም ከእርሱ ያልሆነው ከቁርዓን ጋር ይቀላቀላል ተብሎ ስለተፈራ፡፡ ከሞቱ በኋላ ግን ይህ ስጋት በመወገዱ ቁርዓን ከመሞታቸው በፊት በተሟላ ሁኔታ ተደራጀ፡፡ ሙስሊሞችን ከጥፋት ለመጠበቅ ሱናን በኪታብ ጠረዙ፡፡ ስለኢስላም እና ሙስሊሞች ለዋሉት ውለታ አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው፡፡ የጌታቸውን መጽሐፍ የነብያቸውን ሱና ከጥፋትና ከቀልደኞች ጥፋት ጠበቁት፡፡

https://t.me/alateriqilhaq

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

كن على بصيرة

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

22 Oct, 05:29


የመርካቶው ቃጠሎ ብዙ ሰዎችን ለአመታት የለፋበትን ንብረት ሀብት አውድሞባቸዋል። አላህ በተሻለ ይተካላቸው። እኛም አቅማችን በፈቀደው ልክ ልናግዛቸው ይገባል። ያልቻልን ደግሞ ዱአ እናድርግላቸው።

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

21 Oct, 04:04


"እድለኛ ብሎ ማለት ቀኑን በቁርአን እና በዚክር የጀመረ ነው እድለ ቢስ ብሎ ማለት ደግሞ ቀኑን በዛዛታ እና በሀራም ወሬ የጀመረ ነው"

እና ከየትኞቹ ናቹህ? መልሱን ለእናንተ ተውኩት። ለማንኛውም ቁርአን ያልቀራቹ ቅሩ ለምን አንድ አያ አይሆንም።

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

20 Oct, 20:04


"በሌሎች የምንቃወመውን በራሳችን ሲሆን የማቀፍ ስራ የለንም በማንም ላይ ድንበር ማለፍ አልተፈቀደልንም ሸር በሸር አይመለስም  የአህለል ቢደአዎች (ኢኽዋኖች፣ኢብኑ መስኡዶች ፣ እነ ኢብኑ ሙነወር፣ሀጁሪዮች) ጥፋቶች በኢልም ኒቃሽ ይደረጉ እንጂ በሙሃተራ መሆን የለበትም ብዙ ጊዜ  ወጣ ያሉ ቃላቶች ሲሰነዘሩ እመለከታለው የሰው ወዳጅ ቢኖረንም የወንጀል ወዳጅ የለንም በኢልም በፈዋኢድ እናተኩር በልካችን እንኑር ምክሬ ለሁላችንም ነው።"
የኡስታዛችን አቡ አብዱራህማን ምክር ነው እናም ውድ ሰለፊዮች እኔንም እናንተንም ጨምሮ ያካተተ ምክር ነው። ስለዚህ ከአሁን በኃላ በቻልነው ልክ ከማይሆኑ እኛን ከማይመጥኑ ንግግሮች ምልልሶች መራቅ አለብን። በኛ ምክንያት ዲናችን መንሃጃችን ኡለሞቻችን ሊሰደቡብን አይገባም።

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

19 Oct, 09:07


ከውጭ በተለይም ከአረብ ሃገር ወደ ኢትዮ የምትገቡ ወገኖች በተለይ እህቶች አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ላይ እባካችሁ ጥንቃቄ አድርጉ …ደጋግመን እያሳወቅን ነው ግን ብዙዎቻችሁ አትሰሙም ስትነገሩ

የራሳችሁ የምታውቁት ሰው ቤተሰብ ካልሆነ ማንንም ሰው አትቅረቡ ልሸኛችሁ ቢላችሁ አምናችሁ መኪና ላይ አትግቡ

አሁን ላይ ደግሞ አረብኛ ተናጋሪ ሴቶችን አሰማርተው ነው እየዘረፉ ያሉት ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ አራት እህቶች ሙሉ ሻንጣና ንብረታቸውን በዚህ መንገድ ተዘርፈዋል

