Wondirad School @wondiradschool Channel on Telegram

Wondirad School

@wondiradschool


It is all about Dejazmach Wondirad School

Wondirad School (English)

Welcome to the Wondirad School Telegram channel, dedicated to all things related to Dejazmach Wondirad School. If you are interested in learning more about the history, achievements, and impact of this esteemed educational institution, then this channel is the perfect place for you. Established with the mission of providing quality education to students, Wondirad School has been a beacon of knowledge and excellence in the community for many years. Who is it? Dejazmach Wondirad School is a renowned educational institution known for its commitment to academic excellence and holistic development of students. With a rich history and a legacy of producing successful graduates, the school has earned a reputation for its high standards and innovative approach to education. What is it? The Wondirad School Telegram channel is a platform where students, alumni, and anyone interested in the school can come together to discuss, share, and celebrate all things related to Wondirad School. From updates on events and achievements to stories from alumni and faculty members, this channel is a hub of information and inspiration for anyone connected to the school. Join us on this journey of discovery and celebration as we explore the past, present, and future of Dejazmach Wondirad School. Whether you are a current student, a proud alum, or simply curious about this esteemed institution, there is something for everyone on the Wondirad School Telegram channel. Stay connected, stay informed, and be a part of the Wondirad School community today!

Wondirad School

21 Jan, 09:32


ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች
የስራና ተግባር ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና በመጪው ዓርብ በ16/5/2017 ዓም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል። የፈተና መርሀግብሩ የተዘጋጀው በዚህ የስም ቅደም ተከተል መሆኑን አውቃችሁ በመተደባችሁበት የመፈተኛ ክፍል ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ ስንል እናሳውቃለን።

Wondirad School

21 Jan, 09:28


የስራና ተግባር ትምህርት ፈተና መርሀግበር
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፦ ዓርብ በ16/5/2017 ዓም
ፈተናው የሚሰጥበት ሰዓት፦ 8፡00-11፡00

Wondirad School

19 Jan, 04:17


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ።
"ደጃ/ወንድይራድ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት"

Wondirad School

18 Jan, 18:37


Please share share for students on Dj school telegram students channel
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/metamaths922



Thank you for your corporation

Wondirad School

18 Jan, 09:30


በደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ  ት/ቤት በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከሚወስዱ 12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ጋር
@በት/ቤቱ የውጤማነት ስትራቴጂዎች :
@ በውጤታማነት የአጠናን ስልት:
@ምን ያህል የክፍል ውስጥ ት/ርት የተከታተለ ተማሪ ፈተና ላይ እንደሚቀመጥ:
@በውጤታማ የት/ቤቱ ተማሪዎችና በውጤታማ የኢትዮጲውያን ተማሪዎች በኩል በነበረው የአጠናን እና የጊዜ አጠቃቀም ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ :
@በቀጣይ አጭር ጊዜያት በሚተኮርባቸው ጉዳዮች ላይ የተፈታኝ ተማሪዎች ሚና ምን መሆን አለበት?
በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።
"ተማሪዎች 12 ዓመት: እኛም ቀላል የማይባል ብዙ የደከምንበት ወርቃማ ጊዜያችንን በተግባር በውጤት የታጀበ እንዲሆን ለአንዲትም ደቂቃ ሳንዘናጋ ሁላችንም እንተጋለን"
ት/ቤቱ

Wondirad School

17 Jan, 15:37


ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ነገ ቅዳሜ በ10/05/2017 በጥምቀት ከተራ በዓል ምክንያት የቅዳሜ ማጠናከሪያ ት/ርት የማይኖር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ

Wondirad School

17 Jan, 12:16


visited yared music school by dej/ wendirad vocal music students

Wondirad School

17 Jan, 12:16


thank you

Wondirad School

03 Jan, 14:23


CHEMISTRY

Wondirad School

02 Jan, 19:17


ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የቅዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርት ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከጥቅምት 9/2/2017 ዓም ጀምሮ ሳይቆራረጥ በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። በመጪው ቅዳሜ ማለትም በ26/4/2017 እስካሁን በማጠናከሪያ ትምህርቱ ሲሰጡ በነበሩ የትምህርት ዓይነቶች እና የትምህርት ይዘቶች ላይ ምዘና /ፈተና/ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ሁላችሁም ይህን አውቃችሁ ከታች በተገለፀው መርሀግብር መሰረት በምዘና ስርዓቱ እንድትሳተፉ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ፈተና መሰጠት የሚጀምርበት ጊዜ ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ይሆናል!!!
•ፈተናው የሚሰጠው በመማሪያ ክፍላችሁ ነው፡፡
•ሁሉም ተማሪ ምዘናው /ፈተናው/ ላይ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡ በማይገኙ ተማሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል!!!

Wondirad School

02 Jan, 09:01


ከዚበላይ ስማችሁ የተዘረዘረ ተማሪዎች ከጥበቃ ቢሮ አንፀባራቂ ዩኒፎርም በመውሰድ የመስተባባር ስራችሁን ከሰኞ ጀምሮ እንድታከነዉኑ በጥብቅ እናሳስበለን፡፡

Wondirad School

02 Jan, 08:56


የደጃ/ወ/ከ/2ኛ ደ/ት/ቤት የተማሪ አስተባባዎች ስም ዝርዝር

Wondirad School

01 Jan, 11:32


#እንድታውቁት

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በበየነ መረብ (ኦንላይን) መመዝገብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበት አድራሻ https://register.eaes.et/Online እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የበይነ መረብ (አንላይን) ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

(እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል ከላይ ይመልከቱ)

(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

@tikvahethiopia

Wondirad School

31 Dec, 06:18


Biology Exercise for grade 12 units 1 to 3

Wondirad School

30 Dec, 09:38


በደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የዛሬ 21/04/17 የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር

