ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ ) @sireturesul Channel on Telegram

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

@sireturesul


ምንጊዜም ቢሆን በሂወታችን ውስጥ
በሚገጥሙን ሀዘንም ይሁን ደስታ
መማር ያለብን ከረሱል ሱ ዐ ወ ህይወት ነው።።

ሀሳብ አስተያየት ካሎት
@muhammedoumer
@tewfikseid

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ ) (Amharic)

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ ) ቡድን በሕወታችን ድንቅ አለበት። በሚገጥሙን ሀዘንም ይሁን ደስታ እንደሆነ ቀስተ ስራውን ለመግባት የሰ.ዐ .ወ ህይወት ታሪክ ተጠቀሙበት። ይህ ታሪኩ የነብዩ ሰ.ዐ .ወ እና ቢለካ አስተያየት ካሎት ነው። በሀዘንም ይሁን ሀሳብ አስተያየት ከረሱል። እባኮት በመሳሳት የነብዩ ሰ.ዐ .ወ ታሪክዎን እና ወሬዎቹን በመጠን ማግኘት ወደ @muhammedoumerና @tewfikseid ላይ ያወዳሉ።

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

25 Sep, 09:56


ለ60 ተማሪወች ደብተርና እስክርቢቶ እንደየ ክፍላቸው ማለት እንደ ሳብጀክታቸው ብዛት አድርሰናል።
በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ
ሀገራችንንም ሰላም እኛንም ሰላም
መልካም ቀን

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

13 Sep, 13:17


ሰላም በያላችሁበት የሀገሬ ልጆች
ለ2017 የትምህርት ዘመን በአቅማችን
ካለችን ለአቅመደካሞች ደብተርር እና እስክርቢቶ በመግዛት እኩል እንለግስ
መልካምነት ወሰን ገደብ የለውም ከቻልን ከነዩኒፎርሙ ካልቻልን ደግሞ 1 እስክርቢቶም
ቢሆን በመግዛት መሳኪኖችን እናስደሳ

ሂወታችንም የቀጣዩ ዓለምም ደስተኛ ሊሆን ዘንድ

ሀሳብ አስተያየት   ካሎዎትእና ደረሰኝ ለመላክ በዚህ ያገኙናል
+251962746659
1000311944097
NAME
የመንታውሃ  ወጣቶች ጀመዓ
02/01/2017

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

07 Sep, 15:06


የኸይር ስራ ትንሽ የለውም  ሼርር ይደረግ

1000137049337CBE
1002058100001HB
መንታውሃ መስጅደ ሶፋ አሰሪ ኮሚቴ
ሀሳብ አስተያየት
+251962746659
+251918229957 ደውሉልን

ሰላም ለሀገራችን
በያለንበት ሰላም

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

02 Jul, 20:35


አሁንላይ ብረት ጠጠር አስገብተን የስሚንቶ   ግብአት ስለሌለን የበኩላችሁን ድጋፍ አድርጉል  ። የኸይር ስራ ትንሽ የለውም  ሼር ላይክ አድርጉልን

1000137049337CBE
1002058100001HB
መንታውሃ መስጅደ ሶፋ አሰሪ ኮሚቴ
ሀሳብ አስተያየት
+251962746659
+251918229957 ደውሉልን

ሰላም ለሀገራችን
በያለንበት ሰላም

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

06 Jun, 11:02


📌 ጨረቃ በመታየቷ የዙልሒጃ ወር ነገ ጁምዓ አንድ ብሎ ይጀምራል!

📌 ከነገ ጀምሮ ያሉትን 10ቱን ቀናት በኢባዳ እናሳልፈው
!

