ልብ ወለድ❤ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች❤ @ethiofilm2adey_drama Channel on Telegram

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

@ethiofilm2adey_drama


#በቻናሉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮችን + እዉነተኛ የፍቅር ታሪኮችን + የፍቅር ደብዳቤዎችን + ግጥሞች + የፍቅር ጥቅሶችን + ሞቲቬሽናል ስፒቻች እና latest ፊልሞችን ያገኙበታል !!!

ልብ ወለድ❤ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች❤ (Amharic)

ልብ ወለድ❤ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች❤ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮችን እዉነተኛ የፍቅር ታሪኮችን የፍቅር ደብዳቤዎችን ግጥሞች የፍቅር ጥቅሶችን ሞቲቬሽናል ስፒቻች እና latest ፊልሞችን ያገኙበታል! በቻናሉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮችን የሚገቡበት መረጃ ነው። የተለያዩ ፊልሞችን፣ የፍቅር ጥቅሶችንና ሞቲቬሽናል ስፒቻችንን እናታይም። ዋና ከተማን ጀምሮ በሚኖሩበት በጣና ዙርያ እዚህ እዚህ ገብተዋል።

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

20 Feb, 18:26


..ልጄ ፍፀም ልዩ ሰው ሆኖ ነበር የመጣው.ያው ታውቃለህ የእምሮ በሽተኛ ስለሆነ ሁኔታው ሁሉ ወሰድ መለስ ነበር የሚያደርገው...በዛን ቀን ግን እንደዛ አልነበረም….መልኩ ጥርት ያለ …አለባበሱ ጠርት ያለ…ንግግሩ ጥርት ያለ ነበር…፡፡ተደሰትኩ፤ተስፋ አደረኩ፤ጓጓው…በውስጤ ለአንድ ሺ ጊዜ ደጋግሜ ፈጣሪን አመሰገንኩ…ልጄ ሙሉ በሙሉ እየዳነልኝ ነው አልኩ….በደስታ እየተጫወተንና እየተቃለድን ቁርስ በላን..እማዬ ጸጉርሽ ተንጨብርሯል አለና ፀጉሬን ፈቶ ሲያበጥርልኝ ..መልሶ እየጎነጎነ ሲሰራልኝ …አቤት የተደሰትኩት መደሰት.ለካ እሱ እየተሰናናተኝ ነበር.ለመቸረrሻ ጊዘዜ ሰውነቴን እዳበሰኝ ነበር…የልጅ እጅ ሰውነትህ ላይ ሲያርፍ የሚሰማህን ስሜት ታውቀዋለህ…?በምንም ሊገለፅ የማይችል ልዩ ነው....እንደዚህ እንደዚህ እያልን አምስት ሰዓት ተኩል ሆነ፡፡
‹‹.ከዛ በቃ እማዬ ክፍሌ ናፍቆኛል ››አለኝ
‹‹እሺ ግባ እኔም እስከዛ ቆንጆ ምሳ በራሴ እጅ ሰራልሀለው›› አልኩና እሱን ወደክፈሉ ሸኝቼ ወደኪችን ገባው፡፡ ከዛ ሚወደውን ምግብ ሁሉ አንድ ሳላስቀር ሰርቼ ጠረጳዛውን ሞላውና ወደክፍሉ ሄጄ አንኳኳው መልስ የለም…እስኪደክመኝ አንኳኳው ‹እንቅልፍ ወስዷት ይሆን?› የሚል ጥርጣሬ ገባኝ…‹‹እንደለመደው ወጥቶ በመሄድ ጠፈቶብኝ ይሆን? ›ስልም ተጠራጠረርኩ…ቁልፍ አስመጣውና ከፍተን ስንገባ ..ልጄ በሰማያዊ ሲባጎ እራሱን አንጠልጥሎ በድኑ በአየር ላይ እየተሸከረከረ ነበር፡፡
ማንኛዋም እናት በእኔ የደረሰው ሀዘን አይድረስባት…ያው አሁን እኔም በህይወት መኖሬን እርግጠኛ አይደለውም…ውስጤ ደክሟል..ተስፋዬ መክኗል…ለህይወት ያለኝ ጉጉተት ጠፍቷል..የምበላው ምግብ ጨው ይኑረው አይኑረው እራሱ መለየት ትቼያለው…የምጠጣው ውሀ ይሁን በረኪና ግድ አይሰጠኝም…የዩኒቨርሲተ አስተማሪ ልሁን የፅዳት ሰራተኛ እርግጠኛ አይደለውም…ፕሮፌሰር ብለው ሲጠሩኝ እራሱ ማንነው? ብዬ መደንገጥ ጀምሬያለው..እኔ ይሄ ሁሉ ቀርቶብኝ እናት ብቻ ነበር መሆን የምፈልገው… የቢላል እናት መሆን…፡የቢላል እናት በሚል በፀጋ በተሞላ አስደናቂ ስም መጠራት.፡፡

ፖሊሱ ራሱ የሁሉቱ ሴቶች ሀዘን በጥልቀት ተጋባበት….ምንአይነት የተለየ ሰው ቢሆን ነው በዚህ መጠን ይወዱት የነበረ…?ሲል በውስጡ አሰበ….ከመሳቢያው ኪስ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና ጠረጳዛ ላይ አሰቀመጠ….እና በሁለቱ መካከል ገፋ አደረገና አስጠጋላቸው.ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ
‹‹…ምንድነው ኢንስፔክተር?›ሲፈን ነች ጠያቂዋ
የቢላልን ክፍል ስንመረምር ያገኘነው ነው…ለሁለታችሁ ከመሞቱ በፊተ የተወላቸሁ መልዕክት ነው.፡
ሲፈን በፍጥነት አፈፍ አድርጋ አነሳችው….ድምፃን ከፍ አድርጋ ማንበብ ጀመረች፡፡

I hope you are blessed
With a heart like a wildflower
Strong enough to rise again
After being trampled on
Tough enough to weather
The worst of the summer
and even able to grow and flowrish
In the most broken of places
//
ማን ነበር እነዚህን የሀዘንና የተሰፍ እንጉርጉሮ ያንጎራጎረው.?.እኔ እንጃ ተረሳኝ/እማዬ….አንቺ የአለሞ ቁጥር አንድ እናት ነሽ...በጣም ነው የምወድሸ….ጤነኛም ስሆንም እዕምሮዬም በተቃወሰ ጊዜም ጭመር አንቺን ባለመቋረጥ እወድሻለው…እናም ደግሞ ከሞትኩ ቡኃላም እንደምወድሽ እንዳትጠራጠሪ፡፡ደምፅሽ እያወራሽኝ ሁሉ ይናፍቀኝ ነበር፤.ጠረንሽ ጉያሽ ተሸጉጬ እራሱ እራበዋለው…እማዬ ጥዬሽ ስለሞትኩ በጣም አዝናለው….ግን የግድ ማድረግ ስላላብኝ ነው፡፡አዎ በፍጥነት ውሳኔ ወስኜ እራሴን ካላጠፋው የምወዳትን ልጅ አጠፋለው….እሷን ገድዬም ደግሞ ብተርፍ አንድ ነገር ነበር …..ከገደልኮት ቡኃላ ደግሞ እራሴን ማጥፋቴ የማይቀር ነው..ሁለት ኪሳራ.፡፡..እና እማዬ ይቅር በይኝ…
ሲፈን ….አንቺ በነፍሴ የማፈቅራት ልዩ ሴት ነሽ….በጣም ልዩ ሴት..፡፡በንግግርሽ በጣም ከመደንዜ የተነሳ የእውነትም አንቺን ስለማግባት እያሰብኩ ነበር…ቃል እንደገባሽልኝ ገነት መሳይ በተፈጥሮ ያሸበረቀች ልዩ የብቻችን ቦታ ወስደሺኝ .እዛ ጎጆችንን ቀልሰን ..ልጆቻችንን ወልደን….ብርቱካንና መንጎ ከጎሮ እየቀነጠስና…ጥልል ባለ የወንዝ ውሀ ገላችንን እየታጠብን …በዝሆንና ቀጪኔ ጀርባ ላይ ሰርከስ እየሰራን..ብዙ ብዙ ነገር እንዳልም አድርገሺኛል….
ግን አንዳንዴ መራር ቢሆን እውነታን መጋፈጥ የጀግኖች ባህሪ ነው.እና እኔም ጀግና መሆን ወሰንኩ…፡፡ለአንቺ ህይወት የሚበጀውን ዘላቂ ነገር ማስብ እንዳለብኝ ወሰንኩ…አንቺን አንቄ ከመግደሌ በፊት እራሴን ማንጠልጠል እንዳብኝ ወሰንኩ…፡፡.እንደዛ ያደረኩት ለአንቺ አስቤ አይደለም፡፡.ጥዬሽም ለመሄድ አንጀቴ ጨካኝ ሆኖ አይደለም…አብረን ብንሞት እና አንድ መቃብር ብንቀበር ደስ ይለኝ ነበር…ግን እንደዛ ማደርረግ አልቻልኩም .፡፡ለምን? ለልጃችን ስል፡››
.ማንበቧን አቋረጠችና አንዴ ፕሮፌሰሯን አንዴ ኢንስፔክሩን እያፈራረቀች ተመለከተች‹‹..የምን ልጁ?››
ፕሮፌሰሯ ትከሻዋን በመነቅነቅ ‹እኔ ምን አውቄ ›የሚል መልስ ሰጠች..
እንስፔክተሩ ‹‹ማንበብሽን ቀጥይ ›› አለት
ማንበብ ቀጠለች…
‹እማዬ እና ሲፈን…እድለኛ ከሆንኩ አንድ የምስራች ልንገራችሁ…ማለቴ ይሄን ደብዳቤ ከማንባችሁ በፊት በሌላ መንገድ ዜናውን ካልሰማችሁ ማለቴ ነው፤እማዬ ልጅ ትቼልሽ ነው የሞትኩት…የልጅ ልጅ ሊኖርሽ ነው..ሲፈን እርጉዝ ነች የእኔ .ል..ጅ…..አርግዛ..ለች.›
ሲፈን ከመቀመጫዋ ተነሳች..ሆዷን በእጆቾ ዳበሰች..
‹‹ምን ማለት ነው.?››ማርገዜን እንዴት ነው ያወቀው…?እንዴት እንደዛ ሊሆን ይችላል?››
‹‹ምነው? ግንኘነት አልፈፀማችሁም እንዴ…?››ኢንስፔክሩ ነው የጠየቃት
‹‹አይ.. እሱማ ፈፅመናል..አዎ በደንብ ፈፅመናል..ግን ያልገባኝ እኔ ማርገዜን ሳላውቅ እሱ እንዴት..?ደሞ እኮ ምንም አይነነት የእርግዝና ምልክት እየታየብኝ አይደለም››
‹ኢንስፔክተር ይቅርታ አድርግልን ከፈለከን በሚመችህ ሰዓት ተመልሰን መምጣት እንችላለን ..አሁን ሆስፒታል ሄደን ይህንን ተአምር ማረጋገጥ አለብን.››ከመቀመጫዋ ተነስታ ሲፈንን እየጎተተች የኢንስፔክተሩንም ይሁንታ ሳትጠብቅ ይዛት ወጣች፡፡ወደ ሆስፒታል፡
///
አለም በምንም ጉዳይ ላይ ሚዛን የምትጠብቅበት የራስዋ የሆነ ስውር ቀመር አላት…፡፡ገፍትራ ከገደል አፍፍ ላይ ብትጥለንም ስንወድቅ ግን አስከመጨረሻው ተሰባብረን እንዳንደቅ ማረፊያችንን በተደላደለ የሰንበሌጥ ሳር አልብሰሳ ትጠብቀናለች ፡፡ድንገት ሳናስበው በአስፈሪ የአዞ አፍ ተሰልቅጠን ብንዋጥም ሆዱን ሰንጥቀን አረሳችን ነፃ የምናወጣበት ጩቤ ከጎናቸን እናገኛለን፡፡
ቢላለ በምን አይነት ተአምር እንዳወቀ ለሁለቱም እንቆቅልሽ ቢሆንባቸውም በምርመራ እንዳረጋገጡት ሲፈን የሶስት ሳምንት እርጉዝ ነች፡፡አዎ ከጭለማ ቡኃላ ብርሀን ይፈነጥቃል..ከምሽት ብሃል ንጊት አይቀሬ ነው….ከስቅለት ቡኃላ ትንሳኤም የሚጠበቅ ነው…በሁለቱ ሴቶች በሀዘን የደቀቀ ልብ ውስጥ የሆነች ብጣቂ ተስፋ ለመነቃቃት ስትንፈራገጥ ትታያለች፡፡

ይቀጥላል...

#ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀረዉ!!

┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿

                  💗

https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama

                   💗

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

20 Feb, 18:26


😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 43
.
.
#ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀረዉ!!
.
.
ፀሀይ በደመቀ ብርሀኗ እና ለብ ባለው ሙቀቷ በፈገግታሽ ብትወጣም ሰዓቷን ጠብቃ መክሰሟና መጥለቋ አይቀሬ የተፈጥሮ ግዴታ ነው..ጨረቃም ምሽቱን ጠብቃ በዝግታ እየተሳበች በመውጣት ሰማዩ ላይ በመገማሸር ብርሀኗንም ውበቷንም ብተረጭም ንጊት ሲቃረብ መጥፋቷ የሚጠበቅና የግድ የሆነ የተፈጥሮ ግዴታ ነው፡፡ደጅ ላይ የተተከለ አበባም ፈንድቶ በማዓዛውም በውበቱም አካባቢውን አድምቆ ለንቦችም ለቢራቢሮዎችም የሚገባቸውን ምግብ ያለስስት ለግሶ የማታ ማታ ወይ በአንድ አድናቂው ተቀንጥሶ ወይ ደግሞ በራሱ የተፈጥሮ ኡደት ጊዜው ደርሶ መድረቁና መርገፉ የማይቀር ነው፡፡
ሰውም እንደዛ ነው፡፡ከተወለደ..መቼም ይሁን መቼ የሞት ዕጣ እንዳለበተ ቅንጣት የማያጠራጥር ንፅህ እውነት ነው፡፡እንደውም ለሰው መለቀስ ካለበት ተክክለኛው ወቅት ሲወለድ ነው፡፡ብልሁ ሰው ለሞት ቀለብነት እየተፈጠረ ነውና፡፡ዳሩ ሰው ሰው የሚሆነው ምንአልባት ለእናት ካልሆነ በስተቀር ለሌላው ሰው ቅርፅ የሚመዘን ውበት የሚኖረው ከተወለደ ብኃላ በእድገቱ እና በኑሮ ውጣ ውረዱ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር በሚፈጥረው መስተጋብር ፤በእያንዳንዱ ነጠላ ገጠመኝ በየግለሰቦቹ ልብ ውስጥ ባለው ግዛት የሚገነባቸው የትዝታ ግንባታዎች አይነት ነው ፡፡
አንዳንዱ እድሜ ልክ አጠገባችን ኖሮ በውስጣችን ያለው ትዝታ ከእጅ መዳፍ የማይበልጥ ይሆናል...ሌላው ደግሞ ሶስት ቀን ስራችን ቆይቶ ሀገር የሚያህል ግዛት በልባችን ተመርቶ በደግነት ጡብ የታነፁ በፍቅር ልስን ያማሩ ለዘመነት የሚበቁ የትዝታ ግንብ ገንብቶ እናገኘዋለን፡፡
ቢላል በሲፈን ልብ ውስጥ የፈጠረው እንደዛ አይነት ታአምር ነው፡፡እንደውም ከዛም በላይ ነው.፡፡ለሰው ሊያስረድት ከሚችሉት በላይ...ለራስም አስበው ሀሳቡን ለመቋቋም ከሚችሉት በላይ…በመኖር እና ባለመኖር መካከል ያለች የሳሳች በጣም ቀጭን የህይወት ክር ላይ አንጠልጠሎ የሚያላጋ ስሜት ላይ የሚያስቀምጥ፡፡
ሙሉ በሙሉ ጥቁር ለብሳለች….ከለቅሶ ብዛት አይኗቹ ከተገቢው በላይ ማበጣቸው ካደረገችው ግዙፍ ጥቁር መነፅር እንኳን ሙሉ በሙሉ ሊከልላቸው አልቻለም፡፡ከሁለት ቀን እራስን የመሳትና የሆስፒታል ቆይታ ቡኃላ ነው እንደምንም ተደግፋ ቀብር ላይ የተገኘችው፡፡የፕሮፈሰሯ ሆነ የእሷ ቤተሰቦችና ወዳጇች በብዛት ተገኝተዋል፡፡ከዛም በላይ ወሬ ቃራሚ የሚዲያ ሰዎች ከለቀስተኛው ጋር በመመሳሰል ፤ አንዳንዱ መንነታቸውን የሚለይ ባጅ አንገታቸውን አንጠልጥለው በግልጽም ተገኝተዋል፡፡
የቀብር ፕሮግራሙ ብዙ ሀሜቶችና ጉረምርማተዎች የታጀበ ነበር....የአልቃሹ ቁጥር የአንድ ሰው የእጅ ጣት አይበልጥም…በሀዛን የተሰበሩት ፤.ከልባቸው በመንሰፍሰፍ የሚያለቅሱት ደግሞ ፕሮፌሰሯና ሲፈን ብቻ ናቸው….እርስ በርስ የእየተቃቀፉ..እርስ በርስ እየተደጋገፉ…እርስ በርስ እየተፅናኑ ይህንን የጨለማ ቀን ግዙፍ ተራራን ለመግፋት እየጣሩ ነው….ከገቡበት ጥቅጥ የብቸኝነት ጨለማ ዋሻ በእንዴት አይት ፅናት ገብተው ሳይፈራርሱና ማንነታቸውን ሳያጡ ከዚህ ክፉ ፈተና እንዴት ማገገም እንደሚችሉ በየልባቸው እየተማከሩ ነው፡፡
ቀብሩ ከተጠናቀ ብኃላ ያው በደንቡ መሰረት ቀጥታ ወደፕሮፌሰሯ ቤት ነው ያመሩት ፡፡ቤተሰቦቾም ሆኑ ሄኖክ ከሚከታተሏት ሰዎች ጋር የነበራቸውን ውል ሙሉ በሙሉ አቋርጠዋል፡፡እናም አሷ ግድ ባይኖራትም አሁን በየሄደችበት እየሄደ የሚከታተላት ሰው ከጀርባዋም ሆነ ከፊቷ የለም፡፡
///
..ቀብሩ ከተጠናቀ በሶስተኛው ቀን ቡኃላ ፕሮፌሰሯ እና ሲፈን ፖሊስ ጣቢያ ተጠሩና ሁለቱም በአንድላይ መርማሪ ፖሊስ ፊት ለፊት ቀረቡ፡፡
‹‹ከቢላል ጋር ያላችሁን ዝምድና ወይም ግንኙነት?››የፖሊሱ ጥያቄ ነበር
‹‹ሁለቱም ተራ በተራ አብራሩ››
‹‹ሲፈን ..ቢላልን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሽው መቼ ነው?››
‹‹ከሞቱ ከስድሰት ወይም ከሰባት ሰዓት በፊት››
‹‹የት ?››
‹‹እቤቴ ማለት አባቴ ቤት እኔ ክፍል››
‹‹ምን ሊሰራ ነበር የመጣው ..?››
‹‹ያው እደነገርኩህ ቤላል ጓደኛዬ ነው…ድንገት ከተሰወረ ከ22 ቀን ቡኃላ ለሊት ላይ የቤታችን ጣሪያ ቀዶ ነበር የገባው…እና ያንን በማደረጉ በነፍሴ ጭምር ነበር የተደሰትኩት፡፡ ከዛ ቡኃላ በተከታታይ ሀያ ለሚሆኑ ቀናት ከዛ ክፍል አልወጣም ነበር.››
‹‹ሀያ ቀን ሙሉ››
አዎ …ብዙ ነው እንዴ …?.ለእኛ ግን የሁለት ቀን ያህልም ርዝመት አልነበረውም….እንዴት መሽቶ እንዴት እንደሚነጋ አናውቅም ነበር…ዋናው ጭንቀታችን የእሱን እዛ መኖር እቤተሰቦቼ ወይም ሌላ ሰው እናዳያውቅ ማማረግ ነበር.ያም ተሳክቶልና.፡፡.በህይወቴ ትልቅ ትርጉም ያለው የሚገርም ጊዜ ነበር ያሳለፍነው….እድሜ ልኬን ከእዛ ክፍል የመውጣት እቅዱም ፍላጎቱም አልነበረኝም…የውጩን አለም ጠቅላላ ዘንግቼው ነበር..ምንም የሚናፍቀኝ ነገር አልነበረም…ስራዬ..ሀብቴ ሰሜ ..በእቅፌ ከነበረው ቢላል ጋ ሲነፃፀሩ ምንም ትርጉም አልነበራቸውም፡፡››ረጅም ትንፋሽ ወሰደችና በጉንጮቾ ላይ ያለከልካይ የሚፈሰውን እንባ በሶፍት መጠራረግ ጀመረች…ከዛ ፀጥ አለች
‹‹ቀጥይ ..እየሰማውሽ ነው››አንስፔክተሩ ነው በገለፃዋ እንድትቀጥላ ያበረታታት.ፕሮፌሰሯ በእንባ ከማገዝ ውጭ በዝምታ እንደተዋጠች ነው፡
‹‹ወደዋናው ነጥብ ልምጣልህና የሞተ ቀን ማለቴ አሁድ አብረን በደስታ አደርን ጥወታ በማለዳ ነቃንና ….ብዙ የደስታ ወሬዎች አወራን...ሳቅን.. .ተላፋን…..የምንወደውን ሙዚቃ በአንድ ኤሮፎን አዳመጠን….ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ልክ እንደሌሎቹ ቀናት የምንበላውን ቁርስ ለማምጣት በውጭ ቆለፍኩበትና ወደኪችን ሄድኩ፡፡ ብዙም አልቆየውም .. ከ10 ወይም ከ12 ደቂቃ ቡኃላ የምንበላውን ቁርስ ይዤ ስመጣ ክፍሉ ባዶ ነበር…ሻወር ቤት ፈልኩ ..አልጋ ስር ሳይቅር ፈለኩ…በጣም ደንገጥኩ.. ልጮህ ሁሉ ነበር፣.ቡኃላ ጠረጳዛ ላይ መልዕክት ትቶልኝ ነበር›
‹‹ምን ይላል መልዕክቱ?››
‹‹እማዬ ናፍቃኛለች…እሷ ጋር ሄጄያለው…በተለመደው መልክ ማታ ተመልሼ መጣለው…በጣም እወድሻለው›› ይላል፡
ከዛ ተረጋጋው.‹. ቢሆንም መንገድ ላይ አደጋ ያጋጥመው ይሆን…?› የሚል ስጋት ስላለብኝ ከአንድ ሰዓት ቡኃላ መሰለኝ ለፖሮፌሰር ደወልኩና ጠየቅኳት ..በደስታ እሷ ጋር እንዳለ ነገረችኝ..፡፡
ከዛ ቡኃላ በቃ ሰባት ሰዓት ላይ ተደውሎልኝ እራሱን አጥፈቷል ተባልኩ…መአት ነው የወረደብኝ…ከከረምኩበት ገነት የሆነ ክፉ አጋንንት በእንዴት አይነት ፍጥነት አሽቀንንሮ ሲኦል እንደጨመረኝ አልገባኝም…አለም ግን እንዴተ አስቀያሚ ነች….ጠንካራ አለት ነው ብዬ የቆምኩበት አፈር ነው ድንገት ተደርምሶ እንጦሮጦስ ወስዶ ያሰመጠኝ፡፡››በእንባዋ እየታጣበች በመሪር ሀዘን የነበረውን ነገር አስረዳችው፡፡
‹‹እሺ ፕሮፌሰርስ?››
‹‹እሷ እንዳለቸው ነው.ሶስት ሰዓት ሲሆን ሳሎን ቁጭ ብለን ቁርስ አየበላን ሳለ . በሩ በዝግታ ተከፈተ… አይኔን ወደዛ ስልክ የእኔ ምስኪን ልጅ ነበር..፡፡ብታይ አምሮበታል…እነዛ ሰማያዊ አይኖቹን እላዬ ላይ ሲያንከባልላቸው የተሰማኝ የደስታ ስሜት ልግልፃልህ አልችልም...ከአርባ ምናምን የጭንቅ ቀን ቡኃላ ነበር ልጄን ያቀፍኩት …እቤቱን በጪኸት አስነካውት፤ ግቢው ውስጥ ያሉት ሰዎች ሁሉ ተሰበሰቡ ፡፡

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

19 Feb, 20:50


ሰላም ለእናንተ ይሁን። የተወሰኑ ችግሮች ስለገጠሙኝ ነዉ የተጠፋፋነዉ። ፈልጌዉ ባልጠፋም ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏 ታሪኩን ሰሞኑን የምፅፍላችሁ ይሆናል። ሁላችሁንም ከመጥፎ ሰዎች ይጠብቃችሁ!!

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

10 Feb, 17:35


‹‹እሱ ብቻ አደለም ችግሩ በአንቺ ደረጃ ያሉ ሰዎች እርቴፌሻል ህይወትና  ነው  ያላቸው..እያንዳንዷን በእለት ውሎቸው የሚከውኗቸው  ነገሮችን  እቅድ በሚል ስም መጀመሪያ በወረቀት ላይ እስክሪፒቱን  ይጻፍና   ከዛ ሳያዛንፉ ሲተውኑ ይውላሉ.. ንግረግራቸው በተመረጠና የሆነ ውጤት እንዲያመጣ በተሰላ መንገድ የሚነገር…አለባበሳቸው የሆነ መልዕክት የሚያስተላልፍ …አበላላቸው.አጠጣጣቸው..ሁለነገራቸው አርቴፊሻል ነው..እና ባለሽበት ተውኩሽ››..
‹‹በነፈስ ማፍቀር እንዲህ ለመተው ቀላል ነው እንዴ?››ሞጋች ጥያቄ ጠየቀችው፡
‹‹አዎ ..አልከበደኝም.፡፡ምክንያቱም እኔ ማስባትን አይነት እንደሆንሽና የሆነ በደን በተከበበ   የአራዊት ማጎራት በቅርብ በሚሰማበት.፤የወፎች ዝማሬ መንፈስን በሚያድስበት፤ ፎፎቴ  ከተራራው አናት ከሚከነበልበት፤ ልዩና ንፅህ ቦታ ልክ እንደሄዋን በቅጠል እፍረትስጋዋን ብቻ ሸፍና ከእንጨት ተጠርቦ የተሰራና በሀረግ የተጠቀለ ጫማ አድርጋ፤ ፀጉሯና ከወዲህ ወዲያ ንፋስ እየተበተነባት፤ ከበለስ ግንድ ላይ የበሰለውን ስትቀነጥስ በምናቤ እያየውና  እየጎመዣው እችለዋለው፡››
‹‹ስለገኘኸን እና እንዲህ ስለሆነ ቅር ብሎሀል?››አለችው ቅር በተሰኘ የስጋት ድምፅ
‹‹አላለኝም ..ምክንያቱም የዛን ጊዜ ስለአንቺ  የወሰድኩት  ግምቴ ላይ  ግማሽ  ሰህተትም ነበረበት››
‹‹እንዴት?››
‹‹…አንቺን  ፍጽም አርቴፊሸል ሴት እንደሆንሽ መገመቴ  የእኔ  ስህተት ነበር  ፡፡ያንን ስህተን ደግሞ የተረዳውት አሁን ባልሽው ለመጀመሪያ ቀን ሻወር ፍለጋ እቤቴሽ መጥቼ ዘበኛሽ  አበሻቅጦ ሲመልሰኝ አንቺ ተቀበለሽ በሳተናገድሺኝ ቀን ነው፡፡በአንቺ ቦታ እና ደረጃ ያለች ሴት የፈለገ በውስጧ ብትፈልግ እንኳን  እንደእኔ አይነት ሰውን ወደቤቷ አታስገባም…››
‹‹እና የመጀመሪያውን ፈተና በመጀመሪያው ቀን አልፍኩ ማለት ነው››
‹‹አዎ…..እስከአሁንም ያልተቀየረ ፅናት ነው ያለሽ….ከልብሽ ለሚፈልቀው  እውነት በዓለም ፊት በድፍረት የመቆም ፅናት . ..››
‹‹እሺ ትክክል የሆንከውስ?››
‹‹….አነቺ ተራ ሰው ባለመሆንሽ በዙሪያሽ ብዙ ጣጣ እንዳለ መገመቴ ትክክል ነበርኩ፡፡እንቺ ባትፈልጊም በዙሪያሽ ብዙ ኮተትና  እና ግሳንግስ መኖሩን አይቀሬ ነው…ለምሳሌ ልታገቢው ቀለበት ያሰርሽለት ሰው...››
‹‹ሄኖክ ..እሱ ምን  ሆነ?››
‹‹ያፈቅርሻል አውቃለው….ግን  ካንቺ በላይ ንብረትሽንና ዝናሽን ነው የሚያፈቅረው..ያንንም የማሳጣው ስለመሰለው ሊያስገድለኝ አራት ሰው ቀጥሯል…››
‹‹እንዴ !!!አንተ ይሄንን እንዴት ልታውቅ ቻልክ..?››
‹‹ይሄንንም አልነግርሽም…ደግሞ ቤተሰብ የለኝም እንጂ ጓደኞች የሉኝም አላልኩሽም… በመጀመሪያ እኔን መስሎቸው ለገደሉትና ከዚህ አለም መከራ ለገላገሉት ሰው 1 ሚሊየን ብር ከፍሎቸው ከስሯል…አሁንም ሁለተኛ ስመምነት በስድስት መቶ ሺ ተስማምተው ቅድመ ክፍያ 150 ሺ ብር ከፍሏቸዋል.ከአንቺ ከመገናኘቴ  በፊተአግኝተው ሊገድለኝ መከራቸውን እየበሉ ነው ››
‹‹ምንድነው የምታወራው…?››
‹‹ከፈለግሽ  ግድያውን የመራውን ግለሰብ ስም ..የተጻፈለትን ቼክ እና ቼኩን የመነዘረበትን የባንክ ቅርንጫፍ ሁሉ ልነግርሽ እችላለው..ከዛ አንቺ ደግሞ ባለሽ ተፅዕኖ በቀላሉ ማረጋገጥ ትችያለሽ፡፡እናም ደግሞ ትዕዛዙን ሲያስተላልፍ ገዳዩ ቀድቶታል….እኔ ደግመ ሞባይሉን በሆነ መንገድ ተቀብየዋለው..ከፈለግሽው ጃኬቴ ኪሴ ውሰጥ አለልሽ..››
ከመኝታዋ ተስፈንጥራ ተነሳች….ጃኬቱ ወደተንጠለጠለበት የልብስ መስቀያ አመራች…ደልደል ያለ ሰውነቷንና  የሚገለባበጥ መቀመጫዋን በተኛበት በስስት እያየ ነው…እጇን በጃኬቱ ኪስ ውስጥ ከተተች..ለመጀመሪ ጊዜ እጇ  ላይ የገባላትን አወጣች...አብረቅራቂና ስል ጩቤ ነው.አገላብጣ አያችው..አይኗን ወደቢላል ላከች…መልሳ እጇን ወደጃኬቱ  ኪስ  ሰደች…አሁንም ያገኘችውን ነገር ይዛ ወጣች...በግምት 10 ሜትር  የሚረዝም ጠንካራና መካከለኛ ውፍረት ያለው  ሲባጎ ገመድ ነው…ዝግንን አላት…፡፡ይህን ጩቤም ሆነ በእጇ  የያዘችውን  ገምድ ታውቀዋለች…ቢላል በጠፋ ቀን ጥሎላት በሄደው ስዕል ላይ ጩቤው እሷ የታረደችበት አይነት ሲሆን ገመዱ ደግሞ እሱ የተሰቀለበት ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ነው››
‹‹ምንድነው ይሄ››አለችው ሁለቱንም እጇን ወድሱ እየዘረጋች
‹‹አጥር ዘልዬ ጣሪያቸሁን  ቀድጄ እኮ ነው እዚህ ስርሽ የተገኘው…ይሄን ሁሉ ደግሞ ባዶ እጄ ብቻ ላደርገው አልችልም…በዛ ላይ..››
‹‹በዛ ላይ ምን?››
‹‹ተይው …ስልኩ በደረት ኪስ ውስጥ መሰለኝ ያለው ››.
የያዘችውን ጩቤና ገመድ ጠረጳዛው ላይ  አስቀመጠችና ወደጠቆማት ኪስ እጇን ሰደደች .. .ዘመናዊ ሳምሰንግ ስልክ አገኘች፣ይዛ ወደአልጋው ተመለሰች… .ከፍቶ  እንዲያሰማት አቀበለችው..
የሶስት ደቂቃ ቆይታ ያለውና ሌላ ደግሞ የ5 ደቂቃ ቆይታ ያለው የስልክ ልውውጥ ነው…እሷን እየተከታተሏት መሆኑን..ቢላል እንዲገደል የተሰጠ ትዕዛዝ..የልጁ በስህተት መገደል….ሁሉን በግልፅ ያሰርዳል፡፡
‹‹ወይኔ ምኗ  ጅል ኖሬያለው…ወደስልኬ ላክልኝ፡፡››
‹‹አረ እኔ ምን  ያደርግልኛል.ስልኩን እኮ ለአንቺ ነው ያመጣውት..ከፈለገሺው ማለቴ ነው፡፡››
‹‹አረ በጣም  ነው የምፈልገው…..በል አሁን ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሆነ እኮ… ትንሽ እንተኛና ምን እንደምናደርግ ሲነጋ እናወራለን››
‹እሺ እንዳልሽ….››
ማብራን ተንጠራርታ አጠፋችና እቅፉ ውስጥ ተሸጎጠች…ለተወሰነ ጊዜ እንቅልፍ እንዲወስዳት በመፈለግ ተገለባበጠች ..ግን ሊወስዳት አልቻለም‹ቢላሌ›በለሆሳሳ ድምፅ ተጣራች፡
‹‹አቤት የእኔ ፍቅር››
‹‹ብንጋባ ምን ይመስልሀል?››
‹‹እየቃዠሽ ነው እንዴ?››
‹‹አይ እውቴን ነው….››
‹‹እብድ አግብተሸ አንዴት እንዴት ልትሆኚ ነው..?በዛ ላይ ከእብድ መውለድ አለ…ነው ወይስ አሁን ጤና ስለሆንኩ  ሁልጊዜ እንደዚሁ የሚቀጥል መሰለሽ›
‹‹ግድ የለህም ..ከእኔ ጋር ከተጋባህ ለዘላለም ጤነኛ ትሆናለህ…ባትሆንም ደግሞ ከጎኔ እስካለህ ድረሰ ግድ የለኝም…››
‹‹አይ ሚሆን አይመስለኝም…..ቅድም እኮ ነገርኩሽ .አንቺ ብዙ ጣጣ ያለብሽ የአደባባይ ሴት ነሽ›
‹‹ለአንተ ስል ሁሉን ነገር ተዋለው.በእዕምሮህ ያለችውን አይነት ሴት ሆንልሀለው…እልም ያለ ገጠር እንገበለን በደን የተሸፈነ ፤እንስሳት የሚተረማመሱበት፤ ወፎች የሚደንሱበት ፤የሰው  ግርግር የሌለበት አንድ አነስተኛ ገነት መሳይ  ደሴት እንገዛና እዛ እንኖራለን….›
‹‹ወይ .ለዚህ እኮ ነው በነፍሴ የማፈቅርሽ..እና ደግሞ በጣም ነው ያስጎመዠሺኝ ….ግን ሌላ  ሁለት ችግር አለ››
‹‹ምንና ምን?››
‹‹አንደኛው የአባትሽ ጉዳይ ነው…ጋብቻሽን በተመለከተ ስለተፈራረምሽው ውል አውቀለው››
‹‹አሱን  ለእኔ ተወው የሆነ መፍትሄ አገኝለታለው…ሁለተኛውን ችግር ንገረኝ››
‹‹ሁለተኛው እረሴው ነኝ…እስከዛው ካልገደልኩሽ….›
‹‹ከገደልከኝማ ተገላገልን …ሁሉ ነገረ እዛ ላይ ይገባደዳል››
‹‹እንደዛ ከሆነ እሺ…ምን አልባት ልንጋባ እንችላለን…አሁን ደህ እደሪ››
‹‹ደህና አደርልኝ.››
‹‹ጭኑ መካከል  አስገባትና ቅልፍልፍ ብለው ተኙ…ሁለቱም በደቂቃዎች ውስጥ ነበር ጭልጥ ያለ ሰላማዊ እንቅልፍ  የወሰዳቸው፡፡


ይቀጥላል ....


┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿

                  💗

https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama

                   💗

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

10 Feb, 17:35


😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 42
.
.
///

ሁለቱም ነጭ ፎጣ ከወገባቸው በታች አገልድመው ጣጣቸውን ጨርሰው   ከሻወር ወጡ..አልጋው ጠርዝ ላይ  ጎን ለጎን ተቀመጡ..
‹‹እርቦሀል?›› አለችው::
‹‹በጣም….መቼ ምግብ እንደበለው አላስታውስም››መለሰላት፡፡
‹‹እንግዲያው እንብላ .እኔም እራቴን እስክጠግብ የበላው ቢሆንም አሁን ሆዴ ውስጥ አውሬ እንደታሰረ እየቧጠጠኝ ነው›››አለችና ከመቀመጫዋ  በመነሳት ምግብና መጠጥ የተደረደረበትን አነስተኛ ጠረጳዛ ቢላል ወደ ተቀመጠበት ቦታ እያስጠጋች፡፡
‹‹ቡዙ ኃይል ስላወጣሽ ነዋ….››
‹‹ቀላል ኃይል…ሙጥጥ ነው ያደረከኝ.››
///
ቀላል ጫወታ እየተጫወቱና እየተጎራረሱ ምግብን በሉ…ከሚጠጠውም ጠጡ.
//
‹‹አሁን ብንተኛ ምን ይመስልሀል.?››.
‹‹ደስ ይለኛል››
‹‹ቢጃማ ልስጥሀ?››
‹‹…አንቺን ማረብሽሽ ከሆነ…እንዲሁ ብተኛ ደስ ይለኛል››
‹‹ግድ የለህም በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መረበሽ እራሱ የራሱ የሆነ  ጣፋጭ ጣእም አለው.››
‹‹እንግዲያው አጣጥሚው …››.አለና ያገለደመውን ፎጣ ከላዩ ላይ ተርትሮ አነሳና ጠረጵዛ ላይ አስቀመጠ…መለመላውን  ወደ አልጋው ወጣ ….ገልጦ ከውስጥ ገባ….እሷም ልክ እንደእሱ አደረገች…አዎ ይህቺን ቀን በተደጋጋሚ በህልሟ  አይታታለች….ህልሟ ህልም ሆኖ ይቀራል የሚል ጠንካራ ጥርጣሬ ነበራት….አሁን ግን ይሄው ባላሰበችው ተአምራዊ መንገድ ህልሟን እየኖረችው ነው..…የነፋሷን ጌታ በስጋዋ እቅፍ ከታ..በትንፋሹ ውስጧን እያሞቀች ….በሙቀቱ እየቀለጠች…በደስታ ስካር ላይ ነቸ….ይህ ተአምር ነው፡፡ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች…እጆቹን በአንገቷ ስር  አሸግሮ አቀፋታ አንዱን እግሯን አነሰችና እግሮቹ ላይ ጫነች..አንደኛው  እጇን ደረቱ ላይ አሳረፈችና የደረቱን  ጸጉሮች ማፍተልተል  ጀመረች…..
‹‹ግን  ይሄን ሁሉ ቀናት የት ሄደህ ነበር?››ካገኘችው ደቂቃ ጀምሮ ለመጠየቅ ፈልጋ ግን ደግሞ እስኪረጋጋ በሚል የማዘን ስሜት አፍናው  የነበረውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹እንዲህ በነፍሴ ጭምር ስጨናነቅ የምሄድበት ቦታ››
‹‹እኮ ያ ቦታ የት ነው?››
‹‹እሱን አሁን አልነግርሽም››
‹‹እሺ እንዳሰብከው መሄድህ ጠቀመህ?››
‹‹አንቺ ምን  ይመስልሻል?››
‹‹እሱማ  እንደማይህ በጣም ጠቅሞሀል….ካሰብኩት  በላይ ተረጋግተህል…. ፍፅም ጤነኛ ሆነህ ነው የመጣሀው››
‹‹ፍፅም ጤነኛ አልሽ..ፍፅም ጤነኛ እና ፍፅም በሽተኛ የሚባል ሰው የለም…ሁላቸንም ጤነኝነት እና በሸተኝነትን በደባልነት  አዝለን ነው የምንዞረው …. ልዩነቱ  የመጠን ጉዳይ ነው.እንዳልሺው ግን መሄዴ ጠቅሞኛል….ቢያንስ እስከዛሬ አንቺን አልገደልኩሸም…››
‹‹ለእኔ  ግን  ዝም ብለህ አድራሻህ ሳታሳውቅ እንደዛ ጠፍተህ በፍለጋ ከምታሰቃየኝ ..ብትገድለኝ ይሻለኝ ነበር››
‹‹አዎ እኔም ለብዙ ቀን  በነገሩ ላይ ካሰላሰልኩበት  ቡኃላ‹ ….እስከመቼ ገና ለገና ልገድላት እችላለው በሚል ስጋት  ከእሷም ሆነ ከእናቴ እሸሻለው…?ወደእሷው ተመለሼ እውነታውን መጋፈጥ አልብኝ..ደግሞ እጣፈንታን   ይጋፈጡታል  እናጂ ሸሽተው አያመለልጡትም ›  ብዬ  ወሰንኩ እናም እንደምታይው መጣው..››
‹‹ከግድያ  ወሬ እንውጠና ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ?››
‹‹ያንቺው ነኝ.. .እንደፈለግሽ››
‹‹ስለቤተሰቦችህ››
‹‹ስለቤተሰቦችህ ምን.?››
‹‹ፕሮፌሰር ወላጅ እናትህ እንዳልሆነች አውቄያለው››
‹‹ለእኔ ግን  እንዳዛ አይሰማኝም›
‹‹እሱ ጥሩ ነው…ግን ስለወላጆችህ ምን ታውቃለህ?››
‹‹ምነው አንቺ ስለቤተሰቦቼ የምታውቂው ነገር አለእንዴ ?››
‹‹በፍጽም››
‹‹እንግዲህ እኔም ምንም አላውቅም…እናት፤ አባተ የለኝም፡፡ልጅነቴ ትዝ አይለኝም፡፡የሞለ ህፃናት ቆይታዬ እንዴት እንደነበር አላውቅም…ትምህር ቤት የት ሀገር እንደተማርኩ እንኳን  አላውቅም፡፡.ከአስተማሪዎቼ መካከል አንዱ እንኳን   ትዝ አይለኝም…ግን እንደተማርክ  አውቃለው… በከፍተኛ ደረጃ እውቅ የተባሉ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተምሬያለው….የት ? እኔ እንጃ……ስለ እነዚህ ነገሮች ምንም የማስታውሰው ነገር የለውም..ከልጅነቴ  ጀምሬ ለረጅም  አመት የሆነ ግዙፍ ዋርካ ስር በጥላው ተመስጬ  በመተኛት ወጣትነቴን ካጋመስኩ ቡኃላ ድንገት የነቃውና ስነቃ ደግሞ የፕሮፌሰሯሮ  እጅ ላይ እራሴን ያገኘው ነው የሚመስለኝ፡፡አዎ ያንን ብቻ ነው በግልፅ የማስታውሰው፡፡
‹‹ስለእኔ ምን  ታስባለህ?››ሌላ ጥያቄ
‹‹ስለአንቺ ምን?››
‹‹እንዴት ልታፈቅረኝ ቻልክ….?መቼስ እንደሌላው ገንዘቤ ላንተ ትርጉም እንደማይሰጥህ አምናለው…መልኬ …?ንግግሬ…  ?ምኔ..?
‹‹ከዚህ በፊት የነገርኩሽ መስሎኝ..›
‹‹ለእኔ?››
‹‹አዎ ለአንቺ…የማፈቅረው ነፍስሽን ነው ብየሽ ነበር››
‹‹አዎ አስታውሳለው….እሱ ግን   አገላለፅ እኮ ነው…ነፍስ ተጨባጭና ተዳሳሽ አይደለችም››
‹‹ፍቅርም ተጨባጭና ተዳሳሽ ቁስ አይደለም..ግን ግልፅ ለማድረግ በነፍሴ ነው ያፈቀርኩሽ ሰል ላስረዳሽ የፈለኩት  ያወቅኩሽ ወይም ያፈቀርኩሽ በአካል ያገኘውሽ ቀን እንዳልሆነ ለመግለፅ ፈልጌ  ነው››
ወደምትፈልገው መስመር እየገባላት ሰለሆን በአድናቆት ከደረቱ ቀና በማለት  ተንከባላይ አይኖቹን በፍቅርና በጉጉት እያች‹‹ይበልጥ አብራራልኝ.››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እብድ ባልሆን ኖሮ ይሄንን ማስረዳት ይከብደኝ  ነበር…ግን ምንም አይነት ወጣ ያለ ነገር ብናገር ወይም ያልሆነ ነገር ብሰራ እብድ ስለሆነ ነው ስለሚባል ብዙም አያስገረምም. .እኔ አንቺን ከማግኘቴ በፊት፤ እቤትሽ ከመምጣቴ በፊት፤ ከፕሮፌሰሯ እናቴ ከመገናኜቴም በፊት፤ ምን አልባትም ከመወለዴም በፊት ይመስለኛል የማውቅሽ…..አማዬ  አልነገረችሸም እንዴ አንቺን ከማግኘቴ በፊት ገና ሆስፒታል በሰንሰለት ታስሬ ስታከም እራሱ ያንቺን ስዕል እየሳልኩ አሳያት ነበር…እሷ እንደውም ወላጅ እናቴ ወይም  እህቴን የምስል ይመስላት ነበር…አሁን ነው ነገሩ የገባት….››
‹‹ስለዚህ መጀመሪያ እቤቴ መጥተህ ሻወር ፈልጋለው ብለህ ያስደመምከኝ  ሆነ ብለህ ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹በፍጽም …ለምን እንደዛ  አልሽ..?››
‹‹በወቅቱ ሰታየኝ ብዙም የተለየ ነገር አላሳየህማ…የዛን ቀን በአካል ያገኘኸኝ የመጀመሪያ ቀን ቢሆን ኖሮ ያሰታውቅብህ ነበር.››
‹‹እውነትሽን ነው….በአካል ሳይሽ ያ የመጀመሪያ ቀኔ አልነበረም…ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬ አመት አካባቢ ስለካማፓኒሽ በቲቪ  መግለጫ ስትሰጪ  ነበር ያየሁሽ..
‹‹እና ምን አደረክ?››
‹‹ምንም አላደረኩም….በወቅቱ  ሰውነትን በጠቅላላ የሚነዝር የደስታ ስሜት ነበር የተሰማኝ….ሙሉ እብድ እንዳልሆንኩ ያወቅኩት የዛን ቀን ነው…..ምክንያቱም ተጨባጭ ነገሮችንም በአዕምሮዬ  አለማለው ማለት ነው የሚለውን የአንቺ የሆነ ቦታ በአካል እውን ሆኖ መገኘት ማረጋገጨ ሆነኝ .ይሁን እንጂ  እኔ በነፍሴ አፍቅሬያት በእየእለቱ እያለምኳት የነበረችው ሴት ተራና  ንፅህ   የመንደር ሴት እንድትሆን ነበር ፍላጎቴ…ከተቻለ ጭልጥ ያለ ገጠር የምትኖር .
‹‹አና እኔ ንፅህ አይደለውም ማለት ነው.?.››

https://t.me/ethiofilm2adey_drama

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

10 Feb, 12:25


ታሪኩን መልቀቅ እንዳለብኝ ለመወሰን እንዲረዳኝ ነዉ። ምን ያህሎቻችሁ ቴሌግራም እየሰራላችሁ ነዉ? Like በማድረግ አሳዉቁኝ ።

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

05 Feb, 18:26


😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 41
.
.