Wondirad School

27 Dec, 03:28


ማስታወቂያ
      ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና ወላጆቻችሁ በሙሉ
የነገ ቅዳሜ 19/04/17 ማጠናከሪያ ትምህርት በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላል፤ አቴንዳንስም የሚያዝ ይሆናል፡፡
                              ት/ቤቱ
🙏🙏🙏

Wondirad School

26 Dec, 17:01


📩ማሳሰቢያ

1.ከ4-12ኛ ክፍል የማጠቃለያ ፈተና(6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ሞዴልን ጨምሮ) ወጥ በሆነ table of specification የሚዘጋጅ ስለሆነ ለት/ቤቶች TOS ሰሞኑን የምናወርድ መሆኑን እናሳውቃለን::

2.የ6ኛ እና8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሚዘጋጀው የ6ኛክፍል ፈተና( ከ5ኛ እና 6ኛ ክፍል) እንዲሁም የ8ኛ ክፍል(7ኛ እና 8ኛ ክፍል) መሆኑን አውቃችሁ ለተማሪዎቻቹህ አስፈላጊውን እገዛ አድርጉ

3.የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚያካትተው የ9ኛ ክፍል አሮጌው ስርዓተ ትምህርት እና የ11ኛእና 12ኛ ክፍል ከአዳሱ ስርዓተ ትምህርት መሆኑ ታውቆ ለተፈታኝ ለተማሪዎች አስፈላጊው እገዛ ይደረግላቸው(10ኛ ክፍል አይካተትም)

4.የ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚዘጋጅ ይሆናል!!

5.contnous assessment እስከ ት/ቤት ድረስ ውይይት ተደርጎና ጸድቆ ከከተማ እስኪመጣ ድረስ በጀመራቹህት አግባብ ቀጥሉ

6.ሁሉም የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ምዘና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 3/2016 ረቂቅ መመሪያ መሰረት መስራት ይጠበቅባቸዋል!!

Wondirad School

26 Dec, 17:00


በደጃ/ወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፀረ- ትንባሆ ቀን አከባበር በሰልፍ ስነ ስርዓት ላይ

Wondirad School

26 Dec, 16:54


ተግባራዊ የመማር ማሰተማር አገልግሎት በመ/ር ሞቲ ጉርሜሳ

Wondirad School

26 Dec, 16:23


የሙያና ተግባር ትምህርት ለሚያስተምሩ መምህራን ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

(ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም) መርሀ ግብሩ ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል የሙያና ተግባር ትምህርት መምህራን እየተሰጠ እንደሚገኝ ከቢሮው የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የሙያና ተግባር ትምህርት በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሀሳብ ከሚያገኙት ዕውቀት ባሻገር ሙያዊ ክህሎታቸውን አሳድገው በቀጣይ ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ የትምህርት አይነት መሆኑን ጠቁመው ዛሬ በተጀመረው ስልጠና መምህራኑ በክፍል ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ከሚገባቸው የማስተማር ስነ ዘዴ ጋር በተገናኘ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ የስልጠና ማኑዋልን መሰረት አድርገው ስልጠናውን ከሚሰጡ የዘርፉ ምሁራን በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

Wondirad School

26 Dec, 16:23


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው ማህበራቸው የመምህራንን ጥቅምና መብት ከማስከበር ባሻገር ሙያዊ ክህሎታቸውን ማሻሻል የሚችሉበትን የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኙ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸው በዛሬው እለት የሙያና ተግባር ትምህርት ለሚያስተምሩ መምህራን የተዘጋጀው ስልጠናም የዚሁ አካል በመሆኑ መምህራኑ ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው የሚያገኙትን ዕውቀት በክፍል ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ስልጠናው በዘርፉ የረጅም ዘመን የማስተማር ልምድ ባላቸው የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህራን እንደሚሰጥ የቢሮው የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ገልጸው በመርሀግብሩ 275 የሚሆኑ የሙያና ተግባር መምህራን በስድስት ቡድን ሆነው ስልጠናውን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል ።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- [email protected]

Wondirad School

24 Dec, 19:56


Reference!

Wondirad School

24 Dec, 15:16


ቀን 15/04/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረው ተማሪዎች ጉዳያችሁ በዲሲፕሊን እስኪታይ ድረስ ከት/ቤት የታገዳችሁ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
1.አቤል ታምራት ጁፋራ -10-05
2. ሚኪያስ ሙሉጌታ ዘገዬ -10-09

ት/ቤቱ

Wondirad School

24 Dec, 14:35


በደጃ/ወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሂሳብና እንግሊዘኛ ት/ርት ስተራቴጂ አተገባበር በእንግሊዘኛ ዲፓርትመንት መምህራን የተዘጋጀ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር Pre-Test ትግበራ ሂደት

Wondirad School

01 Dec, 02:16


በዳጃ /ወንድይራድ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ውጤትን ለማሻሻል በተዘረጉ ስልቶችና በቅዳሜ ማጠናከሪያ ት/ርት ክትትል እየተከናወነ በለው አፈፃፀም ላይ ከ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆችጋር የተደረገ ውይይት

Wondirad School

30 Nov, 19:25


ቀን 21/3/2017
ለሚመለከታችሁ መምህራን በሙሉ
ከታች ባለው ሰንጠዥ ስም ዝርዝራቸው የተጠቀሰ ተማሪዎች ከ16-19/3/2017 ዓም በተሰጠው የአጋማሽ ፈተና ላይ በኩረጃ ተግባር  መሳተፋቸው በፈታኝ መምህራን ተረጋግጦ ሪፖርት የተደረገ በመሆኑ አስፈላጊውን እርምጃ እንድትወስዱ ስል አሳውቃለሁ።