📌 አሏህ  ሆይ  !  የዙል ሂጃህ ወር  ሲወጣ (ሲፈነጥቅ)    አብሮ  ፦

ለእያንዳንዱ ወንጀል  ሁሉ   ይቅርታን  ፤
ለእያንዳንዱ ጭንቀት  ሁሉ  ፈረጃን ፤ 
ለእያንዳንዱ በሽታ  ሁሉ  መድሃኒትን  ፤
ለእያንዳንዱ  ክፋት  ሁሉ መግራራትን   ፤
ለእያንዳንዱ  ላጣነው  ሁሉ   እዝነትን  ፤  ለእያንዳንዱ  ስብራት ሁሉ  ጥገናን   !! 🤲 

👉የመልካም  ነገሮች  ሁሉ  ቁልፍ  በአንተ እጅ  ነው  ያለው   ፤ አንተ  የነገሩ  ሁሉ  አዋቂ  እና  ቻይ  ነህ  አሏህዬ :
🤲🤲🤲
https://t.me/sireturesul

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

03 Jun, 07:13


📌 10ሩ የ ''ዙል ሂጃ''  ቀናቶች


📌 ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ የተባሉ የ ዙል-ሂጃ አስርቱ ቀናቶች ሊገቡ 4 ቀናት ብቻ ይቀሩናል ።

የአላህ መልዕክተኛ በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ

"أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّة.

ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀናቶች አስርቱ የዙል ሂጃ ቀናቶች ናቸው ::

📌 በሌላም ሀዲስ እንዲህ በማለት በነዚህ ቀናቶች የሚሰራ ስራ ያለው ደረጃ ያስቀምጣሉ

👈 ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر،*

👈 قالوا ولا الجهاد في سبيل الله؟

     قال ولا الجهاد في سبيل الله، إلاّ رجلا خرج بنفسه وماله فلم يرجع من ذلك بشيء* »*

📌 ከነዚህ ከአስር ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ ወደ አላህ ሚወደድበት ቀን የለም አሉ

👉 ሰሀቦችም በአላህ መንገድ ላይ መታገል { መጋደል } ቢሆንም?  ብለው ሲጠይቋቸው

''አው በአላህ መንገድ መታገል ቢሆንም ግን አንድ ሰው ሲቀር'' አሉ

👉 እሱም '' በአላህ መንገድ ለመታገል ነፍሱንም ንብረቱንም ይዞ ወጥቶ እስከ ንብረቱ እዛው የቀረ'' አሉ

🔻  አላህ በሰላም አድርሶን ተጠቅመንባቸው የምናልፍ ያርገን

https://t.me/sireturesul

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

16 Feb, 13:06


አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏህ ከ 5,ሺብ ( የ1 ካሬ ዋጋ) ጀምሮ  በሚል ለመስጅዳችን  በትንሹም ቢሆን መንቀሳቀሳችን ይታወቃል።

ሆነም ዛሬ በዚሁ በጀመርነው በካሬ 5000 ብር በሚለው የግንባታ እንቅስቃሴ መንታውሃ ላይ በተደረገ መንቀሳቀስ

82 ካሬ ሜትር ቃል ተገብቷል ማሻ አሏህ
አላህ አክበር በብር ደረጃ 410,000 ብር ማለት ነው። በተጨማሪም 3 ወይፈን እና
1/ኩ በቀሎ ተነይቷል። ከዚህ ውስጥ    72,800 ብር በጥሬው ተቀብለናል።

በአጠቃላይ በድምሩ 470,000 ብር ተነይቷል
የኔ አባቶች የኔ ዘመን ጀግኖች አላህ ያቆይልኝ  አላህ ያስደሳልኝ ያረቢ እናንተ በሀያት እያላችሁ እኛም እያለን የምንሰግድበት ያድርገን 