//

ሄኖክ ነገሮች ሁሉ ከእቅድና ከቁጥጥሩ ውጭ እያፈተለኩ ተቸግሯል።‹‹ፊት ለፊት ተቃጥረውና ተዘጋጅተው የሚገጥሙት ጠላት እንዴት የተባረከ ነው›› አለ.‹‹.እኔ ነኝ እንጂ ከመንፈስ ጋር ድብብቆሽ የምጫወት"ሲል ተማረረ......አሁን ቢላል እስኪገኝና በቀጠራቸው ሰዎች እስኪያስገድለው ድረስ ዝም ብሎ እያማረረ ከሚቀመጥ መስራት የሚችለው አንድ ነገር እንዳለ ተሠማው....ከሲፈን ጋር ያለውን የሻከረ ግንኙነት ማለስለስ...አዎ ይሄ ሁሉ ፈተናና ውጣ ውረድ እሷን የራሱ ለማድረግ ነው...ከሰሞኑ ደግሞ በመካከላቸው በተፈጠረ ተደጋጋሚ ግጭት እና መፋተግ የተነሳ በጣም እንደተራራቁ ይሰመዋል ..ደግሞም ተራርቀዋል፡፡:ስልኩን እንኳን ማንሳት ካቆመች ቀናቶች አልፈዋል...፡፡ይሄም ቢሆን ግን በህይወቱ ሌላ ጥሩ ዜና አልጠፋም. …ከእሷ አባት ጋር ተዋውቀዋል..ከዛም አልፈው እሷን በተመለከተ ሊመካከሩና መፍትሄ ሊያበጅ ከሶስት ጊዜ በላይ በአካል ተገናኝተው አውርተዋል...በእሷ ላይም ዶልተዋል።ይሄንን ጉዳይ እሷ ፈፅሞ አታውቅም።
እና ለሄኖክ ከሲፈን ጋር ቀለበት ካሠረበት ቀን ብኃላ የገጠመው አንድ መልካም ነገር ከአባትዬው ጋር የፈጠረው መግባባትና በመተባበር ለአንድ አላማ አብሮ መስራት መቻሉ ብቻ ነው፡፡..እና አሁን ከሲፈን ጋር የተፈጠረውን መሻከር ለማለዘብ ሽማግሌ በሚቀጥለው እሁድ መላክ አለበት ..ይሄ የእሱ ብቻ እቅድ አይደለም የሲፈን አባትም ምክር አለበት...ክፍሉን ለቀቀና ወደ አባቱ ክፍል አመራ...አንኳክቶ ገባና ቀጥታ ወደጉዳዩ ገባ
"አባዬ በዚህኛው እሁድ ሌላ ኘሮግራም እንዳይዙ ለሽማግሌዎቹ ደውልና ቀድመህ አሳውቃቸው"
‹‹እሺ..እደውልላቸዋለው..አንተ አታስብ"
‹‹እሺ አባዬ አመሰግናለው"አለና እንደአመጣጡ በፍጥነት ፊቱን አዙሮ ሊሄድ ሲል "ሄኖኬ"ጠሩት
‹‹አቤት አባዬ››
አንድ ነጭ ፓስታ አቀበሉት‹‹ምንድነው አባዬ?››
‹‹አላወቅኩም...ሲፈን ነች የላከችልህ"
የሲፈንን ስም ሲሰማ ጊዜ አላጠፋም …ተስገብግባ የመንጠቅ ያህል ከአባቱ እጅ ፓስታውን ተቀበለና ወደክፍሉ ተንደረደረ….ገባና መቀመጥ እንኳን ሳይሞክር ፓስታውን ከፈተው..ውስጡ ያለውን ወረቀት ሲያወጣ የሆነ ነገር ተስፈንጥሮ ወለሉ ላይ ወደቀ...አይኑን የወደቀው ነገር ምንነት ለማወቅ አንከራተተ..ኪሊሊሊሊሊ እያለ የሚሽከረከረው ጥቂት አንፀባራቂ ብረት ነው..ጎንበስ ብሎ አነሳው. ቀና ማለት ከበደው ፡፡ከወገብ ላይ የሆነ ደም ስር ጧ ብሎ የተበጠሰ መሠለው...፡፡እጅ ላይ ያለው ቀለበት ነው..፡፡ሲፈን ጣቶች ላይ በደስታ በሰከረ መንፈስ ውስጥ ሆኖ በኩራት ያጠለቀላት ውድ ባለ አልማዝ ፈርጥ ቀለበት..
‹‹.እስከወዲያኛው አልፈልግህም እያለቺኝ ነው"ሲል ድምፅ አውጥቶ ጨኸ.."እገድላታለው...የእኔ ካልሆነች የማንም አትሆንም...መሞት አለባት….ቢላል የተባለው ጂል ተሳክቶለት ባይገድላት እንኳን እኔ አለቃትም"...ወሰነ
/// ሲፈን
በመከራ ስትገላበጥ ቆይታ ነው እንቅልፍ የወሰዳት...‹‹ ከመቼው ነጋና ነው የሚቀሰቅሱኝ...?ደግሞስ ለምን ይቀሰቅሱኛል..?.ምን ተፈጠረ.?.›ስትል አጉተመተመች፡፡እንደምንም ተንጠራራችና አይኖቾን አጨንቁራ ከፈተች..... እባብ እንደተጠመጠመበት ሰው ጆሮ ሰንጣቂ ጩኸቷን ለቀቅችው…. ከአ
ልጋው ተስፈንጥራ በመውረድ ወለሉ ላይ በባዶ እግሯ ቆመች….በአንድ ሜትር ርቀት ፊት ለፊቷ ተገትሮ ቆሟል...ጩኸቷን የሠሙት እናቷና ሰራተኛዎ እየተጋፍ መጥተው በራፍን በማንኳኳት ላይ ናቸው፡፡
"ልጄ ሰላም ነሽ..?"
"በራፍን ክፈቺ"
ሲፈን በቆመችበት ወደበራፍ አይኖቾን ላከች. ….እንደተቀረቀረ ነው ‹‹...ታዲያ በየት ገባ?›እራሷን ነው ምትጠይቀው
"እማዬ ሰላም ነኝ ...ቃዠቼ ነው።"
"እኔን ልጄ..ምነው አመመሽ እንዴ?"
"ደህና ነኝ እማዬ"
"ክፈቺልኝና አብሬሽ ልተኛ"
"እማዬ...ሠላም ነኝ አልኩሽ እኮ..አሁን ሂጂና ተኚ ..እኔም ልተኛበት"
"እሺ ካልሽ ልጅ ..ደህና እደሪ ...ከፈለግሺኝ ጥሪኝ ወይም ደውይልኝ"
"እሺ እማዬ.."
.የእግራቸው ኮቴ እየራቀ ሲሄድ ሰማች….ዘላ ተጠመጠመችበት...እያገላበጠች ሳመችው..ግንባሩን ..ጉንጩን ..ከንፈሩን ምንም አልቀራትም...አዎ ህልም አይደለም ሰውነቱን እየዳበሰችው ነው..ጠረኑን ወደውስጧ እየማገችው ነው፡፡ከራሷ አራቀችውና መላ ቁመናውን መረመረችው ...ድባይ ወይም አውስትራሊያ ለእረፍት ሰነባብቶ የመጣ ነው የሚመስለው።ጉንጮቹ ሞልተዋል ..ፊቱ ጠርቷል...ጥርሶቹ እንደበፊቱ ፍፅም ነጭ ናቸው...አለባበሱ ዝንጥ እንዳለ ነው፡፡
"እዚህ ክፍል እንዴት ገባህ...?ዘበኛቹን በምን አስማት አለፍካቸው?የሳሎኑን በር ማን ከፈተልህ?ይሄንንስ ክፍል እንዴት?"ማለቂያ የሌለው ግትልትል ጥያቄ፡፡
ወደ ላይ አይኑን አንጋጠጠ..ወደኮርኒሱ እሱን ተከትላ እሷም አንጋጠጠች"ዉይ በፈጣሪ ...አንተ ማፍያ ነበርክ እንዴ ?" ከበላዩ ያለው ኮርኒስ ሆነ ከእሱ በላይ ያለው ቆርቆሮ ሰው ሊያሾልክ በሚችል መጠን በክብ ተቀርፎ ወጥቷል..ቀጥታ ሰማዩ ላይ የተንጠባጠብት ደማቅና ደብዛዛ ኮከቦች ጭምር በጥራት ይታያሉ።
እስከአሁን እራሷም ቆማ እሱንም አቁማ መሆኑን ስታስታውስ ጎተተችና አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀመጠችው...
‹‹ሰላም ነህ ግን..?.ውዴ አንተን ለመፈለግ እኮ ያላስበረበርኩት የአዲስአባ ጥግ አልነበረም...ምነው እንዲህ ጨከንክብኝ..?.እኔስ ይሁን እንዴት በእናትህ እንዲህ ልትጨክን ቻልክ....?በጣም ነው አኮ ውስጤን ያሰቃየኸኝ...፡፡ልቤ እስኪደክማት ድረስ...አእምሮዬ እንዴት እንደሚታሰብ ግራ እስኪገባው ድረስ....ማን መሆኔ ሁሉ እስኪጠፋኝ ድረስ ነው የተሰቃየውብህ...››ከአንጀቷ ያለምንም ይሉኝታ የውስጧን አውጥታ ተናዘዘችለት፡፡
"እንግዲያው ባለውለታሽ ነኛ"
‹‹እንዴት ማለት የእኔ ውድ?"
‹‹እንዲህ ከስርሽ ርቄ ባልጠፋ ስለእኔ እንዲህ አይነት ስሜት እንደሚሰማሽ ማወቅ አትቺይም ነበር"
"እሱስ እውነትህን ነው....በጣም እንደማፈቅርህ አሁን መናዘዝ አለብኝ"
"ግን እኮ ሌላ ሰው ልታገቢ ነው?"
"እሱን አሁን እርሳው....ደግሞም እኮ አንተም ልትገድለኝ እቅድ አለህ?"
"ያ እቅድ የእኔ አይደለም ...የአማልክቱ ነው....እስከአሁንም የውሳኔ ለውጥ መኖሩን አላውቅም"ኮስተር ብሎ ነው እንዲህ ሚላት።
"ጉዳዬ አይደለም...አንተ የሌለህበት ኑሮም ያው ከሞት አንደማይለይ በሰሞኑ ሁኔታዬ አረጋግጬያለው... ለማንኛውም ስትገባ ዘበኞቹ እንዳላዩህ እርግጠኛ መሆን አለብኝ..በራፍን ከውጭ ቆልፌብህ ሄዳለው ...እስከዛ ሻወር መውሰድ ትችላለህ"
"አዎ መታጠብ ፈልጋለው..ለራስሽ እርግጠኛ ለመሆን ሂጂ....ስገባ ማንም ሊያየኝ እንደማይችል ግን እርግጠኛ ነኝ"
"እንደዛ ከሆነ ደስ ይለኛል...ለማንኛውም መጣው"አለችና በለበሰችው ስስ ቢጃማ ላይ ወፈር ያለ ጋወን ደርባበት እንዳለችውም ክፍሉን ከውጭ ቆለፈችና በዝግታ እየተራመደች ወደሳሎን አመራች...ከውስጥ እንደተቆለፈ ነው… ቀስ ብላ ከፈተችውና ወደውጭ ወጣች...ሁሉ ነገር ፀጥ ብሏል..ዘበኞቹ በንቃት የበራፍን ግራና ቀኝ ይዘው ሁለቱም ዘመናዊ ክላሻቸውን ሰድረው ከወዲህ ወዲያ ይንጎራደዳሉ፡፡

https://t.me/ethiofilm2adey_drama

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

05 Feb, 18:26


በረንዳውን ለቃ ወደእነሱ ተጠጋች..በውድቅት ለሊት ባልተለመደ ሁኔታ ግቢ ውስጥ ሲያዬት ሁለቱም ግራ በመጋባት እርስ በርስ ተያዪ...አንደኛው ወደእሷ ተራመደ
"እመቤቴ እባክሽ ወደመኝታሽ ተመለሺ...እንድትወጪ እንደማንፈቅድልሽ ታውቂያለሽ..ለዛውም በዚህ ሰዓት?"
"እኔ መች ልውጣ አልኩ?"
"ይቅርታ አድርጊልኝ እንደዛ መስሎኝ ነው...ታዲያ ምን እንርዳሽ?"
‹‹አይ የሆነ የመንጓገጓት ድምፅ ግቢው ውስጥ የሠማው መስሎኝ ነው..!ሁሉ ነገር ሰላም ነው ግን?"
….ፈገግ አለ
‹‹<ምነው ጥያቄዬ ያስቃል እንዴ?››
"አረ በፍፁም...ግን ይሄው በግልፅ እንደምትመለከቺው ስራችንን በንቃት እየሠራን ነው ...ወፍ እንኳን ብትሆን ከእይታችን ተሠውራ ወደዚህ ግቢ ዘልቃ መግባት አትችልም..እና ምን አልባት በእንቅልፍ ልብሽ ድምጽ የሠማሽ መስሎሽ ነው... አሁን እኔ የምመክርሽ ልክ እንደወላጆችሽ በእኛ ላይ እምነትሽን ጥለሽ ያለምንም ስጋት የሠላም እንቅልፍሽን እንድትተኚ ነው።››
በተራዋ እሷ ፈገግ አለች
"ምነው አላመንሺኝም?"
‹‹አረ በደንብ አምኜሀለው..በሉ ደህና እደሩ›› አለችና ፊቷን አዙራ ወደ ቤት ተመለሰች..‹‹እንዴት አድሮጎ ነው ከእይታቸው ተሰውሮ ሊገባ የቻለው?ይሄን ያህል እንዳጃጅላቸው ቢሰሙ ምን ይሰማቸዋል?››እነዚህንና መሠል ገራሚ ጥያቄዎችን በምናቧ እያብሠለሠለች የሳሎኑን በራፍ እንደነበረ መልሳ በመቀርቀር ድምፅ ላለማሠማት እየተጠነቀቀች ወደ ኪችን ሄደች‹‹...ምን አልባት ምግብ ከቀመሠ ረጅም ጊዜው ይሆናል ..ሊረብ
በው ይችላል›› በማለት የተወሰነ ምግብና የሚጠጣ ነገር ይዛ ወደ ክፍሏ ተመለሰች .፡፡
ከፍታ ስትገባ ክፍል ውስጥ የለም ፡፡ አመዷ ብን አለ"ተመልሶ ሄደ እንዴ?"አንገቷን ወደላይ ቀስራ ተመለከተች …በሽንቁሩ ወደላይ ስታማትር ከሰማዩና ሰማዪ ላይ ከተንጠባጠብት ከዋክብት ውጭ የሚታይ ምንም ነገር የለም።የያዘችውን ምግብና መጠጥ ጠረጰዛ ላይ አስቀምጣ በራፍን መልሳ ቀረቀረችና ተንደርድራ ወደ ሻወር ቤት በመሄድ በራፍን በልቅጣ ከፈተችው
..ረጂም የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰች..."አለህ?"አለችው፡፡ መለመላውን ቆሞ ከላይ በሚፈሰው ውሀ ሰውነቱን በማስገረፍ ላይ ያለውን ጉብል ወጣት
የሻወሩን ውሀ ዘጋና"ምነው እንድሄድ ጠብቀሽ ነበር እንዴ?"
‹‹አረ በፍፅም "አለችው ልስልስ ባለ ሰርሳሪ ድምፅ....
.ወደ እሷ ተንቀሳቀሰ...ወደኃላዋ ለመንቀሳቀስ አሰበች… ግን ደግሞ ልክ በእጆቾ ከያዘቻቸው የሻወር በራፍ ጋር አቆራኝተው እንዳሰሯት ነገር ምንም ማድረግ አልቻለችም..ቀኝ እጇን ያዘና እየጎተተ ወደ ውስጥ አስገባት‹‹...ምን ሊያደርገኝ ይሆን?››የልቧ ምት በእጥፍ ጨመረ"በቃ ሊገድለኝ ነው..."ብርክ ያዛት ...ምንም ለመታገል አልሞከረችም...ከእሱ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ በፀጋ ለመቀበል ከወሰነች ቆይታለች...ይሁንና አሁን እንዲህ የቁርጡ ቀን ሲመጣ በፍራቻ ጣር ከመቃተት ልታመልጥ አልቻለችም..አይን አይኑን እያየች በሚለማመጥ አንደበት"እስቲ ምን አስቸኮለህ?" አለችው፡፡
"ለምን አልቸኩል...በጣም እኮ ናፍቀሺኛል"
"ሰው የናፈቀውን ለመግደል እንዲህ አይቸኩልም"
"የምን መግደል...?ዛሬ የማፈቀር እንጂ የመግደል ሙድ ላይ አይደለውም።"
ወደራሱ ጎተታትና ከራቁት ሠውነቱ ጋር አጣበቃት ...ትንፋሽ እስኪያጥራት ከንፈሮቾን መጠጣቸው...ከዛ ከራሱ አራቃትና የለበሰችውን ጋወን ከላዬ አውልቆ ወለሉ ላይ ወረወረው...ላመል ያህል ሰውነቷ ላይ በተጣለ ስስ ቢጃማ ብቻ ቀረች..
…መልሶ ወደራሱ ጎተታትና ከጠንካራ ደረቱ ላይ ለጠፋት...ጠቅላላ የሠውነቱ ልስላሴ ሲመቻት ከታች ግን ቆረቆራት .."".አፍቅረኝ...በጣም እንድታፈቅረኝ እፈልጋለው"አለችው..፡፡
"በዛ ጥርጣሬ አይግባሽ...በነፍሴ ጭምር ነው የማፈቅርሽ...እሱን ደግሞ በደንብ ታውቂያለሽ"አያለ ሻወሩን ከፈተው..ሿሿሿዋዋዋዋዋ...እንዳቀፋት በቀጥታ ቆሙ..ከሻወሩ ጭንቅላት እየተበታተነ ወደታች እየተስፈነጠረ የሚረግፈው ውሀ በሁለቱ ጭንቅላት ጋር እየተላተመ መላ ሰውነታቸውን ያረሰርስ ጀመር ...ቀኝ እጅን በወገቧ አሽከርክሮ እንዳቀፋት በግራ እጅ ቢጃማውን ከታች ጀምሮ ወደላይ መሠብሠበብ ጀመረ..ከዛ ወደላይ ሰበሰበ..በሁለት እጅ ወደላይ በመሳብ በጭንቅላቷ ሞሽልቆ በማውለቅ ልክ እንደ ጋወኑ ወለሉ ላይ ወረወረው...ቀኝ እጅን መልሳ በወገቧ ዙሪያ አሽከረከረና አቀፋት ..ከሰውነቱ ጋር ያለርህራሄ በኃይል አጣበቃት ..ጡቶቾ ተጨፈለቁ....ቃተተች....ግራ እጅን በፓንቷ እና በመቀመጫዋ መካከል ሰነቀረቸው........የሆነ ህልም ውስጥ ያለች ነው የመሠላት...ለመጀመሪያ ጊዜ ድንግልናዋን ባስወሰደች ቀን የተሠማት አይነት ውጥረት ውስጥ ነው የገባችው..ጉጉት...ፍር
ሀት...ደስታ...ዝብርቅ ያለ የሚያንሳፍፍ ስሜት....ይሄ ስሜት ለቢላል ካላት የተለየ ፍቅር ይሁን ወይስ ከወንድ ጋር መተኛት ካቆመች አመት በላይ ስለሆናት አልገባትም....ከንፈሯን በረጅሙ ሲመጣቸው..ከጠንካራ ደረቱ ጋር አጣብቆ ጡቶቾን ሲጨፈልቃቸው..ቀኝ ቂጧን በግራ እጅ ጭምቅ ሲያደርጋት..እና እንትኑ ጭኗ መካከል ድንገት ገብቶ ሲርመሠመስ...እነዚህን ሁሉም ልክ እንደሙሉ ባንድ ህብራቸውን ጠብቀው በተመሳሳይ ጊዜ ሲፈፀሙ....ሲፈን በዛው መጥፋት ማለት ነው የተመኘችው....ሳትነቃ ለዘላለም በዛ ስሜት ውስጥ መቆየት..፡፡

ይቀጥላል.....

┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿

                  💗

https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama

                   💗

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

05 Feb, 11:50


ከሶስቱ ባለትዳሮች አንዷ ደወለችልኝ ፤ በቅንነት አነሳሁት ፤ ቤት ስለምፈልግህ ቶሎ ና አለችኝ ፤ በቅንነት እየከነፍኩ ወደ ቤቷ ሄድኩኝ ፤ ባሌ ጅቡቲ ስለሄደ ቤት ውስጥ ብቻዬን ፈርቻለሁና ለዛሬ አስተዳድረኝ አለችኝ ፤ በቅንነት እሺ አልኩኝ።

እራት አቀረበች ፤ በቅንነት በላሁ ፤ አጎረሰችኝ ፤ አጎረስኳት ፤ ሌሊት ሆነ ፤ አንተ ሶፋ ላይ ተኛ እኔ መኝታ ቤት ተኛለሁ አለችኝ ፤ እሺ ብዬ በቅንነት ሶፋ ላይ ወጣሁ ፤ ተመልሳ መጥታ ሳሎን ውስጥ ቢንቢ ስለማያስተኛህ መኝታ ቤት እንግባና አንተ ፍራሽ ላይ እኔ አልጋ ላይ እተኛለሁ አለችኝ ፤ በቅንነት እሺ አልኳት።

መኝታ ቤት ገባን ፤ አልጋ ላይ ተኛች ፍራሽ ላይ ተኛሁ ፤ መብራቱን አጠፋችው ፤ ከብዙ ሰአት በኋላ ተነስታ የመኝታ ቤቱን መብራት አበራችው ፤ ሰውነቷን የሚያሳይ ስስ ፒጃማ ለብሳለች ፤ አንተ ቀዝቃዛ መሬት ላይ ተኝተህ እኔ አልጋ ላይ መተኛት
ከብዶኛልና አልጋው ስለሚበቃን አልጋ ላይ ተኛ አለችኝ ፤ በቅንነት እሺ አልኳት ፤ አልጋ ላይ ወጣሁ ፤ እቀፈኝ አለችኝ ፤ በቅንነት አቀፍኳት ፤ ሳመኝ አለችኝ ፤ በቅንነት አፀፋውን መለስኩላት ፤ አልጋው መነቃነቅ ጀመረ።

ተሳቢ መኪናውን እየጎተተ ጅቡቲ የሄደው ባሏ ትውስ ብሎኝ ለስራ ያለውን ፍቅር አስቤ አደነቅኩት ፤ በረዥሙሙሙ ተነፈሰች ፤ በቅንነት የጀመርኩት ነገር በቅንነት ተፈፀመ።