አረብኛ ስለተናገሩ ብቻ አትመኑ…ተናግረናል

መል ዕክቱን ለሌሎችም ሼር በማድረግ አስተላልፉ በጎነት ለራስ ነው🙏

ኮፒ
https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

16 Oct, 18:32


👉  ከጭንቅ መውጫው መንገድ

     ኢብኑል ጀውዚ ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-

" ነገሩ ከብዶኝ ተጠበብኩኝ የማይላቀቅ የሆነ ጭንቀት ያዘኝ , በምችለው ዘዴና አቅም ከዚህ ጭንቅ ለመውጣት የምችለውን ሁሉ ማሰብ ጀመርኩ ። ምንም መውጫ እንደሌለ አየሁ ። በዚህን ጊዜ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃል መጣልኝ :–
" አላህን የፈራ ሰው ከጭንቅ ሁሉ መውጫ ያደርግለታል " 
      ከዚያም አላህን መፍራት የጭንቅ ሁሉ መውጫ መሆኑን አወቁኝ ። በምችለው ሁሉ አላህን መፍራት ጀመርኩ ። ከጭንቄም መውጫ አገኘሁ ። ለሰው ልጅ ማሰብም ሆነ መመካት ያለበት የአላህን ትእዛዝ በመፈፀም ላይ ነው
ይህ ለሱ የተዘጋን ሁሉ ለማስከፈት ሰበቡ ነው "

ሰይዱል ኻጢር ገፅ ( 63 )

https://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

12 Oct, 17:53


🔹 የአላህ ጥበብ እያደር ግልፅ ይሆናል

    ለኮንፈረሱ የመግቢያ ትኬት የተላከላችሁ
ወንድሞች የተሸጠው በአካውንቱ አስገብታችሁ ቀሪው ትኬት እናንተው ዘንድ አድርጉት ። በፕሮግራሙ መራዘም በተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች የወጣው የተወሰነ ገንዘብ ቢከስርም አብዛኛዎቹ አላህ ካለ የምንጠቀምባቸው ይሆናል ። ለአዳራሹ ተከፈለው ላይ የተወሰነ እዳ ይኑር እንጂ ፕሮግራሞች ሲስተካከሉ እንደምንጠቀምበት ነግረውናል ። ባጠቃላይ በፕሮግራሙ መራዘም የተገኙ ድሎችና የአላህ ሒክማ እኛ አሁን ያየናቸው ያሉ ሲሆን ወደፊት ደግሞ አብረን የምናየው ይሆናል ። 
       የአላህ መልእክተኛ 1400 ሶሓቦችን ለዛው በአላህ ትእዛዝ ወደ መካ ዑምራ ሊያደርጉ ሐርመው ይዘው መጥተው ለዘንድሮ ተመለስ በሚቀጥለው አመት ታደርጋለህ መባሉ በሶሓቦች ስነልቦና ላይ ያሳደረው ተፅኖና እናስታውስ ። ወደ መካ እየተመለሱ ሳሉ ድል መሆኑ በወሕይ ከመነገሩ ጀምሮ መካ እስከተከፈተና የተውሒድ ባንዲራ ከየአቅጣጫው ከፍ ብሎ እየተውለበለበ ወደ ካዕባ ሲያመሩ ሙሉ በሙሉ ሒክማው ለሁሉም ፍንትው ማለቱን ስናይ የድሉና የጥበቡ ውጤት በተስፋ እንድንጠብቅ ያደርገናል ።
      መርሳት የሌለብን አላህ ያለ ሒክማ ምንም ነገር የማይሰራ መሆኑንና  ሒክማውን ለባሮቹ በየደረጃው እንደየአስፈላጊነቱ ግልፅ የሚያደርግ መሆኑን ነው ።

http://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

11 Oct, 20:37


ኮንፈረንሱ የሚካሄድበት ቀን መተላለፉን ስለማሳወቅ

ጥቅም 3 አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ኮንፈረንሱ የሚካሄድበትን ጊዜ ወደ ፊት የምንገልፅ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እናስታውቃለን።

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

11 Oct, 11:34


👉አድርሱለት

አላሁ አክበር❗️

አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች

"ኢብኑ ሙነወር ኮንፈረንሱን ተገኝቶ መማር ፈልጎ ነገር ግን መግቢያው ብር የበዛበት ስለ መሰለኝ የእርሱን ትኬት እኔ ልክፋልለትና ይግባ። "

