ሱመያና ያሲር፣ አነስና ሐምዛ የእስልምናን የበላይነት የከፍታና የኃያልነት ዘመኑን አልተመለከቱም
የዑመርን ፉቱሐት የኻሊድን ድል አላዩም
"አንቺ ዳመና ሆይ አዝንቢ የትም ብታካፊ የምድርሽ ቡቃያ ይደርሰኛል" የሚለውን የሐሩን አርረሺድን ኹጥባ አላዳመጡም
ሙሐመድ አልፋቲህ ከቆስጠንጢኒያ ድል በኋላ መርከቡን በየብስ ላይ ሲጎትት አልተመለከቱም
አለም በኢስላም ርዕዮተ ዓለም ሲተዳደር አላዩም
እነርሱ መንገዱን ገና ከመጀመራቸው መጨረሻውን ሳያዩ፣ የዘራቸውን ፍሬ ሳይቀምሱ ይህቺን ምድር ለቀው ሄዱ
ስለጉዞው መጨረሻ አትጠይቅ ዓላማና ግብ ባለት በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆንህ በቂ ነው!!
@Sycotube™||ኢስላሚክ ሳይኮ Tube