ሁላችንም ቅን እንሁን! ቅንነት መልሶ ይከፍላልና!😉😄

┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿

                  💗

https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama

                   💗

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

03 Feb, 17:09


👆👆ክፍል 40 ተለቋል!!🔥

#ያዉ 176 ግሩፑ ላይ add ስላደረጋችሁ በቃሌ መሰረት ክፍል 40 ተለቋል። 200 ሰዉ add ግሩፑ ላይ ካደረጋችሁ ዛሬዉኑ ምሽት 3 ሰአት ቀጣዮቹን ሁለት ክፍሎች በተከታታይ እለቅላችኋለሁ።🔥 ከስር ተቀመጠዉን ሊንክ በመጫን ግሩፑን እየተቀላቀላችሁ Add አርጉ🙏
🔥Join Join👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇Join


https://t.me/lovestorey23
https://t.me/lovestorey23
https://t.me/lovestorey23

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

03 Feb, 17:03


‹‹የሄኖክ ምር ነው አይደል እንዲህ እንድትቀየርና ክፍ ሀሳብ በልብህ እንዲበቅል ያደረገው.››
የማንም ምክር ሆነ የማንም ዋናው ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑ ነው››
‹‹እስከመቼ አፍነህ ታስቀምጠኛለህ?ስራዬስ ?››
‹‹ጥንቅር ብሎ ይቅር፡፡ ምን አሳሰበሽ አስሬ ተመላልሰሽ ብትፈጠሪ አንቀባሮ የሚያኖርሽ ሀብት አለሽ...በዛ ላይ ልጁን ከመፈለግ ውጭ ሌላ ሌላስራ መስራት ካቆምሽ መሰንበተሽን ያልሰማው መሰለሽ?››
‹‹አባዬ››
‹‹አቤት ልጄ››
‹‹ባለፈው ከሄኖክ ጋር ቀለበት ያስርኩት በስህተት ነው….ትቼዋለው››
‹‹ትቼዋለው ማለት? አንቺ ልጅ ግን አዕምሮሽ ጤነኛ ነው?››
‹‹በቃ እሱን አላገባም ማለት ነዋ››>
‹‹እና ማንን ልታገቢ ነው?ዋ ነግሬሻለው በስምምነታችን መሰረት ከሶስት ወር በታች እንደቀረሽ ተሳስተሸ እንኳን እንዳትረሺ››
በዚህ ሁኔታ ነበር መታገቷን ያወቀችው …ለጊዜው እሷም ብዙ የምትንቀሳቀስበት የአካልም ሆነ የመንፈስ ጥንካሬ ላይ ስለማትገኝ ከአባትዬው ጋር ብዙ እሰጣ ገባ ውስጥ መግባት አልፈለገችም…..በዛ ላይ በቀደም ቢላል መስሎቸው ሌላ ሰው ለመግደል የሞከረው ሰው ማን እንደሆነ እስከአሁን እርግጠኛ አይደለችም…ከሄኖክና ከአባቷ አንዳቸው እንደሚሆኑ ግን እርግጠኛ ነች፡፡ይሄንንም እንዲያጣራላት ለኤርሚስ ተጨማሪ የቤት ስራ በስልክ ሰጥታው ነበር…..እስከአሁን እንደአቀረበላት ሪፖርት ከሆነ ነገሮች ወደሄኖክ ነው የሚያመሩት…ይሄ ከተረጋገጠ ደግሞ የእሷ አፀፋዊ መልስ ምን ሊሆን እንደሚችል ስታስብ በውስጣ የበቀል እሳት ይነዳል፡፡
ወደክፍሏ ተመልሳ ብዙ ስትገላበጥ ከቆየች ቡኃላ ስልኳን አነሳችን ለሄኖክ አባት ደወለችላቸው
‹‹ሄሎ ጋሼ››
‹‹የኔ ንግስት ሰላም ነሽ…?ያንቺ ነገር በጣም አሳስቦኝ ነበር….ስለደወልሺልኝ በጣም ተደስቼያለው››
‹‹ሰላም ነኝ ጋሼ …አያስቡ››
‹‹የልጁስ ወሬ የለም..?እስከአሁን አልተገኘም?››
‹‹እንግዲህ በተቻለን አቅም እየፈለግነው ነው...እስከአሁን ምንም ፍንጭ የለም››
‹‹ልጄ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅሽ?.››
‹‹ይጠይቁኝ››
‹‹ይሄ ልጅ ከእኛ ታሪክ ጋር የሚያገናኘው ጥቂትም ቢሆን የሆነ ነገር አለ እንዴ…?ማለቴ የንግስቴን ደብዳቤ ስታነቢ እንደዛ ተሰምቶሽ ይሆን?
‹‹ጋሼ .እርግጠኛ አይደለሁም…ግን በምን አይነት ተአምር እንደሆነ እስከአሁን ባይገለፅልኝ ሁለቱን ወንዶች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ…..ማለቴ እኔና የእርሶ ባለቤት ከምንመሳሰለው በላይ ሁለቱ ይመሳሰላሉ››
‹‹አውቄዋለው..ለእኔም ተሰምቶኝ ነበር..ልጄ እኔ እንድረዳሽ የምትፈልጊው ማንኛውም ነገር ካለ አሳውቂኝ ..አንቺኑ ለማገልገል ነው በህይወት ያለውት››
‹‹አመሰግናለው ጋሼ.. .በአሁኑ ሰዓት ከእርሶ ጋር ጋር ሳወራ ብቻ ነው በውስጤ ሰላም የሚሰማኝ…አሁን ግን ከደብዳቤዎቹ መካከል አንዱን ቢያነቡልኝ ጥሩ እንቅልፍ ይወስደኝ ነበር፡፡›››
‹‹ምን ችግር አለው...ሁለት ደቂቃ ስጪኝ ልዘጋጅና ደውልልሻለው› በማለት ስልኩን ዘጉት..እንዳሉትም ደወሉና ያነቡላት ጀመሩ
////
ተአምር ነው!!!
ስምሽ ግዙፍ ነው ህያው..ከህዋ ጠፈር ይልቃል
ድምፅሽ ጥዕም ሙዚቃ..ከአርያም ምንጭ ይፈልቃል
መልክሽ ብሩህ ነበልባል...ከጨረቃም ይደምቃል
ልብሽ ተራራ ግዙፍ…በፍቅር ሁሉን ያቀልጠል፡፡
///
አንቺና ፀሐይ ትመሳሰላላችሁ፡፡ፀሐይ የሶላር ሲስተምትን 99 ፐርሰንት ክብደት ይዛላች… አንቺም በዛው መጠን የእኔን ልብ ተቆጣጥረሽዋል፡፡ፀሀይ ፖቶን በተባለ ቅንጣት የተመረተች የእሳት ኳስ ነች…አንቺም ከነፍስ ቅንጣት የተሰራሽ የፍቅር ኳስ ነሽ፡፡በፀሀይ አስኳል መሀከለኛ ስፍራ የተፈጠረው ብርሀንና ሙቀት ከመነሻው ተነስቶ የላይኛው የፀሀይ ቅርፊት ለመድረስ 40ሺ ዓመት ይፈጅበታል በአንቺም ልብ ውስጥ የተፈጠረው የፍቅር ስሜት አድጎና ጎልብቶ ከንፈርሽ ጋር በመድረስ ቃላት ሆኖ ለመገለፅ ዓመታት ይፈጅበታል፡፡በፀሀይ አስኳል ውስጥ በአንድ ጊዜ የተፈጠሩ 60 ሚሊዬን ቶን የሚመዝኑ ሀይድሮጂን አተሞች እርስ በርስ በመፋፋተግ እና በመጋጨት ብርህንና ሙቀትን ይፈጥራሉ…..ባንቺም አዕምሮ ውስጥ በሰከንድ ሚሊዬን ሀሳቦችና ናፍቆቶች እርስ በርስ በመፋጨት ፍቅርና ተስፋን ያስገኘሉ፡፡
አለም እና በውስጧ ያሉት ነፍሳት በአጠቃላይ በፀሀይ ህልውና ላይ ጥገኛ እንደሆነ ሁሉ የእኔም ህልውና ሙሉ በሙሉ በአንቺ ፍቅር ላይ ጥገኛ ነው፡፡እና ከዚህ በፊት እንዳልኩሽ በፍቅራችን ተስፋ አልቆርጥም….መቼም፡፡እና በአዲሱ ትዳረሽ ተረጋግተሸ ኑሮሽን እንዳትቀጥይ..የቤትሽን ወዝና የባልሽንም ጠረን እንዳትለምጂ…..ምክንያቱም ወደእኔ መመለሰሽ አይቀርም፡፡አዎ የዛሬ አመትም ሆነ የዛሬ 100 ዓመት አንቺ የእኔ ሚስት ትሆኚያለሽ..12 ልጆችም ትወልጂልኛለሽ፡፡
ይሄንን ደብዳቤ ከሀያ አምስት አመት በፊት ሞች የሄኖክ አባት ለእናትዬው በወቅቱ ከፃፈላት አያሌ ደብዳዎች መካከል ተመዛ የወጣ ነው፡፡ከሁሉም በላይ የአንባቢው የሄኖክ አባት ናቸው፡፡ስለቀድሞ ሟች ሚስታቸውና ፍቅረኛዋ ስለሆነ ሌላ ሰው ታሪክ ማነብብ ከባድ ትዕግስታና ጠንካራ ፅናት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡
‹‹ስላነበቡልኝ ደስ ብሎኛል››አለቻቸው ደብዳቤውና አንብበው ሲጨርሱ፡፡
አዘውንቱ በለስላሳ አንደበታቸው ደብዳቤውን ሲያነቡላት እውነትም እያንዳንዶ የፍቅር ውዳሴ ቃላት ቀጥታ ለእሷ ከቢላል የተፃፈ አድርጋ በማሰቧ ልቧ ላይ በመንጠባጠብ በደም ስሯ ነው የተሰራጨው…እደዛም በመሆኑ ጭንቅላቷን ወጥሮትና ልቧንም ጨምድዷት ነበረው ውጥረት በግማሽም ቢሆን ሲቀንስላት ታወቃት…ለዛ ነው ከልቧ ያመሰገነቻቸው፡፡
‹‹ምስጋናው ለእኔ ነው..የራስሽውን ደብዳቤ ለራስሽው እንዳነበብኩልሽ ነው.የተሰማኝ.››
‹‹ቢሆንም በእርሷ ቦታ ሌላ ሰው ቢሆን መቋቋም አይችልም…››
‹‹ስለእኔ አትጨነቂ….መጥቼ እንዳይሽ ትልጊያለሽ እንዴ?››
‹‹አይ አልፈልግም…ግን እንደዚህ እየደወልኩሎት ብናወራ ደስ ይለኛል››
‹‹በፈለግሽ ሰዓት ቀንም ሆነ ለሊት ሳትሳቀቂ ደውይልኝ…››
‹‹እሺ አመሰግናለው››
‹‹እግረመንገዴን አንድ ነገር ልጠይቅሽ..?.››
‹‹ምንድነው ጋሼ?››
‹‹ስልጄ ስለሄኖክ››
‹‹ስለእሱ ምን.?››
‹‹ማለቴ ያው እንደሰማሁት ቀለበት አስራችሆል…በሚቀጥለው እሁድ ሽማግሌ ይላክ እያለኝ ነው...እንዳውም ያለፈው እሁድ ነበር ያለኝ….የተለያየ ምክንያት ፈጥሬ እምቢ አልኩት እንጂ››
‹‹ጋሼ እውነቱን ልንገሮት አሁን ባለው ስሜቴ እርግጠኛ አይደለውም…ይሄ ግር ግር አልፎ ነገሮች እስኪረጋጉ ምንም አይነት ሽማግሌ መላክ በሽማግሌዎቹም ሆነ በእኔ ወላጆች ጊዜ መቀለድ ነው የሚሆው፡፡ስለዚህ ጋሼ እንዳዛ አያድርጉ›
‹‹እሺ እንዳልሽ…ግን ልጄ እባክሽ አንቺው ደውለሽለት እንዳይልክ ብታሳምኚው ይሻላል…እኔ ምን ብዬ ተው አይሆንም ማለት እችላለው…?ብለውስ ይሰማኛል?››
‹‹ግድ የሎትም አኔው እነግረዋለው.እርሶ ግን ይቅርታ››
‹‹እኔ በነፍሴ ጭምር ነው የምረዳሽ….እስከመጨረሻው አላገባህም ብትይው አራሱ ይገባኛል፡፡››
‹‹እሺ አመሰግናለው ጋሼ…የእውነቴን ነው የምሎት እሱን የማገባው አይመስለኝም…››
‹‹ቸግር የለውም ግን ልጄ በዚህ የተነሳ የእኛ ግንኙነት ላይ ምንም እንከን እንዲኖር አልፈልግም››

https://t.me/ethiofilm2adey_drama

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

03 Feb, 17:03


😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 40
.
.

///
ሄኖክ በእለቱ የቢላልን መገደል ከሰማ ቡኃላ በስምምነቱ መሰረት የአንድ ሚሊዬን ቼክ ፅፎ በፖስታ አሸገ፡፡የገዳዬቹን ኃላፊ ግዬን ሆቴል ቀጠረው…ግቢው ድረስ ቢሄድም ሰውየው ወደሚገኝበት ወንበር ግን አልተጠጋም፡፡ፖስታውን ለሹፌሩ አስይዞ በሩቁ ከጠቆመው ቡኃላ እንዲሰጠው አደረገ እናም ፖስታውን እንደተቀበለ ካረጋገጠ ቡኃላ ደወለለት፡፡
‹‹እቃው ደርሶሀል?፡፡››
‹‹አዎ አመሰግናለው…ግን ከላዩ ላይ የፍንጥር ልጋብዝህ እኮ አስቤ ነበር››
‹አይ ይቅርብኝ….ሁኔታዎች እስኪረጋጉ አንድ ላይ መታየት የለብንም…ለማንኛውም ስፈልግህ ደውልልሀለው›› በሚል ነበር የተለያዩት..ይህን ሲለው ምን አልባት በሚቀጥሉት ስድስት ወር ወይም በአመታት ውስጥ እሱ ጋር መልሶ ሚያስደውለው ጉዳይ እንደማይኖረው በውስጡ እርግጠኛ በመሆን ነበር፡፡የሆነው ግን ሁለት ሰዓት በማይሞላ የጊዜ ልዩነት ነበር እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ ለቅሶ ቀረሽ በሆነ ንዴት የደወለት›
‹‹አንተ››
‹‹አቤት አቶ ሄኖክ››
‹‹ምን አይነት ቀላባጆች ናችሁ በፈጣሪ?››
‹‹ምን አልክ?››
‹‹አትረቡም …እንዴት እንዲህ ይደረጋል….አኔን ታታልሉኛላችሁ?››
‹‹አረ ተረጋጋና አስረዳኝ ….ምን ተፈጠረ?››
‹‹አሁንም እያሾፍክብኘ ነው…ክፉ ደረጃ ሳንዳረስ ብሬን በአስቸኮይ መልስልኝ፡፡››
‹ሰውዬ ብሩን ልጆቹ ወዲያውኑ በውላችን መሰረት አከፋፋልኮቸው››
‹‹እሱ አያገባኝም...እኔ ውሌ ካንተጋር ነው ከገባህበት ግባና ብሬን መልስልኝ..ዝም ብላችሁ የማንንም የጎዳና ተዳዳሪ ገድላችሁ አንድ ሚሊየን ብር መቀበል ትልቅ ማጭበርበር አይሆንም?፡፡››
‹‹ሰውዬ የምታወራው ምኑም አልገባኝም…ልጁ ተገኝቷል ብለውናል አልኩህ…ቶሎ ግደሉት አልከን በትዕዛዝህ መሰረት አደረኩት...ነው ወይስ በወቅቱ ዲ.ኤን. ኤ አስርቼ ካረጋገጥን ቡኃላ ነበር መግደል የነበረብን?›
‹‹ቀለድክ ማለት ነው?፡፡››
‹‹አንተ ነህ እንጂ እየቀለድክ ያለሀው…ይልቅ አንድ ነገር ልንገርህ .ብሩን የሆነ ቁማር ተጫውተህ በእድለቢስነት እንደተበላሀው ቁጠርና አርፈህ ቁጭ በል…በእኔ ላይ የሆነ አደጋ አደርሳለው ብለህ እንዳታስብ.. .የሰጠሀኝን እያንዳንዱን ትእዛዝ ቀድቼዋለው…ወዲያው ነው ለእጮኛህም ለፖሊስም የምበትነው፡፡ ይልቅ ሌላ ክፍያ አዘጋጅና ትክክለኛውን ሰውዬ ፈልገን እንግደልልህ…ባይሆን ክፍያውና በአስተያየት እናደርግልሀለን፡፡››
እራሱን መቆጣጠር ሲሳነው ስልኩን ጠረቀመው፡፡በብስጭት ጨጎራው እስኪገለባበጥ ሲጠጣ አነጋ፡፡11 ሰአት ለመተኛት አልጋ ላይ ከነልብሱ ተዘረረ….ከቀኑ 6 ሰዓት በእህቱ ቀስቃሽነት ከመኝታው ተነሳ .ከዛ ቡኃላ ያደረገው የመጀመሪያ ነገር ቢኖር ስልክ ደውሎ ትክክለኛውን ቢላላን እንዲገድሉት ከራሳቸው ጋር መደራደር ነበር…እንደበፊቱ በስልክ ሳይሆን ቀጥታ በአካል ተገናኝተው በስንት ጭቅጭቅ በስድስት መቶ ሺ ብር ተስማሙ.፡፡የዚህኛው ስምምነት ግን ከቀደመው ስምምነት የሚለየው የዚህ ክፍያ 20 ፐርሰንቱ ቀድሞ ለስራ ማስኬጃ ሲከፈል ቀሪው ግን ሙሉ በሙሉ በትክክልም ቢላል መገደሉ በሀኪም ከተረጋገጠ ቡኃላ የሚፈፀም እንዲሆን ነው የተስማሙት፡፡
////
ሲፈን…
ከ5 ቀን በፊት የቢላልን ሞት ከሰማች ቡኃላ በአጋቾቻ ሆስፒታል ተወስዳ ነበር..ወደቀልቦ ለመመለስ በጣም ከባድ ሆኖባት ነበር፡፡፡ከብዙ ማፅናናትና ማስረዳት ቡኃላ ነው እራሷን ገዝታ ወደቀልቦ ተመልሳ ከሆስፒታል ልትወጣ የቻለችው፡፡
በወቅቱ እሷ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደች ከሶስት ሰዓት ቡኃላ የቢላል እናት የሞች ሬሳ ለምርመራ ወደተወሰደበት ሚኒሊክ ሆስፒታል በእንባ እያታጠበች በሀዘን ተኮራምታ በፖሊሶች በመታጀብ ተወስዳ ነበር፡፡የልጇን መሞት ትክክለኝነት እንድታረጋግጥ፡፡የተፈጠረው ግን ተአምር ነበር፡፡ሞች በሰውነት አቆሙና በፊቱ ቅርፅ ቢላልን ቢመስልም እውነታው ግን ቢላል አልበረም...እዛው የገለጠችውን የሬሳ ልብስ ወደቦታው ሳትመልስ ነው ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ ኃይል በእልልታ የሆስፒታሉን ድባብ ያናወፀችው ፡፡
ቡኃላ ሲጣራ ሞቹ በቅርብ ከክፍለሀገር መጥቶ መገናኛ አካባቢ ካሉ የሀብታም በረንዳዎች በአንድ የከተመ የአዕመሮ ህምተኛ መሆኑ በፖሊስ ምርመራ ተረጋገጠ…ይሄም ከነመረጃውና ማስረጃው በፕሮፌሰሯ አማካይነት እራሷን ስታ በተኛችበት ሆስፒታል ቢላል እንዳልሞተ እና በእሱ ቦታ የተገደለው ሌላ ሰው እንደሆነ ማብራሪያ ተሰጣት..ይሄም በሰመመንን ወደእብደት ዓለም እየተጓዘች ከነበረችበት ቀስ በቀስም ቢሆን ወደቀልቧ እንድትመለስ ከፍተኛ እገዛ ቢያደርግላትም ከመንፈስ መረበሽና ከመወራጨት በቀላሉ ማገገም ግን እስከዛሬም አልቻለችም፡፡
በ4ተኛው ቀን በአባትዬው ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከሆስፒታል ወጥታ ወደወላጆቾ ቤት ተወሰድችና ያደገችበት ክፍሎ ተኝታ እንድታገግም ሁኔታዎች ተመቻቹ ….እቤት ድረስ ተመላልሳ የጤናዋን ሁኔታ እድትከታተላት በእውቅ ሰው ምርጥ የተባለች የእምሮ ሀኪም ተቀጠረችላት፡፡የግቢው በራፍ ግራና ቀኝ በተጠንቀቅ የሚቆሙና በየ8 ሰዓት ልዩነት በሚለዋወጥ ፈረቃ የሚቀያየሩ ሁለት ወጠምሾች ተቀጥራው ስራቸን ጀምረዋል፡እንግዲህ እነዚህ ቀድሞ ከነበሩት መደበኛ ዘበኞች በተጨማሪ ማለት ነው፡፡
ለእነዚህ ፕሮፌሽናል ጠባቂዎች ከቀጣሪያቸው ከሲፈን አባት የተሰጣቸው አንድ ትዕዛዝ ቢኖር ከእሳቸው ፍቃድ ውጭ ማንም ሰው ወደግቢው መግባትም ሆነ መውጠት እንደይችል ነው፡፡ይሄ ሲፈንንም ያጠቃልላል፡፡እሷ ሙሉ በሙሉ የአባትዬው ታጋች ሆናለች፡፡ይሄንን ያወቀችው ትናንት ነው ፡፡
እግሯን ለማፍታታትና በዛውም የሆነ ካፌ ቁጭ ብላ ማኪያቶ እየጠጣች መናፈሷን ዘና ለማድረግ አስባ ከግቢ ልትወጣ ስትል..ዘበኛው‹‹ አይቻለም›› አላት
‹‹ማለት?››የእሷ በገረሜታ የተሞላ ጥያቄ ነበር
‹‹አባትሸሽ ሳይፈቅዱ ማንንም ማስገባት ሆነ ማስወጣት አልችልም››
‹‹እኔ እኮ ማንም አይደለውም››
‹‹አውቃለው››
‹‹እና?››
‹‹አባትሽ አንቺን በተመለከተ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ነው የሰጡን…እኔ ሳልፈቅድ እንዳትወጣ ብለውኛል››
እየተወረገረገች ወደአባቷ መኝታ ቤት‹‹አባዬ ምን እየተካሄደ ነው?››
‹‹ምን ሆንሽ ደግሞ?››
‹‹በራፍ ላይ ላቆምከው ወጠምሻ ደውልለት››
‹‹አንድ አይን ያለው በእሳት አይጫወትም፡፡››
‹‹ማለት?››
‹‹ይሄ የምትሉት ልጅ ከጠፋበት እስኪገኝና አንድ መፍትሄ እስኪበጅለት ከዚህ ግቢ መውጣት አትችይም››
ከት ብላ ሳቀች…የማየቋርጥ ረጅም ሳቅ …‹‹ኪ.ኪ.ኪ.ኪ……….››
‹‹ምነው ያስቃል?››
‹‹በደንብ ያስቃል እንጂ …እኔ እኮ ሁሉንም በቃኝ ብለህ ለአምላክህ ፀሎት በማድረግ ብቻ የተወሰንክ መለኩሴ ነበር የምትመስለኝ…ለካ አባቴ ፕሮፌሽናል ማፍያ ኖሯል..ለዛውም የገዛ ልጁን በ15 ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የሚያፍን ፡፡››
‹‹ለአንቺ ልጄ ስል የትኛውንም ምድራዊ ሆነ ሰማያዊ ህግ ለመጣስ የማላመነታ ሰው መሆኔን ከዚህ ቀድመሽ ማወቅ ነበረብሽ››
‹‹ለእኔ ስትል መግደል ቢኖርብህ በዚህ እድሜህ ተደርገዋለህ ማለት ነው?››
‹‹ለሰከንድ አላስብበትም…አንድ ሰው አይደለም የከተማውንም ህዝብ ልጨርስ እችላልው››