ት/ቤቱ

Wondirad School

29 Nov, 16:40


የነገ ቅዳሜ የ12ኛ ክፍል ማጠናከሪያ ት/ርት በተጠናከረ አገባብ የሚቀጥል ይሆናልና ሁላችሁም በሰዓታችሁ እንድትገኙ፤ ወላጅ እንድታመጡ የተነገራችሁም ተማሪዎች ወላጆቻችሁ አዳራሽ ሲገቡ እናንተ ት/ርታችሁን የምትከታተሉ ይሆናል፡፡
ት/ቤቱ

Wondirad School

29 Nov, 04:14


ትናንት ሀሙስ በየክፍሉ ለቅዳሜ 21/03/2017 ወላጅ/አሳደጊ እንድታመጡ የተናገራችሁ የቅዳሜ ማጠናከሪያ ት/ርት ላይ የማትመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በተባላችሁት ሰዓት ወላጆቻችሁን ይዛችሁ እንድትገኙ በድጋሜ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

Wondirad School

29 Nov, 04:13


ትናንት ሀሙስ በየክፍሉ ለቅዳሜ 21/03/2017 ወላጅ/አሳደጊ እንድታመጡ የተናገራችሁ የቅዳሜ ማጠናከሪያ ት/ርት ላይ የማትመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በተባላችሁት ሰዓት ወላጆቻችሁን ይዛችሁ እንድትገኙ በድጋሜ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

Wondirad School

28 Nov, 12:10


ለተማሪዎች በሙሉ
ከሰኞ 16/3/2017 ዓም ጀምሮ ሲሰጥ የነበረው የአጋማሽ ፈተና ዛሬ ሀሙስ 19/3/2017 ዓም ተጠናቋል። በመሆኑም ነገ ዓርብ 20/3/2017 ዓም መደበኛ የመማር ማስተማር ስራው የሚቀጥል መሆኑን አውቃችሁ በተለመደው ሰዓት በመማሪያ ክፍል ተገኝታችሁ የሚሰጠውን ትምህርት እንድትከታተሉ ስንል እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፦ የአቴንዳንስ ቁጥጥር በተጠናከረ መንገድ ይከናወናል።

Wondirad School

27 Nov, 07:01


Grade 9 Chemistry Worksheet.pdf

Wondirad School

26 Nov, 15:35


በደጃ/ወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም የት/ርት ለትውልድ አካል የሆነው ምቹ የት/ቤት አካባቢን ለመፍጠር በት/ቤታችን ወተመህ አስፈፃሚ ኮሚቴ ህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ይህን ሲመስል ቀሪ ስራዎችለማከናወን በሂደት ላይ እንገኛለን፤

Wondirad School

26 Nov, 15:35


በደጃ/ወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ምየተቀናጀ የከተማ ግብርና ምርት፤

Wondirad School

25 Nov, 03:18


⭐️ስለምን  ማንበብ ይፈልጋሉ??????

ከኬጅ እስከ 12ኛ ክፍል መጽሀፍ ይፈልጋሉ?? ይኸው
     👇👇👇👇👇👇👇
✔️https://t.me/dam76/3773

የሞባይል ጥገና ማንዋሎችን ይፈልጋሉ??
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3748
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3743

ኮንፒውተርን ከፕሪንተር ለማስተዋወቅ  ይፈልጋሉ?
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3615

ስለ ልዩ ቁስ ምንነት ማወቅ ይፈልጋሉ?
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3613

ስለ leaf parts ክፍሎች ማወቅ ይፈልጋሉ?
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3606

ስለ endemic animals በኢትዮጵያ ማወቅ ይፈልጋሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3604?single

ስለ  Tenses ማወቅ ከፈለጉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3599

ለህጻን ልጅዎ ማስተማሪያ  ስዕሎችን ከፈለጉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3806?single

ስለ ዝግ glands ማወቅ ይፈልጋሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/3596

ሞዴል ጥያቄዎችንና  ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/4125

መማሪያ መጽሀፍትን  ከፈለጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76/4614

✉️ከናንተ የሚጠበቀው ይህንን ቻናል ሸር ማድረግ ብቻ ነው!!
👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76

🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤

🔤🔤🔤🅰️ 🔤🔤🔤

🔠🔠🔠🅰️  🔠🔠🔠

Wondirad School

24 Nov, 07:53


Grade 10 History worksheet

Wondirad School

23 Nov, 20:49


በፈተና ወቅት የሚከሰት የኩረጃ ተግባርን ለማጥፋት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ

