ያን ሰሞን •••
ቀርበህ ስታወራኝ በጨዋታ በቀልድ
ከብሶት ወጥቼ ከድብርቱ መንገድ
ሀሳብ የለሽ ሁኜ ስቂያለሁ ከልቤ
የደስታን ቡልኮ ካካሌ ደርቤ
ያን ሰሞን ••• 🌹
ለኔ ያለህ ክብር ፍፁም ትህትና
የጨዋነት ለዛህ ላየህ ስታስቀና
በማሰብም ሆነ ወዲህ በመጨነቅ
አቻህም አልነበር ጎኔን በመጠየቅ
ያን ሰሞን •••• 🌹
ፅዶች ከበዙበት ሰፊው መናፈሻ
በሀሴት ፈክቼ ልክ እንደ ፈንዲሻ
ፍቅር በማሾክሾክ መውደደ ስታወጋኝ
የነገውን ጉዞ በተስፋ ስትሞላኝ
ከቅፍህ ገብቼ ተንተርሼ አንተኑ
ተመኝቼ ነበር ባልመሼ ስል ቀኑ
ያን ሰሞን ••• 🌹
ወክ እያደረግንም ስሼኜኝ ወደቤት
በጨረቃ ታጅበን በንፋሱ ፉጨት
ምነው በረዘመ መንገዱ በራቀ
እንዲሁ ስንጓዝ ጎህ በፈነደቀ
እያልኩ በውስጤ ብዙ ጎጉቻለሁ
በቃ ያንን ሰሞን ላየኝ አስቃለሁ
ያን ሰሞን ••• 🌹
አንተነትህ ገዝፎ መውደድህ በርትቶ
አቅሜን ሲያዳክመው በፍቅርህ እረቶ
እስከ መጨረሻው ላደርግህ የራሴ
አቀድኩህ ከልቤ ለብቼኛ ነፍሴ
ከዛም እኔነቴን የሴትነት ልኬን
ሰጠሁህ ፈቅጄ አሳልፌ እራሴን
ያን ሰሞን ••• 🌹
ክርና መርፌ አይነት ባንድ ተጣበቅን
ቅፅበት መደብ ልፊያ በላብ ተጠመቅን
ባአፍታ ጥብብቆሽ በደቂቆች እልፈት
እርካታን ጎበኜን የስሜቱን ግለት
ከዛ ቀን በዃላ ••••🚶♂
እሱ ብልጥ ሆነ እኔዋ ተላላ
የማቀው ወዳጄ ከቦታው ወረደ
መቀዝቀዝ ጀመረ እያለም በረደ
የቆለለው ክብሬም ሳይቆይ ተናደ
ጨዋታና ቀልዱም እንደጉም ተነነ
መደወሉም ቀረ አብሮነት መከነ
ይወደኛል ያልኩት
ለብቻዬ ትቶኝ ከሌላ መነነ
❣
ለካ ሁሉም ነገር ነበር የውሻሼት
ያንድ ሰሞን ፍቅር የገላ ፍላጎት
ያኔ ሁሉም በቃኝ
ስተቴም አነቃኝ
ቢረፍድም ግን ገባኝ
ውስብስብ መሆኑ የዚህ አለም መንገድ
ኗሪም እንደበዛ ሳይመጣ የሚሄድ
ዛሬ ብቻዬን ነኝ 🤷♀
አሁን ስላብሮነት አልጓጓም በጭራሽ
የሚያስጀምር እንጂ የለምና አስጨራሽ