https://t.me/ethiofilm2adey_drama

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

03 Feb, 17:03


‹‹በዛ ጥርጣሬ አይግባዎት ጋሼ…ምን አልባት ጊዜ ሚያመጣውን ነገር ምን እናውቃለን..እኔም ልክ ንግስት እንደወሰነችው አይነት ውሳኔ ወስን ይሆናል››
ፀጥ አሉ…ይሄንን ከእሷ አንደበት ለዛውም እንዲህ በቅርብ እሰማለው ብላው አስበው አያውቁም ነበር
‹‹ጋሼ አሉ?››
‹‹አዎ.አለው፡፡ ልጄ እኔ የፈለግሽውን ውሳኔ ብትወስኚ ከጎንሽ ነኝ..….ከአባትሽ ገር የገባሽውን ውል አውቃለው…ልብሽን የሚያቀልጠውንፍቅርሽን እስክታገኚ ድርስ እኔ ጉያ ለፈለግሽው ያህል ጊዜ ልትሸሸጊ ትችያለሽ…››
እንባዋ መጣ‹‹አመሰግናለወው ጋሼ…ይሄንን በመስማቴ የእውነት ደስ ብሎኛል…በሉ ደህና ይቆዩልኝ. ማታ ደውልሎታለው››
‹‹እጠብቅሻለው‹‹አሏት ልክ በፍቅር ያቀለጠችውን ፍቅረኛውን እንደሚሰናበት ወጣት አፍቃሪ በለሰለሰ ድምፅ
///

ይቀጥላል....

┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿

                  💗

https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama

                   💗

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

02 Feb, 15:19


👆👆ከፍል 39 ተለቋል🔥🔥
#ወዳጆቼ አንባቢዎች እንዲቀላቀሉን የመወያያ ግሩፓችን ላይ እየገባችሁ ጓደኞቻችሁን #add በማድረግ ተባበሩኝ። ለሁላችንም ብዙ ጥቅሞች አሉት : 1) ሰዎችን add ስታደርጉ የሚያነብ ትዉልድ ይበዛሉ። በእናንተ ምክንያት ሰዎች ይለወጣሉ።... 2) ግሩፑ ላይ 200 ሰዎች add ካደረጋችሁ ምንም ጊዜ ሳጠብቁ 200 ሰዎቹ add እንደተደረጉ ቀጣዩን ክፍል ወዲያዉ ሁሌም እለቀዋለሁ። ቃሌን እጠብቃለሁ❤️

#ዳይ ሁላችሁም ተሳተፉ ! 200 ሰዉ ግሩፑ ላይ add እንዳደረጋችሁ ቀጣይ ክፍሉ 40 ወዲያዉ እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ይለቀቃል ።.. ስለዚህ እንደናንተ ፍጥነት ይወሰናል። ከስር ተቀመጠዉን ሊንክ በመጫን ግሩፑን እየተቀላቀላችሁ Add አርጉ🙏
🔥Join Join👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇Join


https://t.me/lovestorey23
https://t.me/lovestorey23
https://t.me/lovestorey23

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

02 Feb, 14:16


😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 39
.
.
///

ከሞት ቡኃላ እንኳን …
እንደው እድል ኖሮ.. ማፍቀር ከተቻለ
ውዴ በእኔ ነፈስ ውስጥ…ለዘላለም ሚኖር… ካንተ ውጭ የት አለ.
//
ሲፈን ከቢላል መጠፋት ጋር ተያይዞ እየገጠማት ያለው ፈተና ቃላል አይደለም፡፡ ከፈቅረኛዋ ከሄኖክ ጋ ሙሉ በሙሉ መነጋገር ካቆመች እራሱ አራት ቀናት አልፎቸዋል..
በዛ ላይ ወላጆቾ በተለይ አባቷ ያለችበትን ሁኔታ ሰምቶ ‹‹ልጄንማ የሆነ መድሀኒት አቅምሰዋት እራሷም አብዳ እንጂ በጤናዋ እንደዚህ የለየለት እብድ ፍለጋ ከተማዋን አታስስም›› በማለት ልክ ፍቅረኛዋ ሄኖክ እንዳደረገው ሁሉ እሷቸውም በቅርብ እርቀት በየሄደችበት እየሄዱ ደህንቷን የሚከታተሏት አራት ሰዎች ቀጥረው አሰማርተዋል፡፡
የሄኖክም ሰዎች መኪና በየቀኑ ይቀያይራሉ እንጂ ክትትላቸውን አላቆሙም፤ልዩነቱ የሄኖክ ሰዎች አሁን ያላቸው አላማ የእሷን ደህንነት መከታተል አይደለም፡፡አሁን ከዛ ያለፈ ሌላ ተልዕኮ ተስጥቷቸዋል….ተፈላጊው እብድ ሲፍንን ፍለጋ እሷ ወደአለችበት ከመጣ ሊያጠቃትና ጉዳት ሊያደርስባ ይሆን አልያም ሊያናግራት ወደእሷ ከመጣ ያለምንም ማንገራገር ወዲያው መግደልና ማሰናበት.፡፡ይሄ ከሄኖክ የተሰጣቸው ተልዕኮ ነው፡፡እርግጥ መጀመሪያ ይሄን ለመተግበር በ120 ሺ ብር ክፍያ ነበር የተስማሙት…ግን ምን ያደርጋል በየጋዜጣው እሱን ያገኘ የ500 ሺ ብር ሸልማት ይሰጠዋል የሚል ማስታወቂያ ከተበተነ ቡኃላ ስምምነቱ አደጋ ላይ ወደቀ፡፡…እሱን ገድለው እድሜ ልክ የሚያሳስር ወንጀል ሰርተው 120ሺ ብር ከእሱ ከሚቀበሉ ቀጥታ ልጁን ከነህይወቱ ይዘውት በሰላም ለእሷ ቢያስረክቡ አይቀላቸውም? ፡፡ስለዚህ በከፍተኛ ንዴት እና ቁጭት ደግሞም ምርጫ በማጣት ክፍያው በስድስት እጥፍ አሰደገላቸው፡፡
..///.
የሄኖክ ቢሮ ጠቅላላ ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ በሀገሪቱ በታተሙ በጋዜጣችና በመፅሄቶች ተሞልቷል፡፡እያንዳንዱን ጋዜጣና መፅሄት በንዴትና በቁጭት እያገላበጠ ማንበብና መመርመር ከጀመረ ሰዓታት አልፈዋል፡፡
‹‹አዋረደሺኝ›አለ ከጎን ያለው ቢሮ እስኪሰማ ድረስ ጠረጳዛውን በኃይል እየነረተ፡፡
‹‹ ለአንድ ጥቅም አልባ እብድ 500 ሺ ብር ሽልማት....›የፍቅረኛው ሰሞኑ ሁኔታ ከእምሮው የማሰብ አቅም በላይ ነው የሆነበት…
‹‹ውይ ሴት .እንዲህ በስሜቴም በክብሬም እንደተጫወትሽ…እኔም በቅርብ ሙሉ በሙሉ እጄ አስገባሽና ስለእያንዳንዷ ቀን መከፋቴ እበቀልሻለው….ባንቺ የተነሳ በተከፋውባቸው እና አንገት በደፋውባቸው በእያንዳንዱ ቀናት ልኬት ሺ እጥፍ በሚሆን መጠን አስከፈልሻለው፡፡የምትመኪበትን እረብጣ ብር ቀስ በቀስ ወደካዝናዬ አዘዋውርና በመጨረሻ እንደማንኛውም ተራ ሴት ባዶ እንድትሆኚ በማድረግ ሁኔታሽን በፈገግታ እከታተላለው፡፡››ሳያስበው ሲኦላዊ የበቀል ፅንስ በውስጡ በቀለ፡፡ካገባት ቡኃላ ምን ሊያደርገት እንደሚችል አስቦና ወስኖ ሳይጨርስ ስልኩ ጠራ..የሚፈልገውና ስልክ ነው፡፡አነሳው፡፡
‹‹አሺ ፍንጭ ተገኘ?››
‹‹መገናኛ አካባቢ ተገኘ የሚል ወሬ ሰምተን ነበር ››
‹‹እና?››
‹‹ያው ልጆቹ አዛ ደርሰው ሁኔታዎችን እየተከታተሉ ነው…እኔምሁኔታውን በቅርበት ለመምራት ወደእዛ እየሄድኩ ነው፡፡››
‹‹ይሄውል ነገሬሀለው…ይሄኔ እሷም ተደውሎላት ወደእዛው እየሄደች ይሆናል…በምንም አይነት በህይወት እንድታገኘው አልፈልግም…ያለምንም ማቅማማት አስወግዱት….አሁኑኑ ለልጆችህ ደውልላቸው››
‹‹ደርሰዋል እኮ…ቦታቸውን ይዘው ትዕዛዝ እየጠበቁ ነው፡፡››
‹‹በእርግጠኝነት ልጁን አግኝተውታል?››
‹አዎ ልጆቼ እንደነገሩኝ ከሆነ ያገኙት ሰዎች የሆነ ክፍል ውስጥ አስቀምጠው ለእሷ ደውለውላታል….ያው የ500 ሺ ብር ቼክ ይዛ እየመጣች ይመስለኘኛል፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ልትሆን ትችላለህ..…ስለዚህ ሰዎችህ መስራት የሚገባቸውን ያድርጉ…በህይወት እንድታገኘው አልፈልግም…..ሰምተሀኛል አይደል… .ደግሞ ሲደነባበሩ እሷ ላይ አደጋ እንዳያደርሱ›› ለሶስተኛ ጊዜ ደገመለት፡፡
‹‹ሰምቼያለው …ግን ሁኔታው አደገኛ ነው…ማለቴ ቀን ነው..ቡዙ ሰው በቦታው ላይ አለ…..እና ገዳዬቹ በቀላሉ ሊለዩና ሊያዙ ይችላሉ››
‹‹ስራችሁ መስሎኝ…?ይሄ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው..ይሄን ልጅ አስወግዱት…ከዛ የፈለጋችሁትን ብር ጠይቀኝ፡››
‹‹እንደዛ ከተስማማ እሺ...ስራውን ጨርሼ እደውልልሀለው፡፡
‹‹እጠብቃለው፡፡›
///
የእኛ ሰው ሲመክር በስሜት አትነዳ ይላል..ሰው ግን እንዴት ነው በስሜት ከመነዳት እራሱን ማገት የሚችለው?፡፡የሰው ልጅ ትልቁ ሀብቱ ስሜቱ ነወ :፡የመፍቀር ስሜት..የመጥላት ስሜት …ይፍርሀት ስሜት… የመከፋት ስሜት ….የመደሰት ስሜት… .የጉጉት ስሜት… ተስፋ የማቁረጥ ስሜት… እነዚህ ተፈራረቂ እና ተለዋዋጭ ስሜቶች ናቸው በህይወት ሰልፍ ተገፍተን ወይም ተዳክመን ወደዳር እስክንወጣ ድረስ ወደፊት እንድንቀጥል የሚያግዙን ፡፡
..ሲፈን አሁን ድብልቅልቅ ባለ የስሜት መናወጥ ውስጥ ነው ያለችው....ቢላል ተገኘ ብለው ደውለውላት በሹፌር በሚዘወር መኪና ወደመገናኛ እየከነፈች ነው፡፡እንደተሰጣት አካላዊ ገለፃ ተገኘ የተባለው ሰው እራሱ ቢላልን ይመስላል፡፡ጥራት የለውም እንጂ ፎቶውንም አንስተው ልከውላታል...እርግጥ ከስቷል፤በጣም ገርጥቷል ..ፀጉሩም ከሚገባው በላይ አድጎል..በዛ ላይ አደጋ ደርሶበት ሲሶ ፊቱ በፋሻ ታሽጎል…..ቢሆን እሱ እራሱ እንደሆነ እርግጠኛ ነች…በዛም ምክንያት ለእናቱ ደውላለት እሷም ከላችበት ቦታ በሌላ መኪና ወደእዛው እየሄደች እንደሆነ ነግራታለች፡፡
‹‹አምላኬ ሆይ በቃችሁ በለን ›ስትል አይኗን ወደመኪናው ጣሪያ አንጋጣ ፈጣሪዎን ተማፀነች..የቢላል መጥፋት ሁለነገሯን ነው ያፈራረሰባት..እንደሰው እንኳን በቅጡ ማሰብ አቅቷታል…ማሰብ ብቻ አይደለም መኖር እራሱ ደክሞታል.. .
የተነገራት ቦታ እየደረሰች ነው።አዎ ከ13 የስቃይና የጣር ቀናት ቡኃላ ልታገኘው ነው፡፡የልቧ ድውድውታ ፍጥነት ከመደበኛው በላይ ከመሆኑም በላይ ከቦታዋ ተነቅላ በመንቀሳቀስ በጉሮሮዋ በኩል ወደውጭ እየወጣች ያለች መስሎ እተሰማት ነው፡፡ደረቷን እያፈናት ጉሮሮዋን እየባጠጣት ነው፡፡
ቦታው ሲደርሱ ከ30በላይ ሰዎች አካባቢውን ወረውታል።ሸፌሩን እንዲያቆም ነገረችውን ተፈናጥራ ከመኪናው ወረደች ፡፡ በአባቷ የተቀጠሩ አራት ሰዎችም በቅርብ እርቀት መኪናቸውን አቁመው በእግር ተከተሏት….የሄኖክ ሰዎች ቀድመው ቦታ ላይ ስለተሰማሩ አሁን አይታዩም፡፡የሰውን አጀብ በመሰነጣጠቅ በመሀላቸው የተሽለኮለኮችና ያለይሉኝታእየገፈታተረች ወደፊት እየቀረበች ነው፡፡
‹‹ታድለው…አሁን 500ሺ ብር ሊቀበሉ ነው..ሎቶሪ እንደወጣላቸው ይቁጠሩ.››አንድ ነው የሚያወራው
ሌላው ይመልሳል‹እባክህ ዋቴ እንዳይሆን..ለአንድ እብደ 500ሺ ብር ይክፍላሉ ብሎ ለማሰብ እራሱ እብድ መሆን ይጠይቃል፡፡›
‹‹ባክህ ትከፍላለች..ፍሬንዱ እኮ ቢሊየነር ነች….እኔ እንደውም አንሱን ብሆነ አንድ ሚሊየን አድርጉት ብዬ አደራደር ነበር››
‹‹አይገርምም ግን እኛ ጤነኞቹ ዞር ብሎ የሚያን አላገኘን እብዱ በቢሊየነር ተፈቅሮ..?.››.

