የፍቅር ግጥም

@yefkr_gtm


የስነፅሁፍ ተሰጥኦዎች
📜ግጥም
💆የጭንቅላት ጨዋታዎች
💭አባባሎዎች፣
👽Psychology Facts🌷
❤️ልብ_ወለድ እና ጠቃሚ ምክሮች ያለገደብ #ከልብ_ዲያሪ ወደናንተ ይደርሳሉ
በተጨማሪም💎
ግጥም 💖የፍቅር❤️ የይቅርታ🙏 የመልካም ምኞት መግለጫ

የፍቅር ግጥም

01 Apr, 17:23


ከጨለመ አይደል...
ኩራዝ ትዝ ሚልህ
መሸት ሲል አይደል...
የብርሃን ጥቅሙ የሚገለጥልህ
ሲበርድህም አይደል...
ፀሀይ ምትናፍቀው
[እንግዲህ እሷንም]
ያጣሃት እለት ነው...
ፍቅሯን እምታውቀው
@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

01 Apr, 11:11


አይንሽ ሲርበኝ ሳቅሽ ሲጠማኝ
ህመምሽ ህመም ሆኖ ሲሰማኝ
ስሜ ይመስል ስምሽ ሲጠራ
ድንግጥ እርብትብት ስል እያየሽኝ
.
.
.
''ጠላሁሽ ስልሽ ለምን አመንሽኝ''

@yefkr_gtm @yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

01 Apr, 11:01


እንዲህ እንዳሁኑ
መራቅሽ
መሄድሽ
ውስጤን ሊያሳንሰው
መንፈሴን ሊያምሰው
(ሊ ያ ተ ረ ማ ም ሰ ው)
.
.
.
ለምን ተይኝ አልኩሽ...
አቅም እንዳለው ሰው

@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

01 Apr, 08:02


ዝም ብላ ምትስቀው
ልቤን እስክትሰርቀው

ያወራሁት ወሬ
ሚገርማት አስሬ

ስሜን በየቦታው
[ ሺ ግዜ ምትፈታው ]
ምጥን ንግግሯ
ቃሏ ሚጣፍጠው
ዝም ያለ አንደበቴን
ማብራሪያ ምትሰጠው

ህልሜን ከእውኔ ጋር
አይኔን ልትገልጠው
በቄንጥ ተራምዳ
መርጣ ምትረግጠው

ፀጉራ ሲዘናፈል
ሽንጧ ሲውረገረግ
ከአለም ነጥላ
ከስሯ ለማድረግ

እስካልቆጥር እድሜ
የሆነችኝ ህልሜ

ከ'ናት በላይ ቀርባኝ
ሆዴን ምታባባኝ

ዜማ ወረብ ሳቋን
የመኖር ሲር ሀቋን

አሳይታኝ ልትበር
ከጎኔ ያረፈችው
እስክወዳት ነበር

✍️ አዲብ
@yefkr_gtm
@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

30 Jul, 14:48


ቢቀናኝ እሰየው ባይቀናኝ ምን ገዴ
አንቺን ይዞ መኖር አይታክተው ሆዴ
.
.
የአለምን ጎዳና ብወጣ ብወርደው
አንቺን አይቼ እንጂ ብቻውን አሎደው

join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

07 Jun, 07:28


ይሄ ንፁህ ሳቅሽ ጥርሴን አስገለጠኝ
እሄ ተአምር ቃልሽ እምባዬን አስዋጠኝ
ሳይዉል ሳያድር ጨነቀኝ
በሀሳብ ገምቦ ተገፋው
ግዜያዊ ሳቅሽን ሳስብ
ከመሞት በላይ ተከፋው

