❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️ @yefikrclinic Channel on Telegram

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

@yefikrclinic


🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ

ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤

HBD ለማለት፤ 🎂

ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀

ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂

🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን። @yefikrclinic_bot


contact us 👉 @yefikrclinic
ላይ ይላኩሉን

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️ (Amharic)

አሁንም መከላከያዎችን ለፍቅር ክሊኒክ የተለያዩ ይላኩን! እኛ እናሰራለን የፍቅርዎ በመግለፅ surprise እና ለምሳሌ እናመልከታለን! የልደት ቀንን የመፈለግ እና ለናፍቆትዎ በመግለፅ እንድታስቱ ለመጠየቅ እና እንዲህም በፍጥነት እናደርሳለን! የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ ላይ ይላኩልን በትክክለኛ ቦታ @yefikrclinic_bot በመጠቀም እናመልከት። በመጫን እናለዋለን @yefikrclinic በመጠቀም ለማለት እናመልከት።

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

11 Feb, 08:10


🌹♥️🌹የሴት ጓደኛ ለመያዝ አስበህ ታውቃለህ ምን ልበላት ብለህ ቃላትስ አተህ ታውቃለህ🌹🌹 እንግዲያውስ የፍቅር ቃላት ፍለጋ አበቃ በቀላሉ ማግኘት ትችላለህ🥰🌹👇🌹👇🌹

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

08 Feb, 18:07


​​🥰 ልጩህበት! 🥰

ክፍል ~~~~ሁለት(➋)

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••
አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!
ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች••
••••
እንደፈራች ገባኝ
እኔ ሽምቅቅ ልበልልሽ አልኩ በሆዴ
ዝም ብዬ ሳያት ሳቋ መጣ ፍርሀት የተቀላቀለበት ሳቅ ሳቀች
የፈለከውን አርገኝ ስትይ?
"በቃ ብዙ ሳናወራና ሳንቀራረብ ልንገርህ ብዬ
ነው "
እኮ የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ነው?
"እየተጫናነኩኝ ነበረ እኮ እይታይክም እንዴ በቃ ሲጨንቀኝ ነው እንጂ አንተ ባጃጅ ውስጥ የገባሁት ምንም ብር የለኝም ለዛ እኮ ነው ጨንቆኝ እኮ ነው ዝም ብዬ ግንቡን ተደግፌ ስቆም የነበረው"
ከጥያቄዬ እየሸሸች ስትቀበጣጥር የኔም ሳቅ መጣ ቢሆንም ለሶስተኛ ግዜ ጥያቄዬን ሰነዘርኩ
በዚህ መሀል መልሷን በጉጉት እየጠበኩ
አንድ ሰካራም ለሱ ያቆምኩ መስሎት ነው መሰለኝ ኬት መጣ ሳይባል ግራ ቀኝ እየተጋጨ ከውሃላ ገብቶ አጠገቧ ተቀመጠ።
ድንገት ስለገባ ደንግጣ •••
"እማ"
ብላ እየተጣራች ከነበረችበት መሀል ወደ ጥግ ተጠጋች ከሰውየው ራቅ ለማለት።
እሱም መደንገጧን አይቶ ዘወር አለና ወደሷ •••
በመሀል በመሀል ስቅ እያለው•••
"አይዞሽ የኔ ቆንጆ አስደነገጥኩሽ አደል ይቅርታ አንቺኮ - ሀበሻ ሴት ስለሆንሽ ብቻ በጭለማ ውስጥ ያለሽ የ-የ-የ-የ የብርሀን ጭላንጭል ነሽ አይገርምሽም"
አይገርማትም አሁን ባጃጁን ያቆምኩት ላንተ አይደለምና ውረድ አልኩት ድንገት በንዴት!።

ለኔ ንዴት ቦታም አልሰጠው •••
"ለኔማ ነው ያቆምከው! ለሌላ የቆምክ መስሎህ ነው እንዴ?
እኔን እኮ ነው እዛ ጋር ቆሜ ያየከኝ። ሌላ ሰው ቢኖር ለምን እስካሁን አልመጣም? ይልቅ አንተ ስራህን ስራ ከልጅቷ ጋር ላውራበት" ብሎ ሲመልስልኝ ልጅቷ ሳቋን ለቀቀችው።

ሰካራሙ ሰውዬ አንገቱን ከኔ ላይ መንጭቆ በፍጥነት ወደሷ ዞረና•••
"ምን ምን ምን ምን እስቲ በናትሽ ሳቅሽን ድገሚው የተኮረኮረ ህፃን ልጅ እኮ ነው እምትመስይው !
ወይኔ ልጄ ለምን እንደምጠጣ ታውቂያለሽ የልጄን ናፍቆት ለመርሳት !

ልጅ በልጅነት ሲሉ ሰምቼ ምንም ሳይኖረኝ ወልጄ ፍቅረኛዬ እኔ ላይ ጥላብኝ ስትሄድ እኔ ደግሞ አሮጊቷ እናቴ ላይ ጥየባት መጣሁ።

እናቴ ግን መጣያም ቢኖራት የሚጥል አንጀት የላትም እና እኔን ፍዳዋን በልታ ያሳደገችኝ እንዳይበቃት ላስርፋት ሲገባኝ እረፍት እምትነሳ የአንድ አመት ህፃን ልጅ ጥየባት ከመጣሁ ስድስት አመት ሞላኝ አንዴ ብቻ ነው ልጄን ያየሁዋት!!

ግን ግን በናትሽ ካላስቸገርኩሽ ያሁኑን ሳቅ አንዴ ድገሚልኝ !"
ተበሳጨሁ።

ስማ የሷ ሳቅ ስትጋት ያመሸከው ጠጅ መሰለህ እንዴ እሚደገመው አሁን እምትወርድ ከሆነ በፀባይ ውረድልኝ? አልኩት።

"ጠጅ አልጠጣሁን አረቄ ነው ጠጅ ስጠጣ አይተሀል? ነበርክ? ደሞ ሳቅ እንጂ ሌላ ነገር ድገሚኝ አላልኳት ምን አቃጠለክ ኪኪኪኪ " ብሎ ሳቀና ደሞ ወደሷ ዞሮ

"እኔኮ ተሳፋሪ መስለሽኛል ! ፍቅረኛሽ ነው እንዴ ለካ! በቅናት አንገበገብኩልሻ አንበሳ ነኝ አደል አንበሳ••••" እያለ ሳቁን ቀጠለው።
ትግስቴ አለቀ ጎትቼ ላወርደው ተፈናጥሬ ስወርድ•••

"በናትህ ተው እንዳትጣላ " ብላ ጮከች ልጅታ እጇን እያውለበለበች እና እንዴ ወደኔ አንዴ ወደሱ እየተመለከተች

"አፌ ቁርጥ ይበልልሽ አንቺ ባትኖሪ ምን ይውጠኝ ነበር
ሆሆሆሆ ሊበላኝ ነው እንዴ?
እውነቴን ነው እድሜ ለሴቶች እንበል እናንተ ባትኖሩ እኮ እኛ ወንዶች እሄን ግዜ እንደ ዳይኖሰር እርስ በርስ ተበላልተን ከምድረገፅ በጠፋን ነበር!

አሁን እራሱ ኮረና ያላጠፋን ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? አታውቂም?
እንደኔ ከሆነ ከረና ድምጥማጣችንን ያላጠፋን ኢትዮጲያዊያን ሴቶች ጨዋዎች ስለሆናችሁ ነው
እድሜ ለናንተ!

እውነቴን ነው አሁን እኔ ልሙት እንኳን ማክስ ሱሪስ እምታስወልቁን እናንተው አደላችሁ ።

እናንተ ጨዋ ባትሆኑ ማነው ማክስ አላወልቅም የሚለው እንደ ብራዚል ሴቶች ብትሆኑ ማን ይተርፋል ? አልቆልን ነበር ሙች እውነቴን ነው!
እሱ ይለፈልፋል እሷ ትስቃለች !
ሰውየው የባጥ የቋጡን እየቀባጠረ ደሜን ቢያፈላውም ለምን እንደሆነ ባላውቅም በሱ ንግግር የምትሰቀውን ልጅቷን ማየት ስላስደሰተኝ ነው መሰለኝ ሳላስበው ብዙ ታገስኩት
አሁን ትወርዳለህ አትወርድም አልኩት ወደሱ እየተጠጋሁ
"እራስህ እኮ ነህ አቁመህ የጫንከኝ !"
ላንተ አልቆምኩም አልኩህ እኮ!
"ታድያ ለማን ነው የቆምከው?"

ለሷ!
"ለሷ ካካካ እሷኮ አብራህ ነው የመጣችው••••
እሀሀሀ ልታወርዳት ነበር እንዴ የቆምከው ገባኝ !

ታድያ ምን አጣደፈህ ቀስ ብለህ አትቆምም ብቻሽንማ አትወርጂም ነይ በይ እንውረድ!"
ሲላት•••

ሳላውቀው በንዴት ውስጥ ሆኜ ሳቄ መጣብኝ እንደምንም ላለመሳቅ እየታገልኩ ኮሌታውን ይዤ ጎትቼ ላወርደው ስል•••
"እባክህ ተወው እንደዛ አታድርግ ! ቆይ የት ነው መሄድ እምትፈልገው አንተ ?!" አለችው።
"ብዙ አርቅም እኮ እሄኛው መጠጥ ቤት ስለተዘጋብኝ እቅዴ ደሞ አዳሬን መጠጣት ስለሆነ ቤት ልቀይር ነው እዛች ጋ ያለችው ግሮሰሪ ደሞ ካልታሸገች በስተቀር አትዘጋም ወደዛ ነው እምሄደው " ሲላት
"በናትህ ጣል አርገነው እንለፍ ?" እለችኝ ባይኗ እያባበለች
ምነው በሱ ምክንያት የምታመልጪ መሰለሽ እንዴ እሱን አውርጄው የጀመርነውን እንጨርሳለን እሺ አልኳት ኮስተር ልልባት እየሞከርኩ።
ባጃጁን አስነስቼ ከነፍኩ።

"ምን አርጊ ነው እምትላት እነጨርሳለን እንጫረሳለን እያልክ ታስፈራራለህ እንዴ?" አለ
እስቲ ዝምበል ስለው ጭራሽ ባሰበት•••
"ዝም አልልም እንደውም እሱን ተይው አንቺ ብቻ ፍቀጅልኝ?"
"ምን ?"
"አንዴ ልጩህ በናትሽ ?"
"እንዴ ለምን ምን ሆንክ?" አለችው ግራ ተጋብታ ሰውየው መች ያልቅበትና እኔ በማታ ስራ ብዙ ሰካራም ጭኛለሁ እንደዚህ ሰውዬ ግራ ያጋባኝ ሰው አልገጠመኝም ቀጠለ•
"አንቺ ምን ስትሆኚ ነው እምትጮሂው?"
"ምን አይነት ጩኸት?"
"እሄውልሽ እኔ ደስ ሲለኝም እጮሀለሁ ሲጨንቀኝም እጮሀለሁ በናትሽ አሁን አንዴ ልጩህ ? ፈቀድሽልኝ አለና
በጣም በሚያስፈራ ድምፅ አቀለጠው።

እሷም ደነገጠች እኔም ባጃጁን አቁሜ በደምፍላት ወደሱ ዞርኩና
አንተ ሰውዬ እብድ ነህ እንዴ?ስለው

"የፈለከውን በለኝ ግን በናትህ ልጩህበት ተወኝ ?"

እስቲ ወንድ ነህ ድገመው አልኩት። የጉድ ቀን አይመሽም አሉ ዛሬ የጉድ ለሊት አይነጋም ሆነብኝ እሷ በኔና በሱ ሁኔታ ትስቃለች ሰውየው ቀጠለ
ልጩህበት ተወኝ ተወኝ ልጩህበት
በአፌ ቢወጣ የውስጤ እንፋሎት
ለየልኝ እሄ ሰውዬ አላበዛውም እንዴ ግጥምህንም አንተንም አልፈልግም ውረድልኝ

እቺን ግጥም ሳልጨርስልህማ አልወርድም

ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ
ንዴቴን
ብሶቴን
ናፍቆቴን ባከስመው
እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!!
••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ•••

"አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ•••
ይቀጥላል......

━━━━━━━━ ✦
✎ ክፍል 3 ይቀጥላል....
@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

07 Feb, 09:36


​​🥰 ልጩህበት! 🥰

ክፍል ~~~~አንድ(1)

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.

ስራዬን በጀመርኩ በ ሀያኛው ቀን ላይ እንደተለመደው እራቴን በልቼ ቡናዬን ጠጥቼ ከምሽቱ 3:15 ላይ ወደ ስራ ወጣሁ እስከ ምሽቱ አምስት ሰአት ድረስ ሲዝናኑ ካመሹት መሀል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ቤታቸው ከፊሉን ከመጠጥ ቤት አልጋ ወደያዙበት ሌላ ሆቴል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ሌላ መጠጥ ቤት ሳገላብጥ ቆየሁ።

ከምሽቱ አምስት ሰአት ካስር አከባቢ አንድ
ቀን ቀን ሆቴል ሆኖ ማታ ማታ ቅልጥ ወዳለ ጭፈራ ቤት ወደ ሚቀየር ሆት-ጭፈራ ቤት ከውስጥ የሚወጣ እና ትራንስፖርት መጠቀም የሚፈልግ ሰው እስኪወጣ ለመጠባበቅ ጠጋ ብዬ እንደቁምኩ አይኔ አንዲት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሚጣል ነገር የለላት በዛው ሰአት ሰማይ ላይ እንዳለችው ጨረቃ ደስ የሚል ውበት ያላት ልጅ መግቢያ በሩ በስተቀኝ ብርዱን ለመቋቋም ከጡቶቿ በታች እጆቿን አጠላልፋ በማጣመር ቆማለች።

ሁኔታዋ ሲታይ ግራ ግብት ያላት ትመስላለች እዛው ቆማ አንዴ ቁልቁል አንዴ ሽቅብ ትገላመጣለች ።

እድሜዋ በግምት በ 19 እና በ21 መካከል ቢሆን ነው ይቺን የመሰለች ልጅ በዚህ ሳአት ሊያውም ብቻዋን እንዴት? ትልቁ የውስጤ ጥያቄ ነበር ።

አከባቢው ለኔ አዲስ ባይሆንም ልጅቷ ግን ለአከባቢው እዲስ ሳትሆን አትቀርም ከዚህ በፊት አይቻት አላውቅም ከባጃጄ ወርጄ ምነው ብቸሽን ልበላት አልበላት እያልኩ ከፍርሀቴ ጋር ስነታረክ አንዱ ስልክ ሊያናግር ከውስጥ ወደ ውጪ ወጣና ወድያው ስልኩን አናግሮ እንደጨረሰ አብረን እንግባ ብሎ ልጅቷ ላይ ሙዝዝ አለባት ከዛ በፊት እንደማይተዋወቁ ከሁኔታዋ ተረዳሁ።

ድርቅ ሲልባት ብስጭት ብላ ውዝውዝ ቅንጥስ ብጥስ እያለች ቀጥታ ወደኔ ባጃጅ መጣች ከመድረሷ በፉት ባላየ ፍቴን ወደ ፊት ለፊት አዞርኩ።

ደርሳ " ይቅርታ ወንድም ግቢ ትወስደኛለህ? ኮንትራት "
አለች ዩንቨርስቲ ማለቷ ነው ልጅቷ የዩንቨርስቲ ተማሪ እንደሆነች ለማወቅ ግዜ አላጠፋሁም ዩንቨርስቲው ደግሞ ከከተማው ትንሽ ወጣ ይላል

200 ብር ትከፍያለሽ አልኳት
ግማሽ ፉቷ ላይ ዘንፈል ብሎ ጋደም ያለውን ፀጉሯን በቀኝ እጃ ሁለት ጣቶች ወደ ጀርባዋ ብትን አደረገችና

"200 ብር ለተማሪ አይበዛም ወንድሜ ቤተሰብ በወር የሚልክልኝ እኮ 300 ብር ነው !" አለችኝ

መጀመሪያ አሳዘነችኝ !
ቆይቼ ደግሞ ታድያ አርፈሽ ትምህርትሽን አታጠኝም በዚህ ሰአት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ?!ልላት ፈለኩና እሷን እንዲህ ለማለት ምንም አይነት መብት እንደሌለኝ ቶሎ በማስታወሴ ምላሴን ሰበሰብኩ።

"እ ምናልክ " አለችኝ ።
በደንብ ተመለከትኳት። ውስጤ ተላወሰ ።

እሺ ግቢ እንሂድ አልኳት
"በስንት?" አለችኝ

ደስ ያለሽን ትከፍያለሽ ዘላ ገባች ። ትንሽ በዝምታ እንደተጓዝን ድንገት ዘወር አልኩና•••••ሂሳብም አስቀንሰሽ ዝምም ብለሽ አያዋጣኝም !

"ኦኬ እእእእእ ግን ይቅርታ በናትህ ከሚከብዱኝ ነገሮች አንዱ ጫወታ ቀድሞ መጀመር ነው" አለች እየተቁነጠነጠች

ምን አይነት ጫወታ ? አልኳት

"ያው ወሬ ነዋ ሌላ ምን አለ?"
ኧረ ብዙ አይነት ጫወታ አለ ተጫውተሽ አታውቂም እንዴ?
"እንዴ ! ክክክክክ እሱማ ብዙ አይነት ጫወታ አለ እኔ ለማለት የፈለኩት ግን ወሬውን ነው"
ሳቋ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ ደስ የሚል ለዛ አለው ።

ምን አይነት ጫወታ ይቀልሻል? ወይም ትወጃለሽ?

"እቃቃና እኩኩሉ ልበልህ "
ተሳሳቅን ሳቋን ወደድኩት።
ወደ ዩንቨርስቲው እየተቃረብን ነው።

እሺ እኔ ጫወታ በመጀመር ላግዝሻ?

"ከዚህ በላይ እሄው ጀመርከው እኮ! አለችኝ

እኔ ግን ጥያቄ ነበረኝ
የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆነሽ በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ወይ ገብተሽ አልተዝናናሽ

በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••

አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!

ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች•••

ይቀጥላል......

━━━━━━━━ ✦
✎ ክፍል 2 ከ 100Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል.... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።

@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

04 Feb, 11:55


የፍቅር ክሊኒክ

ዝም ብለህ ስማኝማ… ልክ ጥዋትህ ነግቶልህ ከእንቅልፍህ ስትነቃ

ባልካፈትከው በሌለህ የባንክ አካውንት ውስጥ 86,400 ብር ቁጭ ብሎ ቢያድርልህና ውሰደው ይሄ ቀን መሽቶ እስክትተኛ ድረስ በትክክል ተጠቅመህ ጨርሰው ብትባልስ?

አስበሃዋል በምን ፍጥነት ልታጠፋው እንደምትችል… ለሌላ ሰው ማበደርም ሆነ መለገስ አትችልም ለራስሀ ብቻ አጥፍተህ ጨርሰው ቀኑ እስኪመሽ አጥፍተህ ባትጨርሰው ይቃጠላል expired ያደርጋል… በቃ ሁሌ ጥዋት ስትነቃ የትላንቱ አልቆ ወይም ተቃጥሎ አዲስ ሰማንያ ስድስት ሺ አራት መቶ ብር አለህ በዛሬዋ ቀን አጥፍተህ ጨርሰው ብትባልስ?

ይሄን ሁሉ ብር በየቀኑ እንዴት አድርገህ ልታጠፋው እንደምትችል አስበው… ።
ምን ብትገዛ በምን ብትዝናና በየቀኑ ሰማንያ ስድስት ሺ አራት መቶ ብር ልታጠፋ ትችላለህ።

ለነገዬ ብለህ መቆጠብ አትችል ደሞ ነገ ሌላ ተመሳሳይ ብር ይሰጥሃል እንዴት ታጠፋዋለህ? አስብከው? ምን ልታደርገው እንደምትችል መጣለህ? ወይስ መጀመሪያ ላግኘውና አስብበታለው አልክ…

እኔ ግን በምን አይነት ፍጥነት ተንገብግቤ እንደማጠፋው እያሰብኩ ነው… ለማንኛውም ምን ልልህ መሰለህ በየቀኑ ሰማንያ ስድስት ሺ አራት መቶ ሰከንዶች በነፃ ያለጥያቄ ይሰጥሃል በልዋጩ የምትከፍለው ነገር የለም መታውቂያ እንኳን አትጠየቅም።

ማመልከቻ ሳታስገባ ሳትከፍል በቅጡ ሳትለምነው የትላንቱን ቀንህን በዝባዝንኬ ነገር እንዳሰለፍከው እያወቀም ለዛሬው ቀንህ ሰማንያ ስድስት ሺ አራት መቶ ሰከንድ አምላክ በነፃ ሰጥቶሃል እንዴት ልትጨርሰው አስበሃል? ምን ልታደርግበት እየወሰንክ ነው?

በየትኛው ሰክንድ ላይ የዛሬ ኮታህ እንደሚጠናቀቅ የምታውቀው ነገር የለም… ከምትወዳት እናትህ እራሱ አንዲት ሰከንድ መበደር ማበደር አትችልም ሰከንዱ ሲጠናቀቅ አለቀ ትሞታለህ።

ገንዘብ አላቂ ነው ብለህ እንደምታጠፋው ጊዜ አላቂ ነው ተጠቀምበት።
የዛሬው ቀንህ ልክ መጠቀምህ ማጥፋትህ ግዴታ እንደሆነ ገንዘብ አድርጋህ ተጠቀምበት ነገ መኖሩን አታውቅምና።

አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

27 Jan, 18:32


😘አንቺዬ ... አራዳ😘

🔥ክፍል 8

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ራስ ምታት አናቴን ይፈልጠኛል።ብርዱ አጥንቴ
ድረስ ሰርስሮ ሲገባ ይታወቀኛል።ተንጋልዬ ከወደኩበት ራሴን ተቆጣጥሬ ቀስ ብዬ ተነሳሁ።መልኬ አጠገቤ ተዘርሯ ተኝቷል።ያለንበት ቦታ ሽታው ይቀረፋል።ምን እንደተፈጠረ ለማስታወስ ሞከርኩ። ትቦ ውስጥ ነን!! ትቦ ውስጥ ወድቀን ማደራችንን ላምን አልቻልኩም። መልኬን ለመቀስቀስ ሞከርኩ።አይሰማም። ተጠግቼ ሰውነቱን ነካሁት። በጣም ያተኩሳል።ሰውነቱ በላብ ተነክሯል።አስሙ ተነስቶበታል!! ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ።ትቦ ውስጥ ወጥቼ አካባቢውን ቃኘሁ። ገና በወጉ አልነጋም።ወፎች ይንጫጫሉ።ነጠላ አጣፍተው ከቤተክርስቲያን ከሚሄዱ አንዳንድ ሰዎች በቀር አካባቢው ጭር ብሏል። ውስጥ ለውስጥ ጉራንጉር የበዛበት ሰፈር ነው። ዞረብኝ!በቆምኩበት ብዥ ሲልብኝ ይታወቀኛል።ብዥዥዥዥ...ራሴን በሁለት እጆቼ ግጥም አድርጌ ያዝኩት ብዥታውን ለማስለቀቅ..... ከፊቴ ሁለት ሴቶች ወደ አቅጣጫ ሲመጡ ይታየኛል። መልካቸውን መለየት አልቻልኩም።
<<ወንድም ሰላም ነህ?? አመመህ እንዴ?>>ራሴን በሀይል ያዞረኛል።እንደምንም ራሴን ተቆጣጣሬ<<ጓደኛየን አሞታል... >> አልኳቸው ጣቴን ወደ ትቦው እየጠቆምኩ።
............. ............. ..........
የቤት መኪና ውስጥ ያለን ይመስለኛል። መልኬ አጠገቤ ወንበሩን ተደግፎ ተቀምጧል። ከፊት ወንበር ነጠላ የለበሰች ልጅ ደጋግማ ወደኛ ትዞራለች። ድምጿን በሰመመን ውስጥ ሆኜ እሰማዋለሁ። መልኳን ማየት ግን አልቻልኩም። ብዥታው አሁንም አለቀቀኝም።ወደ ክሊኒክ...
..............ከሳምንት በኋላ..............
መልኬ ክሊኒክ አልጋ ከያዘ ሳምንት ሆነው። ዛሬ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሆነና መውጣት እንደሚችል ዶክተሩ ነግሮታል። ወደ መልኬ ቤት እየሄድን ነዉ። እኔ፣መልኬና የመልኬን ህይወት ያተረፈችው ልጅ ሄለን!! ትቦ ውስጥ አግኝታ የረዳችን ልጅ ነች።ሳምንቱን ሙሉ እየተመላለሰች ያስታመመችን ደግ ሴት!!! አንዳንድ ሰዎች የመላእክትን ያክል ናቸው። መላእክቶቹ መድረስ በሚገባቸው ጊዜ ይከሰታሉ።መልኬም ሂወቱን የሚያተርፍለት መላአክ በሚያስፈልገው ጊዜ ደርሳለታለች።እነሱን ወክላ ወይም ከነሱ ቀድማ ተከስታለች!!! መልኬም ይህ የገባው ይመስለኛል። እንደሚገባው አምናለሁ...
........... ከአንድ አመት በኋላ...........
ዛሬ ሚይዜ ነኝ።አንደኛ ሚይዜ!! ለመልኬ ሰርግ!! አዎ!ዛሬ መልኬ ያገባል።ሄለንን!! ሄለን መልኬ ህክምናውን ጨርሶ ቤት ከተመለሰ በኋላ ተመላልሳ ትጠይቀው ነበር። ለመግባባት ብዙ ጊዜ አልወሰደባቸውም።ፍፁም ቅንና ደግ ባህሪዋ ቀልብን ይገዛል። ለሌላ ሰው ማሰብ መቻል ከሰው ልጅ ባህሪያት በላጩ ነዉ። የማንንም ቀልብ ይገዛል። የማንንም ልብ ማሸነፍ ይችላል። የመልኬንም ቢሆን!!
.................... ................ ...............
የሰርጉ አዳራሽ በሰዎች ጢም ብሎ ተሟልቷል። የሰርግ ዘፈን ተከፍቷል። ሰው ጥንድ ጥንድ ሆነው መወዛወዝ ጀመሩ። መልኬና ሄለን ወደ ሰዎቹ ተቀላቀሏቸው።መሀል ላይ ሆነው በዝግታ መደነስ ጀመሩ።
ዘፈኑ ይቀጥላል...እኔ ግን ታሪኬን እዚህ ጋር ጨርሻለሁ።
.
.
---------ተፈፀመ--------------

አንቺዬ አራዳ ይሄን ይመስላል....ታሪኩን እንደወደዳችሁት ተስፋ እናደርጋለን።
.