https://t.me/ethiofilm2adey_drama

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

02 Feb, 14:16


‹‹እብድ መሆኑን አትይ ..ሲሰራ ቀላል አይምሰልህ ..እብዶች አንጀት አርስ ናቸው አሉ…አንዴ የእብድ የቀመሰች ሌላ ዞር ብላም አታይም››ረጅም የሽፍደት ሳቅ
ይሄን ሁሉ እሷን የተመለከተ ሀሚትና ተረባ ምትሰማው በደቂቃዎች ሽርፍራፊ ወደፊት እየተራመደች ነው.፡፡ድንገት ግን የሰዎቹን አጀብ ሰነጣጥቃ አልፋ የቤቱ ግቢ በራፍ ጋር ደርሳ ከውስጥ ላለ ሰው ማነነቷ ነግራ ወደውስጥ እንዲያስገባት ለመጠየቅ አፎን ስታነቃንቅ ጆሮ ሰንጣቂ የሽጉጥ ድምፅ ተሠማ.. ድው...ድው. .ተደገመ...ሶስት ተከታታይ ተኩስ...አካባቢው በሰዎች ያልተጠናና አቅጣጫ አልባ የሽሽት ሩጫ ተተረማመሠ...ሲፈን የምታደርገው ነገር ግራ ገብቷት ባለችበት ደንዝዛ ቆማ ሳለ በእንዲህ አይነት ወከባ እና ግር ግር በቂ ልምድ ያላቸው የአባቷ ቅጥረኞች በደቂቃ ውስጥ ዙሪያዋን በመክበብ ያለፋቃዷ አንጠልጥለው ከአጀብ በማውጣት ወደመኪናቸው ይዘዎት ተፈተለኩ...ጮኸች ፤ተወራጨች፤.ከእጃቸው ሾልካ በማምለጥ ወደተኩሱ ስፍራ ለመመለስ በቻለችው አቅም ሞከረች..ከፈርጣማ ጡንቻቸውና ቆፍጣና ውሳኔያቸውን ግን መቋቋም አልቻለችም..በደቂቃዎች ውስጥ ስለተፈጠረው ነገር ምንነት መገመት ተሳኗት ፡፡፡ መንግስት ተገለበጠ እንዴ? ስትል አሰበች፡፡ እንደዛ ልታስብ የቻለችው ህግ ባለበት ሀገር ይሄ ሁሉ ተኩስና እንዲህ እሷ ላይ እንደተደረገው በጠራራ ፀሀይ ሰው ማገት እንዴት በግልፅና በድፍረት ይከወናል በሚል ስሌት ነው፡፡አጋቾቻ ሰማያዊ ሚኒበስ መኪና ውስጥ አስገቧት
‹‹ልቀቁኝ..ማን ናችሁ? ከእኔ ምንድነው የምትፈልጉት?››
‹‹ተረጋጊ ወይዘሪት ሲፈን...ለራስሽው ደህንነት ነው...››ከመካከላቸው ሀለቃ መሳዩ ሰውዬ ነው ተናጋሪው፡፡ከዛም ወደአንደኛው ባለደረበው ዞረና‹‹አንተ ሂድና ምን እንደተፈጠረ አጣራ ››ብሎ ላከው..ሶስቱ ከእሷ ጋር መኪና ውስጥ ተቀመጡ..
"ሰውን ማፈን ከባድ ወንጀል እንደሆነ አታውቁም...››የመለሰላት የለም
‹‹አሁን ልሂድ ልወቁኝ*የግድ ማግኘት ያለብኝ ሰው አለ››ይቅርታ የላክነው ሰው ስለተኩሱ ምንነትና ስለአካባቢው ደህንነት አጣርቶ ሳይነግረን ልንፈቅድልሽ አንችልም››ፍርጥም በሎ መለሰላት.
ከለበሰችው ጅንስ ሱሪ ስልኳን አወጣችና ደወለች፡አንተ ሰው ለምን አትተወኝም…?በጣም እያስጠላሀኝ እንደሆነ ታውቃለህ…..?ገረድህ ወይም የገዛኸኝ ባሪያ አደረከኝ እንዴ?››በሚንቀጠቀጥ ሰውነቷና በሚርገበገብ ድምፃ አንደበቷ ላይ የመጣላትን ሁሉ ዘረገፈችው
‹‹ምነው የእኔ ፍቅር ….ምን ተፈጠረ?››ሄኖክ ነው ምን ሰምታ ይሆን በሚል ስጋት በለሰለሰ አንደበት የመለሰላት፡፡
‹‹ሰዎችህ እሁኑኑ እንዲለቁኝ ደውለህ ንገራቸው..ከዛ ቡሃላ የማደርገውን እኔ ነኝ የማውቀው..አንተ ለመሆኑ ማን መሰልኩህ....?እንደአንተ አራትና አምስት ሰው ሳይሆን ከፈለኩ 5 ሺ ወታደር ቀጥሬ ከነዛር ማንዘርህ በደቂቀ ውስጥ ላስለቅምህ እችላለው..››
‹‹ተናደሻል ተረጋጊ.እኔ ስለምን እንደምታወሪ አላውቅም››
‹‹ሰውዬ ታግቼያለው እያልኩህ ነው…ሰዎችህ ሚኒባሳቸወ ውስጥ አፍነው አስገብተውኝ እንዳልነቀሳቀስ ከልክለውኛል.››
‹‹ያለሽበትን ንገሪኝ››
በጥያቄው ይበልጥ አበሳጫት‹‹ያለውበትንማ ሰዎችህን ጠይቀቸው››
‹‹እውነቴን ነው የእኔ ሰዎች አይደሉም...ፖሊስ ይዤ ልምጣ ቦታውን ንገሪኝ››
ስለኩን ጠረቀመችው….አና ሀለቃ ወደሚመስለው ሰውዬው ዞራ…‹‹የቀጠራችሁ ሄኖክ አይደለም?››
‹‹ሄኖክ መን ነው…?የምትይውን ሰው አናውቀውም››
‹‹እና ታዲያ ማን ነው? የልብ ልብ ሰጥቶችሁ እኔን እንደድታግቱ የከፈላችሁ ደፋር ማን ነው?›
‹‹ምን መሰለሽ….››መልሱን ከመጨረሱ በፊት ሁኔታውን እንዲያጣራ የተላከው ሰው መጣና የሚኒባሶን በራፍ ከፈቶ ወደውስጥ ገባ፡፡
‹‹እሺ ምንድነው የተፈጠረው?›>›
‹‹ግድያ ነው››
‹‹ምን አይነት ግድያ?››
‹‹ሰዎቹ 500 ሺ ብረ ከሰሩ….ለገኘው 500 ሺ ብር ይከፈላል የተባለለትን ልጅ አግኝተው ለሴትዬዋ በማስረከብ ብሩን ለመቀበል እየጠበቁ ሳለድንገት ቤታቸውን ሰብረው የገቡ ሰዎች በሶስት ጥይት ጨንቅላቱን አፍርሰው ገደሉት….>>
<<ምን?>>
<<አዎ 500 ሺ ብር እንደቀልደ ውሀ በላው››ለሞቹ ሳይሆን ለባከነው ገንዘብ በማዘን፡፡
በዚህ ጊዜ ሲፈን ባለችበት ሸርተት ብላ ወደጎኖ ዘንበል በማለት ወደቀች.. ተረባርበው አነሷት… ውሀ ጭንቅላቷ ላይ ቢያፈሱባትም መንቃት አልቻለችም…‹‹ቶሎ በል ወደ ሆስፒታል . ቶሎ ንዳው››
///
ሂኖክ ከቢሮ ሳይወጣ ምን‹‹ ይፈጠር ይሆን?› በሚል ጭንቀት ተወጣጥሮ በማሰላሰል ላይ ሳለ ስልኩ በድጋሚ አንቃጨለ…አነሳው፡:፡
‹‹እሺ›
‹‹ስራው .ባልከው መሰረት ተጠናቋል ››
‹‹እውነትህን ነው?››በደስታ እና በፍራቻ ድበብልቅ ስሜት
‹‹አዎ በራስህ መንገድ ማረጋገጥ ትችላለህ..ብሩን አዘጋጅልኝ .መጥቼ ወስዳለው፡፡››
‹‹አይ ደውይ የሆነ ቦታ አቀብልሀለው ...መጠንቅ አለብን .ቢሮ እንዳትመጣ›አለው
‹እሺ እንዳልክ›አለው በፈገግታ.፡
.ያስፈገው እስከአሁን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ምንም ጥናቃቄ ሳያደርግ ቆይቶ አሁን ስራው ካለቀ ቡኃላ ለመጠንቅ ማሰቡ አስገርሞት ነው፡፡ በእንዲህ አይነት ስራ ልምድ የሌለው እና ምን አልባትም የመጀመሪያው ሳይሆን እንደማይቀር ገመተ…እያንዳንዱን ድርድራቸውን የሰጠቸውን ትዕዛዝ ቀጥታ በስልክ ልውውጥ የተከወነ በመሆኑ ለምን አልባቱ በማለት ሁሉንም ቀድቶ ይዞታል..‹‹ምን አልባት አንድ ቀን ሊያስፈልገኝ ይችላል››በማለት፡፡

ይቀጥላል....


┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿

                  💗

https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama

                   💗

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

30 Jan, 18:53


መኪናዋን አንቀሳቀሰችና ወደ መንገድ አስገባችው..በዝግታ መንዳት ጀመረች.. በእስፖኪዬና ወደኃላ ተመለከተች …አዎ እነሱም እንደእሷ ነው ያደረጉት …እየተከተሏት ነው፡፡
‹‹ይሄውልህ አቶ ሄኖክ በደንብ ስማኝ ..በሚቀጥለው መጠመዘዣ ታጥፈው ወደኃላ ካልተመለሱ ለፖሊስ ደውዬ አሳስራቸዋለው፡››
‹‹ተይ እንጂ… ምንን መሰለሽ?…..››አላስጨረሰችውም ስልኳን ጠረቀመችው፡፡.
ወዲያው መልሶ ደወለላት.. .ዘጋችበትና አንድ ደህንነት የሚሰራ ባለስልጣን ወዳጆን ስልክ ከስልኳ ውስጥ ፈለገችና ዝግጁ ሆና መጠባበቅ ጀመረች፡፡ መታጠፊያውን አልፋ ነዳች ...ከኃላ ያሉት አጃቢዎቾ ምን እንደሚያደርጉ በጉጉት እና በስጋት እየተጠባበቀች ነው ‹‹ወይ እግዜር ይሰጣችሁ›አለች.ደስ ያላት እንደፈለገችው ባለችው መታጠፊያ ታጥፈው ወደኃላ ስለተመለሱ ነው.፡፡፡


ይቀጥላል....

┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿

                  💗

https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama

                   💗

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

30 Jan, 18:53


‹‹እንደዛ ይከሰታል እንዴ?››
‹አዎ…ይሄ እኮ የተለመደ ነው፡፡አእምሮችንን ልከ እንደኮምፒተር በይው…በሆነ አጋጣሚ የሆነ ቫይረስ ወደ ኮምፒተራችን ውሰጥ ሲገባና ሲያጠቃ እንደየጥቃቱ መጠን የተከማቹ መረጃዎች መሰረዝ እና ኮራብትድ መሆን እንደሚያጋጥም ሁሉ አዕምሮም በሆነ አጋጣሚ ሲጎዳ ተመሳሳዩ ነው የሚከሰተው፡፡በነገራችን ላይ ብዙ ጊዜ በጋዜጣ ፎቶውን በማስወጣት ቤተሰቦቹ እንዲያገኙት ሞክሬያለው..ሲደክመኝ ነው የተውኩት…ምን አልባት ከአዲስ አበባ በጣም አርቀው ሚኖሩ የገጠር ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ፡፡››
‹‹እና አሁን ምን ይሻላል?››ሲፈን ነች የበለጠ ግራ በመጋባት የማያልቅ ጥያቄዋን ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ እንጃ …እኔም በጣም ፈርቼያለው…አየሽ አሁን ጭንቅ ላይ ሰላለን እና የግድ ማወቅ አለብሽ ብዬ ስለወሰንኩ ነው እውነቱን የነገርኩሽ እንጂ ..ቢላል ማለት ለእኔ አሁንም እውነተኛ ልጄ ነው…ብዙ መስዋዕትነት የከፈልኩበት በጥልቀት የምወደው ልጄ ነው…..ምን አልባትም ህይወቴን ልሰጥለት የምችል ብቸኛ ሰው ቢኖር እሱ ብቻ ነው..ለእሱ ስል ብዙ መስዋዕትነት ከፍዬለው...ላገባው ከምፈልገው ከ5 አመት የፍቅር ጎደኛዬ ተለያይቼያለው….ምክንያቱም ከእሱ እና ከእኔ አንዳችንን ምረጪ ስላለኝ…..፡፡ብዙ ገንዘቤን ለህክምናውም ሆነ ያስደስቱታል ብዬ የማስበውን ነገር ለማሟላት አውጥቼያለው.ጎደኞቼ በሚያገኙት ገቢ ኪኒሊክ ሲገነቡ እኔ እሱ ላይ ነው ኢንቨስት ያደረኩት..እንደዛም በማድረጌ በዛም በጣም ደስተኛ ነኝ..ግን ቢሆንም መስዋዕትነቴ ሁሉ እንዲህ በቀላሉ መና እንዲቀር አልፈልግም… ልጄ እንዲገኝልኝ እፈልጋለው..ልጄ ሙሉ በሙሉ ድኖ ልክ እንደእኩየቹ ያፈቀራትን አግብቶ ልጅ እንዲወልድና አያት እንደያደርገኝ እፈልጋለው…ልጄ ጭንቅላቱ ውስጥ ያለውን ጥልቅ እውቀት ወደመጽሀፍ ቀይሮ አስደማሚ መረጃዎችን ለትውልዱ እንዲያስተላልፍ እፈልጋለው..ልጅ ፓሪስ ወይም ሎንዶን ላይ አስደማሚ ስዕሎቹን ይዞ በመሄድ ከአለም አቀፍ ሰዓሊዎች ጋር የስእል ኤግዚቪሽን እንዲያቀርብና አለምን ሁሉ እንዲያስደምም እፈልጋለው…ልጄ ባለው አስደማሚ የአስትሪኖሚ ዕውቀት ናሳ ተቀጥሮ የሚወዳት ማርሰ ላይ ደርሶ እንዲመጣ እፈልጋለው…ከእዚህ ሁሉ በላይ ግን ልጄ ተገኝቶልኝ ማቀፍ ነው የምፈልገው…አዎ ጥዋት ከእንቅልፌ ባንኚ አይኔን ስገልጥ አልጋዬ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብሎ መንቃቴን ሲጠብቅ እንዳገኘው ነው የምፈልገው…‹‹እማዬ ተነሽ ቁርሴን እንድትሰጪኝ ፈልጋለው›› ሲለኝ መስማት ነው የምፈልገው...አዎ አሁን ያለኝን ነገር ሁሉ ሰጥቼ ልጄን ማግኘት ብቻ ነው የምፈልገው››
‹‹እኔም እንደዛው››አለች ሲፈን በተሰበረ ድምፅ ….የፕሮፌሰሯ ንግግር ይበልጥ ልቧ እንዲሰባበር እና ሀዘኗም ጥልቅ ሆነ እንዲያማት ነው ያደረገው. .ስልኳን አነሳችና ደወለች
‹‹ኤርሚ ይቅርታ አሁንም መልሼ ደወልኩ››
‹‹ችግር የለም.ምን ልታዝ?››
‹‹ሽልማቱን 500ሺ አድርገው››
‹‹እርግጠኛ ነኝ?››
‹‹አዎ መላው የአዲስ አባ ህዝብ በየጉራንጉሩና በየጎደናው ግር ብሎ ወጥቶ እዲፈልገውና በአፋጣኝ እንዲያገኙልኝ እፈልጋለው..አጥቼወው ብዙ መቆየት አልችል››
‹‹እሺ ባልሺው አስተካክለዋለው››
ስልኩን ዘጋችው.እና ካቆመችበት ለፕሮፌሰሯ ማውራቷን ጀመረች
‹‹በቃ አይዞሽ.እናገኘዋለን››
‹‹እንደአፈፍሽ ያድርግልን..ለማንኛውም አንቺ እራስሽን ጠብቂ….እንደ አጋጣሚ ብቻሽን አግኝቶሽ እንዳይጎዳሽ››
‹‹አንቺም ሊገድለኝ እንደሚችል ታስቢያለሽ?››
‹‹እኔ አላውቅም.ልጄን እንደማውቀው ዝንብም ለመግደል እንኳን ጭካኔው የለውም ይሁን እንጂ አንድ በጣም የሚያፈቅራት ልጅ ጥላው እንደሄደችና ጥላው የሄደችው ደግሞ ከእሱ የተሻለ ሌላ ተመራጭ ሰው ለማግባት እንደሆነ የሚያስብ አንድ የአዕምሮ ህመምተኛ ሰው የተባለውን ነገር አያደርግም ብሎ በድፍረት መናገር አይደለም ለእኔ ለባለሞያዋ ለተራውም ሰው ይከብዳል...በዛ ላይ ሊያደርገወ እንደሚችል ግልፅ ማመላከቻ በተደጋጋሚ ሰጥቶናል
‹እኔን ለማጥቃት አስቦ እንኳን ከተደበቀበት መውጣት ችሎ ብናገኘው ምኞቴ ነው››ሲፈን ነቸ ግራ ገብቶት ግራ የተጋባ ንግግር የተናገረችው፡፡
‹‹ልጄ ከአለበት ተገኝቶ ቀጥታ ወደእኔ ወደእናቱ ወይም የህክምና እርዳታ ወደሚያገኝበት ሆስፒታል ነው መሄድ ያለበት …ቀጥታ አንቺን አግኝቶ ጥቃት ከሰነዘረብሽ ቡኃላ ምን እንደሚደርግ ታውቂያለሽ ..ወዲያውነው የሚያጠፋው፡፡››
‹‹እሺ እጠነቃለው.አሁን ልሄድ›ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡ሁለቱም .እየተደዋወሉ መረጃ ሊለዋወጡ ተነጋረው ተለያዩ..
ሲፈን መኪናዋ ውስጥ ገባችና ወደቤተሰቦቾ ቤት መንዳት ጀመረቸ…ወዲያው ግን አንድ ነገር ታዘበች.ቅድም ከፕሮፌሰሯ ጋር ተቀጣጥራ ከቤት ወደእዚህ ሰትመጣ ከኃላዋ ሚከታሏት ሁለት ጥቋቁር ማርቼዲስ ሚኪኖች እንዳሉ የሆነ መጠራራር በውስጥ ገብታ ነበር ግን ደግሞ ወዲያው ዘንግታው ነበር.አሁን መኪናዋን አስነስታ ስትሄድ እነዛው ተመሳሳይ መኪናዎች በቅርብ እርቀት ሲከተሏት እያች ነው..ይበልጥ አርግጠኛ ለመሆን በማትፈልገው መንገድ ታጠፈች.. አልተሳሳተችም .. አብረዋት ታጠፉ.
ምንድነው ጉዱ…‹‹ደግሞ የገባውበትን ጣጣ ሳልወጣ ሌላ ጣጣ ሊመጣኘ ነው እንዴ..?አሁን የመንግስት ግብር በማጭበርበር ብለው እስር ቤት ቢወረውሩኝስ.?››እንዴት አድርጌ ነው በደቂቃዎች ሽርፍራፊ ዝም ብሎ ከአየር ላይ በውስጦ የተሰነቀረ ስጋት ነበር.
‹‹እንዴት ላድርግ?›› እራሷን ነው ምትጠይቀው…መልስ ከማግኘቷ በፊት ስልኳ ጠራ….. ዳር ይዛ መኪናዋን አቆመች...ከኃላዋ እየተከተሏት የነበሩት መኪኖችም ርቀታቸውን እንደጠበቁ ቆሙ…ሁኔታው ይበልጥ አሳሳቢ ሆነባት ..በሀሳቡ እየተብሰለሰለች ስልኩን አነሳችው፡፡
‹እሺ ሄኖክ›
‹‹ሰላም ነሽ እኔ ፍቅር?››
‹‹ሰላም ነኝ..››
‹‹በሚቀጥለው ሳምንት .ማለቴ የፊታችን እሁድ ሽማግሌ ልልክ መሆኑን ልነግርሽ ነው››
‹‹የምን ሽማግሌ? ማን ጋ?››
‹‹እናንተ ቤት ነዋ…እናትና አባሽ ጋር….ቆንጅዬ ልጃቸውን እንዲሰጡኝ››አንጀቷ ቅጥል አለ...እሷ ሰማይ ምድሩ ተገለባብጦባት የምትይዘውን የምትጨብጠውን አጥታ በስቃይ ላይ እያለች እሱ በቅንጦት ቀን ስለሚደረግ ሽማግሌ መላክ ያወራል…አሁን ከእሱ ጋር ለመጨቃጨቅ አቅሙም ፍላጎቱም የላትም…
‹‹እንደፈለክ›
‹‹ለምን አሁን ወዳአለሁበት አትመጪም.ስለሁኔታው በዝርዝር እንነጋጋራለን፡››
‹‹አልችልም ስራ ይዤያለው››
‹‹አረ ተይ..ስለምንሽ የእኔ ፍቅር››
‹‹አልችልም አልኩህ …በዛ ላይ ከ10 ደቂቃ ቡኃላ የማናጀምንት ስብሰባ አለብኝ›
‹‹ማናጀመንት ማለት ከእናትና ከአባትሽ ጋር ነው?››ሳያስበው አመለጠው
‹‹አንተ ቆይቆይ .. ምን አልክ?›››
‹‹አይ ማለቴ..››
‹‹የምን ማለቴ ነው..ያለውበትን እንዴት አወቅክ?››
‹‹ያው አለ አይደል.ማለቴ….አዎ ስልክ ስደውልልሽ እኮ ያለሽበትን ቦታ….››
አላስጨረሰችውም‹‹<በቃ በቃ..አሁኑኑ ከኃላ እንዲከተሉኝ ያሰማረሀቸውን ውሾችህን አስወግድልኝ››
‹‹ለራስሽው ብዬ እኮ ነው.እባክሽ እንደዛ አታድርጊ ከአደጋ ሊጠብቁሽ ነው የሚከታተሉሽ›