join @yefkr_gtm @yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

25 May, 18:04


[..ልክፍት..]
. .
አዉቃለሁ ጠልተሽኛል፣
አትወጅኝም ይገባኛል..፣
መቼስ አንዴ ለክፈሽኛል፣..
(መቼስ አንዴ..
ታምሜያለሁ፣)
ዛሬም አንቺን አስባለሁ።
.
(አዎ..!)
ከሄድሽ በሁዋላ...
'ምወዳቸዉ ሴቶች..
'ማደንቃቸዉ ሴቶች..
ከ'ኔ ጋር ያደሩ..
ከ'ኔ ጋር የዋሉ፣
(በጥቂቱም ቢሆን)
አንቺን ይመስላሉ።
.
ተመልከቻት እሷን፣
ዉብ አረማመዷን...
እግር አነሳሷን፣
'ያነጋገር ስልቷን
ደግሞ አለባበሷን፣
"ቁርጥ እራስሽን!"
(ማለት ቢያስቸግርም፣)
የሆነ ነገሯ..
እንዳ'ንቺ እንደሆነ
አያጠራጥርም!!
.
(እያት ደግሞ ያቺን...)
'ካፍንጫዋ በታች
ያለዉ ከፊል ገጿ፣
ከንፈርና ጥርሷ..
የንግግር ድምጿ፣
ደግሞ ሳቅ ስትል..
የጉንጯ ስርጉዳት፣
ያንችን በመምሰሉ
ነፍሴን ሲያሻፍዳት፣
ልቤን ሲያሟሽሻት፣
(አየሽኝ?)
አየሻት?

እናልሽ..
ከብዙ ሴቶች ላይ
ጥቂት አንችነትን እያነፈነፍኩኝ፣
ያቺንም
ያቺንም
"ወደድኩዋት" ስላልኩኝ፣
'ባገር በመንደሩ "ሴሰኛ" ተባልኩኝ።
.
ሰማሽልኝ ስሜን?!
ልክፍቴን ህመሜን?
ስራብሽ
ስጠማሽ
በሰዉ አፍ መክረሜን?!
.
አየሽልኝ ህልሜን?!
አንችን ባላገኝሽ...
'ካምሳያሽ ጋራ ነኝ
እድሜ ዘላለሜን!!
........
{}
/በቃሉ ሹምዬ/
Join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm
@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

13 May, 09:19


ዘመንም ልክ እንደፊደል
እገልጥሽ ብሎ ቢታትር
በንቀት አይን አየሽው
ከፈልሽው በሳቅሽ በትር

በቁጥር ችሎ ላይዘልቀው
ላይረጋ ከነብስሽ እኩል
ፊትሽን ቋጥሮ ሊፈታው
መጣብሽ በእድሜ በኩል

ጠይም ነሽ ቡናማ መሳይ
አይደንቅሽ የከውኑ ግዳይ

ወተሻል ከሰውልጅ መደብ
ቀድመሻል ከግዜ አረንቋ
አታውቂም በቁስ መለካት
አይደለሽ ጌጣጌጥ ብርቋ

እኔ እንኳ
ሳቅሽን ተቋደስኩ እንጂ
ማን ችሎ ከዚ አተረፈኝ
ጥላዬን ይዤ ብማትር
ናፍቆትሽ ብቻ ገረፈኝ

ይበለኝ ይግረፈኝ በጣም
ያንድደኝ ለኩሶ በሳት
ድካሙስ የወጉ ነበር
መንገድ ነው የእግሬ ትኩሳት

መንገድሽ ተሰውሮኛል
ባልመጣም ስቀሽ ጠብቂኝ
ከዘመን አንሼ እንዳልቀር
ከራሴም እንዳታርቂኝ

አዲብ
join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

26 Apr, 18:39


💔የማያሽር...ጠባሳ💔
፨።።።💘💘💘።።።፨

ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ
ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ
.
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።

Join & Share

@yefkr_gtm
@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

22 Apr, 10:33


​​◈ ━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━ ◈


​​ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ

ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ
ቀልደሽ ተጫውተሽ ስቀሽ እያሳቅሽኝ
ሳታውቂው ሄደሻል ፍቅር አሲዘሽኝ
ለካ አንቺ ልብሽን አሳምነሽዋል
ንፁህ ወንድሜ ነው ብለሽ ነግረሽዋል
አልሰማ አለኝሳ የኔን ልብ ብነግረው
አንቺን እንደ እህትህ ውደድልኝ ብለው
ልቤን ብጠይቀው አጫወተኝ ብዙ
በመውደድ መስከሩን በፍቅርሽ መያዙ