━━━━━━━━ ✦
ሀሳብ አስተያየታችሁን

@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

25 Jan, 12:48


😘አንቺዬ.. አራዳ😘

🔥ክፍል 7

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
ሊጠናቀቅ 1 ክፍል ብቻ ቀረዉ...
.
.
በሚቀጥለው ቀን ኤደን መልኬ ቤት መጣች። እኔ ዘራፍ አልኩ<<አንቺ ልክስክስ! እንዴት እዚህ ደፍረሽ ትመጫለሽ? ውሻ ነሽ እሺ!>>ገላመጠችኝ።ፊቷን ወደ መልኬ አዙራ <<መልኬ እንዴት ነህ?>>አለችው። እሱ እስኪናገር አልጠበኩም። <<አረ ባክሽ! አሁን ነው የሱ ደህንነት የሚያሳስብሽ?? ያኔ ከማንም... >><<ሳሚ!>>መልኬ ጮሀብኝ።<<የራስህ ጉዳይ ነው እሺ! ሞሮ!>>ብየው ጥየው ወጣሁ።ታረቁ።
................ .............. .............
ከሳምንት በኋላ መልኬ ኤደንን ለማስመረቅ ሄደ።ሲመለስ ይቅርታ ጠይቆኝ የሆነውን አጫወተኝ። ግቢ ፍቅረኛ እንዳላት ከጓደኛዋ አፍ እንደሰማ ነገረኝ።<<ለምን አትጠይቃትም?>>
<<ጠይቂያታለሁ። ምንም ግንኙነት የለኝም ፣አሳይመንት የሚሰራልኝ እሱ ስለሆነ ነው! ምናምን ትላለች >>
<<ታምናታለህ ? >>
<<አላውቅም!! ለትንሽ ጊዜ ራቅ ብዬ ማሰብ እፈልጋለሁ!!ከራሴ ጋር ማውራት እፈልጋለሁ>>አለኝ። እሱ መሆኑን ተጠራጠርኩ። ግን ትክክል ነው!! መልኬ ኤደን ግቢ ከሄደች በኋላ ራሱን አይደለም። ኤደን አሁን ላይ እንደማትወደው ለሶስት አመት ሙሉ እያወቀ ራሱን ሲያታልል ቆይቷል።አሁን ግን ፊቱ ላይ የድካም ስሜት ይታየኛል። አዎ!ራሱን መሸወድ ደክሞታል።ውስጡን መስማት ፈልጓል።ለመጀመሪያ ጊዜ ከሷ መሸሽ ፈልጓል። ምናልባትም እስከ መጨረሻው....
................. ............. .............
ከሳምንት በኋላ ደወለልኝ። መሲ ጋር ነበር የቆየው። ስልኩን አጥፍቶ ስለነበር ጮህኩበት።ዛሬ እንደሚመጣና ማታ ሊያገኘኝ እንደሚፈልግ ነግሮኝ ቀጠሮ ያዝን።
.............. ............. ...........
ኤደን ካፌ ውስጥ ተቀምጣ መልኬን እየጠበቅች ነበር። ብዙም ሳይቆይ መልኬ መጣ። ሰላም ብሏት ተቀመጠ።ግራ የተጋባች ትመስላለች። ሰላምታው ቀዝቅዞባታል።
<<እምም ምን መሰለሽ ኤደን ዛሬ የፈለኩሽ..>>የኤደን ስልክ አቋረጠው።ዘጋችው። <<እስከ ዛሬ.. >>አሁንም ስልኳ ጠራ። ስልኳን ተሽቀዳድሞ አነሳው። ስፒከር ላይ አድርጎ በምልክት እንድታዋራው ነገራት። <<ሄ...ሄሎ ቢንያም >><<ማን?ቢንያም? ኤዲ አይደለሽም? >>
<<ነኝ ለምን ደወልክ?>>
<<ዛሬ አልሰማሽም እኔ ጋር ነው ምታድሪው!! ቆጣ ቆጣ ምትይው ይተወኛል ብለሽ ከሆነ ተሳስተሻል። ይልቁንስ ነይልኝ ናፍቀሽኛል በጣም... >>ስልኩን ዘግቶ ወረወረው።
<<ጨርሰናል!! >>ብሏት ጥሏት ሄደ።ይሄን ሁሉ ካደረገችው በኋላ በአንድ ቃል ጨረሰናል ብሎ ጨረሰው። ካፌዉ ዉስጥ የነበሩ ሰዎች አይን ሲገርፋት እየሮጠች ወጣች።
.................. .............. ..........
የመልኬ ልደት ለማክበር መጠጥ ቤት እንደተሰየምን ነው። ጥንብዝ ብለን ሰክረናል። ሂሳባችንን ከፍለን።ወጣን።ሰው ሲሰክር አዕምሮውን ይስታል ይባላል። እኔ ግን ሙሉ ለሙሉ አላምንበትም። ይልቁን የሰከሩ ሰዎች ለእዉነት እና ለጥበብ ቅርብ ይሆናሉ። ለዚህ ደግሞ ብዙ ሰካራሞች በሰከረ አንደበታቸው እየተለፋደዱ የሚዘፍኑትን ዘፈን መስማት በቂ ነው። ቢያንስ ሂወታቸውን በአጭር ግጥም እና ዜማ ፈልገዉ አያጡም።መልኬም ቢሆን!!!! በስካር በተሳሰረ አንደበቱ ማንጎራጎር ጀመረ።
<<አንቺዬ አንቺዬ አራዳ
ስትመለስ ዩኒቨርስቲ ሄዳ
አንቺዬ ቀሚሷን በሚኒ
አንቺዬ መልካሙን በቢኒ
አንቺዬ ቀይራ መጣለች....
ይቀጥላል....

ሊጠናቀቅ 1 ክፍል ብቻ ይቀረዋል!!


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን

@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

23 Jan, 05:12


😘አንቺዬ.... አራዳ😘

🔥ክፍል ስድስት

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
በዚህ ሁኔታ የኤደንና የመልኬ
ግንኙነት ቀጠለ።በመሀል ለስድስት ወር ከከተማ አልነበርኩም። ኤደንም የመመረቂያ ፅሁፏን ለመጨረስ ተመልሳ መጣች። ዛሬም ቀጠሮ አለኝ።የሆነ ፀጥ ያለ ሰላማዊ ቦታ ነው መሄድ የምፈልገው። በኤደን ምርጫ አዲስ ወደ ተከፈተ ክለብ ለመሄድ ተወሰነ። መልኬ ምንም አልተናገረም። መሄድ እንደማይፈልግ ግን አውቃለሁ ። <<እንደንስ በናታችሁ?>>
<<ሳሚ!>><<መልኬ>>ምላሽ አጣች።<<እኔ መዝናናት እፈልጋለሁ። ጉዳያችሁ.. >>ብላ ስትነሳ<<አንቺ እሱን አስቀምጠሽ ከሌላ ወንድ ጋር መደነስ ግን አይደብርሽም?>>
<<ሃሃ ሃ..አራዳ ትመስለኝ ነበር። ለካ ከሌላ ሰው ጋር መደነስ መወስለት ከሚመስላቸው አንዱ ነህ!! >>ሳቋ የንዴት ነበር። ገላምጣኝ ሄደች።አዎ ገላመጠችኝ።የኤደን ግልምጫ"ስር ይነቅላል" የሚባለው አይነት ነው። (አጋነንክ አትበሉኝ እና ኤደን አንዴ የግብፅን መሪ ብትገላማጠው የአባይን ግድብ የማደናቀፉን ሀሳብ እርግፍ አርጎ ይተው ነበር😂)አስታውሳለሁ ብዙ ጊዜ ሞቅ ብሎኝ ሳወራ ገላምጣኝ ምርቃናየ እንደ ጉም ተኗል። ወደ መድረኳ እየተውረገረገች ካገችው ወንድ ጋር መደነስ ፣መተሻሸት ጀመረች።መልኬ ዝም ብሎ ሲያያት ቆይቶ ተነሳ።ሊያስደንሳት!! በኤደን አገላለፅ ከአራዳዎቹ ወገን ለመሆን!! መልኬ መደነስ አይወድም።በተለይ እንደዚህ ተፋፍጎ!! አዎ አስሙ ይነሳል።ኤደንን ስደንስ ከነበረው ሰው ላይ በሀይል ወሰዳት።ጎትቶ ወደ ዳር ሆነው መደነስ ጀመሩ።አብሯት የነበረው ልጅ ወደነ መልኬ አቅጣጫ ሲሄድ አየሁት። ረጅም ግዙፍ ሰውነት አለው። መልኩም ቢሆን ጠይም ፣አፍንጫው እንደ ንጉሳውያን ዘር ስልክክ ያለ ፣ፀጉሩ ችምችም ብሎ በስታይል የተቆረጠ ፣ባጠቃላይ መልከ መልካም.... አድናቆቴን ሳልጨርስ ደርሶ የመልኬን አፍንጫ በቦክስ ጠለዘው። መልኬ ወደቀ።ከውስጥ የነበሩ ሰዎች መጯጯህ ጀመሩ።ኤደንን እየጎተተ ይዟት ወደ ኮሪደሩ ሄደ።ነገሩን ለማረጋጋት ሞከርን። መልኬን ወደ መታጠቢያ ክፍል ወስጄ የደማ አፍንጫውን አየሁለት።ደሙ መፍሰሱን አቆመ።ወደ ቤት ለመሄድ ወጣን። ኤደንን ለመጥራት ተመልሼ ገባሁ።ቆሜ በአይኔ ፈለግኳት።ኤደን አሁንም ከሰውየው ጋር ነች።ኮሪደር ላይ ሆነው እያወሩ ነበር።ወደነሱ ለመሄድ መሀል ላይ ስደርስ እጇን ጠረጴዛው ላይ አንስቷ ሳመው።ቆሜ መመልከቱን ጀመርኩ። ሲያወሩ ቆይተው ለመሄድ ተነሱ። እጇን በእጁ ቆልፎ ያዛቸው።ከዚህ በላይ ማየት አልፈለኩም። ከዚህ በላይ ዝም ልል አልችልም። መልኬ መንገር አለብኝ። ለሱ እንደማትሆነው። መልኬ የወደደው ኤደንን እንዳልሆነ ማስረዳት አለብኝ።መልኬ የወደደው አንቺናሉን ነው።ምንም የማታውቀውን የዋኋን አንቺናሉን። ኤደን አንቺናሉን አይደለችም።በእሷ ስጋ የተመሰለች ሌላ ሰው ነች።....ወደ ውጭ ለመውጣት ስዞር መልኬ ከኋላየ ነበር። ሁሉንም እንዳየ አልጠራጠርም። አይቷል ግን አሁንም ምንም እንዳላየ ሊሆን ነዉ።ወጣን። ወደ ቤት እየሄድን ነው። የመልኬ ፊት አየሁት። ምንም አይታይም። ዝም ብሏል። የሚከብድ ዝምታ
<<መልኬ መቼ ነው ይሄ ነገር የሚበቃው? እስከ መቼ አይተህ እንዳላየህ ትሆናለህ?እሺ ምን ለውጥ ያመጣልሀል? >>አፈረጥኩት። ዝም እንዳለ ነው። ዝምምም...ተናደድኩ።
............ .............. .............
ለሶስት ቀን መልኬ ቤት አልወጣም። ማንንም አላገኘም።ሀይለኛ ድብርት ውስጥ ነው የቆየው። ብቻውን እንዳይሆን አብሬው ቆየሁ።መንፈሱን እያስታመመ መሆኑን አልጠላሁትም።
በሚቀጥለው ቀን ኤደን መልኬ ቤት መጣች...

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን

@yefikrclinic

@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

21 Jan, 18:30


😘አንቺዬ.... አራዳ😘

🔥ክፍል አምስት

አዘጋጅ፦ የፍቅርን ክሊኒክ
.
.
.
.. አያቷ ሲያዬን ደነገጡ። <<ምነው ልጆቼ በምሽት? ቀን ቀን ብትዝናኑ? እናታችሁ አይደለሁም ትጨነቃለችም አትሉ?>>አሏቸው። <<እንዴ እማማ ኤደንን ፈልገን ነበር የመጣነው እኮ የለችም እንዴ?>>አላቸው።<<አየ ልጄ ምኑን ብለህው ነወ?😔እንደ ጎረምሳ አምሽታ ነው የምትገባው ፣እሷን መጠበቅ ሆነ የኔ ስራ!!>>በጣም ተናናደድኩ።በመልኬም ተናደድኩ። <<ና እንሂድ! እንፈልጋት>>አለኝ <<የት ብለን ነው የምንፈልጋት? >>
<<ትሄዳለህ ወይስ...>>አምባረቀብኝ።ዝም ብየ ተከተልኩት። በየምሽት ክለቦች ፣ግሮሰሪዎች ዘው ብለን እየገባን ፈለግናት።ደከመኝ።ቤት ሄደን እስክትመጣ እንድንጠብቃት ብነግረውም ሊሰማኝ አልቻለም።እንደማይመለስ ስለገባኝ ተውኩት።ድንገት አንድ ሀሳብ መጣልኝ። ባለፈው የሄድንበት ክለብ ልትሆን እንደምችል ነገርኩት። ኮንትራት ታክሲ ይዘን ወደዛው ክለብ.. ልክ ስንገባ ተቀምጠንበት ከነበርንበት ቦታ ኤደን ከሌላ ወንድ ጋር እየተሳሳመች ነበር። በድንጋጤ ካለሁበት ቆምኩ።መልኬ ወደነሱ አቅጣጫ ቀጥ ብሎ ሄደ። በሁለት እጁ ሁለቱን ይዞ መንጭቆ አለያያቸው።እጇን ይዞ እየጎተተ ወጣ። ኤደን ስካሯ ሊያራምዳት አልቻለም።የለበሰችው ሂል አደናቅፏት ወደቀች።መልኬ አቅፎ መኪና ውሰጥ አስገባት። መንገድ ጀመርን።ስካሯ ቀስ በቀስ እየለቀቃት ሄደ። <<ለምን መጣችሁ?>>ተራ በተራ አየችን
<<ለምንድን ነው የምታመሽው?እኔን ተይኝ አያትሽ አያሳዝኑሽም? ለምንድንነው እንደዚህ የምትሆኝው? >>አምባረቀባት። <<ለምንድነው የምትቆጣኝ?አትጩህብኝ!!>>አለችው ፊቷ ላይ ንቀት ይነበባል። ሰፈር ደረስን። ከመኪናው ወርዳ እየተመናቀረች ወደቤት ገባች።
............... ............. .............
ከታክሲ ከወረድን በኋላ ወክ ማድረግ ጀመርን። መልኬ እጁን ኪሱ ውስጥ ከቷቸዉ አይኑ ቡዝዝ ብሎ ተክዟል <<መልኬ መቼ ነው ግን የጀመራችሁት?>> ውስጤ ሲመላለስ የነበረውን ጥያቄ ጠየኩት።<<አስረኛ ክፍል የወደኩ ጊዜ ነው። ያኔ በጣም ነበር ያፅናናችኝ።በጣም ነበር የተሰማኝ ታስታውሳለህ?>>አንገቴን በአዎንታ ነቀነኩ።<<በዛ ላይ መሲ(አብራቸው ትኖር የነበረች የአክስቱ ልጅ) አግብታ ወጣ ነበር። ብቻየን ነበርኩ። ቤት ትመጣ ነበር። >>በረጅሙ ተነፈሰ። አፈጠጥኩበት።<<ከዛስ ምን?ንገረኝv እንጂ? >>የእፍረት ሳቅ ሳቀ።<<በቃ መሳሳም ብቻ ነው >>አይኑን አየሁት። አንገቱን ደፋ።<<አረ አጅሬው አልተቻልክም!!..>>እየተሳሳቅን ወደ መልኬ ቤት ገባን።


ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን

@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

21 Jan, 16:40


🌹 የፍቅር ክሊኒክ 🌹

🔥 እንቅልፍና ሴት 📝

••••••••

በአንድ አልጋ ላይና
በአንዲት ሴት ላይ
ሶስት አይነት አንድነት
ህልም-ፍቅር-ህይወት

ከነዚህ መሀከል-ህልም የምንለው
ፈቺ የሚፈልግ አሳሪ የሌለው
የኔና ያንቺ ፍቅር ያልጋ ላይ ህይወት ነው
ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ፍቅር እንደዚህ ነው።

ከራስ አስበልጦ ሌላ ሰውን መውደድ
ባንድ አለም ተከብሮ ባንዲት ሴት መዋረድ
ክብር ነው ትርጉሙ
በሴት ልጅ ተማርኮ ከዙፋን ላይ መውረድ።

ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ህይወት እንደዚህ ነው

ተኝቶ መነሳት
የታወሰን መርሳት
ያሰሩትን መፍታት
ኖሮ ኖሮ መሞት።

ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ሴትና እንቅልፍ ያው ነው

የትኛውም ፍጥረት ባልጋው ያንቀላፋል
ማንም ወንድ ነኝ ቢል በሴት ይሸነፋል።

┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄

          


🪴🌹አሁኑኑ ሼር አድርጉ 🌹🪴

♥️ @yefikrclinic ♥️
🌹 @yefikrclinic 🌹
...........♥️💍••●🍃🌹🍃●•........

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

20 Jan, 17:49


😘አንቺዬ.... አራዳ😘

🔥ክፍል አራት

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
.

ገና መግቢያው ላይ ስንደርስ ኤደን እየደነሰች መሀል መድረኩን ያዘች።እኔና መልኬም በመገረም ከተያዬን በኋላ መጠጥ አዘን ተቀመጥን። ብዙም ሳትቆይ እየተውረገረገች ወደ እኛ መጣች።የለበሰችው አጭር ቀሚስ ደረቷን አጋልጦታል። ለዳንስ ጋበዘችን። በፈቃደኝነት ስላልተቀበልን በእጇ እየጎተተች ወደ መድረኩ አስገባችን።ክለቡ ውስጥ ከተቀመጡት አብዛኛው ተመልካች አይናቸው እኛ ላይ እንዳረፈ ስላወቅኩ የአዳምን ዘር ላለማሰደብ ያለ የሌለ አቅሜን በመጠቀም ተውረገረግኩ።ለሁለት አልቻልናትም።(በድሮ አራድኛ ቋንቋ ዲስኮ ሆናለች😂)ግቢ ውስጥ ስትማር መቆየቷ አጠራጠረኝ🤔።መልኬ እጇን ይዞ ወደ መቀመጫችን ወሰዳት።
<<ምንድን ነው? >>
<<በቃ ደነስን!አሁን ቁጭ ብለን እናውራ>>በሸቀች።<<ልንዝናና አይደል እንዴ የመጣነው?>>ዝም አላት።እንደተኮፈሰች ቁጭ አለች።ድባቡ ደስ ስላላለኝ ወክ የማድረግ ሀሳብ አቀረብኩ። ብዙም ሳንቆይ ሂሳባችንን ከፍለን ወጣን።

አንቺናሉ ዩኒቨርስቲ በሄደች በወሯ የመልኬ እናት አረፉ። መልኬም በጣም ተጎዳ።የአንቺናሉ ናፍቆትና የእናቱ ሀዘን ተደማምሮ ከሰው ተራ አውጥተው ነበር። (ምስኪን መልኬ!)አባቱ በህይወት ስላልነበሩና ቀዳሚና ተከታይ የሌለው ብቸኛ ልጅ በመሆኑ የሚኖሩበት ቤት ውስጥ ሰራተኛ መቅጠር ነበረበት። አጎቱ (የእናቱ ትንሽ ወንድም) ምንም እንኳ ከአስረኛ ክፍል ያቋረጠ ቢሆንም የእናቱን ሀዘንና ብቸኝነቱን ያስረሳዋል በሚል እሳቤ ከሱቆቹ አንዱን እንዲቆጣጠር ከትልቅ አደራ ጋር ሰጡት።መልኬ የስራ ጫና ስለሚኖርበት ለሀዘኑ ጥሩ ማስታገሻ ሆኖለት ነበር። ለአንቺናሉም በየወሩ ገንዘብ ይልክላት ነበር።

ክለብ በወጣን በሳምንቱ ማታ መልኬ ደወለልኝ።አነሳሁት <<ኤደንን አግኝታሀታል ሰሞኑን? >>
<<ማናት ኤደን?(የኔ ነገር ረስቼው)እ ማለቴ አላገኘኋትም!>><<የት ነህ? >><<ቤቴ ነኝ! ችግር አለ?>>ጠየኩት። <<እሺ መጣሁ >>ስልኩን ዘጋሁት። መጣ።ኤደን ሳምንቱን ሙሉ እንዳላገኛትና ስልኳ እንደማይሰራ ከሱ እየራቀች እንደሆነ ነገረኝ። ትንሽ ስናወራ ከቆየን በኋላ ወደ ኤደን ቤት ሄድን ኤደንን ፍለጋ።አያቷ ሲያዬን ደነገጠ...