መሰሎቹም አክቲቪስቶች ካሉ መሸፈት ይብቃ ይምጡና ከኡለማዎች ይማሩ

https://t.me/conference1447

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

09 Oct, 17:32


🔷 ሰበር የምስራች

የታላቁ ኮንፈረንስ ቀንና ቦታ

በኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር የተዘጋጀውና በአይነቱ ልዩ የሆነው ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ፣ አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል።
ቀን:- ጥቅምት 3/2017
ቦታ:- በሚሊኒየም አዳራሽ (ቦሌ ኤርፖርት አጠገብ)

የኮንፈረንሱ መሪ ሀሳብ:-
ዲናችንን ማወቅ፣ መተግበርና ማስተማር

የመግቢያ ትኬትዎን ቶሎ ከእጅዎ ያስገቡ!

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة
ትኬቱም እየገዛቹ አቅሙ ሌላቸው ወገኖቻችንም እየነየትን

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

08 Oct, 07:49


ቀልድ ማብዛት ልብ ያደርቃል👉 ልብ ሲደርቅ ተቅዋ ይጠፋል👉 ተቅዋ ሲጠፋ ወንጀል መስራት ይበዛል👉 ወንጀል መስራት ሲበዛ  ዱኒያም አኼራም ይበላሻል።

ቀልድ ምታበዙ ወንድም አና እህቶቼ አላህን ፍሩ ከዚህ ተግባራቹ ተቆጠቡ። በተለይ እህቶች ቀልድ ማብዛታቹ የሴትነት ጌጣቹ ማለትም ሀያእ እንዲጠፋባቹ ያደርጋል። ስለዚህ ለዱኒያቹም ለአኼራቹም እንዲሁም ለክብራቹ ጉዳት ያለውን ነገር ራቁ።

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

04 Oct, 18:31


ሼር ሼር አድርጉት

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

04 Oct, 18:31


👉 ሬቻ ባህል ወይስ ባእድ አምልኮ

አብዛኞች ሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ባአል ነው ይላሉ ። በዚህም ሙስሊሙም ክርስቲያኑም እንዲያከብረው ብዙ ይወተውታሉ ።
ለዚህም ይመስለኛል አብዛኛዎች ሙስሊሞች እንደውም ተውሒድን ተረድተናል የሚሉትም ጭምር ይህን ባአል ሲያከብሩ የሚታዩት ። ለማንኛውም ለባአሉ የሚሰባሰቡ አካላት የሚፈፅሙትን ተግባር በማየት ምንነቱን ማወቅ ይቻላል ።
በዚህ ባአል ላይ ከሚፈፀሙ ተግባራት ውስጥ የአባ ገዳ ምልክት የሆነውን ዛፍ ቅቤ መቀባት ፣ መሳለም ፣ አጠገቡ ደርሶ ስጁድ መውረድ ፣ እጅ ዘርግቶ መለመን እንዲሁም ወንዝ አጠገብ ስጁድ መውረድ ፣ በሳር ከወንዙ ነክሮ በራስ ላይ መርጨትና የመሳሰሉ ተግባራቶች ይገኙበታል ።
እነዚህ ተግባራት በየትኛው መመዘኛ ነው የፈጣሪ ማመስገኛ የሚሆኑት ? ምናልባት ፈጣሪዬ እንጨት ነው ብሎ የሚያምን ካልሆነ በስተቀር ። እንዴት አንድ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ ሌላ አምላክ የለም ብሎ የምስክርነት ቃሉን የሰጠ ሙስሊም በእንደዚህ አይነት የባእድ አምልኮ ውስጥ ይዘፈቃል ?
እስልምና አላህ ማለት ሁሉን የፈጠረ ፣ የፍጥረተ ዐለሙ አስተናባሪ የሆነ ፣ አምሳያ የሌለው ፣ ያልወለደ ፣ ያልተወለደ ፣ ያማሩ ስምና ባህሪይ ያሉት ፣ በአምልኮት ብቸኛ የሆነ አምላክ እንደሆነ ነው የሚያስተምረው ። አማኞች አላህን የሚገዙባቸው የአምልኮ አይነቶች ፈርድና ሱና ( ግዴታና በፈቃደኝነት የሚሰሩ ) ብሎ ደንግጓል ።
የአላህ መልእክተኛ እኔ ባላዘዝኩት መልኩ አላህን የተገዛ ሰው ስራው ተመላሽ ነው አላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ብለው አላህን የምንገዛባቸው የአምልኮ አይነቶች በመረጃ ላይ የተገደቡ መሆናቸውን ገልፀው ትልቅ መርህ አስቀምጠዋል ።
ለአላህ ብቻ የሚገቡ የአምልኮ አይነቶች እንደ ስጁድ ፣ ስለት ፣ ዱዓእ ( ሰላምን ፣ ፍቅርን ፣ ዝናብን ፣ ጤናን ፣ በረከትን ፣ ስኬትን ፣ መለመንን) ከአላህ ውጪ ካለ አካል ከመላኢካም ፣ ከነብይም ፣ ከወልይም ፣ ከጅንም ፣ ከአድባርም ፣ ከቆሌም ፣ ከጨሌም ፣ ከእንጨትም ፣ ከድንጋይም … ወዘተ መፈለግ ከእስልምና የሚያወጣ የሽርክ ተግባርና አላህ የማይምረው መሆኑን ቁርኣንና ሐዲስ አፅኖት ሰጥቶ ገልፆታል ።
ታዲያ እንዴት ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት የሚከናወኑበትን ሬቻ ሙስሊሞች ያከብሩታል ? እንዴትስ ለእንጨት መስገድና ቁርባን እያቀረቡ ችግራቸውን ነግረው ፈረጀት መጠየቅ ባህል ሊሆን ይችላል ? ለወንዝ እየሰገዱ ፈውስ ፍለጋ ከውሀው መረጨት እንዴት ከአምኮትነት ወጥቶ ባህል ይሆናል ? ከሆነም የሽርክና የኩፍር ባህል ነው ሊሆን የሚችለው ። ኢስላም የዚህ አይነቱን አምኮ ፈጣሪን ሳይሆን ሸይጣንን ማምለክ እንደ ሆነ ነው የሚያስተምረውና ሙስሊሞች አኼራችሁን እንዳትከስሩ ተጠንቀቁ !!! ።