ከዚያን ቀን ጀምሮ

ውስጤ ይፈራ ጀመር አንቺን ሲያይ አይኔ
ልቤ ሲሄድ ታየኝ ተለይቶኝ ከኔ
ጠየቁኝ ጓዶቼ
የኔ እንደዚ መሆን ግራ ቢገባቸው
የት እንሂድ ሲሉ አንቺ ጋር ስላቸው
ስለወደድኳት ነው ብዬ ነገርኳቸው
ስቀውብኝ ነበር ምቀልድ መስሏቸው
ጨዋታዬ ጠፍቶ በዝቶ መጨነቄ
ሲገባቸው ዛሬ በፍቅርሽ መውደቄ
ንገራት እያሉኝ እያለፍኩኝ ስቄ

ዘገየሁ

መሄጃሽ ደረሰ ካይኖቼ ልትርቂ
ስታወሪ ላልሰማ ላላይሽ ስትስቂ
ሳልነግርሽ ማፍቀሬን ዛሬ ነገ እያልኩኝ
ሄደሽብኝ አዘንኩ በሀሳብ ባከንኩኝ
ጨዋታሽ ሳይበቃኝ ሳልጠግብሽ አይቼ
ማፍቀሬ ሳይገባሽ ሳልነግርሽ ፈርቼ
መውደዴን ማስረጃ አንደበት አጥቼ
አዘንኩኝ በራሴ ሄደች ያሉኝ ለታ
ጨለመብኝ በቃ ቀኑም እንደማታ
አስጠላኝ ሰፈሩ አንቺ የሌለሽበት
ልቤ ሀዘን ገባው ሄደሽ ቀርተሽበት
ልነግርሽ ወስኜ
ጠይቄ ጓዶቼን ምን ልበላት ብዬ
ብነግርሽ ደፍሬ ፍራቻን ገድዬ
መውደዴን ጠላሽው ማፍቀሬን ገፋሽው
ለስንት የታሰበው በአጭር ቋጨሽው

እኔኮ ሆዴ

አልጠላም ነበረ ባይሽ እንደ እህቴ
ሳላስበው ገብተሽ ባትበይው አንጀቴ
አንቺን መርሳት አልቻልኩ አቃተኝ ሞክሬ
ከሀሳቤ አትጠፊም ትላንት ሲያልፍ ዛሬ
በሀሳብ አይሻለሁ ላይኔ ስትርቂብኝ
ትዝታሽን ብቻ ጥለሽ ሄደሽብኝ
ተጎዳሁኝ ውዴ አንቺን ስል ቀን ማታ
በአካል ነይልኝ በትዝታሽ ፈንታ፨



━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃
join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

15 Mar, 20:48


​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━ ◈


ማፍቀር መረገም ነው

ድሮ ልጅ እያለን ገና ጨቅላ ሆነን
ለእቃቃ ጨዋታ ባልና ሚስት ልኖን
አብረን ተሰብስበን ፊልም ላይ እንዳየነው
አንደኛው ሲፈቀር አንዱ ነው ሚያፍቅረው

እኛም ይሄን አይተን እኔ ነኝ ማፈቅረው እየተባባልን
ሁለት አፍቃሪ ሆንን ጠልተን መፈቀርን
በማፍቀር መጣላት አብዝተው ተገርመው
አንድ አባት እያዩን ሳቁ ጮክ ብለው

አባ እርሶ ይፍረዱን ማነው የሚያፈቅረው
እኔ ወይስ እሷ ብለን ጠየቅናቸው
እሳቸው በመልሱ እንባ ተናንቋቸው
መፈቀርን ፀጋ ማፍቀር መታደል ነው
ሄዋኗ ትፈቀር አፍቅር ደሞ አዳም
ብለው አስተማሩን ፍቅር አያጣላም