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን

@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

18 Jan, 23:35


😘አንቺዬ... አራዳ😘

🔥ክፍል 3

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
.
.... አንዲት ሴት ወደኔ አቅጣጫ ስትመጣ አየሁ። (አውቃታለሁ ልበል? 🤔)ትኩር ብየ ተመለከትኳት።ከኋላዋ ትልቅ ቦርሳ እየጎተተች መጣች።ፀጉሯ ቡናማ ቀለም ተቀብቷል።አጪርና እምብርቷን የሚያሳይ ሚጢጥየ ሹራብ ለብሳለች።ከስር ከጭኗቿ ከፍ የሚል ጂንስ ቁምጣ አድርጋለች። ፊቷ በሜካፕ ተዥጎርጉሯል።የቀባችው የከንፈር ቀለም ሳንባ የበላች ድመት አስመስሏታል።ጥፍሯ ተሰርቷል።የተቀባችው ሽቶ ገና ከሩቁ ሰው ይጠራል(በሽቶ ነው እንዴ ሻወር የወሰደችው ያስብላል)የእጅ ጣቶቿ ላይ ቀለበቶች ተደርድረዋል (መቼም ይሄን ሁሉ አንድ ሰው አያደርግላትም ፣የወርቅ ቤት ዘራፊ መሆን አለባት ብየ አሰብኩ 😂)ደረሰች!!አጠገቤ ደረሰች።<<ሀይ ሳም!እንዴት ነህ? ቦርሳው እንዴት እንደከበደኝ!!>>መልስ አላገኘችም <<አንተ ብቻህን ነው እንዴ የመጣሀው?>>አላወኳትም።ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ ተመለከትኳት። <<አይሆንም!! አንቺናሉ ነሽ?>>አልኳት በግርምት። ፊቷን ለጥጣ<<አህ..ከዚህ በኋላ ኤደን በለኝ እሺ! ኤዲ...>>መልኬ እየሮጠ መጥቶ አጠገቧ ቆሞ<<ሳሚ የለችም!ፈልጌያታለሁ ሳሚ አልመጣችም!!>> አለኝ እያለከለከለ ፊቱ በድንጋጤ ገርጥቷል።<<ኦ ማይ ጋድ መልኬ.... >>አንገቱ ላይ ተጠመጠመች።ግራ ገባው ከእቅፉ መንጭቆ አወጣት << ማነሽ? ምን ዘለ....ሽ.. አንቺዬ??>><<አሀ ረስተኸኝ ነበር አይደል?>>
<<አረ አይደለም!! ስለተቀየርሽብኝ ነዉ.. እንዴት ነሽ?>>
<<አለሁ>>
<<እንሂድ? በጣም ደከመሽ? ጉዞው እንዴት ነበር? >>ደስታ አሰከረው።የጥያቄ መአት ያዘንብላታል...

ከመልኬ ድግስ ያልተጠሩ የሰፈሩ ሰዎች ጥቂት ነበሩ። የአንቺናሉ(የኤደን) አያት ድግሱ ላይ ተገኝተው ስለ እማማ ብርጣሉ ደግነት ፣ስለ መልኬ ብሩክነት እንዲሁም መልኬና ኤደን ከልጅነት ጀምሮ ስላላቸው ወዳጅነት ረዘም ያለ መግለጫ ሰጡ።ኤደን ከድግሱ በኋላ አረፍ ልበል በሚል ሰበብ ወደ ቤቷ ሄደች። እኔና መልኬ ብቻ ቀረን። እንደ ህፃን ልጅ ይፈነድቃል። <<አይተሀተል ሳሚ?አለባበሷ እንዴት እንደተቀየረ አነጋገሯስ ብትል?ሙድ እንደያዛችሁባትም አትቀሯትም ብቻ...>>ብዙ ነገር ነገረኝ። እሷ ላይ ስላየው ለውጥ፣ ምን እንደቀየራት የመታውን መላምት ፣ዩኒቨርስቲ እንዴት የተማሪዎቹን አለባበስና አኗኗር ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያሳድር፣ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ለአዲስ ነገሮች ፈጣን ምላሽ እንደሚያሳዩ... በሰፊው አስረዳኝ።
የዚያን ሰሞን አንድ ቀን ማታ እኔ ፣ኤደንና መልኬ ለመዝናናት ወጣን።(ያው አሁን አሁን መዝናናት የሚለው ቃል የምሽት ክለቦችን እየተካ ያለበት ሁኔታ ነው ያለዉ 😂)ገና መግቢያው ላይ ስንደርስ...

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@yefikrclinic

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

15 Jan, 19:29


😘አንቺዬ አራዳ😘

ክፍል 2

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.

ከሶስት አመት በፊት አንቺናሉ ዩኒቨርሲቲ መሄዷ ግድ ሆነ።ለመሄጃዋ ሳምንት ሲቀራት የሰፈሩን ሰዎች መሰናበት ጀመረች። በየተራ መደዳውን ቤቶች እየገባች በመሰናበት ስም እንባዋን ትረጭ ጀመር። (ምን አለፋችሁ መንደሩን መለስተኛ ለቅሶ ቤት አስመሰለችው😂)በሳምንቷ ሄደች።ይሄኔ የመልኬ ፀባይ መቀያየር ጀመረ።መነጫነጭንና ማላዘንን የዘወትር ተግባሩ አደረገው።ታዲያ በዚያ ሰሞን የመልኬ እናት እትዬ ብርጤ ክፉኛ አሞቸው ስለነበር በእሳቸው ህመም ስለሚመስለኝ አዝንለት ነበር። ግን አልነበረም። እንድንጠጣ ጥያቄ አቀረበልኝ። እምቢ የምልበት ወኔ ስላልነበረኝ በሀሳቡ ተስማማሁ።ለመጀመሪያ ጊዜ እየጠጣ መሆኑን ልብ አላልኩም።ወዲያው ሰክሮ ማላዘን ጀመረ።<<እ..እኔ እኮ አትሂጂ ብያት ነበር!እንደማልችል እያወቀች... እሞታለሁ እያልኳት..>>ስካር ባሳስረው አፉ ተለፋደደ።እኔም እማማ ብርጤን መስሎኝ ቆጣ ብዬ <<የምን ማሟረት ነው! ስለምን መሄድ ነው የምታወራው? የታመመው ሁሉ አይሞትም እሺ!!>>ብየ አምባረኩበት።ሳቀ።ከት ብሎ ሲስቅ ቆየና ለሳቅ በከፈተው አፉ ባልገባኝ ምክንያት ወደ ለቅሶ ቀየረው።ፈራሁት። ምንም አላልኩትም። ድንገት ለቅሶው አቁሞ <<አንቺዬን እወዳታለሁ ሳሚ!ማለቴ አብረንነን.. ነበርን>>አለኝ።ክው ብዬ ደነገጥኩ። (የት ሄጄ ነበር? 🤔እንዴት አልነገረኝም?) በጣም አናዶኛል።<<ምን ማለት ነው አብረን ነን? ነበርን?ከመቼ ጀምሮ? እንዴት አትነግረኝም?ትገርማለህ!ጎደኛህ አይደለሁም?እኔኮ በእማማ ምክንያት መስሎኝ...>>የጥያቄና የወቀሳ እሩምታ አወረድኩበት።
* * * * * * *
አንቺናሉ ከዩኒቨርስቲ ቆይታዋ በኋሏ ለመጀመሪያ ጊዜ መጣች።ከአስር ወረ በኋላ።ለእረፍት አልመጣችም ነበር። እኔና መልኬ እሷን መናሃሪያ ሄደን እንድንቀበል ተወሰነ።9 ሰአት ለሚመጣ ባስ 7 ሰአት ሲል በመልኬ መሪነት ወደ መናሃሪያ።(እውነት ለመናገር መልኬ ዛሬ ተኝቶ ማደሩንም እጠራጠራለሁ😂)አንቺናሉን ለመቀበል መልኬ ቤቱ ድግስ ቢጤ (ለኛ ሰፈር ሰርግ ሊባል የሚችል) አዘጋጅቷል።የለበሰውን ተመለከትኩ ሁሉም አዲስ ነው። መናሃሪያ ደረስን።የሚገቡት መኪኖች ተሳፋሪዎችን ማራገፍ ጀመሩ። መልኬ ተቁነጠነጠ።<<እ ሳሚ! እንዴት ነኝ? አምሮብኛል?ይደብራል እንዴ አለባበሴ? >>ሲል ለሰባተኛ ጊዜ ጠየቀኝ።መመለስ ታከተኝ።አፌን እንደገጠምኩ ፈገግ አልኩለት።በላይ በላይ ይተነፍሳል። በጣም ከመጨነቁ የተነሳ በጠራራ ፀሀይ ጣቶቹ ቀዝቅዘዋል።ጥፍሮቹን በጥርሱ ይበላቸዋል። ይቀመጣል። ወዲያው ይነሳል። ፀጉሩን ያካል።መኪና ባየ ቁጥር አንገቱን አስግጎ ሰዎቹን ይመለከታል። ልብሱን ፣ጫማውን ያስተካክላል። ፊቱን ወደኔ ሲያዞር ለስምንተኛ ጊዜ ሊጠይቀኝ መሆኑን በመገመት ፊቴን አጨግጌ ወደ ጎን አዞርኩ።ባሱ ሲመጣ አየሁት። (ተመስገን.. እፎይ መጣች!ልትገላግለኝ ነው።) ከባሱ የነበሩት ተማሪዎች አንድ ባንድ መውጣት ጀመሩ። አንቺናሉ የለችም!! ከወረዱት ተማሪዎች መሀል ጉርድ(ቀሚስ) ያደረገች ልጅ ፍለጋ በአይኔ አማተርኩ።የለችም። መልኬ ባስ ውስጥ ሊፈልጋት እየሮጠ ሄደ።ግራ ገባኝ🤔።ፊት ለፊቴ አንዲት ሴት ወደ እኔ አቅጣጫ መጣች።
.

.
. ይቀጥላል....

@yefikrclinic

@yefikrclinic

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

14 Jan, 18:04


😘አንቺዬ አራዳ😘

🔥ክፍል 1

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
የስልኬ ጥሪ ከተኛሁበት ቀሰቀሰኝ።
የደወልኝን አውቀዋለሁ። መልካሙ ነው። መልኬ!አብሮ አደጌ! የሰፈሬ ልጅ.. ወንድሜ!!ከትራሴ ስር በእጄ ዳስሼ አይኔን እያሸሁ አነሳሁት። <<ሄሎ>>አልኩት እንቅልፍ በተጫጫነው ድምፅ.. <<አንተ አትመጣም እንዴ?አንተን እኮ ቁጭ ብየ ምጠብቀው?!>>የሙዚቃ ድምፅ ይሰማል።ቀጠሮ ነበረን።
<<ኦ ይቅርታ! በናትህ በቃ አሁን እመጣለሁ። 10 ደቂቃ ብቻ!!>> ስልኩን ዘግቼ እየተጣደፍኩ ሄድኩ።
<<ምን ሆነህ ነው እስካሁን የቆየኸው?>>ጠየቀኝ። ብዙ እንደጠጣ ያስታውቃል። ፊቱ ልክ አይደለም። ከፍቶታል።
<<ባክህ ትንሽ ደክሞኝ እኮ እንቅልፍ ጣለኝ>>አልኩት የፀፀት ስሜት ስለተሰማኝ ለማሳሳቅ እየሞከርኩ. <<አንተ ተኛ ምን አለብህ >>አለኝ ፈገግ እያለ። ይሄን ፈገግታ አውቀዋለሁ። የእውነት አይደለም። ጥርሱ ብቻ ነው ሚስቀው።ፊቱ አይስቅም። አይኑም አይስቅም። (ፊት እና አይን ከመቼ ወዲህ ነው ሚስቁት እንዳትሉኝ🙄)የመልኬ አይን ጠባብ ነች።ሲስቅ የበለጠ ትጠባለች።ጥፍት ትላለች። ፊቱ ከወትሮው ያጥራል። ባጠቃላይ ህፃን ያስመስለዋል። ነብሳቸውን ይማረውና እማማ ብርጣሉ(ብርጤ ነው😂 የምንላቸው፣የመልኬ እናት ናቸው)<<መርፌ አይን፣በኛ ቤት እንደዚህ ያለ አይን ያለውም የለ ከየት እንዳመጣው >>ይሉት ነበር። በኃላ እሳቸውን በአልባሌ ሊያስጠረጥራቸው እንደሚችል ሲታሰባቸው እርግፍ አርገው ተውት። ስለ መልኬ አይን ይሄን ያህል ካልኩ ወደ ታሪኬ ልመለስ.. መልኬ ሆድ የባሰው መሰለኝ። ቀጥታ ምክንያቱን መጠየቅ አልደፈርኩም። ወሬውን ለመቀየር አሰብኩና ያለ ምክንያት ወቀሳ አዘል ቀልድ አልሰነዘረም ብዬ ለመጠየቅ ወሰንኩ።
<<ዛሬ ደግሞ እኛ ብቻ ነን እንዴ?ኤደንስ?>>የለበጣ ሳቅ ሳቀ።(አለ አይደል አፉን ወደ ጎን አጣሞ የፌዝ ሳቅ (የለበጣ ሳቅ ለማታውቁ)) <<ተጣላን! ተጣላኋት!!አስጠላችኝ>>አለ። <<ተጣላሀት? >>ባለማመን ጠየኩት <<አዎ!!>>እየቀለደ አልነበረም። <<እንድናከብር ነው የጠራውህ>>አለኝ። አዎ!ከኤደን መጣላት ለመልኬ ጥል አይደለም። ዳግም መወለድ ነው። አዎ!የመልኬን ልደት ነው የምናከብረው.. ሙሉ ጠርሙስ አሰወረድን።
* * * * * *
ኤደን የሰፈራችን ልጅ ናት። ሶስታችንም አንድ ሰፈር ተጫውተን አንድ ትምህርት ቤት ተምረን ነው ያደግነው።
ኤደን ኤደን ከመሆኗ በፊት አንቺናሉ ነበረች። እናቷ ገጠር ሁለተኛ ባል ከማግባታቸው በፊት ለአያቷ(እኛ ሰፈር) ሰጥተዋት ሄዱ።ያኔ የ8 አመት ልጅ ነበረች።ሹሩባዋን ተሰርታ ሽንሽን ቀሚስ ለብሳ ነበር የመጣችው። በመጣች በአመቷ ት/ቤት ተመዘገበች።አገሩ አዲስ ስለሆነባትና ከሰፈር ልጆች እንዳትለይ በማሰብ አያቷ ከኛ ት/ቤት አስገቧት።ለኔ ና ለመልኬ አደራ የሰጠች። እስክትለምድ ድረስ እሷን ት/ቤት ማመላለስ የዘወትር ተግባራችን ሆነ።አንቺናሉ ምንም የማትናገር፣የዋህ ና ምስኪን ልጅ ነበረች። አስፓልት መንገድ ለማቋረጥ የምትፈራ፣እጇን ለቀን መንገድ ስንሄድ የምታለቅስ፣አስተማሪዋ ክፍል ውስጥ ስሟን ስትጠራት እሷን በማክበር <<እመት >>ትል ነበረ።አንቺናሉ ሹርባ ናሽንሽን ቀሚስ ነበር የምታደርገው። ከውጭ የመጣላትን ሱሪ <<አለብስም፣ካራ ባንገቴ>>(እንደሷ አገላለፅ 😂)ብላ አምባጓሮ ትፈጥር ነበር። አንቺናሉ.....
ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

13 Jan, 15:44


🔥 እንቅልፍና ሴት 📝

••••••••

በአንድ አልጋ ላይና
በአንዲት ሴት ላይ
ሶስት አይነት አንድነት
ህልም-ፍቅር-ህይወት

ከነዚህ መሀከል-ህልም የምንለው
ፈቺ የሚፈልግ አሳሪ የሌለው
የኔና ያንቺ ፍቅር ያልጋ ላይ ህይወት ነው
ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ፍቅር እንደዚህ ነው።

ከራስ አስበልጦ ሌላ ሰውን መውደድ
ባንድ አለም ተከብሮ ባንዲት ሴት መዋረድ
ክብር ነው ትርጉሙ
በሴት ልጅ ተማርኮ ከዙፋን ላይ መውረድ።

ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ህይወት እንደዚህ ነው

ተኝቶ መነሳት
የታወሰን መርሳት
ያሰሩትን መፍታት
ኖሮ ኖሮ መሞት።

ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ሴትና እንቅልፍ ያው ነው

የትኛውም ፍጥረት ባልጋው ያንቀላፋል
ማንም ወንድ ነኝ ቢል በሴት ይሸነፋል።

┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄

          

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

13 Jan, 15:42


አዳሜን ሸኝቼ አንቺን ባስቀርለት
ልቤ ቀን ወጣለት

እፎይ
ተቃረብኩ ለሰማይ
ተቃረብኩ ለፀሀይ
በስምሽ ተነቀስኩ በሁለቱም ክንፌ ላይ።

በሁለቱም ክንፌ ላይ ስምሽን ብነቀስ
ገነት ደጃፍ መድረስ
(ገባሁ)
ተጫወትኩ
ተፏገርኩ
ከመላክ ከፃድቃን
በቀልዳችን አዳም በሳቅ እስከሚያለቅስ።

የሰው ልጅ ሲደላው ሲደሰት በነብሱ
አርያም መቅደሱ።

ገባኝ
ደላኝ
ሰፋኝ
ተወለድኩ እንዳዲስ
ከእቅፍሽ ስትከቺኝ።

(ተመስገን)
አዳሜን ሸኝቼ አንቺን ባስቀርለት
ልቤ ቀን ወጣለት።

━━━━━━━━✦🔵✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

20 Dec, 19:54


ልበ_ዱሪቆን


አለሜ......
በአፍላነት እድሜ ገና በልጅነት
የደወርነው ፍቅር ደርሰው ያልፈተሉት
የትዝታ መንጋ ልባችን ያዘለው
ማደግ ያልዘነጋው
አርያም ባይሰማው ይህን አይነት ፍቅር
ህቡዕ ነው ልንገርሽ የኔና አንቺስ ነገር
እዚህ ከኛ ልብ ውስጥ ንዴት አሸልቧል
ያልወለድነው ፍቅር ልባችን አርግዟል
የኔም የአንቺ አንደበት ዝምታውን መርጧል
ይሁን ይሁን ልቀበለው
ያ ልባችን አማን አለው
.
ትዝ ይልሻል
በማሪያም ዕለት ከንግስ መልስ
ከሜዳው ላይ ከአፀዱ ስር ምሽት ሳይደርስ
ተቀምጠን ተጠጋግተን በፍንደቃ ስናወጋ
ተሰምቶኛል አንዳች እውነት ከሙቀትሽ የላብ ቀጋ
.
ያ ልብሽ ደጋ ነው በማፍቀር የናኘ
የኔ ልብ ቆላ ነው አንቺን የተመኘ
ምክኒያቱ ይህ ነው የልበ ዱሪቆን
ልባችን ተማምኖ አንደበት ቢከዳን
በቃ ተፈጥረን ነው እሳት ውሃ ሆነን
.
ደግሞ ጊዜው ቢተም
ምሽት ደርሶ ቢጨላልም
ከውብ አይንሽ ቅሬታሽን አነባለው
ክንድሽ ሲያቅፈኝ ጭንቀትሽን እረዳለው
.
በሌላ ቀን ተነፋፍቀን ስንገናኝ
ትንፋሽሽ ነው ማፍቀርሽን የሚያወጋኝ
እርግብ ሆነሽ እኔ ቁራ
ተራርቀን ባንድ ጣራ
እሳት ስሆን አንቺ ውሃ
ያልታደልኩሽ የኔ አምሃ
.
ዱሪቆን ነው በቃ እንቅር
እኔና አንቺ አንናገር
በሀሳብ መንገድ እንሳፈር
በልባችን እንፋቀር
አርግዚኝ በተስፋ ልብሽ ከኔ አይሽሽ
ልታገስሽ እኔም በተስፋ ላርግዝሽ
.
በማሪያም ዕለት ከንግስ መልስ
ከሜዳው ላይ ከአፀዱ ስር ምሽት ሳይደርስ
ተቀምጠን ተጠጋግተን በፍንደቃ ስናወጋ
ተሰምቶኛል አንዳች እውነት ከሙቀትሽ የላብ ቀጋ

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

14 Dec, 16:09


How woman cheat

1,Accepting money and gifts without your partner knowing about them is cheating.

2 .Giving attention to another man means cheating.
3,Make another man feel like he has a chance is called cheating.

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

12 Dec, 15:49


ተጣልተናል_እኮ
.
እንደማንመለስ ምለን በታቦቱ፣
ንግግር ካቆምን አልፈዋል ወራቱ፣
ኧረምን ወራቱ አመታቱም ነጉዷል፣
ሌላ ወድጃለው እሱም ሌላ ወዷል፣

ግና....
ቁልምጫ በሚሉት እዳ ተለክፌ፣
ሙሉ ስሙን መጥራት አለመደም ኣፌ፣
ተጣብቆብኝ አንዴ የቁልምጫው ነገር፣
ስለሱ ስጠየቅ ለሰዎች ስናገር፣
ውዴ፡ ማሬ፡ ፍቅር፡ ላለማለት ስጥር፣
ይቀድመኛል ኣፌ ባስታዎስኩት ቁጥር።

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

11 Dec, 17:54


When she looks into your eyes, don't look away until she does.

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

10 Dec, 15:34


When you see her crying, hug her and don't say anything.

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

09 Dec, 10:55


When she's cold give her your hoodie

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

08 Dec, 10:46


When you see her crying, hug her and don't say anything.

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

05 Nov, 07:48


😔😔 #መልስህን ንገረኝ 😔😔

ድሮስ የወደደውን መች ሰው ይፈልጋል
የማይፈልገውን ሄዶ ይለምናል።

እኔም ከነዛ ውስጥ አንዷ ነሽ ብለዋል
አንተ የኔ እንደሆንክ ማን በቅጡ ያቃል።

እኔ ስፈልግህ አንተስ እርቀሀል
እንዴት የኔ ላርግህ ሌላ ሰው ይዘሀል።

የኔን ልብ ስሰጥህ መች አንተ ይገባሀል
ለኔ ያለህን ስሜት ማወቅ ተስኖኛል።

እኔ አንተን ስፈልግ አንተ ስትል ሌላ
የኔ ልብ በስቃይ በሀዘን ተሞላ።

አሁን የማሳይህ ላይገባህ ይችላል
ስታቀው ሲገባህ እግርህ ይመልስሀል።

ተስፋ እንዳትቆርጥ ልቤ ይቀበልሀል
ጥላቻንም ገፍቶ ፍቅርን ያለብስሀል።

በርግጥ አልዋሽህም ልቤ ይፈልግሀል
በአፍ ባልነግርህም አይኔ አሳይቶሀል።

አልገባኝም ማለት አውቃለው እንደምችል
ግን ጥቅም የለውም አይገባኝም ብትል።

አውቃለው እንደሌለህ የኔ እምትላት
እኔ እኮ የለኝም የቅናት ስሜት።

ለኔ ያለህን ስሜት ንገረኝ እባክህ
ልሂድልህ በቃ ሙሉ ከሆነ ልብህ።

ልቤ መውደድ ይበቃሀል
ለእሱ እኔ አለሁ ለኔ ማን ያስብልብኛል።

የሰማዩ ጌታ የኔ ሁን ካላለው
ለኔ የፃፈውን እስኪ ልፈልገው።

ካንተ ጋር መሆኑን ልቤ ይመኘዋል
ያላንተ መኖሩን እንዴት ይችለዋል።

አንድ ቀን አስበህው ይገባህ ይሆናል
የሰው ልብ እንዲ ነው በተራው ይመጣል።

ፈላጊ ነኝ እንጂ ማን ይፈልገኛል
የሚፈልገኝስ መቼ ፍቅር ያውቃል
እስኪጠግበኝ ብቻ ከጎኔ ይቆያል።


@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

26 Oct, 04:29


🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌹 ክፍል 1⃣2⃣

👉 የመጨረሻ ክፍል
.
.
.
.
...ይሄው ጅማ ከገባሁ 4 ወራትን አሥቆጠርኩ...ከዚያ ከብቸኝነትና ከሥቃይ ኑሮ ተገላግዬ እናቴ ጉያ ተወሽቄ የማያልቅ የእናትነት ፍቅሯን እያገኘሁ..ጠረኗን እየማግሁ እገኛለሁ.....እናቴy ከምንም በላይ ኮርታብኛለች.. በቆራጥነቴና ለዚህ በመብቃቴ "አጃኢብ ነው..ከወለዱሥ እንደ ሠሚራ አይነት"የማይል የለም.....አከራዬ እንኳን ባጠገቤ ሲያልፍ በሀፍረት አንገቱን ደፍቶና ተሸማቆ ነው የሚሄደው..እኔ ግን ይቅር ብዬዋለሁ..በሱ ምክንያት አይደል ዛሬ ሙሉ ሰው ለመሆን የበቃሁት...