Wondirad School

23 Nov, 18:59


ኩረጃ ምንድን ነው?
ኩረጃ የራስ ያልሆነን ስራ እንደራስ አድርጎ ማቅረብወይም የማይገባውን ውጤት ለማግኘት የሚደረግ ጥረት እና ያልተገባ ውጤት ለማግኘት ፈታኝ መምህርን በማታለል የሚከናወን ፀያፍ የሌብነት ተግባር ነው፡፡ ጓደኛ እንዲኮርጅ መርዳት፣ በግል የተሰጠ የምዘና ተግባርን በቡድን መስራት ወይም ለሌላ ሰው ማሰራትም ሆነ መስራት በኩረጃ ስር የሚጠቃለሉ አላስፈላጊ ተግባራቶች ናቸው። ይሁንና ተማሪዎች በጓደኞቻቸው ዘንድ ሰነፍ ሆኖ ላለመታየት ወይም በውጤት አንሶ ላለመገኘት ሲሉ ብዙ ጊዜ ወደ ኩረጃ ተግባር ሲገቡ ይስተዋላል።
ተማሪዎች የሚኮርጁት ለፈተናው ወይንም ደግሞ ምዘናው በቂ የስነልቦና ዝግጅት ሳይኖራቸው ሲቀር ነው። ተማሪዎች በተገቢው መጠን ራሳቸውን ካለመዘጋጀት ውጪ፣ ትምህርትን በአግባቡ አለመከታተል እና ኩረጃ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሌለው ግንዛቤ መያዝ ወደ ኩረጃ የሚገፉ ሌሎች ምክንያቶች ናቸው ። ነገር ግን ኩረጃ ከክፍል ክፍል ሲኬድ እያደገ የሚሄድ ብቻ ሳይሆን፣ በሕይወት ውስጥ ዘላቂ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በትምህርት ዓለም የነበረን የኩረጃ ሕይወት ወደ ሥራ ዓለም ስንገባም ያንኑ የመተግበር እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ እና ተያያዥነት እንዳለው ነው፤ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በኩረጃ ታግዞ ወደ ከፍተኛ ተቋም ሲገባ፣ እዚያም በኩረጃ ታግዞ ቢመረቅ በስራው ዓለም መደለያ ለመቀበል አያቅማማም።
ተማሪዎቹ ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባታቸው በፊት፣ ለኩረጃ ሲዘጋጁ ኔትወርክ ፈጥረው፣ የመጀመሪያው እቅድ ባይሳካ በሚል ሁለት እና ሶስት እቅዶችን ነድፈው ይገባሉ። ከዚህ በተጨማሪ የነደፉት ስልት በፈተና የመጀመሪያ ቀን ካልሰራ፣ ለቀጣዩ ፈተና ቀን ሌላ ስልት ነድፈው ሊመጡም ይችላሉ። የተንቀሳቃሽ ስልከ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው በሚያደርጉት ኩረጃም ከትምህርት ቤት ውጪ ያሉ ግለሰቦችን ያሳተፈ የኩረጃ ተግባርም ሊፈፅሙ ይችላሉ። ለፈተና ስርቆት እና ኩረጃ መስፋፋት እገዛ የሚያደርገው ቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን የፈታኝ መምህራን እና የትምህርት ቤቱ አስተዳደሮች ቁርጠኛ አለመሆን ጭምርም ነው።

Wondirad School

23 Nov, 18:59


ከዚህ አንፃር ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ማለትም ከ 16/3/2017- 19/3/2017 ዓ.ም ድረስ በሚሰጠው የአጋማሽ ፈተና ከኩረጃ የፀዳ እንዲሆን ለማድረግ በትምህርት ቤታችን ሰፊ ዝግጅት የተደረገ መሆኑን እየገለፅን፤ በኩረጃ ሲሳተፉ/በመኮረጅም ሆነ በማስኮረጅ/ የተገኙ ተማሪዎች ላይ ትምህርት ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 ዓ.ም ለአንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ያዘጋጀውን የተማሪዎች የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት አድርጎ አስተማሪ የርምት እርምጃዎችን በአፋጣኝ የሚወስድ እና የተወሰደውን እርምጃም ለትምህርት ማህረሰቡ ወዲያውኑ ባሉን የመገናኛ ዘዴዎች ሁሉ ተጠቅመን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
ፈታኝ መምህራንም በተመደባችሁበት የመፈተኛ ክፍል የፈታኝነት ኃላፊነታችሁን በትጋት እና በንቃት እንድትወጡ እና ኩረጃን ሊያስቀር የሚችል ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር በመፈተኛ ክፍላችሁ እንድታደርጉ እና ያጋጠማችሁ ችግርም ካለ ለርእሰ መምህራን ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ ኃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት በቸልተኝነት ፈታኝ ሆናችሁ በተመደባችሁበት ክፍል ተማሪዎች የተኮራረጁ መሆኑ በማስረጃ የሚረጋገጥ ከሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርትምህርት ቢሮ ያዘጋጃቸውን የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር ሙያዊ የስነ ምግባር፤የዲሲፕሊን አፈጻጸምና ቅሬታ አቀራረብ መመሪያ ቁጥር 161/2016 እና የአጠቃሊይ ትምህርት ምዘና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 3/2016ዓ.ም መሰረት አድርገን ተጠያቂነትን የምናሰፍን መሆኑን እንገልፃለን፡፡


በኩረጃ ተግባር ሲሳተፉ/በመኮረጅም ሆነ በማስኮረጅ/ የተገኙ ተማሪዎች ላይ የሚወሰዱ የእርምት እርምጃዎች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 ዓ.ም ለአንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ባዘጋጀው የተማሪዎች የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት፡-
1. ከኩረጃ ጋር ተያይዞ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የሚያሰጡ ጥፋቶች
• በት/ቤት ቅጥር ግቢ መታወቂያ ይዞ አለመገኘት እና ሲጠየቅ አለማሳየት
2. ከኩረጃ ጋር ተያይዞ ለአንድ ዓመት ከትምህርት ቤት የሚያሳግዱ ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋቶች
• በፈተና ወቅት መኮረጅና ማስኮረጅ፣
• በፈተና ወቅት ሁከት መፍጠር ፣ የፈተና ሰርዓቱ እንዲደናቀፍ ማድረግ
• ፈታኝ መምህራንን፤ ሱፐርቫይዘሮችን እና ሌሎች የተመደቡ የፈተና አሰተባባሪዎችን እና ማንኛውንም የትምህርት ቤቱን ሰራተኛ መሳደብ፣ ማንጓጠጥ እና ለመደባደብ መሞከር፤
3. ከኩረጃ ጋር ተያይዞ ከትምህርት ቤት እስከ መጨረሻው የሚያሳግዱ ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋቶች
• በፈተና ወቅት ስልክ፣ታብሌት ይዞ መምጣት፤ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ መጠቀም ተገቢ ያልሆነ ተግባር ማከናወን፤ (ተማሪ የሚያወናብዱ መረጃዎች ማስተላለፍ፤ ወዘተ)


ደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
አዲስ አበባ
ህዳር 2017 ዓ.ም

መልካም ፈተና!!!