ታድያ እነዛ አባት እንዲህ ብለው መክረው
በልጅነት እድሜ ማፍቀርን ተርጉመው
ዛሬ ትልቅ ስሆን የእውነት አፍቅሬ
ማፍቀር መታደል ነው እያልኩኝ ተምሬ

ዛሬ ላይ ሄዋኔን አፈቀርኩሽ ብላት
ሴጣን እንደያዘው እንደ እብድ አረጋት
መፈቀር ፀጋ ነው ነበር የተባልኩት
ማፍቀር መታደል ነው ብዬም ነው ያደግኩት

#ታ
#ድ
#ያ

አፈቀርኩሽ ስላልኩ ልቤን ካደማችው?
ያፈቀራት ልቤን ካቆሳሰለችው?
አባ ተሳስተዋል ያስተምሩ ደግመው
ማፍቀርን ሀጥያት መረገም ነው ብለው


━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━

▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██
join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm

የፍቅር ግጥም

05 Feb, 17:24


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓  ግጥም  ▓▓▓▓▓▓


ቃላቶች ያንሱኛል ምን እደምልሽ
የኔ ፍቅር ብዬ በቃል አላሞግስሽ
ፍቅር የሚለዉ ቃል ዉዴ ያስብኛል
ቅድስቴ ማን እደምልሽ ግራ ይገባኛል
ፎርሙላ የለኝም የዉለታሽ የሚሰራ
እደዉ በፊዚክስ ወይም በማትስ ብሰራ
ዉዴ በየትኛዉ ቁጥር በምን ይጠራ
ያኔ የድሮዉ ኧረ እደዉ ይቅር ሳላስበዉ
ለምን እዳትይኝ ዝምብዬ አመሰግናለዉ
ዉድዋ እህቴ የልብ የዉስጤ አማካሪ ብርታቴ
ዉድ ወንድሜ አጋዥ ሙግቴ
ኧረ ልበልሽ የደስታዬ ምንጭ ፍቅረኛዬ
ሳዝንምታዝን ሊከፋኝ ማትፈልግ ነች እማዬ
እናቴ ሳትኖር ሆናለች ዉብዋ እማዬ
እደዉ ልበላት ምርጥ ወዳጅ ጓደኛዬ
ማን ልበልሽ ንገርኝ በየቱ ልሰይምሽ
በፍቅር አለም ማልሰለችሽ እህቴ
አብሬሽ ምትናፍቂኝ በሞቴ
ደግሞ በሂወት ብቸኛ የእቅልፌ ዳኛ
ድምፅሽ ካልሰማሁ ያመኛል
አይንሽ ካላየሁ ከልጅነቴ ጀምሮ ይከፋኛል
ልቤ በምድር ላይ እደ እሱዋ ሰዉ የለም ይለኛል
እስኪፍረጅኝ አንዱ ንገሪኝ
ይኸዉ ነዉ ልቤ ዛሬ እወቂኝ
ማነህ እዳትይ ማንነቴ አላዉቅም
ወንድምሽ አልልም አቅሙ የለኝም
እህትሽ አልልም አቅሙ የለኝም
እናትሽ አልልም አቅምሙ የለኝም
ፍቅረኛሽ አልልም አቅሙ የለኝም
ጓደኛሽ አልልም አቅሙ የለኝም
አባትሽ አልልም አቅሙ የለኝም
ግን ዉዴ ከሁሉ በላይ ብሆንሽ
ለሁሉም ቦታ ብሸፍ እደ ከፍ ባረግሽ
አሳዝናለሁ ግን መች ተሳካልኝ!!!!
ለዚ ነው አቅሙ የለኝም በቃኝ
ፈጣሪ አላደለኝ ልቤም አልሞላልኝ
አንድቀን እደምሆንሽ ሁሌም እተጋለሁኝ
እርስ የለዉም ግጥሜ እርስ ስጩ አለሜ
በገሀዱ አለም ያለሽ ብቸኛዋ ህልሜ