ደሥታ እኛ ቤት እንደጎርፍ አጥለቅልቆናል...
ዛሬ ቤታችን ከወትሮው በተለየ ድምቅምቅ ብሏል..ግቢያችን በሠፈር ሠው ተሞልቷል...አከባቢው ምግብ ምግብ ይሸታል.....ድንኳን ሁለት ቦታ ተጥሏል.......ጓደኞቼ እኔን ውብ ለማድረግ ሽር ጉድ እያሉ ነው...... ይሄ ሁሉ ለምን እንደሆነ መቼም ገብቷችሁዋል..የልጅነት ህልሜን ሁሲን የማገባበት ቀን ነው ......በሚያፈቅሩት ሠው መፈቀር፤ልብ ለልብ መገናኘት...የሚያፈቅሩትን ሠው የግል ማድረግ ከዚህ በላይ ምን አለም አለ እናንተዬ......ፌቪ አንደኛ ሚዜዬ ናት....ጉድ ጉድ ማለቱን ተያይዛዋለች...

ዲጄው ቤቱን በሰርግ ነሽዳ አድምቆታል..

ባረከላሁ ለኩማ ወባረከ አለይኩማ ወጀመአ በይነኩማ ፊል ከይር.......

ማሻአላህ ማሻአላህ ማሻአላህ ማሻአላህ......(3*)

ብቸኛ መሆንን በትግእሥት አልፋችሁ
አላህ አድሏችሁ ጥንድ አደረጋችሁ
ማሻአላህ ብለናል እንኳን ደሥ ያላችሁ
ኢላ የውሚል ቂያም ፍቅር አይለያችሁ
ሪዝቃችሁ ከሡ ነው ከጀሊል ከአላህ
እኛም ደሥ ብሎናል ብለናል ማሻአላህ.................

ሁሲ በአንደኛ ሚዜው ማሜ በቢና በሌሎች ሚዜዎቹም ታጅቦ እየገባ ነው....እልልታው ደመቀ ሴቶች በተፈቀደላቸው ቦታ ላይ ሆነው ሙሾ ያወርዳሉ...ዜማ እንደጉድ ያዘንባሉ...............
በድንገት ግን ካሊዶ ከመጠን በላይ ጠጥቶ ሲለፈልፍና እየጮኸ ሲሳደብ ሰማሁ...."ሰሙ የኔ ናት.....ማንም ሊወስድብኝ አይችልም....ህልሜንና ህይወቴን ሊነጥቀኝ የተዘጋጀውን እንዲኖር አልፈቅድለትም" አለ
ወዲያው የጥይት ድምጽ ቤቱን አደበላለቀው...በደመ ነፍሥ ካለሁበት ቦታ እየሮጥኩ ሥመጣ የሆነ ሠው ዝንፍል ብሎ ተኝቷል..አይኔን እየፈራሁት ወደ ከበቡት ሠዎች ሳመራ ሁሲ "ወይኔ ማሜ ወይኔ ወንድሜ እኔ ልጋደምልህ" እያለ...ይጮሃል ይንፈራፈራል.....ለሁሲ የተተኮሰችው ጥይት የጓደኛችንን የማሜን ህይወት ቀጠፈችው...በጓደኛው አለም ሊደሠት የመጣው ማሜh ባላሠበውና ባልጠበቀው መንገድ ህይወቱን አጣ።እዚህች ምድር ላይ ስንኖር የሠከንዶች ያህል የመኖሪያ ፍቃድ እንዳለን እንኳን እርግጠኛ መሆን አንችልም...ሞት ሣያማክረንና ሳያሥጠነቅቀን ድንገት ብቅ ይላልና.....አያችሁ ህይወት እንደዚህ ናት በቅጽበት ደሥታ በቅጽበት ሀዘን....እንደዚያ በደሥታና በፍንደቃ ጣሪያ ነክቶ የነበረው ቤት በሠከንዶች ልዩነት በዋይታና በሀዘን ድባብ ተውጧል። ጽልመት ነግሶበታል.................

/////////////********//////////

ህይወት ትቀጥላለች...የማሜ ሀዘን ክፉኛ ቢጎዳንም የወደፊት ኑሯችንን የተቃና ለማድረግና ደሥተኛ ጥንዶች ለመሆን እየሞከርን ነው.....አሁንም ማሜ ከሞተ ከ40 ቀን በሁላ የብቻችን የፍቅር ጊዜ እንዲኖረን በማሰብ ሀዋሳ ከትመናል....ሀዋሳ እጅግ ውብ ናት...አየሯ መንፈሥን ያድሳል...የሁሲ እቅፍ ውሥጥ ገብቼ ከሀይቁ ማዶ በቃኝ ብላ ልትጠልቅ የተቃረበችውን ጸሀይ እየተመለከትኩ ነው...እየመሸ ሥለሆነ አየሩ ማጉኝ ማጉኝ ይላል...በድንገት ሁሲ"የኔ ፍቅር ብንገባ አይሻልም" አለኝ ከምሽቱ 1 ሰአት አከባቢ....
እሺ ብዬው ከእቅፉ ወጣሁና እጅ ለእጅ ተያይዘን መንገድ ጀመርን..
እራት እየተጎራረሥን በላንና ወደ ክፍላችን አመራን...በጣም ደሥተኛ ነኝ በህይወቴ የመጀመሪያውን ጣፋጭ የፍቅር ምሽት በውቢቷ ሀዋሳ ላይ አሣለፍኩ ..መቼም የማይረሣ ትዝታ.....


////////////*******//////////////

ከ 9 ወር በሁዋላ.........

ፌቪ ዘንድሮ ጅማ ካሥመረቃቸው ተማሪዎች መካከል አንዷ ሆናለች..
ሚኪ ትዳር ይዞ የልጅ አባት ሆኗል...
ካሊዶ 18 አመት ተፈርዶበት ከርቸሌ ወርዷል...
እኔም የመጀመሪያ ወንድ ልጄን ለመገላገል ቀናቶችን እየቆጠርኩ ነው........ዶክተሬ በሆዴ የተሸከምኩት ወንድ ልጅ እንደሆነ አብስሮኛል...ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ እየጮኸ ሊቀላቀለን በመሆኑ ሁሲ ከመጠን በላይ ተደስቷል።.... ልጃችንንም በኛ ደሥታ ላይ በተሠዋው ማሜ ሥም ልንሠይመው በጉጉት እየጠበቅነው ነው....


ከችግር በሁዋላ በእርግጥም ምቾት አለ።.....ሰደቀላሁል አዚም(አላህ እውነት ተናገረ)...
.

.

.
​​•════•••ተፈፀመ•••════•
    


ወዳጆቼ ሳገባህ ላፍቅርህ እንዴት ነበር...?

📨📨ያላችሁን ማንኛውንም አስተያየት comment @Yaddiii አድርሱኝ....ያበረታኛልና‼️

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

25 Oct, 07:16


🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌹 ክፍል 11


.
.
👉 ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀረው‼️


ስነቃ ግሉኮሥ ተተክሎብኝ እራሴን ሆሥፒታል አገኘሁት።ነገሩ እንዲህ ነው የአሰሪዬ ልጅ በአጋጣሚ ሲያልፍ ሁኔታዬ አላምር ብሎት በርቀትም ቢሆን እየተከታተለኝ ነበር....ግንድሥ ብዬ ስወድቅ እየሮጠ ሄዶ ሚስቱን ጠራት...ገና ሲያዩኝ ያሳዘንኳቸው ጥንዶቹ የማንንም እርዳታ ሳይጠብቁ አፋፍሠው ወደ ሆሥፒታል ወሥደውኝ ህይወቴን አተረፏት።..

እንደነቃሁ ልጅ ነሽ በጣም ወደ ሀገርሽ እንላክሽ አሉኝ። በጣም አዘንኩ...የአከራያችን ስድብ ትዝ አለኝ... ማሚ ያላት ገንዘብ በሙሉ ለኔ መምጣት ወጪ ሆኗል..በዛ ላይ ብድር ሁሉ አለብን።
"እእእእእእእ ኧረ እሰራለሁ አላመመኝምኮ" በእንግሊዘኛ እየተንተባተብኩም ቢሆን እንዳይመልሱኝ ተማጸንኳቸው።

////////***///////////

በእንደዚህ አይነት ህይወት 2 አመት ቆየሁ ሳር እያጨድኩ፤ግቢውና ቤቶቹን በሙሉ እያጸዳሁ..

ዛሬ ደግሞ አሰሪዬ 600 ሪያልና ወርቅ ጠፍቶብኛል ብላ እያበደች ነው።.. ወሰደሻል ባትለኝም ንግግሯ እንደዛ ነው..ውይ ሥቃይ ካገሩ የወጣ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረሥ አይደል የሚባለው..ባትናገርም ተናጋሪ ነህ፤ብትሰራም ልግመኛ ነህ፤ባትሠርቅም ሌባ ነህ።...
በጣም መረረኝ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። የአሱር ሰላቴን ሰግጄ አላህን ከዚህ የተሻለ ስራ እዲገጥመኝ እያነባሁ ለመንኩት።...
እንባዬ ይፈሳል የአሰሪዬ ልጅ "ብርና ወርቁን እኔ እከፍላታለሁ አታልቅሽ በያት ብሎ ለሚስቱ ነገራት"..አያችሁ ክፉ ሰዎች በመርዛቸው ጥላቻንና በቀልን ቢዘሩብህም ጥሩ ሠዎች ደግሞ ብልጭ ብለው ፍቅርን ያሥተምሩሃል..በውሥጥህ የተከማቸውን ጥላቻ ያፈራርሡታል..ምክንያቱም ፍቅርና ይቅር ባይነት ከአላህ ሲሆን..ጥላቻና በቀል ደግሞ ከሸይጧን ነው....አላህ የባረከውን ይሄን የአሰሪዬን ልጅ እዩት ከእሷ ማህጸን ወጥቶ..በእሷ እጆች አድጎ እሷ ጨካኝ ብትሆንም እሱ ግን አዛኝና አሥተዋይ ነው...

የልጁ ሚሥት ከጎኔ ቁጭ ብላ ብታባብለኝም እኔ ሆድ ብሶኛል.. እንባዬ አሁንም አላባራም መግሪብ ከሰገድኩ በሁዋላ "ኧረ የአላህ እቃዋን አስገኝተህ አሳርፈኝ..እናታችን አኢሻን(ረ.ዐ) ህዝቡ ዘሙታለች ብሎ ሲጠቋቆባት ቁርአን አውርደህ ንጹህ መሆኗን ያወጅክላት ፈጣሪዬ ሆይ እኔንም እርዳኝ አንተ ውሥጥ አዋቂ ነህና"ብዬ እየተንሰቀሰቅኩ ከመስገጀዬ ስነሳ እቃዋን እንዳገኘችው ነገረችኝ።..
"አልሀምዱሊላህ አላህ አሳፍሮኝ አያውቅም.. በሳምንቱ ከዚያ ለቅቄ አሪፍ ስራ ቀየርኩ።አልሀምዱሊላህ...

"አላህ ታጋሾችን በመልካም ነገር ያበሥራል"...

አሁን ላይ ሁሉም ነገር ቀላል ሁኖልኛል...አረብ አገር ከመጣሁም ድፍን ሶስት አመታትን አሥቆጠርኩ።...
2007 ዓ.ም መስከረም 1 በጣም ደስ ብሎኛል...ነፍሴ በእርካታ ጠፍታለች..ለምን አትሉኝም..
ስመኘው የነበረውን ቤት የምንሰራበትን ቦታ ገዝቻለሁ።በቅርቡ ግንባታው ይጀምራል.. በዛ ላይ ስልክ ገዝቼ ፌስቡክ ከፍቺያለሁ።..
የሁልግዜ ህልሜን ሁሲን ላገኘው እችላለሁ በሚል ተሥፋ ሙሉ ስሙን ሰርች አረኩት..ብዙ ተመሳሳይ ስም ቢመጣም እንደምንም አገኘሁት።...ሰሙ እንደሆንኩ ነገርኩት...
ደነገጠ "ዳግም የተወለድኩ ያህል ነው የተሠማኝ።"አለኝ
የኔንማ ተውት እያበድኩ ነው...ብጮህና አለምን ባደበላልቃት ብዬ ተመኘሁ..

ምንም ጊዜ ሳናጠፋ ሥልክ ቁጥር ተለዋወጥን..
2 አመት ሙሉ በፍቅር አወራን በኢሞ፣በላይን፣በቫይበር ....ወዘተ..ሚዲያ በተባለ ሁሉ እንደዋወላለን.. እናወራለን።.. በቻልኩት ፍጥነት እንደምመጣና እንደምንጋባ ተነጋገርን ጨረስን።...

//////////*****///////////

ሁሲ ከአዲሥ አበባ ወደ ጅማ ተጠቃሎ ገብቶ ንግድ ጀምሮ እያጧጧፈው ነው።.....
እናቴ አዲሥ የተሠራውና የተንጣለለው ግቢያችን ውሥጥ ፈታ ብላ መኖር ከጀመረች አምሥት ወር ሆኗታል...ይሄን የምነግራችሁ ከሳውዲ ወደ ኢትዮጵያ በሚበረው አይሮፕላን ውሥጥ ተደላድዬ ተቀምጬ ነው።...ከአምሥት አመት ከመንፈቅ የስደት ኑሮ በሁዋላ ወደ እናት ሀገሬ እምዬ ኢትዩጽያ ለመግባት ከአይሮፕላኑ ጋር እኩል እያኮበኮብኩ...የእናቴ እቅፍ ውሥጥ ለመሸጎጥ እየቸኮልኩ..የሁሲን ፊት በእጆቼ ለመንካት እየቋመጥቅኩ.........

መጣሁልሽ እናቴ....መጣሁልህ ፍቅሬ......

ይቀጥላል...
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

25 Oct, 07:14


ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

♥️ ክፍል 1⃣0⃣
.
.
.
.
ፕሌኑ ቶሎ ስላልመጣ አርፍደን ነው ጉዞ የጀመርነው... ጥዋት ላይ ሪያድ ደረስን።..
አሰሪወቼ ቶሎ መጥተው ተቀበሉኝ...
ሰውዬው እንዳየኝ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ልጅ ናት ሲል የሚመልሰኝ መስሎኝ ቅስሜ ተሰበረ።.. እንደምንም ብዬ ሰራሁ ግን የገባሁበት ቤት ስራው በጣም ከብዶኛል።..በዛ ላይ ሴትዬዋ ትልቅ ሴት ሰለሆነች ይመስለኛል ትጨቃጨቃለች ምንም ብሠራ ማማሯ አይቀርም..
ግን እናቴ ዱአ ስታደርግ !ልጄን ጎረምሳ የማይበዛበት ቦታ አሥገባልኝ...አንተ ጠብቅልኝ ያንተ ጥበቃ ከሠው የተሻለ ነውና" ትል ነበር እጆቿን ወደ ላይ ከፍ አድርጋ.....የእናቴ ዱአ ተከትሎኛል የአሠሪዬ ጎረምሳ ልጆቿ ትዳር ይዘው ከቤት ወጥተዋል።..
ማታ ላይ ከአስርዬ ጋር ወደ እህቷ ቤት ሄድን ስንገባ በጭራሽ ያልገመትኩት ነገር ገጠመኝ።... ገና በሩን ከፍታ በአማርኛ ስታወራኝ እንባዬ ወረደ.... እእእእእእእእ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የአማርኛን ቋንቋ የተለየሁት መስሎኝ ነበር.. አላሀምዱሊላህ በጣም ደሥ ብሎኛል።ከሀበሻ ጋር ነው የምሰራው ማለት ነው እያልኩኝ ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጥን.. ደጋግማ ሳመችኝ ናፍቆቷን እየተወጣች መሆን አለበት...ልትለቀኝ ነው አገላብጣ ሳመችኝ...ጨሰችኝኮ...
"አልሀምዱሊላህ ሀበሻ አገኛለሁ ብዬ አላስብኩም ነበር" አልኳት ዝም ብላ አየችኝና "አሁን ልሰሪ ነው የመጣሽው"አለች..
"አይ ልጎበኝ ነው" አልኳት ጥያቄዋ ገርሞኝ...
" ክክክክክክክክክ የእውነት ልጅኮ ነሽ ለምን ትምህርትሽን አልጨርሽም"
"ተማሪው የውሎ አበል ካልተከፈለን አንማርም ብሎ ትምህርት ቤቱ ተዘግቷል...ክክክ ባክሽ ትምህርት እሥከ ስድስት ዘመድ እስክ አክስት ሲባል አልሰማሽም...ከስድሥት በላይ የተማርኩበትን አስበው ቢሰጡኝ ደስ ይለኛል".. "ክክክክክክክክክክክክክክ አንቺ በጣም ቀልደኛ ነሽ"...
"እሺ ግን አብረን ነው የምንሰራው..?" አልኳት ለማርጋገጥ ያክል...
" አይ አንቺ ገጠር ነው የምትሄጂው።" አለችኝ እንደማዘን እያለች...
"እእእእእእእእእ አሰሪዬ ሌላ ናት እንዴ....?"..
" አይ ያመጣችሽ ናት.. ኑሮዋ ገጠር ነው...ነገ ትሄዳላችሁ".. ስንስቅ ስንጫወት አደርን..ንጋት ላይ ተነሽ ልትሄዱ ነው አለችኝ። ልቤ ደነገጠ እፍፍፍፍፍፍፍ ከሷም ልለይ ነው ሲደብር.. ምናለበት አብረን ብንሰራ...ኡፍፍፍፍ

ገጠር ስደርስ የግቢው ስፋት የኛን ሰፈር ያክላል..
"ኤዥሪደይ ክሊር ዘይዝ" ይላል ልጇ.......
ወይ ጉዴ አይቼው ብቻ ደከመኝ ወደ ውስጥ ስገባም ሌላ ግቢ አለ.. ከውስጡ በጎች "ባባባባባባባ" እያሉ ይጮኻሉ። ወይ ስቃይ ለእረኝነት ብቻ እንዳይሆን ያመጣችኝ..እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ እእእእእእእእእ ቤት ስገባ ትልልቅ የአራት ሰው ቤት አሳየችኝ...ክላስ አይደለም ያልኳችሁ አስቡት እንግዲህ ቤት እንጂ....
"እእእእእእእእእ ሁሉንም ቀስ በቀስ ታጸጂያለሽ"..
"እንደገና ማጭድ ሰታይ ሳርም ለበጎቹ እጨጂ" አለችኝ..
እኔ በሂወቴ ሳር ላጭድ ቀርቶ ማጭድ እራሱ እንዴት እንደሚያዝ አላውቅም..
እሺ ብዬ የቻልኩትን ያህል ሞከርኩ...
ከዛ ስመለስ ደግሞ ግቢውን ጥረጊው አለችኝ ውይ ፈተና እንዴት ሠው ይሄን ሁሉ በአንድ ቀን ያከናውናል ለዛውም ያለምንም እረፍት..ሙቀቱ እራሱ አንድ ፈተና ነው..የፀሀዩ ንዳድ አያፍለከልክም ጥውልግ አድርጎኛል...በቃ ማረሚያ ቤት መግባት ይሻላል.. እፍፍፍፍፍፍፍፍ ምን አንቀለቀለኝ እግሬን በሰበረው እሥክል ተማረርኩ እናቴ ትዝ ሥትለኝ እንደምንም እየተነጫነጭኩ መሥራቴን ቀጠልኩ.. ልሞት 5 ደቂቃ ሲቀረኝ ጨረስኩ አልሀምዱሊላህ.....


ዛሬ ሶስተኛ ቀኔ ነው እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ሳር ላጭድ ሄድኩ.. እያጨድኩ እያለ ግን እጄን ማጭዱ ቆረጠኝ..ርሃብ ነው መሠል ልቤንም እያቅለሸለሸኝ ነው...እጄ ክፉኛ እየደማ ነው..እንጃ ብቻ የደም ሥሬን ቆርጬው ይሁን አላውቅም ደሜ እንደ ውሃ እየፈሠሠ ነው...ኧረ እራሤን ቀሥፎ ያዘኝ..ሠማይ ምድሩ ተገላበጠብኝ..ሁሉም ነገር ብዥ ብሎ ነው የሚታየኝ...ዘፍ ብዬ ወደቅኩ.....

ይቀጥላል....
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

22 Oct, 11:36


​ምንም አይነት ያረጀ ቤት የለም...ሁሉም ያፈዛሉ....እዚያው የሚገኘው ኤድናሞል ወሰዱኝ...እዚያ አከባቢ ሥደርስ ግን ከፋኝ የሃብታም ልጆች ማሚ..ዳድ እያሉ ይዝናናሉ..ይሞላቀቃሉ..ገንዘብ እንደ አሸዋ ይበትናሉ..ህይወት እንዲህ ናት እንግዲህ የኔ ቢጤውን ሚሥኪን ካደገበት ቀዬው ታፈናቅላለች..ያለለትን ደግሞ እንዲህ ታድለዋለች...

ጨርሰን ስንወጣ ሰሙ...ሰሙ እያለ ጮኽ ብሎ ጠራኝ ሁሲ ነው ብዬ ደንግጬ ስዞር ጅማ የማውቀው የካሊዶ ጓደኛ ባቢ ነበር።.."እእእእእእ ባቢዬ" አልኩት.. ሰላም ተባባልን... መኪናውን አቁሞ አወራን "ቆይ ግን ሰሙ" አለ አይን አይኔን እያየ..
" እእእእእእእ አንተ እንከፍ".. አልኩት የሆነ ነገር እንደሚለኝ እያሰብኩ...
"ዳይመንዱን ለላይ ቤት ነው እንዴ ያስቀመጥሽው"...
' "ክክክክክክክ ማፈርያ እንዲህ ይባላል አሁን"
"አይ ጓደኛዬ ካሊዶ ለሀጩን ጥሎብሽ ነበር"..
" መቼም ወሬ አለብህ በቃ ልሂድ እየጠበቁኝ ነው"..
"ሲጀመር እንዲህ አይነት ወሬ ይነስርሻል አይደል እሺ ይመችሽ ባይ"አለ...
እኔም ባይ ብዬው ተለያየን።
ግን በአላህ ሁሲን አንዴ እንኳን ቢያገናኘኝ ብዬ እያሠብኩ ወደ ዘመድ ተብዬዎቹ ሄድኩ።..

1 ሰአት ደርሶ ቦሌ አየር ማረፊያ ገብቻለሁ።.. እፍፍፍፍ ውይ ማጣት... ከሀገሬ እና ከእናቴ እለያለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር..
ቶሎ አየሩ ሰላልመጣ አርፍደን ነው ጉዞ የጀመርነው.....ደህና ሁኚ ማሚ....ደህና ሁን ሁሲ..አንድ ቀን እንደምንገናኝ በልቤ ተሥፋን ሠንቄ ነበር ጉዞ የጀመርኩት....