Wondirad School

23 Nov, 18:59


ኩረጃን ማስቀረት ይቻላል?
ኩረጃን ለማጥፋት ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ ተማሪዎች ስለታማኝነት እየተማሩ መምጣት አለባቸው። ታዳጊዎች ከታች ክፍል ጀምሮ መኮረጅ አስፀያፊ መሆኑን እየነገሩ ማሳደግ በኋላ በከፍተኛ ትምህርት ተቋምም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ ላይ በስነምግባር የታነፀ ትውልድ እንዲኖር ይረዳል።ከሥርዓተ ትምህርት አንጻርም ስለኩረጃ፣ ስለታማኝነት በየትምህርት ዓይነቶቹ ላይ ማካተት አስፈላጊ ነው። ፈታኝ መምህራንም ቢሆኑ ኃላፊነት ተሰምቷቸው ኩረጃን ሊያስቀር የሚችል ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር በመፈተኛ ክፍል ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ፈተና በሚሰጥበት ክፍል ፈታኝ መምህሩ በአግባቡ መፈተን መቻሉ ኩረጃን ለማጥፋት የራሱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
የትምህርት አመራሮችም ቢሆኑ ለተማሪዎች የሚያወጧቸው መመሪያዎችን እና መተዳደሪያ ደንቦችን በአመቱ መጀመሪያ ላይ ለተማሪዎቹ በሚገባ ማስተዋወቅና ግንዛቤ መፍጠር አለባቸው፡፡ ከኩረጃ ጋር ተያያዥነት ኖሯቸው የወጡ መመሪያና ደንቦችን ተከትሎ ለሚፈፀሙ የደንብ መተላለፎች የተቀመጡ ተገቢ ቅጣቶችን ሳይዘገዩ ተፈጻሚ ማድረግ ኩረጃን ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚና ከፍ ያለ ነው ።

Wondirad School

23 Nov, 17:28


ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን):-

• ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
• በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::
• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤
• በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።

Wondirad School

23 Nov, 17:27


በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች
ከህዳር 16-19/2017 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ቤታችን የአጋማሽ ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ውጥረት ለመቆጣጠር :-
ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን :-
• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
• ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ መሆኑን አውቀን በመርሀግብር የተመራ በቂ ዝግጅት ካደረግን የምንፈልገውን ዉጤት ማምጣት እንደምችል በማመን ከት/ቤት መልስ በቤት ዉሥጥ በመምህራን የተሰጡ የመማር ተግባራት / የቤት ስራ፣ የግል ስራ ወ.ዘ.ተ/ በአግባቡ መሰራትና እርማት መውሰድ፤ በተጨማሪም በቤት ዉስጥ ቋሚ የጥናት መርሀግብር ማዘጋጀት እና በተዘጋጀው መርሀ ግብር መሰረት ጥናት ማከናወን፡፡
• ማወቅ ያለብን አንድ ነገር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።

Wondirad School

23 Nov, 05:28


✍️ለተማሪዎቻቹህ ይህንን ቻናል በማጋራት የብዙ አመታት ጥያቄዎችንና የተለያዩ ትምህርታዊ መረጃዎችን እንዲያገኙ ይደረግ!!
👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76

🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤

🔤🔤🔤🅰️ 🔤🔤🔤

🔠🔠🔠🅰️  🔠🔠🔠

Wondirad School

19 Nov, 18:16


ቀን 10/03/2017 ዓ.ም
ጥብቅ ማስታወቂያ
ለተማሪዎችና ወላጆች በሙሉ
ለተማሪዎች የተለያዩ የት/ቤቱን መልዕክቶች እና ትምህርታዊ መረጃዎች የምናሳውቀበት ህጋዊ ቴሌግራም ቻናል ይህ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በሌሎች ህገ-ወጥ ግሩፕ ቻናል እየተወዛገባችሁ አላስፈላጊ መረጃ የመያዝና አላስፈላጊ ህገ-ወጥ ድርጊት ውስጥ የምትሳተፉ ተማሪዎች እና እንዲሳተፉ እየፈቀዳችሁ ያላችሁ የተማሪ ወላጆች በሙሉ ከዚህ ድርጊት እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚደርስባችሁ ችግርና ተጠያቂነት ሁሉ ሀላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ

Wondirad School

19 Nov, 10:00


ቀን 10/03/2017 ዓ.ም
አስቸኳይ ማስታወቂያ
ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘራችሁ ተማሪዎችና ወላጆቻችሁ ያልተፈቀደ (Black Day) ለማክበር ሙከራ ያደረጋችሁ በመሆኑ ጉዳያችሁ በዲሲፕሊን እስኪጣራ ድረስ ከት/ቤት የታገዳችሁ መሆኑን እየገለፅን በጉዳዩ ላይ በዝርዝር ለመነጋገር ነገ ረቡዕ በ11/03/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ላይ ያስመዘገቧችሁን ወላጆች በመያዝ በት/ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- እራሱንና ወላጁን በተጠቀሰው ሰዓት ይዞ የማይቀርብ በምንም መልኩ ጉዳዩ የማይታይና በህግ ጭምር የሚያስጠይቅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Wondirad School

18 Nov, 06:47


Sharing file...