Barmura




━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
   ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ

የፍቅር ግጥም

06 Dec, 11:48


​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓



ሶስተኛው አለሜ 🌍👼💘

🌍
በፊተኛው አለም በአካል ማንነት
ችግር ከሞላበት
ተድላውም ካለበት
አንዴ ጣፋጭ እለት
ቀጥሎም ውጥንቅጥ
መላ ቂጡን ያጣ ሁሉ ሚታይበት።

👼
ሁለተኛው ደግሞ መንፈሳዊው አለም
የሚታይ አይደለም
ሚዳሰስ አይደለም
ትልም ነው ሚተለም
በምናብ ሚታለም።

🌍👼
ስጋና መንፈሴ በጎራ ሲፋጅ
አንዱም ሳያሸንፍ ህይወቴን ሲፈጅ
ነፍሴም ከጭንቀት ለመውጣት ስትዳክር
ስትደርስ ከደጅ

💘💘💘
መጣሽና አንቺ
ፈጥረሽ ሌላ አለም ልቤ ምታርፍበት
ፍቅርና መውደድ ደስታ የሞላበት
ነፍሴ ሳትወጣ ከስጋዬ ላይ
ሌላኛውን አለም ገብቼ ሳላይ

በአካል እንዳለው እኔ በዚች አለም
ከልቤ ጥላቻ ክፋት ሲጠራቀም
ከዛ ወጣሁና

የፍቅርሽን አለም ሳየው አስቀድሜ
መንፈሴ ሲነግረኝ እንዳለ ሰላሜ
ላልወጣ ወሰንኩኝ ዘጋሁት ጠርቅሜ
ፍቅርሽ
ፍቅርሽ ነው ሶስተኛው አለሜ

ተፃፈ;-በበሱ



━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ

የፍቅር ግጥም

30 Nov, 11:32


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓



Block......un block


ቀን አትናፍቀኝም
ጭራሽ ትዝ አትለኝ

ስምህም ሲጠራ ድንቄም አልደነግጥ
ፎቶህንም ሳየዉ ልቤ አትልም ድልቅ።

ድንገት ትዝ ካልከኝ
ራሴን 'ረግማለሁ
ምን አጃጅሎኝ ነዉ ብዬ እገረማለሁ።

ያንተ ስም ሲጠራ
ብዙ መሠል ስሞች ይመጣል ከኔ ጋር
ሌላም አስባለሁ ከትዝታ ጋራ

የአፍቃሪዬን ብዛት..............

በቃ ረስቻለሁ ብዬ ስደሳሰት
Block🤜

ልክ ሲመሻሽ ደርሶ
ስምህ ይጨንቀኛል
ሳቅህ ይሰማኛል

እንደ ቀኑ አይደለ ፎቶህ ግርማ አለዉ
መፀፀት አይደለ ልቤ አምጪዉ ነዉ ሚለዉ

ምን አተሽ ነዉ ከሱ
እድል ነበር እሱ

እያለኝ እንደቀልድ
ቀን ያመንኩት ልቤ ካንተ ጋራ ሲነጉድ
እንዲሁ አነጋለሁ
ስላንተ አነባለሁ።


ከዛ..............
un block ሳደርግህ ራሴን አገኛለሁ።

ድሮስ ከጨለማ ምን ነበር ጉዳዬ
አንተ መቼም አታዉቅ ሆነ እድል ፈንታዬ

አንተና ጨለማዉ ግብራችሁ አንድ ነዉ
ብቸኝነት ፍርሀት መልሳችሁ ዝም ነዉ።

ደሞ ዛሬም ነጋ.................


ተፃፈ በትዝታ ወልዴ


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢

የፍቅር ግጥም

29 Nov, 10:58


​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥም ▓▓▓▓▓▓▓


ቃል ብዬ ጠራሁሽ

ስላንች ለመፃፍ ብእር እቀርፅና
ቀለሙን አቅልሜ ፈቅፍቄ ብራና

ፊደልና ቃላት እንደልጅ እያማጥኩ
ሀረግ እየመዘዝኩ ምሳሌ እየጠቀስኩ

ቃል ባጣው ልሳኔ ስፅፍ ውዬ አድሬ
ገልጨሽ ሳይበቃኝ ትደርቃለች ብእሬ

ደግሞ ተመልሼ................