ይቀጥላል....
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

22 Oct, 11:36


🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌹 ክፍል 9⃣

.
.
.
.
በተደጋጋሚ ሲደውል ምን ሆኖ ነው ብዬ ደንግጬ የፌቪ መኝታ ቤት ገብቼ ስልኬን
አነሳሁት..
"ሠላም ነው ሠሙ"አለኝ.. ሁሲ ዛሬ ደግሞ እንደማልቀስ እያረገው ነው የሚያወራው...
ውስጤ ተረበሽ "ሰላም አይደለም እንዴ ሁሲ"
"አይ ሰላም ነው ሠሙ.. በአላህ ከቻልሽ እንገናኝ እባክሽ"..
ግራ ገባኝ ምን እንደምለው አላውቅም የተጎዳ ይመስላል... ድምፁን ስሰማው አሳዘነኝ..
"እነ ፌቪ በራፍ ላይ ነኝ".. "እእእእእእእ እንዴ እዚህ ሁሲ!".. "አዎ መስኮቱን ብትከፍቺው ታይኛለሽ"..
እእእእእእእእእእ ምን አይነት አጣብቂኝ ውሥጥ ነው የገባሁት እሺ ብዬ እንዳልወጣ ወንድሜ አብሮኝ አለ..ደግሞም ማሚ ቤት ነች በአጋጣሚ ብትወጣ ከሁሲ ጋር ታየኛለች።..እንቢ እንዳልለው ከአንዴም አራት ጊዜ ለምኖኛል.. እሺ ምን ላርግ..መልስ ሳልመልስለት ዝም አልን ሁለታችንም...
" እእእእእእእ ሰሙ" አለና ከገባሁበት የሀሳብ ናዳ አወጣኝ።..
"ይቅርታ አ....." እንዳልኩኝ ሳያስጨርሰኝ "እሺ በቃ" ብሎ ሥልኩን ዘጋው...
እእእእእእእእእ በአላህ መሮታል ማለት ነው። እፍፍፍፍፍፍፍፍ ሲያስጠላ እሱ እራሱ ቤቴ አከባቢ ምን አስመጣው....
ወደ ሳሎን ሂጄ የወንድሜ ጉልብት ላይ ቁጭ ብዬ መረበሽ ጀመርኩ..
"ማስቲካ ካልገዛችሁልኝ እበጠብጣለሁ ብዬ አሳበድኳቸው..
ጋጋታው፤መበሻሸቁ ሰለሚያስደስተኝ ነው እንጂ ከነሱ ጋር የምሆነው እግርኳሥ ማየት ፈልጌ አይደለም።..
"እሺ ይገዛልሻል አንቺ በረሮ ዝምበይ"አለኝ ቢኒ...
"ግዛልኛ...ዝም እንድል ከፈለክ አፍጥነው ዳይ"..
"እጁን ኪሱ ውስጥ እየከተተ "የኔን ቡድን ከደገፍሽ 10 ብር እሰጥሻለሁ".. አለኝ
"አግኝቼ ነው...እሺ መጀመሪያ ስጠኝ"..
"እሺ ብሎ ሰጠኝ"...
እኔ እሱ የሚደግፋቸው ጎል ሲያስቆጥሩ አሽቃብጥለታለሁ... ኳሱ ሲያልቅ እኔና ወንድሜ ወደ ቤት ሄድን።..
ዝም ብዬ ሰለ ሁሲ ሳስብ አልተኛሁም.. ሁሲ ሳይደውልልኝ ሶስት ቀን ሞላው።..እንዴ ምን ሆኖ ነው አስጨነቀኝ ሰፈር ላይም አይታይም ስደውልለት ስልኩ አይስራም።..
የቅርብ ጓደኛውን ማሜን ደውዬ ስጠይቀው ስልኩ እንደማይሰራና በቅርብም እንዳልተገናኙ ሲነግረኝ በጣም ደነገጥኩ።.. በቃ ቤት ሂደህ ቼክ አድርግልኝ ብዬው ስልኩን ዘጋሁት...
አላስችል አለኝ በዛ ላይ ድምፁ ልክ አልነበረም ሲያወራ...እፍፍፍፍፍፍፍ
ለፌቪ ነግሪያት አብረን ሰፈራቸው ሄድን..በአጋጣሚ እህቱን አገኘናት.. ደስ አለኝ ሞቅ ያለ ሰላምታ ከተለዋወጥን በሁዋላ
ፌቪ "ሁሲ በሰላም ነው የጠፋው...?" አለቻት.. "እእእእእእእእእእእ በቀደም ማታኮ አዲስ አበባ ዘመድ ጋር ሄዷል በዛውም ስራ ሊጀምር ነው።"... የሰማሁትን ማመን አቃተኝ ለስንብት ነበር ሰፈር ድረስ የመጣው ማለት ነው.. እንባዬ መጣ
እህቱ እንዳትነቃብኝ ምንም እንዳልሰማሁ አስመስዬ ከአጠግባቸው ዞር አልኩ።
ፌቪ "እሺ ቻው በሰላም ይመልሰው"ብላት ተከተለችኝ... ምንም ሳልል ቤት ገብቼ የያዝኩትን እንባ ዘረገፍኩት።

/////////**********////////

ወንድማገኝ ማሚን ሲናገራት ይሰማኛል... "ቤቱን ልቀቁልን እስካሁን በዝምታ ጠብቀናችዋል.. ከሳምንት በሁዋላ ካልወጣችሁ እቃችሁን ነው የምበትነው" እያለ ይናገራል።..
ማመን ተሳነኝ ወንድማገኝ ማለት ያከራያችን ልጅ ነው.. አንድም ቀን እንደ ተከራይ እና አከራይ ተያይተን አናውቅም።.. ከቤተሰብም በላይ ነው የምንቀራረበው እና ዛሬ ምን ታየው...ምንሥ ተገኘ...
ባዳ ያው ባዳ ነው የሚባለው ለካ እውነት ነው...
ማሚ "አንድ እንኳን ቤት አጥቼኮ ነው..እየፈለኩ ነው.. በቅርብ እወጣለሁ" አለችው..
"ብትፈልጊማ አታጪም አውቀሽ ነው እንጂ"ምናምን ሲል መታገስ አቃተኝ...
ከመኝታ ክፍሌ ወጥቼ ወረድኩበት
"ይወጣልካላ ምን ታቅራራለክ ደሞ ማሚን እንዲህ ትሰድባታለክ...ከእጇ በልተህ ጠጥተህ ትንሽ እንኳን አታፍርም.. አንተን ብሎ ባለቤት"..እእእእእእእእእእ እንባዬ መንታ መንታ ይወርዳል...
ልጁ ደንግጦ ዝም ብሎ ያየኛል.. "እእእእእእእእእ ሰሙ አልተሳደብኩምኮ"እያለ ተጠጋኝ..
" አትጠጋኝ አሁን እንወጣልሃለን አንተ ማፈሪያ ቤትህን ቀቅለህ ብላው"..
ማሚ በጥፊ ልትለኝ ምንም አልቀራትም ተቆጥታ ቤት አስገባችኝ።.. የኔን ለቅሶ ያዩ አንድ ጎረቤታችን አባብለውኝ እነሱ ግቢ እንደምንገባ ነገሩኝ...ወዲያውም እቃችንን ጠቅልለን ገባን።..
ከሶስት ቀን በሁዋላ ማሚን አረብ አገር መሄድ እንዳለብኝና ቤት መግዛት እንዳለብኝ ነገርኳት።..
እሷ በጭራሽ አይሆንም ብትልም እያለቀስኩ አሳመንኳት።........

በ 3 ወር ውስጥ ጨርሼ ዛሬ ልሄድ ነው... ማሚ የሰው ፍቅር አላት በጣም ብዙ ሰው እኛ ቤት መጥተዋል..ከመሄዴ በፊት ዱአ ሊያረጉልኝ ነው..የኔ ጓደኞች በርከት ብለዋል.. ግማሾቹ ያለቅሳሉ አንዳንዶቹ ደንግጠዋል።.. እንዴት ይሄን ውሳኔ ወሰነች እያሉም ይገረማሉ....
ፌቪ በጭንቀት ወባ አሟት ተኝታለች..ውይ የኔ መሄድ ያላሳበደው የለም።የግድ ግን መሄድ አለብኝ....

የሆነው ሁኖ ለሊት አዲሥ አበባ ወደሚወስደኝ መኪና ውስጥ ገባሁ።..ከጅማ ሥወጣ ቅር ቢለኝም..ከእናቴ ጉያ መውጣት ቢያሥተክዘኝም...ከነፌቪ ጋር መለያየት ምን ያህል የከፋ ቢሆንም..የምሄድበት አላማ እያጠነከረኝ...ለእናቴ እንደማሳልፍላት ሳስብ ይበልጥ ደንዳና እየሆንኩ ጅማን ተሰናበትኳት።..
ልክ አዲስ አበባ ስደርስ ሁሲ ትዝ አለኝ..እንባዬ መጣ እእእእእእእእእ
ብጣራና ቢሰማኝ ተመኝሁ... ስልኩ ደግሞ አይሰራም።.. ሳንገናኝ ልሄድ እንደሆነ ሳስብው የተንቀረዘዘው እንባዬ ፈሰሰ።..

ሳሪስ የሚገኙት የማሚ ቤተሰቦች ጋር ነው ያረፍኩት። ቤታቸው እጅግ ያምራል.. ፎቁን አከራይተው ከታች ነው የሚኖሩት። ግቢያቸው እራሱ ውጡብኝ ውጡብኝ አይልም...
አይ ማሚ የቤተሰብ ሀብት ምን ያደረጋል አለች።.. እውነቷን ነው እሷ ለዛች ቤት እንደዛ ሲላገጥባት ቤተሰቧ እንዲህ ተንደላቀውና ተሞላቀው ይኖራሉ።.......
የማሚ ቤተሰብ እኔን ሲያዩ ደነገጡ "እእእእእእእእእ ኧረ አንቺማ አትሄጂም.. የወጣውን ወጪ እኔ እከፍላለሁ..አንቺ እዚህ ሆነሽ ትማሪያለሽ ቢያንስ 18 አመት እስኪሆንሽ እሺ".. አለ ከማሚ ዘመድ ውሥጥ አንዱ..
"አይ እኔ ኢትዮጵያ ውሥጥ ለ3 ቀን እንኳን መቀመጥ አልፈልግም።"አልኩት እስካሁን የት ነበርክ በሚመስል አሥተያየት ፍጥጥ ብዬበት...

የማሚ ቤተሰቦች ልጥጥ ሀብታም ናቸው..ማሚ አባቴን ስታገባ ሙስሊም ሆና ነበር ያገባችው...እንዴት የቤተሠባችንና የኖርንበትን ሃይማኖት ትቀይራለች በሚል ተልካሻ ምክንያት ተናደውባት ሙሉ ቤተሰቡ አገለሏት..
ባባ እኛ ህፃን እያለን ነው የሞተው የዛኔ መሄጃ ስታጣ ትመጣለች ብለው ቢያስቡም እሷ ግን በቆራጥነት እራሷን ጎድታ ለኛ ምንም ሳታጓድል አሳድጋናለች...የኔ ጀግና..የኔ ምሳሌ....

ኧረ ተይ አትችይውም ገና ልጅ ነሽ ብለው ሊያሳምኑኝ ቢሞክሩም.. እኔ በጭራሽ አልኩና ፎቅ ካለችው ሱማሌ መስገጃ ተውሼ ሰላቴን ሰግጄ ስቅስቅ እያልኩ አላህን ለመንኩት እሱ እንደማያሳፍረኝ እርግጠኛ ሆኜ...እነዚህ ዘመድ ነን ተብዬዎቹ ያሰብኩትን ሳላሳካ ልጅ ነሽ ብለው የሚመልሱኝ እየመሰለኝ ፈራሁ።...

ዛሬ 1 ሰዓት ላይ በረራዬ ነው።እሥከዛ ሸገርን ዞር ዞር አድርገው ሊያሳዩኝ ወጥተናል.. አዲሥ አበባን ተሽከረከርናት በጣም ሰፊ ናት...ቦሌ አካባቢ ስንደርስ ከኢትዩጵያ ውጭ ያለሁ እሥኪመሥለኝ ድረሥ አፌን ያዝኩ..

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

18 Oct, 17:14


🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌹 ክፍል 8⃣

.
"ምነው ቆየሽ ልጄ ኢሻ አዛን ሊል እኮ ነው"..አለችኝ ለስለስ ባለ ድምፅ...የምለው ጠፋኝ ማሚን እንዴት ልሸውዳት...
ከፌቪ ጋር እንደነበርኩ ነገርኳት ምንም ሳላሥነቃ... አጠገቧ ቁጭ አልኩና እሷን ላግዛት እጄን ፍራፍሬው ላይ ጣል አረኩት....ሀሳቤ ግን ሌላ ቦታ ሂዷል።.....
'እእእእእእእ ካሊዶን እሺ ልበለው....?'
ብዙ ጓደኞቼ ካሊዶን እንድቀበለው ቢገፋፉኝም እኔ ግን ፍንክች አላልኩላቸውም ነበር።...
ዛሬ ግን መሮኛል ሁሲን መርሳት እፈልጋለሁ!.........ከመወሰኔ በፊት ግን ማሚን ማማከር አለብኝ።
" ማሚ"አልኳት..
"ወዬ ልጄ" አለችኝ..
እእእእእእእእእእእእእእ ደፍሬ ልንገራት ወይስ ይቅርብኝ...በቃ ልንገራት..
"ማም ካሊዶን ታውቂዋለሽ..?"
"ማነው እሱ... በቀደም እንደውም ፍራፍሬ ገዝተን ስንመጣ መኪና አቁሞ የጫነንን ቀዩን ልጅ ነው...?"..
" እእእእእእእእ አዎ"..
"ምን ሆነ! ደንገጥ ብላ.. አረ እንደውም በጣም ሰላምተኛዬ ነው... ምን ሆነ ልጄ...?"ማሚ ተጨናነቀች...
"ኧረ ምንም አልሆነም.. ሀብታም ምን ይሆናል ክክክክክክክክክክክ"
"የማታመጡት የለም መቼም እንዲህም አላችሁ".. አለች ማሚ በሚያምር ፈገግታ ታጅባ..
"እሺ ምነበር እማ ሥለሱ ላማክርሽ ፈልጌ ነው"..
"ምንድነው ልጄ ተንተባተብሽኮ በሠላም ነው...?በይ እሥቲ ንገሪኝ"..
" እእእእእእእ የፍቅር ጥያቄ አቅርቦልኛል..እናም እሺ ካላልሽኝ እያለ ነው።..እኔ ደግሞ እሺ ብዬው አንቺን ልረዳሽ እያሠብኩ ነው..ያን ያህል ልቤ ባይፈልገውም ሀብታም ነው..አንቺን ከዚህ ሁሉ ድካምሽ ማሳረፍ እፈልጋለሁ እባክሽ"..
"ሆይ አንቺ አንድ ፍሬ ልጅ ምን ሆኚልኝ ብሎ ነው እሺ ካላልሽኝ የሚልሽ"...ማሚ ቱግ ብትልም ሰከን ብላ ማሥረዳቱን ተክናበታለች
" ልጄ አንቺ አንድ ፍሬ ልጅ ነሽ እሱም እንደዛው..
ደግሞ ሀብታም ነው የምትይው እሱ ከየት አመጣው የቤተሰቡ ቢሆን እንጂ.. የቤተሰብ ሀብት የሚጠቅም ቢሆን ኖሮ እኔን በጠቀመኝ ነበር።.. ከዛ ከናጠጠ ዲታ ቤተሰብ ተወልጄ እናንተን የማሳድግበት ቤት እንኳን ያጣሁ ሚስኪን ነኝ አታይኝም.."የእናቴ አይኖች እንባ አቆሩ..ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ብላ በረዥሙ ተነፈሰችና ንግግሯን ቀጠለች...... "የኔ ቤተሰቦች ምን ጠቀሙኝ አንቺ ተማሪ ነሽ አንድ ፍሬ ልጅ ወደፊት ችግር መከራና ሥቃይ ሊያጋጥምሽ ይችላል እነዚህን መጥፎ ጊዜዎች ማለፍ ያለብሽ ግን በሠው ትካሻ ሳይሆን በራሥሽ ጥረት መሆን አለበት ..ሌላው ደግሞ ልጄ ስንቶቹ መሰሉሽ ገና በጨቅላ እድሜያቸው በፍቅር ስም ተታለው በየጎዳናው የወደቁ..ወደድኩሽ አበድኩልሽ እያለ አንድ ጥግ ያስገባትና የሚፈልገውን ካገኘ በሁዋላ በወር በሶስት ወሩ ይተዋታል።.. የአላህን ትእዛዝ ስንዳፈር የማንችለው ጣጣ ውስጥ እንገባለን።... አላህ ዝሙትን እንዳንቀርብ አዞናል.. ፍቅሩን ብትቀበይው ምን ሊያደርግ ነው ሽማግሌ ሊልክ ሊያገባ ዝግጁ ነው...? ወይስ ዝግጁ እስኪሆን በሀራም ልትጨማለቁ ነው....?.....
ረሱል(ሰ ዐ ወ) "ተቃራኒ ፆታወች አይቀላቀሉ".. ያሉት ለምን ይመስልሻል የአላህ ድንበር እንዳይጣስ ነው...ሠዎች እራሳቸውን ለዝሙት እንዳያዘጋጁ ነው...ነፍሥያቸው እንዳታሸንፋቸውና ወደ ሀራም እንዳይገቡ ነው...ልጄ እኔም ደሞ ሀብታም ወንድ ይዘሽ እድትረጂኝ ሳይሆን ጥሩ ውጤት አምጥተሽ እንድታስደሚሚኝ ነው"..ብላ ንግግሯን ጨረሰችና አይን አይኔን አየችኝ...
"እማ እሺ በቃ ይቅርታ አውፍ በይኝ" አልኳትና እጆቿን ሳምኳት..
"ልጄ ምንም ከማድረግሽ በፊት ሰላማከርሽኝ አድንቄሻለው...ኮርቼብሻለሁም። ሁሌም የምፈልገው እንዲህ የምታማክረኝ እና እንደ ጓደኛ የምትቀርበኝ ልጅ እንዲኖረኝ ነበር".. ብላ ሳመችኝ..
ወደ መኝታ ክፍሌ ሄጄ አረፍ አልኩ ወይ ጉዴ ሁሲ ለምን አይጠይቀኝም ብዬ በቅጽበት ካሊዶን አሥባለሁ እንዴ..ቆይ ግን ምን እየሆንኩ ነው...

የእናቴን ምክር ተኝቼ መላልሼ አስበዋለሁ... ልክ ነች
እያልኩ ለራሴ እነግረዋለሁ...
አንዳንዴ እናቴ ከሠው ሁሉ ገዝፋ ትታየኛለች መላእክ አደርጋታለሁ በህይወት ላይ ያላት ብሥለትና ልምድ ከአእምሮዬ በላይ ነው...እኛ ቤት ገንዘብ የለም ግን ለሁሉ የሚበቃ ፍቅር አለ።..
አልሃምዱሊላህ ፈጣሪዬ እቺን የመሰለች ወርቅ እናት ሥለሰጠኸኝ ምሥጋና ይገባህ....

/////////////**////////

.. የማይነጋ የለም ነጋ በጥዋቱ ሁሲ ደውሎ ክላስ እንገናኝ ሲለኝ ማታ ማሚ ያለችኝ ነገር ብልጭ አለብኝ...
እእእእእእእእእእ ምን ልበለው... ደግሞ ክላስ ለምን ይቀጥረኛል....?ሆሆሆሆሆሆ
"ይቅርታ አይመቸኝም" ብዬ ስልኩን ዘጋሁት...
በተደጋጋሚ ሁሲ እንድንገናኝ ቢጠይቀኝም እንቢ አልኩት።

ዛሬ ደግሞ ሰብሰብ ብለን እነ ፌቪ ቤት እግርኳስ እያየን ነው..
የአለም ዋንጫ ሰለነበር በጣም ብዙ ልጆች አሉ.. መንትያ ወንድሜና እኔ አጠገብ ላጠገብ ነበር የተቀመጥነው..
በአጋጣሚ ስልኬ ጠራ ወንድሜ እንዳያይ እየተጠነቀቅኩ ቀስ ብዬ ሳየው ሁሲ ነው።.. ሳይለንት አድርጌ ዝም አልኩ በተደጋጋሚ ሲደውል ምን ሆኖ ነው ብዬ ደንግጬ የፌቪ መኝታቤት ገብቼ ስልኩን አንሳሁት...

ይቀጥላል....
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

18 Oct, 17:11


🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

ክፍል 7⃣

.
.
.
..ሰዎች ወደ መኪናው ይሮጣሉ ይተራመሳሉ...ግማሹ ተክዟል ግማሹ ጭንቅላቱን ይዞ አንገቱን ይወዘውዛል ብቻ ሠው ብቻ ሆኗል ቦታው....ፌቪ ወይኔ ሁሲ እያለች ታለቅሳለች...እኔ በድንጋጤ አንደበቴ ተለጉሞ መላ አካላቴ አልታዘዝ ብሎኝ ባለሁበት ደርቅያለሁ..ምንም ድምጽ ሣላወጣ እንባዬ ብቻ ኩልል እያለ በፊቴ ላይ ይወርዳል...

ከትንሽ ደቂቃ በሁዋላ ሁሲ ሲመጣ ፌቪ አየችው..."ሰሙ ያንቺ ሁሲ ያውና ምንም አልሆነም"እያለች ትጮሃለች እኔ ግን መጥታ አቅፋኝ እሥከምትነቀንቀኝ ምንም አልታየኝም ምንም አልተሠማኝም በቃ በህይወት ያለ ሙት ሆኛለሁ...
ከገባሁበት ቅዠት እንደመባነን ስል ተንደርድሬ ተጠመጠምኩበት...ተንሰፈሰፍኩለት ከዚህ በሁዋላ የማየው አልመሥል አለኝ..ልሥመው ሁላ ቋመጥኩ..እንባዬ እንደ ወንዝ ይጎርፍ ነበር.. እንደ ህጻን ልጅ ሥንሠቀሠቅ..
"አለሁኮ ምንም አልሆንኵም ይሄው አጠገብሽ ነኝ ተረጋጊ"..አለኝ..
"አልሀምዱሊላህ" አልኩና ከእቅፉ ውሥጥ ወጣሁ..
ነገሩ እንዲህ ነው ሁሲ ሊሻገር ሲል በሰከንዶች ቅፅበት ነው የሆነ የአእምሮ ህሙማን የተገጨው...አደጋው በተፈጠረበት ቦታ እያለፍን አንጀቴ ተላወሰ።ገና ወጣት ነበር ግን አልፏል... ወደዛኛው አለም ሄዷል..ይሄ ሚሥኪን፤ይሄ አለሁ ባይ ያጣ፤ይሄ ህይወት ገፍታ ወደ ዳር የጣለችው፤ይሄ መታከሚያና መጠለያ አጥቶ ጎዳና ላይ የተጣለው ወጣት ካለጊዜው ተቀጠፈ....አይ እምዬ ሀገሬ ሥንቱ ልጅሽ እንደዘበት ያልፍልሻል..ይቀጠፍልሻል..
ይገርማችሁዋል እሥካሁን አንቡላንሥ አልመጣም..አያችሁ ምን ያህል ወደ ሁዋላ እንደቀረን ነጮቹ እንቅፋት ቢመታቸው እንኳን በሠከንዶች የአንቡላንሥ አገልግሎት ሲያገኙ እኛ ጋር ግን ህይወት እያለፈች እንኳን አንቡላንሥ የለም..ሀኪም የለም...ምጽጽጽጽጽ ያሳዝናል።..