Wondirad School

15 Nov, 18:37


ማስታወቂያ
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ
የቀዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርትን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት ያሳያችሁት ተሳትፎና ክትትል የቀነሰ መሆኑን እየገለፅን ቀጣይ ቅዳሜ በ07/03/2017 ዓ.ም ዕለትም ማጠናከሪያ ት/ርቱ የሚቀጥል መሆኑን እና የናንተም ክትትል የበለጠ መጠናከር እንዳለበት በጥብቅ እያሳሰብን ወላጆችም ይህንንው ተገንዝባችሁ ልጆቻችሁን ውጤታማ ለማድረግ ወደ ማጠናከሪያ ት/ርት እንድትልኩ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ
ማሳሰቢያ፡-
ለ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤታማ እንድትሆኑ e-temari,net I-Tutor ን ጨምሮ ሌሎች አማራጮች ላይም የምትሳተፉበትን ሁኔታ ኦረነረቴሽን ስለሚሰጥ በሰዓቱ በየክፍላችሁ እንድትገኙ፡፡

Wondirad School

14 Nov, 15:41


ቀን 5/3/2017 ዓም
ለሚመለከታችሁ ክፍል ሀላፊ መምህራን
ከታች ስማቸው የተዘረዘረው ተማሪዎች በተደጋጋሚ ጊዜ በማርፈድ የት/ቤቱን የተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ የጣሱ በመሆኑ እና በተደጋጋሚ ምክር እና ተግሳፅ ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ በመሆኑ ት/ቤቱ የጣለባቸውን ቅጣት ተፈፃሚ እስከሚያደርጉ ድረስ ከክፍል የታገዱ መሆኑን አውቃችሁ ውሳኔውን በጥብቅ ዲሲፕሊን እንድታስፈፅሙ ስንለ እናሳስባለን።
1. ቤልሄም ሞገስ 9-4
2. ሜላት ደጀኔ 9-9
3. ዮሀናን ከተማ 9-11
4. ማርታ ዳመና 10-1
5. ዳግማዊ ወንደሰን 11-3
6. እዮሲያስ ጌታነህ 11-4
7. ሩት እንዳለ 11-11
8. ሚኪያስ ንጉሴ 12-2

Wondirad School

14 Nov, 12:30


FROM TEACHER BELAY ENGLISH TEACHER

Wondirad School

11 Nov, 17:13


ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ለሚሠጡ ለእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነቶች፣ ማትሪክን በማሳለፍ በሚታወቁ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ የማስተማር ልምድና ዝና ባለቸው መምህራን በጥራት የተዘጋጀ ተጨማሪ ኮርሶችን ያግኙ፡፡
አስተማማኝ ግንዛቤ እንዲኖር ከሚያስችል በበቂ ሁኔታ ከተዘጋጀ የክለሳ ማስታወሻ ጋር!

ተማሪዎች ለማትሪክ ፈተና የሚያደርጉትን ዝግጅት በእጅጉ የሚያቀል የኦንላየን መተግበሪያ-እነሆ!  እስከ አሁን የወጡትን የ7 ዓመታት ማለትም ከ2009 እስከ 2015 ዓ.ም. ሙሉ የማትሪክ ፈተናዎች ጥያቄ ከእነ መልሶቻቸው ከአጥጋቢ ማብራሪያ ጋር የያዘ ሲሆን፣ በተጨማሪም:

✍️ተማሪዎች ራሳቸውን በቀላሉ እንዲፈትሹ የሚያስችላቸውን የፈተና መለማመጃዎች እንዲሁም ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን ከቀላል አጠቃቀም ጋር ይዞ መጥቷል። ይሞክሩት!
✍️ ድረገፅን ይጎብኙ!

Wondirad School

11 Nov, 04:56


grade 10 physics

Wondirad School

11 Nov, 03:40


ቀን 30/02/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለት/ቤታችን ተማሪዎች በሙሉ
ከሰኞ 02/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ስትመጡ፡-
1.ማንኛውም ኮፍያ ያለው ልብስ መልበስ የተከለከለ መሆኑን፤
2.የተቀየረውን አዲሱን መታወቂያ ሳይዙ መግባት የተከለከለ መሆኑን፤
3.ወንዶች ፀጉር አንጨብርሮ፣ ሴቶች ሱሪና ፓሬ ቀሚስ ለብሶ መምጣት የተከለከለ መሆኑን፡፡
4.ከ2፡20 በኋላ አርፍዶ መምጣት የተከለከለ መሆኑን፤
5.ካለ ደብተር/የግል ማስታወሻ ባዶ እጅ መምጣት የተከለከለ መሆኑን እንዲታወቅ በድጋሜ አጥብቀን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ

Wondirad School

11 Nov, 03:39


ቀን 30/02/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለት/ቤታችን ተማሪዎች በሙሉ
ከሰኞ 02/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ስትመጡ፡-
1.ማንኛውም ኮፍያ ያለው ልብስ መልበስ የተከለከለ መሆኑን፤
2.የተቀየረውን አዲሱን መታወቂያ ሳይዙ መግባት የተከለከለ መሆኑን፤
3.ወንዶች ፀጉር አንጨብርሮ፣ ሴቶች ሱሪና ፓሬ ቀሚስ ለብሶ መምጣት የተከለከለ መሆኑን፡፡
4.ከ2፡20 በኋላ አርፍዶ መምጣት የተከለከለ መሆኑን፤
5.ካለ ደብተር/የግል ማስታወሻ ባዶ እጅ መምጣት የተከለከለ መሆኑን እንዲታወቅ በድጋሜ አጥብቀን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ

Wondirad School

10 Nov, 15:24


For all of Our Students please use this link for Your English lesson (@geez1995)

Wondirad School

10 Nov, 15:20


Channel photo updated

Wondirad School

05 Nov, 19:43


ቀን 26/02/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረው ተማሪዎች ጉዳያችሁ በዲሲፕሊን እስኪታይ ድረስ ከት/ቤት የታገዳችሁ መሆኑን እየገለፅን የጥፋታችሁን ዝርዝር በጥልቀት ለመነጋገር ነገ ረቡዕ በ27/02/17 ከቀኑ 9፡30 ላይ ር/መ/ር ቢሮ በተያዥነት ካስመዘገቧችሁ ወላጆቻችሁ ጋር እንድትገኙ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
1.አማኑኤል ወንድሙ ካብቲመር =9-09
2. አሸናፊ አለማየሁ ጌታቸው =9-09
3.ናትናኤል ለሜሳ ኦሉማ =9-12
4.ዳዊት ገለቶ በነበረው =10-10
5.አቤሴሎም ለማ ወርቁ =12-09
6.ብስራት እሸቱ መካሻ =11-02
7.ጴጥሮስ ይገረም ሀይለሚካኤል =12-09
8.ዮሀንስ ዳዊት መለሰ =11-04
ት/ቤቱ