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

30 Jan, 18:53


ነፍስ ስታፈቅር

ክፍል 38
.
.
//
ቢላል የገባበት ከጠፋ አምስት ቀን አልፎታል፡፡የሲፈንን ቤት መስታወት አርግፎ ከወጣ ቡኃላ እዚህ ቦታ አይቼዋለው የሚል አንድ ሰውም አልተገኘም፡፡በዚህን ወቅት ለሁሉም ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት ተደርጎና ፎቶውም ተበትሎ በቤተሰቦቹም በመንግስትም እየታሰሰ ይገኛል፡፡
ሲፈን እና ፕሮፈሰር ቦሌ ካሊዲስ ካፌ አንድ ጠረጵዛ ከበው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡ሁለቱም በጥልቅ ሀዘን ላይ ናቸው..ሁለቱም አይናቸው ከወዲህ ወዲያ እየተንከባለለ የሆነ ሰው ፊት ለማየት ይቅበዘበዛል…
‹‹-አሁን ምን ብናደርግ ይሻለናል?››ፕሮፈሰሯ ነች ጠያቂዋ
‹‹እኔም እኮ ግራ ግብት አለኝ.እንደው የሚቀርበው ዘመድ ወይም ሌላ ቦታ የሚኖር የቤተሰብ አበላት ጋር እየዞርን ብንፈልገው››
‹‹ምን መሰለሽ…››ፕሮፌሰሯ መልስ ልትሰጣት አፎን ስትከፍት የሲፈን ስልክ ጠራ… አነሳችው፡፡
‹‹ወ.ሪት ሲፈን ኤርሚያስ ነኝ… ፈልገሺኝ ነበር መሰለኝ….ይቅርታ ከሸሪኮቻችን ጋ ስብሰባ ላይ ነበርኩ››
‹‹ጥሩ ነው...አዎ ፈልጌህ ነበር››አለችው.፡፡ኤርሚያስ ማለት የሲፈን ካማፓኒ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆኖ የሚሰራ ከፍተኛ የኮሚኒኬሽን ኤከስፐርት ነው፡፡ከሞያው ጋር ተያይዞ ከሚዲያ ተቋማት ገርም ሆነ ከሚያስተዳድሯቸው ሰዎቹ ጋ ከፍተኛ ግንኙነት ነው ያለው…እና የፈለገችው ይሄንን ችሎታውን ልትጠቀምበት ነው፡፡
‹‹እሺ ምን ልታዝ?››
‹‹አንድ ውለታ አንድትውልልኝ እፈልገለው››
‹‹ደስ ይለኛል…ምንድነበር?››
‹‹ካምፓኒው ውስጥ ያለህን ኃላፊነት ላልተወሰነ ጊዜ ለሌላ ሰው ውክልና ስጥ››
‹‹ምነው በሰላም….?የተበላሸ ነገር አለ እንዴ?››ምቾት ባጣና በደነገጠ ቃና ጠየቃት...እሱ የሚያውቀው ስራውን በትጋት እና ብቃት እየሰራ እንዳለ ነው…‹‹ከስራ የሚያሳግድ ምን እንከን ተገኘብኝ?››እራሱን በራሱ የጠየቀው ጥያቄ ነበር፡፡››.እርግጥ ነው ከስራው ቢሰናበት ወዲያው በእለቱ የፈለግውን አይነት ስራ ብዙ ቦታ አማርጧ መቀጠር እንደሚችለው ያውቃል….ግን አሁን ያለበትን ካምፓኒ ይወደዋል...የስራ ነፃነቱን ይወደዋል…አሁን ደውላ ስራህን በውክልና አስተላልፍ በሚል ዜና እያስደነገጠችው ያለችውን ሀለቃውን በጣም ያከብራታል….ለእሷ ስኬት ከልቡ ይጥራል.እና ምን ተፈጠረ…?
ሲፈን ማብራራቷን ቀጠለች‹‹ሰላም ነው…ምን መሰለህ አሁን የቅርቤ ሰው ጠፍቶብኝ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ነው ያለውት….የጠፋው ሰው ትንሽ የእምሮ በሽተኛ ነው…ፎቶውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በኢሜልህ አያይዤልሀለው..››
‹‹ይህን በመስማቴ በጣም አዝናለው…እንዳደርግ የምትፈልጊውን ነገር ንገሪኝ…የምችልውን ሁሉ አደርጋለው››
‹‹ሙሉ ትኩረትህን እዚህ ጉዳይ ላይ አድርገህ ሁሉንም ኮኔክሽኖችህን ተጠቀምና አፋልግልኘ ፤በቴሌቪዝን ጣቢያዎች፤ በኤፍ ኤም ጣቢያዎች፤ በፌስ ቡክ ብቻ ይሆና ባልከው መንገድ ሁሉ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ይበተን…ለደላሎች፤ ለታክሲ ሺፌሮች እኔ እንጃ ብቻ መደረግ ያለበትህን ሁሉ አድረርግ…የ ወጪው መጠን ከግምት ውስጥ አይገባም››
‹‹እሺ… እንዳልሽ አደርጋለው… አንቺ ምንም አታስቢ ››
‹‹ይሄውልህ ኤርሚ.. ይንን ልጅ እንዳገኘው ከረዳሀኝ የእድሜ ልክ ውለታ እንደጣልክብኝ ቁጠረው››
‹ኸረ ግድ የለም….ደግሞ ላንቺ እንኳን ይሄን ..››
‹‹ከዚህ በላይ ልታደርግልኝ የምትችለው ነገር አይኖርም...ይሄ በሌላ ሰው ለእኔ ሊያደርግልኝ የሚችለው የመጨረሻ ውለታ ነው፡፡እሱ እስኪገኝ እኔም እንደጠፋው ቁጠረው...እሱን ስትፈልገው እኔን እየፈለከኝ እንደሆነ እየያሰብክ አድርገው፡፡››
‹‹እሺ ገብቶኛል›አለ.እውነታው ግን አልገባውም ነበር..ጭንቅላቱ ሙሉ በጥያቄ እንደተሞላ ነበር…ጠፋ የተባለው ወንድሟ እንዳልሆነ ያውቃል…ለቤተሰቦቾ ብቸኛ ልጅ እንደሆነች የታወቀ ነው….‹‹.እና ይሄን ያህል ከራሷ ጋር የመታነፃፅረው ምኗ ቢሆን ነው…?ለዛውም የእምሮ ህመምተኛ ለሆነ ሰው››
ስልኩን ዘጋችውና ትኩረቷን ፊት ለፊቷ ወደተቀመጠችው ፕሮፌሰር ለመመለስ እየጣረች
‹‹ምን እያወራን ነበር?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹የሚሄድበት ዘመድ ወይም የቅርብ ሰው ካለ እያልሽኝ ነበር..?››
‹‹አዎ …ቆይ አንድ የረሳውት ነገር አለ..››አለችና ስልኳን መልሳ ደወለች
‹‹ሄሎ ኤርሚ››
‹‹አቤት ?
‹‹አንድ ነገር እረስቼ .. ላገኘው 200 ሺ ብር ሽልማት ወዲያው እንደምንከፍል ጨምርበት.›
‹‹ሀለት መቶ ሺ ብር?››
‹‹ምነው ?አነሰ ?››
‹‹አረ እንደውም በዛ››
‹‹እንግዲያው ይሁን 200ሺ ብር ሽልማት እከፍላለው››ስልኩን ዘጋችው፡፡
‹‹ይቅርታ ፕሮፌሰር የቅርብ ዘመድ ወይም ቤተሰብ የለውም?››
‹‹ማንም የለም››
‹‹እንዴት? ቢያነስ አባቱስ?››
ፕሮፌሰሯ አንገቷን አቀረቀረችና በፀጥታ ተዋጠች…ሲፈን ግራ ገባት.‹‹ምነው ችግር አለ..?አባቱ በህይወት የለም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ስለአባቱ ምንም አላውቅም››
ማይታመን ነገር ነው እንደ ፕሮፌሰሯ አይነት ለምድር ለሰማዩ የከበደ ስብዕና ያላት ሰው ከማይታወቅ አባት ወላደች ብሎ ማን ያምናል?.ተደፋራ ነው….?.ጭፈራ ቤት አንድ ቀን ከተዋወቀችውና አብራው ካደረችው ሰው ነው ያረገዘችው…?ብዙ ብዙ የቢሆናል መላ ምቶች በአእምሮዋ ተመላለሱባት..የፕሮፌሰሯ መልስ ግን ከግምቷ በተቃራኒ ነበር
‹‹ቢላል ከእኔ ሌላ የሚያውቀው ሰው መኖሩን እኔ አላውቅም…››
‹አሁንም አልገባኝም?››
‹‹ሲፈን አንድ ያልነገርኩሽ ነገር አለ….ቢላል የወለድኩት ልጄ አይደለም››
‹‹ምን ?በፈጣሪ…እና ወላጆቹ የት ናቸው?››
‹‹ማንም የሚያውቅ ሰው የለም…እኔ ያገኘው ከማስተማር ስራዬ ጎን ለጎን አማንኤል ሆስፒታል አሰራ ስለነበር እዛ ህክምና ላይ ሳለ የዛሬ 8 ዓመት ገዳማ ነው፡፡እዛ የገባው ከመንገድ ላይ ሰዎችን ተተናኮለ ተብሎ በመንግስት የፃጥታ አካሎቸ አስገዳጅነት ነበር፡፡በወቅቱ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ እኔ እንድከታተለው ተመደብኩ..ከዛ በሂደት ሳጠናውበጣም የተለየ ስብዕና ያለው..በእውቀቱ የመጠቀ፤ ከአምስት ቋንቋዎች በላይ አቀላጥፎ የሚናገር፤በማንኛውም ርዕስ ላይ ከአቭሬጅ በላይ እውቀት ያለው..በተወሰኑት ለምሳሌ በአስትሮኖሚ ፤በስነፅሁፍ፤ በፍልስፍና ላይ በጣም የጠለቀ እውቀት ያለው…እንደቀልድ እየጫጨረ የሚጥላቸው ስዕሎች አስደማሚ የሆኑ ተአምረኛ ሰው ሆኖ አገኘውት፡..ይህም ቢሆን ግን የጤንነቱ ሁኔታ በጣም ከባድና ክሪቲካል የሚባል አይነት ነበር፡፡..ቡኃለ ግን ከአምስት አመት አታካቸ የህክምና ክትትል ቡኃላ በጣም አበረታችና አስደሳች የጤና መሻሻል አመጣ..ከእኔ ጋርም ያለን ቀረቤታ በጣም የጠበቀ ሆነ ...ልጄ ቢሆን ስል ተመኘው…ልጄ ሁን ብዬ ስጠይቀው እናቴ ብሎ ጠራኝ….በደስታ ፈነጠዝኩ…ኃላፊነቱን ወስጄ ከሆስፒታል አስወጣውት…ልጄ ብዬ ወደቤቴ ወሰድኩት….የእውነትም ፍፅም ልጄ ሆነ….እኔም እናቱ ሆንኩ፡፡
‹‹እየነገርሺኝ ያለውን ነገር ማመን ይቸግረኘኛል››
‹‹እመኚ እውነታው ነው የነገርኩሽ›››
‹‹እሺ ይሁን አንቺ ጋር ጤናው ተሻሽሎ ከመጣ ቡኃላ ስለቤተሰቡ አልጠየቅሺውም?››
‹‹ብዙ ጊዜ ጠይቄው ነበር…መልሱ አላውቅም ነው፡፡የልጅነት ጊዜውን ትዝታ ሙሉ በሙሉ ከእምሮው የተሰረዘ ይመሰለኛል፡፡››

ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች

29 Jan, 18:47


Calm Down (Rema, Selena Gomez)

#ዛሬ በተከታዬ Fitsita ምርጫ እንድዘፍንላት የጠየቀችኝን ሙዚቃ ነዉ የተጫወትኩላችሁ። ሙዚቃዉ አሁን ላይ popular ስለሆነ ታዉቁታላችሁ ብዬ እገምታለሁ። አዳምጡት ድምፄን ከወደዳችሁት እንድዘፍንላችሁ የምትፈልጉትን እንግሊዘኛ ሙዚቃ ልክ እንደ Fitsi ኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ። እየጨፈራችሁ አምሹልኝ💗

#Music Covered by Shefa ❤️🎤


https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama
https://t.me/ethiofilm2adey_drama

                   💗