///////////////******/////////

ድንጋጤዬ ባይለቀኝም አሁን ተረጋግችያለሁ ወደ ካፌውም እያመራን ነው።..ሁሲ ቀድሞ ጥግ ላይ ቦታ ይዞ ሥለነበር ቀደም ብሎ ሄዶ ወንበሮቹን እየሳበ "ኑ እዚህ ጋር ሴቶች" አለ
"እናመሠግናለን"ብለን ተቀመጥን...
ሁሲ ግን ምን እንደሚያሠላሥል ባላውቅም ቶሎ አልተቀመጠም.. ፈዟል።
"ቁጭ በል እንጂ" አለችው ፌቪ ሙድ እየያዘችበት..
" እእእእእእእእ እሺ" አለና ቶሎ ተቀመጠ..
"ምን ልታዘዛችሁ" አለች አስተናጋጇ ካንገቷ ጎንበስ በማለት..
"ማኪያቶ" አለች ፌቪ ፈጠን ብላ..
እኔ እና ሁሲ ፈዘናል.. "እእእእእእእእእእእ እናንተ"ብላ ሳቋን ለቀቀችው ፌቪ..
እእእእእእእእ ምን እንዳሳቃት ባላውቅም የእፍረቴን አብሬያት ሳቅኩኝ... እሷ የኔ መሳቅ በድጋሚ አሰቃት።.. የባሰ ካፌውን ቀወጠችው...ኪኪኪኪኪኪኪኪካካካካካ.......
"ኧር በአላህ የሰፈር ልጆች ያዩናል።".. በድንጋጤ ቁጭ ብድግ እላለሁ...እሷ ባሰባት ወይኔ አዋረደችኝ...
"አስተናጋጇ እየሳቀች በድጋሚ "ምን ልታዘዝ?"..አለችኝ... "እእእእእእእ ምነበር የሚባለው.. ደስ ያለሽን"አልኳት እንደ ህጻን እየተኮላተፍኩና እየተንተባተብኩ... ክክክክክክክክክክክክካካካ ሁሲ በተራው በሳቅ ወደቀ።..
"ወይኔ እነዚህ እብዶች አስነቁብኝ በቃ"..አልኩኝ ሳላስበው..
"ንገሩኝ እንጂ" አለች አሥተናጋጇ "እእእእእእእእ ይቅርታ ምን ይሁንላችሁ" አለ ሁሲ ወደእኛ ዙሮ..
"ለእኔ ማኪያቶ ለሰሙ"...።።።።።።ሳቋ መጣ ፌቪ...
"በቃ እኔ እጨርሰዋለሁ ሳቁን አጀምሪው ማቆሚያ የለሽም".. አልኳት እና አዘዝኩ።..
ትንሽ እንደቆየን
" ከዚህ ሱቅ እቃ ልግዛ ስጨርሱ ነይ እጠብቅሻለሁ".. ብላኝ ወጣች..
" እእእእእእእእእእ ሁሲ"..አልኩት ለመጀመር ያህል..
"እሺ ሰሙ እንዴት ነሽ?"..
" እኔ አላሀምዱሊላህ ሠላም ነኝ.. አንተስ?"
"አለሁልሽ ባክሽ"..
ለትንሽ ጊዜ ዝምታ ሰፈነ..
" ምነው ከቤት ሀርድ ናቸው እንዴ?"አለኝ..
" እእእእእእእእ አይ ብዙም አይደለም... ያው የተለመደ ነው።"
እኔ ከአሁን አሁን ሰሙ እወድሻለሁ ይለኛል እያልኩ እየጠበኩ... እሱ ሌላ ነገር ያወራል። ምን አይነት አዝግ ነው በአላህ።..

ፌቪ ደወለች... ላነሳው ስል ሰዓት አየሁ 1:30 ይላል።..
"ወይኔ ጉዴ ልሂድ በቃ ረፍዷል" አልኩትና ተነሳሁ...
"እንዴ ሠሙ ገናኮ ነው"..
.."ኧር በአላህ በጣም ነው የረፈደው ቻው"..
" እሺ ልሸኝሽ?"...
" አይ እዚሁ ቅርብ ናት ፌቪ ቻው በቃ"..ብዬው ተሰናበትኩት..

ፌቪ ልክ እንዳየችኝ "መግቢያሽን ፈልጊያት..አሁን ምንድን ነው የምንለው"...እያለች ትነጫነጭብኛለች...
" ባክሽ አታካብጂ".. ብዬ ወረድኩባት..
" እእእእእእ ምን አለሽ ሁሲ?" አለችኝ..ለመስማት ጓጕታ..
"ባክሽ ምንም አላለኝም።"
" እንዴ ለምን ጠራሽ ታድያ".. "ሊያየኝ ይሆናላ አልኳት".. በንዴት
" ክክክክክክክክክክክክክክክ"
ሳቀች ፌቪ..
" ሳቂ አንቺ ምን አለብሽ"..
"የእውነት ግን እንደሚያፈቅርሽ አልነገረሽም?"..
" አዎ ባክሽ ካንቺ ይደበቃል ቢነግረኝ"...አልኳት
"እፍፍፍፍፍፍፍፍ ምን አይነቱ ገገማ ነው በጌታ..በቃ ለምን ካሊዶን እሺ አትዪውም የክላሥሽ ልጅ ነው..በዚያ ላይ ጽድት ያለ ነው... ሙቶ እራሱ ይበልጠዋል"አለች.. አይን አይኔን እያየች..
" ምን የሀብታም ልጅ ሰለሆን ነው.. ሙቶ የሚበልጠው".. አልኳት እየተናደድኩ..
"ባክሽ የወንድ ልጅ ውበቱ ኪሱ ነው...ደግሞም ቆንጆ ነው።"..

/////////////////********//////

እኔ ጋር እንደነበረች ለእማማ ነግሪያቸው እቤቷ አሥገባሁዋትና ወደ ቤቴ አመራሁ...ቀሥ ብዬ ሳይ ማሚ ቀን የገዛችውን ፍራፍሬ ነገ ለመሸጥ እያስተካከላቻቸው ነበር..ትንፋሼን ውጬ ምንም ድምጽ ሳላሰማ ወለሉን የመንካት ያህል እየተረገጥኩ ወደ መኝታ ክፍሌ ልገባ ሥል..
" ምንው ቆየሽ ልጄ ኢሻ አዛን ሊል እኮ ነው".. አለችኝ ለስለስ ባለ ድምፅ...

ይቀጥላል....
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

17 Oct, 07:45


🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌹 ክፍል 6⃣


.
.
.
.
...ስልክ ተደወለ ሁሲ ነበር። ማንሳት ፈራሁ...
" እእእእእእእ ፌቪ አንሺው"..አልኳት
"ምን ልበለው?"
"እኔንጃ"...
ሥልኩን አነሳችው "ሄሎ" "አሎ"አጠፋዉን መለሰች ..
"ይቅርታ የሠሙ ስልክ አይደለም እንዴ?"..
"አይ ነው ግን ሻዋር ቤት ነች።".. "ኦኬ ስትወጣ ምልክት ታርግልኝ"..
"እሺ ቻው".. ስልኩ ተዘጋ... ኡፍፍፍፍ.....
"በቃ እንዳይጠብቅሽ ትንሽ ቆይተሽ ደዊይለት".....
እሺ አልኳትና ከ15 ደቂቃ በሁዋላ ደወልኩለት..
"ሄሎ ...አሰላሙአለይኩም"..
"ወአለይኩምሰላም ሰሙ እየጠበቅኩሽ እኮ ነው።"አለኝ...
"ውይ ከማሚ ጋር እኮ የሆነ ቦታ ልንሄድ ነው።...ዛሬ ይለፈን በቃ ሌላ ቀን እእእእእእእእእ"..አልኩት ውሸቴ ለራሴው እያሳፈረኝ...
"እሺ በቃ ሰሙ ካልተመቸሽ ቻው.. ከሰው ጋር ነኝ እሺ ሠሙ አታሥቢ"...
"እሺ ሰላም ሁን"..ስልኩን ዘጋሁት....
ፌቪ እየሳቀች "መዋሸት አትቺይም ተንተባተብሽ እኮ"
'ክክክክክክክክክክክ' እኔም ሳቅኩ...
"ግን በጣም አደነቅኩሽ"አለችኝ ፌቪ በትልቁ ከተነፈሰች በሁዋላ...
"እንዴት"አልኳት ለመሥማት እየጓጓሁ...
"እእእእእእእ እንዴ እንደ አለም ዋንጫ ስጠብቂው የኖርሺውን ነገር ለማሚ ስትይ መተውሽ ነዋ..እኔ ብሆን ምድርም ብትናወጥ የምተው አይመስለኝም።".. አለች ያግራሞቷን እያየችኝ..
'ይገባታል ባክሽ በብርድ እና ፀሀይ ተሰቃይታ አሳድጋኝ ለምን ላስወቅሳት'..አልኩና ዞር ብዬ አየዋት.....
"ልክ ነሽ ግን ብዙ ጊዜ እኛ እንዲህ አናስብም እንጂ...ምርጥ ልጅኮ ነሽ..እሟሟሟሟሟሟ....በቃ ዉሳኔ የሚባል ፊልም ሰላመጣሁ እኛ ቤት ሄደን እንይ"..አለችኝ
እሺ ለማሚ ልንገራት አልኳትና አስፈቅደን ወጣን።... ልክ ፊልሙን ሳየው አንድ እናት ለልጆቿ ሥትል ያሳለፈችውን መከራና መሰዋእትነት...ውይ ሲያሳዝን እንባዬ ኩልልልልልልልልል እያለ ይወርድ ጀመረ እንደ ህጻን ልጅ ተነፋረቅኩ..የእናቴ ውጣ ውርድ ጥርት ብሎ ታየኝ..በውሳኔዬም ኮራሁ።..

/////////////////*********/////////

1...2..3..4..እያለ ሳምንት ሞላን ዛሬም ደውሎ ሊያገኘኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ...
'የት?'...አልኩት እየፈራሁ.. "እእእእእእእእእእ ሻይ ቡና ካልን በሁዋላ ወክ ብናረግ ደስ ይለኛል"...
'እሺ ከተመቸኝ'...
"ስንት ሰዓት ላይ?"አለ....
"12 ሰዓት ላይ..1ሳት ላይ እመለሳለሁ።"አልኩት...
"እእእእእእእእ ምንድነው ተገናኝን ብቻ ለማለት ያክል ነው እንዴ?.. ሰዓት ይጨመር።". አለ
"እእእእእእእእ እሱን እያየን እንጨምራለን"..አልኩት
ክክክክክ "እሺ ባይ ባይ"...............

ዳግም ሲደውል ከቤት እንዳልተፈቀደልኝ እየተነጫነጭኩ ነገርኩት።...
እእእእእእእእእእእእእ በጣም ተናደደ....."አንቺ ሁሌም ምክያት አታጪም"..አለና ዘጋው...
እንዳስቀይምኩት ተሰማኝ ግን ምን ላርግ..እኔምኮ ናፍቆኛል..በጣም..እፍፍፍፍፍፍፍፍ ሲያስጠላ የአላህ እንዴት ይከብዳል...ውሸቶቼ ሰላሜን ነሱኝ...

ሶስት ጊዜ እንደቀጠረኝና በጣም እንደተቀየመኝም ለፌቪ ስነግራት...
"በቃ ካፌ ቀጥረሺው አብርን ብንሄድስ..አንድ ላይ ከሆንን ማሳበቢያ አናጣም።" አለችኝ.... woooooooooow ደስ የሚል ሀሳብ...
ጊዜ ሳላጠፋ ደወልኩለት....
እየፈራ እእእእእእእእ ሰሙ"... አለ መገናኘት እንደምንችልና 12 ሰዓት ላይ ካፌ እንዲጠብቀኝ ነግሬው ስልኩ ተዘጋ።..

እኔ እና ፌቪ ቶሎ ቶሎ ተዘጋጅተን ሄድን.....ካፌው አካባቢ እንደደረሥን ሳንሻገር ቆም አልንና
ምልክት አደረግንለት..በብርሃን ፍጥነት መለሰልን............. "እእእእእእእእእ ሠሙ የቱ ጋር ናችሁ?
"አስፋልቱን ሳንሻገር ጥግ ላይ ቆም ብለን ነው"..
"እእእእእ እሺ መጣሁ በቃ ልቀበላችሁ.."
ወዲያው ፈጠን ፈጠን እያለ ሲመጣ አየነው...አሥፋልቱን እያቋረጠ ግን አሥደንጋጭ የመኪና ድምፅ ተሠማ የሚረብሽ አይነት ድምጽ.. .........ሲሲጢጢጢጥጥጥጥጥጥ......

ይቀጥላል...

@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

17 Oct, 07:42


🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌺 ክፍል 5⃣


.
.
.
ነገ ደርሶ እስክንገናኝ ቸኩያለሁ።..... እፍፍፍፍፍፍፍፍ ምንድ ነው መሸ አይደል አይነጋም...? ነው ወይስ ሳላውቀው ነግቶ ይሆን..... ሆሆሆ እያበድኩ ነው እንዴ የቀረኝኮ ፈጣሪን ለምን ሰአቱን አንቀረፈፍከው....ለምን አታነጋውም.... ከኔ ጋር ምንድነው ችግርህ እረ ተወኝ....ለዛሬ እንኳን ደሥታዬን ላጣጥምበት ብዬ መቀወጥ ብቻ ነው...

አይፈረድብኝም ለስንት ጊዜ ስጠብቀው የነበረ እድልኮ ነው ባላብድና ባልጣደፍ ነበር የሚገርመው.....
እንደምንም ነጋ እፍፍፍፍፍፍፍ... ደስ ሲል ዛሬ ከሁሲ ጋር እንደምንገናኝ ሳስበው...ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ...እንደ ህጻን መቧረቅ፤መጮህና መዝለል አማረኝ.....ቶሎ ተንስቼ ማሚን ስራ አግዤያት የምለብሰውን ልብስ ስመርጥ ቆየሁ።....
ፌቪን ጠርቻት ተነጋገርንበት... እሷም ቶሎ ብትን፤ሽር..ድምቅ በይና ልይሽ አለችኝ... እኔም ቶሎ ቀያይሬ ልክ እንደ ፋሽን አሥተዋዋቂ ጎምለል..ጎምለል እያልኩና ቄንጥ እየተራመድኩ ብቅ አልኩላት።.... "woooooooooooooow ሠሙ ምንድነው እንዲህ ማማር" እያለች ጉንጬን ሳመችኝ.....
' እእእእእእእ ተመቸሽ' አልኳት።.. "በጣም እንጂ! ደሞ ሂጃብሽ ሲያምርብሽ" አለችኝ..
"owwwwww ያንገት ሀብሌን እረሳሁት..በቃ ሂጄ ከመኝታ ክፍሌ ላምጣው።" አልኳትና ሥገባ ማሚን ሳሎን ቁጭ ብላ አገኘዋት።...

በጣም ደነገጥኩ.... "ፌቪ እእእእእእእእእ ትቼው ተመለስኩ።".. አልኳት
"አቤት እእእእእ ምነው?"አለችኝ የተረበሸ ፊቴን እያየች...
"አልሄድም በቃ ትቼዋለሁ"
"ምነው..በዚህ ቅጽበት ምን ተፈጠረ?..እየቀለድሽ መሆን አለበት።"...
"እይ ባክሽ እውነቴን ነው።" አልኳት ሊፈስ የቀረበውን እንባዬን እንዳይዘረገፍ እየታገልኩ....
"እሺ ለምን? ምክንያትሽን ንገሪኝ እባክሽ.."ብላ ተማጸነችኝ በተጨነቀ ድምፅ...
"ቃል አለብኝ። አልኳት... "እእእእእእእእእ ሠሙ ነቅተሽም ትቃዥያለሽ እንዴ?... ሥለምን ቃል ነው የምታወሪው".......
"የሚስኪኗ እናቴ በቀን ስራ ለፍታ ያሳደገችኝ.... የመኖርን ሚስጥር ያስተማረችኝ የእሷ ቃል ነው ያለብኝ።"...አልኳት እንባዬን እየጠረኩ...
"እሺ ንገሪኛ አስጨነቅሽኝኮ አልታወቀሽም ሠሙ"....
"አንድ ቀን ከት/ቤት እየመጣው ሚኪ ደረሰብኝና ደብተሬን ቀማኝ...ሚኪ በጣም ደራቃና ሞዛዛ ነው...ሚኪ ማለት ከልጅነቴ ጀምሮ የሚያፈቅረኝ የሠፈር ልጅ ነው።....ማሚ በፊት ወተት የምትከራየው ከነሱ ቤት ነበር..እናቱ ሂድ ልጄ ለሚሥትህ ሠሚራ ይሄን ወተት አድርሥ እያሉ ሲልኩት ደሥ እያለው ነበር የሚላከው...ሥናድግም የእውነት አፍቅሮኝ አረፈው።...አልፈርድበትም እኔሥ ሠሙ የሁሲ ናት እያሉ አሥወርተው አይደል ፎንቃ የጠገረረኝ...እናም ሚኪን በእምነት ሥለማንገናኝ እንዲረሳኝ በተደጋጋሚ ብነግረውም ለጊዜው እኔን መርሳት አስቸግሮት ነበር።...የመጀመሪያዬ...
ፍቅርን ሀ...
ሁ...
ያልኩት ባንቺው ነበር..ምናምን እያለ ሲከተለኝ ያሳዝነኝ ነበር...ግን.............እምነት ይለየናል።...........
እና ሚኪ ደብተሬን ይዞ ሲሮጥ..እኔ ተከትዬ ሳባርረውና ከእሱ ደብተሬን ልቀበለው ስታገል ነው እንግዲህ ማሚ ያየችኝ...ሀገር አማን ብዬ ቤት ስገባ ማሚ አኩርፋለች።... ምነው ብዬ ስጠይቃት "እንዴት ከወንድ ልጅ ጋር ትታገያለሽ? ሴት ያሳደጋት እያሉ እንዲጠቋቆሙብሽ ነው...በድህነቴ ያላባት አሳድጌሽ እንዴት ታሰድቢኛለሽ"...እያለች እንባዋን ለቀቀችው።...እኔም ጨነቀኝ አብሪያት አለቀስኩ። እናቴ በእርግጥ ደሀ ነች...ግን ከሀብታም ልጅ የበለጠ አሞላቃ ነው ያሳደገችኝ።..እናቴ ሁሌም ትመክረኛለች እንጂ አትመታኝም...
ልክ እንደ ጓደኛዋ ታማክረኛለች። ሚስጥር የሚባሉ ነገሮችን ሁሉ ትነግረኛለች..የዛኔም ልጄ የሆኑ ቂሷዎችን ልንገርሽ ብላ ጀመረችልኝ..."ልጄ የሆነ ሠው ስለ ኢሥላም ግራ ገብቶት የሆነ ሼክ ጋር ይሄድና ሁለት ጥያቄ አለኝ ይላቸዋል...
ሼኩም "ጠይቅ አንተ ሠው በአቅሜ ልረዳህ ዝግጁ ነኝ።"ይሉታል
ሠውዬውም "ሴቶቻችሁ የሚሸፋፈኑት ለምንድነው?...የወንድን እጅሥ የማይጨብጡት ለምነው?"ብሎ ጠየቃቸው...
ሼኩም በተረጋጋና በሚገባው መልኩ ለማሥረዳት ሥለፈለጉ
"አንተ ወንድሜ ሁለት ከረሜላ አለህ አንዱ የተሸፈነ ሌላው ያልተሸፈነ ሁለቱንም አፈር ላይ ብጥለውና አንሥቼው ከሁለቱ ምረጥ ብልህ የቱን ትመርጣለህ?" አሉት...
ሠውዬውም"የተሸፈነውን ከረሜላ እመርጣለሁ አፈር ሥላልነካው" አላቸው...
ሼኩም "አየህ ሴት ልጅ ሥትገላለጥ ሁሉም ሠው ይከባታል...ክብሯን ለጊዜያዊ ደሥታ ታጣለች.. ከጊዜ በሁዋላ ግን ፈላጊ አይኗራትም ልክ ሣይሸፈን አፈር ላይ እንደወደቀው ከረሜላ....ውድ የሆኑ ነገሮች አልማዝን..ብረትን..ወርቅን ብናይ እንኳን ተሸፍነውና ተደብቀው ነው የሚገኙት..የሠው ልጅም እነሡን ለማግኘት በየፊናው ይኳትናል...ለኛ ሴቶቻችን አልማዞቻችን ናቸው በኒቃብ ተሸፍነው ክብራቸውን የሚጠብቁ"ብለው መለሡለት...
ሼኩም ትንፋሽ ወሠድ አረጉና"ሁለተኛው ጥያቄህ ደግሞ ለምን ሴቶቻችሁ ወንድን አይጨብጡም ነው...ወንድሜ የንግሥትን እጅ ለመሣም ከባሏና ከተከበሩ ሠዎች ውጭ ይፈቀድላቸዋልን? ብለው ሼኩ ጠየቁት...
ሠውዬውም" አይ ያ ሼክ አይፈቀድላቸውም"አለ...
ሼኩም"አየህ ወንድሜ ለኛም ሴቶቻችን ንግስቶቻችን ናቸው።..ከባሏና ከተፈቀደላቸው ዘመዶች በቀር ማንም አይጨብጣቸውም።" ብለው መለሡለት...ሠውየውም ተገርሞና ተደንቆ ሄደ።....እናቴ ታሪኩን እንደጨሰችልኝ ኡኡኡኡኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ብላ በረዥሙ ተነፈሰችና ጸጉሬን ትዳብሥልኝና ታሻሽልኝ ጀመር....እናቴ የነገረችኝ ታሪክ በደም ሥሬ ነበር የተሰራጨው ከዚያች ደቂቃ በሁላ ጅልባብ እንደማደርግና ወንድ እንደማልጨብጥ ለራሤ ቃል ገባሁ.......።......ዳግም ከወንድ ልጅ ጋር እንደማልታይም ለእናቴ ቃሌን ሠጥቼ አረጋጋዋት።.......

////////*********///////////

ፌቪ ሁሉን ነገር ዝም ብላ አይን አይኔን እያየች ካዳመጠችኝ በሁዋላ አብራኝ እያለቀሰች "እና አሁን ምን አሰብሽ?"አለችኝ... "እእእእእእእእእእ እኔንጃ ፌቪ
ይሄን ሁሉ ጊዜ በጉጉት ስጠብቀው የነበረን ነገር ባንዴ ይቅር ማለቱ ከብዶኛል.....
የማሚን ቃል መተውም ከብዶኛል።"....
ፌቪ እንደኔ ግራ ገብቷት "እእእእእእእእእእእእ" አለችኝ በድጋሜ....
"በቃ አልሄድማ" አልኳት ቢጃማዬን እየቀየርኩ...
"አሁን ምን ትይዋለሽ...ደሞ ትውጂው የለ"..አለችኝ
"አዎ ግን ከወንድ ልጅ ጋር ታይቼ ማሚ ከምትበሳጭ ቢቀር ይሻላል.. እያልኩኝ ሳለ ስልክ ተደወለ....ሁሲ ነበር...ወይኔ ጉዴ...

ይቀጥላል....
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

24 Sep, 19:30


​​​​🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌹ክፍል 4⃣

ድርሰት፦ በፍቅር ክሊኒክ
.
.
ትካሻዬን ይዘው ወደ እራሳቸው አዞሩኝና "ልጄ ነይ እኛ ጋር ተቀላቀይን" አሉኝ....የሁሲ እናት ነበሩ።አናቴን የሆነ ነገር የመታኝ ያህል ደነገጥኩ..እንደምንም እሺ አልኩና ሄድኩኝ..ሁሉም ማለት ይቻላል.. የሁሲ እናት፤ አባት ወንድሞቹ፤እህቶቹ.. ባጠቃላይ ሙሉ ቤተሰቡ እዛ ናቸው።የሁሲ እናት የልጇ ፍቅረኛ እንደሆንኩ ነው የምታውቀው።...የሆነ ቀን ፌቪን እያበሸቅኳት ሥንሄድ በአጋጣሚ የሁሲ እናት ፊት ለፊታችን ነበረች.. ተንኮለኛዋ ፌቪ ጉድሽን ለአማችሽ ነው የምነግርልሽ ስትለኝ..እየቀለደችና ከ ትልቅ ሰው ጋር የምትሳፍጥ ሰላልመሰለኝ.. ልብ አልሽ እስቲ አንቺ አይጥ ስላት ፍጥጥ ብላ ሄዳ አማችሽ እቺ ቆንጅዬ ናት።...የሁሲ ፍቅረኛ ናት ብላ አሳፍራኛላች። እናቱም የእውነት መስሏት ደስ አላት..ሁሌ ስታግኘኝ ፈገግ ብላ ሰላም ትለኛለች።..አዳራሹ ውስጥም ስታየኝ እሱን ለማስመርቅ እንደመጣሁ አውቃለች..ለዚያ ነው በትህትና ነይ ተቀላቀይን ያለችኝ..ያ ሳይበቃ "ነይ እዚህ ተቀመጭ" ብላ ተንሳችልኝ..በጣም ተሸማቀቅኩ...ልቤ ባፌ ልትወጣ ደረሰች።
እኔ እና እሱ ምንም የፍቅር ግኑኙነት ሳይኖረን ህዝቤ ሁሉ ሰምቷል።..ጉድ በል ጎንደር ትላለች አያቴ..እንደዚህ ነው......
'ኧረ በአላህ አይገባም ብዬ መሽኩርመም ጀመርኩ...ሁሲ ይሄን ሁሉ ጉዱን አላየም.. አክት ምናምን እያሳየ ነበር..የኔ ጀትሊ..