መነየት የምትፈልጉ አሁንም የጀነት በሮች
እናንተን ለመቀበል ክፍት ናቸው።
የኸይር ስራ ትንሽ የለውም

1000137049337 ኢትዮ ንግድ ባንክ
1002058100001 ሂጅራ ባንክ
መንታውሃ መስጅደ ሶፋ አሰሪ ኮሚቴ

ሀሳብ አስተያየት
+251962746659
+251922671095
+251918229957 ይደውሉ

08/06/2016 ዓ/ል

.መስጠት በራሱ መሰጠት ነው
ሀገራችንንም ሰላም
እኛንም ሰላም
በያላችሁበት ሰላም

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

03 Feb, 12:29


አንብቧት በጣም አስተማሪና አዝናኝ ሴትየዋና_ጂኒው

አንድ ሰው ሚስቱ ጂኒ እንደያዘው ሲያደርጋት "ጂኒሳይዛት አይቀርም" ይልና እንዲቀራባት ወደ አንድ ሸህ ይዟት ይመጣል
ከተቀራባት በኋላ ጂኒው ለመውጣት ዝግጁ እንደሆነና ለመውጣት ግን አንድ መስፈርት እንዳለው ይናገራል
"ካለመስፈርት ነው መውጣት ያለብህ" በማለት ሸይኹ ያስተባብላሉ
ጂኒውም "እስቲ መስፈርቱን ስማኝ"
ሸይኹም "እሺ ተናገር"
ጂኒው "እወጣና ባሏ ውስጥ እገባለሁ"
ባልየው ይህን ሲሰማ በድንጋጤ ብድግ ይልና
"በፍፁም አይሆንም" ይላል
ጂኒው "ለምን በሱ አካል ልገባ እንደፈለኩ ታቃለህ?"
ሸይኹ "ለምንድነው?"
ጂኒው "ሰላት አይሰግድም"
ሸይኹም ባልየውን "ጂኒው ባለው ትስማማለህ ወይ?" ብሎ ጠየቀው
ባል በፍፁም እንደማይስማማ ተናገረ
ኸይኹም ለጂኒው "ከሴቷ ውጣና ከቤታቸው አቅራቢያ ሁን ሰላት የማይሰግድ ከሆነ ግን ትገባበታለህ" የሚል ሀሳብ አቀረበለት
ጂኒው ተስማማ
ከጊዜያት በኃላ ሴቲቱ ሸይኹን ለማመስገን ደወለች
ሸይኹም ስለባሏ ሁኔታ ጠየቃት
ሚስትም "የመስጂድ በር የሚከፍተው እሱ ነው፡፡ አንዲት ሰላት አምልጣው አታቅም" አለች

የሚገርመው ሚስት ሲጀምርም ጂኒ አልያዛትም ነበረ ቧሏ ሰላት ስለማይሰግድ ጂኒ እንደያዘው ሰው መስላ ቧሏ ሰጋጅ እንዲሆን ከኸይኹ ጋ ተነጋግረው የፈጠሩት ዘዴ ነበረ
በዱንያም በአኺራም ለባሏ ቅጣትን የምትፈራለት ባሏን ከልቧ የምትወድ ምርጥ ሴት ማለት ይህች ሴት ናት

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)
https://t.me/sireturesul

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

26 Jan, 07:06


https://t.me/sireturesul

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

25 Jan, 07:55


በመቀድምም ወደኋላ በመቅረትም ኢማምህን አትቃረን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِنَّمَا جُعِلَ الْإِمَامُ لِيُؤْتَمَّ بِهِ، فَلَا تَخْتَلِفُوا عَلَيْهِ،﴾

“ኢማም የተደረገው ሊከተሉት ነው። በሱ ላይ አትለያዩ (አትቃረኑት)።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 722
https://t.me/sireturesul

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

11 Jan, 07:08


📌 የታላቁ የረመዷን ወር ሁለት ወራት ብቻ ቀሩት!
🔻 ረጀብ
🔻 ሸዕባን
🔸 አላህ በሰላም ከሚደርሱትና ፁመው ተቀባይነትን ከሚያገኙት ባሮቹ ያርገን🤲🤲

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

04 Jan, 15:24


በትናንትናው ምሽት ማለትም በቀን 24/04/2016 ዓ/ል (Jan-03-2024)

📕📗📒 ለመስጅደ ሶፋ እስላቭ(ሶሌታ) ማሰሪያ የነየቱ :-
         👇👇👇
1ኛ, ሙሀመድ ኡመር  =1 ካሬ
2ኛ, ሀያት ፀጋየ    =1 ካሬ
3ኛ,ከሚላ መኮነን = 1ካሬ
4ኛ,ሽኩር እንድሪስ = 2ካሬ
5ኛ,አስያ ደሴ  =1ካሬ
6ኛ,እስማይል ክንዱ =1ካሬ
7ኛ,ማህሙድ አህመድ =2,000 ብር
8ኛ,አህመድ ሰይድ =11,300ብር
9ኛ,ፋጢማ መብሬ = 1ካሬ
10,ዚነት ፋሪስ = 100 እሪያል
11,ሀሰን እንድሪስ = 3ካሬ
12,ጅብሪል ሙሀመድ =4ካሬ
13,አብዱ ሙሀመድ =2ካሬ
14,ረሽድ ኑሩ  = 1ካሬ
15,ሰሙ ያልተጠቀሰ = 1ካሬ
16, አህመድ ሀሰን = 1ካሬ
17, አህመድ እንድሪስ(ገብሬ) =1 ካሬ
18,
19,
20,