http://t.me/bahruteka

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

04 Oct, 11:51


⚠️የጁምአ ኹጥባ

በኡስታዝ አቡ አብዱራህማን አብዱልቃዲር ቢን ሀሰን

✳️በአዳማ ኢብኑ ተይሚያህ መስጂድ

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

04 Oct, 11:51


"ኢኽዋኖቹ እነ በድሩ ሁሴን እና መሰሎቹ በዳእዋ ስም ዝሙት እንዲስፋፋ ሰበብ እየሆኑ ነው ያም ሴት እና ወንድ በአንድ አደራሽ በኢኽጢላጥ እየጋበዙ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ እነ ኢልያስ አህመድ እና መሰሎቹ እነኚህ ሰዎች ጥፋት ሲሰሩ እያዩ ማስጠንቀቅ ሲገባቸው አብረዋቸው አንድነት ከነሱ ጋር መመስረታቸው ነው።"

https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

28 Sep, 19:53


ኒቃብ መለብስ ከኢማን ነው። ምክንያቱም ኒቃብ ምትለብስ ሴት ሀያእ ስለምትላበስ ሀያእ ደግሞ ከኢማኑ አንዱ ክፍል ነውና ስለዚህ እህት ሀያእ ኢማንም ያላት የአላህ ባሪያ መሆን ከፈለግሽ የሸሪአውን መስፈርት ያሟላ ኒቃብ ልበሺ።

ሼር

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

26 Sep, 20:09


አላማ ያላቸው ሰዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ ይጠቀማሉ አላማ የሌላቸው ደግሞ ጊዜያቸው በማይጠቅም ነገር ወይም አላህን በማመፅ  ይገላሉ። የአላህ ባሮች ሆይ  እስኪ ራሳቹህን ፈትሹ ከየትኞቹ እንደሆናቹ።ጊዜያቸውን በአግባቡ ከሚጠቀሙት ናቹህ ወይስ ጊዜያቸውን ከሚገድሉት?

Share

https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1

8,002

subscribers

969

photos

122

videos