እምር ብሎበታል..በጣምም አልቦት ነበር።ዞር ብሎ ሲያይ እኔ ሆዬ ከቤተሰቡ ጋር ተሰልፍያለሁ.. ሆሆሆሆሆ ምን አይነት ፈጣጣና ደራቃ ናት ሳይል አልቀርም..

እንደምንም ፕሮግራሙ ሲያበቃ መድረክ ላይ ወጥቼ ስጦታዬን ማበርከት ሰለፈራሁ እስኪመጣ ጠብቄ ልሰጠው ስል እንደመቀማት በሚመስል መልኩ እንደ ሌባ መንትፎኝ አመሰግናለሁ እንኳን ሳይለኝ ሊሄድ ሲል...
እናቱ "ና እንጂ ልጄ ፎቶ ተነሱ" ብላ ይበልጥ ሀፍረቱን ጨመረችበት።.. እሱም ዘወር ብሎ ሳያይ እየተደናበረ "መጣሁ" ብሎ ጠፋ።..እኔ ግን ዉስጤ ተቃጠለ... ለምን አልናደድ...ለምንሥ አልቃጠል...
ሰወች ሁሉ በእሱ እያሙኝ ለምን ፍቅሩን አይነግረኝም?..አብዝቼ ተማረርኩ።..


እንዲህ እንዲህ እያለ ወራቶች ተቆጠሩ ሰሙ የእሱ ናት ከተባለ ድፍን 4 አመት ሆነን።..እኔ በብዙ ጎሩምሶች ብጠየቅም...ብዙ ወንዶች ቢያንዣብቡብኝም ለማንም ፊት አልሠጥም.. ምክንያቱም ሁሲን እወደዋለሁ።...
እሱም ሌላ ሴት አልያዘም....አይወደኝም እንዳልል አይኖቹ እንደሚወደኝ ይነግሩኛል........አንገርምም ሠው እንዴት ቅርብ ሆኖ እንዴት እንዲህ ይራራቃል..ሠው እንዴት እወድሻለሁ የምትለውን ቃል ከላንቃው ማላቀቅ አቅቶት ድፍን 4 አመት ሙሉ ፍቅሩን በልቡ አምቆ ብቻውን ይሠቃያል.......በአላህ ግን ከምን አይነት ደረቅ ሰው ነው እንዲህ አይነት ጥልቅ ፍቅር የያዘኝ.. በቅርቡ ጨርቄን ጥዬ እንደማብድ ሣይታለም የተፈታ ነው.......


አሁን አሁን እድሜዬም እየጨመረ ነገሮችን በሠከነ አእምሮዬ ማሰብ ጀምሬያለሁ...እንደ ድሮው ቀሚሥ መልበሥ አቁሜ በጅልባብ ውብ መሆንን መርጫለሁ። ቅርጽ የሚያወጡ ልብሶቼን የተለያየ ከለር ባላቸው ጅልባቦች ተክችያለሁ... በቅርቡ ኒቃብም አደርግ ይሆናል።.......ከወንድ ጋር መላፋትና አፍ ለአፍ ገጥሞ ማውራት አቁሜያለሁ..ወንድን ሠላም ብዬ በእጄ መጨበጥ ሁላ እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ..ቢሆንም የሁሲ ፍቅር በልቤ ውሥጥ እንዳለ ነው..ሁሲ በማይጠፋና በማይደበዝዝ ብእር እልቤ ላይ ተጽፏል።...

ዛሬ ከፌቪ ጋር 12 ሰአት ላይ ወክ ምናምን ለማድረግ አሥበናል።...በምሽት ሰለማይፈቀድልን ውሃ ልንቀዳ በሚል ሠበብ ከቤት ወጥተናል... ትንሽ አየር ከቀየርን በሁዋላ ዉሃ ቀድተን እየተመለስን ሳለ ሁሲ ወክ ሊያደርግ ከጓደኛው ጋር ሲመጣ አይን ላይን ተገጣጠምን.. "ሰሙ" አለ እንደመደንገጥ እያለ... 'እእእእእእእእ ሁሲ ሰላም ነው' አልኩት ተስፋ በቆረጠ ድምፅ... ሰላም ተባባልን ያው በኢስላም ከአባት፤ከወንድም፤ከአጎትና ከባል ውጪ በአጠቃላይ ሀጅነብይ ሊሆን ከሚችል ወንድ ጋር መጨባብጥ ሰለማይቻል በሩቁ ነው ሰላም የተባባልነው...
እኔን ሲያይ ከመደንገጡ የተነሳ ፌቪን ረሥቷቷል..ሰላም እንኳን አላላትም.....................'ሰላም በላት እንጂ' አልኩት.....ፌቪ ያን ተንከትካች ሳቋን ለቀቀችውና ሲበቃት እንደተናደደ ሠው ግንባሯን አጨማዳ"ኧረ ተይው አንቺ ካለሽ መች እኛ እንታየዋለን"አለች ደጋግማ...
እኔ እና ሁሲ ተያይተን ሳቅን.... ክክክክክክክክክ....ኪኪኪኪ..ካካካካካ...
የኔ ሳቅ ባሰ... የደስታ ሳቅ... የእልኽ ሳቅ...
"ከቻልሽ ነገ ብንገናኝ" ብሎ ከአፉ ይወጣዋል ብዬ ገምቼም አሥቤም የማላቀውን ጥያቄ አቀረበልኝ...'ከተመቸኝ እሞክራለሁ' ብዬው ተለያየን...እናንተዬ ምን ማለቱ ነው እንገናኝ ሲል..? ምን ሊለኝስ ይሆን..?

ይቀጥላል....
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

23 Sep, 07:50


የፍቅር ክሊኒክ

እንዳላጣህ ፈራሁ💖
══════❁✿❁ ══════

በልጅነት ግዜ ገና በለጋ እድሜ
በማልችለው አቅሜ በፍቅር ታምሜ
ሳይፈታ ሲቀር የልጅነት ህልሜ
እንዳልሆነ ሁኖ ተሰበረ ቅስሜ💔
ከኔ ወድያ አፍቃሪ ከሱ ወድያ ፍቅር
ቢፈለግ ቢታሰሰ ላይገኝ በምድር
~እኔም ከዛ ወድህ ብየ ነበርeko~
ፍቅር በሱ ይብቃኝ
ሌላም ሰው አይሻኝ
ብየ ነበር እኮ
~ግና አንተን ያየሁኝ ለት
ያሁሉ ጀግንነት ፉከራየ ቀረ
ከእንግድህ ሰው በቃኝ ብሎ እንዳልነበረ🤦‍♀
ልቤ ሰለ ፍቅርህ ማሰብ መጨነቅ ጀመረ
መክፈቻውን ቁልፉን በጅህ አስረከበ
የከሰመው ህይወቴ በፍቅርህ አበበ🤗
የታመመው ልቤ ባንተ አገገመ
መላው ሰውነቴ ፍቅርህ ታከመ
ታዳ ውደ
ያበበው ህይወቴን ፍሬውን ለማየት
እንዳላጣህ ፈራሁ እኔም የእዛን እለት💗
   ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌  ┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄



@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

20 Sep, 14:57


​​🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ

🌹 ክፍል 3

ድርሰት፦ በፍቅር ክሊኒክ ተዘጋጅቶ የቀረበ
.
.
.
ዞር ብዬ ሳይ ሁሲ ነበር...አቤት አልኩኝና ከመቀመጫዬ ተነሳሁ... የመግቢያ ካርድ ለመሥጠት እጁን እየዘረጋ.. "ከቻልሽ ብታስመርቂኝ".... አለኝ..
በጣም ደስ አለኝ.. ውስጤ ሲሥቅ ሲፍለቀለቅ ተሠማኝ..በሆዴ አግኝቼ ነው እያልኩኝ ለወጉ ያህል ግን..'ከተመቸኝ እሞክራለሁ' አልኩትና ተለያየን።

ለሁላችንም የጋበዘን መስሎኝ ሁሲን ለማስመረቅ ስንት ሰአት ላይ እንደምንሄድ ከጓደኞቼ ጋር ልወያይ ጠየቅኳቸው....።
እነሱን እንዳልጋበዛቸው ነግረውኝ እኔን ማብሸቅ ጀመሩ...ኧረ ባሉካ ኧረ ይመቻቹ... ቀሥ እያለ ደግሞ እራት ልጋብዝ ማለቱ አይቀርም...ይሄማ የሆነ ነገር አለ ምናምን ይላሉ። እኔ በውስጤ ምነው ባረገው እያልኩ እናንተ ደሞ 'ደሜን አታፍሉታ ብዬ ተነጫነጭኩባቸው..ምንቅርቅር አልኩባቸው።...

እቤት ገብቼ ለታላቅ እህቴ የሴት ጓደኛዬን ማስመረቅ እንደምፈልግ ነገርኳት።...እሷም ሳታቅማማ አሪፍ አበባ ገዝታ ፏፏፏፏ ብትን አርጋ ሸኘችኝ።..
ዋው በጣም አምሮብኛል! እንዲህ ሆኜ አይቶኝ ፍቅሩን ካልገለፀልኝማ እንዴት እንደምናደድ እፍፍፍፍፍፍ...

//////////////////

ለማንኛውም ጉዞ ወደ አዳራሽ ..ልክ ስደርስ በጣም ያስፈራል። የሰው አይን ድንብርብሬን አወጣው..የግርግሩን ብዛት ፈርቼ ወደ ጓደኞቼ ጋር ተመለስኩና አብረን እንድንሄድ ፎዚንና ፌቪን ጠየቅኳቸው... "አንሄድም እንዴት አንቺን ለይቶ ይጠራሻል ምንድነሽ አንቺ እያሉ ተንጫጩ...እነሱ እንደዛ ሲሉ ድል ያረኩ ያክል ኩራት ተሰማኝ..ይወደኛል ማለት ነው? አዎን ይወደኛል ግን ለምን አይነግረኝም...
እፍፍፍፍፍፍፍፍፍ እኔ ልንገረው? ሆሆሆሆሆሆ አላረገውም... ግን ጓደኞቼን ለምን አልጠራቸውም?
ለነገሩ ጋደኞቼ የሱም የጓደኞች ሰለሆኑ መጥራት ነበረበት ግን አላደረገውም....ለብቻዬ የሚነግረኝ ነገር ኑሮት ይሆን? ወደ አዳራሹ እየተመለሥኩ የማብሠለሥላቸው ጥያቄዎች ነበሩ።

///////////////////

..እጄን ይዞ ወደራሱ እያሥጠጋኝ..ሰሙ አላህ አደምን ለሃዋ እንደሠጠው ሁሉ ሁሉም ወንድ የራሱ ሀዋ አለችው..የኔ ሀዋ ደግሞ አንቺ ነሽ..ፈጣሪ እዚህች ምድር ላይ በሚፈቅድልኝ እድሜዬ ዘላለማዊ ፍቅርን ሳልሰሥት እሠጥሻለሁ..ለአንቺ ያለኝን ጥልቅ ሥሜት መግለፅ አልችልም ከአቅሜ በላይ ነው..ሠሙ በጣም አፈቅርሻለሁ..ብሎ አይን አይኔን ሲያየው..እኔም ይበልጥ ተለጥፌበት ባንተ ፍቅር ሥሰቃይ እንደከረምኩ አታውቅም..በጣም አፈቅርሃለሁ ብዬ እቅፍ አረኩት።...ቀሥ በቀሥ ሠውነታችን እየጋለ መጣ ሙቀት ያለው ትንፋሹ አንገቴ ላይ ሢያርፍ እሥከ ጥፍሬ ድረሥ አንዘፈዘፈኝ...ሌላ አለም ውሥጥ ገባሁ...ከንፈራችን መቼ እንደተገናኘ ባላውቅም ተላትሟል ...ሠሙ ሠሙ የሚል ድምጽ ሥሠማ ብርግግ አልኩ ለካ በህልሜ ነበር...ምናለ በህልሜ እንኳን ትንሽ ብመጠምጠው ብነክሠው..ሁሉ ነገሩን ብዳብሠው..ደግሜ ወደ ህልሜ መመለሥ ሁላ ተመኘሁ..እንደ ጁሊየት መሆንን ማን ይጠላል..ታይታኒክ ላይ እንዳለችው ሮዝ መሆንንሥ ማን የማይፈልግ አለ...ፍቅር እሥከ መቃብር ላይ እንደነበረችው ሠብልዬን መምሠልሥ ማን የማይመኝ አለ...ሁሉም ሠው በፍቅር መኖርን..በሚያፈቅሩት ሠው አፍ መቆለጳጰሥን ይፈልጋል...በፕሌን ይሁን በጀት እንደመጣሁ ባላውቅም አዳራሹ ጋር ደርሼ ነበር...ከህልሜም ያናጠበኝ የጓደኛዬ የቢኒ ጥሪ ነበር ፌዴራል ይጥራውና...
እዚያው እንደቆመ "ዋው ሰሙ አምሮብሻል!" አለኝ...
ዞር ብዬ ቀዮ 'ና'አልኩት ደስ እያለኝ..
"እእእእእእእ እንዴት ነው ባክሽ አምሮብሻል.."እያለ መጣ
"እ ባሉካን ልታስመርቂ ነው?" አለኝ እርግጠኛ ሆኖ...
'አንተ ደሞ የቱ ባሉካ ነው..' አልኩት ኮስተር ብዬ..
"የምናውቀው ነዋ እስከመቼ ነው ምደብቁት"አለኝ በተራው እንደመኮሳተር ብሎ..
እኔ በውስጤ ምነው ባረገልኝና ሀገር ሁሉ በሰማ እያልኩ.."ባክክህ ወፍ የለም ዝምብላቹ ነው ወሬ ምታባዙት.....'ባይሆን እንግባ'... አልኩት እንዲቀድመኝ እየጋበዝኩት። "እሺ"ብሎ ገባን.. አሁን ከቅድሙ ግርግሩ ቀንሷል... ሰውም ቦታ ቦታውን ይዟል..መድረኩ ድምቅምቅ ብሏል ድኩሬሽን በድኩሬሽን..ዲጄው ሙዚቃ ይመርጣል መድረክ አሥተዋዋቂው ወፈርና ጎርነን ባለ ድምጽ "እንኳን ደህና መጣችሁ" እያለ ይለፍፋል..እኔም ለመቀመጥና ክፍት ቦታ ለማግኘት በአይኔ እያማተርኩ ሳለ በድንገት ከሁላ በኩል የሆነ ለሥላሣ እጅ ትካሻዬን ሲይዘኝ ተሰማኝ...

ይቀጥላል....
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

18 Sep, 20:08


ሲወደኝ ስኮራ፤ ሲቀርበኝ ስርቀው
ክብር እየሰጠኝ፤ ደርሼ ስንቀው😔
ሳጠፋ ታግሶ፤ ሳኮርፍም አባብሎ
እኔን አስቀድሞ፤ እንዳልሽ ይሁን ብሎ😊

            ሁኖልኝ ሳለ አልጋ
               ስሆንበት ቀጋ😕
ደከመው መሰለኝ ብዙ መታገሱ
ታከተው መሰለኝ ጥፍቴን ማበሱ
የለም ጠፍቶብኛል ካየሁት ሰንብቷል
ስልኩንም ሞከርኩኝ፤አይሰራም ተዘግቷል🤦‍♀
        እንጃ ውስጤ ሰግቷል😔
ምናልባት እናንተ ድንገት ካያቹህት
አደራ አደራ ይህንን ንገሩት‼️🙏❤️

"እያለህ ያልታያት የሰጠሀት መውደድ
ስትሄድ ገብቶታል ስትጀምር መንገድ!
አራቅ'ክ እንደሆነ ልብህ አልቆረጠህ
ተመለስ ልካስህ_ካንተ በበለጠ
ብላለች በሉልኝ ካያቹህት ድንገት🙏
አደራ ንገሩት ካሁኑ አቅቶኛል
ያለሱ መኖሩ ዳገት ሆኖብኛል!🥺

🪴🌹አሁኑኑ ሼር አድርጉ 🌹🪴
@yefikrclinic
   

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

17 Sep, 18:14


​​🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌹 ክፍል 2

ድርሰት፦ በፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
.....ሁሲ መጣና ሁሉንም ሠላም ብሎ እኔ ጋር ሲደርሥ ተፋፈርን የኔንማ ተውት ልቤ እንደከበሮ
ይደልቃል የሞት ሞታችንን ሠላም ተባባልን... ሠፈር ውስጥ ጭቃ እያቦካን እንዳለደግን...ካደግን በሁላ እራሡ ሥንት አመት ሙሉ እንዳልተላፋን እንዳልተደባደብን እንዲህ ለሠላምታ መንቀጥቀጥ ምን ይሉታል ይሄን...ይባሥ ብሎ ...
"ሰሙ በጣም አምሮብሻል"....አለኝ... እናንተዬ ቅልጥ አልኩላችሁ ሙቀት በሙቀት ሆንኵላችሁኮ ፈራረሥኩላችሁ።..ደሞኮ ሥሜን አቆማጠለው...
አንገቴን ደፍቼ እየተሽኮረመምኩ ለራሤ በሚመሥል ድምጽ 'አይደል'የምትል ቃልን ተነፈሥኩ...ኡኡህ..ኡህህ...
ሁኔታችንን ሥትከታተል የነበረችው ተንኮለኛዋ ፌቪ ተንከትክታ ሥትሥቅ ሁለታችንም ተሸማቀቅን..

ፌቪ ግዜ ሳታጠፋ "ሠዎች ዛሬ የመጀመሪያ ቀን ሥለሆነ ትምህርት ብዙም አይኖርም..ለምን ካፌ ገብተን ረፈድፈድ ሲል አንሄድም"ብላ ሃሣብ አቀረበች...ሁሉም ሲስማሙ እኔ አንገራገርኩ..ምንም ማድረግ ስላልቻልኩ አብሬ ሄድኩ። ፌቪ እንዲሁ እኛን እያየች ሙድ ሥትይዝና ሥትደበርብን አረፈደች...3 : 30 ሲል ከካፌው ወጥተን መሄድ ጀመርን...ጅማ ደማምቃለች እምር ሽብርቅ ብላለች። ሠው ይተረማመሣል...ጫት ነጋዴዎች ተኮልኩለው እንደጉድ ይቸበችቡታል።.. እንግዲህ ቁርስ ተበልቶ የጀበና መሆኑ ነው...ጫት ለመግዛት የሚተረማመሠውን ህዝብ ሣይ በጣም አዘንኩ...ሠው እንዴት መርዝን ተጋፍቶና ተሻምቶ ይሸምታል..ህጻኑ፤ወጣቱ፣አዛውንቱ፤ባለትዳሩ ሁለም ይሯሯጣል... ይሄኔ ቤቱኮ ልጅና ሚሥቱ በቀን ሶሥት ጊዜ አይመገቡም....ይሄኔኮ ለጨቅላ ህጻን ልጁ የወተት መግዣ አጥቶ እያሥለቀሠው ይሆናል...ይሄ መርዝ ተክል ብዙ መዘዞች አሉት...ሲጃራ ማጨሥ...ሺሻ ማጨሥ የሚለመዱት ከዚሁ ከጫት ጋር ነው...አለፍ ሢባል ደግሞ ምርቃና መሥበሪያ በሚል ወደ መሽታ ቤቶች ጎራ መባሉ አይቀርም... ቡጊ..ቡጊ..እእ..አያችሁት ሥንት ነገር እንደሚያበላሽ ጤናችን፤ኢኮኖሚያችን፤ቤተሥብና ትዳራችን ሁሉም ላይ ጥላሸት ይቀባል።...እየሄድኵ በውስጤ ያብላላሁት ሃሣብ ነበር...
ድንገት ሣላሥበው ጮክ ብዬ 'ምድረ ጫታም ሁላ ምንድነው እንዲህ እንደ ፍየል ማመንዠግ'..አልኩኝ...

ጓደኞቼ ዘወር ብለው ሢያፈጡብኝ
ድንግጥ ብዬ አይገርሙም አልኳቸው...

/////////// //////////#///////

ጊንቢ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ደርሰናል ማሜና ሁሲ 8ተኛ ክፍል ሥለሆኑ ቻው ብለው ተለዩን...ፎዚ፤ፌቪ፤ቢኒና እኔ አንድ ክፍል ሥለሆንን አብረን ሄድን። ግን ሃሣቤ ሁሲ ጋር ሄዷል...ልቤ 8ተኛ "ለ" ክፍል ጠቅልሎ ገብቷል...

ውሎ ሲያድር ግን ወሬ መናፈሥ ጀመረ..ታውቁት የለ ሃበሻን ትንሽ የወሬ ጫፍ ከያዘ ይተረትረዋል..ወሬው በሠአታት አረብ ሀገር፤ አሜሪካ፤አውሮፓ የማይደርሥበት የአለም ክፍል የለም..እኛ ቁጭ ብለን ወሬ በምንፈትልበት ሠአት ግን ቻይና 100,000 መኪና እንደምታመርት ቁባ የለንም።..
እና እኔንም ፍቅር ምን እንደሆን በማላውቅበት ወቅት ነበር ጓደኞቼ በሁሲ የሚጠረጥሩኝ... ገና በ13 አመት እድሜዬ... አይገርሙም ሆሆሆ...እርግጥ ነው ለሱ ጥሩ ሥሜት አለኝ ግን ሥሜቱ ፍቅር ይሁን ምን ይሁን ለኔ እራሱ ግልጽ አይደለም።..

...ከዛም አልፈው ሁሲን በኔ ስም መጥራት ጀምረዋል..እሱ ለነገሩ በኔ ስም ሲጠራ በጣም ነበር ደስ የሚለው።
ብዙ ጓደኞቹ ሲያበሽቁት S ይሉታል..ይሁን እንጂ እሱ በጣም ደስ ይለዋል።

እሥካሁን ግን አይን ላይን ከመተያየት ያለፈ ስለፍቅር አውርተን አናውቅም...አሁን አሁንማ እድሜዬ እየጨመረ ፍቅሩ እየናረብኝ እያቅበጠበጠኝ ነው..አናቴ ላይ ሳይወጣ መጥቶ እንደ ቻንድራ ሊያቅፈኝ ይገባል!! ይሄ ፈሪ...

እንዲህ እንዲህ እያልን እኔ 16 አመት ሆነኝ እሱም 18 ሆኖታል..ይሄው ዛሬም ፍቅሩን አምቆ ይዞታል።..ይሄ ቋጣሪ...እንደው መቃጠል ነው ወዳጆቼ...
ግን ሰፈር ላይ በተገናኘን ቁጥር እየተደናበረ ያናግረኛል..ለሰላምታኮ ነው የሚደናበረው ይሄ ደንባራ።....

////// ////// ////////////

ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው ምክንያቱም እኛ ሰፈር የማርሻል አርት ቴኳንዶ የምርቃት ልዩ ዝግጅት አለ።.. በዛ ላይ ሁሲ ተመራቂ ነው ደሥ አይልም?.......

ሁሲ ህዝብ በተሰበሰበበት መድረክ ላይ ወጥቶ ሲንጎራደድ.. ተመልካች ሲያጨበጭብለት በሀሣቤ እየሣልኩኝ እፍለቀለቃለሁ....ለምን ታዲያ ትራምፕን አጠብሺም መድረክና ጭብጨባ ካማረሽ እንዳትሉኝ.. የኔ ትራምፕ ሁሲ ነው።..........
ቀኑ እሁድ ነው ከጓደኞቼ ጋር ሰብሰብ ብለን ቁጭ ብለናል።.. ደሥ የሚለው እኔ እና ሁሲን አንድ የሚያረገን ነገር የሁለታችንም ጓደኞች አንድ መሆናቸው ነው...ሁሉም የሚፈልጉት አንድ ላይ እንድንሆን ነው።... እናም ቁጭ ብለን ሳለ ሰሙ የሚል መረዋ የሆነ ድምፅ በጆሮዬ ጥልቅ አለ...ዞር ሥል........

ይቀጥላል....