Wondirad School

05 Nov, 19:39


ቀን 26/02/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረው ተማሪዎች ጉዳያችሁ በዲሲፕሊን እስኪታይ ድረስ ከት/ቤት የታገዳችሁ መሆኑን እየገለፅን የጥፋታችሁን ዝርዝር በጥልቀት ለመነጋገር ነገ ረቡዕ በ27/02/17 ከቀኑ 9፡30 ላይ ር/መ/ር ቢሮ በተያዥነት ካስመዘገቧችሁ ወላጆቻችሁ ጋር እንድትገኙ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
1.አማኑኤል ወንድሙ ካብቲመር =9-09
2. አሸናፊ አለማየሁ ጌታቸው =9-09
3.ናትናኤል ለሜሳ ኦሉማ =9-12
4.ዳዊት ገለቶ በነበረው =10-10
5.አቤሴሎም ለማ ወርቁ =12-09
6.ብስራት እሸቱ መካሻ =11-02
7.ጴጥሮስ ይገረም ሀይለሚካኤል =12-09
8.ዮሀንስ ዳዊት መለሰ =11-04
ት/ቤቱ

Wondirad School

04 Nov, 21:00


የREMEDIAL ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

(ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም) በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን

Website: https://placement.ethernet.edu.et
Telegram: https://t.me/moestudentbot

ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- [email protected]

Wondirad School

04 Nov, 06:32


ስማችሁ ያልተካተተ ተማሪዎች online registration ያላከናወናችሁ በመሆኑ በአፋጣኝ ሪፖርት አድርጉ

Wondirad School

02 Nov, 18:45


በደጃ/ወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም የት/ርት ለትውልድ አካል የሆነው ምቹ የት/ቤት አካባቢን ለመፍጠር በት/ቤታችን ወተመህ አስፈፃሚ ኮሚቴ ህብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወነ ያለው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ አተገባበር ጅማሮ

Wondirad School

02 Nov, 18:34


በደጃ/ወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የከተማ ግብርና አተገባበር አሁናዊ ሁኔታ በዚህ መልኩ የሚታይ ሲሆን ከምርት ተጠቃሚነት ባሻገር ለተማሪዎች ተግባራዊ የ Agriculture, Biology, Geography, Economics እና ተያያዥ ትምህርቶች ዓይነተኛ ማስተማሪያነት እያገለገለ ይገኛል፡፡

Wondirad School

02 Nov, 18:34


https://www.ena.et/web/amh/w/amh_5386697

Wondirad School

01 Nov, 16:53


ማስታወቂያ
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የቀዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርት ነገ ቅዳሜ በ 23/02/2017 ዓ.ም ዕለትም የሚቀጥል በመሆኑ ሁላችሁም በሰዓቱ ተገኝታችሁ እንድትከታተሉ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ

Wondirad School

30 Oct, 22:28


የት/ቤታችን Quantum Crew ሳይንስና ፈጠራ ቡድን በ2017 ዓ.ም የት/ርት ዘመን በተለያዩ ዘርፎች የሳይንስና ፈጠራ ስራዎችን ለመስራት በዛሬው ዕለት ከቀደምት ስኬታማ የቡድኑ አባላት ጋር የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብርና ከሳይንስና ICT መምህራን እንዲሁም ከት/ርት አመራሮች ጋር የውይይት እና የክበቡን አስተባባሪ ተማሪዎች የመምረጥ ተግባር ተከናወነ፡፡

Wondirad School

30 Oct, 16:18


https://t.me/AcFn2017

Wondirad School

30 Oct, 00:28


ቀን 19/02/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለ12ኛ ክፍል የቀን ተማሪዎች በሙሉ
የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች መረጃችሁን ወደ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለመላክ የስም፣ የፆታ እና የፊልድ ስህተት ካለ ባስቸኳይ እስከ ሀሙስ 21/02/2017 ዓ.ም ድረስ ICT Lab.3 (መ/ር አለባቸው) ጋር እንድታሳውቁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ
ማሳሰቢያ፡-
ስም ዝርዝር ከተላከ በኋላ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድና ሀላፊነቱንም ተማሪው ራሱ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል፡፡

Wondirad School

30 Oct, 00:26


ቀን 19/02/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለ12ኛ ክፍል የቀን ተማሪዎች በሙሉ
የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች መረጃችሁን ወደ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለመላክ የስም፣ የፆታ እና የፊልድ ስህተት ካለ ባስቸኳይ እስከ ሀሙስ 21/02/2017 ዓ.ም ድረስ ICT Lab.3 (መ/ር አለባቸው) ጋር እንድታሳውቁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ
ማሳሰቢያ፡-
ስም ዝርዝር ከተላከ በኋላ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድና ሀላፊነቱንም ተማሪው ራሱ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል፡፡

Wondirad School

29 Oct, 17:36


ለ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ
የ 2017 ዓም የሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን በአስቸኳይ እንድናሳውቅ የተጠየቅን በመሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከታች ባለው መረጃ የስም ስፔሊንግ እና ፆታ በትክክል መሞላቱን አይታችሁ እንድታረጋግጡ ስማችሁ ያለተካተተ ተማሪዎች ካላችሁም ነገ በ20/2/2017 ዓም ለመ/ማ/ም/ር/መ/ር ቢሮ ሪፖርት እንድታደርጉ ስል አሳስባለሁ