  ተጋግዘን መስጅዱን እንገነባዋለን።

ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን
አጅርያህል ያገኛል።ረሱል( ሰ ዐ ወ)

መልካም ኸሚስ ምሽት
https://t.me/mentawuhamesjdesofa

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

03 Jan, 16:04


አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ

👉 ከአሁን በፊት መንታውሃ ከተማ ላይ ለሚገነባው ሶፋ መስጅድ  እናንተን ደጋግ ልብ ያላችሁ ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችንን የበኩላችሁን ሰደቃ እንድታደርጉ እና የመልካም ስራው ተካፋይ እንድትሆኑ ጠይቀናል።
==============
👉 በመሆኑም በናንተው በወንድም እና እህቶቻችን እገዛ መስጅዳችን የመጀመሪያውን ዙር ማለትም የመሰረት ማውጣት እና የኮለን ግንባታ በምታዩት መልኩ ተገንብቶ አልሀምዱሊላህ ለዚህ ደረጃ በቅቷል ።
===============
👉 አሁንም መስጅዱ ወደ ሁለተኛ ዙር ግንባታ ማለትም የመስጅዱን እስላቭ(ሶሌታ) የማልበስ ስራ ልንገባ ዝግጅታችንን አጠናቀን ወደናንተው መልካም አሳቢ ወንድም ፣ እህቶቻችን በድጋሚ መጥተናል።
===============
መስጅዱ ባጠቃላይ 445 ካሬ ሜትር የሚሞላ እስላቭ(ሶሌታ) ያለው ሲሆን እንድ ካሬ ለመገንባት አሁን ባለው የገበያ ሁኔታ በአማካኝ 5,000 ብር ይፈልጋል።
===============
በመሆኑም እናንተ መልካም አሳቢ ወገኖቻችን መስጅዱን ለመገንባት የበኩላችሁን በማበርከት የሰደቃተል ጃሪያው ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ በአሏህ ስም እንጠይቃለን።
================
ሰደቃውን ለራሳችሁ ፣ ለቤተሰቦቻችሁ ፣ እንዲሁም ወደአሂራ ለሄዱ ወዳጅ ዘመዶቻችሁ በመነየት

በCBE 1000137049337 ንግድ ባንክ
          ወይንም
1002058100001 በሂጅራ ባንክ

መስጅደ ሶፋ አሰሪ ኮሚቴ

በማስገባት መሰደቅ ትችላላችሁ።

"መጭውን ረመዳን ወደመልካም ስራ በመሽቀዳደም እንቀበለው"።
=================

መስጅደ ሶፋ አሰሪና አስተባባሪ ኮሚቴ
ታህሳስ 24/2016 ዓ/ል
https://t.me/mentawuhamesjdesofa

ሲራ (የነብዩ ሰ.ዐ .ወ የህይወት ታሪክ )

02 Jan, 08:56


መልካም ለመስራት ቀጠሮ አትስጠው
እንዳየኸው የሚያስታውስህ መልካም
ጓደኛ ጥሩ ቤተሰብ ካለህ እንዳስታወሱህ
ያን ጥሩ ስራ ያንን ለነገ የሚሆንህን ስራ ስትሞት
የሚከተልህን ስራ አሁኑኑ ስራው በቻልከው ልክ አንተን በማይጎዳ መልኩ ወዲያውኑ ስራው ባንተልክ ስራው ምክኒያቱም አንተማለት ነገን የማታቅ ፍጡርነህ መች እንደምትሞት አታቅም
መልካምን ስራ ሰርተህ እለፍ!
መልካምነት ለራስ ነው።
1000137049337 ንግድ ባንክ
1002058100001ሂጅራ ባንክ
መንታውሃ መስጅደ ሶፋ አሰሪ ኮሚቴ
ሀሳብ አስተያየት
+251962746659
+251922671095
+251918229957

ሰላም ለሀገራችን
መልካም ቀን

1,545

subscribers

39

photos

8

videos