@yefikrclinic ይቀላቀሉን

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

16 Sep, 17:04


​​🔥 ሳገባህ ላፍቅርህ 📖

🌷 ክፍል 1⃣

ድርሰት፦ በፍቅር ክሊኒክ ተዘጋጅቶ የቀረበ
.
.
.
ይሄ ታሪክ 70%ቱ እውነተኛ ሲሆን ቀሪው 30%ቱን ደግሞ በታሪኩ ላይ የተመሠረተ ልብ_ወለድ አድርጌዋለሁ.........
♦️
♦️
♦️
♦️

....ጊዜው 2002 መሥከረም 8 ነው...የክረምቱ ወራት አልቆ... ጭጋጋማው ወራት ተገፎ.. ሠማዩ የጠራበት፤ደመናው ቦታውን ለጸሀይ ያሥረከበበት ፤ አደይ አበባ በየቦታው የፈኩበት፤ ሠዎች ከካፓርትና ጃኬት ተላቀው በነጻነት የሚራመዱበት፤ ሴቶች ጸጉራቸው ከፌሥታል ተገላግሎ ዘንፈል ዘንፈል እያለ ነጻነት የሚያውጅበት፤ አካላቸው ከሚደራርቡት ልብሥ ኡፈይ ብሎ ቅርጻቸው የሚታይበት..ዳሌያቸው ተጋልጦ ምራቅ የሚያሥውጥበት፤ በአጠቃላይ ቆንጆ ሆነው የሚወጡበት ነው.. ለኛ ለተማሪዎች ደግሞ የናፈቁን ጓደኞቻችንን የምናገኝበት..ካለ ጭንቅ ያጣጣምናቸውን ሁለት ወሮች እያሠብን ውይ አሁንሥ እንደው ብለን የምናማርበት ነው።


.....ሠሚራ እባላለሁ..ውልደቴና እድገቴ ጅማ በጊንቤ ቀበሌ ነው።....ጌንቤ በአጋሮ እና ጅማ መካከል የምትገኝ ትንሽዬ ቀበሌ ነች.... ብዙዎቹ በፍራፍሬና በቡና ምርቷ ያውቋታል....
ህይወቴን የምመራው እናትም አባትም ሆና ካሳደገችኝ ከብርቅዬዋ እናቴ፤ ከሁለት እህቶቼና ከመንትያው ወንድሜ ጋር ነው።..... እኔና ጓደኞቼ ከትምህርት ቤት መልስ ቤተሰባችንን የምናግዘው መክንተራ አከባቢ ፍራፍሬ በመሸጥ ሲሆን... በዚህም ምክንያት ጓደኝነታችን እንደ ብረት የጠነከረ ነው...
.....የ7ተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ ቲሽ አንቺ ጩጬ ልትሉ ነው አይደል...ሁልሽም ከሁዋላ ብታዪኝ ኖሮ ግን ምራቅሽን ትውጪ ነበር...እኔ ማለት ጠይም መካከለኛ ቁመት ያለኝ ከዳሌዬ ወጣ ብዬ ከወገቤ ቀጠን ያልኩ ወንዶች ሁላ ለሃጫቸውን እያዝረኵረኩ የሚከተሉኝ አንድ ፍሬ ልጅ ነኝ..በሠአቱ የጎመራሁ እንቡጥ ጽጌሬዳ... ጅማ ላይ እትብቴ ተቀብሮ ጅማ ላይ ያደግኲ የአባ ጅፋር ልጅ ነኝ..አቤት መንሠፍሠፍ አንቺን ነበር ቅርጥፍጥፍ አርጎ መብላት ትሉ ይሆናል.. እኔ ግን አልሠማችሁም ወሥዳችሁ ለመሮጥ አይደል
ማንንም አልሠማም.. በባህሪዬ ተጨዋችና ሣቂታ ነኝ።..
ዛሬ ለየት ባለ ሁኔታ በጠዋት ተንሥቼ ሽር ጉድ እያልኩ እራሤን እያሽሞነሞንኩ ነው...መሥታወት ጋር እያወራሁ ነው በሜይካፓቼ....
ከ20 ደቂቃ መበጃጀት በሁላ ዛሬ ቂጤን ቡዳ እንዳይበላው እያልኩ ድምቅ ብዬ ከቤቴ ወጣሁ..ለምን አትሉኝም ትምህርት ልንጀምር ነው.. የሠፈርም የትምሮ ቤትም ጓደኞቼን የተለመደው ቦታ ቀድሜ ሥለደረሥኩ መጠበቅ ጀመርኩ።..

//////////////////////


በነገራችን ላይ ጓደኞቼ 5 ናቸው እሥከኔ 6 ማለት ነው..ሶስት ወንድ ሶስት ሴት..ሃሃሃሃ ተጣምራችሁዋላ..ይሄ ምን ጓደኝነት ነው ፍቅረኞች ሆናችሁዋል እንጂ አላችሁ አይደል..ሃሚተኞች!! ሃበሻ እንደሆንን ነጋር ማጣመም ላይ ተክነንበታል..ግን ወፍ የለም ንጹህ ጓደኛሞች ብቻ ነን..እሥኪ እሥከሚመጡ እኔም ከሚደብረኝ አንድ ባንድ ላሥተዋውቃችሁ...
ከሴቶቹ ልጀምር ፎዚ ዝምተኛና የጥቁር ቆንጆ ሥትሆን ልክ እንደ ፕሮፌሰር መነጽር ታዘወትራለች። ቀለሜም ናት..ፌቪ ቀይ የደም ግባት ያላትና ቀውጢ ፎጋሪ ናት...ለኔም ከሁሉም ይበልጥ ትቀርበኛለች...የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ነን ማለት ይቀላል።..
ከወንዶቹ ደግሞ ቢኒ በጠይምና በቀይ መካከል ያለ የፊት መልክ ያለው ሲሆን.. ቀጠንና ረዘም ያለ ነው..ሌላው መሀመድ ነው ቸንኮሌት ከለር ያለው፤ወፈር ያለና ተጫዋች ነው...የመጨረሻው እንግዲህ ሁሴን ነው..ቀላ ብሎ ረዘም ያለ...የተረጋጋና ዝምተኛ ሢሆን ሢናገር ቁጡብ ነው። ሲራመድ ታዋቂ አርቲሥት ይመሥላል.. የዛኔ ቃና ቲቪ ባይኖርም አሁን ላይ ሥገልጸው ግን ማነው ጠፋኝ!! ያ አክተር የዛራ አፍቃሪ ቻንድራራራ.... አረማመዱን ሣይ ቻንድራ.. ቁመቱን ሳይ ኩዚ... ወቼው ጒድ ይሄ ቃናኮ ሊያሣብደን ነው አሁንሥ.. ወደው ነው እንዴ ምን ትውልድ አለና ሴቱ በቃና ወንዱ በምርቃና ተይዞ ብለው የተረቱብን ...አሁን አሁንማ ናሆ፤ጄቲቪ፤ኢቢኤሥና የመሣሠሉትን ሥርጭቶች የሚመሩት ጋዜጠኞች እዚያ የማይልቅ ማሥታወቂያ ለቀው ቁጭ ብለው ቃናን እያዩ ተመስጠው ውሥጤ ነው ሢሉ እንደነበር አፈትላኪ ወሬዎች ይናገራሉ..ዘንድሮ ወሬ አይደበቅ...ብዙ ለፈለፍኩባችሁ አይደል እንዲህ ነኝ እንግዲህ ከጃመርኩ አላቆምም መተርተር ነው ምናባቱ...አሁን ጓደኞቼ እየተንጠባጠቡ በየተራ እየመጡ ነው..ፎዚ...ፌቪ...ቢኒና መሀመድ..ሁሉም ጋር ሞቅ ያለ ሠላምታ ተሠጣጠን...ግን አንድ ሠው ጎሏል።በጣም ቅር አለኝ የኔዋ ቻንድራ ጎሏል...የኔዋ ኩዚ አልመጣም። በሃሣብ እንደተዋጥኩ

"ሁሲ እየመጣሁ ነው ብሎ ደውሎልኛል።" መሀመድ ነበር የተናገረው...
ይሄን ሥሠማ ውስጤ በሃሤት ተሞላች...
ከትንሽ ደቂቃ ጥበቃ በሁዋላ ሁሲ ሲመጣ ተመለከትኩ.. ድንብርብሬ ወጣ..ውስጤ እርብሽብሽ ሢልብኝ ይሠማኛል።..ጓደኞቼ እንዳያውቁብኝ እየተጠነቀቅኩ 'ሁሲ መጣ'አልኩኝ....ውይ እናንተዬ ምን እየሆንኩ ነው ግን እንዲህ ያለ ሥሜት መሠማት የጀመረኝ በቅርቡ ነው...
.
. ክፍል 2 ይቀጥላል....

@yefikrclinic ይቀላቀሉን

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

16 Sep, 16:38


😔ምን ነካኝ🤷‍♀

ምን ነካው ይህ ልቤ ባንተ የወደቀ
ለምን ይሆን ከቶ ያየህ እንደ ነፍሴ
በስምህ የሚምል ምን ነካው ምላሴ

በህልም አለምቀምሶህ በተግባር የፆመ በሌላ አንተንነትህ ፍቅርን ያጣጣመ ምን ነካው ከንፈሬ አንተን እየሰበ እራሱን የሳመ😏

መን ነካው አይኔንስ😳 ባለመደው ሰው ላይ እንዲህ ያፈጠጠ ነፍስህን ለማየት እንዲህ የቋመጠ፣
እስኪ ለምን ይሆን ጊዜው የረዘመ የሚሬጠው ሰዓት ስቀጥርህ የቆመ😢

እንደው ምን ነክቶኝ ነው እንዲያ ተጨንቄ እንደዛ ቀጥሬ እየተብረከረከ አልሄድ ያለኝ እግሬ ምንድነው ያረከኝ ንገረኝ በሞቴ
ሴታሴትነቴ የት ሄደ ኩራቴ 😔

#ያድ
🌸🌺🌸🌸🌺🌸🌺🌸🌺 🌺
🌷❤️🌷❤️🌷❤️🌷❤️🌷❤️

💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

16 Aug, 19:50


🫧 የእናቴ ልጅ 🫧

  ✧ ክፍል ሰላሣ ሁለት ✧
👁👁የመጨረሻ👁👁

🌷
.
.
,.

ቀን ቀንን እየተካ በሄደ ቁጥር በወንድሜ ላይ የነበረኝ የመረረ ጥላቻ እና ቂም እየደበዘዘ ሲመጣ ይታወቀኛል  ይህን ስሜት ወደድኩት ምክንያቱም እኔ ቂመኝነት በውስጤ ሰርፆ ቤቱን እንዲሰራብኝ የምፈልግ ሰው አይደለውም ። መጥፎ እና ልክ ያልሆኑ ጉዳዮች ጭንቅላቴ ውስጥ ጊዜ ወስደው በቁዩ ቁጥር እታመማለው ፡መረጋጋት አልችልም ። ያንን ስሜት ለማስታገስ ስል ነውጠኛ ነው የምሆነው ፡ከዚበፊት የእናቴን ጥላቻ እና የሰፈሬን ሰው ግልምጫ ለመወጣት ስል ንዴቴን ካገኘውት ሰው ጋር ሁሉ ነገር ፈልጌ እጣላ ነበር ። አሁን ላይ ከጉርምስናውም እየወጣው ነው እና ያ ስሜት እንዲቆጣጠረኝ አልፈልግም ። ስለዚ በወንድሜላይ ያለኝ ብስጭት እየቀነሰልኝ ሲመጣ ተጠቃሚ ነኝና ደስታ እየተሰማኝ ነው ። እሱ በሰው አገር ላይ ምን እያሳለፈ እንዳለ የምናውቀው ነገር የለም ። ሲዊዲን መድረሱን ከተቀባዮቹ ጋር ሆኖ ለእናቴ ደውሎ ከነገራት በዋላ ።ድጋሚ ደውሎም አያውቅም ። እናቴም ብትሆን ጨከን ብላበታለች ። 'ከአሁን በዋላ ቤተሰብ አለኝ ብለህ ወደእኛ እንዳታስብ 'ብላ እንደተናገረቸው አባቴ ነግሮኛል ። በእርግጥ ምንእንደሚሰማት  እሷው ነው የምታውቀው ።የእናት አንጀት እንዲ በቀላሉ ይቆርጣል ማለት ዘበት ነው ። አባታችንም ቢሆን ስሙን ለማንሳት ድፍረቱ ባይኖረውም አንዳንዴ በጨዋታችን መሃል ተክዞ ተክዞ በረጅሙ ሲተነፍስ አጋጥሞኛል ።ምን አልባት ስለ አቤል እያሰበ ይሆናል ብዬ እጠረጥራለው  ።
እኔ እራሱ ሳስበው ለአቤል እንዲመሆን ጥፋተኛው ማነው ? ብዬ አስባለው ። ያለ አባት አድገናል ፣እናታችን የሌለ አቅርባው አቅብጣውም ነበር ። የራሱስ አስተዋፆ ? እኔስ ብሆን ጥፋቶቹን በኔ ሲያላክክ የረዘመ ዝምታ አሳይቼስ አልነበረ ? ብቻ አንዳንዴ ሳስበው አቤል እንዲ እንዲሆን ትንሽ አስተዋፅዖ ሳይኖረን አይቀርም እላለው !!!!
🍑እሁድ ቀን  ተሰብስበን እንደተለመደው እየተጨዋወትን ፡ ቤቱን ሞቅ ደመቅ አድርገነዋል ፣ አባታችን እናቴን እየቀለደባት ያስቀናል ማማ በእናቴ ዙሪያ እየዞረች ባልገባት ነገር ትፈነድቃለች የኛ ሳቅ ሳይጋባባት አይቀርም ፣ እናቴ  ስለተሳቀባት አልከፋትም በጣም ደስተኛ ትመስላለች በባሏ ጎኗ መሆን ሙሉነት ሳይሰማት አይቀርም ልዩ ሆናለች ፡ በዛላይ ትላንትና የማማን እናት በማግኘቷ እፎይታ ተሰምቷታል ፡ የአቤልን ትልቅ ስህተት እንዳረመች ሳይሰማት አይቀርም ፡ የማማን እናት ይዛት መጥታ በማንኛውም ሰአት ልጇን የማየት መብት እንዳላት ነግራ ፡ ነገር ግን እፃኗ ከኛጋር መኖር እንዳለባት አስረግጣ አስረድታታለች እሷም ብትሆን ለልጇ ያን ያክል የምትጓጓ መስላ አልታየችም ።እንዲ መሆኑን የፈለገች ነው የምትመስለው ይሄ በራሱ ለኔም እንደ ግልግል ነው ።በአራስነቷ የተረከብኳትን ስንት ነገር ያየውባትን ልጅ ልውሰድ ብትል ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ።  ማማ ለኔ ትምህርት ቤቴ ናት በሷ የተነሳ እራሴን ገዝቻለው  ስለ ዓለም ክፋት ደግነት አይቻለው  ማጣት ምን ያክል እንደሚፈትን ገብቶኛል ። ብቻ ብዙ ብዙ ,,,,,
ዛሬ ላይ ግን በዛ ሂደት ውስጥ ስንት የምወዳቸውን ሰው አውቄ አለው ።ለየት ባለ መልኩ ባዩሽን የክፉ ቀኔ ። ብሌኔን ፍቅሬን የወደፊት ሚስቴ የአይኔን ማረፊያ ፡የልብ ምቴ የሕይወቴ ቅመም ማጣፈጫዬን ፡ ብሌኔ ውዴን ብሌኔ ብሌኔ ፡ስሟን እንኳ ስጠራው የሆነ መሃዛ ከአፌ ወጥቶ አብሮ ያውደኛል  ብሌኔ ብሌኔ ......
እረፋዱ ላይ አንዳችን በአንዳች እየሳቅን ጨወታችን ደርቶ ፡  ሳለ የእናቴ ስልክ ጮኽች ።እናቴ እንደሌላው ጊዜ አልፈጠነችም ታነሳዋለች ብለን ስንጠብቅ ፡ወደኛ ማየት ሆነ ። ስትዘገይብኝ ስልኳን አንስቼ ቁጥሩን አየውት የውጪ ለጠ ር ነው ደንገጥ አልኩ ። እናቴ በፍርሃት ስታየኝ
"የውጪ ስልክ ነው አንሺው አልኳት "
"አንተአንሳው "አለች እንደፈራች ስለገባኝ ፡ እኔው አነሳሁት
"ሄሎ "
"ሄሎ የወይዘሮ ዘውድነሽ ስልክ አይደለም "አለኝ የሴት ድምፅ ድንጋጤዬ ጨመረ አቤል ምን ሆኖ ነው
"ነው ማን ልበል አንቺን"አልኳት
"ዲና እባላለው እእ ከሲዊዲን ነው የምደውለው "አለች
"እሺ ምምን የየተፈጠረ ችግር አለ ወንድሜ ምን ሆኖ ነው "አልኳት እየተርበተበትኩ ።እናቴ ስታቃስት ሰማው ዞሬ ሳይ ዕንባዋ ቀድሟል ።
"ኧረ ተረጋጋ እሱ ምንም አልሆነም እኔ ፍቅረኛው ነኝ ያው ብቻ ስለ እናንተ ብዙጊዜ ያወራኛል እና ዛሬ አበረታትቼው አብረን እናወራቸዋለን ብዬ ነው በስንት መከራ የደወልኩት "አለች ፈጠን ፈጠን ብላ
"ድምፁን መስማት እንችላለን "አልኳት
"አዎ እባክህ አንተ ወንድሙ ከሆንክ በጣም ተፀፅቷል እና ይቅር በለው  "አለች
"ችግር የለም ይቅር ብዬዋለው አጠገብሽ ካለ ስልኩን ለሱ ስጪው እናቱን ያናግራት "አልኳት
"እሺ "ብላ ስታስተላልፍ እኔም ስልኩን ለእናቴ ሰጠዋት ።እናቴ ልትደብቀው የማትችለው የልጇ ፍቅር ገንፍሎ ወጣ ፡ በቃ ከአቤል ጋር በናፍቆት አወሩ በተደጋጋሚ ይቅር በይኝ ሲላት ይሰማል ልቡ የተሰበረ ይመስላል ፡ ከአባታችንም ጋር አወራ ፡አባታችንም አለቀሰ ፡ብዙ ነገር ተናገረው እንደዚ አይነት ክፋት ከገዛ ልጁ ስላልጠበቀ እስካሁንም ድረስ እየተሰቃየ እንደሆነ ነገረው አቤል ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ ይሰማል ፡ጓደኛው ነኝ ያለችው ሴት ታባብለዋለች ፡ላውድ አድርገነው ስለሆነ የምናዳምጠው ፡አክስቴ ደግነሽም ባዩሽም ማልቀሳቸው አልቀረም ፡ አክስቴ ደግነሽ ወደኔ እያየች "ይቅር በለው ልጅነት ነው አውሬ ያደረገው "አለችኝ ሆደባሻነቷ አይሎ ፡  እኔ ውስጤ ተረጋግቷል ሞተ የምባል መስሎኝ ስለነበር ክፉ ነገር ስላልሰማው ሰላም ሰፍኖብኛል ። ዓለም እንግዴ እንደዚ ናት እንደ ዥዋዥዌ ነው ነገሯ ወደዚ ወደዚያ ፣ እንደ ፈለገች አንተ ጠንክረ ገመዷን ይዘህ እየተቆጣጠርክ ካልተጫወጥክ ፈንግላ ልትጥልህ ትችላለች ፡ እራስህን ከማንም ጋር ሳታወዳድር የማንንም ንዋይ ሳትመኝ የሕይወት መንገድህን በራስህ በንፁ ሕሊናህ ታግዘህ አስምር መስመሩ ሲበላሽ በትህግስት እያስተካከልክ  ወደፊት ቀጥል ። ለሌሎች የደስታ የሰላም ምንጭ እንጂ ፣የስቃይ የመከራ ምንጭ አትሁን ፣ አንተ ደስተኛ የምትሆነው በዙሪያህ ደስተኞች ሲኖሩነው ፡ 'ብቻህን በሚያለቅሱ ሰዎች መሃል ብትስቅ እብድ ነው የምትባለው'
             ,
                 👁ተፈፀመ👁
@yefikrclinic

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

13 Aug, 20:20


🫧 የእናቴ ልጅ 🫧

  ✧ ክፍል ሰላሣ ሁለት ✧
👁👁የመጨረሻ👁👁

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ 🌷

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

09 Aug, 19:05


የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል ሠላሳ አንድ ✧

.
.
ከባባድ የሚባሉ ጉዳዮችን አለፌለው ነገሮችን ሲናገሩት እንደሚቀሉ ሆነው አታገኛቸውም ፡በውስጡ ማለፍ እንደመናገር ላይሆን ይችላል ፡ ነገር ግን ምን አማራጭ አለህ ፡ አልችልም አልቻልኩም ካልክ ፡ አይምሮህ በራሱ ጠላት ነው የሚሆንብህ ።
አልቻልኩም ስትለው አዎ አትችልም የሚለውን አሳብ ወስዶ ይደጋግመዋል ፡ ይበልጥ እንዳትችል ያደርግሃል። ለራስህ መንገር ያለብህ ይሄ ጉዳይ ከባድ ነው ነገርግን ፡ እወጣዋለው !በየቀኑ የመጣብኝን ችግር ለመቅረፍ አእሰራለው እታገላለው ፡ እናም ደሞ ቀስ በቀስ አሸንፈዋለው ማለት መቻል አለብህ።
    እውነት ለመናገር አልችልም አይሆንልኝም ብትልስ ቁጭብለህ አደጋዎችን ከማስተናገድ ውጪ ምን ታመጣለህ ?ምንም ! ከዛ ይልቅ እየተንቀሳቀስክ እየታገልክ በሕይወት ጎዳና ላይ  ወደፊት ብትራመድ አይሻልም።  በነገራችን ላይ ፈጣሪም በኑሮህ በግንኙነቶችህ ላይ ለውጥ እንዲመጣ እየጣርክ ስትፀልይ ነው የሚሰማህ ።
🍀ከነገሮች ማለፍ በዋላ ዛሬ ሁላችንም እንደ ቤተሰብ ተሰብስበናል ።ቤተሰቦቼ ተሟልተዋል ማለት ይቻላል ፡እናትና አባቴ ፣አክስቴ ደግነሽ እና ፡ በችግሬ ወቅት ያገኘዋት የእናት ያህል የማያት ባዩሽ ፣  ትንሿ  ማማ ፣ሁሉም ተሰብስበው ቡና እየተፈላ ምግብ ቀርቦ እየበላን ንፁ የሆነ ጨዋታ እየተጫወትን ቅዳሜን ቀን በጥሩ መንፈስ ጀምረነዋል ፡ እንዲ አይነት የተረጋጋ ቤተሰባዊ ግንኙነት መፍጠር ቀላል አይደለም ፡ ሰላም እና ጤና ያለው ደስተኛ ቤተሰብ  ያለው ሰው እሱን መቼም እንዳይበረዝ መንከባከብ አለበት ፡ ምክንያቱም  የአገር ሰላም እራሱ የሚጀምረው ከቤት ነው ፡ ቤት የተሰራነገር ነው አንዳንዴ  ወደውጭ ወጥቶ ፡ ማህበረሰቡን ብሎም አገርን የሚረብሸው ።
እናም ለቤተሰብህ የምትሰጠውን ትኩረት ከልብህ አድርገው  እልሃለው
አቤልን በሰው ሀገር ሕይወት የራሷን ምክር ትስጠው ብለን ትተነዋል  ።እናም የማማን እናት ጭምር እናቴ እያፈላለገቻት ነው ።እናቴ እሷም ወዳ አይደለም ልጇን እኛላይ እንድትጥል የሆነችው ።አቤል ነው አላፊነቱን መውሰድ ያለበት የሚል አሳብ አምጥታለች ።እኔም ብሆን ነገሩን በተረጋጋ መንፈስ ሳስበው ልክ ናት ፡ ለዚሁሉ ጥፋት መነሻ አቤል ነው ። እሱው ነው መቀጣት ያለበት ያቺ ሴት ከልጇ ጋር የሚገባትን ቦታ እንሰጣታለን ብዬ እኔም በእናቴ ውሳኔ ተስማማው.....

ይቀጥላል........
@yefikrclinic