ደሜን አንጠፍጥፌ ቀለሙን አቀለምኩ
አጥንቴን ፈቅፍቄ ላንች ብእር ቀረፅኩ

ብእሬን በደሜ ነክሬ ሳወጣው
አንችን እገልፅበት ቅንጣት ቃላት አጣው

ለካንስ ቃልዬ!!!

በፍቅር ነሁልሎ መንፈስ ከደከመ
ናፍቆት አገርጥቶት ልብ ከታመመ

እንኳን ቃል ተዋቅሮ ቅኔ ሊመሰጠር
ደግሞ ስንኝ ሁኖ ግጥም ሊደረደር

ደህና አደርክ ሲባል ለእግዚአብሄር ይመስገን
አንደበት ቃል ያጣል ሲመርቁት ለአሜን

ለዛ ነው ቃልዬ!!!

መግለጫ ቃል ባጣ እልፍ ዘመን ሙሉ
የብራናዬ ገፅ ግራ ገብቶት ውሉ

እየደጋገምኩኝ የፃፍኩት አንድ ቃል




ብቻ ይላል

ሌላ ቃል ተገኝቶ
ወይ ልሳንህ ፈቶ

ህቡእ በሆነ ቃል እስከምትገልፃት
ቃልህ እሷ ነችና ቃሌ ብለህ ጥራት

እናም አንች ቃሌ ነሽ ሀረግና ስንኝ
ካጠገቤ ሁነሽ ሰርክ የምትርቢኝ

እናም የኔ ንግስት

ገፅሽን አድምቄ በልቤ መዝገብ ላይ
ቃሌ ብዬ ፃፍኩሽ ቃል አጣው ቃሌ ላይ


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ


🇪🇹 ሠላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹

የፍቅር ግጥም

26 Nov, 05:50


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓



የፍቅር ፀብ
( በላይ በቀለ ወያ )

ባብሮነታችን ውስጥ
ጥላቻ ባይኖርም - በመናናቃችን
በመናናቃችን
መለያየት መጣ - አብሮ መኖር ቀረ
አብሮ መብላት ቀረ
አብሮ መዋል ቀረ
አብሮ ማደር ቀረ
ቀረ
ቀረ
ቀረ
ሁሉም ነገር ሲቀር - ናፍቆት ተጀመረ
በናፈቅሽኝ ጊዜ - እንዲህ ስል ነበረ
እንኳን ተለያየን - እንኳን አብረን በላን
እንኳንም ናፈቅሽኝ - ፍቅር ነው ያጣለን፡፡
ባብሮነታችን ልክ
መናናቅ ልብ ላይ - ያኔ የተሰቀለ
አሁን የሚታየኝ
ናፍቆት የምንለው - ናፋቂ ፍቅር አለ፡፡
እንኳን ተለያየን!