Wondirad School

26 Oct, 06:45


በዳጃ /ወንድይራድ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስመ-ጥርና ተወዳጁ የሂሳብ ዲፓርትመንት የመማር ማስተማር ስራውን ለማሳለጥ ወጤታማ ለማድረግ በዚህ መልክ የ Lesson Study መርሀ ግብር ያካሄደ ሲሆን ይህ የመልካም ተግባር ተሞክሮ በሌሎች ዲፓርትመንቶችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ

Wondirad School

25 Oct, 14:21


ለተማሪዎች በሙሉ
ከመጪው ሰኞ ማለትም ከ18/2/2017 ዓም ጀምሮ ከታች ባለው መርሀ ግብር መሰረት መፅሀፍ የሚሰራጭ በመሆኑ ሁላችሁም በወጣላችሁ መርሀ ግበር መሰረት ንብረት ክፍል በአካል በመገኘት እንድትወስዱ ስንል እናሳውቃለን።
ሰኞ 18/2/2017 ዓም 10ኛ ክፍል በሙሉ
ማክሰኞ 19/2/2017 ዓም 11ኛ ክፍል በሙሉ
ረቡዕ 20/2/2017 ዓም 12ኛ ክፍል በሙሉ
ማሳሰበዒኣ የ9ኛ ክፍል መፅሀፍ እንደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል።

Wondirad School

25 Oct, 12:26


FROM YOHANES

Wondirad School

24 Oct, 09:38


ቀን 14/2/2017 ዓም
ማስታወቂያ
ለተማሪ ቤተልሄም ደረጄ አሰፋ እና ለተማሪ በረከት ሰለሞን ሙላት
ከላይ ስማችሁ የተጠቀሰ የ10-2 ክፍል ተማሪዎች ትምህርት ከተጀመረበት ከ8/1/2017 ዓም ጀምሮ በትምህርት ገበታችሁ ላይ ያልተገኛችሁ መሆኑን በያዝነው አቴንዳንስ አረጋግጠናል። በመሆኑም በተከታታይ ባሉ 3 የትምህርት ቀናት ውስጥ /ከ14/2/2017 ዓም-18/2/2017 ዓም ድረስ ብቻ/ የቀራችሁበትን ህጋዊ ማስረጃ ይዛችሁ የክፍል ሀላፊያችሁ መምህር ጋር ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን። ይህ ሰቃይሆን ቢቀር ግን በተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የእርምት እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።


ት/ቤቱ

Wondirad School

24 Oct, 03:43


ቀን 14/02/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የቀዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርትን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት ያሳያችሁት ተሳትፎና ክትትል የሚበረታታ መሆኑን እየገለፅን ቀጣይ ቅዳሜ በ16/02/2017 ዓ.ም ዕለትም ማጠናከሪያ ት/ርቱ የሚቀጥል መሆኑን እና የናንተም ክትትል የበለጠ መጠናከር እንዳለበት ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ት/ቤቱ
ማሳሰቢያ፡-
የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በብቃት ለማለፍ ጥቃቅን ሰበብ ከማብዛት ይልቅ የትኛውንም ለትምህርታችሁ የምትከፍሉትን መስዋትነት መክፈል እንዳለበችሁ እንዳትዘነጉ፡፡

Wondirad School

24 Oct, 03:19


Tutorial Notice

Wondirad School

15 Oct, 08:06


ሰሌክት ኮሌጅ በመማር ማስተማር ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች እየተመራ ሙሉ ዕውቅና ባገኘንባቸው በጤና፣ በቢዝነስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች በማስተርስ፣ በዲግሪና በቴክኒክና ሙያ መርሀ ግብር በሪሜዲያል ፕሮግራም በምዝገባ ላይ ነን!
ለ2016 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የሪሜድያል ፕሮግራም ለመስጠት ዝግጅታችንን አጠናቀናል።
ልዩ የሚያደርገን
• በ2016 በኮሌጃችን የሪሚዲያል ፈተና የወሰዱ ተማሪወች በከፍተኛ ውጤት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ማሳለፋችን
• በonline የታገዘ ትምህርት መስጠታችንና
አድራሻ፦ አየር ጤና ካምፓስ - አየር ጤና አደባባይ / መገናኛ ካምፓስ - መገናኛ አደባባይ ደራርቱ ህንጻ
ስልክ ቁጥር፦ 9521/ 0905433333 / 0975202020
ለተጨማሪ መረጃ፡-
https://www.Select.edu.et
Telegram https://t.me/SelectBTCollege
TikTok: https://www.tiktok.com/@selectcollege?is_from_webapp=1

Wondirad School

14 Oct, 07:38


ቀን 4/2/2017 ዓም
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን ከ4-5/2/2017 ዓም ብቻ ከ9፡00 ቡሀላ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝታችሁ የተዘጋጀውን ፎርም እንድትሞሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ምዝገባውን እንዲያስፈፅሙ የተወከሉት መምህር መምህር አለባቸው ብርሀን መሆናቸውንም እንገልፃለን።

Wondirad School

10 Oct, 12:09


👉የድጋሜ ማሳሰቢያ

የዩንቨርስቲ ምርጫን በተመለከተ

👉የ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ ምርጫ ለማካሄድ ፖርታሉ እየሰራ ስላልሆነ  በትግስት ጠብቁ!!

✍️ተማሪዎች በተባለው ቀን ምርጫ ስላልመረጡ ችግሩ ሲቀረፍ የሚመርጡ መሆኑን ግንዛቤ ይፈጠርላቸው!!

Wondirad School

09 Oct, 07:03


Dej. Wondirad 2dary

Wondirad School

08 Oct, 16:59


#MoE

👉በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።

👉በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

👉በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

👉በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

👉በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

Via 👉tikvahuniversity

🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤
ቻናላችን ይህ ነው
👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/dam76