━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢

የፍቅር ግጥም

21 Nov, 08:41


​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥም ▓▓▓▓▓▓▓


ሰባኪ ነው መሪ

መግደል መሸነፍ ነው ቢል ንጉስ ተብየው
እና ለማሸነፍ ሞትኩ ብየ ተኛሁ

ከእንቅልፍ ስነቃ ግን

የንጉሱ ስብከት ቃሉ ተገልብጦ
ሲያሸንፍ አየሁት ገዳይ ጦር ጨብጦ

ከዘመናት በፊት ሞቶ ያሸነፈ
ቆሽሸሀል ብሎ ሰው ያልተፀየፈ

በጅራፍ ሲነቅሱት ጀርባው ሲቆሳስል
መስቀል ላይ የወጣ ስለሀጥያን በደል

የመውደዱ ልኬት የማይመረመር
እንደተቀበረ ከመሬት የማይቀር

ሁሉን አሸናፊ በሞቱ ያዳነን
ሀሞት ተጎንጭቶ ወይን ጠጅ ያጠጣን

አንድ እሱ ብቻ ነው ስሙኝ ሰባኪያችን
እኛ አናሸንፍም ሞትን በሞታችን

ግን ደግሞ

አንድ ንጉስ አለ ሞቶ ድል ያመጣ
ውሀ እየተጠማ
ለናት ክብር ብሎ ባሩዱን የጠጣ

ከዚያ በኋላ ግን

ሞቶ ያሸነፈ ፈሪ ነው ልንገርህ
ገድለው ሲጨርሱህ አትመን ዝም ብለህ
ይልቅ አንተም ታገል ድል አምጣ ሰው ገለህ

መግደል ስታስብ ግን

መጀመሪያ ግደል እረኛውን ፈጥነህ
እሱኮ ነው አንተን
ለቀበሮ ሰጥቶህ በቀበሮ መሪ የተሸለመልህ
እሱ እኮ ነው ጠላት
ምርኩዝ ነህ እያልከው ገፍትሮ የጣለህ

እሱኮ ነው ገዳይ

ከእባብ ተፈልፍሎ እርግብ የሚመስልህ

እሱኮ ነው ዋሾ
መብራት ባጣች ሀገር አምፖል የሚያድልህ
እሱኮ ነው እባብ
በለስላሳ ምላስ መርዝ የሚረጭብህ




━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ

🇪🇹 ሠላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹

የፍቅር ግጥም

25 Jan, 18:37


​​⊶⊷⊶⊷❍ የእብደት ሚስጥሬ ❍⊶⊷⊶⊷


ፍቅሬን በቃላቶች ~ ደርድሬ ባልገልፀው
የኔ ነሽ የምልሽ ~ ያንቺ ነኝ የምለው
ድምፅሽ መዳኒቴ ~ የህይወት እጣዬ
አካልሽ ጉልበቴ ~ የስኬት ማማዬ
ሌላ ማንም የለም ~ ባንቺ ነው ማማሬ
እውነት እልሻለሁ ~ የእብደት ሚስጥሬ

↪️ @yefkr_gtm
━━━━✦🌹🌹✦━━━━

የፍቅር ግጥም

10 Jan, 17:04


​​​​━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━

​​​​━🔹ናፍቆት​​​​🔹

"የሃምሌ ዶፍ መጣ
ብርድ ተከናንቦ
ውርጭ አዝሎ ባንቀልባ፣
ሙቀቴ አንች ነበርሽ
ዘንድሮስ ምን ልሁን-የት አባቴ ልግባ?"
ብሎ ሰው ቢቀኝም፣
እንደዚህ ማርገድ ግን
እኔስ አያምረኝም።
እኔማ...
በጠራራ ፀሃይ-ገላ በሚያቃጥል፣
የለበሱትን ጨርቅ-የትሙን በሚያስጥል፣
እጠብቅሻለሁ-ካቦርቴን ደርቤ፣
በሳሳ አካላቴ-ናፍቆት ተኮንቤ።
እጠብቅሻለሁ...
ቁሩ ቢወበራም
መስኮቴን ከፍቼ ሳንቃየን ሳልዘጋ፣
አንቺ የሌለሽበት
መች ይበርዳል ክረምት
መች ይሞቃል በጋ?


🔘በዘነበ ወላ 🔘


➲ @yefkr_gtm

🟩🟨🟥🇪🇹🟩🟨🟥🇪🇹🟩🟨🟥

የፍቅር ግጥም

27 Dec, 05:39


​​◈ ━━━⸙⊶⊷⊶⊶⊷⊶⸙━━━━ ◈



➲ ⊷⊶⊷❍ ነግሬሽ ነበረ ❍⊶⊷⊶



ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!

ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!

ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!

ነግሬሽ ነበረ
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።

ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡

ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።

ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።

ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይመኟታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!


➲ @yefkr_gtm

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